Inadequacy of Marx's Theory: The Case of Ethiopia

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 5

ማርክሲዝም በአጭሩ

ካርል ማርክስ በአለም ታሪክ ላይ ባሳረፈው ተጽእኖ እስከ ዛሬ በታሪክ ከተነሱ ፈላስፎች የሚተካከለው የለም ቢባል እብለት
ይሆን ይሁን? ሰሞኑን "ማርክሲዝም በአጭሩ" በሚል ርዕስ አጫጭር ጽሑፎች በተከታታይ ለመለጠፍ እሞክራለሁ።

ግን ከዚያ በፊት:

ማርክሲስት ነኝ በሚለው ደርግ ከተከሰተው እልቂት እና በካፒታሊስት ሀገራት ከሚነዛው ፕሮፖጋንዳ የተነሳ ስለ ማርክስ
ፍልስፍና አሉታው አመለካከት ያላችሁ ሰዎች ማወቅ ያለባችው ነገሮች፦

1 ኛ: ማርክስ በመጀመርያ ደረጃ ፈላስፋ ነው፤ ከዚያ በመቀጠል ፖለቲከኛ፣ አብዮተኛ፣ የስነ-ሰብእ ተመራማሪ እና ወዘተ ሊባል
ይችላል። የፍልስፍና ሀሳብ ነው ይዞ የቀረበው። የማርክስን ፍልስፍና በቅጡ ለመተቸት ፍልስፍናውን መረዳት እና relevant
ትችት የመሰንዘር አቅም ማዳበር ይጠይቃል።

2 ኛ ማርክስ የሚነበበው ማርክሲስት ለመሆን ብቻ አይደለም። የኮሚኒዝም ባላንጣ የሆነውን ካፒታሊዝምን ለመረዳትም
ማርክስ ነው የሚነበበው። የማህበረሰብን የኢኮኖሚ መሠረትና ስርዓት መረዳት ማህበረሰብን ለመረዳት ቁልፍ መሆኑን ልብ
በል።

3 ኛ በሶሲሎጂ እና በአንትሮፖሎጂ የትምህርት መስኮች የማርክስ ተጽዕኖ እጅግ የላቀ ነው። ለምሳሌ አስተማሪዎቻችን
ሊያስተምሩን ክፍል በገቡ ቁጥር እያንዳንዳቸው ቢያንስ ሶስቴ የማርክስን ስም ይጠራሉ።

4 ኛ: ፖለቲካ እንዲገባው የፈለገ ሰው ማርክስን ማንበብ ግዴታው ነው፤ አሊያ አልቃሻ ብሔርተኛ ወይም ሴራ ተንታኝ የሆነ
እንደው እንጂ የሀገሩም ሆነ አለም አቀፉ ፖሎቲካ ፈጽሞ የሚዘልቀው አይመስለኝም።

5 ኛ የነዋለልኝ እንቅስቃሴ፣ የደርግ አና የወያኔ ፖለቲካ የተመራው የነ ማርክስን ፍልስፍና ባነበቡ ሰዎች ነው። ማርክስን ብታነብ
የእነርሱ ፖለቲካ ይገባኻል።(ስልሳዎቹን፣ ደርግን እና ኢህአዴግን ለመረዳት ማርክስን ማንበብ ያለብኝ ከሆነ ብልጽግናን
ለመረዳትስ ማንን ላንብብ? ትለኝ ይሆናል። መልሱ ቀላል ነው፥ ኦሾን አንብብ)

ማርክሲዝም በአጭሩ - ክፍል 1

ማርክስ እና ሄግል!

Dialectic of history

የፈላስፎችን ሀሳብ፣ በተለይ ደግሞ የ continental ፈላስፎችን ሀሳብ ለመረዳት በጊዜያቸው የነበረውን ገዢ ፍልስፍና መረዳት
ቁልፍ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም አብዛኛው ፍልስፍናቸው በጊዜአቸው ከነበረው ገዢ ፍልስፍና ጋር በሚደረግ ግጭትና ፍጭት
የሚወለድ ነው። በማርክስ ዘመን የነበረው ገዢ ፍልስፍና የሄግል ፍልስፍና ነው። ማርክስ ራሱ በአንድ ወቅት ሄግሊያን ነበር።
በኋላ idealistic ከሆነው የሄግል ፍልስፍና ወደ materialism በማዘንበል ከወጣት ሄግሊያንስ ማህጋር ራሱን አገለለ። ሆኖም
የሄግልን ፍልስፍና መሉ በሙሉ ጠቅልሎ አልተወም።

ስለዚህ ሄግልን ቃኘት አድርገን እንመለስ። የሄግል ፍልስፍና ከውስብስብነቱም በላይ እጅግ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ለመረዳት
አዳጋች ነው። ስለዚህ ከፍልስፍናዎቹ መሀል ከማርክስ ፍልስፍና ጋር የሚያያዙትን ክፍሎች ብቻ ነጥለን በጥቂቱ
እንመለከታለን።
ማርክስን እና ሄግልን ከሚያመሳስሏቸው ወሳኝ ጉዳዮች አንዱ ለታሪክ የሚሰጡት አጽንኦት ነው። ለሄግል ታሪክ የራሱ የሆነ
ግብ እና ትርጉም ያለው ምክንያታዊ ሂደት(process) ነው፤ ትርጉም አልባ የሆነ የክስተቶች ጥርቅም አይደለም። ለአንድ የዚህ
ዘመን ኢአማኒ ታሪክ ማለት ባለፉት ዘመናት የኖሩ ሰዎች የሰሯቸው ስራዎችና ክስተቶች ጥርቅም ከመሆን ያለፈ ትርጉም
ላይኖረው ይችላል። ለአንድ ክርስቲያን አማኝ ግን ታሪክ ማለት ጅማሬው፣ ሂደቱ እና ፍጻሜው በአምላክ ቁጥጥር ስር ያለ፣ ግብ
አላማ እና ትርጉም ያለው ነገር ነው። “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው የእግዚአብሔር ሀሳብ በሰማይና በምድር ያለውን
ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።” እንዲል መጽሐፉ።

የሄግል የታሪክ እይታም ከክርስቲያኖቹ ጋር ይመሳሰላል። ነገር ግን ታሪክ ትርጉም አልባ ስላለመሆኑ ያላቸው አቋም ነው
የሚያመሳስላቸው። በዝርዝሩ ይለያያሉ። ሄግል የታሪክን ጅማሬ፣ ሂደት፣ ፍጻሜ እና ግብ የሚቆጣጠረው ከአለም የተነጠለ
የራሱ ኑባሬ ያለው አምላክ ነው የሚል አቋም የለውም።

በምን መሠረት ነው ታድያ ሄግል ታሪክ ትርጉምና ግብ ያለው ሂደት ነው የሚለው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ተገቢ ጥያቄ
ነው። ነገር ግን ይህንን ጥያቄ በሙላት መመለስ ውስብስብ የሆነውን የሄግል ፍልስፍና በስፋት መተንተንን የሚጠይቅ
ይመስለኛል፤ ስለዚህ ከያዝነው ርዕስ ጋር ተያያዥነት ያለውን ክፍል ብቻ መዝዘን እንመልከት።

በምን መሠረት ነው ታሪክ ትርጉምና ግብ ያለው ሂደት ነው የሚሆነው? ታሪክ ወደ ግቡ የሚያደርገውን ጉዙ የሚቃኘው እና
የሚገዛው ሀይል ምንድነው? ለዚህ ጥያቄ 'dialectic of history' የተሰኘው የሄግል ፍልስፍና መልስ ይሰጣል። dialectic of
history ውስጥ thesis, antithesis እና synthesis የተሰኙ ሶስት ቁልፍ ሀሳቦች አሉ።

ይህንን ቲኒሽ አስቸጋሪ የሆነ ሀሳብ በቀላሉ ለማስረዳት ያህል፦ Thesis ማለት አንድ ጭብጥ ነው፤ antithesis ደግሞ ከዚህ
ጭብጥ ጋር የሚቃረን ሌላ ጭብጥ ነው፤ synthesis ማለት በ thesis እና antithesis ተቃርኖ የሚወለድ አዲስ ጭብጥ ነው፤
synthesis ም በተራው thesis ይሆንና ሌላ antithesis ይነሳበታል፤ ከዚያም ሌላ synthesis ይወለዳል። በዚህ ሁኔታ ሀሳብ ወደ
ፊት ይጓዛል። የታሪክን ሂደት ወይም ጉዙ ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው ሀይል ይህ thesis, antithesis and synthesis የተሰኘ
የሀሳብ ኡደት ነው ይላል ሄግል፤ ከቅድመ ታሪክ ጀመሮ እርሱ እስከኖረበት ዘመን ድረስ የተከሰቱ ዋነኛ የአለም ታሪኮችን አንድ
በአንድ አጣቅሶ ይህንን ሀሳቡን ለማስረገጥ ይሞክራል፤ ታሪክ ከጊዜ ጊዜ እንዴት እየተሻሻለ እና ወደ ግቡ እየቀረበ እንደመጣ
ያሳያል። ሄግልን ማንበብ ከፍልስፍና ባለፈ ታሪክንም ማንበብ ነው የሚባለው ለዚህ ነው።

የታሪክን ሂደት ወይም ጉዙ ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው thesis, antithesis እና synthesis የተሰኘው የሀሳብ ኡደት እንደሆነ
ተመልክተናል። ይህ የሀሳብ ኡዱት እንዴት ነው በዘመናት መካከል ባለማቋረጥ እያውጠነጠነ ሊቀጥል የቻለው? ይህንን የሀሳብ
ሁደት በቋሚነት ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው ሀይል ምንድነው? ሀሳቦች ያለማቋረጥ እየተፋጩ፣ እየታደሱ እና ደግሞ እንደገና
እየተፋጩ ወደፊት የሚቀጥሉ ከሆነ የሚያውጠነጥኑበት አንድ ቋሚ ጉዳይ አለ ማለት ነው፤ ይህ ጉዳይ ነጻነት ነው። የነጻነት
ጥያቄ ነው ይህንን የሀሳብ ኡዱት በዘመናት መካከል ባለማቋረጥ እያውጠነጠነ ወደፊት እንዲቀጥል የሚያደርገው።

ሄግል ታሪክ ትርጉም እና ግብ ያለው ሂደት ወይም ጉዞ ነው የሚል አቋም እንዳለው ከላይ ተመልክተናል፤ ይህ የታሪክ ግብ ነጻነት
ነው። ታሪክን ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው የሀሳብ ኡደት ታሪክን ወደ ነጻነት ነው የሚነዳው። የባርያ ንግድን ክላልኝ እያለ፣
ፊውዳሊዝምን ወግድልኝ እያለ፣ ፍጹም ነጻ ወደ ሆነ የማህበረሰብ ስርዓት ነው ታሪክ የሚያንደረድረው። ይህ የሄግል ሀሳብ
dialectic of history ይሰኛል። ነጻ የሆነ ማህበረሰብ ምን አይነት ነው ለሚለው ጥያቄ የሄግል መልስ የምትጠብቁት አይነት
ላይሆን ይችላል። በዚህ ጉዳይ ማርክስም ከሄግል ጋር ተቀራራቢ አቋም አለው።
ሳላስበው ጽሑፉ ስለረዘመብኝ ከሄግል ሀሳብ ጋር ተቀራራቢ የሆነውን የማርክስን የታሪክ እና የነጻነት አረዳድ በቀጣይ ክፍሎች
እንመለከታለን። እኔ ብዙ በጣም ጥሩ ጥሩ የፌስቡክ ጓደኞች አሉኝ። ምናልባት ስስት ካያችሁበት አርሙኝ፤ ግልጽ ያልሆነ ነገር
ካለም ኮሜንት ላይ ጻፉ።

ማርክሲዝም በአጭሩ - ክፍል 2

ሄግላዊ የማርክስ የታሪክ አረዳድ

historical materialism

ክፍል 1 ላይ ሄግል «ታሪክ ግብ እና ትርጉም ያለው ሂደት ነው፤ ግቡም ነጻነት ነው።»የሚል አቋም እንዳለው ተመልክተናል።
የማርክስም የታሪክ አረዳድ ከሄግል የተቀዳ ነው፤ ሆኖም ማርክስ materialist፣ ሄግል ደግሞ idealist ስለሆኑ የታሪክ
አረዳዳቸውም በዛው ልክ ይለያያል።

ሄግል «የታሪክን ጉዙ ከኋላው የሚዘውረው የሀሳብ ፍጭት ነው፤ የታሪክ ግብ ደግሞ ነጻነት ነው» የሚል አቋም ሲኖረው፣
ማርክስ ደግሞ «የታሪክን ጉዙ ከኋላው የሚዘውረው የማህበረሰብ የኢኮኖሚ ሁኔታ ነው፤ የታሪክ ግብ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ
ነጻነት ነው» ብሎ ይከራከራል።

ማርክስም ልክ እንደ ሄግል የራሱ የሆነ thesis, synthesis and antithesis አሉት። ለምሳሌ ፊውዳሊዝም ጠቅላላውን ሀብት
ለንጉሡ ሰጥቶ ሰፊውን ህዝብ ጭሰኛ የሚያደርግ ጨቋኝ ስርዐት ነው፤ እንደ thesis ወሰዱት። በከበርቴው መደብ እና በሰፊው
ህዝብ መሀል ባለው ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት ምክንያት የሚፈጠረውን የተዛባ የኢኮኖሚ ሁኔታ ደግሞ እንደ antithesis
ውሰዱት። በ thesis እና በ antithesis ግጭት ምክንያት የተወለደውን ካፒታሊዝም ደግም synthesis ነው።

ካፒታሊዝም ደግሞ በተራው thesis ሆነ። ይህንን በዝባዥ ስርዐት ተቃውሞ የተነሳው የብዝበዛው ሰለባ ሰራተኛው መደብ
ደግሞ aantithesis ነው። በ thesis እና antithesis ተቃርኖ የሚወለደው communism ደግሞ synthesis ነው።

ትልቅ የሄግል ተጽዕኖ ያረፈበት ማርክስ ከሄግል የወረሰውን የታሪክ አረዳድ ከራሱ materialism ጋር አዋህዶ እና አዋድዶ ይህንን
የመሰለ የታሪክ አረዳድ ቀመረ። ይህ ለኮሙኒዝም ፍልስፍናው መሠረት የሆነው የማርክስ የታሪክ አረዳድ historical
materialism ይሰኛል።

ብዙ ጊዜ «ካፒታሊዝም ነጻ ገበያ ነው፤ ነጻነት ላይ የተመሰረተ ነው» ሲባል እንሰማለን። ሄግል የዳበረ የነጻነት ፍልስፍና አለው፤
ነገር ግን የነጻነት ፍልስፍናው ከካፒታሊቶች የነጻነት ብያኔ ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም። ማርክስም የሄግልን የነጻነት ፍልስፍና
ይከተላል። የሄግል የነጻነት ፍልስፍና መነሻው የታላቁ ፈላስፋ የኢማኑኤል ካንት ፍልስፍና ነው።

በሚቀጥለው ክፍል ይህንን የእነ ሄግልን የነጻነት ፍልስፍና እንመለከታለን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳነብ እና ስረዳ የተሰማኝን ደስታ
እስካሁን አስታውሳለሁ፤ እናንተም በጣም እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለሁ።

ማርክሲዝም በአጭሩ - ክፍል 3

የማርክስ የነጻነት አረዳድ


የማርክስ የነጻነት አረዳድ በሄግል በኩል አቋርጦ ከኢማኑኤል ካንት የስነምግባር ፍልስፍና የመጣ ይመስላል። ካንት «ነጻነት ማለት
ያለ አንዳች ውጫዊ ገደብ የፈለጉትን ማድረግ መቻል ነው» የሚለውን የሊብራሎች የነጻነት ብያኔ አይቀበልም፤ ነጻ ሰው
ምክንዮአዊ በሆነ ሁኔታ ከህሊናው ጋር ስምሙ የሆነ ምርጫ የሚመርጥ፣ ኑሮ የሚኖር ነው... አይነት አቋም አለው።

ሄግልም እንደ ካንት የሊብራሎችን የነጻነት ብያኔ አይቀበልም፤ «ይህ የነጻነት ብያኔ የግለሰቦችን ምርጫ የነጻነት መነሻ ያደርጋል፤
ግለሰቦች እንዴት እና በምን መሠረት እንደሚመረጡ አይገልጽም» ብሎ ይተቻል። ይህንን ጉዳይ ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ
በጥያቄ እና መልስ መልክ እንመልከተው፦

{A: ነጻ ምርጫ ምን አይነት ነው?

B: ከማንኛውም ውጫው ሀይል ተጽእኖ ነጻ የሆነ።

A: ውስጣው መሠረቱስ ምንድነው?(አንዱን ትተን ሌላውን የምንመርጠው በምን መሠረት ነው?)

B: የግለሰቦች ፍላጎት

A: የግለሰቦች ፍላጎት መሠረቱ ምንድነው?

B: ስሜት ነው።

A: ስሜት ከሆነ እንዴት "ነጻ ምርጫ" ሊሆን ይችላል? የሰዎች ምርጫ መሠረቱ ስሜት ከሆነ ሰዎች የስሜታቸው ባርያ እንጂ
እንዴት "ነጻ" ሊባሉ ይችላሉ?

B: 🙄🤔😣 }

ስሜት ካልሆነ ሌላ ምን ቀረን? አለመምረጥ ደግሞ አይቻል ነገር፤ ምንም ነገር አልመርጥም ብለህ ተጠቅልለህ ብትተኛም
አለመምረጥን መርጠሃልና።

ሄግል «ሊብራሎች የሚሉት አይነት ነጻነት የለም፤ ቢኖር እንኳ መሠረቱ ደራሽ ስሜት ነው። ምርጫን "ነጻ" የሚያደርገው
የሚነሳበት መሠረት ነው» አይነት አቋም አለው። ቆይ እንደው የራሱን ጽሑፍ ላስነብባቹ፦

“If we hear it said that the definition of freedom is ability to do what we please, such an idea can only be taken
to reveal an utter immaturity of thought, for it contains not even an inkling of the absolutely free will, of right,
ethical life, and so forth.”

ታድያ በሄግል እይታ ምርጫ 'ነጻ' የሚሆነው ምን ላይ ሲመሠረት ነው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ተገቢ ጥያቄ ቢሆንም
ከተነሳንበት የማርክስን የነጻነት አረዳድ የማየት አላማ በተወሰነ መጠን ሊያደናቅፈን ስለሚችል የዚህን ጥያቄ መልስ በዚህ
ጽሑፍ አንመለከትም።

ሄግል ደራሽ ስሜትን የ'ነጻ ምርጫ' መሠረት የሚያደርገውን የሊብራሎችን የነጻነት ብያኔ እንደማይቀበል ተመልክተናል፤
ማርክስም አይቀበልም። አሁን ወደ ማርክስ እንመለስ። የማርክስን የ"ነጻ የኢኮኖሚ ስርዓት" አረዳድ ለመረዳት በኢኮኖሚስቶች
መኻል ያለውን የዚህ ዘመን ጭቅጭቅ እንመልከት።

ሊብራል ኢኮኖሚስቶች የአንድ የኢኮኖሚ ስርዓት ጤንነት(ነጻነት) የሚለካው ሰዎች ማንኛውንም ምርጫቸውን እና
ፍላጎታቸውን እንዲያማሉ ባስቻለበት ልክ ነው ይላሉ፤ ይህ የሰዎች ምርጫ መሠረቱ ምንድነው የሚለው ጥያቄ
አይገዳቸውም።
ለምሳሌ በአንድ ማህበረሰብ አንድ ነጋዴ ይነሳና አንድ ከማህበረሰቡ መሠረታዊ ፍላጎቶች ጋር የማይገናኝ ምርት ያመርታል፤ ይህ
ምርት ከመምጣቱ በፊት ማህበረሰቡ ያለዚህ ምርት ምንም ሳይጎድልበት ይኖር ነበር። ነገር ግን ነጋዴው በተለያዩ የማስታወቂያ
ስራዎች እና ዘዴዎች አዲሱ ምርት ለማህበረሰቡ ልክ እንደ ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶች አስፈላጊ እንዲሆን አደረገ።

ለሊብራል ኢኮኖሚስቶች እንዲህ ያሉ ነገሮች ጤነኛ ናቸው። ራዲካል ኢኮኖሚስቶች ግን ይህንን ፈጽሞ አይቀበሉም፤ የአንድ
የኢኮኖሚ ስርዐት ነጻነት(ጤንነት) የሚለካው ሰዎች ማንኛውም ምርጫ እና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ ባስቻለበት ልክ
ሳይሆን መሠረታዊ እና ለማህበረሰብ እድገት እና መሻሻል ጠቃሚ የሆኑ ምርጫዎችን እንዲያሟሉ ባስቻለበት ልክ ነው የሚል
አቋም አላቸው።

ማርክስም እንደ ሊብራሎቹ፥ በጥቂቶች እጅ ከበቂ በላይ ሀብት ተከማችቶ ብዙዎች መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት
ተስኗቸው ጉልበታቸውን እንዲሸጡ የሚገደዱበትን የካፒታሊስት ስርዐት ነጻ ነው ብሎ አይቀበልም። የማርክስ የነጻነት እይታ
በግርድፉ ይህንን ይመስላል ልንል እንችላለን። ክፍል አራት ይቀጥላል።

ማርክሲዝም በአጭሩ - ክፍል 4

ከዚህ ቀደም ባሉ ክፍሎች ማርክሲዝምን ለመረዳት መደላድል የሚሆኑንን ሀሳቦች ስንመለከት ቆይተናል፤ ከዚህ በመቀጠል
ደግሞ ወደ ማርክሲዝም እንገባለን።

የፈላስፎች ሀሳብ የፍልስፍናቸው አቀንቃኝ ነን ከሚሉ ሰዎች ተግባር ተለይቶ መታየት አለበት። በተለይ ማርክሲዝምን
ማርክሳዊያን ነን ከሚሉ ሰዎች ለይተን መመልከት አለብን። ማርክስ ዶግማዊ አስተሳሰብን ይጸየፋል፤ በአንድ ወቅት
ማርክሳዊያን ነን ለሚሉ ሰዎች "ብቻ እኔ የማውቀው ማርክሳዊ አለመሆኔን ነው" ብሎ መልሶላቸዋል ይባላል በቀልድ መልክ።

ማርክስ ራሱን የስርነቀል ዴሞክራሲ እና የሰብዓዊ ነጻነት(radical democracy and human freedom ) ተሟጋች አድርጎ
ይቆጠራል። ማርክስ ካፒታሊዝምን የተቃወመው ካፒታሊዝም ሰፊውን ህዝብ አቅሙን አውጥቶ እውን የማድረግ እድል
የሚነፍግ ምክንያታዊ ያልሆነ ስርዓት ነው ብሎ ስላመነ ነው። የካፒታሊዝም አቀንቃኞች «ካፒታሊዝም ችግር ሊኖርበት
ይችላል፤ ነገር ግን ነጻነት ላይ የተመሰረተ ስርዓት መሆኑን መካድ አይቻልም» ብለው ይሞግታሉ። ማርክስ ግን «ይህ
ቅዠት(illusion) ነው» ይላቸዋል።

ማርክስ አንድን ማህበረሰብ ለመረዳት የማህበረሰብን የምርት ሁኔታ(the way it organizes production) መረዳት ቀዳማይ
ጉዳይ ነው የሚል አቋም ያለው ማቴሪያሊስት ነው። የማህበረሰብን የምርት ሁኔታ መረዳት በሁለት ቁልፍ ጉዳዮች ይወሰናል፦
1 ኛው የምርት ሀይል(production force) ሲሆን 2 ኛው ደግሞ የማህበረሰብ ምጣኔ ሀብታዊ መዋቅር ነው(economic
structure of society)።

የምርት ሀይል መሬት፣ ጥሬ እቃ፣ ቴክኖሎጂ፣ ክህሎት፣ እውቀት እና የመሳሰሉትን ያመለክታል። የማህበረሰብ ምጣኔ ሀብታዊ
መዋቅር ደግሞ ይህ የምርት ሀይል በማን ቁጥጥር ስር ነው? እንዴትስ ባለ ሁኔታ? የሚሉትን እና ተያያዥ ጉዳዮችን
ያመለክታል።

የምርት ሀይል እና የማህበረሰብ ምጣኔ ሀብታዊ መዋቅር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው። የምርት ሀይል እያደገ በመጣ ቁጥር
የማህበረሰብ ምጣኔ ሀብታዊ መዋቅርም እየተቀየረ የመጣል። ለምሳሌ የፊውዳል ስርዓት የማህበረሰብ ምጣኔ ሀብታዊ መዋቅር
እና የካፒታሊስት ስርዓት የማህበረሰብ ምጣኔ ሀብታዊ መዋቅር ትልቅ ልዩነት አላቸው። ይህም የሆነው በሁለቱ ስርዓቶች
የምርት ሀይል መኻከል ትልቅ ልዩነት ስላለ ነው። ማርክስ፣ የምርት ሀይል እድገት ከማህበረሰብ ምጣኔ ሀብታዊ መዋቅር ጋር
ግጭት የሚፈጥርበት ደረጃ አለ፤ የምርት ሀይል በቋሚነት እያደገ ሊቀጥል አይችልም የሚል አቋም አለው።

You might also like