Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 5

ጥበበ ሳይንስ ዘ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ በተለያዮ ጥበቦች ትታወቃለች


ነገር ግን በ ምዕራባውያን አጉል ስራ ተለክፈን
የሀገራችንን ጥበብ ትተን ሄደናል እናም አሁን
በሚዲያው እንደሚታየው የሀገራችንን ባህል
ለማውጣት እየጣሩ ያሉ ሰዎች አሉ ከ ህፃናት እስከ
አዛውንትታት እናም ወሬ ሳላበዛ ወደ ጉዳዮ ስገባ ዛሬ
ምንመለከተው ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ማዕድናት ነው።

፩ #የድመት አይን
የድመት አይን የሚባለው ማዕድን ብዙ ጥቅሞች አሉት
ከጥቅሞቹ መካከል
፩ ከክፉው ዐይን ለመከላከል ነው ጠቢባኑ የድመት
ዐይን
ያሉአቸውን እና ማዕድናቱ አንጓዎች እንዲለብሱ
ይመክራሉ።
፪ ሊመጣ ስለሚችል የአካል ጉዳት ማስጠንቀቂያ
ይሰጣል (አንድ ሰው ቁስለት የሚያጋጥመው ወይም
የሚወድቅ ከሆነ ማዕድኑ ለስላሳ ይሆናል)
፫ እጮኛ በማግኘት በፍቅር ጉዳዮች ውስጥ እገዛ
ያረጋል።
፬ የጋብቻ ታማኝነት ይሰጣል።
፭ በንግድ ላይ ስኬታማነትን መሳብ
፮ ከ "ክፉው ዓይን" እና ከምቀኞች ሰዎች ጥበቃ
ያረጋል።
፯ ግጭቶችን እና አለመግባባቶችን ለመፍታት እገዛ
ያረጋል።
፰ ለባለቤቱ ውበት ይሰጣል።
ከቀለም አንፃር “የድመት ዐይን” የሚባሉት ድንጋዮች-
፩ ግራጫ-አረንጓዴ
፪ ነጣ ያለ አረንጓዴ
፫ ቢጫ-አረንጓዴ
፬ ቢጫ
፭ ወርቃማ ቡናማ
፮ ጥቁር አረንጓዴ
#በህክምና ዘርፍ ደግሞ
፩ የማዕከላዊውን የነርቭ ሥርዓት እንቅስቃሴ መጣስን
ያክማሉ።
፪ ድብርት, ጭንቀት ያስለቅቃሉ።
፫ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ለማከም ያገለግላሉ።
፬ የሰውነት ስብራት ለመጠገን አገልግሎት ላይ
ይውላሉ።
፭ የመገጣጠሚያ ህመም ለማከም ያገለግላሉ።

፪ ቤቡዋ፦ በ ድንጋይ ሲመቱት ድምፁ እየጎላ እና


እየጎለበተ የሚሄድ ነው ለሙዚቃ ብታደርገውና
አምላክህን ብታመሰግንበት ክፉ መንፈስ ይርቃል።

፫ ቦቦ፦ ቦቦ እንደ ሐውልት የቆመ ድንጋይ ነው


በተለያዩ ፊደሎች ስምህን በዚያ የፃፍክ እንደሆነ
ስምህ በክፉ አይነሳም ሰው ያዘዝክ እንደሆነ
ይፈፅሙልሀል ሙሉ ጤነኛ ትሆናለህ የጠየከውን
ይሰጥሀል በሁሉ ዘንድ የከበርክ ትሆናለህ።

፬ ቤባን፦ አዳምና ሔዋን ከገነት ወደ ምድረ ፍይድ


እንደወረዱ ለብዙ አመታት የኖሩበት የድንጊያ አዳራሽ
ቤት ነው ፫ በሮች አሉት ለብዙ ዘመን አዕዋፋት የዱር
እንስሳት ይኖሩበታል።ይህም ድንጋይ መስሎ በኤልዳ
ምድር ይገኛል በእርሱ ውስጥ ሆነህ ሱባኤ የገባህ
እንደሆነ ወደፊት የሚሆነው ነገር ሁሉ ይታይሀል።
፭ በረቅ፦ ነጭ አፈር ካለበት የሚገኝ አረንጓዴ
ድንጋይ ነው ይህ ድንጋይ ባለበት ምስጥ አይኖርም።

፮ ሰንፔር፦ሕብሩ ፍህም ይመስላል ይላሉ፤እባብ


ለነደፈው በጥተው የቀበሩት እንደሆነ መርዙን
መጥምጦ ያወጠዋል።ከዚያም ዕንቁው ይጠቁራል።ያን
ጊዜ ወስደው ከባህር ውስጥ ባስቀመጡት ጊዜ
ከሶስት ቀንና ከሶስት ለሊት የባህር ውስጥ ቆይታ
በኃላ ወደቀድሞ ሕብሩ ይመለሳል።

፯ ዋውየ፦ድምፁ ከአገር አገር የሚሰማ የከበረ ድንጋይ


ነው።የከበረ ድንጋይ ከሁለት ከፍለን አንዱን በሌላ አገር
ሌላውን በሌላ አገር አድርገን አንዱን እየመታን በአንዱ
ብናዳምጥ ስንት ጊዜ እንደመታን ይታወቃል/ይሰማናል።
በዚህ ድንጋይ የተሰራ መሳሪያ ድምፁ ያማረ እና ልብን
የሚወስድ ይሆናል።
፨ኦፈ ያሬድ፡ የተባለችው ወፍ ለድምጿ ማማር ስትል
ዋውየ የተባለውን የከበረ ድንጋይ ወቅራ እና ሸርፋ
ትውጣለች እኛም እንዲሁ ብናደርግ ድምፃችን ከቀን
ወደ ቀን እያማረና እየተዋበ ይመጣል።
፰ ዮራኔ-ዮራ፦ ሀይል ያለውና ፍንዳታ ሚፈጥር
ነው።ከሀይለኛ ቢጫ እንቁ ጨረር ጋር አገናኝተህ ወደ
ዋሻ ብታፈልቀው ይንደዋል ያቀልጠዋል እንዳልነበር
ያደርገዋል እሱ ባለበት አረንጓዴ ቢጫ አፈር አለ
ከእርሱ ጋር የብረት ድንጋይ ብታደርግ ያጠራዋል ዘይም
ያቀልጠዋል።

፱ ኢዮቤል፦ አቤል የተገደለበት ድንጋይ ነው።መልኩ


ድቡልቡል ሆኖ ቡና ወይም ወይን ጠጅ
ይመስላል።አልፎ አልፎ ደም የተንጠበጠበበት
ይመስላል ይህን ድንጋይ ወስደህ በፍርድ ቦታ
ብትቀብረው በግድያ የተጠረጠረውን ሰው ከተቀበረበት
አቁመው ከገደለ ገደልኩ ይላል ካልገደለ አልገደልኩም
ይላል።

ሶፎንያስ ነበርኩ ከ ጥበበ ሳይንስ ዘኢትዮጵያ

ይቀጥላል

You might also like