Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 43

ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ

‚ኢትዮጵያዊው ሱራፊ‛ ተሰኝቶ በዱያቆን ዲንኤሌ ክብረት


የተ዗ጋጀው መጽሏፍ ሊይ የቀረበ ትችት

በርናባስ ሽፈራው
ሏምላ ፣ ፳፻፲፪ ዓ.ም.
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 1

መቅዴም
ዱያቆን ዲንኤሌ ክብረት ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ በተሰኘው መጽሏፉ ከ26 በሊይ የሚሆኑ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት
ቅጅዎችን እና ላልችንም ጥንታዊ ሰነድች መርምሮ እንዱሁም ዗መናዊ የታሪክ ሥራዎችን አጣቅሶ በእኔ ዕውቀት እስከዚሬ
ስሇ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከተጻፉት መጻሕፍት የሰፋ እና በብዘ መረጃዎች የታጨቀ ሥራ አቅርቦሌናሌ። የመጽሏፉ ስፋት
እና በውስጡ ያለት መረጃዎች ብዚት መጽሏፉ ምን ያህሌ የተሇፋበት መሆኑን ይመሰክራለ። አሥር አመታት የፈጀውን
ሌፋት አይቶ የጸሏፊውን ትጋት አሇማዴነቅ ንፉግነት ይሆናሌ።
መጽሏፉን መጀመሪያ እንዯታተመ ሰሞን አግኝቼ መግቢያውን፣ ማውጫውን እና በሽፋኑ የጀርባና የውስጥ ገጾች
የተሰጡትን አስተያየቶችን ካየሁ በኋሊ ወዱያውኑ ነበር ማንበብ የጀመርሁት። ነገር ግን ከመግቢያው አሌፌ የመጀመሪያውን
ምዕራፍ ማንበብ ስጀምር አንዲንዴ ነገሮች ግር እያሰኙኝ መጡ። ገሇሌተኝነት የጎዯሇው የሚመስሌ የክርክር ዴምጸት ተሰማኝ
፤ እንዱሁም ያሇ በቂ ማስረጃ ወዯ ዴምዲሜ የመሮጥ አዜማሚያ ታየኝ። ሇጊዛው ማንበብ አቆምሁ። ቆይቼ በዴጋሚ
ማንበብ ስጀምር ፤ አሁንም ተመሳሳይ ነገር አጋጠመኝ።
መጽሏፉ ሁሇት መሠረታዊ ችግሮች እንዲለበት ተሰማኝ። አንደ የተሰበሰቡትን መረጃዎች በአግባቡ የማዯራጀት፣
የመተርጎም እና የማመሳከር ሥራዎች ሊይ ጉዴሇት መኖሩ ነው። እንዱህ እንዴሌ ያዯረጉኝ በመጽሏፉ ውስጥ በተዯጋጋሚ
ያጋጠሙኝ የሏቅ እና የዴምዲሜ (premises and conclusions) መጣረሶች ናቸው። ሁሇተኛው ዯግሞ ጸሏፊው
ምርምሩን ከማካሄደ አስቀዴሞ ዴምዲሜዎች ሊይ መዴረሱ እና የሰበሰባቸው መረጃዎች ዴምዲሜዎቹን እንዱያስቀይሩት
አሇመፍቀደ ነው። ይህን እንዴሌ ምክንያት የሆኑኝ ዯግሞ በመጽሏፉ ውስጥ ያሇ በቂ መረጃ የተዯረሰባቸው ዴምዲሜዎች፣
ወዯ አንዴ አቅጣጫ የሚወስደ መረጃዎች በመጽሏፉ ውስጥ እያለ ጸሏፊው የመረጃዎቹን ደካ ሳይከተሌ የቀረባቸው
አጋጣሚዎች እንዱሁም እርሱ የተቀበሊቸውን ዴምዲሜዎች የሚቀናቀኑ ሏቆችን እና ሏሳቦችን ሇመዴፈቅ የሚያሳየው
ፍጥነት ናቸው።
እናም ያየኋቸውን እና መጽሏፉን አጉዴሇውታሌ ብዬ ያሰብኋቸውን ነገሮች በጽሐፍ ሇምን አሊቀርባቸውም ስሌ
አሰብሁ። በተሇይም ጸሏፊው በመግቢያው፣ ስሇ መጽሏፉ አስተያየት የሰጡትም ሰዎች በመጽሏፉ ሽፋን የጀርባ እና የውስጥ
ገጾች፣ መጽሏፉ የታሪክ ጥናት ሥራ መሆኑን የገሇጹ በመሆኑ እና እውነትም በመጽሏፉ ውስጥ ሇታሪክ ጥናት ጠቃሚ የሆኑ
ብዘ ነገሮች ያለ በመሆኑ በመጽሏፉ ዘሪያ ጥያቄዎች መነሳታቸው በጉዲዩ ሊይ የዲበረ ውይይት እንዱኖር እና ያን ተከትልም
የተሻሇ የሏሳብ ጥራት እንዱፈጠር ይረዲሌ ብዬ በማመን ፤ መጽሏፉን በጥንቃቄ ካነበብሁ በኋሊ የሚከተሇውን ትችት
አ዗ጋጀሁ።
አሊማዬ ጸሏፊው የዯረሰባቸውን የታሪክ ዴምዲሜዎች የሚተኩ አማራጭ ዴምዲሜዎችን ማቅረብ አይዯሇም፤ ያን
ሇማዴረግ አቅሙም ዕውቀቱም የሇኝም። ይሌቁንም ጥረቴ እንዯ አንዴ አማካይ አንባቢ መጽሏፉን ሳነበው የተፈጠሩብኝን
ጥያቄዎች እና ግርታዎች አብራርቶ በማቅረብ የጸሏፊውን፣ እንዱሁም የታሪክ ባሇሙያዎችን ትኩረት ወዯ ጉዲዩ ሇመሳብ
ነው። መጽሏፉን ሊነበቡት እና ሇሚያነቡትም ሰዎች በመጽሏፉ እና በውስጡ በተነሱት ጉዲዮች ሊይ አማራጭ ዕይታ
ማቅረብ ነው።
አሊማዬ አማራጭ የታሪክ ዴምዲሜዎችን ማቅረብ ስሊሌሆነም ጽሐፌ በአብዚኛው በመጽሏፉ የተገዯበ ነው ፤
ምናሌባት አንዲንዳ ሇንጽጽር ያህሌ አጠገቤ ወዲለ የታሪክ መጻሕፍት ጎራ ካሊሌሁ በቀር።
ዱያቆን ዲንኤሌ ክብረት በታሪክ እና በሃይማኖት ዗ርፎች ያካበተውን ሰፊ ዕውቀት አንዱሁም መጻሕፍትን በማ዗ጋጀት
ያሇውን ሌምዴ ሳስብ ይህ ሙከራዬ ከትሌቅ ቋጥኝ ጋር በኃይሌ እንዯመጋጨት ያሇ ሆኖ ይሰማኛሌ። ነገር ግን ሕሉናዬ
ያሌተቀበሊቸውን ጉዲዮች ‚እገላ‛ ስሇጻፈው ብዬ ሳሌረዲ ሌቀበሊቸው ስሇማሌችሌ ጥያቄዎቼን አቅርቤ ነገሩን መረዲትን
መርጫሇሁ። ራሱ ዱያቆን ዲንኤሌም ቢሆን እንዱህ ሲሌ ጉዲዩን እንዴገፋበት አበረታቶኛሌ።
‚በፖሇቲካው መስክ ብቻ ሳይሆን በዕውቀቱ መስክም እገላ የተባሇ የምዕራብ ታሪክ አዋቂ፣ የስነ ሌቡና ሉቅ፣
የፍሌስፍና ምሁር፣ የአርኬዎልጂ ተመራማሪ፣ የባህሌ ባሇሞያ አንዴ ጊዛ ከተናገረ እርሱን ተከትል ማስተጋባት፣
እና የርሱን መጽሏፍ እየጠቀሱ መከራከር እንጂ እርሱ ሉሳሳት ይችሊሌ፣ ያሊወቀው ሉኖር ይችሊሌ፣ ዯግሞም እኔም
ከርሱ የተሻሇ ሊውቅ እችሊሇሁ ብል የሚያስብ ያሇ አይመስሌም።‛ (ዲንኤሌ ክብረት፣ ጠጠሮቹ)
እናም ትችቴን እነሆ።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 2

1. አጠቃሊይ ችግሮች
ኢትዮጵያዊው ሱራፊ ውስጥ በጠቅሊሊው አራት ዏቢይ ችግሮች አስተውያሇሁ። የመጀመሪያው የአመክንዮ መዚባት
ነው። ሁሇተኛው የአወቃቀር ችግር ነው። ሦስተኛው ዗መናዊውን የታሪክ አጻጻፍ በቅጡ አሇመከተለ ነው። የመጨረሻው
ብዘ እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ምንባቦችና መረጃዎች በውስጡ መኖራቸው ነው። ከእነዙህ ችግሮች በተጨማሪም
አንዲንዴ የቃሊት እና የቁጥር ስህተቶች ሌብ ብያሇሁ፤ ነገር ግን መታረማቸው አስፈሊጊ ቢሆንም የመጽሏፉን መሠረታዊ
ይ዗ት ያን ያህሌ የማይጎደት ስሇሆኑ ትኩረት ሰጥቼ አሊነሳቸውም።
1. የአመክንዮ መዚባት
በመጽሏፉ ውስጥ ጥቂት የማይባለ የአመክንዮ ስህተቶች ይታያለ። ከእነዙህ ስህተቶች ሇአብዚኞቹ ምንጭ የሆነው
ጸሏፊው ማስረጃዎቹን ከመመሌከቱ በፊት ዴምዲሜ ሊይ የዯረሰ መሆኑ ነው። ከዙህ የተነሳ ብዘ ቦታዎች ሊይ
ማስረጃዎቹ ጸሏፊውን ወዯ ዴምዲሜ መምራታቸው ቀርቶ፣ ጸሏፊው ማስረጃዎቹን እርሱ ወዯሚፈሌጋቸው
ዴምዲሜዎች ሲመራቸው ይገኛሌ። አንዲንዳ አመክንዮአዊ ግንኙነት የላሊቸውን ማስረጃና ዴምዲሜ አንዴ ሊይ
ያስቀምጣሌ፤ አንዲንዳ ዯግሞ ማስረጃዎቹን መኖር ካሇባቸው ቦታ ያስቀራቸዋሌ (omission) ፣ ተገቢ ያሌሆኑ
ንጽጽሮችን (false equivalence) ያካሂዲሌ፣ ወ዗ተርፈ። ከእነዙህ ስህተቶች አብዚኞቹ በኋሇኛው የጽሐፉ ክፍሌ
የተነሱበት ዏውዴ እየተብራራ ስሇሚቀርቡ እዙህ ጋ በዋናው ታሪክ ሊይ ተጽዕኖ የላሊቸውን ሁሇት ምሳላዎች ብቻ
ጠቅሼ አሌፋሇሁ።
ጸሏፊው ገጽ 254 ሊይ ስሇ አክሱም ዗መን ክርስትና እንዱህ ይሊሌ።
‚እስከ 7ኛው መክ዗ ዴረስ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአራት ዓይነት ሏዋርያዊ አገሌግልቶች ተሰማርታ ነበር። . . .
ሦስተኛው (ዓይነት ሏዋርያዊ አገሌግልት) ገዲማዊ ሕይወትን በመመስረትና ሇዯቡብ ኢትዮጵያ ገዲማዊ መሰረት
በመሆን (ነው)።‛
ቀጥልም ሇዙህ አባባለ ማስረጃ ይሆን ዗ንዴ በኅዲግ ማስታወሻ 597 አቡነ ተክሇ ሃይማኖት እና አቡነ ኢየሱስ
ሞዏ ወዯ ዯብረ ዲሞ መሄዲቸውን እና በዙያም መማራቸውን ያነሳሌ። ነገር ግን እነዙህ ሁሇት አባቶች ወዯ ዯብረ ዲሞ
የሄደት በ13ኛው መክ዗ ነው። ይህን ከ7ኛው መክ዗ በፊት ከነበረው ሏዋርያዊ አገሌግልት ጋራ ምን አገናኘው?
ላሊ ምሳላ።
‚ግራኝ አሕመዴ ሊሉበሊን ባቃጠሇ ጊዛ በአሰራሩ እጅግ ተዯንቆ እንዯነበር ዏረብ ፋቂህ ይነግረናሌ። ቤተ
ክርስቲያኑንም እንጨት አስገብቶ ነው ያቃጠሇው። እንዱያውም የክርስቲያኖቹን ጽንዏት ሇመፈተን <<ከእናንተ እና
ከእኛ ማን ወዯ እሳቱ ይገባሌ?>> ሲሌ በጠየቀ ጊዛ የገዲሙ መምህር ሇመግባት ወሰኑ። አንዱት መነኩሲት ግን
<<እርሱ ወንጌሌ ያስተማረኝ መምህሬ ሲገባማ ቆሜ አሊይም>> ብሊ ቀዴማ እሳቱ ውስጥ ገባች። ግራኝም ዯንግጦ
እንዱያወጧት አ዗዗። ያን ጊዛ ግን ከፊሌ አካሎ በእሳት ተቃጥል ነበር። የቅደስ ሊሉበሊ አብያተ ክርስቲያናት ይህን
ያህሌ ይወዯደ ነበር።‛ (ገጽ 296)
የሊሉበሊ አብያተ ክርስቲያናት በኖረባቸው እና ባገሇገሇባቸው ሰው ዗ንዴ ቀርቶ በዜና በሚያውቋቸው ሰዎችም
዗ንዴ የሚወዯደ መሆናቸውን አሌጠራጠርም። ስሇዙህ ከጸሏፊው ዴምዲሜ ጋራ በመሠረቱ ምንም ቅራኔ የሇኝም። ነገር
ግን የቀረበው ታሪክ ይህን ዴምዲሜ እንዳት እንዯሚዯግፍ ምንም ሉታየኝ አሌቻሇም። ታሪኩ የሚያሳየው መምህሩ
ሇእምነታቸው ያሊቸውን ቅንዓት፣ መነኩሲቷ ዯግሞ ሇመምህሩ ያሊትን ፍቅር ነው። ክርስቲያኖቹ ቤተ ክርስቲያኑ
ሲቃጠሌ አሊስችሌ ብሎቸው ማንም ሳይጠይቃቸው ወዯ እሳቱ ገብተው ቢሆን የጸሏፊው ዴምዲሜ ትክክሌ ይሆን
ነበር። ነገር ግን ግራኝ ፈተና እስኪያቀርብሊቸው ዴረስ ወዯ እሳቱ አሌገቡም። እናም በቀረበው ታሪክ እና እዙያ ሊይ
በመመሥረት በተዯረሰበት ዴምዲሜ መሃሌ የሚታይ ግንኙነት የሇም። እንበሌና ይህ ታሪክ በሊሉበሊ መፈጸሙ ቀርቶ
በአንዴ ስሙ በማይታወቅ፣ የሕንፃው ውበት እዙህ ግባ በማይባሌ ዯብር ተፈጽሞ ቢሆን ምን ሌዩነት ይኖረው ነበር?
ምንም።
እነዙህ ሁሇት ምሳላዎች ከመጽሏፉ ዋና ጉዲዮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት የሊቸውም። ወዯፊት በሚመጡት ክፍልች
ግን ስሇ ትሌሌቅ ታሪካዊ ጉዲዮች ዴምዲሜ ሊይ በመዴረስ ሂዯት ውስጥ የተፈጸሙ መሰሌ ስህተቶችን እንመሇከታሇን።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 3

2. የአወቃቀር ችግሮች
ካስተዋሌኋቸው ችግሮች ሁሇተኛው የመጽሏፉን አወቃቀር የሚመሇከት ነው። መጽሏፉ ሇንባብ የበሇጠ ምቹ ሆኖ
ሉሰናዲ ይችሌ ነበር ባይ ነኝ። ጸሏፊው የመጽሏፉ መግቢያ ሊይ (ገጽ 6-7) ስሇ መጽሏፉ አወቃቀር አስረዴቷሌ። ነገር
ግን ያ ሏተታ ረ዗ም ስሇሚሌ እኔ እዙህ ጋ አጠር ያሇ መግሇጫ እሰጥና ከዙያ ዯግሞ ቢሻሻለ ብዬ ያሰብኋቸውን ነጥቦች
አቀርባሇሁ።
መጽሏፉ በአራት ክፍልች የተከፈሇ ነው። የመጀመሪያው ክፍሌ ‘ማስረጃና ታሪካዊ ዏውዴ’ የተሰኘ ሲሆን ዋና
አሊማው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የኖሩባትን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጀርባ (ዏውዴ) እና ጸሏፊው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን
ሕይወት ሇመጻፍ የተጠቀመባቸውን ሰነድች የተመሇከቱ መረጃዎች ሇአንባቢው ማቅረብ ነው። ይህ ክፍሌ በሦስት
ምዕራፎች ተከፍሎሌ።
ምዕራፍ አንዴ ‘ስሇ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የሚነሱ ሌዩ ሌዩ ሏሳቦች’ የሚሌ ርዕስ ተሰጥቶታሌ። ይህ በጸሏፊው
አገሊሇጽ ‚እንዯመነሻ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን በተመሇከተ የሚነሱ ሏሳቦችን የሚዲስስ ምዕራፍ‛ ነው። ምዕራፍ ሁሇት
‚ስሇ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ያለን የመረጃ ምንጮች‛ የሚሌ ነው። ጸሏፊው አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የተመሇከቱ
መረጃዎችን የሰበሰበባቸው ምንጮች በየዓይነታቸው ተከፋፍሇው ከማብራሪያ ጋር ቀርበዋሌ። ሦስተኛው እና ‚ቤተ
መንግሥቱ እና ቤተ ክህነቱ ቅዴመ እና ጊዛ ተክሇ ሃይማኖት‛ የተሰኘው ምዕራፍ ዯግሞ ‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን እና
ስራቸውን በሚገባ ማየት እንዱቻሌ ከእርሳቸው በፊት የነበረችውን ኢትዮጵያ የሚያሳይ ክፍሌ‛ ነው።
ሁሇተኛው ክፍሌ ‚ጻዴቁ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ማን ናቸው?‛ የሚሌ ሲሆን በስዴስት ምዕራፍ ተከፍል የአቡነ
ተክሇ ሃይማኖትን ታሪክ ከ዗ር ሏረጋቸው እና ሌዯታቸው እስከ እረፍታቸው እና ፍሌሰተ ዏጽማቸው የሚያስቃኝ ነው።
ይህ በርዜመትም ሆነ በይ዗ት የመጽሏፉ ዋና ክፍሌ ሉባሌ ይችሊሌ። ሦስተኛው ክፍሌ ‚ተክሇ ሃይማኖታውያን ከጥንት
እስከ ዚሬ‛ የተሰኘ ሲሆን ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ዕረፍት በኋሊ ያሇው የዯብረ ሉባኖስ ገዲም እና የእጨጌዎቹ ታሪክ
ቀርቦበታሌ። በመጨረሻው ክፍሌ ‚አባሪ ታሪኮች‛ ተብሇው ላልች ሰዎች ያሳተሟቸው የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት
ቅጅዎች፣ በስንክሳሮች ውስጥ የቀረቡ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ታሪኮች እና መሌክዏ ተክሇ ሃይማኖት ተካተውበታሌ።
ከዙህ ቀጥል በመጽሏፉ አወቃቀር ሊይ ንባብን አስቸጋሪ ያዯርጋለ ብዬ ያሰብኋቸውን ጉዲዮች አቀርባሇሁ።
ሀ. የመጀመሪያው ክፍሌ የመጀመሪያ ምዕራፍ
የመጀመሪያው ክፍሌ የመጀመሪያ ምዕራፍ (ጸሏፊው እንዯገሇጠው) ‚እንዯመነሻ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን
በተመሇከተ የሚነሱ ሏሳቦችን የሚዲስስ‛ ብቻ ሳይሆን ጸሏፊው ከዙያም አሌፎ የተነሱትን ሏሳቦች የሚሞግትበት
እና ፍርዴ የሚሰጥበት ነው።
ችግሩ ሙግቱ እና ፍርደ ሳይሆን የቀረበበት ቦታ ነው። ይህ የሚሆነው አንባቢው ገና የአቡነ ተክሇ
ሃይማኖትን ታሪክም ሆነ የኖሩበትን የታሪክ ዏውዴ እንዱሁም የመረጃ ምንጮቹን ሳያውቃቸው ነው። ጸሏፊው
መጽሏፉን ሲጽፍ የሰበሰባቸውን መረጃዎች መርምሮ የዯረሰበት ዴምዲሜ ሉኖር ይችሊሌ። ነገር ግን አንባቢው
ሁለንም መረጃዎች አይቶ የሕሉና ፍርዴ ይሰጥ ዗ንዴ የጸሏፊው ክርክሮች ወዯኋሊ መ዗ግየት ነበረባቸው።
ጸሏፊው በዙህ ክፍሌ ያቀረባቸው ሏሳቦች በሙለ እርሱ የማይስማማባቸው ናቸው። ስሇዙህ ጸሏፊው እና የእነዙህ
ሏሳቦች ባሇቤቶች ተቃራኒ ወገኖች ናቸው። አንባቢው ዯግሞ ዲኛ ነው። እናም ሙግቶቹ እና ፍርድቹ በመጽሏፉ
መጀመሪያ ሲቀርቡ ዲኛው ሁለንም መረጃዎች ሳያይ እና መስቀሇኛ ጥያቄዎች ሳይጠይቅ ፍርዴ ይሰጥ ዗ንዴ
እየተጠየቀ ነው ማሇት ነው። ፍርደን ካስተሊሇፈ በኋሊ ነው መረጃዎቹ የሚቀርቡሇት።
እንዯኔ እንዯኔ ጸሏፊው የዯረሰበትን ዴምዲሜ ያሇሙግት ቢያስተዋውቅና (በፍርዴ ሂዯቱ መጀመሪያ የእምነት
ክህዯት ቃሌ እንዯሚጠየቀው ያሇ) በመጽሏፉ የአስኳሌ ክፍሌ ሇዴምዲሜዎቹ ምንጭ የሆኑትን መረጃዎች
ቢያቀርብ (ምስክሮች የሚቀርቡበት እና መስቀሇኛ ጥያቄዎች የሚጠየቁበት ክፍሌ) በመጨረሻ ዯግሞ ሏሳቦቹን
አንዴ በአንዴ እያነሳ ሇአንባቢው ካቀረባቸው መረጃዎች መካከሌ እየጠቀሰ ቢሟገት (እንዯ መዜጊያ ንግግር ያሇ)
በጣም ጥሩ ነበር ብዬ አምናሇሁ። ዯራሲው የሞከረው ግን ከአንዴ ሺህ በሊይ ገጾች ባለት መጽሏፍ ውስጥ ዋና
ዋና የሚባለት የመጽሏፉ ጉዲዮች ሊይ የተነሱትን ሏሳቦች ሁለ በመጀመሪያዎቹ 56 ገጾች ሞግቶ ከጥቅም ውጪ
ሇማዴረግ እና አንባቢውንም ሇማሳመን ነው።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 4

በዙህ ሊይ ዯግሞ ያቀረባቸው ሙግቶች ምለዕነት የጎዯሊቸው እና እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱም ናቸው።
ይህን ያሌሁበትን ምክንያት አንዴ ምሳላ አቅርቤ ሊስረዲ። አሌሜዲ የተባሇው የካቶሉክ ሚሲዮናዊ አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት በሰባተኛው መክ዗ አጋማሽ ነበሩ ብል ያምናሌ። ምክንያቱ ዯግሞ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በዯብረ ዲሞ
ያገኟቸው አቡነ ዮሏኒ የገዲሙ ሰባተኛ አበምኔት ናቸው መባለ ነው። ሏሳቡ የገዲሙ መሥራች አቡነ አረጋዊ
በ5ኛው መክ዗ የኖሩ እንዯመሆኑ 7ኛው አበምኔት በ7ኛው ወይም በ8ኛው እንጂ በ13ኛው መክ዗ ሉኖሩ አይችለም
የሚሌ ነው።
ጸሏፊው ዯግሞ በዙህ አይስማማም። ይህን አቋሙን ሇመዯገፍ ዯግሞ አቡነ ዮሏኒ ሇምን በ13ኛው መክ዗
ኖረው ሉሆን እንዯሚችሌ የሚያሳዩ መከራከሪያዎች ያቀርባሌ። (ገጽ 11-12) መጀመሪያ የሚያቀርባቸው ሦስት
መከራከሪያዎች ዋና አሊማቸው እንዱህ ያሇው ክፍተት እንዳት ሉፈጠር እንዯቻሇ ማብራራት ነው። ክፍተቱ
የተፈጠረው (1) ወይ ገዲሙ በጦርነት ወይም በላሊ አዯጋ ምክንያት የመቋረጥ ችግር ዯርሶበት በአበምኔቶቹ መሃሌ
የነበረው ቅብብልሽ በመቋረጡ፣ አሉያም (2) በመሃሌ ብዘ አባቶች ኖረው ሳሇ ነገር ግን በቅዴስናቸው የታወቁት
የገዲሙ አበምኔቶች ብቻ እየተቆጠሩ ላልቹ ሳይቆጠሩ ስሇቀሩ፣ (3) ወይ ዯግሞ ከአበምኔቶቹ ብዘዎቹ ስሇተረሱ
አቡነ ዮሏኒ (በስህተት) 7ኛ አበምኔት ተዯርገው ተቆጥረው ሉሆን ይችሊሌ ይሇናሌ። (አባ ዮሏኒ ስማቸው ከአቡነ
ኢየሱስ ሞዏ ጋርም ጭምር ስሇተያያ዗ በ7ኛው መክ዗ ሉኖሩ የሚችለበት ዕዴሌ ጠባብ መሆኑን የሚያስረዲ ጥሩ
መከራከሪያም – እንዯ ንዐስ ነጥብ – አቅርቧሌ።)
ታዱያ እነዙህን ሦስት መከራከሪያዎች ካቀረበ በኋሊ አንዴ ላሊ መከራከሪያ ይጨምራሌ። ይህም – አቡነ
ተክሇ ሃይማኖት አንዱያውም መጀመሪያ በተጻፈው የገዴሊቸው ቅጅ ወዯ ዯብረ ዲሞ መሄዲቸው አሌተጻፈም፣
ስሇዙህ አሌሄደም። እናም አቡነ ዮሏኒ በ7ኛው ወይም በ13ኛው መክ዗ ቢኖሩ ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ጋር ምንም
የሚያገናኘው ነገር የሇም። – የሚሌ ነው።
እንግዱህ ይህ አራተኛ ክርክር ከቀዯሙት ሦስቱ ክርክሮች መነሻ ጋር የሚጋጭ ነው። መቼም (ሦስቱ
መከራከሪያዎች እንዯሚያዯርጉት) አቡነ ዮሏኒ በ13ኛው መክ዗ መኖራቸውን ማሳመን የሚያስፈሌገው አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት ወዯ ዯብረ ዲሞ ሲሄደ ያገኟቸው መሆኑን ከተቀበሌን ነው። ካሌሆነ እነዙህ ክርክሮች ጉንጭ የማሌፋት
ኪሳራ እንጂ ምንም ዓይነት ትርፍ የሊቸውም። አራተኛው መከራከሪያ ዯግሞ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዯብረ
ዲሞ አሌሄደም፤ አቡነ ዮሏኒንም አሊገኟቸውም ነው የሚሇው።
ነገር ግን በአንዴ ጊዛ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዯብረ ዲሞ ሄዯዋሌም፣ አሌሄደምም ብል መከራከር
አይቻሌምና ጸሏፊው ወይ የቀዯሙትን ሦስቱን ወይም የመጨረሻውን የክርክር ነጥብ ሉተወው ይገባ ነበር።
ሁሇተኛ ፡ የጸሏፊው የመጨረሻ መከራከሪያ (የሚቀበሇውን ሰው) ወዯ ሁሇት ዴምዲሜዎች የሚያዯርስ
ነው። የመጀመሪያው ‘አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዯብረ ዲሞ አሌሄደም።’ የሚሌ ሲሆን ሁሇተኛው ዯግሞ
‘መጀመሪያ የተጻፈው የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ ነው ትክክሇኛውን ታሪክ የያ዗ው።’ የሚሌ ነው።
ይሁን እንጂ አንባቢው የመጽሏፉን ገጾች እየገሇጠ ሲሄዴ ጸሏፊው በመጽሏፉ ሁሇተኛ ክፍሌ እነዙህን ሁሇት
ዴምዲሜዎች ሲቃረን ያገኘዋሌ። አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዯብረ ዲሞ መሄዲቸውን ተቀብል ይጽፋሌ። ዯግሞም
በመጀመሪያው ቅጅ ሊይ የተጻፉ ታሪኮች ውዴቅ እያዯረገ ከነዙያ ጋራ የሚቃረኑ ታሪኮችን ላልች ቅጅዎችን
በመጥቀስ ሲያጸዴቅ ያገኘዋሌ።
ጸሏፊው የአሌሜዲን ሏሳብ ሇመቃወም ይህን (አራተኛ) ክርክር ሲያቀርብ በኋሇኛው የመጽሏፉ ክፍሌ ከዙህ
ጋር የሚቃረን ዴምዲሜ ሊይ እንዯሚዯርስ ያውቃሌ። የመጀመሪያው ገዴሌ አይመዜግበው እንጂ ላልች
ጥንታውያን ገዴሊት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዯብረ ዲሞ መሄዲቸውን በተመሇከተ እንዯሚተባበሩ ያውቃሌ።
ስሇዙህ ‚ሇምን አሊማ ነው ይህን የሚያዯርገው?‛ ብል መጠየቅ ተገቢ ይመስሇኛሌ።
መግቢያው ሊይ የመጽሏፉ ዋና አሊማ ተብል የተጠቀሰው ‚እነዙህ ትችቶች ያነሷቸውን የተሳሳቱ ሏሳቦች
በታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ሰነድች መነሻነት መሞገት‛ ነው። ሏሳቡ መሌካም ነበር ግን የተሄዯበት መንገዴ እኔ
በግላ ትንሽ ቅንነት የጎዯሇው ይመስሇኛሌ። ምክንያቱም ጸሏፊው ሙግቱን ሲያካሂዴ የራሱን ዴምዲሜዎች
የሚዯግፉሇትን ማስረጃዎች ብቻ እያቀረበ እና ‚የተሳሳቱ‛ የሚሊቸውን ዴምዲሜዎች የሚዯግፉ ማስረጃዎችን ግን
ከአንባቢው እየዯበቀ ስሇሆነ ነው።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 5

ጸሏፊው ምንም እንኳን ‘የተሳሳቱ’ ያሊቸው ትችቶች ከክፉ አሊማ የመነጩ ናቸው ብል ቢያስብ ሏሳቦቹን
ከጀርባቸው ካሇው ክፉ አሊማ ነጥል በገሇሌተኝነት መርምሮ እውነት መሆን አሇመሆናቸውን ማጣራት አሇበት ባይ
ነኝ። እንጂ እነዙህን ትችቶች ፉርሽ ሇማዴረግ ሲሌ ብቻ እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ክርክሮችን የሚያቀርብ እና
ሇትችቶቹ ግብአት ሉሆኑ ይችሊለ የሚሊቸውን ማስረጃዎች ከአንባቢ የሚሰውር ከሆነ እሱም ከእውነት እየራቀ
መሄደ ነው። ይህ ዯግሞ የጸሏፊውን የራሱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው የሚሆነው። የተሳሳቱ
የተባለትም ሏሳቦች በእንዱህ አይነት ሙግቶች ምንም ያህሌ ጉዲት አይዯርስባቸውም።
ይህን ጉዲይ ሇማጠቃሇሌ ያህሌ፣ ይህኛው የመጽሏፉ ክፍሌ ጸሏፊው የአንባቢውን አፍንጫ ይዝ እርሱ
ወዯሚፈሌጋቸው ዴምዲሜዎች ሇመጎተት የሞከረበት ሆኖ ነው የታየኝ።
በዙህ ክፍሌ ያስተዋሌሁት ላሊው ችግር ጸሏፊው ተነስተዋሌ የተባለትን አምስት ሏሳቦች የከፈሇበት መንገዴ
ነው። ከአምስቱ ሦስቱ የይ዗ትም ሆነ የአመክንዮ ሌዩነት የሊቸውም። ‘ዚግዌ ዯገፍ ሉቃውንት’ ፣ ‘ዯጋፊ
ሰልሞናውያን’ እንዱሁም ‘ዛና መዋዕሊውያን’ ተብሇው የተጠሩት ቡዴኖች ሁለም አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ይኩኖ
አምሊክን ረዴተውታሌ ብሇው ያምናለ፤ ጸሏፊው ከሦስቱም ጋር የሚሟገተው ይህን ሏሳብ ተቃውሞ ነው። ታዱያ
ሦስቱም ሏሳባቸው ይህ ሆኖ ሳሇ የሚሇያዩት በፍርዴ ነው። ዚግዌ ዯገፍ የተባለት ሉቃውንት አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት ሇይኩኖ አምሊክ አዯረጉት የሚባሇውን እገዚ በበጎ ዏይን አይመሇከቱትም። በተቃራኒው የተቀሩት ሁሇቱ
ቡዴኖች ይህን እንዯ መሌካም አስተዋጽዖ ነው የሚቆጥሩት። እነዙህ ሁሇት ቡዴኖች ዯግሞ በ዗መን ከመሇያየት
በቀር የሏሳብም ሆነ የፍርዴ ሌዩነት የሊቸውም።
የእነዙህ ቡዴኖች ሏሳብ ተመሳሳይ ሆኖ ሳሇ ሇምን እንዯ ሦስት ሏሳብ ተዯርጎ እንዯቀረበ ግሌጽ አይዯሇም።
እኔ እንዯተረዲሁት ይህ ጸሏፊው ከሏሳቦቹ ይሌቅ የተቺዎቹ ማንነት ሊይ የማተኮሩ ውጤት ነው።
ሇ. የገዴለ ቅጅዎች ተአማኒነት ቅዯም ተከተሌ
በመጽሏፉ ሊይ ጥሊ አጥሌቷሌ ብዬ የማስበው ላሊው ጉዲይ ጸሏፊው መጽሏፉን ሇመጻፍ የተጠቀመባቸውን
መዚግብት ተአማኒነት በቅዯም ተከተሌ ሳይበይን መነሳቱ ነው። ይሌቁንም በአንደ ጉዲይ ክርክር ሲነሳ እርሱ
ሇሚዯግፈው ሏሳብ የሚስማሙትን መዚግብት ብቻ እየመረጠ ይጠቀምባቸዋሌ። ሇምሳላ ቀዯም ብሇን እንዲየነው
የአሌሜዲን ሏሳብ ሇመምታት ሲፈሌግ እጨጌ ዮሏንስ ከማ ያስጻፉትን የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ ይጠቅሳሌ።
ነገር ግን ላልች ጥንታውያን ቅጅዎች ጉዲዩን አስመሌክቶ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ጋራ ተቃርነው መቆማቸውን
አያነሳውም። ይህ ጉዲይ ዯግሞ በመጽሏፉ ዋናው ክፍሌ ሲነሳ የእጨጌ ዮሏንስ ከማን ቅጅ ወዯ ጎን ትቶ ላልቹን
ቅጅዎች መከተሌ ይመርጣሌ።
ላሊ ምሳላ ሇማከሌ ያህሌ ዯግሞ (ወዯፊት በዯንብ የምናየው ቢሆንም) ጸሏፊው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት
ይኩኖ አምሊክን ሇምን ረዴተውት ሉሆን እንዯማይችሌ ሇማስረዲት ሲፈሌግ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ቅስና
የተቀበለት በሱ ዗መን መሆኑን የሚያትቱ ቅጅዎችን ይጠቅሳሌ። በኋሊ ዯግሞ ላልች ቅጅዎችን ጠቅሶ (እና በፊት
የጠቀሳቸውን ቅጅዎች ውዴቅ አዴርጎ) ጻዴቁ ከይኩኖ አምሊክ ንግሥና 27 ዓመታት ቀዴመው ቅስና መቀበሊቸውን
ይተርካሌ። በዙህ የተነሳ የመጽሏፉ ውስጣዊ ስምምነት እጅግ ተጎዴቷሌ። ይህ መታረም ያሇበት መስል
ይሰማኛሌ።
በኔ ግምት የገዴለ ቅጅዎች በሚሇያዩባቸው ጉዲዮች ሊይ ስምምነት ሊይ መዴረስ ይቻሌ ዗ንዴ ጸሏፊው
አስቀዴሞ ቅጅዎቹን ግሌጽ በሆኑ መስፈርቶች መዜኖ (ሇምሳላ ጥንታዊነት ፣ የጸሏፊው ማንነት ፣ ከላልች ገዴሊት
ጋር ያሇው ስምምነት ወ዗ተርፈ) የበሇጠ ተአማኒ ናቸው የሚሊቸውን ቅጅዎች መ዗ር዗ር እና አከራካሪ ጉዲይ ሲነሳ
የዲኝነት ቅዴሚያውን ሇእነዙያ ቅጅዎች መስጠት ነበረበት ባይ ነኝ።
ሏ. የመረጃ ምንጮችን በተመሇከተ የሚናገረው ምዕራፍ
የክፍሌ አንዴ ሁሇተኛ ምዕራፍ ጸሏፊው መጽሏፉን ሇመጻፍ የተጠቀመባቸውን መዚግብት የተመሇከቱ
መረጃዎችን ያቀረበበት ክፍሌ ነው። በዙህ ክፍሌ ስሇ ገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች የቀረቡት ማብራሪያዎች
አንዴ ዓይነት ቀመር ያሊቸው አይመስሌም። የአንዲንድቹ ቅጅዎች የጽሕፈት ዗መን ፣ የተጻፉበት ቦታ ፣ ያስጻፋቸው
ሰው ማንነት እና የመሳሰሇለት መረጃዎች ጠቅሇሌ ካሇ የይ዗ት መግሇጫ ጋር ሲሰጥ የላልች ገዴሊት ይ዗ት ግን
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 6

ሳይገሇጥ ቀርቷሌ። ይ዗ቱ ሲገሇጥም በ዗ፈቀዯ እንጂ በታሰበበት መንገዴ አይመስሌም። አንደ ማብራሪያ ሊይ
የተጠቀሱ ታሪኮች የላሊው ቅጅ ማብራሪያ ሊይ በዜምታ ታሌፈዋሌ።
ላሊው አንባቢን ግራ ሉያጋባ የሚችሇው ጉዲይ ጸሏፊው በዙህ ክፍሌ ይህኛው ታሪክ ወይም ያኛው ታሪክ
(ሇምሳላ የዝረሬዋ ሴት ታሪክ ፣ የጋኔኑ ጥምቀት) እያሇ ሲጠቅስ አንባቢው ገና ስሇ ታሪኩ ምንም የሚያውቀው
ነገር ስሇላሇ ጎዯሇ ወይም አሇ የተባሇውን ነገር አስፈሊጊነት እና መኖሩ ወይም አሇመኖሩ ያሇውን ትርጉም ሉያጤን
አይችሌም።
በዙሁ ክፍሌ ስንክሳሮችን በተመሇከተ በቀረበው ሏተታ ጸሏፊው ስንክሳሮቹን የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን
ታሪክ የ዗ገቡበትን መንገዴ መሰረት በማዴረግ በሰባት ይከፍሊቸዋሌ።ነገር ግን የከፈሇበት መንገዴ አንዴ ስንክሳር
ከአንዴ በሊይ ምዴቦች ውስጥ እንዱወዴቅ የሚፈቅዴ ነው። የመጀመሪያዎቹ አራት ክፍልች ነገረ ሌዯቱን ጉዲይ
ያዯረጉ ሲሆኑ የተቀሩት ሦስቱ ዯግሞ ፍሌሠተ ዏጽሙን ጉዲይ ያዯረጉ ናቸው።
ሇምሳላ አንዯኛው ክፍሌ ‘ነገረ ሌዯቱ ያሌተጻፈባቸው’ የሚሌ ሲሆን አምስተኛው ምዴብ ዯግሞ ‘ፍሌሠተ
ዏጽሙ ያሌተጻፈባቸው’ የሚሌ ነው። ሌዯቱም ፣ ፍሌሰተ ዏጽሙም ያሌተጻፉባቸው ስንክሳሮች ቢኖሩ የት ነው
የሚመዯቡት? ይህ ጉዲይ በርግጥም ችግር እንዯፈጠረ የምናየው የተወሰኑ ስንክሳሮች (ሇምሳላ፡ ስንክሳር ዗ዯብረ
ዲሞ (1801-1818) ፣ ስንክሳር ዗ጣና ቂርቆስ ፣ ስንክሳር ዗አዱግራት ዯብረ መንክራት ቅደስ ቂርቆስ) ከአንዴ በሊይ
በሆኑ ምዴቦች ውስጥ መጠቀሳቸውን ስናይ ነው።
እንዯኔ እንዯኔ ጸሏፊው ሰባቱን ክፍልች በአንዴ ከማቅረብ ላሊው ቢቀር ሁሇት አይነት አከፋፈሌ መጠቀሙን
ገሌጾ (አንዴ በነገረ ሌዯቱ ሊይ የተመሠረተ፣ ላሊ ዯግሞ በፍሌሰተ ዏጽሙ ሊይ የተመሰረተ) ሁሇቱን አይነት ምዴቦች
ሇያይቶ ቢያቀርባቸው የተሻሇ ነበር ፣ አሁንም ነው።
በተጨማሪም በምዴቦቹ ውስጥ የስንክሳሮች ዜርዜር እንጂ ላሊ ሇንባብ የሚመች ይ዗ት ስሇላሇበት በዙህ
ክፍሌ ምሳላዎች ብቻ ተሰጥተው (እሱም ሊያስፈሌግ ይችሊሌ) ዜርዜሮቹ እንዯ አባሪ ቢያያዘ ይሻሌ ነበር ብዬ
አስባሇሁ።
መ. ክፍሌ ሁሇት፡ ጻዴቁ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ማን ናቸው?
ይህ ክፍሌ በጣም ረዥሙና የተሇያዩ ገዴሊትን እያጣቀሰ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ታሪክ የሚተርከው ፣
የመጽሏፉ አስኳሌ የሆነው ክፍሌ ነው። በጸሏፊው አገሊሇጥ በዙህ ክፍሌ ‚በተሇያዩ መዚግብት የሚገኙ መረጃዎችን
በአንዴ ዏጽመ ታሪክ ውስጥ ምክንያታዊ በሆነ መንገዴ በማስገባት አንዴ ወጥ ፍሰት እንዱኖራቸው (ሇ)ማዴረግ‛
እንዱሁም ‚የገዴሊቱ ቅጅዎች ፣ ላልች መዚግብት እና ዴርሳናት በአንዴ ጉዲይ ሊይ በሚሇያዩበት ወቅት ብያኔ
(ሇ)መስጠት‛ ተሞክሯሌ። ከዙህ ቀዯም እንዲሌሁት ጸሏፊው የተወሰኑ ፣ የበሇጠ ተአማኒ የሆኑ የገዴሇ ተክሇ
ሃይማኖት ቅጅዎችን መርጦ ታሪኩን በእነርሱ ሊይ አሇመመስረቱ እና ገና መረጃዎቹን ከመሰብሰቡ በፊት የራሱን
ዴምዲሜዎች ይዝ መነሳቱ ‚ብያኔ‛ የመስጠቱን ሙከራ ብዘ ቦታዎች ሊይ ያሰናከሇበት ይመስሇኛሌ።
በዙህ ክፍሌ ያስተዋሌሁት ዋናው ጉዲይ የዴግግሞሽ ችግር ነው። ጸሏፊው በገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች
ውስጥ የተጻፈን አንዴ ሁነት ሲተርክ ሁሇት ወይም ከዙያ በሊይ የሚሆኑ ገዴሊት ሁነቱን ይህ ነው የሚባሌ ሌዩነት
በላሇው መሌኩ ተርከውት ሳሇ ጸሏፊው ግን እነዙያን ቅጅዎች ተራ በተራ እየጠቀሰ ትረካውን ይዯጋግመዋሌ።
ሇምሳላ ያህሌ ከገጽ 330-40 ስሇ ፍሬምናጦስ የቀረበው ሏተታ በዴግግሞሽ የተሞሊ ነው። ከገጽ 368-72 ዴረስ
እግዙእ ኀረያ እና ፀጋ ዗አብ ዲግም የመገናኘታቸው ትረካም ተዯጋግሟሌ። ላልችም እንዱህ ዓይነት ዴግግሞች
አለ።
እንዯኔ አስተያየት ይህን ዴግግሞሽ ሇማስወገዴ በተአማኒነቱ፣ በስፋቱ እና በግሌጽነቱ የተሻሇውን ትረካ
መርጦ ማቅረብና በታሪኩ ሊይ ተጽዕኖ የማያሳዴሩ ሌዩነቶችን መተው፣ ተጽዕኖ ይኖራቸዋሌ ተብሇው
የሚገመቱትን ዯግሞ ወይ በኅዲግ ማስታወሻ አሉያም ከትረካው ቀጥል መግሇጥ ጥሩ አማራጭ ነው። ጸሏፊውም
እነዙህን አማራጮች የተጠቀመባቸው ቦታዎች አለ።
ሠ. የስሞች ማውጫ (መጠቁም) አሇመኖር
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 7

ላሊ መጽሏፉ የጎዯሇው የሚመስሇኝ ነገር ፕ/ር ጌታቸው ኃይላ መጠቁም የሚለት የስሞች ማውጫ (Index)
ነው። መጽሏፉ ከአንዴ ሺህ በሊይ ገጾች ያለት እንዯመሆኑ አንዴን ሰው ወይም አንዴን ቦታ የተመሇከቱ
መረጃዎችን ከውስጡ ፈሌጎ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ስሇዙህ ይህን ችግር ሇማቅሇሌ በመጽሏፉ መጨረሻ
መጠቁም ቢጨመርበት የመጽሏፉን ዋጋ ይጨምረዋሌ ብዬ አስባሇሁ።
3. ዗መናዊውን የታሪክ አጻጻፍ በቅጡ አሇመከተሌ
ጥንታዊና መንፈሳዊ የሆነው የገዴሌ አጻጻፍ ከ዗መናዊው የታሪክ አጻጻፍ በጣም የተሇየ መሆኑ ነጋሪ አያሻውም።
ገዴሊት በ዗መናዊው የታሪክ አጻጻፍ ውስጥ ጥቅም ሊይ የሚውለበት መንገዴ ውሱን ነው። በገዴሊት ውስጥ በብዚት
የምናገኛቸውን ከተሇመዯው የተፈጥሮ ሂዯት ውጭ እና ከሰው አእምሮ በሊይ የሆኑ ጉዲዮች ዗መናዊው ታሪክ
አይቀበሊቸውም። ምክንያቱ ዯግሞ መረጋገጥ ስሇማይችለ ነው። ነገር ግን በገዴሊት ውስጥ የሚጠቀሱ መረጋገጥ
የሚችለ እና ተፈጥሮአዊውን ሂዯት የሚከተለ ታሪካዊ ሁነቶችን፣ የቦታ እና የሰው ስሞችን ወ዗ተርፈ ዗መናውያን
የታሪክ ጸሏፊዎች እየወሰደ ይጠቀሙባቸዋሌ።
በላሊ በኩሌ ገዴሊት (አሁን በተጠቀሱት መንገድች) የታሪክ ምንጮች እንዯመሆናቸው፣ በ዗መናውያን የታሪክ
ጸሏፊያን አማካይነት ከተጻፉባቸው ቋንቋዎች ሇታሪክ ምርምር ሲባሌ እየተተረጎሙ እና የኅዲግ ማስታወሻዎች
እየታከለባቸው የሚቀርቡበት ጊዛም አሇ። ይህ ሲሆን ታዱያ ነባሩ የገዴለ (የመዜገቡ) ይ዗ት በፍጹም አይነካም።
ጸሏፊው በዙህ መጽሏፍ ውስጥ ጥንታዊ ገዴሊትን የተጠቀመበት መንገዴ ግን ከነዙህ ሁሇት መንገድች ያፈነገጠ
ነው። ሇምሳላ በመጽሏፉ ውስጥ (ገጽ 513-16) አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከዲሞት ወዯ አምሏራ ሲሄደ የብዘ ቀን መንገዴ
የሚፈጀውን ጉዝ በሁሇት ቀን እንዯጨረሱት ተተርኳሌ። ጸሏፊው ይህን ትረካ ከገዴሊት ቅጅዎች እንዯወረዯ ትርጉሞ
አቅርቦታሌ። ይህን ማዴረጉ ትክክሌ ነው።
ላሊ ቦታ ዯግሞ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በአንዴ ዓመት ውስጥ ሦስት ጊዛ ኢየሩሳላም መውረዲቸው ተገሌጧሌ።
ጸሏፊው ይህኛው ትረካ ሊይ ግን አስተያየት ይሰጣሌ።
‚ምንም እንኳን የቅደሳንን ሥራ በተራ አእምሮ ሇመገመት ቢከብዴም ፣ በአንዴ ዓመት ውስጥ እነዙህን ሁለ
ነገሮች ሇማከናወን እና ኢየሩሳላም ሦስት ጊዛ ሇመሄዴ ግን የሚቻሌ አይዯሇም።‛ (ገጽ 587)
ጸሏፊው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ኢየሩሳላም አሌሄደም ብል ሇመከራከር (በ዗መናዊ የታሪክ አጻጻፍ) ላልች
ከገዴለ ውጭ ያለ ምክንያቶችን ሉያቀርብ ይችሊሌ፤ አቅርቧሌም። ሇምሳላ፡ ላልች ገዴልች ይህን ታሪክ
አሇመ዗ገባቸውን። ነገር ግን ‚የሚቻሌ አይዯሇም‛ ብል ሉከራርከር አይችሌም፤ ፈጽሞ። ምክንያቱም በገዴሌ ዓሇም
ውስጥ ይህ ሉሆን የማይችሌ ነገር አይዯሇም። ይህን ጉዲይ ሉሆን አይችሌም ብል ካሇ ዯግሞ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት
ያዯረጓቸው ተአምራት ሊይ ሁለ ተመሳሳይ ውሳኔ ማሳሇፍ አሇበት።
የዙህ ችግር መነሻ የሚመስሇኝ ጸሏፊው ታሪኩን ከየትኛው አቅጣጫ እንዯሚጽፍ ግሌጽ ያሇ ሏሳብ ይዝ
አሇመነሳቱ ነው። ሁሇቱን አጻጻፎች ይቀሊቅሊቸዋሌ። ይህን ነጥብ የበሇጠ የሚያስረግጥ አንዴ ምሳላ ሌጨምር።
ጸሏፊው ስሇ ቅደስ ያሬዴ ሲጽፍ ‚በመጨረሻም የተሰወረው በራስ ዯጀን ተራራ፣ ጸሇምት ውስጥ ነው።‛ ይሊሌ (ገጽ
254)። ይህን የሚሇን ላሊ ሳይሆን ጸሏፊው ራሱ ነው። ‚እንዯ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት‛ ወይም ‚ተሰውሯሌ ተብል
ይታመናሌ‛ አሊሇም። ‚ተሰውሯሌ።‛ ብል ጽፎ አንባቢው እንዱቀበሇው ጠብቋሌ። አንባቢው መጽሏፉን የሚያነበው
እንዯ ምዕመን ከሆነ ይህን ሉቀበሌ ይችሊሌ። ነገር ግን ምዕመን ያሌሆነ ወይም (ምዕመን ሆኖም) ከ዗መናዊ የታሪክ
ጥናት አንጻር መጽሏፉን ሇማንበብ የተነሳ ሰው ይህን ታሪክ የሚቀበሌበት ምክንያት የሇም።
እናም ጸሏፊው የገዴሊቱን ትረካ እንዲሇ እያቀረበ ስሇ ታሪካዊ ሁነቶች ሲናገር ግን በእምነት እንጂ በማስረጃ
ሉዯገፉ የማይችለ ትረካዎችን ከተዋሥዖቱ እያስወጣ ቢሆን የተሻሇ ነበር እሊሇሁ።
4. የሏቅ እና የዴምዲሜ መጣረሶች
ማንኛውም ጸሏፊ በመጽሏፉ ውስጥ የሚ዗ረዜራቸውን መረጃዎች አንደ ከአንደ የማይጋጭ መሆኑን ማረጋገጥ
አሇበት። የሚጋጩ መረጃዎችን ሲያገኝ እንኳን ይህን ግጭት ሇአንባቢያን በግሌጽ አሳውቆ ከቻሇ የተጋጩትን መረጃዎች
ሇማስታረቅ መሞከር፣ ካሌሆነ የበሇጠ ተአማኒ የሆነውን ተቀብል ላሊኛውን ውዴቅ ማዴረግ፣ ሁሇቱም እኩሌ ተአማኒ
ሆነው ሲገኙ ዯግሞ ሁኔታውን በግሌጽ አስረዴቶ እና የራስን አስተያየት አስቀምጦ ወዯፊት አዱስ መረጃዎች ተገኝተው
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 8

ነገሩ እሌባት እንዱያገኝ ሇራስ እና ሇላልች ታሪክ ጸሏፊያን መሠረት መጣሌ እና የቤት ሥራ መተው ነው ያሇበት ብዬ
አምናሇሁ።
ነገር ግን ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ ውስጥ ብዘ ስሇ ተመሳሳይ ጉዲይ የተነገሩ እርስ በራሳቸው የሚቃረኑ እና
ጸሏፊውም ሇማስታረቅ ሳይሞክር የተቀበሊቸው መረጃዎች እንዱሁም ዴምዲሜዎች እናገኛሇን። ወዯፊት
በምንዲስሳቸው ርዕሶች ውስጥ ብዘ ይህን የመሰለ ጉዲዮችን የምናገኝ ቢሆንም ሇጊዛው ግን አንዴ ምሳላ እሰጣሇሁ።
አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በነበሩበት ዗መን በሸዋ የነበረውን የሃይማኖት ስርጭት፣ በተሇይ ዯግሞ የእስሌምናን ይዝታ
በተመሇከተ በተሇያዩ ቦታዎች እና ዏውድች ሊይ ጸሏፊው የሚሰጠን መረጃዎች አንደ ከአንደ የሚቃረን ሆኖ
እናገኘዋሇን።
‚(አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሙስሉሞችን ሊሇማግኘታቸው ምክንያት የሆነው) እስከ ዏፄ ዗ርዓ ያዕቆብ ዗መን
ዴረስ እስሌምና (እሳቸው ወዯ አስተማሩባቸው) ወዯ ሰሜን፣ ምዕራብ እና ዯቡብ ኢትዮጵያ በተጽዕኖ አዴራጊነት
ዯረጃ አሇመዴረሱ ነው።‛ (ገጽ 12)
ይህ መረጃ የቀረበው አሌሜዲ ‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በ13ኛው መክ዗ ከነበሩ እንዳት ሙስሉሞችን ሳያስተምሩና
ሳያጠምቁ ቀሩ?‛ ሲሌ ሊቀረበው ጥያቄ መሌስ ሇመስጠት ነው። ሇማሇት የተፈሇገው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ተ዗ዋውረው
ባስተማሩባቸው ቦታዎች (በተሇይም በሸዋ እና በዲሞት) እስሌምና ይህ ነው የሚባሌ ይዝታ አሌነበረውም ነው። አሇፍ
ብሇን ገጽ 30 ሊይ ስንሄዴ ስሇዙሁ ጉዲይ ላሊ መረጃ እናገኛሇን።
‚ይኩኖ አምሊክ (ወዯ ሸዋ መምጣቱ) ጠቅሞታሌ። በአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ስብከት ወዯ ክርስትና የገባው
የዲሞት መንግሥት ከሸዋ ጋር የነበረውን ጠሊትነት አስቀርቶታሌ። ይህም ሇሸዋዎች እፎይታን ሰጥቷሌ።‛ (ገጽ 30)
‚ከዙህም በተጨማሪ የዯቡቡ የሀገሪቱ ክፍሌ በኃያለ በዲሞት ንጉሥ መያዘና በሸዋ የሚገኙ ክርስቲያኖች
ረዲት ማጣታቸው በመንግሥቱ (ዚግዌ) ሊይ ቅሬታ እንዱያዴርባቸው አዴርጓሌ። . . . የሸዋ ሙስሉሞችም
የዲሞትን ጣዖት አምሊኪ ንጉሥ ጫና መቋቋም አቅቷቸዋሌ። የዲሞት ጫና ጋብ ያሇው ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት
ሏዋርያዊ አገሌግልት በኋሊ ነው። ይህም በኋሊ ዗መን የዯቡቡን ኃይሌ (ክርስቲያንና ሙስሉሞችን) ይዝ ሇተነሳው
ሇንጉሥ ይኩኖ አምሊክ ዕዴሌ ፈጥሮሇታሌ።‛ (ገጽ 304)
‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇይኩኖ አምሊክ የጠቀሙት ነገር ቢኖር ሇዚግዌ መንግሥት ዋና ተቀናቃኝ የነበረውን
የዲሞት መንግሥት ወዯ ክርስትና በመመሇሳቸው ሇይኩኖ አምሊክ ተቃዋሚ ሉሆነው አሇመቻለ ነው።‛ (ገጽ 510)
እዙህ ጋ የጸሏፊው አሊማ ይኩኖ አምሊክ እንዳት በሸዋ ዴጋፍ ሉያገኝ እንዯቻሇ ማስረዲት ነው። ከምንባቦቹ
እንዯምንረዲው አረማዊ የነበረው የዲሞት ንጉሥ ሞተሇሚ ወዯ ክርስትና መመሇስ በዲሞት እና በሸዋ መሃሌ ሰሊም
ፈጥሯሌ እያሇን ነው። በፊት ግን ሞተሇሚ በተዯጋጋሚ ሸዋን ይወርና ብዘዎችን እየማረከ ወዯ ግዚቱ ይወስዴ ነበር።
ሞተሇሚ ክርስትናን ሲቀበሌ ከሸዋ ጋር ሰሊም የሚፈጥረው የሸዋ ሰዎች ክርስቲያን ከሆኑ ነው። በተጨማሪም በሸዋ
የነበሩ ክርስቲያኖች በወቅቱ ይኩኖ አምሊክን አሸናፊ ሇማዴረግ የጎሊ አስተዋጽዖ የማዴረግ አቅም ያሊቸው አዴርጎ
አቅርቧሌቸዋሌ። ስሇዙህ ጸሏፊው እዙህ ጋር ሸዋ በወቅቱ የክርስቲያኖች የበሊይነት የሰፈነባት ግዚት ነበረች እያሇን ነው።
ወዯ ገጽ 52 ዯግሞ እንሇፍ።
‚በዙያ ዗መንም በሸዋ ዋናዎቹ ባሊባቶች ሙስሉሞችና አረማውያን (በተሇይም ጋፋቶች) ስሇነበሩ አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት ሇፖሇቲካ ጉዲይ የሚያሳምኗቸው አይዯለም።‛ (ገጽ 52)
‚. . . ራሱ ገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት የሚነግረን የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ቤተሰቦች በሸዋ በዙያን ጊዛ አናሳዎች
(minorities) ናቸው። አብዚኛው ስሌጣን የተያ዗ው በላልች ነው። . . . ምናሌባትም ዯግሞ ዚሬ ሸዋ የምንሇው
አብዚኛው ክፍሌ የጋፋቶች፣ የዲሞቶችና የይፋቶች የግዚት አካባቢ ነው። ክርስቲያኖቹ በእነዙህ መካከሌ አናሳ
ሆነው የሚኖሩ ናቸው። . . . በመሆኑም <የሸዋን ባሊባቶች አቡነ ተክሇ ሃይማኖት አስተባበሩ> የሚሇውን እውነት
ነው ብል መቀበሌ አስቸጋሪ ነው። ‛ (ገጽ 53-4)
እዙህ ጋ ዯግሞ የጸሏፊው ጥረት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ይኩኖ አምሊክን ሇምን ረዴተውት ሉሆን እንዯማይችሌ
ማስረዲት ነው። በሸዋ የነበሩት ባሊባቶች አቡነ ተክሇ ሃይማኖትንም ሆነ ይኩኖ አምሊክን የማይመስሎቸው
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 9

ሙስሉሞችና አረማውያን ስሇሆኑ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት እነዙህን ባሊባቶች አሳምነው ከይኩኖ አምሊክ ጋራ እንዱሰሇፉ
ሇማዴረግ አሇመቻሊቸውን ነው የሚነግረን።
እንግዱህ የተሇያየ ክርክር በተነሳ ቁጥር ስሇ አንዴ ጉዲይ የተሇያዩ መረጃዎችን ነው ጸሏፊው የሰጠን።
በመጀመሪያው መረጃ መሠረት እስሌምና በወቅቱ በሸዋ ይህ ነው የሚባሌ ይዝታ ካሌነበረው በሦስተኛው ምንባብ
እንዯገሇጸሌን የሸዋ ዋና ባሊባቶች ሙስሉሞች ሉሆኑ አይችለም። በሁሇተኛው ምንባብ መሠረት ሄዯን ክርስቲያኖች
በሸዋ ተጽዕኖ ሇመፍጠር የሚያስችሌ ይዝታ ነበራቸው ካሌንም ሦስተኛውን ምንባብ ተቃርነን መቆማችን ይሆናሌ።
በርግጥ የመጀመሪያውን እና ሦስተኛውን ምንባቦች በተወሰነ መሌኩ ማስታረቅ ይቻሌ ይሆናሌ። በወቅቱ
መካከሇኛውና ምዕራብ ሸዋ የአረማውያን የበሊይነት የሰፈነበት ሲሆን በሸዋ ምሥራቅ የሚገኘው ይፋት ዯግሞ
የሙስሉሞች የበሊይነት የሰፈነበት አካባቢ ነበር፤ ምሥራቅ ሸዋም በይፋት የሙስሉም ሥርወ መንግሥት የመሠረቱት
የዋሊስማ ቤተሰብ መቀመጫ ነበር።1 በዙህ መሌኩ ስንመሇከተው ሁሇቱ አባባልች ሉታረቁ ይችሊለ። ነገር ግን ይህ
ሲሆን ሁሇተኛው ምንባብ በፍፁም ከቀሩት ከሁሇቱ ጋር ሉታረቅ አይችሌም።
በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በተመሇከተ ፕ/ር ታዯሰ ታምራት የሚነግሩንም ከሁሇተኛው ምንባብ ጋር የሚቃረን
ነው። የዲሞት ንጉሥ ክርስትናን ስሇተቀበሇ ከሸዋም ሆነ ክክርስቲያኑ የይኩኖ አምሊክ መንግሥት ጋር የፈጠረው ሰሊም
የሇም፤ እንዱያውም ዲሞት ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ስብከት በኋሊም አረማዊ ሆኖ መቆየቱን ነው ፕ/ሩ የሚነግሩን።
ይሌቁንም ይኩኖ አምሊክ የሸዋን ግዚቶች በማስገበር የዲሞት መንግሥት በአካባቢው የነበረውን የበሊይነት ወስድበታሌ።
በኋሊ ዗መን በዏምዯ ጽዮን ጊዛ ዲሞት ፈጽሞ የክርስቲያኑ መንግሥት ገባር እስኪሆን ዴረስም በሁሇቱ መንግሥቶች
መሃሌ ሰሊም አሌነበረም። በሸዋም በይኩኖ አምሊክ እና በተተኪዎቹ በተሇይ በአቡነ ያዕቆብ አማካይነት ክርስትና
እስኪስፋፋ ዴረስ የክርስቲያኖች ቁጥር አናሳ፣ ኃይሊቸውም ዯካማ ነበር።2
ስሇዙህ የሸዋ ክርስቲያኖች ከዲሞት ጋር ሰሊም ሇመፍጠርም ሆነ ይኩኖ አምሊክን በዚግዌው ንጉሥ ሊይ ዴሌ
ሇማቀዲጀት ሉጫወቱ የሚችለት ሚና ዜቅተኛ ነው የሚሆነው።ይኩኖ አምሊክ ከሸዋ አረማውያን እና ሙስሉሞች
ዴጋፍ ማግኘቱም ስሊስገበራቸው እንጂ የሃይማኖት ጉዲይ አሌነበረም። ያ ቢሆን በተሇይ ሇአረማውያኑ ከይኩኖ አምሊክ
ይሌቅ የዲሞቱ ንጉሥ ነበር የሚቀርባቸው።
ከዙህ የምንረዲው ጸሏፊው ይህን ጉዲይ በተመሇከተ እንዯተነሳው ክርክርና ዏውዴ የተሇያዩ፣ እርስ በራሳቸው
የሚጣረሱ የታሪክ ዴምዲሜዎችን ያስቀመጠ መሆኑን ነው። ላልችም ጥቂት የማይባለ፣ ይህን የመሰለ መጣረሶች
በመጽሏፉ ይገኛለ። ወዯፊት እንመሇከታቸዋሇን።
በዙህ ክፍሌ ያነሳናቸው ጉዲዮች ከይ዗ት ይሌቅ አካሄዴ ሊይ ትኩረት ያዯረጉ፣ ሉታረሙ ይገባሌ ብዬ ያሰብኋቸውን
የችግር ዓይነቶች ያነሳሁባቸው ነበሩ። ትኩረቴ አካሄደ ሊይ ስሇነበረም ችግሮችን ስጠቅስ ሇምሳላ ያህሌ ብቻ ነበር።
በሚቀጥለት ክፍልች ግን በመጽሏፉ ውስጥ የተወሱ ዏቢይ የታሪክ ጉዲዮችን አንዴ በአንዴ እያነሳን በጥሌቀት
እንመሇከታሇን። በዙህ ክፍሌ ያሊነሳናቸውን የአመክንዮ ስህተት ያሇባቸውን ክርክሮች እና በመጽሏፉ ውስጥ የሚገኙትን
ተጣርሶዎች በየዏውዲቸው እያነሳን እናያቸዋሇን።

1
Trimingham, J.S. (1952), Islam In Ethiopia, Oxford University Press, pp. 64-5
2
Taddesse Tamrat (1968), Church and State in Ethiopia, pp. 230-40
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 10

2. የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሕይወት የጊዛ ሰላዲ


‘አቡነ ተክሇ ሃይማኖት መቼ ምን ሠሩ፣ የት ነበሩ?’ የሚሇውን በተመሇከተ ጸሏፊው በተሇያዩ የመጽሏፉ ገጾች
የተሇያዩ፣ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ነገሮችን ነው የሚነግረን። ይህን ሇማየት እንዱረዲን በመጀመሪያ ጸሏፊው ገጽ 510
እንዱሁም ገጽ 600 ሊይ ያስቀመጠውን የጊዛ ሰላዲ እንመሌከት። አቡነ ተክሇ ሃይማኖት፡
- በ1206 – ተወሇደ።
- በ1220 – ዱቁና ተቀበለ።
- በ1236 – ቅስና ተቀበለ (በዙያውም የሸዋ ሉቀ ካህናት ሆነው ተሾሙ)፤ ወሊጆቻቸውም ብዘ ሳይቆዩ አረፉ።
- በ1243 – ከሰባት አመታት የቤት ውስጥ ቆይታ በኋሊ ሇስብከት ወጡ። ሦስት ዓመት ያህሌ በከታታ፣ አንዴ ዓመት
ያህሌ ዯግሞ በዝረሬ አስተማሩ።
- በ1247 – ወዯ ዲሞት ሄደ፥ ሞተልሚን እና ሕዜቡን አጥምቀው ሇ12 ዓመታት በዙያው ቆዩ።
- በ1259 – ከዲሞት ወጥተው ግሼ ወዯሚገኘው የአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም አመሩ። በዙያ አሥር አመታትን
አሳሇፉ።
- በ1269 – ከአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም ወጥተው ወዯ ሏይቅ እስጢፋኖስ ገዲም ሄደ። በዙያም እንዱሁ አሥር
አመታትን አሳሇፉ።
- በ1279 – ከሏይቅ ወጥተው ወዯ ዯብረ ዲሞ ተጓዘ፤ ሇሁሇት አመታትም በዙያ ቆዩ።
- በ1281 – ወዯ ሸዋ ተመሇሱ። ሇሰባት አመታት ተ዗ዋውረው አስተማሩ።
- በ1288 – ዯብረ አስቦን መሠረቱ።
- በ1298 – በዋሻ ተወስነው መጸሇይ ጀመሩ።
- በ1305 – አረፉ።3
እንግዱህ ይህን በአዕምሯችን ይ዗ን (ወይም ተመሌሰን እያየን) አንዲንዴ ምንባቦችን ከመጽሏፉ እያወጣን እንመሌከት።
የመጽሏፉ ገጽ 32 ሊይ ሄዯን ብንመሇከት እንዱህ የሚሌ ንባብ እናገኛሇን።
‚ይኩኖ አምሊክ የነገሠው በ1263 ዓ.ም. ነው። በዙህ ጊዛ ዯግሞ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ገና ከዝረሬ ወጥተው
በስብከተ ወንጌሌ አሌተሰማሩም ነበር።‛
ከ዗ጠኝ ገጾች በኋሊ ዯግሞ ስሇ ተመሳሳይ ጊዛ የተነገረ ላሊ ነገር እናገኛሇን።
‚ይኩኖ አምሊክ ወዯ ሥሌጣን ሲመጣም እርሳቸው በሸዋ እና በዲሞት በስብከት አገሌግልት ሊይ ስሇነበሩ
ሇእርሱ ኃይሌ የሚያሰባስቡበት ዕዴሌ አሌነበራቸውም።‛ (ገጽ 41)
በግሌጽ ማየት ኣንዯሚቻሇው ሁሇቱ ምንባቦች እርስ በእርሳቸውም ሆነ ዯራሲው በኋሇኛው የመጽሏፉ ክፍሌ
ካስቀመጠው የጊዛ ሰላዲ ጋር አይጣጣሙም። ከሊይ እንዲየነው ጸሏፊው ራሱ ባስቀመጠው የጊዛ ሰላዲ መሰረት አቡነ
ተክሇ ሃይማኖት ሇስብከት የወጡት ይኩኖ አምሊክ ከመንገሡ ከ20 ዓመታት በፊት በ1243 ዓ.ም. ነው። በ1263 ዯግሞ
ከዲሞት ስብከታቸው ተመሌሰው በአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም ነበሩ።
ነገሩ በዙህ አያበቃም። ስሇዙሁ ዗መን ላሊም የሚሇን ነገር አሇ። ገጽ 566 ሊይ ብንሄዴ
‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የሸዋ ሉቀ ካህናት ሲሆኑ ዕዴሜያቸው 55 ዓመት ነበር።‛
የሚሌ ዓረፍተ ነገር እናገኛሇን። መጀመሪያ ባስቀመጥነው የጊዛ ሰላዲ መሰረት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት 55 ዓመት የሞሊቸው
በ1261 ነው። የሸዋ ሉቀ ካሀናት ሆነው የተሾሙት ዯግሞ ቅስና በተቀበለ ጊዛ ነው – በ1236 ዓ.ም.፣ በ30 ዓመታቸው። ይህ
እንዳት ይታረቃሌ?
ላሊ ምሳላ። ገጽ 402 ሊይ የዯብረ ሉባኖሱ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ይኩኖ አምሊክ ይነግሥ
዗ንዴ በጸልት አግ዗ውታሌ ማሇቱን ጠቅሶ ይህ ሇምን ሉሆን እንዯማይችሌ እንዯሚከተሇው ያብራራሌ።

3
ጸሏፊው ‘አራቱ ኃያሊን’ በተሰኘው በቀዯመው መጽሏፉ (ገጽ 38-41) ስሇ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ያቀረበው ሏተታ እና የጊዛ ሰላዲ በዙህ መጽሏፍ
ከቀረበው ጋር ይሇያያሌ። ምናሌባት ‘አራቱ ኃያሊን’ን ካ዗ጋጀ በኋሊ ሏሳቡን የሚያስቀይረው ነገር ገጥሞት ይሆናሌ።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 11

‚...በትክክሌም ስናየው ይኩኖ አምሊክ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ጸሌዩሌኝ ሇማሇት የሚችሌበት ጊዛ ሊይ
አሌነበረም። ገና አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በአካባቢው መታወቅ አሌጀመሩምና። የሀገረ መንግሥትን ነገር ሉያውቁ
የሚችለት ወዯ አምሏራው ሀገር ከገቡ በኋሊ መሆን አሇበት። አንዲንዴ መዚግብት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ይኩኖ
አምሊክን ያነገሡት በሏይቅ 12 ዓመት ከቆዩ በኋሊ ነው ይሊለ። ይህ ከሆነ ዯግሞ ይኩኖ አምሊክ ከነገሠ ከ32 ዓመት
በኋሊ ይሆናሌ።‛
በጸሏፊው የጊዛ ሰላዲ መሰረት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከሏይቅ የወጡት በ1279 ዓ.ም. ነው። ይህ ዯግሞ ይኩኖ
አምሊክ ከነገሠ ከ16 ዓመታት በኋሊ እንጂ ከ32 ዓመታት በኋሊ አይዯሇም።
እነዙህ መጣረሶች የመነጩት በዋነኝነት ጸሏፊው እርሱ የማይስማማባቸውን ተረኮች ፉርሽ ሇማዴረግ ከሚያዯርገው
ጥረት ነው። ከሊይ ከቀረቡት ምንባቦች ሦስቱ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇምን ይኩኖ አምሊክን ረዴተውት ሉሆን እንዯማይችሌ
ሇማስረዲት በተዯረጉ ሙከራዎች ሊይ የተፈጠሩ ናቸው። ጸሏፊው ፊቱ ያሇውን ክርክር ሇማሸነፍ ሲሞክር የመጽሏፉን
አጠቃሊይ የይ዗ት ስምምነት መስዋዕት አዴርጎ በማቅረብ ጭምር ነው። የሚገርመው ይህን ያህሌ ዋጋ መክፈሌ ሳይጠበቅበት
ብዘዎቹን ክርክሮች ከሊይ በተቀመጠው የጊዛ ሰላዲ ሊይ ተመስርቶ ማሸነፍ እየቻሇ ሇምን ዋጋውን መክፈሌ እንዯሚመርጥ
ነው።
ክዙህ በተጨማሪ ጸሏፊው እንዱህ ዓይነት ክርክሮችን ሇማሸነፍ ሲሌ ካለት መረጃዎች መካከሌ ሇያ዗ው ክርክር
የሚስማሙትን ብቻ እየመረጠ ማቅረብም ይችሌበታሌ። ላሊ ቦታ ሊይ ጠቃሚ ሆነው ሲያገኛቸው ዯግሞ የዯበቃቸውን እና
ቅዴም ያጋጠመውን ክርክር ሇመርታት ከተጠቀመባቸው መረጃዎች ጋር የሚቃረኑ ላልች መረጃዎችን መዜዝ
ይጠቀምባቸዋሌ።
ምሳላ ሊቅርብ። ገጽ 31 ሊይ ይኩኖ አምሊክ ሲነግሥ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የት እንዯነበሩ የሚገሌጥ እና ሇምን
አንግሠውት ሉሆን እንዯማይችሌ ሇማስረገጥ (አሁንም) ላሊ መረጃ ቀርቧሌ። ይህ ገና የመጽሏፉ የመጀመሪያ ክፍሌ ሊይ
ሲሆን ጽሏፊው ከሊይ ያሇውን የጊዛ ሰላዲ ሇአንባቢው አሊስተዋወቀም።
‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የተወሇደት በ1206 ዓ.ም. አካባቢ ነው። በ1417 ዓ.ም. በዯብረ ሉባኖስ ገዲም በእጨጌ
ዮሏንስ ከማ አማካይነት የተጻፈው ገዴሌ እንዯሚነግረን ይኩኖ አምሊክ ሲነግስ እርሳቸው በዝረሬ በሚገኘው
የቅደስ ሚካኤሌ ቤተ ክርስቲያን በአባታቸው ምትክ እያገሇገለ ነበር። የፓሪሱ ዛና መዋዕሌ እንዯሚተርከው ዯግሞ
ይኩኖ አምሊክ በ1263 ዓ.ም. ሲነግስ እርሳቸው የ55 ዓመት ሰው ነበሩ። ከዙህ በኋሊ ነው ከአቡነ ጌርልስ ክህነት
ተቀብሇው በከታታ፣ በዯቡብ ኢትዮጵያ እና በዲሞት ያገሇገለት።‛
አንባቢው ይህን ክርክር አይቶ እና ተቀብል ንባቡን ቀጥል ገጽ 401 ሊይ ሲዯርስ (በርግጥ ግራ ሳይጋባ እዙህ መዴረሱን
አጥብቄ እጠራጠራሇሁ) ጸሏፊው
‚አጭሩ (የፓሪሱ) ዛና መዋዕሌ ይኩኖ አምሊክ ነግሶ ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ጋር ቃሌ ኪዲን ሲያዯርግ አቡነ
ተክሇ ሃይማኖት የ55 ዓመት ሰው ነበሩ ይሊሌ...የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ እንዯሚነግረን እግዙእ ኀረያ እና ፀጋ ዗አብ
ያረፉት (ስሇሆነም አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ቅስና የተቀበለት) . . . በ1263 ዓ.ም. ነው። ከሊይ ያለትን (ላልች)
መዚግብት ስናመሳክር ግን አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ዱቁናና ቅስና የትቀበለት ከይኩኖ አምሊክ (ንግሥና) በፊት ነው።
(ቅስና የተቀበለት) (ከይኩኖ አምሊክ ዗መን) ቢያንስ 30 ዓመት ቀዴመው . . . ከ1228 እስከ 1236 ዓ.ም. ባሇው
዗መን ነው።‛
ብል ሲያጠቃሌሌ እንዴታሇሇ ቢሰማው አይገርምም። ቢያንስ እኔ ማታሇሌ እንዯተሞከረብኝ ተሰምቶኛሌ። ይህ ዓይነቱ ነገር
እዙህ ጋር ብቻ ሳይሆን በላልችም የመጽሏፉ ገጾች እና ጉዲዮች የሚገኝ ነው።
የሁነቶች የጊዛ ሰላዲ መ዗በራረቅ በአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሕይወት ብቻ የተገዯበ አይዯሇም። ላልች ታሪካዊ
ሁነቶችንም በተመሇከተ ተመሳሳይ ችግሮች በመጽሏፉ ውስጥ ይገኛለ። ሇምሳላ የቅደስ ሊሉበሊን መዋዕሌ በተመሇከተ
ጸሏፊው (የተሇያዩ ምንጮችን እየጠቀሰ) የተሇያዩ፣ የሚጣረሱ መረጃዎችን ነው የሚሰጠን። የሚከተለትን፣ ከተሇያዩ
የመጽሏፉ ገጾች የተወሰደትን ምንባቦች እንመሌከት።
‚(ቅደስ ሊሉበሊ ሇዯብረ ሉባኖስ ዗ሺምዚና ያዯረጋቸው) የርስት ስጦታዎች በ1196 እና በ1201 ዓ.ም.
የተበረከቱ ናቸው። . . . እንዯ ገዴሇ ቅደስ ሊሉበሊ ከሆነ ሊሉበሊ የነገሠው በ1178 ዓ.ም. ነው። ውቅር አብያተ
ክርስቲያናቱንም የፈጸመው በ1201 ዓ.ም. መሆኑን ይገሌጣሌ።‛ (ገጽ 278-9)
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 12

‚መጀመሪያ ክብረ ነገሥት በሊሉበሊ ዗መን አቡነ ጊዮርጊስ ጳጳስ እያለ በ1218 ዓ.ም. ከግብጽ ወዯ ኢትዮጵያ
እንዱገባ ተዯረገ።‛ (ገጽ 302) (ከታች፣ በኅዲግ ማስታወሻ ቁ. 802 ‚ይህ ዗መን ሊሉበሊ የርስት ስጦታውን ሇዯብረ
ሉባኖስ ዗ሺምዚና የሰጠበት ዗መን ነው። ኮንቲ ሮሲኒ ይህንን ዗መን በ1218 አዴርገውታሌ።‛ ሲሌ ይጨምርበታሌ።
(ምንጭ፡ L’Evangelo d’Oro))
‚ቅደስ ሊሉበሊ ያረፈው በ1173 ዓ.ም. ነው።‛ (ገጽ 390፣ ምንጭ፡ ባሕረ ሏሳብ)
‚በ1182 ዓ.ም. ሳሊሕዱን ኢየሩሳላምን ሲቆጣጠር ሇኢትዮጵያውያን ቅደሳት መካናትን የሰጠው በንጉሥ
ይምርሏነ ክርስቶስ ዗መን ነው።‛ (ገጽ 286፣ ምንጭ፡ Ethiopia, The Red Sea and the Horn)
‚በግብጽ ፓትርያርኮች ታሪክ በፓትርያርክ ገብርኤሌ ዗መን (1124-1139 ዓ.ም.) . . . የንጉሥ ሏርቤ
መሌእክተኞች (ተጨማሪ ጳጳስ ከኢትዮጵያውያን መካከሌ ይሾም የሚሌ ጥያቄ) ሇሡሌጣኑ አቅርበው ነበር።‛ (ገጽ
287፣ ምንጭ፡ History of the Patriarchs of the Egyptian Church, Vol, II)
ይምርሏነ ክርስቶስ፣ ሏርቤ እና ሊሉበሊ ተከታታይ ነገሥት ናቸው። በመጀመሪያ በ1173 ያረፈው ሊሉበሊ ከ1178 እስከ
1201 ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱን ሉያንጽ አይችሌም፤ በ1218ም ሥሌጣን ሊይ ሉኖር አይችሌም። ሁሇተኛ ንጉሥ ሊሉበሊ
ከ1178 እስከ 1201 በዘፋኑ ከነበረ ወይም በ1173 ከሞተ የቀዲሚው ቀዲሚ የነበረው ይምርሏነ ክርስቶስ በ1182 በሕይወቱ እና
በዘፋኑ ሉኖር አይችሌም። በተመሳሳይ ይምርሏነ ክርስቶስ በ1182 ከነበረ የሱ ተከታይ ሏርቤ ከ1124-1139 ባሇው ዗መን
ነግሦ ሉሆን አይችሌም። በተጨማሪም በመጀመሪይው ጥቅስ መሠረት ሊሉበሊ ሇዯብረ ሉባኖስ ዗ሺምዚና የርስት ስጦታ
ያዯረገው በ1196 እና በ1201 ሲሆን በሁሇተኛው ጥቅስ መሠረት ግን ይህ የሆነው በ1218 ነው። በ1218 የተዯረገው ላሊ የርስት
ስጦታ ነው እንዲንሌ የመጀመሪያው ጥቅስ የተዯረጉት ስጦታዎች ሁሇት መሆናቸውን በግሌጽ ነግሮናሌ።
ከዙሁ ርዕስ ሳንወጣ ይምርሏነ ክርስቶስን በተመሇከተ ከሊይ ከቀረበው (በ1182 ሥሌጣን ሊይ እንዯነበረ ከሚነግረን)
ምንባብ (ገጽ 286) በተጨማሪ ላልችም በአንዴ ንጉሥ ዗መን ተዯርገው ሉሆኑ የማይችለ ነገሮች ከእርሱ ጋር ተያየ዗ው
ተነስተዋሌ። በ1166 ሇግብጹ ከሉፋ ዯብዲቤ መጻፉ ተነግሯሌ፤ በ1084 ዯግሞ (ሥርግው ሏብሇ ስሊሴ እና አባ አየሇ ተክሇ
ሃይማኖት ተጠቅሰው) ወዯ ግብጽ መሇእክተኞች የሊከውም እርሱ ነው ተብሎሌ። መቼም በ1084 ዯብዲቤ የጻፈ ንጉሥ
በ1166 እና በ1182 በሕይወቱና በሥሌጣኑ ሉኖር አይችሌም።
በርግጥ ጸሏፊው እነዙህን ነገሮች ፈጥሯቸው ሳይሆን ከላልች መጻሕፍት ወስዶቸው ነው። ያ አይዯሇም ችግሩ። አንዴ
ጸሏፊ ሇሚጽፈው ታሪክ አንዴ የጊዛ ሰላዲ አበጅቶ ነው መነሳት ያሇበት። እዙህ ጋ ግን ጸሏፊው ከሊይ የተጠቀሱትን እርስ
በእርሳቸው የሚጣረሱ የታሪክ ዗ገባዎች ያሇምንም የማስታረቅ ሙከራ እርሱ ሉጽፍ ሇተነሳው ታሪክ መሠረት ሇመጣሌ
እንዱሁም ታሪኩን ሇማዋቀር እንዯ ግብዏት ነው የተጠቀመባቸው። ሇምሳላ ከገጽ 390 ሊይ የወሰዴነው ምንባብ ‘አቡነ
ተክሇ ሃይማኖት መቼ ዱቁና ተቀበለ?’ የሚሇውን ጥያቄ ሇመመሇስ በተዯረገው ሙከራ ውስጥ እንዯ ግብአት ሆኖ ያገሇገሇ
ነው። ገጽ 278 ሊይ የተጠቀሰው ቀዲማዊ ምንጭ (ጥንታዊ መዜገብ ሊይ የተመ዗ገበው የርስት ስጦታ) ከዙህ የሚቃረን ሆኖ
ሳሇ፣ ጸሏፊው ሁሇቱን ምንጮች ሇምን ሇማስታረቅ እንዲሌሞከረ፣ ማስታረቁም ካሌሆነሇት ሇምን ቀዲማዊ ሇሆነው ምንጭ
ቅዴሚያ እንዲሌሰጠ እንቆቅሌሽ ነው የሆነብኝ።
ችግሩ በሁሇቱ (ወይም) በሦስቱ ነገሥት መዋዕሌ ብቻ የተወሰነ አይዯሇም። በአጠቃሊይ የዚግዌ ሥርወ መንግሥትን
ቆይታ በተመሇከተም የተወሰነ የጊዛ ሰላዲ የሇም። በራሱ በመጽሏፉ ገጽ 275 ሊይ እንዯተገሇጸው ይህ ጉዲይ በታሪክ
ተመራማሪዎች መካከሌ ስምምነት የተዯረሰበት አይዯሇም። የሥርወ መንግሥቱን ምሥረታ በተመሇከተ የተቀመጡት
ግምቶች ከ960 ዓ.ም. እስከ 1143 ዓ.ም. ባሇው ዗መን ውስጥ የሚወዴቁ ናቸው። ጸሏፊው በእነዙህ ዓመታት መሃሌ
የተፈጸሙ ታሪካዊ ሁነቶችን ሇዚግዌ ነገሥት ሲሰጥ ነገሩ በርግጥም በነሱ ዗መን መፈጸሙን ሇመወሰን የሚያስችሌ የጊዛ
ሰላዲ ቀዴሞ ሳያ዗ጋጅ ነው። ሇምሳላ ገጽ 284 ሊይ በ11ኛው መክ዗ በዓባይ ምክንያት ከግብጽ ጋር የተዯረገውን ንግግር
‚በእነሱ ዗መን የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም‛ ብል ይጠቅሰዋሌ። ነገር ግን በብዕሇ ነገሥት ወይም በኮንቲ ሮሲኒ ግምት
መሠረት ብንሄዴ ይህ ከዚግዌ ዗መን በፊት የሆነ ነገር ነው።
ይህን በተመሇከተ አንዴ የመጨረሻ ምሳላ ሌስጥ። የሚከተሇው ምንባብ ገጽ 739 ሊይ የሚገኝ ነው። ከምንባቡ በፊት
አንዴ የብራና መጽሏፍ ተጠቅሷሌ። መጽሏፉ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን እረፍት በተመሇከት ሁሇት መረጃዎችን ሰጥቷሌ።
አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ያረፉት፡
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 13

1. በያግብዓ ጽዮን ዗መን በስምንተኛው ዓመት ነው። (ያግብዏ ጽዮን የነገሠው ሇ዗ጠኝ ዓመታት መሆኑንም
ይገሌጣሌ።)
2. ከሌብነ ዴንግሌ 13ኛ ዓመት 228 ዓመታት በፊት ነው።
በእነዙህ ፍንጮች መሰረት የዕረፍታቸው ጊዛ ሲሰሊ በትክክሌ በ1285 ዓ.ም. ይሆናሌ። ነገር ግን (በሚቀጥለት
የመጽሏፉ ገጾች እንዯምናየው) ጸሏፊው የተቀበሇው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በ1305 አርፈዋሌ የሚሇውን የታዯሰ ታምራትን
ዴምዲሜ ነው። ስሇዙህ የብራና መጽሏፉን መረጃ እርሱ ከዯረሰበት ዴምዲሜ ጋር በሚከተሇው መንገዴ ሇማስማማት
ይሞክራሌ።
‚ምናሌባት ግን የያግብዏ ጽዮን ሌጆች የነገሡበትን ዗መን ሇያግብዏ ጽዮን የመስጠት ሌማዴ ስሊሇ የያግብዏ
ጽዮን የመጨረሻ ዓመት የተባሇው በመጨረሻው ሌጁ በውዴም ረዓዴ የመጨረሻ ዓመት ሇማሇት ሳይሆን
አይቀርም።‛
በመጀመሪያ ጸሏፊው አሇ ያሇው ‚የያግብዏ ጽዮን ሌጆች የነገሱበትን ዗መን ሇያግብዏ ጽዮን የመስጠት ሌማዴ‛ በየት
እንዲሇ አሌነገረንም። ግን እንዱህ ዓይነት ሌማዴ አሇ እንኳን ብንሌ ምንም የሚቀየር ነገር አይኖርም። ምክንያቱም አንዯኛ
የብራናው መጽሏፍ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ያረፉት በያግብዏ ጽዮን ‚የመጨረሻ ዓመት‛ ነው አይሌም፤ በያግብዏ ጽዮን
‚ስምንተኛ ዓመት‛ ነው ይሊሌ እንጂ። ዯግሞም መጽሏፉ ራሱ የያግብዏ ጽዮንን ዗መን በ዗ጠኝ ዓመታት ስሇሚወስነው
የሌጆቹን ዗መን ሇሱ ሰጥቶት ሉሆን ይችሊሌ የሚያስብሌ ክፍተት የሇም። ሁሇተኛ፡ ብራናው ‚የመጨረሻ ዓመት‛ ብል
እንኳን ቢሆን ላሊኛው፣ ከሌብነ ዴንግሌ 13ኛ ዓመት የሚነሳው ሌኬት የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን እረፍት 1285 ሊይ ነው
የሚያዯርገው።
ይህ የሚያሳየን ብራናው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የእረፍት ዗መን በተመሇከተ የማያዯናግር መረጃ ማስቀመጡን ነው።
ስሇዙህ ጸሏፊው ከብራናው የጊዛ ሰላዲ ጋር የማይስማማ ከሆነ ብራናው ያሊሇውን ነገር ሉያስብሇው ከመሞከር ይሌቅ
አሇመስማማቱን ገሌጦ ይህን አቋሙን ከብራናው የበሇጠ ተአማኒ በሆኑ መረጃዎች መዯገፍ ነው የነበረበት።
ከጊዛ ሰላዲ ርዕስ ሳሌወጣ ሁሇት አስተውልቶች ሊክሌ።
አንዯኛ፡ በሁለም ገዴሊት መሠረት ሞተሇሚ እግዙእ ኀረያን ሉያገባ ከነበረበት ጊዛ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዲሞት
መጥተው ከሕማሙ እስኪፈውሱት ዴረስ ያሇው ዗መን 25 ዓመት ነው። ይህ ማሇት የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ዕዴሜ በወቅቱ
ገና 25 ቢሆን ነው። ጸሏፊው ይህን ሁለም ገዴሊት የሚተባበሩበትን ጉዲይ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የጊዛ ሰላዲ ሲበይን
ከግምት ውስጥ አያስገባውም። ይህ በጣም ትሌቅ ጉዴሇት ይመስሇኛሌ። ነገሩን ባይቀበሇው እንኳን ነገሩን ከስላቱ
ከማስወጣቱ በፊት ያሌተቀበሇበትን ምክንያት ማስረዲት ይጠበቅበት ነበር።
የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሕይወት የጊዛ ሰላዲ ይህን መሰረት አዴርጎ ቢሰሊ ቅስና የተቀበለት በ22 ዓመታቸው
ይሆናሌ። ጸሏፊው በኅዲግ ማስታወሻ ቁ. 1182 እንዯገሇጸው ከዙህ ጋር የሚስማሙ ገዴሊት አለ።
‚አብዚኞቹ የዯብረ ሉባኖሱን ቅጅ የሚከተለ ቅጅዎች በወሊጆቻቸው ቤት የኖሩት ሇ22 ዓመታት መሆኑን
ይገሌጣለ። ቅስና የተቀበለት ወዯ ዲሞት ከመውረዲቸው በፊት ነው። ያ ከሆነ ቅስና የተቀበለት በ22 ዓመታቸው
አካባቢ ነው። የሚጣቁ ቅጅ ግን በ30 ዓመታቸው ነው ይሊሌ። የሏይቁ እና የጣና ቂርቆሱ ቅጅዎች ዕዴሜያቸውን
አይናገሩም። ከጥንታዊነቱ አንጻር የሚጣቁን መቀበለ ይሻሊሌ።‛ (የኅዲግ ማስታወሻ ቁ. 1182)
ጸሏፊው ‚ከጥንታዊነቱ አንጻር የሚጣቁን መቀበለ ይሻሊሌ።‛ ይበሌ እንጂ የሚጣቁን ሊሇመቀበሌ ሦስት ምክንያቶች
አለን። አንዯኛ ያን ያህሌ ጥንታዊ ከሚባለት ገዴሊት የሚመዯብ አይዯሇም፣ የ18ኛው መቶ ክፍሇ ዗መን ቅጅ ነው። ማሇትም
ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት እረፍት ቢያንስ የ400 ዓመታት በኋሊ፣ ከመጀመሪያው ገዴሌ ዯግሞ ቢያንስ ከ300 ዓመታት በኋሊ
የተጻፈ ገዴሌ ነው። ሁሇተኛ ጸሏፊው ስሇገዴለ በጻፈው ሏተታ እንዯገሇጠው ገዴለ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ቅስና የተቀበለት
በይኩኖ አምሊክ ዗መን ነው ይሊሌ። ይህ ማሇት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት 50ዎቹ ውስጥ እያለ ነው፣ ስሇዙህ (ጸሏፊው ተሳስቶ
ካሌሆነና) በርግጥም ገዴለ ቅስና የተቀበለት በ30 ዓመታቸው ነው የሚሌ ከሆነ ራሱን በራሱ እየተጣረሰ ነው። ሦስተኛ
ዯግሞ ገዴለ የተነሳንበትን እና ሁለም ገዴልች (ራሱን ጨምሮ) የሚስማሙበትን አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዲሞት
ሲዯርሱ 25 ዓመታቸው ነበር ከሚሇው ትረካ ጋራ ይጣረሳሌ።
በላሊ በኩሌ ግን በተሇይ ‚አብዚኞቹ የዯብረ ሉባኖሱን ቅጅ የሚከተለ ቅጅዎች‛ ከተባለት መካከሌ ራሱ የዯብረ
ሉባኖሱ ቅጅ የሚገኝበት ከሆነ፣ የእነሱ ትረካ በ25 ዓመታቸው ወዯ ዲሞት ሄደ ከሚሇው ትረካ ጋራ የተስማማ በመሆኑ
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 14

እነሱን መቀበለ የተሻሇ ይመስሇኛሌ። በነገራችን ሊይ ጸሏፊውም ከሊይ በጠቀስሁት ‘አራቱ ኃያሊን’ በተሰኘው መጽሏፉ (ገጽ
38) ሊይ ስሇቅደሱ ባቀረበው ሏተታ ይህን ተቀብል ‚የመጀመሪያውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በአካባቢያቸው ተምረው
በ22 ዓመታቸው በ1229 ዓ.ም. ከቤት ወጡ።‛ ሲሌ ጽፏሌ።
በዙህ መንገዴ ስንሄዴ ከቅስናቸው በኋሊ ሇ7 ዓመታት በወሊጆቻቸው ቤት ተቀመጡ የሚሇው ትረካ ፉርሽ ይሆናሌ።
ይሌቁንም ከዙያ በኋሊ ብዘ ሳይቆዩ ሇስብከት ወጥተዋሌ። ሦስት ዓመት በከታታ፣ ዗ጠኝ ወራት በይፋት ቆይተው ወዯ
ዲሞት አምርተዋሌ። በዙያ 12 ዓመት ከቆዩ በኋሊ በ1243 ዓ.ም. ዯግሞ ወዯ አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም ሄዯው 10 ዓመት፣
ከዙያ ዯግሞ በሏይቅ ላሊ 10 ዓመታትን አሳሌፈው በ1263 ወዯ ዯብረ ዲሞ ያመራለ (በዙህ ትረካ መሠረት አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት በሏይቅ ቆይታቸው ከይኩኖ አምሊክ ጋራ የመገናኘት ዕዴሊቸው ሰፊ ነው)። ከዙህ በኋሊ በትግራይ ገዲማት ብዘ
ገዴሊት ኣንዯሚለት ሇ12 ዓመታት ቢቆዩ እንኳን (ጸሏፊው 2 ዓመታት ቆዩ ነው የሚሇው፤ ነገር ግን እንዱህ የሚሌ የገዴሇ
ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ የሇም) በ1275 ወዯ ሏይቅ፣ ከዙያም ወዯ ሸዋ ይመሇሳለ። በሸዋ ተ዗ዋውረው ሇማስተማር እና ዯብረ
አስቦን ሇመመስረት ገና 30 ዓመት ይኖራቸዋሌ።
ነገር ግን ይህ ብዘ ምርምር የሚሻ ጉዲይ ነው። የጻፍሁትም እንዯ አንዴ ሉሆን የሚችሌ ነገር ነው እንጂ፣ በርግጥም
ታሪኩ ይህ ነው ሇማሇት አይዯሇም።
ሁሇተኛ፡ ጸሏፊው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከዲሞት መሌስ ወዯ አምሏራ ሄዯው በአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም ሇአሥር
ዓመታት ተቀመጡ ቢሌም ፕ/ር ታዯሰ ታምራት ይህን አይቀበለትም።4 በገዴለ የተጠቀሱት አባት አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ
዗ጋስጫ ናቸው ብሇው ያስባለ፤ አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ጋስጫ ዯግሞ በውዴም ረአዴ ዗መን (1292-1306) ገና ወጣት
የነበሩ ሲሆን በአንጻሩ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በዙያ ዗መን በዯብረ አስቦ የዕዴሜያቸውን የመጨረሻ ዓመታት በማሳሇፍ ሊይ
ነበሩ።5 ስሇዙህ አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ጋስጫ በ13ኛው ምዕት ዓመት አጋማሽ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ሉያገኙ እና
ሥርዓተ ምንኩስናን ሉያስተምሯቸው የሚችለበት ዕዴሌ የሇም።
ጸሏፊው ግን አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ያገኟቸው አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ጋስጫ ሳይሆኑ ላሊ አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ
(዗ግሼ ወይም ዗አምሏራ) ናቸው ይሊሌ። ነገር ግን የተባለት አባት ከገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች ውጪ አይታወቁም።
የማያነሷቸው የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎችም አለ። የሚታወቅ ገዴሌ የሊቸውም፣ ስንክሳርም ሊይ የለም። ማኅበረ ቅደሳን
ያሳተመው መዜገበ ቅደሳን ሊይም አሊገኘኋቸውም።6 ጸሏፊው እሳቸውን በሚመሇከት ሁሇት ቦታዎች ሊይ ነው መረጃ
የሚሰጠን።
‚የዯብረ ሉባኖሱ ገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት እንዯሚነግረን አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ አምሏራ ሲሄደ ያገኟቸው
አባት <አባ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ግሼ> ናቸው። በአባ ጊዮርጊስ ገዲም የታተመው ገዴሇ አባ ጊዮርጊስም ዯብረ ጎሌን
<ዯብረ ግሼ> ይሊታሌ። ቀዯምቱ መዚግብት <ግሴ> ነው የሚሎት። ይህ ከሆነ ዯግሞ በአካባቢው ከአቡነ በጸልተ
ሚካኤሌ ዗ጋስጫ በፊት የነበሩ አባት ነበሩ ማሇት ነው። ገዴሇ በጸልተ ሚካኤሌ በዙያ ጊዛ ከዯብረ ጎሌ ላሊ ብዘ
ገዲማት በምዴረ ወሇቃ እንዯነበሩ መረጃ ይሰጠናሌ።‛ (ገጽ 512)
‚የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ እንዯሚነግረን አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሥርዓተ ምንኩስናን የፈጸሙት ከአቡነ
በጸልተ ሚካኤሌ ዗ግሼ ነው። በሏይቅ እስጢፋኖስ ሥርዓትን ነው የተማሩት። ገዴለ በዙያ ጊዛ የነበሩትን የሏይቅ
አበምኔት ስም እንኳን አይነግረንም። በቀዴሞው የዯብረ ሉባኖስ ሥርዓተ ቅዴስና መሠረት ከዏሊውያን ነገሥታት
ጋር ስሇ እውነት ብሇው የተጋዯለ አበው ክብር ነበራቸው። አባ በጸልተ ሚካኤሌ በዙህ ተጋዴሎቸው
በመካከሇኛው ዗መን ይታወቁ ነበር። . . . በ1508 የተጻፈው የዯብረ ሉባኖስ ቅጅ ከነገሥታት ጋር በመገዲዯራቸው
የተነሣ የቤተ መንግሥቱን ሞገስ ካጡት ከአባ በጸልተ ሚካኤሌ ይሌቅ ሇቤተ መንግሥቱ ቅርብ የሆኑትን አባ
ኢየሱስ ሞዏን መረጠ።‛ (ገጽ 774-5 ፣ የኅዲግ ማስታወሻ ቁ. 2327)
ከመጀመሪያው ምንባብ መረዲት የምንችሇው ጸሏፊው አባ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ግሼ በአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ዗መን
የነበሩ እና ከዯብረ ጎለ አባ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ጋስጫ የተሇዩ እንዯሆኑ እንዯሚያስብ ነው። የዙህም ሏሳብ ምንጭ የገዴሇ
ተክሇ ሃይማኖት ትረካ ነው እንጂ ላሊ ጥንታዊ ወይም ዗መናዊ ሰነዴ አይዯሇም። ከዙህ ላሊም ስሇእኚህ አባት መረጃ
የሇውም።
4
Taddesse Tamrat (1968), Church and State in Ethiopia, p. 212
5
ዲንኤሌ ክብረት (2007)፣ አራቱ ኃያሊን፣ ገጽ 124-5
6
ገብረ ሥሊሴ (2009)፣ መዜገበ ቅደሳን፣ ማኅበረ ቅደሳን
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 15

ሁሇተኛው ምንባብ ግን የተሇየ ነገር ነው የሚነግረን። እኚሁ አባት ከዏሊውያን ነገሥት ጋር የተጋዯለ መሆኑን እና በዙህ
ተጋዴሎቸውም ስማቸው ተጠርቶ እንዯነበር ይገሌጣሌ። ይሁን እንጂ ይህ የተባሇው ተጋዴል ያሇ ምንም ጥርጥር የአባ
በጸልተ ሚካኤሌ ዗ጋስጫ ነው። ጸሏፊውም ይህን ተጋዴሎቸውን የሚተርከውን ገዴሊቸውን ወዯ አማርኛ መሌሶ
አሳትሞታሌ። በተጨማሪም በአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ጊዛ ነበሩ ስሇሚሊቸው አባ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ግሼ ይህን የመሰሇ
ዜርዜር መረጃ እንዯላሇው ከመጀመሪያው ምንባብ ተረዴተናሌ።
ይህን የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የሕይወት ምዕራፍ በርግጠኝነት መቀበሌ ያስቸግራሌ። ብዘዎቹ ገዴሊት አቡነ በጸልተ
ሚካኤሌን ቢጠቅሷቸውም የሚሎቸው አባት የዯብረ ጎለ አሇመሆናቸውን አሌገሇጡም። ዯግሞም አንዲንዳ ይህን የገዴለ
ቅጅዎች ሉሆኑ የማይችለ ታሪኮችን ይ዗ው የሚቀባበለበት ወቅት አሇ። ሇምሳላ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በይኩኖ አምሊክ ጊዛ
ቅስና መቀበሊቸውን የሚተርኩ ቅጅዎች ጥቂት አይዯለም። ይሁን እንጂ ከሊይ እንዲየነው ይህ ሉሆን የሚችሌ አይዯሇም፣
በገዴለ ውስጥ ካለ ላልች ትረካዎች ጋርም ይጋጫሌ። ስሇዙህ ‘ፕ/ር ታዯሰ እንዯጻፉት የገዴለ ጸሏፊዎች ከአቡነ ተክሇ
ሃይማኖት በኋሊ የኖሩትን አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ የኖሩበትን ዗መን አሳስተው ወዲሌነበሩበት ዗መን ወስዯዋቸው ይሆን?’
የሚሌ ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ነው።
ጸሏፊው ራሱ እንዯነገረን ዯብረ ጎሌ ዯብረ ግሼ ተብሊ ተጠርታሇች። ይህ ዯግሞ ቀዴሞ ቀሲስ አኖሬዎስ የተባለ
ባሕታዊ ብቻቸውን ይኖሩበት የነበረ እና የእርሳቸው ተከታይ የነበሩት አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ እንዯ ማኅበር ያቋቋሙት
ገዲም ነው።7 ከዙህ በመነሳት የገዴለ ቅጅዎች ‘አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ’ ሲለ የዯብረ ጎለን እያለ ይመስሊሌ።
ላሊው መጠየቅ ያሇበት ጥያቄ ዯግሞ ‘አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም ሇአሥር ዓመታት ከቆዩ
እንዳት በዙያ ሥርዓተ ምንኩስናን ሳይፈጽሙ ቀሩ?’ የሚሇው ነው። በርግጥ አንዲንዴ የገዴለ ቅጅዎች በአቡነ በጸልተ
ሚካኤሌ ገዲም ነው ሥርዓተ ምንኩስናን የፈጸሙት ይሊለ። ነገር ግን በብዘዎቹ ቅጅዎች፣ በስንክሳር እና በሌዯተ አበው
የተጻፈው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ምንኩስናን ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ መቀበሊቸው ነው። ጸሏፊው ይህን ጉዲይ በኅዲግ
ማስታወሻ ቁ. 2327 ሇማብራራት ቢሞክርም ከሊይ እንዲየነው ማብራሪያው አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ዗ጋስጫን የሚመሇከት
ስሇሆነ ‘አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ያገኟቸው አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ የጋስጫው ሳይሆኑ ከዙያ በፊት የነበሩ ላሊ አባት ናቸው’
ከሚሇው አባባለ ጋር የሚቃረን ነው። ይህም ጸሏፊው ራሱ የራሱን ዴምዲሜ ሙለ በሙለ እንዲሌተቀበሇው ያሳያሌ።
እነዙህን ነገሮች ስመሇከት የእኔ አስተያየት ወዯ ፕ/ር ታዯሰ ታምራት ዴምዲሜ ያ዗ነብሊሌ።
ይህን ጉዲይ ያነሣሁበት ዋና ምክንያት የሚከተሇው ነው። ስሇ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት እና ከእሳቸው ጋር ተያይ዗ው
ስሇሚነሱ ታሪኮች በእርግጠኝነት መናገር እንችሌ ዗ንዴ የቅደሱን ሕይወት የጊዛ ሰላዲ በአስተማማኝ መረጃዎች ሊይ
ተመሥርተን መሥራት አሇብን። ይህን ተግባር በጣም አስቸጋሪ ከሚያዯርጉት ትረካዎች አንደ ዯግሞ ይህ አሻሚ ትረካ
ነው። ስሇዙህ ይህን ታሪክ በተመሇከተ በማስረጃ የተዯገፈ ዴምዲሜ ሊይ መዴረስ ይቻሌ ዗ንዴ የገዴለ ቅጅዎች የያዞቸው
ትረካዎች እና ላልች ሇዙህ ጉዲይ መሌስ ሉሰጡ የሚችለ የጥንት መዚግብት በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥሌቀት ሉፈተሹ
ይገባሌ።

7
Taddesse Tamrat (1968), Church and State in Ethiopia, p. 215
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 16

3. የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች ቅዴምና እና ዜምዴና


በመጽሏፉ ውስጥ 26 ያህሌ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች ተ዗ርዜረዋሌ። ከእነዙህ መካከሌ የተወሰኑት በዋናው
የመጽሏፉ ክፍሌ እና በላልቹም ከፍልች ተዯጋግመው ይጠቀሳለ። ጸሏፊው በየቦታው እነዙህን ቅጅዎች በሚጠቅስበት ጊዛ
ሦስት ዓይነት ስህተቶችን ይሠራሌ።
1. ገዴልቹ የተጻፉበትን ዗መን የተመሇከቱ መጣረሶች
የመጀመሪያው ዓይነት ስህተት ገዴልቹ የተጻፉበትን ዗መን በተመሇከተ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ መረጃዎችን
መስጠቱ ነው። ሇምሳላ ገጽ 92 ሊይ ስሇገዴለ በተጻፈው ሏተታ የዋሌዴባው ቅጅ በ15ኛው መክ዗ የመጀመሪያ አጋማሽ
የተጻፈ መሆኑ ተገሌጧሌ። ነገር ግን ገጽ 144 ሊይ ጸሏፊው ከአወቃቀሩ በመነሳት ‚ከ15ኛው ዗መን ሁሇተኛ አጋማሽ
በኋሊ የተጻፈ መሆን አሇበት።‛ ይሊሌ። ይህን የሚሇው ገዴለ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የትግራይ ጉዝ ስሇያ዗ ነው። ‚ይህ
ትረካ ከ15ኛው መክ዗ በኋሊ የመጣ ነው።‛ ይሇናሌ።
ነገር ግን በመጽሏፉ ውስጥ የምናገኘው መረጃ ይህን የሚቃረን ነው። ሇአብነት ያህሌ (ከዋሌዴባው ቅጅ ላሊ)
በ15ኛው መክ዗ የተጻፉት የጣና ቂርቆሱ እና የሏይቁ ቅጅዎች የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የትግራይ ጉዝ መዜግበውታሌ።
ይህም ታሪኩ ‚ከ15ኛው መክ዗ በኋሊ የመጣ‛ ሊሇመሆኑ ማረጋገጫ ነው። በተጨማሪም በእኔ አረዲዴ (የሁሇቱ ቅጅዎች
ምስክርነት ባይኖር እንኳን) የዋሌዴባው ቅጅ የቅደሱን የትግራይ ጉዝ መ዗ገቡ እንጂ ትረካው መቼ እንዯመጣ ሉያሳይ
የሚገባው – የተገሊቢጦሽ አይዯሇም። በርግጥ ይህ የሚሆነው የዋሌዴባው ቅጅ መቼ እንዯተጻፈ የሚያረጋግጡሌን
ላልች ማስረጃዎች ሲኖሩ ነው፤ ገጽ 92 ሊይ ስሇገዴለ ከተጻፈው ሏተታ የምንረዲው ዯግሞ እንዱህ ዓይነት መረጃዎች
እንዲለ ነው። በዙህ ሁኔታ ውስጥ ትረካው መቼ እንዯመጣ ሉያሳይ የሚገባው ገዴለ የተጻፈበት ጊዛ ሆኖ ሳሇ ጸሏፊው
ግን ከትረካው ተነስቶ፣ ላልቹን መረጃዎች ወዯ ጎን በመተው፣ የገዴለን የጽሕፈት ዗መን ሇመበየን በመሞከሩ ከፈረሱ
ጋሪውን ያስቀዯመ መስል ተሰምቶኛሌ።
የዲጋ እስጢፋኖሱን የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ በተመሇከተም ጸሏፊው የሚጋጩ ነገሮች ጽፏሌ። ገጽ 81 ሊይ
‚(ራሱ ገዴለ) የተጻፈው በዏፄ ይስሏቅ ዗መነ መንግሥት፣ በ77 ዓ.ም. መሆኑን ይገሌጻሌ። ይሄውም በ1418 ዓ.ም. ነው።‛
ይሊሌ። ገጽ 82 ሊይ ዯግሞ ‚የእጅ ጽሐፉ የ15ኛው መክ዗ መሆኑን ያመሇክታሌ።‛ ሲሌ ያኑ ሏሳብ ያጠናክረዋሌ። ገጽ
145 ሊይ ግን
‚የዲጋው ቅጅ የ15ኛው መክ዗ ሁሇተኛ አጋማሽ ወይም የ16ኛው መክ዗ የመጀመሪያ አጋማሽ መሆን
አሇበት። በጥንታውያን ቅጅዎች የማናገኘውን በዕሇተ ኀሙስ እና በሰንበት ዕባብ ስሇገዯሇ ሰው የተሰጠውን
ቃሌ ኪዲን ይዞሌ።‛
በማሇት የቀዯመውን በተአማኒ መረጃዎች ሊይ የተመሰረተ ዴምዲሜ ያፈርሰዋሌ። እዙህም ጋ ጸሏፊው የዋሌዴባውን
ቅጅ በተመሇከተ የሠራውን ይ዗ቱ ብቻ የገዴለን ዕዴሜ እንዱወስን የማዴረግ ስህተት የዯገመው ይመስሇኛሌ።
የሚገርመው ነገር ላልች ቦታዎች ሊይ ጸሏፊው መሌሶ የዲጋውን ቅጅ ከላልች ጥንታውያን ከሚሊቸው የ15ኛው መክ዗
ቅጅዎች ጋር እየቆጠረ ይጠቅሰዋሌ። ሇምሳላ ገጽ 590 ሊይ የራሱን ዴምዲሜ ሽሮ እንዱህ ሲሌ ጽፏሌ፡
‚በ15ኛው መክ዗ መጀመሪያ ሊይ በተጻፉት በዲጋውና በፓሪሱ (2ኛ) ቅጅዎች ሊይ (የአቡነ ተክሇ
ሃይማኖት የትግራይና የኢየሩሳላም ጉዝ እና ቆይታ) የሇም።‛
2. የቅጅዎቹን ይ዗ት የተመሇከቱ መዚባቶች
ሁሇተኛው ዓይነት ስህተት የቅጅዎቹን ይ዗ት በተመሇከተ በተሇያዩ አጋጣሚዎች የተሇያዩ ነገሮች የሚነግረን መሆኑ
ነው። ሇምሳላ ገጽ 774-5 ሊይ በሚገኘው የኅዲግ ማስታወሻ 2327 ሊይ ጸሏፊው በ1508 የተጻፈው የዯብረ ሉባኖሱ
ሁሇተኛ ቅጅ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዯብረ ዲሞ የመሄዲቸውን እንዱሁም ምንኩስናን ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ
የመቀበሊቸውን ታሪኮች ሇመጀመሪያ ጊዛ የመ዗ገበ አስመስል ጽፏሌ።
‚ሁሇተኛው የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ ‚(ምንኩስናን) ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ተቀበሇ።‛ ይሊሌ። በ1508 ዓ.ም.
ገዴለ ሇሁሇተኛ ጊዛ በእጨጌ ጴጥሮስ አማካኝነት ሲጻፍ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የምንኩስና ታሪክ ወዯ ዯብረ
ዲሞ እና ወዯ ኢየሩሳላም ዯርሷሌ። በዙህ ምክንያት ከመጡት ዋና ዋና ሇውጦች አንደ ብዘም
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 17

የማይታወቁትን አቡነ በጸልተ ሚካኤሌን በሚታወቁት በአቡነ ኢየሱስ ሞዏ መተካት ነው። የእጨጌ ዮሏንስ
ከማ ቅጅ እንዯሚነግረን አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሥርዓት ምንኩስናን የፈጸሙት ከአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ
዗ግሼ ነው። በሏይቅ እስጢፋኖስ ሥርዓትን ነው የተማሩት። . . . በ1508 የተጻፈው የዯብረ ሉባኖስ ቅጅ
ከነገሥታት ጋር በመገዲዯራቸው የተነሳ የቤተ መንግሥቱን ሞገስ ካጡት ከአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ8 ይሌቅ
ሇቤተ መንግሥቱ ቅርብ የሆኑትን አቡነ ኢየሱስ ሞዏን መረጠ።‛
በዙህ አባባለ ከ1508 በፊት የተጻፉት የገዴለ ቅጅዎች በአጠቃሊይ የቅደሱን የዯብረ ዲሞ ጉዝ ያሌመ዗ገቡ፣
እርሳቸውን የማመንኮሱን ክብርም ሇአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ የሰጡ አስመስልታሌ። ነገር ግን ራሱ በመጽሏፉ
የመጀመሪያ ክፍሌ፣ ሁሇተኛው ምዕራፍ ሊይ ስሇገዴለ ቅጅዎች ባቀረበው ሏተታ መሠረት በ15ኛው መክ዗ መጀመሪያ
የተጻፉትና ፣ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ጋር ይህ ነው የሚባሌ የዕዴሜ ሌዩነት የላሊቸው የጣና ቂርቆሱ (ገጽ 89) ፣
የዋሌዴባው (ገጽ 95) እና የሏይቁ (ገጽ 107) ቅጅዎች አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ምንኩስናን ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ እጅ
መቀበሊቸውን እና ወዯ ዯብረ ዲሞ መጓዚቸውን ይተርካለ።
እዙህ ጋ ብቻ ሳይሆን ላልችም ቦታዎች ሊይ (ሇምሳላ ገጽ 567፣ 602) የገዴሊቱን ይ዗ት እያዚባና እየገዯፈ
ጽፏሌ።
ላሊው ከዙህ ጋራ የተያያ዗ው ጉዲይ ጸሏፊው በገዴሊቱ ቅጅዎች መሃሌ ያሇውን የይ዗ት ሌዩነት ሇማብራራት
የሞከረበት መንገዴ እና የተጠቀመባቸው ምሳላዎች ናቸው። መጽሏፉን የሚያነብ ሰው ከሚፈጠሩበት ጥያቄዎች
መካከሌ ‚በገዴለ ቅጅዎች ውስጥ የምናየው የትረካዎች መሇያየት እና አንዲንዳም መጣረስ እንዳት መጣ።‛ የሚሇው
ነው። የመጣረሱን ጉዲይ ሇጊዛው ወዯ ጎን ትተን፣ በተወሰኑት የገዴለ ቅጅዎች ሊይ የላለት ታሪኮች በላልቹ በተሇይም
በኋሇኞቹ የገዴለ ቅጅዎች ሊይ እንዳት ሉገኙ ቻለ ሇሚሇው ጥያቄ ገጽ 362 ሊይ የተሰጠውን ማብራሪያ እንመሌከት።
‚ይህ በተሇያዩ ምክንያቶች ይሆናሌ‛ ይሇናሌ – ጸሏፊው።
‚የመጀመሪያው የቅደሳት መጻሕፍት ጠባይ ነው። በኋሊ ከተጻፉት የለቃስ እና የዮሏንስ ወንጌልች
ይሌቅ መጀመሪያ የተጻፈው የማርቆስ ወንጌሌ አጭርና ዜርዜር የላሇው ነው።‛
ይህ ጥሩና ተገቢ ንጽጽር አይዯሇም። ሇምን ቢለ፣ አንዯኛ፡ ከወንጌሊቱ ሁለ ቀዴሞ እንዯተጻፈ (ያም እንኳን
ባይሆን ከማርቆስ ወንጌሌ ምንም ያህሌ እንዲሌ዗ገየ) የሚገመተው9 የማቴዎስ ወንጌሌ ረዥም እና ብዘ ዜርዜር ያሇው
በመሆኑ ነው። እናም ከዙህ ምሳላ በመነሳት ‚ይህ የቅደሳት መጻሕፍት ጠባይ ነው።‛ ብል ማጠቃሇሌ ሕጹጽ
ይመስሇኛሌ።
ነገር ግን ይህን እንኳን ወዯ ጎን ብንተወው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ገዴሌ ቅጅዎች በተጻፉባቸው ዗መናት መሃሌ
እና ወንጌሊውያኑ የየራሳቸውን ወንጌሌ በጻፉባቸው ዗መናት መሃሌ የነበሩት ሌዩነቶች ሇየቅሌ ናቸው። ወንጌሊውያኑ
ሁለም ሇጻፉት ታሪክ ወይ የዏይን ምስክሮች ወይም የዏይን ምስክሮችን ያዩ ናቸው። በመጨረሻ የተጻፈው የዮሏንስ
ወንጌሌ እንኳን በዏይን ምስክር የተጻፈ ነው። ስሇዙህ በመካከሊቸው ያሇው የጊዛ ሌዩነት ስሇ ጉዲዩ ያሊቸው ዕውቀት
ሊይ ሌዩነት አያመጣም። በተቃራኒው የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት የመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች እንኳን ከእርሳቸው ዕረፍት
ከመቶ ዓመታት በሊይ የሚሆን ጊዛ ካሇፈ በኋሊ ነው የተጻፉት። የኋሇኞቹ ቅጅዎች ዯግሞ የመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች
ከተጻፉ ከ100 ፣ 200 እና 300 ዓመታት በኋሊ የተጻፉ ናቸው። ምሳላው አቻነት የሇውም።
‚ሁሇተኛው ምክንያት ዯግሞ የመረጃዎቹ እየተሰባሰቡ መምጣት ነው። . . . በኋሊ ዗መን የእነዙህ
(በየቦታው ባለ ዯቀ መዚሙርት የተሰበሰቡ) መረጃዎች ወዯ አንዴ ቦታ መሰባሰብ እና የቃሌ መረጃዎችም
እየተሰባሰቡ መሄዴ መጻሕፍቱን በመረጃ የዲበሩና ዜርዜር ነገሮችን የሚገሌጡ ያዯርጋቸዋሌ። በተሇይም
በቅደሱ የተሰየመው ገዲም የመነኮሳት እና መምህራን ማዕከሌ ሲሆን መዚግብቱና የቃሌ መረጃዎችም ወዯ
አንዴ ማዕከሌ ሇመሰባሰብ ዕዴሌ ያገኛለ።‛ (ይህን ሇመዯገፍም የተሇያዩ ገዴሊት እንዳት ተአምራት
በተዯረገሊቸው ሰዎች ምስክርነት፣ አንዴም በኋሊ ዗መን በተጨመሩ ታሪኮች እንዳት እንዯዲበሩ ምሳላዎች
ቀርበዋሌ።)

8
በቀዯመው ክፍሌ እንዯተጠቀሰው ይህ ሏተታ ጸሏፊው ስሇ አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ማንነት ከተናገረው ጋር የሚጋጭ ነው። በዙህ ምንባብ
ከዏሊውያን ነገሥት ጋር ተጋዴሇዋሌ የተባለት አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ዗መን በኋሊ በዏምዯ ጽዮን ዗መን የነበሩ አባት ናቸው።
9
Scaff, Philip, History of the Christian Church, Vol. I, pp. 491-2 (www.ccel.org)
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 18

ይህ በአንዴ በኩሌ ጥሩ ማብራሪያ ነው። እውነትም መረጃዎች እየተሰበሰቡ የሚሄደበት ዕዴሌ ሰፊ ነው። ነገር
ግን ተአምር የተዯረገሊቸው ሰዎች መጠቀሳቸው ትክክሌ አይዯሇም፣ ከእንዱህ አይነት ሰዎች የሚመጣ ምስክርነት
የተአምራቱን ዜርዜር ሉያዲብር ቢችሌም ሇዋናው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ገዴሌ ግን የሚጨምረው ነገር እይኖርም።
ምክንያቱም ከሊይ እንዯተጠቀሰው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ገዴሌ መጻፍ የጀመረው እርሳቸው ከሞቱ ከመቶ ዓመት
በሊይ በኋሊ ነውና፣ በዙያ ጊዛ እና ከዙያ ጊዛ በኋሊ የዏይን ምስክሮች ሉኖሩ ስሇማይችለ ነው።
ነገር ግን ሇምሳላ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በብዘ የኢትዮጵያ ክፍልች ተ዗ዋውረው እንዯማስተማራቸው እና
እንዯመኖራቸው፣ በአንዴ ቦታ (ሇምሳላ የትግራይ ገዲማት) የፈጸሟቸው ተግባራት በላልቹ ገዴሊቸው በተጻፈባቸው
አካባቢዎች (ሇምሳላ በዯብረ ሉባኖስ) ባሇመታወቃቸው በመጀመሪያዎቹ ገዴሊት ሳይመ዗ገቡ ቀርተው፣ ከጊዛ በኋሊ
መረጃው ሲገኝ ከዙያ በኋሊ በተጻፉት የገዴለ ቅጅዎች ሊይ ሉጨመሩ ይችሊለ።
ነገር ግን በዙህ አይነት ሁኔታ ሉጨመሩ የሚችለ ታሪኮች ዓይነት አሊቸው። ሇምሳላ ጸሏፊው ከሊይ የተጠቀሱትን
ምክንያቶች የሰጠው እግዙእ ኀረያ በዲሞት ያዯረገችው ጸልት በፊተኞቹ ቅጅዎች ጥቅሌ ሆኖ ቀርቦ ሳሇ በሁሇተኛው
የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ ሊይ እንዳት በዜርዜር ሉጻፍ እንዯቻሇ ሇማብራራት ነው። ነገር ግን ይህ ዜርዜር ምናሌባት
ከመገሇጥ ነው ካሌተባሇ በቀር ከ዗መናት ብዚት ከየቦታው በሚሰባሰቡ መረጃዎች ሉዲብር የሚችሌ አይዯሇም።
እንዱያውም በጊዛ ብዚት እንዱሁም ከሰው ወዯ ሰው እየተሊሇፈ ሲመጣ የበሇጠ እየዯበ዗዗ የሚሄዴ ዓይነት መረጃ
ነው። መገሇጥ ቢሆን ዯግሞ ከገዴለ የጽሕፈት ዗መን ጋር የሚያገናኘው ነገር የሇም።
ይሌቁንም ትረካዎች ከጊዛ ወዯ ጊዛ በሚሰባሰብ መረጃ እየዲበሩ ሉሄደ የሚችለት የብዘ ሰው ሕይወት የሚነኩ
(ብዘ ምስክር ያሊቸው) እንዱሁም ከቃሊት ይሌቅ በዴርጊት የተሞለ ሁነቶችን (ጉዝ፣ ተአምራት፣ ወ዗ተርፈ) የያዘ
ሲሆኑ ነው፤ ሇምሳላ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የትግራይ ጉዝ።
ነገር ግን ጸሏፊው ብዘ ጊዛ አመክንዮውን እርሱ ሇተቀበሇው ታሪክ በሚስማማ መሌኩ ስሇሚያካሂዴ፣ እርሱ
ያሌተቀበሊቸውን ታሪኮች (በጥንታውያን ቅጅዎች የተመ዗ገቡትንም ጭምር) የመረጃ መሰባሰብ ውጤት አዴርጎ
ከመቁጠር ይሌቅ፣ ፖሇቲካዊ ወይም ላሊ አይነት ታርጋ መሇጠፍ ይቀናዋሌ።
የጸሏፊው ትንተና አሌተጠናቀቀም። ‚ላሊው ምክንያት ዯግሞ የ዗መን ጥያቄ ነው።‛ ይሌና ጸሏፊው የነገሥቱን
ከአሕዚብ ጋራ የመጋባት እንዱሁም ብዘ የማግባት (ከይኩኖ አምሊክ በኋሊ የመጣ) ሌማዴ በማየት ይህን ነገር (የእግዙእ
ኀረያን በሞተሇሚ መታጨት) ትኩረት ስሇሰጡት ይሆናሌ የሚሌ መሊምት ያስቀምጣሌ። ሇዙህም የአቡነ አሮንን፣
የአቡነ በጸልተ ሚካኤሌን፣ የአቡነ ፊሌጶስን እና የአቡነ አኖሬዎስን ገዴልች ይጠቅሳሌ።
የምክንያቱ ጥሩነት እንዯተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን የተጠቀሱት ቅደሳን የነበሩት እና ከአሕዚብ ጋራ መጋባትን ብዘ
ማግባትም የተሇመዯው በ14ኛው መክ዗ መሆኑ ይታወቃሌ። የተጠቀሱት አባቶችም በሙለ የነበሩት በ14ኛው መክ዗
ነው። ይህን ሇማረጋገጥ የጸሏፊውን የራሱን ‘አራቱ ኃያሊን’ የተሰኘውን ላሊኛውን መጽሏፉን ማየት በቂ ነው። የአቡነ
ተክሇ ሃይማኖት ጥንታውያን ቅጅዎች ዯግሞ የተጻፉት በ15ኛው መክ዗ የመጀመሪያ አጋማሽ ነው። እንዱያውም ከሊይ
ከተጠቀሱት አባቶች መካከሌ የአቡነ ፊሌጶስን ገዴሌ ያስጻፉት የመጀመሪያውን የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ ያስጻፉት
እጨጌ ዮሏንስ ከማ ናቸው። ስሇዙህ፡ ላሊ የማናውቀው መረጃ ኖሮ ካሌሆነ በቀር፡ ሇጉዲዩ የመጀመሪያዎቹ ገዴሊት ያነሰ
ትኩረት ሉሰጡ የሚችለበት አሳማኝ ምክንያት አሇ ብዬ ሇመቀበሌ እቸገራሇሁ።
3. የትኛው ገዴሌ ከየቱ ተቀዲ?
በመጸሏፉ ከ143 እስከ 146 ባለት ገጾች ‘የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ታሪካዊ ሂዯት’ የሚሌ በሥዕሌ የተዯገፈ ሏተታ
ይገኛሌ። አሊማው የገዴለ የተሇያዩ ቅጅዎች ያሊቸውን ዜምዴና መበየን ነው። በሥዕሊዊ ገሇጻው መሠረት በቃሌ
እየተነገረ ከትውሌዴ ወዯ ትውሌዴ ሲተሊሇፍ የነበረው የቅደሱ ገዴሌ መጀመሪያ በጽሐፍ የሰፈረው በዯብረ ሉባኖስ
(በእጨጌ ዮሏንስ ከማ አማካይነት) ፣ በዋሌዴባ እና በሏይቅ ገዲማት ነው። እነዙህ ሦስቱ ቅጅዎች በተሇያየ ዗መን እና
ቦታ ሇየብቻቸው (independently) የተጻፉ ናቸው፤ ሇቀሩት ቅጅዎች በሙለ መነሻ ሆነዋሌ። (በዙህ ክፍሌ ከሊይ
ከተጠቀሱት ገዴሊት በተጨማሪ ሊተኩርባቸው የምፈሌገው) የጣና ቂርቆሱ እና የዲጋ እስጢፋኖሱ ቅጅዎች ዯግሞ
ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ የተወሇደ ወንዴማማች ናቸው። የጽሕፈት ዗መናቸውም ተመሳሳይ ነው።
ይህን ሥዕሌ በአእምሮአችን ይ዗ን ሁሇት ጉዲዮችን እንመርምር።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 19

ሀ. የእጨጌ ዮሏንስ ከማ እና የጣና ቂርቆሱ ቅጅዎች ዜምዴና


የሁሇቱን ቅጅዎች ዜምዴና በተመሇከተ ጸሏፊው ገጽ 86 ሊይ ስሇጣና ቂርቆሱ ገዴሌ በጻፈው ሏተታ እንዱህ
ብሎሌ።
‚. . . በመጽሏፉ ሊይ ግን ዗መኑን የሚገሌጥ ነገር የሇውም። አንዲንዴ ሉቃውንትም የጣና ቂርቆሱ ቅጅ
በ1417 ዓ.ም. በእጨጌ ዮሏንስ ከማ የተጻፈ መሆኑን ይገሌጣለ። እንዯኔ ግምት ግን ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ
ቀጥል የተጻፈ ቅጅ ነው። የተአምራት ቁጥሩና ዜርዜሮቹ ተመሳሳይ ናቸው። በአንዲንዴ አገሊሇጥ ግን
ይሇያያሌ። . . . በላሊ በኩሌ ዯግሞ የ዗ማዊቷን ሴት ፈተና አሌመ዗ገበውም።‛
ስሇእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ በጻፈው ሏተታ ሊይ ዯግሞ እንዱህ ብሎሌ።
‚በገዴለ ሊይ የሚገኙት ተአምራት ከጣና ቂርቆሱ እና ከአዝዝው ቅጅ ጋር ተመሳሳይ ናቸው። የጣና
ቂርቆሱ ቅጅ የእጨጌ ዮሏንስ ከማን ቅጅ ገዴሌና ተአምር ወስድ ሲጻፍ፣ የአዝዝው ግን ተአምራቱን ብቻ
ወስዶሌ።‛
ላልችም ቦታዎች (ሇምሳላ ገጽ 144 ፣ 506) ሊይ የጣና ቂርቆሱ ቅጅ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ የተወሰዯ መሆኑ
ተገሌጧሌ። ይሁን እንጂ በሁሇቱ ገዴልች መሃሌ ያለትን የይ዗ት ሌዩነቶች ስንመሇከት ይህን የጸሏፊውን ዴምዲሜ
ሌንጠራጠር እንገዯዲሇን።
አንዯኛ የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ የመ዗ገባቸው፣ የጣና ቂርቆሱ ቅጅ ግን ያሊካተታቸው ታሪኮች መኖራቸው ነው።
ይህ ሇጥርጣሬ ምክንያት የሚሆነው ግሌባጩ (ወይም ዗ግይቶ የተጻፈው ገዴሌ) የተገሇበጠበትን (ቀዴሞ የተጻፈውን)
ገዴሌ ይ዗ት አሟሌቶ ከዙያ በኋሊ አዲዱስ ታሪኮች ይጨምርበት ይሆናሌ እንጂ ከነበረው ሊይ ያጎዴሊሌ ተብል
ስሇማይጠበቅ ነው።
ሇምሳላ ጸሏፊው ራሱ እንዯጠቀሰው የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ የ዗ገበውን ‘የ዗ማዊቷን ሴት ፈተና’ የጣና ቂርቆሱ
ቅጅ አሌያ዗ም። በርግጥ ይህን ታሪክ በኋሊ ዗መን የተጻፉ ገዴልች የ዗ሇለት መሆኑ፣ ከአንዲንዴ ጥንታውያን ገዴሊት
(ሇምሳላ ከዲጋው) ሊይም የተዯመሰሰ ወይም ሇመዯምሰስ ሙከራ የተዯረገበት መሆኑ እና ሇዙህም ምክንያቱ ‚የቅደሱን
ክብር ዜቅ ያዯርገዋሌ ተብል ስሇተፈራ‛ መሆኑ ተገሌጿሌ። ነገር ግን የጣና ቂርቆሱ ቅጅ የእጨጌ ዮሏንስ ከማን ቅጅ
ያህሌ ጥንታዊ ስሇሆነ እና በውስጡም የተዯመሰሰ ክፍሌ ስሇላሇ የታሪኩ በውስጡ አሇመኖር በዙህ ሉብራራ
አይችሌም። ይህ ብቻ አይዯሇም። ገጽ 529 ሊይ ‘ሦስተኛው የምዴረ አምሏራ ተአምር’ ተብል የተሰየመውን ታሪክ
የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ሲመ዗ግበው የጣና ቂርቆሱ ቅጅ ግን እንዲሌመ዗ገበው ተገሌጧሌ።
ላሊው የጥርጣሬ ምንጭ ሁሇቱ ገዴልች አንዲንዴ ጉዲዮችን በተመሇከተ የሚጣረስ መረጃዎች የሚሰጡን መሆኑ
ነው። የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ቅስና ከወሊጆቻቸው ዕረፍት በፊት የተገኘ ሲያዯርገው የጣና
ቂርቆሱ ቅጅ ግን ከዙህ (እና ከላልቹ ገዴልች ሁለ) ተሇይቶ ከወሊጆቻቸው ዕረፍት በኋሊ የተገኘ ነው ይሊሌ።
እንዱሁም በእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ መሰረት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ምንኩስናን የተቀበለት ከአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ
እጅ ሲሆን፣ በጣና ቂርቆሱ ቅጅ መሰረት ግን ምንኩስና የተቀበለት ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ እጅ ነው።
ከዙህም ላሊ፡ የጣና ቂርቆሱ ቅጅ የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ያሌያዚቸውን ብዘ ታሪኮች ይዞሌ። አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት ወዯ ትግራይ ገዲማት ያዯረጉት ጉዝ እና በዙያ የነበራቸው ቆይታ፣ በዯብረ ዲሞ ሳለ አስኬማ ከአቡነ ዮሏኒ
ተቀብሇው ወዯ ሏይቅ ሲመሇሱ ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ መስጠታቸው በጣና ቂርቆሱ ቅጅ የምናገኛቸው፣ በእጨጌ ዮሏንስ
ከማ ቅጅ ሊይ ግን የላለ ታሪኮች ናቸው። እነዙህ ሌዩነቶች የይ዗ት ብቻ የሚባለ አይዯለም። የሁሇቱን ገዴልች ቅርጽም
የተሇያየ የሚያዯርጉ ናቸው።
ከእነዙህ ሁለ ነገሮች በመነሳት ጸሏፊው ስሇሁሇቱ ቅጅዎች ዜምዴና የዯረሰበትን ዴምዲሜ አሌተጋራሁትም።
መጽሏፉ ውስጥ ካለ መረጃዎች በመነሳት የጣና ቂርቆሱ ቅጅ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ይሌቅ ከዋሌዴባውና ከሏይቁ፣
ከሁሇቱ ዯግሞ በይበሌጥ ከሏይቁ ጋራ ዜምዴና ያሇው ይመስሊሌ። ሇምሳላ ሦስቱም ቅጅዎች በቅርጽ ይመሳሰሊለ፣
በሦስቱም ቅጅዎች ትረካ መሰረት የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የሰሜን ጉዝ ትግራይ ይዯርሳሌ፣ አስኬማም ከአቡነ ዮሏኒ
ተቀብሇው ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ይሰጣለ። ምንኩስናንም የሚቀበለት ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ነው እንጂ ከአቡነ በጸልተ
ሚካኤሌ አይዯሇም።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 20

ገጽ 654 ሊይ እንዯተጠቀሰው ዯግሞ ሦስቱም ቅጅዎች (ከላልቹ ቅጅዎች ተሇይተው) በተመሳሳይ ቦታ


ከመዜሙረ ዲዊት ተመሳሳይ ጥቅስ ይጠቅሳለ። ጸሏፊውም ይህን ይዝ (ከበፊት ዴምዲሜው በተቃራኒ) ‚የሦስቱ
ቅጅዎች ምንጭ አንዴ ሳይሆን አይቀርም።‛ የሚሌ ግምት ያስቀምጣሌ።
በርግጥ በሦስቱ ቅጅዎች መካከሌ መመሳሰልች ይኑሩ እንጂ ሌዩነቶችም አለ። ሇምሳላ ከሦስቱ መካከሌ የሏይቁ
ቅጅ ተሇይቶ የ዗ማዊቷን ሴት ታሪክ መዜግቦታሌ። የዋሌዴባው ቅጅ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇሁሇተኛ ጊዛ ወዯ ዲሞት
እንዯሄደ ይተርካሌ፣ ወዯ አቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም መሄዲቸውን ዯግሞ አይተርክም። የጣና ቂርቆሱ ከሊይ
እንዲየነው ቅስናቸውን ከወሊጆቻቸው ዕረፍት በኋሊ ያዯርገዋሌ። ላልችም ሌዩነቶች ሉኖሩ ይችሊለ። ነገር ግን ያም ሆኖ
የጣና ቂርቆሱ ቅጅ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ይሌቅ ከሁሇቱ ቅጅዎች ጋር የተሻሇ መመሳሰሌ አሇው። ጥሩ ግምት
የሚመስሇኝ ጸሏፊው እንዲሇው (የሁለም ምንጭ ተመሳሳይ ባይሆን እንኳን) በመሃሊቸው ሆነው የሚያዚምዶቸው
ያሌታወቁ ቅጅዎች መኖራቸው (ወይም የሩቅ ዜምዴና ያሊቸው መሆኑ) ነው። በመሃሊቸው ያለት ‚አዚማጅ ቅጅዎች‛
ምናሌባት በግራኝ ወረራ ጊዛ ጠፍተው፣ ላሊ ጥፋት አግኝቷቸው ወይም ዯግሞ ያለበት ሳይታወቅ ቀርቶ ሉሆን ይችሊሌ
ብዬ ገምታሇሁ። ይህን ግምት የሚያጠናክሩ ተጨማሪ ነጥቦችን በሚቀጥሇው ርዕስ ስርም እናገኛሇን።
ሇ. ጸሏፊው ቅጅዎቹን በትውሌዴ ሇመከፋፈሌ የተጠቀመባቸው መስፈርቶች
ጸሏፊው የቅጅዎቹን ቅዴምና እና ዜምዴና በተመሇከተ ሲጽፍ ‘የመጀመሪያ ትውሌዴ’ ፣ ‘ሁሇተኛ ትውሌዴ’ ወ዗ተ
የሚለ ብያኔዎችን ተጠቅሟሌ። ነገር ግን እነዙህ ብያኔዎች ምን ማሇት እንዯሆኑ እና የትኞቹ ቅጅዎች በየትኛው ብያኔ
ስር እንዯሚወዴቁ ጊዛ እና ቦታ ወስድ አሊስረዲም። ምናሌባት ግሌጽ ነው ብል ስሊሰበ ሉሆን ይችሊሌ። ነገር ግን እኔ
እነዙህ ብያኔዎች በሁሇት ዓይነት መንገድች ሉተረጎሙ ይችሊለ ይመስሇኛሌ። አንዯኛ፡ ቅጅዎቹ የተጻፉበትን ዗መን
ሉያመሊክቱ ይችሊለ። ሁሇተኛ፡ (በተሇይ በሥዕሊዊ መግሇጫው መሠረት) በቅጅዎቹ መካከሌ ያሇውን ዜምዴና ሉያሳዩ
ይችሊለ።
ሇእኔ የተሻሇ የሚመስሇኝ ሁሇተኛው መንገዴ ነው። ምክንያቱም አንዯኛ በመጀመሪያው መንገዴ መሄዴ ከፈሇግን
ትውሌድችን የሚበይን የጊዛ ገዯብ ያስፈሌገናሌ – ያ ዯግሞ የሇንም። ሁሇተኛ አንዲንዴ የጸሏፊው ብያኔዎች
የመጀመሪያውን መንገዴ እንዴንከተሌ አይጋብዘንም። ሇምሳላ ሥዕሊዊ መግሇጫው እና እሱን የሚከተሇው ሏተታ።
ላሊኛው ምሳላ ዯግሞ ጸሏፊው የጣና ቂርቆሱን ቅጅ (በጸሕፈት ዗መን ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ጋራ ይህ ነው
የሚባሌ ሌዩነት ባይኖረውም) በተዯጋጋሚ ‘ሁሇተኛ ትውሌዴ’ ነው ሲሌ መበየኑ ነው። ስሇዙህ በቀዲሚነት ሁሇተኛውን
የብያኔ መንገዴ ይዤ እቀጥሊሇሁ። በዙህ ብያኔ መሰረት የእጨጌ ዮሏንስ ከማ፣ የዋሌዴባውና የሏይቁ ቅጅዎች
የመጀመሪያ ትውሌዴ ሲሆኑ፣ የጣና ቂርቆሱ እና የዲጋ እስጢፋኖሱ ቅጅዎች ግን ሁሇተኛ ትውሌዴ መሆናቸው ነው።
ጸሏፊው የየትውሌደ መሇያ አዴርጎ የወሰዲቸውን ትረካዎች አንዴ ቦታ ተ዗ርዜረው ባናገኛቸውም፣ ነገር ግን
የተሇያዩ ገጾች ሊይ ከጻፋቸው ነገሮች ሦስት ትረካዎች የተጠቀመ ይመስሊሌ።
‚በዝረሬ የፈተነቻቸው ሴት ታሪክ የሇም። የጣና ቂርቆሱ ቅጅ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ሁሇተኛ ቅጅ
ነው። የመጀመሪያው ትውሌዴ ቅጅ(ዎች) የዝረሬዋ ሴት ታሪክ አሊቸው። ወዯ ዯብረ ዲሞ ሄደም አይለም።‛
(ገጽ 88)
‚ያጠመቁትን ‚ሰይጣን‛ በተመሇከተ ገዴለ (የጣና ቂርቆሱ) ‚ጋኔን እም ሥጋውያን‛ ይሇዋሌ። በዙህ
አገሊሇጡም ሁሇተኛ/ሦስተኛ ትውሌዴ መሆኑን ያሳያሌ።‛ የመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች ‚ባሪያ‛ ነው የሚለት።‛
(ገጽ 90)
በእነዙህ ሁሇት ምንባቦች መሰረት ጽሏፊው የገዴለን ቅጅዎች በትውሌዴ ሇመከፋፈሌ የተጠቀመው ‚ሰይጣን‛
ባርያ ወይም ጋኔን ማሇታቸውን፣ የ዗ማዊቷን ሴት ታሪክ መ዗ገብ አሇመ዗ገባቸውን፣ እንዱሁም ወዯ ዯብረ ዲሞ ሄደ
ማሇት አሇማሇታቸውን ነው። እስቲ እያንዲንደን መስፈርት በነጠሊ እንመርምር።
፩. ባሪያ/ጋኔን
የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ፣ የዲጋው እና የፓሪሱ ቅጅዎች ተጠማቂውን ‚ባርያ‛ ነው የሚለት። ገጽ 622 ሊይ
ጸሏፊው እነዙህን ቅጅዎች ጠቅሶ ‚የመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች ተጠማቂውን ባርያ እያለ ይጠሩታሌ።‛ ይሇናሌ።
የዋሌዴባው ‚ነገር‛ ብል ይጠራዋሌ እንጂ ጋኔን ወይም ባርያ አይሇውም። ላልቹ ቅጅዎች (የጣና ቂርቆሱንና
የሏይቁን ጨምሮ) ጋኔን ነው የሚለት።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 21

እንግዱህ በጸሏፊው ብያኔ መሰረት የመጀመሪያ ትውሌዴ የሚሆኑት የእጨጌ ዮሏንስ ከማ፣ የሏይቁ እና
የዋሌዴባው ቅጅዎች በዙህ ጉዲይ ሊይ ይሇያያለ። የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ብቻ ነው ‘ባርያ’ የሚሇው። የጣና
ቂርቆሱ እና የዲጋው ቅጅዎችም በተመሳሳይ ጊዛ ከሱ የተቀደ እንዯመሆናቸው ሁሇቱም ‘ባርያ’ ማሇት ነበረባቸው፤
ግን የዲጋው ‘ባርያ’ ሲሌ የጣና ቂርቆሱ ‘ጋኔን’ ይሊሌ። ይህም የጣና ቂርቆሱን ቅጅ ከዋሌዴባው ጋር እንጂ ከእጨጌ
ዮሏንስ ከማ ቅጅ ጋር የሚያዚምዯው አይዯሇም።
ከዙህም ላሊ የዲጋው ቅጅ በማናቸውም ረገዴ (በጸሏፊው በራሱ ብያኔ መሰረት) መቆጠር ያሇበት ወሊጁ
ከሆነው ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ጋራ ሳይሆን እንዯሱ እና በተመሳሳይ ዗መን ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ
ተገሌብጧሌ ከተባሇው ከጣና ቂርቆሱ ቅጅ ጋራ ነው። በርግጥ ‚ከሁሇቱ ቅጅዎች የቱ ይቀዴማሌ?‛ ሇሚሇው ጥያቄ
ጸሏፊው እርስ በርሱ የሚጋጭ መሌስ ነው የሚሰጠው።
‚ነገር ግን ቅጅው (የዲጋው) ከጣና ቂርቆሱ ቅጅ ይቀዴማሌ፤ አተራረኩ በቀጥታ የእጨጌ ዮሏንስ
ከማን ቅጅ ስሇሚከተሌ።‛ (ገጽ 82)
‚እጨጌ ዮሏንስ ከማ የመጀመሪያውን ቅጅ እንዲ዗ጋጁ ወዱያው ተከታትል ወዯ ጣና አካባቢ
መጥቷሌ። መጀመሪያ ጣና ቂርቆስ ቀጥልም በዲጋ ሁሇት ቅጅዎች ተ዗ጋጁ። (ገጽ 144-5) (ከዙህ ወረዴ
ብልም ‚የዲጋው ቅጅ የ15ኛው መክ዗ ሁሇተኛ አጋማሽ ወይም የ16ኛው መክ዗ መጀመሪያ አጋማሽ መሆን
አሇበት’።‛ ይሊሌ።)
እንግዱህ ከእነዙህ ጥቅሶች የትኛውን መምረጥ እንዲሇብኝ ይቸግረኛሌ። በእንዱህ አይነት ሁኔታ ፍርደ
ከቅጅዎቹ ይ዗ት ውጪ ባለ ነገሮች ቢወሰን የተሻሇ ነው። ምክንያቱም ከቅጅዎቹ ይ዗ት ተነስቶ የገዴለን ቅጅዎች
ዕዴሜ የመወሰኑ አካሄዴ ሇክብ አመክንዮ (circular reasoning) ስሇሚጋብዜ። ማሇትም ይህ አካሄዴ በመጀመሪያ
ቅጅዎቹ የሆነ ትረካ የመያዚቸውን እውነታ በጽሕፈት ዗መናቸው ካመካኘ በኋሊ፣ የጽሕፈት ዗መናቸውን ዯግሞ
መሌሶ ከያዘት ትረካ በመነሳት ሇመበየን ይሞክራሌ።
ከዙያ ይሌቅ የብራናው ዕዴሜ፣ የእጅ ጽሁፉ፣ በገዴለ የተጠቀሱ ታሪካዊ ሁነቶች (historical references)
ሊይ የተመሰረተው ፍርዴ ነው የተሻሇ ውጤት ሊይ የሚያዯርሰን። በዙህ መሰረት ስንሄዴ ዯግሞ ሁሇቱም ገዴልች
በ15ኛው መክ዗ ሁሇተኛ አሥርት ውስጥ፣ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ምንም ያህሌ ሳይ዗ገዩ የተጻፉ ሆነው
እናገኛቸዋሇን (ገጽ 81 ፣ 86)። ስሇዙህም የጽሕፈት ዗መንን መሠረት አዴርገን እንኳን በትውሌዴ ብንመዴባቸው
በተሇያየ ምዴብ ውስጥ ሉወዴቁ አይችለም።
፪. የዝረሬዋ ሴት ታሪክ
ይህ ታሪክ ዯግሞ በእጨጌ ዮሏንስ ከማ፣ በዲጋው፣ በፓሪሱ እና በሏይቁ ቅጅዎች ሲገኝ፥ በዋሌዴባው እና
በጣና ቂርቆሱ ቅጅዎች ውስጥ ግን የሇም። ከሊይ እንዯተጠቀሰው ፣ ጸሏፊው ‚የመጀመሪያው ትውሌዴ ቅጅዎች
ይህ ታሪክ አሊቸው‛ ብልናሌ።
የመጀመሪያው ትውሌዴ የተባለት በቃሌ ከነበረው ትውፊት ተወስዯው ሇመጀመሪያ ጊዛ ተ዗ጋጁ የተባለት
ቅጅዎች ከሆኑ የዋሌዴባው ቅጅ ይህ ታሪክ ሉኖረው ይገባ ነበር። በተቃራኒው የዲጋው ቅጅ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ
የተወሰዯ እንዯመሆኑ ሁሇተኛ ትውሌዴ ነውና ይህ ታሪክ ሉኖረው አይገባም ነበር።
‚አይ፣ የመጀመሪያ ትውሌዴ የተባለት ቀዴመው የተጻፉት ቅጅዎች ናቸው።‛ ከተባሇ ዯግሞ የጣና ቂርቆሱ
ቅጅ ከዲጋው ቅጅ በተመሳሳይ ዗መን ነውና የተጻፈው እሱም ከመጀመሪያው ትውሌዴ ሉቆጠር ይገባሌ። ነገር ግን
የዝረሬዋ ሴት ታሪክ የሇውም። የሏይቁ ቅጅ ዯግሞ ይህን ታሪክ ስሇያ዗ የመጀመሪያ ትውሌዴ ቅጅ ይሆናሌ። ነገር
ግን በላልቹ ሁሇት መስፈርቶች መሰረት ሁሇተኛ ትውሌዴ ተብል ነው የሚበየነው።
፫. የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የዯብረ ዲሞ ጉዝ
እንዯ ጸሏፊው አባባሌ የመጀመሪያው ትውሌዴ ቅጅዎች የዯብረ ዲሞውን ጉዝ ታሪክ አሌያዘም። ይህን ታሪክ
የያዘት የሁሇተኛው ትውሌዴ ቅጅዎች ናቸው። በዙህ መሰረት የእጨጌ ዮሏንስ ከማ፣ የዲጋው እና የፓሪሱ ቅጅዎች
ይህን ታሪክ ስሇያዘ የመጀመሪያ ትውሌዴ ሉባለ ነው። የዋሌዴባው፣ የሏይቁ እና የጣና ቂርቆሱ ቅጅዎች ግን ይህን
ታሪክ ስሇያዘ ሁሇተኛ ትውሌዴ ሉሆኑ ነው።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 22

እዙህም ጋ ተመሳሳይ ችግር ነው የሚገጥመን። ጸሏፊው ከቃሌ ትረካ ተወስዯው ተጽፈዋሌ ያሊቸው የሏይቁና
የዋሌዴባው ቅጅዎች ዯግሞ ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ተነጥሇው ሁሇተኛ ትውሌዴ ሉሆኑ ነው። በዕዴሜም ሆነ
ከእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ በመቀዲት ተመሳሳይ ናቸው የተባለት የጣና ቂርቆሱ እና የዲጋው ቅጅዎችም በተሇያየ
የትውሌዴ ምዴብ ሉወዴቁ ነው።
ከዙህ ሁለ የምንረዲው ጸሏፊው የገዴለን ታሪካዊ ሂዯት ሇማብራራት የተጠቀመባቸው መስፈርቶች ትክክሌ
አሇመሆናቸውን ነው። ላሊው ችግሩ ዯግሞ በማብራሪያው ውስጥ ሇጠፉ ግን አሁን ሇሚታወቁት ቅጅዎች እንዯ ምንጭ
ሊገሇገለ ቅጅዎች ቦታ አሇመተዉ ነው።
ሇምሳላ ያህሌ በቋንቋ ጥናት ውስጥ ሁሇት ቋንቋዎች ብዘ ተመሳስል ሲገኝባቸው የግዴ አንደ ከአንደ መጥቷሌ
ማሇት አይሆንም። ሁሇቱም አሁን የጠፋ ጥንታዊ ቋንቋ ሌጆች ሉሆኑ የመቻሊቸው ዕዴሌ ግምት ውስጥ ይገባሌ።
ጸሏፊው ግን የተጻፉትን ገዴልች ሁለ እንዯምናውቃቸው አዴርጎ በመቁጠር ነው የቅጅዎቹን ዜምዴና ሇመመርመር
የሞከረው። ይህ ችግር የፈጠረበት ይመስሇኛሌ።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 23

4. አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ ሰጥተዋሌ?


በአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ገዴሌ ውስጥ አከራካሪ ከሆኑት እና ጸሏፊው በመጽሏፉ መሌስ ሇመስጠት ከሞከረባቸው
ጉዲዮች አንደ ‘አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ ሰጥተዋሌ’ የሚሇው ትረካ ነው። ይህ ታሪክ በብዘዎቹ
የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች፣ በአቡነ ኢየሱስ ሞዏ እና በአቡነ አረጋዊ ገዴሊት እንዱሁም በሌዯተ መነኮሳት የተጻፈ ነው።
ጸሏፊው ይህ ነገር በኋሊ የመጣ ታሪክ ነው እንጂ በውኑ ያሌተፈጠረ ነገር ነው ይሇናሌ። ነገር ግን ይህን ዴምዲሜውን
ሇመዯገፍ የተጠቀመባቸው ክርክሮች ስህተቶች እና ግዴፈቶች ያለባቸው ሆነው ስሊገኘኋቸው እነዙህን ስህተቶች እና
ግዴፈቶች በመጠቆም በጉዲዩ ሊይ የተሻሇ ጥራት እንዱኖር ነው ሏሳቤ። ችግሬ ከሂዯቱ እንጂ ከዴምዲሜው አይዯሇም ማሇቴ
ነው።
ይህን የአስኬማውን ጉዲይ እና የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የትግራይ ጉዝ በተመሇከተ ጸሏፊው የራሱን ሏሳብ ገጽ 566-7
ሊይ አስቀምጧሌ።
‚በገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ሊይ በ15ኛው መክ዗ መጨረሻ እና በ16ኛው መክ዗ መጀመሪያ ከተዯረጉት ሇውጦች
አንደ የዯብረ ዲሞው ታሪክ ነው። . . . ከዙህ ዗መን በፊት ዯብረ ሉባኖስ ከዯብረ ዲሞ ጋር የምትገናኘው በሏይቅ
በኩሌ ነበር። . . . በኋሊ የዯብረ ሉባኖስ ተሰሚነት እየጨመረ ሲመጣ ግን ዯብረ ሉባኖስን በቀጥታ ከዯብረ ዲሞ
ጋር ማገናኘት ተጀመረ። በዙህም ምክንያት እስከ ዯብረ ዲሞ የሚዯርሰው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ታሪክ እንዱጻፍ
ተዯረገ። . . . ይህ ታሪክ ከሦስት ነገሮች አንጻር ትክክሌ አይመስሌም።‛
ከምንባቡ መንፈስ የምንረዲው ጸሏፊው የዯብረ ዲሞው ታሪክ በኋሊ የተጨመረ ፈጠራ ነው ብል ማሰቡን ነው። ይህ
እምነቱ ከሦስት ነገሮች ይመነጫሌ። ነገር ግን ወዯ ‚ሦስቱ ነገሮች‛ ከመዜሇቃችን በፊት በዙህ ምንባብ ውስጥ ያለትን
ስህተቶች እንንቀስ። በቀዯመው ክፍሌ እንዲየነው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የዯብረ ዲሞ ጉዝ በጣና ቂርቆሱ፣ በዋሌዴባውና
በሏይቁ ቅጅዎች ተ዗ግቧሌ። እነዙህ ገዴልች ዯግሞ ጸሏፊው ትረካው መጣ ካሇበት ዗መን ቀዴመው በ15ኛው መክ዗
የመጀመሪያ አጋማሽ የተጻፉ ናቸው፤ ያውም ከዯብረ ሉባኖስ ውጭ እና ዯብረ ሉባኖሳውያን ባሌሆኑ ጸሏፊያን። ጸሏፊው
እንዯሚሇው ‘በቤተ መንግሥት የበሊይነት የተወሰዯባቸው’ የሏይቅ መነኮሳት ይህን የዯብረ ሉባኖስ የበሊይነት በ዗ሊቂነት
ሇማንበር የሚረዲውን ትረካ ከራሳቸው ከዯብረ ሉባኖሳውያን ቀዴመው በመጻፍ የበሊይነታቸውን ማስወሰጃ መሣሪያ
ያቀብሊለ ብል እንዳት ማመን ይቻሊሌ?10
ይህን ብሇን ወዯ ሦስቱ ነገሮች እንሇፍ።
‚የመጀመሪያው ከጻዴቁ ዕዴሜ፤ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የሸዋ ሉቀ ካህናት ሆነው ሲሾሙ ዕዴሜያቸው
ቢያንስ 55 ዓመት ነበር።‛ (ይሌና የሸዋ እና የዲሞት ቆይታቸውን 5 ዓመት፣ የአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም
ቆይታቸውን 7 ዓመት፣ የሏይቁን 10 ዓመት አዴርጎ፣ ዯብረ ዲሞ 12 ዓመት ቢቆዩ ዕዴሜያቸው 90 ዓመት
ስሇሚሆን ወዯ ሸዋ ተመሌሰው ተ዗ዋውረው ሇማስተማር፣ ዯብረ አስቦን ሇመገዯም እና 7 ዓመት በዋሻ ሇመጸሇይ
ጊዛ አይኖራቸውም፣ ዕዴሜያቸው 105 ዓመት ካሌሆነ በቀር – የሚሌ ክርክር ነው የሚያቀርበው።)
ይህ (ከይቅርታ ጋራ) በጣም ቅንነት የጎዯሇው ክርክር ነው። አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የሸዋ ሉቀ ካህናት ሆነው የተሾሙት
ቅስና በተቀበለ ጊዛ ነው። ቀዯም ባሇ ክፍሌ ውስጥ እንዯተመሇከትነው ጸሏፊው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ቅስና የተቀበለበትን
ጊዛ በተመሇከተ ገጽ 403 ሊይ የተሇያዩ ቅጅዎች በጉዲዩ ሊይ የሚለትን ካቀረበ በኋሊ ‚ቅስና የተቀበለት በ55 ዓመታቸው
ነው።‛ የሚለትን ቅጅዎች ውዴቅ አዴርጎ፡
‚(አቡነ ተክሇ ሃይማኖት) ቅስና ከይኩኖ አምሊክ ዗መን ቀዯም ብሇው በወጣትነታቸው (ከ22-30 ዓመት)
ቅስና ተቀብሇዋሌ።‛
ብል ዯምዴሟሌ። አሁን ከ160 ገጾች በኋሊ ግን የያ዗ውን ክርክር ሇማሸነፍ ሲሌ የራሱን የጊዛ ሰላዲ ተቃርኖ ይከራከራሌ።
በዙያኛው የጊዛ ሰላዲ መሰረት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በ30 ዓመታቸው ስሇሆነ ቅስና የተቀበለት ከትግራይ ወዯሸዋ
የተመሇሱበት ዕዴሜ 90 ሳይሆን 65 ነው የሚሆነው። ‚የሸዋና የዲሞት ቆይታቸው (ጸሏፊው እዙህ ጋ እንዲሇው 7 ዓመት
መሆኑ ቀርቶ) 15 ዓመት ቢሆን ራሱ በ75 ዓመታቸው ይመሇሳለ። ይህም በሸዋ ተ዗ዋውረው ሇማስተማር፣ ዯብረ አስቦን

10
በኋሊ እንዯምናየው ዯብረ ሉባኖስ ሏይቅ በቤተ መንግሥት የነበረውን የበሊይነት በተባሇው ዗መን ሇመረከቡ የቀረበ ተጨባጭ ማስረጃ የሇም።
እንዱያውም እኔ ያገኘኋቸው መረጃዎች የሏይቁ ዏቃቤ ሰዓት እስከ ግራኝ አሕመዴ ወረራ ዴረስ የበሊይነቱን ይዝ መቀጠለን የሚያሳዩ ናቸው።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 24

ሇመመስረት እና 7 ዓመት በዋሻ ሇመጸሇይ 25 ዓመት ይኖራቸዋሌ። የአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም ቆይታቸውን 12 ዓመት
ብናዯርገውም (አንዲንዴ ገዴልች እንዱያ ስሇሚለ) አሁንም 20 ዓመት ይኖራቸዋሌ።11 ስሇዙህ ከሦስቱ ምክንያቶች
የመጀመሪያው ተቀባይነት የሇውም።
በሁሇተኝነት የቀረበው ምክንያት ዯቀ መዜሙር ሇመምህሩ አስኬማ መስጠት አሇመቻለ ነው።
‚. . . ዯቀ መዜሙር ሇመምህሩ አስኬማ የመስጠት ስርዓት ሉኖር የሚችሌ አይዯሇም። በላልች ገዴሊትም
አናየውም። አስኬማም በተሌዕኮ ሉመጣ አይችሌም። ምንም እንኳን በ16ኛው መክ዗ ሇዯብረ ሉባኖስ ሁሇተኛው
ቅጅ መሌስ ሇመስጠት የተ዗ጋጀው ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ ከዯብረ
ዲሞ አመጡ የሚሇውን ታሪክ ቢቀበሇውም አቡነ ኢየሱስ ሞዏ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት አስኪመጡ ዴረስ ወዯ ዯብረ
ዲሞ የሚሌኩት ሰው አጡ ብል ማሇት አስቸጋሪ ነው። ቅደስ አትናቴዎስ ሲያርፍ በአባ እንጦንስ ዕፅ ገንዚችሁ
ቅበሩኝ እንዲሇ አባ ኢየሱስ ሞዏም ከዯብረ ዲሞ ያስመጡት አንዲች ገዲማዊ በረከት ይኖራሌ።‛
ይህን ክርክር በሦስት ከፍሇን እንመሌከተው።
1. ዯቀ መዜሙር ሇመምህሩ አስኬማ መስጠት ያሇመቻለን ስርዓት በተመሇከተ፣ የገዴለ ጸሏፊዎች (ሇምሳላ
የሁሇተኛው የዯብረ ሉባኖስ ገዴሌን ያስጻፉት እጨጌ ጴጥሮስ) ይህ ስርዓት እንዳት ሳያውቁት ቀሩ? ሉሊው ቢቀር
ጸሏፊው ሌክ ‚የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወሊጆች በዏቢይ ጾም ወቅት ተራክቦ ሉፈጽሙ ቻለ?‛ ሇሚሇው ጥያቄ
መሌስ ሇማግኘት ሉቃውንትን እንዯጠየቀ ሁለ ይህንም ጠይቆ ቢነግረን መሌካም ነበር።
ምናሌባት የዯብረ ሉባኖስ ሰዎች (እጨጌ ጴጥሮስን ጨምሮ) ስርዓቱን እያወቁ የቤተ መንግሥት
የበሊይነታቸውን ሇማስጠበቅ ሲለ ጻፉት ብንሌ እንኳን – ጸሏፊው ‚ሇዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ መሌስ ሇመስጠት
ተጻፈ‛ ያሇው የገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ጸሏፊዎች ሥርዓቱ የማይፈቅዯውን፣ ስሇገዚ መምህራቸው በላሊ ዯብር መነኮሳት
የተነገረውን እና የነሱን የበሊይነት ሇመንጠቅ ታስቦ የተ዗ጋጀውን ትረካ እንዳት ተቀብሇው እና አረጋግጠው
ይጽፋለ? ጨርሶ የማይመስሌ ነገር ነው።
(ይህን ክርክር ጸሏፊው ባስቀመጣቸው የተሳሳቱ መነሻዎች ብንሄዴም እንኳን የትም እንዯማያዯርስ ሇማሳየት
አቀረብሁት እንጂ፣ ከሊይ ስሇ ዯብረ ዲሞው ጉዝ እንዯተነገረው ሁለ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ
አስኬማ የመስጠታቸው ነገር ከዯብረ ሉባኖስ ቀዴሞ የተጻፈው በ15ኛው መክ዗ የሏይቁን የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት
ቅጅ ባ዗ጋጁት የሏይቅ መነኮሳት ነው።)

2. ላሊው በዙህ ክርክር ውስጥ የምናገኘው ችግር ‚ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ በ16ኛው መክ዗ ሇዯብረ ሉባኖስ ሁሇተኛው
ቅጅ መሌስ ሇመስጠት ተ዗ጋጀ‛ መባለ ነው። ይህ ገጽ 329 ሊይ ስሇ ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ከተነገረው ጋራ ይቃረናሌ።
‚በ15/16ኛው መክ዗ የተጻፈው ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ገዴሌን ከዛና መዋዕሌ ጋራ አዚምድ የቤተ
ክህነቱንም የቤተ መንግሥቱንም ታሪክ ጽፏሌ። ሁሇተኛው የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅም ሲጻፍ ይህን ቅርጽ
በመከተሌ ቤተ መንግሥታዊውን ታሪክ ከቤተ ክህነታዊው አዚምድ ጽፏሌ።‛ (አጽንዖት የኔ)
እንግዱህ የቱ ነው ትክክሌ? ወይስ ሁሇት ቅጅዎች ኖረው ነው? ሇዙህ ጥያቄ ገጽ 568 ሊይ ያሇው የኅዲግ
ማስታወሻ ቁ. 1669 ሊይ መሌስ እናገኛሇን። ‚እስካሁን ያገኘናቸው የገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ቅጅዎች ከ16ኛው መክ዗
በኋሊ የተጻፉ ናቸው።‛ ይሊሌ። በዙህ መሰረት የመጀመሪያው ጥቅስ ሊይ ያሇው መረጃ (ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ከዯብረ
ሉባኖሱ ሁሇተኛ ቅጅ በኋሊ መጻፉ) ትክክሌ ነው ብሇን እንዯመዴማሇን። ይህን መጣረስ ማስወገዲችን ወዯፊት
በምናገኘው ላሊ ርዕስ ሊይም ጠቃሚ ሆኖ እናገኘዋሇን።
የያዜነውን ጉዲይ በተመሇከተ ግን ይህ እውነታ የሚሰጠን ትርጉም ‚በፊትም አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇአቡነ
ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ የመስጠታቸውን ነገር ከዯብረ ሉባኖሳውያን ቀዴመው በሏይቁ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ
ሊይ የመ዗ገቡት የሏይቅ መነኮሳት፣ በ16ኛው መክ዗ ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏን ሲጽፉም ይህን ታሪክ ዯግመው
አረጋግጠውታሌ።‛ የሚሌ ነው።
11
ሉልች ገዴልችን ተከትሇን የቅስናቸውን ዕዴሜ 22 ብናዯርገው ዯግሞ ተጨማሪ ስምንት ዓመታት ይኖሯቸዋሌ። ፕ/ር ታዯሰ የሚለትን ተከትሇን
የአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ገዲም ጉዝኣቸውን ከገዴሊቸው ብናስወጣ ዯግሞ ወዯ ሏይቅ፣ ትግራይ እና ዯብረ አስቦ ቆይታዎቻቸው የሚተሊሇፍ 10
ወይም 12 ተጨማሪ ዓመታት ይኖሩናሌ። እነዙህን ሁሇቱንም አንዴ ሊይ ብናዯርግ ዯግሞ የሚጨመረው ጊዛ 18-20 ዓመት ይሆናሌ።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 25

3. ‚. . . አቡነ ኢየሱስ ሞዏ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት አስኪመጡ ዴረስ ወዯ ዯብረ ዲሞ የሚሌኩት ሰው አጡ ብል


ማሇት አስቸጋሪ ነው። ቅደስ አትናቴዎስ ሲያርፍ በአባ እንጦንስ ዕፅ ገንዚችሁ ቅበሩኝ እንዲሇ አባ ኢየሱስ ሞዏም
ከዯብረ ዲሞ ያስመጡት አንዲች ገዲማዊ በረከት ይኖራሌ።‛ የሚሇውን ነጥብ በተመሇከተ የተሌዕኮውን ትሌቅነት
ግምት ውስጥ ስናስገባ ነገሩ ጸሏፊው ያሇውን ያህሌ አስቸጋሪ አይመስሌም። ሇምን ቢለ ጸሏፊው ራሱ አስኬማ
እጅግ ከባዴ መዓርግ እንዯሆነና ጥቂቶች ብቻ እንዯሚዯርሱበት ነግሮናሌና።
‚በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ወዯ መዓርገ አስኬማ የሚዯርሱ ጥቂቶች ናቸው። በዋሌዴባ ገዲም ታሪክ
ሇዙህ መዓርግ የበቁት አራት አበው ብቻ መሆናቸውን የዋሌዴባ ገዲም ታሪክ ይገሌጣሌ።‛
እንግዱህ መሌዕክቱ ከባዴ ሲሆን ያን ክብዯት ሇመሸከም የሚችሌ ዯንዲና ትከሻ ያሇው መሌዕክተኛ ያሻሌ።
አቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ እንዱያመጣሊቸው የሚሌኩት ሰው፣ መጀመሪያ አስኬማውን በተጋዴል ሇማግኘት
እንዯሚበቃ የሚያምኑበት መሆን አሇበት። ስሇዙህም እዙህ ዯረጃ ሊይ የዯረሰ ሰው በቶል ባያገኙ አስገራሚ
አይሆንም። ይሌቁንም አስገራሚ የሚሆነው ማንም ሰው ሉያመጣሊቸው የሚችሇውን ‚አንዲች ገዲማዊ በረከት
ሇማስመጣት‛ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ቢጠብቁ ነው።
ስሇዙህ ሁሇተኛውም ምክንያት ተቀባይነት ያሇው አይዯሇም።
ወዯ ሦስተኛው ምክንያት እንሇፍ።
‚ሦስተኛው ምክንያት ዯግሞ በመጀመሪያው የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ ሊይና በእርሱ ዗መን በተጻፉ ሁሇት
ቅጅዎች (የዲጋውና ፓሪሱ (2ኛ) ቅጅ) ሊይ ይሄ ነገር የሇም። የምናገኘው ከ15ኛው መክ዗ ሁሇተኛ አጋማሽ በኋሊ
በተጻፉት ገዴሊት ነው። ይህም ፉክክሩ ያመጣው መሆኑን የሚያሳይ ነው።‛ (ይሌና ቀጥል ገዲማውያን የተሰዏቱን
ቅደሳን ገዲማት የመሳሇም ሌምዴ አንዲሊቸው፣ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትም ወዯ ትግራይ የሄደት ሇዙሁ ሳይሆን
እንዯማይቀር የእጨጌ ዮሏንስ ከማው ቅጅም ታሪኩን የ዗ሇሇው ‚ከዙህ አንጻር ተመሌክቶት‛ ሉሆን እንዯሚችሌ
ይገሌጣሌ።)
ጸሏፊው (አሁንም እንዯገና) ገዴሊቱንም፣ ሉቃውንቱንም፣ ራሱንም ተቃርኖ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የዯብረ ዲሞ ጉዝ
እና ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ የመስጠታቸውን ታሪክ የያዘትን እና በ15ኛው መክ዗ የመጀመሪያ አጋማሽ የተጻፉትን የጣና
ቂርቆሱን፣ የዋሌዴባውን እና የሏይቁን ቅጅዎች እንዯላለ በመቁጠር (ወይም የጽሕፈት ዗መናቸውን አሳስቶ በማስሊት)
ታሪኩ የሚገኘው ‚ከ15ኛው መክ዗ ሁሇተኛ አጋማሽ በኋሊ በተጻፉት ገዴሊት ነው።‛ ይሇናሌ። አጭሩ መሌስ ‚አይዯሇም፣
ታሪኩ በ15ኛው መክ዗ የመጀመሪያ አጋማሽ በተጻፉ ገዴሊትም ውስጥ ይገኛሌ።‛ ነው።
ግን ይህኛው የመከራከሪያ ነጥብ ከበፊቶቹ፣ በተሇይም ከመጀመሪያው፣ የተሇየ ነው፤ ምክንያቱም እዙህ ጋ ጸሏፊው
ወዯ ዯብረ ዲሞ መሄዲቸውን ተቀብል የሄደበትን አሊማ እና የቆዩበትን ጊዛ ነው የማይቀበሇው (የአንቀጹ መጨረሻ ሊይ
‚ብዘ ዗መንም የቆዩ አይመስሌም‛ ይሊሌ)። የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የዯብረ ዲሞ ታሪክ ዯብረ ሉባኖስ በቤተ መንግሥት
ያሇውን ተሰሚነት ሇመጨመር እና በዙያ ያሇውን ሥሌጣንም ሇማንበር ነው የተጻፈው ከሚሌ መነሻው አንጻር ጸሏፊው
አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ዯብረ ዲሞ ሄዯዋሌ ብል መስማማቱ ይገርማሌ፣ ግርም ይሊሌ። ግን መቀበለ መሌካም ነው –
መረጃዎቹ የሚመሩት ወዱያ ነውና።
ነገር ግን ሇጠቅ አዴርጎ የጉዞቸውን አሊማ እና የቆይታቸውን ርዜመት በተመሇከተ ሦስቱን ገዴልች (የዋሌዴባው፣
የጣና ቂርቆሱ እና የሏይቁ) ስሇ ዯብረ ዲሞ ጉዞቸው የሚለትን በመጥቀስ የጻፋቸውን ነገሮች እኔ የተረዲኋቸው ‚አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት አስኬማ ሇማምጣት ወዯ ዯብረ ዲሞ አሌሄደም፣ ተቀብሇውም ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ አሌሰጡም።‛ የሚሇውን
አቋሙን ሇማጠናከር የቀረቡ ማስረጃዎች ናቸው ብዬ ነው። ያ ከሆነ አሁንም ጸሏፊው ወይ አውቆ የተወሰነ መረጃ ብቻ
በመምረጥ ይህን ክርክር ሇማሸነፍ የሞከረ አሇዙያ ዯግሞ መረጃዎቹን በዯንብ የማቀናጀት እና የመጽሏፉን ክፍልችም እርስ
በርሳቸው እንዱጣጣሙ የማዴረግ ሏሊፊነቱን ባሇመወጣቱ ስህተት ሊይ የወዯቀ ይመስሇኛሌ።
‚የሏይቁ ቅጅ በትግራይ የነበራቸውን ጉዝ ሲገሌጥ ‘ሥርዓትን ሇማጽናት ሲ዗ዋወር፣ በውስጣቸውም
ሇመቀመጥ መካናትን ሲመርጥ በዙህ ዓይነት ወዯ አባ አረጋዊ ገዲም ወዯ ዯብረ ዲሞ ዯረሰ።’ ያሇው፤ የጣና ቂርቆሱ
ቅጅም ‘ሥርዓትን ሇማጽናት ሲጓዜ መካናትንም ይቀመጥባቸው ዗ንዴ ሲመርጥ ሳሇ ወዯ ወዯ ዯብረ ዲሞ ዯረሰ።’
ብል የገሇጠው ሇዙህ (ወዯ ትግራይ የተጓዘት ቅደሳን ገዲማትን ሇመሳሇም ስሇሆነ) መሆን አሇበት። የዋሌዴባው
የ15ኛው መክ዗ ቅጅ ወዯ ዯብረ ዲሞ መሄዲቸውን ያነሳሌ። የሄደት ሇበረከት ነው።‛
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 26

ግምቴ ሌክ ከሆነ እና እነዙህ ነጥቦች እዙህ ጋ የተጠቀሱት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ
አሌሰጡም ሇማሇት ከሆነ፣ ጸሏፊው ስሇሦስቱ ቅጅዎች ከጻፈው ሏተታ ሊይ ቅጅዎቹ ይህን ጉዲይ በተመሇከተ ምን
እንዯሚለ በመጥቀስ መሌስ ሌስጥ።
‚(የሏይቁ ገዴሌ) ቆብና አስኬማ የተቀበለት በሏይቅ ሳይሆን በዯብረ ዲሞ መሆኑን ይነግረናሌ።‛ (ገጽ 107)
‚(የጣና ቂርቆሱ ገዴሌ) በየገዲማቱ የቆዩበትን ጊዛ አይነግረንም። በዯብረ ዲሞ ቆብንና አስኬማን ተቀበለ።
ከማን እንዯተቀበለት ግን አይተርክም።‛ (ገጽ 90)
‚(በዋሌዴባው ቅጅ መሰረት) ወዯ ዯብረ ዲሞ አቡነ አረጋዊ ገዲም ገቡ። በገዲሙም <<ወነሥአ ቆብ
ወአስኬማ>> ይሊሌ። በዯብረ ዲሞ ያገኙት ቆብና አስኬማ ከሆነ በሏይቅ የወሰደት ቀሚስና ቅናት ነበር ማሇት
ነው።‛
እነዙህ ጥቅሶች ሦስቱ ገዴልች የአስኬማውን ጉዲይ በተመሇከተ የሚለትን ግሌጥ ባሇ መሌኩ ያሳያለ ብዬ አስባሇሁ።
ምናሌባት ጸሏፊው ወዯትግራይ ስሇሄደበት አሊማ ሲያወራ ‚ዋና አሊማቸው አስኬማ ማምጣት አሌነበረም።‛ ወይም/እና
‚በገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ እንዯተባሇው አቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ አምጣሌኝ ብሇው አሊኳቸውም።‛ ሇማሇት ፈሌጎ ከሆነ ችግር
የሇውም። ቅጅዎቹ ይህን በመሰለ ዜርዜሮች ቢሇያዩ አይገርምም፤ ይህ በእኔ አስተያየት ‘ሌዩነት የማያመጣ ሌዩነት’ ነው። ይህ
ብቻ ሳይሆን ገጽ 593 ሊይ እንዯተጠቀሰውም ከዯብረ ዲሞ የተቀበለትና ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ የሰጡት ቆብና አስኬማ ነው
ወይስ አስኬማ ብቻ ነው የሚሇው ነጥብም ሊይ በገዴሊቱ መሃሌ ሌዩነቶች አለ። ነገር ግን ከዙህ አይነቱ ሌዩነት ተነስቶ
ታሪኩን ሙለ በሙለ መጣሌ የሚቻሌ አይመስሇኝም።
እንግዱህ በዙህ መሰረት ጸሏፊው ‚ይህ (የዯብረ ዲሞውን ጉዝ እና የአስኬማውን ጉዲይ የያ዗ው) ታሪክ ከሦስት ነገሮች
አንጻር ትክክሌ አይመስሌም።‛ ሲሌ ያቀረባቸው ሦስቱም ምክንያቶች ውሃ የሚቋጥሩ ሆነው አይገኙም።
ጸሏፊው የአስኬማውን ነገር በዙሁ አይተወውም። ገጽ 593-4 ሊይ መሌሶ ያነሳዋሌ። በእውነቱ እዙህ ጋ ጸሏፊው ምን
እያሇ እንዯሆነ ሇመረዲት ቸግሮኛሌ። ነገር ግን የአስኬማውን ታሪክ በተመሇከተ ሁለንም ቀዲዲዎች ሇመዴፈን የተነሱትን
ነጥቦች (ከሞሊ ጎዯሌ ከዙህ በፊት መሌስ የተሰጠባቸው ቢሆኑም) እንያቸው።
‚በ15ኛው መክ዗ አጋማሽ ሊይ <<አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ምንኩስናን የተቀበለት ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ነው>>
የሚሌ ሏሳብ መነሳት ሳይጀምር አሌቀረም። ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ሇዙህ በዜርዜር መሌስ ይሰጣሌና። በኛ ገዴሊት
የአጻጻፍ ሌማዴ ዯግሞ ጥያቄውን ማን እንዲነሳ ሳይጠቅሱ መሌሱን ይሰጣለ። ይህ ጉዲይ በሁሇት መሌኩ መሌስ
ተሰጥቶታሌ። የመጀመሪያው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትና የአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ግንኙነት አስኬማን ከዯብረ ዲሞ
በማምጣት ሊይ አንጂ ሥርዓትን በመፈጸም ሊይ እንዲሌተመሰረተ በአተራረክ መግሇጥ ነው። የሏይቁ የገዴሇ ተክሇ
ሃይማኖት ቅጅ፣ የሏይቁ ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ እና የሏይቁ ገዴሇ አረጋዊ ቅጅዎች በዙህ መሌኩ የተ዗ጋጁ ናቸው።
የዋሌዴባው ገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅና የጣና ቂርቆሱ ቅጅም ይህን አተራረክ መሠረት አዴርገው ጽፈዋሌ። ጉዲዩ
እየጠነከረ ሲመጣ እና በ16ኛው መክ዗ መጀመሪያ ሊይ በእጨጌ ጴጥሮስ በተጻፈው ቅጅ ሊይ የቆብና የአስኬማው
ነገር በአጽንዖት ሲጻፍ ዯግሞ ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ በዜርዜር መሌስ ሰጥቶበታሌ። የዙህ ሁለ ክርክር መነሻ <<ማን
ማንን አመነኮሰ?>> የሚሇውን በመግሇጥ ሁሇቱ ገዲማት የበሊይነታቸውን ሇማረጋገጥ የተከተለት አተራረክ ነው።‛
የዙህ ክርክር የመጀመሪያው ችግር ‚በ15ኛው መክ዗ አጋማሽ ሊይ <<አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ምንኩስናን የተቀበለት ከአቡነ
ተክሇ ሃይማኖት ነው>> የሚሌ ሏሳብ መነሳት ሳይጀምር አሌቀረም።‛ የሚሇው መነሻው በምንም አይነት ማስረጃ ያሌተዯገፈ
መሆኑ ነው። ዯብረ ሉባኖሳውያን (ወይም ላልች ሰዎች) መቼም ቢሆን (መጽሏፉ ውስጥ ባለት መረጃዎች መሠረት) አቡነ
ተክሇ ሃይማኖት አቡነ ኢየሱስ ሞዏን አመነኮሱ ብሇው አያውቁም።
ሁሇተኛው ችግሩ ዯግሞ ‚ተነሳ‛ ሇተባሇው ክርክር ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ መሌስ ሰጥቶ ሉሆን አሇመቻለ ነው፤ ምክንያቱም
ቀዯም ሲሌ አንዯተጠቀሰው ጸሏፊው በ15ኛው መክ዗ የተጻፈ የገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ቅጅ ያሊገኘ መሆኑ ነው። ስሇዙህ ላሊ
መረጃ እስካሌቀረበ ዴረስ በ15ኛው መክ዗ ተፈጠረ የተባሇው ክርክር ነበረ ብል ማመን አይቻሌም። እንዱያውም የሏይቁ
የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ አስኬማ ሰጥተዋሌ ብል መጻፉ እንዱህ ዏይነት
ክርክር እንዲሌነበረ ነው የሚነግረን።
‚በ16ኛው መክ዗ መጀመሪያ ሊይ በእጨጌ ጴጥሮስ በተጻፈው ቅጅ ሊይ የቆብና የአስኬማው ነገር በአጽንዖት ሲጻፍ
ዯግሞ ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ በዜርዜር መሌስ ሰጥቶበታሌ።‛ የተባሇውም ስህተት ነው። የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ ስሇ አስኬማ
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 27

የጻፈውን ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ አረጋግጦ አጸዯቀው እንጂ ተቃውሞ የጻፈው ምንም ነገር የሇም። የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅም ቢሆን
አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከአቡነ በጸልተ ሚካኤሌ ምንኩንስናን ተቀበለ የሚሇውን የእጨጌ ዮሏንስ ከማ ቅጅ ትረካ ወዯጎን
በመተውና የጣና ቂርቆሱን፣ የዋሌዴባውንና የሏይቁን ቅጅዎች ፈሇግ በመከተሌ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የማመንኮሱን ክብር
ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ነው የሚሰጠው።
የቆብ ሏረግ ሲ዗ረ዗ርም ሁሇቱም አባቶች የአባ ዮሏኒ ሌጆች ሆነው እና አንደ ሇአንደ ምን እንዯሰጠ ተጠቅሶ
በእኩሌነት አንጂ በማበሊሇጥ አይዯሇም።12 ከሊይ የተጠቀሱት ቅጅዎች በሙለ ዯግሞ ቆብና አስኬማውን በተመሇከተ ‘ሌዩነት
ከማያመጡ አንዲንዴ ሌዩነቶች’ በቀር ተመሳሳይ ነገር ነው የሚናገሩት። እናም በመጽሏፉ የቀረቡት መረጃዎች አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት ወዯትግራይ ገዲማት መጓዚቸውን እና ከዯብረ ዲሞ አስኬማ ወስዯው ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ መስጠታቸውን
የሚያረጋግጡ አንጂ የሚያስተባብለ አይዯለም።

12
ገብረ ሥሊሴ (2009 ዓ.ም.) ፣ መዜገበ ቅደሳን ፣ ማኅበረ ቅደሳን (ሇሁሇተኛ ጊዛ ተሻሽል የቀረበ)፣ ገጽ 219
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 28

5. የዚግዌ ነገሥት ሰልሞናዊነት


በመጽሏፉ ውስጥ በጣም ካስገረሙኝ ነገሮች መካከሌ አንደ የዚግዌን ነገሥት ሰልሞናውያን ሇማዴረግ የተዯረገው
ጥረት ነው። ይህን በተመሇከተ ጸሏፊው የዯረሰበት ዴምዲሜ ከታወቀው የኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ የተሇየ ነው።
ከዴምዲሜው በሊይ ግን ያስገረመኝ ዴምዲሜው ሊይ ሇመዴረስ ጸሏፊው የሄዯበት መንገዴ ነው። የዚግዌ ነገሥት ከይኩኖ
አምሊክ አና እርሱ የመሠረተው ሥርወ መንግሥት ካፈራቸው ነገሥት የበሇጠ ሰልሞናውያን መሆናቸውን ሇማሳመን
ያሌፈነቀሇው ዴንጋይ የሇም። ባሌስማማበትም ሇምን አንዱህ እንዲዯረገ ይገባኛሌ ፤ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የአገው ሰዎች
ከሆኑት ከዚግዌ ነገሥት ይሌቅ የሸዋ ሰው ሇሆነው ሇይኩኖ አምሊክ አዴሌተዋሌ ከመባሌ ሇመታዯግ ነው፤ አንዴም የዚግዌ
ነገሥት ሇሀገራቸውና ሇቤተ ክርስቲያን ባሇውሇታዎች ሆነው ሳሇ ያሌተገባቸውን ዘፋን ያዘ መባሊቸው ስሊስቆጨው ነው።
ስሇዙህ ጉዲይ ሲጽፍ ስሜታዊነት ይነበብበታሌ። የዚግዌ ነገሥትን አሁን ቀርቶ በ዗መናቸውም ያሌተቀበሎቸውን ሰዎች
ይበሳጭባቸዋሌ።
‚. . . ይህን ሁለ ስናይ በ዗መናቸውና ከ዗መናቸው በኋሊ የተነሱ የፖሇቲካ ተቀናቃኞቻቸው (የዚግዌ
ነገሥታት) <<ሰልሞናዊ አይዯለም ሲለ የነዘት ወሬ ፖሇቲካዊ ዓሊማ ያሇው እንጂ ታሪካዊ መሰረት ያሇው
አሇመሆኑን ያሳየናሌ። እነሱንም ከላሊ ፕሊኔት የመጡ ሇማስመሰሌ የተሠራው ሥራ ሁለ እውነት
አሌነበረም።የኢትዮጵያን ሥሌጣኔ ከቀዯምቶቹ ተቀብል፣ በዙያ መሠረትነት የራስን አሻራ ትቶ ወዯ አዱስ ምዕራፍ
ማሸጋገር አንጂ ላሊ ትርፍ አንጀት የመሆን ነገር የሇበትም።‛ (ገጽ 281)
በምንባቡ መጨረሻ ስሇ ኢትዮጵያ ሥሌጣኔ ባሕርይ በተባሇው ነገር ሙለ በሙለ እስማማሇሁ። በአሁኑ ዗መን
የዚግዌን ነገሥት ‚ከላሊ ፕሊኔት እንዯመጡ ሇማስመሰሌ’ የሚሰሩ ሰዎች ካለም ተሳስተዋሌ። የዚግዌ ነገሥት ኢትዮጵያውያን
ናቸው። ነገር ግን በወቅቱ የተነሱት የፖሇቲካ ተቀናቃኞቻቸው ወይም ተቃዋሚዎቻቸውን በተመሇከተ ጸሏፊው
የሚያሳየውን ብስጭት ግን አሌጋራውም – በሁሇት ምክንያት። አንዯኛ ያኔም ሆነ ከዙያ በኋሊ ሇረዥም ዗መን፣ ዚሬም
ጭምር የንግሥተ ሳባን ታሪክና ከሱ የሚመ዗዗ውን የሠልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ የሚያምንበት ብዘ ሕዜብ ነበረ፣ አሇም።
ስሇዙህ ሰዎቹ የዚግዌ ነገሥት ሰልሞናውያን አይዯለም ብሇው ካመኑ ቢቃወሟቸው የተሇየ ሴራ ሰርተዋሌ አሌሌም።
ሁሇተኛ ይኩኖ አምሊክም ሆነ ላልች ተቀናቃኞቻቸው የዚግዌ ነገሥት ጀማሪዎች ቀዲሚዎቻቸው በነበሩት የአክሱም ነገሥት
ሊይ ያሊዯረጉትን አይዯሇም ያዯረጉባቸው። ጉሌበት ያሇው ያስገብራሌ ነው የ዗መኑ ፍሌስፍና፤ ጉሌበታቸውን ሇመገንባት
ዯግሞ ፕሮፖጋንዲ መጠቀማቸው ሳይታሇም የተፈታ ነው።
ጉዲዩን ሇመመርመር ጸሏፊው አጽንዖት ሰጥቶ ካስቀመጠው ዴምዲሜ እንነሳ።
‚የጠፋም የተመሇሰም ሰልሞናዊ መንግሥት የሇም።‛ (ገጽ 26)
ይህ አባባሌ ምን ማሇት ነው? በሁሇት መንገድች መተርጎም ይችሊሌ። በአንዴ በኩሌ እንዱያውም ሰልሞናዊነት ያሇበት
ሥርወ መንግሥት የሇም ማሇት ሉሆን ይችሊሌ። ሰልሞናዊው ስርወ መንግሥት መጀመሪያም ስሊሌነበረ አሌጠፋም፣
ያሌጠፋ ዯግሞ ሉገኝ አይችሌምና – አሌተገኘም።
በላሊ በኩሌ ‘ሰልሞናዊ ሥርወ መንግሥት ነበረ ፣ ኋሊም አሌጠፋም፣ ስሊሌጠፋ ዯግሞ አሌተገኘም።’ ማሇትም ሉሆን
ይችሊሌ። ሦስተኛ ዯግሞ ሁሇቱንም ማሇት ሉሆን ይችሊሌ። ይህ የሚሆነው ጸሏፊው ስሇ ሰልሞናዊው ሥርወ መንግሥት
መኖር ወይም አሇመኖር አቋም ያሌወሰዯ እንዯሆነ ነው – ‚ይኑር አይኑር አሊውቅም፣ ግን ከነበረ አሌጠፋም ፤ ካሌነበረ
ዯግሞ አሌተገኘም።‛ እንዯማሇት።
አብዚኛውን ጊዛ ጸሏፊው አቋም አሇመውሰዴን የመረጠ ይመስሊሌ። አንዲንዴ ቦታዎች ሊይ ዯግሞ አቋም የወሰዯ
መስል ይታያሌ። ዋና ጉዲዬ ነው ብል የያ዗ው በዚግዌ ሥርወ መንግሥት እና ይኩኖ አምሊክ በመሠረተው ሥርወ
መንግሥት መካከሌ የሰልሞናዊነት ሌዩነት እንዯላሇ እና ካሇም የዚግዌ ነገሥት የበሇጠ ሰልሞናዊ አንዯሆኑ አንባቢውን
ማሳመንን ነው። (ሇጊዛው ከእነዙህ ሁሇት ጉዲዮች መካከሌ ሁሇተኛው ሊይ ነው የምናተኩረው። የመጀመሪያውን በላሊ
ክፍሌ የምናየው ይሆናሌ።)
ይህን ሇማዴረግም አንዴ ጊዛ ሰልሞናዊነት ክብረ ነገሥትን ተከትል ከ14ኛው መክ዗ በኋሊ የመጣና ብሔራዊ ስሜት
ሇመፍጠር የተፈጠረ ትረካ መሆኑን (በተ዗ዋዋሪ የይኩኖ አምሊክ ሥርወ መንግሥት የምር ሰልሞናዊ አሇመሆኑን)
ያስረዲናሌ፣ ላሊ ጊዛ ዯግሞ ክብረ ነገሥትን ሳይቀር እየጠቀሰ የዚግዌ ነገሥት እንዳት ሰልሞናዊ እንዯሆኑ ሉያስረዲን
ይሞክራሌ፤ አሇፍ ብል የዚግዌ ነገሥት የአክሱም ባሕሌና ስሌጣኔ አስቀጣዮች ስሇሆኑ ሁሇቱ ሥርወ መንግሥቶች ሁሇት
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 29

ሳይሆኑ አንዴ ናቸው ይሇናሌ፤ በመጨረሻም ይኩኖ አምሊክ ራሱ እንዯ ዚግዌ ነገሥት የቡግና ሰው ስሇሆነ የዚግዌና እርሱ
የመሰረተው ሰልሞናዊ ሥርወ መንግሥት ከዚግዌ የበሇጠ ሰልሞናዊ ሉሆን አይችሌም የሚሌ ዓይነት ሏሳብ ያሇው ክርክር
ያቀርባሌ።
ከዙህ ሁለ የምንረዲው ከሊይ አንዲሌሁት የጸሏፊው ሏሳብ በባላም ሆነ በቦላ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን መዴሌዖ
ፈጸሙ ከመባሌ ማዲን እና የዚግዌ ነገሥት ሇ዗ውደና ሇዘፋኑ ባዕዴ ተዯርገው መታየታቸውን ማስቀረት መሆኑን ነው።
እነዙህ አራት መከራከሪያዎች የተሇያየ ነገር የሚለ ስሇሆኑ ጸሏፊው ሁለንም በአንዴነት መጠቀሙ ትክክሌ አይዯሇም ባይ
ነኝ። ነገር ግን ቀርበዋሌና አንዴ በአንዴ እሄዴባቸዋሇሁ።
በመሠረቱ የቀረቡት ሏሳቦች በሁሇት መከፈሌ ይችሊለ። የመጀመሪያው ሏሳብ በአመዚኙ ሰልሞናዊነት ሇጥሩ አሊማ
የተፈጠረ ትረካ እንጂ የምር ነገር ባሇመሆኑ ሰልሞናዊ ሉባሌ የሚችሌ ሥርወ መንግሥት (የአክሱም፣ የዚግዌ ወይም ይኩኖ
አምሊክ ያስጀመረውም ቢሆን) የሇም ወዯሚሌ ዴምዲሜ የሚወስዴ ነው። በዙህ ክርክር መሰረት ሰልሞናዊነት ከስላቱ
ሉወጣ የሚገባው ጉዲይ ነው።
የተቀሩት ሦስቱ ሏሳቦች ዯግሞ በተሇያዩ መንገድችም ቢሆን የዚግዌ ነገሥት ሰልሞናዊ ናቸው ብሇው የሚከራከሩ
ናቸው።
1. ሰልሞናዊ ሥርወ መንግሥት የሇም
ከሊይ አንዲሌሁት ጸሏፊው አፍ አውጥቶ የሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ ፈጠራ ነው አይሌም። ግን እንዱያ አይነት
ትርጉም ያሊቸውን ነገሮች ጽፏሌ። የሚቀጥለትን ምንባቦች እንመሌከት።
የክብረ ነገሥትን የጽሕፈት ዗መን በተመሇከተ (ገጽ 23-25) ቅዴመ ክርስትና ተጻፈ፣ በ6ኛው መክ዗ ተጻፈ እና
በ14ኛው መክ዗ ተጻፈ የሚለ ሦስት አማራጭ ሏሳቦችን ካቀረበሌን በኋሊ ‘ሇምን አሊማ ተጻፈ’ በሚሌ ርዕስ ሥር
ሦስተኛውን አማራጭ የሚያጸዴቅ ሏተታ አቅርቧሌ።
‚የክብረ ነገሥት ዋና አሊማው ሦስት ነበር። በዮዱት ዗መን የጠፋውን የኢትዮጵያ ቀዯምት ታሪክ መ዗ገብ፣
ሇኢትዮጵያ ነገሥታት ሕጋዊነት የሚሰጥ <ሕገ መንግሥት> ማ዗ጋጀት እና ሇአዱሱ የይኩኖ አምሊክ ሥርወ
መንግሥት ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ሕጋዊ መዯሊዴሌ መፍጠር። . . . ንግሥናን ከእሥራኤሌ ዗ር በሚገኝ የ዗ር
ተዋርድ ብቻ እንዱሆን የሕግ መሠረት አስቀመጠ። <<ሰልሞናዊ>> የሚሇውም ሏሳብ በሚገባ ጎሌቶ ወጣ። ይኩኖ
አምሊክም የሰልሞናዊው ሥርወ መንግሥት መሊሽ ተባሇ።‛ (ገጽ 25)
ከዙህ ምንባብ የምንረዲው ጸሏፊው ክብረ ነገሥት በ14ኛው መክ዗ ነው የተጻፈው የሚሇውን ሏሳብ የተቀበሇው
መሆኑን ነው። እንቀጥሌ።
‚የክብረ ነገሥት አ዗ጋጆች ዋና አሊማቸው ኢትዮጵያን አዱሲቱ እሥራኤሌ፣ ኢትዮጵያውያንንም እሥራኤሌ
዗ነፍስ አዴርገው ማቅረብ ነበር። ሇዙህ የሚረደ አስተሳሰቦች፣ ንዋያተ ቅዴሳት፣ ታሪኮች፣ እና ቅደሳት መካናት
ተ዗ጋጅተዋሌ። . . . እነዙህ ነገሮች ዜም ብሇው የመጡ አይዯለም። ሕዜቡ <<ቅደስና የተመረጠ የእግዙአብሔር
ሕዜብ>> ፣ ሀገሪቱ <<ሀገረ እግዙአብሔር>> ፣ መሆናቸውን ሇማስረገጥ ፣ ሇእሥራኤሌ ሕዜብ የተሰጠው ቃሌ
ኪዲን እሥራኤሌ የማይገባት ሆና በመገኘቷ ሇአዱሲቷ እሥራኤሌ ሇኢትዮጵያ መሰጠቱን ሇመግሇጥ፣ በዙያው
አያይዝም ሀገሪቱን ከጠሊት መጠበቅ ምዴራዊ ብቻ ሳይሆን ሰማያዊ ግዳታ፣ ሀገሪቱንም መንካት ሰማያዊ ቅጣት
የሚያመጣ መሆኑን ሇማሳየት ነው። ኢትዮጵያን በነጻነት ከጠበቋት ምክንያቶች አንደ ይኼ ጠንካራ እምነትና
አስተሳሰብ ነው። ‛ (ገጽ 325፣ አጽንዖት የኔ)
እንግዱህ ከዙህ ምንባብ እንዯምንረዲው ክብረ ነገሥት የሀገሪቱን ቅዴስና እና አንዴነት ሇማጠየቅ የተ዗ጋጀ
መጽሏፍ ነው። አሊማውም ታሪክን መዜግቦ ማቆየት ሳይሆን ይህን አስተሳሰብ በሕዜቡ መካከሌ ማስረጽ ነው። እኔ
ከሊይ ካለት ምንባቦች ዴምጸት የምረዲው ጸሏፊው ክብረ ነገሥት አበው ሇበጎ አሊማ (ብሔራዊ ስሜትን ሇማጎሌበት)
ሲለ የፈጠሩት ታሪክ ነው የሚሌ ሏሳብ ያሇው መሆኑን ነው። ግን በዙህ ሁለም ሰው ሊይስማማ ይችሊሌ። ስሇዙህ
ይህን የሚያጠናክር ምንባብ ምስክርነት ሌጥራ።
የሚቀጥሇው ምንባብ ከገጽ 25 ተወስድ ከሊይ ከቀረበው ምንባብ የሚቀጥሌ ነው።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 30

‚በኢትዮጵያ ታሪክ ራሱን ከእስራኤሌ ጋር የማያገናኝ ንጉሥ ነበር ማሇት አስቸጋሪ ነው። ይሁን እንጂ
የአኩስም ነገሥታት በሳንቲሞቻቸውም ሆነ በዴንጋይ ሊይ ጽሐፎቻቸው <<ሞዏ አንበሳ ዗እም ነገዯ ይሁዲ>>
የሚሇውን አሌተጠቀሙም። ራሳቸውንም <ሰልሞናዊ> ብሇው የጠሩበት መረጃ የሇንም።‛
‚ከእሥራኤሊዊ ዗ር ጋር ራስን ማገናኘት የሕዜባችን ባህሌ መሆኑን የምናየው በታሪከ ነገሥታቱ ብቻ ሳይሆን
በገዴሇ ቅደሳኑም ይህንኑ ባህሌ ማግኘታችን ነው። በባህሊዊው የ዗ር ቆጠራ ውስጥም አሇ። ስሇዙህ ነገሥታቱን
ሰልሞናዊና ሰልሞናዊ ያሌሆነ ብል መከፋፈለ አዋጭ አይዯሇም።‛ (ገጽ 31 ፣ አጽንዖት የኔ)
በእነዙህ ምንባቦች መሰረት የአኩስም ነገሥት ራሳቸውን ከእሥራኤሌ ጋራ ያያያዘበት መረጃ ስሇላሇ ይህ አይነቱ
ትረካ የመጣው ከአክሱም ዗መን በኋሊ ነው ማሇት ነው። የሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብም የ14ኛው መክ዗ ፈጠራ እና
የራስን የ዗ር ሏረግ ከእሥራኤሌ ጋር የማገናኘት ባህሌ ውጤት እንጂ ከዙያ በፊት ያሌነበረ ነው ማሇት ነው።
(በርግጥ ገኖ የወጣው ሏሳብ ይህ ይሁን እንጂ ይህን የሚቃረን የሚመስሌ ነገርም መጽሏፉ ውስጥ አሇ። ጸሏፊው
ታቦተ ጽዮንን አስመሌክቶ ሲጽፍ ታቦተ ጽዮን ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሯን የተቀበሇ ነው የሚመስሇው። ገጽ 308 ሊይ
የታቦተ ጽዮን መኖር በሀገሪቱ ውስጥ የኦሪት እምነት የነበረ ሇመሆኑ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧሌ። ገጽ 253 ሊይ ዯግሞ
እንዱህ ይሊሌ፡
‚በ9ኛው መክ዗ የአኩስም ካህናት ታቦተ ጽዮንን ይ዗ው ወዯ ዜዋይ የመጡት ከዙያ በፊት ስሇቦታው
የሚያውቁት ነገር ቢኖር ነው።‛
ጸሏፊው በአንዴ በኩሌ ‚ሰልሞናዊ ሥርወ መንግሥት አሌነበረም‛ የሚሌ መንፈስ ያሊቸው ክርክሮች የሚያቀርብ
ቢሆንም በላሊ በኩሌ ግን ከሰልሞናዊነት ትርክት (ከንግሥተ ሳባ እና ሰልሞን ታሪክ) ጋራ በማይነጣጠሌ መሌኩ
የተያያ዗ውን የታቦተ ጽዮንን በኢትዮጵያ መኖር መቀበለ ግርታ ይፈጥራሌ።
ጸሏፊው ታቦተ ጽዮን ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሯን ከተቀበሇ የአኩስም ነገሥት ራሳቸውን ሰልሞናዊ ብሇው
አሇመጥራታቸውን ሰልሞናዊ ሥርወ መንግሥት ሊሇመኖሩ እንዯ ማስረጃ እንዲቀረበው ሁለ ይህን ዯግሞ ሰልሞናዊ
ሥርወ መንግሥት ሇመኖሩ እንዯ ማስረጃ ማቅረብ ነበረበት።
ያ ካሌሆነ ዯግሞ ‘ታቦተ ጽዮን ወዯ ኢትዮጵያ እንዳት መጣች?’ ሇሚሇው ጥያቄ ከንግሥተ ሳባ ታሪክ ጋር
የማይያያዜ አማራጭ መሌስ ማቅረብ ነበረበት። ጸሏፊው ግን ሁሇቱንም አሊዯረገም። የሆነ ሆኖ ሇጊዛው ይህን መጣረስ
መዜግበን እንሇፈው።)
ጸሏፊው የሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ በ14ኛው መክ዗ ከክብረ ነገሥት መጻፍ በኋሊ የመጣ ነው ሲሌ ሊነሳው
ሏሳብ ግን ይህ ነገር ከዙያ በፊትም በሕዜቡ ዗ንዴ የነበረ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎችን ከመጽሏፉ ውስጥና ከላልች
ቦታዎች ሊቅርብ።
ጸሏፊው ገጽ 290 ሊይ አቡ ሳሊህ የተባሇው የአርመን ጸሏፊ ‘The Churches and Monasteries of Egypt and
Some Neighboring Countries’ በሚሇው መጽሏፉ በዚግዌ ዗መን ስሇነበረችው ኢትዮጵያ አንዱህ ሲሌ መጻፉን
ጠቅሷሌ።
‚የሏበሻው ንጉሥ ከዲዊት ዗ር የመጣ አይዯሇም። ነገር ግን ሙሴ ኢትዮጵያዊቱን ባገባ ጊዛ ከተገኘው
ትውሌዴ የወረዯ ነው። . . . ታቦተ ጽዮንም በኢትዮጵያውያን እጅ ናት።‛
ከዙህም በተጨማሪ ወዯ ፕሮፌሰር ታዯሰ ታምራት ይህን ጉዲይ በተመሇከተ የሚከተለትን መረጃዎች
አጋርተውናሌ። ዏፄ ካላብ ወዯ ዯቡብ አረቢያ ባዯረገው ዗መቻ ዋዛማ ኢትዮጵያን የጎበኘው ኮስማስ ‚Christian
Topography‛ በተሰኘው መጽሏፉ ንግሥተ ሳባ (ሆሜራዊ ከሆነ ሀገር መሆኗን ገሌጦ) ‚ብርቅዬ የስጦታ ዕቃዎቿን
ያገኘችው ከኢትዮጵያ ምዴር ነው።‛ ሲሌ መጻፉ ተገሌጿሌ። አንዱሁም ከሦስት ክፍሇ ዗መን በኋሊ የኖረ የግብጽ ቤተ
ክርስቲያን ዛና መዋዕሌ ጸሏፊም ‚ሰፊው ሀገር አቢሲንያ፣ ሰሇሞንን የጎበኘችው ንግሥተ ሳባ የመጣችበት ሀገር ነው።‛
ብል ጽፏሌ።13

13
Taddesse Tamrat (1968), Church and State in Ethiopia, pp. 456-7
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 31

ፕ/ር ሥርግው ሏብሇ ሥሊሴ ዯግሞ ጥንታዊውን የኢትዮጵያ ታሪክ በጥሌቅ በመረመሩበት ሥራቸው እንዱህ
ይለናሌ።
‚ኢትዮጵያን ከእሥራኤሌ የሚያገናኘው ይህ ጠንካራ እምነት ከጥንት ጊዛ ጀምሮ የነበረ ነው። በስዴስተኛው
ምዕት ዓመት የ(ዏፄ) ካላብን ሌጅ ‘ቤተ እሥራኤሌ’ የሚሌ ስያሜ ይዝ እናገኘዋሇን። የሰባተኛው ወይም
የስምንተኛው ምዕት ዓመት ሥሪት የሆነ ሳንቲምም ‘የጽዮንን ንጉሥ’ አፈ ታሪክ ይዞሌ። ዲግማዊ ኮስማስ
በተባሇው የግብጽ ፓትርያርክ ታሪክ ውስጥ የንግሥተ ሳባ ምዴር ወዯ ሆነችው ወዯ ኢትዮጵያ ጳጳስ መሊኩን
የሚያትት ምንባብ እናገኛሇን። በመካከሇኛው ዗መን ሇተወሰነ ጊዛ ወዯሥሌጣን የመጣው የዚግዌ ሥርወ
መንግሥትም የጥንቱ የእሥራኤሌ ሥርወ መንግሥት አስቀጣይ ባሇመሆኑ በቤተ ክህነቱ እና በሕዜቡ ዗ንዴ
ተቀባይነት አሌነበረውም። እነዙህ ነጥቦች ኢትዮጵያውያን (ይህን) ከጥንት የመጣ እና በውስጣቸው የሠረፀ እምነት
የሚያከብሩትና የሚጠብቁት መሆኑን ያሳያለ።‛14 (ትርጉም የኔ)
አንግዱህ ይህ ሁለ15 የሚያሳየን – ጸሏፊው አንዲሇው አክሱማውያን ነገሥት ራሳቸውን ሰልሞናዊ ብሇው
ባይጠሩም – የሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ እና ንግሥተ ሳባን ከኢትዮጵያ ጋራ ማያያዜ ግን ከአክሱም ዗መን ጀምሮ
የነበሩ እና በተሇያየ መንገዴ ሲገሇጹ የነበሩ መሆኑን ነው። በዙህ መሠረት የሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ በ14ኛው መክ዗
የመጣ ነው ማሇት አይቻሌም።
የሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ እውነት ሆነም አሌሆነም፣ ኢትዮጵያውያን ከአክሱም ዗መን ጀምሮ ሲያምኑበት ነበር።
የዚግዌ ነገሥትም በዙህ እምነት የተነሳ ምንም አንኳን ብዘ ታሊሊቅ ነገሮችን ቢሰሩም የተነሳባቸውን የሕጋዊነት ጥያቄ
ሉመሌሱት አሌቻለም። ሉሰመርበት የሚገባው ጉዲይ የሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ ከታሪካዊ እውነታነቱ የተሻገረ ሚና
ያሇው መሆኑ ነው። ሕዜብ ተቀብልታሌ፣ አንዳ ሕዜብ ከተቀበሇው በኋሊ ዯግሞ በሀገራችን ጉዝ ውስጥ ሉተካ
የማይችሌ ሚና ተጫውቷሌ። ስሇዙህ ታሪክ ሲጻፍ ሰልሞናዊነት ከስላቱ ሉወጣ አይችሌም። ሇዙህ ነው የጸሏፊው
‚ነገሥታቱን ሰልሞናዊና ሰልሞናዊ ያሌሆነ ብል መከፋፈለ አዋጭ አይዯሇም።‛ የሚሇው አስተያየት ተቀባይነት
የማይኖረው፤ የነገሥቱ ቅቡሌነት ወይም ቅቡሌነት ማጣት ሇብዘ ዗መናት ከሰልሞናዊነት ጽንሠ ሏሳብ ጋራ የተሳሰረ
ነበርና።
የጸሏፊው ‘዗ርን ከእስራኤሌ ጋራ ማገናኘት የቆየና በነገሥቱም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ዗ንዴ የተሇመዯ ነገር ነው’
የሚሇው መከራከሪያ ውሃ የማይቋጥረው ይህ ሌማዴ ከየት መጣ የሚሇውን ወሳኝ ጥያቄ ያሌመሇሰ በመሆኑ ነው።
ሌማደ ከራሱ ከሰልሞናዊነት ትርክት የመነጨ ከሆነ ሇሰልሞናዊነት ትርክት መነሻ ተዯርጎ ሉቀርብ አይችሌም፤ ይህ
circular reasoning የሚባሇውን የአመክንዮ ስህተት መፈጸም ይሆናሌ። ጸሏፊው ‚አይ፣ ላሊ ምንጭ አሇው‛ ካሇ
ዯግሞ ያን ማቅረብ አሇበት።
ይህን ጉዲይ ፕ/ር ሥርግው ከሊይ በዙያው ገጽ ከጠቀስነው ምንባብ ቀጥሇው ያስቀመጡትን እና ሇኔ በጣም
የተስማማኝን ሏሳብ በመጥቀስ እንዜጋው እና ወዯሚቀጥሇው፣ የዚግዌ ነገሥትን ሰልሞናዊ ወዯሚያዯርገው ክርክር
ጉዲይ እንሻገራሇን።
‚(ይህን ጉዲይ በተመሇከተ) የታሪክ ተመራማሪው አቋም ከተራው ሕዜብ አቋም ምንም ያህሌ አይሇይም።
ምንም ማስረጃ ሳይኖረው የሕዜቡን እምነት ወይም አመሇካከት መሇወጥ አይችሌም። ስሇዙህ አዲዱስ ትረካዎችን
ይ዗ን ከመምጣታችን በፊት ማስረጃ ማግኘት አሇብን። ‚Status quo‛ የሚሇው አባባሌ እዙህ ጋ ተመራጭ
የሚሆነው አዱስ ነገር ካሌተገነባ ማፍረስ ብቻውን በቂ ስሊሌሆነ ነው። ፍርስራሽ መተው ቀሊሌ ነው፤ መሌሶ
መገንባት ግን ከባዴ ነው። በቦታቸው የተሻሇ ነገር ማስቀመጥ እስካሌቻሌን ዴረስ የኢትዮጵያን ጥንታውያን
ትረካዎች አንጣሊቸው።‛16

14
Sergew Hable Sellassie (1972), Ancient and Medival Ethiopian History, p. 42
15
በምንባቡ ውስጥ ኮስማስ የተባሇው አሥረኛው መቶ ክፍሇ ዗መን የኖረ የግብጽ ፓትርያርክ መሆኑ በዙያው መጽሏፍ (ገጽ 215) ሊይ ተገሌጿሌ።
16
Ibid
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 32

2. የዚግዌ ነገሥት ሰልሞናውያን ናቸው


በታወቀው የሰልሞናዊነት ብያኔ መሰረት አንዴ ሰው ‘ሰልሞናዊ ነው’ የሚባሇው የንግሥተ ሳባ እና የንጉሥ
ሰልሞን ሌጅ ከሆነው ከቀዲማዊ ምኒሌክ ዗ር ሲወሇዴ ነው። ሇምሳላ በ1931 የወጣውን የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት
ሦስተኛ አንቀጽ ሄዯን ብንመሇከት ይህን ነው የሚሇው።17 ነገር ግን ጸሏፊው የዚግዌን ነገሥት ሰልሞናዊነት ሇማሳመን
ያቀረባቸው ምክንያቶች ሇሰልሞናዊነት ላሊ መስፈርት የሚያወጡ ናቸው።
ከእነዙህ ውስጥ የመጀመሪያው የዚግዌ ነገሥት ‚ሇእስራኤሌ ባህሌና እምነት ቅርብ ስሇነበሩ ሰልሞናውያን ናቸው‛
የሚሇው ነው።
‚. . . የዚግዌ ነገሥታትን ያህሌ ራሱን ሇእስራኤሌ ባህሌና እምነት ያቀረበ ማንም ኢትዮጵያዊ ሥርወ
መንግሥት የሇም። ከሁለም ሥርወ መንግሥቶች ወዯ ኢየሩሳላም በመጓዜ የዚግዌ ነገሥታትን የሚስተካከሌ
የሇም። ቅደስ ሊሉበሊና ይምርሏነ ክርስቶስ ሇዙህ ማሳያ ናቸው። ቅደስ ሊሉበሊ የሮሏን ውቅር አብያተ
ክርስቲያናት ሲሠራ በሰማያዊቷና ምዴራዊቷ ኢየሩሳላም አምሳያ ነው። የዚግዌ ነገሥታት በሠሯቸው ውቅር
አብያተ ክርስቲያናት ሁለ የዲዊት ኮከብ ምስሌ ይገኛሌ። ታዴያ በምን መሌኩ ነው የዚግዌ ነገሥት ከላልች
ነገሥታት ተሇይተው <ሇሰልሞናዊነት> የማይበቁት?‛ (ገጽ 27) (እነዙህን ተመሳሳይ ነጥቦች ‚ታዱያ ማን ከማን
በሌጦ ሰልሞናዊ ይሆናሌ?‛ ከሚሌ ኃይሇ ቃሌ ጋራ ገጽ 29 ሊይ በዴጋሚ እናገኛቸዋሇን።)
ገጽ 280 ሊይም ‘የዚግዌ ነገሥት አበርክቶት’ በሚሌ ርዕስ ስር ከሊይ የተጠቀሱትና ላልችም ተመሳሳይ ክርክሮች
ቀርበዋሌ። እዙህ ጋ የተጨመሩት ክርክሮች
- ከዚግዌ ነገሥት መካከሌ የሆነው ጠጠውዴም ‘ሰልሞን’ የሚሌ የንግሥና ስም ተጠቅሟሌ፤
- የዲዊትን ኮከብ በአርማነት ተጠቅመዋሌ፤
የሚለ ናቸው። እነዙህ ሁለ ነገሮች ግን እውነት ሆነው ሳሇ ከሊይ ባስቀመጥነው መስፈርት መሠረት
ከሰልሞናዊነት ጋራ ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የሇም። የአኩስም ነገሥትን ወይም ይኩኖ አምሊክን እና ተከታዮቹን
ከእሥራኤሌ ጋር የሚያገናኛቸው ታሪክ አሇ። ስሇዙህ ሳንቲሞቻቸው፣ ስሞቻቸው ወይም መዓርጎቻቸው ሊይ
ከእሥራኤሌ ጋር የተያያዘ ነገሮች የመገኘታቸው መሠረት ያ ታሪክ ነው። ዚግዌ ነገሥት ይህ የታሪክ ግንኙነት የሊቸውም
፤ ሳንቲሞቻቸው እና ስሞቻቸውም በነበሩበት ዗መን ራሱ ተቀባይነት ሉያስገኙሊቸው አሌቻለም። ስሇዙህም እነዙህ
ነገሮች ሇዚግዌ ነገሥት ሰልሞናዊነት ማስረጃ ሆነው ሉቀርቡ አይችለም።
ሁሇተኛው የዚግዌ ነገሥትን ሰልሞናዊ የማዴረግ ሙከራ ዯግሞ እነሱን የአኩስም ሥርወ መንግሥት አስቀጣይ
አዴርጎ ማቅረብ ነው። ወዯ ገጽ 33 እንሂዴ።
‚መራ ተክሇ ሃይማኖት . . . የንጉሡን ሌጅ አግብቶ በአማቱ ሊይ በማመጽ ከገዯሇው በኋሊ ጠንካራ የሆነ
ዴጋፍ ሉያገኝ ወዯሚችሌበት ወዯ ሊስታ መጥቶ የዚግዌን ሥርወ መንግሥት መሠረተ። . . . ይህ ታሪክ ሁሇት
ነገሮችን ያሳየናሌ። የመጀመሪያው የዚግዌ ነገሥታት ራሳቸውን የአኩስም ሥርወ መንግሥት አስቀጣይ እንጂ የተሇዩ
መንግሥታት አዴርገው የማያዩ መሆናቸውን . . . ነው።‛
እዙህ ምንባብ ውስጥ የቱ ጋ የዚግዌ ነገሥት ራሳቸውን የአኩስም ሥርወ መንግሥት አስቀጣይ አዴርገው
አንዯሚያዩ የሚያሳይ ነገር እንዲሇ ሇኔ አይገባኝም። የተገሇጸው ሁኔታ የሚመስሇው መፈንቅሇ መንግሥት ነው። መራ
ተክሇ ሃይማኖት የንጉሡን ሌጅ ቢያገባም ሇንግሥና አሌታጨም፣ ስሇዙህ ያካሄዯው መፈንቅሇ መንግሥት ነው።
ሇዙህ በጣም ጥሩ ምሳላ የሚሆነው የሳኦሌና የዲዊት ታሪክ ነው። ዲዊት የሳኦሌን ሌጅ አግብቷሌ። ግን
የሚቆጠረው የአዱስ ሥርወ መንግሥት መስራች ተዯርጎ እንጂ የሳኦሌ ሥርወ መንግሥት አስቀጣይ ተዯርጎ አይዯሇም።
ወዯ ኢትዮጵያ ታሪክ መጥተን የቅርብ ጊዛ ምሳላዎችን ብናነሳም ሇምሳላ ራስ ጉግሳ ወላ የወይ዗ሮ ዗ውዱቱ ባሌ የነበሩ
ቢሆንም ወይ዗ሮ ዗ውዱቱ እንዱነግሡ ሲወሰን እርሳቸው ከባሇቤታቸው ተሇይተው ወዯ ግዚታቸው እንዱመሇሱ ነው
የተዯረገው። የኃይሇ ሥሊሴን ሴት ሌጆች ያገቡት ዯጃዜማች ኃይሇ ሥሊሴ ጉግሳም ሆኑ ራስ ዯስታ ዲምጠው የመንገሥ
ዕዴሌ አሌነበራቸውም። እናም መራ ተክሇ ሃይማኖት ከንጉሡ ጋር የነበረው ዜምዴናም ሆነ ዘፋኑን የተቆጣጠረበት

17
ቃሇአብ ታዯሰ፣ ሕገ መንግሥት በኢትዮጵያ ከፍትሏ ነገሥት እስከ ኢፌዱሪ ፣ ገጽ 56
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 33

መንገዴ የዚግዌ ነገሥት ራሳቸውን የአክሱም ሥርወ መንግሥት አስቀጣዮች አዴርገው እንዱመሇከቱ የሚያዯርጋቸው
አሌነበረም። ሕዜቡም እንዱያ አዴርጎ አሌተመሇከታቸውም።
ገጽ 28 ሊይም ጸሏፊው ይህኑ ዴምዲሜ ሇመዯገፍ የሚከተለትን ነጥቦች አቅርቧሌ።
- የዚግዌ ነገሥት የአኩስምን ትውፊት ወርሰዋሌ፣ ይህንም በስነ ጽሐፋቸው፣ በኪነ ሕንፃቸው ወ዗ተርፈ
አንጸባርቀዋሌ፤
- ሊሉበሊ ራሱን ከኢዚና ጋራ በተመሳሳይ መንገዴ ገሌጧሌ፤
- የዚግዌ ነገሥት ሰሜናዊ መሠረት አሊቸው፤
- በግዕዜ ቋንቋ ተጠቅመዋሌ፤
እነዙህ ነጥቦች በራሳቸው ትክክሌ ናቸው። በኢትዮጵያ የተሇያዩ ሥርወ መንግሥታት መካከሌ የተካሄዯውን
የታሪክና የባህሌ ቅብብልሽም ያሳያለ። ግን የዚግዌ ነገሥት ከአኩስም ነገሥት ጋራ ተመሳሳይ ቋንቋ እና ባህሌ
መጋራታቸው የአንዴ ሥርወ መንግሥት አባሊት አያዯርጋቸውም። ሇምሳላ በ዗መኑ የነበሩት የንጉሣዊ ቤተሰብ ተወሊጅ
ያሌሆኑ የአኩስም ሰዎች ተነስተው ሥሌጣን ቢይዘ ኖሮ ራሱ በባህሌ እና በቋንቋ ምንም ሌዩነት ባይኖራቸውም፣
ከንጉሣዊ ቤተሰብ ባሇመወሇዲቸው ብቻ የአዱስ ሥርወ መንግሥት መስራች ተዯርገው መታየታቸው አይቀሬ ነበር።
ሦስተኛው የክርክር መንገዴ ዯግሞ ‚የዚግዌ ነገሥት አና የሰልሞናዊው ሥርወ መንግሥት መስራች ይኩኖ አምሊክ
ሁሇቱም የቡግና ተወሊጆች ስሇሆኑ የዚግዌ ሥርወ መንግሥት እና ይኩኖ አምሊክ የመሠረተው ሥርወ መንግሥት
ሰልሞናዊ ሇመባሌ ያሊቸው መብት እኩሌ ነው።‛ የሚሌ ነው።
‚. . . ወዯ ኢየሩሳላም በመጓዜ የዚግዌን ነገሥታት የሚተካከሌ የሇም። ታዴያ ማን ከማን በሌጦ ሰልሞናዊ
ይሆናሌ? የሰልሞናዊ ሥርወ መንግሥት መሊሽ የሚባሇው ራሱ ይኩኖ አምሊክም በእናቱ የቡግና ሰው መሆኑን
ነው ትውፊቱ የሚተርከው። የተማረውም ወል ሏይቅ ገዲም ነው። እንዯነገሠ መጀመሪያ ያነጸውም ወል ሊሉበሊ
የምትገኘውን ገነተ ማርያምን ነው። . . .‛ (ገጽ 29)
‚. . . ይህ ታሪክ (መራ ተክሇ ሃይማኖት የንጉሡን ሌጅ ካገባ በኋሊ ንጉሡን ገዴል፣ ወዯ ሊስታ ሄድ መንገሡ)
ሁሇት ነገር ያሳየናሌ። . . . ሁሇተኛው ዯግሞ የዚግዌን ሥርወ መንግሥትም ሆነ በኋሊ ተመሇሰ የሚባሇውን
የሰልሞን ሥርወ መንግሥት የመሠረቱት ሁሇቱም የቡግና ሰዎች መሆናቸውን ነው።‛ (ገጽ 33)
ሲጀመር ይኩኖ አምሊክ የቡግና ሰው ነው መባለ ትክክሌ አይዯሇም ብዬ ነው የማምነው። ግን ነው እንኳን ቢባሌ
ከሰልሞናዊነት ጋር ወይም አዱስ ሥርወ መንግሥት ከመመሥረት ጋራ ምን አገናኘው? ከሊይ እንዯተባሇው
የሰልሞናዊነት መስፈርቱ ከቀዲማዊ ምኒሌክ ዗ር መወሇዴ ብቻ ነው። ሁሇት ነገሥትም ከተመሳሳይ አካባቢ ስሇመጡ
ብቻ የግዴ የአንዴ ሥርወ መንግሥት አባሊት ናቸው ወይም ዗ራቸው የግዴ ከተመሳሳይ ግንዴ ይመ዗ዚሌ ማሇት
አይዯሇም።
በመጨረሻ ሊነሳት የምፈሌጋት አንዱት ክርክር አሇች፤ ጸሏፊው የዚግዌን ነገሥት ሰልሞናዊነት ፍሇጋ የክብረ
ነገሥትን ብር የሚያንኳኳባት።
‚ሰልሞናዊ የሚያሰኘው ከሰልሞን ዗ር ጋር መያያዜ ከሆነ ራሱ ክብረ ነገሥትም እንዯጠቀሰው የዚግዌም
ነገሥታት ከሰልሞን ጋር የተያያ዗ የ዗ር ሏረግ አሊቸው።‛ (ገጽ 26-7)
ጸሏፊው ይህን ሲሌ የዚግዌ ነገሥት ከሰሇሞን እና ከንግሥተ ሳባ አገሌጋይ የተወሇዯው ሌጅ ዗ር መሆናቸውን
የሚናገረውን ታሪክ እየጠቀሰ መሆን አሇበት። ሥርግው ሏብሇ ሥሊሴ ይህ ታሪክ የዚግዌ ነገሥት ሰልሞናዊ አይዯለም
የሚሇውን እምነት በማፍረስ በሕዜቡ ዗ንዴ ተቀባይነት ሇማግኘት የፈጠሩት መሆኑን ይነግሩናሌ።18 ነገር ግን ታሪኩ
የፈሇጉትን ቅቡሌነት አሊስገኘሊቸውም። ታሪኩ ክብረ ነገሥት ሊይ መኖሩን እርግጠኛ መሆን አሌቻሌሁም – ጸሏፊው
ይህን ሲሌ ምንም አሌጠቀሰም፣ ፕ/ር ሥርግው ዯግሞ ላሊ መጽሏፍ ነው የጠቀሱት። ነገር ግን ጸሏፊው ክብረ ነገሥትን
ሇዚግዌ ነገሥት ሰልሞናዊነት ምስክር አዴርጎ መጥራቱ ፈገግ ያሰኛሌ፣ ምነው ቢለ በጸሏፊው በራሱ ሏተታ መሠረት
(ገጽ 25) የክብረ ነገሥት አንደ አሊማ የዚግዌ ነገሥትን በተሇይ ከዘፋኑ በማግሇሌ ሇይኩኖ አምሊክ ወራሾች
ንግሥናቸውን ማጽናት ነበርና ነው።
18
Sergew Hable Sellassie (1972), Ancient and Medival Ethiopian History, p. 241
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 34

6. አቡነ ተክሇ ሃይማኖት እና የይኩኖ አምሊክ ንግሥና


በመጽሏፉ ውስጥ ጸሏፊው አጥብቆ ከተቃወማቸው ጉዲዮች አንደ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ይኩኖ አምሊክ ወዯ ዘፋን
ይወጣ ዗ንዴ እገዚ አዴርገዋሌ መባለ ነው። አዯረጉ የሚባሇው እገዚ ከመዜገብ መዜገብ በመጠንም በዓይነትም ይሇያያሌ ፤
ጸሇዩሇት፣ በኅብረተሰቡ ዗ንዴ ያሊቸውን ተቀባይነት በመጠቀም ሕዜቡ ከእርሱ ጎን እንዱቆም አዯረጉ (ቀሰቀሱ)፣ ሥሌጣኑን
ይሇቅሇት ዗ንዴ የወቅቱን ንጉሥ፣ ይትባረክን፣ አሳመኑት፣ ዗ውዴ ጫኑሇት፣ ወ዗ተርፈ።
የተሇያዩ ጸሏፊዎች ይህን ጉዲይ በተመሇከተ የተሇያየ አቋም ወስዯዋሌ። ጸሏፊው ዯግሞ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት እንኳን
ሇይኩኖ አምሊክ እገዚ ሉያዯርጉ፣ ሁሇቱ ሰዎች እንዱያውም ተገናኝተው አያውቁም ባይ ነው። ይህ አዱስ አቋም አይዯሇም።
ፕሮፈሰር ታዯሰ ታምራትም ይህን አቋም አራምዯዋሌ።19 በላሊ በኩሌ ፕሮፈሰር ሥርግው ሏብሇ ሥሊሴ አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት ይህን መሰሌ ሚና መጫወታቸውን አረጋግጠው ጽፈዋሌ።20 ይህ የሚያሳየን ዗መናውያን ታሪክ ጸሏፍያን
መካከሌም ቢሆን በዙህ ጉዲይ ዘሪያ ስምምነት ሊይ ያሌዯረሱ መሆኑን ነው።
የኔ ትችት የሚመነጨው ዴምዲሜው ተገቢ አይዯሇም ከሚሌ ሳይሆን ጸሏፊው ዴምዲሜውን ሇመዯገፍ
ከተጠቀመባቸው መከራከሪያዎች የተወሰኑት አመክንዮአቸው የተዚባ እና በመጽሏፉ ከተጠቀሱት ላልች መረጃዎች ጋራ
የሚጣረሱ ከመሆናቸው ነው። ነገር ግን ችግር አሇባቸው ወዯምሊቸው ነጥቦች ከመዜሇቄ በፊት ጸሏፊው የያ዗ውን አቋም
የሚዯግፉሇትን ጥሩ ነጥቦች ሊስቀምጥ።
- በመጀመሪያ ፡ (ጸሏፊው እንዯሚሇው ከሆነ) በ15ኛው መክ዗ የተጻፉት የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች ይህን
ጉዲይ አያነሱትም።
- ሁሇተኛ ፡ አብዚኞቹ የገዴለ ቅጅዎች ውስጥ የተቀመጡት የጊዛ ሰላዲዎች ሇዙህ ጉዲይ ክፍተት የሚተዉ
አይዯለም። (ነገር ግን፡ ወዯፊት እንዯምናየው፡ ይህ ማሇት በሁለም ቅጅዎች ውስጥ ምንም ክፍተት የሇም ማሇት
አይዯሇም።)
ከዙህ ቀጥል ዯግሞ መዚባት እና መጣረስ ያየሁባቸውን መከራከሪያዎች አንዴ በአንዴ እሄዴባቸዋሇሁ።
1. አቡነ ኢየሱስ ሞዏ እያለ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት አንጋሽ አይሆኑም።
ጸሏፊው ገጽ 32 ሊይ እንዱህ ይሊሌ።
‚(በ1263) ቀዴመው በመመንኮስም ሆነ በዕዴሜ (አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን) የሚቀዴሟቸው አቡነ ኢየሱስ
ሞዏ በሕይወት ነበሩ። ይኩኖ አምሊክም የአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ተማሪ ነበር። በወቅቱም በገዲማቱ ተሰሚነት
የነበራቸውና ራሳቸውን አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ጨምሮ አያላ ዯቀ መዚሙርት ያፈሩት አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ናቸው።
ታዱያ በምን ምክንያት አቡነ ኢየሱስ ሞዏ እያለ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት መንግሥት አ዗ዋዋሪ ይሆናለ?‛
አቡነ ተክሇ ሃይማኖት መንግሥት በመ዗ዋወሩ ውስጥ ሚና ነበራቸው ማሇት አቡነ ኢየሱስ ሞዏ በጉዲዩ
አሌነበሩበትም ማሇት አይዯሇም። ሇምሳላ ሥርግው ሏብሇ ሥሊሴ ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏን፣ ገዴሇ ተክሇ ሃይማኖትን እና
ላልችንም ሀገርኛ መዜገቦች ጠቅሰው የጻፉት ሁሇቱም አባቶች በዜውውሩ ሚና እንዯነበራቸው ነው።21 አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት አዯረጉት የሚባሇው አስተዋጽዖም ከሊይ እንዯተገሇጸው ከመዜገብ መዜገብ ይሇያያሌ። አቡነ ተክሇ ሃይማኖት
የሸዋ ሉቀ ካህናት ሆነው መሾማቸውን ብዘዎቹ ገዴሊት መዜግበውታሌ፣ ጸሏፊውም ተስማምቶበታሌ። በመጽሏፉ
ውስጥ የተጠቀሱ ላልች መዚግብት ይህን ሹመት እስከ ኤጲስቆጶስነት ያዯርሱታሌ። ከሹመታቸውም ላሊ አቡነ ተክሇ
ሃይማኖት በወቅቱ ሸዋ ውስጥ ሇነበረው ክርስቲያን ኅብረተሰብ (ቁጥሩ ብዘም ባይሆን) የመንፈስ አባት ነበሩ። አቡነ
ተክሇ ሃይማኖት ተ዗ዋውረው ያስተማሩባቸውንም ቦታዎች ስንመሇከት ይኩኖ አምሊክ ዴጋፍ ሰበሰበባቸው ከተባለት
ቦታዎች ጋራ ተመሳሳይ ናቸው። ስሇዙህ ይኩኖ አምሊክ ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ በተጨማሪ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን
ወዲጅነት ቢፈሌግ አይገርምም።

19
Taddesse Tamrat (1968), Church and State in Ethiopia, p. 126
20
Sergew Hable Sellassie (1972), Ancient and Medival Ethiopian History, pp. 282-9
21
Ibid
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 35

‚ኮንቲ ሮሲኒ በኤርትራ አግኝቶ ባሳተመው አንዴ ጥንታዊ የግእዜ መዜገብ ሊይ ይኩኖ አምሊክን የረደት ሰባት
ቤት ጉዲም – ወግዲ መሇዚይ፣ ዱን ዯበራይ፣ ሙገር እንዯዚቢ፣ ወጅ፣ ወረብ እነካፌ፣ ጽሊሌሽ እነጋፊ እና መዋይ
አውዣዣይ – መሆናቸውን ይገሌጣሌ። ይህም አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከተወሇደበት ቦታ አንሥቶ ያስተማሩባቸው
አብዚኞቹ የሸዋ አካባቢዎች የጋፋቶች አካባቢዎች መሆናቸውን ያሳየናሌ።‛ (ገጽ 606)
ስሇዙህ አቡነ ኢየሱስ ሞዏ በሕይወት መኖራቸው ምናሌባት አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ዗ውዴ ጫኝ ከመሆን
ይከሇክሊቸው ካሌሆነ በቀር ሇይኩኖ አምሊክ ዴጋፍ ከማዴረግ ግን አያግዲቸውም።
ጸሏፊው በዙሁ የክርክር መስመር ላልች ነጥቦችንም አንስቷሌ።
‚ይህ ነገር (አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የመንግሥት አ዗ዋዋሪ አዴርጎ ማሰብ) የመጣው . . . አቡነ ተክሇ
ሃይማኖትን እና ይኩኖ አምሊክን አዚምድ እርሳቸው ሇሱ ያዯለ አዴርጎ ከማሰብ . . . ነው።‛ (ገጽ 32)
‚ይህ ታሪክ (የመራ ተክሇ ሃይማኖት ወዯ ሥሌጣን አመጣጥ) ሁሇት ነገር ያሳየናሌ። . . . ሁሇተኛው ዯግሞ
የዚግዌን ሥርወ መንግሥትም ሆነ በኋሊ ተመሇሰ የሚባሇውን የሰልሞን ሥርወ መንግሥት የመሰረቱት ሁሇቱም
የቡግና ሰዎች መሆናቸውን ነው። ያም ብቻ ሳይሆን የሏይቅ እስጢፋኖስን ገዲም የመሠረቱት አቡነ ኢየሱስ ሞዏም
የዲህና ተወሊጅ ናቸው።‛ (ገጽ 33)
ከነዙህ ሁሇት ምንባቦች የምንረዲው የክርክር ጭብጥ ‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖትና ይኩኖ አምሊክ የአንዴ አካባቢ
ሰዎች አይዯለም፤ አቡነ ኢየሱስ ሞዏና ይኩኖ አምሊክ ግን ናቸው። ስሇዙህም አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ናቸው ይኩኖ
አምሊክን ዗ውደን እንዱያገኝ ሉረደት የሚችለት።‛ የሚሌ ነው። ይኸው ሏሳብ ገጽ 40 ሊይ በዯንብ ተቀምጧሌ።
‚በዙህ የሥሌጣን ሽግግር ወቅት ብርቱ ሚና የተጫወቱት አቡነ ኢየሱስ ሞዏና ሏይቅ አስጢፋኖስ ናቸው።
አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ይኩኖ አምሊክን በማስጠሇሌ ረዴተውታሌ። ወዯ ቤተ አምሏራ ተሻግሮ ከቤተ አምሏራና ከሸዋ
ኃይሌ ሉያሰባስብ የቻሇው በሏይቅ አስጢፋኖስ እያሇ ባገኘው ዕውቀትና ዕውቅና ነው። ከዙህም በተጨማሪ ይኩኖ
አምሊክና አቡነ ኢየሱስ ሞዏ በአንዴ አካባቢ በቡግና ያዯጉ መሆናቸው በቀሊለ ሇመተዋወቅና ሇመቀራረብ
ሳይረዲቸው አሌቀረም።‛
በበኩላ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትም ሆኑ አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ይኩኖ አምሊክ ዗ውደ ይገባዋሌ ብሇው እስካመኑ ዴረስ
ረዴተውት ቢሆን ችግር አሇው ብዬ አሊስብም። ነገሮች በሰሊማዊ መንገዴ እንዱያሌቁ አስተዋጽዖ አዴርገው ከሆነ ዯግሞ
እንዱያውም ሉመሰገኑበት ይገባሌ። ይሁን እንጂ የተሇያዩ ጸሏፊዎች ጉዲዩን ከዜምዴና እና ከጥቅም ጋር አያይ዗ውታሌ።
ምንም አንኳን (የ዗መናዊው የታሪክ አጻጻፍ ጠባይ ሆኖ) የግሌ ጥቅምና ዜምዴና ምክንያት ሉሆኑ ይችሊለ ተብሇው
ቢገመቱም – ይህ ግን መረጋገጥ የሚችሌ ነገር አይዯሇም። ይሌቁንም ከሊይ እንዲየነው የነገሥቱ ዗ር ከቀዲማዊ ምኒሌክ
መመ዗ዜ ከረዥም ጊዛ በፊት ጀምሮ በሕዜቡ የሚታመንበት ነገር ነበር። የዚግዌ ነገሥትም በዙህ ጉዲይ ተቸግረውበት
አንዯነበር አይተናሌ። ስሇዙህ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትም ሆኑ አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ይህን ቢያምኑበት እና ሇይኩኖ አምሊክ
በጸልት ወይም በማዯራዯር ዴጋፍ ቢያዯርጉ ጥቅመኛ የሚያሰኛቸው አይመስሇኝም። ይኩኖ አምሊክም ውሇታቸውን
ሇመክፈሌ ሇቤተ ክርስቲያን መሬት፣ ሇእነርሱና ሇሌጆቻቸው ዯግሞ ሹመት ቢሰጥ ተገቢ አይዯሇም የሚባሌበት
ምክንያት አይታየኝም።
ይህን ካሌሁ ዗ንዲ የጸሏፊውን ክርክር ወዯ መተቸት ሌሇፍ። የመጀመሪያው የክርክሩ ችግር ይኩኖ አምሊክ ከአቡነ
ተክሇ ሃይማኖትም ሆነ ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ እንዱሁም ከሸዋና ከአምሏራ ሰዎች ያገኘውን ዴጋፍ እና ከነገሠ በኋሊ
ያገኘውን ተቀባይነት ምንጭ ጠሇቅ ብል አሇመመርመሩ ነው። ይኩኖ አምሊክ ይትባረክን አሸንፎ ዗ውዴ ሲዯፋ
በሕዜብ ዗ንዴ ተቃውሞ ያሌተነሳበት ሇምንዴነው? ምንም የጦር ኃይሌ ቢኖረው በሕዜቡ ዗ንዴ ቅቡሌነት
የሚያስገኝሇት የታሪክና የሕግ መሠረት ከላሇው የትኛውም ባሇሥሌጣን ወይም ንጉሥ በሰሊም መግዚት እንዯማይችሌ
ነው የኢትዮጵያ ታሪክ የሚነግረን። የዚግዌ ነገሥት ሊይ የተነሳው ተቃውሞ፣ በመካከሇኛው ዗መን የነበሩ መኳንንት
ሥሌጣናቸውን ሇማጠናከር ሲዋጉ ሁሌጊዛም ሌዐሊኑን ከፊት አዴርገው መሆኑ፣ የመሳፍንት የበሊይነት እና ገዢነት
በአገር የታወቀ በሆነበት በ዗መነ መሳፍንትም እንኳን መሳፍንቱ ዗ውዴ ሇመጫን አሇመዴፈራቸው የሚያሳየን ይህን
ነው። ስሇዙህ ጉዲዩ የኃይሌ፣ የዕውቅና ወ዗ተ አይዯሇም። የሸዋና የአምሏራ በኋሊም የላልች አካባቢዎች ሕዜቦች ይኩኖ
አምሊክን የተቀበለት ራሱን ከአኩስም ነገሥት ጋር ስሊገናኘ ነው። የዚግዌ ነገሥት ዯግሞ ተቀባይነት ያጡት ይህ
ግንኙነት ስሊሌነበራቸው ነው እንጂ የቡግና ሰዎች ስሇነበሩ አይዯሇም። ይህ ግንኙነት የላሊቸው ሰዎች ከአኩስምም
መጡ ከሊስታ፣ ከሸዋም ተገኙ ከአምሏራ በሕዜቡ ዗ንዴ ቅቡሌነት ሉያገኙ አይችለም ነበር።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 36

ጸሏፊው ይህን አማራጭ የትረካ መንገዴ ሇመከተሌ የወሰነው ‘ዚግዌ ዯገፍ’ ሲሌ የጠራቸው ሉቃውንት አቡነ
ተክሇ ሃይማኖት ሇይኩኖ አምሊክ አዯረጉት የተባሇውን ዴጋፍ በበጎ አይን ስሇማይመሇከቱት፣ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን
ከክሱ ነጻ ሇማውጣት ነው ብዬ አስባሇሁ። በተቃራኒው ሚናውን ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ሚናውን የሰጣቸው ዯግሞ
እርሳቸው የዙያው የቡግና ሰው ስሇሆኑ እና በዙህ ሳቢያ ሇበፊቱም ሆነ ሇአዱሱ ንጉሥ እኩሌ ቀረቤታ ስሊሊቸው፣ ይህን
ሚና ቢጫወቱ ‚ሇ዗መዲቸው አዯለ‛ አይባለም ከሚሌ ስላት ይመስሇኛሌ። ግን ይህ አካሄዴ ምንም እንኳን ሏሳቡ ቀና
ቢሆን አመክንዮው ትክክሌ አይዯሇም። ዚግዌ ዯገፍ የተባለት ሰዎችም ነገሩን ከ዗ር እና ከዜምዴና ጋር ከሚያያይዘት
ይሌቅ ከንግሥተ ሳባ ታሪክ ጋር የተያያ዗ው ትረካ በወቅቱ የነበረውን ተቀባይነት ቢያጤኑት የተሻሇ ይመስሇኛሌ።
ጸሏፊው ከዙህ በተጨማሪ የዚግዌ ነገሥት ሇቤተ ክርስቲያን ያሊቸውን ቀረቤታ በማውሳት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት
ከእነርሱ ይሌቅ ሇይኩኖ አምሊክ ሉያዯለ እንዯማይችለ ተከራክሯሌ።
‚ምንም እንኳን በወቅቱ በነበሩት የቤተ መንግሥት እና የቤተ ክህነት ሌሂቃን ዗ንዴ ተቀባይነቱ አናሳ የነበረ
ቢመስሌም የዚግዌ ሥርወ መንግሥት በኋሊ ከመጣው ሥርወ መንግሥት ይሌቅ ሇቤተ ክርስቲያን ቅርብ ነው።
በሥርወ መንግሥቱ ከተነሱት ወዯ አሥራ አንዴ ነገሥታት መካከሌ አራቱ ቅደሳን ናቸው። . . . ከይኩኖ አምሊክ
በኋሊ ከመጣው ከሰልሞናዊ ሥርወ መንግሥት ውስጥ ግን ከዏፄ ቴዎዴሮስ አንዯኛና ከሰማዕቱ ከዏፄ ገሊውዳዎስ
በቀር በይፋ የታወቀ ቅደስ ንጉሥ የሇም። ይኼም የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተሳሰብ ከፖሇቲካው እሳቤ የተሇየ
መሆኑን ያሳየናሌ። ሇዙህም ነው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከዚግዌ ነገሥታት ይሌቅ ሇይኩኖ አምሊክ የሚያዯለበት
ምክንያት የማይኖረው።‛
ይህ በጣም አስገራሚ እና ፈጽሞ ትርጉም የማይሰጥ ክርክር ነው።
አንዯኛ፡ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሇይኩኖ አምሊክ የሚያዯለበት ምክንያት ከላሇ አቡነ ኢየሱስ ሞዏስ በምን
ምክንያት ሇእርሱ ያዯሊለ? አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የቤተ ክርስቲያንን አስተሳሰብ የሚወክለ፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ግን
ከቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ ውጪ ናቸው እንዳት ሉባሌ ይችሊሌ? ሁሇቱም ሰዎች በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህድ ቤተ
ክርስቲያን ቅዴስና የተሰጣቸው ናቸው። እንዱያውም ጸሏፊው ራሱ እንዯገሇጠው በዕዴሜም ሆነ በመመንኮስ አቡነ
ኢየሱስ ሞዏ ከአቡነ ተክሇ ሃይማኖት ይቀዴማለ። ታዱያ በምን መስፈርት ነው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የቤተ
ክርስቲያንን ሏሳብ የሚወክለ፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ዯግሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሇየ ‚ፖሇቲካዊ‛ አስተሳሰብ አራማጅ
የሚሆኑት?
ሁሇተኛ፡ ‚የቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ‛ ማሇት ምን ማሇት ነው፣ በማንስ ነው የሚወከሇው? እኔ የማውቀው እና
በመጽሏፉም በየቦታው የተገሇጠው ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ጽዮን በቀዲማዊ ምኒሌክ አማካይነት መጥታ በአክሱም
ማረፏን እና ከቀዲማዊ ምኒሌክ የተነሳው እና እስከ ቀዲማዊ ኃይሇ ሥሊሴ የቀጠሇው ሥርወ መንግሥት ሕጋዊ
የኢትዮጵያ ገዥ መሆኑን በተሇያየ ጊዛ በተዯረሱ የብራና መጻሕፍቷ ሊይ የመሰከረች መሆኑን ነው። ቤተ ክርስቲያን
ሇአራት የዚግዌ ነገሥት ቅዴስና ብትሰጥ እኮ ቅዴስናው የተሰጠው ሇግሇሰቦቹ ነው እንጂ ሇሥርወ መንግሥቱ
አይዯሇም። ይህ ዯግሞ የሚያሳየው ቤተ ክርስቲያን የዚግዌ ነገሥትን ሕጋዊነት ባትቀበሌም ነገሥቱ በግሊቸው
ሇፈጸሟቸው የቅዴስና ተግባራት ግን ዕውቅና የሰጠች መሆኑን ነው።
ሦስተኛ፡ የሥሌጣን ሽግግሩ በሚፈጸምበት ወቅት ስሊሌነበሩት – ገና ወዯፊት ስሇሚነግሡት ሰልሞናውያን
ነገሥት ቅዴስና በምን ታውቆ ነው ቤተ ክርስቲያን በዙያ ዗መን ከነሱ ይሌቅ የዚግዌ ነገሥትን የምትመርጠው?
አነዙህ ሦስት ነጥቦች ክርክሩ ምን ያህሌ አመክንዮ የራቀው መሆኑን ሇማሳየት በቂ ናቸው ብዬ አስባሇሁ፤ ስሇዙህ
ወዯላሊ ጉዲይ አሌፋሇሁ።
2. አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት እያሊቸው ሇምን ጥሬና ፍሬ እየበለ በዋሻ ይኖራለ?
ላሊው ጸሏፊው በተዯጋጋሚ ያነሳው መከራከሪያ ‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት (በይኩኖ አምሊክ)
ተሰጥቷቸው ከነበረ ሇምን በዋሻ ተወስነው፣ ጥሬ እና ፍሬ እየበለ፣ ውሃ ብቻ እየጠጡ ይኖራለ?‛ የሚሌ ነው።
‚አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ከይኩኖ አምሊክ ሲሦ መንግሥት ተቀብሇዋሌ ብሇው የሚተርኩ ሰዎች ሲሦ
መንግሥት ያሇው ሰው የደር ቅጠሌና ፍሬ፣ ከዙያም ሲያሌፍ ዏተርና ጥሩ ውሃ ሇሌጆቹ ሇምን ይሰጣሌ የሚሇውን
ቢመሌሱት በጣም ጥሩ ነበር።‛ (ገጽ 672)
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 37

የዙህ አነጋገር ችግሩ የደር ቅጠሌና ፍሬ መብሊትን የማጣት ውጤት አዴርጎ መመሌከቱ ነው። አቡነ ተክሇ
ሃይማኖትም ሆኑ ላልች ሰዎች የምንኩስናን የትሕርምት ሕይወት ሲመርጡ የዙህን ዓሇም ምቾት ሇመተው ወስነው
ነው እንጂ ስሊጡ አይዯሇም። አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በመጀመሪያ ሇስብከት ሲወጡ እኮ የነበራቸውን ንብረት ሇዴሆች
አከፋፍሇው ነው። ስሇዙህ ከዙያ በኋሊ የነበራቸው የንዳት (simplicity) ሕይወት ምርጫቸው ነበር ማሇት ነው።
በዯብረ አስቦ በነበሩባቸው የመጀመሪያ ዓመታትም እርሻ ሊሇማረስ የመረጡት እየቻለ መሆኑን በኋሊ የገዲሙ ነዋሪዎች
እየበዘ ሲሄደ እርሻ ሇመጀመር ያዯረጉት ውሳኔ ያሳየናሌ። ከዙያም ላሊ ብዘዎች መሳፍንት እና ነገሥት (ሇምሳላ
አዴያም ሰገዴ ኢያሱ፣ እና አቤሌ ተብል በመጽሏፉ (ገጽ 676-7) የተጠቀሰው መኮንን) ይህን ወዯ መሰሇው ኑሮ
የገቡት በምርጫ እንጂ በማጣት አይዯሇም። ቁም ነገሩ ምንዴነው፣ ጸሏፊው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት
እንዲሌተቀበለ ሇማሳየት ላልች ማሰረጃዎችን ሉያቀርብ ይችሊሌ። እርሳቸውም ሆኑ ሌጆቻቸው በደር ፍሬ እና በጥሩ
ውሃ መወሰናቸው ግን የምርጫ እንጂ የዴህነት ጉዲይ ስሊሌሆነ ሇዙህ ጉዲይ በመከራከሪያነት ሉቀርብ አይችሌም።
3. አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ከመንግሥት ምሇሳ ጋራ የሚያገናኘው ትረካ በኋሊ ዗መን የመጣ ነው።
ጸሏፊው ይህ አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ከይኩኖ አምሊክ ጋራ የሚያያይ዗ው ትረካ በኋሊ ዗መን የተጨመረ ነው
ብል ያምናሌ። ይህንም በመጽሏፉ ከገጽ 42-50 በሰፊው አስረዴቷሌ። ቀዯም ብዬ እንዯጠቀስሁት ይህ ነጥብ እውነት
አሇው። እርሱ እንዯሚሇው ከሆነ በ15ኛው መክ዗ የተጻፉት የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች እንዱሁም ላልች
መዚግብት ስሇዙህ ጉዲይ አይናገሩም። ይህ ታሪክ ዯግሞ ቢጻፍ ምንም አይጨምርም ተብል የሚተው አይነት
አይዯሇም።
በርግጥ ከዙህ በፊት አንዲየነው ሇምሳላ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የዯብረ ዲሞ ጉዝ እንዱሁ የ዗ሇለት ቅጅዎች
አለ። ይህ ብቻ ሳይሆን ጸሏፊው የተቀበሇው፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዏ ሇይኩኖ አምሊክ አዯረጉት የተባሇው እገዚም አንዱሁ
በ16ኛው መክ዗ የመጣ ነው። እንዱያውም የዯብረ ሉባኖሱ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ ገና በ16ኛው መክ዗ መጀመሪያ
(በ1507) አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ከይኩኖ አምሊክ ጋራ ስሇሚያገናኛቸው ከአቡነ ኢየሱስ ሞዏ ይሌቅ ስማቸው ቀዴሞ
ከይኩኖ አምሊክ ጋራ የተያያ዗ው አቡነ ተክሇ ሃይማኖት ናቸው ማሇት ይቻሊሌ።22 ስሇዙህ በኋሊ ዗መን መምጣቱ
ብቻውን ታሪኩን ወዯጎን ሇመተው በቂ ምክንያት አይሆንም።
ይሁን እንጂ ጸሏፊው ስሇትረካው አጀማመር በጻፈው ሏተታ ውስጥ የተሇያዩ መጣረሶች ይታያለ። ሇምሳላ ገጽ
43 ሊይ እንዱህ ይሊሌ።‛
‚እስከ 18ኛው መክ዗ የነበሩት የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅዎች አቡነ ተክሇ ሃይማኖት በሰልሞናዊው ሥርወ
መንግሥት ምሇሳ ሊይ ሚና ተጫውተዋሌ የሚሌ ሏተታ አሌነበራቸውም።‛
ይህን አባባሌ ከሚቀጥሇው ምንባብ ጋር እናስተያየው።
‚በዙህ (የዯብረ ሉባኖሱ የ1507) ቅጅ የ዗ር ሏረጎችን ከኢየሩሳላም በማንሣት ከይኩኖ አምሊክ ጋር የነበረውን
ግንኙነት በማከሌ፣ የኢትዮጵያን የመንግሥትና የክርስትና ታሪክ በማካተት፣ የተአምራቱን ብዚት አስከ 66 ዴረስ
በመጨመር ታሪኩ እጅግ ሰፍቷሌ።‛ (ገጽ 145)
አንግዱህ ሁሇተኛው ምንባብ የሚነግረን በ16ኛው መክ዗ የተጻፈው የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ በአቡነ ተክሇ
ሃይማኖት እና በይኩኖ አምሊክ መሃሌ ግንኙነት መኖሩን እንዯ዗ገበ ነው። ይህ ከሊይኛው ምንባብ ጋራ በቀጥታ
የሚጋጭ ነው። ይህ ቅጅ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ሚና ምን ብል እንዯሚገሌጠው ዯግሞ ላሊ ቦታ እንዱህ ሲሌ
ነግሮናሌ።
‚በ16ኛው መክ዗ የተጻፉት ገዴሊተ ተክሇ ሃይማኖት ይኩኖ አምሊክን በመመሇሱ ሂዯት የአቡነ ተክሇ
ሃይማኖትን ተሳትፎ ከጸልት ባሇፈ አይገሌጡትም።‛ (ገጽ 42)
አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የጸልት እገዚ አዴርገው ከሆነ፣ ሁሇቱ ሰዎች ተገናኝተዋሌ፣ ተዋውቀዋሌ ፤ እውቂያቸውን
ተከትልም አቡነ ተክሇ ሃይማኖትም በጉዲዩ ሇአንደ ወገን ዴጋፍ ሰጥተው ነበር ማሇት ነው። ስሇዙህ ትረካው በ18ኛው
መክ዗ የመጣ አይዯሇም።

22
ይህ ዴምዲሜ ጸሏፊው ‚በ15ኛው ምዕት ዓመት የተጻፈ የገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ቅጅ አሊገኘሁም‛ ማሇቱ ሊይ የተመሠረተ ነው።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 38

ላሊው የብዕሇ ነገሥት ጉዲይ ነው። ጸሏፊው ብዕሇ ነገሥትን አቡነ ተክሇ ሃይማኖትን ከይኩኖ አምሊክ መንገሥ
ጋር የሚያገናኘው ትረካ ዋና ምንጭ ነው ይሇዋሌ። የጽሕፈት ዗መኑንም በ1760 ያዯርገዋሌ። ሇዙህ ያቀረብወ ምክንያት
ዯግሞ ቀጥል ያሇው ነው።
‚<<ብዕሇ ነገሥት>> የተጻፈው በ1760 ዓ.ም. ነው። በራሱ በመጽሏፉ ሊይ እንዱህ ይሊሌ ፤ (የግዕዘ ጽሕፈት)
. . . ‘ይህን ቅብዏት ከእርሱ በኋሊ የሚነግሡ ሁለም ነገሥታት የሚቀቡት አይዯሇም። ከ዗ርዓ ያዕቆብ በቀር። ከብዘ
዗መንም በኋሊ በ7260 ዓመት (የሚነግሠው ይቀባዋሌ)። ይህን ቅብዓት ተቀብተው የሚነግሡ የእነዙህ የሁሇቱ
ነገሥታት ዗መናቸው 42 ዓመታት ነው።’
‚ይሄ ንባብ መጽሏፉ የተጻፈበትን ዗መን አስመሌክቶ መረጃ ይሰጠናሌ። የተጻፈው በአቡነ ተክሇ ሃይማኖት
዗መን ሳይሆን ከ዗ርዓ ያዕቆብ ዗መን በኋሊ ነው። ከ዗ርዓ ያዕቆብ ዗መን በኋሊ ስሇሚነግሡት ነገሥታት ይናገራሌና።
ከ዗ርዓ ያዕቆብም ዗መን ዗ግይቶ መጻፉን ያሳያሌ። እንዯ ዯብረ ሉባኖሱ ገዴሌ የ2004 ዓ.ም. እትም ከሄዴንም
዗መኑ 1762 ዓ.ም. ይሆናሌ። ኢዮአስ (1747-1761) ወይም 1762 የሚሇውን ከያዜን በዲግማዊ ተክሇ ሃይማኖት
዗መን (1762-1769 ዓ.ም.) ይሆናሌ። ይኼም በዏፄ ዮሏንስ አንዯኛ ዗መን ሊይ ነው። ይህ ወቅት በኢትዮጵያ ታሪክ
ወሳኝ ጊዛ ነበር። የ዗መነ መሳፍንት ጀማሪ ራስ ሚካኤሌ ስሐሌ ወዯ ጎንዯር መጣሁ መጣሁ የሚለበትና
የነገሥታቱ ስሌጣን አዯጋ ሊይ የወዯቀበት ጊዛ ነው። << ሰልሞናዊው ሥርወ መንግሥት አዯጋ ሊይ ነው>> ተብል
ተገምቷሌ ማሇት ነው። በመሆኑም ይህን ቃሌ ኪዲን በመጻፍ አሌጋውን የሚያሠጉትን ሇማስታገሥ፣ እግረ
መንገደንም የተረሳውን የዯብረ ሉባኖስ ገዲም ሇማስታወስ ሲባሌ መጽሏፉ የተ዗ጋጀ ይመስሊሌ።‛23 (ገጽ 45)
የምንባቡ መጀመሪያ ሊይ ከብዕሇ ነገሥት የተጠቀሰው ምንባብ ሇእኔ የሚነግረኝ ጸሏፊው እርሱን መሠረት አዴርጎ
ከዯረሠበት ዴምዲሜ ጨርሶ የተሇየ ነው።
1. ‚ይህን ቅብዓት ከእርሱ በኋሊ የሚነግሱ ሁለም ነገሥታት የሚቀቡት አይዯሇም።‛ የተባሇሇት ንጉሥ ማን እንዯሆነ
አሌተገሇጠም። ግን ከ዗ርዓ ያዕቆብ በፊት የነበረ ንጉሥ ነው። ምክንያቱም ከ’እርሱ’ በኋሊ ያን ቅብዓት ከሚቀቡት
ሁሇት ነገሥት አንደ ዗ርዓ ያዕቆብ ነውና።
2. ‚ይህን ቅብዓት ተቀብተው የሚነግሡ የእነዙህ የሁሇቱ ነገሥታት ዗መናቸው 42 ዓመታት ነው።‛ የሚሇው ዓረፍተ
ነገር የሚያሳየን መጽሏፉ ስሇ ዗ርዓ ያዕቆብም ትንቢት እየተናገረ መሆኑን ነው። ምክንያቱም ዗ርዓ ያዕቆብ የነገሠው
ሇ34 ዓመታት ነው። መጽሏፉ ከ዗ርዓ ያዕቆብ ዗መን በኋሊ ቢጻፍ ኖሮ ይህን ቁጥር አይሳሳትም ነበር።
3. በላሊ በኩሌ ‚ይቀባለ‛ ከተባለት ሁሇት ነገሥት አንደ በስሙ ሲጠራ የላሊው ግን አሌተጠራም። ዗ርዓ ያዕቆብ
ዯግሞ ስሙ እንዲሌተጠቀሰው ንጉሥ በዙህ ዗መን ይነግሳሌ ተብል ትንቢት አሌተነገረሇትም። ስሇዙህ መጽሏፉን
ያ዗ጋጁት ሠዎች ዗ርዓ ያዕቆብን ያውቁታሌ ማሇት ነው። በዙህ መሠረት የምንዯርስበት ዴምዲሜ መጽሏፉ በ዗ርዓ
ያዕቆብ ዗መን የተጻፈ ነው የሚሌ ነው። እኔ በግላ (መጽሏፉ ሊይ ባለት መረጃዎች መሠረት) የምቀበሇው ይህን
ዴምዲሜ ነው።
ነገር ግን የ዗ርዓ ያዕቆብ ዗መን 42 ዓመት ተብል የተገሇጠው በስህተት ነው አንጂ ከሱ ዗መን በኋሊ የተጻፈ ነው
ቢባሌ እንኳን የጽሕፈቱ ዗መን በ1760 ሉሆን አይችሌም። መጽሏፉ እንዳት ስሇ 1760 እየተነበየ በ1760 ሉጻፍ
ይችሊሌ? በዙህም ምክንያት ጸሏፊው ሇብዕሇ ነገሥት መጻፍ እንዯ ምክንያት የጠቀሳቸው የራስ ሚካኤሌ ስሐሌ
‚መጣሁ መጣሁ ማሇት‛ እና የዯብረ ሉባኖስ መረሳት ተቀባይነት ሉኖራቸው አይችሌም።
በዙሁ ርዕስ ስር ቢነሳ ጥሩ ይሆናሌ ብዬ የማስበው የአቡነ ተክሇ ሃይማኖት የ዗ር ሏረግ ከእሥራኤሌ የመመ዗ዘ
ነገር ነው። ጸሏፊው ገጽ 328 ሊይ ስሇ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት የ዗ር ሏረግ ሲተርክ ግን የዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ የአቡነ
ተክሇ ሃይማኖትን የ዗ር ሏረግ የእሥራኤሌ ሉቀ ካህናት ከነበረው ከአብያታር እንዯሚመዜ዗ውና ይህን ዜርዜር
በቀዯሙት የገዴለ ቅጅዎች ሊይ የማናገኘው መሆኑን ይገሌጣሌ። ታዱያ የዙህን ‚አዱስ‛ የ዗ር ሏረግ ዜርዜር አመጣጥ
ሲተነትን (ገጽ 328) እንዱህ ይሊሌ።
‚የመጀመሪያው በሏይቅ አስጢፋኖስ ተይዝ የነበረው ከጳጳሱ በታች ቤተ ክህነቱን የማስተዲዯር ሥሌጣን ወዯ
ዯብረ ሉባኖሱ እጨጌ እየዝረ ሲመጣ ሇዙህ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ምክንያቶች ሇመስጠት ሲባሌ ነው። . . .
ሁሇተኛው ምክንያት ዯግሞ ዯብረ ሉባኖስ የሏይቅን ሥሌጣን ሲወስዴ የገዴሌ አጻጻፍ ስሌቱንም ከቀዯምቱ

23
ምንባቡ ዏፄ ዮሏንስ አንዯኛ ያሇው በስህተት ነው። በ዗መኑ የነበሩት ዲግማዊ ዮሏንስ ናቸው።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 39

መንገዴ ቀይሮ የገዴሇ ኢየሱስ ሞዏን መሌክ አንዱይዜ አዴርጎታሌ። በ15/16ኛው መክ዗ የተጻፈው ገዴሇ ኢየሱስ
ሞዏ ገዴሌን ከዛና መዋዕሌ ጋር አዚምድ የቤተ ክህነቱንም የቤተ መንግሥቱንም ታሪክ ጽፏሌ። ሁሇተኛው የዯብረ
ሉባኖስ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅም ሲጻፍ ይህን ቅርጽ በመከተሌ ቤተ መንግሥታዊውን ታሪክ ከቤተ
ክህነታዊው አዚምድ አቅርቦታሌ።‛
በመጀመሪያ የአቡነ ተክሇ ሃይማኖትን የ዗ር ሏረግ ከእሥራኤሊውያን ጋራ ማገናኘት (እንዯ ዯብረ ሉባኖሱ ቅጅ
ከአብያታር የሚነሳ ዜርዜር ባይኖራቸውም) በቀዯምት የገዴለ ቅጅዎችም የነበረ ነገር ነው። የእዮከ ቅጅ ‚(የአቡነ ተክሇ
ሃይማኖት አባት ቀዯምቶች) ጥንተ ሀገራቸው ግብጽ እንዯነበር አና ከእሥራኤሌ ጋር ወዯ ኢትዮጵያ እንዯወጡ‛
ይናገራሌ (ገጽ 328)። ስሇ ዲጋ እስጢፋኖሱ ቅጅም ‚዗መድቹ የመጡት ከእሥራኤሌ መሆኑን ይጠቁማሌ። በኋሊ
ተ዗ርዜሮ የተጻፈው ይህ ነው።‛ ተብሎሌ (ገጽ 83)። ይህን የምጠቅሰው ነገሩ በ16ኛው መክ዗ ዴንገት የመጣ አሇመሆኑ
ሌብ እንዱባሌ ነው።
በኋሊ ተ዗ርዜሮ የተጻፈውን የ዗ር ሏረግ አመጣጥ በተመሇከተ ጸሏፊው ያቀረባቸውን ሁሇት ምክንያቶች
እንመርምር። ሁሇተኛው ምክንያት ብዘ ምርምር አይጠይቅም፣ ስህተት ነው። ምክንያቱም ቀዯም ብሇን እንዲየነው
ጸሏፊው ከ16ኛው መክ዗ በፊት የተጻፈ የገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ቅጅ አሇማግኘቱን ነግሮናሌ። ስሇዙህ በዙህ መሠረት
በ16ኛው መክ዗ መጀመሪያ የተጻፈው የዯብረ ሉባኖሱ የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ቅጅ ከገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ቅርጽም ሆነ
ላሊ ነገር ሉኮርጅ አይችሌም፣ ምናሌባት ገዴሇ ኢየሱስ ሞዏ ከእሱ ኮርጆ እንዯሆነ እንጂ።
የመጀመሪያው ምክንያት ግን ትንሽ ምርምር ይፈሌጋሌ። ምክንያቱን ሇመቀበሌ ወይም ውዴቅ ሇማዴረግ በአቃቤ
ሰዓትና በእጨጌ መሃሌ ያሇውን ሌዩነት እንዱሁም ሁሇቱን መዓርጋት የተሸከሙት ሰዎች በ15ኛው መክ዗ መጨረሻ እና
በ16ኛው መክ዗ መጀመሪያ በቤተ መንግሥቱ የነበራቸው ሚና ምን እንዯነበር ማወቅ ያስፈሌጋሌ። ጸሏፊው ከሊይ
ከተጠቀሰው በተጨማሪ ገጽ 841 ሊይም በዙህ ጉዲይ ምንጭ ሳይጠቅስ እንዱህ ብሎሌ።
‚ዏፄ ይስሏቅ ወዯ ዯብረ ሉባኖስ ከመጣ በኋሊ የተጀመረው ግንኙነት ዲብሮ በዏፄ ዗ርዓ ያዕቆብ፣ ይበሌጥ
ዯግሞ በዏፄ በዕዯ ማርያም ጊዛ ዯብረ ሉባኖስ የዏቃቤ ሰዓቱን ቦታ ተረከበ።‛
የዯብረ ሉባኖስ አበምኔቶች ከግራኝ አሕመዴ ወረራ በፊት ከቤተ መንግሥት ጋራ የነበራቸውን ቀረቤታ
በተመሇከተ ጸሏፊው የዯብረ ሉባኖስ አበምኔቶችን የተመሇከቱ መረጃዎችን በመጽሏፉ ውስጥ ስሊካተተ ያን ማየት
ይቻሊሌ። የዯብረ ሏይቅ ዏቃብያነ ሰዓት በተመሳሳይ ወቅት በቤተ መንግሥት የነበራቸውን ቦታ በተመሇከተ ግን
ጸሏፊው በዜርዜር የሚነግረን ነገር ስሇላሇ ይህን ሇማጣራት ስሇ ዗መኑ ከተጻፉ መጻሕፍት ሰፊ ተቀባይነት አሇው
ወዯሚባሇውና ጸሏፊውም በተዯጋጋሚ ወዯሚጠቅሰው የፕሮፌሰር ታዯሰ ታምራት ‚Church and State in
Ethiopia‛ ሄዯን እንመሇከታሇን።
የዯብረ ሉባኖስን እጨጌዎች በተመሇከተ ጸሏፊው ስሇ዗መኑ እጨጌዎች ባስቀመጠሌን ሏተታ ውስጥ ማየት
የምንችሇው ዯብረ ሉባኖሳውያን ከቤተ መንግሥት ጋራ የወዲጅነት ግንኙነት የጀመሩት በዏፄ ይስሏቅ ዗መን አቡነ
ዮሃንስ ከማ የገዲሙ አበምኔት ሳለ መሆኑን ነው። ይህ ግንኙነት አጅግ የጠበቀው ዯግሞ በዓፄ ዗ርዓ ያዕቆብ እና
በእጨጌ መርሏ ክርስቶስ ዗መን ነው። ከሁሇቱ አበምኔቶች በፊት ግን በተሇይ ሦስተኛው የገዲሙ አበምኔት አቡነ
ፊሌጶስ ከ዗መኑ ንጉሥ ከዏምዯ ጽዮን ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ተግ዗ው እና ላሊም ብዘ መከራ ተቀብሇው ነበር።
አምስተኛው አበምኔት አቡነ ቴዎዴሮስ ዯግሞ የወቅቱ ንጉሥ ዏፄ ዲዊት እና እኅቱ ዴሌ ሴፋ ሇገዲሙ ንዋያትን
ሇመስጠት በፈሇጉ ጊዛ ከሌክሇዋቸው እንዯነበር ይገሌጣሌ። በአቡነ ዮሏንስ ከማ እና በአቡነ መርሏ ክርስቶስ መካከሌ
የገዲሙ አበምኔት የነበሩት አቡነ እንዴርያስም ከዏፄ ዗ርዓ ያዕቆብ ጋራ በፈጠሩት ግጭት የተነሳ ሇግዝት ተዲርገው
ነበር። የግጭቱን መንስዔ በተመሇከተ ግን የተሇያዩ ግምቶች ተሰንዜረዋሌ።
በአቡነ መርሏ ክርስቶስ ዗መን ገዲሙ ከቤተ መንግሥቱ ጋራ በጣም ተቀራርቦ የነበረ መሆኑ ግሌጽ ነው። ነገር ግን
አሇፍ ብሇን አንዯምንመሇከተው በእርሱ የኋሊ ዗መን እና ከእርሱ ቀጥል በነበረው በእጨጌ ጴጥሮስ ዗መን የቤተ
መንግሥቱን ሁኔታ የቀየሩ ክስተቶች ተፈጥረዋሌ። በእነዙህ ክስተቶች ምክንያትም ገዲሙ ከቤተ መንግሥቱ ጋር
የነበረው ግንኙነት እንዯነበረ አሌቀጠሇም።
ዏቃብያነ ሰዓቱን በተመሇከተ፣ ፕሮፌሰር ታዯሰ በመካከሇኛው ዗መን ስሇነበረው ተንቀሳቃሽ ቤተ መንግሥት
ባዯረጉት ገሇጻ ሊይ አቃቤ ሰዓቱን ‚የቤተ መንግሥቱ እጅግ ታሊቁ የቤተ ክርስቲያን ሹም‛ ነው ሲለ ይገሌጡታሌ።
ይህን በማስከተሌ በሰጡት የግርጌ ማብራሪያም የሚከተሇውን ብሇዋሌ።
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 40

‚ በ15ኛው መክ዗ ተጽፈዋሌ ተብሇው እንዯሚገመቱ ገዴሊት ትረካ ከሆነ ይህ መዓርግ (ዏቃቤ ሰዓትነት) አቡነ
ኢየሱስ ሞዏ በ1263 አካባቢ በሥርወ መንግሥታት መሃሌ በነበረው ሽኩቻ ሊዯረጉሇት ዴጋፍ ራሱ በራሱ በይኩኖ
አምሊክ ሇአቡነ ኢየሱስ ሞዏ እና ሇተተኪዎቹ የተሰጠ ነው። ነገር ግን የመዓርጉ ፖሇቲካዊ ተጽዕኖ የጎሊው የዏፄ
ዲዊት የሌብ ጓዯኛ በነበረው በዏቃቤ ሰዓት ሰረቀ ብርሃን ዗መን ነው። ዗ርዓ ያዕቆብ ዯግሞ ዏቃቤ ሰዓት አምኀ
ኢየሱስን እጅግ የታመነ አማካሪው በማዴረግ የቦታውን (የመዓርጉን) ክብር እና ተጽዕኖ ይበሌጥ ከፍ አዯረገው።
አሌቫሬዜ ኢትዮጵያን በጎበኘበት ወቅት (በዏፄ ሌብነ ዴንግሌ ዗መን) ዏቃቤ ሰዓቱ ትሌቅ ተጽዕኖ ነበረው፤
አሌቫሬዜም ‚የሀገሩ ሁሇተኛ ሰው‛ ሲሌ ጠርቶታሌ። የግራኝ ዛና መዋዕሌ ጸሏፊም በጎጃም የተገዯሇውን ይህኑ ሰው
‚የክርስቲያኖቹ ቃዱ . . . ሁሇተኛ ጳጳሳቸው ነው። . . . የሀገሩ አንዴ አራተኛ የእርሱ ነው።‛ በማሇት ነው
የገሇጠው። ዏቃቤ ሰዓቱ የንጉሡን ሞት ተከትል በሚፈጠረው የውርስ ሽኩቻ ውስጥም ጉሌሕ ሚና ይጫወት
ነበር። በአሌቫሬዜ ጉብኝት ወቅት ዏቃቤ ሰዓቱ (በንጉሡ ተንቀሳቃሽ ቤተ መንግሥት ውስጥ) ከንጉሡ እሌፍኝ ጎን
ብዘ ዴንኳኖች ነበሩት።‛24 (ትርጉም የኔ)
ላልችም ይህን የሚዯግፉ ምንባቦች መጽሏፉ ውስጥ አለ።
‚የታሊሊቆቹ ገዲማት አበምኔቶች አ዗ውትረው በንጉሡ እሌፍኝ ይገኙ ነበር። የሏይቁ ዏቃቤ ሰዓት ዯግሞ
በተሇይ በቤተ መንግሥቱ ከንጉሡ ጋራ እንዱቀመጥ ይጠበቅበት ነበር። የዯብረ ቢ዗ኑ አባ ጴጥሮስ ከንጉሡ ጋር
ሇሁሇት ዓመታት መቀመጡ ተገሌጧሌ። የዯብረ ሉባኖሱ መርሏ ክርስቶስም ዗ርዓ ያዕቆብን በተዯጋጋሚ ይጎበኘው
የነበረ ሲሆን በበዕዯ ማርያም ዗መን ዯግሞ በ዗መቻዎቹ ወቅት ጭምር ከንጉሡ ጋራ አብሮት ተጉዞሌ።‛25 (ትርጉም
የኔ)
‚ከበዕዯ ማርያም ዕረፍት በኋሊ ወጣቱ እስክንዴር ሲነግሥ እንዯ ሞግዙት ሆነው በንጉሡ ስም ሀገሩን
ያስተዲዴሩ የነበሩት ንግሥት ሮምና፣ ዏቃቤ ሰዓት ተስፋ ጊዮርጊስ እና ቢትወዴዴ ዏምዯ ሚካኤሌ ነበሩ። . . .
ከእነዙህ መካከሌ በጣም ጠንካራ የነበረውና በአስተዲዯርም የሊቀ ሌምዴ የነበረው ቢትወዴዴ ዏምዯ ሚካኤሌ
ነበር። ሮምና እና ተስፋ ጊዮርጊስ በምክር ቤቱ ውስጥ እንዱገቡ የተዯረገው በያዞቸው የእናት ንግሥትነት እና
የዏቃቤ ሰዓትነት ቦታዎች ከፍታ የተነሳ ሳይሆን አይቀርም።‛26 (ትርጉም የኔ)
ከዙህም በተጨማሪ፣ ፕሮፈሰር ታዯሰ በመጽሏፋቸው እንዲብራሩት ከሆነ ቢትወዴዴ ዏምዯ ሚካኤሌ እና ከእርሱ
ሞት በኋሊ በፖሇቲካው መዴረክ ተመሌሳ የገነነችው ንግሥት ዕላኒ ጠበኞች ነበሩ። ሇዙህም ነው ዏምዯ ሚካኤሌ
አብዚኛውን የመንግሥት ሥሌጣን ጨብጦ በነበረበት በዏፄ እስክንዴር ዗መን ዕላኒ ከፖሇቲካው እንዴትገሇሌ የሆነው።
ዏምዯ ሚካኤሌ በንጉሡ ትዕዚዜ እንዱገዯሌ ሲዯረግም ጉዲዩ የዕላኒ (እና የዏቃቤ ሰዓት ተስፋ ጊዮርጊስም) እጅ
ነበረበት። ዏምዯ ሚካኤሌ ዯግሞ የዯብረ ሉባኖሳውያን ወዲጅ እና የገዲሙም ጠባቂ ነበር። እጨጌ መርሏ ክርስቶስንም
እንዯ መንፈስ አባቱ ነበር የሚያየው። ይህ በመሆኑም፣ ዏምዯ ሚካኤሌ በተገዯሇ ጊዛ የተቀበረው በዯብረ ሉባኖስ ነበር፤
ዯብረ ሉባኖሳውያንም ግዴያውን ተቃውመውታሌ። በዙህ የተነሳ በንግሥት ዕላኒ እና በዯብረ ሉባኖሳውያን መሃሌ
የነበረው ግንኙነት መሌካም የሚባሌ አሌነበረም። የዯብረ ሉባኖስ መዚግብትም በዙህ የተነሳ ይመስሊሌ የንግሥቲቱን
ስም ጨርሶ አያነሱትም።27
የዓፄ ናዖዴን ሞት ተከትል ሌብነ ዴንግሌ በ11 ዓመቱ ሲነግሥ በበሊይነት ሀገሪቱን የምታስተዲዴረው ንግሥት
ዕላኒ ሆነች። እንግዱህ በዙህ ዗መን ነው የገዴሇ ተክሇ ሃይማኖት ሁሇተኛው የዯብረ ሉባኖስ ቅጅ በእጨጌ ጴጥሮስ
አማካይነት የተጻፈው። ታዱያ አንዳት ሆኖ ነው በዙያ ዗መን ዯብረ ሉባኖስ ዯብረ ሏይቅ ይዝት የነበረውን የበሊይነት
እየወሰዯ ነበር ማሇት የሚቻሇው።
በርግጥ አቡነ ተክሇ ሃይማኖት እና ዯብረ ሉባኖስ በ዗መኑ ገናና ስም ነበራቸው። አፄ ሌብነ ዴንግሌም ቢሆን
በእጨጌ ጴጥሮስ ዗መን አዱስ ቤተ ክርስቲያን ሲሰራ ሇገዲሙ ዴጋፍ አዴርጓሌ። ሕንፃው ሲመረቅም በቦታው ተገኝቶ
የሥርዓቱ ተካፋይ ሆኗሌ። ይህ ግን የዯብረ ሉባኖሱ እጨጌ በቤተ መንግሥት ከሏይቁ ዏቃቤ ሰዓት የበሇጠ ቦታ ነበረው
ወይም ዏቃቤ ሰዓትነቱን ተረክቧሌ ሇማሇት የሚያስችሌ መረጃ አይዯሇም።

24
Taddesse Tamrat (1968), Church and State in Ethiopia, p. 520
25
Ibid, p. 565
26
Ibid, p. 562
27
Ibid, pp. 564-5
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 41

ከዙህም ላሊ ከሊይ የፕሮፌሰር ታዯሰን መጽሏፍ ጠቅሰን እንዲየነው፣ በዏፄ በዕዯ ማርያም ዗መን ዏቃቤ ሰዓትነቱ
በሏይቅ አበምኔቶች እጅ ሆኖ ነው የቀጠሇው። በዏፄ እስክንዴር ዗መንም እንዱሁ። ፕሮፌሰር ታዯሰ ዏቃቤ ሰዓት ሆኖ
ከዏፄ እስክንዴር ሞግዙቶች አንደ የነበረው ተስፋ ጊዮርጊስ በኋሊ ጊዛ ‘መክብበ ቤተ ክርስቲያን' የሚሌ መዓርግ
እንዯያ዗ እና ተክሇ ኢየሱስ ሞዏ የሚባሌ የዯብረ ሏይቅ ሰው ዏቃቤ ሰዓትነቱን እንዯወሰዯ ጽፈዋሌ።28 ዏፄ እስክንዴር
ባዯረገው የርስት ስጦታ ሊይ ከተ዗ረ዗ሩት ሰዎች መካከሌ ተስፋ ጊዮርጊስና ተክሇ ኢየሱስ ሞዏን የሚቀዴሟቸው
ንግሥት ዕላኒ እና የንጉሡ ሚስቶች ብቻ ናቸው። በዏፄ ሌብነ ዴንግሌ ዗መንም የነበረው ዏቃቤ ሰዓት ነገዯ ኢየሱስ
የሚባሌ ነበር። ይህ ከሊይ በቀረበው ምንባብ አሌቫሬዜ ‚የሀገሩ ሁሇተኛ ሰው‛ ሲሌ ገሌጦታሌ የተባሇው ነው።
የሞተውም በግራኝ ወረራ ጊዛ በጦርነት ሊይ ነው። በተቃራኒው የዯብረ ሉባኖስ የወቅቱ እጨጌ አቡነ እንባቆም ከግራኝ
ወረራ ጥቂት ጊዛ በፊት በንጉሡ ትዕዚዜ በግዝት ሊይ ነበሩ። በግራኝ ወረራ ወቅትም ከንጉሡ ጋር አሌነበሩም። ይህ ሁለ
ዓቃቤ ሰዓትነት እስከ ግራኝ አሕመዴ ወረራ ጊዛ በፍጹም ከሏይቅ አበምኔቶች እጅ እንዲሌወጣ የሚያሳይ ሆኖ ሳሇ
ጸሏፊው ከምን ተነስቶ ይሆን ‚በዏፄ በዕዯ ማርያም ጊዛ ዯብረ ሉባኖስ የዏቃቤ ሰዓቱን ቦታ ተረከበ።‛ ሉሌ የቻሇው?
(ምናሌባትም እዙህ ጋ ሳሌጠቅስ ማሇፍ የላሇብኝ ዏቃቤ ሰዓት ሠረቀ ብርሃን ያገባ መሆኑ በገዴሇ ፊሌጶስ፣
እንዱሁም ዏቃቤ ሰዓት ነገዯ ኢየሱስም ሲሞት ከወንዴ ሌጁ ጋር የነበረ መሆኑ በአሌቫሬዜ መጽሏፍ ውስጥ የተጻፈ
መሆኑን ነው።29)
ከእነዙህ ሁለ ነገሮች በመነሳት አቡነ ተክሇ ሃይማኖት እና ይኩኖ አምሊክ ተገናኝተዋሌ የሚሇውን ሏሳብ ሇመሞገት
በጸሏፊው የቀረቡት ክርክሮች መታረም እና መሻሻሌ የሚገባቸው ይመስሇኛሌ።

28
Ibid, pp. 565-6
29
Ibid, p. 420
ያሌተጠናቀቀው ረዥም ጉዝ 42

7. መጠቅሇያ
ባሇፉት ገጾች ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ን አስመሌክቶ ያለኝን ትችቶች አቅርቤያሇሁ። ነገር ግን ሁለንም አሊቀረብሁም።
ምክንያቱም አለ ያሌኋቸውን ችግሮች ሇማሳየት እስካሁን የቀረበው በቂ ነው ብዬ ስሇማስብ ነው። ቀዴሞም የዙህ ጽሐፍ
አሊማ መጽሏፉ ውስጥ ያለትን ችግሮች በመጠቆም መጽሏፉ ውስጥ በዴጋሚ መታየት ያሇባቸው ነገሮች እንዲለ ማሳሰብ
ነው እንጂ ያየኋቸውን ችግሮች ሁለ መ዗ር዗ር አይዯሇም። ከዙህም ላሊ ችግሮቹ አንዴ፣ ሁሇት ተብሇው ተ዗ርዜረው
የሚታረሙ ብቻ ናቸው ብዬ አሊስብም። ይሌቁንም ጸሏፊው መጀመሪያ ይዝ የተነሳው አሊማ እና መጽሏፉን በመጻፍ ሂዯት
ውስጥ የተከተሊቸው ስሌቶች ጭምር በዴጋሚ መፈተሽ አሇባቸው ባይ ነኝ።
አንዴ የታሪክ ተመራማሪ፣ ከዙያም አሌፎ የትኛውም የትምህርት ዗ርፍ የተሰማራ አጥኚ፣ ስሇአንዴ ጉዲይ ሉመራመር
ሲነሳ ያሌጠበቀውን ነገር ሇማግኘት መ዗ጋጀት አሇበት። መረጃዎች ከጠበቀው በተቃራኒ አቅጣጫ ሲወስደትም ተከትል
መሄዴ አሇበት። የምርምር ትክክሇኛው አካሄዴ ያ ነው። በርግጥ ተመራማሪ ሰው ነውና ወዯ የትኛውም ምርምር ሲገባ አንዴ
አይነት ጥበቃ (Expectation) በውስጡ ሊይኖር አይችሌም። ነገር ግን አዲዱስ መረጃዎችን ባገኘ ቁጥር ጥበቃውን በዙያ ሊይ
ተመስርቶ ሇመሇወጥ ዜግጁ መሆን አሇበት እንጂ የሱን የቀዯመ ግምት ስሊሊረጋገጠሇት ተጨባጭ የሆነውን መረጃ ወዯጎን
ሉተወው አይገባም። እርስ በራሳቸው የሚጣረሱ መረጃዎች ሲያገኝም ተጣርሶውን በግሌጽ መጋፈጥ እና ከተቻሇ መፍታት፣
ካሌተቻሇ ግን ወዯፊት ላልች መረጃዎች እና አዱስ መነጽር ይ዗ው የሚመጡ ተመራማሪዎች እንዱፈቱት መተው ነው እንጂ
አንዴ አይነት ዴምዲሜ ሊይ ሇመዴረስ ሲሌ በአንዴ ወገን ያለትን መረጃዎች ከስላቱ ማስወጣት የሇበትም።
በተሇይ ዯግሞ በታሪክ ምርምር ውስጥ እንዱህ አይነቱ አጣብቂኝ ይጎሊሌ። የታሪክ ምርምር በመሠረቱ ዚሬ ሊይ ካለን
መረጃዎች ተነስተን ያሇፈውን ዗መን የምንገምትበት ዗ርፍ ነው። ማዴረግ የሚቻሇው ባለት መረጃዎች ሊይ ተመስርቶ የተሻሇ
ግምት መገመት ነው እንጂ ስሇሁለም ነገር በተሟሊ እርግጠኝነት መናገር አይቻሌም። በተሇይ ዯግሞ የሚመረመረው ዗መን
ወዯኋሊ እየራቀ ሲመጣ ያለን መረጃዎች እየቀነሱ ስሇሚሄደ ስሇጊዛው ያሇን ምስሌ በዙያው መጠን አየዯበ዗዗ ፣
እርግጠኝነታችንም እየቀነሰ ነው የሚሄዯው። ሇዙህ ነው በታሪክ ሥራዎች ውስጥ ‘ይመስሊሌ’ ፣ ‘ሳይሆን አይቀርም’ ፣ ‘ሆኖ
ሉሆን ይችሊሌ’ ወ዗ተ የሚለ ቃሊትን በብዚት የምናገኘው። ሇዙህም ነው አዲዱስ መረጃዎች ሲገኙ ሲተረክ ከኖረው የተሇየ
ምስሌ የሚያስገኙት።
አንዲንዳ በዴሮ ዗መን የነበሩ ሰዎችን የማግኘት አጋጣሚ ኖሮን በእኛ ዗መን እነሱ ስሇኖሩበት ጊዛ የሚነገረውን ታሪክ
ብንነግራቸው ከትረካዎቻችን አንዲንድቹን ሲሰሙ ሉስቁብን እንዯሚችለ አስባሇሁ፣ ነገር ግን ያም ቢሆን ተገቢውን የታሪክ
አጻጻፍ ተከትሇን ታሪክን ስንጽፈው መሌኩን ብናሳስት እንኳን ዏጽሙን በትክክሌ መሳሌ የምንችሌ ይመስሇኛሌ። የተቀረው
ዯግሞ መረጃው በተገኘ ቁጥር እየተሟሊ ሄድ ሇትክክሇኛው ታሪክ በጣም የተጠጋ ሥዕሌ ይኖረናሌ ብዬ አምናሇሁ።
ጸሏፊው ሇዙህ መጽሏፍ የሰበሰባቸውን መረጃዎች ያቀናጀበት፣ ያመሳከረበት መንገዴ በዴጋሚ መፈተሽ አሇበት ብዬ
አምናሇሁ። አንዲንዴ የታሪክ ሁነቶችን እና በላልች ሰዎች የተነሱ ሏሳቦችን የተመሇከተበት መንገዴ ገሇሌተኝነት የጎዯሇው
ነው ብዬ አስባሇሁ። ጸሏፊው መጻፍ ከመጀመሩ በፊት የሚጽፈው ታሪክ ምን እንዯሆነና በምርምሩ መጨረሻ የትኞቹ
ዴምዲሜዎች ሊይ መዴረስ እንዲሇበት በአዕምሮው ወስኖ የነበር ይመስሇኛሌ። ነገር ግን እንዱህ አይነት ውሳኔ ሊይ በቅዴሚያ
ከተዯረሰ፣ ከዙያ በኋሊ ምን ዓይነት ምርምር ሉኖር ይችሊሌ? ስሇዙህ ጸሏፊው ምናሌባት መነሻውን እና አካሄደን በዴጋሚ
ቢፈትሽ እና የበሇጠ flexible የምርመራ መንገዴ ቢጠቀም የመጽሏፉ ይዝታ የበሇጠ እንዯሚሻሻሌ እና ሇታሪክ የሚኖረው
አስተዋጽዖም በጣም ከፍ ያሇ እንዯሚሆን አምናሇሁ።
ላሊው በጣም ወሳኝ ጉዲይ የሚመስሇኝ አርትዖት ነው። መጽሏፉ ሊይ በአርታኢነት የተጠቀሰ ሰው የሇም። ነገር ግን
እንዯዙህ በብዘ መረጃዎች የታጨቀ እና ረዥም ጊዛ የፈጀ ትሌቅ መጽሏፍ ከዯራሲው ቁጥጥር ውጪ የመውጣት ዕዴለ ሰፊ
ነው። በመጽሏፉ ውስጥ የምናገኛቸው የሏቅ መጣረሶች እና የስም ፣ የ዗መን ወ዗ተርፈ ስህተቶች ሇዙህ ምስክር
ይመስለኛሌ። መረጃውን ሰብስቦ በአግባቡ አዋቅሮ እና አገናዜቦ፣ የገዴለን ቅጅዎች ተርጉሞ፣ ከላልች የታሪክ ሥራዎች ጋራ
አመሳክሮ ይህን መጽሏፍ ማ዗ጋጀት በጣም ከባዴ ነው። በዙህ ሂዯት ውስጥ ስህተቶች መሠራታቸው የግዴ ነው። የራስን
ስህተቶች ከራስ ሥራ ሊይ መንቀስና ማስተካከሌ ዯግሞ የሚቻሌ አይዯሇም፤ አሇባበስን ያሇመስታወት ወይም ያሇላሊ ሰው
ተመሌካችነት ሇማስተካከሌ እንዯመሞከር ያሇ ነገር ነው፣ አይቻሌም። እናም ይህ መጽሏፍ ከመታተሙ በፊት እንዯ
መስታወት ሆኖ ዯራሲው በራሱ ሉያያቸው የማይችሊቸውን ነገሮች ሉያይሇት እና ሉያሳየው በሚችሌ ሰው ሉታይ ይገባ
የነበረ ይመስሇኛሌ። ይህ ዯግሞ አንብቦ አስተያየት ከመስጠት ያሇፈ፣ የመጽሏፉ ዜግጅት አካሌ መሆን የነበረበት ሥራ ነው
ብዬ አስባሇሁ።

You might also like