Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 5

መሬት ቢሮ ባዘጋጀው ‘’ለኢንቨስትመንት የሚውል የገጠር መሬት አሰጣጥ እና አጠቃቀምን ለመወሰን እና የባለሃቶችን

የልማት አፈፃፀም ለመገምገም ተሸሽሎ በወጣው ረቂቅ መመሪያ ቁጥር 17/2015 ዓ/ም’’ ላይ የተሠጠ የግምገማ
ሃሳብ

1. የመመሪያው አስፈላጊነት
 ለመመሪያው መነሻ ተደርጎ የተወሰደው የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር
252/2009 ዓ/ም እና ደንብ ቁጥር 159/2010 ዓ/ም በክልሉ የቢሮዎች ማቋቋሚያ አዋጅ 280/2014
ዓ/ም የተሸረ መሆኑን በአዋጁ አንቀፅ 41/3 የሚገልፅ በመሆኑ የተዘጋጀው መመሪያ ተቀባይነት
የለውም የሚል ሀሳብ አቅርበናል፡፡
 በረቂቅ መመሪያው እንደተጠቀሰው መመሪያውን ለማሻሻል ያስፈለገበት እንደ ዋና ምክንያት
የተወሰደው ለግብርና ሆነ ከግብርና ውጭ ለሚቀርቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች የገጠር መሬትን
በማቅረብ የስራ ዕድል መፍጠር እና የቴክኖሎጅ ሽግግርን ማፈጠን ተብሎ የተጠቀሰው ተግባር
የኢንቨስትመንት ዋና አለማ ተደርጎ በአዋጅ 1180/2012 ዓ/ም አንቀፅ 5/2 ላይ በመደንገጉ
ለኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተሰጠው ስልጣን በመሆኑ በመሬት ቢሮ የቀረበው ረቂቅ
መመሪያ ተቀባይነት የለውም የሚል ሃሳብ አቅርበናል፡፡
 በኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለሃብቶችን በተሸለ ሁኔታ ለመደገፍ የሚስችል ወጥነት ያለው ክልል
አቀፍ መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ የሚለው ስልጣን እና ተግባር አዋጅ 280/2014 ዓ/ም

ለኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተሰጠ ስልጣን መሆኑን አንቀፅ 15/23 ይደነግጋል፡፡ በክልሉ

ውስጥ በኢንቨስትመንት ሥራ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ያበረታታል፣ ይደግፋል፣ ፈጥነው ወደ


አፈጻጸም በማይገቡ ፕሮጀክቶች ላይ ደግሞ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ፈቃድ
የመሰረዝና መሬት የማስመለስ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፣ እንዲወሰዱ ያደርጋል፤
2. የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሰን
ለኢንቨስትመን የሚውል መሬት ተለይቶ ለባለሃቱ በተቀላጠፈ ሁኔታ በማስተላለፍ የኢንቨስመንት ዓላማዎችን
ማሳካት እና የባለሃቶችን እርካታ ማሰደግ እንዲቻል በአንቀፅ 24 መሰረት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት
ሲገባ ባለሃብቱ ላልተፈለገ እንግልት በመዳረግ ቢሮክራሲ የበዛበት አስልቺ እንዲሆን የሚያደርግ አሰራር በመሆኑ
በመሬት ቢሮ ለኢንቨስትመንት በሚውል በማናቸውም ከከተማ ፕላን ወሰን ውጭ በሆነ የገጠር መሬት ላይ
ተግባራዊ ይሆናል የሚለው አግባብነት የለውም፡፡
 የክልሉ የቢሮዎች ማቋቋሚያ አዋጅ ለመሬት ቢሮ ከሰጠው ዋና ዋና ተግባራት ውጭ ለኢንዱስትሪ
እና ኢንቨስትመንት በተሰጡ ተግባራት ላይ መመሪያ ማውጣት የቢሮውን ህጋዊ ሰውነት የሚንድ
በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡ለዚህም ማሳያ

1|Page
 በፌዴራል የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012 ክፍል አራት አንቀፅ 10 (1) እና (2) መሰረት

በተለያዩ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ለማልማት ፍላጎት ያላቸው የውጭና የሀገር ውስጥ

ባለሃብቶች፤በቅንጅት ለሚሰሩ ለሀገር ውስጥና ውጭ ባለሃብቶች፤ የተፈቀዱ ማበረታቻዎችን

ለመጠቀም የሚፈልጉ የአገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶች የኢቨስትመንት ፈቃድ አስላጊ መሆኑ

በአንቀፅ 10 (1) ከፊደል ሀ-መ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ እንዲሁም አንቀጽ 11 ተራ ቁጥር 3

ማንኛውም የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያወጣ ባለሃብት ወደ ትግበራ መግባት ካልቻለ የኢንቭትመንት

ፈቃዱ እንደሚሰረዝ ተጠቅሷል፡፡

 በክፍል ስምንት አንቀፅ 38 (16) የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጣቸውን ማንኛውም ባለሀብቶች


የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ደረጃ እና አፈጻጸም የመከታተል፣ የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የያዛቸው
ሁኔታዎች መከበራቸውን የማረጋገጥ፣ ማበረታቻዎች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን
የመከታተልና የመቆጣጠር ስልጣን በየደረጃው ለሚገኙ የኢንቨስትመንት መስሪያ ቤቶች የሰጠ
መሆኑ፣
 አንቀፅ 50 (3) የኢንቨስመንት ፈቃድ ያገኙ ባለሀብቶች በክልል የሚያገኙትን የቅድመ- እና የድህረ-
ኢንቨስትመንት አገልግሎት የተሳለጠ ለማድረግ እና የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለማቃለል እንዲቻል
በየክልሎች ኢንቨስትመንት አስተዳደር ዴስክ/ ተቋም ማቋቋም እንደሚቻል ይጠቅሳል
 የኢንቨስትመንት መሬት አቅርቦትን በተመለከተ በክፍል 8 በአንቀፅ 51 (1) መሠረት ክልሎች
አግባብነት ባላቸው የፌደራል የመሬት አስተዳደር ሕጎች የተሰጣቸውን ሥልጣን መሠረት በማድረግ
ለማምረቻ ዘርፍ፣ ለእርሻ እና ሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች የሚውሉ የመሬት አቅርቦት

ጥያቄዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ማስተናገድ፣ በዚሁ አንቀፅ ንዑስ እንቀፅ (2) ላይ የኢንቨስትመንት

መሬት አቅርቦትን በተመለከተ ክልሎች ለኢንቨስትመንት ስራ የሚውል መሬትን አስቀድሞ

በመለየት፣በመመደብ አግባብነት ላለው የኢንቨስትመንት መስሪያ ቤት ያስተላልፋሉ፤ በንዑስ አንቀፅ

(3) የኢንቨስትመንት የተሰጠ ፈቃድን መሠረት በማድረግ ለክልል አካል የሚቀርቡ የመሬት አቅርቦት

ጥያቄዎች በተሳለጠ ሁኔታ ተፈፃሚ እንዲሆኑ ከክልል መስተዳድሮች እና አግባብነት ካላቸው

የኢንቨስትመንት መስሪያ ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፡፡ በንዑስ አንቀፅ (4) መሰረት ደግሞ

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለተሰጠው ባለሀብት ለኢንቨስትመንት ሥራ የሚውል መሬት አቅርቦት ጥያቄ


የቀረበለት የክልል መስተዳድር አካል ለማምረቻ ዘርፍ በ 60 ቀናት ውስጥ እና ለሌሎች ዘርፎች
የሚውል መሬትን አስመልክቶ በሚቀርብ ጥያቄ ላይ በዘጠና (90) ቀናት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ

የተደነገገ መሆኑ፤

2|Page
 በደንብ 474/2012 አንቀፅ 4 መሰረት ለሀገር ውስጥ ባለሃብት የተለዩ የኢንቨስትመንት መስኮች
በፋይናንስ ስራዎች፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፍ እና ማከፋፈል፤በህክምና አገልግሎቶች፤የነዳጅ
ምርቶች ማቅረብ፤ ቡና፣ ጫት፣ የቅባት እህል፣ጥራጥሬ ፣ ማዕድናት፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የተፈጥሮ ደን
ውጤቶች፣ዶሮ እና የጋማ ከብችን የመግዛትና የመላክ በኮንስትራክሽን፣የሆቴል፣ሎጅ፣ሪዞርት፣ሞቴል
የእንግዳ ማረፊያ እና የፔንሲዮን አገልግሎቶች፤የሬስቶራንት፣በማስጎብኜት፣ ማሽኖች እና
ተሸከርካሪዎች የማከራየት አገልግሎት በመሳሰሉት የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት የሚችሉ
መሆኑ፣
 በአማራ ክልል ለአበባ፣አትክልት እና ዕፀ-ጣዕም ልማት የሚውል መሬት በገጠርና ከተማ

ስለሚዘጋጅበትና በምደባ ለባለሃብቱ ስለሚተላለፍበት ሁኔታ በክልሉ ካቢኔ የተዘጋጀው መምሪያ

ቁጥር 17/2006 ፀድቆ እየተተገበረ መሆኑ፤

 እንዲሁም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የአስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ

እና ሥልጣንና ተግባራት ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር 280/2014 ዓ.ም በአንቀፅ 17 እና 18 መሰረት

በተዘጋጀ የኢንቨስትመንት ቀጠና አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች

እንዲስፋፉ ይሰራል፣የቀጠናዎችን ወሰንና የአጠቃቀም ለውጥ በመሬት አስተዳደር መስሪያ ቤቱ

እንዲመዘገብ ያደርጋል፣ በተለዩት ቀጠናዎች የሚገቡ ፕሮጀክቶችን እንዲቀበል እና እንዲገመግም፣

ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የሚውል የመሬት መጠን በመወሰን ውል ይዞ የማስተላለፍ ፤በማያለሙ

ባለሃብቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ መሬቱን ተመላሽ በማድረግ እና ለመሬት ቢሮ በማሳወቅ

ለሌላ አልሚ ያስተላልፋል፡፡

 እንዲሁም በአንቀፅ 22 እንደተጠቀሰው ባለሃብቶች የሚያቀርቡትን የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች

መርምሮ አግባብ ባላቸው የኢንቨስትመንት አዋጅ እና ደንቦች ላይ የተደነገጉትን አሟልተው ሲገኙ

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል የሰርዛል… በሚል የተገለፀው የኢንቨስትመንት ፈቃድ

ለሚጠይቁ ፈቃድ የመስጠት እና ከአላማ ውጭ ሲያውሉ የመሰረዝ፣ በተጨማሪም በአንቀፅ 23

በክልሉ ውስጥ በኢንቨስትመንት ስራ ተሰማርተው ፈጥነው ወደ አፈጻጻም በማይገቡ ፕሮጀክቶች

ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ፈቃድ የመሰረዝ እና መሬት የማስመለስ አስተዳደራዊ

እርምጃ ይወስዳል፣ እንዲወሰድ ያደርጋል፣ በአንቀፅ 27 ላይ በፌዴራል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኩል

በፈቃድ አግንተው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶችን ተግባራት

በቅርብ የመከታተል፣ የመደገፍ እና ትክክለኛ የስራ እንቅስቃሴ ላይ የማይገኙትን መሬት ነጥቆ

3|Page
ውሳኔውን ለመሬት ቢሮ እና ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያሳውቃል፣ በአንቀፅ 28 መሠረት

የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጣቸውን ፕሮጀክቶች አፈጻጻም በቅርብ የመከታተል፣ የኢንቨስትመንት

ፈቃዱ የያዛቸውን ሁኔታዎች እና ማበረታቻዎች ለታለመላቸው አላማ መዋላቸውን የማረጋገጥ፣

ከአላማ ውጭ በሚያውሉት ላይ እርምጃ የመውሰድ ስልጣን እና ተግባር ለቢሮው የተሰጠ በመሆኑ

በመሬት ቢሮ በኩል የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ በቢሮው በኩል ተቀባይነት የለውም

 በመመሪያው ክፍል ሶስት አንቀፅ 6/1 ስር 1.12 በክልሉ ለሚካሄድ የአበባ፣አት/ፍራፍሬ፣ዕፀ ጣዕም

፣የቡና ልማት ፣የመስራች ዘር፣የዘር ብዜት እና የደን ልማት ፐሮጀክት በአልሚ ባለሃብቶች

አስፈላጊው የፕሮጀክት ሰነድ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ የመሬት ጥያቄ ፣ጉዳዩ በመሬት ቢሮ ተገምግሞና

መሬት መኖሩ ተረጋግጦ የውሳኔ ሃሳብ ሲቀርብ በኢንቨስትመንት ቦርድ ውሳኔ በምደባ ይሰጣል በሚል

ተቀምጧል፡፡ነገር ግን ይህ ከላይ የተዘረዘረው ተግባር በኢንቨስትመንት ቦርዱ ደንብ ቁጥር 205/2015

ዓ.ም የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ተግባርና ኃላፊነት መሆኑ በሌላ መንገድ ጉዳዩ በኢንዱ/ኢንቨ ቢሮ

ተገምግሞ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያቀርብ ክልል ም/ቤት ባወጣው መመሪያ ቁጥር 17/2006 ዓ.ም

ተግባሩ ለኢንዱ/ኢንቨ ቢሮ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ስለሆነም መመሪያው እነዚህን ህጎች የሚቃረን ነው፡፡

 በመመሪያው ክፍል ሶስት ከግብርና ውጭ (ኢንዱስትሪ+አገልግሎት) ለሆኑ የኢንቨስትመንት ዘርፎች

የገጠር መሬት ለባለሃብቶች የሚተላለፍበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ይሁን እንጅ ተግባሩ የኢንዱስትሪና

ኢንቨስትመንት እንደሆነ አዋጅ ቁጥር 280/2014 ዓ.ም አንቀጽ 15/17 እና 18 በግልጽ ይደነግጋል

እንዲሁም በኢንቨስትመንት ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር 1180/2012 አንቀጽ 38/22 የኢንቨስትመንት

ቦርድን መመሪያዎችና ውሳኔዎች ይፈፅማል፣በሚመለከጻቻ ሌሎች አካላት መተግበራቸውን

ይከታተላል በሚል ይደነግጋል ፡፡ ለዚህ ማሳያዎች


 17) “በሚመለከተው አካል ተለይቶ በተዘጋጀው የኢንዱስተሪ ቀጠና አምራች ኢንዱስትሪዎች እና

ሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች እዲስፋፉ ይሠራል፣ የቀጠናዎቹ ወሰንና የአጠቃቀም ለውጥ በመሬት

አስተዳደር መሥሪያ ቤቱ እዲመዘገብ ያደርጋል፣”

 18) “ከዚህ በላይ በንኡስ አንቀጽ 17 በተደነገገው መሠረት ተለይቶ የተዘጋጀውን ወደ የኢንዱስትሪ
ቀጠና እንዲገቡ ለተመረጡ አልሚዎች ያቀረቧቸውን ፕሮጀክቶች በመገምገምና የመሬት መጠን

በመወሰን ውል ይዞ መሬት ያስተላልፋል፣ እንዳስፈላጊነቱ የመሠረተ-ልማት ማሟላት ተግባራትን

ያከናውናል፣ በውላቸው መሠረት በማያለሙት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል፣ መሬቱን ተመላሽ

በማድረግ እና ለመሬት ቢሮ በማሳወቅ ለሌላ አልሚ ያስተላልፋል፤”

4|Page
 በኢንቨስትመንት ቦርድ ደንብ ቁጥር 205/2015 ዓ.ም አንቀፅ 6 “በአገልግሎት
ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከ 5000(ከአምስት ሺህ ካሬ ሜትር) በላይ መሬት ለሚፈልጉ
የሆቴል፣ሎጅ፣ሪል ኢስቴት ፕሮጅክት በዞንና ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ቦርድ
የውሳኔ ሀሳብ ወይም ጉዳዩ በሚመለከተው ተቋም/ቢሮ ተገምግመው ሲቀርቡ
በሚያቀርቡት መነሻ የውሳኔ ሃሳብ መሰረት መሬት በልዩ ሁኔታ በምደባ እንዲያገኙ ልዩ
ውሳኔ ይሰጣል፡፡እንዲሁም የጤና ፣ትምህርት፣ ስፖርት ልማት ኢንቨስትመንቶች ከላይ
ከተጠቀሰው የካሬ ሜትር መጠን ሳይገድባቸው በልዩ ሁኔታ መሬት በምደባ እንዲያገኙ
ያደርጋል፣አፈፃፀሙን ይከታተላል” በሚል ተግባሩ ለቦርድ ተሰጥቷል፡፡

ማጠቃለያ

 የገጠር መሬት ኢንቨስትመንት መሬት ሊዝ አሰራሩንና ተመኑን በየጊዜው እያጠና ለክልሉ መንግስት

በማቅረብ ያስወስናል ፣ለኢንዱስትሪ የሚውሉ ቦታዎችን ይለያል፣ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት

ቢሮ ያስተላልፋል፣ በገጠር በእርሻ ኢንቨስትመንት ለሚሳፉ ያቀረቡትን ፕሮጀክት በመገምገምና


የመሬት መጠን በመወሰን ውል ይዞ ለሶስተኛ ወገን መሬት ያስተላልፋል ፣ወደ ስራ ከገቡ በኋላ
ለታለመለት አላማ ስለመዋሉ ይከታተላል፣ይቆጣጠራል በእቅዳቸውና በውላቸው መሰረት
ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር በህግ መሰረተ 6 እርምጃዎችን

ይወስዳል፣እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡ በሚል በአዋጅ ቁጥር 280/2015 ዓ.ም አንቀፅ 17/6 በግልፅ

ተደንግጓል፡፡በአጠቃላይ ሲታይ መመሪያው የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት አዋጅ፣ደንብና መመሪያን

የሚቃረን በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 280/2015 ዓ.ም አንቀፅ 17/6 መሰረት መቃኘት ይገባዋል የሚል

አስተያየት አለን፡፡

5|Page

You might also like