Professional Documents
Culture Documents
የአምራች ኢንዱስትሪው የሰው ሀብት ልማት አቅጣጫ.docx
የአምራች ኢንዱስትሪው የሰው ሀብት ልማት አቅጣጫ.docx
ከላይ በምስል 1 እንደተመላከተው በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ፈጣን እና ዘላቂ የሆነ ልማትን በማረጋገጥ
የታሰበውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በመጀመሪያ ደረጃ በለዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር
አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ከታች ባሉት ምስሎች እንደተመላከተው የመጀመሪያው ምዕራፍ የሰው ሀብት የአቅም ልማት እቅድ በዋናነት
የሚያተኩረው ኢንዱስትሪውን ባሳተፈ መልኩ ለቀላል ኢንዱስትሪዎች እድገት አስተዋጽኦ የሚያስፈልጉ
ቴክኖሎጂዎችን ከወቅቱ ፍላጉት አንጻር ለይቶ መቅዳትና ማላመድ እንዲሁም በተግባር ላይ የሚተኩሩ
ስልጠናዎች እና የትምህረት መስኮች ላይ ነው፡፡
ሁለተኛው ምዕራፍ በአንጻሩ ትኩረት የሚያደርገው የመጀመሪው ምእራፍ አፈጻጸም የሚፈጥራቸውን ከባድ
ኢንዱስትሪዎች ፍላጉት ማሟላት ላይ ነው፡፡ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች የአመራረት ስርዓታቸው በከፍተኛ እና
ውስባስብ ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚመሰረት በመሆኑ ይህን ፍላጎት ማሳካት የሚችል የቴክኖሎጂ አቅምን
በጥናትና ምርምር በታገዘ ፈጣራ መደገፍን እንዲሁም በከፍተኛ የክህሎት ደረጃ የሰለጠነ እና በተመረጡ
የትምህርት መስኮች በእውቀት ስፔሻላይዝድ ያደረገ የሰው ሀብት ማልማት ላይ ያተኩራል ፡፡