PDF

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 32

ሙስናን መታገል በተግባር

0
1. መግቢያ

ሙስናና ብልሹ አሰራር ልማትን በማዳከም የሀገር ኢኮኖሚ እንዲገታ፣ የሞራልና የሥነምግባር
ቀውስ እንዲባባስ፣ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፣ ህዝብ በመንግስትና በህግ የበላይነት ላይ
አመኔታ እንዲያጣ የሚያደረግ አደገኛና ድንበር ዘለል ባህሪ ያለው አለማቀፋዊ ወንጀል ነው፡፡
ሙስና ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም የዓለማችን ሀገራት የሚገኝና የሁሉም ሀገራት ተግዳሮት
ነው፡፡ ይሁንእንጂ የችግሩ ዋነኛ ተጠቂዎች እንደአፍሪካ ያሉ ታዳጊ ሀገሮች ናቸው፡፡ ሀገራችን
ኢትዮጵያም የዚህ አደገኛ ወንጀል ተጠቂ ነች፡፡

የዓለም ህዝብ ይህን ድንበር የለሽ ዓለምአቀፋዊ ችግር በአግባቡ መከላከል እና መዋጋት ካልቻለ
ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገትን እንዲሁም ሰላምና መረጋጋትን ተግባራዊ ማድረግ
አይቻልም፡፡

በመሆኑም ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ሀገሮች በተናጠል ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ


በተጨማሪ በጋራ ለመታገል የሚያስችላቸው ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን እንዲኖር በተባበሩት
መንግስታት ድርጅት በኩል ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በተደረገው የረዥም ጊዜ ጥረትም የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን ተረቆ እ.ኤ.አ


ከዲሴምበር 9-12/2003 በሜክሲኮ “ሜሪዳ” ከተማ ለአባል ሀገራት ለፊርማ ቀርቧል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤም በውሳኔ ቁጥር 58/422 ኮንቬንሽኑ እንዲፀድቅ አድርጓል፡፡
ኮንቬንሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአባል ሀገራት ለፊርማ የቀረበበትን ቀን ለማሰብም ዲሴምበር 9
በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ ህዳር 30 ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተብሎ እንዲሰየም ወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት ቀኑ በየዓመቱ ኮንቬንሽኑን በፈረሙ ሀገሮች ዘንድ ስለኮንቬንሽኑ ምንነትና


አፈፃፀም፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር በሚያስከትለው ጉዳትና በመከላከያ ዘዴዎቹ ላይ ለህብረተሰቡ
ግንዛቤ በሚፈጥሩ ሰፋፊ የህዝብ ንቅናቄዎች በድምቀት ይከበራል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያም የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽንን ከማርቀቅ ጀምሮ እሰከ


ማፅደቅ በነበረው ሂደት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን ከዚያ በኋላም
በዓለምአቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ለሚገኘው የፀረ-ሙስና ትግል አጋርነቷን በማሳየት ላይ ትገኛለች፡፡

1
የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽንን ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
በማቅረብ እ.ኤ.አ ዲሴምበር 26/2007 በአዋጅ ቁጥር 544/1999 በማፀደቅና የሀገሪቱ የህግ አካል
እንዲሆን በማድረግ ረገድም ሀገራችን የራሷን ሚና ተጫውታለች፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የአፍሪካ
ህብረት የሙስና መከላከያና መዋጊያ ኮንቬንሽንንም በአዋጅ ቁጥር 545/1999 አፀድቃለች፡፡ ይህ
ደግሞ በ1987 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 9(4) መሰረት ኢትዮጵያ
የምታፀድቃቸው ዓለምአቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ የህግ አካል ተደርጎ እንደሚወሰድ የሚደነግግ
በመሆኑ ስምምነቱ በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የሀገሪቱ የህግ አካል ሆኖ በአስገዳጅነት ተኳቷል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ አንድ አካልና የኮንቬንሽኑ ፈራሚና አፅዳቂ እንደመሆኗ ዓለም
አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ላለፉት 17 ዓመታት የስምምነቱን ጠቀሜታ በማስረዳትና ሌሎች
በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ዙሪያ ግንዛቤ በሚፈጥሩ ዝግጅቶች ስታከብር ቆይታለች፡፡

ዘንድሮም በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የፀረ-
ሙስና ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ታከብራለች፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ሙስናን መታገል


በተግባር!" በሚል መሪ ቃል ነው፡፡

መሪ ቃሉ የተመረጠው የሙስናን ምንነትና የሚያስከትለውን ዘርፈ-ብዙ ጉዳት ከማወቅና ከመረዳት


ባሻገር የሙስናና ብልሹ አሰራር ድርጊቶችን ባለመፈፀም፣ በሌሎች ሲፈፀምም አምርሮ በመታገልና
በማጋለጥ የተግባር ሰው መሆን መስናን ትርጉም ባለው መንገድ ለመታገል ወሳኝ መሆኑን
ለማመላከት/ለማስገንዘብ ነው፡፡

በሀገራችን እንዲሰፍን የምንፈልገውን ሁሉንአቀፍ እድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ የመልካም


አስተዳደር ችግር የሆነውን ሙስናን አምርሮ በተግባር መታገል እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በየደረጃው የሚገኘው አመራር ሙስና በሀገር ላይ የሚያስከትለውን አስከፊ ገፅታ ተረድቶ


ተግባራዊ ምላሽ ካልሰጠ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ከቶውኑ አይቻልም፡፡

መንግስትም ይህን በመረዳት በፀረ-ሙስና ትግሉ እያሳየ የሚገኘው ቁርጠኝነት ይበል የሚያሰኝ
ነው፡፡ ይህም ለፀረ-ሙስና ትግሉ ትልቅ አቅም ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ውጤታማ መሆን የሚችለው
በየደረጃው የሚገኘው ሁሉም አመራርና ህብረተሰብ ከቃላት ባለፈ በተግባር ሙስናና ብልሹ

2
አሠራርን መታገል ሲችል ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው የዘንድሮው አለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን
ሙስናን መታገል በተግባር በሚል መሪ ቃል የሚከበረው፡፡ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-
ሙስና ኮሚሽን በ2015 ዓ.ም የሚከበረውን የዘንድሮውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ
በየተቋማቱ ለሚካሄድ ውይይት መነሻ እንዲሆን ይህ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡ ተቋማት ሰነዱን
እንደመነሻ በመጠቀም ከራሳቸው ተቋማዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥመው ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

3
ክፍል አንድ
የሙስና ፅንሰ-ሀሳብ
1.1 የሙስና ምንነት፣
ሙስና እንደየ ሀገሩ ተጨባጭ ሁኔታ በተለያየ መንገድ መጠንና አይነት የሚከሰት በመሆኑ
አንድ ወጥና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ትርጉም የለውም፡፡

በመስኩ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን፣ ዓለምአቀፋዊና አህጉራዊ ተቋማት የተለያዩ


መገለጫዎችን መሠረት በማድረግ ሙስና ለሚለው ቃል የሰጧቸው ትርጉሞች በአገላለፃቸው
ይለያዩ እንጂ በይዘታቸው ተቀራራቢ ናቸው ፡፡ ይህን ለማሳየት የተወሰኑ የሙስና ትርጉሞችን
መመልከት ተገቢ ነው፡፡

በአደራ የተሰጠን ሥልጣን ለግል ጥቅም ማዋል፣ እምነትን ማጉደል ወይም አለመታመን፣
በጉቦ፣ በምልጃና በአድሎ ሃቅን፣ ውሳኔን ወይም ፍትህን ማዛባት ነው (Transparency
International 2008)፡፡
ሙስና የመንግስትን ሥራ ሥነምግባራዊ እና ህጋዊ መሠረት ባለው መመሪያና ደንብ ላይ
ተመርኩዞ ማከናወን አለመቻል ነው ይለዋል /የሙስና ቅኝት በኢትዮጵያ 1993/፡፡
ሙስና ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ሥርዓቶችን፣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ አሰራሮችን፣
መርሆዎችን የመጣስ ማንኛውም ተግባር ነው (Kato, 1995)፡፡
ሙስና በግል ወይም በቡድን፣ በፖለቲካ መሪዎች ወይም በቢሮክራቶች ሥልጣንና ኃላፊነትን
መከታ በማድረግ የህዝብን ጥቅምና ፍላጐት ለግል ጥቅም የማዋል ኢ-
ሥነምግባራዊ ድርጊት ሲሆን፣ በመንግስትና በህዝብ ሃብትና ንብረት ላይ ስርቆት መፈጸም፣
ዝርፊያ ማካሄድ፣ ማጭበርበር፣ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ከመሥራት ይልቅ በዝምድና፣
በትውውቅ፣ በፖለቲካ ወገንተኝነት፣ በጐሰኝነት፣ በኃይማኖት ትስስር ላይ ተመርኩዞ
በመሥራት አድሎ መፈፀም፣ ፍትህን ማጓደልና ሥልጣንና ኃላፊነትን በህገወጥ መንገድ
የጥቅም ማግኛ የማድረግ እኩይ ተግባር ነው /ኬምፔሮናልድና ሰርቦርዌል 2000/፡፡
ሙስና የፖለቲካና የመንግስት አስተዳደራዊ ኃላፊነትን ካለመወጣት የሚመነጭ፣ ማህበራዊና
አስተዳደራዊ ሥርዓቶችን የመጣስ የሥነምግባር ግድፈት ሲሆን ይህም ለግል ጥቅም ሲባል

4
በህዝብ የተሰጠ ሥልጣንና ኃላፊነትን አላግባብ በመጠቀም ህግና ደንብ የመጣስ እኩይ
ተግባራትን ያካትታል / ቻርለስ ሳን ፎርድ 1998/፡፡

ከላይ የቀረቡትን የሙስና ትርጉሞች ስንመለከት የሙስና ወንጀል በግልም ይሁን በመንግስት
ተቋማት ውስጥ ሊፈጸም የሚችል መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በተጨማሪም ሙስና ህግና ሥርዓትን
ተከትሎ ከመሰራት ይልቅ ስልጣንና ኃላፊነትን መከታ በማድረግ ህግና ሥርዓትን በመጣስ የግል
ጥቅምን ማካበትና ሌላን ወገን ተገቢ ባልሆነ መንገድ መጥቀም ወይም መጉዳት እንደሆነ መረዳት
ይቻላል፡፡

1.2 የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት


የተለያዩ ጥናቶችና ልምዶች እንደሚያመለክቱት ሙስና ከሚከሰትበት ሁኔታ እና አፈጻጸም አንፃር
ከሌሎች ወንጀሎች የሚለይበት ባህሪያቶች አሉት፡፡

የሙስና አንዱ ባህሪ በተለያዩ ዘርፎች እና በተለያየ ደረጃ ከታችኛው እርከን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው
እርከን ድረስ የሚከሰት መሆኑ ነው፡፡

ሌላው የሙስና ልዩ ባህሪ የአፈጻጸሙ ሂደትና ስልት ውስብስብ መሆኑ ነው፡፡ ሙስና እንደ ግድያ
እና ሌሎች የተለመዱ ደረቅ ወንጀሎች በስሜታዊነት፣ በግብታዊነትና በጀብደኝነት ሳይሆን
የአፈጻጸሙን ሂደትና ሥልት እንዳይደረስበት ለማድረግ በከፍተኛ ጥናት፣ በጥንቃቄና በሚስጢር
የሚፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ ወንጀሉ ስለመፈጸሙ የሚጠቁም መረጃ ለማግኘት አዳጋች ነው፡፡

ለጉዳዩ ባለቤት ነኝ ባይ አለመኖር ሌላው የሙስና ልዩ ባህሪ ነው፡፡ የሙስና ወንጀል የሚያደርሰው
ጉዳት በአንድ ወይም በተወሰነ ቤተሰብና ግለሰብ ላይ የሚወሰንና በቀጥታ የሚታይ ሳይሆን
አገርንና ህዝብን በሙሉ የሚያጠቃልል መጠነ ሰፊ ነው። በመሆኑም የሙስና ወንጀል ሲፈጸም
ወንጀሉን የማጋለጥ ወይም የመታገል ሀገራዊ ግዴታ አለብኝ፣ እንደ ዜጋ ይመለከተኛል በማለት
ማስረጃ አሰባስቦ ጉዳዩን ለህግ የሚያቀርብ ሰው በጣም ጥቂት መሆኑ የሙስና ወንጀልን ከሌሎች
ወንጀሎች የተለየ ያደርገዋል፡፡
ከፍተኛ የሙስና ተግባር የሚፈፀመው በኑሮ ደረጃቸው የተሻሉ፣ ከፍተኛ እውቀት፣ ሥልጣንና
ገንዘብ ባላቸው ሰዎች ነው፡፡ ስለዚህ የሙስና ወንጀልን የሚፈጽሙት ሰዎች አስቀድሞ በተጠናና

5
በረቀቀ ዘዴ በተቀነባበረ መንገድ ራሳቸውን አደራጅተው፣ ስልቶችን በጥንቃቄ ነድፈው፣
ከተጠያቂነት ማምለጥ የሚችሉበትን መንገድ ሁሉ ቀድመው አመቻችተው መሆኑ ወንጀሉን
የተለየና ውስብስብ ያደርገዋል፡፡

እነዚህ ሙሰኞች የመወሰን አቅምና ሥልጣን ስላላቸው ምርመራ እንዳይካሄድ በማደናቀፍ ሂደቱን
እንዲዘገይ ምርመራው ቢካሄድም ልፍስፍስ እንዲሆን በማድረግ የተጠርጣሪዎችን የተጠያቂነት
ደረጃ በማሳነስ ወይም ነጻ እንዲወጡ በማድረግ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ፡፡ የተጀመረ ምርመራ
እንዲኮላሽ ማድረግ ሲሳናቸው ደግሞ መርማሪውንም ሆነ ከምርመራው ጋር ግንኙት ያላቸውን
ግለሰቦች በተለያየ መንገድ ያስጠቃሉ፡፡ የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ ሙስናን የሚመረምረውንና
የሚከሰውን አካል በሙስና እንዲወነጀልም ያደርጉታል፡፡

የሙስና ወንጀል በአብዛኛው ሰው ዘንድ እንደ ነውር አለመታየቱ የፀረ-ሙስና ትግሉን ውስብስብና
ልዩ ባህሪ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው፡፡ በሀገራችን በሙስና የተዘፈቀ ሰው እንደብልጥና ቀልጣፋ
ሲደነቅ ይስተዋላል፡፡ “የሺን ገንዘብ ብላው የሺን ወንድም ፍራው፣ሲሾም ያልበላ ሲሻር
ይቆጨዋል፣ወዘተ…” ምሳሌያዊ አባባሎች ሙስናን እንደ ነውር ሳይሆን እንደብልጥነት፣
በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ተቀጥሮ ቅንና ቀና መሆን እንደሞኝነትና ስልጡን አለመሆን
የሚታይ እንደሆነ የሚያመለክቱና ሙስናን የሚያበረታቱ አባባሎች ናቸው፡፡ በመሆኑም
ህብረተሰቡ የማያነውረው ተግባር ላይ ማስረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ይህም ሙስናን
በመዋጋት ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚደርስባቸው ጥላቻና ውግዘት ከሚፈጥርባቸው
የሥነልቦና ጫና የተነሳ ስለሚሸማቀቁ ለፍርድ ሂደቱ አጋዥ የሆኑ መረጃዎችን እንዳያገኙ
እንቅፋት ይሆንባቸዋል፡፡

ምንም እንኳን ሙስና በብዙ ሰዎች ዘንድ እንደ ነውር ያለመታየቱ ችግር ቢኖርም አሁን አሁን
በአገራችን ኅብረተሰቡ የሙስና ወንጀል ስለሚያስከትለው ጉዳት ግንዛቤው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ
በመምጣቱ ድርጊቱ ሰለመፈጸሙ ጥቆማ የሚያቀርቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡

በአጠቃላይ ሙስና ውስብስብና አስቸጋሪ፣ የሚያደርሰውም ጉዳት ከፍተኛና ልዩ ባህሪ ያለው


ወንጀል መሆኑን በመረዳት ለዚህ የሚመጥን ከቃል ያለፈ ተግባራዊ ትግል ማድረግ ከሁሉም
አካል ይጠበቃል፡፡

6
1.5. የፀረ-ሙስና የህግ ማዕቀፎች

ሀገራችን ሙስና ለመከላከል አጋዥ የሆኑ ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎች ያሏት ሲሆን በአህጉር እና
በዓለምአቀፍ ደረጃ የወጡ ስምምነቶችንም የሀገሪቱ የህግ አካል አድርጋ ደንግጋለች፡፡ ለአብነት
የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል፡፡
አዋጅ ቁጥር 1/1987 የ1987 የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ለማፅደቅ የወጣ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 544/2007 የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን ማፅደቂያ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 545/2007 የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከያ እና መዋጊያ ኮንቬንሽን
ማፅደቂያ
አዋጅ ቁጥር 668/2002 የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 699/2003 የወንጀል ጠቋሚዎች እና የምስክሮች ጥበቃ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 883/2007 የተሻሻለው የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ማቋቋሚያ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 882/2007 የተሻሻለው የልዩ የፀረ-ሙስናና የማስረጃ አቀራረብ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 943/2008 የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 720/2004 የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ እና አዋጅ ቁጥር 944/2008
(ማሻሻያው)፣
አዋጅ ቁጥር 1097/2011 የፌደራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር
ለመወሰን የወጣ አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 881/2007 የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ፣
አዋጅ ቁጥር 1236/2013 የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ማሻሻያ አዋጅ፣

እነዚህን ህጎች ሙስናን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያላቸው ናቸው፡፡ ችግሩ እነዚህን ሀገራዊና
አለማቀፋዊ ህጎች ተግባራዊ አለማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን
ለማድረግ እነዚህን ህጎች ማክበርና መስከበር የሁላችንም ድርሻ መሆን አለበት፡፡

7
ክፍል ሁለት

በኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ትግል፣ አስቻይ ሁኔታና ተግዳሮቶች

2.1 በኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ትግል የእስካሁን እንቅስቃሴ

ሙስና በሁለንተናዊ ልማት ላይ ከሚያሳድረዉ አሉታዊ ተጽእኖ አንጻር በአሁኑ ወቅት


የአለማችን ግንባር ቀደም ስጋት ከሆኑ የወንጀል ድርጊቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ከዚህም አልፎ
ለሌሎች የአለም የደህንነት ስጋት ተብለዉ ለሚለዩ ወንጀሎች መስፋፋት እንደ ማሳለጫ
/Catalyst/ ሆኖ ይታያል፡፡ በተለይም ደግሞ እንደኢትዮጵያ ላሉ በማደግ ላይ ያሉ አገራት
ከሚገኙበት ዝቅተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ደረጃ ጋር ተዳምሮ የሚያስከትለዉ ተጽእኖ
ጉልህ ነዉ፡፡

በኢትዮጵያ የሙስናና ብልሹ አሰራር ጥልቀቱና ስፋቱ ይለያይ እንጂ ብዙ አመታትን ያስቆጠረ
እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ባለፉት ስርአቶች በተለይ የመንግስት ሹማምንትና ፈፃሚ አካላት ጉዳይን
ለመፈፀም እጅ መንሻ ከመቀበል አንስቶ በዘመድ አዝማድ፤ በአምቻና ጋብቻ ላይ የተመሰረተ
አገልግሎት አሰጣጥን ለአብነት ማንሳት ይቻላል /ፌሥፀሙኮ፤ 2008/፡፡

ከዚህም በመነሳት በአሁኑ ጊዜ የአለም ሃገራት ፣መንግስታት፣ አለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች
እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ከሚነጋገሩባቸው አጀንዳ፤
ከሚቀርፁባቸው ህግጋትን ከሚደነግጉባቸው እና ትብብርና አጋርነት ከሚዘረጉላቸው አንገብጋቢ
ጉዳዮች መካከል ሙስና አንዱ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ረጅም የመንግሥትነት ታሪክ ቢኖራትም፣ ተፃራሪና አደናቃፊ በሆኑ መጥፎ


አጋጣሚዎች የተነሳ የተመቻቸ የፖለቲካና የማኅበራዊ ሕይወት ለማደላደል አልበቃችም፡፡
በ1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተካሄደዉን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ ሙስናና ብልሹ አሠራር
ለሀገሪቱ የልማት፣ የሠላም የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ጉዞ ከፍተኛ እንቅፋት መሆኑን
በመረዳት የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡ ከነዚህ እርምጃዎች ውስጥ በሲቪል

8
ሰርቪሱ ውስጥ ይስተዋሉ የነበሩ የአሰራርና የሥነምግባር ችግሮችን ለመከላከል ከ1987 ዓ/ም
ጀምሮ የተተገበረዉ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሽ ነዉ፡፡
የዚህ ሪፎርም አንድ ዉጤት በመሆን የተቋቋመዉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ይህን
ሀገራዊ የሙስናና ብልሹ አሠራር ችግር ተቋማዊ በሆነ አደረጃጀት የመዋጋትና የመከላከሉን
ስራ በባለቤትነት ይዞ እንዲንቀሳቀስ በማሰብ ከ1993ዓ/ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር235/1993
ተቋቁሞ ችግሩን ለመቅረፍ የሚግዝ ጥረት ላለፉት 21 አመታ ሲከናወን ቆይቷል፡፡

በዚህ ሂደትም ችግሩን ለመከላከልና ለመዋጋት የሚረዱ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወን የቆዩ
ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ተቋማቱን በፌዴራልና በክልል ደረጃ እንዲዋቀሩ የማድረግ ፣አስፈላጊ
የፀረ-ሙስና ህጎችን የማዉጣትና የማሻሻል፣ የስነምግባር ትምህርት የማስፋፋት፣አሰራሮችን
በማጥናት ሙስናና ብልሹ አሰራርን የመከላከል፣ ወንጀለኞችን በመመርመርና በመክሰስ በህግ
ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም የተመዘበረ ሃብትን ለማስመለስ ጥረት ሲያደርግ
ቆይቷል፡፡

ይሁንና ከችግሩ ስፋትና ዉስብስብነት አኳያ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትም ሆኑ የተመዘገቡ


ዉጤቶችን ስንመለከት ጎልተዉ ሊታዩ የሚችሉ አይደሉም፡፡ በአንዳንድ አለማቀፍ ተቋማት
መመዘኛ መስፈርት መሰረት ከጊዜ ወደጊዜ የደረጃ መሻሻሎች መኖራቸዉን የሚያመላክቱ ጉዳዮች
ቢኖሩም ሙስና አሁንም የአገራችን ቀዳሚ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግር ነው፡፡
በሀገራችን ካሉ አንገብጋቢ ችግሮች ዉስጥ አንዱና በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ መሆኑም
በጥናት ተረጋግጧል፡፡ በተጨባጭም የማህበረሰባችን ዋነኛ የእሮሮ ምንጭ ሆኖ ይታያል፡፡

መንግስት በሀገራችን ስር እየሰደደ የመጣውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመቀነስ ባለፉት አራት
ዓመታት የተለያየ ጥረት እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ መሰረታዊ ለውጥ
ለማምጣት የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይቷል፡፡ የሚከተሉት ዋና ዋና ስራዎች ተከናውኗል፡፡
የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች በሀገር ደረጃ ውጤታማ በሆነ መልኩ
የሚፈፀመው ብቁ የሆነ አደረጃጀት እና አሰራር ሲኖር ነው ፡፡ በዚህ መሰረት፤ ነፃና ገለልተኛ
ተቋም የሆነ እንዲሁም ለፀረ-ሙስና ትግሉ የሚመጥን አደራጃጀት በማጥናትና የሰው ሀይል
ምደባ በማድረግ እንዲሁም ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ትግል የሚመራበት ፖሊሲና ስትራጂ

9
በማዘጋጀት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብቷል፡፡ ኮሚሽኑ የተመቻቸ የስራ አከባቢ እና ዘመናዊ
የመረጃ ልውውጥ ስርዓት እና የመረጃ ተደራሽነት የሚያዘምኑ እርምጃዎች ተወስዷል፡፡
የሙስናና ብልሹ አሰራር ዋነኛ ምንጭ የስነምግባር ብልሽት ወይም መጓደል በመሆኑ የአመለካካት
ለውጥ የሚያመጡ እርምጃዎች እየወሰደ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከናወኑ የግንዛቤ
ማስጨበጫ እና የስልጠና ስራዎች ጥራትና ተገቢነታቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ ለማድረግ
የሚያስችል አሰራር የተዘረጋ ሲሆን የሚከናወኑ ማንኛውም የስነምግባር ግንባታና ሙስና
መከላከል መደበኛ ስልጠናዎች በጥናት ውጤቶች እና ተጨባጭ ኬዝ ላይ ተመሰርተው
እንዲከናወን እየተሰራ ይገኛል፡፡ ዋና ዋና የሚባሉ ባለድርሻ አካላት እና የተለያዩ የህብረተሰብ
አደረጃጀቶች በመለየት በፀረ-ሙስና ትግሉ የሚሳተፉበት መድረኮች እና ሁኔቶች ተዘርግቶ
የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛል፡፡ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች በእያንዳንዱ
ዘርፍ እና የመንግስት ተቋም እንዲደራጁና ተገቢውን ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ
የሚያስችል የድጋፍ ፤ ክትትልና ግምገማ ስርዓት በመዘርጋት እንዲጠናከሩ ፤ በህግ የተሰጣቸውን
ሓላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ አቅም የመገንባት እና የመደገፍ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ኮሚሽኑ ሙስና በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ ለመከላከል በመጀመሪያ ደረጃ በተቋማት ያሉ
ዋና ዋና ስራዎች የሙስና ስጋት ደረጃ ልየታ ጥናት በማካሄድ ተቋማት ሙስና ለመቀነስ
የሚያስችል ስትራተጂ እንዲያዘጋጁ እና ተግባራዊ እንዲያደረጉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡
ዘርፍ-ተኮር የሙስና መከላከል ስትራተጂ በመዘርጋት በሁሉም ዘርፎች የሚከሰቱ ሙስናና ብልሹ
አሰራር ለመከላከል አቅዶ እየሰራ ሲሆን በ2014 ዓ.ም በትምህርት ዘርፍ ፤ በፍርድ ቤት እና
በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ ጥናት ያካሄደ ሲሆን የጥናቱ ውጤት ላይ ተመሰርቶ የባለድርሻ አካላት
እየተወያዩበት የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ዘርፍ-ተኮር የሙስና መከላከል ስትራተጂ ተዘጋጅተው
ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
የመንግስት ሰራተኞች እና አመራሮች ሀብትና ንብረታቸውን በኦንላይን የሚያስመዘግቡበት
ሥርዓት ተዘርግቶ ሀብት የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን የተመዘገበውን ሀብት
ከሙስና የፀዳ መሆኑንና አለመሆኑን እንዲሁም የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች ከጥቅም
ግጭት በፀዳ መልኩ ተገቢውን ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ የመከታተል እና ወደ ጥቅም ግጭት
ትስስር ውስጥ የገቡ አካላት ካሉ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ
ይገኛል፡፡

10
ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ትግሉ በመረጃ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን እንደመሆኑ መጠን ከህዝቡ
የሚቀርቡ የሙስና መረጃ በመተንተንና በማደራጀት ለፍትህ ተቋማት የማቅረብ እና የመከታተል
ሥራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ ከሕዝብ መረጃ ለመቀበል የሚያስችል የመረጃ ማእከል
በማደራጀት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛል፡፡ ከጠቋሚዎች የሚቀርቡ አቸኳይ
ሙስና መረጃዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር መፍትሔ እንድያገኙ ጥረት
እየተደረገ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ ጅምር እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም ከተሰራዉ ይልቅ ያልተሰራዉ አመዝኖ የሚታይ
ሲሆን በቀጣይ ከፍተኛ ጥረትና የተቀናጀ ርብርብ ካልተደረገ የሙስና ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየጨመረ እንዲሄድ እድል ይፈጥራል፡፡
ለእስካሁኑ የፀረ-ሙስና ትግል የሚፈለገዉን ያህል ዉጤት ያለማስመዝገብ በርካታ ምክንያቶች
የሚጠቀሱ ሲሆን የተቋማት የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራር ሥርዓት ዝርጋታ ብዙ የሚቀረዉ
በመሆኑ፣ ሕዝባችንን በፀረ-ሙስና ትግሉ በበቂ ሁኔታ ያለመሳተፍ፤ የባለድርሻ ተቋማት
የተቀናጀና የተደራጀ የጸረ-ሙስና እርምጃ አለመዉሰድ እንዲሁም የሙሰኞችን የሥነምግባርና
የሞራል መዛነፎችን በበቂ ደረጃ ያለማረም፤ ጎልተዉ የሚታዩ ክፍተቶች መሆናቸዉን ጥናቶች
ያመላክታሉ፡፡

2.2 ምቹ ሁኔታዎች
2.2.1 ሀገራዊ የፖሊቲካል ኢኮኖሚ ለዉጥ፤

ባለፉት አራት ዓመታት በሃገራችን እየተካሄደ ያለዉ የለዉጥ እንቅስቃሴ ለፀረ-ሙስና ትግል ምቹ
ሁኔታ የሚፈጥር ነዉ፡፡ መንግሥት ሙስና መከላከል ቁልፍ ተግባር ማድረጉ ለኮሚሽኑ አስቻይ
ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ አገራዊ የፖሊቲካል ኢኮኖሚ ለዉጡን ተከትለዉ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎችን
በዋናነት በግልጽነት እና በተጠያቂነት ቁልፍ መሳሪዎች ትኩረት ባደረጉት ተቋማት ለፀረሙስና
ትግሉ ጥሩ መደላድል እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ ቁርጠኛ አመራሮች በተሰማሩበት ተቋማት የጸረ-
ሙስና ትግሉ ጠንካራ መሰረት እየጣለ ነዉ፡፡ በአንጻሩ፤ ግድየለሽነት የሚታይባቸዉ፤ እኔ ሙሰኛ
እስካልሆንኩ አይመለከተኝም ብለዉ ተቋማቸዉን ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ዉስጣዊና ዉጫዊ
ጥቃት ያጋለጡት አመራሮች በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ከደንበኞቻቸዉ ከፍተኛ እሮሮ
እያጋጠማቸዉ ይገኛል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ወደአደባባይ የመዉጣት ዕድል እያገኙ
ስለሆነ፤ ለጸረ-ሙስና ትግል አሰቻይ ሁኔታ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

11
2.2.2 በማደግ ላይ ያለዉ የህብረተሰቡ የፀረሙስና ትግል

ህብረተሰቡ በሙስና አስከፊነት ዙሪያ ግንዛቤው መጨመሩና በፀረ-ሙስና ትግሉ ተጨባጭ


ተሳትፎና አስተዋፅኦ ማድረግ መጀመሩ፣የሥነምግባር ችግር እና ሙስና በህብረተሰቡ ዘንድ
አጀንዳ መሆኑ፣በአጠቃላይ የማህበረሰባችን የጠያቂነት ዝንባሌ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱ
በተለይም ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አንጻር ሙሰኞችን በማጋለጥና ኢ-ሥነምግባራዊ
ድርጊቶችን በግልጽ በመኮነን የሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ ጉልህ ነዉ፡፡

2.2.3 የደጋፊና ተባባሪ አካላት መኖር

የፀረ-ሙስና ትግል ከሚጠይቀዉ ሙያዊና የገንዘብና ቁሳዊ ሃብት አንጻር እንደሃገራችን ባሉ


ታዳጊ ሀገራት አንዱ የድክመታቸዉ ምንጭ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ይህን ከማቃለል አንጻር
በተለይም ልዩ ልዩ ዓለማቀፍ ተቋማትና ተባባሪ አካላት መኖር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት
ይታመናል፡፡

2.2.4 ቴክኖሎጂያዊ ሁኔታዎች ማደግ

ሚዲያዎች እየተስፋፉ መምጣትና እነዚህ ሚዲያዎች በሥነምግባር ግንባታ እንቅስቃሴ ላይ


የአጋዥነት ሚና ያላቸዉ መሆኑ፣ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በሥነምግባር ግንባታ
ሥራ ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወት መጀመሩ፣የህብረተሰቡ የሚዲያ አጠቃቀም ማደግ፣የማህበራዊ
ሚዲያዎች ተጠቃሚዎች መበረካት ችግሩን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት አጋዥ ሚና
ይኖረዋል፡፡

2.3 ተግዳሮቶች
2.3.1 የተደራጀ ፖሊሲ ያለመኖር

በሃገራችን ምንም እንኳ የሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን ለመቅረፍ የሚረዱ ህጎች እና ተቋማት
ቢኖሩም፤ አገራዊ የፀረ-ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ይህም ለጸረ-
ሙስና ትግል አገራዊ እና የተደራጀ አቅም በማቀናጀት የጋራ አቅጣጫ እና ግብ ይዞ ከመንቀሳቀስ
አንጻር ዉስንነት ፈጥሯል፡፡ ስለሆነም፤ ኮሚሽኑ ይህን ክፍተት ሊሞላ የሚችል አገራዊ የፀረ-
ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

2.3.2 በአንዳንድ የመንግስት አመራሮች ትኩረት ያለማግኘት

12
በአንዳንድ የመንግስት ሃላፊዎች ለሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራ የሚሰጠዉ
ትኩረት አነስተኛ ከመሆኑ አልፎ የሥነምግባር ደረጃ በሚጠበቀዉ ልክ አለመሆኑ፤ ለዚህም
በአገር ደረጃ የወረዱ እቅዶችና አቅጣጫዎች በአግባቡ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ያደርጋል፡፡

2.3.3 በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ አለመረጋገት


አገራችን ኢትዮጵያ ካጋጠማት ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመላቀቅ ባለፉት
አራት ዓመታት ትግል በማድረግ ላይ ቆይታለች፡፡ በዚህ ምክንያት መንግስት እና መላው
ህብረተሰብ በሙስና መከላከል ላይ ትኩረት እንዳያደርግ የራሱ የሆነ አስተዋፀኦ አድርገዋል፡፡
ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በሚኖርበት ጊዜ ሙሰና እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር የህዝብ
ሀብትና ንብረት ለግል ጥቅማቸው የሚያዉሉ “ከራባት ለባሽ” ሙሰኞች ይበራከታሉ፡፡

2.3.4 የኑሮ ዉድነት መጨመር


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኑሮ ውድነት በሁሉም የህብረተሰብ አካላት አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፡፡ ሙስና
እና ኑሮ ውድነት ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ሲሆኑ ለኑሮ ውድድነት መጨመር ሙስና የራሱ
አሰተዋፀኦ እንዳለው ይታመናል ፡፡ በኑሮ ውድነት መጨመር ምክንያት ሰዎች ሙስና እንደ አንድ
አማራጭ የገቢ ምንጭ የመውሰድ አዝማምያ እየታየ ሲሆን ይህም በፀረ-ሙስና ትግሉ ጥረት
ላይ የራሱ የሆነ ተፅእኖ አለው፡፡

13
ክፍል ሦስት

የፀረ-ሙስና ትግል ቀጣይ አቅጣጫዎችና የባለድርሻ አካላት ሚና

3.1 የፀረ-ሙስና ትግል ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች

ሙስና በአገራችን የሚከናወኑትን የልማት ሥራዎችን በማደናቀፍና የተቋማትን የአገልግሎት


አሠጣጥ ቀሰ በቀስ እንዲዳከሙ በማድረግ፤ የህግ የበላይነት በመሸርሻር እና በህግ ጥበቃ
የተደረገላቸውን የዲሞክራሲ እና ሰብኣዊ መብት ድንጋጌዎች እንዲጣሱ በማድረግ ሕዝባችንን
በመንግስት ያለው እምነት እንድያጣ የሚያደርግ የሁሉም የመልካም አሰተዳደር ችግሮች ቁንጮ
ነው፡፡ ይህ የመልካም አሰተዳደር ፀር የሆነውን ወንጀል በዘላቂነት ለመከላከል ሕዝባዊ መሰረት
ያለዉ፤ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አደረጃጀቶችና ባለድርሻ አካላትን በተገቢዉ ሁኔታ ያሳተፈ
የፀረ-ሙስና ትግል ሰርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ውጤታማ እና አሳታፊ የፀረ
ሙስና ትግል እንዲኖር ለማድረግ ሀገራዊ የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የትብብር እና የትስስር ሰርዓት
ተዘርግቶ ሙስና በሀገራችን ኢኮኖሚ ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን
ሁለንተናዊ ስጋት ለመቀነስ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ የተዘረጉ የአሰራር እና
የትብብር ማዕቀፎች ተግባራዊና ውጤታማ የሚሆኑት ሁሉም በየደረጃው የሚገኙ ባላድርሻ
አካላት እና ተቋማት ለህዝብ የገቡት ቃል መሰረት ሲፈፅሙ እና የተግባር ሰው ሆነው መገኘት
ሲችሉ ነው ፡፡

በመሆኑም የተጀመረውን ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ትግል ተቋማዊ አደረጃጀት እና አሰራር ላይ


ተመስረቶ እንዲከናወን፤ ዜጎች በመንግስት ባለስልጣናት እና ሰራተኞች የሚፈፀሙ ሙስናና
ብልሹ አሰራሮች በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመሰርተው እንዲያጋልጡ ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ
እንዲኖራቸው ለማድረግ እንዲሁም የተባለሹ አሰራሮችን ለማረም የሚያስችል አሰቀድሞ የሙስና
ስጋት ጥናት ላይ የተመሰረተ የቅደመ መከላከል አሰራር መዘርጋት እና የተደራጀ እና የጥቅም
ትስስር የዘረጉ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት የሚያካብቱ አካላት ፖለቲካዊ እና ህጋዊ ተጠያቂነት
የሚያረጋግጥ አሰራሮች ላይ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን ይህን ለማሳካት የሚያስችሉ የሚከተሉት
ዋና ዋና አቅጣጫዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡ አቅጣጫዎቹ ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጀው
የሚገኙ ባለድርሻ አካላት እና ዜጎች ባሳተፈ መልኩ የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

3.1.1 ተቋማዊ አደረጃጀትና አሠራር ማጠናከር

14
የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽኖች በህግ የተሰጣውን ሓላፊነት የሚወጡት በቁ የሆነ የአደረጃጀት፤
የህግ እና የአሰራር ሰርዓት ሲኖራቸው ነው፡፡ ይህ ካልሆነ እንኳን በሀገር ደረጃ የተንሰራፋውን
ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመቀነስ ይቅር ራሳቸው ለዚህ የተጋለጡ እና በአፈፃፀም ደረጃ እምነት
የሚጣልባቸው ብቁ እና ገልለተኛ ተቋም ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በህዝብ የሚሰጣቸው ክብር እና
ተአማኒነት ይቀንሳል፡፡ ብቁ እና ገለልተኛ የሆነ ተቋማዊ አደረጃጀት እና አሰራር ስርዓት
እስካልተዘረጋ ድረስ ህብረተሰቡን የሚያሳትፍ ሰፊ መሰረት ያለው የፀረ-ሙስና ትግል መፍጠር
አይቻልም ፡፡ የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን
እና በሀገራችን ሌሎች ህጎች የተሰጠውን ተቋማዊ ሓላፊነት በአግባቡ መወጣት የሚችለው
ከሙስና ተለዋዋጭ ባህሪ ጋር ተጣጥሞ የሚሄድ ጠንካራ የአደረጃጀት፤ የአሰራር፤ የፖሊሲ፤
የህግ ማዕቀፎች እና ዘመናዊ የመረጃ አሰተዳደር ስርዓት ሲኖረው ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በሁሉም
የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ተቀራራቢ የሆነ አደረጃጃት እና አሰራር ለመዘርጋት ጥረት
እየተደረገ የሚገኝ ቢሆንም የተሟላ ባለመሆኑ በቀጣይ የኮሚሽኖቹ የአሰራር ነፃነት፤ ገለልተኝነት
እና ብቁ የሆነ የሙስና መከላከል የአደረጃጀት እና አሰራር ስርዓት ከመፍጠር አኳያ የተጀመረውን
ስራ የሚያጠናክሩ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይከናወናሉ፡-

የፌዴራል፤ የክልል እና የከተማ አሰተዳደሮች ተቋማዊ ብቃት እና አሰራር ለማጠናከር


በፌዴራል የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተጀመሩ ስታንዳርዶች በሁሉም ኮሚሽኖች
ተግባራዊ እንዲሆኑ ድጋፍ እና ክትትል ይደረጋል፤
በህግ ፤ በአደረጃጃት እና አሰራር ላይ ቅንጅት በሚጎድላቸው ተግባራት ላይ የሚኖርን ክፍተት
በየጊዜው በመለየትና የክትትልና ግምገማ ሰርዓት በማጠናከር ከክልል/ከተማ አስተዳደር
የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች እና ከሚመለከታቸው አግባብነት ያላቸውን ባላድርሻ
አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ያላቋቋሙ የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የስነ ምግባርና
የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንድያቋቋሙ ሙያዊ ድጋፍና እገዛ ይደረጋል፤
ሀጋራዊ የፀረ ሙስና ትግሉ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግሩ የተጀመሩ ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች
ፀድቀው በሁሉም አካላት ተግባራዊ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፤
የመንግስት አስፈጻሚ አካላት የሥነምግባር ክትትልና የጥቅም ግጭት መከላከል ደንብ ጸድቆ
ሥራ ላይ እንዲውል ክትትል ይደረጋል፤
የኮሚሽኖች ስራ በዲጂታል የተጋዘ እንዲሆን በፌዴራል የተጀመረውን የማዘመን ስራ
በክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች በስፋት እንዲከናወን ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ይሆናል፤
15
ጠቋሚዎች እና ምስክሮች ይበልጥ ለማበረታት የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በአፋጣኝ እንዲፀደቅ
ወደ ተግባር እንዲቀየር ከሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ፤
የሀብት ምዝገባና የማሳወቅ ተግባር የዲጂታል አሠራር ሥርዓት በማልማት በፌዴራል ደረጃ
ሥራ ላይ እንዲዉል የተደረገ ሲሆን አሰራሩ ተግባራዊ በመድረጉ የመረጃ ጥራት፤ ተገቢነትና
ተደራሽነት ከመሻሻልም ባሻገር ወጪ ቆጣቢና ወረቀት አልባ ሰርዓት እንዲፈጠር ምቹ ሁኔታ
ፈጥረዋል፡፡ ይህን አሰራር በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አሰተዳደሮች ተግባራዊ እንዲሆን
ከሚመለከታቸው አካላት በቀጣይ በቅንጀት ይሰራል፤
ሙስና መከላከል የሚቻለው በተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ይህን
አሰራር ለማጠናከር የተጀመረውን ሀገራዊ የሙስና መረጃ ቋት የማደራጀትና የማዘመን ስራ
ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ ሙስና የመከላከል ስራችን በመረጃ ላይ የተመሰረተ
እንዲሆን ይደረጋል፡፡

3.1.2 የሥነምግባር እና የሞራል ዕሴቶች ግንባታ ማጠናከር

ሙስና ከጅምሩ በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚደረግ የአሰተሳሰብ ጉድለት ውጤት ነው፡፡ እንዲህ
አይነት የአሰተሳሰብና የአመለካከት ጉድለት ሲኖር መቀየር የሚቻለው ያንን አመለካከት ለመቀየር
የሚያስችል የስነምግባርና የሞራል እሴቶች ግንባታ ማከናወን ሲቻል ነው፡፡ ኮሚሽኑ በአዋጅ
ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንዱ ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ የአመለካከት ግድፈቶችን
ለመድፈን የሚያስችል የሥነምግባር እና የሞራል እሴቶችን ግንባታ በማከናወን እና ሙስና እና
ብልሹ አሰራር በጽናት የሚጠየፍ እና የሚታገል ማህበረሰብ መፍጠር ነዉ፡፡ ሙስናና ብልሹ
አሠራር ለማዳከም፤ ጠንካራ ሕዝባዊ መሰረት ያለዉ የፀረ-ሙስና ትግል ለመፍጠር በጀመሪያ
ደረጃ ስለ ሙስና እና ብልሹ አሰራር በቂ እውቀት እና ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብ መፍጠር
ያስፈልጋል፡፡ ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብ መፍጠር ለፀረ-ሙስና ትግሉ ስኬት መሰረት ነው ብሎ
መውሰድ ይቻላል፡፡

አንድ ደረቅ ወንጀል የሚሰራ ሌባ ብርሃን ባለው አካባቢ እንዳይማይቆም ወይም እንደማይሰርቅ
ሁሉ የነቃ ማህበረ ሰብ / ዜጋ ያለው ሀገር ወይም ተቋም መፍጠር ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል
ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ትልቅ አሰተዋፀኦ ይኖረዋል፡፡ ሙስኞች ሁልጊዜ የሚያስፈራቸው
የተዘረጋው የአሰራር አጥር ርዝመት እና ቁመት ብቻ ሳይሆን የህዝብ አይን እና ጆሮ ጭምር
ነው፡፡ ምክንያቱም የነቃ ማህበሰብ ወይም ህዝብ ባለበት አካበቢ ለመስረቅ አይደፍሩም፤ ቢደፍሩ
እንኳን ከህዝብ አይን እና ጆሮ ሰለማይሰወሩ ህዝቡ በቀላሉ እንዲያጋልጣቸው ብሎም በህግ

16
እንዲጠየቁ ሊያደርጋቸው ይችላል ፡፡ ሙስና ፈፅመው ሲገኙ የሚሸሸጉበት መደበቅያ ዋሻ
አያገኙም፡፡ ስለዚህ ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል የህብረተሰብ አመላከከት እና አሰተሳሰብ
መቀየር እስከተቻለ ድረስ የሙስና ጉዳት መቀነስ የሚቻል ሲሆን ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ምንም
ያህል ጠንካራ የአሰራር እና የአደረጃጀት አጥር ቢዘረጋ እንኳን ሙሰኞች የህዝብ ሀብትና ንብረት
ከመዝረፍ አያግዳቸውም፡፡

ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለውን የህብረተሰባችን ቢሂል ከኮሚሽኑ ተልዕኮና ዓላማ


ጋር አስተሳስረን ብናየው፤ ሙስና የመከላከል ስራ ትልቅ ትኩረት ካልተሰጠ የሚያደርሰው ጉዳት
ማስቀረት አሰቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ በሙስና የታመመ ሀገር እና ተቋም ማከም ከፍተኛ ወጪ
የሚጠይቅ በመሆኑ የመንግስት አመራሮች እና ሰራተኞች አውቀው ይሁን ሳይወቁ ወደ ወንጀል
እንዳይገቡ፤ አውቀው የገቡም ካሉ የጣሱት ህግ እና አሰራር እንደምያስጠይቃቸው አስቀድሞ
ማስገንዘብ እና ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በሙስና የተመዘበረ ሀብት ከተመዘበረ በኋላ ለማስመለስ
የሚወጣውን ወጪ ከመመዝበሩ በፊት ለመከላከል የምናወጣውን ወጪ ካነፃፅርን ከፍተኛ ወጪ
የሚያስወጣ ከመሆኑ በተጨማሪ አላሰፈላጊ ጊዜ እና ጉልበት እንዲባክን የሚያደርግ በመሆኑ
አስቀድሞ መካለከል የሚያስችል አሰራር መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ አንደ ኮሚሽን አመራጭ
የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ሙስና የአመለካከት ጉድለት ውጤት በመሆኑ መፍትሄው መሆን ያለበት
ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል የሚያስችል የአመለካከት ግንባታ በማከናወን ነው፡፡

በመሆኑም የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አሁን የተንሰራፋውን ሙስናና የአሰተሳሰብ ዝንፈት


ጉድለት ለመከላከል አስቀድሞ ሙስና ምን እንደሆነ በቅጡ ተረድቶ የሚታገል ማህበረሰብ እና
ዜጋ መፍጠር አሰፈላጊ በመሆኑ በቀጣይ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ትኩረት ተሰጥቶባቸው
የሚከናወኑ ይሆናሉ ፡፡

ሙስና እና ብልሹ አሰራር በብቃት ለመመከት የሚያስችል የተጀመረው ደረጃውን የጠበቀ


የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል የስልጠና አሰራር ጥራት፤ ተገቢነት እና ፍትሐዊ
ተደራሽነት ያለዉ ሁነዉ፤ በሀገርዓቀፍ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል፤
የመንግሥት ተቋማት፤ የልማት ድርጅቶችና ሕዝባዊ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች
ኃላፊነታቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ ፤ በሥነምግባር የበቁ እና ሙስና በተጨባጭ ለመከላከል
የሚያስችል ክህሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችሉ ተከታታይነት ያላቸውን ስልጠናዎች
እንዲሰጥ ይደረጋል ፤

17
ዜጎች ሙስና እና ብልሹ አሠራር የሚያመጣዉን ጉዳት የጋራ መሆኑን ተገንዘበው በፀረ-
ሙስና ትግሉ በበቂ ሁኔታ ተደራጅተው እንዲሳተፉ ለማድረግ የተጀመረውን አሰራር
ሊያጠናክሩ የሚችሉ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ በዚህም የተቋማት ተወካዮች፤ የምርመራ
ጋዜጠኞች፤ የሲቪል ማህበራት ተወካዮች፤ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች ፤የባህል
ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም የህዝብ እንደራሴዎች በፀረ-ሙስና ትግሉ በአግባቡ እንዲሳተፉ
ይደረጋል ፡፡
ዜጎች ሙስና ጎጂ መሆኑን ተገንዘብው እንድያጋልጡና በፀረ-ሙስና ትግሉ የሚጠበቅባቸውን
ተሳትፎ እንድያደርጉ ተከታታይና በሚዲያ የታገዘ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችን
በማዘጋጀት ለህዝብ ተደራሽ ይደረጋል፤
በሁሉም የመንግስት መሰሪያ ቤቶች፤ የልማት ድርጅቶችና ህዝባዊ ተቋማት ላይ የስነ
ምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች የተሟላ አደረጃጀት እና የሰው ሀይል እንዲኖራቸው
አቅምና ብቃት በማሳደግ እና አገር ዓቀፍ ህብረት በመፍጠር የፀረ- ሙስና ትግሉን የተደራጀ
እንዲሆን ይደረጋል፤
ከአገርዓቀፍ፤ ከክልልና አከባቢያዊ ሚዲያዎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር በስነ ምግባር ግንባታ፤
በሙስና እና ብልሹ አሠራር ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ላይ የግንዛቤ ማጎልበቻ
ተግባራት እንዲከናወኑ ይደረጋል ፤

3.1.3 የሙስና መከላከል ጥናትና ክትትል አሠራርን ማጠናከር


እያንዳንዱ የመንግስት አሰራር በግልፅነት እና በተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ
በተጨባጭ እና በመረጃ ላይ የተመሰረት የሙስና ስጋት ደረጃ ልየታ ስራ መከናወን አለበት፡፡
ዝንቦች የሚያንዣብቡት በአብዛኛው ማር እና ስኳር ባለበት አከባቢ ነው እንደሚባለው ሁሉ
ሙስኞችም የህግ እና አሰራር ክፍተት ያላቸው አካባቢዎች በመለየት በማንኛውም መንገድ
ለመጠቀም ሙከራ የሚያደርጉ በመሆናቸው ለሙስናና ብልሹ አሰራር ቀዳዳ የሚከፍቱ አሰራሮችን
አስቀድሞ በማጥናትና በመለየት የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮች በተጫባጭ ለመከላከል የሚያስችሉ ዘርፍ-


ተኮር ምክረ-ሀሳቦች ተግባራዊ ከመሆናቸው በፊት በመጀመሪያ ደረጃ በዘርፉ ያሉትን የሙስና
ስጋት መለየት ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል መረጃ በበቂ ሁኔታ በማሰባሰብ የስጋት
ደረጃው ላይ ተመስርቶ ተቋማት ሙስና ለመቀነስ የሚያስችል ስትራተጂ አዘጋጅተው ተግባራዊ
እንድያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ኮሚሽኑም ስትራጂው በዘርፍ እና በተቋም ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን

18
ክትትል የማድረግ ኃሃላፊነት አለበት፡፡ በዚህ መሰረት እስከ አሁን የትምህርት ዘርፍ፤ የገቢዎችና
ጉምሩክ እና የፍርድ ቤት ዘርፍ ላይ የሙስና ስጋት ጥናት ተካሂዶ በተቋማት ተግባራዊ ለማድረግ
ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ጥናት በተካሄደባቸው ዘርፎች እና
ተቋማት ላይ የሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች ለአሰላስፈላጊ የጥቅም ግጭት እና ትስስር
እንዳይጋለጡ ፤ የተጋለጡ ካሉም ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አስራር በመዘርጋት
ተጠያቂነት የማረጋገጥ ስራ ይከናወናል ፡፡ ሙስና መታገል የሚቻለው በመረጃ ላይ የተደገፈ
በመሆኑ የሚቀርቡ የሙስና መከላከል ጥቆማዎች እና መረጃዎች በአግባቡ ተደራጅተው እና
ተተንትነው ሙስናና ብልሹ አሰራር በብቃት ለመከላከል በሚያስችል መልኩ ጥቅም ላይ መዋል
አለባቸው፡፡ በአስቸካይ መልክ የሚቀርቡ ጥቆማዎችና መረጃዎች በአግባቡ ተጣርተው መፍትሄ
እንዲሰጣቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ አኳያ ኮሚሽኑ ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል የሚያስችል መረጃ እና ማስረጃ በብቃት
በማደራጀት የሚከተሉት የሙስና መከላከል ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶባቸው የሚከናወኑ
ይሆናሉ፡-

ሙስና በብቃት ለመከላከል እንዲቻል መረጃዎች በአገርዓቀፍ ደረጃ በማደራጀትና


በመተንተን ይህን ለመቀበል የሚያስችል ሀገራዊ የሙስና እና ብልሹ አሠራር የጥቆማ
መረጃ መቀበያ ሰርዓት በማደረጃትና የቀረቡ ጥቆማዎችን በመተንተን ለህዝብ ይገለፃል፤
ለሙስና መከላከል ስራ በግብዓት እንዲውሉ ይደረጋል፤
ዘርፍ-ተኮር የሙስና መከላከል ጥናት በሁሉም ዘርፎች ላይ እንዲካሄድ በማድረግና
የሙስና ስጋቶች በመለየት እና ደረጃ በመስጠት ተቋማት የሙስና መከላከል ስትራተጂ
አዘጋጅተው ተግባራዊ እንድያደርጉ እና በራሳቸው ሙስና መከላከል የሚችሉበት ሁኔታ
እንዲፈጠር ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል፤
በተመረጡ ተቋማት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ ተግባር አሰራሮች ወይም
አከባቢዎች ላይ የሙስና መከላከል የአሰራር ሰርዓት ጥናት በማካሄድ እና የማሻሻያ
ሀሳቦችን ተግባራዊ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፤
የመንግሥት ፕሮጀክቶች ከሙስና እና ብልሹ አሠራሮች ነጻ ስለመሆናቸዉ ክትትል
በማድረግ አገርዓቀፍ የባለድርሻ መድረኮችን በማካሄድ የግኝት ሪፖርት ላይ የጋራ ግንዛቤ
ይፈጠራል፡፡

19
በተቋማት አሠራር ሥርዓት ላይ የሚካሄዱ፤ ዘርፍ-ተኮር የሙስና መከላከል ስጋት ጥናት
ግኝቶች እንደምክረ-ሀሳብ በማደራጀት በተቋማት ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው
ተቋማት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
የሙስና መከላከል ጥናት በተካሄደባቸው ዘርፎች ላይ የሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች
ሀብታቸው እንዲያስመዘግቡ እና የተመዘገበው መረጃ ትክክለኝ ስለመሆኑ የማረጋገጥ ስራ
ይከናወናል፡፡ የጥቅም ግጭት ምልክቶች ሲኖሩ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ይደረጋል፤
በሀብት ምዝገባ እና ጥቅም ግጭት ልየታ ስራ ላይ ለመተባበር ፈቃደኛ ያልሆኑ
አመራሮችና ሰራተኞች ሲኖሩ አስተዳደራዊና ሕጋዊ ተጠያቂነት እንዲወሰድባቸው ክትትል
ይደረጋል፤
የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥትታት የጸረ-ሙስና ስምምነቶች የአገራችን የሕግ
አካል የተደረጉትን፤ በተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የተሰጠዉን ግብረ-መልስ ክትትል
በማድረግ አገርዓቀፍ የግንዛቤ ማጎልበቻ ዉይይት ይካሄዳል፡፡ የባለድርሻ አካላትም ትኩረት
እንዲሰጡ ክትትል ይደረጋል፤
የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ክትትል ሥራዎችን በተቀናጀ አሰራር በማከናወን የተገኙ
ዉጤቶችን በየወሩ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ የመንግሥትና የህዝብ የፀረ-ሙስና ትግል
አጋርነት እንዲረጋገጥ ይደረጋል፤
የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች ጨምሮ ዜጎች ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን
በማጋለጣቸዉ የሚደርስባቸዉን ማንኛዉንም ጥቃት በተባበረ ክንድ በመመከትና ተገቢውን
ከላላ እንዲሰጣቸው ከሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ፤

በአጠቃላይ፤ የፌደራል የሥነምግባርና የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልል እና ከተማ አስተዳደር


ኮሚሽኖች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት፤ በሕግ አዉጪ፤ በህግ አስፈጻሚ እና
በሕግ ተርጓሚ ሥር ያሉ ተቋማት ከሙስና ሥጋት ነፃ እንዲወጡ የተጠናከረ የጸረ-ሙስና ትግል
በኢትዮጵያ እንዲቀጣጠል የበኩል ሚና መጫወት ይጠበቅበታል፡፡

20
3.2 የባለድርሻ አካላት ሚና

ሙስና በሀገራት ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ


እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ሙስናና ብልሹ አሠራር በእያንዳንዱ ዜጋ ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ
ተፅዕኖ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

የሙስና ወንጀል ካለው ውስብስብነትና ልዩ ባህሪ አንፃር በአንድ ወይም በተወሰኑ ተቋማት
በሚደረግ እንቅስቃሴ ብቻ ውጤት የሚገኝበት ሳይሆን የሁሉንም አካላት የተቀናጀና የተባበረ
ትግል የሚጠይቅ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በዋናነት የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት በተለያየ መልኩ
የሚገለጽ ሚና ይኖራቸዋል፡፡

3.1.1 የፌደራል፤ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የሥነምግባና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ሚና

የፌደራል የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የፀረ-ሙስና ተቋማት ሥነምግባርን የመገንባት፣ ሙስናን


የመከላከልና የፀረ-ሙስና ትግሉን በበላይነት የማስተባበር ሀላፊነት በህግ የተሰጣቸው አካላት
ናቸው፡፡

የፀረ-ሙስና ተቋማት በህግ የተሰጣቸውን ሙስናን የመከላከል ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት


የትውልድን የሥነምግባር እና የሞራል እሴቶች መገንባት፣ በመንግስት ተቋማትና በህዝባዊ
ድርጅቶች ውስጥ የሚስተዋሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዲለዩና እንዲፈቱ ማድረግ፣ ሀብት
መመዝገብና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ በተቋማት የግልፀኝነትና የተጠያቂነት ስርዓት እንዲሰፍን
ማድረግና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትንና መላውን ህበረተሰብ የፀረ-ሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆን
ማስቻል ይኖርባቸዋል፡፡

የፀረ-ሙስና ተቋማት እራሳቸውን ከሙስናና ብልሹ አሰራር በማፅዳት ሙስናን በተግባር በመታገል
አርአያነት ያለው ተግባር ሊያከናውኑ ይገባል፡፡ ተቋማቱ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል
ረገድ እያከናወኑ ያሉት እንቅስቃሴ አሁን ካለው የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ጋር
ሲታይ ገና ብዙ የሚቀረው መሆኑን ተረድተው ሚናቸውን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣት
ሌት ተቀን ሊሰሩ ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ መንግስት ሙስናን ለመከላከል እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት
ከፍተኛ አቅም ይሆናል፡፡ በመሆኑም በተቋማት እየተንሰራፋ የመጣውን የመልካም አስተዳደር
ችግር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ በተግባር የተደገፈ ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

21
3.1.2 የዲሞክራሲ ተቋማት ሚና

በሕገ-መንግሥቱ የተቀመጠውን የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ እንዲተገበር በማድረግና


የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ጠንቅ የሆነውን ሙስናን በመታገልና በመዋጋት ረገድ
የዲሞክራሲ ተቋማት ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ሙስና በተንሰራፋበት ሀገር የዜጎች ሰብአዊና
ዲሞክራሲያዊ መብቶች በእጅጉ ይጣሳሉ፡፡ ዜጎች ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚያገኙትን
አገልግሎት በገንዘብ እንዲገዙ ይገደዳሉ፡፡

በመሆኑም የዲሞክራሲ ተቋማት የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ


በማድረግ፣ ዜጎች መብታቸውን በገንዘብ እንዳይገዙ፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርሆዎች
እንዲከበሩ በማድረግ፣ ከሁሉም በፊት ደግሞ የዲሞክራሲ ተቋማት ራሳቸውን ከሙስናና ብልሹ
አሰራር በማፅዳት ሙስና የሚያስከትለውን የመልካም አስተዳደር ችግር በፅናት በመታገል
ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ ተቋማቱ ሚናቸውን በአግባቡ ይወጡ ዘንድ ደግሞ ከሌሎች የፀረ-
ሙስና ተዋንያን ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ከቃላት ባለፈ በተግባር
ሊገለፅ ይገባል፡፡

3.1.3 የፍትህ አካላት ሚና

የፍትህ አካላት የግልፅነትና የተጠያቂነት ስርዓት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ


የሚሰሩ አካላት ናቸው፡፡ በፀረ-ሙስና ትግሉ ውስጥ የእነዚህ አካላት ሚና የጎላ ነው፡፡ የፍትህ
አካላት ከፀረ-ሙስና ተቋማት፣ ከዜጎች፣ ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎች የሚያገኟቸውን መረጃዎችና
ጥቆማዎች መሠረት በማድረግ በሙስና ወንጀሎች ላይ ምርመራ የማድረግ፣ ክስ የመመስረት፣
የማስቀጣትና በሙስና ወንጀል የተዘረፉ ንብረቶችን የማስመለስ ሀላፊነት የተሰጣቸው አካላት
ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዜጎች ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረት ለተለያዩ
ጥቃቶች እንዳይጋለጡ ህጉ በሚፈቅደዉ መሰረት ተገቢዉን ከለላና ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ
ሥራን ትኩረት ሰጥተዉ ማከናወን ይኖርባቸዋል፡፡

የፍትህ ተቋማት ከፀረ-ሙስና ተቋማትም ሆነ ከሌሎች አካላት ያገኙት መረጃ ወይም የተቀበሉት
ጥቆማ ያለበትን ደረጃ በየጊዜው የማሳወቅ ሲጠናቀቅም ለህብረተሰቡና ለፀረ-ሙስና ተቋማት
ሪፖርት የማድረግ ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ጉዳይ በራሱ ለሙስናና ብልሹ
አሰራር የሚያጋልጥ እንደመሆኑ ይህ ተግባር በከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ጥራትና በላቀ ሥነምግባር

22
መካሄድ ያለበት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ተቋማቱ ራሳቸውን ከሙስናና ብልሹ አሠራር በማንፃትና
ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት በመስራት ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል፡፡

3.1.4 የመንግስት ተቋማት፣ ህዝባዊ ድርጅቶችና አመራሮች ሚና

በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት የልማት እና ህዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ የመልካም


አስተዳደር ችግሮች እየተንሰራፋ መምጣታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ የፌደራል የሥነምግባር
እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያስጠናው 3ኛው የሙስና ቅኝት ጥናት ላይ እንደተመለከተው ሙስና
ሦስተኛው የሀገሪቱ አንገብጋቢ ችግር ሆኗል፡፡ ከዚህ በፊት በተጠናው 2ኛው የሙስና ቅኝት
ጥናት ላይ ሙስና በ7ኛ ደረጃ ላይ ነበር የተቀመጠው፡፡ ይህም ሙስናና ብልሹ አሰራር ከጊዜ ወደ
ጊዜ እየሰፋ መምጣቱን አመላካች ነው፡፡

በብዙ የሀገራችን ተቋማት ውስጥ ለዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማግኘት አስቸጋሪና እንግልት
የበዛበት ሆኗል፡፡ በዚህ ምክንያት ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት መብታቸውን በገንዘብ ለመግዛት
የተገደዱበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህም የተለመደና የዕለት ተዕለት ተግባር እየሆነ መምጣቱን
ይስተዋላል፡፡

ይህን ችግር በመቅረፍ በኩል ተቋማት ከፍተኛ ስራ ይጠብቃቸዋል፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት


በመገንዘብ በየተቋማቱ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች የተደራጁ ቢሆንም በሁሉም
ተቋማት ተመሳሳይና ወጥ የሆነ እንቅስቃሴ እየተደረገ አይደለም፡፡ የተሻለ ድጋፍና ክትትል
የሚያደርጉ አመራሮች ባሉበት ሥራው በተነፃፃሪነት በተሻለ ሁኔታ እየተሰራ ሲገኝ ይህ
ባለሆነባቸው ተቋማት ደግሞ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመታገል ያለው ተነሳሽነት የተዳከመ
ነው፡፡

ስለሆነም እነዚህ ተቋማት በየተቋማቸው ያለውን የሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች በመለየትና
በመከላከል በተቋማት ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታት የተሰጣቸውን ተልዕኮ
መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ የየተቋማቱ አመራሮችም ይህን ተረድተው ለፀረ-ሙስና ትግሉ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ ላላቸው የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች ከፍተኛ ድጋፍ ክትትል በማድረግ
ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እንዲወጣ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

23
3.1.5 የሲቪክ ማህበራት ሚና

በዓለማችን ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ፣ የላቀ
ተሳትፎና ኃላፊነት ካላቸው አካላት መካከል የሲቪክ ማኅበራት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው።
ሕዝብን ወክለው በመንግሥት ተቋማት አሠራር ውስጥ እንዲሁም ሕገመንግሥቱ ያስቀመጠውን
የግልጽነትና የተጠያቂነት መርሕ ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የሚስተዋሉ ግድፈቶች እንዲታረሙ
ሕዝብን በማንቃትና በማሰለፍ በሕጋዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ የማድረግ አቅማቸው ከጊዜ
ወደ ጊዜ ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ በመሆኑ በዚህ ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው።

ሲቪክ ማኅበራት፣ መሻሻል ያለባቸው ሕጎች እንዲሻሻሉ፣ አስፈላጊ ፖሊሲዎች እንዲቀረጹ፤


የሙስናና ብልሹ አሠራር ምንጭና ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች እንዲስተካከሉ በማድረግ፣ ማኅበራዊና
ኢኮኖሚዊ ፍትሕ እንዲሰፍን የማድረግ አቅማቸው ከፍተኛ ነው።

ስለዚህ ሲቪክ ማኅበራት የግልጽነትና ተጠያቂነት መርሆ ጠላት የሆነውን ሙስናን በመከላከል
ረገድ ከመንግሥትና ከግል ተቋማት ባልተናነሰ ሁኔታ አቅማቸውና ሚናቸው ሊጎለብት ይገባል።

ሲቪክ ማህበራት ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት ረገድ ትልቅ ሚና ቢኖራቸውም በሀገራችን
የሚገኙ የሲቪክ ማህበራት ይህን ሚናቸውን የሚመጥን እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ለማለት
አያስደፍርም፡፡

በመሆኑም ሲቪክ ማህበራት በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ ድርሻ በመገንዝብ ከፀረ-
ሙስና ተቋማትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

3.1.6 የኃይማኖት ተቋማት ሚና

ኃይማኖት፣ በሰዎች ባሕርይ ላይ ተጽእኖ የማሳደር ከፍተኛ አቅም አለው። የእምነት ተቋማት
ኃይማኖታዊ እሴቶችንና ሕጎችን በማስተማር ምእመናንን በሥነምግባር የመገንባት አቅም
እንዳላቸው ይታመናል። ምዕመናን ወደሚያመልኩት ተቋም የሚመጡት በፈቃዳቸው ነው፡፡
በእምነታቸው ውስጥ ያሉ እሴቶችንም ፈቅደው ይጠብቋቸዋል፡፡ ይህ ትውልድን በመልካም ሥነ-
ምግባር ለመቅረጽና የሥነምግባር ወድቀትን በማቃናት ሙስናን ለመዋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ
አለው፡፡

24
በሌላ በኩል የኃይማኖት መሪዎችና አባቶች በሙስና ከተዘፈቁ በእምነቱ ተከታዮችና በመላው
ኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነትና ተደማጭነትን ያጣሉ። የእነሱ እምነት ተቀባይነት ማጣት፣
የፀረሙስና ትግሉን በከፍተኛ ደረጃ ያጨናግፈዋል። ስለዚህ፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ሙስናን
የመከላከል ኃላፊነታቸውን የመወጣት ጥረታቸውን መጀመር ያለባቸው ራሳቸውን ከሙስናና
ብልሹ አሠራር በማጽዳት ነው።

ሥነምግባርና ኃይማኖት የተቆራኙ መሆናቸው ይታወቃል። በሀገራችን አብዛኛው ህብረተሰብ


የአንዱ ወይም የሌላው እምነት ተከታይ ነው። ምዕመናን በሚሰማሩበት የሥራ መስክና
በሚያከናውኗቸው ተግባራት ሁሉ የኃይማኖታቸው ገንቢ ተጽዕኖና የአስተምሮ ፍሬ መንጸባረቅ
አለበት። ይህን ማስረጽ ያለባቸው ደግሞ ተቋማቱ ናቸው። ተቋማቱ ተከታዮቻቸው የያዙትን
እሴት ወደሚሠሩበት ተቋም ይዘው እንዲሔዱ ማድረግ ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል፡፡

የኃይማኖት ተቋማት በመደበኛ የእምነት ጉባኤዎችና ስብከቶች ስለሙስና አስከፊነት በማስተማር


ኃላፊነታቸውን ቢወጡ ለውጥ እንደሚመጣ የአንዳንድ ሀገራት ተመክራዎች ያመለክታሉ።
በመሆኑም በሀገራችን የሚገኙ የሀይማኖት ተቋማት በፀረ-ሙስና ትግሉ ውስጥ ያላቸውን የገዘፈ
ሚና ተረድተው በትጋትና በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል፡፡

3.1.7 የመገናኛ ብዙኃን ሚና

በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው ባለድርሻ አካላት መካከል መገናኛ ብዙኃን
ወይም ሚዲያ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ያለሚዲያ ተሳትፎ የፀረ-ሙስና ትግል እውን ማድረግ
አዳጋች ነዉ፡፡ ሚዲያ አራተኛው የዴሞክራሲ አምድ (pillar) ወይም አራተኛው መንግስት
እየተባለ የሚጠራው ያለምክንያት አይደለም፡፡ ምክንያቱም መገናኛ ብዙኃን ማህበረሰብን ለጋራ
ዓላማ የማስተባበር፣ የጋራ እሴቶችን የማጎልበትና የማስፋፋት፣ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም
የመስራት እንዲሁም ሀገራዊ መግባባት የመፍጠር ተልዕኮ ያላው ነው፡፡ ሚዲያ ልዩነቶችን
በውይይት የመፍታት ባህል እንዲበለፅግ፣ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለፍትህ ተፃራሪ
የሆኑ እንደ ሙስናና ብልሹ አሰራር ያሉ ተግባራትን የማጋለጥና የመዋጋት ሀላፊነትም አለው፡፡
መገናኛ ብዙኃን፣ ህግ አውጪው አካል፣ ተርጓሚውና አስፈፃሚ አካላት ሥራቸውን በተገቢው
መንገድ መስራታቸውን በመከታተል የመንግስት አሰራር በግልፅኝነትና ተጠያቂነት መርህ ላይ
ተመስርቶ እንዲፈጸም የህዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ የማገልገል ከፍተኛ ሀላፊነትም አለው፡፡

25
ሚዲያ በፀረ-ሙስና ትግሉ ውስጥ የጎላ ሚና ቢኖረውም በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ይህን
ሚናውን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ በዕለት ተዕለት የስብሰባና የሁነት ዘገባዎች
ላይ ተጠምዶ ሲውል ይስተዋላል፡፡ ሚዲያ በሥነምግባር ግንባታና በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ
ያለውን ከፍተኛ ሚና መወጣት ይኖርበታል፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ከኮሚሽኑና እና ከሌሎች
ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራት ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨመሪም ራሱን
ከሙስናና ብልሹ አሰራር ማፅዳትም ከሚዲያ አካላት የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡

3.1.8 የቤተሰብ ሚና

የትውልድ መሰረት ቤተሰብ ነው፡፡ በመሆኑም ቤተሰብ ትውልድን በመልካም ሥነምግባር


ለመገንባት ትልቅ ኃላፊነት ካላቸው ማህበራዊ ተቋማት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ልጆች
ወደ ማህበረሰቡ የሚቀላቀሉት ከቤተሰብ የገነቡትን እሴት ይዘው ነው፡፡ ዛሬ በአደባባይ
የሚያሸልሙም ሆነ የሚያስወግዙ ተግባሮች የአስተዳደግ ድምር ውጤቶች ናቸው፡፡ የዛሬዎቹ
ህፃናት የነገዎቹ ሀገር ተረካቢዎች በሥነምግባራቸው እንዲመሰገኑ ወይም እንዲወገዙ የቤተሰብ
ድርሻ ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ ዛሬ የመረጃ ዘመን እንደመሆኑ ልዩ ልዩ መረጃዎች በተለያዩ
መንገዶች ሊገኙ ይችላሉ፡፡ መልካም ሥነምግባር የማግኛ ዋነኛ መንገድ ግን ቤተሰብ ነው፡፡
ስለዚህ ቤተሰብ በመልካም ሥነምግባር ለልጆች የቅርብ አርአያ በመሆን፣ ቃልን በተግባር
በመተርጎም፣ ልጆች ጥሩውን ከመጥፎው እንዲለዩ በመምከርና በማስተማር፣ በጥሩ እሴቶች
ጎልብተው እንዲያድጉ በመርዳት በመልካም ሥነምግባር የተገነባ ትውልድ የመቅረጽ ኃላፊነትን
መወጣት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሲሆን በአቋራጭ ከመክበር ይልቅ ሰርቶ የመለወጥ በሙስና ከመዘፈቅ
ይልቅ የመልካም ሥነምግባር ባለቤት የመሆን አመለካከት ይዳብራል፤ በሂደትም ለራሱና ለሀገሩ
ታማኝ የሆነ ትውልድ ማፍራት ይቻላል፡፡

3.1.9 ትምህርት ተቋማት ሚና

ከቤተሰብ ቀጥሎ ትውልድን በመልካም ሥነምግባር በመገንባት ሙስናን የማይሸከም ትውልድ


በመፍጠር ሂደት ትልቅ ኃላፊነት ያለባቸው የትምህርት ተቋማት ናቸው፡፡ የትምህርት ተቋማት
ሥነምግባርን በመገንባትና ሙስናን በመከላከል ረገድ ድርብ ሀላፊነት አለባቸው፡፡ በአንድ በኩል
እንደማንኛውም ተቋም ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመፈተሸ በተቋማቸው
26
ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የመፍታት ሀላፊነት ሲኖርባቸው በሌላ በኩል የነገ ሀገር
ተረካቢዎችን በመልካም ሥነምግባር በማነፅ ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ የማፍራት ተልዕኮም
አላቸው፡፡

ከዚህ አንፃር የመምህራን ድርሻ ገዝፎ ይታያል፡፡ መምህራን ከሚሰጡት የትምህርት እውቀት
ባሻገር በሥነምግባራቸው አርአያና የተግባር ሰው ሊሆኑ ይገባል፡፡ ከተጻፈው ሥርዓተ ትምህርት
ባሻገር መምህራን የሚያደርጉት ተግባርና እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ሌላው በተማሪዎች የሚነበብ
ድብቁ ሥርዓተ ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህ ተማሪዎች የሚያነቡት ሁለቱንም ሥርዓተ ትምህርቶች
ነውና መምህራን በመልካም ሥነምግባርም ጭምር አርአያ ሊሆኑላቸው ይገባል፡፡ ዛሬ ለተማሪዎቹ
አርዓያ መሆን ያልቻለ መምህር ነገ በተለያዩ ተቋማት ከሚሰሩ ተማሪዎቹ መልካም ሥነምግባርን
ወይም ከሙስና የጸዳ አገልግሎትን መጠበቅ የለበትም፡፡ ከመምህሩ ሌላ በትምህርት ተቋማት
ውስጥ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር ሠራተኞች በሚሰጡት መልካም አገልግሎት ለተማሪዎቻቸው
አርአያ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ይህንን በማድረግም በመልካም ሥነምግባር የተገነባ ትውልድን የመገንባት
ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

3.1.10 የማህበራዊ ተቋማት ሚና (ዕድር እና ዕቁብ)

በማህበረሰብ ውስጥ ጠንካራ የሆነ ማህበራዊ ተቋም መኖር የትውልድ መሠረት ከሆነው ቤተሰብ
የወጣውን የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ሥነምግባር ጠብቆ ለማቆየት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
በየአካባቢው መልካም ሥነምግባርን የሚያበረታቱ፣ ስርቆትን፣ዘረፋን፣ በአቋራጭ
መበልፀግን፣የራስ ያልሆነን ነገር መመኘትን የሚያወግዙ በርካታ ባህሎች በሀገራችን አሉን፡፡
እነዚህን ባህሎች ሳይበረዙ መጠበቅ የሚቻለው በእነዚህ ጠንካራ ማህበራዊ ተቋማት አማካኝነት
ነው፡፡ በሀገራችን በሁሉም አካባቢዎች ከሚገኙ ማህበራዊ ተቋማት መካከል እንደዕድር፣ ዕቁብና
ማህበር ያሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የእነዚህ ማህበራዊ ተቋማት ዋነኛ ዓለማ ህብረተሰቡ ያለውን
ጠንካራ እሴት ጠብቆ ማቆየት ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ተቋማት መልካም ሥነምግባርን
በማጎልበትና ሙስናን በመከላከል ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ ለነገ የማይባል ተግባር
ስለሆነ ከነዚህ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት ይገባል፡፡

27
ማጠቃለያ

በሀገራችን ሙስናና ብልሹ አሠራር ሥር እየሰደደ ለመምጣቱ የህብረተሰቡ እሮሮና በዘርፉ


የተደረጉ ጥናቶች አመላካች ናቸው፡፡ ይህ ተግዳሮት በዚሁ ከቀጠለ የምናልመው የዕድገትና
የብልፅግና ጉዞን ያደናቅፋል፡፡ በመሆኑም እንደከዚህ ቀደሙ በተገኘው መድረክ ሁሉ የሙስናን
አስከፊነት፣የሚያደርሰውን ጉዳት በመደስኮር ብቻ ይህን ነቀርሣ የሆነዉን የመልካም አስተዳደር
ችግር ማስወገድ አይቻልም፡፡ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀረ-ሙስና ትግሉ ከንግግር ባለፈ
ተግባራዊ እርምጃን ይሻል፡፡ በመሆኑም በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው
የተገለፁ አካላት በሙሉ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ በአጠቃላይ፤ ቀጣዩ የኢትየጵያ የፀረ-
ሙስና ትግል ምዕራፍ ሕዝባዊ መሰረት ያለዉ፤ የባድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ያረጋገጠ፤ መረጃና
ዕዉቀት ላይ የተመሰረተ ከንግግር ተሻግሮ በተግባር ለዉጥ ያሳየ ሊሆን ይገባል፡፡ ሙስና እና
ብልሹ አሠራር መለየት፤ ማጋለጥ እና ማረም እንዲሁም የሥነምባርና የሞራል እሴቶች ግንባታ
ጎንለጎን ተያይዘዉ ሊሰሩ ይገባል፡፡ ይህን የዕድገት፤ የልማትና የመልካም አስተዳደር ነቀርሳ
የሆነዉን ሙስና ከሥር መሰረቱ ለመንቀል ሁሉም እንደየሚናዉ ቁርጠኛ መሆን ይገባል፡፡

ሙስናን መታገል በተግባር!

28

You might also like