Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

በወቅቱ በነበረው ጦርነት

[  ] በሆስፒታሉ የተፈጠረውን የቦታ ጥበት ለመቅረፍ በተደረገ ርብርብ ላይ በመሳተፍ ድንኳን መትከል ፣ አልጋ ማስገባት
፣ ፍራሽ ፣ ብርድ ልብስ አንሶላ ወዘተ ከስቶር እንዲሁም ከመኪና አውርዶ በማምጣት ለቁስለኞች የሚሆኑ መተኛ
ክፍሎችን ማዘጋጀት

[  ] የተጎዱ ቁስለኞችን ትሪያዥ በማደራጀት ከመኪናና ከአምቡላንስ መቀበል ፣ ማውረድ ፣ ኢሜጂንግ መውሰድ እና
ማስነሳት ፣ የተለያዩ የመጀመሪያ እርዳታዎችን መስጠትና ማገዝ ፣ ወደ የሚተኙበት ክፍል መውሰድ ፣ በአስቸኳይ ወደ
ቀዶ ጥገና ክፍል መግባት የለባቸውን ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል በፍጥነት ማድረስ ወዘተ

[  ] ከዚህም በተጨማሪ በቦታ ጥበት ወይም የተሻለ ህክምና እንዲሁም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ የሚያስፈልጋቸው
ቁስለኞች ተለይተው ወደ የተለያዪ የጤና ተቋማት እንዲሁም ማቆያ ቦታዎች ሲላኩ ከአምቡላስ ጋር አብሮ በመሄድ 
ተገቢው ቦታ ማስገባት

[  ] በሆስፒታሉ የነበረው የሰው ሃይል እና የባለሙያ ችግር ሆስፒታሉ በዚህ ወሳኝ ጊዜ አገልግሎት ከመስጠት
እንዳያግደው በተፈለገው ቦታ ሁሉ በመግባት ቁስለኞችን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ፣ wound dressing መስራት ፣ ገላ
ማጠብ ፣ ልብስ ማልበስ እና መቀየር ወዘተ በአጠቃላይ bed side care ላይ መደረግ የሚችሉ ነገሮችን በግልም ሆነ 
ከባለሙያዎች ጋር በመሆን የነበረውን ክፍተት መሸፈን

[  ] ከሚመጡ ቁስለኞች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች በጉዞ ላይ የሚያርፉ ቁስለኞችን የሰው ሀይል እጥረት በነበረ ሰዓት
ተረባርቦ ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመተባበር አስከሬናቸውን በማውረድ ፣ በማጠብ እና በመገነዝ

[ ] በየቀኑ የሚገቡትን ቁስለኞች ስም ከነ ሙሉ መረጃ በመመዝገብ ለሆስፒታሉ ሪከርድ በማቅረብ ፣ ለውጦችን


በመከታተል እና በማሳወቅ በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ ባሉ የፅሁፍ እና ምዝገባ ስራዎች ላይ ከሆስፒታሉ staff ጋር
በመሆን በመስራት

[  ] በአንድ ወቅትም በጊቢው ከነበሩ ሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን በተሰጠ ግዳጅ በከሚሴ ግንባር የነበሩ የወገን ጦር
ቁስለኞችን በማውጣት ወደ ተሰጠው ቦታ በደህንነት ማድረስ እና ሌሎች መሰል ስራዎችን በሞራል እና በታላቅ
ተነሳሽነት ሲሰራ ቆይቷል

You might also like