Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

በ 2023/2024 በሰሚር ሰብሳቢነት የሚከናወን እቁብ መመሪያ እና መተዳደሪያ

ደንብ

1. የሰብሳቢ ሃላፊነት

1.1. በወቅቱ ከእቁብተኞች ገንዘብ መሰብሰብ።

1.2. በወቅቱ ለእቁብተኛው እጣ ማውጣት።

1.3. በወቅቱ እጣው ለደረሰው ግለሰብ ሙሉ የገንዘብ መጠን መክፈል።

1.4. የእቁብተኞችን ጥያቄ እና ቅሬታ ማስተናገድ።

2. የእቁብተኞች ሃላፊነት

2.1. የገንዘቡን መጠን ወር በገባ (እ.ኤ.አ) እስከ 3 ተኛ ቀን የመክፈል ግዴታ

አለባቸው።

2.2. በወቅቱ ያልተቆራረጠ ገንዘብ ማስገባት አለባቸው።

2.3. የገንዘቡን መጠን በ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ገንዘብ ምንዛሬ 2000 Aed

ወይም ባለው የኢትዮጵያ ምንዛሬ ማስገባት አለባቸው።

2.4.ቁብ እጣው የደረሰው ያለበትን አገር መግባቢያ ቼክ ግዴታ አለበጥ።


የእቁብተኞች መመሪያ ህግ

1. እቁቡን ‘’ችግር ላይ ስለሆንኩ ለኔ ቅድሚያ’’ ብሎ መጠየቅ ፈጽሞ የተከለከለ

ነው።

2. እስከተጠከሰው ቀን ድረስ ብር አለማስገባት እጣው ውስጥ አያሳትፍም።

3. እቁብ እጣው የሚወጣው ወር በገባ በ 4 ተኛው ቀን ሲሆን ለእጣው ባለቤት

በ 5 ተኛው ቀን ገንዘቡ ገቢ ይደረጋል።

ለምሳሌ JUN 1 – 3 (መሰብሰቢያ ቀን)

JUN 4 (እጣ የሚወጣበት ቀን)

JUN 5 (ለደረሰው የሚሰጥበት ቀን)

4. እጣው የሚወጣው በ Zoom Application ሲሆን LIVE ገብቶ መከታተል

ይቻላል።

5. እጣው የሚወጣው 4 ተኛ ቀን 8 PM ላይ ይሆናል ፤ ለተሳታፊዎች ሊንክ ይላካል።

6. እጣው ሳይደርስ ሰው ቢያቋርጥ ብሩ መጨረሻ ላይ ተጥሎ ይሰጠዋል።

7. እጣውን ከወሰደ በኋላ ማቋርጥ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።


8. እቁቡ እየተካሄደ ድንገተኛ አደጋ ለምሳሌ ጦርነት፣የመሬት

መንቀጥቀጥ፣የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም እቁቡ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ

የሚቀጥል ይሆናል።

9. አያድርገውና እቁብተኛው ህይወቱ ቢያልፍ ወይም የአእምሮ መሳት

ቢያጋጥመው ቤተሰቡን እቁቡን ህጉንና መመሪያውን ተከትሎ እንድያስፈጽም

ከስር በፊርማ ያረጋግጣል።

10. ፊርማ_______________________

ስም _______________________

11. የአደጋ ጊዜ ተጠሪ የሆነ የቤተሰብ

ስም ______________________

ፊርማ ______________________

You might also like