Doc1 - For Merge

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የመንግሥታቱ ድርጅት የኢትዮጵያን ጥያቄ እንዳይቀበል የመብት ተሟጋቾች ጠየቁ።

ዓለም አቀፍ ሲቪል ማኅበራት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት
ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶች ላይ የሚደረገውን ምርመራ እንዲቋረጥ የኢትዮጵያ
መንግሥት የሚያደርገውን ጥረትን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት
አባላት እንዳይቀበሉት ጥሪ አቀረቡ።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋችን ጨምሮ ሌሎችም ከስድሳ በላይ
የሚሆኑት ተቋማት ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣
ኢትዮጵያ በተመድ የሚከናወነው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ እንዲቋረጥ ለማድረግ
የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ ማቀዷ አሳስቦናል ብለዋል።
ይህ የሲቪል ማኅበራቱ እና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥሪ የተሰማው የተባበሩት
መንግሥታ t እ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በጄኔቭ ለአምስት ሳምንታት
በሚያካሂደው ስብሰባው ስለሰሜን ኢትዮጵያው ጉዳይ እንደሚወያይ ከተገለጸ በኋላ ነው።
ሮይተርስ የዜና ወኪልም እንዲሁ ኢትዮጵያ በድርጅቱ የተሰየመው ኮሚሽን ሥራ እንዲቋረጥ
ለምታቀርበው የውሳኔ ሐሳብ ድጋፍ እያሰባሰበች ስለመሆኑ አምስት ዲፕሎማቶች ነገረውኛል
ሲል ዘግቧል።

ኢትዮጵያ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ለሁለት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት ተፈጽሟል የተባሉ
የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር የተሰየመውን የተባባሩት መንግሥታት የሰብዓዊ
መብቶች ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን ከምሥረታው ጀምሮ ስትቃወም ቆይታለች።
ኢትዮጵያ የባለሙያዎቹ አሰያየም ፖለቲካዊ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ነው በማለት ኮሚሽኑ
በጀት እንዳያገኝም ጥረት አድርጋ ነበር።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት አዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ ምክትል
ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አገራቸው ኢትዮጵያ ‘ትክክለኛ ውክልና’ የለውም
የምትለው ኮሚሽን እንዲበተን የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ለኅብረቱ አባላት ጥሪ
አቅርበው ነበር።
ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥሪ ያቀረቡት ዓለም አቀፍ ሲቪል ማኅበራት እና የመብት
ተሟጋች ግን የኢትዮጵያ ጥረት ‘ያልተጠበቀ’ እና ዓለም አቀፍ ምርመራን ለማስቀረት
የሚደረግ ጥረት ነው ብለዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች ከጦር ወንጀል ጋር
የሚስተካከሉ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለመፈጸማቸው የተባበሩት መንግሥታት
ድርጅት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎችም ባወጧቸው
ሪፖርቶች ማሳወቃቸው ይታወሳል።
የሰላማዊ ሰዎች ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም እና ሌሎች ከፍተኛ
የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዚህ ጦርነት የተፈጸሙ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ጥሰቶች
ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ ነበር።
ሦስት አባላት ያሉት ኮሚሽን ምርመራውን ከጀመረ በኋላ በጦርነቱ የተሳተፉ ተዋጊዎች የጦር
ወንጀል እና ሌሎች የመብት ጥሰቶችን ስለመፈጸማቸው የሚያሳምኑ መረጃዎችን ማግኘቱን
ገልጿል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በመላው ዓለም የሰብዓዊ መብት ጥበቃ
የማድረግ ኃላፊነት ያለባቸው የ 47 አገራት ስብስብ ነው።
ቻይና መሳሪያ ለሩሲያ ልትሰጥ ትችላለች ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ያለችውን
ጦርነት ለመደገፍ ቻይና ጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ለመስጠት እያጤነች ነው አሉ።
ብሊንከን ለሲቢኤስ ሲናገሩ የቻይና ኩባንያዎች ወታደራዊ ያልሆኑ ድጋፎችን ቀድሞውኑ
ለሩሲያ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸው፤ አሁን ላይ አሜሪካ ያላት መረጃ ቤጂንግ ወታደራዊ
ድጋፍ ልታደርግ እንደምትችል ነው ብለዋል።
ቻይና የጦር መሳሪያ ድጋፉን ለሞስኮ የምታደርግ ከሆነ የሚጠብቃት ምላሽ አደገኛ ይሆናል
ሲሉ ብሊንከን አስጠንቅቀዋል።
ቻይና በበኩሏ ከሞስኮ ወታደራዊ ድጋፍ ቀርቦላታል የሚሉ ሪፖርቶችን አጣጥላለች። የአገሪቱ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤጂንግ ከሞስኮ ጋር ባላት ግንኙነት ምክንያት ከአሜሪካ
‘ማስፈራሪያዎችን’ እንደማትቀበል አስታውቋል።
ብሊንከን ግን ቤጂንግ ድጋፉን የምታደርግ ከሆነ ለአሜሪካ እና ቻይና ግንኙነት ከባድ ችግር
ይሆናል ብለዋል።
የፕሬዝዳንት ቭላደሚር ፑቲን አጋር የሆኑት ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በጉዳዩ ላይ እስካሁን
ያሉት ነገር የለም። ፕሬዝዳንቱ ለሰላም ጥሪ ካቀረቡ ወዲህ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አስተያየት
ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ብሊንከን ጀርመን ሚዩኒክ በተካሄደው የደኅንነት ኮንፍረንስ ላይ ከቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማት


ጋር ከተገናኙ በኋላ ቻይና ወታደራዊ ድጋፍ ለሩሲያ ልታደርግ መቻሏ ‘እጅጉን አሳስቦናል’
ብለዋል።
“እስከ ዛሬ የቻይና ኩባንያዎች ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ጦርነት ወታደራዊ ያልሆኑ
ድጋፎችን ሲያደርጉ ነበር። አሳሳቢ የሆነው አሁን ባለን መረጃ መሠረት ወታደራዊ ድጋፎችን
ስለማድረግ እያጤኑ ነው” ብለዋል።
ብሊንከን በቃለ ምልልሳቸው በቻይና ኩባንያዎች እና በቤጂንግ አስተዳደር መካከል ምንም
ልዩነት የለም ብለዋል።
ከዚህ ቀደም አሜሪካ የዩክሬንን የሳተላይት ምስል ዋግነር ለተሰኘው የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደራዊ
ቡድን ሰጥቷል ባለችው የቻይና ኩባንያ ላይ ማዕቀብ ጥላ ነበር።
ብሊንከን ቻይና ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እያጤነች ነው ከማለታቸው በተጨማሪ
ምዕራባውያን ሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ የተፈለገውን ውጤት እንዳያመጣ እያደረገች ነው
ሲሉ ቻይናን ከሰዋል።
ሩሲያ ዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ ምዕራባውያን አገራት የሞስኮን ምጣኔ ሃብት
ለማዳከም በርካታ ማዕቀቦችን መጣላቸው ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ቤጂንግ ከሞስኮ ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ እያደገ በመሄዱ የምዕራባውያን
ፍላጎት ተፈጻሚ እንዳይሆን እያደረገች ነው የሚል ወቀሳ ቻይና ላይ ይነሳል።
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት ለዩክሬን ታንክን ጨምሮ ጦር
መሳሪያዎችን እና ተተኳሾችን ሲልኩ ቆይተዋል።
ብሊንከን ይህን ይበሉ እንጂ በሚዩኒኩ የደኅንት ኮንፍረንስ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የቻይናው
ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ አገራቸው ጦርነቱን በተመለከተ ‘ዳር ቆማ አልተመለከተችም’
እንዲሁም ለጦርነቱ ተሳታፊዎች ድጋፍ በማድረግ ‘እሳቱ ላይ ቤንዚን አላርከፈከፈችም’ ሲሉ
ተናግረዋል።
ዋንግ ጦርነቱን ለማቆም በተለይ ደግሞ በአውሮፓ የሚገኙ ወዳጆቻችን ምን አይነት ጥረት
ማድረግ እንዳለባቸው በጥሞና ማጤን አለባቸው ብለዋል።
የቻይናው ከፍተኛ ዲፕሎማት “ድርድሩ እንዳይሳካ ወይም ጦርነቱ በፍጥነት እንዳያልቅ
የሚፈልጉ አንዳንድ ኃይሎች አሉ” ብለዋል።

You might also like