Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ከወደ ሃገረ ቻይና ተነስቶ ከመጣው የስራ አጋራችን ጋር በስራ ጉዳይ ስናወጋ ከቆየን በሁዋላ ቢሮአችንን ለቆ

ለመሄድ ተነሳ።ከተሰነባበትን በሁዋላ ወደ ሆቴሉ የሚወስደውን ታክሲ ለመጥራት የስልክ መተግበርያውን


ለመጠቀም ሲሞከር እንግዳ ተቀባይነታችን ከአባቶቻችን የወረስነው ነው የሚል የሃገርን ገጽታ የመገንባት
ወኔን ሰንቄ ለምን እኔ አላደርስህም? የት ነው ሆቴል የያዝከው በማለት አከታትዬ ጠየቅኩት።ካፒታል ሆቴል
እንደያዘ ነገረኝ።ከቢሮዬ ብዙም አይርቅም ቢያንስ 10 ደቂቃ ያክል ቢወስድብኝ ነው በማለት ቶሎ የመመለስ
እቅድ ይዤ ጉዞ ጀመርን።በጉዞአችን መሃል" ግዜ ካለህ ለምን እራት አልጋብዝህም?" በማለት ጥያቄ
አቀረበልኝ።ቶሎ የመመለስ እቅድ የያዝኩ ቢሆንም እኛን ብሎ ከሩቅ ምስራቅ የመጣውን ባልደረባዬን እንቢ
በማለት ላስከፋው ባለመፈለጌ እና ሊኖረን ከሚችለው የስራ ጥቅም አንጻር እሺታዬን ገለጽኩለት።ሌላው እሺ
ያልኩበት ምክንያት ደግሞ ፍሪማን ያረፈበት ሆቴል ካፒታል ሆቴል በመሆኑ እራት ልንበላ የምንችለው እዛው
ካፒታል ሆቴል ነው የሚል የራሴን ቅድመ እሳቤ በመያዜ ምክንያት ነው። ዳሩ ግን እሺታዬን ከገለጽኩለት
በሁዋላ ቆንጆ የቻይና ምግብ ነው ምጋብዝህ በማለት ወደ ሃያ ሁለት የነበረውን ጉዞ አስቀይሮኝ ወደ ቦሌ
መድኃኒአለም እንድንሄድ ጠየቀኝ።መድኃኒአለም ያውጣኝ አልኩ በልቤ።የቻይና ሬስቶራንት? አሁን አንዴ እሺ
ብዬአለሁ ምን ብዬ ሐሳቤን ልቀይር? ምክንያት አጣሁ።የቻይና ምግብ አልበላም እንዳልል ኢትዮጵያዊ
አይደለሁ ይሉኝታ ያዘኝ።ምንም አማራጭ ስላልነበረኝ ውስጤ ባይስማማም ጭንቅላቴን በማነቃነቅ
መስማማቴን ገልጬለት ቦሌ መድኃኒአለም ወደሚገኘው ሞርኒንግ ስታር ሞል አመራን።

ቤቱ በቻይናውያን ተሞልቶአል።እንደገባን አንዲት ቻይናዊት በቻይንኛ እንኳን ደህና መጣችሁ ያለችን


መሰለኝ በፈገግታ ተቀበለችን።ቦታችንን ከያዝን በሁዋላ ቤቱን ለመቃኘት ስሞክር አንድ ሁለት
ኢትዮጵያውያንን ተመለከትኩ።ደስ አለኝ። የሆነ ጥብስ ፍርፍር ምናምን ያለ መሰለኝ።ባይሆን ታድያ ምን
ይሰራሉ እነዚህ ኢትዮጵያውያን? አልኩ ለራሴ።እንደተቀመጥን አንዲት አስተናጋጅ ወደ እኛ ቀርባ ታብሌት
ኮምፒውተር አምጥታ ፊትለፊታችን አስቀመጠችልን።ሜኑ መሆኑ ነው።ፍሪማን አስራ ሦስት ያህል ምግብ
መረጠ።ግር አለኝ።የሚሆነውን ዝም ብዬ በትዕግስት መከታተል ቀጠልኩኝ።ምግባችን መጣ።ከመጡት
ምግቦች ውስጥ የማውቃቸው ሦስቱን ብቻ ነው።ሦስቱንም ያወቅኳቸው ፍሪማን አስረድቶኝ ነው።አንዱ
የተቆራረጠ ጥሬ የበሬ ጨጓራ ሲሆን ሁለተኛው የበግ አንገት ነው።ሦስተኛው አፒታይዘር ተብሎ መጨረሻ
ላይ የመጣልንን ሐባብ ነው።የምግቦቹን አይነት አንድ በአንድ እየነገረኝ ሳለ በዛ በታፈነ ቤት ውስጥ ብርድ
ብርድ ይለኝ ጀመር።ይሄ የዶሮ ኩላሊት ነው።ዶሮ ኩላሊት እንዳላት ያወቅኩት ዛሬ ነው።ይሄ የኦክቶፐስ እግር
ነው።ይሄ ቀንድ አውጣ ነው።በጣም ቴስቲ ነው ትወደዋለህ ይለኛል።ተጨነቅኩ።ተረበሽኩ።ምንም
እንዳልመሰለው ለመሆን ግን እየጣርኩ ነው።የተቀዳልንን ሻይ የሚመስል ነገር አንስቶ ቺርስ በማለት የመልካም
እራት ምኞቱን ገለጾልኝ እንድበላ ጋበዘኝ።ለመጸለይ አንገቴን አቀረቀርኩኝና ምን ብዬ እንደምጸልይ ማሰብ
ጀመርኩ።እስከ ዛሬ ድረስ ስጸልይ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለው ኮመን ጸሎቴ ነበረ። ዛሬ ግን እንደዛ ብሎ ለመጸለይ
የሚያስችል ምግብ አይደለም እፊት ለፊቴ የሚገኘው።በመሆኑም ከክፉ ጠብቀኝ ጤናዬን ሁሉ ላንተ አደራ
አሳልፌ ሰጥቻለሁ የሚል እንድምታ ያለው ጸሎት ጸለይኩ።ቻይኖች እንደማንኪያ የሚጠቀሙበትን ሁለት
አነስ ያሉ እንጨቶችን አንስቼ ለመመገብ ሞከርኩ።ከማውቀው ልጀምር ብዬ ጥሬ ጨጓራ እንደምንም
በትንንሾቹ እንጨቶች ደጋግፌ ጎረስኩ። how is it? አለኝ። oww it is tasty አልኩት። ያለማጋነን ሰላሳ ሁለት
ደቂቃ ሳኝከው ቆየሁ።ሌሎቹንም እንደዛው።እሱ ግን እያጣጣመ ይበላል።በትንንሾቹ እንጨቶች ለመብላት
ስታገል ሸሚዜን እና ሱሪዬን አበላሸሁዋቸው።ሹካ አስመጣልኝ።በሹካ ደግሞ ትግል ገባሁ። ሰዓቱ አልገፋ
አለኝ።የተመቸኝ ለማስመሰል እየጣርኩ በግድ እየበላሁ ነው።የቤቴ ሽሮ ናፈቀኝ።የማልወዳቸው ምግቦች ሁሉ
ናፈቁኝ።ሽሮ ለመጀመርያ ጊዜ በአይነ ህሊናዬ መጣችብኝ።ናፈቀችኝ።ምስር ወጥ ሁሉ ትዝ አሉኝ።በዚህ
ሁሉ ስሜት ውስጥ ሆኜ በይሉኝታ እየበላሁ ሳለሁ አንድ ሐሳብ መጣልኝ። በቃኝ የማለት ሐሳብ።የመጣው
ይምጣ ከልኩ አያልፍም ብዬ በቃኝ አልኩ።Are you sure? አለኝ yes indeed አልኩት ቆፍጠን ብዬ።"ወደድከው
አይደል አለኝ?" " አዎ አልኩት" በይሉኝታ ግብዣውን ማሳነስ እንደይሆንብኝ ብዬ በመስጋት።በቃ ሌላ ቀን
ገርል ፍሬንድህን እዚ ይዘሃት ና አለኝ።አዎ ከሷ ጋር መጣላት የፈለግኩ ቀን አልሁ በልቤ።የቻይና ሬስቶራንት
ስገባ የመጀመርያዬም የመጨረሻዬም እንደሆነ አላወቀም።

You might also like