Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

I.

የሠርግ ግጥሞች
1. አታሞ ሲመታ ተሰበረች ጣቴ
እንግዲህ አለላው ብሩ ቀለበቴ
ትርጉም ፡- ታሞ ተመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ
2. የሙሽራው ማማር የሙዚየው ውበት
አነውሎኝ ሄደ እንዳልሰራ ቤት ፡፡
ትርጉም ፡- በጣም የሚያምሩ በመሆናቸው የሰዎችን ልብ ያዋልላሉ ፣
3. የሙሽሪት አባት እላይ ይቀመጡ
የሙሽሪት እናት እላይ ይቀመጡ
ልጅ አሳድገዋል እየቆነጠጡ ፡፡
ትርጉም ፡- ልጃቸው ቁም ነገረኛ በመሆኑ አባት እናቷ በልጅቷ ኮርተዋል ፡፡
4. ሙሽሪት ለምዳለች
እንዝርቴን ደጋኔን ላኩልኝ ብላለች ፡፡
ትርጉም፡- ከዚህ በኋላ የምሰራውን ስራ እንደለመደች ያመላክታል ፡፡
5. የኛ ሙሽራ ሰራ መደብ
ከንግዲህ ቀረ መደባደብ ፡፡
ትርጉም፡- ከዚህም በኋላ መደባደብ ቀረ
6. እንዳላይሽ እንዳላይሽ ወርቁን ፣
ጋረደት ሚዜዎችሽ
ትርጉም ፡-
7. ጡረው ጡረው አማጭህን ፣
ከዚህ ቆንጆ ያጋባህን ፡፡
ትርጉም ፡-
8. የእኛ ሙሽራ ሹራብ ሰሪ
ወሠዳት አስተማሪ ፡፡
ትርጉም ፡-
9. ሊወስዳት ነው እኮ ሊወስዳት ነው እኮ
ባልቴት ሽማግሌ አማላጅን ልኮ ፡፡
ትርጉም ፡-
1 ዐ. ወንድምየ ወንድም አባ
ይዘህ በጊዜ ግባ ፡፡
11. አስመስላ ታጥቃ ወረዳ ክዳን
ታስመሰግናለች እናት አባቷን ፡፡
ትርጉም ፡- ቆንጆ የሆነች ሴት ለራሷ ቀርቶ ወላጆቿን ማስመስገን ትችላለች ፡፡
12. የጥርሷን ንቅሳት አለው እርከን እርከን
የእሷ እናት ይውለዱ ድፍን ዳሞት ይምከን፡፡
ትርጉም ፡- ከብዙ ደካማ አንድ ጠንካራ ይበቃል ፡፡
13. እሄድ እሄድና እላለሁ ታከተኝ
መውደድ በጐራዴው እየከተከተኝ ፡፡
ትርጉም ፡- ትክክለኛ ፍቅር ከባድ መሆኑን ያመላክታል ፣
14. ኪሴ ባዶ ሚሆንም ምንም ባልጠቅማቸው
እናትና አባቴ ለኔ ክብሬ ናቸው ፡፡
ትርጉም ፡- ለቤተሰቦቿ ክብር መስጠትን ያመላክታል ፡፡
15. እኛስ ተውበናል ተውበሀል ወይ
በዉበት ላይ ውበት ደርበሀል ወይ ፡፡
ትርጉም ፡- ውስጣዊ ውበትና ውጫዊ ውበት ለሰዎች የሚያመላክት ነው ፡፡
16. የቆላ ማሽላ ቅጠለ ሰፋፊ
እንዴት አርጐ ሳመሽ ያመኪና ሰፊ ፡፡
ትርጉም ፡- የልጅቱን ውበት የሚነገረን መሆኑን ያመላክታል ፣
17. እረዥም መቀነት ሳይስቡት ይጠብቃል
ሀይማኖቴን ሁሉ ከአላንች ማን ያውቃል ፡፡
ትርጉም ፡- ልቤን ለአንች ብቻ መስጠቱን የሚያመላክት መሆኑ
18. ልኬልሽ ነበር ሁለት ወረቀት
አንዲን ለሰላምታ አንዱን ለናፍቆት፡፡
19. እንደጫጐ በሬ አንገተ ዝንጉርጉር
መንገዱን አስትታ ሰደደችኝ በዱር ፡፡
ትርጉም ፡- ልጅቷ በጣም የምታምር መሆኗን የሚያመላክት
20. እረ ጠይም ጠይም አሳ መሳይ
እኔ እናቷን በሆን ለሰውም አላሳይ
ትርጉም ፡- ልጅቷ በጣም የምታምርናት ግን እንደማትገኝ የሚያመላክት
ምንጭ የደ/ዳ/ወ/ባቱ ጽ/ቤት

You might also like