Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

1.

ባህልና ማህበራዊ አደረጃጀት በጎፋ ማህበረሰብ

1.1. ባህል
ባህል የሚለው ቃል በተለያዩ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን እንደየጥናት ዘርፉ ጽንሰ ሃሳብ ብያነ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከእነዚህ
ብያኔዎች መካከከል፣ ‹ኪዳነ ወልድ ክፍሌ› የባህልን ምንነት ሲገልጹ፡

ባህል ማለት ነገር፣ ክርክር፣ አባባል፣ አነጋገር፣ የነገር ስልት፣ ትርጓሜ ምሥጢር፣ ድርሳን፣ ልማድ፣ ሕግ ሥርዓት፣
የሃይማኖት ትምህርት፣ ቃለ ድምጽ ነው፡፡

ባህል የሚለው ስያመ ሰፊ ጽንሰ ሃሰብ እና በነጠላ አገላለጽ ለመበየን የሚያስቸግር ቃል ነው፡፡ ጥቅል ሲያሜ

1.1.1. የባህል ባህርያት

የባህል ጥናት ምሁራን እንደሚያስረዱት ባህል የተለያዩ ባህሪያት ይኖሩታል፡፡ ከእነዚህም የባህል ባህሪያት መካከል፤

 ባህል ሰዋዊ ነው፡፡ በጋሪዮሽ ሕይወት ይገለጣል፡፡ ሰው ይፈጥረዋል፤ ሰው ይጠቀምበታል፡፡


 ባህል ተለዋዋጭ ነው፡- ለውጡ ከጊዜና (ከዝግመተ-ለውጣዊ እሳቤ፣ በቻርሌስ ዳሪዊን የተፈጠረ እሳቤ ጋር
ይገናይኛል) ከቦታ አንጻር ይታያል፡፡
 ባህል አንጻራዊ ነው፡-
 ባህል አዳጊ ነው፡-
 ተወራራሽ ነው፡-

1.2. ማህበራዊ አደረጃጀት በጎፋ ማህበረሰብ

የጎፋ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ማህበራዊ አደረጃጀቶች አሉት፡፡ ከእነዚህም መካከል አከባቢው ሰው ሁሉ የራሱ
ቆሞ (ነገድ) ያለው መሆኑ፣ ለጋብቻና መሰል ማህበራዊ ትስስሮች ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው መሆኑ የሚጠቀስ
ነው፡፡ በሁሉም ኦማዊያን ማህበረሰብ ውስጥም በዋናነት ሁለት ማላ እና ዶጋላ የሚባሉ የጎሳ ነገዶች
እንዳሉት ከመረጃ ማረጋገጥ ይቻላል (የሰሜን ኦሞ ዞን ህዝቦች ታሪክ ገጽ 12-13)

ማህበራዊ ትስስርና አወቃቀር ስንል በጎፋ ማንኛው የማህበረሰቡ አባል የሆነ ሰው የአባትን መስመር ተከትሎ
የሚቆጠር የዘር ሀረግ አለው፡፡ በጎፋ ማህበረሰብ ሁለት ዐበይት ቆሞ (ጎሳዎች) አሉት፡፡ እነዚህም ማላ እና
ዶጋላ ይባላሉ፡፡ የማላ ቆሞዎች (ጎሳዎች) በአከባቢው ከሌላ ቦታ በመምጣት የሚኖሩ ጎሳዎች እንደሆኑ
ይነገራል፡፡ የዚህኛው መላምት ደጋፊዎች እንደሚሉት ማላዎች ከስማቸው ወይም ከንዑሳን ጎሳዎች
መጠሪያ ላይ የመጡበት ቦታ ቅድመ ቅጥያ ተደርጎ በመጨመር እንደሚጠሩ ይታመናል፡፡ የዶጋላ ጎሳዎች
ከጥንት ጀምሮ የአከባቢ ሰፋሪዎች እንደሆኑ ይታመናል፡፡ በሁለቱም ጎሳዎች ስር በርካታ ንዑስ ጎሳዎች
አሉት፡፡

በላይነህ (2009፣32) በሁለቱም ዐበይት ጎሳዎች ስር የሚገኙ ንዑሳን ጎሳዎች እንደሚከተለው


ዘርዝረዋቸዋል፡፡
ዶጋላ፡- አይጉራ፣ ሙጉርታ፣ ካናጻ፣ ማካ፣ ማሻ፣ አማሓ፣ ዜቃ፣ ጋጂሪቴ፣ ሲራሮ፣
ኢሎቴ፣ አዤ፣ አዲማኖ፣ ማዮ፣ ዋላቃ፣ አጋርሻ፣ ኦዳ፣ ቃሊቻ፣ ፃታ፣ ጻማ፣
ጎዲንታ፣ዎይካ፣ ዳራ፣ ሻዬ፣ ጉዳሪቴ፣ ቡቡላ፣ ዎሪዛ፣ካላታ፣ ጋጫ፣ አይፋርሲ፣
ጋውራሮ፣ ሒራሮ፣ ዙቱማ፣ ዛላ፣ ጋናዜ፣ ሳዎ፣ ሶዚና፣ከውካ፣ ማይላ፣ ዎቂሮ፣ ቱምኦ፣
ከራዜ

ማላ፡- ጎሎ ማላ፣ ቦሮዳ ማላ፣ ቡይላ ማላ፣ ሎንሦ ማላ፣ ሲሊ ማላ፣ ቆጎ ማላ፣ ዳሞታ
ማላ፣ ሓዮ ማላ፣ ሱዶ ማላ፣ ላይሺ ማላ፣ ቡኪ ማላ፣ አሺ ማላ፣ ጋሞ ማላ፣ ጎሻና
ማላ፣ አይካ ማላ፣ ጉይላ ማላ፣ ዚርጋ ማላ፣ ዳሻ ማላ፣ ጉራ ማላ...

በማለት በሁለቱ ጎሳዎች ስር የሚቆጠሩት ንዑሳን ጎሳዎች ዘርዝሯል፡፡ ከእነዚህ ሁለቱ ጎሳዎች
ውጭ የተለያዩ ዘሮችም በአከባቢው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ፋጽጋራ፣ መንዝ፣ አማራ ወዘተ.
ይጠቀሳሉ፡፡

በጎፋ በማህበረሰብ ውስጥ የተለያዩ ማህበራዊ ደረጃ ያላቸው ማህበረሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ ከእነዚህም በተለያዩ
እደ ጥበብ ሙያ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በማህበረሰቡ ውስጥ ዝቅተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ‹ማና›
እና ‹ወጋጨ› የሚባሉት ይገኛሉ፡፡ ማናዎች ሸክላ የሚሰሩ (ኦቶ ማና) ወይም ግታ ማና (አንዳንድ ቦታ ብረት
የሚሰሩ) ወጋጨ የሚባሉት ብረት የሚሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ በተለያዩ ማህበራዊ ተስስር ማለትም በጋብቻ፣
በዝምድና እና ሌሎች ሁኔታዎች ላይ የሚገለሉ ናቸው፡፡ ማናዎች በማህበረሰቡ ዘንድ የሚገለሉ የኅብረተሰብ
ክፍሎች መሆናቸውን፤ ሄኖክ ‹‹በቀደመው የጎፋዎች እሳቤ ’ማና’ዎች የሚባሉት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች፤
የማንም ቤት ገብተው አብሮ መብላት አይፈቀድላቸውም›› በማለት ይገልጻል፡፡

በአገራችን በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ እደ ጥበብ ባለሙያዎች ዝቅተኛ ቦታ እንደሚሰጣቸው እና ለእነዚህ


ህብረተሰብ ክፍሎች የተለየ ስያሜ እና ቦታ በመስጠት አሳንሰው የማየት ችግር እንደሚስተዋል ከመዛግብት
መረጃ መመልከት ይቻላል፡፡ ባሕሩ (2013፣188-189) በአፄ ምሊልክ መንግሥትም እደ ጠቢባንን ዝቅ
አድርገው የመመልከቱ ጉዳይ ንገሡ ህግ እስከ ማስወጣት ድረስ ደርሶ ያሳሰበ ጉዳይ እንደሆነ ሲገልጹ
አለቃ ታየ በ 1899 ዓ.ም ለአፄ ምኒልክ በጻፉት ድብዳቤ ብሉይና ሐዲስ ኪዳንን ከሁሉ
በፊት የተቀበለችው ኢትዮጵያ የመንፈሳዊና ቁሳዊ ኋላቀርነቷ ምንጭ የትምህርት
(በተለይም የወንጌል ትምህርት) እጦትና ማህበረሰቡ ለምሁራንና ዕደ ጠቢባን የነበረው
ንቀት ነው፡፡ ስለሆነም ዕደ ጠቢባንን የሚዘልፉ አጠራሮችና ስያሜዎች በአዋጅ
እንዲያግዱ›› የሚል ሐሳብ አቀረቡ፡፡

ከዚህ ሀሳብ የምንረዳው በኢትዮጵያ ዕደ ጥበብ ባለሙያዎችን ዝቅ አድርጎ የመመልከቱ ጉዳይ ስር የሰደደ
እንደሆነ ነው፡፡

በጎፋ ማህበረሰብ ዘንድ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎች በተጨማሪ በተለያዩ ዘመናት፣ በልዩ ልዩ
ምክንያቶች ማህበራዊ ደረጃቸውን በማጣት ወደ ዝቅተኛው ማህበራዊ ደረጃ የተመደቡ አይሌ
(ባርያ) የሚባሉት ክፍሎችም ይገኛሉ፡፡ በአከባቢው አይሌ ወይም ባሪያ ተብሎ የሚታወቁት፣
ከማንኛው ቆሞ (ጎሳ) አባል ሆኖ በቀደሙት ዘመናት፣ ለሀብት የተገዙ፣ በጦርነት የተማረኩ፣ ፈርቶ
ከጦርነት የሸሹ፣ የተበደሩትን ዕዳ መክፈል ያልቻሉ፣ ቤታቸውን እንደገና መሥራት አቅቷቸው
እላያቸው ላይ የወደቀባቸው፣ በገንዘብ የተሸጡ፣ የሟች አስከሬን በባዳ ጨርቅ ተከፍኖ የተቀበረባቸው
ሁሉ፣ ባሪነት የገቡ ተብሎ ይታወቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ የጎፋ ማህበረሰብ ይህ የማህበራዊ ደረጃ
ልዩነት እየጠበበ እንደመጣና በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር አጋጣሚዎች እምብዛም ልዩነት ሳይፈጥሩ
እየተግባቡ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

You might also like