Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የአርባምንጭ ትምህርት ኮለጅ የስርዓተ ፆታ ክፍል 2015 የ 6 ወር ሪፖርት

 . በ 2015 ዓ.ም አዲስ ለገቡ 302 ሴት ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም
በማዘጋጀት የኮሌጁን አከባቢ ከማስተዋወቅ ጀምሮ ተማሪዎቹ ስለኮሊጁ አጠቃላይ
መረጃ እንዲኖራቸዉ የተደረገ ሲሆን በዚህም ዝግጅት ላይ ስለ
ትምህርት አሰጣጥ ሊኖራቸው ስለሚገባ ስነ ምግባር ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል
ግተደርጓል፡፡
 አዳዲስ የስርዓተ ጾታ ክበብ አባላት እንዲመዘገቡ ማስታወቂያ በማዉጣት ፍቃደኝ
የሆኑ ተማሪዎች ተመዝግበዋል ከተመዘገቡት ዉስጥም የክበብ አመራሮች
ተመርጠዋል፡፡አዲስ ለተመረጡ አመራሮች ስለ ክበቡ የ ግንዛቤ ማስጨበጫ
ተሰጥቷቸዋል፡፡
 በኮሌጁ ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች ለአላስፈላጊ እርግዝና እና ለኤች አይቪ ኤድስ
እንዳይጋለጡ አስገዳጅ ሁኔታወች ሲከሰቱ እንዴት እራሳቸዉን መጠበቅ እንዳለባቸዉና
ከየትኛዉም አካል ፆታዊ ትንኮሳ ቢደርስባቸዉ ለማን ሪቶርት እንደሚያደርጉ በተለያዩ
መድረኮች ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

 ሴት ተማሪዎች ያለምንም ስጋት ለብቻቸው እንዲያነቡ ከዋናዉ ላይብረሪ የሴቶች


ማንበብያ ክፍለ በድጋሚ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ፡፡ስለ ስርዓተጾታ እና ተያያዥነት
ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያብሮሸሮችን በማዘጋጀት በአንደኛ ዓመት ሴት ተማሪዎች
አቀባበል ላይ 250 ኮፒ ተዘጋጅቶ ተሰራጭቷል::

 የኮሌጁ ሴት ተማሪዎች በትምህርት ሰዓት ከትምህርታቸዉ እንዳይስተጓጎሉ


ማለትም የወር አበባቸዉ ትምህርት ላይ እያሉ ከመጣባቸዉ ወደቤት ከሚሄዱ የንህጽና
መጠበቅያ /ሞዴስ/ እንዲጠቀሙ ተደርጓል፡፡
 አዲስ ለገቡ 302 ሴት ተማሪዎች በኮሌጁ ውስጥ ካሉ ሳይኮሎጂ መምህራን ጋር በመሆን በህይወት
ክህሎት፣በአጠናን ዘዴ እና በውጥረት አፈታት ተግባብቶ በመኖር ዙሪያ የ 2(ሁለት) ቀን ስልጠና
ተሰጥቷቸዋል፡፡

 ሴት ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባ ግንኙነት፣በፈተና ወቅት


ሊኖራቸው ስለሚገባ ስነምግባር፣በአጠቃላይ በኮሌጁ ሊኖራቸው ስለሚገባ ባህሪ በስርዓተ ፆታ
ተጠሪ እና በልምድ በተሻሉ መምህራኖች በሴቶች ክበብ ፕሮግራም የምክር አገልግሎት
ሲሰጥ ቆይቷል፡

 የበዓል አከባበርን በተመለከተበ 22/03/2015 ዓ.ም በተደረገዉ የዓለም ነጭ


የሪቫይን ቀን በኮሌጁ ሴትን አከብራለሁ ጥቃቷንም እከላከላለሁ!! በሚል
መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ በዓሉን አዝናኝና ትምህርት አዘል በሆነ ዝግጅት
በኮሌጁ ቅጥር ግቢ እንዲከበር ተደርጓል በእለቱ የነጭ ሪቫን ታሪካዊ አመጣጥ
ና ሙዚቃ የተለያዩ ግጥሞች ፤መልእክት አዘል እስቲከሮች ፤ መልክት አዘል
ብሮሸሮች ፤ባነር በማዘጋጀት ወንዶች ነጭ ሪቫን በማደረግ ለሴቶች አጋር
መሆናቸዉን በመግለጽ በዓሉ አስተማሪና አዝናኝ በሆነ መልኩ ተከብሯል፡፡

የልምድ ልዉዉጥን በተመለከተ


 በኮሌጃችን የሚገኙ አጠቃላይ ሴት መምህራን ሴት አስተዳደር
ሰራተኞች በቁጥር 86 የሚሆኑ ሰራተኞችን የከተማ ግብርና የሌማት
ቱሩፋት ከማስገኘቱም በላይ የኑሮ ዉድነትን በማረጋጋት ለበርካታ
ወገኖች የስራ እድል መፈጠሩ ይታወቃል በመሆኑም ሴት
ሰራተኞቻችንን በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በመዉሰድ የተለያዩ የጓሮ
አታክልት በጢቂት ቦታ በምንና እንዴት ባለ ሁኔታ እንደሚተከል ትልቅ
ልምድ እንዲቀስሙ ተደርጓል፡፡

You might also like