Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 24

‫التَّ ْج ِويد‬

ተጅዊድን በተመለከተ ከተለያዩ


ትምህርቶችና ፅሁፎች ተወስዶ
ለጀማሪዎች በአጭሩ የቀረበ

ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ
Revised 1439 ‫جماد الثاني‬
ካሚል አረጋ
‫كامل ابن خليل‬
‫الرِح ِ‬
‫يم‬ ‫بِ ْس ِم اللَّ ِه َّ‬
‫الر ْح َٰم ِن َّ‬
‫والسَلم على نبِيِّ نا مح َّم ٍد الْقائِل‬ ‫الْح ْمد لِلَّ ِه الَّ ِذي أنْ زل على ع ْب ِدهِ الْكِتاب ول ْم ي ْجع ْل له ِعو ًجا َّ‬
‫‪.‬الصَلة َّ‬
‫خ ْي رك ْم م ْن ت علم الْق ْرآن وعلَّمه‪ .‬وعلى آله وأصحابه أجمعين‪.‬أما بعد‪:‬‬

‫ْكتاب ي ْت لونه ح َّق تَِلوتِِه [البقرة‪.]121 :‬‬


‫فقال اهلل تعالى ‪ :‬الَّ ِذين آت يناهم ال ِ‬
‫ْ‬

‫ت‪ :‬قال رسول اهلل صلَّى اهلل عل ْي ِه وسلَّم‪:‬‬ ‫ضي اهلل ع ْن ها قال ْ‬‫وعن عائِشة ر ِ‬
‫ْ‬
‫السفرةِ الْ ِكر ِام الْب ررةِ‪ ،‬والَّ ِذى ي ْقرأ الْقرآن وي تت ْعتع فِ ِيه وهو عل ْي ِه شاق له أ ْجر ِ‬
‫ان»‬ ‫آن مع َّ‬ ‫«الْم ِ‬
‫اهر بِالْقر ِ‬
‫ْ‬ ‫ْ‬
‫أه ِميَّة التَّج ِو ِ‬
‫يد!!!!‬ ‫ْ‬
‫المام ابْن الْجزِرى رِحمه اهلل‪:‬‬
‫وقال ِْ‬
‫و ْال ْخذ بِالتَّج ِو ِ‬
‫يد ح ْتم ل ِزم ‪ ...‬م ْن ل ْم يج ِّوِد الْق ْرآن آثِم‬ ‫ْ‬
‫الله أنْ زل ‪ ...‬وهكذا ِم ْنه إِل ْي نا وصَل‬ ‫ِلنه بِ ِه ِْ‬
‫ك ْيف ي ْؤخذ الْع ْلم؟‬
‫اب ذكرها ب ْعضه ْم فِي ق ْولِِه‪:‬‬
‫والْ ِع ْلم ل ي ْؤخذ ق ْسرا وإِنما ي ْؤخذ بِأ ْسب ٍ‬
‫ً‬
‫أ ِخي لن ت نال الْ ِع ْلم إَِّل بِ ِست ٍة ‪ ...‬سأنْبِيك عن ت ْف ِ‬
‫صيلِها بِب ي ٍ‬
‫ان‬ ‫ْ‬ ‫ْ‬
‫اذ وطول زمان‬ ‫ذكاء و ِحرص واجتِهاد وب ْلغة ‪ ...‬وإِرشاد أست ٍ‬
‫ْ‬ ‫ْ‬ ‫ْ‬ ‫ْ‬
‫ادئ الْعشرة!!!‬ ‫الْمب ِ‬
‫الصبان عل ْي ِه ر ْحمة اهلل فِي ق ْولِ ِه‪:‬‬
‫اظم محمد بْن علِي َّ‬
‫ادئ الْعشرة الَّتِي جمعها النَّ ِ‬
‫الْمب ِ‬
‫إِ َّن م ِ‬
‫بادئ ك ِّل ف ٍّن عشره ‪ ...‬الح ُّد والموضوع ث َّم الثَّمره‬
‫ع‬ ‫ال ْسم ِال ْستِ ْمداد ح ْكم َّ‬
‫الشا ِر ْ‬ ‫ضله والو ِ‬
‫اض ْع ‪ ...‬و ِ‬ ‫ونِ ْسبة وف ْ‬
‫ض ا ْكت فى ‪ ...‬وم ْن درى الج ِميع حاز َّ‬
‫الشرفا‬ ‫مسائِل والب ْعض بِالب ْع ِ‬

‫‪1‬‬
‫التجويد‬
መግቢያ
1. የተጅዊድ ምንነት ፡
 ቋንቋዊ ትርጓሜው ፡ ማሳመር ማለት ነው
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጋጎም ፡ ሁሉንም ፊደሎች ከትክክለኛ ቦታቸው ማውጣትና የሚገባቸውን
ባህሪያት በመስጠት ቁርአንን ማንበብ ማለት ነው፡፡
 የፊደላት ባህሪ ስንል ሁለት ነገሮችን ይይዛል፡
o መሰረታዊ ባህሪ ፡ ሁልጊዜ ከፊደሉ ጋር የሚኖሩ ባህሪያት
o ምክንያታዊ ባህሪ ፡ አንዳንድ ጊዜ ፊደሉ ላይ ላይኖሩ የሚችሉ ባህሪያት
2. የተጅዊድ አላማ ፡
 በቁርአን ንባብ ላይ ከሚፈጠሩ ስህተቶች ምላስን ለመጠበቅ
ለምሳሌ፡- መጨመር ፣ መቀነስ ፣ መለወጥ ፣ ማዛባት …..
 አላህ ቁርአንን በትክክል ለሚያነቡ ሰዎች ያዘጋጀውን ሙሉ ስጦታና ዘውታሪ ከሆነው የጀነት ፀጋ
ተካፋይ ለመሆን ነው፡፡
3. የተጅዊድ ውሳኔ ፡
 የተጅዊድን ውሳኔ ለመስጠት የተጅዊድ ምሁራን በሁለት መልኩ ይመለከቱታል፡፡
1) ቁርአንን በተጅዊድ ማንበብ ፡ ግዴታ (ፈርደል አይን) ነው፡፡
2) የተጅዊድ ህግጋቶቹን ማወቅ ፡ ማወቁ የተወሰኑ ሰዎች አውቀውት ሌሎች ባያውቁት ችግር
የሌለው (ፈርደል ኪፋያ) ነው፡፡

4. የተጀዊድ ደረጃው እና አስፈላጊነቱ ፡


 ቁርአን ማለት መነበቡ ኢባዳ(አምልኮ) የሆነ፣ በጅብሪል አማካኝነት ለነብዩ ሙሐመድ(‫) صلى اهلل عليه وسلم‬
የተወረደ የጌታችን አላህ ቃል ነው፡፡
 ስለዚህ ተጅዊድ ደግሞ ከቁርአን(ከአላህ ንግግር) ጋር በመመያያዙ ምክንያት አንገብጋቢ፣ ወሳኝ እና
ትልቅ ደረጃ አለው፡፡
 ቁርአንን አሳምረን መቅራታችን ደግሞ ቁርአንን እንድንወድና ከቁርአን ጋር ብዙ ጊዜ እንድናሳልፍ
ያደርገናል፡፡ ይህ ደግሞ በዱንያም በአኼራም ትልቅ የሆነን ጥቅም ይሰጠናል፡፡
1) በዱንያ፡
o ለቁርአን ረጅም ጊዜ መስጠታችን አኽላቃችንን ያስተካክልልናል ፣ በኢባዳ እንድንጠነክርም
ያደርገናል፡፡
2) በአኼራ፡
o አቡ ኡማማህ (‫ )رضي اهلل عنه‬የአላህ መልእክተኛ (‫ )صلى اهلل عليه وسلم‬እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ፡-
‹‹ ቁርዐንን አንብቡ እሱ (ቁርዐን) የትንሳኤ እለት (በዱንያ) ላነበበው ሰው መስካሪ ሁኖ
ይመጣልና፡፡›› (ሙስሊም ዘግበውታል)
o የአላህ መልዕክተኛ (‫ )صلى اهلل عليه وسلم‬መናገራቸውን የሙእሚኖች እናት ዓይሻ ( ‫ )رضي اهلل عنها‬ሲገልጹ ፡-
‹‹ ቁርዐንን በተጅዊድ ጥሩ አድርጎ የሚያነብ ሰው ደረጃው መልካም እና አላህን ታዛዥ ከሆኑ
መላኢኮች ጋር ሲሆን ያ ቁርአንን በትግል(እየተኮለታተፈ) የሚያነብ በትግሉና በማንበቡ
ሁለት ምንዳ አለው ፡፡ ››(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2
በመጨረሻም ተጅዊድን ለመረዳት(ተጅዊድን የጠበቀ አቀራር ለመቅራት) አራት መሰረታዊ ነገሮች አሉ፡፡ እነሱም፡-
‫ )أ‬የፊደላትን መውጫ ማወቅ
‫ )ب‬የፊደላትን ባህሪ ማወቅ
‫ )ج‬አንድ ፊደል ከሌሎች ፊደሎች ጋር ተያይዞ(ተቀጥሎ) ሊኖረው ሚችለውን ሁኔታና
ለብቻው ሲነበብ ሊኖረው ሚችለውን ሁኔታ ለይቶ ማወቅ
‫ )د‬ምላስን ማለማመድ እና ደጋግሞ መቅራት
እነዚህ አራቱ ከተሟሉ የተጅዊድ ትምህርት እጅግ በጣም ቀላልና ቀላል ነው፡፡ ግን አላህ ለረዳው ሰው፡፡
ምንም መስፈርት ቢያሟሉ ፣ ምንም ጉጉት ቢኖር የአላህ እርዳታ ካልታከለበት የትም ሊደርስ አይችልም፡፡ ለዚህ
ነው ሁሌም፡- }‫ست ِعين‬
ْ ‫ ]إِيَّاك ن ْعبد وإِيَّاك ن‬ልንል ሚገባው፡፡

አል-ኢስቲዓዛህ አል-በስመላህ

አል-ኢስቲዓዛህ
 በአላህ ስም እርጉም ከሆነው ሸይጣን መጠበቅ ማለት ነው ፡፡
 ማንኛውም ሰው ቁርአንን ከመጀመሪያ ሱራህ(ምዕራፍ) ወይም ከመካከል አንቀጽ ላይ ለማንበብ ከፈለገ
ِ ‫الرِج‬
በኢስቲዓዛህ (‫يم‬ َّ ‫ان‬ َّ ‫ ) أعوذ بِاهلل ِمن‬ብሎ መጀመሩ ግዴታ ነው፡፡
ِ ‫الش ْيط‬
 ‹‹ ቁርዐንን ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሸይጣን በአላህ ስም ተጠበቅ፣›› (አንነህል 98)

አል-በስመላህ

 ቁርአንን ከመጀመሪያ ሱራህ ጀምሮ ሚያነብ ሰው ላይ ከሱረቱ ተውባ (‫ )ب راءة‬በስተቀር በሁሉም ሱራህ
ِ ‫الرِح‬
መጀመሪያ ላይ በበስመላህ (‫يم‬ َّ ‫ )بِ ْس ِم اللَّ ِه‬ብሎ መጀመሩ ግዴታ መሆኑን ሁሉም የተጅዊድ
َّ ‫الر ْحم ِن‬
ምሁራን ይስማማሉ፡፡
 ነገርግን ከሱራህ መካከለኛ አንቀፅ ላይ ለማንበብ የፈለገ ሰው በስመላን ተጠቅሞም ሆነ ሳይጠቀም መጀመር
ይችላል፡፡

3
አንዳንድ በተደጋጋሚ የሚመጡ ቃላት ፍቺ፡

1. ‫ الْح ْرف‬፡
 ሀርፍ ማለት ፊደል ማለት ሲሆን ሁሩፍ)‫ (حروف‬ማለት ደግሞ ፊደሎች ማለት ነው፡፡
 የአረብኛ ፊደላት ሁሩፉል ሂጃእያህ(‫ ) الحروف الهجائية‬በመባል ይታወቃሉ፡፡
 የአረብኛ ፊደላት ብዛት 29 ናቸው ::
 ማሳሰቢያ ፡ "አ” የሚለው ደምፅ የሀምዛ እንጂ የአሊፍ አይደለም፡፡ አሊፍ እንደ መድ (መሳቢያ)
ወይም ሀምዛን እንደማስቀመጫነት ነው የምታገለግለው፡፡
2. ‫ الْح ْركة‬፡
 በቋንቋ ደረጃ እንቅስቃሴ ማለት ሲሆን የሚያመለክተውም ሶስቱን የአረብኛ አናባቢዎች ነው ፡፡
 የአረብኛ አናባቢዎች ሶስት ናቸው እነሱም፡
َ , َ‫أ‬
َ ,‫ب‬
1. ፈትሀ ፡__________ ፈትሀ ያለበትን ፊደል ስናነብ አፋችን ይከፈታል፡፡ ›››››››››› ‫ت‬
2. ከስራ ፡ __________ ከስራህ ያለበትን ፊደል ስናነብ አፋችን ወደ ጎን ይሰፋል፡፡
3. ደማህ ፡ __________ ደማህ ያለበትን ፊደል ስናነብ አፋችን ይሰበሰባል፡፡
 ሀረካ ያለበትን ፊደል ሙተሐሪክ(‫ )متح ِرك‬ብለን እንጠራዋለን፡፡
3. ‫السكون‬
ُّ ፡
 መርጋት ማለት ሲሆን ይህም የተባለበት ምክንያት ሱኩን ያለበት ፊደል በሚነበብበት ሰአት አፋችን
ላይ ምንም እንቅስቃሴ ስለማይኖር ነው፡፡
 የሚያመለክተውም የአናባቢ አለመኖርን ነው፡፡
 ሱኩን በቁርአን ላይ በሁለት አይነት መልኩ ይመጣል፡፡
1. የሱኩን ምልክትን ይዞ፡ ፊደላት ላይ የሱኩን ምልክት በሚገኝበት ግዜ ፊደላቶች ግልጽ ተደርገው
ይነበባሉ ማለት ነው፡፡
2. የሱኩን ምልክት ሳይኖረው (ባዶ ሆኖ ምንም ምልክት ሳይኖረው)፡ ቁርአን ላይ ፊደላት ምንም
ምልክት ሳይኖራቸው ከመጡ ግልጽ ተደርገው የማይነበቡ አልያም ደግሞ መሳቢይዎች(መዶች
)ይሆናሉ፡፡
 የሱኩን ምልክት ያለበትን ፊደል ሳኪን(‫ )ساكن‬ብለን እንጠራዋለን፡፡
4. َّ
‫الش ْكل‬ :
 ሸክል ማለት ቅርፅ ወይም ሁኔታ ማለት ሲሆን ሚያመለክተውም ሱኩንን እና ሀረካዎችን ነው፡፡
5. ‫ التَّ ْن ِّوين‬፡
 ተንዊን ማለት በስም መጨረሻ ላይ የምትገኝ ጭማሪ የሆነች ኑን ሱኩን ናት፡፡
 የሚያመለክታትም ፈትሐተይን(ሁለት ፈትሐ) ፣ከስረተይን(ሁለት ከስራ) እና ደመተይን(ሁለት
ደማ) ናቸው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ያሉበት ፊደል መጨረሻቸው ላይ የኑን ሱኩን ድምፅ ተጨምሮ
ይነበባል፡፡
 ፈትሐተይን ሲፃፍ መጨረሻ ላይ አሊፍ ይፃፋል፡፡ ‫بًا تًا ثًا‬
‫ت‬ ٍ , ‫ ًتا‬, ٌ‫ ب‬, ‫ب‬
ٌ ,‫ت‬ ٍ , ‫ بًا‬, ‫ ٌم‬, ‫ ٍم‬, ‫مًا‬

4
6. َّ ፡
‫الشدة‬
 ሸድዳ ማጥበቅ ማለት ሲሆን ይህ ምልክት ያለበትን ፊደል አጥበቀን እናነበዋለን፡፡ ከሀረካዎች ጋር
በአራት መልኩ ሊመጣ ይችላል፡፡
 ሁለት አንድ አይነት ወይም ተቀራራቢ ፊደሎች የመጀመሪያው ፊደል ሱኩን ሆኖ የሁለተኛው ፊደል
የተሀረከ ከሆነ ሱኩን የሆነው ፊደል ከተሀረከው ፊደል ውስጥ መግባቱንና ጠብቆ እንደሚነበብ
የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ ‫ أَنَّ = أَ ْن َن‬, ‫ْب‬
َ ‫أَبَّ = أَب‬
7. ‫ ه ْمزة‬፡
 ሁለት አይነት ሀምዛዎች ይገኛሉ፡፡ እነሱም፡-
1. ‫ )أ( ه ْمزة الْقطْ ِع‬፡ በማንኛውም ሁኔታ የምትነበብ ሀምዝ ናት፡፡

2. ‫ص ِل‬ ‫ٱ‬
ْ ‫ ) ( ه ْمزة الْو‬፡ ከሷ ከጀመርን ብቻ ነው የምትነበበው ፡፡

8. ‫ الْكلِمة‬፡
 ከሊማህ ማለት ቃል ማለት ነው፡፡ ቃል ማለትَደግሞ ትርጉም ያለው የፊደላት ስብስብ ነው፡፡
9. ‫ الْكَلم‬፡
 ንግግር(አረፍተ ነገር)፡ ሙሉ ሀሳብ የሚሰጡ የቃላት ስብስብ ነው፡፡
 አረብኛ ሶስት የንግግር ክፍሎች አሉት፡፡ እነሱም፡
‫ال ْسم )أ‬ِْ ፡ ስምَ
‫ الْ ِف ْعل )ب‬፡ ግስ
‫ الْح ْرف )ج‬፡ ፊልደ(ትርጉም ያለው)
10. ِْ ፡
‫ال ْسم‬
 ከጊዜ ጋር ሳይቆራኝ በራሱ ትርጉም መስጠት የሚችል ቃል ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ، ‫ جمل‬، ‫ رجل‬، ‫ خديجة‬، ‫ فاطمة‬، ‫ محمد‬، ‫هللا‬
 ስሞች ከታዋቂነታቸው አንፃር ለሁለት ይከፈላሉ፡
1. ٌ ‫ َب‬፡ ቤት
‫ النكرة‬፡ የማይታወቅ ምሳሌ፡ ‫ جدي ٌد‬፡ አዲስ ፣ ‫يت‬
2. ‫ المعرفة‬፡ የሚታወቅ ምሳሌ፡ ‫ الجديد‬፡ አዲሱ ፣ ‫ ال َبيت‬፡ ቤቱ
11. ‫ الْ ِف ْعل‬፡
 ተግባር ከተሰሩበት ጊዜ አንፃርَየሚገልጽልንَቃልَነው፡፡ስለዚህ ከጊዜያቸው አንፃር ለሶስት
ይከፈላሉ፡፡
1. ‫( الفعل الماضى‬አላፊ ግስ) ፡ ምሳሌ ፡- ሄደ ‫ذهب‬
2. ‫( الفعل المضارع‬የአሁንና መጪ ግስ)፡ ምሳሌ ፡ ይሄዳል/ እየሄደ ነው ‫يذهب‬
3. ‫( الفعل األمر‬ትእዛዛዊ ግስ) ፡ ምሳሌ ፡ ሂድ ‫اذهب‬

5
12. ‫ََالْح ْرف‬:
 በራሱ ይህ ነው የሚባል ትርጉም የማይሰጥ ነገርግን ከአረፍተ ነገር ጋር ሲቆራኝ ትረጉም መስጠት
የሚችል ቃልَነው፡፡ ምሳሌ፡- ..............َ‫َبل‬:َ‫َهل‬:َ‫َفي‬:َ‫َعلى‬:َ‫َإلى‬:َ‫من‬
13. ተጅዊድ ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ቃላት፡
‫( الظهار )أ‬ኢዝሀር) ፡
 ቋንቋዊ ትርጓሜው ፡- ግልጽ ማለት ነው፡፡
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጋጎም ፡- ሁሉን ፊደል ያለ ጉና ከሚወጡበት ቦታ ማስወጣት ማለት
ነው።
‫( الدغام )ب‬ኢድጋም) ፡
 ቋንቋዊ ትርጓሜው ፡- ማስገባት ማለት ነው፡፡
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጋጎም ፡- ሳኪን ከሆነ ፊደል በኋላ ሙትሐሪክ የሆነ ፊደል ሲመጣ
ሱኩን የሆነውን ፊደል የተሐረከው ፊደል ውስጥ በማስገባት ልክ እንደ አንድ ሸዳ የሆነ ፊደል
አድርጎ ማንበብ ማለት ነው፡፡
‫( الخفاء )ج‬ኢኽፋእ)፡
 ቋንቋዊ ትርጓሜው ፡- መደበቅ ማለት ነው፡፡
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጋጎም ፡- በኢዝሀር እና በኢድጋም መሀል አድርጎ ማንበብ ማለት ነው።
‫( القَلب )د‬ኢቅላብ)፡
 ቋንቋዊ ትርጓሜው ፡- መገልበጥ
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጋጎም ፡- ኑን ሳኪናን ወይም ተንዊንን ኢኽፋእ እና ጉና በመጠቀም
ወደ ሚም ሳኪና መገልበጥ ማለት ነው።
‫( الغنة )ه‬ጉና) ፡ ከአፍንጫችን የውስጠኛው ክፍል የሚወጣ ማራኪ ድምፅ ነው፡፡

ِ ‫( مخا ِرج الْحر‬የፊደላት መውጫ ቦታ)


1 ‫وف‬

 ማንኛውም ፊደል የሚወጣበት ወይም የሚፈጠርበት ቦታ ማለት ነው፡፡


 የፊደል መውጫ ቦታዎችን መጠበቅና አንድን ፊደል ቦታውን ጠብቆ ማውጣት ዋጂብ በመሆኑ ላይ ዑለማዎች
ይስማማሉ፡፡ምክንያቱም አንድ ፊደል ቦታው ተቀይሮ ከወጣ ምናነበው ቃል ላይ የሀሳብ ለውጥ ይመጣል፡፡
 ከመድ ፊደላት ውጭ ያሉትን የዐረብኛ ፊደላት ትክክለኛ መውጫ ቦታ ለማወቅ በመጀመሪያ የተሀረከች ሀምዝ
ቀጥሎ መውጫ ቦታውን ማወቅ የምንፈልገውን ፊደል ሱኩን አድርገን ማወቅ ይቻላል፡፡
ለምሳሌ፡- ﴾‫ث‬ْ ‫﴿أ ْم﴾ ﴿ إِ ْن﴾ ﴿أ‬
 የፊደላት የመውጫ ቦታ 17 ሲሆን እነሱም ከ5ቱ የሰውነታችን አካሎች ይወጣሉ፡፡ እነሱም፡
1. ‫) الْج ْوف‬ጀውፍ(፡ ………………………………………………… 1 ቦታ 3 ፊደል
 የአፍና የጉሮሮ ባዶ ቦታ ነው፡፡
 ከጀውፍ ሶስቱ የመድ ፊደሎች ይወጣሉ፡፡ (‫) ا و ي‬
2. ‫ ) الْح ْلق‬ጉሮሮ) ፡ ………………………………………………… 3 ቦታ ፣ 6 ፊደል
 ሶስት የመውጫ ቦታዎች አሉት፡፡ እነሱም፡-
 የጉሮሮ ሩቅ ክፍል ፡ ‫ ه‬،‫ء‬

6
 የጉሮሮ መካከለኛ ክፍል ፡ ‫ ح‬، ‫ع‬
 የጉሮሮ ቅርብ ክፍል ፡ ‫ خ‬، ‫غ‬

3. ‫( اللِّسان‬ምላስ)፡ ………………………………………………… 10 ቦታ ፣ 18 ፊደል


 አራት ዋና ዋና ቦታዎች አሉት፡፡ እነሱም፡-
 የምላስ ሩቅ ክፍል ፡ ]‫[ ك‬، ]‫[ ق‬
 የምላስ መካከለኛ ክፍል ፡ ]‫ي‬، ‫ ش‬، ‫[ج‬
 የምላስ የጎን ክፍል ፡ ]‫[ ل‬، ]‫[ ض‬
 የምላስ ጫፍ ክፍል ፡ ]‫َث‬،َ‫َذ‬،َ‫[ظ‬،]‫َز‬،َ‫َص‬،َ‫[س‬،]‫َت‬،َ‫َد‬،َ‫[ط‬،]‫[ر‬،]‫َ[ن‬
ِ ‫الشفت‬
4. ‫ان‬ َّ (ሁለቱ ከንፈሮች) ፡ ………………………………………………… 2 ቦታ ፣ 4 ፊደል
 የሚከተሉት አራት ፊደላት ይወጣሉ፡ ]‫ و‬، ‫ م‬، ‫[ ب‬، ]‫[ف‬
5. ‫( الخيشوم‬ኸይሹም)፡
 የአፍንጫ ሩቅ ክፍል
 ከሱም የጉና ድምፅ ይወጣል፡፡

2 ‫( صفات الحروف‬የፊደላት ባህሪ)


 አንድ ፊደል ከመውጫ ስፍራው ሲወጣ ሊኖረው የሚችለው ባህሪያት ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ማወፈር፣ ማቅጠን ፣ ጠንካራ መሆን ፣ መርዘም ፣ ማጠር ……የመሳሰሉት ይገኛል፡፡
 የፊደላትን ባህሪ ማወቅ ከአንድ ቦታ የሚወጡ ፊደሎችን በትክክል ለይቶ ለማውጣት ይጠቅመናል፡፡
 በአጠቃላይ 17 የፊደላት ባህሪ አሉ፡፡ አራት ባህሪዎች ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል፡፡
I. የሚወፍሩ እና የሚቀጥኑ ፊደላት፡ (‫)اإلستعالء واإلستفال‬
 የዐረብኛ ፊደላት ከመወፈራቸው እና ከመቅጠናቸው አንፃር ለሶስት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-
 1. ሁል ጊዜ ወፍረው የሚነበቡ ፈደላት
o ሁል ጊዜ ወፍረው የሚነበቡ ፈደላት ሰባት (7) ናቸው፡፡ እነሱም፡- ‫ خ ص ض غ ط ق ظ‬በአጭሩ
ለመያዝ ‫ض ْغطٍ ق ِْظ‬
َ ْ‫ خص‬፡፡ እነዚህን ፊደሎች ቁርአን ውስጥ ስናገኛቸው አወፍረን እናነባቸዋለን፡፡
 2. አንዳንድ ጊዜ የሚወፍሩና የሚቀጥኑ ፈደላት
o ሶስት (3) ሲሆኑ እነሱም አሊፍ ፣ ላም እና ራ (‫ ر‬، ‫ ل‬، ‫ )ا‬ናቸው፡፡
ሀ. አሊፍ)‫( ا‬፡
 ከአሊፍ በፊት የሚወፍር ፊደል ከመጣ አሊፍ ወፍራ ትነበባለች፡፡
ምሳሌ፡- ﴾‫﴿خالِ ِدين﴾ ﴿الضَّالِّين‬
 ከአሊፍ በፊት የሚቀጥን ፊደል ከመጣ አሊፍ ቀጥና ትነበባለች ፡፡
ለምሳሌ ፡- ﴾‫ك﴾ ﴿إِيَّاك‬ ِ ِ‫﴿مال‬
ለ. ላም(‫) ل‬፡
 አላህ ሚለው ቃል ለፍዘል ጀላላህ(‫ )لفظ الجاللة‬ተብሎ ይታወቃል፡፡ የአላህ ስም ላይ ያለችዋ ላም
ደግሞ ላመል ጀላላህ(‫ ) الم الجاللة‬ተበላ ትታወቃለች፡፡
 ከላመል ጀላላህ በፊት ፈተሀ ወይም ደምማ ከመጡ ላመል ጀላላህ ወፍሮ ይነበባል፡፡
ለምሳሌ ፡- ﴾‫﴿ي ثبِّت اللَّه﴾ ﴿اللَّه﴾ ﴿هو اللَّه‬
 ከላመል ጀላላህ በፊት ከስራህ ከመጣ ላመል ጀላላህ ቀጥኖ ይነበባል፡፡
ለምሳሌ ፡- ﴾ ‫س ِم اللَّ ِه‬ ِ ِِ
ْ ‫﴿ق ِل اللَّه َّم﴾ ﴿للَّه﴾ ﴿ب‬
ሐ. ራ(‫) ر‬፡ ገፅ 9፣10 እና 11 ላይ በሰፊው ተዳሷል
7
 3. ሁል ጊዜ ቀጥነው የሚነበቡ ፊደላት ፡
o የተቀሩት አስራ ዘጠኝ ፊደላት ናቸው፡፡ እነዚህ ፊደላት ሁል ጊዜ ቀጥነው ይነበባሉ፡፡

II. አል-ቀልቀላህ
 ቋንቋዊ ትርጓሜው ፡- ‹‹ መንቀሳቀስ ›› ማለት ነው፡፡
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጓጎም፡- ‹‹ ከቀልቀላህ ፊደሎች አንዱ ሱኩን ሆኖ መውጣት ካለበት ስፍራ
በሚወጣበት ጊዜ ምላስ በሀይል መንቀሳቀሱና በሀይል መንቀሳቀሱን ተከትሎ ጠንከር ያለ ድምፅ
መውጣት ›› ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ መንጠር ማለት እንችላለን፡፡
 የቀልቀላህ ፊደሎች አምስት (5) ናቸው፡፡ እነሱም (‫)ق ط ب ج د‬በአጭሩ ለመያዝ (‫)قطب َج ْد‬፡፡
 ቀልቀላህ ለሁለት ይከፈላል፡፡
1. ቀልቀላህ ኩብራህ፡ የሚፈጠረው የቀልቀላህ ፈደል ላይ በሱኩን ስናቆም ነው፡፡
ِ ‫السم ِاء ذ‬
ምሳሌ፡- ﴾ ‫ات الْب روج ﴾ ﴿ ول ْم يول ْد‬ َّ ‫﴿ وتب ﴾ ﴿ و‬
2. ቀልቀላህ ሱግራህ፡ የሚፈጠረው የቀልቀላህ ፊደል ሱኩን ሆኖ በቃላት መካከል ሲመጣ
ነው፡፡
ምሳሌ፡- ﴾ ‫ون‬ ْ ‫﴿ ول ت ْش ِط‬
ِ ‫ط و ْاه ِدنا ﴾ ﴿ يط ِْعم‬
III. ጉናህ
 ቋንቋዊ ትርጓሜው፡- ‹‹ ከአፍንጫ የውስጠኛ ክፍል የሚወጣ ድምጽ›› ማለት ነው፡፡
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጓጎም ፡- ‹‹ በሚምና በኑን አካል ላይ ሁል ጊዜ የሚገኝ ከአፍንጫ የውስጠኛ
ክፍል የሚወጣ ማራኪና ጣፋጭ የሆነ ድምጽ ›› ማለት ነው፡፡
 ጉናህ ከሚምና ከኑን በማንኛውም አይነት ሁኔታቸው የሚገኝና ሊለያቸው የማይችል መሰረታዊ
የሆነ ባህሪያቸው ነው፡፡
ሁለት ፊደሎች ተከታትለው ሲመጡ ከባህሪያቸውና ከመውጫ ቦታቸው አንፃር አራት ሁኔታ አላቸው፡፡
 1. አል-ሙተማሲላን ፡ (‫)المتماثالن‬
o በመውጫ ቦታቸው እና በባህሪያቸው አንድ የሆኑ ፊደሎች ማለት ነው፡፡
 2. አል-ሙተጃኒሳን ፡ (‫)المتجانسان‬
o በመውጫ ቦታቸው አንድ ሆነው በባህሪያቸው ሲለያዩ፡፡
ለምሳሌ፡- ‫ ب‬እና ‫ م‬፣ ‫ ث‬እና‫ ذ‬፣ ‫ د‬እና‫ ت‬፣ ‫ ذ‬እና ‫ ظ‬፣ ‫ت‬እና ‫ط‬
 3. አል-ሙተቃሪባን ፡ (‫)المتقاربان‬
o 3.1. በመውጫ ቦታቸው ተቀራርበው በባህሪያቸው ሲለያዩ፡፡ ለምሳሌ፡- ‫ د‬እና ‫س‬
o 3.2. በመውጫ ቦታቸው ተለያይተው በባህሪያቸው ሲቀራረቡ፡፡
ለምሳሌ፡- ‫ س‬እና ‫ ش‬፣ ‫ ت‬እና ‫ ث‬፣ ‫ ذ‬እና ‫ج‬
o 3.3. በመውጫ ቦታቸው እና በባህሪያቸው ሲቀራረቡ፡፡
ለምሳሌ፡- ‫ ن‬እና ‫ ل‬፣ ‫ ق‬እና ‫ ك‬፣ ‫ ل‬እና ‫ ر‬፣ ‫ ذ‬እና َ‫ز‬
 4. አል-ሙተባዒዳን ፡ (‫)المتباعدان‬
o በመውጫ ቦታቸው እና በባህሪያቸው የሚለያዩ ፊደሎች ማለት ነው፡፡
ሁለት ፊደሎች ተከታትለው ሲመጡ እላያቸው ላይ ባለው ሸክል መሰረት ሶስት ሁኔዎች አላቸው፡፡
 1. ሰጊር (‫ )الصغير‬፡
የመጀመሪያው ፊደል ሱኩን ሆኖ ሁለተኛው ሙተሀሪክ ከሆነ፡፡
 2. ከቢር (‫ )الكبير‬፡
ሁለቱም ሙተሀሪክ ከሆኑ፡፡
 3. ሙጥለቅ (‫ )المطلق‬፡
የመጀመሪያው ፊደል ሙተሀሪክ ሆኖ ሁለተኛው ሱኩን ከሆነ፡፡

8
ከላይ ባየነው ትንታኔ መሰረት ሁለቱንም ገለፃዎች አንድ ላይ ከምሳሌ ጋር በሚከተለው ሠንጠረዥ እንመልከት
ምሳሌ ፊደሎች ሁክሙ ባህሪ መውጫ
ለምሳሌ ቦታ
﴾‫ ت ﴿فما ربِحت تِّجارت ه ْم‬እና ‫ ت‬ኢድጋም ሰጊር
አል ሙተማሲላን
﴾‫ك‬ ِ ِ‫الرِح ِيم مال‬
َّ ﴿ ‫ م‬እና ‫م‬ ኢዝሀር ከቢር አንድ አንድ ((‫))المتماثالن‬
መሆን መሆን
﴾ ‫ود‬ٍ ‫﴿ َّممد‬ ‫ م‬እና ‫م‬ ኢዝሀር ሙጥለቅ
ْ

﴾‫﴿إِذ ظَّلموا‬ ‫ ذ‬እና ‫ظ‬ ኢድጋም ሰጊር


አንድ አል-ሙተጃኒሳን
ْ ‫س ز ﴿ وإِذا النُّفوس زِّوج‬
﴾‫ت‬ ኢዝሀር ከቢር መለያየት መሆን (‫)المتجانسان‬
﴾ ‫﴿ َّم ْب عوثون‬ ‫ب‬ ‫م‬ ኢዝሀር ሙጥለቅ

﴾ ‫﴿ ق ْد س ِمع‬ ‫س‬ ‫د‬ ኢዝሀር በሶስቱም መለያየት መቀራረብ


ሁኔታ
ْ ‫﴿ ك َّذب‬
﴾ ‫ت ثمود‬ ‫ث‬ ‫ت‬ ኢዝሀር በሶስቱም መቀራረብ መለያየት አል-ሙተቃሪባን
ሁኔታ (‫)المتقاربان‬
﴾‫ب‬ ِّ ‫﴿قل َّر‬ ‫ر‬ ‫ل‬ ኢድጋም ሰጊር

﴾ ‫اصبِ ْر‬ ِ
ْ ‫﴿ ولربِّك ف‬ ‫ر‬ ‫ل‬ ኢዝሀር ከቢር መቀራረብ መቀራረብ
ኢዝሀር ሙጥለቅ

በሶስቱም አል-ሙተባዒዳን
ኢዝሀር ሁኔታ መለያየት መለያየት (‫)المتباعدان‬

የ ራ ህግጋት
 ራ ፊደል ከመወፈር እና ከመቅጠን አንፃር ሶስት ሁኔታዎች አሏት ፡፡
 በስምንት ቦታዎች ላይ ተወፍራ ትነበባለች ፣
 በአራት ቦታዎች ተቀጥና ትነበባለች ፣ እና
 በሁለት ቦታዎች ደግሞ ተወፍራ ወይም ተቀጥና ትነበባለች፡፡

መሰረታዊ ሱኩን፡ የሱኩን ምልክት ያለባት


ምክንያታዊ ሱኩን፡ በመቆም ምክንያት የተፈጠረ ሱኩን

9
1. ራ የምትወፍርባቸው ስምንት ቦታዎች

1.1. ራ ፈትሀ ሁና ስትመጣ፡


﴾ ‫﴿ وغفر ﴾ ﴿ بِربِّك ْم ﴾ ﴿ ر ِحيم‬
1.2. ራ ደማ ሁና ስትመጣ ፡
﴾ ً‫﴿ ر ْحما‬ ﴾ ‫صرون‬ ِ َّ‫﴿ والظ‬
ِ ‫اهر ﴾ ﴿ بِما ت ْب‬
1.3. ራ ሱኩን ሁና ስትመጣ፡
1.3.1. ራ መሰረታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ፈትሀ ሲመጣ
﴾ ‫سخ ْر ﴾ ﴿ وم ْريم‬
ْ‫﴿لي‬
1.3.2. ራ መሰረታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ደማ ሲመጣ
﴾ ً‫﴿ أ ِن ا ْشك ْر ﴾ ﴿ وق ْرآنا‬
1.3.3. ራ መሰረታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ምክንያታዊ የሆነ ከስራ ሲመጣ
﴾‫ار ِج ِعي‬ ِ
ْ ﴿ ﴾ ‫﴿ لم ِن ْارتضى ﴾ ﴿ أِم ْارتابوا‬
1.3.4. ራ መሰረታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ከስራ ሲመጣ እና ከሷ ቀጠሎ ደግሞ ፈትሀ የሆነ የሚወፍር
ፊደል ከመጣ (ይህም ቁርአን ላይ የተከሰተው 5ት ቦታ ላይ ብቻ ነው)፡፡
ٍ ‫﴿ قِ ْرط‬, ﴾ ‫ ﴿ فِ ْرق ٍة‬, ﴾ ‫ادا‬
﴾ ‫اس‬ ً ‫ ﴿ وإِ ْرص‬, ﴾ ً ‫ ﴿ ِم ْرص‬, ﴾ ‫اد‬
‫ادا‬ ِ ‫﴿لبِال ِْمرص‬
ْ
1.3.5. ራ ምክንያታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ከያ ውጭ ሱኩን የሆነ ፊደል ሲመጣና ከሱኩኑ በፊት
ፈትሀ ሲመጣ
َّ ‫﴿ إِ َّن ْال ْمر ﴾ ﴿ و‬
﴾ ‫الدار‬
1.3.6. ራ ምክንያታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ስኩን የሆን ፊደል ሲመጣና ከሱኩኑ በፊት ደማ ሲመጣ
َّ ﴿ ﴾ ‫﴿ ص ْفر‬
﴾ ‫الشكور‬
2. ራ የምትቀጥንባቸው አራት ቦታዎች

2.1. ራ ከስራ ሁና ስትመጣ ﴾ ً‫﴿ ب ِرق ﴾ ﴿ ِر ْزقا‬ ‫﴾ وصَل فى آخر الكلمة‬ َّ ِ‫﴿ ب‬
‫الص ْب ِر‬
2.2. ራ ሱኩን ሁና ስትመጣ፡
2.2.1. ራ መሰረታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት መሰረታዊ ከስራ ሲመጣ እና ከሷ ቀጠሎ ደግሞ የሚወፍር
ፊደል ካልመጣ ﴾ ‫﴿ وفِ ْرع ْون‬
2.2.2. ራ ምክንያታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት የሊን ፊደል የሆነችው ያ ሲመጣ
﴾‫﴿ ل ض ْي ر ﴾ ﴿ خ ْي ر‬
2.2.3. ራ ምክንያታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ከሚወፍሩ ፊደሎች ውጭ ሱኩን የሆነ ፊደል ሲመጣ እና
ከሱኩኑ በፊት ከስራህ ሲመጣ ﴾ ‫﴿ ق ِدير﴾ ﴿ ِح ْج ٍر‬

10
3. ራ የምትወፍርባቸው ወይም የምትቀጥንባቸው

3.1. ራ መሰረታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ከስራህ ሲመጣ እና ከሷ ቀጠሎ ደግሞ ከስራህ የሆነ የሚወፍር
ፊደል ከመጣ ﴾ ‫﴿ فِ ْر ٍق‬
3.2. ራ ምክንያታዊ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ሱኩን የሆነ የሚወፈር ፊደል ሲመጣ እና ከሱኩኑ በፊት ከስራህ
ِ
ሲመጣ ﴾ ْ ‫﴿ ال ِْقطْ ِر ﴾ ﴿ م‬
‫صر‬

ሀ. የኑን ሳኪና እና የተንዊን ህግ


 የኑን ሳኪና እና የተንዊን ምንነት ፡
 ኑን ሳኪና ማለት ሱኩን የሆነ ኑን ማለት ነው፡፡
 ተንዊን ማለት በስም መጨረሻ የሚገኝ ተጨማሪ የሆነ ኑን ሱኩን ማለት ነው፡፡
 የኑን ሳኪና እና የተንዊን ህጎች ፡- አራት ህጎች አላቸው፡፡ (ከነሱ በኋላ የመጡትን ፊደሎች በመመልከት)
1. ኢዝሀር
o ከኑን ሳኪና ወይም ተንዊን ካለበት ፊደል በኋላ የኢዝሀር ፊደሎች ከመጡ ኑን ሳኪና ወይም ተንዊን ግልጽ
(ኢዝሀር ) ተደርገው ይነበባሉ።
o የኢዝሀር ፊደሎች ስድስት ናቸው፡፡ እነሱም ‫ خ‬، ‫ غ‬، ‫ ح‬، ‫ ع‬، ‫ ه‬، ‫ء‬
o ስድስቱም የኢዝሀር ፊደሎች ከጉሮሮ ስለሚወጡ ‫ الظْهار الْحل ِْقي‬በመባል ይታወቃል፡፡
o ምሳሌ፡
ከተንዊን ጋር በሁለት ቃል (ኑን በአንድ ቃል (ኑን ሳኪናውና የኢዝሀር ፊደሉ
ሳኪናውና የኢዝሀር ፊደሉ)
ፊደሉ)
﴾ ‫﴿ عذاب ألِيم‬ ﴾ ‫﴿ م ْن ءامن‬ ﴾ ‫﴿ وي ْنأ ْون ع ْنه‬ ‫ء‬

﴾ ‫﴿ إِ ِن ْامرؤ هلك‬ ﴾ ‫اد‬ٍ ‫﴿ ِمن ه‬ ﴾ ‫﴿ ي ْن ه ْون ع ْنه‬ ‫ه‬


ْ
﴾ ‫﴿ ح ِقيق على‬ ﴾ ‫﴿ ِم ْن عل ٍق‬ ﴾ ‫﴿ أنْع ْمت‬ ‫ع‬

﴾‫﴿ نار ح ِامية‬ ﴾ ‫﴿ ِم ْن حسن ٍة‬ ﴾ ‫﴿ وانْح ْر‬ ‫ح‬

﴾ ‫﴿ فظًّا غ ِليظ‬ ﴾ ‫﴿ ِم ْن ِغ ٍّل‬ ﴾ ‫﴿ فسي ْن ِغضون‬ ‫غ‬

﴾ ‫﴿ ذ َّرةٍ خ ْي ًرا ي ره‬ ﴾ ‫﴿ وإِ ْن ِخ ْفت ْم‬ ﴾ ‫﴿ والْم ْنخنِقة‬ ‫خ‬

2. ኢድጋም
o ከኑን ሳኪና ወይም ተንዊን ካለበት ፊደል በኋላ የኢድጋም ፊደሎች ከመጡ ኑን ሳኪናን ወይም ተንዊኑን
የኢደጋም ፊደሎች ውስጥ በማስገባት እናነበዋለን፡፡
o የኢድጋም ፊደሎች ስድስት ናቸው፡፡ እነሱም ‫ ي ر م ل و ن‬በአጭሩ ለመያዝ፡ "‫"يرملون‬
o ኢድጋም ለሁለት ይከፈላል፡፡ እነሱም
2.1. ኢድጋም ቢጉና፡ ከኑን ሳኪና ወይም ከተንዊን በኃላ የኢድጋም ፊደሎች በሁለት ቃል ላይ ሲመጡ ኑን
ሳኪናን ወይም ተንዊንን ከፊደሎች ውስጥ በማስገባትና ጉናን በመጠቀም እናነበዋለን፡፡ ፊደሎቹም አራት
ናቸው፡፡َእነሱም ‫ ي ن م و‬በአጭሩ ለመያዝ፡ ‫ينمو‬

11
ተንዊን በሁለት ቃል(ኑን ሳኪናውና የኢድጋሙ ፊደል) ፊደሉ
﴾‫﴿ق ْوٍم ي ْؤِمنون‬ ﴾‫﴿من ي قول‬ ‫ي‬

﴾‫﴿ ِحطَّة نَّغْ ِف ْر لك ْم‬ ﴾‫﴿ ِمن نَّ ِذي ٍر‬ ‫ن‬

﴾‫اط ُّم ْست ِق ٍيم‬ٍ ‫صر‬ ِ﴿ ٍ ‫﴿ ِمن َّم‬


﴾ ‫ال‬ ‫م‬
ٍ ‫َّات وعي‬
﴾‫ون‬ ٍ ‫﴿جن‬ ﴾ ‫﴿ ِمن ورائِ ِه ْم‬ ‫و‬

o ማሳሰቢያ፡ የኢደጋም ፊደሎች እና ኑን ሳኪና በአንድ ቃል ላይ ከመጡ ኑን ሳኪናው ኢዝሀር ተደርጎ ይነበባል፡፡
‫ الظْهار الْمطلق‬በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም ቁርአን ላይ አራት ቃሎች ላይ ብቻ ነው የተከሰተው፡፡
ِ ﴿ ﴾‫الدنْيا﴾ ﴿قِ ْن وان‬
ምሳሌ፡- ﴾‫ص ْن وان‬ ُّ ﴿ ﴾‫﴿ب ْن يان‬
2.2. ኢድጋም ቢገይሪ ጉና ፡ ኑን ሳኪናውን ወይም ተንዊኑን ኢደጋም ስናደርግ ጉናን አንጠቀምም፡፡
ፊደሎቹም ሁለት ናቸው፡፡ እነሱም ‫ ل ر‬ናቸው፡፡
ተንዊን በሁለት ቃል(ኑን ሳኪናውና የኢድጋሙ ፊደሉ) ፊደሉ
﴾ ‫﴿ ويْل لِّلْمط ِّف ِفين‬ ﴾ ‫﴿ أن لَّن ينقلِب‬ ‫ل‬

﴾ ً‫﴿ ثمرةٍ ِّرْزقا‬ ﴾ ‫﴿ ِمن ربِّ ِه ْم‬ ‫ر‬

3. ኢቅላብ
o ከኑን ሳኪና ወይም ተንዊን ካለበት ፊደል በኋላ ባ ከመጣች ኑን ሳኪናን ወይም ተንዊንን ኢህፋእ እና ጉና
በመጠቀም ወደ ሚም ሳኪና መገልበጥ ማለት ነው። በኑን ላይ እንዲሁም በተንዊኖቹም ላይ ትንሽ ሚም
ይመጣል፡፡
o ምሳሌ፡
﴾ ‫إ َّن هللا َِسي هع ب ِصري‬ ﴿ ﴾ ‫بهو ِرك‬ ‫﴿ ٱن ِبئۡ هم ﴾ ﴿ ٱن‬
4. ኢኽፋእ
o ከኑን ሳኪና ወይም ተንዊን ካለበት ፊደል በኋላ የኢኽፋእ ፊደሎች ከመጡ ኑን ሳኪናን ወይም ተንዊኑን ደብቀን
(በኢዝሀር በኢድጋም መካከል አድረገን) ከጉና ጋር እናነበዋለን፡፡
o ይህ አይነቱ ኢኽፋእ ‫ الخفاء الْح ِق ِقي‬በመባል ይታወቃል፡፡
o የኢኽፋእ ፊደሎች የተቀሩት 15 ፊደላት ናቸው፡፡
‫صذثكجشقسدطزفتضظ‬
o ምሳሌ፡
ከተንዊን ጋር በሁለት ቃል (ኑን በአንድ ቃል (ኑን ሳኪናውና ፊደሉ
ሳኪናውና የኢኽፋው ፊደሉ)
የኢኽፋው ፊደሉ)
﴾‫يحا ص ْرص ًرا‬ ً ‫﴿ ِر‬ ﴾ ‫﴿عن صَلتِ ِه ْم‬ ﴾‫ب‬ ْ ‫﴿فانص‬ ‫ص‬
﴾‫ب‬ ٍ ‫﴿ن ًارا ذات له‬ ﴾ ‫﴿من ذا الَّ ِذي‬ ِ ‫﴿ وأ‬
﴾‫نذ ْره ْم‬ ‫ذ‬
﴾ ‫﴿ ُّمط ٍاع ث َّم أ ِمي ٍن‬ ﴾ ‫﴿ أن ث بَّْت ناك‬ ﴾‫﴿ و ْالنْثى‬ ‫ث‬

12
‫﴿ كِتاب ك ِريم ﴾‬ ‫﴿ ومن كان ﴾‬ ‫﴿ف ِ‬
‫انكحوا ﴾‬ ‫ك‬
‫﴿ رطبًا جنِيًّا﴾‬ ‫﴿ ِمن ج ٍ‬
‫وع ﴾‬ ‫﴿ فأنج ْي ناه ﴾‬ ‫ج‬
‫﴿ جبَّ ًارا ش ِقيًّا﴾‬ ‫﴿ إِن شاء اللَّه ﴾‬ ‫﴿ أنشره ﴾‬ ‫ش‬
‫﴿ س ِميع ق ِريب﴾‬ ‫﴿ عن ِق ْب لتِ ِهم ﴾‬ ‫﴿ أنقض ﴾‬ ‫ق‬
‫﴿ ق ْوًل س ِدي ًدا ﴾‬ ‫﴿ ِمن سَلل ٍة ﴾‬ ‫﴿ ِْ‬
‫النسان ﴾‬ ‫س‬
‫﴿ قِ ْن وان دانِية ﴾‬ ‫﴿ من د َّساها ﴾‬ ‫ادا ﴾‬
‫﴿ أند ً‬ ‫د‬
‫﴿ كلِم ًة طيِّبةً﴾‬ ‫﴿ ِمن ِطي ٍن ﴾‬ ‫﴿ي ِ‬
‫نطقون ﴾‬ ‫ط‬
‫سا زكِيَّةً ﴾‬
‫﴿ ن ْف ً‬ ‫﴿ من زَّكاها ﴾‬ ‫﴿ تن ِزيل ﴾‬ ‫ز‬
‫ب لِي ﴾‬ ‫ِ‬
‫﴿عاق ًرا ف ه ْ‬ ‫ض ِل اللَّ ِه﴾‬
‫﴿ ِّمن ف ْ‬ ‫﴿ ي ِنفقون ﴾‬ ‫ف‬
‫﴿ي ْومئِ ٍذ ت ْعرضون ﴾‬ ‫﴿ ومن تاب﴾‬ ‫﴿ أنت ْم ﴾‬ ‫ت‬
‫﴿ ق ْوًما ضالِّين ﴾‬ ‫﴿ ومن ض َّل ﴾‬ ‫﴿ َّمنض ٍ‬
‫ود ﴾‬ ‫ض‬
‫﴿ ِظ ًَّل ظلِ ًيَل ﴾‬ ‫﴿ من ظلم ﴾‬ ‫﴿ ينظرون﴾‬ ‫ظ‬

‫‪ለ. የሚም ሳኪና ህግ ፡‬‬


‫‪ የሚም ሳኪና ምንነት ፡‬‬
‫‪ ሚም ሳኪና ማለት ሱኩን የሆነ ሚም ማለት ነው፡፡‬‬
‫)‪ የሚም ሳኪና ህጎች ፡ ሶስት ናቸው፡፡ (ከነሱ በኋላ የመጡትን ፊደሎች በመመልከት‬‬
‫‪1. ኢኽፋእ‬‬
‫‪) ከመጣች ሚም ሳኪና ኢኽፋእ ትሆናለች።‬ب(‪ከሚም ሳኪናበኋላ ባ‬‬
‫‪o ጉናን በመጨመር እናነባታለን፡፡‬‬
‫شف ِوي ‪o ይህ አይነቱ ኢኽፋእ‬‬
‫‪ በመባል ይታወቃል፡፡‬الخفاء ال َّ‬
‫‪o ምሳሌ፡-‬‬
‫﴿ ذلِكم بِأنَّكم ﴾ ﴿ ما لهم بِ ِه ِم ْن ِعل ٍْم ﴾‬
‫‪2. ኢድጋም ፡‬‬
‫‪o ከሚም ሳኪና በኋላ ሚም ከመጣች ሚም ሳኪና ኢድጋም ትሆናለች፡፡‬‬
‫‪o ጉናን በመጨመር እናነባታለን፡፡‬‬
‫الصغير ‪o ይህ አይነቱ ኢድጋም‬‬
‫‪ በመባል ይታወቃል፡፡‬الدغام المتماثلين َّ‬
‫‪o ምሳሌ፡-‬‬
‫﴿ ف ل َّما جاءهم َّما عرفوا ﴾ ﴿ وما لهم ِّمن دونِِه ِمن و ٍال ﴾ ﴿وِم ْن هم َّمن كفر﴾‬
‫‪3. ኢዝሀር‬‬
‫‪o ከሚም ሳኪና በኋላ ከሚም እና ባ ውጪ የተቀሩት 26ቱ የአረብኛ ፊደላት ከመጡ ሚም ሳኪና ኢዝሀር‬‬
‫‪ትሆናለች፡፡‬‬
‫‪ በመባል ይታወቃል፡፡‬ألظهار الشفوي ‪o ይህ አይነቱ ኢዝሀር‬‬

‫‪13‬‬
o ከሚም ሳኪና በኋላ ዋው(‫ )و‬እና ፋ (‫ ) ف‬ሲመጡ ኢኽፋእ እንዳይሆኑብን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡
o ምሳሌ፡-
﴾ ‫﴿ مث له ْم كمث ِل ﴾ ﴿ أنْ ع ْمت عل ْي ِه ْم ﴾ ﴿ ت ْمسون‬

ሐ. የኑን ሸዳ እና የሚም ሸዳ ህግ
 የኑን ሸዳ እና የሚም ሸዳ ምንነት ፡
 ኑን ሸዳ ማለት የሸዳ ምልክት ያለው ኑን ማለት ነው፡፡ ‫ ن‬+ ْ‫نَّ = ن‬
 ሚም ሸዳ ማለት የሸዳ ምልክት ያለው ሚም ማለት ነው፡፡ ‫ م‬+ ‫َّم = ْم‬
 ሚምና ኑን ሸድዳ ሆነው በቃላት መካከል፣ በቃላት መጨረሻ፣በስም በግስና በፊደል ላይ ይመጣሉ፡፡
 የኑን ሸዳ እና የሚም ሸዳ ህግ ፡
 ኑን ላይ እና ሚም ላይ ሸዳ ካለባቸው ሁልጊዜም በጉና ይነበባሉ፡፡
 ምሳሌ፡
﴾ ‫﴿ ول َّما ﴾ ﴿ ث َّم ﴾ ﴿ وأ َّن ﴾ ﴿ الْجنَّة‬
መ. የላም ሳኪና ህግ ፡
 የላም ሳኪና ምንነት፡
 ላም ሳኪና ማለት ሱኩን የሆነ ላም ማለት ነው፡፡ ከሚገኙበት ቦታ አንፃር አምስት(5) አይነት የላም
ሱኩኖች ቁርአን ላይ መተዋል፡፡ እነሱም ‫( المات الساكنة‬ላማቱ አሳኪናህ) በመባል ይታወቃሉ፡፡
 የላም ሳኪና አይነቶች፡
1. ‫ الم التعريف‬/ ‫ الم ال‬፡በስም መጀመሪያ ላይ ሀምዘቱል ወስል ቀድማት የምትመጣ ላም ሱኩን ናት፡፡
2. ‫ الم الفعل‬፡ በግስ ላይ የምትገኝ ላም ሱኩን ናት፡፡
3. ‫ الم الحرف‬፡ በሀርፍ ላይ የምትገኝ ላም ሱኩን ናት፡፡
4. ‫ الم اإلسم‬፡ ስም ላይ የምትገኝ ላም ሱኩን ናት፡፡
5. ‫ الم األمر‬፡ ከፊዕሉል ሙዳሪዕ በፊት አያያዥ ፊደላት ሁል ጊዜ ኢዝሀር አድርገን እናነባቸዋለን
ቀድመዋት የምትመጣ ትዕዛዛዊ ላም ሱኩን ናት

1. ላመል አል (ላም አት-ተዕሪፍ)፡


 በስም መጀመሪያ ላይ ሀምዘቱል ወስለል ቀድማት የምትመጣ ሱኩን የሆነች ላም ማለት ነው፡፡
 በሁለት ይከፈላል፡፡
i. አል-ቀመሪያ ፡ ግልፅ(ኢዘሀር) የምትሆነዋ ላመል አል
o ከላመል አል በኋላ የአል-ቀመሪያ ፊደል ሲመጡ ላም ሱኩንዋን ግልፅ አድርገን እናነባታለን፡፡
o የአል-ቀመሪያ ፊደላት አስራ አራት ናቸው፡፡በሚቀጥለው አረፍተ ነገር ላይ ተሰብስበዋል፡፡
o ‫ف ع ِقيمه‬
ْ ‫إِبْغِ ح َّجك وخ‬
o ምሳሌ፡

*‫ٱ ْل َّول* ٱلْكبِير* ٱلْقيُّوم* ٱلْباب* ٱلْوادود* ٱلْي ِّم* ٱلْغابِ ِرين* ٱلْخبِير ٱلْملْك* ٱلْح ْمد* ٱلْف ْج ِر‬
ِ ‫ٱلْهدى * ٱلْجبَّار ٱل‬
*‫ْعاملِين‬

14
ii. አሽ-ሸምስያ ፡ ኢድጋም የምትሆነዋ ላመል አል
o ከላመል አል በኋላ የአሽ-ሸምሲያ ፊደላት ሲመጡ ላም ሱኩንዋን ኢድጋም እናደርጋታለን፡፡
o የአሽ-ሸምሲያ ፊደላት አስራ አራት ናቸው፡፡ እነሱም የተቀሩት 14 ፊደላት ናቸው፡፡
‫ل‬،‫ش‬،‫ز‬،‫ظ‬،‫س‬،‫د‬،‫ن‬،‫ذ‬،‫ض‬،‫ت‬،‫ر‬،‫ص‬،‫ث‬،‫ط‬
o ምሳሌ፡

ِ ‫لش ْم‬
*‫س‬ ِ ‫لصابِ ِرين* ٱلن‬
َّ ‫َّاس* ٱ‬ َّ ‫ات* ٱ ُّلزجاجة* ٱ‬ ِ ‫لذاكِر‬ ِ ‫ٱلطَّ َّامة * ٱلضَّالِّين* ٱلظَّانِّين * ٱلثَّق‬
َّ ‫َلن* ٱ‬
‫لسائِحون‬ َّ ‫اب* وٱللَّْي ِل* ٱلتَّائِبون * ٱ‬ َّ ‫ٱ َّلرِح ِيم* ٱ‬
ِّ ‫لدو‬

2. ላመል ፊዕል፡
ِ ‫) فِعل ٱلم‬፣ በአሁንና በመጪ ጊዜ
 በሶስቱም የግስ አይነቶች ላይ ትገኛለች፡፡ማለትም በአላፊ ግስ( ‫اضي‬
ግስ( ‫ ) فِعل ٱلمضارِع‬ወይም በትእዛዛዊ ግስ ) ‫)فِعل ٱلم ِر‬ሊሆን ይችላል።
ِ ‫ )فِعل ٱلم‬፡ ﴾ ‫﴿ أنزلْنا‬
 ምሳሌ፡ አላፊ ግስ( ‫اضي‬
የአሁንና የመጪ ጊዜ ግስ ( ‫ ) فِعل ٱلمضارِع‬፡ ﴾ ‫﴿ي لْت ِقطْه‬
ትእዛዛዊ ግስ ) ‫)فِعل ٱلم ِر‬፡ ﴾ ‫﴿ وت وَّك ْل‬
 ሁለት አይነት ሁኔታዎች አላት፡
1. ኢድጋም ፡ ከነሱ በኋላ ላም ወይም ራ ከመጡ ላም ሱኩንዋ ኢድጋም ትሆናለች፡፡
ምሳሌ፡ ﴾ ‫ب‬ ِّ ‫﴿ قل َّر‬
2. ኢዘሀር ፡ ከነሱ በኋላ ከላም እና ራ ውጪ የተቀሩት 26ቱ የአረብኛ ፊደላት ከመጡ ላም ሱኩንዋ
ኢዘሀር(ግልፅ) ትሆናለች፡፡
ምሳሌ፡ ﴾ ‫﴿ وجعلْنا ﴾ ﴿ ق ْل ن ع ْم‬
3. ላመል ሀርፍ
 በሀርፎች(‫ ) ح ْرف الْم ْعنى‬ላይ የምትገኝ ላም ሱኩን ነች፡፡ቁርአን ውስጥ በሁለት ሀርፎች ብቻ ነው
የምትገኘው፡፡ እነሱም ‫ بل‬: ‫ هل‬ናቸው፡፡
 ሁለት አይነት ሁኔታዎች አላት፡
I. ኢድጋም፡ ከነሱ በኃላ ላም ወይም ራ ከመጡ ላም ሱኩንዋ ኢድጋም ትሆናለች ፡፡
ምሳሌ፡ ﴾ ‫﴿ هل لك ْم ﴾ ﴿ بل رف عه اللَّه إِل ْي ِه ﴾ ﴿ ك ََّل بل ل ت ْك ِرمون الْيتِيم‬
II. ኢዘሀር ፡ ከነሱ በኃላ ከላም እና ራ ውጪ የተቀሩት 26ቱ የአረብኛ ፊደላት ከመጡ ላም ሱኩንዋ
ኢዘሀር(ግልፅ) ትሆናለች ፡፡
ምሳሌ፡ ﴾ ‫﴿ ه ْل أتاك ﴾ ﴿ ك ََّل ب ْل تك ِّذبون بِالدِّي ِن‬

15
መድ(‫) المد‬
 የመድ ምንነት፡
 ቋንቋዊ ትርጓሜው ፡- መጨመር ወይም መወጠር ማለት ነው፡፡
 በተጅዊድ ምሁራን አተረጋጎም ፡- የመድ ፊደሎች ላይ ድምጽን ማስረዘም ማለት ነው፡፡

 የመድ ፊደሎች፡
 የመድ ፊደሎች ሶስት ናቸው፡ እነሱም፡
1. አሊፍ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ፈትሀ ሲመጣ ፡ ለምሳሌ፡- ﴾ ‫﴿ قال‬
2. ያ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ከስራ ሲመጣ ፡ ለምሳሌ፡- ﴾ ‫﴿ قِيل‬
3. ዋው ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ደማ ሲመጣ ፡ ለምሳሌ፡- ﴾ ‫﴿ ي قول‬
 የሊን ፊደሎች ሁለት ሲሆኑ እነሱም፡-
1. ዋው ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ፈትሀ ሲመጣ ﴾ ‫﴿ ي ْوم‬
ٍ ْ‫﴿ ق ري‬
2. ያ ሱኩን ሁና ከሷ በፊት ፈትሀ ሲመጣ ﴾ ‫ش‬
 የመድ አይነቶች፡
 በአጠቃላይ መድ በሁለት ይከፈላል።እነሱም ፡
 መዱል አስልይ(‫الصلي‬ ‫)المد‬
 መዱል ፈርዒይ(‫الفرعي‬ ‫)َالمد‬
1. መዱል አስልይ( ‫)المد األصلي‬፡
 ከመድ ፊደላት በኃላ ከሀምዛ ወይም ከሱኩን ውጪ ያሉት ፊደሎች ከመጡ ይህ መድ መዱል አስልይ ይባላል፡፡
የሚሳበውም በሁለት(2) ሀረካ ነው፡፡
ምሳሌ፡ ﴾ ‫صراط الَّ ِذين‬ ِ ‫﴿ن‬
ِ ﴿ ﴾ ‫وحيها‬
 ይህ አይነቱ መድ መዱል አስልይ (መሰረታዊ መድ) የተባለበት ምክንያት ለመዱል ፈርእይ መሰረት ስለሆነ
ነው።
 መዱል አስልይ በሌላ አጠራር መዱ ጠብእይ(‫ ) المد الطبعي‬ወይም መዱ ዛትይ(‫ ) المد الذاتي‬ተብሎ
ይታወቃል፡፡ ይህም የተባለበት ምክንያት እሱ ከተወገደ የቃሉ ማንነት አብሮ ስለሚወገድ ነው፡፡
2. መዱል ፈርዒይ(‫)المد الفرعي‬
 ከመድ ፊደላት በኃላ ሀምዛ ወይም ሱኩን ከመጡ ይህ መድ መዱል ፈርዒይ ይባላል፡፡
 በዚህ የመድ አይነት ግዜ በመዶቹ ፊደል አናት ላይ ~ ምልክት ይቀመጣል፡፡
 በአጠቃላይ መዱል ፈርዒይ በ 5 ይከፈላል። እነሱም፡
 1. መዱል ሙተሲል(‫)َالمدَالمتصل‬፣
 2. መዱል ሙንፈሲል(‫)َالمدَالمنفصل‬፣
 3. መዱል አሪዱ ሊሱኩን (‫)المد العارضَللسكون‬፣
 4. መዱል በደል ( ‫ )المد البدل‬፣
 5. መዱል ላዚም( ‫)المدَالالزم‬

16
2.1. መዱል ሙተሲል ፡
 ሙተሲል ማለት የተያያዘ ማለት ነው፡፡
 ከመድ ፊደል በኋላ ሀምዛ ከመጣና የመዱ ፊደል እና ሀምዛ በአንድ ቃል ላይ ከሆኑ የመዱ አይነት መዱል
ሙተሲል ይባላል።የመዱ መጠን በ 5 ወይም 4 ሀረካ ተደርጐ ይነበባል፡፡ ምሳሌ ፡

ُّ ‫ و‬،}‫ و {سواء‬،}‫ و {م ِريئًا‬،}‫ و {هنِيئًا‬،}‫ و {و ِجيء‬،}‫{جاء‬


،}‫{السوء‬
2.2. መዱል ሙንፈሲል ፡ }‫{أولئِك‬
 ሙንፈሲል ማለት የተነጣጠለ ማለት ነው፡፡
 ከመድ ፊደል በኋላ ሀምዛ ከመጣና የመዱ ፊደል እና ሀምዛ በሁለት ቃል ላይ ከሆኑ የመዱ አይነት መዱል
ሙንፈሲል ይባላል፡፡
 የመዱ መጠን ሲያጥር በሁለት(2)ሀረካ፣በመካከለኛ ከሆነ በአራት(4)ሀረካ፣ሲረዝም በአምስት(5)ሀረካ
ተደረጐ ይነበባል። ምሳሌ፡

،}‫ و {بنِي إِ ْسرائِيل‬،}‫ و {قوا أنفسك ْم‬،}‫{أتى أ ْمر اللَّ ِه‬

2.3. መዱል በደል ፡


 ከመድ ፊደል በፊት ሀምዛ ከመጣ የመዱ አይነት መዱል በደል ይባላል፡፡ በሁለት ሀረካ ይሳባል። ምሳሌ ፡

}‫ و {أوتوا ال ِْعلْم‬،}‫ و {إِيمانًا‬،}‫{ءادم} و {ءازر‬


2.4. መዱል አሪዱ ሊሱኩን ፡
 ከመድ ወይም ከሊን ፊደል በኋላ ድንገተኛ የሆነ ሱኩን(በመቆም ምክንያት የተከሰተ ሱኩን ) ከመጣ የመዱ
አይነት መዱል አሪዱ ሊሱኩን ይባላል፡፡
 የመዱ መጠን ሲያጥር በሁለት(2)ሀረካ፣በመካከለኛ ከሆነ በአራት(4)ሀረካ፣ሲረዝም በስድስት(6)ሀረካ
ተደረጐ ይነበባል። ምሳሌ ፡

}‫ و {ٱلْم ْف ِلحون‬،}‫ و {ن ْست ِعين‬،}‫{ٱ َّلر ْحم ِن ٱ َّلرِح ِيم‬


2.5. መዱል ላዚም ፡
 ከመድ ወይም ከሊን ፊደል በኋላ መሰረታዊ የሆነ ሱኩን(በምናቆምበትም ሆነ በምንቀጥልበት ጊዜ የሚገኝ
ሱኩን) በአንድ ቃል ከመጣ የመዱ አይነት መዱል ላዚም ይባላል፡፡
 የሚከሰተውም በቃል(‫ )كلمة‬ወይም በፊደል(‫ )حرف‬ሊሆን ይችላል፡፡
 የመዱ መጠንም ግዴታ በስድስት(6) ሀረካ ተደርጎ ይነበባል፡፡
 መዱል ላዚም ከቦታቸው አንጻር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነሱም፡
 ከሊሚይ፡- የመዱ ፊደል እና ሱኩኑ ቃል(‫)كلمة‬ላይ የሚገኙ ከሆነ፣ እና
 ሀርፊይ ፡- የመዱ ፊደል እና ሱኩኑ ፊደል(‫ )حرف‬ላይ የሚገኙ ከሆነ ፡፡
 መዱል ላዚም ሀርፊይ ሚከሰተው የሚከተሉትን ሶስት መስፈርቶች ባሟሉ የፊደላት መጠሪያ ስሞች
ላይ ነው፡፡
I. የፊደሉ መጠሪያ ስም ከሶስት ፊደላት መገንባት አለበት፡፡
II. ከሶስቱ ፊደላት መካከለኛው የመድ ፊደል መሆን አለበት፡፡
III. ሶስተኛው ፊደል መሰረታው ሱኩን መሆን አለበት፡፡
 መዱል ላዚም ሀርፊይ የሚከሰተው ከላይ የተጠቀሰውን ሶስት መስፈርቶች ባሟሉ የሱራ መክፈቻ
ላይ በመጡ ስምንት ሀረፎች ላይ ነው፡፡ እነሱም፡- ‫ ك م ع س ل ن ق ص‬ናቸው፡፡ በአጭሩ

17
‫كم عسل نقص‬ ‫ صا ْد‬,‫اف‬
ْ ‫ ق‬,‫ نو ْن‬,‫ ل ْم‬,‫ين‬ ِ ِ ْ
 = ْ ‫ س‬,‫عي ْن‬
ْ ,‫يم‬
ْ ‫ م‬,‫كاف‬
= በ6 ሀረካ ይሳባሉ፡፡
 ሌላ በሱራ መክፈቻ ላይ የሚመጡ ቃሎች ስድስት ናቸው፡፡ እነሱም ‫ ح ي ط ا ه ر‬በአጭሩ፡፡

 ‫حي طاهر‬ = ‫ را‬,‫ ها‬,‫ طا‬,‫ يا‬, ‫حا‬ በ2 ሀረካ ይሳባሉ፡፡


‫إ‬ = ‫ الف‬የመድ ፊደል ስለሌለው ምንም ሀረካ አይሳብም፡፡
 ሁለቱም የመዱል ላዚም አይነቶች ለሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡
 ሙኸፈፍ(َ‫) ُمخفف‬፡ ሱኩኑ ግለፅ ከሆነ እና
 ሙሠቀል(‫)م َثقل‬፡ ሱኩን የሆነው ፊደል ከሚቀጥለው ፊደል ጋር ኢድጋም ከተደረገ
 ስለዚህ መዱል ላዚም በአጠቃላይ በአራት(4) ይከፈላል።እነሱም
 1. መዱል ላዚም ከሊሚዩን ሙሰቀል፡ በአንድ ቃል ላይ ከመድ ፊደል በኋላ መሰረታዊ የሆነ ሱኩን
መምጣትና ሱኩኑ ኢድጋም ከተደለገ፡፡

﴾‫لصاخَّة﴾ ﴿ٱلطَّ َّامة‬


َّ ‫﴿ٱلضَّالِّين﴾ ﴿ٱلْحاقَّة﴾ ﴿ٱ‬
 2. መዱል ላዚም ከሊሚዩን ሙኸፈፍ፡ በአንድ ቃል ላይ ከመድ ፊደል በኋላ ግልፅ የሆነ መሰረታዊ
የሆነ ሱኩን ከመጣ፡፡

﴾ ‫﴿ ءآلْئن‬
 3. መዱል ላዚም ሀርፊዩን ሙሠቀል ፡ በአንድ ፊደል ላይ ከመድ ፊደል በኋላ መሰረታዊ የሆነ ስኩን
መምጣትና ሱኩኑ ኢድጋም ከተደለገ፡፡

“ላም“ ስንል የተፈጠረው : ﴾‫يم = ﴿ إلم‬ ْ ِ‫أل‬


ْ ‫ف لم ِّم‬
 4. መዱል ላዚም ሀርፊዩን ሙኸፈፍ፡ በአንድ ፊደል ላይ ከመድ ፊደል በኋላ ግልፅ የሆነ መሰረታዊ
የሆነ ሱኩን ከመጣ፡፡

“ላም“ ስንል የተፈጠረው : ﴾ ‫﴿ إلر‬ = ‫ألِ ْف ل ْم را‬


 ማሳሰቢያ፡ በቁርኣን ውስጥ 29 ሱራዎች በፊደላት ብቻ ይጀምራሉ፡፡ ትርጉማቸውን አላህ(‫ )سبحانه وتعالى‬ያውቃል፡
፡ ነገር ግን የአላህ(‫ ) سبحانه وتعالى‬ቃል መሆናቸውንና ልክ እንደወረዱ አድርጎ ማንበቡ ግዴታ ነው፡፡ ፊደሎቹም
በአጠቃላይ 14 ሲሆኑ
እነሱም፡- )‫ ك‬,‫ ع‬,‫ ط‬,‫ ق‬, ‫ ن‬,‫ م‬,‫ ا‬,‫ ر‬,‫ ي‬,‫ ح‬,‫ س‬, ‫ ه‬,‫ ل‬,‫(ص‬
በአጭሩ ለመያዝ፡ )‫(صِ ْله س َحيْرً ا مِنْ َق ْط َع َك‬

 ከቁርአን ለአስራ አራቱም ፊደሎች ምሳሌ፡-


﴾ ‫﴿يس ﴾ ﴿طس ﴾ ﴿طسم ﴾ ﴿طه ﴾ ﴿كهيعص ﴾ ﴿ المر﴾ ﴿الر ﴾ ﴿المص ﴾ ﴿إلم‬
﴾ ‫﴿ن ﴾ ﴿ق ﴾ ﴿ ح عسق ﴾ ﴿ ح ﴾ ﴿ص‬

18
ተጨማሪ የመድ አይነቶች
A. መዱል ዒወድ( ‫ ) المد العوض‬፡ በፈትሀተይን በምናቆምበት ጊዜ ወደ አሊፍ መድ ቀይረን እናነባለን፡፡ ይህ
አይነት መድ መዱል ዒወድ ይባላል፡፡ ሚሳበውም ሁለት ሀረካ ነው፡፡
ምሳሌ፡-
 ﴾‫﴿ حسنًا‬ ﴾‫﴿ حسنا‬
 ﴾ ‫﴿أح ًدا‬ ﴾ ‫﴿أحدا‬

ማሳሰቢያ ፡
 ሀምዛ ላይ ፈትሀተይን በሚፃፍበት ወቅት ከአሊፍ ጋር ወይም ያለ አሊፍ ልትፃፍ ትችላለች፡፡ ነገርግን
በፈትሀተይን የተፃፈች ሀምዛ ላይ ሁል ጊዜ በመዱል ዒወድ እናቆማለን፡፡

 ﴾‫﴿ مآ ًء‬ ﴾‫﴿ مآءا‬


 ﴾ ‫﴿ش ْيئًا‬ ﴾ ‫﴿ ش ْيئا‬

 ታ መርቡጣ )‫ (ة‬ላይ ፈትሀተይን በሚፃፍበት ወቅት አሊፍ አይፃፍም ስናቆምም ወደ ሀ(‫ )ه‬ሱኩን
ቀይረን ነው፡፡

 ﴾‫﴿ وشجرًة‬ ﴾‫﴿ وشجرْه‬


 ﴾ً‫﴿جنة‬ ﴾ ‫﴿ جن ْه‬

B. መዱ ሲላህ( ‫) المد الصلة‬፡ በሁለት በተሀረኩ ፊደሎች መሀል የምትመጣ እሱነትን የምታመለክት ሀ(‫ )ه‬ላይ
የሚፈጠር የመድ አይነት ነው፡፡ መድ መኖሩን ትንሽዬ የሆነች ዋው ወይም ያእ ያመለክታሉ፡፡ መዱ ሲላህ
በሁለት ይከፈላል ፡
1. መዱ ሲለቱ ሱገራህ፡ ከሀምዘተል ቀጥዕ ውጪ ያሉት ፊደሎች ከሓእ በኃላ ሲመጡ የሚፈጠር የመደ
ሲላህ አይነት ነው፡፡ ሚሳበው ሁለት ሀረካ ነው፡፡
ምሳሌ፡-

2. መዱ ሲለቱ ኩብራህ ፡ ከ ሀ በኃላ ሀምዘቱል ቀጥዕ ሲመጣ የመሚፈጠር የመደ ሲላህ አይነት ነው፡፡
ሚሳበውም በ2 ፣4፣5 ሀረካ ነው፡፡
ምሳሌ፡-

19
የመድ ደረጃ
 ላዚም፡ ሁሉም የተጅዊድ ምሁራኖች በመሳቡና የሚሳበው ሀረካ ላይ ይስማማሉ፡፡
ምሳሌ፡ የመዱ ላዚም ክፍሎች
 ዋጂብ፡ ሁሉም የተጅዊድ ምሁራን በመሳቡ ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን ስንት ሀረካ ይሳባል በሚለው ላይ
ተለያይተዋል፡፡
ምሳሌ፡ መዱል ሙተሲል
 ጃኢዝ፡ በመሳቡና በማሳጠሩ እንዲሁም በሚሳበው ሀረካ ላይ የተጅዊድ ምሁራን ተለያይተዋል፡
ምሳሌ፡ መዱል ሙንፈሲል፣ መዱ ሲለቱል ኩብራህ፣ መዱል ዓሪዱን ሊሱኩን እና መዱ ሊን

ማሳሰቢያ፡
 በአንድ የመድ ፊደል ምክንያት የተለያዩ መዶች ከመጡ ደካማ የሆነውን መድ በመተው ብርቱ በሆነው
መድ ይስባል፡፡
َّ ‫ ﴿ ء‬በመዱል ላዚም እናነበዋለን
ምሳሌ፡ መዱ ላዚምና መዱል በደል፡- ﴾‫آلذكريْ ِن‬
መዱ ሙተሲልና መዱል በደል፡- ﴾ ‫َّاس‬ ِ ‫ ﴿ ِرئاء الن‬በመዱል ሙተሲል እናነበዋለን
መዱ ሙንፈሲልና መዱል በደል፡- ﴾‫ ﴿ وجاءوا أباه ْم‬በመዱል ሙንፈሲል እናነበዋለን
 ከመድ ፊደል በኋላ ሱኩን ከመጣ እና ሱኩኑ እና የመዱ ፊደል በሁለት ቃል ላይ ከሆኑ መዱ
ይወድቃል፡፡
 ምሳሌ፡- ِ ‫ات وما فِي ْٱل ْر‬
﴾‫ض‬ َّ ‫﴿ ول ٱلضَّالِّين ﴾ ﴿ له ما فِي‬
ِ ‫ٱلسماو‬

ሀምዘቱል ወስል
 እሷን ከያዘው ቃል የምንጀምር ከሆነ የምትነበብ እንዲሁም እሷን ከያዘው ቃል በፊት ሌላ ቃል ኖሮ ሁለቱንም
(ማለትም ሀምዘቱል ወስልን የያዘውን ቃል እና ከሱ በፊት ያለውን ቃል) አያይዘን በምናነብነት ጊዜ የማትነበብ
የሆነች ሀምዛ ነች፡፡
 በቃላት መጀመሪያ ሱኩን በሚመጣበት ጊዜ ንባቡን ቀላል ለማድረግ ትመጣለች፡፡ስለዚህ አያያዝ ሀምዛ ተብላ
ትታወቃለች፡፡
 በግስ )‫( الْ ِف ْعل‬፣ በስም)‫ال ْسم‬
ِْ (ና በፊደል )‫ (ح ْرف الْم ْعنى‬ላይ ትገኛለች ፡፡
 ከሀምዘቱል ወስል ጀምረን ስናነብ ሊኖራት የሚችለው ሁኔታ፡፡በሶስት ከፍለን ልናይ እንችላለን፡፡

1. ከላመተዕራፍ በፊት የምትመጣው ሀምዘቱል ወስል


 በዚህ ጊዜ ሀምዘቱል ወስል ሁልጊዜ ፈትሀ ተደርጋ ትነበባለች ፡፡
ِ ‫﴿ ٱ َّلرِح‬
ምሳሌ፡ ﴾ ‫يم ﴾ ﴿ ٱلْح ْمد‬
2. በስም መጀመሪያ ላይ የምትመጣዋ ሀምዘቱል ወስል
 በስም ውስጥ ሀምዘቱል ወስል ሁልጊዜ ከስራህ ተደርጋ ትነበባለች
ምሳሌ፡ ﴾ ‫﴿ ٱبْنت ﴾ ﴿ ٱ ْمرأت‬
3. በግስ መጀመሪያ ላይ የምትመጣዋ ሀምዘቱል ወስል
 በግስ ላይ ሀምዘቱል ወስል ስትመጣ ሁለት ሁኔታ ብቻ ነው ያላት፡፡ እነሱም ደማህ እና ከስራህ
ናቸው፡፡

20
 ሀምዘቱል ወስል በግስ ላይ ደማህ የምትሆነው በአንድ ሁኔታ ብቻ ነው፡፡
3.1. ከሀምዘቱል ወስል ተጀምሮ ሲቆጠር የግሱ ሶስተኛ ፊደል መሰረታዊ የሆነ ደማ ከሆነ ሀምዘቱል ወስል
ደማ ተደርጋ ትነበባለች ፡፡
ምሳሌ፡- ﴾ ‫َّت‬
ْ ‫﴿ ٱ ْدعوا ﴾ ﴿ ٱ ْجتث‬
 ሀምዘቱል ወስል በግስ ላይ ከስራህ ተደርጋ የምትነበበው በሶስት ሁኔታ ነው፡፡
3.2. ከሀምዘቱል ወስል ተጀምሮ ሲቆጠር የግሱ ሶስተኛው ፊደል ከስራህ ከሆነ ሀምዘቱል ወስል ከስራህ
ተደርጋ ትነበባለች፡፡
ምሳሌ፡- ﴾ ‫صبِ ْر‬ْ ‫ف﴾ ﴿ٱ‬ْ ‫﴿ ٱ ْك ِش‬
3.3. ከሀምዘቱል ወስል ተጀምሮ ሲቆጠር የግሱ ሶስተኛው ፊደል ፈተሀ ከሆነ ሀምዘቱል ወስል ከስራህ
ተደርጋ ትነበባለች፡፡
ምሳሌ፡- ﴾ ‫﴿ ٱتَّقوا‬ ﴾ ‫﴿ ٱ ْست ْغ ِفروا‬
3.4. ከሀምዘቱል ወስል ተጀምሮ ሲቆጠር የግሱ ሶስተኛው ፊደል ምክንያታዊ ደማ ከሆነ ሀምዘቱል ወስል
ከስራህ ተደርጋ ትነበባለች፡፡ይህም ቁርአን ላይ የተከሰተው በአራት ግሶች ብቻ ነው፡፡

ምሳሌ፡- ﴾ ‫﴿ ٱئْ توا ﴾ ﴿ ٱقْضوا ﴾ ﴿ ٱ ْمشوا ﴾ ﴿ ٱبْ نوا‬

የሀምዘቱል ወስል በግስ መጀመሪያ ላይ


ሀምዝ ከስራህ የምትሆነው ፡- ሀምዝ ደማህ የምትሆነው ፡-
1. ሶስተኛው ፊደል ከስራህከሆነ
2. ሶስተኛው ፊደል ፈትሀ ከሆነ ሶስተኛው ፊደል መሰረታዊ ዶምማ ከሆነ ብቻ
3. ሶስተኛው ፊደል ምክንያታዊ ዶምማ ከሆነ ነው፡፡

በቁርአን ውስጥ የመጨረሻ ቃላት ላይ አቋቋም


 በዐረብኛ ሰዋሰው ማንኛውም ቃል በሱኩን አይጀመርም በሀረካ ደግሞ አይቆምም፡፡

1. የመጨረሻ ፊደላቸው ሱኩን ወይም የተሀረከ የሆነ ቃላቶች ላይ እንዴት ማቆም እንዳለብን የሚያሳይ
ሰንጠረዥ
የአቋቋም አይነት (በሱኩን) ምሳሌ የመጨረሻው ፊደል ላይ ያለው
ምልክት
﴾ ‫﴿ ِم ْن‬ ﴾ ‫﴿ ِم ْن‬ መሰረታዊ ሱኩን

﴾ ‫ين‬ ِ ﴾ ‫﴿ الْعال ِمين‬


ْ ‫﴿ الْعالم‬
ፈታሀ

﴾ ‫يم‬ ِ َّ ﴿ ﴾ ‫الرِح ِيم‬


ْ ‫الرح‬
ከስራ
َّ ﴿
﴾ ‫ين‬ ِ ﴾ ‫﴿ ن ْست ِعين‬
ْ ‫﴿ ن ْستع‬
ዶምማ
ማብራሪያ፡- ሁሉንም የመጨረሻ ፊደሎች ሱኩን አድርገን እናቆማቸዋለን፡፡

21
2. የመጨረሻ ፊደላቸው ተንዊን የሆኑ ቃላቶች ላይ እንዴት ማቆም እንዳለብን የሚያሳይ ሰንጠረዥ

የአቋቋም አይነት ምሳሌ ተንዊን


﴾ ‫﴿ علِيما‬ ﴾ ‫يما‬ ِ
ً ‫﴿ عل‬
ፈተሀተይን

﴾ ‫يم‬ ِ ﴾ ‫﴿ ح ِكيم‬
ْ ‫﴿ حك‬
ደምመተይን

﴾ ‫﴿ وإِ ْست ْب ر ْق‬ ﴾ ‫﴿ وإِ ْست ْب ر ٍق‬ ከስረተይን


ማብራሪያ፡- ፈተሀተይን ብቻ ወደአሊፍ ቀይረን ስናነብ ሌሎቹን ተንዊኖች ግን ሱኩን አድርገን እናቆማለን፡፡
3. የመጨረሻ ፊደላቸው መድ ከሆኑ ምናቆመው ባሉበት ሁኔታ ነው፡፡

የአቋቋም አይነት ምሳሌ የመዱ አይነት


﴾ ‫﴿ أن ي ْدخلوها‬ ﴾ ‫﴿ أن ي ْدخلوها‬ አሊፍ መድ

﴾ ‫﴿ أ َّل ت ْحزنِي‬ ﴾ ‫﴿ أ َّل ت ْحزنِي‬ ያ መድ

﴾ ‫﴿ ول ت ْعتدوا‬ ﴾ ‫﴿ ول ت ْعتدوا‬ ዋው መድ

22
‫‪በቁርአን ውስጥ ያሉ የተለያዩ የማቆሚያ ምልክቶች‬‬

‫‪-----የዚህ አይነት ምልክት ያለበት የቁርአን ቃል ላይ ማቆም ግዴታ ነው፡፡‬‬

‫ۘ‬ ‫سمعون والْم ْوتى ي ْب عث هم اللَّه ث َّم إِل ْي ِه ي ْرجعون ﴾ ‪ምሳሌ፡-‬‬ ‫َّ ِ‬ ‫ِ‬
‫﴿ إِنَّما ي ْستجيب الذين ي ْ‬

‫ال‬ ‫‪----- የዚህ ዓይነት ምልክት ያለበት የቁርአን ቃል ላይ ማቆም ክልክል ነው፡፡‬‬

‫صحاب النَّا ِر إَِّل مَلئِكةًۙ وما جعلْنا ِع َّدت ه ْم إَِّل ِف ْت ن ًة لِّلَّ ِذين كفروا ﴾ ‪ምሳሌ፡-‬‬
‫﴿ وما جعلْنا أ ْ‬

‫‪---- የዚህ ዓይነት ምልክት ያለበት የቁርአን ቃል ላይ ማቆም በላጭ ነው፡፡‬‬

‫ۘ‬ ‫﴿اتَّبِعوا ما أن ِزل إِل ْيكم ِّمن َّربِّك ْم ول ت تَّبِعوا ِمن دونِِه أ ْولِياء ۙ ق ِل ً‬
‫يَل َّما تذ َّكرون﴾ ‪ምሳሌ፡-‬‬

‫‪---- የዚህ ዓይነት ምልክት ያለበት የቁርአን ቃል ላይ ማቆምም ሆነ መቀጠል እኩል ደረጃ አላቸው፡፡‬‬

‫ۘ‬ ‫﴾‪ምሳሌ፡-‬‬ ‫﴿ لهم ِّمن جهنَّم ِمهاد وِمن ف ْوقِ ِه ْم غو ٍ‬


‫اش ۙ وك َٰذلِك ن ْج ِزي الظَّالِ ِمين‬

‫‪---- የዚህ ዓይነት ምልክት ያለበት የቁርአን ቃል ላይ መቀጠሉ በላጭ ነው፡፡‬‬

‫ۘ‬ ‫‪ምሳሌ፡-‬‬ ‫﴿ ختم اللَّه عل َٰى ق لوبِ ِه ْم وعل َٰى س ْم ِع ِه ْم ۙ وعل َٰى أبْصا ِرِه ْم ِغشاوة ۙ وله ْم عذاب ع ِظيم ﴾‬

‫‪ከሁለቱ በአንዱ ምልክት ላይ ብቻ ማቆም ይቻላል፡፡ ነገር ግን በሁለቱም ላይ ማቆም‬‬


‫‪አይቻልም፡፡‬‬

‫‪ምሳሌ፡‬‬

‫والحمد هلل الذى بنعمته تتم الصالحات وصلى اهلل على خير خلقه نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم‬

‫‪23‬‬

You might also like