Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 15

መግቢያ

በ 1996 ዓ.ም የተዘጋጀው የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ አፈጻጸም መመሪያ
አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም፣
 በስራ ላይ ያለው መመሪያ አሁን ላይ ሆኖ ሲታይ የሥራ ልብስ የሚያስፈልጋቸውን የሥራ መደቦች
ሙሉ በሙሉ ያላካተተ ሆኖ በመገኘቱ፣

 በአዲስ መልክ ከተካሄደው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) ጥናት ጋር ተያይዞ
አንዳንድ የሥራ መደቦች በመታጠፋቸው፣ በመጣመራቸው፣ የመጠሪያ ለውጥ
በማድረጋቸውና አዲስ የተፈጠሩ የሥራ መደቦችም በመኖራቸው ፣
 በነባሩ መመሪያ መሰረት ለሥራ መደቦች የተፈቀዱ የሥራ ልብሶች እንዲሻሻሉ
ከመ/ቤቶች በየወቅቱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች በመቅረባቸው ፣ እና
 በመመሪያው ውስጥ ያሉ ሌሎች ችግሮችን በማረምና ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን
በማካተት መመሪያውን ማውጣት በማስፈለጉ ይህ መመሪያ በአቅም ግንባታና ሲቪል
ሰርቪስ ቢሮ አማካኝነት ተዘጋጅቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1.1 አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ የመንግስት ሠራተኞች የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያዎች አጠቃቀም መመሪያ ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡

1.2 ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፣

1.2.1 " የመንግሥት መ/ቤት" ማለት በየትኛውም የአስተዳደር እርከን እራሱን ችሎ በአዋጅ ወይም
በደንብ የተቋቋመ እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከመንግስት በሚመደብለት በጀት የሚተዳደር
የክልል መንግስት መስሪያ ቤት ነው፡፡
1.2.2 "ቢሮ" ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አቅም ግንባታና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ነው፡፡
1.2.3 "የሥራ ልብስ" ማለት አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ እንደየሥራው
ጠባይ ለሠራተኛው ደህንነት ወይም ንጽህናውን ለመጠበቅና ለመለያነት እንዲያገለግለው
የሚሰጠው ልብስና ጫማ ነው፡፡

1
1.2.4 "የሥራ መሣሪያ" ማለት ሠራተኛው ሥራውን በጋራ ወይም በግል ለማከናወን እንዲጠቀምበት
የሚሰጥና ሥራውን ሲጨርስ በሥራ ቦታው የሚቀመጥ ልዩ ልዩ የሥራ መሣሪያ ወይም እቃ ማለት
ነው፡፡
1.2.5 “ቲትረን 6000" ማለት ከፖሊስተር የተሻለ ሆኖ የቀለሙ ልዩነት ሣይወሰን ከጥጥ ወይም ተመሳሳይ
ከሆነ ጥሬ ዕቃ የተሠራ ጨርቅ ነው፡፡
1.2.6 “አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ” ማለት ከአንድ ዓይነት ጨርቅ የተሰፋ ሆኖ ያለ ኮት ሊለበስ የሚችል
ሸሚዝና ሱሪ ነው፡፡
1.2.7 “ሸሚዝ” ማለት ቀለሙ እንደተፈለገው ሆኖ የሴንቴትኩ መጠን ዝቅ ካለና የጥጡ መጠን ከፍ ካለ
ለሸሚዝ እንዲሆን ከተመረተ ጨርቅ የተሠራ ነው
1.2.8 “ቀሚስ” ማለት ቀለሙ እንደተፈለገው ሆኖ ሙሉ በሙሉ ከጥጥ ወይም የጥጥና የሲንተቲክ
ድብልቅ ከሆነ ጥሬ እቃ የተሠራ ነው፡፡
1.2.9 "ጋዋን ወይም ሙሉ የሥራ ካፖርት ወይም ካፖርት" ማለት ቀለሙ እንደተፈለገው ሆኖ ከቲትረን
6000 ጨርቅ የሚሰፋ ገበር የሌለው ጋዋን ወይም ሙሉ የሥራ ካፖርት ወይም 3/4 ኛ ካፖርት ነው፡፡
1.2.10 "ካፖርት" ማለት ከሱፍ የተሰራ ወይም ሙቀት እንዲሰጥ ገበር ያለው ሆኖ ከጥጥ ወይም ከሲንተቲክ
የተሰራ የብርድ መከላከያ ልብስ ነው፡፡
1.2.11 " የዝናብ ልብስ" ማለት ከጥጥና ከሲንተቲክ የተሰራ የዝናብ መከላከያ ልብስ ነው፡፡
1.2.12 "ጃንጥላ" ማለት ለዝናብ ወይም ለፀሐይ መከላከያ የሚያገለግል ነው፡፡
1.2.13 "ካባ" ማለት በችሎት ወቅት ዳኞች የሚለብሱት ከቲትረን 6000 ጨርቅ የተሰፋ ጥቁር ልብስ ነው፡፡
1.2.14 "ሽርጥ" ማለት ከጥጥ ወይም ከሌላ ተስማሚ ጥሬ እቃ የተሰራ ሆኖ የልብስን መቆሸሽ ለመከላከል
የሚለበስ የሥራ መሣሪያ ነው፡፡
1.2.15 "ቱታ" ማለት ከጥጥ ወይም ከሌላ ጥሬ እቃ የተሠራና ሱሪው ከጃኬት መሰል ልብስ ጋር ተያይዞ
የተሰፋ ሆኖ የልብስን መቆሸሽ ለመከላከል በልብስ ላይ ተደርቦ የሚለበስ የሥራ ልብስ ነው፡፡
1.2.16 "አጭር ቆዳ ጫማ" ማለት ማሠሪያ ያለው ወይም የሌለው ሆኖ ለሲቪል ሥራ አገልግሎት
የሚውልና ቁመቱ ከቁርጭምጭሚት የማያልፍ ከቆዳ የተሠራ ጫማ ነው፡፡
1.2.17 "የላስቲክ ቡት ጫማ" ማለት ከተፈጥሮ ጐማ የተሠራ ገበር ያለው ሆኖ በክረምትና ጭቃ
በሚበዛበት ወቅት የሚደረግና በቀላሉ የሚፀዳ ጫማ ነው፡፡
1.2.18 "ፊልድ ጃኬት" ማለት ከጥጥ ወይም ከሌላ ተመሣሣይ ጨርቅ የተሠራ ሆኖ ሙቀት የሚሰጥ ገበር
ያለው ልብስ ነው፡፡

ክፍል ሁለት
የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ ስለሚሰጥበት ሁኔታ እና የሚሰጠው የጨርቅና የጫማ
ዓይነት
2
2.1 የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ ስለሚሰጥበት ሁኔታ

2.1.1 ለየሥራ መደቦች የተፈቀደው የሥራ ልብስ ዓይነትና መጠን የሚሰጠው በሥራ መደቡ ላይ
ተመድበው በመሥራት ላይ ለሚገኙ ቋሚና የሙከራ ቅጥር ሠራተኞች ነው፡፡

2.1.2 በውክልና ወይም በያዙት የሥራ መደብ ላይ በተደራቢነት እንዲሰሩ ለተመደቡ ሠራተኞች ለሥራ
መደቡ የተፈቀደው የሥራ ልብስ ይሰጣቸዋል፡፡ሆኖም የያዙት የስራ መደብ የደንብ ልብስ ያለው
ከሆነና በውክልና ደርበው እንዲሰሩ የተሰጣቸው የስራ መድብም የደንብ ልብስ ያለው ከሆነ
የአንዱን የስራ መደብ ብቻ መርጠው እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡

2.1.3 የሥራ ልብስ የሚሰጠው የሥራ ልብስ በተፈቀደበት የሥራ መደብ ላይ ለተመደበና ሥራውን
በመሥራት ላይ ለሚገኝ ሠራተኛ ነው፡፡ ሆኖም የሥራ ልብስ በተፈቀደበት የሥራ መደብ ላይ
ተመድቦ ነገር ግን በትምህርትና በመሣሰሉት ምክንያቶች ሥራውን ለማይሰራ ሠራተኛ የሥራ
ልብስ አይሰጥም፣

2.1.4 የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ የሚሰጠው ሠራተኛው/ባለሙያው/ በበጀት ዓመቱ መሥራት
ያለበትን ሥራ ማከናወኛ በመሆኑ በበጀት ዓመቱ ውስጥ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

2.1.5 አልፎ አልፎ ሰራተኞች የደንብ ልብስ ከወሰዱ በኋላ በመልቀቃቸው ምክንያት በቦታው ላይ
ለሚተኩ ሰራተኞች የደንብ ልብስ ለመስጠት የሚያስቸግርበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ በዚህ ጊዜ
የተተኩት ሰራተኞች ቢያንስ የሚቀጥለውን የደንብ ልብስ ለማግኘት ሶስት ወርና በላይ
ከቀራቸውና መስሪያቤቱ በጀት ካለው በልዩ ሁኔታ ወስኖ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አስገዳጅ ግን
አይደለም ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የለቀቁት ሠራተኞች የወሰዱትን የሥራ ልብስ እንዲመልሱ
አይጠየቁም ፣

2.1.6 በበጀት እጥረት፣ በአሠራር ስህተትና በመሳሰሉት ችግሮች በበጀት ዓመቱ ውስጥ ያልተሰጠ የደንብ ልብስ
በቀጣዩ በጀት ዓመት ከሠራተኞች የደንብ ልብሱ ይሰጠኝ ጥያቄ ሲቀርብ የተፈቀደው የስራ ልብስ
ይሰጣል፡፡ሆኖም የደንብ ልብሱ ሳይሰጥ የቀረው በአሰራር ስህተት ከሆነ የሚመለከተው አካል
ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡

2.1.7 በሞቃታማና በውርጭ አካባቢዎች የተመደቡና የሥራ ልብስና መሣሪያ በተፈቀደባቸው የሥራ መደቦች ላይ
ተመድበው በመሥራት ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች በመመሪያው ላይ ለተፈቀዱት የጨርቅና የጫማ ዓይነቶች
ምትክ ለአካባቢው የአየር ጠባይ ተስማሚ የስራ ልብስ መስጠት ይቻላል፡፡ ሆኖም ዋጋው ተመጣጣኝ
ስለመሆኑና ለስራው አስፈላጊ መሆኑ በቅድሚያ ሊታመንበት ይገባል፡፡

2.1.8 አንድ ሰራተኛ በህመም ምክንያት ከሶስት ወር በላይ ስራውን የማይሰራ ከሆነ ለስራ መደቡ
የተፈቀደው የደንብ ልብስ አይሰጠውም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰራተኛ ማግኘት እየተገባው

3
በተለያየ ምክንያት ሳይሰጠው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ያልተሰጠው የደንብ ልብስ ወደ ገንዘብ
ተቀይሮ ለህጋዊ ወራሾቹ ይሰጣል፡፡

2.2 የሚሰጠው የጨርቅና የጫማ ዓይነት

ለሥራ ልብስ የሚውል የጨርቅ ዓይነት፡-

2.2.1 ለቱታ፣ለአንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ፣ ለጃኬትና ጉርድ ቀሚስ፣ለኮትና ሱሪ፣ለሙሉ


ካፖርት፣ለ 3/4 ካፖርት፣ ለጋዋንና ለሽርጥ የሚሰጠው የጨርቅ ዓይነት በሃገር ውስጥ
የተመረተ ቴትረን 6 ዐዐዐ ወይም ተመሣሣይና ተመጣጣኝ የልብስ ጥራትና የዋጋ መጠን
ያለው ጨርቅ ይሆናል፣

2.2.2 ለከረባት የሚሰጠው የጨርቅ ዓይነት በሃገር ውስጥ የተመረተ ቲትረን 6000 ወይም
በጥራቱና በዋጋው ተመጣጣኝ ሆኖ ከብር 5 ዐ ያልበለጠ ዋጋ ያለው ይሆናል፣

2.2.3 ለካፖርት የሚሰጠው የጨርቅ ዓይነት ሙቀት የሚሰጥና ገበር ያለው ሆኖ የጥጥ ወይም
የሲንተቲክ ወይም ከጥጥና ከሲንተቲክ ጥሬ እቃ የተሰራ ይሆናል፡፡ ይህ የማይገኝ ከሆነ
በምትኩ ሙቀት የሚሰጥና ገበር ያለው ፊልድ ጃኬት ከመንግስት ወይም ከግል ድርጅቶች
በማወዳደርና በወቅቱ ያለውን የካፖርት ዋጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ገዝቶ መስጠት
ይቻላል፡፡

2.2.4 የሚሰጠው የዝናብ ልብስ ከጥጥና ከሴንተቲክ የተሰራ የዝናብ ልብስ ነው፡፡ የዝናብ
ልብሱ የማይገኝ ከሆነ በምትኩ ጃንጥላ ይሰጣል፡፡

2.2.5 ለካባና ለፈረጅያ የሚሰጠው ጨርቅ ቲትረን 6000 ወይም ተመሣሣይና ተመጣጣኝ ዋጋ እና
የጥራት ደረጃ ያለው ጥቁር ጨርቅ ነው፡፡

2.2.6 በየወቅቱ ያለውን የገበያ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በጥራታቸው፣በዋጋቸውና በደረጃቸው


ተመጣጣኝ የሆኑ የአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚመረቱ ጫማዎችን ገዝቶ
መስጠት ይቻላል፡፡ ይህም ሆኖ የአንድ ጥንድ ጫማ ዋጋ ከብር 250.ዐዐ መብለጥ የለበትም፡፡

ክፍል ሦስት
አዲስ ወይም ማሻሻያ የስራ ልብስ ጥያቄ በተመለከተ፣

የስራ ልብስ ላልተፈቀደላቸው የስራ መደቦች እንዲፈቀድ ወይም ማሻሻያ ሲያስፈልግ፡-

4
3.1 ተጠሪነታቸው ለስራ ሂደት መሪ /አስተባባሪ/ ለሆኑ የስራ መደቦች የስራ ሂደት መሪው/አስተባባሪው/
የስራ ልብሱ አስፈላጊ ስለመሆኑ ከበቂ ማብራሪያ ጋር ለሰው ሃይል ሥራ አመራር ደጋፊ የስራ ሂደት
ያቀርባል፡፡

3.2 ተጠሪነታቸው ለስራ ሂደት መሪ/አስተባባሪ ላልሆኑ የስራ መደቦች የመ/ቤቱ ኃላፊ የስራ ልብሱ አስፈላጊ ስለመሆኑ
ከበቂ ማብራሪያ ጋር ለሰው ሃይል ሥራ አመራር ደጋፊ የስራ ሂደት ያቀርባል፡፡

3.3 የሰው ሀይል ሥራ አመራር ደጋፊ የስራ ሂደት የቀረበውን አዲስ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ
በመመርመር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ ተገቢው ውሣኔ
እንዲሰጥበት የክልል፣ የብሔረሰብ ዞኖችና ወረዳዎች በቀጥታ፣ ከብሔረሰብ ዞኖች ውጭ
ያሉት ዞኖች ግን በእናት መስሪያ ቤታቸው በኩል ለአቅም ግንባታና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ
እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ የክልሉ አቅም ግንባታና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮም የቀረበውን ጥያቄ
በመመርመር አስፈላጊውን ውሣኔ ይሰጣል፡፡

3.4 የሰው ሀይል ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት የደንብ ልብስ የተፈቀደላቸውን ሠራተኞች፣
ማግኘት የሚገባቸውን የሥራ ልብስ ዓይነትና መጠን በመለየት ለግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት
አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ይልካል፡፡

3.5 በየደረጃው የተቋቋመው የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደትም
በተላከለት ዝርዝር መሠረት ግዥ የመፈጸምና የሚሰፋ ካለም የማሰፋት ተግባራትን
ያከናውናል፡፡

ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ጉዳዮች
4.1 አፈፃፀሙን የመከታተልና የመቆጣጠር ተግባር

4.1.1 በማንኛውም የመንግሥት መ/ቤት ሠራተኛው የተሰጠውን የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ
ተጠቅሞ በሥራ ሰዓት ካልተገኘ ራሱን ለሥራ አዘጋጅቶ እንዳልመጣ ተቆጥሮ አስፈላጊው
የዲስፕሊን እርምጃ በሰው ኃይል ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት በኩል ይወሰድበታል፡፡

4.1.2 የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ በተፈቀደላቸው የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሰሩ
ሠራተኞች በመመሪያው የተፈቀደው የሥራ ልብስ እንደሥራው ባህሪ አንድ አይነት ቀለም
መያዙንና የተፈቀደው መጠን ብቻ የተሰጣቸው ለመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የውስጥ
ኦዲተሮች ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

4.1.3 በውስጥ ኦዲተሮች ተመርምሮ በመመሪያው ከተፈቀደው ዓይነትና መጠን ውጭ አላግባብ


የተሰጠ የሥራ ልብስና መሳሪያ ካለ እንዲሰጥ ጥያቄውን ያቀረበ እና ያፀደቀው የሥራ ኃላፊ
5
አላግባብ የወጣውን ወጪ እንዲመልስ ይደረጋል፡፡በዞንና በወረዳ ደረጃ የገንዘብና ኢኮኖሚ
ልማት የውስጥ ኦዲተሮች ይህን የምርመራ ተግባር ያከናውናሉ፡፡

4.1.4 የአቅም ግንባታና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ለዚህ መመሪያ አፈጻጸም ተገቢውን ድጋፍና ቁጥጥር
ያደርጋል፡፡

4.1.5 የሥራ ልብስ ለተፈቀደላቸው የሥራ መደቦች የሚያስፈልጋቸውን የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ በወቅቱ
አዘጋጂቶ ያላቀረበ የሰው ሐይል ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደትና በወቅቱ የማሰፊያ ዋጋን ጨምሮ የግዥ
ተግባራትን ያላከናወነ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ባለሙያ አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡

4.1.6 የሚሰጠው የደንብ ልብስ ከመለዮ ለባሹጋር ተመሳሳይ እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

4.2 የመረጃ አያያዝ

4.2.1 በክልል መ/ቤቶች የሚገኙ የሰው ሀይል ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደቶች በዓመቱ መጨረሻ
ላይ የሥራ ልብስ የተሰጣቸውን ሠራተኞች ቁጥር በየሥራ መደቡ በመለየትና የተሰጠውን
የልብስና የስራ መሳሪያ ዓይነትና ብዛት የሚገልጽ መረጃ አዘጋጅተው ይይዛሉ፡፡ከሚመለከተው
አካል ሲጠየቁም መረጃውን ያቀርባሉ፡፡

4.2.2 በዞንና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የሰው ኃይል ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደቶች በዓመቱ
መጨረሻ ላይ የሥራ ልብስ የተሰጣቸውን ሠራተኞች ቁጥር በየሥራ መደቡ በመለየትና
የተሰጣቸውን የልብስና የስራ መሳሪያ ዓይነትና ብዛት የሚገልጽ መረጃ አዘጋጅተው ይይዛሉ፡፡
ከሚመለከተው አካል ሲጠየቁም መረጃውን ያቀርባሉ፡፡

4.3 የቅሬታ አቀራረብ

በሥራ ልብስና መሣሪያዎች አሰጣጥ አፈፃፀም ላይ ከመመሪያ ውጭ አላግባብ በደል ተፈጽሞብኛል


ብሎ ለሚቀርብ ጥያቄ ከመ/ቤቱ ጀምሮ እስከ ክልል ደረጃ ለተቋቋመው ቅሬታ ሰሚ አካል
በማቅረብ በቅሬታ አፈታት ደንብ መሠረት ቅሬታው እንዲፈታ ማድረግ ይቻላል፡፡

4.4 . የመመሪያው ተፈፃሚነት


ይህ መመሪያ ተፈፃሚነት የሚኖረው በሲቪል ሰርቪስ አዋጅ በሚተዳደሩ መ/ቤቶችና ሠራተኞች ላይ
ብቻ ነው፡፡

4.5 መመሪያውን ስለማሻሻል


4.5.1 ይህን መመሪያ የመለወጥ፣ የማሻሻል ወይም በሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ማብራሪያ ወይም
ትርጉም የመስጠት ሐላፊነት የቢሮው ነው፡፡
6
4.5.2 ከዚህ በፊት በሥራ ላይ የነበረው የሥራ ልብስ እና የሥራ መሣሪያዎች አሰጣጥ መመሪያ በዚህ
መመሪያ ተተክቷል፡፡

4.6. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ


ይህ መመሪያ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ ይውላል፡፡

አባሪ አንድ

የተፈቀደ የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ ዓይነትና መጠን የሚያሳይ ሠንጠረዥ

ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት


1 ዘበኛ ወንድ የቀንና የሌሊት ወይም  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
የሌሊት ብቻ ወይም በሽፍት  ሸሚዝ በዓመት ሁለት
የሚሠራ  አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በየ 3 ዓመቱ አንድ
2 ዘበኛ ሴት የቀንና የሌሊት ወይም  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
የሌሊት ብቻ ወይም በሽፍት  አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
የምትሰራ  ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 የቆዳ ጫማ አጭር በዓመት ሁለት ጥንድ
 ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ 3 ዓመት አንድ
3 ዘበኛ ወንድ የቀን ብቻ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
4 ዘበኛ ሴት የቀን ብቻ  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
5 ዘበኛና አትክልተኛ ወንድ የቀንና  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
የሌሊት ወይም በሽፍት የሚሠራ  ቱታ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ 3 ዓመት አንድ
6 ዘበኛና አትክልኛ ሴት የቀንና  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
የሌሊት ወይም በሽፍት የሚሠራ  አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 ቱታ በዓመት አንድ
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 የላስቲከ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ 3 ዓመት አንድ
7 ዘበኛና አትክልተኛ ወንድ የቀን  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ብቻ  ቱታ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
7
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

8 ዘበኛና አትክልተኛ ሴት የቀን ብቻ  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ

ተ.ቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት

 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ


 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 ቱታ በዓመት አንድ
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
9 የደን ዘበኛ  ቱታ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 ረዥም የቆዳ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ 3 ዓመት
አንድ
 የዝናብ ልብስ በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ 3 ዓመት
አንድ
10 የዘብ ኃላፊ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
11 የዘብ ኃላፊ ሴት  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
12 አትክልተኛ ወንድ  ቱታ በዓመት አንድ

 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ


 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
13 አትክልተኛ ሴት  ቱታ በዓመት አንድ
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
14 የጽዳት ኃላፊ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
15 የጽዳት ኃላፊ ሴት  ቀሚስ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
16 የጽዳት ሠራተኛ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
17 የጽዳት ሠራተኛ ሴት  ቀሚስ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
በዓመት ሁለት

8
ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት

18 የበረት ጽዳት ሠራተኛ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ


 ቱታ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
19 የበረት ጽዳት ሠራተኛ ሴት  ቀሚስ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 ሽርጥ በዓመት አንድ
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
20 ተላላኪ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት አንድ
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
21 ተላላኪ ሴት  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት አንድ
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
22 ጽዳትና ተላላኪ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
 የእጅ ጓንት እንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
23 ጽዳትና ተላላኪ ሴት  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
 የእጅ ጓንት እንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
24 መጥሪያ አዳይ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት
 ጃንጥላ በዓመት አንድ
25 መጥሪያ አዳይ ሴት  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ጃንጥላ በዓመት አንድ
26 እግረኛ ፖስተኛ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 ጃንጥላ በዓመት አንድ
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
27 እግረኛ ፖስተኛ ሴት  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ጃንጥላ በዓመት አንድ
28 በሞተርሳይክል የሚሠራ ፖስተኛ  ቆዳ መሰል የላስቲክ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ወይም ጃኬትና ሱሪ

9
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 የዝናብ ልብስ በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ 3 ዓመት አንድ
 የብረት ቆብ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በ 3 ዓመት አንድ
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
29 የመለስተኛ መኪና ሾፌር  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
 ቱታ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
30 የከባድ መኪና ሾፌር  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
 ቱታ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
31 የሾፌር ረዳት  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
 ቱታ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
32 ትራክተር ኦፕሬተር  ቱታ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
33 ረዳት የትራክተር ኦፕሬተር  ቱታ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
34 በመጸዳጃቤት መምጠጫ መኪና ላይ  ቱታ በዓመት ሁለት
የሚሠራ  አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የላስቲክ ሽርጥ/አፕሮን/ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
 ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
35 የቅባት፣ነዳጅና ዘይት አዳይ /የተሸከረካሪ/  ቱታ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለተ ጥንድ
36 ጐሚስታ  ቱታ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
37 የጋራዥ ሠራተኛ፣መካኒክ፣ረዳት  ቱታ በዓመት ሁለት
መካኒክ፣ቀጥቃጭ፣የአውቶ ኤሌክትሪሽያን የጥገና
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሠራተኛና መካኒክ፣ በያጅ፣ብረታብረት ሠራተኛ፣
ቦይለርቴክኒሽያን፣የማቀዝቀዣ መጋዘን መካኒክ፣ማሽን ሾፕ  የእጅ ጓንት እንደ ስራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
ሠራተኛ፣ በያጅና ረዳት መካኒክ
38 መኪና አጣቢ፣ግሪስ የሚያደርግናዘይት  ቱታ በዓመት ሁለት
የሚቀይር፣ሁለገብ የጉልበት ወይም የጥገና  አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ሠራተኛ  የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
39 ባትሪ ሠራተኛ  ቱታ በዓመት ሁለት
 አጭር ቡት የቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የላስቲከ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የላስቲክ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
 የላስቲክ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
40 የተሽከርካሪ ጥገና ኃላፊ፣የሾፌር አሰልጣኝ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
41 ንብረት ኦፊሰር ወይም ንብረት ሠራተኛ ፣  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
42 መዝገብ ቤት/ሪከርድ ሠራተኛ/  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ

10
የተማሪዎች ሪከርድ ሠራተኛ
43 ማባዣና ፎቶኮፒ ሠራተኛ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
44 የቢሮ መሣሪያዎች ጠጋኝ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
45 የጥረዛ ክፍል ሠራተኛ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
46 የቤተመፃህፍት ሠራተኛ ወይም  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
ላይብራሪያን
47 ቮይስ ሪኮግኒሽን መሳሪያ ኦፕሬተር  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
48 ፋይል ከፋች  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
49 ልዩ ልዩ የእደጥበብ ሙያ አሰልጣኝ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
50 የብሉ ፕሪንት ማሽን ባለሙያ(ለከተሞች  የወተት ክፍያ በወር 100 ብር
ፕላን ኢንስቲትዩት መስሪያቤት ብቻ)
51 የብረታብረት መምህር፣የእንጨት ሥራ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
መምህር፣የምግብ ሥራ መምህር፣
አጠቃላይ የሙያ መምህር፣ አውቶሞቲቭ
መምህር
52 የስፖርት መምህር ወይም አሰልጣኝ  ቱታና ቲሸርት በዓመት አንድ
በሙያው የሰለጠነና በሥራው የተመደበ  ቶርሸን ስኒከር ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
53 ባሬስታ ወንድ  ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
54 ባሬስታ ሴት  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት አንድ
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
55 አስተናጋጅ ወንድ  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ከረባት በዓመት አንድ

ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት

56 አስተናጋጅ ሴት  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ

 ሸሚዝ በዓመት ሁለት

 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ

 ከረባት በዓመት አንድ

57 ንብረት ክፍልና ልብስ አጣቢ ወንድ(ለርዕሰ  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ


መሠተዳድርና ለክልል ምክር ቤት)
 ቱታ በዓመት አንድ

 ሸሚዝ በዓመት ሁለት

 አጭር የቆዳ ጫማ በዐመት አንድ ጥንድ

11
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዐመት አንድ ጥንድ

 የፕላስቲክ ሽርጥ/አፕሮን/ እንደ ሥራ መሣሪያ የሚሰጥ

58 ንብረት ክፍልና ልብስ አጣቢ ሴት(ለርዕሰ  ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
መስተዳድርና ለክልል ምክር ቤት)
 ቱታ በዓመት አንድ

 ሸሚዝ በዓመት ሁለት

 አጭር ቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

 የላስቲክ ሽርጥ/አፕሮን እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ

59 የፕሮቶኮል ባለሙያ( በህጋዊ መንገድ የፕሮቶኮል  ባለገበር ሱፍ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ


ባለሙያ ለተመደበላቸው የስራ ሀላፊዎች ብቻ)
 ሸሚዝ በዓመት አንድ

 ቆዳጫማ አጭር በዓመት አንድ

 ከረባት በዓመት አንድ

60 የጂኦሎጂ፣አፈርና ግንባታ ጥራት ናሙና ምርመራ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ


አናሊስት
61 የአፈር ምርምር ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ

62 የእጅ ፖምፕ አቴንዳንት፣ ቧንቧ ሠራተኛ  ቱታ በዓመት ሁለት

 አጭር ቡት ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

63 የሙዚየም ባለሙያ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ

 የእጅ ጓንት/ቆዳ/ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ

 ¾ ካፖርት በዓመት ሁለት


64 ነርስ፣አሰልጣኝና ተመራማሪ፣የምግብ ቤት
ኃላፊ፣የጤናመኮንን፣ የጤና ባለሙያዎች፣
ፋርማሲስት፣ግንባር ቀደም የጤና
ሱፐርቫይዘር፣የጤና ኤክስቴንሽንባለሙያ፣የወባ
ቴክኒሽያን፣የጤና ባለሙያ ሠልጣኞች፣ጤና
ረዳት፣ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን ፣ራዲዮትራፒስት
የህክምና ቴከኒሽያን፣የጤና አጠባበቅ
ተቆጣጣሪዎች/በሆስፒታል ብቻ የሚሰሩ/ ላቦራቶሪ
ተቆጣጣሪ፣የላቦራቶሪ ረዳት፣ላቦራቶሪ ውስጥ
ለሚሰሩ አንቲሞሎሀዳስትና ፖቲዮሎጂስት፣የተባይ
መከላከያ ላቦራቶሪ ሠራተኛ፣የመድሃኒት መጋዝን
ሠራተኛ ፣የመድሃኒት አስተዳደር
ኤክስፐርት፣ፕሮተር/ራነር/፣እንግዳ ተቀባይ፣
ምግብ ተቆጣጣሪ/የምግብ ጉዳይ ኃላፊ/

12
ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት

65 የቆዳና ሌጦ ባለሙያ  ቱታ በዓመት አንድ


 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ
 የፕላስቲክ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
በዓመት አንድ
66 የእንስሳት ሀኪም፣ረዳት የእንስሳት ሀኪም፣የእንስሳት  ካፖርት በሁለት ዓመት አንድ
ጤና ኳራንቲ፣የዱር እንስሳት ሀኪም፣ረዳት የዱር  የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
እንስሳት ሀኪም  የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
በዓመት አንድ
67 የአሣ ርባታ ባለሙያ፣አሣ አጥማጅ/አስጋሪ/  ቱታ በዓመት አንድ
 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
በዓመት አንድ
68 የጀልባ ካፕቴን  ቱታ በዓመት አንድ
 ነጭሸሚዝና ሱሪ በዓመት ሁለት
 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ
 ቆብ በዓመት አንድ
69 የአሣ ማስገሪያ መሣሪያዎች ቴክኒሽያን፣የመረብ ሥራ  ቱታ በዓመት አንድ
ቴክኒሽያን፣የማስገሪያ መሣሪያዎች ረዳት ቴክኒሽያን  የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
70 የመስክ ነፍሳትና የጐተራ ተባይ ጥናት መከላከል  ቱታ በዓመት አንድ
ባለሙያ፣የእጽዋት በሽታና አረም ጥናት መከላከል
ባለሙያ፣የአይጥና ወፍ ኬሚካል መርጫ መሣሪያ
ጥናትና መከላከል ባለሙያ፣የኬሚካል መርጫ አያየዝና  የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
አጠቃቀም ባለሙያ፣የአረም ጥናትና መከላከል ባሙያ

71 የሥነ ተዋልዶና ጤና ባለሙያ፣የርባታ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ


ባለሙያ፣የአባለዘርና ፈሳሽ ናይትሮጅን፣  ቱታ በዓመት አንድ
ላቦራቶሪ ቴክኒሽያንና ማሽን ኦፕሬተር  ሸሚዝ በዓመት አንድ
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
72 ዳኛ፣ አቃቢህግ፣ ተከላካይ ጠበቃና ነገረፈጅ  ካባ በ 5 ዓመት አንድ
73 የደሮ ማስፈልፈያ ባለሙያ(ወንድ)  ቱታ በዓመት አንድ

 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ


 ¾ ካፖርት በዓመት አንድ

 የጨርቅ ቆብ በዓመት አንድ


74 የደሮ ማስፈልፈያ ባለሙያ /ሴት/
¾ ካፖርት በዓመት አንድ

 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

 ሙሉ ሽርጥ በዓመት አንድ


 የጨርቅ ቆብ በዓመት አንድ

ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት

75 የእንጨት ሥራ ቱል ኪፐር፣ የብረታብረት  ¾ ካፖርት በዓመት ሁለት


ሥራ ቱል ኪፐር
76 ኤሌክትሪሽያን፣ ረዳት ኤሌክትሪሽያን፣  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ

13
የብረታ ብረት ቴክኖሎጅስት፣ የምርት  አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ጥራትና ቁጥጥር ሠራተኛ
77 ከፍተኛ ማሽኒስት፣ ማሽኒስት፣ ብረታብረት  ቱታ በዓመት ሁለት
ሠራተኛ፣ የእንጨት ሥራ ቴክኒሽያን፣  አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
የእንጨት ሠራተኛ፣
78 ቀለም ቀቢ  ቱታ በዓመት አንድ
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
 ቆብ በዓመት አንድ
79 እንጨት ፈላጭና ጉልበት ሠራተኛ፣ ልብስ  ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ሰፊ፣ ልብስ ዘምዛሚ፣ ልብስ ተኳሽ  አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ሸሚዝ በዓመት አንድ
80 ወተት አላቢ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት

 የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዐመት አንድ ጥንድ


 ቆብ/ከጨርቅ የተሰራ በዓመት አንድ
 ሽርጥ በዓመት አንድ
81 ችግኝ ጣቢያ ሠራተኛ  ቱታ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት

 የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ


82 እንጀራ ጋጋሪ  ቀሚስ በዓመት ሁለት
 ቨሚዝ በዓመት ሁለት
 ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ሙሉ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
 ከጨርቅ የተሠራ ቆብ በዓመት አንድ
83 ሰንጋ ተንከባካቢ  ቱታ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

 ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ


 የዝናብ ልብስ በሦስት ዓመት አንድ
84 ከብት ጠባቂ  ቱታ በዓመት አንድ

 ሸሚዝ በዓመት ሁለት


 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 የዝናብ ልብስ በሦስት ዓመት አንድ
85 የእጽዋት ጥራት ክሊኒክ ረዳት  አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
 ቱታ በዓመት አንድ
86 ታፒ ሰሪ /ፎቴሰሪ/  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
 አጭር ቆዳ ጫማ በአመት ሁለት ጥንድ

የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት


ተ.ቁ
87 የእስካውት ኃላፊ ፣እስካውት፣የመስክ ሥራ  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ተቆጣጣሪ  ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
 ካፖርት በሦስት ዓመት አንድ
 ቆብ በዓመት ሁለት
88 የመድሃኒት መጋዘን ሠራተኛ ፣ህትመት  ቱታ በዓመት አንድ
ሠራተኛ፣የቅርስ እንክብካቤና ጥገና  አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
ኦፊሰር፣የአፈርና እጽዋት ናሙና

14
አዘጋጅ፣የመስክ ጥራት ኢንስፔክተር
ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን ፣የእጽዋት ጥራት
ክሊኒክ ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን
89 አናፂ፣ግንበኛ፣አናፂና ግንበኛ  ቱታ በዓመት አንድ
 አጭርቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
90 ፎረንሲክ ባለሙያ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
91 የትራንስፖርት ስምሪት ጋራዥ ክፍል ኃላፊ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
92 ሰዓሊ  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
93 የተሽከርካሪዎች መርማሪ የማንኛውም  ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
ተሽከርካሪ ፈታኝ
94 የንብ ምርምር ተመራማሪ ፣የንብ ምርምር  ከቆዳ የተሰራ የእጅ ጓንት በዓመት አንድ ጥንድ
ቴከኒክ ረዳት  አይን ርግብ በዓመት አንድ
 ባለዚፕ ቱታ በዓመት አንድ
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
95 ግሪን ሀውስ ሠራተኛ  ቱታ በዓመት ሁለት
 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት ሁለት
96 የህክምና መሣሪያዎች ጥገና ክፍል ሠራተኛ፣  ቱታ በዓመት ሁለት
የሬዲዮ ጥገና ሠራተኛ  አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት
97 አስከሬን ቤት ተቆጣጣሪ፣/ሠራተኛ/  ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
98 አበነፍስ  ጥቁር ፈረጅያ በሁለት ዓመት አንድ
 ቀሚስና ሱሪ በዓመት አንድ
 የአገር ውስጥ ሸሚዝ በዓመት አንድ
 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ክብ ቆብ በዓመት አንድ
99 የላውንደሪ ሠራተኛ /ኃላፊ/ ወንድ  ቱታ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር የቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ፕላስቲክ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
100 የላውንደሪ ሠራተኛ /ኃላፊ/ሴ  ቀሚስ በዓመት አንድ
 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
 አጭር ቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
 ፕላስቲክ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ

15

You might also like