Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 16

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ

ትያትር ጥበባት ትምህርት ክፍል

<<ስንብት>>የአማርኛ ፊልም ከፊልም ትወና ባህርያት አንፃር

በ ሰናይት ጥላሁን

ለ መምህር ቢኒያም ገብሩ

<<ስንብት>>የአማርኛ ፊልም ከፊልም ትወና ባህርያት አንፃር


ለአርትስ ኦፍ ባቺላር የቀረበ ጥናታዊ ፅሁ
ምዕራፍ አንድ
1 መግቢያ
ኪነ-ጥበብ የሰው ልጆች ማንነት ፣ማህበራዊ ሁኔታ ፣ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ፣ ባህል ፣ወግ ፣ልምድ ፣እምነት
እንዲሁም የሰው ልጆች በሂወት ዘመኑ በሚያደርጋቸው የእለተእለት ገጠመኞች ውጣ ውረዶች ---- ዘወተ
በማዋህድ በፊልም ፣በቲያትር ፣በልቦለድ ---- ወዘተ አማካኝነት ለተደራሲያን ባማረእና ታማኝነት ባለው
መልኩየሚቀርብ ጥበብ ነው ፡፡ ኪነ - ጥበብ በውስጡ በርካታ ዘርፎች አካቶ የያዘ ሲሆን ከእነሱም አንዱ ፊልም
ነው ፡፡

ፈልም አንድን ታሪክ ተንቀሳቃሽ ምስልን በመጠቀም ሀሳብን ምናስተላልፍበት ታሪክን የምንነግርበት መንገድ
ሲሆን ሰለሞን መኮነን" የፊልም ጥበብ ገበታ"በሚለው መፅሐፍ ላይ የኢትዩጲያ የፊልም ታሪክ አጀማመር
በዚህ መልኩ አስቀምጧል ፡-

‹‹ ፈልም በኢትዩጲያ የተጀመረው በአፄምኒልክ ዘመን ሲሆን በኢትዩጲያለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ፍልም


‹‹ሂሩት ምስል የታየው በአፄ ሚኒሊክ ዘመን ነው ፡፡ የኢትዩጲያ የፈልም ታሪክ በሶስት ዘመን የተከፈለ
ነው የመጀመሪያ ፈልም ዘመን ከ 1950-1980 ዋችነው፡፡ ሁለተኛው ፈልም ዘመን ከ 1980-1995 ዓ.ም ፡፡
የሶስተኛ ፈልም ታሪክ 1995 እስከ አሁን ያለው ዘመን ነው ፡፡›› (2007፡4)

ከላይ እንደተገፀው የፈልም ታሪክ በዚህ ዘመን ብዙስራዎች ተስርተዎል ፡፡ስለዚህ ፈልም ማለት በአይን
የሚታይ በጆሮ የሚደመጥ የጥበብ ዘርፍ ሲሆን በውስጡ በርካታ አለባዊያን አካቶ የያዘ ሲሆን ከእነሱ
መካከል አንዱ ትወና ነዉ።

ትወና በድርጊት፣በድምፅ ፣ በእንቅስቃሴ የሚተወን ሙያ ሲሆን ስሜት


፣ድምፅ፣እንቅስቃሴ ተጨምሮበት ሊተላለፍ የተፈለገውን ስሜት ወይም መልዕክት
በተገቢው መልኩ ለተመልካች ማሳየት ነዉ ፡፡ እንዲሁም የተሰጠን ታሪክ ህይወት
ሰጥቶ ፣ ድርጊት ፣ እንቅስቃሴ ድምፅ በመጠቀም በተዋናይ አማካኝነት የሚሰራ የጥበብ
ዘርፍ ሲሆን የትወና የጀርባ አጥንት የሆነዉ ተዋናይ ነዉ።

ተዋናይ በአንድ ድርሰት ውስጥ ያሉ ገፅ- ባህሪ ወክሎ የሚጫወት ወይም የሚተወን
ትወና ባለሙያ ሰዉ ነወ፡፡

ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚያጠናው ከፊልም ዝግጅት


አለባውያን አንዱ የሆነው ትወና ላይ ነዉ፡፡ በሃገራችን ኢትዮጲያ በርካታ ፊልምቸ
ተሰርቷል ፡፡አሁንም እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ፈልሞች መካከል አንዱ ‹‹ስንብት››
ነው፡፡ ስንብት ፊልም በአንተነሀ ሃይሌ ደራሲነት እና አዘጋጅነት በዳኒ ቦይ
ፈልምፕሮዳክሽን በ 2013 ዓ.ም በላባ ኢንተርቴመንት ለተመልካች የቀረበ ምርጥ
የሀገራች ፊልም ሲሆን ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ‹‹ ስንብት ›› የአማርኛ ፈልም ከፊልም
ትወና ባህሪያት አንፃር በተገቢው ሁኔታ መጠቀሙን በመገምገም ላይ ትኩረት
ያደረገ ነው ፡፡

1.1 የጥናቱ ዳራ
አጥኝዋ ‹ ስንብት ›› የተሰኘው ፊልም ከፊልም ትወና ባህሪያት አንፃር ለመስራት
ያነሳሳት ምክንያት አጥኝዋ ስንብትን ፊልም በምትመለከትበት ጊዜ የፊልሙን
ትወና የወደደችው ሲሆን ስንብትን ፊልም ከተመሰጦ ፣ ከውስጣዊ ፍቺ፣
ከስሜት፣ ከማስተዋል፣ እና ከድምፅ አወጣት ትወና አንፃር የፈልሙ ጠንካራና
ደካማ ጎኑ በመገምገም ሌሎች ፊልሞች ሲሰሩ ትወናው ላይ አንዴት መስራት
እነዳለባቸው በማወቅ እክፍተታቸው በመሙላት የ ፊልም ትወና ኢንዱስትሪው
ከፍ እንዲል ካላት ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡

1.2 ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች

- ስንብት ፊልም ከፊልም ትወና ባህሪያት አንፃር ሲተነተን ምን ይመስላል ?


- ስንብት ፊልም ላይ ያሉ ተዋናዮች የፊልሙን ትወና በሚገባ ተውነውታል ወይ
?
- የስንብት ፊልም ትወና ጥሩ እና ደካማ ጎኑ ምንድነው?
1.3 የጥናቱ አላማ
1 .3.1 የጥናቱ አብይ አላማ
የዚህ ጥናታዊ ፁሁፍ ዋና አላማዉ ‹‹ስንብት›› ፊልም ከፊልም ትወና
ባህሪያት አንፃር ትንታኔ መስጠት ነው፡፡

1.3.2 የጥናቱ ንዑስ አላማ

- ስንብት ፊልም ከፊልም ትወና ተመስጦ አንፃር መተንተን


- ስንብት ፊልም ከፊልም ትወና ውስጣዊ ፈች አንፃር መተንተን
- ስንብት ፊልም ከፊልም ትወና ስሜት አንፃር መተንተን
- ስንብት ፊልም ከፊልም ትወና ማስተዋል አንፃር መተንተን
- ስንብት ፊልም ከፊልም ትወና ድምፅ አወጣጥ አንፃር መተንተን

1.4 የጥናቱ ጠቀሜታ


ስንብት ፊልም ከፊልም ትወና ተመስጦ፣ዉስጣዊ ፍቺ፣ስሜት፣ማስተዋልእና
ከድምፅ አወጣጥ ትወና አንፃር እንዴት እንደተተወነ ግንዛቤ ይሰጣል ፡፡
- ለባችለር ኦፍ አርትስ ድግሪ ሟሟያነት ያገለግላል ፡፡
- የዚህን አይነት ተመሳሳይ ካላቸው ጥናታዊ ፁሁፍ ለሚሰሩ አጥኝዎች እንደመረጃ
ያገለግላል ።
1.5 የጥናቱ ወሰን
- ይህ ጥናታዊ ፁሁፍ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ‹ስንብት › ፊልምከፊልም ትወና
ባህሪያት አንፃር መገምገም ላይ የተወሰነ ነው፡፡

1.6 የጥናቱ ዘዴ

ይህ የጥናታዊ ፁሁፍ የሚጠቀሙ ገላጭ ያጠናን ዘዴ ሲሆን አለም እሸቱ ‹መሰረታዊ


የምርምርና የዘገባ አፃፃፍ › ላይ እንደተነተነው ገላጭ ምርምር ገለፃን ፣ ትንታኔና
አተረጓጎም መሰረት የሚያደርግ ሲሆን በሁለት ተለዋዋጭን መካከል የሚኖረውን
ተዛምዶ እያወዳደረና እያነፃፁ መመልከት ይቻላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ መረጃዎችን
ከተለያዩ ምንጮች የሚያሰባስን ሲሆን ትኩረት ግን የአንዱን ተጨባጭ ሁኔታ
ትክክለኛ ባህርይ መግለፅ ወይም ማሳወቀወ ይሆናል ፡፡(1994፤48) አጥኝዎ ይህን
ጥናትዊ ፁሁፍ ለመስራት የተለያዩ የመረጃ ዘይዎችን ትጠቀማለች ፡፡ከተጠቀመቻቸው
መካከል

- ከጥናቱ ጋርየሚዛመድ ጥናታዊ ፅሁፎች በማንበብ


- ከጥናቱ ጋር የሚዛመድ መፅሀፎች በማንበብ
- ከድህረ ገፅ ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች በማሰባሰብ እና
- ስንብት ፊልም ደጋግማ በማየት የመረጃ ማሰባሰቢያ ተጠቅማለች ፡፡

ምዕራፍ 2
2.1 የፊልም ምንነት

ፊልም በካሜራ አማካኝነት ምስልን አከታትሎ የገሀዱ እዉነታ የሚያስለን የኪነጥበብ


ዘርፍ ሲሆን የአንድን ማህበረሰብ ማህበራዊ አኗኗር ፡ሀይማኖት ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ፡
ታሪካዊ ክሰተቶችን ወይም ክንዉኖች እዲሁም የዕለተ ዕለት የኑሮ ሁኔታዎችን እና
ገጠመኞችን ወዘተ ... በተንቀሳቃሽ ምስል አማካኝነት ለተመልካች የሚያሳይ ልዩ ጥበብ
ነዉ ፡፡ ይህንን ሀሳብ የሚያጠና ክርልን የጳዉሎስ አእምሮ “የፈልም ጥበብ አዘገጃጀት
ዘዴ ” የተሰኘዉ መጸሀፍ ላይ እንዲህ ገልጾታል

”የእይታ ጥበበ የሆነዉ ፈልም የተለያዩ ምስሎችን

በተቀሳቃሽ ኪነ- ጥበብ ዘርፍ ነዉ ፡፡ ይህ ኪነ-ጥበብ

ዘርፍ በዉስጡም ምስልን ፣ድምጽን፣ ተግባራዊን


እንቅስቃሴዎችን በማቀነባበር የእይታን ምትሀት
በግበአት አማካኝነት እንቅሳቃሴ ልክ በገሀዱ
አለም የምናየዉ ድርጊት ይመስላል ፡፡ ”(2010፡9)

ከላይእንደተገለፀውፊልም ታሪክንበምስል፣በድርጊት፣በድምፅና፣እንቅስቃሴ
ቅንብርየመግለፅና

የመንገር ፡፡

ፊልም ምስል ቅንብር ብቻ አይደለምም ፡፡ የፈልሙ ታሪክ የሚያደንቅልን


ወይም ተወዳጅ ፈልም እንዲሆንል በውስጡ ሰው ሰራሽ ትእይምቱ የሚያግዙ
የሚደግፍ አልበናሳት፣ መብራት ፣ገፀቅ፣ሙዚቃ አርትአት ፣ ግብአተ ድምፅ ፣ምስል
ቅንብር ዝግጅት አለባውያን አንዱ ትወና ነው፡፡

2.2 የትወና ምንነት


ትወና ከፊልም ዝግጅት አላባዊያን አንድ ነው ።ትወና በድርሰት ወይም
በወረቀት ላይ ተጽፎ ያለማንነት በመላበስ ለተመልካች የሚቀርብበት መንገድ
ሲሆን ሰዎች የራሳቸዉን ማንነት በመተዉ ገጸ ባህሪዉን በመላበስ ሆነም ወይም
መስለዉ መተወን ማለት ነዉ ፡፡ ዘላለም ተፈሪ ”የፊልም ትወና ጥበብ
”በሚለዉ መፅሀፍ ላይ ስለ ትወና እደሚከተለዉ ገልጾታል ፡-
”ትወና ሙያ ነዉ ፡፡ ሰዎች በቲያትር ፣ በቴሌቬዥን ፣
በፊልም ፣በሬዲዬ እና በምስል የተለያዩ ታሪክን
በሚተርኩ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች በደራሲያን
ምናብ የተቀረጸ ገጸ -ባህሪያትን በመሆን የተጻፈ
(ያልተፈጸመ ሊሆን ይችላል ፡፡) ታሪክን በምስል ፣

በእንቅስቃሴ ፣በንግግር ፣በዘፈን ፣በድርጊት

ወዘተ ለተደራሲያን የሚተረኩበት ኪነ- ጥበባዊ


ሙያ ነዉ፡፡”(2010፡35)
ከላይ እደተጠቀሰዉ ትወና የመሆን እና የመምሰል ብቃት የሚጠይቅ ሲሆን
ተዋናዮቹ የገጸ-ባሀሪዉ አካላዊ ፣ማህበራዊ ፣ስነ- ልቦናዊ እና ስነ-ምግባራዊ የገጸ
ባሀሪያት አሳሳል በጥልቀት በመገንዘብ መስሎ ወይም ሆኖ ገጸ-ባህሪዉን መተወን
ይጠበቅባቸዋል ፡፡ እንዲሁም ትወና የማስመሰል ጥበብ እደመሆኑም መጠን
መጀመሪያ ተዋናዩ ስለ ገረ -ህሪዉ በሚገባ ማወቅ እና የተሰጠዉን ገጸ- ባህሪ
እሰራለዉ ብሎ እራሱን ሊያሳምን ይገባል ፡፡
በአጠቃላይ ትወና ማለት በድርሰት ወይም በቀወረቀት ተጽፎ የለ ታሪክ
ተወናዮቹ የሴት ወይም የወድ አሮጊት ፣ወጣት ፣ህጻን --- ወዘተ የመሳሰሉትን ገጸ
-ባህሪ ዉን በመላበስ በትያትር ፣በፊልም ፣በሬዲዬ ፣በቴሌቭዥነን ሲተወኑ
የምናቃቸዉ ጥበብ ነዉ ፡፡
2.3. 1.ትወና ታሪካዊ ዳራ
“ history of the there” መፀሃፍ ላይ በተገኝው የትወና ታሪካዊ አመጣጥ
መረጃ መሰረት በአጥኝዋ ስለትወና ታሪክዊ አመጣጥ እንዲህ ተብራርቶ
ቀርቧል ፡፡
ትወና በአፈታሪክ እንደሚነገረው ትወና የተጀመረው የሰው ልጅ አድኖ
በሚበሉበት ሰዓት ቀን በሚበሉበት ሰአት ቀን ሲያድኑ የነበረ ማታ ያደኑትን
እየበሉ የቀኑን ስራቸው በእንቅስቃሴ ፣ በጭፈራ ፣ በድምፅ እየተዝናኑበት
እንደተጀመረ በአፍ ታሪክ ይነግራል ፡፡ እንዲሁም የብሉይ ትወና ከሃይማኖታዊ
ስርአት ጋር ተያይዞ የመጣ ሲሆን ሰዎች ተሰባስበው አምላካቸው
ለማመስገን ስርአትነበር። ከክርስቶስ በፊት በአምስተኛዉ አመት አለም ገዳማ
በግሪክ ማህበረሰብ የቀብር ሰነ- ስርዓት የሃይማኖት በአላት ፣የፌስትቨል
አከባበርና ለአማልክቶች ክብር የሚዘጋጅ ዝግጅትቶች ለትወና ዉልደት
መምጣት እንደምልክት ይጠቀሳል።ይህ ክንዋኔ የመጣው ለረጅም ጊዜ በሚዘመሩ
የዳይናሲስ የምስጋና መዝሙሮች እና ውዝዋዜዎች እንደሆነ ይነገራል ፡፡
በወቅቱ መዝሙሮች የሚቀርቡበት በተመረጡ ብዛት ባለባቸው ህብረ
ዝማርያን ነበረ፡፡
በጥንት ግሪክ በ 6 ተኛ አመተ አለም ደያኖስስ የተባለ ሀይማኖታዊ
ክብረ በዓልን ለማክበር የማዘጋጃ ክንዋኔ ለትወና መነሻ እንደሆነ የሚገልፅ
ሲሆን
በ 6 ተኛ አመተ አለም ግሪክ ውስጥ ቴስፒስ የተባለ የመጀመሪያ
ተዋናይ መጣ ፡፡ይህሰው እረጅም የምስጋና መዝሙር ወደ ትራጀዲ የለወጠ
ሲሆን ከህብረ ዘማሪያን የመጀመሪያ ተዋናይ እንደሆነ ይነገርለታል ፡፡ከቴስፒስ
በኋላ የመጀመሪያው የትራጀዲ ፀሀፊ የነበረው ኤስክለስ የተባለ ደራሲ
ሁለተኛ እና አምስተኛ ተዋንያንን ጨመረ፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ቃለ-ተውኔት ሊፈጠር ችሏል ፡፡ ከዚህ በኋላ ሶፎክለስ የተባላ
ፀሀፊ ተውኔት ደግሞ የህብረ ዘማሪያንን ቁጥር ከአስራሁለት ወደ አስራስምንት
በመጨመር ሶስተኛው ተዋንኛን ሊጨምር ችሏል ፡፡ተዋንያን
ጭምብላልበመጠቀም ሁለትና ከዚያም በላይ ገፀ- ባህሪያትን ይጫወቱም ነበር።
በ 14 ተኛ ክፍለ ዘመን በጣልያን ኮሜዲያን ዴላርቴ በሚባል አስቂኝ
ትያትር አይነት የተጀመረ ሲሆን ዋና ታሪኩን ብቻ በመፃፍ ተዋንያን በራሳቸው
ፈጠራ ታሪኩ እያስፋፉ እና ቃለ ተውኔት እየጨመሩ (እየፈጠሩ)ይከወኔ ነበር ፡፡
ይህሰው ገፀ-ባህሪያትን በአልባስስ፣ በገፅቅብ ወይም ጭንብላል በመልስ በመላው
ጣቢያን ተወዳጅነት ሊያገኝ ይችላል ፡፡
በመቀጠል ኤልዛቤታን ትወና በምንቃኝበት በእንግሊዝ እስካሁን
ድረስ ዘመን ተሻጋሪ በሆነ ስራቸው የምናውቃቸው እነ ዊሊያም ሼክስፔር
፣ክርስተፎር ማርሎው እና ቤን ጆንሰን የመሳሰሉ ስመጥር ደራሲያን ተፈጠረበት
ዘመን ነበር፡፡ በኤልዛቤትን ትወና በምንቃኝነት ጊዜ ሴት ተዋናዩች
ባለመኖራቸው ምክንያት ወንዶች የሴቶችን ሚና እንዲጫወቱ ይደረግ
ነበር፡፡ ከዚያ ጋር ተያይዞ እስፔን ወረቃማየትወና ዘመንን ስናይ የጣልያኖቹ
የኮሜዲያን ዴልአርቴ ተዋንያኖች በእስቴን ሀገር ዘናቸው ጎልቶ ስለነበር
የሃላኛው እስፔን ወርቃማው የትወና ዘመን ተዋንያን ላይ ጉልህ ተፅኖ አሳድሮ
ነበር ፡፡
በ 16 ተኛ ክፍለ ዘመን ገዳምማ ፈረንሳይ ኒዎ ክላሲካል ትወና ታላላቅ
ተዋናች በፈረንሳይ አንድ አንድ አካባቢዎች እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ በፈርንሳይ
ትያትሮች በመድረኩ ለህይወት ቅርብ በመሰለ የመድረክ ግንባታ ይጠቀሙ
እንደነበርና ፈረንሳይ እና የጣልያን ተዋናዮቹ ብዙን ጊዜ ይከናወን የ ነበረ የህዝብ
ቀልዶችን ከዘፈንና ውዝዋዜ በማቀረብ ነው ፡፡
እንዲሁም እንግሊዝ ሃገር ሴቶች እንዳይተዉኑ ይከለከል ነበር ።በፈረንሳይ ሀገር
ግን ሴቶች እንዲተወኑ ይደረግ ነበርእና ከ እንግሊዝ የተሀድሶ ዘመን በተሻለ
አንዱእና ዋነኛው ሴት ተዋናዮችን መድረክ ላይ ማሳየቱ ነበር ፡፡
የ 18 ተኛ ክ/ዘመን ትወና በምናይበት ጊዜ ዝነኛ ተዋናዮቹ የነበሩበት እና
በመላዉ አዉሮፓ አህጉር ስኬታማ ተዋናዬች ብቅ ያሉበት ዘመን ነዉ ፡፡
ይተዉኑትም የነበረዉ የተዉኔትን ጥበብ ሙያ ለማህበረሰቡ ዘንድ ከፍ ለማድረግ
ነዉ ፡፡ በዚህ ዘመን የነበሩ ተዋናዬች በሚተዉኑበት ወቅት ንግግራቸዉ
ተፈጥሮአዊ ለማድረግ ይጨነቃሉ ፡፡
ዘመናዊ ትወነም በ 1800-1875 ብዙ ተመልካች ኮኮብ ተዋናዬችን
ይመኙ የነበረበት እና እንደ አርአያ ይቆጥራቸዉ የነበረበት ጊዜ ነዉ፡፡ ይህ
የመሰረተዉ ደግሞ ኮንስታነቲግ እስታነስ ላቨስኪን ነወ፡፡የሞስኮ ተዉኔት መስራች
እና የቸኮቨን ዋና ተዉኔት አሰልጣኝም ነበር ፡፡ አጠቃላይ የተዉኔት ታሪክ
አመጣጥ የሰዉ ልጅ ከጥናት ፍጥረቱ ጀምሮ በእለት ተእለት አኗኗር ዘይቤዉ
በግል ሆነ በጋራ የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ለተወና መነሻ እንደሆነ እና ዲያናሲስ
የተባለ ሃይማኖታዊ ክብረበአልን ለማክበር የሚዘጋጁ ክንኔ ለትወና መጀመር
መነሻ እንደሆነ ይነገራል ፡፡

2.3.1.1 የፊልም ትወና አጀማመር


https://fr-fr.facebook.come.የፊልም ትወና አመጣጥ በአደም ጌታቸው
ባብራራው እና https:// the film word .come. በተገኝው መረጃ መሰረት በአጥኝዋ
ስለ ፊልም አመጣጥ እንዲህ ተብራርቶ ቀርቧል
በብዙ አጥኝዎች አደሚባለዉ ፊልም ጀመረ የሚበለዉ በ 19 ኛ መቶ ክፍለ
ዘመን ሲሆን ከክርስቶስ ዉልደት በፊት ሉክርሰቲየስ የተባለዉ ሮማዊ ገጣሚ
እይታዊ መንፈሰ ጠንካራነት የሚያመለክ ሀሳብ አገኝ ፡፡ እ.አ.አ በ 1832 ጆሴፍ
አንቶኒ ፈርዲናድ ፕላቶ ለመጀመርያ ጊዜ የተለያሱ ሳክሎችን አንድ ላይ
ማንቀሳቀስ የሚችል ፈንስቶኮፕ የተሰኘ መሳሪያ ሰርቶ የፊልምን ስራ እርምጃ
ላይ አደረስ ፡፡
እ.አ.አ 1877 ስንፍራሲስኮዊዉ የፎቶ ግራፍ ባለሙያ ኤድዋርድ ሙይብሪጅ
እንቅስቃሴን በሚመለከት አንድ ምስል በመጠቀም እና የተለያዩ ቅርጽ በመስጠት
እና በካሜራ በመደገፍ የፈረስ እንቅስቃሴን እንደፊልም አድርጎ ለማንሳት ሞከረ፡፡
1877 እ.አ.አ አሜሪካዊ ካህን ሀኒባል ጉድዊን ዘላቂና ተለዋዋጭ የሆነ

በዘመናችን ለእራጅ ማንሻ የምንጠቀምበት ወረቀት በመጠቀም ተቀሳቃሽ


ፎቶዎችን በማሳየት ጀምረን የካሜራ ባከለሙያ የሆነው በጆርድ ኢስትማን ጋር
በመተጋገዝ ሰሩት።
በዚህ ዘመን ቶማስ አልቮ ኤድስን ደግሞ ከባልደረቦቻቸው ዊሊያም ኬኔዲ
ላውሪ ዳክሰን ጋር በመሆን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መቅረፅ የሚችል መሳሪያ
በመስራት ያዘጋጀዉን ተንቀሳቃሽ ምስል በኒዎርክ፣በለንደን፣እና በፓሪስ
ከተማዎች ለህዝብ አቀረበ።
እ.አ.አ በታህሳስ 28/1885 የሉሞሪ ወንድማመቾች የህዝብ ፕሮጀክት
1894 ለህዝብ የቀረበው ተቃሳቃሽ ምስል በእስክሪን በመታገዝ ለመጀመሪያ ጊዜ
በፓሪስ ውስጥ ባለ ካፌ አሳዩ ፡፡
እ.አ.አ ሚያዚያ 23/1886 ቶማስ አልባ ኤድሰን በእስክሪን ፕሮጀክተር
በመታገዝ ተቀሳቃሽ የህዝብ ምስልን የያዘ ስራ በኒዎርክ ከተማ በኮስትርና
በቢያል የሙዚቃ አዳራሽ የተሸለ ኪንቶሶኮፕ ፕሮጀክተር ይዞ በመቅረብ ስራውን
ሊያቀርብ ችሏል።
እ.አ.አ 1889 ፈረንሳዊዉ ጠንቋይ እና አስማተኛው ጆርጅ ሜልስ የተለያየ
ታሪኮችን የያዘ ፈልሞችን በማሳየት የመጃመሪያው የፊልም ኢንዱስትሪ አርቲስት
ሆነ ፡፡ ይህ ሰው በማዘጋጀት እናም በመተወን ተሳትፏል ።የፊልም ትወና
የጀመረውን ይህ ሰው ነው ፡፡ ስለዚህም በፊልም ትወና ታሪክ ውስጥ ግንባር
ቀደምና የመጀመርያው ሰው ጆርጅ ሜልስ ነው ማለት ይቻላል ፡፡
በ 20 ኛው 100 ክፍለ ዘመን እ.አ.አ በ 1900 የፊልም ትወና የተስፋፋበት
እና የህዝብን ትኩረት በአስገራሚ ሁኔታ በመሳብ በሙዚቃ አዳራሽ ሙዝሞቸና
የ በተለያዩ የቲያትር ክበብ ውስጥ በተለያዩ ሀገራት ውስጥ መታዩ የቀጠለ ሲሆን
1903 እ.አ.አ አሜሪያካዊዉ አዘጋጅ ኤድዊር ፓርተር በጣም ጠቃሚ የሆነ
ዘመናዊ የፊልም ቴክኒኮችን የተጠቀመ”ዘግራት ትረን እሮበፊ” የተሰኘውን
ፊልም ለእዕታ አበቃ፡፡
እ.አ.አ በ 1970 በአሜሪካ ወደ 500 የሚጠጉ ፊልሞች ለእይታ ያበቃ
ሲሆን ከዚህ በፊት ፊልምች የሚሰሩት በኒዎርክ እና ዊርትሊ ነበር ።ታድያ
ይህንን በማገናዘብ የፊልም ሰራተኞች እና ተዋናዮች ሎሳንጀለስ ለፊልም
ጥሩ በማጥናት ወደዛው አዞሩት፡፡
በ 1940 ዎቹ የፊልም ቁንጮዎች መወጣት ሳይጀምሩ በፊት የፈልም ትወና
ልክ እንደ መድረክ ትወና ነበር ተዋንያኑ በስም አይታወቁም ነበር፡፡ በ 1911
የኔስቶር ኩባንያ የመጀመሪያውን ሆሊውድ የተባለውን ስትድዩ በሎሳንጀለስ ገነባ
፡፡ ከዚያም ሆሊውድ በፊልሙ ዘርፍታዋቂ ሆነ፡፡
በ 1912 እ.አ.አ በመድረክ ትወና ታዋቂ የነበረችው ሴት ተዋናይ ሳአራ
ባርንሀንድ በ”ካውቦይ” ላይ ከተወነው ብራንኮ በሊአንዳርስን እና
ከኮሜዲንጅቡኒ ጋር በመሆን”ኪዊን ኤልሳቤት ”የተሰኝ ፊልም ላይ በመተወን
መጀመሪያዎቹ ኮከብ የፊልም ተዋና ይ ሆኑ፡፡በዚህ ወቅት ነበር ፈቱ አርቡክል
እና ቻርሊ ቻፒሊን ወደ ፊልም ትወና አለም የተቀላቀሉት።እነዚህ ተዋናዮች
በድርጊት እና በእንቅስቃሴ ነበር የሚተወኑት ፡፡ በ 1913 አሜሪካው አዘጋጅ
ዴዳብለው ግሪፋትስ የተለያዩ ፅንሰ ሀሳቦች የያዘአጫጭር ፊልሞችን
ከመግለጫዎቻቸዉ ጋር አንድ ላይ ለህዝብ አቀረበ፡፡

በአንደኛ አለም ጦርነት ወቅት በ 1914 የተንቀሳቃሽ ምስል ኢንዱስትሪ


በአውሮፓ በቁሳቁስ ችግር ምክንያት እየቀዘቀዘ መጣ ።በ 1915 የፎቶግራፎችና ምስሎች
ባለቤት የነበረው ቶማስ ኢንስ የተለያዩ ፊልሞችን እና ህዝብን የሚያስትፋ የተለያዩ
ፊልሞችን እደ ፕሮዳክሽኖችን ያዘጋጀ ነበር፡፡

እ.አ.አ በ 1922 የፊልም አዘጋጅ ሌብ ኩልሽቭ አዲስ የፊልም ቅንብር ቴክኒኮችን


በማሳየት እና በማስተማር የተለያዩ ፊልሞችን አዘጋጅተዋል ፡፡ በ 1925 የተለያዩ
የፊልሞች ስቱዲዩዎች ተመስርተዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ
foxunuprsal,metior,Goldwynmaver(MGM)paramount ,unitied artisistis,
wearbrothers, ይገኙበታል፡፡1926”wamer brog hers the jazz singer”የተሰኙ
በሙዚቃዊ የታጀበው ፊልም የተለያዩ ሙዚቃዎችን የያዙ ፊልም ሰርተዋል፡፡
በዚህ ሙሺቶን የተሰኘ አዲሰና የተሻለ ግብአተ ድምፅ ያለው የፊልም አላባ
ተሰርቶ ነበር ፡፡ የመጀመርያው ባለድምፅ ፊልም ይህ ፊልም ነው፡፡ በ 1930
ለህዝብ የተለያዩ ፊልሞች ቀርበው የነበረ ሲሆን ከነዚህም ጋር
ሙዚቃዎች፣ዘመናዊ ፊልምች እና አስፈሪ ፊልሞች ይሰሩ ነበር፡፡
በ 1935 “ዘ ኢንፎርመር”የተሰኙ በሙዚቃ ታጀበ በአሜሪካዊ ለህዝብ ቀረበ።
በ 1980 በ”M.GM”ህብረት በመፍጠሩ በአርቲስቶች ፊልሞች እየተሰሩ ለገቢያ
መቅረብን አጣጥፈዋል።
በ 1988‹‹ሁፈርምድ እሮዘር እሮይቢት›› የተሰኘዉ በቴክኖሎጂ የታገዘ
ፊልም ለእይታ አበቃ ፡፡ እ.አ.አ በ 1940<< ኒዉ ላይን ሲኒማ >> የሮበርት <<
ሊትል ማንን ዘፐሌየር >> የተባለዉ የጉርቫን ሳንትን << ማይ አዉን ፕራይቬት
አይዴዋ >>የተሰኙ ኮሜዲ ፊልሞችን አሳይቷል ፡፡
በ 1994 ሶስቱ የሆሊዉድ አቀናባሪ ዴቪድ ጂፈን በተለያዩ ስራዎች ላይ
መሳተፍ ለፊልም ማደግ ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክተዋል ፡፡ በ 1995<< አም አይ
ሰርዲ mirmax >>የተሰኘ አስራ አምስት ሚሊዬን ዶላር የፈጀ የአርባ ደቂቃ
<<ዊንግ ኦፍ ስሬጅ>> የሚል ፊልም ለዕይታ በቃ ፡፡በአጠቃላይ የፊልም ትወና
የፎቶ ግራፍ እና የትያትርን መፈጠር ተከትሎ የመጣ የስነ_ጥበብ ዘርፍ ነዉ።
በ 21 ኛ ክፍለ ዘመን ሞያዉ እጅግ ወደ ተወሳሰበ የኮምፒዩተር ዘመን ላይ
የደረሰ ቢሆንም በአንጻሩም ወደ ሀገራችን በተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ እጅጉ
ወደሀላ የቀረ የፊልም ደረጃ ባይሆንም መካከለኛ የሆነ ደረጃን የሚሆን ትወናን
እናቴክኖሎጂ በመጠቀም ይስሩ ነበር ፡፡
በአሁጉራችን ጥሩ የሚባል ትወና ባይኖርም ጥሩ ላይ ለመድረስ
እየተፍጨረጨረች ትገኛለች፡፡ በሀገራችን ኢትዮጲያ ፊልም የተጀመረዉ በንጉስ
ሚኒሊክ ዘመን ሲሆን ጣልያኖች የራሳቸው ዝና እና ባህል እንደማሳየት
ተጠቅመውበታል ፡፡በወቅቱ የውጭ ሀገር ፊልሞች ነበር የሚታየው በኢትዮጲያ
የመጀመርያ ጊዜ ‘’ሂሩት አባቷ ማነው’’?በሚል ርዕስ ተሰራ፡፡ ከዛም"
አስቴር" ለእይታ በቃ ፡፡ በ 1956 ሜሼልፓፓላሲ የተባለው ሰው በአባታቸው
ግሪካዊ ዜግነት ባላቸው አዘጋጅ ‹‹ጉማ››የተባለዉ የመጀመሪያ የቀለም ፊልም
ለእይታ በቃ። እንዲህ እንዲህ እያለ ለፊልም ትወና እድገት አመቺ የሆኑ
ቴክኖሎጂዎችንም በዚሁ ዘመን እየታየይገኛል ፡፡ ከ 3D አልፎ በ 7D እየተሰራ
ይገኛል ፡፡
2.4 የተዋናይ ምንነት
ተዋናይ ማለት የትወና ባለሙያ ሰው ሲሆን በአንድ ድርሰት ውስጥ ያለ ገፀ-ባህሪ
ወክሎ ስሜት ድምፅ ፣እንቅስቃሴ የተለያየ ድርጊቶችን በደንብ ተላብሶ ሆኖ ወይም
መስሎ የሚተወን የትወና ባለሙያሰዉ ነው፡፡በአዘጋጅ ሳሙኤል ተስፋዬ‹‹የትወና
ጥበብ ››በሚለው መፅሀፍ ላይ ስለተዋናይ ትርጉም እንዲህ ገልፆታል ፡-
’’ተዋናይ ማለት በፅሁፍ ተውኔቱ የተፈጠሩ ምናብ
አለም ፍጡራንን ወክሎ በአካሉ፣በአንደበቱ ክፍሎች አና
በአእምሮ ተጠቅሞ በመድረክ ላይ ግዙፍ
እንደነሱ የሚያደር ክሎት ፣እውቀትና ስልጠና
ያለው በቴአትር ጥበብ ውስጥ ጉልህ ሚና የሚጫወት
ሙያተኛ ሰው ነው፡፡ (2010፡49)
በዚህ ትንታኔ እንደምንረዳው ትወና ተዋናይ በስራ አካላቱ በአዕምሮና በአንደበት
ክፍሎቹ ሁሉ ተጠቅሞ የህይወት ልምድ ከተፈጥሮ የተቀበለው በህይወት እና በሰዉ
የቀዳውን መልሶ ለሰው ልጅ በአስገራሚ ክሎት ሚያሳይ ጥበብ ነው፡፡እንዲሁም
ደራሲው በሳለው ገፅ-ባህሪ የተለያዩ የስሜት ለውጦች ፣አካል እንቅስቃሴ ፣የተለያዩ
ድምፆችን አስመስሎ ተላብሶ የሚተወን የትወና ባለሙያ ሰው ነው፡፡ በሌላ በኩል
ወሰንየለህ ጥላሁን’’የፊልም ጥበብ ቅኝት ’’ በሚለው መፅሃፍ ላይ ስለተዋናይ
እንዲህ ገልፆታል ፡-
’’ አንድ ፊልም ለማየት ከመወሰናችን በፊት የምናነሳው
የመጀመሪያ ጥያቄ አዘጋጁ ወይም ሲኒማቶግራፊዉ ማነው?
የሚለዉ አይደለም ።እነማን ይሰሩበታል ? ነውየምንለው፡፡ (2005፡270)
ከዚህ ሃሳብ እንደምንረዳው ተዋናዮቹ የተሰጣቸው ገፀ-ባህሪ በ ደንብ ተላብሰው
ሲተውኑ ተመልካች ዘንድ ተቀባይነት እንዳላቸው እንዲሁም ጥሩ አድርገው
ማይተውኑ ተዋናዮች ተመልካች ዘንድ ተቀባይነት እንደሌላቸው ያሳያል ፡፡ስለዚህ
ተዋናዮቹ በትወናቸው የተመልቻች ቀልብ በመያዝ በደንብ መተወን እንዳለባቸው
እና የተሰጣቸውን ገፀ- ባህሪ በደንብ ተላብሰው መተወን ይጠበቅባቸዋል ፡፡

2.5 የፊልም ትወና

የፊልም ትወና ተፅፎ የተቀመጠን ታሪክ ይህወትን ሰጥቶ ድርጊት፣ እንቅስቃሴ እና


ድምፅን በመጠቀም ሚሰራ የጥበብ ዘርፍ ነው፡፡በሚተወንበት ሰዐት በተወሰነልን
ስፍራ ቆመን ፣ ተቀምጠን ፣እተራመድን እና ተለያዩ ስልት ለተመልካች ማሳየት
ብቻ ሳይሆን ምናደርገውን ድርጊት በመናገርም ምናስተላልፍበት መንገደው ነው ፡፡
የፊልም ትወና እንደ መድረክ ትወና ብዙ ብቃትን አይጠይቅም ፡፡
በድህረ ገፅ https:/www. Actiing basic/ acting /basic/gvied በተገኘው መረጃ
በአጥኝዋ እንዲህ ተብራርቶ ቀርቧል ፡-
’’ ተመልካች ፊታችን ባለመኖሩ ፍርሃት አይኖርብንም ።
ንግግር እና እንቅስቃሴ ቢጠፋብን አቋርጠን
አስታውሰን መቀጠል እድሉ አለን ፡፡ሁለተኛውና
የመጨረሻው ሰው እንዲሰማን ድምፃችን መጮህ ና
ከፍተኛ ጉልበት መጠቀምና የተጋነነ እንቅስቃሴን በማሳየት
ድርጊታችን ለማጉላት ልፋት የሌለበት ትወና የፊልም ትወና ነው፡፡
ከዚህ ፅንሰ ሃሳብ በመነሳት የፊልም ትወና ድክመት የሌለበት ትወና ነው
ማለትም እንደፍራለን፡፡ አንድ ተዋናይ ገፀ-ባህሪ ወክሎ ለመተወን በሚነሳበት ሰዓት
የሚተዉንበት ታሪክ ማህበረሰቡ ባህልና ወግ አምኖ አስተሳሰብ፣ የኑሮ ደረጃ
፣ማንነት ልምምድና የመሳሰሉ በደንብ ማጥናት ለፊልም ትውና ዋናዉ እና
አስፈለጊው ነገር ነው፡፡ የፊልም ትወና በትኩረት የሚሰራ በመሆኑ አንድ የፊልም
ተዋናይ ብዙ ማንበብና መማር ይጠበቅበታል። እንዲሁም የፊልም ትወና ትኩረት
ሰጥቶ በደንብ መስራት አለበት። በአካል ፣በቀለም ፣በግብር፣በምግባር፣ በስም፣
በአድራሻ፣ እና በመሳሰሉት አንድ ስው መገለጫና መታወቂያ መለይተን
የምናቃቻው ም በትወና በመሆኑ ለፊልም ትወና ትኩረት ሰጥተን በደንብ መስራት
አለብን። አንድ ተማሪ ለመማር መሟላት ያለበት ደብተር፣ እስክሪብቶ …………
፣ወዘተ እንሚያስፈልገው ሁሉ ተዋናዮችም በመድረክ በፊልም እና በሬድዮ
በሚተውኑበት ጊዜ ስሜት፣ተመስጦ፣ማስተዋል፣ ድምፅ ፣ ውስጣዊ ፊቺ አስፈላጊ
መሳሪያዎች ናቸዉ። ከዚህ ሃሳብ በመነሳት ለፊልም ትወና አስፈላጊው የሆኑትን
ዋና ዋና መስፈርቶች እንዲህ ታስቃኛለች።
2.5.1 ተመስጦ

መመሰጥ ማለት ሃሳብህን አንድ ቦታ ላይ ሙሉ በሙሉ ስብዕና ማቆት ማለትነዉ።


ይህ ማለት አንድ ሰው በማንኛውም የሙያ ዘርፍ ሲሰራ ለዛስራው ትኩረት ሰጥቶ
ሙሉ በሙሉ በስራው ላይ በመመሰጥ ሲሰራ የሚሰራው ስራ ስኬታማ ሲሆን እና
የተሳካ ስራ ሲሰራ ነው በተመስጦ ተሰራ የምንለው። አንድ ጆርሚ ኮሚ ’’the art
of film acting ’’ በሚለው መፅሃፍ ላይ ስለተመስጦ እንዲህ ሲል ገልፆታል

’’የተመስጦ ጥበብ ትኩረት የሚያደርግዉ


በተዋናዩ ሃሳብ ላይሲሆን ነገር ግን ግለሰቡ
ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላኛው ተዋንያን ስሜት ላይ መሆን ይኖርበታል
ለለ’’(2002፡30)

ከላይ እንደተገለፀዉ ተመስጦ በተዋናዩ ስሜት ላይብቻ ሳይሆን በሌላኛው


ተዋንያን ምላሽ ላይ ይኖርበታል ፡፡እንዲሁም ብዙ ጊዜ በትወና የሰለጠኑ እውቀት
ያላቸው ተዋናዮች በሚተወንበት ጊዜ በሚጫወቱት ገፀ-ባህሪ ታሪክ ውስጥ
ለመመሰጥና ከገፅ ባህሪ ሳይወጡ መቆየት ለመተወን አይቸገሩም፡፡ ጀማሪ ተዋናይ ግን
ከገፀባህሪው ጋር ከመመሰጥ ይልቅ በስራቸው ፈርሀት ውስጥ ሲቸገሩ ይታያል ፡፡ለምሳሌ
ስሰራ ሰዎች ምን ይሉኛል ? ቃለ ተዉኔቱ ቢጠፋብኝስ በሚሉ ምክንያቶች ከመመሰጥ
ይወጣሉ፡፡ስለዚህ አንድ ተዋናይ የተመልካችን ቀልብ ገዝቶ ሊይዝ ፣ሊያሰምንየሚችለው
እርሱ ሲመሰጥ ብቻ ነው፡፡

2.5.2 ዉስጣዊ ፍቺ

ውስጣዊ ፍቺ ማለት አንድን ቃል ቀጥታ ከመተርጎም እና አንደበታዊ ፍቺ ምን


እንደሆነ ከማወቅ በፊት ቀጥተኛፍቺ ለይተን ካወቅን በኋላ ከፋፍሎ ማስተላለፍ
የፈለገውን መልዕክት በእንቅስቃሴ እና በድርጊት መግለፅ ማለት ነው፡፡ዘላለም
ተፈሪ’’ የፊልም ትወና ጥበብ’’ በሚለው መፅሃፍ ውስጥ ስለ ውስጣዊ ፍቺ
እንደሚከተለው አሰፍሯል፡፡

በፊልም ዉስጥ ዉስጣዊ ፍች የምንለዉ በስሜት አማካኝነት የሚከወን ንግግር


የታጀበ ወይም ድመፅ አልባ ተግባቦት ነዉ ፡፡(2010:117) በአጠቃላይ ዉስጣዊ ፍችን
ማለት ለፊት ገጽታ ፣ለሰዉነት እንቅስቃሴ እና በአካላችን በምናሳያቸዉ ገጽታዎች
ይገልጻሉ ፡፡ ሌላዉም ማንኛዉም ቃላት ሊሆን ይችላል በሚናገሩበት ጊዜ ተመልካች
ታሪኩ እዲገባዉ እና ገፀ-ባህሪ ምን ማለት እደፈለገ ማስረዳት አለበት ፡፡ስለዚህ አንድ
ተዋናይ በሚተዉንበት ጊዜ የቃላት ዉስጣዊ ፍቺን በሚገባ ማጥናት አለበት ፡፡
2 .5 3 ስሜት

ስሜት ማለት ከአምስቱ የስሜት ህዋሳት የሚመነጭ ስሜት ሲሆን በፊልም ላይ


የመጀመሪያዉ እና አስፈላጊ ነገር ስሜት ነዉ። ተዋናይ በሚተዉኑበት ሰአት ከእርሱ
ጋር የሚመስራዉ ተዋናይ ስሜት ዉስጥ ሆኖ ሲሰራ እሱጋ የሚሰራዉ ስሜት ተጋርቶ
የፊልሙ ታሪክ (ስሜት)በሚገባ ለማንጸባረቅ የሚረዳ ክፍል ነዉ ፡፡በዘላለም ተፈሪ
"የፊልም ትወና ጥበብ "በተሰኘዉ መጸሀፍ ዉስጥ ስለ ስሜት እንዲህ ገልፆታል" ስሜት
ስንል በአመለካከታችንና በአስተሳሰባችን ላይ የሚመረከዝ በአእምሮአችን አስገዳጅነት
የሚከሰት ክስተት ነዉ፡፡ (2010፡116)

ከዚህ ሀሳብ በመነሳት ስሜት በልምድ ወይም በሙከራ የሚመጣ አይደለም።


በአእምሮ አስገዳጅነት የሚከሰት ክስተት የሚመጣ ሲሆን አንድ የፊልም ተዋናይ
የሚተዉንበትወቅር ከእርሱጋር የሚተዉንበት ተዋናይ ስሜት የሚደነገጥ ሲሆን
የመደንገጥ ፣የመደሰት፣የማዘን አብረዉ ተጋግዘዉ ስሜቱ ለተመልካች ማድረስ እና
ተመልካችን ወደ እራሳቸዉ ስሜት ማዉጣት አለባቸዉ፡፡

2.5.4 ማስተዋል

ማስተዋ ል ማለት የዉስጥን መረዳት ሲሆን ተዋናይ የተሰጠዉን ገጸ ባፀ-ባህሪ


ምንነት እና ሁኔታ በማየት ወደ እራሱ መምጣት መሞከር ማለት ነዉ ፡፡ግሩም
ኤርሚያስ መሰረታዊ ትወና በሚለዉ መጸሀፍ ላይ ስለማስተዋል እዲህ ገልጾታል ፡-"
ምንጊዜ የምታየዉ ሰዉ ትእይንቶችና ድርጊትቶች ያስተዋልከዉን ነገር ለምትጫወተዉ
ገፀ-ባህሪ ዉስጥ በተመልካች ህሊና ዉስጥ ግልጽና ጠሚታመን ሆኖ መቅረብ
አለበት ፡፡"(2008፡25)

በዚህ መሰረት የሰዎች ባህሪን አለባበስ ፣ቅርጽ፣አበላል ---- ወዘተ ማጥናት ለፊልም
ትወና በጣም ይረዳል ፡፡እንደ ተዋናይ የማስተላለፍ ችሎታ ለማዳበር ዝግጁ ፡መሆን
ስኖርበት ስልቹ መሆን ግን የለበትም ፡፡ ስለዚህ አንድ ተዋናይ በጥልቀት አስተዉሎ
መመልከት ትልቅ የሆነ ማስተዋልን ይፈጥርበታል ፡፡ስለዚህ አንድ ሰዉ በጥልቀት
አስተዉሎ መመልከት ለትወናዉ ጥልቅ የሆነ ማስተዋልንን ይፈጥርበታል፡፡

2.5.5 ድምጽ አወጣጥ

የሰዉ ልጅ እርስ በ እርስ ስ የሚግባባ በቃላት እና ድምጽ በማዉጣት ነዉ። ድምጽ


ለአንድ ተዋናይ መገልገያ መሳሪያ ሲሆን ተዋናዬቹ የሚናገራቸዉ ሀሳቦች እና ንግግሮች
ለተመልካች በጥራት ማስማት አለበት ፡፡ካቲሀሲ" Acting for film"በሚለዉ መፀሀፍ
ዉስጥ ስለ ድመፅ አወጣጥ እንዲህ ገለጾታል ፡-
<< ተመልካች የተዋናዬቹን ድምጽ ጥርት ያለ
መልኩ ሊሰማ ይገባል ፡፡የተዋናዩ ድመፅ ከፍ
አድርጎ ለተመልካች ማሰማት ይጠበቅብናል ፡፡
እናም የሚያወጣዉ ድመጽ ጥርት ያለ
ድምፅ መሆን አለበት ፡፡>>(2003 ፡31)

ስለዚህ የትወና ትልቁ አላማ እና ቁም ነገር ታሪኩን ወደ ተመልካች ማድረስ ስለሆነ


በፊልሙ እስክሪብት ዉስጥ ያለቀለ-ተዉኔት በስርአት ሳይቆራረጥ ለተመልካች ማድረስ
ግዴታዉ ነዉ ፡፡ ስለዚህ አንድ የፊልም ተዋናይ እለት ተእለት የድምፅ ሁኔታ መጠበቅ
እና መከታተል ብሎም መንከባከብ ይኖርበታል፡፡

You might also like