መልሶ ማልማት

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 20

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ

የከተሞች መልሶ ማልማትና ማደስ የአፈጻጸም መመሪያ

ግንቦት 2006 ዓ/ም

ባህር ዳር

0
መመሪያ ቁጥር 6/2006 ዓ.ም

ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ የስራና የመኖሪያ ስፍራ እንዲሁም ተወዳዳሪ የልማት እና የእድገት ማእከል መሆን እንዲችሉ
እንደየከተሞቹ ተጨባጭ ሁኔታ የደቀቁና ለሥራና ለመኖሪያ ምቹ ያልሆኑ አካባቢዎችን የመቀየር ሥራን መስራት
በማስፈለጉ፤

በምዕተ አመቱ የደቀቁና የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በግማሽ ለመቀነስ ግብ ተይዞ በእንቅስቃሴ ላይ የምንገኝ ከመሆኑም
በላይ ተግባሩም ከተሞች ከሀገራዊ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመነሳት ድህነትን ለመቀነስ የሚደረጉት ጥረት
አካል በመሆኑ፣

የደቀቁ የከተማ ክፍሎችን ወደ ምቹ የስራና የመኖሪያ አካባቢ ለመቀየር ከተሞች ተግባራዊ ከሚያደርጓቸው የመሬት
ልማትና ማኔጅመንት ቁልፍ ተግባራት አንዱ የከተማ መልሶ ማልማት/ማደስ ፕሮግራም እንደሆነ ስለታመነበት፤

በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ባሉ የደቀቁና ያረጁ አካባቢዎች ላይ በርካታ ነዋሪዎች በተፋፈገና በተጨናነቀ ሁኔታ የሚኖሩ
በመሆናቸው ይህን ሁኔታ ለውጦ በአካባቢው የተጓደሉ መሰረታዊ አቅርቦቶችን በማሟላት ለነዋሪዎች ተስማሚ እና
ምቹ የሆነ አካባቢን ለመፍጠር የመልሶ ማልማት/ማደስ ሥራውን በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ በህግ አግባብ መምራት
ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 33 ንዑስ አንቀጽ 2፣ የከተማ ቦታ
በሊዝ ስለመያዝ በወጣው የክልሉ ደንብ ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 2 እና የክልሉን አስፈጻሚ
አካላት እንደገና ለማቋቋምና ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 176/2003 አንቀጽ 11
ንዑስ አንቀጽ 1/ሠ/ ድንጋጌዎች ስር በተሰጠው ስልጣን መሰረት የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ይህንን
የአፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል፡፡

1
ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1. አጭር ርዕስ:-

ይህ መመሪያ “የከተሞች የመልሶ ማልማትና ማደስ መመሪያ ቁጥር 6/2006” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ:-

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ

1. “አዋጅ” ማለት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 ዓ.ም
ነው፡፡

2. “ደንብ” ማለት በአማራ ክልል ከተሞች የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣ የክልሉ መስተዳደር
ደንብ ቁጥር 103/2004 ነው፡፡
3. “የከተማ አስተዳደር” ማለት በሕግ በታወቀ ወሰን ተደራጅቶ የአንድን ከተማ ነዋሪ ህዝብ የፖለቲካ፣
የአስተዳደር፣ የልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ሥልጣንና ኃላፊነት በመረከብ የሚመራ የአካባቢ
አስተዳደር ነው፡፡

4. "የከተማ መሬት" ማለት በከተማው አስተዳደር ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኝ መሬት ነው፡፡

5. “የሊዝ መነሻ ዋጋ” ማለት ዋና ዋና የመሠረተ ልማት አውታሮችን ለመዘርጋት የሚያስፈልግ ወጪ፣
ነባር ግንባታዎች ባሉበት አካባቢ የሚነሱ ግንባታዎችና ንብረቶች ለማንሳት የሚያስፈልገዉን ወጪና
ለተነሺዎች የሚከፈል ካሣን እና ሌሎች አግባብነት ያላቸዉ መስፈርቶችን ታሳቢ ያደረገ የመሬት
የሊዝ የጨረታ መነሻ ዋጋ ነው፡፡

6. "የደቀቀ ወይም የተጎዳ አካባቢ" ማለት በከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ የሚገኝ የደቀቁ እና ያረጁ
ግንባታዎች እና ከደረጃ በታች የሆነ አሰፋፈር የሚገኝበት ለኑሮ እና ለስራ አመቺ የሆኑ አቅርቦቶች
በመሰረታዊነት የተጓደሉበት የከተማ ክፍል ነው፡፡

7. "መልሶ ማልማት" ማለት በከተማ የደቀቀ ወይም የተጎዳ አካባቢን በሙሉ ወይም በከፊል አፍርሶ
በማንሳትና ሙሉ በሙሉ ነጻ በማድረግ መልሶ ከሚለማው ቦታ ውስጥ በከተማው ፕላን መሰረት
ዝቅተኛውን የግንባታ ከፍታና እስታንዳርድ የሚያሟሉና ታሪካዊ ቅርስነት ያላቸው ግንባታዎች
እንደተጠበቁ ሆነው ሌላው ቦታ በፕላኑ መሰረት እንደገና እንዲለማ የማድረግ ሂደት ነው፡፡

2
8. "ከተማ ማደስ" ማለት የከተማ የተጎዳ አካባቢን መሰረታዊ አቅርቦቶችን በመዘርጋት ወይም የቤቶችን
ደረጃ በማሻሻል ወይም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአሰፋፈር አግባብን በማስተካከል ገጽታ
ለማሳደግ የሚከናወን ተግባር ነዉ፡፡

9. ”ብሎክ” ማለት ሰፋ ተደርጎ የተያዘ የመሬት ክፍል ሲሆን አብዛኛው ዳርቻዎቹ ለመንገድ ተደራሽ የሆኑ ነገር ግን
በውስጡ የሚያቋርጥ መንገድ የሌለበት ቦታ ነው፡፡

10. “ የብሎክ ልማት ” ማለት መልሶ በሚለማዉ አካባቢ የሚገኙ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ብሎኮችን
ደረጃ በደረጃ የከተማውን አቅም ባገናዘበ መልኩ የሚከናወን የመልሶ ማልማት ተግባር ነው፡፡

11. “የኪስ ቦታ ልማት” ማለት በአካባቢ ልማት ፕላን ውስጥ የተካተቱም ሆኑ የአካባቢ ልማት ፕላን
ባልተዘጋጀላቸው ዋና ዋና መንገዶችንና አደባባዮችን ተከትሎ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ አርፎበት
ለአካባቢው ከተፈቀደው ወይም ከሚፈቀደው አገልግሎት በታች በመስጠት ላይ የሚገኝና ደረጃውን
ጠብቆ ያልለማ ቦታን በልዩ ሁኔታ መልሶ ማደስ ነው፡፡

12. "የሕዝብ ጥቅም" ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቡ በመሬት ላይ ያለውን ተጠቃሚነት
ለማረጋገጥና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በቀጣይነት ለማጎልበት አግባብ ያለው አካል በከተማ
መዋቅራዊ ፕላን ወይም በልማት ዕቅድ መሠረት ለሕዝብ ጥቅም ብሎ የሚወስነው የመሬት አጠቃቀም
ነው፡፡

13. "የግል ባለይዞታ" ማለት መልሶ በሚለማዉ ወይም በሚታደሰዉ ቦታ ላይ ሕጋዊ የባለይዞታነት መብት
ያለው ሆኖ በመሬቱ ላይ ንብረት ያሰፈረና ያፈራ የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት
የተሰጠው ማንኛውም አካል ነው፡፡

14. "የመንግስት ቤት ተከራይ" ማለት በሕጋዊ አግባብ ለመኖርያነት ወይም ለንግድ አገልግሎት የከተማዉ
አስተዳደር ወይም የመንግስት ቤቶች አስተዳደር በሚያስተዳድራቸው ቤቶች በዋና ተከራይነት ወይም
በህጋዊ ደባልነት በመገልገል ላይ የሚገኝ ነዉ፡፡

15. "ኪራይ ቀመስ ይዞታ" ማለት በግል ይዞታነት የሚተዳደር ቤት እና የከተማዉ አስተዳደር ወይም የመንግስት ቤቶች
አስተዳደር የሚያስተዳድረዉ ቤት በጣምራ የሚገኙበት ይዞታ ነዉ፡፡

16. "ካሳ" ማለት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዲለቀቅ በተፈለገው መሬት ላይ በህጋዊ መንገድ ለሰፈረ ንብረት በዓይነት፣
በገንዘብ ወይም በሁለቱም በካሳ መመሪያው ላይ በተቀመጠው የስሌት ቀመር መሰረት የሚፈፀም ክፍያ ነው፡፡

3
17. "ተነሺ" ማለት ለህዝብ ጥቅም በሚፈለግ መሬት ላይ የግል ይዞታ ባለመብት የሆነ ወይም የከተማዉ አስተዳደር
ወይም የመንግስት ቤቶች አስተዳደር በሚያስተዳድረዉ ቤት በዋና ተከራይነት ወይም በህጋዊ ደባልነት በመገልገል ላይ
የሚገኝ ነዉ፡፡

18. ‘’ቢሮ’’ ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ነው::

19. ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ይጨምራል፡፡

3. የተፈጻሚነት ወሰን
1. ይህ መመሪያ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ከተሞች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

2. የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ቢኖርም ቢሮው እንዳስፈላጊነቱ መመሪያው ተፈጻሚ
የሚሆኑባቸውን ከተሞች ቅደም ተከተል ለመወሰን ይችላል፡፡

ክፍል ሁለት
4. የከተሞች የደቀቁና የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን መከለል እና መለየት

1. በመልሶ ማልማት ወይም በከተማ ማደስ አግባብ እንዲለሙ የሚደረጉ አካባቢዎች


በዝርዝር ጥናት ተለይተዉ በፕላን የሚከለሉ እና በካርታ የሚመላከቱ ይሆናሉ፡፡

2. ከተሞች በመልሶ ማልማት አግባብ ለሚለሙ አካባቢዎች ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን በማዘጋጀት
እና በከተማ ማደስ የሚለሙ አካባቢዎች ዝርዝር የማስተግበሪያ እቅድ በማዘጋጀት በከተማው ምክር
ቤት በማስጸደቅ እንዲተገበሩ ያደርጋሉ፡፡

3. የተዘጋጀ የአካባቢ ልማት ፕላን የጊዜ ቆይታ ለ 5 ዓመት ሆኖ ጥናቱ ተግባራዊ ሳይደረግ ከዚህ በላይ ከቆየ
እንዳስፈላጊነቱ ሊከልስ ይችላል፡፡

5. የከተሞች የደቀቁ እና የተጎዱ አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት/ ከተማ ማደስ ስለሚቻልበት


ሁኔታ

5.1 የከተማ መልሶ ማልማት


የከተማ መልሶ ማልማት ትግበራ እንደ ስራው ስፋት ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ
የሚጠናቀቅ ሆኖ በከተማ መልሶ ማልማት የሚለማ አካባቢ ከሚከተሉት ዝቅተኛ መስፈርቶች ቢያንስ
አንዱን ያሟላ መሆን ይኖርበታል፡-

4
ሀ. ለመልሶ ማልማት በተከለለው አካባቢ በአማካይ በአንድ ሄ/ር ዉስጥ ስልሳ በመቶ እና ከዚያ በላይ የሆነዉ
ግንባታ በእድገት ፕላኑ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የፕላን ስታንዳርድ ያላሟላ ሲሆን፣

ለ. ለመልሶ ማልማት በተከለለው አካባቢ ሀምሳ በመቶ እና ከዚያ በላይ የሆነዉ ግንባታ የደቀቀ እና ያረጀ
ሲሆን፣

ሐ. ለመልሶ ማልማት በተከለለው አካባቢ በአካባቢዉ ላይ በቂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ የሌለ እና ነዋሪዎች
በትፍፍግ እና ለኑሮ በማይመች አግባብ የሚገኙ ሲሆን፣

መ. ለመልሶ ማልማት በተከለለው አካባቢ በአማካይ በአንድ ሄ/ር ዉስጥ ያለዉ ከሀምሳ በመቶ እና ከዚያ
በላይ የሆነዉ ግንባታ የይዞታ አስተዳደር መመሪያ የሚፈቅደዉን ዝቅተኛዉን የቦታ ስፋት ያላሟላ
ሲሆን፣

ሠ/ አካባቢውን በመልሶ ልማት ትግባራ ማልማት ለከተማው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ገጽታ
ግንባታ አስፈላጊ መሆኑ በከተማው ም/ቤት በኩል ውሳኔ ሲሰጥበት፣

5.2 ከተማ ማደስ


የከተማ ማደስ ተግበራ እንደስራው ስፋት ከአንድ እስከ አምስት ዓመት ባለዉ ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም
ይሆናል፡፡ በከተማ ማደስ የሚለማ አካባቢ ከሚከተሉት ዝቅተኛ መስፈርቶች ቢያንስ አንዱን ያሟላ
መሆን ይኖርበታል፡-

ሀ. በከተማ ማደስ በተከለለው አካባቢ በአማካይ በአንድ ሄ/ር ዉስጥ ሀምሳ በመቶ እና ከዚያ በታች የሆነዉ
አሰፋፈር የሚጠበቀዉን የፕላን ስታንዳርድ ያላሟላ ከሆነ ወይም፣

ለ. በአማካይ በአንድ ሄ/ር ዉስጥ ያለዉ ከሀምሳ በመቶ እና ከዚያ በታች የሆነዉ ግንባታ በህንጻ ህጉ
ከተቀመጠው የግንባታ እስታንዳርድ በታች ከሆነና ከቦታ ሽንሻኖ እስታንዳርድ አኳያ ዝቅተኛዉን
የቦታ ስፋት ያላሟላ ሲሆን፣

ሐ. አካባቢው የመሰረተ ልማት (ውሃ፣ መንገድ፣ የቆሻሻ እና ፍሳሽ ማስወገጃ) ችግር ያለበትና ለስራ አካባቢ
ምቹ ማድረግን ብቻ የሚጠይቅ እና በቀላሉ ለማደስ የሚቻል ሲሆን፣

መ/ አካባቢውን በከተማ ማደስ ትግባራ ማልማት ለከተማው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስፈላጊ
መሆኑን በከተማው ወይም በወረዳው ካብኔ በኩል ውሳኔ ሲሰጥበት፣

5
6. የከተሞች የመልሶ ማልማት/ የከተማ ማደስ ወሰን

በከተሞች የደቀቁ እና የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማልማት ወይም ከተማ ማደስ በሚከተለዉ የአደረጃጀት
አግባብ የሚፈጸሙ ይሆናል፡፡
6.1 የከተማ መልሶ ማልማት

ሀ. ስፋታቸዉ ከ 10 ሄ/ር በላይ የሆኑ አካባቢዎች በመልሶ ማልማት የሚካተቱ ሲሆን በመልሶ ማልማት ልማት
ቀጠና ደረጃ የሚለሙ ይሆናል::

ለ. ስፋታቸዉ ከ 10 ሄ/ር በታች የሆኑ አካባቢዎች በብሎክ የልማት አግባብ የሚለሙ እና ከሁለት የበጀት ዓመት
በታች የሚፈጸሙ ይሆናል፡፡

ሐ. የከተማ መልሶ ልማት ትግበራ ከአንድ እስከ አምስት የበጀት ዓመት የሚጠናቀቅ ይሆናል::

6.2 የከተማ ማደስ

ሀ. ስፋታቸዉ ከ 5-10 ሄ/ር የሆኑ አካባቢዎች ለከተማ ማደስ ስራ ሊለዩ ይችላሉ::

ለ. ስፋታቸዉ ከ 5 ሄ/ር በታች የሆኑ አካባቢዎች ወይም ወርዳቸው አስከ 150 ሜትር የሆኑ እና ቁመታቸው
አስከ 260 ሜትር የሆኑ የዋና መንገድ ዳርቻዎችና አደባባዮች በኪስ ቦታ ልማት አግባብ የሚለሙ
ይሆናል፣

ሐ. የከተማ ማደስ ትግበራ ከአንድ እስከ አምስት የበጀት ዓመት የትግበራ ጊዜ ይኖራቸዋል::

1. በከተማ መልሶ ማልማት/ከተማ ማደስ አካባቢ የተነሺዎችን ይዞታዎች መረጃ ማሰባሰብና


ማደራጀት፣
1. የተነሺዎች መሬት የስፓሻል እና ሶሺዮ ኢኮኖሚ መረጃዎች በተዘጋጀው ፎርማት
መሰረት እንዲሰበሰቡ ይደረጋል፡፡ የግንባታው ያለበትን ሁኔታ ደረጃ ለማወቅ በፎቶ እና ከተቻለ በቪዲዮ
በማስደገፍ መረጃው ይያዛል፡፡

2. ለካሳና ምትክ ባለመብትነትን ለመወሰን እና ለንብረት ግምት፣ ለውሳኔ የሚያስፈልጉ


የሶሺዮ ኢኮኖሚና የስፓሻል መረጃዎች ይሰበሰባሉ፡፡

3. በመልሶ ልማት/ከተማ ማደስ ከይዞታቸው ተነሺ የሆኑ ወይም ይዞታቸው የሚነካባቸው የይዞታ
ባለመብቶች መረጃ እራሱን የቻለ አዲስ ፋይል ተከፍቶላቸው ተደራጅቶ እንዲያዝ ይደረጋል፡፡

6
5. በመስክ የልኬት መረጃ ሲሰበሰብ የይዞታው ባለቤት/ሕጋዊ ወኪል ተገኝቶ ስለማስለካቱ፣ የነዋሪዎች
ተወካዮች በታዛቢነት በተገኙበት መረጃው ይሰበሰባል፡፡ ይህንም በተዘጋጀው ቅጽ ላይ እንዲፈርሙ
ይደረጋል፡፡

2. ከከተማ መልሶ ማልማትና ከተማ ማደስ አካባቢ ተነሽዎች የንብረት ካሳ እና ትክ አሰጣጥ፣


8.1 የግል ባለይዞታዎች የካሳ ክፍያ ግምትና የምትክ ቦታ/ቤት ባለመብትነትን ስለመወሰን

ሀ. ለህጋዊ የነባር ይዞታ ባለመብት በከተማው የቦታ ሽንሻኖ እስታንዳርድ መሰረት ምትክ ቦታ በነባሩ
የኪራይ ስሪት መሰረት ይሰጠዋል፣

ለ. የተሟላ ሰነድ የሌላቸው እና ሰነድ አልባ ይዞታዎች ምትክ ቦታና ካሳ ማግኘት እንዲችሉ በስራ ላይ
ባለው የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት ተጣርቶ በቅድሚያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማግኘት
አለባቸው፡፡

ሐ. ለሊዝ ባለይዞታው ለቀሪው የሊዝ ዘመን ተመሳሳይ ስፋትና ደረጃ ያለው ምትክ ቦታ በነባሩ ሊዝ አግባብ
ይሰጠዋል፣ ክፍያዉን በተመለከተ በነባሩ ክፍያ ስሌት መሰረት የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ሆኖም በሽንሻኖ
ምክንያት የቦታ ስፋት ልዩነት/መቀነስ ወይም መጨመር ካለ የልዩነት ክፍያውን የመክፈል ግዴታ ወይም
የቀሪውን ቦታ የሊዝ ዋጋ የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡

መ. ተነሺ ለሆኑ የግል ባለይዞታዎች በስራ ላይ ባለው የክልሉ የንብረት ግምት እና ካሳ መመሪያ መሰረት
ይስተናገዳል፡፡

ሠ. በዚህ አንቀጽ ፊደል ተራ መ የተገለጸው ቢኖርም ለህዝብ ጥቅም ሲባል በተወሰደባቸው ቦታ ላይ


ከሰፈረው ንብረት ውጪ በግል ይዞታቸው ላይ ለሚያለሙ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች
በቦታው ላይ ለነበራቸው ንብረት ካሳ አይከፈልም፣

ረ. በምትክነት የተሰጠ ነባር ይዞታ የግንባታ መጀመሪያ እና ማጠናቀቂያ ጊዜ በአዋጁ እና በደንቡ በተቀመጠዉ መሰረት
ይሆናል፡፡

8.2 የመንግስት ቤት ህጋዊ ተከራይ የንብረት ካሳ እና ትክ አሰጣጥ፣

8.2.1 የመኖሪያ ቤት ተከራዮች

7
የጋራ ቤቶች ልማት ፕሮግራም በሚከናወንባቸው ወይም ፕሮግራሙ በሌለባቸው ከተሞች በመልሶ
ማልማት ምክንያት ተነሺ ለሚሆኑ ህጋዊ ተከራዮች በሚከተሉት ቅደም-ተከተል መሰረት
የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

ሀ. በማህበር ተደራጀተው የጋራ መኖሪያ ኮንደሚኒየም ቤት ለመገንባት ከፈለጉና የግንባታ ወጪ ግምት


30-35% በዝግ የባንክ ሂሳብ የአቅም ማሳያ በማስቀመጥ የአካባቢ ልማት ጥናቱ በሚፈቅደው
የፕላን ምደባና የቦታ ሽንሻኖ መሰረት እንዲስተናገዱ ይደረጋል፡፡

ለ. የኮንዶሚኒየም ቤት በቅድሚያ ግዢ ወይም ምትክ የመኖሪያ ቤት በኪራይ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

ሐ/ ከላይ በዚህ አንቀጽ ፊደል ተራ ሀ እና ለ በተቀመጡት አማራጮች ማስተናገድ በማይቻልበት ጊዜ


በከተማው ዝቅተኛው የቦታ ስታንዳርድ ስፋት የአቅም ማሳያ የግንባታ ወጪውን ግምት 20%
በዝግ የባንክ ሂሳብ በማስያዝ በሊዝ መነሻ ዋጋ በምደባ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ በህጋዊ ደባልነት
የተመዘገቡ ተከራዮች ተመሳሳይ መብት ይኖራቸዋል፡፡

መ/ ከላይ በዚህ አንቀጽ ከሀ እስከ ሐ የተገለጸው ቢኖርም ተነሽዎቹ በስማቸው ወይም በትዳር ጓደኛቸው ስም
የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በከተማዉ ውስጥ ያላቸው ከሆኑ የዚህ መብት
ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

8.2.2 የንግድ ቤት ህጋዊ ተከራዮች


1. የአካባቢው ልማት ፕላን በሚፈቅደው መሰረት ግንባታ በጋራ ተደራጅተው ለማከናወን ፍላጎት
ሲኖራቸው ለዚሁ ግንባታ የሚሆን ተመጣጣኝ ቦታ፡-
ሀ. ለሜትሮፖሊታን ከተሞች 25 ካ/ሜትር፤
ለ. ለመካከለኛ ከተሞች 75 ካ/ሜትር፤
ሐ. በአነስተኛ ከተማ 100 ካ/ሜትር፤
መ. በማዘጋጃ ቤት ከተሞች 150 ካ/ሜትር በነፍስ ወከፍ በሊዝ/ኪራይ መነሻ ዋጋ የሚስተናገዱ
ይሆናል፡፡
ሠ. በፕላኑ የተመለከተው ሽንሻኖ ከዚህ በላይ ከፊደል ተራ ሀ እስከ መ ለአባላቱ በነፍስ ወከፍ
ከተፈቀደው ጠቅላላ ስፋት በላይ ከሆነ ቀሪውን ቦታ በአካባቢው ከፍተኛ የጨረታ ዋጋ
ከፍለው የሚመደብላቸው ይሆናል፡፡

2. የአካባቢ ልማት ፕላኑ በሚፈቅደው መሰረት ለማልማት አቅም ከሌላቸው ቅድሚየ የድርጅት ቤት በኪራይ
እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ይህ ማድረግ በማይቻልበት ሁኔታ ለመልሶ ልማት ከተከለለው አካባቢ ውጭ

8
በጋራ ለማልማት ተደራጅተው ከቀርቡ በቦታ ሽንሻኖ እስታንዳርድ መሰረት በሊዝ መነሻ ዋጋ/ኪራይ
በምደባ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
3. ከላይ በዚህ አንቀጽ ተ.ቁጥር 1 ከፊደል ተራ ሀ-ረ እና ተ.ቁጥር 2 የተጠቀሰው ቢኖርም ተነሽዎቹ በስማቸው
ወይም በትዳር ጓደኛቸው ስም የንግድ ቤት ወይም የንግድ ቤት መስሪያ ቦታ በከተማዉ ውስጥ ያላቸው
ከሆኑ የዚህ መብት ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

9. የከተማ መልሶ ማልማት/ማደስ ትግበራ አደረጃጀት

1. መልሶ ማልማት /ማደስ በሚከናወንባቸው ከተሞች የመልሶ ማልማት /ማደስ ባለድርሻ አካላትን
ያካተተ ከአምስት እስከ ሰባት ያሉት አብይ ኮሚቴ ይኖረዋል፣ይህም በከተማው ከንቲባ የሚመራ
ይሆናል፡፡

2. ለመልሶ ማልማት/ማደስ ስራው እራሱን የቻለ የበጀትና የግብዓት ግዥ ቡድን እንዳስፈላጊነቱ


ሊኖረው ይችላል፣

3. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የመልሶ ማልማት ስራው


እንደከተሞች አቅምና ፍላጎት የፕሮጀክት ጽ/ቤት በማቋቋም ሊመራ ይችላል፣

4. በከተማ አስተዳደሮች በቴክኒክ ዘርፍ በም/ስራ አስኪያጅ የሚመራ ወይም በማ/ቤት ከተሞች
በስራ አስኪያጅ የሚመራ የቴክኒክ ቡድን ይቋቋማል፡፡ይህም በዋናነት የከተማው መልሶ
ማልማትና ማደስ ባለሙያዎችን እና የከተማ ፕላነርን ያካተተ ይሆናል፣

5. የመልሶ ማልማት ትግበራው በም/ ሥራ አስኪያጅ የሚመራ የቴክኒክ ቡድን ይቋቋማል፣

6. በከተሞች የሚከናወኑ የመልሶ ማልማትና ማደስን ስራ ለመከታተልና ለመደገፍ በክልል ደረጃ


በኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ የሚመራ ቴክኒካል ቡድን ይቋቋማል፣

7. የከተማ መልሶ ማልማት ትግበራ አደረጃጀትና የባለድርሻ አካላት ተግባርና ሃላፊነት በመልሶ ማልማት
የትግበራ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተለይቶ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡

8. በመልሶ ማልማት ትግበራ ሂደት ከእቅድ ዝግጅት እስከ አፈፃፀም ግምገማ ድረስ የህዝብ ተሳትፎ
እንዲረጋገጥ ይደረጋል፣

ክፍል ሶስት
የከተማ ልማት ፕሮግራም ተፈጻሚነትን ስለማረጋገጥ

9
3. በከተማ መልሶ ማልማት/ማደስ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዋናነት የሚከተሉት ተግባራት
የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

1. በመልሶ ማልማቱ አካባቢ ላይ የሚገኙ እና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በመልሶ ማልማቱ ሥራ


በሚኖረዉ የልማት እንቅስቃሴእንዲሰማሩ በአነስተኛ እና ጥቃቅን አደረጃጀት፤ የስልጠናና የብድር
ድጋፍ ማመቻቸት፤

2. በመልሶ ማልማቱ ክልል ላይ የሚገኙ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ እና በህጋዊ አግባብ መኖሪያ ወይም
የድርጅት ቤት ከመንግስት አካላት ተከራይተዉ የሚኖሩ ትክ የኪራይ ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣

3. የቤት ልማት ፕሮግራም በሚከናወንባቸው ከተሞች የኮንዶሚኒየም ቤት በቅድሚያ ግዥ እንዲያገኙ


ማድረግ፤

4. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 እና 3 ማስተናገድ ካልተቻለ ትክ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በሊዝ ደንቡ
እና መመሪያው በተገለጸው መሰረት እንዲያገኙ ማድረግ፤

1. የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራምን ስለማረጋገጥ


የቤቶች ልማት ፕሮግራም በሚከናወንባቸዉ ከተሞች የመልሶ ማልማት ስራ የተቀናጀ እና የተሳካ
እንዲሆን በሚከተሉት ጉደዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ይሆናል፡፡

1. ከተማ አስተዳደሩ በአካባቢ ልማት ፕላን ላይ ለመኖሪያ አገልግሎት የተመደበ ቦታን የቤቶች ልማት
ፖሊሲና አስትራቴጂን መሰረት በማድረግ ለጋራ ቤቶች መገንቢያ እንዲውል በኮንስትራክሽንና
ቤቶች ልማት ኤጀንሲ በኩል እንዲገነባ ማድረግ ይችላል፡፡

2. በመልሶ ማልማት አካባቢ ላይ ከሚገነባዉ የጋራ ቤቶች ውስጥ እስከ 30 በመቶ የሚሆነዉ በመልሶ
ማልማት አግባብ ተነሽ ለሚሆኑ አካላት በተለይም ለሴቶች እንዲመደብ ይደረጋል፤

3. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም ከተጠቃሚዎች ፍላጎትና አቅም ማነስ ጋር ተያይዞ
በጋራ ቤቶች የግንባታ ፕሮግራም በመጠባበቂያ የሚያዙ ቤቶችን ለተነሽዎች ማስተላለፍ
በማይቻልበት ሁኔታ ቤቱ በጨረታ አግባብ ለሌሎች ነዋሪዎች የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

2. የነዋሪዎችን ተሳትፎ ስለማረጋገጥ


በመልሶ ማልማት ወይም ማደስ የሚለሙ አካባቢዎች ነዋሪዎችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚከተሉትን
ተግባራት ማከናወን ይገባል፡-

1. ነዋሪዎችን በአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት ጥናቶችና የግንዛቤ ፈጠራ ውይይቶች በስፋት እንዲሳተፉ ማድረግ፤

10
2. በመልሶ ማልማት ወይም ማደስ ትግበራ ሂደት ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም ግምገማ ድረስ
በተወካዮቻቸው አማካኝነት እንዲሳተፉ ማድረግ፣

3. የተነሽዎች የካሳና ትክ ባለቤትነት ማስረጃ እንዲሁም በይዞታ ልኬታ መረጃዎች አሰባሰብ ላይ በተወካዮቻቸው
አማካኝት እንዲሳተፉ ማድረግ፤

4. ካሳና ምትክ ከመሰጠቱ በፊት የካሳና ምትክ መረጃ የልማት ተነሺዎች ያላቸውን አስተያየት ጥቆማ
እንዲሁም ቅሬታ እንዲያቀርቡ ለሕዝቡ አመቺና ተደራሽ በሆነ መንገድ ለ 5 የስራ ቀናት ለሕዝብ
ይፋ ይደረጋል፣

5. የምትክ ቦታና ቤት ለሕጋዊና የሚመለከታቸው የልማት ተነሺዎች በዕጣ የሚሰጥ ሆኖ የዕጣ አወጣጡ
በነዋሪ ተወካዮች እንዲመራ በማድረግ ተሳትፎአቸው እንዲጠናከር ይደረጋል፣
ክፍል አራት

በመልሶ ማልማት ትግበራ በይዞታቸው ላይ እንዲያለሙ ስለሚፈቀድላቸው አካላት

3. በመንግስት ቤት ህጋዊ ተከራዮች በተመለከተ


12.1. የመኖሪያ ቤት ተከራዮች
የመንግስት የመኖሪያ ቤት ህጋዊ ተከራዮች የመከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ በሊዝ
መነሻ ዋጋ የሚስተናገዱ ይሆናል፣

ሀ. በአካባቢ ልማት ፕላኑ እስታንዳርድ መሰረት የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት


በጋራ ተደራጅተውና እውቅና ይዘው ሲቀርቡ፣

ለ. የማህበሩ አባላት ሙሉ በሙሉ ህጋዊ ተከራዮች ሲሆኑና በሚኖሩበት ከተማ በስማቸዉ ወይም
በትዳር አጋራቸዉ ምንም ዓይነት የመኖሪያ ቤት የሌላቸዉ መሆኑ በከተማው ሲረጋገጥ፣

ሐ. የሚፈለገዉን ልማት ለመገንባት አቅሙ ያላቸው ለመሆኑ የግንባታውን ወጭ 30-35 ፐርሰንት በባንክ
ዝግ ሂሳብ ማስያዝ የሚችሉ፣

መ. ከላይ ከሀ-ሐ በተገለጸው መሰረት ጥያቄ ካልቀረበ በሊዝ አዋጁ እንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 3 እና
በሊዝ ደንቡ አንቀጽ 24 ንኡስ አንቀጽ 5 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

13. የንግድ ቤት ተከራዮች

የንግድ ቤት ህጋዊ ተከራዮች የመከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ የሚስተናገዱ ይሆናል፣

11
ሀ. በሽርክና ወይም በአክሲዮን ተደራጅተው እውቅና ያገኙ ሲሆን፣

ለ. በአካባቢ ልማት ፕላኑ እስታንዳርድ መሰረት ለመገንባት ፈቃደኛ ሆነው ተቀባይነት ያለዉ
የግንባታ ፕሮፖዛል ሲያቀርቡ፣

ሐ. ለማልማት በሚፈልጉት በያዙት ቦታ ላይ የሚገኙ እስከ 50 በመቶ የሚሆኑትን ተነሺዎች ያካተተ


ሲሆን፣

መ. የቦታ መጠኑ በሊዝ ደንቡ አንቀጽ 24 ንኡስ አንቀጽ 6 እና 7 መሰረት የሚወሰን ይሆናል፣

ሠ. በሊዝ ደንቡና መመሪያው ላይ በተቀመጠው የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ


መሰረት ለመፈጸም ግዴታ የገቡ ሲሆን፣

4. ለመልሶ ልማት በተለየ አካባቢ የግል ይዞታቸዉን ለሚያለሙ ግለሰቦችን በተመለከተ፣


ለመልሶ ማልማት በተለየ አካባቢ የግል ይዞታ ያላቸው ነዋሪዎች የመከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው
ሲቀርቡ የሚስተናገዱ ይሆናል፣

1. በአካባቢ ልማት ፕላኑ እስታንዳርድ መሰረት ለመገንባት ፈቃደኛ ሆነው ተቀባይነት


ያለዉ የግንባታ ፕሮፖዛል ሲያቀርቡ፣

2. በሊዝ ደንቡና መመሪያው ላይ በተቀመጠው የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ


የጊዜ ገደብ መሰረት ለመፈጸም ግዴታ የገቡ ሲሆን፣

3. የይዞታ ቦታ መጠናቸው በፕላኑ ላይ የተቀመጠውን የግንባታ አይነትና ደረጃ የሚያስገነባ ሆኖ ሲገኝ


ወይም ለተጨማሪው ቦታ በአካባቢው ከፍተኛ የጨራታ ዋጋ ለመክፈልና ይዞታው ወደ ሊዝ
ለማጠቃለል ፈቃደኛ ሲሆኑ፣

5. በአካባቢ ልማት ፕላኑ ሽንሻኖ መሰረት እራሳቸውን ችለው የማይለሙ ኩታገጠም የሆኑ
የግል ይዞታዎችን መልሶ ማልማት በተመለከተ
በመልሶ ልማት አካባቢ በፕላን ሽንሻኖ መሰረት እራሳቸውን ችለው የማይለሙ ኩታ ገጠም የግል
ይዞታቸውን በጣምራ ወይም በጋራ ለማልማት የመከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ
የሚስተናገዱ ይሆናል፣

1. በአካባቢ ልማት ፕላኑ መሰረት ይዞታቸውን ተደራጅተው በጋራ ለማልማት የእውቅና ሰርተፊኬት
ይዘው ሲቀርቡ ወይም በአንድ የግንባታ ዲዛይን ለመገንባት ስምምነታቸውን በማመልከቻ
ሲያቀርቡ፣

12
2. በጋራ የግንባታ ዲዛይን ይዞታቸውን ለማልማት ተስማምተው ጥያቄ በሚያቀርቡበት ሁኔታ ግንባታው
ሲጠናቀቅ የሚኖራቸውን የባለቤትነት ድርሻ በጽሁፍና በፌርማቸው አረጋግጠው ሲያቀርቡ፣

3. በሊዝ ደንቡና መመሪያው ላይ በተቀመጠው የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ መሰረት
ለመፈጸም ግዴታ የገቡ ሲሆን፣

6. በመልሶ ማልማት አካባቢ ይዞታቸውን ለሚያለሙ መንግስታዊ ተቋማት በተመለከተ፣


ለመልሶ ማልማት በተለየ አካባቢ ይዞታ ያላቸው ቢሮዎችና የልማት ድርጅቶች የመከተሉትን
መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ የሚስተናገዱ ይሆናል፣

1. በአካባቢ ልማት ፕላኑ መሰረት በፕላን ምደባው ስታንዳርዱን የጠበቀ ግንባታ ለማከናወን በተቋሙ
የበላይ ሃላፊ ፍላጎቱ ያላቸው መሆኑንና በጀት ስለመያዙ የስምምነታቸውን በደብዳቤ
ሲያሳውቁ፤

2. ከነባር ይዞታቸው ውጪ ተጨማሪ ቦታ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከይዞታው ላይ


ተነሺዎች የተከፈለውን የንብረት ካሳ በቅድሚያ ለከተማው ገቢ ሲያደርጉ

3. በሊዝ ደንቡና መመሪያው ላይ በተቀመጠው የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ


መሰረት ለመፈጸም ግዴታ የገቡ ሲሆን፣

ክፍል አምስት
መልሶ በሚለማ ቦታ ላይ የሚኖር የህግ ተፈጻሚነት
7. በመልሶ ማልማት ትግበራ ሂደት የህግ ተፈጻሚነትን በተመለከተ
1. በይዞታቸው ላይ እንዲያለሙ ለሚፈቀድላቸው አካላት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 12፣ 13፣ 14 እና 15
ላይ በተቀመጠው መሰርት ከተማው የመልሶ ልማት ትግበራ ስራውን ለህዝብ ይፋ ካደረገበት ጊዜ
ጀምሮ በ 3 ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠበቅባቸውን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፣

2. የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች በወቅቱ አሟልተው ያላቀረቡ ከሆነ ከተማው እንደ አስፈላጊነቱ ካሳና
ትክ ቦታ በመስጠት ቦታውን ነጻ አድርጎ ለተፈለገው ልማት የሚያውለው ይሆናል፣

3. ይዞታቸውን ለሚያለሙ አካላት የውል ስምምነት የሚሰጠው በቦታው ላይ ያለውን ንብረት አንስተው
ቦታውን ነጻ ሲያደርጉ ይሆናል፣

13
4. በይዞታቸው ላይ እንዲያለሙ ለሚፈቀድላቸው አካላት በሊዝ ደንቡና መመሪያው ላይ በተቀመጠው
የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ ተፈጻሚ ይሆናል፣ በውላቸው መሰረት ግዴታቸውን
የማይወጡ አካላት ላይ በደንቡ አንቀጽ 48 እና 50 መሰረት ተፈጻሚ የሆናል፡፡

ክፍል ስድስት
የመልሶ ማልማት የትግበራ ዕቅድ ዝግጅትና የክትትል አግባብ
8. የመልሶ ማልማት/ከተማ ማደስ ፕሮግራም ስለመንደፍ፣

የከተማዉ አስተዳደር የመልሶ ማልማት/ ከተማ ማደስ ስራዉን የሚመራበት የረጅም ጊዜ፣ የመካከለኛ እና
የአጭር ጊዜ የመልሶ ማልማት/ከተማ ማደስ ፕሮግራም በመንደፍ ልማቱን የሚመራ ይሆናል፡፡ በዚህም
መሰረት፡-

1. የረጅም ጊዜ የመልሶ ማልማት/ ከተማ ማደስ ፕሮግራም ከከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ፖሊሲ
እንዲሁም ከከተማዉ አስተዳደር የልማት ግቦች አንጻር የተቃኘ እና የ 10 ዓመት የጊዜ ማዕቀፍ የሚኖረዉ
ሆኖ ሰነዱ በከተማዉ አስተዳደር ምክር ቤት የሚጸድቅ ይሆናል፡፡

2. የመካከለኛ ጊዜ የመልሶ ማልማት/ከተማ ማደስ ፕሮግራም በረጅም ጊዜ ፕሮግራሙ የአፈጻጸም ማዕቀፍ


ዉስጥ የሚካተት፣ በመካከለኛ ጊዜ ለማልማት ትኩረት የተደረገባቸዉን አካባቢዎች በዝርዝር በመለየት
የአፈጻጸም አቅጣጫዉን ጭምር የሚያካትት እና ከሶስት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የጊዜ ማዕቀፍ
የሚኖረዉ ሆኖ ሰነዱ በከተማዉ አስተዳደር ምክር ቤት የሚጸድቅ ይሆናል፡፡

3. የአጭር ጊዜ የመልሶ ማልማት / ከተማ ማደስ ፕሮግራም ከመካከለኛዉ ጊዜ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም
ማዕቀፍ ዉስጥ የተካተተ ሆኖ የሚለማዉን አካባቢ በፕሮጀክት እና በንኡስ ፕሮጀክት በመለየት ዝርዝር
ተግባራት ግቦችን፣ በጀትን እና የአፈጻጸም አቅጣጫ የሚቀመጥለት ይሆናል፡፡ የአጭር ጊዜ የመልሶ
ማልማት ፕሮግራም የጊዜ ማእቀፍ ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት የሚይዝ ሆኖ ሰነዱ በከተማዉ
አስተዳደር ካቢኔ የሚጸድቅ ይሆናል፡፡

9. የመልሶ ማልማት /ከተማ ማደስ ትግበራ ክትትል አግባብ፣

የከተማዉ አስተዳደር የመልሶ ማልማት /ከተማ ማደስ ትገግበራ በአግባቡ እየተፈጸመ ስለመሆኑ በሚከተለው
አግባበብ ክትትል መደረግ ይኖርበታል፡፡

1. የመልሶ ማልማት /ከተማ ማደስ ትግበራው ከከተማው የእድገት ፕላንና የአካባቢ ልማት ፕላን ጋር
በማይጣረስ መልኩ እንዲዘጋጅና ልማቱ በፕላን እንዲመራ ይደረጋል፣

14
2. የሚዘጋጀው አካባቢ ልማት ፕላን ተገቢውን ጥራት እንዲጠብቅ የክትትል ስራዉን በራሱ በከተማው
አደረጃጀት ወይም ለመንግስታዊ ተቋም በዉክልና በመስጠት ወይም

3. ለግል አማካሪ ተቋማት ክትትሉን በዉል በመስጠት ወይም

4. በመንግስታዊ እና በግል አማካሪ ተቋማት በጣምራ ክትትሉን በማድረግ ተገቢዉ ስለመፈጸሙ


ያረጋግጣል፡፡

ክፍል ሰባት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
10. የመተባበር ግዴታ እና የወንጀል ሃላፊነት

1. ማንኛውም ሰው ይህን መመሪያ ለማስፈጸም ለሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ አግባብነት ያለው ትብብር


እንዲያደርግ ሲጠየቅ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

2. ይህን መመሪያ የጣሰ ወይም አፈጻጸሙን ያሰናከለ ማንኛውም ሰው በአዋጁ አንቀጽ 35 ወይም አግባብ
ባለው የወንጀል ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

11. የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ህጎች

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሌላ መመሪያ ወይም የተለመደ አሰራር በዚህ መመሪያ ውስጥ
በተሸፈኑት ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

12. መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በቢሮ ከጸደቀበት ከግንቦት 15/2 ዐዐ 6 ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

15
አባሪ 1

½ »wG
½ ከተማ FS| @G|ና GŒýËF«| ዋና የስራ ሂደት
የካሣና ምትክ መረጃ መሰብሰቢያ ፎርማት
I. ጠቅላላ መግለጫ ፡-
1. የተነሽው ሙሉ ስም ከነአያት ------------------------------------------------------------------------
አድራሻ -------------------------------- ከተማ ------------------------ ቀበሌ -----------------------
የቤት ቁጥር -------------------------- ብሎክ ------------------------ ፖርስልቁጥር ----------------

2. የይዞታው የባለቤትነት ሁኔታ ፡-


የግል መያድ
የቀበሌ የህዝባዊ ድርጅት
የቤቶች ልማት ድርጅት የሃይማኖት ተቋም ሌላ -----------------------

3. ይዞታው የሚሰጠው አገልግሎት


ለድርጅት የግጦሽ ቦታ
ለመኖሪያና ለድርጅት የተክል ቦታ
የእርሻ ቦታ ጊዜያዊ መጠቀሚያ ቦታ
የጓሮ አትክልት ሌላ -------------------------------
ለድርጅት

4. ስለ ይዞታው የቀረበ ሰነድ


የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ደረሰኝ
ደብተር የመሰረተ ልማት አቅርቦት ደረሰኝ/ቢል/
የሃይለስላሴ ካርታ የቦታ ጊዜያው መጠቀሚያ ውል
የግብር ካርኒ ሌላ ----------------------------------------

5. ግንባታው የጸደቀ ፕላን


አለው የለውም

6. ግንባታው የተገነባው ጸድቆ በተሰጠው ፕላን


ነው አይደለም

16
7. ከተሰጠው የግንባታ ዲዛይን ውጭ የተገነባ ግንባታ የለውጥ መጠን
ከፍተኛ መካከለኛ አነስተኛ
አባሪ 2

8. ከዲዛይን ውጭ የተገነባው ግንባታ የቦታ መጠን ---------------- ካ.ሜ

9. ለልማት ከተፈለገው ቦታ ላይ የሰፈረው ንብረት ዓይነት


ቤት የግጦሽ መሬት
አጥር የቋሚ ተክል መሬት
ተነቅሎ የሚተከል የጓሮ አትክልት መሬት
የእርሻ መሬት

10. ለልማት የተፈለገው ንብረት የሚነሳበት አግባብ


ሙሉ በሙሉ
በከፊል

11. ለልማት የተፈለገው የመሬት ይዞታ መጠን


በካ.ሜትር --------------------- በሄ/ር -----------------------

12. ይዞታው የተፈለገበት የልማት ዓይነት ወይም ፕሮጀክት መጠሪያ


-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
---------------------------------------------------------------------------------------------------------------
II. የይዞታው የባለመብትነት ማረጋገጫ

1. ይዞታው ከይገባኛል ባይ

ነፃ ነው ነፃ አይደለም
2. ከይገባኛል ባይ ነፃ ካልሆነ ምክንያት
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------
III. የካሣና ምትክ ባለመብትነት አግባብ ፡-
1. የካሣ ባለመብት
ነው አይደለም
2. የምትክ ቦታ ባለመብት
ነው አይደለም
3. የምትክ ቤት ባለመብት
ነው አይደለም
IV. የካሣና ምትክ መጠንና ስታንዳር

17
1. የካሣ ክፍያ መጠን በብር -------------------
አባሪ 3

2. የምትክ ቦታ መጠን --------------------------


ለመኖሪያ በካ/ሜትር -------------------------
ለድርጅት በካ/ሜትር ------------------------

3. የምትክ ቤት መጠንና ዓይነት


የኮንዶሚኒየም የቀበሌ ቤት

የካሣና ምትክ መረጃውን የሰበሰበው ባለሙያ

ስም-------------------------------------------- ፊርማ ---------------------------------


ቀን --------------------------------------------
የስራ ሂደቱ ማህተም ----------------------

18
19

You might also like