Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

Marota cinematography and software academy

የፊልም ድርሰት አፃፃፍ ፠

#የፊልም ድርሰት አፃፃፍ መሠረታውያን!

#Basics of Screenwriting!

★★★

ለፊልም/ሲኒማ የሚሆን የፊልም ድርሰትን/ስክሪፕትን እንዴት መፃፍ እንችላለን?

የፊልም ድርሰት አፃፃፍን ማወቅ በፊልም ስራ ውስጥ አስፈላጊና እና የፊልም ስራን ለመራዳት የሚያስችለን ወሳኙ
እውቀት ነው። ከዚህ አንፃርም በአለም አቀፍ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ በርካታ አይነት የፊልም አፃፃፍ
አስተምህሮቶች፣ መንገዶችና ቴክኒኮች ይኖራሉ ነገርግን የሁሉም ዋና ግብ የተለያዩ ታሪኮችን/ ሁነቶችን በተለያየና
ዘርፈ ብዙ በሆነ ዘዴ ነገር ግን ለሲኒማነት/ፊልምነት እንዲበቃ አረጎ እንዴት መፃፍ/መተረክ ይቻላል የሚለውን
ማስተማር ነው።

ታዲያ እኛም በርካቶቻችሁ ፊልም ለመፃፍ የተዘጋጃችሁ፣ እንዴት መፃፍ እንደለባችሁ ባለመረዳት ሀሳባችሁን
በአይምሯችሁ ይዛችሁ ለያቆችሁ ወይንም በተከታታይ የምንለጥፋቸውን የፊልም ስክሪፕት አፃፃፍ ተረድታችሁ
ለምትፅፉ ሁሉ የተለያዩ የፊልም ድርሰት አፃፃፍ መንገዶችን በተለያዩ ጊዜ እናቀርብላችሇለን እናተ ደግሞ ተከታተሉን፣
አንንቡ በተግባር ተርጉሙና ጠንካራ ጥበባዊ እና ማህበራዊ ዋጋ ያላቸው ድርሰቶችን አምርቱ፣ ለሲኒማውም
አቅርቡ!!

የፊልም ድርሰት/ስክሪፕት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት!/Understand What a Script is!

የፊልም ድርሰት/ስክሪፕት/ስክሪንፕሌይ ምንድነው?

የፊልም ድርሰት/ስክሪፕት ማለት ለአንድ ፊልም ወይም ቲቪ ድራማ ሊቀርብ የሚገባው ታሪክ መናገርና ማሳየት
የሚችል ድምፅ፣ ምስል፣የተለያዩ ባህርያት፣ ንግግር እና ሌሎች ግብዓቶችን ያካተተ በስርአት የተፃፈ ድርሰት/የፈጠራ
ፅሁፍ ማለት ነው።

ስክሪፕት መፃፍ ማለትስ ምን ማለት ነው?

ስክሪፕት/ስክሪን ፕሌይ መፃፍ ማለት ለሲኒማ/ለፊልም ሚድየም የሚሆን ታሪክ መፃፍ ማለት ነው።

ስክሪፕት መፃፍ እንቅስቃሴን፣ ድርጊትን፣ ገለፃዎችን፣ እና የገፀባህርያትን ስሜት ገለፃዎችን አጠቃሎ የያዘ የፊልም
ድርሰት አፃፃፍ ፎርማትን ተከትሎ የሚፃፍ ነው። የፊልም አፃፃፍ ከልብወለድ፣ ቴያትር ትረካ ና መሰል ድርሰቶች አፃፃፍ
በመሰረቱ የተለየ ነው። ስለዚህ ድርሰታችን ለሲኒማ/ፊልምነት ከሆነ የግድ የፊልም ታሪክ አፃፃፍን ሊከተል ግድ
ይለናል።

1|P ag e
Marota cinematography and software academy
የስክሪንፕሌይ አፃፃፍ በዋናነት ምስላዊ/ምስል ከሳች ሆኖ መፃፍ ይኖርበታል። ምክንያቱም ስክሪፕት ፀሀፊዎች
ወይንም ስክሪን ፀሀፊያን የሚፅፍት ለሲኒማ ፊልምነት፣ ለቴሌቪዥን ድራማና ተከታታይነት ፣ለቪድዮ ጌም አሁን
አሁን ደግሞ ለኢንተርኔት ድህረገፆች ሙቪነት እና ተከታታይነት ስለሆነ ነው።

እንግዲህ ስክሪፕት ፀሀፊያን ደግሞ በዋናነት ለተለያዩ ካምፓኒዎች እና ፕሮዲውሰሮች ተቀጥረው ሲሰሩ በሌላ በኩል
በራሳቸው ስክረንፕሌዮችን በማዘጋጀት በረሳቸው ወይም በወኪሎቻቸው አማካይነት ለሽያጭ ያቀርባሉ ማለት ነው።

፠ የቅድመ ስክሪፕት ሂደቶች ፠

✔️ሃሳብን/ዘውግን ማግኘት

✔️ጥናት

✔️ያገኙትን ሃሳብ ማጣጣም

✔️ ሎግላይን መፍጠር/ማዘጋጀት

✔️የስክሪፕቱን ትሪትመንት መፃፍ

✔️ የስክሪፕቱን አውትላይን መፃፍ

✔️እንዴት የመጀመሪያውን ረቂቅ መፃፍ ይቻላል

፠ ስክሪፕትን በምንፅፍበት ወቅት ፠

★የስክሪፕት መፃፊያ ድህረ ገፅ

★እንዴት ገቢርን/አክትን መፃፍ ይቻላል

★እንዴት ትዕይንትን/ሲንን መፃፍ ይቻላል

★እንዴት ቢት/አነስተኛ ድርጊትና ሁነቶችን መፃፍ ይቻላል

★እንዴት ገፀባህሪያንን መፃፍ ይቻላል

★እንዴት ንግግርን/ዲያሎግን መፃፍ ይቻላል

★እንዴት ከምስል ጋር መፃፍ ይቻላል

★ከስክሪፕት አውትላይን ውጪ በሚሆን ጊዜ

★እንዴት ስክሪፕትን/ድጋሜ መፃፍ ይቻላል

2|P ag e
Marota cinematography and software academy
★★★

✔️ገንቢ አስተያየት ከየት እናገኛለን

✔️ለምንድነው በመሃል እረፍት መውሰድ ያለብን

✔️በሠንጠረዥ ውስጥ የተቀመጡ ይዘቶች

✔️ከመፃፋችሁ በፊት

✔️የመጀመሪያው ረቂቆች

✔️ነፃ የስክሪንፕሌይ ማሳያዎች

እንግዲህ እነዚህን ዝርዝር ሂደቶች ቀስ በቀስ በዝርዝር የምናያቸው ይሆናል እስከፍፃሜው አብራችሁን ሁኑ!

የስክሪፕት አፃፃፍ ቅድመ ዝግጅት አለ ወይ ካላችሁ አዎ በሚገባ አለ፤ ሊያውም አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ነው
መልሱ! እንግዲህ ብዙ ፀሀፊያን ከሚሰሯቸው የመጀመሪያ ስህተቶቸ መካከል ስክሪፕት ለመፃፍ በፈለጉ ጊዜ
ያለምንም ዝግጅት ዘለው ወደመፃፉ መግባታቸው ነው። ይህ ማለት እንግዲህ ወዴት እንደምንሄድ ሳናውቅ ጉዞ
እንደመጀመር ማለት ነው። ታዲያ ይህ ጉዞ በኃላ ቆይቶ ነው ዋጋ የሚያስከፍለው ይህውም በሞራል የተጀመረውን
ስክሪፕት/ ድርሰት ሃሳብ አባክኖ መተው ወይንም ድርሰቱ በየጊዜው ከሚገባበት ቅርቃር ለማውጣት ወይንም እሱን
ለማስተካከል ወደኃላና ወደፊት እየተመላለሱ በሳምንታት ላቅ ሲልም በወራት የሚቆጠሩ አድካሚ ጊዜያትን
መፍጀት!

በስክሪፕት ፅሁፍ ሂደት ውስጥ የቅድመ ፅሁፍ ዝግጅት ሂደት በጣም አስፈላጊው ክፍል ነው። ምክንያቱም
ስለምትፅፉት ድርሰት አንድ አይነት መዋቅር/አፅመታሪክ ማወቅ በኃላ ከሚገጥማችሁ የፈጠራ
መድረቅ/መንገጫገጭ ይታደጋችኃል። እርግጠኛ ሁኑ ከመጀመራችሁ በፊት የታሪካችሁን አንድ አይነት አነስተኛ የጉዞ
ካርታ ማዘጋጀቱ በጣም ይጠቅማችኃል፣ ጉዟችሁንም ቀለል ያረግላችኃል።

ከሞላ ጎደል ሁሉም ስክሪንፕሌይ ፀሐፊያን በሚባል ደረጃ የቅድመ ስክሪፕት ዝግጅት በተለያየ መጠን እና ዝግጀት
መሰረት ያሰናዳሉ፤ አንዳንዶቹ ፀሐፊያን ከጥናት ይጀምራሉ ሌሎች ደግሞ በአይምሯቸው ለረዥም ጊዜ
በማውጠንጠን ሊሆን ይችላል ብቻ መታወቅ ያለበት ዋናው ነጥብ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ጊዜ ሰጥተው
ይዘጋጁበታል። ታዲያ እነዚህ የቅድመ ስክሪፕት ዝግጅት ሂደቶች ምን ይመስላሉ??

3|P ag e

You might also like