Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 105

የስራ ላይ ደህንነትና የድንገተኛ አደጋ

ምላሽ

አዘጋጅ፡- መርዕድ በሻህ


 0968573578
የስራ ላይ ደህንነት
 የስራ ላይ ደህንነት አሽከርካሪዎች ከማሽከርከር ተግባርና ከተሸከርካሪው ሁኔታ ጋር
በተያያዘ የሚያከናውኗቸው ድርጊቶችና ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋ በመረዳት
የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ ነው፡፡

በአደጋ ግዜ የሚከሰቱ የጉዳት አይነቶችና መገለጫዎች


1. በተሸከርካሪ ሳቢያ የሚመጡ የአደጋ ውጤቶች
• የሞት አደጋ
• የአካል ጉዳት
• የንብረት ውድመት
2. ድንገተኛ አደጋ
ቃጠሎ
ሀ. ደረቅ ቃጠሎ፡- በእሳትና በጋለ እቃ የሚደርስ የቃጠሎ አይነት ነው፡፡
ለ. እርጥብ ቃጠሎ፡- በፈላ ውሀና ዘይት የሚደርስ የቃጠሎ አይነት ነው፡፡
ሐ. የመርዛ ቃጠሎ፡-በአሲድ ወይም በሚያቃጥል ጨው የሚደርስ የቃጠሎ አይነት ነው፡፡
መ. የኬሚካል ቃጠሎ፡- በኬሚካል የሚደርስ የቃጠሎ አይነት ነው፡፡
3. ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች
• እራስን መሳት
• ትንታ
• የሰውነት ስብራት
በማሽከርከር ወቅት የአደጋ መንስኤዎች
• የተሸከርካሪ ብልሽት
• የእሳት አደጋ
• ከተሳፋሪና ከሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች ጋር የሚፈጠሩ አለመግባባቶች
• የመጋጨት፡የመገልበጥና ከተሸከርካሪ የመውደቅ
የአደጋ ውጤቶችና የጉዳት አይነቶች
• የሞት አደጋ
• አካል ጉዳተኛነት
• የጤና መታወክ
• አከባቢያዊ ጉዳት
• ማህበራዊ እና ኢኮኖሞያዊ ጉዳቶች
የግል የደህንነት መጠበቂያዎች
• የእጅ ጓንት፡- በእጅ መዳፍና በጣቶች አከባቢ ሊደርስ የሚችል ጉዳትን ይከላከላል፡፡
• የደህንነት ጫማ፡- አሽከርካሪዎች በእግራቸው ላይ አደጋ እንዳይደርስ ይከላከላል፡፡
• ካፖርት፡-ዝናብና ቅዝቃዜ ባለበት የአየር ሁኔታ የሚለበስ ሆኖ ልብሳቸው በቆሻሻ እንዳይበላሽ
ይከላከላል፡፡
• አንጸባራቂ ልብስ፡-አሽከርካሪዎችና የመንገድ ተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲለዩ ያደርጋል፡፡
• የጭንቅላት መከላከያ፡-በአብዛኛው ለሞተር ሳይክልና ለልዩ ተንቀሳቃሽ መሳሪያ አሽከርካሪዎች
ሲሆን በግጭት ወቅት ጭንቃላት አከባቢ አደጋ እንዳይደርስ ይከላከላል፡፡
• ጭንብል፡-ከመርዛማ ጭስ፤ፊትን ከእሳት ከመለብለብና መተንፈሻ ክፍሎችን ከተለያዩ ተላላፊ
በሽታዎች ይከላከላል፡፡
1.አደጋ የሚያደርሰው የጉዳት ዓይነት ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ፈጣን የሞት አደጋ ለ. አካል ጉዳት ሐ. ሀ እና ለ መ. መልሱ የለም
2. የሰዎች ሞት በአደጋ ምክንያት ብቻ የሚከሰት የጉዳት ዓይነት ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
3.በድንገተኛ አደጋ ወቅት ቅድሚያ እርዳታ ሊያገኝ የሚገባው የቱ ነው?
ሀ. ንብረት ለ. አካባቢ ሐ. ሰው መ. መልሱ የለም
4.ዋነኛ የአደጋ ውጤት መግለጫ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለ. ማህበራዊ ጉዳት ሐ. ስነልቦናዊ ጉዳት መ. ሁሉም
5. በትራፊክ አደጋ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚሰጥባቸው ንብረቶች ይወድማሉ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
6. የመንገድ አደጋ የቤተሰብ ኃላፊዎችንና ሌሎችን በሞት የመቅጠፍ አስከፊ ገጽታ አለው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
7______________ የራስ ቅልን ከአደጋ ይከላከላል
ሀ. ጭንቅላት መከላከያ /ሄልሜት/ ለ. ካፖርት ሐ.ጓንት መ. ጭምብል
8. መንገድ ተጠቃሚዎችን በቀላሉ ለመለየት የሚጠቅም የቱ ነው?
ሀ. አንፀባራቂ ልብስ ለ. ጓንት ሐ. ካፖርት መ. ሔልሜት
9.በአደጋ ምክንያት የትኞቹ ችግሮች ይፈጠራሉ?
ሀ. የሞት አደጋዎች ለ. አካል ጉዳተኝነት ሐ. የአካባቢ ብክለት መ. ሁሉም
10.ከሚከተሉት ውስጥ የአደጋ መነሻ ምክንያት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. አለመግባባት ለ. የተሽከርካሪ ብልሽት ሐ. የእሳት አደጋ መነሳት መ. መልስ የለም
11. በማሽከርከር የሚደርስ ጉዳት በየትኛው ክፍል ላይ ይደርሳል?
ሀ. በመንገድ ተጠቃሚ ላይ ለ. በአሽከርካሪ ሐ. በተሳፋሪ ላይ መ. በሁሉም
12. የስራ ላይ ጥንቃቄና ደህንነት እውቀት የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥን ያጠቃልላል ሀ. እውነት
ለ. ሀሰት
13. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ በእጅ መዳፍ ላይና አካባቢው ሊደርሱ የሚችሉ መጠነኛ ጉዳቶች
ይከላከላሉ
ሀ. ጓንቶች ለ. ካፖርት ሐ. አንፀባራቂ ልብስ መ. ጭምብል
14. ሔልሜት አይንን ከመርዛማ ጭስ እና ከመለብለብ ለመከላከል ይረዳል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
15.አደጋ የመቆጣጠር ተግባር የስራ ላይ ደህንነትና ጥንቃቄ አካል ነው ሀ. እውነት ለ.ሀሰት
16. አንድ አሽከርካሪ ለአደጋ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን አስቀድሞ መለየት አያስፈልገውም
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
17. አንድ አሽከርካሪ የተሸከርካሪ ክፍሎችን ከጉዞ በፊትና በኃላ መፈተሸ ጊዜን እንደማባከን ይቆጠራል
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
18.ጤንነትን ማረጋገጥ በስራ ላይ ደህንነት ቅድመ ሁኔታ ውስጥ አይካተትም ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
19. ስለ ስራ ያለውን እውቀት ከግንዛቤ መክተት የስራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ ሒደት ነው፡፡ሀ. እውነት ለ.ሰት
20.አንድ አሽከርካሪ የስራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ እውቀት ባይኖረውም ብቃት ያለው አሽከርካሪ መባል
ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
21. የስራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ አደጋን ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን የመቀነስ እርምጃ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ንቁና ቀልጣፋ መሆን ለ. ስለ መደንገዱ ሁኔታ በቂ መረጃ መያዝ ሐ. ሀ ና ለ መ. መልሱ የለም
22. የስራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ የመጀመሪያ እርዳታ አሠጣጥ የሚጠቃለል ነው?
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
23. የስራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ ጠንቅቆ መረዳትና መተግበር ማለት ምን ማለት ነው
ሀ. የተሟላ ችሎታን ይጠይቃል ለ. የጥንቃቄ ደረጃን ያሳያል ሐ. ተነሳሽነትን ያሳያል መ. ሁሉም
24. የተሽከርካሪ መገልበጥ ሀ. የአደጋ አይነት ነው ለ. የጉዳት አይነት አይደለም ሐ. ሀ ና ለ
መ. መልሱ የለም
25. የአደጋ መንስኤ ሊሆን የሚችለው?
ሀ. ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሸከርከር ለ. በተከለከለ ቦታ ላይ ማቆም ሐ. የትራፊክ ሕግና ደንብን
መጣስን መ. ሁሉም መልስ ናቸው
26.. አደጋን መከላከል ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. የስራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ አላማ ነው ለ. የድንገተኛ ምላሽ አደጋ አላማ ነው ሐ. ሀ ና ለ
መ. መልሱ የለም
የትራፊክ አደጋ
የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች
1. በአሽከርካሪዎች ስህተት
2. በተሽከርካሪዎች ብልሽት
3. የአከባቢ ሁኔታዎች
1.በአሽከርካሪዎች ስህተት
• አልኮል: አደንዛዥ እጽና ከባድ መድሀኒት
• አልተኝነት/ግዴለሽነት
• የችሎታ ማነስ
• እድሜ
2.በተሽከርካሪዎች ብልሽት
• የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ብልሽት
• የመገናኛ መሳሪያዎች ብልሽት
• የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ብልሽት
• የዳሽ ቦርድ ጠቋሚ መሳሪያዎች ብልሽት
የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ብልሽት
• መሪ
• ፍሬን
• ነዳጅ መስጫ
• ፍሪሲዮን ከማርሽ ጋር
• ቁልፍ
የመገናኛ መሳሪያዎች ብልሽት
ፍሬቻ
የግራ ፍሬቻ
¾k˜ õ_‰
 ወደ ግራ ለመታጠፍ
 ወደ ቀኝ ለመታጠፍ
 ወደ ግራ ዞሮ ለመመለስ
 ለመቆም
 ከቆሙበት ለመነሳት
 ለማስቀደም
 ለመቅደም
 ከግራ ወደ ቀኝ ረድፍ ለመቀየር
 ከቀኝ ወደ ግራ ረድፍ ለመቀየር
የማስጠንቀቂያ መብራት/ሀዛርድ

 በመሪና በፍሬን የማንከላከለው አደጋ ሊፈጠር ሲል


 ተሽከርካሪዎች በድንገተኛ ብልሽት በተሽከርካሪ መሔጃ መንገድ ላይ ሲቆሙ
 በአስቸጋሪ የአየር ጸባይ
 የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች በከፍተኛ ፍጥነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ
የማቆሚያ/የፓርኪንግ/ መብራት
 የሚባሉት ከፊት ትንንሽ ነጣ ያሉና ከኃላ ደግሞ ቀይ ፈዘዝ ያሉ መብራቶች ሲሆኑ
ተሽከርካሪ በምሽት መንገድ ዳር ማቆም በተፈለገ ጊዜ የሚበራ ሲሆን ጥቅምቸውም ሌሎች
ተላላፊ አሽከርካሪዎች የቆመ ተሽከርካሪ መኖሩን አውቀው እንዲጠነቀቁ።

የፍሬን መብራት
 ይህ መብራት ከማቆሚያ ጋር አንድ ላይ ያለ ሲሆን አሽከርካሪው የፍሬን ፔዳል በረገጠ
ጊዜ በመብራት ከኃላ ለሚከተሉው አሽከርካሪ ፍጥነት መቀነሱንና እየቆመ መሆኑን
ለማጠንቀቅ የሚጠቅም መብራት ነው።
የኃላ ማርሽ መብራት
ይህ መብራት አሽከርካሪው የኃላ ማርሽ በሚያስገባበት ጊዜ የሚበራ ነጭ መብራት ነው
የሰሌዳ መብራት
በመንገድ ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለ ተሽከርካሪ ምን አይነት ፣ለምን አገልግሎት ጠዋለ
ተሽከርካሪ መሆኑን የመንገድ ተጠቃሚውና የትራፊክ ደህንነት ተቆጣጣሪ ፖሊሶች
ለማሳወቅ ሰሌዳው በጉልህ እንዲታይ የሚበራ መብራት ነው።
ጥሩምባ
አሽከርካሪዎች ሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎችን በድምጽ ለማስጠንቀቅ የሚጠቀሙበት ሲሆን
ጥሩምባ ማሰማት ክልክል በሆነበት ቦታና ተገቢ ባልሆነ ምክንያት በማሰማት አከባቢውንና
እንቅስቃሴን ማወክ የተከለከለ ነው።
የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ብልሽት
የዝናብ መጥረጊያ፡- በዝናብ ወቅት የግንባር መስታወት በዝናብ እንዳይሸንና አሽከርካሪው
በግልጽ ማየት እንዲችል በማድረግ አደጋ እንዳይከሰት መስታወቱን ለማጽዳት ያገለግላል።

የግንባር መብራቶች፡- አሽከርካሪዎች በምሽት በሚጓዙበት ጊዜ አጭሩን ወይም ረጅሙን


መብራት በመጠቀም የመንገዱን ሁኔታ በግልጽ ለማየትና ለመቆጣጠር የሚያስችል
መብራት ነው።
 ስፖኪዮ
 የጭጋግ ማቅለጫ
 የጨረር መከላከያ
 የውስጥ መብራት
የዳሽ ቦርድ ጠቋሚ መሳሪያዎች ብልሽት
ስፒዶ ሜትር/የፍጥነት መቆጣጠሪያ
ተሽከርካሪው በሰዓት ምን ያህል ኪ.ሜ. እየተዘ
እንደሆነ ለአሽከርካሪው የሚያመለክት መሳሪያ
ነው።
¾’ÇÏ SÖ” ›SM"‹
በነዳጅ መያዣ ጋን ውስጥ በቂ የነዳጅ
መጠን መኖሩንና አለመኖሩን ለአሽከርካሪው
የሚያሳውቅ መሳሪያ ነው።
ኦዶ ሜትር/የጉዞ መቆጣጠሪያ
ተሽከርካሪ ከተሰራበት ጊዜ ጀምሮ ምን ያህል
ኪ.ሜ. እነደተጓዘ የሚመዘግብ መሳሪያ ነው።

ትሪፕ ኦዶ ሜትር
ተሽከርካሪው በአንድ ጉዞ ብቻ ምን ያህል
ኪ.ሜ. እንደተጓዘ የሚመዘግብ መሳሪያ ነው።
የሞተር ዙር አመልካች/ታኮ ሜትር
የሞተር ዙር በደቂቃ ምን ያህል እንደሆነ የሚገልጽ
ሲሆን በገባው ማርሽ ተመጣጣኝ ያልሆነ ነዳጅ
እየተጠቀምን መሆኑን የሚያስጠነቅቅ ነው
የሞተር ሙቀት አመልካች
ሞተሩ ሊሰራ የሚችልበት ጤናማ የሙቀት ክልል ውስጠ መሆኑንና ያለመሆኑን
ለአሽከርካሪው የሚያመለክት መሳሪያ ነው።
የዘይት ግፊት አመልካች
ሞተር ተነስቶ መስራት ሲጀምር ወደ ሞተረ ክፍል በቂ የዘያት
ስርጨትና ዝውውር መኖሩንና ያለመኖሩን በቀስት፣በቁጥርና
በመብራት ለአሽከርካሪው የሚያመለክት መሳሪያ ነው።
የማሞቂያ መሳሪያ አመልካች/የግሉ ፕለግ/የካዴሊቲ መብራት
 የናፍጣ ሞተር ለማስነሳት ባስፈለገ ጊዜ የማሞቂያ መሳሪያው
የማቀጣጠያ ክፍሉን በትክክል ማሞቅና ያለማሞቁን ለአሽከርካሪው
የሚያመለክት መሳሪያ ነው።
 የፍሬን ማስጠንቀቂያ መብራት

 የቻርጅ ማስጠንቀቂያ መብራት

 የሞተር ማስጠንቀቂያ መብራት

 የችንጋ ማስጠንቀቂያ መብራት

 የፊልትሮ ማስጠንቀቂያ መብራት


 የእጅ ፍሬን አመልካች

 የግንባር መብራት አመልካች

 የጭጋግ መብራት አመልካች

 የፍሬቻ መብራት ሁኔታ አመልካች


 የደህንነት ቀበቶ አመልካች

 የበር ሁኔታ አመልካች

 የአክስል ሎክ ማስጠንቀቂያ
3.የአከባቢ ሁኔታዎች
 ÅS“T  Çу
 ›vD^T  lMlKƒ
 ´“vT  ÖS´T³
 ßÒÒT
የተፈጠሮ ህጎች
በማሽከርከር ላይ ተጽእኖ የሚያደርጉ< የተፈጥሮ ህጎች የሚባሉት

1.የመሬት ስበት
2.ኢነርሻ
3.ሞመንተም
4.የካይኔቲክ ሀይል
5.የፖቴንሺል ሀይል
6.ሰበቃ
7.ሴንተርፉጋል
1.የመሬት ስበት/ግራቪቲ

የመሬት ስበት ሁሉም ነገሮች ወደ መሬት መሀል የሚስብ ሀይል ነው። የመሬት ስበት
ዳገት ስንወጣና ቁልቁለት ስንወርድ በጉዞ ፍጥነታችን ላይ ተጽእኖ ያመጣል። የመሬት
ስበት ጎማና መሬት ቆንጥጦ እንዲይዝ የሚያደርግ ሀይል ነው።ዳገት ሲወጣ የመሬት
ስበት የተሽከርካሪውን ፍጥነት ይቀንሳል። ቁልቁለት ሲወርድ የተሽከርካሪውን ፍጥነት
ይጨምራል ስለዚህ ቁልቁለት ሲወረድ ፍጥነትን ለመቆጣጠር ከባድ ማርሽ መጠቀምና
ፍሬን በትንሹ መያዝ ተሽከርካሪን ለመቆጣጠር ይረዳል።
2.ኢነርሻ
ሌላ ተጨማሪ ሀይል እሳካልመጣ ድረስበመንሳቀስ ላይ ያሉ ነገሮች እንቅስቃሴያቸውን
መቀጠል ይፈልጋሉ የቆሙ ነገሮች ደግሞ እንደቆሙ መቅረት ይፈልጋሉ።ይህ የኢነርሻ
ህግ ነው።ፍሬን ካልተያዘ መሬቱ ወይም ሌላ ቋሚ ከፊት ካላገደ በስተቀር መጓዝ የጀመረ
ተሽክርካሪ በኢነርሻ ምክንያት ጉዞውን ይቀጥላል።ተሽከርካሪ ከጉዞ በድንገት ሲቆም
ሰውና የተንጠለጠሉ ነገሮች ላይ አደጋ ሊያደርስ ይችላል።
3.ሞመንተም
ሁለት ያልተመጣጠኑ ሀይሎች በተቃራኒ አቅጣጫግፊታቸውን ሲያሳርፉ
የሚንሳቀስ ነገር የያዘው ሀይል ሞመንተም ይባላል።የዚህ መጠን ሀይል እንደ
ተንቀሳቃሹ ነገር ክብደትና ፍጥነት ይወሰናል።
4.የኬኔቲክ ሀይል
እንቅስቃሴ ላይ ያለ ነገር የሚኖረው ሀይል ኬኔቲክ ኢነርጂ ይባላል።

5.የፖቴንሺያል ሀይል
ነገሮች ባሉበት ቦታ ወይም ቅርጽ ምክንያት የሚኖራቸው የተጠራቀመ ሀይል ፖቴንሺዯል
ኢነርጂ ይባላል።
6.ሰበቃ
አንድ ነገር ከሌላ ነገር ጋር ሲነካካ የሚፈጠር ሀይል ሰበቃ ይባላል።ሰበቃ አንድ ነገር
በሌላ ነገር እንዳይንቀሳቀስ ያደርጋል።
7.ሴንተርፉጋል
አንድ ነገር በሌላ ነገር ዙሪያ ሲዞር ወደ ውጪ የመጎተት ዝንባሌ ሴንተርፉጋል
ሀይል ይባላል።
አደጋን መከላከልና ማስወገድ
ሀ.ለአደጋ መንስኤ የሚሆኑ ነገሮችን አስቀድሞ መለየት
 አንድ አሽከርካሪ ከፊት የሚያየው ርቀት በከተማ ውስጥ ከሆነ ከ12 እስከ 15 ሰከንድ
ከከተማ ውጪ ከሆነ ከ20 እስከ 30 ሰከንድ በሆነ ግዜ ሊደርስ የሚችልበትን ርቀት መሆን
አለበት። በ38 ከ.ሜ. በሰአት የሚያሽከረክር አሽከርካሪ ከ161-201 ሜ.ያለውን ርቀት
ከ12-15 በሆነ ግዜ ይደርስበታል።
 ከፊት ማየት ሲባል አንድ ተሽከረካሪ ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ቦታ በአይን መቃኘትና
መቆጣጠር ይጠይቃል።
ለ.የሰከንድ ህግ
ከፊት ለፊት ካለ ተሽከርካሪ ርቀታችንን የማናስተካክልበት ህግ ነው።
1.የ3 ሰከንድ ህግ
የ3 ሰከንድ ህግ ማለት ተሽከርካሪ በ3 ሰከንድ የሚሄደው ርቀት ማለት ነው።በመንገድ ላይ ስናሽከረክር
ከፊታችን ካለው ተሽከርካሪ ምን ያህል ርቀት ላይ እንዳለን ለማወቅ የ3 ሰከንድ ህግ የላቀ ጠቀሜታ
አለው።ከፊትህ ያለው ተሽከርካሪ ያለበትን ቦታ ምልክት ያዝና አንድ ሺህ አንድ፣አንድ ሺህ ሁለት፣ አንድ ሺህ
ሶስት በማለት ቁጠር። ቁጥሩን ሳትጨርስ ከቦታው ከደረስክ ተጠግተህ እያሽከረከርክ ስለሆነ የተወሰነ መራቅ
ይጠበቅብሀል ማለት ነው።
2.የ4 ሰከንድና ከዚያ በላይ
• በአንሸራታች መንገድ
• በትክክል ለማየት በሚያስቸግር ቦታ
ሐ.የጉዳት መጠንን መቀነስ

ብዙ አደጋዎችበአንድ ግዜ እንዳይከሰቱ መከላከል አንዱ የማሽከርከር ስልት


ነው። ለምሳሌ በቀኝ በኩል እግረኛ በግራ በኩል ደግሞ ከባድ ተሽከርካሪ
ቢገጥምህ ማድረግ ያለብህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተሽከርካሪ ማሳለፍና
እግረኛውን በጥንቃቄ ማለፍ ነው
መ.ከአደጋ የማምለጥ ስልት

በአደገኛ ሁኔታ አደጋ እንዳይከሰት የሚዯደርጉ 3 ነገሮች አሉ። እነሱም


1.በመቆም
2.በመሪ ማዞር
3.ፍጥነት መጨመር ናቸው
ሠ.ፍጥነትን ተቆጣጥሮ በማሽከርከር አደጋን መከላከል

የተሽከርካሪ ፍጥነት የሚወሰው


• በሌሎች ተሽከርካሪዎች ብዛትና ፍጥነታቸው
• በመንገዱ ሁኔታ
• በመንገድ ዳር በሚኖሩ እግረኞች ብዛት
• በአየሩ ሁኔታ
የእሳት አፈጣጠርና የማጥፋት ዘዴ
እሳት ከሶስት ነገሮች ሊፈጠር ይችላል፡፡ እነሱም ፡-
1. ከኦክስጅን /አየር/፣
2. ከነዳጅ /ተቀጣጣይ ከሆነ ነገሮች/
3. ከሙቀት /የሰበቃ ውጤት/ ናቸው፡፡
የሚቀጣጠሉ ነገሮች በሦስት ዓይነት መልክ ሊገኙ ይችላሉ፡፡

1. ጠጣር፡- እንጨት፣ ወረቀት፣ ጥጥ ...


2. ፈሳሽ፡- ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ ዘይት...
3. ጋዝ፡- ቡቴን፣ ሚቴን፣ ፕሮፔን...
መቀጣጠል የጀመረን እሳት በሚከተሉት ዘዴዎች ማጥፋት ይቻላል፡፡ ይኸውም፦
1. በማፈን /ኦክስጂን በማሳጣት/፣

2. በማቀዝቀዝ /ሙቀት በማሳጣት/፣

3. በማስራብ/ነዳጅ በማሳጣት/፡፡
የእሳት አመዳደብና የማጥፊያ
መሣሪያዎች
1. የ/ሀ/(A) ክፍል ( 1ኛ ደረጃ ) እሳት

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው ከጠጣር ነገሮች ማለትም


እንጨት፣ ወረቀት፣ ጥጥ....ወ.ዘ.ተ ከመሳሰሉት ሲሆን
የማጥፊያ መሣሪያው ውሀ ሊሆን ይችላል፡፡
2. የ/ለ/(B) ክፍል ( 2ኛ ደረጃ ) እሳት

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው ከፈሳሽ ነገሮች


ማለትም ቤንዚን፣ ናፍጣ ...ወ.ዘ.ተ ከመሳሰሉት
ሲሆን የማጥፊያ መሣሪያዎቹም ፎም፣ ግፊት
ያለው ማፈን የሚችል ካፊያ ውሀና ካርቦን
ዳይኦክሳይድ ናቸው፡፡
3. የሐ(C)ክፍል ( 3ኝ ደረጃ ) እሳት

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው ከጋዝ ማለትም ቡቴን


ሚቴን...ወ.ዘ.ተ ከመሳሰሉት ወይም ከኤሌክትሪክ
ሲሆን የማጥፊያ መሣሪያዎቹም ካርቦንዳይ ኦክሳይድና
ድራይ ፓውደር ናቸው፡፡
4. የመ (D)ክፍል ( 4ኛ ደረጃ ) እሳት፡

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው ከብረት ንጥረ ነገሮች


ማለትም ፖታሼም፣ ማግኒዚየም ከመሳሰሉት ሲሆን
የማጥፊያ መሣሪያዎችም ድራይ ፓውደርና ደረቅ
ደቃቅ አሸዋ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
• በ/ለ/ ክፍል እሳት ላይ ካፊያነት የሌለው ውሀ መጠቀም እሳቱን ሊያባብሰው ይችላል፡፡
• በ /ሐ/ እና በ /መ /ክፍል እሳት ላይ ውሀና እርጥበት ያለውን ነገር መጠቀም በፍጹም የተከለከለ
ነው፡፡
በተሽከርካሪ ላይ እሳት እንዲነሳ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች
• በነዳጅ መስመር ላይ የሚያፈስ ቦታ መኖር፣
• የተላላጡና የተዝረከረኩ የኤሌክትሪክ መስመሮች፣
• የሞተር ከመጠን በላይ መሞቅ፣
• ባትሪ በሚፈታና በሚታሠርበት ወቅት የሚኖር የጥንቃቄ ጉድለት፣
• የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን ያለመከደንና በዚያ አካባቢ ሲጋራ ማጨስ ወይም ሌሎች እሳት ሊያስነሱ
የሚችሉ ነገሮች መኖር፡፡
1.በተሽከርካሪ ውስጥ ዘወትር የእሳት ማጥፊያ እንዳለ መከታተል የስራ ላይ ደህንነት አተገባበር ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
2.የእሳት ማጥፊያ ወሣኘ የጥንቃቄ መሣሪያ ነው ሀ/ እውነት ለ/ ሐሰት
3.የ “መ” ክፍል እሳት ምድብ የሆነው የቱ ነው
ሀ/ ሚቴን ለ/ ላምባ ሐ/ ካልሲያም መ/ ሁሉም መልስ ነው
4. በእንጨት የተነሳ እሳት በውሃ ስናጠፋ የተጠቀምንበት የማጥፊያ ዘዴ የቱ ነው?
ሀ/ ማቀዝቀዝ ለ/ ማፈን ሐ/ ማስራብ መ/ ማራቅ
5. የእሳት ማጥፊያ ዘዴ በ ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባል ሀ/ 2 ለ/ 3 ሐ/ 4 መ/ 5
6. ሙቀትን በማስወገድ የማጥፋት ዘዴ
ሀ/ ማስራብ ለ/ ማቀዝቀዝ ሐ/ ካርቦን ዳይኦክሳይድ መ/ ፎም
7.ቡታ ጋዝ፣ ቡቴንና ሚቴን የተባለ ተቀጣጣይ ነገሮች በስንተኛ ደረጃ የእሳት ምድብ ውስጥ ይገኛሉ?
ሀ/ በአንደኛ ደረጃ (ሀ) ለ/ በሦስተኛ ደረጃ(ሐ) ሐ/ በሁለተኛ ደረጃ (ለ) መ/ በአራተኛ ደረጃ(መ)
8. ተቀጣጣይ ነገሮች በማራቅ እሳትን የምናጠፋበት ዘዴ ምን ይባላል፡፡
ሀ. ማስራብ ለ. ማፈን ሐ. ማቀዝቀዝ መ. ሁሉም
9. በተሽከርካሪ ላይ በኤሌክትሪክ ምክንያት እሳት ቢነሳ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ማጥፊያ መጠቀም ያለባቸው የማጥፊያ
መሳሪያ የትኛው ነው? ሀ. ውሃ ለ. ፎም ሐ. ካርቦን ዳይኦክሳይድ መ. ሁሉም
10.እሳት በተሽከርካሪ ላይ ሊከሰት የሚችልበት ምክንያት ውስጥ ሊከተት የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. የነዳጅ ማመላለሻ ቱቦ ነዳጅ መፍሰስ ለ. የኤልክትሪክ ገመዶች መላላጥ
ሐ. የሞተሩ ከመጠን በላይ መሞቅ መ. ሁሉም
11. እሳት የማይፈጠርበት መንገድ የሆነው የቱ ነው? ሀ. ባትሪ ሲታሰርም ሆነ ሲፈታ በቂ ጥንቃቄ አለማድረግ
ለ. የነዳጅ ታንከር በአግባቡ ካልተከደነና ሲጋራ በአካባቢው የሚጨስ ከሆነ ሐ. የነፋስ ኮምኘሬሰር ከፈነዳ
መ. መልሱ የለም
12. የእሳት ማጥፊያ ዘዴ የሆነው የቱ ነው? ሀ. ማፈን ለ. ማቀዝቀዝ ሐ. ማስራብ መ. ሁሉም
የማንዋል አጠቃቀም
የማንዋል አይነቶች
ሀ. የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል
በውስጡ የተሸከርካሪውን የተለያዩ ክፍሎች የሚገልጽ ሲሆን የተሸከርካሪዎችን፡-
• የምርት ቁጥር
• ሞዴል
• የሞተር ቁጥር
• የተመረተበት ዓመተ ምህረት
• የሻንሲ ቁጥር
• የአክስል ክብደት መጠን
• ጠቅላላ ነጣላ ክብደት
• የአካል ቀለም አይነት ወ.ዘ.ተ. የሚገልጽ ማንዋል አይነት፡፡
ለ. የጥገና ማንዋል
ተሽከርካሪ ብልሽት ሲያጋጥመውና እንዴት ተደርጎ መጠገን እንዳለበት የሚገልጽ ማንዋል አይነት ነው፡፡
• ርዝመት
• ስፋት
• ውፍረት
• በተሸከርካሪ መካከል መሀከል ያለውን ክፍተት
• የመጥበቅና የመላላት ሁኔታ
• ልዩ የሆነ የጥገና መሳሪያ አጠቃቀም
• የአፈታትና የአስተሳሰር ቅደም ተከተል
• የአጠቃቀም ጥንቃቄ የሚያብራራ የማኑዋል
• አይነት ነው፡፡
ሐ. የመለዋወጫ እቃ ማንዋል፡-
ተሸከርካሪ ላይ ያሉ የተለያዩ ክፍሎች ተበላሽተው መቄር ሲያስፈልግ በምን አይነት
ተመሳሳይ መለዋወጫ መቀየር እንደሚገባ የእቃውን አይነትና መለያ ቁጥርና አጠቃላይ
የእቃው መግለጫ የሚገኝበት የማንዋል አይነት ነው፡፡ለምሳሌ፡-
• የመለዋወጫ አይነትና ብዛት
• የግራ ወይም የቀኝ አቅጣጫ
• የእቃ መለያ ቁጥር
መ. የተሸከርካሪ የአጠቃቀም ማንዋል፡- የተሸከርካሪዎችን የተለያዩ ክፍሎች አጠቃቀም የሚገልጽ
የማንዋል አይነት ነው፡፡ ለምሳሌ
የሞተር አነሳስና አጠፋፍ
የማርሽ አቀያየር ቅደም ተከተል
የፍሪሲዮን አጠቃቀም
የፍሬን አጠቃቀም
የበር አዘጋግና አከፋፈት
የወንበር ማስተካከል ሁኔታ
የደህንነት ቀበቶ አጠቃቀም
በዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ ጠቃሚ ምልክቶች
መለኪያዎችን መለየት

 የመለኪያ መስፈርቶች በአለም አቀፍ ደረጃ የሚወጡ ሲሆኑ እንደ አምራች ድርጅቱ ሁኔታ
ሊለያዩ ቢችሉም ተመሳሳይ መልዕክ የሚያስተላልፉ በመሆናቸው ማንኛውም ተሸከርካሪም
ሆነ አሽከርካሪየሚጠግን ባለሙያ በማንዋል ውስጥ የተቀመጡትን መለኪያዎች እንደ ሚሊ
ሜትር፤ኢንች፤ሲሲ፤ግራም ወ.ዘ.ተ.መሆናቸውን በማወቅ መጠቀም አለባቸው፡፡
1. የሻንሲ ቁጥርና የሞተር ቁጥር በየትኛው የማንዋል ዓይነት ውስጥ ይካተታሉ፡፡
ሀ. የመለዋወጫ ዕቃ ማንዋል ለ. የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል ሐ. የአጠቃቀም ማንዋል መ. መልሱ አልተሰጠም
2. ስለ በር አዘጋግ የሚናገር የማንዋል ዓይነት ይባላል፡፡
ሀ. የአጠቃቀም ማንዋል ሐ ለ. የመለዋወጫ ዕቃ ማንዋል . የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል መ. የጥገና ማንዋል
3. ለአሽከርካሪዎች በተለይ ጠቃሚ የማንዋል ዓይነት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የጥገና ማንዋል ለ. የመለዋወጫ ልኬት ማንዋል ሐ. የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል መ. የአጠቃቀም
ማንዋል
4. በዕቃዎች መካከል የሚኖርን እርዝመት፣ ውፍረትና ስፋት የሚገልጽ የማንዋል ዓይነት ይባላል፡፡
ሀ. የመለዋወጫ ዕቃ ማንዋል ለ. የጥገና ማንዋል ሐ. የአጠቃቀም ማንዋል መ. የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል
5. ሜትር በማንዋል ውስጥ ለመለኪያ መስፈርትነት ያገለግላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
6. ለጋራዦችና ለመካኒኮች የሚጠቅም የማንዋል ዓይነት ይባላል፡፡
ሀ. የአጠቃቀም ማንዋል ለ. የበላቤት ማንዋል ሐ. የጥገና ማንዋል መ. መልሱ አልተሰጠም
7. በተሽከርካሪው ላይ ያለ አንድ ዕቃ ሲበላሽ በምን ዓይነት ሁኔታ መቀየር እንዳለብን የሚናገር የማንዋል ዓይነት ይባላል፡፡
ሀ. የጥገና ማንዋል ለ. የአጠቃቀም ማንዋል ሐ. የመለዋወጫ ዕቃ ማንዋል መ. የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል
8.የደህንነት ቀበቶ አጠቃቀምንና ወንበር ማስተካከል በየትኛው የማንዋል ዓይነት ውስጥ ይገልፃል
ሀ. በአጠቃቀም ማንዋል ለ. በመለዋወጫ ማንዋል ሐ. በጥገና ማንዋል መ. በአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል
9. በማንዋሉ ውስጥ ከምናገኛቸው የመለኪያ መስፈሪያዎች ውስጥ አንዱ አይካተትም ሀ. ሚሊ ሜትር ለ. ክንድ ሐ. ኢንች መ. ሲ.ሲ
10. ማንዋሎች ሁልጊዜ ተገቢው ጥበቃና በቀላሉ ሊገኙበት የሚችሉበት ቦታ መቀመጥ አለባቸው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
11.ከሚከተሉት ውስጥ ስለሞተር አጠፋፍና ማርሽ አቀያየር የሚገልጸው የማንዋል ዓይነት የትኛው ነው
ሀ. የመለዋወጣ እቃ ማንዋል ለ. የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል ሐ. የአጠቃቀም ማንዋል መ. የአምራች ድርጅት ልማት ማንዋል
12. የተሽከርካሪው የአካል ቀለም ዓይነት በየትኛው የማንዋል ዓይነት ውስጥ ይካተታል፡፡
ሀ. በአጠቃቀም ማንዋል ለ. በመለዋወጫ እቃ ማንዋል ሐ. በአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል መ. መልሱ አልተሰጠም
13. ከሚከተሉት አንዱ ከማንዋል ዓይነቶች ውስጥ አይደለም
ሀ. የአጠቃቀም ማንዋል ለ. የጥገና ማንዋል ሐ. የመለዋወጫ እቃ መ. መልሱ አልተሰጠም
የአከባቢ ብክለት
 የአከባቢ ብክለት ማለት የምንኖርበት አከባቢ ንጽህና የሚያበላሽ እና ህይወታችንን
አስፈላጊ የሆነውን ኤር ከፋብሪካ በሚወጣ ጭስ፤ የተለያዩ አይነት ፈሳሾች፤ከተሽከርካሪ
የሚወጣ አገልግሎቱን የጨረሰ የሞተር ዘይት እንዲሁም ጭስ ሲሆን ይህምበሰው
ጤንነት ላይ እና በእጽዋቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ በማድረስ ለተለያየ አይነት
ችግሮች ያጋልጣል፡፡
አከባቢ እንዴት ይበከላል

 የምንኖርበት አከባቢ በተለያየ መልኩ የአከባቢ መበከል ችግር


ያጋጥመዋል፡፡ከተሸከርካሪ ጋር በተያያዘ መልኩ የአከባቢ ብክለትን
የሚያስከትሉ ሁኔታዎች፡-
• ሲነዱ
• ሲጠገኑና
• ሲታጠቡ
ተሸከርካሪዎች ሲነዱ የአከባቢ ብክለት ምክንያቶች
 አሽከርካሪዎች ተሸከርካሪያቸውን በሚያሽከረከሩበት ወቅት የአከባቢ ብክለት ይፈጠራል፡፡ይህም ሲባል
የነዳጅ፤የዘይት እና የአከባቢ ብክለትወደ ውጪ መፈሰስ
 ተሸከርካሪን በወቅቱ ሰርቪስ ሳይደረግለት ሲቀር ለምሳሌ የሞተር ዘይትበወቅቱ ካልተቀየረ በተሸከርካሪ
ውስጥ አላስፈላጊ ጭስ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
 ከመጠን በላይ በፍጥነት በማሽከርከር ነዳጅ በአግባቡ በሞተር ውስጥ ስለማይቀጣጠል ነዳጅ ከጭስ ጋር
አብሮ በመውጣት ለአከባቢ ብክለት ምክንያት ይሆናል፡፡
 የተለያዩ ጎጂ ጭሶችና ድምጽ መቀነስ፡፡ተሸከርካሪ ረጅም ዕድሜ ሲሰራ በውስጡ የተለያዩ የሞተር ክፍሎች
ስለሚያልቁ ጭስ ከመጠን በላይ በመውጣት አከባቢን በከፍተኛ ሁኔታ ለመበከል ምክንያት ይሆናል፡፡
 ከተሸከርካሪ የሚወጣ አደገኛ ጭስ ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ፤ናይትሮጂን ኦክሳይድና ሀይድሮ ኦክሳይድ፡፡
በጥገና ወቅት የአከባቢ ብክለት ምክንያቶች
 በጥገና ወቅት አከባቢን ሊበክሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን አሽከርካሪዎች አስቀድመው መረዳትና መቀነስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 የተሸከርካሪ ጭስ ማውጫ ሲቀደድ ቶሎ ማስጠገን
 ተስማሚ የማጽጃ መሳሪያዎችን መጠቀም ለምሳሌ ኮምፕረሰር፤ግፊት ያለው ውሃ፤ንጹ እስትራቾ የመሳሰሉት ነው፤፤
 የተሸከርካሪ የመጠገኛ ቦታዎችንና መጠገኛ መሳሪያዎችን በጥንቃቄ መጠቀም፡፡
 ያገለገሉ ተሸካሪዎችን በተወሰነ ቦታ በማስቀመጥ በአግባቡ ማስወገድ፡፡
 ጭስን የሚከላከሉ መሳሪያዎች መጠቀም/ማስገጠም/ ለምሳሌ ካታሊክ ኮንቨርተር፤፤
በጽዳት ወቅት የአከባቢ ብክለት ምክንያቶች
 ተሸከርካሪዎች በተገኘበት ቦታ ሁሉ የምናጥብ ወይም የምናረዳ ከሆነ ከተሸከርካሪው ሞተርና
አካል የሚወጣ የተለያየ አይነት ጎጂ ነገር አከባቢን በከፍተኛ ሁኔታ ሊበክል ይችላል፡፡

 ተሸከርካሪን በወንዝና በረጋ ውሀ ውስጥ ማጠብ ሰውም ሆነ እንስሳት ለመጠጥ አገልግሎት


ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ ከተሸከርካሪው የወጣውን ዘይትና ቆሻሻ ነገር ውሀውን ስለሚበክል
ለከፍተኛ አደጋ ያጋልጣል፡፡
በማሽከርከር ላይ የሚፈጠርን ብክለት ለመቀነስ በዋናነት አሽከርካሪዎች ነዳጅ ፍጆታን
መቀነስ አለባቸው፡፡የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ በማሽከርከር ሂደት ላይ ማድረግ ያለባቸው
ክንዋኔዎች፤-
• የጎማ ንፋስ ከመጠን በታችና ጎማ ሊሾ እንዳይሆን መከላከል/ማስወገድ/፡፡
• አላስፈላጊ ጭነት አለመጫን፤
• በሚኒሞ/በአይድል/ ረጅም ሰአት አለማሰራት፤
• እግርን ፍሬንና ፍሪሲዎን ላይ አስደግፎ አለማሽከርከር
• ያለ አግባብ ፍሬን አረጋገጥን ማስወገድ
• ተሸከርካሪዎች የሚበዙበት ቦታ ማሽከርከርን/ትራፊክ ሲስተም የሚጨናነቅበት
ቦታ /ማስወገድ፤
• ተሸከርካሪን በአግባቡ ሰርቪስ ማስደረግ
• ኤርኮንዲሽነርን/ማሞቂያና ማቀዝቀዣ/ በአግባቡ መጠቀም
1. ከተሸከርካሪ የሚወጣው ጭስ አደገኛ የጋዝ ልቀት የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ CO ለ/ CH2 ሐ/ CH3 መ/ NSO
2. የአካባቢ ብክለት የሚከሰተው በማሽከርከር ወቅት ብቻ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
3. የተሽከርካሪን ንጽህና መጠበቅ ለተሸከርካሪው እድሜ መራዘም ምንም አስተዋጽኦ የለወም፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
4.በአጠባ ወቅት በሚፈጠር ስህተት ውሃ በነዳጅ አስተላላፊ ክፍል ውስጥ ቢገባ ምን ይፈጠራል?
ሀ. ሞተሩ ይጠፋል ለ. የሞተሩ ድምጽ ይቆራረጣል ሐ. ነዳጁ ይቋረጣል መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
5. እጥበት በሚከናወንበት ወቅት ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የኤሌክትሪክ ክፍሎችን መሸፈን አ ለ. በሮችን በደንብ መዝጋት ሐ. ነዳጁ ይቋረጣል መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ አሰጣጥ
1. የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ

የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ ማለት አንድ ሰው በተለያየ ምክንያት በድንገት ጉዳት ደርሶበት
ሲታመም መደበኛውን ህክምና ወደሚያገኝበት የህክምና ተቋም እስከሚደርስ ድረስ በቅድሚያ
የሚደረግለት ዕርዳታ ማለት ነው፡፡
2. የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ
መስጫ ሳጥን የሚይዛቸው ቁሳቁሶች • አንድ ሰፊ የላስቲክ ሺት፣
• ቢያንስ በቁጥር ሁለት የሆኑ የጥጥ ወይም የወረቀት
• አንድ ስኩዌር ሜትር ስፋት ያለው አንድ ከጥጥ የተሰራ
ጥቅሎች /ፓዶች/፣ ጨርቅ፣
• ቢያንስ በቁጥር ስድስት የሆነ ሶስት ማዕዘን ፋሻዎች
• አንድ የቁስል መጥረጊያ መድኃኒት/አንቲሴፕቲክ/፣
ወይም ባንዴጅ፣ • አንድ የላስቲክ ቀረጢት፣
• በቁጥር ሁለት የሆኑ የተቀቀሉ የጨርቅ ፓዶች፣ • አንድ ምላጭ/መቀስ/፣
• በቁጥር አስር የሆኑ ጥቅል ፋሻዎች፣ • ሁለት ድጋፎች/እስፓሊንት፣
• አራት የቁስል ፕላስተሮች፣ • አንድ ሳሙና ከነማስቀመጫው፣
• አንድ የውሀ መጠጫ ኩባያ • አራት ትናንሽ የእጅ ፎጣዎች፣
• አራት የእጅ ጓንቶች/ግላቭ/፡፡
3. አስፈላጊ ዝግጅቶች
 ድንገተኛ አደጋ የሚደርስበት ጊዜ፣ ስፍራና አጋጣሚ ስለማይታወቅ የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ ተግባር
የሚጠየቅበትም ጊዜና ቦታ እንደዚሁ ባላተጠበቀና በማንኛውም ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡
 ይሁን እንጂ ማንኛውም አሽከርካሪ ይህ ሁኔታ በማንኛውም ቦታ ቢገጥመው የሚቻለውን ያህል ዕርዳታ
ለማበርከት ራሱንና የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ መስጫ መሣሪያውን አዘጋጅቶ መገኘት እጅግ
ይጠቅመዋል፡፡
 ድንገተኛ አደጋ ባጋጠመ ጊዜ የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ ሲሰጥ ሊተኮርባቸውና ሊታወሱ
የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
• አደጋው የደረሰበት ሰው በደንብ ይተነፍስ እንደሆነ ማረጋገጥ፣
• አደጋው በደረሰበት ሰው አፍና በአፍንጫው አካባቢ ለመተንፈስ የሚያግደው ነገር ካለ በፍጥነት
ማስወገድ፣
• አደጋው ከደረሰበት ሰው አጠገብ በመንበርከክ አንድ እጅን የተጎዳው ሰው አንገት ስር፣
• ሌላውን ደግሞ ግንባሩ ላይ አድርጎ የተጎዳውን ሰው ወደኋላ በማድረግ አየር መተላለፊያው ክፍት
እንዲሆን ማድረግ፣
• አደጋው ከደረሰበት ሰው ላይ የሚፈሰውን ደም ለማቆም ተገቢውን ፈጣን እርምጃ መውሰድ፣
• አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ አፋጣኝ የሆነ ዕርዳታ ለመስጠት በይበልጥ እንዲረዳ የሚፈልግና ችሎታ ያለው
ሰው ሊኖር ስለሚችል በመምረጥ የሚችለውን ያህል እንዲረዳ ማድረግ፣
• _አደጋው በደረሰበት ሰው ላይም ሆነ በሌሎች ላይ እሳት፣ የትራፊክና ሌሎች ተመሳሳይ የሆኑ አደጋዎች
እንዳይደርሱ አደጋው የደረሰበትን ሰው መጠበቅ፣ ሌሎችም እንዲጠነቀቁ ተገቢውን እርምጅ መውሰድ፣
• አደጋው የደረሰበት ሰው ያረፈበት ቦታ አደገኛ ካልሆነና መነሳት ከሌለበት አደጋው የደረሰበት ሰው ትክክለኛ
ጉዳት ሳይታወቅ በችኮላ አለማንሳት፣ አለማንቀሳቀስ፣
• አደጋው የደረሰበትን ሰው መርምሮ በፍጥነት አስፈላጊውን የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ ማድረግ፣
• አደጋው የደረሰበት ሰው በህዋሳቶች መድከም/መጎዳት/ የተነሳ የሰውነት መደንገጥ/ሾክ/ እንዳይደርስበት
መከላከል፣
• አደጋው የደረሰበትን ሰው ልብስ ከሚገባው በላይ አለማውለቅና ሙቀት እንዲያገኝ ማድረግ፣
• ሌሎች ሰዎች አደጋው ከደረሰበት አካባቢ ራቅ እንዲሉ ማድረግ፣
• አደጋው የደረሰበትን ሰውና የደረሰውን አደጋ ዝርዝር ሁኔታ በማስረዳት ጉዳተኛው ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ
ማድረግ፡፡
4. የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ዕርዳታን በቅልጥፍና ማከናወን የሚቻልበት ዘዴ
• ተገቢውን ዕርዳታ ለመስጠት አለመረበሽና ለዚሁ ሰውነትን ዝግጁ ማድረግ፣
• አደጋው ደረሰበትን ሰው ለመርዳት ኃላፊነቱን ወስዶ በርጋታና በጥንቃቄ ለዕርዳታ
የሚያስፈልገውን ቅደም ተከተል ማቀድ፣ ለዚህም ከሚያስፈልገው ጊዜ በላይ አለማባከን፣
• የሚሰጠውን ዕርዳታ ከሚገባና አቅም ከሚፈቅደው በላይ አለመሞከር፣
• አደጋው የደረሰበትን ሰው በርህራሔና ያለመጠየፍ መርዳት፣
• አደጋው የደረሰበትን ሰው ማፅናናት፣ የዕርዳታውን ተግባር ፀጥታ በተሞላበት አኳኋን
በቅልጥፍናና በፍጥነት ማከናወን፣አደጋው የደረሰበትን ሰው በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም
መውሰድ ናቸው፡፡
5. አደጋ የደረሰበትን ሰው ስለመመርመር
 አደጋ የደረሰበትን ሰው መርምሮ የአደጋው መጠንና ሁኔታ በግልፅ እስከ አልታወቀ ድረስና
አደጋው የደረሰበት ሰው የተኛበት ስፍራ ተጨማሪ ጉዳት የሚያስከትል ካልሆነ በስተቀር
አለማንቀሳቀሱ ይመረጣል›› በተከታታይም፦
 አደጋው የደረሰበት ሰው መድማቱን፣ እስትንፋሱ መቋረጡን ወይም ራሱን ማወቅ ተስኖት
መሆኑን ቶሎ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እንኳን ቢኖር በፍጥነት
ተገቢውን የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡
 አደጋው የደረሰበት ሰው ልብስ በርጥበት ወይም በጭቃና በመሳሰሉት የተበላሸ ከሆነ ልብሱን
በማውለቅ ሰውየውን በማንኛውም ንፁህና ሞቃታማ በሆነ ልብስ በመጠቅለል ትክክለኛውን
የሰውነት ሙቀት እንዲያገኝ ማድረግ፡፡ ሆኖም ግን የሙቀቱ መጠን እስኪያልበው ድረስ
መሆን አይገባም፡፡
 አደጋው የደረሰበት ሰው በመጋጨት፣ በመዳጥ፣ በመውደቅና በመቀጥቀጥ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት ከሆነ በጥንቃቄ በመመርመር
በውስጥ ህዋሳቶቹ ላይ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ በአንዳንድ ጠቋሚ ሁኔታዎች በመገንዘብ ተገቢውን ክትትል ማድረግ፣
 አደጋው የደረሰበት ሰው ራሱን የሚያውቅ ከሆነ ማፅናናትና ማበረታታት እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፣
 ስለአደጋው ሁኔታ በአካባቢው የሚገኙትን ሰዎች ጠይቆ መረዳቱ ወይም የተጎዳው ሰው መናገርና ማስረዳት የሚችል ከሆነ፦
ሀ. ሙሉ ሥምና አድራሻውን በዝርዝር መቀበል፣
ለ. አደጋው የደረሰበትን ሁኔታና የተጎዳ የሰውነት አካሉን በሚገባ የሚያውቅ ከሆነ በዝርዝር መቀበል፣
ሐ. በማየት፣ በመስማትና በጠቅላላ የእንቅስቃሴ አካላቱ ላይ የሚሰማውን ጉዳት ማጣራት፣
መ. ያስታውከው እንደሆነና የመሳሰሉትን በማጣራት አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብ ለሚደረገው እርዳታ ተገቢውን መሰናዶ
ማሟላት ያስፈልጋል፡፡
 በአደጋ ወይም በህመም ምክንያት ብዙ ደም ሲፈስ እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ በተቻለ መጠን
የሚፈሰውን ደም ጥንቃቄ በተሞላበት አኳኋን እንዲቆም ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን በሚመለከት የሚከተሉትን ማወቅ
አስፈላጊ ነው፡፡
 በአደጋ ምክንያት ጉዳት ከተከሰተ በሚደማው ቁስል ላይ ማንኛውንም ንፁህ ጨርቅ ወይም ፓድ በሚደማው ቦታ ላይ ጫን
አድርጎ /ከአስፈላጊው ጥንቃቄ ጋር/ መያዝና ደሙ መፍሰሱ ሲቆም በፋሻ ጠበቅ አድርጎ ማሰር፣ ደሙ እየፈሰሰ ካስቸገረ ከላይ
በተጠቀሰው ዘዴ ደጋግሞ በመጠቀም ለማቆም ጥረት ማድረግ፣
 የራስ ቅል መድማት ካልሆነ በስተቀር ጉዳተኛውን አስተኝቶ የደማውን የአካል ክፍል ከፍ በማድረግ መደገፍ፣
 ጉዳት የደረሰበት ሰው ላይ የጠበቀ የልብስ ቁልፍ ወይም ቀበቶ ካለ ማላላት፣ የተጎዳውን ሰው ማጽናናትና በፍጥነት የህክምና
ዕርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ፣
በውስጥ አካል የመድማት ጉዳት ከደረሰ ተጎጅውን በማንጋለል ማሳረፍና ከሚያስፈልገው በላይ
አለማንቀሳቀስ፣ የሰውነት መንቀጥቀጥ /ሾክ/ እንዳይፈጠር ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ
በአስቸኳይ የሐኪም ዕርዳታ መፈለግ፣ በፍጥነት የህክምና ዕርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም
መውሰድ፣
በሰውነት ላይ የደረሰ ስብራት ምልክቶች
• ስብራት የደረሰበት ሰው ኃይለኛ ሕመም ይሰማዋል፣
• የተጎዳውን የሰውነት ክፍል ማንቀሳቀስ ያስቸግራል፣
• ስብራት የደረሰበት የሰውነት ክፍል ቅርፁን ይለውጣል፣
• እብጠትና አንድ አንዴም የመበለዝ አዝማሚያ ይታያል፡፡
የስብራት ዓይነቶችና የሚያስከትሏቸው ጉዳቶች
1.ዝግ ስብራት
ይህ የስብራት ዓይነት ከውጪ የመድማት/የመቁሰል/ ምልክት አይታይም፡፡
2. ክፍት ስብራት
ሌላው የስብራት ዓይነት ሲሆን ከላይ ያለው አካል ቁስል የተሰበረው አጥንት ድረስ ዘልቆ ይታያል፡፡
/በዚህ ወቅት ጀርሞች ወደተሰበረው አጥንትና አካል ክፍል ሊገቡ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ያሻል፡፡/
3. ኃይለኛ ወይም የተዘባረቀ ስብራት
የደም ስሮች ነርቭ ወይም ሌላ ህዋሳቶች በስብራቱ አካባቢ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡
በኃይለኛ ስብራት ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎች

ሀ. በጎድን ስብራት ሳቢያ ልብና ጉበት ይጎዳል፣


ለ. በራስ ቅል ስብራት ሳቢያ ደግሞ በአንጎል ላይ አደጋ ይከሰታል፣
ሐ. በደንደስ ስብራት የስሜት ስሮችና/ነርቮች/ መስመሮች ይጎዳሉ፣
መ. የዳሌ ስብራት በፊኛ ላይ አስቸጋሪ አደጋዎች ያስከትላል፡፡ ስለዚህ ተጊጂው
በአፋጣኝ የህክምና ዕርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ አስፈላጊ
ነው፡፡
ቃጠሎ
የቃጠሎ ዓይነቶች በሦስት የሚከፈሉ ሲሆን የሚወሰደው እርምጃም በሚከተለው መሰረት ሊሆን
ይገባል፡፡
1. ደረቅ ቃጠሎ
በእሣት፣ በኮረንቲና የጋለ ዕቃ በማንሳት የሚደርስ አደጋ ሲሆን የዚህ ዓይነት አደጋ የደረሰበት ሰው
ሲያጋጥም፦
• ሰውነትን አጥብቆ የያዙ ልብሶችን፣ ቀበቶ፣ አምባሮችንና ሰዓት የመሣሰሉትን በጥንቃቄ ማውለቅ፣
• በደረቅ አሳት የተቃጠለን ልብስ አለማውለቅ፣
• በቁስል ላይ ምንም ሳይጨመር በንፁህ ጨርቅ ላላ አድርጎ በመሸፈን ማሰር፣
• በተጎዳው ሰው ላይ ድንጋጤ እንዳይደርስ በተቻለ መጠን ማጽናናት፣
• በአፋጣኝ የህክምና ዕርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ናቸው፡፡
2. እርጥብ ቃጠሎ
የፈላ ውኃ፣ የፈላ ቅባትና የመሳሰሉት በሰውነት ላይ ሲፈሱ፦
• ጉዳት የደረሰበትን ሰው ቃጠሎ ከአለበት አካባቢ በፍጥነት ማራቅ፣
• ንፁህ የሆነ ቀዝቃዛ ውኃ በተጎዳው አካል ላይ በማፍሰስ ህመሙን ማስታገስ፣
• የፈላ ውኃ ወይም ቅባት የፈሰሰበት ልብስ ካለ በፍጥነትና በጥንቃቄ ማውለቅና የህክምና
ዕርዳታ እንዲያገኝ የተጎዳውን ሰው ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ናቸው፡፡
3. የመርዝ ቃጠሎ
በአሲድ ወይም በሚያቃጥል እንደ ጨው በመሳሰሉ ማዕድኖች መጎዳት ሲሆን፦
• በተቃጠለው አካል ላይ ብዙ ቀዝቃዛ ውኃ ማፍሰስ፣
• በመርዝ የራሰውን ልብስ ማውለቅ የሚገባ ሲሆን በዚህን ወቅት ለራስም ቢሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ
ማድረግ ያሻል፣
• የተጎዳውን ሰው የህክምና ዕርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ፦ በማንኛውም ዓይነት ቃጠሎ የደረሰበትን ቁስል ላይ ቅባት፣ ዘይትና የሚቀቡ ነገሮችን
ማድረግም ሆነ በቃጠሎ አደጋ ውኃ የቋጠረ ቆዳን ማፍረጥ ክልክል ነው፡፡
የሰውነት ቃጠሎ
1. የመጀመሪያ ደረጃ ቃጠሎ
የመጀመሪያ ደረጃ ቃጠሎ የሚባለው ጉዳቱ ውጨጫዊ ነው፡፡ይህ የቆዳችን ውጨጫዊ አካልየሚያጠቃቃጠሎ
ነው፡፡ህመም አለው ነገር ግን ውሃ የቋጠረ ቁስል የለውም፤ የተቃጠለውን የቆዳችንን አካል ስንነካው ነጣ ይላል፡፡
2. ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ
ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ የሚባለው ከቆዳም አልፎ መካከለኛ የቆዳ ክፍሌ ወይም ደርሚስ የሚባለውን
የጠቃል፡፡የህመም ስሜትና ማበጥ እንዲሁም ቅላት ይስተዋላል፡፡የተቃጠለው ቦታ ስንነካው ነዠዠጣ ይላል፤ውሀ
የቋጠረ ቁስል ይኖረዋል፡፡
3. ሶስተኛ ደረጃ ቃጠሎ
ሶስተኛ ደረጃ ቃጠሎ የሚባለው ሶስተኛውን የቆዳችንን ክፍል ያጠቃል፡፡ውጫዊና ውስጣዊ እንዲሁም ቆዳችን ላይ
የሚገብ የጸጉር ቀዳዳዎች እንዲሁም የላብ ነርቮችንና ግላዶችን ያጠቃል፡፡
1.HIV ኤድስን መከላከል የአሽከርካሪዎች ነው ሀ/ ኃላፊነት ለ/ ግዴታ ሐ/ ፈቃድ መ/ መልሱ የለም
2.ኤች∙ አይ∙ ቪ ኤድስ ከሚተላልፍባቸው መንገዶች መካከል ዋነኛው የቱ ነው?
ሀ/ በመነካካት ለ/ በግብረ-ስጋ ግንኙነት ሐ. ከእናት ወደ ልጅ መ. “ለ” እ “ሐ”
3.የ HIV ኤድስ መከላከያ መንገድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. መታቀብ ለ. መወሰን ሐ. መጠቀም መ. ሁሉም
4.ከሚከተሉት አንዱ HIV ኤድስን ለመከላከል አንጠቀምበትም
ሀ. መታቀብ ለ. መወሰን ሐ. መጠቀም መ. መልሱ የለም
5. ከሚከተሉት ውስጥ HIVN የማስፋፋት ከፍተኛ ድርሻ ያለው የትኛው ነው?
ሀ. አልኮል መጠጥ ለ. አደንዛዥ እጽ ሐ. ሀ እና ለ መ. መልሱ የለም
6. በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የ HIV ምርመራ የምናደርገው
ሀ. የ HIV መዛመቻ መንገዶች ብዙ በመሆናቸው ራስን ለማወቅ
ለ. ስለራሳችን በማወቅ ራሳችንና ሌሎችን እንድንጠብቅ ሐ. ሀ እና ለ መ. መልሱ የለም
7.ኤች አይ ቪ ኤድስ የምንከላከልበት መንገድ አንዱ የቫይረሱን ተጠቂዎችን በማግለል ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
8. ኤች አይ ቪ ኤድስን የመከላከያ መንገድ ኮንዶም መጠቀም ብቻ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
Thank you

You might also like