የሴቶች ዳሰሳ ሪፖርት (1)

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 24

በኢ.ፌ.ዴ.

ሪ የህገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሴቶችናወጣቶች አደረጃጀቶች


የስልጠና ፍላጎትና ክፍተት ዳሰሳ
ጥናት ሪፖርት

ግንቦት 2015 ዓ.ም


አዲስ አበባ

ክፍል አንድ

መግቢያ
1.1 የዳሰሳ ጥናቱ ዳራ

1
የህገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ንቃተ-ህገ-መንግስቱ ያደገና ሁለንተናዊ ተሳትፎ
የሚያደርግ ማህበረሰብ ለመገንባት በአዋጅ ቁጥር 1123/2011 ዓ/ም የተቋቋመ የስልጠናና ምርምር ማዕከል
ነው፡፡ማዕከሉ በአዋጅ ከተሰጡት ተግባራትና ሃላፊነቶች መካከል በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ
የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት አፈፃፀማቸውን መከታትና መደገፍ አንዱና ዋነኛ ተግባር ነው።ስለሆነም
የህገመንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በቀጣዩ የበጀት አመት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው
የስልጠና ተግባራት መካከል በሴቶችና ወጣቶች ላይ ነው ለዚህም ምክንያቱ በሀገራችን ውስጥ የሚገኙ
ከግማሽ በላይ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ሴቶችና ወጣቶች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሴቶችና
ወጣቶች በሀገራችን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፣ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍንና የዲሞክራሲና የተቋማት
ስረዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የአስተምህሮ ማዕከሉ በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ዙሪያ ለሴቶችና ወጣቶች ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በተከታታይ ለመስጠት
ያስችለው ዘንድ ይህንን የስልጠና ዳሰሳና ፍላጎት በማዘጋጀት ወደ ተግባር ተሸጋግሯል።

ስልጠናውን ለማዘጋጀት በሀገራችን የሚገኙ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶችን በመጠቀም አሁን ያሉበት
የግንዛቤ ደረጃ በተለይም የእውቀት፣አመለካከትና ክህሎት በመለየት ስልጠና ለማዘጋጀት የዳሰሳ ጥናት
ተደርጓል። የዳሰሳ ጥናቱም በሀገራችን የሚገኙ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት የሚሳተፉ የህብረተሰብ
ክፍሎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸውን የእውቀትና አመለካከት ክፍተት ለይቶ ለማወቅና
ክፍተቶችንም በስልጠና ሊሻሻሉ እንደሚችሉ በግልፅ ያመላከተ ነው ስለሆነም የጥናቱም ዝርዝር ውጤትም
እንደሚከተለው ቀርቧል።

1.2. ዓላማ

የዚህ የስልጠና ፍላጎትና ክፍተት ዳሰሳ ጥናት ዋና ዓላማ በሀገራችን የሚገኙ ሴቶችና ወጣቶች በህገ
መንግስትና በፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸውን የእውቀት፣ የአመለካከትና ክህሎት ችግሮችን በመለየት ስልጠና
በመስጠት አሁን ያሉበትን እውቀትና ግንዛቤ ደረጃ ከፍ ማድረግ ነው፡፡

1.3 የዳሰሳ ጥናት አስፈላጊነት

2
የዚህ የስልጠና ፍላጎትና ክፍተት ዳሰሳ ጥናት ዋና አስፈላጊነቱ የህገ መንግሰትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ
ማዕከል በሀገራችን የሚገኙ የተለያዩ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ያሉበትን
የእውቀት፣ ግንዛቤና አመለካከት ደረጃ በመለየት ለአደረጃጀቱ ሀላፊዎችና አባላት ስልጠና ማዘጋጀት
ስላስፈለገ፣

1.4 የዳሰሳ ጥናቱ ወሰን

የዚህ የስልጠና ፍላጎትና ክፍተት ዳሰሳ ጥናት ዋናው ትኩረቱ በሀገራችን የሚገኙ የሴቶችና ወጣቶች
አደረጃጀቶች ሃላፊዎችና አባላት በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸውን የእውቀት፣ የአመለካከትና
ክህሎት መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

1.5 የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ

ይህ የስልጠናና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ በሀገራችን በሚገኙ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት ሀላፊዎችና
አባላት በህገ መንግስቱና በፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸውን የእውቀት፣ የአመለካከትና ክህሎት ክፍተቶችን
መጠናቸውና አይነታቸውን ለማወቅና ለመረዳት ቅይጥ የጥናት ዘዴ ተመርጧል ፡፡ አይነታዊ የጥናት ዘዴ
ለጥናቱ የሚረዱ መረጃዎችን አይነታዊና ገላጭ በሆነ መልኩ ለማሰባሰብም ሆነ መረጃዎችን አይነታዊ በሆነ
መልኩ ለመተንተን የሚያስችል ዘዴ ሲሆን መጠናዊ ደግሞ በተደራጁ መጠይቆች የተሰበሰቡ መረጃዎችን
በቁጥር ለመግለፅ የሚረዳ ነዉ፡፡

1.6 የአደረጃጀቶቹ አመራረጥ

ለዚህ የስልጠናና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት የተመረጡት አደረጃጀቶች እንደሚከተለው ይሆናል። እነዚህም
በኢትዮጵያ የሚገኙ የወጣቶች ፌዴሬሽን፣ የሴቶች ፌዴሬሽን ፣የወጣቶች ሊግና የሴቶች ሊግ በተመሳሳይ
ደረጃ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በድሬደዋ፣ በደቡብ ህዝቦች ክልል፣በሲዳማ ክልልና በኢትዮጵያ
ደቡብ ምዕራብ ክልል ናቸው። እነዚህ አደረጃጀቶች የሚገኙበት ክልሎች የተመረጡበት ምክንያት ለህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ባለሞያዎች መረጃውን ለማሰባሰብ ቅርበት ስላላቸው ነው።

1.7 የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች

ለዚህ ለስልጠና ፍላጎትና ክፍተት የዳሰሳ ጥናት በመረጃ መሰባሰቢያ መሳሪያነት የተመረጡ አደረጃጀቶች
የሚሰሩ ሃላፊዎችና አባላት የሚሞላ የፁሑፍ መጠይቅ ነው። የተዘጋጀው መጠይቅም ዓይነታዊና መጠናዊ
የሆኑ መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው። በናሙናዉ ከተመረጡ ማህበራት ምላሽ
እንዲሰጡ የተመረጡ ተሳታፊዎች የአደረጃጀቱ አባላት፣ የስልጠና ክፍል ተጠሪዎች ናቸው፡፡መረጃውን
ለማሰባሰብ ለእያንዳንዳቸው ማለትም ለ 48 ተቋማት ሁለት የጽሁፍ መጠይቆቹ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን
ከእነዚህ ተቋማት 96 መጠይቆች በአግበቡ የተሰበሰቡና የተተነተኑ ናቸው። በአጠቃላይ መረጃዎቹ ከተሰባሰቡ
በኋላ የመረጃ መመዝገቢያ ፎርማት በማዘጋጀትና በመመዝገብ የተለያዩ የትንተና ዘዴዎችን ማለትም

3
የስታስቲክስ ስልቶችን በመጠበቅም ማለትም የተገኙ መረጃዎች በሠንጠረዥ በማስቀመጥ ፣አማከዮችን
በመጠቀም እንዲሁም መቶኛ በመጠቀም መረጃዎቹ ትንተና ተደርጓል ፡፡

1.8 የዳሰሳ ጥናቱ አደረጃጀት

የዚህ የስልጠና ፍላጎትና ክፍተት የዳሰሳ ጥናቱ ሶስት ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡የመጀመሪያዉ ክፍል
መግቢያ፣የጥናቱ ዓላማና ዘዴዎች የተካተቱበት ነው፡፡ሁለተኛው ክፍል የመረጃዎች ትንተና የተካሄደበት ነው
ሶስተኛዉ ክፍል የተገኙ ውጤቶችን የያዘ ነው፡፡

ክፍል ሁለት የመረጃ ትንተና

2.1. የአጠቃላይ መረጃዎች ትንተና

2.1.1 አደረጃጀቱ የሚንቀሳቀሱት እንደ፡፡

ተ.ቁ የተቋማቱ መገኛ ብዛት መቶኛ

1 ፌዴራል 5 10.4%

2 ክልል 36 75%

3 ከተማ/ ሌላ 7 19.4%

ድምር 48 100%

4
ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት አደረጃጀቶቹ የሚንቀሳቀሱት 10.4% እንደ ፌዴራል የሚንቀሳቀሱ
አደረጃጀቶች ናቸው። 75% የሚሆኑ አደረጃጀቶች ደግሞ በክልል ደረጃ የሚንቀሳቀሱ አደረጃጀቶች
ናቸው። 19.4% የሚሆኑ አደረጀጀቶች ደግሞ እንደከተማ ወይም ዞን የሚንቀሳቀሱ አደረጃጀቶች
ናቸው። በዚህም አብዛኛው መረጃ የተሰበሰበው በክልል መሆኑን ያሳያል።

2.1.2. በአደረጃጀቱ ውስጥ ያለዎት የቆይታ ጊዜ በተመለከተ

ተ.ቁ ያገለገሉበት ጊዜ ቆይታ ብዛት መቶኛ

1 ከ 1-5 ዓመት 63 65.6%

2 ከ 6-10 ዓመት 22 22.9%

3 ከ 11-15 ዓመት 6 6.2%

4 ከ 16-20 ዓመት - -

5 ከ 21 ዓመት በላይ 5 5.2%

ድምር 96 100%

ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት 65.6% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ያገለገሉበት የቆይታ ጊዜ ከ 1-5
ዓመት ሲሆን። 22.9% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ያገለገሉበት ጊዜ ከ 6-10 ዓመት ነው። 6.2%
የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ያገለገሉበት የጊዜ ቆይታ ከ 11-15 ዓመት ሲሆን 5.2% የሚሆኑ
ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ከ 21 ዓመት በላይ ያገለገሉ ናቸው ፡፡

2.1.3. የምላሽ ሰጪዎች የፆታ ሁኔታ

ተ.ቁ ፆታ ብዛት መቶኛ

1 ሴት 49 51.0%

2 ወንድ 47 48.9%

ድምር 96 100%

5
የምላሽ ሰጪዎች የፆታ ሁኔታ በተመለከተም 48.9% ወንዶች ሲሆኑ 51.0% ደግሞ ሴቶች
ናቸው።ይህም ከባለፉት አመታት ሲነፃፀር የሴቶች ተሳትፎ እጅግ ዝቅተኛ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ
የሴቶች ተሳትፎ ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል።

2.1.4. የምላሽ ሰጪዎች የዕድሜ ሁኔታ

ተ.ቁ የመላሾች ዕድሜ ብዛት መቶኛ

1 ከ 18-29 አመት 31 32.2%

2 ከ 30-35 አመት 44 45.8%

3 36-40 አመት 14 14.5%

4 ከ 40 አመት በላይ 7 7.2%

ድምር 96 100%

መረጃዉ የሚያመለክተው 32.2% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች እድሚያቸው ከ 18-29 አመት ሲሆን።
48.8% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች እድሚያቸው ከ 30-35 አመት ነው 14.5% የሚሆኑ ምላሽ
ሰጪዎች ደግሞ እድሚያአው ከ 35—40 አመት የሚሆኑ ናቸው። 7.2% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች
ደግሞ እድሚያቸው ከ 40 ዓመት በላይ ነው፡፡

2.1.5. የምላሽ ሰጪዎች የትምህርት ደረጃ

ተ.ቁ የትምህርት ደረጃ ብዛት መቶኛ

1 ከ 10 ኛ/12 ኛ ክፍል 2 2.0%

2 የኮለጅ ዲፕሎማ 8 8.3%

3 የመጀመሪያ ዲግሪ 57 59.3%

4 የሁለተኛ ዲግሪ 19 19.7%

5 ሶስተኛ ዲግሪ - 0%

6 ድምር 96 100%

6
ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት 2.0% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች የትምህርት ደረጃቸው ከ 10 ኛ እስከ 12 ክፍል
ደረጃ ሲሆን ።8.3% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች የትምህርት ደረጃቸው የኮሌጅ ዲፕሎማ ነው። መረጃዎቹ
እንደሚያመለክቱት 59.3% የሚሆነዉ ምላሽ ሰጪ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸዉ መሆናቸዉንና ከፍተኛ ቁጥር
ይይዛል ነዉ፡፡19.7% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ሲሆኑ ይህም አደረጃጀቶቹ
በተማረ የሰው ሃይል እየተመሩ መሆኑን ያመላክታል፡፡

2.2.የህገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ጋር የተያያዙ መጠይቆች

2.2.1 በአደረጃጀቱ ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ስልጠና ስለመውሰድ፡፡

ተ.ቁ የቀረበው ምርጫ የተሰጠው ምልሽ ብዛት በመቶኛ

1. አዎ ወስጃለሁ 24 25%

2. ወስጄ አላውቅም 72 75%

መጠይቁን ከሞሉ ባለሙያዎች መካከል 25% የሚሆኑት ምላሽ ሰጭዎች ባሉበት አደረጃጀት ውስጥ
በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ላይ ያተኮረ ስልጠና የወሰዱ ናቸው። ይህም ማለት በቀጥታም
ይሁን በተዘዋዋሪ ስለህገመንግስት እንዲሁም ስለፌዴራሊዝም ግንዛቤ እንዳላቸው ያሳያል። 75%
የሚሆኑ ምልሽ ሰጭዎች በሰጡት መረጃ መሰረት ምንም አይነት ስልጠና በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ዙሪያ ስልጠና ያልወሰዱ መሆኑን ያሳያል ይህ ማለት አባላቱ በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ አናሳ መሆኑና ይህንንም የግንዛቤ ክፍተት ለመቅረፍ ስልጠና
ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማል።

2.2.2. ሴቶችና ወጣቶች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዘሪያ ያላቸው የእውቀትና ግንዛቤ ደረጃ ፡፡

ተ.ቁ የቀረበው ምርጫ ምላሽ የተሰጠውብዛት በመቶኛ

1. በጣም ከፍተኛ 8 8.3%

2. ከፍተኛ 7 7.2%

3. መካከለኛ 31 32.2%

4. ዝቅተኛ 41 42.7%

5. በጣም ዝቅተኛ 9 9.3%

6. ድምር

7
ከላይ በቀረበው ጥያቄ መሰረት ምላሽ የሰጡ ሰዎች መካከል 8.3% የሚሆኑት የአደረጃጀቱአባላት በህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የግንዛቤ ደረጃ በጣም ከፍተኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።በሌላ
መልኩ 7.2% የሚሆኑ ምላ ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የእውቀት ደረጃ
ከፍተኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። 32.2%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ስለህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ያላቸው የግንዛቤ ደረጃ መካከለኛ በማለት መልሰዋል።በአንፃሩ ይህ መጠይቅ ከቀረበላቸው
ባለሞያዎች መካከል 42.7% የሚሆኑ ምላሽ ሰጭዎች ባሉበት አደረጃጀት ውስጥ ስለህገመንግስትና
ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የግንዛቤ ደረጃ ዝቅተኛ በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል። 9.3%የሚሆኑ
ምላሽ ሰጪዎች በህገመንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ በጣም ዝቅተኛ ነው።በአጠቃላይ
ከዚህ መረጃ ለመረዳት እንደሚቻለው ከግማሽ በላይ የሚሁኑ የማህበሩ አባላት ስለህገመንግስትና
ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ደረጃ ዝቅተኛ እንደሆነ ነውይህም በአደረጃጀቱ ውስጥ የአቅም
ግንባታ ስልጠና ባለመኖሩ ለማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች የእውቀት፣ የአመለካከትና የክህሎት ችግሮች
እንዲፈጠር ያደርጋል።

2.2.3. ስለ ህገመንግስትና ፌዴራሊዝም ግንዛቤ ከማሰፋት አንፃር የአደረጃጀቱ ተግባር ያለበት ደረጃ

ተ.ቁ የእርካታ ደረጃ ብዛት በመቶኛ

1 በ/ከፍተኛ 7 7.2%

2 ከፍተኛ 19 19.7%

3 መካከለኛ 38 39.5%

4 ዝቅተኛ 24 25%

5 በ/ዝቅተኛ 8 8.3%

6 ምንም ግንዛቤ የሌላቸው 96 100%

ከላይ በቀረበው ጥያቄ መሰረት ይህንን መጠይቅ ከሞሉት ባለሞያዎች መካከል 7.2% የሚሆነው ምላሽ
ሰጭዎች መካከል አደረጃጀታቸው በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ለማህበራቱ አባላትና ደጋፊዎች
ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር ያሉበት ደረጃ በጣም ከፍተኛ በማለት ገልፀዋል።19.7%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች
ደግሞአደረጃጀታቸው በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ለማህበራቱ አባላትና ደጋፊዎች ግንዛቤ
ከመፍጠር አንፃር ያሉበት ደረጃ ከፍተኛ በማለት ገልፀዋል። 39.5% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ

8
አደረጃጀታቸው በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ለማህበራቱ አባላትና ደጋፊዎች ግንዛቤ ከመፍጠር
አንፃር ያሉበት ደረጃ መካከለኛ በማለት ገልፀዋል። 25% የሚሆነው ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ደግሞ
አደረጃጀታቸው በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ለማህበራቱ አባላትና ደጋፊዎች ግንዛቤ ከመፍጠር
አንፃር ያሉበት ደረጃ ዝቅተኛ በሚል ደረጃ ምልሽ ሰጥተዋል። ሌላው 8.3% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች
አደረጃጀታቸው በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ለማህበራቱ አባላትና ደጋፊዎች ግንዛቤ ከመፍጠር
አንፃር ያሉበት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ በማለት ገልፀዋል። በአጠቃላይ ምንም እንኳን አደረጃጀቶቹ
የሚገኙበት ደረጃ በአብዛኛው መካከለኛ ቢሆንም አደረጃጀቶቹ ካላቸው ሰፊ የሰው ሀይል ብዛት ተደራሽ
ከመሆን አንፃር ብዙ ተግባራት መሰራት እንዳለባቸው ይጠቁማል

2.2..4.በአደረጃጀቱ ውስጥ የሀገራችንን ህገ መንግስትና ፌዴራላዊ ስረዓት ከመረዳት አንፃር

ተ.ቁ የዕዉቀት ግንዛቤ ደረጃ ብዛት በመቶኛ

1 በ/ከፍተኛ 6 6.2%

2 ከፍተኛ 19 19.7%

3 መካከለኛ 43 44.7%

4 ዝቅተኛ 25 26.0%

5 በ/ዝቅተኛ 3 3.1%

6 ድምር 96 100%

ከላይ በቀረበው ጥያቄ መሰረት ይህንን መጠይቅ ከሞሉት ባለሞያዎች መካከል 6.2% የሚሆኑ ምላሽ
ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የእውቀት ወይም የመረዳት ደረጃ በጣም
ከፍተኛ በሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 19.2% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም
ዙሪያ ያላቸው የግንዛቤ ወይም የመረዳት ደረጃ ከፍተኛ በሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 44.7% የሚሆኑ
ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የግንዛቤ ወይም የመረዳት
ደረጃ መካከለኛ በሚል መልስ ሰጥተዋል። 26.0% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የእውቀት ወይም የግንዛቤ ደረጃ ዝቅተኛ በሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
3.1% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ መንግስት ዙሪያ ያላቸው የእውቀት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ
በሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ ከላይ ለመረዳት እንደሚቻለው ከሆነ አደረጃጀቶቾ በህገ

9
መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ አሁን ያላቸው የግንዛቤ ወይም የመረዳት ደረጃ በአብዛኛው
መካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው። ይህ ማለት አስተምህሮ ማዕከሉ በቀጣይ የግንዛቤ
ማስጨበጫዎችን ለአደረጃጀቹ በመስጠት አሁን ያለውን ክፍተት ማሻሻል ያስፈልጋል።

2.2.5.በሀገራችን በተለያዩ መልኩ በሚኖሩ ውይይቶችና የሃሳብ ልውውጦች አብዛኛውን ጊዜ


እንደሚሰማው የፌዴራል ስረዓት ባህሪ ያለመረዳትና በተሳሳተ መልኩ ማየት ይታያል ለዚህም
ምክንያቱ በሰንጠረዥ እንደሚከተለው ይቀርባል

ተ. ቁ የቀረቡት ምሳሌዎች የምላሾች ብዛት የተመረጠው ደረጃ በመቶኛ

1. የስነ ዜጋና ስነምግባር ት/ት ላይ 15 1 21.7%


ጉዳዮችን በተገቢው አለመካተት
2. ከተግባራዊነቱ ጋር የተያያዙ የሚታዩ 11 1 15.9%
ችግሮች
3. ሥረዓቱን ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት 14 1 20.2%
ጋር በማያያዝ ስረዓቱ በበቂ እውቀት
ላይ እንዲመሰረት አለመፈለግ
4. ሥረዓቱን በተገቢው ሳይገነዘቡ 9 1 13.0%
ከመጀመሪያው የመጥላት
5. በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ 17 1 24.6%
ተከታታይ ሳይንሳዊ የሆነ ንድፈ
ሀሳብን ከተግባር ጋር ያቀናጁ
ስልጠናዎችን ያለመስጠት
6. ሥረዓቱ ከሀገራችን ማህበራዊና - 1 0%
ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ የተሻለ
መሆኑን አለመረዳት
7. ሥረዓቱን በትክክለኛው መንገድ 3 1 4.3%
ተግባራዊ ለማድረግ ያለው ቁርጠኝነት
አናሳ መሆን

8. ድምር 69 1 100%

9.

በሀገራችን በተለያዩ መልኩ በሚኖሩ ውይይቶችና የሃሳብ ልውውጦች አብዛኛውን ጊዜ እንደሚሰማው


የፌዴራል ስረዓት ባህሪ ያለመረዳትና በተሳሳተ መልኩ ማየት ይታያል ለዚህም ምክንያቱ በቅደም

10
ተከተል እንደሚከተለው ይቀርባል 24.6%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም
ዙሪያ ተከታታይ ሳይንሳዊ የሆነ ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር ያቀናጁ ስልጠናዎችን ያለመስጠት
የሀገሪቱን ህገመንግስትና ፌዴራሊዝም ያለመረዳት ችግር ነው ብለው ያስባሉ። በመቀጠል
21.7%የሚሆኑ ምላሸ ሰጪዎች የስነ ዜጋና ስነምግባር ት/ት ላይ ጉዳዮችን በተገቢው ሁኔታ
አለመካተት በተለይ ወጣቶችን የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝምን ፅንሰ ሀሳብ በተገቢው ሁኔታ በስፋት
አለመዳሰሱ እንደምክንያት ቀርበዋል። ሌላው 20.2% የ ሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ሥረዓቱን
ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማያያዝ ስረዓቱ በበቂ እውቀት ላይ እንዲመሰረት አለመፈለግ ህገ
መንግስቱን ያለመረዳት እንደምክንያትነት ቀርበዋል። 15.9%የሚሆኑ ምላሸ ሰጪዎች ከተግባራዊነቱ
ጋር የተያያዙ የሚታዩ ችግሮችን እንደምክንያትነት አስቀምጠዋል።13.0%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች
ደግሞ ሥረዓቱን በተገቢው ሳይገነዘቡ ከመጀመሪያው የመጥላት የፌዴራል ስረዓቱን ያለመረዳት
እንደምክንያትነት ይጠቅሳሉ። በመጨረሻም 4.3%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ሥረዓቱን በትክክለኛው
መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ ያለው ቁርጠኝነት አናሳ መሆን እንደምክንያትነት ያስቀምጣሉ።

2.2.6. በአደረጃጀት ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ በቂ ግንዝቤ አለመኖር በሀገሩቱ ላይ
የሚያመጣው ተፅዕኖ

ተ.ቁ የአመለካከት ደረጃ ብዛት በመቶኛ

1 በ/ከፍተኛ 51 53.1%

2 ከፍተኛ 29 30.0%

3 መካከለኛ 7 7.2%

4 ዝቅተኛ 2 2.0%

5 በ/ዝቅተኛ 7 7.2%

6 ድምር 96 100%

ከላይ በቀረበው መጠይቅ መሰረት 53.1% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ትክክለኛ ግንዛቤ አለመኖር በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በጣም
ከፍተኛ ተፅእኖ አለው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። 30.0% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ትክክለኛ ግንዛቤ አለመኖር በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ
ከፍተኛ ተፅኖ አለው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 7.2% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ትክክለኛ ግንዛቤ አለመያዝ ወይም አለመኖር በሀገሪቱ አጠቃላይ
እንቅስቃሴ ውስጥ ይለውደረጃ መካከለኛ ደረጃ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። 2.0% የሚሆኑ ምላሽ
ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ትክክለኛ ግንዛቤ አለመኖር በሀገሪቱ ላይ ምንም ጉዳት
አያስከትልም በማለት ዝቅተኛ ደረጃ በሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 7.2% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ

11
በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ትክክለኛ ግንዛቤ አለመኖር በሀገሪቱ ላይ ምንም ጉዳት
አያስከትልም በማለት በጣም ዝቅተኛ በሚል ደረጃ ምላሽ ሰጥተዋል።
2.2.7. በአደረጃጀቱ ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ ሀገራዊ አንድነት ሊያመጡ
የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያሎት ክህሎት ደረጃ.

ተ.ቁ የአመለካከት ደረጃ ብዛት በመቶኛ

1 በ/ከፍተኛ 13 13.5%

2 ከፍተኛ 22 22.9%

3 መካከለኛ 58 60.4%

4 ዝቅተኛ 6 6.2%

5 በ/ዝቅተኛ 7 7.2%

6 ድምር 96 100%

ከላይ በቀረበው መጠይቅ መሰረት 13.5% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ሀገራዊ አንድነት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያላቸው
የክህሎት ደረጃ በጣም ከፍተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 22.9% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች
በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ሀገራዊ አንድነት ሊያመጡ የሚችሉ
ስራዎችን ለመስራት ያላቸው የክህሎት ደረጃ ከፍተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። 60.4% የሚሆኑ
ምላሽ ሰጪዎች በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ሀገራዊ አንድነት
ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያላቸው የክህሎት ደረጃ መካከለኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
6.2% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች
ሀገራዊ አንድነት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያላቸው የክህሎት ደረጃ ከፍተኛ የሚል
ምላሽ ሰጥተዋል። 7.2% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ሀገራዊ አንድነት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያላቸው የክህሎት
ደረጃ በጣም ከፍተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት ከግማሽ
በላይ የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ ለሚነሱ ሃሳቦች ሀገራዊ
አንድነት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያላቸው የክህሎት ደረጃ መካከለኛ የሚል ምላሽ
ሰጥተዋል።

12
2.2.8.በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ ተያይዞ ለሚነሱ ችግሮች ለመፍታት ያላቸው
የእውቀት ደረጃ

ተ.ቁ የመጠይቁ ምርጫ ምላሽ ሰጪዎች በመቶኛ


ብዛት

2. በ/ከፍተኛ 15 15.6%

4. ከፍተኛ 21 21.8%

5. መካከለኛ 36 37.5%

6. ዝቅተኛ 11 11.4%

7. በ/ዝቅተኛ 3 3.1%

8. ድምር 96 100%

ከላይ በቀረበው መጠይቅ መሰረት 15.6% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በሀገሪቱ ውስጥ
በተለያዩ አካባቢዎች ከህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን
ለመፍታት የአደረጃጀቱ አባላት ያላቸው የእውቀት ደረጃ በጣም ከፍተኛ ነው በማለት
ምላሽ ሰጥተዋል ። 21.8% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ መንግስትም ሆነ
በፌዴራሊዝም ዙሪያ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የአደረጃጀቱ አባላት
ያላቸው የእውቀት ደረጃ ከፍተኛ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።37.5% የሚሆኑ ምላሽ
ሰጪዎች በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ከህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጋር ተያይዞ
የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የአደረጃጀቱ አባላት ያላቸው የእውቀት ደረጃ መካከለኛ ነው
በማለት ምላሽ ሰጥተዋል ።11.4%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ
አካባቢዎች ከህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት
የአደረጃጀቱ አባላት ያላቸው የእውቀት ደረጃ ዝቅተኛ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል
።3.1%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ከህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የአደረጃጀቱ አባላት ያላቸው
የእውቀት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።ከዚህ ለመረዳት
እንደሚቻለው አብዛኛው ምላሽ ሰጪዎች በሀገሪቱ ለሚነሱ ችግሮች ለመፍታት ያላቸው
ክህሎት መካከለኛ እና ከዚያ በታች ናቸው።
2.2.9 በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ ለአባለትና ደጋፊዎች ስልጠና
ለመስጠት ያላቸው ክህሎት ደረጃ

13
ተ.ቁ የምርጫው አይነት የመልስ ሰጪዎች በመቶኛ
ብዛት

1 በ/ከፍተኛ 11 11.4%

2 ከፍተኛ 19 19.7%

3 መካከለኛ 32 33.3%

4 ዝቅተኛ 29 30.2%

5 በ/ዝቅተኛ 5 5.2%

6 ድምር 96 100%

ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት 11.4% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት
ያላቸው የክህሎት ደረጃ በጣም ከፍተኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።19.7% የሚሆኑ ምላሽ
ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች
ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት ያላቸው የክህሎት ደረጃ ከፍተኛ በማለት ምላሽ
ሰጥተዋል።33.3%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ
በማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት ያላቸው የክህሎት ደረጃ መካከለኛ
በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።30.2%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም
ጉዳዮች ዙሪያ በማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት ያላቸው የክህሎት
ደረጃ ዝቅተኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።5.2%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት
ያላቸው የክህሎት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ አብዛኛው
የማህበራቱ አባላት ስልጠና የማዘጋጀት ክህሎት መካከለኛና ዝቅተኛ ስለሆነ የአስተምህሮ
ማዕከሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራ የተሻለ ውጤት ይገኛል።

2.2.10 በእርስዎ አደረጃጀት ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ


በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት የእውቀት ደረጃ

ተ.ቁ የምርጫው አይነት የመልስ ሰጪዎች በመቶኛ


ብዛት

14
1 በ/ከፍተኛ 17 17.7%

2 ከፍተኛ 22 22.9%

3 መካከለኛ 37 38.5%

4 ዝቅተኛ 18 18.7%

5 በ/ዝቅተኛ 7 7.2%

6 ድምር 96 100%

ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት 17.7%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና


ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ
የመስጠት የእውቀት ደረጃ በጣም ከፍተኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።22.9%%የሚሆኑ
ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበረሰቡ ውስጥ
የሚነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት የእውቀት ደረጃ ከፍተኛ በማለት ምላሽ
ሰጥተዋል።38.5%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ
በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት የእውቀት ደረጃ
መካከለኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።18.7%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ
የመስጠት የእውቀት ደረጃ ዝቅተኛ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።7.2%የሚሆኑ ምላሽ
ሰጪዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ
ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት የእውቀት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ በማለት ምላሽ
ሰጥተዋል። በአጠቃላይ አብዛኛው የአደረጃጀቱ አባላትና ደጋፊዎች በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ
የመስጠት የእውቀት ደረጃቸው መካከለኛና ዝቅተኛ ነው በመሆኑም የአስተምህሮ ማዕከሉ
ለአደረጃጀቱ አባላትና ደጋፊዎች ተከታታይነት ያለው ስልጠና በመስጠት ያለውን
የእውቀትና አመለካከት ችግር ማሻሻል አስፈላጊ ነው።
2.2.11.ሴቶችና ወጣቶች በህገመንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ስራዎችን ለመስራት
የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተመለከተ በአጠቃላይ ከምላሽ ሰጪዎች መካከል የሚከተሉትን
ዋና ዋና ችግሮችን አንስተዋል
 የማህበረሰቡ አመለካከት ህገ መንግስቱ የአንድ ወገን አድርጎ መቁጠር
 በቂ እውቀት ያለውና ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱ አሰልጣኞች ወይም ባለሞያ
አለመኖር

15
 ጥቅሙንና አስፈላጊነቱን በአግባቡ ያለመረዳት
 ስለ ህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ ለመረዳት ፍላጎት አለመኖር
 የባለሙያ እጥረት የእውቀት ማነስና የሎጂስቲክ ችግሮች ናቸው
 ወጣቶችን በህገ መንግስት አወጣጥና አካሄድ ላይ እንዲሁም በሀገሪቱ ማህበራዊ
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በበቂ ደረጃ አለማሳተፍ ወዘተ

2.2.12 በአደረጃጀቱ ውስጥ በፌዴራሊዝምና በህገ መንግስት አስተምህሮ ዝግጅት
የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚረዱ የመፍትሄ ሃሳቦች ምን ምን እንደሆኑ
 ህገ መንግስቱ ከፖለቲካ የፀዳ መሆኑን ለማህበረሰቡ ማሳየት መቻል
 አደረጃጀቶች በራሳቸው ነፃና ከፖለቲካ ነፃ በመሆን በተለያዩ ስልጠናዎች ማብቃት
 ከላይ ከፌዴራሊዝም ጀምሮ እስከ ታች ወረዳ ድረስ ያሉትን መዋቅሮች
በመጠቀም ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጥ
 በትምህርት ስራ ማካተት ወዘተ ናቸው
2.2.13 የዜጎችን ህገ መንግስታዊና ፌዴራላዊ አስተሳሰብን ለመገንባት ማዕከሉ በምን በምን
ጉዳዮች ላይ ቢያተኩር መልካም ነው ብለው ያስባሉ
 በስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ውስጥ ማካተት
 በፌዴራሊዝም ዙሪያ ተከታታይነት ያለው ስራ ወይም ስልጠና መስጠት
 በተማሪዎችና በመምህራን ላይ ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጥ
 ቅንጅታዊ አሰራሮችን መዘርጋት ወዘተ በዋናነት የተጠቀሱ ናቸው

2.2.14 የህገ መንግስትና ፌዴራላዊ አስተምህሮ ማዕከሉ ለማሳፋፋት የሚረዱ ተጨማሪ
አስተያየቶች ካሉ
 ስልጠናዎችን እስከ ታችኛው የማህበረሰብ ክፍል ቢሰጥና ግንዛቤው ቢፈጠር
 የሲፊክ ማህበራት አደረጃጀቶች ጠንካራ ቁመና እንዲኖራቸው ማድረግ ቢቻል
 በካሪክለሙ ውስጥ ተካቶ እንደ እንድ የትምህርት ዓይነት ቢሰጥ
 በክልል ተጨማሪ ማዕከላት ቢከፈቱ
 ለሴቶችና ወጣቶች ልዩ ስልጠና ቢሰጥ
2.2.15 በአደረጃጀቱ ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴዳሊዝም ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት
የተቋቋመ የስልጠና ክፍል ካለ
አብዛኛዎቹ አደረጃጀቶች የራሳቸው የሆነ የስልጠና ክፍል ባይኖራቸውም ጥቂትየሚባሎ
አደረጃጀቶች ግን አላቸው ለምሳሌ
 ኮሚኒኬሽና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ
 የፖለቲካ ዘርፍ ወዘተ የሚል ስያሜ አላቸው
16
2.2.16. ወጣቶች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ስረዓትን በተመለከተ የሚያነሱት ዋና ዋና
ችግሮች ሲጠቅሱ
 የፌዴራል ስረዓቱ ላይ ፍታዊነት መጓደል
 ህገ መንግስቱን መጠራጠር ገንጣይ ነው ማለት
 ብሄረሰብ ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ፌዴራላዊ ስረዓት ልዩነት መፍጠሩ
 የፌዴራሊዝም ስረዓቱ የወሰን አከላለል ማንነትን የሚጨፈልቅ ነው
 የህገ መንግስት ማሻሻል ጥያቄ
 እኔ አውቅልሀሉ የፌዴራል ስረዓት መሰጠሩ
 የባንዲራ ጥያቄ
 የብሄር ፌዴራሊዝም ስለሆነ
 ህገ መንግስት ታማኝ አለመሆን
 ህገ መንግስቱ በመንግስት ይጣሳል መሆኑን
 ትክክለኛ ፌዴራሊዝም ስረዓት ያለመፈፀም ችግር
 የህገ መንግስት ማሻሻያ ይሰራ
 ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል አለመኖር
 ወጣቶች በአካባቢያቸው የተሟላ አገልግሎት ማግኘት ይፈላጋሉ ወዘተ

ወጣቶች በኢትዮጵያ ፌዴራል ስረዓት በተመለከተ ዋና ዋና ችግሮች ናቸው ብለው ያስቀመጡትን


ችግሮች በሚከተለው ሰንጠረዥ ቀርቧል

ተ.ቁ ችግሮቹ የተዘረዘሩበት ዘርፍ የመራጮች ብዛት በመቶኛ

1 ማህበራዊ ዘርፍ 16 20.5%

2 ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ 22 28.2%

3 ፖለቲካዊ ዘርፍ 16 20.5%

4 የሀገረ መንግስት ዘርፍ 5 6.4%

5 የፌዴራላዊ አፈፃፀም ዘርፍ 19 24.3%

6 ድምር 78 100%

17
በኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች በፌዴራሊዝም ስረዓት ጋር ተያይዞ ከሚያነሱት ችግሮች ውስጥ 28.2%
የሚሆኑ ምላሽ ስጪዎች ከኢኮኖሚ ዘርፍ ጋር ያያይዙታል። ይህ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ
ወጣቶች ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ጋር በተገናኘ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት
ጋር በተገናኘ ችግሮችን ያነሳሉ። 24.3% የሚሆኑ ማላሽ ሰጪዎች ደግሞ የፌዴራሊዝም ዋና ችግሩ
ከአፈፃፀም ዘርፍ ጋር ይመድቡታል ይህ ማለት ሀቀኛና እውነተኛ ፌዴራሊዝም አለመኖር በህገ
መንግስት ውስጥ የተደነገገው ፌዴራሊዝምና መሬት ላይ ያለው አንድ አለሆን በጥቅሉ የአፈፃፀም
ችግሮችን ይጠቅሳሉ። ሌላው እኩል ምላሽ ያገኙት 20.5%ማህበራዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው።
ይህ ማለት ከማህበራዊ ዘርፍ የግንዛቤን አለመኖር ዋነኛ ችግር አድርገው ይጠቅሳሉ በሌላ መልኩ
ደግሞ ከፖለቲካዊ ዘርፍ ውስጥ አግላይነትን ዘረኝነትን የሚያንፀባርቁ የፖለቲካ አመራሮች
መኖራቸውን እንደችግር ይጠቅሳሉ።

2.2..17. በፌዴራሊዝምና ህገ መንግስት የስልጠና ፕሮግራም ለማዘጋጀት የተመረጡ ርዕሶች በቅደም

ተከተል

ተ. ቁ የስልጠናው ርዕስ የምላሾች ብዛት የተመረጠው ደረጃ በመቶኛ

10. የፌዴራሊዝም ፅንሰ ሀሳብና 44 1 45.8%


አስፈላጊነት
1. የህገ መንግስት ፅንሰ ሀሳብና ህገ 21 1 21.8%
መንግስታዊነት
2. ፌዴራሊዝም ህገ መንግስት ህገ 13 1 13.5%
መንግስታዊነትና የመንግስት ተቋማት
ሚና
3. ፌዴራላዚምና ሀገራዊ አንድነት 9 1 9.3%

4. ፌዴራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት - 1 0%

5. ፌዴራሊዝምና አካባቢያዊ አስተዳደር - 1 0%

18
6. ህብረ ብሄራዊና ፌዴራል ስረዓት 3 1 3.1%

7. ፊዚካል ፌዴራሊዝም - 1 0%

8. ስረዓተ ፆታና ፌዴራሊዝም - 1 0%

9. ሰብዓዊ መብቶችና ፌዴራሊዝም 2 1 2.0%

10. ፌዴራሊዝምና ዴሞክራሲ 2 1 2.0%

11. የህዝብ ፖሊሲና ፌዴራሊዝም - 1 0%

12. ሌሎች ርዕሶች

ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት 45.8% የሚሆኑ መልስ ሰጪዎች ከቀረበላቸው ርዕስ ውስጥ

የፌዴራሊዝምና ፅንሰ ሀሳብና አስፈላጊነት የሚለውን 1 ኛ ደረጃ ሲመርጡ። 21.8% የሚሆኑ መልስ

ሰጪዎች ደግሞ የህገ መንግስት ፅንሰ ሀሳብና ህገ መንግስታዊነት የሚለውን ርዕስ በ 2 ኛ ደረጃ

መርጠዋል። 13.5% የሚሆኑ መልስ ሰጪዎች ደግሞ ፌዴራሊዝም ህገ መንግስት ህገ መንግስታዊነትና

የመንግስት ተቋማት ሚና የሚለውን ርዕስ በ 3 ኛ ደረጃ ተመርጠዋል። 9.3% የሚሆኑ ምላሽ

ሰጪዎች ደግሞ ፌዴራሊዝምና ሀገራዊ አንድነት የሚለውን ርዕስ በ 4 ኛ ደረጃ መርጠዋል።

19
ክፍል ሦስት

3.1 በዳሰሳ ጥናት የተለዩ ችግሮችና መፍትሄዎች

3.1.1 በዳሰሳ ጥናት የተለዩ ችግሮች

1. መጠይቁን ከሞሉ ባለሙያዎች መካከል 75% የሚሆኑ ምላሽ ሰጭዎች በሰጡት መረጃ
መሰረት ምንም አይነት ስልጠና በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ስልጠና በአደረጃጀታቸው
ውስጥ ያልወሰዱ መሆኑን ያሳያል ይህ ማለት አባላቱ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ
ያላቸውን እውቀት ግንዛቤና አመለካከት አነስተኛ መሆኑን ይጠቁማል የዚህም የዳሰሳና ፍላጎት
ጥናት ዋና ዓላማው ይህንን ክፍተት ማየት ስለሆነ ለወጣቶችና ለሴቶች አደረጃጀቶች
የአስተምህሮ ማዕከሉ ሰፊና ተከታታይነት ያለው ስልጠና መስጠት እንዳለበት ያመላክታል።
2. ሴቶችና ወጣቶች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዘሪያ ያላቸው የእውቀትና ግንዛቤ ደረጃ
በተመለከተ መጠይቅ ከቀረበላቸው ባለሞያዎች መካከል 52% የሚሆኑ ምላሽ ሰጭዎች ባሉበት
አደረጃጀት ውስጥ ስለህገመንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የግንዛቤ ደረጃ ዝቅተኛ
ደረጃ የሚባል ነው በሌላ አገላለፅ የአደረጃጀቱ አባላትና ደጋፊዎች ስለህገመንግስትና
ፌዴራሊዝም መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳብ እንዲሁም ግንዛቤ የሌላቸው መሆኑን ይህንን ተከትሎ
በሀገራችን ውስጥ የሚነሱ የተለያዩ የተሳሳቱ አመለካከቶች መነሻቸው ከዚህ እንደሚሆን
ለማወቅ ይቻላል።
3. በሀገራችን በተለያዩ መልኩ በሚኖሩ ውይይቶችና የሃሳብ ልውውጦች አብዛኛውን ጊዜ
እንደሚሰማው የፌዴራል ስረዓት ባህሪ ያለመረዳትና በተሳሳተ መልኩ ማየት ይታያል ለዚህም
ዋና ዋና ምክንያቱ ብለው ምላሽ ሰጪዎች ያስቀመጡት

20
በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ተከታታይ ሳይንሳዊ የሆነ ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር ያቀናጁ
ስልጠናዎችን ያለመስጠት፣የስነ ዜጋና ስነምግባር ት/ት ላይ ጉዳዮችን በተገቢው አለመካተትናሥረዓቱን
ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማያያዝ ስረዓቱ በበቂ እውቀት ላይ እንዲመሰረት አለመፈለግ ወዘተ
ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። ይህም በቁጥር ሲገለፅ በአደረጃጀቱ ውስጥ የሀገራችንን ህገ
መንግስትና ፌዴራላዊ ስረዓት ከመረዳት አንፃር 73.0% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ያላቸው የመረዳት ደረጃ ወይም አቅም መካከለኛና ዝቅተኛ በሚባላ
ደረጃ ላይ ይገኛል። ይህ ማለት በሌላ አገላለፅ በህገ መንግስቱ የሰፈሩ መሰረታዊ ድንጋጌዎች የዜጎች
መብቶችና ነፃነቶች የመንግስት ስልጣንና ተግባራት እንዲሁም ሀገራችን የምትመራበት የመንግስት
አስተዳደር ዓይትና ቅርፅ ያለመረዳት ማላት ነው ይህ ደግሞ በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ እውቀት ወደ
ተሳሳተ አመለካከትና ጥላቻ ሊያመራ ይችላል።
4. በአደረጃጀት ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ በቂ ግንዛቤ አለመኖር በሀገሩቱ ላይ
የሚያመጣው ተፅዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም ይህም 83.3% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች
በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ትክክለኛ ግንዛቤ አለመኖር
በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ በጣም ከፍተኛ ተፅእኖ አለው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።
ህገ መንግስት የአንድ ሀገር የበላይ ህግ እንደመሆኑ መጠን የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ
ፖለቲካዊና ማህበራዊ መርሆችን የያዘ ሰነድ እንደመሆኑ መጠን ዜጎችን ይህን አለመረዳት
በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም የአንድ
ሀገር ዜጎች የሀገሪቱን ህገ መንግስት አለመረዳት ዜጎች ምክንያታዊ ያልሆነ ውሳኔና ድምዳሜ
ላይ እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል በጥቅሉ አሁን ሀገሪቱ የምትገኝበት ቀውስ አንዱ ምክንያ ሊሆን
ይችላል።
5. በአደረጃጀቱ ውስጥ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ ሀገራዊ አንድነት ሊያመጡ
የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያሎት ክህሎት ደረጃ በተመለከተ ከላይ በቀረበው መጠይቅ
መሰረት 73.8% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በአደረጃጀታቸው ውስጥ በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ሀገራዊ አንድነት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት ያላቸው
የክህሎት ደረጃ መካከለኛና ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል። ዜጎችነ ሀገራዊ አንድነት
ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን መስራት የሚችሉት ሰለ ህገመንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ሰፊ
እውቀት ሲኖራቸው ነው ስለሆነም ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የወጣቶች የእውቀት ደረጃ
ዝቅተኛ በመሆኑ የሀገሪቱ ችግሮች መፍትሄ አካል ሊሆኑ አይችሉም።
6. በአጠቃላይ ሴቶችና ወጣቶች በህገመንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ስራዎችን ለመስራት
የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተመለከተ ከምላሽ ሰጪዎች መካከል የሚከተሉትን ዋና ዋና
ችግሮችን አንስተዋል
 የማህበረሰቡ አመለካከት ህገ መንግስቱ የአንድ ወገን አድርጎ መቁጠር
 በቂ እውቀት ያለውና ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱ አሰልጣኞች ወይም ባለሞያ
አለመኖር
 ጥቅሙንና አስፈላጊነቱን በአግባቡ ያለመረዳት
 ስለ ህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ጉዳዮች ዙሪያ ለመረዳት ፍላጎት አለመኖር

21
 የባለሙያ እጥረት የእውቀት ማነስና የሎጂስቲክ ችግሮች ናቸው
 ወጣቶችን በህገ መንግስት አወጣጥና አካሄድ ላይ እንዲሁም በሀገሪቱ ማህበራዊ
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በበቂ ደረጃ አለማሳተፍ ወዘተ

3.1.2. የመፍትሄ ሀሳቦች

1. በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 60% በላይ የሚሆኑት የማህበረሰብ ክፍል ሴቶችና ወጣቶች

እንደመሆናቸው መጠን በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ በተለይ የሀገሪቱን ህገ መንግስት

መሰረታዊ ድንጋጌዎች ማለትም የዜጎች መብቶች የመንግስት የስልጣን አካላትና አወቃቀርን

የስልጣን ገደባቸውን የመንግስት የስልጣን አስተዳደርን ሁኔታን ወዘተ በተመለከተ ሰፊ የግንዛቤ

ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት አለባቸው ምክንያቱም ወጣቶች ስልጠናና ግንዛቤ ካላቸው

ሌሎች የአመለካከትና ክህሎት ችግሮችን መፍታት ይቻላል።

2. በፌዴራሊዝምና ህገ-መንግስት አስተምህሮ አተገባበር ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችንና

ክፍተቶች በመለየት መሙላት፣ በተለይ የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ተያያዥ ጉዳዮችን

ዘላቂነት ባለው መልኩ ለመፍታት ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት

አይነት በሲትዝንሺፕ ትምህርት ውስጥ እንዲካተትና እንዲማሩት ማድረግ፡፡

3. የተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ መድረኮችን ፣ዉይይቶችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡ

በፌዴራላዊ ስርዓቱና በህገ-መንግስቱ ዙሪያ በራሳቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንዲወያዩ

ማድረግ፣

22
3.1.3 የስልጠና ፍላጎቶች

ሌላኛዉ ከዳሰሳ ጥናቱ የተገኘዉ ዉጤት አዘጋጆቹ አፈፃፀማቸዉን ለማሳደግ በምን በምን ርዕሰ

ጉዳዮች ስልጠና ቢወስዱ መልካም ነዉ የሚለዉን ምላሽ ማግኘት ነዉ፡፡ በርከት ያሉ ምላሽ

ሰጪዎች በአራት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶ ስልጠና ቢሰጣቸዉ ፍላጎታቸዉ መሆኑን

ለመረዳት ተችሏል፡፡እነዚህም ፡-

የፌዴራሊዝም ፅንሰ ሀሳብና 44 1 45.8%


አስፈላጊነት

የህገ መንግስት ፅንሰ ሀሳብና ህገ 21 1 21.8%


መንግስታዊነት

ፌዴራሊዝም ህገ መንግስት ህገ 13 1 13.5%


መንግስታዊነትና የመንግስት ተቋማት
ሚና

ፌዴራላዚምና ሀገራዊ አንድነት 9 1 9.3%

በዚህ መሰረት ለስልጠና የተመረጡ ርዕሶች

1 ኛ/ የፌዴራሊዝም ፅንሰ ሀሳብና አስፈላጊነት

2 ኛ/ የህገ መንግስት ፅንሰ ሃሳብና ህገ መንግስታዊነት

3 ኛ/ የፌዴራሊዝም ህገ መንግስት ህገ መንግስታዊነትና የመንግስት ተቋማ ሚና

4 ኛ/ ፌዴራሊዝምና ሀገራዊ አንድነት

አመሰግናለሁ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

23
24

You might also like