(Tiling) : December 30, 2013

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 77

December

ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል


30, 2013

/ / //
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴ ሙ ት ስ ኤጀንሲ

ለጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች አጫጭር ስልጠና ሞጁል

የሙያዉ ዘርፍ፡- የንጣፍ ስራ (Tiling)

አዘጋጅ፡- አሰልጣኝ ምህረተአብ ጋሻው (ከፍተኛ-7 ቴ/ሙ/ማ/ ተቋም)

30/04/2006 ዓ.ም
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ማውጫ ገጽ

1 መግቢያ

2 በመስክና በወርክ ሾፕ የሚደረጉ የጥንቃቄ ህጎች

2.1 የአካል ደህንነት ጥንቃቄ ደንቦች

2.2 የእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች ደህንነትና ጥንቃቄ ደንቦች

2.3 የስራ ቦታ ደህንነት ጥንቃቄ ደንቦች

2.4 የጥሬ እቃ ጥንቃቄ ደንቦች

2.5 የእሳት አደጋ መከላከያ ጥንቃቄ ደንቦች

2.6 የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ

3 የካይዝን ትግብራ

3.1 5 ቱማዎች

3.2 7 ቱብክነቶች

4 ቀላል ልኬት አወሳሰድ

4.1 መግቢያ

4.2 ወጥ ቅርፅ ያላቸውና ወጥ ቅርፅ የሌላቸው ምሰሎችን ስፋት ማስላት

4.3 ይዘትን ማስላት

4.4 ለቆመ ሕንፃ ትክክለኛ ልኬት መውሰድ

5 የግብአት አዘገጃጀት/matiral selection/

5.1 ጥሬ እቃዎች

5.1.1 ስሚንቶ/cement/

5.1.2 አሸዋ/sand /

5.1.3 ታይል/ንጣፍ/tile/አይነቶች
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

5.1.3.1 ሴራሚክ/ceramic/

5.1.3.2 ሴራሚክ ያልሆኑ/non ceramic/

5.1.3.3 ከስሚንቶ የሚሰሩ/cement boneded tile/

5.1.3.4 ከተፈጥሮ ድንጋይ/natural stone/ የሚሰሩ

5.1.4 ማጣበቂያ/adhesive/

5.1.5 የርጥበት መከላከያ/waterproofing/

5.1.5.1 የርጥበት መከላከያ አይነቶች

5.1.5.1.1 በፈሳሽ/liqud/ መልክ ያሉ

5.1.5.1.2 በወረቀት/sheet/ መልክ ያሉ

5.1.5.1.3 ለመሰረት መሰሪያ ፕሪመር/substrate primer/

5.1.6 ውሀ/water

5.2 መገልገያ እቃዎች መረጣ

5.2.1 የፅዳት መሳሪያዎች /Cleaning Tools/

5.2.2 ምልክት ማድረጊያ መሳሪያዎች /Marking Tools/

5.2.3 መለኪያ መሳሪያዎች /Measuring Tools/

5.2.4 መቁረጫ መሳሪያዎች /Cutting Tools/

5.2.5 ማስተካከያ መሳሪያዎች Leveling Tools/

5.2.6 ማዋሐጃ መሳሪያዎች /Mixing Tools/

5.2.7 ተጨማሪ መገልገያመሳሪያዎች/additional tools/

6 ንጣፍ ስራ ሂደት

6.1 ቦታውን ማፅዳት ወይም መፈተሸ

6.2 የሞርታር አይነቶች

6.2.1 የሞርታር ዘዴ/ Thick bed method/

6.2.2 የግሉ ዘዴ/ Thin bed method/

6.3 የታይል አቆራረጥ/Cutting tiles/

6.4 መገጣጠሚያወችን መሙላት/Grouting/

7 የግል ሥራ ፈጠራ /ኢንተርፕርነርሽፕ /የቢዝነስ ማሻሻያ ጥበብ ሥልጠና


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

1. መግቢያ

በአሁኑ ወቅት ሳይንስና ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ፍጥነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሄዱ የንጣፍ

ስራም እየተሻሻለ በዘመናዊና ቀላል በሆነ ዘዴ የህብረተሰቡን ፍላጎት በማሟላት ላይ ይገኛል፡፡

ከንጣፍ ስራ የሚገኘውን ከፍተኛ የህብረተሰብ ፍላጎት ለማሟላት ሙያው የሚጠይቀውን

እውቀትና ክህሎት ያለው የነጣፍ ስራ ባለሙያ በማሰፈለጉ ለዚሁ ስራ የበኩሉን አስተዋጽኦ

የሚያበረክት የስልጠና ጽሁፍ ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡

በዚህ የስልጠና ጽሁፍ እጅግ አስፈላጊ በሆነ የነጣፍ ስራ ሙያ ቅድመ ተከተልን በጠበቀ መልኩ
የተዘጋጀ ሲሆነ በዋናንት በመስክና በወርክ ሾፕ የሚደረጉ የጥንቃቄ ህጎች ፣የካይዝን ትግብራ ፣የንጣፍ ስራ ልኬት
፣የንጣፍ ስራ ግብአት አዘገጃጀት ፣እርጥበትን መከላከያ (waterproofing) ፣የንጣፍ ስራ መስራት እና የግል ሥራ
ፈጠራ /ኢንተርፕርነርሽፕ /የቢዝነስ ማሻሻያ ጥበብ ያካተተ ነው፡፡

ይህንን የስልጠና ጽሁፍ መሰረት በማድረግ አሰልጣኝ መምህራን የራሳቸውን የፈጠራ ክህሎት

በማከል ስልጠናውን ቢያከናውኑ ትምህርቱን የበለጠ ውቴታማ እንደሚያደርጉት የሚተማመኑ

ሲሆን ይህ የስልጠና ጽሁፍ ለአጫጭር ስልጠናና ለመለስተኛ ደረጃ የንጣፍ ባለሙያ የሙያ ብቃት

ማረጋገጫ ምዘና (coc) ተፈታኞችም ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ይታመናለ፡፡


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

1. በመስክና በወርክሾፕ አካባቢ የሚ ደረጉ የጥንቃቄ ህጎች

3.1 መሠረታዊ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች

ዓላማ፡-

ሥልጠናው እንደተጠናቀቀ ሰልጣኞችን በስራ ጊዜ የአካል፣ የጥሬ እቃ፣ የእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች ለስራ ቦታ ተገቢውን

የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች በመገንዘብና በመጠቀም የተግባር ስራቸውን ያከናውናሉ፡፡

መግቢያ፡

በማንኛውም የተግባር ስራ ወቅት አንድ ባለሙያ በሙያው ያገኘውን እውቀትና ክህሎት በተገቢው ስራ ላይ ለማዋል በቅድሚያ

የደህንነት፣ የጥንቃቄ ደንቦችን መጠቀም አለበት፡፡ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች በአካል በእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ

አደጋዎችን ለመቀነስና ለመከላከል እንዲሁም ጥሬ እቃዎችን በቁጠባ ለመጠቀምና ስራን ውጤታማ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡አጠቃላይ

መሠረታዊ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦችን በአምስት ክፍሎች መመደብ ይቻላል

3.2 የአካል የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች

የአካል የግል የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች ፡-

ተገቢ የሆነና ለስራ አመቺ የሆነ ልብስና/የማያንሸራትት ወፍራም ሶል ያለው ጫማ

መጠቀም፣እንደ አስፈላጊነቱ የዓይን መከላከያ መነጽር፣ የእጅ ጓንት፣ የራስ ቆብ

ማድረግ፣የተለያዩ ጌጣጌጥ ነገሮችን በአካል ላይ አለማድረግ፣

መነጸር
( goggle)
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ኮፍያ (helmat)

ቱታ ( Over oll cloth)

የጀሮ ማፈኛ(ear protaction)

ጓንት(glove)

የጉልበት ማፈኛ(knee

pad) ጫማ (safety shoes)

የአካል የግል የደህንነት መጠበቂያ አልባሣት

3.3 የእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች የደህንነት ጥንቃቄ ደንቦች

 መሳሪያውን ለተሰራበት አገልግሎት መጠቀም

 ስለት በሌላቸው፣ በደነዘዙ እጀታ በሌላቸውና በተበላሹ መሳሪያዎች አለመጠቀም

 ስለታም መሳሪያዎችን በኪስ ውስጥ አለመያዝ፣ በአግባቡ መቀባበል፡፡

 አካልን ከሚቆርጡ መሳሪያዎች ማራቅ

 ለማሽኖች የሚያስፈልገውን ዝርዝር የጥንቃቄ መመሪያዎች ከተረዳን በኋላ መጠቀም፣


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

 የእለት ስራ እንደተጠናቀቀ መሳሪያዎቹን በማጽዳት በተገቢው የማስቀመጫ ሳጥንና በቦታቸው መመለስ፣

3.4 የስራ ቦታ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች

 የስራን ቅደም ተከተል ማወቅና በየደረጃው ማከናወን፣

 በመተባበር መስራትና አስፈላጊ እንቅስቃሴ፣ ልፊያ፣ ጩኸት አለማድረግ፣

 ቁርጥራጭ ነገሮችን በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ፣

 የፈሰሱ ዘይትና ቅባቶችን ማፅዳት(ማስወገድ)፣

 የዕለት ስራ ሲጠናቀቅ የስራ ጠረጴዛንና የስራ ቦታን ማፅዳት፣

 በስራ ቦታ አለማጨስ፣

 በቀላሉ በእሳት ተቀጣጣይ ነገሮችን በብረት ሳጥን ውስጥ ማከማቸት፣

 የአደጋ የማምለጫ በሮችን ፣የአደጋ ምልክቶችን ማወቅ፣

3.5 የጥሬ እቃ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች

 የተለያዩ የቧንቧን ዓይነቶች፣ መገጣጠሚያዎችንና ቁሳቁሶችን በዓይነታቸውና በመጠናቸው ለይቶ ማስቀመጥ፣

 ጥሬ እቃዎችን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣

 በስራ አካባቢ እንቅፋት የሚሆኑ ተረፈ ምርቶችን ማስወገድ፣

3.6 የእሳት አደጋ መከላከያ የጥንቃቄ ደንቦች

 እሳትን በቀላሉ ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ ዘይት፣ የቀለም ውጤቶች፣ነዳጅ እና በአግባቡ ያልተዘረጋና የተላላጠ የኤሌክትሪክ

መስመሮች የእሳት አደጋ መንስኤዎች ናቸው፡፡

 ተቀጣጣይ ነገሮችን በብረት ሳጥን ውስጥ ከድኖ በማስቀመጥና በአግባቡ መዘርጋትና የተላላጡትን ሽቦዎች በመሸፈን የእሳት

አደጋ መንስኤ መከላከል ይቻላል፡፡

3.7. የመጀመሪያ ህክምናና እርዳታ መስጫ

- በስራ ጊዜ አደጋን ለመቀነስና ለመከላከል ሀሳብን ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ በማድረግ ተገቢውን የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች

በመከተል ማከናወን ተገቢ ሲሆን ነገር ግን ይህንን በማናደርግበት ጊዜ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል፡፡

- በመሆኑም በስራ ቦታ አደጋ በሚደርስበት ጊዜ አደጋው የደረሰበት የሰውነት አካል እንደአስፈላጊነቱ በጤና ተቋማት ህክምና

እስኪደረግለት ድረስ በስራ ቦታ/ወርክሾፕ/ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ለማድረግ በስራ ቦታ የመጀመሪያ ህክምና መስጫ

ቢያንስ የቁስል መጥረጊያና በሽታ አምጪ ረቂቅ ህዋሳት መከላከያ ፈሳሾችንና የተጎዳን አካል መሸፈኛና ማሸጊያ ጨርቅና

ፕላስተር ያካተተ የህክምና ግላቭ(ጓንት) ሣጥን መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪም እርዳታውን ለማድረግ ተገቢ ሥልጠና የወሰደ

ባለሙያ ያስፈልጋል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

የፈርስት ኤይድ ሳጥን

2. የካይዝን ትግብራ
 5 ቱማዎች
 7 ቱብክነቶች

ለውጥ እፈልጋለሁ ?
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

v
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

3. ቀላል ልኬት አወሳሰድ


 መግቢያ
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

 ወጥ ቅርፅ ያላቸውና ወጥ ቅርፅ የሌላቸው


 ምሰሎችን ስፋት ማስላት
 ይዘትን ማስላት
 ለቆመ ሕንፃ ትክክለኛ ልኬት መውሰድ

1.1 መግቢያ

ልኬት መውሰድ ማለት የአንድን ቁስ አካል ቁመት፣ርዝመት፣ወርድ፣ዙሪያ፣ወዘተ...መጠን በመስፈር የምናውቅበት ሂደት ነው፡፡
የልኬትን መጠን የምናውቅበት የተለያዩ የልኬት መስፈሪያ አሀዶች/units of measurements/ አሉ፡፡ እነሱም ሜትር፣ ሳንቲ ሜትር፣ ሚሊ
ሜትር፣ ወዘተ... ናቸው፡፡

ልኬትን ለመውሰድ የቁስ አካሉን የጂኦሜትሪ ምስል/ቅርፅ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ምስሎችም ክብ፣ሦስት ማዕዘን ፣አራት
ማዕዘን፣ወዘተ...ሲሆኑ የቁስ አካሉን ስፋትና ይዘት ለማስላትና ለማወቅ ይረዳሉ፡፡

መጠነ ዙሪያ (Perimeter measurement)

የአንድ አካል/ምስል ስፋት ለማስላት እነዲቻል መጀመሪያ ቀጥተኛ ልኬት

ወይም መጠነ ዙሪያ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡

ስዕል 1.1 ቀጥተኛ ልኬት/መጠነ ዙሪያ/

ዙ=2(ወ+ር)

የሶስት ጎን ዙሪያ (Perimeter of triangle)

ዙ= ሀ+ለ+ር

ስዕል 1.2 ጎነ ሦስት መጠነ ዙሪያ


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

አራት ጎን

ስዕል 1.3 ጎነ አራት መጠነ ዙሪያ

ትራፒዝይም ዙሪያ (Perimeter of trapezium)

ዙሪያ= ሀ+ለ+ር 1+ር 2

ስዕል 1.4 የትራፒዚየም መጠነ ዙሪያ

1.2 ወጥ ቅርፅ ያላቸቸውና ወጥ ቅርፅ የሌላቸው ምስሎች ስፋት ማስላት (SURFACE AREA MEASUREMENT )

ጎነ ሶስት Triangle)

ስ, 1/2 × ሀ × ለ

ስዕል 1.5 የጎነ ሦስት ስፋት

አራት ጎን (square)
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስዕል 1.6 የአራት ጎን (square) ስፋት

ሬክታንግል()

ስዕል 1.6 የሬክታንግል ስፋት

ሮምቦስ( Rhombus)

ስ= ር+ቁ

መግለጫ

ር = ርዝመት

ቁ = ቁመት

ስ = ስፋት

ስዕል 1.7 የሮምበስ ስፋት

ትራፒዝየም (Trapezium): -.
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስ = 1/2(ር 1+ር 2) ቁ

ስዕል 1.8 የትራፒዚየም ስፋት

መግለጫ ር 1=ትልቁ ርዝመት

ር 2 =ትንሹ ርዝመት

ቁ = ቁመት

ስ = ስፋት

ክብ (Circle)

ስ =π ሬ 2

መግለጫ = / 3.14/
π

ሬ = ሬዲየስ

ስ = ስፋት

ስዕል 1.9 የክብ ስፋት አወሳሰድ

ኢልፕስ (Ellipse)

መግለጫ

ሀ,የረጅሙ ዲያማትር ግማሽ /ራዲየስ/

ለ,የአጭሩ ዲያሜትር ግማሽ

e= ስፋት
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስ=ሀ+ለ

ስዕል 1.10 ኢሊፕስ ስፋት

ወጥ የሌለው ቅርጽ (Irregular shape)

የዚህ አይነት ሁኔታሲያጋጥም ዕቃውን ወይም ስራውን በምስሉ በተመለከትነው መሰረት በመከፋፈል ስፋትን መገመት ይቻላል፡፡ ማለትም
በስራው ውስጥ ያሉትን ካሬዎች መቁጠር ይሆናል፡፡

ስዕል 1.11 ወጥነት የሌለው ቅረፅ ስፋት

1.3 ይዘት ማስላት (Volume measurement)

ሲልንደር(cylinder)

ይዘት= ሬ 2 ቁ
π

መግለጫ

= / 3.14/
π

ሬ = ሬዲየስ

ቁ = ቁመት

ስዕል 1.12 የሲሊንደር ይዘት አወሳሰድ

ፕሪዝም (prism):- የሳጥን ቅርጽ ያላቸው ምስሎች በፕሪዝም ይጠቃለላሉ፡፡


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ይዘት= ሀ*ለ*ቁ

ስዕል 1.13 የፕሪዝም ይዘት

ኮን (cone)

ይዘት= 1/3

ይዘት=1/3 π ሬ 2 ቁ

ስዕል 1.14 የኮን ይዘት

የፍራስተም ኮን ይዘት

ይዘት= ሬ 12 ቁ 1 - ሬ 12 ቁ 2
1/ 3 π 1/3 π

ስዕል 1.15 የፍራስተም ኮን ይዘት

ፒራሚድ (pyramid)

ይዘት= 1/3 ሀ*ለ*ቁ


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስዕል 1.15 የፒራሚድ ይዘት

1.4 ለቆመ ህንፃ ትክክለኛ ልኬት መውሰድ

የአንድን ቦታ ወይም ህንጻ መጠን ለማወቅ ህንፃውን በተለያዩ አቅጣጫዎች መለካት ያስፈልጋል፡፡ በቀላል ልኬት ሥራ ላይ ሦስት ዓይነት ልኬቶችን በመውሰድ
የአንድን ህንጻ አጠቃላይ መጠኑን መናገር እንችላለን፡፡ እነዚህም፡-
የቁም ልኬት
የርዝመት ልኬት
የወርድ ልኬት
የቁም ልኬት፡- የቁም ልኬት ማለት አንድን ህንፃ ወይም ግንብ ከመሬት ወደ ላይ ያለውን ቁመት የምንለካበት የልኬት ዓይነት ነው፡፡

የርዝመት ልኬት፡- የርዝመት ልኬት ማለት አንዱን ህንጻ ወይም ግንብ መሬት ላይ ያረፈበትን ርዝመት ማለት ሲሆን ርዝመቱ
የሚወስነው ህንጻው ወይም ግንቡ መሬት ላይ ሲያርፍ ትልቁ የልኬት መጠን ያለበትን አቅጣጫ በመውሰድ ርዝመቱን መወሰን
ይችላል፡፡

የወርድ ልኬት ፡- የርዝመት ልኬት ማለት አንዱን ህንጻ ወይም ግንብ መሬት ላይ ያረፈበትን ርዝመት ማለት ሲሆን ርዝመቱ የሚወስነው ህንጻው ወይም
ግንቡ መሬት ላይ ሲያርፍ ትንሹን የልኬት መጠን ያለው አቅጣጫ በመውሰድ ወርዱን መወሰን ይችላል፡፡

4. የግብአት አዘገጃጀት /matiral selection /

A. መገልገያ እቃዎች እና
B. ጥሬ እቃዎች መረጣ
I. መገልገያ እቃዎች /Tools & Equipment/
 ለንጣፍ መስሪያነት የሚያገለግሉ የተለያዩ መሳሪያዎች አሉ እነሱም፡-
1. የፅዳት መሳሪያዎች /Cleaning Tools/
2. ምልክት ማድረጊያ መሳሪያዎች /Marking Tools/
3. መለኪያ መሳሪያዎች /Measuring Tools/
4. መቁረጫ መሳሪያዎች /Cutting Tools/
5. ማስተካከያ መሳሪያዎች Leveling Tools/
6. ማዋሐጃ መሳሪያዎች /Mixing Tools/
7. ተጨማሪ መገልገያመሳሪያዎች/ additional tools/
1. የፅዳት መሳሪያዎች /Cleaning Tools/
እነዚህ መሳሪያዎች የሚያገለግሉን ለፅዳት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ
A. ብሩሽ /Brush/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

- ብሩሽ ማለት የማፅጃ መሳሪያ ሲሆን እርሱም የታይሉን መገጣጠሚያ፣የርጥበት መከላከያ


እንቀባበታለን እና ሰርተን ስንጨርስ መሳሪያዎችን እናፀዳበታለን፡፡

B. የቁምመጥረጊያ /Broom/
- ይህ መሳሪያ ልክ እንደ ብሩሽ ሰርተን ስናበቃ የስራንበት አካባቢ የምናፀዳበት መሳሪያ ነው፡፡

C. ስፖንጅ /Sponge/
- ይህ መሳሪያ የሚያገለግለው ንጣፉን ለማፅዳትና መገልገያ እቃዎች ለማፅዳት ወይም ለማጠብ
ይጠቅማል፡፡

D. ስፖንጅ ፍሎት /Sponge Float/


- ስፖንጅ ፍሎት ማለት ልክ እንደ መፋስ ያለ ሲሆን ነገር ግን ከስሩ ስፖንጅ ያለው ነው፡፡
መገጣጠሚያዎችን ለመሙላት
/grouting/ እና ለማጠብ
ያገለግለናል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

2. ምልክት ማድረጊያ መሳሪያዎች


A. ጉልህ እርሳስ /graphite Pencil/
- ይህ መሳሪያ ጥቅሙ ምልክት ለማድረግ ነው፡፡ የሚሰራውም የዚህን ፍላጐት ለማሳካት ነው፡፡

B. መፈቅፈቂያ /Scrapper/
- ይህ መሳሪያ ልክ እንደ ግራፋይት ፔንስል ምልክት ለማድረግ፣አላስፈላጊ ነገሮችን ለመፋቅ እና የሸክላ
ንጣፍ መቁረጫነትም ልንጠቀመው እንችላለን፡፡
3. ማስተካከያ መሳሪያዎች /Leveling Tools/
A. የእጅ ውሐ ልክ /Sprit level/
- ይህ የእጅ ውሐ ልክ አግድም /Horizontal/ ፣ቀጥ ያለ ግድግዳ /Vertical/ እና ዲያጐናል /Inclind/ የሆነ
ቦታ ወይም ጠርዝን ለመለካት እንጠቀምበታለን፡፡
- ዝርመቱም ከ 80 እስከ 120 ሴ.ሜ ይደርሳል
- የሚሰራው ከብረት፣ሴንቴቲክ ማቴሪያሎች እና ከእንጨት ነው፡፡ ሶስት በብሎች አሉት፡፡
የመጀመሪየው መሐከል ላይ የሚገኘው አግድም /Horizontal/ ለመለካት እንጠቀምበታለን፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በአንደኛው ጫፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቀጥ ያለ ግድግዳ /Vertical/ ስንጠቀምበት
የቀረው በሌላኛው ጫፍ ላይ የሚገኘው ደግሞ ዲያጐናል /Inclind/ ለመለካት እንጠቀምበታለን፡፡
ይህ መሳሪያ ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን የምናውቅበት ነው፡፡

B. ቱንቢ /Plumb bob/


- ይህ መሳሪያ የሚሰራው ከብረት ሲሆን በገመድ ተንጠልጥሎ ቀጥ ያለ ግድግዳ /Vertical/ ወይም
ጠርዝ ለመለኪያነት ይጠቅመናል
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

C. ሪጋ /Straight edge/
- ይህ መሳሪያ ከብረት /አሉሚኒየም/ ይሰራል ፤ዝርመቱም ከ 2-4 ሜትር ይደርሳል፡፡
- አንድን ቦታ ትክክል ለማድረግ ይጠቅማል፡፡

D. የጐማ ውሐ ልክ /Hose water level/

- ይህ የጐማ ውሐ ልክ ብርሐን አስተላላፊ የኘላስቲክ ቱቦ ሲሆን ይህን የምንጠቀም ቀጥ ባለ ገፅ ለይ /ለምሳሌ ግድግዳ ላይ አግዳሚ መስመር ከቤቱ
ወለል በኩል ከፍታ ለማስመር /ለወለልና ኮረኒስ ስራ ያለግላል ውሐ ብምንሞላበት ጊዜ በጉማው ውስጥ ምንም አየር መኖር የለበትም ነገር ግን አየር
ከገባበት ልኬቱን በትክክል አያስተላልፍም፡፡

E. ሲባጎ//
- ሲባጎ ወይም ናይለን ገመድ (3 ሚሜ ውፈረት) የመሰረት ጉድጓድ ሲጣል፣ንጣፍ ሲነጠፍ፣ ግንብ ሲገነባ ፣ልስን
ስራ ሲሰራ፣ የአናፂ ስራ ሲሰራ የውሃ ልክ መጠበቂያ እንዲሁም ቀጥ ያሉ ገፆችን ለማውጣት ይረዳል ፡፡

4. መለኪያ መሳሪያዎች /Measuring


Tools/
A. ዚግዛግ ሜትር /Foloding Meter/
- ይህ የዝርመት የመለኪያ መሳሪያ ሲሆን የሚሰራው ከተለያዩ 20 ሳ.ሜ ዝርመት የላቸው የእንጨት
/የጣውላ ቁራጭ ይሰራል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

B. መለኪያ ሜትር /Measuring tape/

ሜትር ርዝመት፣ ጥልቀት፣ ስፋት፣ ውፍረት ለመለካት የሚያገለግል ነው፡፡ብዙ አይነቶች ሜትሮች አሉ ከነዚህም ውስጥ ባለ 3,
5, 30, 50 ወዘተ ይገኙበታል ፡፡

5. መቁረጫ መሳሪያዎች /Cutting tool/


- መቁረጫ መሳሪያዎች የምንላቸው ሁለት አይነት ሲሆኑ እነሱም፡- ያለ በኤሌክትሪክ የሚሰሩና በኤሌክትሪክ
የሚሰሩ ናቸው፡፡
I. ያለ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ
A. መስታውት መቁረጫ /Hand cutter/
- ይህ መሳሪያ በእጅ ለመያዝ የሚያመችና በቀላሉ ሴራሚክ፣ፖርሲልን እና ተመሳሳ ንጣፎችን ለመቁረጥ
እንጠቀምበታለን፡፡

B. ጉጠት /Piler/
- ጉጠት የተለያዩ ቅርፆችን ለመፍጠርና ሚስማርን ለመንቀል እንጠቀምበታለን፡፡

C. መሮ /Chisel/
- መሮ ማለት ከጠንካራ የብረት ዓይነት የሚሰራ ነው ሁለት ዓይነት መሮ አለ፡፡ እነሱም ጫፉ ጠፍጣፋ /Flat
chisel/ እና ጫፉ ሹል /Pointed chisel/ ይህ መሮ የሚጠቅመን ለመጥረብና ለመቁረጥ ያገለግለናል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

D. ታይል መቁረጫ /Tile Cutter/

ይህ የታይል መቁረጫ ቀላልና ምቹ ፈጣን መሳሪያ ሲሆን ታይሎችን በምንቆርጥበት ጊዜ የሴራሚኩን ወይም
የሸክለውን ፓርት በትክክል የሚቆርጥልን መሳሪያ ነው፡፡

II. በ


ክትሪክ የሚሰራ መቁረጫ
- በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መቁረጫዎች ውስጥ
 አንግል ግራይንደር /angle grinder/
 ቴብል ግራይንደር/table grinder/
 ዌስት ሳው /west saw/
A. ግራይንደር /angle grinder/
- ግራይንደር በሁለት እጅ እና በአንድ እጅ የሚያዝ ሲሆን ለተለያዩ ማቴሪያሎች መቁረጫነት እንጠቀምዋለን
ለምሳሌ፡- ለኮንክሪት ፣ለድንጋይ፣ለብረት እና ለታይል ወዘተ መቁረጫነት ያገለግላል ነገር ግር ለታይል
የምንጠቀመው ደስክ የብረት ደስክ ነው፡፡ ነገር ግን ለብረት የምንጠቀመው የሸራ ደስክ ነው፡፡

6. ማዋሐጃ መሳሪያ /mixing tool/


ማዋሐድ መሳሪያዎች /mixing tool/ በሁለት ይከፈላሉ
 ማንዋልና ማዋሐድ /Manual mixer/
 ሜካኒካል ማዋሐድ /Mechanical mixer/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

1. ማንዋል ማዋሐጃ /Manual mixer/


- ማንዋል ማዋሐጃ የምንላቸው
A. አካፋ /spade/

ይህ መሳሪያ ስሚንቶ እና አሸዋን ለማንሳት/ለመጫን፣ ለማደባለቅ ወዘተ… ያገለግላል

ስዕል 5.12 አካፋ

ሜካኒካል ማዋሐድ /Mechanical mixer/

ሞርታር ለማዘጋጀት ስራ በአነስተኛ ጊዜ ፈጣን በሆነ ዘዴ ብዛት ያለው ሞርታር ለማቡኪያ የሚያገለግል ማሽን ነው፡፡አርማታ በሚቦካበት ጊዜ ሚክሰሩ
በተስተካከለ ቦታ መቀመጥና 30-35 ዲግሪ ማንጋደድ ይኖርበታል፡፡ ሞርታር ማቡኪያ ማሽን ዘወትር ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ በሚገባ መፅዳት/መታጠብ/
አለበት፡፡

7. ተጨማሪ መገልገያመሳሪያዎች//
1. ማንኪያ/Towel/

ማንኪያ መሰረታዊ ከሆኑት የንጣፉ ሥራ ዕቃዎች ዋነኛው ሲሆን ሞርታርን፣ ለማነሳት፣ለመሰራጨትና ለማለስለስ ያገለግላል፡፡

ስዕል 5.2 ማንኪያ

2. መፋስ /Float/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

መፋስ ከጠፍጣፋ ብረት/ ወፍራም ላሜራ/ ወይም ከእንጨት የሚሰራ ሲሆን ንጣፉ ሲሰራ ለማሰተከከልና ለማለስለስ ያገለግላል፡፡

መፋስ አይነቶች

ስዕል 5.3 ቀጥተኛ


መፋስ

3. ጋሪ

ለንጣፍ ስራ ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር ወዘተ ለማመላለስ ያገለግላል፡፡

ስዕል 5.8 ጋሪ

4. የአሸዋ ሳጥን

አሸዋን በተፈቀደው መጠን ለመስፈር የሚያገለግል ሲሆን መጠኑም 50× 40×20 ሳ.ሜ፣ 50×40×18 ሳ.ሜ፣ 50×40×16 ሳ.ሜ ይገኛል

ስዕል 5.10 የአሸዋ ሳጥን

5. ሸንኬሎ/ባልዲ
- ውሃ ወይም ሞርታር ለማመላለስ ያገለግላል

ስዕል 5.11 ሸንኬሎ

6. የብረት ማዕዘን/ስኳድራ/try square/

ለቅርፅ ማውቻ ሥራ ማዕዘን መለከያ እና ማስተካከያ ግድፈት መቆጣጠሪያ ሆኖ የገለግላል፡፡


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስዕል 3.8 ብረት ማዕዘን

7. የአናፂ መዶሻ/claw hammer/


- ለሚስማር መምቻና መንቀያነት ያገለግላል፡፡

ስዕል 3.9 የአናጢ መዶሻ

8. የሽቦ መጥረጊያ /Wire brush/


- ከቀጫጭን ሽቦ የተሰራ ሲሆን የቆሻሻ ለማስለቀቅ/ለመፅዳት/ ያገለግላል፡፡

ስዕል 4.15 የሽቦ ብሩሽ

9. ኮርድ/tiling aid/
- በጣም ቀላል ነገር ግን በጣም አስፈላጊ መሳሪያ ነው፡፡ይህ መሳሪያ የምንጠቀመው ለገመድ መወጠሪያነት ሲሆን አንዱን
ከመጀመሪያው ጎን ከሴራሚኩ ጫፍ እና ሌላኛውን ኮርድ ጫፍ ጠርዝ ተደረጎ ይወጠርበታል፡፡

10. የፕላስቲክ መዶሻ/rubber hammer/


- ይህ መሳሪያ የሚጠቅመው የንጣፍ ስራ በምናካሂድበት ጊዜ ለታይል መምቻነት ያገለግላል፡፡

11. የግንበኛ መዶሻ/masson hammer/


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

- ይህ መዶሻ ግማሽ ኪሎ ግራም ክብደት ያለው ሲሆን መሮወችን ለመምታት ያገለግላል፡፡

12. ኖችድ ትራወል/Notched trowel/


- ይህ መሳሪያ የሚያገለግለው ለግድግዳና ለወለል ግሉ(ማጣበቂያ) ወይም ቲን ቤድ(thin bed method) መርጨት ወይም
ለመቀባት እንጠቀመዋለን፡፡

- ይህ ኖችድ ትራዎል የምንጠቀመው እንደ ንጣፉ ውፍረትና ስፋት የመፋሱን ጥርስ ይለያያል፡፡

የንጣፉ(የታይሉ) አይነት የማንኪያው ጥርስ ርዝመት

እስከ 10*10 ሴ.ሜ ለሚደርስ ሞዛይክ 4 ሚሜ


የግድግዳ ታይል 15*15- 20*20 ሴ.ሜ 6 ሚሜ
የግድግዳ ታይል ከ 20*25 ለሚበልጥ 8 ሚሜ
የወለል ታይል 15*15 -20*20 ሴሜ 8 ሚሜ
የወለል ታይል ከ 25*25 ሴ.ሜ ለሚበልጥ 10 ሚሜ

13. የታይል መዶሻ(tile hammer)


- ይህ መሳሪያ የሚያገለግለው ታይሉን ለመብሳት
ነው፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

14. ትራፓኖ(drill)
- ይህ መሳሪያ ኮንክሪት ፣ድንጋይ ፣ታይል እና የተለያዩ ጠንካራ ማቴሪያሎችን ለመብሳት የሚጠቅመን ሲሆን መብሻ ቢቴዎች
የተለያየ መጠንና አይነት አላቸው፡፡ ነገር ግን የሚለያዩት እንደሚሰሩት ስራ ልዩነት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የብረት፣ የእንጨትና የድንጋይ
ይለያያል፡፡

II. ለጥሬ እቃዎች /matrials/


የንጣፍ ስራ ለመስራት የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች

1. ስሚንቶ/cement/
2. አሸዋ/sand/
3. ታይል/ንጣፍ/tile/
4. ማጣበቂያ/adhesive/
5. የርጥበት መከላከያ/waterproofing/
6. ውሀ/water/
1. ሲሚንቶ /cement/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ሲሚንቶ ለአርማታ ሥራ' ለተለያዩ የግንብ ሥራዎች' ለልስን' ለተኩስ ሥራ፣ ለወለል ሥራ' ' ለግድብ ሥራ' ለድልድይና ወዘተ…
የሚያገለግል ሲሆን መጠነ ሰፊ አገልግሎትን ለሚሰጡ የመሠረተ ልማት ተቋማት ግንባታ የሚያገለግል የግንባታ ጥሬ ዕቃ ነው፡፡

የሲሚንቶ ዓይነቶች፡-

በሀገራችን የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ሁለት ዓይነት ሲሚንቶ ያመርታሉ፡፡

እነርሱም፡-

1. ፖርትላንድ ሲማንቶ /Portland Cement/


2. ፖርትላን ፖዞላና ሲሚንቶ / Port Land puzzolana cement/
የሚባሉት ሲሆኑ በአጠቃላይ ግን የሲሚንቶ ዓይነቶች እንደሚሰጡት ጠቀሜታ የተለያዩ ሲሆኑ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. መደበኛ ፖርትላነድ ሲሚንቶ/Ordinary Portland cement /OPC/


2. ቶሎ የሚጠነክር ሲሚንቶ/Rapid Hardening cement /RHC/
3. ዝቅተኛ ሙቀት የሚያመነጭ/ Low heat cement /LHC/
4. ቶሎ የሚደርቅ/Quick setting cement
5. ጨዋማና አሲድን መቋቋም የሚችል ሲሚንቶ/Sulfate resisting cement
6. ነጭ ሲሚንቶ/White cement
7. ፖዞላና ሲሚንቶ/Portland puzzolana cement

መደበኛ ፖርትላንድ ሲሚንቶ /Ordinary Portland Cement ፡-

ይህ ሲሚንቶ በአብዛኛው የግንባታ ሥራ የምንጠቀምበት የሲሚንቶ ዓይነት

ሲሆን ለማንኛውም የግንባታ ሥራ የሚያገለግል ነው፡፡ በተለይ ለመሠረት

ሥራ፣ ለግድግዳና ለወለል ሥራ ወዘተ በአብዛኛው የሚውል የሲሚንቶ ዓይነት

ሲሆን እንደ ጨውና አሲድ የመሳሰሉ ነገሮች አይስማሙትም፡፡

ቶሎ የሚጠነክር ሲሚንቶ/Rapid hardening cement / RHC/

ይህ የሲማንቶ ዓይነት በሶስት ቀን ውስጥ ብቻ የሚፈለግበትን ጥንካሬ መስጠት የሚችል በጣም ደቃቅ ስሚንቶ ነው፡፡ ቶሎ
እንዲጠነክር የሚረዳውም ትራይካለሲየምሲልኬት/3CaSiO2/ የተባለ ወሁድ በከፍተኛ መጠን በውስጡ እንዲገኝ በማድረግ ስለሚመረት
ነው፡፡

ቶሎ የሚጠነክር ሰሚንቶ የሚሠራው ሥራ ተፈላጊውን ጥንካሬ በቶሎ እንዲያገኝና ግንባታው እንዲፋጠን ይረዳል፡፡

ዝቅተኛ ሙቀት የሚያመነጭ/ Low heat cement /LHC/

ይህኛው ሲማንቶ አነስተኛ የሆነ ኖራ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ሲልካና ብረት /Silica and iron/ ከመደበኛው ፖርትላንድ
ሲሚንቶ በበለጠ መልኩ ተጨምሮበት የሚመረት ሲሆን ሙቀት የማመንጨት ሂደቱም /The heat of hydration/ በጣም አዝጋሚና
ከፖርትላንድ ሲሚንቶ በአንድ ሶስተኛ 1/3 እጅ ያነሰ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሲሚንቶ የሚሠራ ሥራ ቶሎ ስለማይደረቅ ለሥራ ጊዜ
የሚሰጥ በመሆኑ ጠንካራ ለሆኑና ብዛት ላላቸው ሥራዎች እንደግድብ ለመሳሰሉት ሥራዎች እንጠቀመበታለን፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ቶሎ የሚደርቅ/Quick setting cement

ቶሎ የሚደርቅ ሲሚንቶ ምንም ጄሶ ያልተቀላቀለበት ሲሆን በሰላሣ ደቂቃ ውስጥ መጠንከርና መድረቅ የሚችል ሲሚንቶ
ስለሆነ በውሃ ውስጥ ለሚገነቡ ግንቦች' ግድግዳዎች ወዘተ… ግንባታ እንጠቀምበታለን፡፡

ጨዋማና አሲድን መቋቋም የሚችል ሲሚንቶ/Sulfate resisting cement

ይህ የሲሚንቶ ዓይነት በውስጡ ሰልፌትን /ጨዋማና አሲድ ነክ ነገሮች/ የመቋቋም ብቃት ያለው በመሆኑ ጨዋማና አሲዳማ
በሆኑ አካባቢዎች የግንባታ ሥራዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ነው፡፡

White cement /ነጭ ሲሚንቶ/'

ነጭ ሲሚንቶ እንደማንኛውም ሲሚንቶ የራሱ የሆነ ባህሪ ስላለው በተለየ መለክ የሚመረትና ነጭ መልክ ያለው የሲሚንቶ
ዱቄት ነው፡፡ በአመራረት ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅና በዋጋውም ከሌሎች ሰለሚወደድ ለማጠናቀቂያ ሥራዎች /Finishing
Works/ ተፈላጊ የሆነ የሲሚንቶ ዓይነት ነው፡፡

ነጭ ሲሚንቶ ለሚከተሉት ሥራዎች ተፈላጊነት ይኖረዋል፡፡

 ለህንፃዎች የማጠናቀቂያ / የማስዋቢያ/ ሥራ ለምሣሌ ለንፁህና ነጣ ላለ የውስጥና የውጭ የልስን ሥራ እንዲሁም


ለሞዛይክ፣ ለሴራሚክ የወለል ሥራና ለስቱኮ ሥራ ወዘተ..............
 ህንፃን የመስዋብ ሥራ /Architectural Ornamental or Decorative Works/
 በአውሮ ý ላን ማረፊያና አካባቢው፣ በመኪና መንገዶችና ድልድዮች ለሚሰሩ ነጣ ያሉ ጠቋሚና በማስገንዘቢያነት
ለሚያገለግሉ የተለያዩ ምልክቶችና ሥራዎች መስሪያ ያገለግላል፡፡

ፖዞላና ሲሚንቶ/Portland puzzolana cement

ፖዞላና ስሚነቶ ከሌላው የሚለየው የሚመረተው ፖዞላኒክ /Puzzuolanic

ጥሬ ነገሮች /ፑሚቼና ሼል/ በመጨመር መሆኑ ነው፡፡

ፓርትላንድ ፖዞላና ሲሚንቶ ምንም እንኳን የፖርትላንድ ሲሚንቶ ያህል

ጥንካሬ ባይኖረውም ለማንኛውም የግንባታ ሥራ ምቹ የሆነ የሲሚንቶ ዓይነት ነው፡

2. አሸዋ/ sand /

አሸዋ በአብዛኛው የምንጠቀምበትና የተለመደ የግንባታ ጥሬ ዕቃ ሲሆን በውስጡ ፈሳሽ ነገር የማያሳልፍ/Impervious/፣ በጣም
የተጠቀጠቀ /Dense/ ጠንካራ የህንፃ አካል ለመሥራት ነው፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስዕል 5.1 አሸዋ

የአሸዋ ዓይነቶች

የአሸዋ ዓይነቶች ከሚመረቱበት ቦታ አኳያ እንደሚከተለው ይመደባሉ፡፡

ሀ. ከድንጋይ ቁጥኝ የሚገኝ አሸዋ /Pit sand/ በቁፋሮ የሚገኝ

ለ. የወንዝ አሸዋ / River Sand/

ሐ. የባህር አሸዋ /Sea sand/

ከድንጋይ ቋጥኝ የሚገኝ አሸዋ /Pit sand/'

ይህ የአሸዋ ዓይነት በተፈጥሮ አንድ ቦታ ላይ ተከማችቶና ተሰብስቦ ወይም የአሸዋ ድንጋይ በመሰባበርና በማድቀቅ ይገኛል፡፡ ይህ አሸዋ
ከሌሎቹ ሲወዳደር ንፁህ በቅርጽም ሹልና ማዕዘን ያለው ደቃቅ በመሆኑ አርማታ ሞርታርና ለማዘጋጀት ተመራጭ ነው፡፡

የወንዝ አሸዋ /River sand/'

የወንዝ አሸዋ ከወንዞች ውስጥና ከወንዞች ዳርቻ በሰፊው ይገኛል፡፡ በቅረፁም ድቡልቡልና ደቀቅ ያለ መጠን ያለው ነው፡፡ይህ የወንዝ አሸዋ
ንፁህ ከመጠን ያለፈ አፈር (4-6%) ያልተቀላቀለበት ከሆነ ለንጣፍ ሞርታር ለማዘጋጀት ያገለግላል፡፡

የባህር አሸዋ /Sea sand/'

የባህር አቨዋ ከባህር ዳርቻ የሚገኝ መጠኑ ደቃቅና ቅርፁም ድቡልቡል የሆነ ከፍተኛ የሆነ የባህር ጨው በተፈጥሮው የተቀላቀለበት
በመሆኑ ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ በንፁህ ውሃ በደንብ ካልታጠበ በስሚንቶ ጥንካሬ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ በተጨማሪም
የተሠራው የአርማታ ሥራ እርጥበት እንዲስብና በሚደርቅበት ጊዜ ሥራውን የጨው አመድ ስለሚያለብሰው እምብዛም ተፈላጊ የአሸዋ
ዓይነት አይደለም /ካልተቸገረ በስተቀር/፡፡

አሸዋ ማሟላት ያለበት መስፈረቶች


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

አሸዋ ለታቀደለት ዓላማ በተገቢ መልኩ እንዲውል የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

1. ለንጣፍ ሥራ የሚውል አሸዋ መጠን ደቃቅ አሸዋ/Fine sand/፣ መካከለኛ አሸዋ/Medium sand/ ከፈተኛ መጠን ያለው
አሸዋ/Coarse sand/ (ከ 0.06-4 ሚ.ሜ) ከሁሉም ዓይነት መያዝ አለበት ምክንያቱም በንጣፉ ጥሬ ዕቃዎች መካከል ያለውን
ክፍተት ወይም /void/ በሚገባ መድፈን የሚችል መሆን አለበት፡፡
2. አሸዋ ንፁህ፣ አፈረና እጽዋቶች የፀዳ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የእነዚህ ነገሮች በአሸዋ ውስጥ መኖር የአርማታ ወይም
የሞርታር ጥንካሬ ስለሚቀንሱ ነው፡፡ የአርማታ ሥራው ጠንካራና በውስጡ ምንም ነገር የማያሣልፍ መሆኑ ቀርቶ በውስጡ ውሃ
የሚያስገባ የመጠንከር ሂደቱም በጣም አዝጋሚ ይሆናል፡፡
3. የአሸዋ ቅንጣት' ጠንካራና' ሹል ጠረዞች ሊኖረው ይገባል፡፡ ሹል' ስለታማ ጠርዝ ያለው አሸዋ ድቡልቡል ወይንም ክብ ቅርጽ ካለው
አሸዋ የበለጠ ተመራጭነት አለው፡፡ ምክንያቱም ከሲሚንቶው ውህድ ጋር የመያያዝ ችሎታው ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡
4. አሸዋ ከጨው አነዲሁም የሰሚንቶን ጥንካሬ የሚቀንሱ ኬሚካሎች የፀዳ መሆን አለበት፡፡

 የአሸዋን ንጽህና ከሞላ ጐደል በሚከተሉት መንገዶች በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡

 ከአቧራ የፀዳ ለመሆኑ ጥቂት አሸዋ በእጅ ዘግኖ በመጨበጥና መልሶ በመበተን እጅ ላይ የሚቀረውን አዋራ ወይም
አፈር በመመልከት ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡
 እንዲሁም ጨው አዘል ስለመሆኑ ጥቂት አሸዋ ቆንጥሮ በምላስ በማጣጣምና በመትፋት ጨዋማ መሆን አለመሆኑን
ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡
 ከሁሉም የተሻለው ግን በላቦራቶር የአፈር መኖር/Silt Test/jar test/ እንዲሁም ሌሎች ኬሚካሎችን
መኖር/Colorimetric Test/ መፈተሽ ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡፡

 አሸዋ ለንጣፍ ሥራ ውስጥ በሚቀየጥበት ወቅት የሚከተሉትን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

 ሲሚንቶና ኖራ ያለአሸዋ ስራ ላይ ቢውል ተፈላጊውን ጥንካሬ ስለማይኖረው አሸዋ መጨመሩ ጥንካሬውን ከመጨመር
አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡
 አሸዋ ከሲሚንቶ ጋር ተቀላቅሎ መቦካቱ የሲሚንቶን ፍጆታ ይቀንሳል፡፡
 የአሸዋ በሞርታር ውስጥ መገኘት የተሰራው ሥራ በቀላሉ በዝናብና በንፋስ በቀላሉ እንዳይጠቃና እንዳይፈርስ
ይረዳል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

3. የንጣፍ ዓይነቶች (types of tile and slab)


- በጣም ብዙ ዓይነት የወለልና የግድግዳ ንጣፎ በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡
- እንዚህ በመጠን ፣በዓይነት፣በቅርጽ፣ በጥቅም የተለያዩ ናቸው

ንጣፍ

ሠው ሰራሽ የተፈጥሮ/Natural /
/Artificial/

 Igneous rock
ግራናይት /
ሴራሚክ ሴራሚክ ያልሆነ ባዛልት
/Ceramic/  Sedimentary
/None ceramic/ rock
ላይም ስቶን
 Metamorphic
rock
እብነበረድ
ለስላሳ ሻካራ ሴራሚክ
ሴራሚክ

-የመስታወት ታይል/ ንጣፍ /


ኧርዝዋር/earthware/ -ኳሪ ታይል
-አስፋልት ንጣፍ
እስቶንዋር/Stoneware/ -ቴራኮታ
-ኮንክሪት ንጣፍ
ፖርስሊን /porcilen / -የቴራዞ ንጣፍ /terrazzo/
ሴራሚክ ታይል -ችፕስ /weshed terrazzo/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ሴራሚክ አይነቶች/Types of ceramic/

ኧርዝዋር/earth ware/፡-
- ይህ የተለመደ የንጣፍ ዓይነት ነው፡፡
- በጣም ደካማ እና የውሃ የሚስብ ነው ምክንያቱም ለግድግዳ ብቻ የሚያገለግል ነው፡፡
- በተለያዩ ቅርፅ ፣ መጠን ይገኛል ነገር ግን ይህ ሴራሚክ ለወለል ስንጠቀመው በቀላሉ ሊሰበር እና
መስታወት ክፍሉ ሊፋቅ ይችላል ስለዚህ ቀላል ክብደት ባለበት ቦታ ብቻ እንጠቀመዋለን፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስቶንዋር/stoseware/፡-
- ይህ ንጣፍ ከኧርዝዋር ጥንካራ ነው፡፡
- ከኧርዝዋር አንፃር ውሃ አይስብም፣ በጣም ጠንካራ እና የተረጋጋ ነው
- በግሉ ቦታ (Private sector) ለወለል ንጣፍ በጣም ምቹ ነው፡፡
- የተለየዩ ስፋት፣ ቅርፅ እና መጠን አላቸው
- ከከኧርዝዋር ስቶንዋር ሰፊ እና ከፍተኛ ድምፅ አለው፡፡

የስቶንዋር እና ኧርዝዋር ፀባይ እና ልዩነት

ስቶንዋር እና ኧርዝዋር ውሃ እንዳይሰርግ ይከላከላሉ፡፡ ከሌላ የወለልና ግድግዳ ንጣፎች አንፃር ብዙ ጥሩ


ጎኖች ፀባይ አላቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ

- በቀላሉ ይፀዳሉ ቆሻሻ በቀላሉ ይለቃል


- በጣም ንፁህ ፤ ብርሃን እና የፀሐይ ጨረር መልካቸውን አይቀይራቸውም
- ሽታ የላቸውም
- በጣም ጥሩ ናቸው
- አሲድና ቤዝ ይከላከላሉ

ልዩነታቸው

- ስቶንዋር ውሃ የሚስበው በራሱ ክብደት 1-3% ኧርዝዋር ግን ውሃ የሚስበው በራሱ ክብደት እስከ
10% የተለያዩ የሙቀት መጠን አላቸው ስቶንዋር በጣም ጠንካራ ሲሆን ኧርዝዋር ግን በጣም ደካማ
እና እርጥበት የሚስብ ነው፡፡
- ስቶንዋር ቅዝቃዘዜ (ውርጭ) ይከላከላል ኧርዝዋር ግን አይከላከልም
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ፐርስሊን/porcelain/፡-
- ይህ ንጣፍ የስቶንዋር አይነት ነው ከስቶንዋር በጣም ጠንካራ ነው፡፡
- ሁለት አይነት ፓርሲሊን አለ፡፡ እነሱም ሻካራ/semi-glazed/ እና ለስላሳ/glazed /
- ፓርሲሊን ወሃ የመሳብ አቅሙ በጣም ዝቅተኛ ነው::

ክለንከር/clinker/፡-
- ይህ ሸክላ አመራረቱ ከከኧርዝዋር ይለያል፡፡ በሁለት ዓይነት መልኩ እናገኛዋልን፡፡ እነሱም ለስላሳ/
glazed / እና ሻካራ/ semi-glazed // ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ለውጭ ግድግዳ ያገለግላል፡፡

ሞዛያክ፡-
- ሞዛያክ የምንላቸው 90 ሴሜ 2/ያልበለጡ ናቸው
- ሞዛይክ የሚባለው ከመጠን አንጻር ነው እንጂ የተለየ ጥሬ ዕቃ /Martial/ አይደለም፡፡ ይህ ማለት
ስቶንዋር ፣ፕርሲሊን እና ኧርዝዋር በጣም ትንሽ መጠን ካለቸው ነው፡፡
- አብዛኛውን ጊዜ ሞዛይክ ከወረቀት እና መረብ ነገር ያለው ፋይበር ላይ ይለጠፋል፡፡ አንዱ ወረቀት
ላይ (3030) ሴ.ሜ ይለጠፋል ነገር ግን እንደ ሞዛይኩ መጠን ይለያል፡፡
- ጠጠሮቹ ከወረቀቱ ፊትና ጅርባ ላይ ሊለጠፉ ይችላሉ፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ሴራሚክ ያልሆነ ንጣፍ (non ceramic tile and slab)

የመስታወት ታይል ንጣፍ( glaze tile & slab)፡-


- የመስታወት ንጣፍ ቀለመሉ የሚያምር ውፍረቱ 6.ሚ.ሜ -10 ሚ.ሜ ነው፡፡
ቅርፁ አራት ማዕዘን ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የምንጠቀመው የመስታወት ሞዛይክ ነው፡፡
- የመስታወት ንጣፍ ምንም ዓይነት ውሃ አይስብም ፡፡ ነገር ግን ከሞርተሩ ጋር ማጣበቅ አስቸጋሪና
ጥሩ አይደለም፡፡ ለዚህ ዓይነት ንጣፎች ፈሳሽ ልክስ አዴቲሲቨ(Liquid latex additive) እና ማጣበቂ
(Adhesive) እንጠቀማለን፡፡
- የስሚንቶ ሞርታር ለወለልና ግድግዳ የመስታወት ንጣፍ በፍፁም አያገለግልም፡፡ የመስወት ሞዛይክ /
glaze mosaic /የተለያዩ ምርት ጌጣጌጥ መፍጠር ይችላል፡፡

የፕላስቲክ ታይል/PVC/

- ይህ የንጣፍ ዓይነት ከፕለስቲክ የሚሰራ ሲሆን የተለያዩ ቅርፅ፣መጠን እና አይነት አላቸው፡፡


- ለመኖሪያ እና ለማንኛውም ቤቶች መስሪያነነት ያገለግላል፡፡
- ፕላስቲክ ታይሉን ከማንጠፋችን በፊት ቦታው የተስተካከለ፣ሊሾ እና ከማንኛውም ቆሻሻ የፀዳ መሆን አለበት፡፡
- የሚሰራው በኖችድ ትራወል/Notched trowel/ ሲሆን ማጣበቂያውን ከተቀባ በኋላ ከ 20-30 ደቂቃ በመጠበቅ
ታይሉን ይነጠፋል ፡፡

የሲሚንቶ ታይል እና ንጣፍ/cement bonded tile and slab/

ቴራዞ/terrazzo/፡-

- ቴራዞ ማለት በሁለት ደረጃ ይሰራል ፡፡


- የመጀመሪያው ደረጃ ከተሰራ በኃላ ሁለተኛው ይደረባል፡፡
- የመጀመሪያው የሲሚንቶ ውህድ ሲሆን ሁለተኛው ግን አርማታ ነው፡፡
- ሁለተኛው የእቨነ በረድና፣ የሲሚንቶ ፣ አሸዋ ውህድ አርማታ ነው፡፡
- የቴራዞ የላይኛውን ክፍል ሲሞረድ የሚያምር ይሆናል፣ለስላሳና ንፁህ ንጣፍ ይሆናል፣
- በጣም ጠንካራና ሰው በሚበዛበት ቦታ እና መንገድ ላይ ይሰራል፣
- ንጣፉ መፋፋቅ ወይም መላላጥን ይቋቋማል፣

ፀባይ/
- የቴራዞ ንጣፍ በጣም ጠንካራ ነው፣
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

- መሰባበርና መፋፋቅን ይቋቋማል፣


- በቀላሉ ይፀዳል እና ውርጭን ይከላከላል ነገር ግን አሲድን አይከላከልም ምክንያቱም የተሰራበት
ሲሚንቶ ስለሆነ ነው፡፡

የተፈጥሮ ንጣፎች/Natural stone /


ግራናይት/granite/
- የግራናይት ድንጋይ በጣም ጠንካራ ንጣፍ ነው፡፡ ይህን የምንጠቀምበት ሰው በሚበዛበት ቦታ እና
መንገድ ላይ እንጠቀመዋለን፡፡
- በጣም አሲድና ርጥበት በመሚበዛበት ቦታ እንጠቀመዋለን ነገር ግን ለየት ያለ ችግር ከሌለ
አንጠቀመውም ምክንያቱም በጣም ውድ ነው፡፡

እብነበረድ/marble/

- ይህን የንጣፍ አይነት የምየምንጠቀመው ለማንኛውም ቤቶች መስሪያ ያገለግላል፡፡ ማለትም


 ለመኖሪያ
ቤት
 ለሆስፒታል እና
 ለሲኒማ ወዘተ ያገለግላል፡፡
- የተለያዩ ቅረፅ እና መጠን አላቸው፡፡
- በጣም ውበት ያለውና ጠንካራም ነው፡፡
4. ማጣበቂያ/
Adhesive /

ማጣበቂያ
በጣም
ዘመናዊ
ቴክኖሎጁ
ያፈራው
ሲሆን
በፋብሪካ
ተመርቶ
በደረቅ እና
ፈሳሽ ውህድ
መልኩ
ይመጣል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

5. የርጥበት መከላከያ /waterproofing/


- የርጥበት መከላከያ ማለት ከወለል በታች እና ከወለል በላይ ላለ ፍሳሽ ወደ መሰረቱ ርጥበት እንዳይሰርግ የሚከላከል
ነው፡፡
 የርጥበት መከላከያ አይነቶች
በፈሳሽ/liqud/ መልክ ያሉ
በወረቀት/sheet/ መልክ ያሉ
ለመሰረት መሰሪያ ፕሪመር/substrate primer/

በፈሳሽ/liqud/ መልክ ያሉ

I. አክራይልስ/acrylices/
II. ፖሊዮሪዝን/polyurethane/
III. ከስሚንቶ የሚሰራ/cementitious/
IV. ሬንጅ/bitumens/

አክራይልስ /acrylices/
- ዳምፕፍሌክስ /dampflex/
- ዳምፕፍሌክስ ሪኦ /dampflex Reo/
- ዱራፍሌክስ /duraflex/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

 ዳምፕፍሌክስ /dampflex/

- ከነጭ አክራይልስ የሚሰራ ውሀ የማያበላሸው ነው፡፡


- ዳምፕፍሌክስ የምንጠቀመው ሰው ሰራሽ ባህሮች ግድግዳ ላይ ለፋይበር ገላስ መረብ መለጠፊያነት ያገለግላል፡፡

- ይህን የርጥበት መከላከያ 4 ሊትር እስከ 1.5 ሜ 2 ለሚሸፍን የፋይበር ግላስ መረብ ያሰራል፡፡

 ዳምፕፍሌክስ ሪኦ /dampflex Reo/


- ይህ የርጥበት መከላከያ መሰረት/substrate/ መሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን የግድግዳ ወይም የወለል መገጣጠሚያ አካባቢ
እንጠቀመዋለን፡፡
- 15 ሊትር የርጥበት መከላከያ ዳምፕፍሌክስ ሪኦ /dampflex Reo/ 1 ሚሜ ውፍረት ላለው ደረቅ ሜምብሬን እስከ 10 ሜ 2
ይሸፍናል፡፡ነገር ግን 0.6 ሚ.ሜ ውፍረት ላለው ደረቅ ሜምብሬን እስከ 15 ሜ 2 የሸፍናል፡፡

 ዱራፍሌክስ /duraflex

- ብቸኛ የውጭ ግድግዳ ውሀ መከላከያ ፣ ብዙ ቦታመሸፍን የሚችል እና ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል ነው፡፡


- በማንኛውም ቤት ሊሰራ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡-አርማታ፣ገርፍ፣አሉምንየም፣ብረት፣ከበሎኬት፣ጡብ እና ከእንጨት ግድግዳ ወዘተ
ይሰራል፡፡
- የተለያዩ ቋሚ ቀለሞች አሉት፡፡እነሱም፡-ነጭ፣ገሬይ እና ብራውን ሆኖ ይገኛል፡፡
- ለጣራ 500 ማከሮ ውፍረት ላለው ደረቅ ሜምብሬን እስከ 1.1 ሜ 2/ሊትር ይሸፍናል፡፡
- ለተሰነጣጠቀ አካባቢ 1000 ማከሮ ውፍረት ደረቅ ሜምብሬን እስከ 0.5 ሜ 2/ሊትር ይሸፍናል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

- ለመገጣጠሚያ/joint/ ከ 500-1100 ማክሮ ውፍረት ደረቅ ሜምብሬን እስከ 0.5-1.1 ሜ 2/ሊትር ትክክለኛ ማጠናከሪያ
እጠቀመዋለን፡፡

ፖሊዮሪዝን / polyurethane/
- ኬ 10 ፕላስ/K 10 plus/

 ኬ 10 ፕላስ/ K 10 plus/
- ከውሃ የሚሰራ ፖሊዮሪዝን የርጥበት መከላከያ ነው፡፡ይህን የርጥበት መከላከያ ለውስጥና ለውጭ ፍሳሽ ለሚበዛበት ቦታ
እንጠቀመዋለን፡፡ለምሳሌ፡-መታጠቢያ ገንዳ፣ሻውር፣በረንዳ እና ጣራ ወዘተ ናቸው፡፡
- 1 ሚሜ ውፍረት ላለው ደረቅ ሜምብሬን 13 ሜ 2 ያሰራል፡፡
- 0.8 ሚሜ ውፍረት ላለው ደረቅ ሜምብሬን 16 ሜ 2 ያሰራል፡፡
- 0.6 ሚሜ ውፍረት ላለው ደረቅ ሜምብሬን 20 ሜ 2 ያሰራል፡፡

ከስሚንቶ የሚሰራ /cementitious/


- ዳቪኮ ኬ 11 /davco k11/

ዳቪኮ ኬ 11 /davco k11/


- በብሩሽ ወይም በመርጫ ይሰራል፡፡
- ከስሚንቶ የሚሰራ ሲሆን ለግንብ እና ኮንክሪት ግድግዳ የርጥበት መከላከያ ነው፡፡

ሬንጅ/bitumens/
 የሬንጅ ርጥበት መከላከያ አይነቶች
- የሬንጅ ቀለም/bitumen panit/
- ብሩሸብል የርጥበት መከላከያ/brusheble waterproof/
- ስሊቨር ሸልድ/seliver sheld/
- አኩስ ሬንጅ/aqueous bitumen/
- ቢቲኮት ቁጥር -3/bitkote no 3/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

- ቢቲኮት ቁጥር-5/ bitkote no 5/

ስዕል 11- ቢቲኮት ቁጥር-5/ bitkote no 5/

በወረቀት /sheet/ መልክ ያሉ

በወረቀት/sheet/ መልክ ያሉ የርጥበት መከላከያ አይነቶች

- ፒቪሲ/PVC/ polyvinyl chloride

- ኢፒዲም/EPDM/ ethylene propylene diene monomer rubber/


- ቡታን/Butane/

- ኢሲቢ/ECB/ ethylene cop bitumen/


- ቢቶኒ ውህድ/Bitonie composite/
ለመሰረት መሰሪያ ፕሪመር/substrate primer/
- ማጣበቂያ/adhesive/
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

- ድሬን ሴል/drainage cell/


- መከላከያ ቦርድ/protaction board/
 የርጥበት መከላከያ በተለያዩ ዘዴ ይሰራል፡፡
- በወረቀት//መልኩ የሚለጠፍ እና የሚረጭ የርጥበት መከላከያ አለ፡፡
- የርጥበት መከላከያ ሬንጆን በሙቀት ስሜት ይዋሃዳሉ፡፡
- በፈሳሽና በቅባት መልኩ እና ከስሚንቶ የሚሰሩ የርጥበት መከላከያ አሉ፡፡

5. ውሃ /Water/:-
ውሃ የንጣፍ ስራ በሚዘጋጅበት ወቅት የማጣበቂያ ጥሬ ዕቃዎችን ለማደባለቅ ይጠቅማል፡፡ ለንጣፍ ሥራ የሚሆን ውሃ
ንፁህ(የሚጠጣ) መሆን አለበት፡፡ ውሃ በሞርታር ዝግጅት ጊዜ በሚጨመርበት ወቅት እንዳይበዛና እንዳያንሰ በሚገባ መጠኑን ጠብቆ
መጨመር ተገቢ ነው፡፡ ካነሰ በሚገባ ሲሚንቶውንና አሸዋውን ሳያርሰው ይቀራል በጣም ከበዛም ሞርታር ይቀጥንና ጥንካሬውን ያጣል፡፡
እንዲሁም ከመቅጠኑ የተነሣ ለአሠራር ፍፁም የማያመች ይሆናል፡፡

6. የንጣፍ ስራ ሂደት
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

/ Carrying out tile laying work/


1. ቦታውን ማፅዳት ወይም መፈተሽ/ Checking and cleaning the surface/
የቦታው /Back Ground/

- ቦታው ላይ ንጣፍን ከመስረተዎ በፊት በደንብ ማረጋገጥ አለበዎት ቦታው/Back Ground/ ወይም መሰረቱ
ማሟላት ያለበት የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነሱም፡-
 ጠንካራ
 የተረጋጋ
 አስተማማኝ
 በጣም ለስላሳ ያልሆነ
 ከዘይት ቀለም የነፃ
 ከዘይት ወይም ከግሪስ የነፃ
 ከአቧራ የነፃ
 የተሰባበሩ ነገሮች የሌሉት
 ከጀሶ ነፃ የሆነ
 ቀጥ ያለ እና እኩል
 የግምብ መገጣጠሚያዎች ዝግ የሆኑ
 በውጥረት ጊዜ የማይሰነጠቅ
- ቦታው/back ground/ ማሟላት ያለበትን ከላይ
የተዘረዘረ ሲሆን ግድግዳ ከሆነ አንድ እጅ ልስን/splsh coat/ ነፁህና ጠንካራ በሆነ አሸዋ 1፡1 or 1፡2

2. የሞርታር
አይነቶች/

Types of mortar/
- የወለልና የግድግዳ ንጣፎችን ለመስራት ሁለት አይነት የሞርታር አነጣጠፍ አሉ፡፡ እነሱም፡-

 የሞርታር ዘዴ/ Thick bed method/


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

 የግሉ ዘዴ/ Thin bed method/

I. በሞርተር ዘዴ/ Thick bed method /


- በሞርተር ዘዴ/ Thick bed method /የቆየ እና ለብዙ ዓመት ሲሰራበት የነበር ሲሆን የሚሰራው
ከአሽዋ፣ስሚንቶ እና ውሃ ነው፡፡ ይህ ሞርታር መልካምና መጥፎ ጎኖች አሉት፡፡
1. መልካምና ጎኖች/ advantage /
- ሞርታሩን በፈለግነው ቦታ እናገኘዋል፡፡
- እስከ 2 ሴሜ ለሚደረስ ያልተስተካከለ ቦታ ካለ በቀላሉ ማስተካከል እንችላለን፡፡
- በጣም ርካሽ ነው፡፡
2. መጥፎ ጎኖች/ disadvantage /
- ፈጥኖ አይደረቅም፡፡
- ለመስራት በጣም ልምድ ይፈልጋል፡፡

በሞርታር የአሰራር / Thick bed method /ቅደም ተከተል

 ከስዕሉ እንደምትመለከቱት የአጀማመር ዘዴ ነው፡፡


1. የክፍሎን ሁሉንም ግድግዳዎችና ኮርነሮች መፈተሽና መለካት
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

2. ቱንበውን ማንጠልጠል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

3. የግድግዳ ሲሆን ከዋናው በር መሬት 4 ሴሜ እና የንጣፉን መጠን ጨምረን /ደምረን/ ሪጋውን እንለጠፋለን፡፡
ነገር ግን የወለል ከሆነ ከወለሉ በምንፈልገው ከፍታ የጎማ ውሃ ልክ እናዞራለን፡፡
- ውሃልክ ካዞርንበት መስመር ወደታች እስከወለሉ ድረስ ያለውን በሜትር ለክተን 4 ሴ.ሜ እንቀንሳለን፡፡
- በ 4 ሴ.ሜ ልክ ገመድ እንወጥራለን፡፡
4. በአንደኛው ጐን ንጣፍን መጀመር /መለጠፍ/
5. መገጠገጣጠሚው እኩል እንዲሆን እስፔሰር መጠቀም አለብን፡፡
6. በየጊዜው ስሚንቶ እንዳይጣበቅበት ማፅደት
7. ስራችን ስንጨርስ መገጣጠሚያዎች መሙላት፡፡
8. ንጣፈን በስፖንጅ ማጠብ

II. በግሉ /ማጣበቂያ/ Thin bed method /


- በደረቅ /በዱቄት/ እና ፈሳሽ ውህድ መልኩ ይመጣል፡፡ ይህ ማጣበቂያ የሚሰራው ከአሸዋ፣ ሲሚንቶ እና
ከተለያዩ ኬሚካል ነው፡፡ ይህ ሞርታር መልካምና መጥፎ ጎኖች አሉት፡፡
A. መልካም ጎኖች( advantage)
- በፍጥነት ለመስራት ይጠቅማል
- ሰራተኛው በቀላሉ መማር ይችላል
B. መጥፎ ጎኖች( disadvantage)፡-
- ጥሬ እቃው በቀላሉ በሀገራችን አይገኝም
- ይህ ማጣበቂያ ከስሚቶና አሸዋ በጣም ውድ ነው፡፡

ለስራ አመቺ እና ፈጥኖ የሚደርቅ ነው፡፡ ነገር ግን ከመጠቀማችን በፊት ከጣሳው ወይም ከቀረጢቱ ላይ ያለውን
መመሪያ መከተል አለብን እነዚህ ማታበቂያዎች የተለያዩ አላማ አላቸው፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

የማጠበቂያ ዓይነት ክፍል የመጠቀሚያ ቦታ ለወለል ለግድግዳ


/types of adhesive/ Classification

ከሲሚንቶ የሚሰራ/cement based/


C1 or C2 በርጥብ እና ደረቅ ይሆናል ይሆናል
በሚረጭ/በፈባሻ/ መልኩ የሚሰራ
/Dispersion/ D1 or D2 በርጥብ እና ደረቅ ይሆናል
ለመገጣጠሚያ መሙያ/grout/
በርጥብ እና ደረቅ ይሆናል ይሆናል
ከሲምቶ የሚሰራ/cement based/ CG1 Or 2
በኢፖክሲ የሚሰራ /Epoxy based/ በርጥብ እና ደረቅ ይሆናል ይሆናል
RG

ማስታወሻ፡- ማጣበቂያው የተመረተበትን ማረጋገጥ አለበዋት፣ ከላይ እንደተገለፀው የመደብ ቁጥር 1 ማለት
መሰረታዊ ፀባይ (standared property) 2 ማለት ደግሞ የተሻሻለ ማለት ነው፡፡ በዲስፕረሽን የተሰራው ማጣበቂያ
D2 ለርጥበት ምቹ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡

- ማጣበቂያ የምንቀባበት ቦታ ትክክልና ቀጥ ያለ መሆን አለበት ነገር ግን ካልሆነ ማስተካከል አለብን፡፡ በስዕሉ ላይ
እንደሚታየው ከቀጥተኛና ትክክል መሆን አለበት ነገር ግን ከቀጥታ መሰመሩ ጋር ያለው ልዩነት ከ 1 ሚ ሜ
መብለጥ የለበትም፡፡

ቦታው/back groud/ ትክክል ካልሆነ ልኬት መለካሄድ አይቻልም ፡፡


በግሉ/ Thin bed method / አነጣጠፍ ዘዴ ንጣፍ የማይሰራባቸውና አስቸጋሪ ቦታዎች ለምሳሌ፡-
 ጀሶ ፡- ምቹ አይደለም
 የጀሶ ቦርድ፡- ሞርታር በጣም ደካማ እና ውሐን አይከላከልም
 ዘመናዊ ቦርድ ትክክለኛ ማጣበቂያ ከሆነ ችግር የለውም ነገር ግን ትክከለኛ ካልሆነ አይቻልም፡

ማስታዎሻ፡- ነገር ግን ለእነዚህ አስቸጋሪ ቦታዎች ሁልጊዜ የርጥበት መከላከያ /Primer/መጠቀም አለብን፡፡

- ይህ የርጥበት መከላከያ 3 ዓይነት አላማ አለው፡፡


 አቧራዎች ከቦታው ላይ የማጣበቅ አቅም አለው
 ውሓ እንዳይሰርግ ይከላከላል
 ንጣፍ እና ማጣበቂያው ከቦታው ላይ እንዲጣበቁ ያደረጋል፡፡
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

- የርጥበት መከላከያ በፈሳሽ መልክ የሚመጣውን የሚቀባሙም በብሩሽ ነው፡፡


- ከመስራታችን በፊት ተቀብቶ ለ 24 ሰዓት መቆየት አለበት

የግሉ/ Thin bed method /የአለጣጠፍ ቅደም ተከተል ከወለል እና ግድግዳ ላይ

1. ከግድግዳው እና ወለሉ ላይ የተበላሹ ንጥረ ነገሮች ካሉ እንዳሉ ማረጋገጥ


2. ወለሉ ወይም ግድግዳው ቀጥ እና ለጥ ማለቱን ማረጋገጥ
3. ሁሉንም ግድግዳውን መለካትና ማረጋገጥ እና ሞርታር ማዘጋጀት
4. ማጣበቂያውን መቀባት
5. ወድያውኑ ከተቀባ በኃላ በኞችድ መፋስ/Notched trowel/ መስመር መስመር እንዲሰራ ማድረግ

ስዕል 1.1 የግድግዳ ስዕል 1.1 የወለል

6. ማጣበቂያውን በእጀችን እንነካና ማጣበቅና አለማጣበቁን ማረጋገጥ


7. በትክክል መስራት /መለጠፍ/ መገጣጠሚያዎች
እንዳይዛቡ ስፔሰር መጠቀም
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

ስዕል 1.1 የግድግዳ ስዕል 1.1 የወለል

8. ካፀዳነው በኃላ በውሐ የደረቀውን አቧራ ማሰወገድ ደረቅ ጨርቅ መጠቀም

3. የታይል አቆራረጥ/ Cutting tiles/


- መለካት
- ምልክት ማድረግ
- መስታዋት ነገሩን መቁረጥ

- መስበር

- የተሰበረውን ማለስለስ
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

የክብ አቆራረጥ ዘዴ

- መለካት
- ክቡን መለካት ማድረግ

- የታይል መዶሻ ከላይ እና የግንበኛ መዶሻ ከስር በማድረግ ወይም በትራፓኖ/drill/ መብሳት ይቻላል፡፡

- የተበሳውን በምንፈልገው መጠን በጉጠት መስፋት፡፡

4. መገጣጠሚያዎችን መመላት / Grouting /


- መገጣጠሚያዎችን ለመመላት የሚያስፈልግ ምጥጥን /ratio/ ከመገጣጠሚያዎች ስፋት አንፃር ይወሰናል፡፡መገጣጠሚያው ከ/1-
2/ሚሜ ሚሆን ከሆነ በንፁህ ነጭ ስሚንቶ ይሞላል፡፡ነገር ግን መገጣጠሚያው እስከ 5 ሚሜ ከሆነ 2፡12 ሁለት እጅ ስሚንቶ እና
አስራ ሁለት እጅ የታይል ማጣበቂያ/ adhesive/ እንጨምራለን፡፡ከ 5 ሚሜ በላይ ከሆነ 1፡1 ምጥጥን// አንድ እጅ ደቃቅ አሽዋ እና
አንድ እጅ ስሚንቶና ማጣበቂያ/ adhesive / በማድረግ ይሞላል፡፡

የአሞላል ቅደም ተከተል


December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

1. በመገጣጠሚያወች መሐከል የወጣና የደረቀ ማጣበቂያ ካለ መፋቅ


2. መገጣጠሚያውን መሙላት
3. ከወለሉ ወይም ከግድግዳው የተሞላው ሞርታር ጫን አድረጎ በመያዝ ዲያጎናል ማፅዳት፡፡

4.
ስዕል 1.1
የግድግዳ ስዕል 1.1 የወለል

5. የተትረፈረፈውን ሞርታር በጨርቅ ማፅዳት


6. ማጠብ
7. ለሁለት ቀን ሳይነካ መቆየት አለበት

8. የግል ሥራ ፈጠራ /ኢንተርፕርነርሽፕ /የቢዝነስ


ማሻሻያ ጥበብ ሥልጠና
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013
December
ለአዲስ አበባ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማሰልጠኛ የተዘጋጀ የንጣፍ ስራ ሞጁል
30, 2013

You might also like