Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 74

/ //

በአዲስ አበባ ቴ ሙያ ት ቢሮ ለአጫጭር ሰልጣኞች የተዘጋጀ የማሰልጠኛ ማንዋል

የሙያዉዘርፍ፡ የሊሾ ስራ(screeding works)

አዘጋጆች፡- አዘጋጅ፡- አሰልጣኞች


1. ሶኒያ ሀብታሙ (0949557317 ) (እንጦጦፖሊ/ቴ/ኮሌጅ)
2. ታምራት ለችሳ(0921597088( (እንጦጦፖሊ/ቴ/ኮሌጅ)
3. ገዛኸኝ ዝቅአርጌ(0922859306) (ምስራቅ ፖሊ/ቴ/ኮሌጅ )

መጋቢት 2010
የሰልጣኞች ፕሮፋይል በአጭር ስልጠና

በዘላቂ የሊሾ ስራ በአጭር ስልጠና ለመሰልጠን ሰልጣኞች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች/ፕሮፋይል


ሀገራችን በያዘችው የቴክኖሎጂ ሽግግር ፣ፖሊሲና ስትራቴጂ እውን ከማድረግ አንፃር እና የዜጎችን የስራ እድል መፍጠርና
ማስፋት ኢኮኖሚውና ገበያው የሚፈልገውን የበቃ የሰው ሀይል ከመፍጠርና ከማብቃት አኳያ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናና የሙያ
ብቃት ማረጋገጥ አስፈላጊ ስለሆነ ከተለያዩ የኮንስትራክሽን የስራ ዘርፎች አንዱ ከሆነው የሊሾ ስራ በአጫጭር ስልጠና
ሰልጣኞች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች/ፕሮፋይል የሚከተሉት ናቸው፡፡
 በማህበር ተደራጅቶ ለመስራት ፍላጎት ያለው/ያላት
 በጉልበት ስራ የአካል ብቃትና የአእምሮ ዝግጁነት ያለው/ያላት
 እድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ/የሆነች
 ማንኛውም ዜጋ
 ለለውጥ ዝግጁ የሆነ/የሆነች
 ፆታ አይለይም

አላማ
- ከዚህ በፊት በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት( ኮሌጅ) በልምድ ክህሎት ያላቸው አንቀሳቃሽ
እውቀታቸውን በማዳበር በራስ የመተማመን ስሜትን እንዲያጎለብቱ፣ ውጤታማ እንዲሆኑና
ህብረተሰባችን በመስኩ የሚፈለገውን አገልግሎት እንዲያገኝ ማስቻል ነው፡፡

ሊሾ (cement screed)
በዚህ የስልጠና መጨረሻ ሰልጣኞች
1 በመስክና በወርክ ሾፕ የሚደረጉ የጥንቃቄ ህጎች ያውቃሉ፡፡
2 የካይዝን ትግብራን ይሰለጥናሉ፡፡
3 ስለ ቀላል ልኬት አወሳሰድ ይሰለጥናሉ፡
4 ንድፍ፣ማፕ እና የስራዝርዝር አንብቦ መረዳት፤
5 የሊሾ ስራ ግብአት አዘገጃጀትይሰለጥናሉ፡፡
6 የሊሾ ስራ ይሰለጥናሉ፡
7 የስራ ቦታን ማጽዳት
8 የግል ሥራ ፈጠራ /ኢንተርፕርነርሽፕ /የቢዝነስ ማሻሻ ጥበብ ይሰለጥናሉ

ለስልጠናው የተካተቱ የብቃት አሀዶች


Unit of competance Module code and Learning out come Hours
title
ስለ ቀላል ልኬት አወሳሰድ CON FCW1 01  Select measuring instruments
ይሰለጥናሉ፡፡ Carry Out 0910
Measurements and 10
Simple Calculations

2
ንድፍ ‹ማፕ ና የስራ ዝረዝር CON FCW1 M03  Identify types of drawings and their 5
አንቢቦ መረዳት 0111 Purposes.
(read and interpretplans
and working drawing

የሊሾ ስራ /cement CON FCW1 10 09 42


screeds 10  Place screeds/የሊሾ ሽራ
 Clean up work area/ የስራ ቦታን ማጽዳት

Use Construction CON FCW1 02 በመስክና በዎርክሾፕ የምደራጉ የጥንቃቄ ህጎች/ 5


Hand and Power 0910
apply safety materials የግብአት አዘገጃጀት
Tools/የእጅ መሳርያ እና
ማሽን መጠቀም
ካይዘን apply kaizen CON FCW 1 18 - 5 ቱማዎች/5s 12
- 7 ቱ ብክነቶች/
0910
የግል ሥራ ፈጠራ CON FCW 1 17  concept and scope of 6
/ኢንተርፕርነርሽፕ /የቢዝነስ entrepreneurship
ማሻሻያ/develop and 0910
understanding
entrepreneurship

የስልጠና ሰዓት እና የግብዓት ዝርዝር


ዝርዝር ተግባራት
ይዘት ስልጠናው የሚፈጀው ጊዜ/ሰዓት ግብአት እና የእጅ መሳሪያ

ንድፈ ተግባር ትብብር ስልጠና
ሀሳብ
1. ንድፍ፣ማፕ እና የተሰጠንን ንድፍ ማንበብ 2 3 - - ፕላን
የምንሰራዉን ስራ - ወረቀት
የስራዝርዝር አንብቦ
ስፋት‹ ዉፍራት አንብቦ
መረዳት መረዳት

2. በመስክና በወርክ ሾፕ - የአካል ደህንነት ጥንቃቄ 2 3 - -ቱታ(over cloth)


የሚደረጉ የጥንቃቄ ህጎች ደንቦች
3
- የእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች -መነጽር (goggle)
ደህንነትና ጥንቃቄ ደንቦች -ጫማ(safty shoes)
- የስራ ቦታ ደህንነት ጥንቃቄ -ኮፍያ(helmet)
ደንቦች -የጆሮ ማፈኛ(ear protection)
- የጥሬ እቃ ጥንቃቄ ደንቦች -የእጅ ጓንት(glove)
- የእሳት አደጋ መከላከያ -የቁስል ፕላስተር
ጥንቃቄ ደንቦች -አልኮል
- የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ - የእሳተ አደጋ መከላከያ(sprinkler)
መስጫ
3. የካይዝን ትግብራ - 5 ቱማዎች 4 8 -
ስልጠና - 7 ቱ ብክነቶች
4. የልኬት አወሳሰድ - መግቢያ 4 6 - እስክብሪቶ
- ወጥ ቅርፅ ያላቸውና ወጥ - ወረቀት
ቅርፅ የሌላቸው ምሰሎችን - ካልኩሌተር
ስፋት ማስላት - ቱምቢ
- ይዘትን ማስላት - ጎማ ውሃልክ
- ሪጋ
5. የግብአት አዘገጃጀት እና 4
መረጣ ስራ

6. - የሊሾ ጥቅሞች 4 33 -
የሊሾ ስራ - የሞርታር አይነቶች - ሲሚንቶ/cement
- የሊሾ አሰራር ዘዴ - አሸዋ/sand
- ቦታውን ማፅዳት ወይም - ውሀ/water
መፈተሸ - ጠጠር /aggregate
- ኖራ /lime
- መፋስ
- ማንኪያ
- ሪጋ
- ውሃ ልክ
- አካፋ
- ገመድ
- መሮ
- ባልዲ
- ሜትር
- ጎማ ውሃልክ

7. የስራ ቦታን ማጽዳት ----- 1 - አካፋ


- ጋሪ
- መጥረግያ
8. የግል ሥራ ፈጠራ 2 4 - እስኪብርቶ
/ኢንተርፕርነርሽፕ - ወረቀት
/የቢዝነስ ማሻሻያ -

አጠቃላይ ለስልጠናው የሚያስፈልገው ሰዓት 80 ሰዓት

4
1. መግቢያ

በአሁኑ ወቅት ሳይንስና ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ፍጥነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሄዱ የሊሾ ስራም እየተሻሻለ
በዘመናዊና ቀላል በሆነ ዘዴ የህብረተሰቡን ፍላጎት በማሟላት ላይ ይገኛል፡፡
ከሊሾ ስራ የሚገኘውን ከፍተኛ የህብረተሰብ ፍላጎት ለማሟላት ሙያው የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት
ያለው የሊሾን ስራ ባለሙያ በማስፈለጉ ለዚሁ ስራ የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያበረክት የስልጠና ጽሁፍ
ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡
በዚህ የስልጠና ጽሁፍ የሊሾ ስራ ቅድመ ተከተሉን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን በዋናንት በመስክና በወርክ ሾፕ
የሚደረጉ የጥንቃቄ ህጎች ፣የካይዝን ትግብራ ፣የሊሾ ስራ ልኬት ፣የሊሾ ስራ ግብአት አዘገጃጀት ፣የሊሾ ስራ መስራት እና የግል
ሥራ ፈጠራ /ኢንተርፕርነርሽፕ /የቢዝነስ ማሻሻያ ጥበብ ያካተተ ነው፡፡

ይህንን የስልጠና ጽሁፍ መሰረት በማድረግ አሰልጣኝ መምህራን የራሳቸውን የፈጠራ ክህሎት በማከል
ስልጠናውን ቢያከናውኑ ትምህርቱን የበለጠ ውቴታማ እንደሚያደርጉት የሚተማመኑ ሲሆን ይህ የስልጠና
ጽሁፍ ለአጫጭር ስልጠናና ለመለስተኛ ደረጃ የሊሾ ባለሙያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና (coc)
ተፈታኞችም ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ይታመ

1 .በመስክና በወርክሾፕ አካባቢ የሚደረጉ የጥንቃቄ ህጎች (CON FCW1 02 0910 )

1.1 መሠረታዊ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች


ዓላማ፡-
ሥልጠናው እንደተጠናቀቀ ሰልጣኞችን በስራ ጊዜ የአካል፣ የጥሬ እቃ፣ የእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች ለስራ ቦታ
ተገቢውን የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች በመገንዘብና በመጠቀም የተግባር ስራቸውን ያከናውናሉ፡፡
መግቢያ፡

5
በማንኛውም የተግባር ስራ ወቅት አንድ ባለሙያ በሙያው ያገኘውን እውቀትና ክህሎት በተገቢው ስራ ላይ ለማዋል
በቅድሚያ የደህንነት፣ የጥንቃቄ ደንቦችን መጠቀም አለበት፡፡ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች በአካል በእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች
ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስና ለመከላከል እንዲሁም ጥሬ እቃዎችን በቁጠባ ለመጠቀምና ስራን ውጤታማ
ለማድረግ ይጠቅማል፡፡አጠቃላይ መሠረታዊ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦችን በአምስት ክፍሎች መመደብ ይቻላል፡፡

1.2 የአካል የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች


የአካል የግል የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች ፡-
- ተገቢ የሆነና ለስራ አመቺ የሆነ ልብስና/የማያንሸራትት ወፍራም ሶል ያለው ጫማ መጠቀም፣እንደ
አስፈላጊነቱ የዓይን መከላከያ መነጽር፣ የእጅ ጓንት፣ የራስ ቆብ ማድረግ፣የተለያዩ ጌጣጌጥ ነገሮችን በአካል
ላይ አለማድረግ፣

መነጸር
(goggle)

ቱታ
(Over oll cloth)

ኮፍያ (helmat)

6
የጀሮ ማፈኛ (ear protaction) ጓንት
(glove)

የጉልበት ማፈኛ (knee


pad) ጫማ (safety shoes)

የአካል የግል የደህንነት መጠበቂያ አልባሣት


1.3 የእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች የደህንነት ጥንቃቄ ደንቦች
 መሳሪያውን ለተሰራበት አገልግሎት መጠቀም
 ስለት በሌላቸው፣ በደነዘዙ እጀታ በሌላቸውና በተበላሹ መሳሪያዎች አለመጠቀም
 ስለታም መሳሪያዎችን በኪስ ውስጥ አለመያዝ፣ በአግባቡ መቀባበል፡፡
 አካልን ከሚቆርጡ መሳሪያዎች ማራቅ
 ለማሽኖች የሚያስፈልገውን ዝርዝር የጥንቃቄ መመሪያዎች ከተረዳን በኋላ መጠቀም፣
 የእለት ስራ እንደተጠናቀቀ መሳሪያዎቹን በማጽዳት በተገቢው የማስቀመጫ ሳጥንና በቦታቸው መመለስ፣

3.4 የስራ ቦታ ደህንነት ጥንቃቄ ደንቦች

 የስራን ቅደም ተከተል ማወቅና በየደረጃው ማከናወን፣


 በመተባበር መስራትና አስፈላጊ እንቅስቃሴ፣ ልፊያ፣ ጩኸት አለማድረግ፣
 ቁርጥራጭ ነገሮችን በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ፣
 የፈሰሱ ዘይትና ቅባቶችን ማፅዳት(ማስወገድ)፣
 የዕለት ስራ ሲጠናቀቅ የስራ ጠረጴዛንና የስራ ቦታን ማፅዳት፣
 በስራ ቦታ አለማጨስ፣
7
 በቀላሉ በእሳት ተቀጣጣይ ነገሮችን በብረት ሳጥን ውስጥ ማከማቸት፣
 የአደጋ የማምለጫ በሮችን ፣የአደጋ ምልክቶችን ማወቅ፣

1.5 የጥሬ እቃ የደህንነት የጥንቃቄ ደንቦች


 የተለያዩ የሊሾ መስሪያ ቁሳቁሶችን በዓይነታቸውና በመጠናቸው ለይቶ ማስቀመጥ፣
 ጥሬ እቃዎችን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣
 በስራ አካባቢ እንቅፋት የሚሆኑ ተረፈ ምርቶችን ማስወገድ፣

1.6 የእሳት አደጋ መከላከያ የጥንቃቄ ደንቦች


 እሳትን በቀላሉ ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ ዘይት፣ የቀለም ውጤቶች፣ነዳጅ እና በአግባቡ ያልተዘረጋና የተላላጠ
የኤሌክትሪክ መስመሮች የእሳት አደጋ መንስኤዎች ናቸው፡፡
 ተቀጣጣይ ነገሮችን በብረት ሳጥን ውስጥ ከድኖ በማስቀመጥና በአግባቡ መዘርጋትና የተላላጡትን ሽቦዎች በመሸፈን
የእሳት አደጋ መንስኤ መከላከል ይቻላል፡፡

1.7. የመጀመሪያ ህክምናና እርዳታ መስጫ


- በስራ ጊዜ አደጋን ለመቀነስና ለመከላከል ሀሳብን ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ በማድረግ ተገቢውን የደህንነት
የጥንቃቄ ደንቦች በመከተል ማከናወን ተገቢ ሲሆን ነገር ግን ይህንን በማናደርግበት ጊዜ አደጋ ሊያጋጥም
ይችላል፡፡
- በመሆኑም በስራ ቦታ አደጋ በሚደርስበት ጊዜ አደጋው የደረሰበት የሰውነት አካል እንደአስፈላጊነቱ በጤና
ተቋማት ህክምና እስኪደረግለት ድረስ በስራ ቦታ/ወርክሾፕ/ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ለማድረግ በስራ ቦታ
የመጀመሪያ ህክምና መስጫ ቢያንስ የቁስል መጥረጊያና በሽታ አምጪ ረቂቅ ህዋሳት መከላከያ ፈሳሾችንና
የተጎዳን አካል መሸፈኛና ማሸጊያ ጨርቅና ፕላስተር ያካተተ የህክምና ግላቭ(ጓንት) ሣጥን መኖር አለበት፡፡
በተጨማሪም እርዳታውን ለማድረግ ተገቢ ሥልጠና የወሰደ ባለሙያ ያስፈልጋል፡፡

8
የፈርስት ኤይድ ሳጥን

2. የካይዝን ትግብራ CON FCW 1 17 0910


 5 ቱማዎች
 7 ቱብክነቶች

ለውጥ እፈልጋለሁ?

9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
v

23
24
25
26
27
28
29
30
3 ቀላል ልኬት አወሳሰድ CON FCW1 01 0910

 መግቢያ
 ወጥ ቅርፅ ያላቸውና ወጥ ቅርፅ የሌላቸው ምሰሎችን ስፋት ማስላት
 ይዘትን ማስላት
 ለቆመ ሕንፃ ትክክለኛ ልኬት መውሰድ

1.1 መግቢያ
ልኬት መውሰድ ማለት የአንድን ቁስ አካል ቁመት፣ርዝመት፣ወርድ፣ዙሪያ፣ወዘተ...መጠን በመስፈር
የምናውቅበት ሂደት ነው፡፡ የልኬትን መጠን የምናውቅበት የተለያዩ የልኬት መስፈሪያ አሀዶች/units of
measurements/ አሉ፡፡ እነሱም ሜትር፣ ሳንቲ ሜትር፣ ሚሊ ሜትር፣ ወዘተ... ናቸው፡፡
ልኬትን ለመውሰድ የቁስ አካሉን የጂኦሜትሪ ምስል/ቅርፅ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ምስሎችም ክብ፣ሦስት
ማዕዘን ፣አራት ማዕዘን፣ወዘተ...ሲሆኑ የቁስ አካሉን ስፋትና ይዘት ለማስላትና ለማወቅ ይረዳሉ፡፡
መጠነ ዙሪያ (Perimeter measurement)
የአንድ አካል/ምስል ስፋት ለማስላት እነዲቻል መጀመሪያ ቀጥተኛ ልኬት
ወይም መጠነ ዙሪያ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡

ስዕል 1.1 ቀጥተኛ ልኬት/መጠነ ዙሪያ/


ዙ=2(ወ+ር)
የሶስት ጎን ዙሪያ (Perimeter of triangle)

ዙ= ሀ+ለ+ር

31
ስዕል 1.2 ጎነ ሦስት መጠነ ዙሪያ

አራት ጎን

ስዕል 1.3 ጎነ አራት መጠነ ዙሪያ


ትራፒዝይም ዙሪያ (Perimeter of trapezium)

ዙሪያ= ሀ+ለ+ር 1+ር 2


ስዕል 1.4 የትራፒዚየም መጠነ ዙሪያ
1.2 ወጥ ቅርፅ ያላቸቸውና ወጥ ቅርፅ የሌላቸው ምስሎች ስፋት ማስላት (SURFACE AREA
MEASUREMENT)
ጎነ ሶስት Triangle)

ስ, 1/2 × ሀ × ለ
ስዕል 1.5 የጎን ሦስት ስፋት

32
አራት ጎን (square)

ስዕል 1.6 የአራት ጎን (square) ስፋት


ሬክታንግል()

ስዕል 1.6 የሬክታንግል ስፋት


ሮምቦስ( Rhombus)
ስ= ር+ቁ
መግለጫ
ር = ርዝመት
ቁ = ቁመት
ስ = ስፋት
ስዕል 1.7 የሮምበስ ስፋት
ትራፒዝየም (Trapezium): -.

33
ስ = 1/2(ር 1+ር 2) ቁ

ስዕል 1.8 የትራፒዚየም ስፋት

መግለጫ ር 1=ትልቁ ርዝመት


ር 2 =ትንሹ ርዝመት
ቁ = ቁመት
ስ = ስፋት
ክብ (Circle)
ስ =π ሬ 2
መግለጫ π = / 3.14/
ሬ = ሬዲየስ
ስ = ስፋት

ስዕል 1.9 የክብ ስፋት አወሳሰድ

ኢልፕስ (Ellipse)
መግለጫ
ሀ,የረጅሙ ዲያማትር ግማሽ /ራዲየስ/
ለ,የአጭሩ ዲያሜትር ግማሽ
e= ስፋት
ስ=ሀ+ለ
ስዕል 1.10 ኢሊፕስ ስፋት
ወጥ የሌለው ቅርጽ (Irregular shape)

34
የዚህ አይነት ሁኔታሲያጋጥም ዕቃውን ወይም ስራውን በምስሉ በተመለከትነው መሰረት በመከፋፈል ስፋትን
መገመት ይቻላል፡፡ ማለትም በስራው ውስጥ ያሉትን ካሬዎች መቁጠር ይሆናል፡፡

ስዕል 1.11 ወጥነት የሌለው ቅረፅ ስፋት


1.3 ይዘት ማስላት (Volume measurement)
ሲልንደር(cylinder)
ይዘት= π ሬ 2 ቁ
መግለጫ
π = / 3.14/
ሬ = ሬዲየስ
ቁ = ቁመት

ስዕል 1.12 የሲሊንደር ይዘት አወሳሰድ

ፕሪዝም (prism):- የሳጥን ቅርጽ ያላቸው ምስሎች በፕሪዝም


ይጠቃለላሉ፡፡

ይዘት= ሀ*ለ*ቁ
ስዕል 1.13 የፕሪዝም ይዘት
ኮን (cone)

ይዘት= 1/3

35
ይዘት=1/3 π ሬ 2 ቁ
ስዕል 1.14 የኮን ይዘት

የፍራስተም ኮን ይዘት

ይዘት= 1/3 π ሬ 12 ቁ 1 -1/3 π ሬ 12 ቁ 2


ስዕል 1.15 የፍራስተም ኮን ይዘት

ፒራሚድ (pyramid)
ይዘት= 1/3 ሀ*ለ*ቁ

ስ ዕል 1.15 የፒራሚድ ይዘት


1.4 ለቆመ ህንፃ ትክክለኛ ልኬት መውሰድ
የአንድን ቦታ ወይም ህንጻ መጠን ለማወቅ ህንፃውን በተለያዩ አቅጣጫዎች መለካት ያስፈልጋል፡፡ በቀላል ልኬት ሥራ ላይ
ሦስት ዓይነት ልኬቶችን በመውሰድ የአንድን ህንጻ አጠቃላይ መጠኑን መናገር እንችላለን፡፡ እነዚህም፡-
የቁም ልኬት
የርዝመት ልኬት
የወርድ ልኬት
የቁም ልኬት፡- የቁም ልኬት ማለት አንድን ህንፃ ወይም ልስን ከመሬት ወደ ላይ ያለውን ቁመት
የምንለካበት የልኬት ዓይነት ነው፡፡
የርዝመት ልኬት፡- የርዝመት ልኬት ማለት አንዱን ህንጻ ወይም ልስን መሬት ላይ ያረፈበትን ርዝመት
ማለት ሲሆን ርዝመቱ የሚወስነው ህንጻው ወይም ግንቡ መሬት ላይ ሲያርፍ ትልቁ የልኬት መጠን
ያለበትን አቅጣጫ በመውሰድ ርዝመቱን መወሰን ይችላል፡፡

36
የወርድ ልኬት ፡- የርዝመት ልኬት ማለት አንዱን ህንጻ ወይም ግንብ መሬት ላይ ያረፈበትን ርዝመት ማለት ሲሆን ርዝመቱ
የሚወስነው ህንጻው ወይም ልስን መሬት ላይ ሲያርፍ ትንሹን የልኬት መጠን ያለው አቅጣጫ በመውሰድ ወርዱን መወሰን
ይችላል፡

4 ንድፈ ሐሳብና ፕላን ማንበብ እና መተርጎም


(read & interpeat maps, plans&spesification)
ዋናው ዓላማ ፡-
ሰልጣኞች ይህን የኮርስ ስልጠና ከሰለጠኑ በኋላ ማወቅ የሚገባቸው ነጥቦች፡-
- ካርታና ፕላኖችን መለየትና ጥቅማቸውን ማወቅ፣
- በካርታና ፕላን ላይ የተቀመጡ ምልክቶችን ማወቅ አለባቸው፣
- የምህንድስና ንድፍ ሀሳብን ለመተግበር (ለመተርጎም) በካርታውና ፕላኑ ላይ የተቀመጡ መፍቻዎችን
መለየት፣
- የግንባታ ዝርዝሮችን መለየት አለባቸው፡፡
ማውጫ
ክፍል አንድ
1. የካርታና ንድፍ ዝርዝሮች
1.1.1 የካርታ ዓይነቶችና ስዕሎች
1.1.2 የካርታ ዓይነቶችና ጥቅማቸው
2. የንድፍ ስራዎች የተቀመጡ ምልክቶችን ማስተዋል እና ማሻሻል
2.1. የንድፍ ስራዎች የተቀመጡ ምልክቶች ማሻሻል
2.2. በተሰጠው ንድፍ ላይ ዝርዝሮችን (specification) አሁን ካለው ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ማሻሻል
3. መሰረታዊ ምልክቶችና ምህፃረ ቃል (abbreviation)
3.1 በንድፈ ሀሳቡ ላይ የተቀመጡ መፍቻዎች፣ ምልክቶችንና ምፃረ ቃልን መተርጎምና መተግበር፡፡
4. የግንባታ አካባቢ ንድፍ (site plan)
4.1 የአካባቢው ንድፈ ሁኔታዎች
4.2 የአካባቢው ንድፍና አካባቢው

መግቢያ
የህንፃ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት መሟላት ያለባቸው ነገሮች
ሀ) የአካባቢ ጥናት (site investigation or site obsevation)

37
አንድ የህንፃ ግንባታ ስራ ከመጀመራችን በፊት የተለያዩ ነገሮችን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል፡፡
እነዚህም ለግንባታ በታቀደው አካባቢ ላይ ያሰሪው ፍላጎት በግንባታው ላይ ያላቸውን አመለካከት ጥሩ
መሆኑንና አለመሆኑን፣ በአካባቢው ላይ ያሉ ግብአቶች እንዳሉ እና እንደሌሉ በአጥኚዎችም ሆነ
በማህበረሰቡ በኩል ጥሩ የሆነ ክንውኖች ከተከናወኑ፣ ለግንባታው የታቀደው ስፍራ የመሬቱ አቀማመጥ
ለግንባታው የተመቸ መሆኑንና አለመሆኑን፣ ወ.ዘ.ተ ነገሮችን በማጥናት ወደተለያዩ ውሳኔዎች
የሚደረስበት ሁኔታ ወይም ሂደት ነው፡፡
ለ) በግንባታ ላይ በአካባቢው መኖር ያለባቸው ነገሮች (requirements of site plans)
የአንድን ግንባታ ለመስራት የተለያዩ ጥናቶች ከተከናወኑ በኋላ ብዙ ነገሮችን
መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ከእነዚህም ጥቂቶቹ፡-
1) በአካባቢው ላይ ለግንባታ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ወይም ግብአቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ፡፡
2) የሰው ሃይል (labor) በአካባቢው ላይ እንደአስፈላጊው መጠን መኖራቸው ከተረጋገጠ እና ለማግኘት
ቀላል መንገድ የሚሆን ከሆነ፣
3) ግንባታውን ለማከናወን ብቁ የሆኑ ባለሙያተኞች መኖር አለባቸው፡፣
4) መኖር አለበት፣
5) ለሰራተኞች የሚሆኑ መሰረታዊ ፍላጎቶች የተመቻቹ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ ንፁህ ውሃ፣ ምግብ
መጠለያ፣ ትራንስፖርት እና መብራት፣
6) ለሙያተኞች (skill persons) እና ለቀን ሰራተኞ (labor) የሚሆን ሽንት ቤት (Toilet) መኖር አለበት፤
7) .የሰራተኞች (አስተዳደር ኃላፊዎች) የሚሆኑ ክፍሎች (office) ያስፈልጋል፡፡
8) የአካባቢው አየር ንብረት የተስማማ መሆን አለበት፡፡
9) ግንባታው የሚገነባበት ቦታ የተመቸ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ የአፈሩ ዓይነት ጥናት የተካሄደበት መሆን
አለበት፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው ላይ የእሳተ ጎሞራ ፍንዳታ የሚያጋጥመው አለመሆኑን የተረጋገጠ
መሆን አለበት፡፡ ወ.ዘ.ተ. ነገሮችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተሟሉ መሆናቸው ከተረጋገጠ የግንባታው
ስራ በጥሩ ሁኔታ ይጀመራል፡፡

4.1. የአካባቢ ንድፈ ሁኔታዎች

38
የህንፃው አካባቢ ንድፍ

የወለል ንድፍ(Floor plan)

39
የጎን እይታ(Elevation view)

ውስጣዊ እይታ(Section view)


የስራ ዝርዝሮች (specification)
እያንዳንዱ የግንባታ እቃዎች(ግባዕቶች) የራሳቸው የሆነ ዝርዝር አላቸው፡፡
ዝርዝር የምንለው የግባዕቶች ወይም ስራዎች (ትክክለኛው) መግለጫ ነው፡፡ የግባዕቶችን ትክክለኛ ዝርዝር
ማወቃችን ስራው ጥራትና ደረጃውን በጠበቀ መካሄዱን ያግዘናል፡፡ በተጨማሪም ደግሞ ዝርዝሮችን
ማወቃችን በተቋራጩና በደንበኛው መሃከል የሚፈጠረውን ችግር ለመፍታት ያስችለናል፡፡

ዝርዝሮች የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት አለባቸው

40
- በቀላልና በግልፅነት የምንረዳቸው መሆን አለባቸው፣
- ትክክለኛ መሆን አለባቸው፣
- ደረጃውን (standard) የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

የዝርዝር አይነቶች
በአጠቃላይ የዝርዝር ዓይነቶችን በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን ልናያቸው እንችላለን፡
ሀ) የግባዕት ዝርዝር (material specification)
የግባዕት ዝርዝሮችን ለመለየት በተጨባጭ በማየት (physical) እና ኬሚካል ፀባዮችን በሙከራ በማረጋገጥ
የምናውቃቸው ይሆናል፡፡ የግባዕት ዝርዝሮችን ስንለይ የሚከተሉትን ነጥቦች ግምት ውስጥ ማስገባት
ይኖርብናል፡፡ እነሱም ፡-
- ተጨባጭ ባህሪያት ፡- ለምሳሌ ጥንካሬ፣ እድሜ፣ ብርታት የመሳሳብ የመሳሰሉት ሁኔታዎች
- የኬሚካል ባህሪያት ፡-(chemical composition)

- የኤሌክትሪክ ባህሪያት ፡-(Electrical property)


- ሙቀትን የመቋቋም ባህሪያት (ternal property)
- የመልካቸውን ባህሪያት (Appearance) ለምሳሌ ቀለማቸውን፣ ይዘታቸውን ቅርፃቸውን ወ.ዘ.ተ

ለ) የሥራ ጥራት ዝርዝሮች (Workmanship specification)


የሥራ ጥራት ዝርዝሮች አንድን ስራ ንድፍ ስራው ላይ በተቀመጠው ደረጃ መሠረት መሰራቱና
አለመሰራቱን የምናረጋግጥበት የስራ ጥራት ዝርዝር ነው፡፡ እነሱም፡-
 የስራውን መጠን መለካት
 የስራውን ቅደም ተከተል ማየት
 የስራውን ጥራት በሙከራ ማረጋገጥ ወዘተ

5. የግብአት አዘገጃጀት/matiral selection/


A. መገልገያ እቃዎች እና
B. ጥሬ እቃዎች መረጣ

41
I. መገልገያ እቃዎች /Tools & Equipment/
 ለሊሾ መስሪያነት የሚያገለግሉ የተለያዩ መሳሪያዎች አሉ እነሱም፡-
1. የፅዳት መሳሪያዎች /Cleaning Tools/
2. ምልክት ማድረጊያ መሳሪያዎች /Marking Tools/
3. መለኪያ መሳሪያዎች /Measuring Tools/
4. መቁረጫ መሳሪያዎች /Cutting Tools/
5. ማስተካከያ መሳሪያዎች Leveling Tools/
6. ማዋሐጃ መሳሪያዎች /Mixing Tools/
7. ተጨማሪ መገልገያመሳሪያዎች/ additional tools/
1. የፅዳት መሳሪያዎች /Cleaning Tools/
እነዚህ መሳሪያዎች የሚያገለግሉን ለፅዳት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ
A. ብሩሽ /Brush/
- ብሩሽ ማለት የማፅጃ መሳሪያ ሲሆን ሰርተን ስንጨርስ መሳሪያዎችን እናፀዳበታለን፡፡

B. የቁምመጥረጊያ /Broom/
- ይህ መሳሪያ ልክ እንደ ብሩሽ ሰርተን ስናበቃ
የስራንበት አካባቢ የምናፀዳበት መሳሪያ ነው፡፡

C. ስፖንጅ /Sponge/
- ይህ መሳሪያ የሚያገለግለው መገልገያ እቃዎች ለማፅዳት ወይም ለማጠብ ይጠቅማል፡፡

42
2. ምልክት ማድረጊያ መሳሪያዎች
A. ጉልህ እርሳስ /graphite Pencil/
- ይህ መሳሪያ ጥቅሙ ምልክት ለማድረግ ነው፡፡ የሚሰራውም የዚህን ፍላጐት ለማሳካት ነው፡፡

B. መፈቅፈቂያ /Scrapper/
- ይህ መሳሪያ ልክ እንደ ግራፋይት ፔንስል ምልክት ለማድረግ፣አላስፈላጊ ነገሮችን ለመፋቅ ልንጠቀመው
እንችላለን፡፡
3. ማስተካከያ መሳሪያዎች /Leveling Tools/
A. የእጅ ውሐ ልክ /Sprit level/

ይህ የእጅ ውሐ ልክ አግድም /Horizontal/ ፣ቀጥ ያለ ግድግዳ /Vertical/ እና ዲያጐናል /Inclind/ የሆነ ቦታ ወይም
ጠርዝን ለመለካት እንጠቀምበታለን፡፡ ዝርመቱም ከ 80 እስከ 120 ሴ.ሜ ይደርሳል፡፡ የሚሰራው ከብረት፣ሴንቴቲክ
ማቴሪያሎች እና ከእንጨት ነው፡፡ ሶስት በብሎች አሉት፡፡ የመጀመሪየው መሐከል ላይ የሚገኘው አግድም
/Horizontal/ ለመለካት እንጠቀምበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በአንደኛው ጫፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቀጥ ያለ
ግድግዳ /Vertical/ ስንጠቀምበት የቀረው በሌላኛው ጫፍ ላይ የሚገኘው ደግሞ ዲያጐናል /Inclind/ ለመለካት
እንጠቀምበታለን፡፡ ይህ መሳሪያ ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን የምናውቅበት ነው፡፡

B. ሪጋ /Straight edge/
- ይህ መሳሪያ ከብረት /አሉሚኒየም/ ይሰራል ፤ዝርመቱም ከ 2-4 ሜትር ይደርሳል፡፡
- አንድን ቦታ ትክክል ለማድረግ ይጠቅማል፡፡

C. የጐማ ውሐ ልክ /Hose water level/

43
- ይህ የጐማ ውሐ ልክ ብርሐን አስተላላፊ የኘላስቲክ ቱቦ ሲሆን ይህን የምንጠቀም ቀጥ ባለ ገፅ ለይ /ለምሳሌ ግድግዳ ላይ
አግዳሚ መስመር ከቤቱ ወለል በኩል ከፍታ ለማስመር /ለወለልና ኮረኒስ ስራ ያለግላል ውሐ በምንሞላበት ጊዜ
በጉማው ውስጥ ምንም አየር መኖር የለበትም ነገር ግን አየር ከገባበት ልኬቱን በትክክል አያስተላልፍም፡፡

D. ሲባጎ//
- ሲባጎ ወይም ናይለን ገመድ (3 ሚሜ
ውፈረት) የመሰረት ጉድጓድ ሲጣል፣፣ሊሾ ስራ ሲሰራ፣ ንጣፍ
ሲነጠፍ፣ ግንብ ሲገነባ የአናፂ ስራ ሲሰራ የውሃ ልክ መጠበቂያ እንዲሁም ቀጥ ያሉ ገፆችን ለማውጣት
ይረዳል ፡፡

4. መለኪያ መሳሪያዎች /Measuring Tools/


A. ዚግዛግ ሜትር /Foloding Meter/
- ይህ የዝርመት የመለኪያ መሳሪያ ሲሆን የሚሰራው ከተለያዩ 20 ሳ.ሜ ዝርመት የላቸው የእንጨት
/የጣውላ ቁራጭ ይሰራል፡፡

B. መለኪያ ሜትር /Measuring tape/

44
ሜትር ርዝመት፣ ጥልቀት፣ ስፋት፣ ውፍረት ለመለካት የሚያገለግል ነው፡፡ብዙ አይነቶች ሜትሮች አሉ
ከነዚህም ውስጥ ባለ 3, 5, 30, 50 ወዘተ ይገኙበታል ፡፡

5. መቁረጫ መሳሪያዎች /Cutting tool/


- መቁረጫ መሳሪያዎች ከምንላቸው ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል
A. መሮ /Chisel/
- መሮ ማለት ከጠንካራ የብረት ዓይነት የሚሰራ ነው ሁለት ዓይነት መሮ አለ፡፡ እነሱም ጫፉ ጠፍጣፋ
/Flat chisel/ እና ጫፉ ሹል /Pointed chisel/ ይህ መሮ የሚጠቅመን ለመጥረብና ለመቁረጥ
ያገለግለናል፡፡

B. ግራይንደር /angle grinder/


- ግራይንደር በሁለት እጅ እና በአንድ እጅ የሚያዝ ሲሆን ለተለያዩ
ማቴሪያሎች መቁረጫነት እንጠቀምዋለን ለምሳሌ፡- ለኮንክሪት ፣ለድንጋይ፣ለብረት እና ለታይል ወዘተ
መቁረጫነት ያገለግላል፡፡

6. ማዋሐጃ መሳሪያ /mixing tool/


ማዋሐድ መሳሪያዎች /mixing tool/ በሁለት ይከፈላሉ

45
 ማንዋልና ማዋሐድ /Manual mixer/
 ሜካኒካል ማዋሐድ /Mechanical mixer/
1. ማንዋል ማዋሐጃ /Manual mixer/
- ማንዋል ማዋሐጃ የምንላቸው

A. አካፋ /spade/

ይህ መሳሪያ ስሚንቶ እና አሸዋን ለማንሳት/ለመጫን፣ ለማደባለቅ ወዘተ… ያገለግላል

ሜካኒካል ማዋሐድ /Mechanical mixer/


ሞርታር ለማዘጋጀት ስራ በአነስተኛ ጊዜ ፈጣን በሆነ ዘዴ ብዛት ያለው ሞርታር ለማቡኪያ የሚያገለግል ማሽን ነው፡፡አርማታ
በሚቦካበት ጊዜ ሚክሰሩ በተስተካከለ ቦታ መቀመጥና 30-35 ዲግሪ ማንጋደድ ይኖርበታል፡፡ ሞርታር ማቡኪያ ማሽን
ዘወትር ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ በሚገባ መፅዳት/መታጠብ/ አለበት፡፡

7. ተጨማሪ መገልገያ መሳሪያዎች//


1. ማንኪያ/ Trowel/

ማንኪያ መሰረታዊ ከሆኑት የሊሾ ሥራ ዕቃዎች ዋነኛው ሲሆን ሞርታርን፣ ለማነሳት፣ለመሰራጨትና


ለማለስለስ ያገለግላል፡፡

2. መፋስ /Float/

መፋስ ከጠፍጣፋ ብረት/ ወፍራም ላሜራ/ ወይም ከእንጨት የሚሰራ ሲሆን ሊሾ ሲሰራ ለማሰተከከልና
ለማለስለስ ያገለግላል፡፡
መፋስ አይነቶች

46
ባለ ረጅም እጀታ መፋስ/Bull Float፡- ርዝመቱ ከ 1 – 1.50 ሜትር ወርዱ 20 ሴንቲ ሜትር የሆነ ጣውላ
ወይም አሉሚኒየም ከ 1.20 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው እጀታ የተገጠመለት የመፋስ ሲሆን
አግልግሎቱም ስፋት ያለው የልስን ሥራ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ነው፡፡

3. ጋሪ

ለሊሾ ስራ ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር ወዘተ ለማመላለስ ያገለግላል፡፡

4. የአሸዋ ሳጥን

አሸዋን በተፈቀደው መጠን ለመስፈር የሚያገለግል ሲሆን


መጠኑም 50× 40×20 ሳ.ሜ፣ 50×40×18 ሳ.ሜ፣ 50×40×16 ሳ.ሜ ይገኛል

5. ሸንኬሎ/ባልዲ
- ውሃ ወይም ሞርታር ለማመላለስ ያገለግላል

6. ስኳድራ/try square/

ለቅርፅ ማውጫ ሥራ ማዕዘን መለከያ እና ማስተካከያ


ግድፈት መቆጣጠሪያ ሆኖ የገለግላል፡፡

47
7. የአናፂ መዶሻ/claw hammer/
- ለሚስማር መምቻና መንቀያነት ያገለግላል፡፡

8. የሽቦ መጥረጊያ /Wire brush/


- ከቀጫጭን ሽቦ የተሰራ ሲሆን የቆሻሻ ለማስለቀቅ/ለመፅዳት/

ያገለግላል፡፡
II. ለጥሬ እቃዎች/matrials/

የሊሾ ስራ ለመስራት የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች


1. ስሚንቶ/cement/
2. አሸዋ/sand/
3. የጠጠር/aggergate/
4. ኖራ/lime/
5. ውሐ/Wáter/

1. ሲሚንቶ /cement/

48
ሲሚንቶ ለአርማታ ሥራ' ለተለያዩ የግንብ ሥራዎች' ለሊሾ' ለተኩስ ሥራ፣ ለወለል ሥራ' ' ለግድብ ሥራ'
ለድልድይና ወዘተ… የሚያገለግል ሲሆን መጠነ ሰፊ አገልግሎትን ለሚሰጡ የመሠረተ ልማት ተቋማት ግንባታ
የሚያገለግል የግንባታ ጥሬ ዕቃ ነው፡፡
የሲሚንቶ ዓይነቶች፡-
በሀገራችን የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ሁለት ዓይነት ሲሚንቶ ያመርታሉ፡፡
እነርሱም፡-
A. ፖርትላንድ ሲማንቶ /Portland Cement/
B. ፖርትላን ፖዞላና ሲሚንቶ / Port Land puzzolana cement/
የሚባሉት ሲሆኑ በአጠቃላይ ግን የሲሚንቶ ዓይነቶች እንደሚሰጡት ጠቀሜታ የተለያዩ ሲሆኑ እነሱም
የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. መደበኛ ፖርትላነድ ሲሚንቶ/Ordinary Portland cement /OPC/
2. ቶሎ የሚጠነክር ሲሚንቶ/Rapid Hardening cement /RHC/
3. ዝቅተኛ ሙቀት የሚያመነጭ/ Low heat cement /LHC/
4. ቶሎ የሚደርቅ/Quick setting cement
5. ጨዋማና አሲድን መቋቋም የሚችል ሲሚንቶ/Sulfate resisting cement
6. ነጭ ሲሚንቶ/White cement
7. ፖዞላና ሲሚንቶ/Portland puzzolana cement

መደበኛ ፖርትላንድ ሲሚንቶ /Ordinary Portland Cement ፡-


ይህ ሲሚንቶ በአብዛኛው የልስን ሥራ የምንጠቀምበት የሲሚንቶ ዓይነት ሲሆን ለማንኛውም
የልስን ሥራ የሚያገለግል ነው፡፡ በተለይ ለመሠረት ሥራ፣ ለግድግዳና ለወለል ሥራ ወዘተ በአብዛኛው
የሚውል የሲሚንቶ ዓይነት ሲሆን እንደ ጨውና አሲድ የመሳሰሉ ነገሮች አይስማሙትም፡፡
ቶሎ የሚጠነክር ሲሚንቶ/Rapid hardening cement / RHC/
ይህ የሲማንቶ ዓይነት በሶስት ቀን ውስጥ ብቻ የሚፈለግበትን ጥንካሬ መስጠት የሚችል በጣም
ደቃቅ ስሚንቶ ነው፡፡ ቶሎ እንዲጠነክር የሚረዳውም ትራይካለሲየምሲልኬት/3CaSiO2/ የተባለ ወሁድ
በከፍተኛ መጠን በውስጡ እንዲገኝ በማድረግ ስለሚመረት ነው፡፡
ቶሎ የሚጠነክር ሰሚንቶ የሚሠራው ሥራ ተፈላጊውን ጥንካሬ በቶሎ እንዲያገኝና ግንባታው
እንዲፋጠን ይረዳል፡፡

ዝቅተኛ ሙቀት የሚያመነጭ/ Low heat cement /LHC/

49
ይህኛው ሲማንቶ አነስተኛ የሆነ ኖራ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ሲልካና ብረት /Silica and iron/
ከመደበኛው ፖርትላንድ ሲሚንቶ በበለጠ መልኩ ተጨምሮበት የሚመረት ሲሆን ሙቀት የማመንጨት
ሂደቱም /The heat of hydration/ በጣም አዝጋሚና ከፖርትላንድ ሲሚንቶ በአንድ ሶስተኛ 1/3 እጅ ያነሰ
ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሲሚንቶ የሚሠራ ሥራ ቶሎ ስለማይደረቅ ለሥራ ጊዜ የሚሰጥ በመሆኑ ጠንካራ
ለሆኑና ብዛት ላላቸው ሥራዎች እንደግድብ ለመሳሰሉት ሥራዎች እንጠቀመበታለን፡፡

ቶሎ የሚደርቅ/Quick setting cement


ቶሎ የሚደርቅ ሲሚንቶ ምንም ጄሶ ያልተቀላቀለበት ሲሆን በሰላሣ ደቂቃ ውስጥ መጠንከርና
መድረቅ የሚችል ሲሚንቶ ስለሆነ በውሃ ውስጥ ለሚገነቡ ግንቦች' ግድግዳዎች ወዘተ… ግንባታ
እንጠቀምበታለን፡፡

ጨዋማና አሲድን መቋቋም የሚችል ሲሚንቶ/Sulfate resisting cement


ይህ የሲሚንቶ ዓይነት በውስጡ ሰልፌትን /ጨዋማና አሲድ ነክ ነገሮች/ የመቋቋም ብቃት ያለው
በመሆኑ ጨዋማና አሲዳማ በሆኑ አካባቢዎች የግንባታ ሥራዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ነው፡፡

White cement /ነጭ ሲሚንቶ/'


ነጭ ሲሚንቶ እንደማንኛውም ሲሚንቶ የራሱ የሆነ ባህሪ ስላለው በተለየ መለክ የሚመረትና ነጭ መልክ
ያለው የሲሚንቶ ዱቄት ነው፡፡ በአመራረት ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅና በዋጋውም ከሌሎች
ሰለሚወደድ ለማጠናቀቂያ ሥራዎች /Finishing Works/ ተፈላጊ የሆነ የሲሚንቶ ዓይነት ነው፡፡
ነጭ ሲሚንቶ ለሚከተሉት ሥራዎች ተፈላጊነት ይኖረዋል፡፡
 ለህንፃዎች የማጠናቀቂያ / የማስዋቢያ/ ሥራ ለምሣሌ ለንፁህና ነጣ ላለ የውስጥና የውጭ
የልስን ሥራ እንዲሁም ለሞዛይክ፣ ለሴራሚክ የወለል ሥራና ለስቱኮ ሥራ ወዘተ..............
 ህንፃን የመስዋብ ሥራ /Architectural Ornamental or Decorative Works/
 በአውሮ ý ላን ማረፊያና አካባቢው፣ በመኪና መንገዶችና ድልድዮች ለሚሰሩ ነጣ ያሉ
ጠቋሚና በማስገንዘቢያነት ለሚያገለግሉ የተለያዩ ምልክቶችና ሥራዎች መስሪያ ያገለግላል፡፡

ፖዞላና ሲሚንቶ/Portland puzzolana cement


ፖዞላና ስሚነቶ ከሌላው የሚለየው የሚመረተው ፖዞላኒክ /Puzzuolanic/ ጥሬ ነገሮች /ፑሚቼና ሼል/ በመጨመር መሆኑ
ነው፡፡ ፓርትላንድ ፖዞላና ሲሚንቶ ምንም እንኳን የፖርትላንድ ሲሚንቶ ያህል ጥንካሬ ባይኖረውም ለማንኛውም የግንባታ
ሥራ ምቹ የሆነ የሲሚንቶ ዓይነት ነው፡
2. ኖራ/lime/

50
ኖራ በሊሾ ሥራ ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ሞርታር ለማዘጋጀትና ለኖራ ቅብ ሥራ ያገለግላል፡፡
ኖራ የፖርትላንድ ሲሚንቶ እና ሌሎች የሲሚንቶ ዓይነቶች ሥራ ላይ እስከዋሉበት ዘመን ድረስ በአብዛኛው
የግንባታ ሥራ ውስጥ ሲያገለግል የቆየ ጥሬ ዕቃ ነው፡፡ የጥንት ግብፃውያን' ሮማውያን ቤተመንግስቶቻቸውን
መኖሪያ ቤታቸውን' እንዲሁም የተለያዩ ህንፃዎችን ትላልቅ የመታሰቢያ ሥራዎችንና የመሳሰሉትን የገነቡት
ኖራን በመጠቀም ነበር፡፡ ኖራ አሁን ባለንበት ዘመንም ከጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡
ኖራ ከኖራ ድንጋይ /Lime Stone/ ይመረታል፡፡ የኖራ ድንጋይ በተፈጥሮ የሚገኝ የድንጋይ ዓይነት ሲሆን
በመልኩም ነጣ ያለ ወይም አመድማ ነው፡፡ የመልኩ በተለያየ ሁኔታ መገኘት የሚያሣየው የኖራ ድንጋይ
በውስጡ ከያዛቸው የተለያየ መጠን ያላቸው ቅይጦች(Impurities) የተነሣ ነው፡፡

ፈጣን/ ንፁህ ኖራ /Quick Lime, Pure lime or Fat Lime/:-


ፈጣን/ ንፁህ/ Rich Lime or Pure Lime/ የሚባለው ኖራ በመልኩ ነጣ ያለና ከፍተኛ የሆነ እርጥበትና
ካርቦንዳይኦክሳይድ ከአየር ውስጥ የመሳብ ችሎታ ያለው በመሆኑ ተመልሶ ወደቀድሞው ጠንካራ ድንጋይነት
የመለወጥ ባህርይ አለው፡፡
የዚህ ዓይነቱ ኖራ የመርጋትና የመጠንከር ሂደት በጣም ፈጣን ነው፡፡ ይህ ኖራ ጥሩ ውህደት እንዲፈጥር
ጠቀሜታ ላይ ከመዋሉ በፊት በውሃ ውስጥ ለተወሰኑ ቀናት ተዘፍዝፎ መሰንበት/Slaking/ ጥሩ ውጤት
ይሰጣል፡፡

ውሃ አዘል ኖራ /Hydrated /Slaked/ Lime:-


በኖራ አመራረት ሂደት ውስጥ ውስን ውሃ እየተጨመረ የሚዘጋጅ የኖራ ዓይነት ሲሆን በውህደቱ /
Composition/ አንፃር ካሊሲየም ሃይድሮክሳይድ Ca(OH)2 ነው፡፡ የዱቄቱ ቅንጣት መጠን ከፈጣን/ንፁህ ኖራ
ያነሰና የላመ ነው፡፡ ይህን ኖራ በግንባታ ወቅት ወዲያውኑ በውሃ ማቡካትና መጠቀም ይቻላል፡፡

ሀይድሮሊክ ኖራ Hydraulic Lime:-


ከላይ ከተጠቀሱት የኖራ ዓይነቶች የሚለይበት መንገድ ቢኖር ኬሚካላዊ ይዘቱ /Chemical composition/
ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከንፁህ ኖራ /CaO/ ካልሲየም ኦክሳይድ/ ሌላ ከ 10-30% ክብደት የሚሆነው አፈር
በውስጡ /Clay/ ስለሚገኝ ነው፡፡ የአፈሩና የኖራው ውህድ /Clay Lime Composition ያለምንም ችግር
ቶሎ የመርጋትና የመጠንከር ችሎታ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ከእነዚህም ሌላ አየር በሌለበት /አነስተኛ በሆነበት/
የህንፃ ክፍሎች ውስጥ እንኳን መርጋትና መጠንከር ይችላል፡፡ ጠቀሜታው ግን ከሌሎች ያነሰ ነው፡፡
3. ጠጠር/Aggregate

ጠጠርን ለልስን ሥራ የምንጠቀመው ለውጭ ግድግዳ ማስጌጫነት ሲሆን የምንጠቀማቸው የጠጠር አይነቶች
ውስጥ የእቭነበረድ ስብርባሪ፣ግራናይት ስብርባሪ ወዘተ ናቸው፡

51
4. አሸዋ/ sand /

አሸዋ በአብዛኛው የምንጠቀምበትና የተለመደ የግንባታ ጥሬ ዕቃ ሲሆን በውስጡ ፈሳሽ ነገር


የማያሳልፍ/Impervious/፣ በጣም የተጠቀጠቀ /Dense/ ጠንካራ የህንፃ አካል ለመሥራት ነው፡፡

ስዕል 5.1 አሸዋ

የአሸዋ ዓይነቶች
የአሸዋ ዓይነቶች ከሚመረቱበት ቦታ አኳያ እንደሚከተለው ይመደባሉ፡፡
ሀ. ከድንጋይ ቁጥኝ የሚገኝ አሸዋ /Pit sand/ በቁፋሮ የሚገኝ
ለ. የወንዝ አሸዋ / River Sand/
ሐ. የባህር አሸዋ /Sea sand/
ከድንጋይ ቋጥኝ የሚገኝ አሸዋ /Pit sand/'
ይህ የአሸዋ ዓይነት በተፈጥሮ አንድ ቦታ ላይ ተከማችቶና ተሰብስቦ ወይም የአሸዋ ድንጋይ በመሰባበርና
በማድቀቅ ይገኛል፡፡ ይህ አሸዋ ከሌሎቹ ሲወዳደር ንፁህ በቅርጽም ሹልና ማዕዘን ያለው ደቃቅ በመሆኑ
አርማታና ሞርታር ለማዘጋጀት ተመራጭ ነው፡፡
የወንዝ አሸዋ /River sand/'
የወንዝ አሸዋ ከወንዞች ውስጥና ከወንዞች ዳርቻ በሰፊው ይገኛል፡፡ በቅረፁም ድቡልቡልና ደቀቅ ያለ መጠን
ያለው ነው፡፡ይህ የወንዝ አሸዋ ንፁህ ከመጠን ያለፈ አፈር (4-6%) ያልተቀላቀለበት ከሆነ ለልስን ሞርታር
ለማዘጋጀት ያገለግላል፡፡

52
የባህር አሸዋ /Sea sand/'
የባህር አቨዋ ከባህር ዳርቻ የሚገኝ መጠኑ ደቃቅና ቅርፁም ድቡልቡል የሆነ ከፍተኛ የሆነ የባህር ጨው
በተፈጥሮው የተቀላቀለበት በመሆኑ ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ በንፁህ ውሃ በደንብ ካልታጠበ በስሚንቶ
ጥንካሬ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ በተጨማሪም የተሠራው የአርማታ ሥራ እርጥበት እንዲስብና
በሚደርቅበት ጊዜ ሥራውን የጨው አመድ ስለሚያለብሰው እምብዛም ተፈላጊ የአሸዋ ዓይነት አይደለም
/ካልተቸገረ በስተቀር/፡፡
አሸዋ ማሟላት ያለበት መስፈረቶች
አሸዋ ለታቀደለት ዓላማ በተገቢ መልኩ እንዲውል የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
1. ለሊሾ ሥራ የሚውል አሸዋ መጠን ደቃቅ አሸዋ/Fine sand/፣ መካከለኛ አሸዋ/Medium sand/ ከፍተኛ
መጠን ያለው አሸዋ/Coarse sand/ (ከ 0.06-4 ሚ.ሜ) ከሁሉም ዓይነት መያዝ አለበት ምክንያቱም
በልስን ጥሬ ዕቃዎች መካከል ያለውን ክፍተት ወይም /void/ በሚገባ መድፈን የሚችል መሆን አለበት፡፡
2. አሸዋ ንፁህ፣ አፈረና እጽዋቶች የፀዳ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የእነዚህ ነገሮች በአሸዋ ውስጥ
መኖር የአርማታ ወይም የሞርታር ጥንካሬ ስለሚቀንሱ ነው፡፡ የአርማታ ሥራው ጠንካራና በውስጡ
ምንም ነገር የማያሣልፍ መሆኑ ቀርቶ በውስጡ ውሃ የሚያስገባ የመጠንከር ሂደቱም በጣም አዝጋሚ
ይሆናል፡፡
3. የአሸዋ ቅንጣት' ጠንካራና' ሹል ጠረዞች ሊኖረው ይገባል፡፡ ሹል' ስለታማ ጠርዝ ያለው አሸዋ
ድቡልቡል ወይንም ክብ ቅርጽ ካለው አሸዋ የበለጠ ተመራጭነት አለው፡፡ ምክንያቱም ከሲሚንቶው
ውህድ ጋር የመያያዝ ችሎታው ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡
4. አሸዋ ከጨው አነዲሁም የሰሚንቶን ጥንካሬ የሚቀንሱ ኬሚካሎች የፀዳ መሆን አለበት፡፡

 የአሸዋን ንጽህና ከሞላ ጐደል በሚከተሉት መንገዶች በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡

 ከአቧራ የፀዳ ለመሆኑ ጥቂት አሸዋ በእጅ ዘግኖ በመጨበጥና መልሶ በመበተን እጅ ላይ
የሚቀረውን አዋራ ወይም አፈር በመመልከት ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡
 እንዲሁም ጨው አዘል ስለመሆኑ ጥቂት አሸዋ ቆንጥሮ በምላስ በማጣጣምና በመትፋት
ጨዋማ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡
 ከሁሉም የተሻለው ግን በላቦራቶር የአፈር መኖር/Silt Test/jar test/ እንዲሁም ሌሎች
ኬሚካሎችን መኖር/Colorimetric Test/ መፈተሽ ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡

 አሸዋ ለሊሾ ሥራ ውስጥ በሚቀየጥበት ወቅት የሚከተሉትን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

53
 ሲሚንቶና ኖራ ያለአሸዋ ስራ ላይ ቢውል ተፈላጊውን ጥንካሬ ስለማይኖረው አሸዋ
መጨመሩ ጥንካሬውን ከመጨመር አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡
 አሸዋ ከሲሚንቶ ጋር ተቀላቅሎ መቦካቱ የሲሚንቶን ፍጆታ ይቀንሳል፡፡
 የአሸዋ በሞርታር ውስጥ መገኘት የተሰራው ሥራ በቀላሉ በዝናብና በንፋስ በቀላሉ
እንዳይጠቃና እንዳይፈርስ ይረዳል፡፡
ውሃ /Water/:-

ውሃ የሊሾ ስራ በሚዘጋጅበት ወቅት የማጣበቂያ ጥሬ ዕቃዎችን ለማደባለቅ ይጠቅማል፡፡ ለሊሾ ሥራ የሚሆን


ውሃ ንፁህ(የሚጠጣ) መሆን አለበት፡፡ ውሃ በሞርታር ዝግጅት ጊዜ በሚጨመርበት ወቅት እንዳይበዛና
እንዳያንሰ በሚገባ መጠኑን ጠብቆ መጨመር ተገቢ ነው፡፡ ካነሰ በሚገባ ሲሚንቶውንና አሸዋውን ሳያርሰው
ይቀራል በጣም ከበዛም ሞርታር ይቀጥንና ጥንካሬውን ያጣል፡፡ እንዲሁም ከመቅጠኑ የተነሣ ለአሠራር ፍፁም
የማያመች ይሆናል፡፡

6. የሊሾ /screeding/ ስራ አዘገጃጀት CON FCW1 02 0910


ዓላማ ከዚህ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ በኋላ ሰልጣኞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በሚገባ ጠንቅቀዉ
ያዉቃሉ፡፡
 የሊሾ አይነቶችንና ምንነት ለይቶ ማወቅ
 የሊሾን ጥቅም መለየት
 የሊሾ እምቅ አቅም እና የውህድ መጠን

የሊሾ ስራ አስፈላጊነት ለማንኛም ወለል ስራ አመችነት እና ጥንካሬ/service life of floor/ ከፍተኛ አስተዋጾ
አለው፡፡ ለምሳሌ፡- ለወለል ሴራሚክ ስንሰራ ወለሉ ሌቭል እና በደረጃው ወጥ የሆነ አሰራር መሆን ይኖርበታል፡፡
ይህም የሚወሰነው በሊሾ ስራው ጥራት እና ጥንካሬ፤ በወለሉ ላይ በሚያርፈው ክበደት መጠን እንዲሁም
በመጨረሻው በምንጠቀመው ማቴሪያል አይነት ይሆናል፡፡
የሊሾ አይነቶች እና ምንነት
ሊሾ ማለት በኮንስትራክሽን ስራ ሂደት ውስጥ የሚካተት ሲሆን በዋናነት ያልተስተካከለ የወለል ገፅታ
እንዲስተካከል እና አመቺ የወለል ስራ የመስራት ሂደት ነው፡፡

54
ሊሾ፡- የማጣበቂያ ጥሬ ዕቃዎች /Binding Agents/፤ አሸዋ /fin Ages / እና ውሃ ድብልቅ ተጠቅመን
የምንሰራው የወለል ማጠናቀቂያ ስራ ነው፡፡
.

የሊሾ ስራ አይነቶች
የሊሾ ስራን በተለያየ መንገድ መስራት እና መጨረስ ይቻላል፡ ሆኖም ግን የምንጨርስበትን አየነት ለመወሰን
የቦታን ይዘት፤ አገልግሎት እና የምንተቀመውን የማቴሪያል አይነት መወሰን አለብን፡፡
በአጠቃላይ በአሰራር ሂደት እና አገልግሎታቸው በመነሳት የሊሾ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. በመፋስ የሚያልቅ(Floating)- ይህ የሊሾ አይነት የሚሰራ ለስላሳ ፋስ በመታገዝ ሲሆን በአብዛኛው
ለመኖሪያ ቤት ውስጥ፤ ለት/ቤት፤ ለሆቴል የመሳሰሉት ይጠቅማል፡፡
2. ኮንክሪት ላይ የተሰራ(Bonded)- ይህ የሊሾ አይነት ሙሉ በሙሉ ከኮንክሪት ጋር የተያያዘ እና ኮንከሪቱ
ሙሉ በሙሉ ከጠነከረ በ=ላ የሚሰራ የሊሾ አይነት ነው፡፡ አገልግሎቱም ከሌሎች አንፃር ከፍተኛ
ውፍረት እና ጥንካሬ ስላለው ክብደት ለሚበዛበት ቦታ ለምሳሌ ፡- ለመኪና ፓርኪንግ፤ ለኢንዱስተሪ፤
ለወርክ ሾፕ የመሳሰሉት ሲሆን የሚሰራም ሸካራ እና ልቫል ባልሆነ ቦታ ላይ ነው፡፡
3. በሽፋን የተሰራ(Un bonded)- ህ የሊሾ አይነት ከኮንክት ጋር ምንም አይነት ትስስር /Bond/ የሌለው
ሲሆን የተለያዩ የማጣበቂያ ማቴሊየሎችን/ binding agents damp proof membrane / በመጠቀም
ይሰራል፡፡
አገልግሎቱም በዋነኛነት ከፍተኛ የሆነ የውሃ ፍሳሽ ባለበት ቦታ ላይ ውሃ እንዳያልፍ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ
መነቃነቅ/ vibration/ በሚበዛበት ቦታ ላይ መሰነጣጠቅን ለመከላከል እና ቢፈጠር ከአንዱ ወደ አንዱ በቀላሉ
እንዳይተላለፍ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
4. በሙቀት የሚሰራ(Heated)- ይህ የሊሾ አይነት በአብዛኛው የሚሰራ በሙቀት እና በማሽን በመታገዝ
ሲሆን አገልግሎቱም ለቀዝቃማ ቦታ፤ ከወለል በታች ለሚሰራ ስራ፤ ለትላልቅ ኢንዱስትዎች ብዛት
ላለው ስራ እና የመሳሰሉት ሆኖ በቂ የሆነ ጥንካሬ በፍጥነት እንዲኖረው እና መሰነጣጠቅ
እንዳይፈጠር ይረዳል፡፡

55
የሊሾ ስራ ሰንሰራ መታሰብ ያለባቸው ነጥቦች
 ወለሉ የሚሰጠው አገልግሎት / service condition/
ለምሳሌ፤ ለንግድ ፤ ለት/ቤት ፤ ለፓርኪንግ፤ ለሆስፒታል ፤ለፋብሪካ፤ ይህ የሚጠቅመን የምንጠቀመውን የማቴሪያል
አይነት እና የሊሾ ውፍረት የአሰራር ሂደት ለመወሰን ነው፡፡
 የቦታውን ሁኔታ(internal & external) ጥንካሬ እና የማቴሪያል አቀራረብ (site condition)
የጥሩ ሊሾ ስራ መገለጫ ባህሪያት

የተስተካከለ የወለል ፊንሽንግ ስራ ሊሾ የሚከተሉት መገለጫዎች ይኖሩታል፡፡


 በቂ የሆነ ውፍረት(suffitient thickness) ፡- የሊሾ ስራ ውፍረት የሚወሰነው በወለሉ የአገልግሎት እና
በሊሾ አይነት እንዲሁም በወለሉ ላይ በሚያርፈው ክብደት ይሆናል፡፡
 ጠንካራ( mechanical resistance)፡-ተሰርቶ ካለቀ በሁላ እንደየ ውፍረቱ መጠን በቂ የሆነ
ጥንካሬ(stability strength) ሊኖረው ይገባል፡፡ይህም ለመጨረሻው የወለል ስራ አመች እንዲሆን
ይረዳዋል፡፡
 የተጠቀጠቀ መሆን(compacted)፡- የሊሾ ስራ በአግባቡ የተጠቀጠቀ እና አንድ አይነት ሰርፌስ ሌቭል
ሊኖረው ይገባል፡፡
 የተረጋጋ መሆን(cured and dimentionally stable) ፡- የሊሾ ስራ ከተሰራ በሁላ በደንብ ውሃ መጠጣት እና
በማንኛውም ሰዓት የወለል ስራ ሲሰራ የማይሰነጣጠቅ መሆን አለበት፡፡
 የማይሰነጣጠቅ(crack free) ፡- ይህም ሲባል ሊሾ በማንኛውም ጊዜ አንድ አይነት እና ወጥ መሆን አለበት፡፡
 ንፁህ (clean)፡- ሊሾ ከተሰራ በሁላ ንፁህ መሆን አለበት፡፡
 ሌቭል(level)፡- ይህም ሲባል ሊሾ በሁሉም አቅጣጫ ሌቭል እና የተስተካከለ ሰርፌስ መሆኑን በተገቢው
መንገድ ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
 ለስላሳ(smooth)፡- የሊሾ ልስላሴ በአጨራረስ ደረጃው እና መጨረሻ ላይ በምንጠቀመው የወለል አይነት
ይወሰናል፡፡

የሊሾ ጥቅም

56
 እረጅም ጊዜ መቆየት ይቻላል፤
 የተስተካከለ ወለል እንዲኖር ይረዳል፤
 ተሰርቶ ካለቀ ከ 3-7 ቀን አገልግሎት ይሰጣል፤
 እረጅም ጊዜ ኮመቆየት አንፃር ኢኮኖሚካል ነው፤
 በማንኛውም አይነት ቅርፅ መስራት ይችላል፡፡

ለሊሾ ስራ ቦታ አዘገጃጀት
1. የእጅ መሳርያ ለምሳሌ ማንክያ (trowel) መፈቅፍቅያ (scraper) በመጠቀም አርማታ ውስት ያሉ ነገሮችን
መዉጠት.
2. የተለያዩ ቆሻሻዎችን እና አዋራ ከኮንክርት ወለሉ ላይ ማስወገድ.
3. ሊሾ የምሰራዉን ቦታ ስፋት መለካት.
4. ለሊሾ ስራ የምያገለግሉ የተዘጋጁ ግብዓቶችን ማንክያን በመጠቀም ክፍታት ያለውን ቦታ መሙላት
5. ዉሃ ማጠጠት.
6. ፋሻ ማዉጣት
7. በተሰጠን ስፋት ልክ ሊሾ ስረ መስራት

ለሊሾ ስራ የምንጠቀምባቸውን ጥሬ እቃዎች/ግብአቶች/ መለየት


 የማጣበቂያ አይነቶችንና ምንነት
 የአሸዋ አይነቶችን ማወቅ
 ውሃ
 የሊሾ ባህሪያትን የሚያሻሽሉ ውህዶችን /አድሚክስቸር/መለየት

ሊሾ የሚጠቀማቸዉ የማጣበቂያ አይነቶቹ፣ የአሸዋ አይነቶች እና ዉሃ ለሞርታር ዝግጅት ከምንጠቀምባቸዉ ግብአቶች ጋር


ተመሳሳይ ሲሆኑ ሊሾ ከአርማታ ሞርታር የሚለየዉ የጠጠር አይነቶችን ስለማይወስድ እና አነስተኛ
ውፍረት/ሙሌት/ ሰለሚያስፈልግ ነዉ፡፡
የሞርታር ባህሪያትን የሚያሻሽሉ ውህዶችን /አድሚክስቸር/ መለየት
 እነዚህ ወህዶች ሞርታር ውስጥ ከተጨመሩ ሞርታሩ ወህዱ ከመጨመሩ በፊት ሊኖሩት የሚችሉትን
ባህሪያቱን ያሻሽሉታል፡፡ ለምሳሌ፡- ሞርታሩ ቶሎ የመጠንከርና የመድረቅ ችግር ካለበት ለዚህ ተግባር
የተዘጋጀ አክስሌረተር /accelerator/ ይጨመርበት እና ይህንኑ ድክመቱን ያሻሽላል ማለት ነው፡፡ ደግሞ
ሞርታሩ ተቦክቶ ለሚፈለግበት ተግባር ሳይውል የሚጠነክር ከሆነ ይህንኑ ባህሪውን ለማሻሻል ረታርዳንት
/RETARDANT/ የተባለውን ወህድ ይጨመርበታል፡፡

57
 በተጨማሪም በጣም ውሃ በዝቶበት ወይንም የአመጣጠኑ ይዘቱ አንሶ ከቀጠነ እንዲሁም ከወፈረ
ለአሰራር ስለማይመች ለአሰራር ምቹ የሚያደርጉ ንጥረ ወህድ /Work ability/ aid admixtures ሲሆን
ይህ ውህድ የበዛውን ውሃ መጠን የመቀነስ እና የያዘውን አየር የማሶገድ ስራ በማከናወን ሞርታሩን ለስራ
የሚያመች ያደርገዋል፡፡

የሊሾ መስሪያ ጥሬ እቃዎችን መለካትና ማዋሃድ

የሊሾ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ማመጣጠንና ማደባለቅ /Batching and mixing for screeding mortar /
የሊሾ አዘገጃጀትና አቀያየጥ ራሱ የቻለ ሊከተሉት የሚገባ ዘዴ አለው፡፡
በዘፍቀደ መቀየጡ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘናል፡፡
ስለዚህ እንደየ ሥራው ዓይነትና ከሚወጣው የሊሾ የጥንካሬ ደረጃ መስፈርት አንፃር ሞርታር ባለው ጉልበት
/manual mixing/ ወይም በማሽን /machine mixing/ ሊቦካ ይቻላል፡፡ የቅይጦች መጠን ስታንዳርዱ
/standard/ በጠበቀ መስፈሪያዎች መከናወን ይኖርበታል የአለካክ ወይም የአሰፋፈር ሁኔታ እንደስራው ዓይነት
እና መጠን ይወሰናል፡፡ ለምሳሌ የሲሚቶ እና የአሸዋ፣ መጠን ይዘት /volume/ ወይም በክብደት /weight/ ሊለካ
ይችላል፡፡
ለምሳሌ፡- ያህል 1፡2 መጠን /ሬሾ / mixing ration/ ያህል የሊሾ መጠን ማለት አንዱ እጅ ሲሚንቶ፣ ሁለት እጅ
አሸዋ ማለት ነው፡፡ ይህ አመጣጠን በክብደት ወይም በይዘት-/volume/ ሊሆን ይችላል፡፡
በአሰፋፈር ምጠና ላይ የበለጠ ግንዛቤ ለማግኝት በሀገራችን የማሰራባቸውን የመስፈራያ ሳጥኖች መጠን
መግለጽ ተገቢ ይሆናል፡፡
የመሰፋሪያ ሳጥን ይዘት
 0.4x0.5 ሜ x0.20 ሜ የሆነ መስፈርት ሳጥን የይዘቱ መጠን 0.04 ሜ.ኩየሆነ
 04 ሜ x 0.5 ሜ x 0.18 ሜ የሆነ መስፈርት ሳጥን የይዘት መጠን 0.36 ሜ.ኩ የሆነ
 0.4 ሜ x 0.5 ጫ x 0.16 የሆነ መስፈሪያ ሳጥን የይዘቱ መጠን 0.32 ሜ.ኩ የሆነ
 የውሃአጠቃቀምን በተመለከተ ለእያንዳንዱ የሞርታር ጥንካሬ ደረጃ የተወሰነለትን የሊትር መጠን መጠቀም
ይቻላል፡፡ የሲሚንቶውን መጠን በእዚሁ /በውሃው/ መልስ መጠቀም ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ከላይ
የተጠቀሱት ሁኔታዎች ተሟልተው በማይገኝበት ሁኔታ/ቦታ/ አንድ አይነት የማይለወጥ መስፈሪያ መጠቀም
/እንደባልዲ ወይም ሰንኬሎ የመሳስሉትን/ መጠቀም ይቻላል ፡፡
 የውሃውን መጠን ግምት በመጠቀም ቡኮውን ቀጭን ወይም ደረቅ እንዳይሆን መጠንቀቅ/ ቀስበቀስ በመጨመር
ሞርታሩን ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

የሞርታር እምቅ አቅምና የውህድ መጠን መለየት

58
ለሊሾ ስራ የሚሆኑት ጥሬ እቃዎችና የሚሸከሙትን መጠን ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸውን የውህድ መጠን
የሚያሳይ ሰንጠረዥ
ተ.ቁ የሥራው አይነት በኪዩቢክ ሜትር የሚያስፈልገው የግብዓት መጠን

1 ሞርታር በእጅ ለሚቀላቀል የቅይጥ ሲሚንቶ 12.74 ኪ.ግ/ሜ 3 ከረጢት


ሬሾ 1፡2 አሸዋ 0.91 ሜ.ኪ
ውሃ 286 ሌትር
2 ሞርታር በማሽን ለሚቀላቀል ሲሚንቶ 477.75 ኪ.ግ/ሜ 3 ከረጢት
የቅይት ሬሾ 1፡3 አሸዋ 1.02 ሜ.ኪ/ሜ 3
ውሃ 214 ሌትር
3 ሞርታር በእጅ ለሚቀላቀል የቅይጥ ሲሚንቶ 11 ኪ.ግ/ሜ 2 ከረጢት
ሬሾ 1፡4 አሸዋ --ሜ.ኪ/ሜ 2
ውሃ 38 ሌትር

በይዘት ውህድን የመለካት ወይም የመስፈር ዘዴ/Volume Baching/


1. ሲሚንቶ የመስፈር ዘዴ ሲሚንቶ የሚለካው ምንም ጊዜም በክብደት ነው በአብዛኛወ ጊዜ የምንጠቀመው
በከረጢት ሲሆን አንድ ከረጢት ሲምንቶ 50 ኪ.ግ ሲሆን በይዘት ሲለካ ደግሞ 35 ሌትር (0.035 ሜ.ኪ)
ይሆናልለ፡፡

ሲሚንቶ በፍጹም በይዘት አይለካም ምክንያቱም በምንለካበት ወይም በምንሰፍርበት ሰዓት የምንሰፍርበት ሳጥን
የመጠቅጠቅ ወይም የማሳነስ ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል ይህ ደግሞ የሲሚንቶውን ተፈላጊ መጠን የማሳነስ ሆነ
የማብዛት ሁኔታዎች ስሚኖሩ ይህ ደገሞ የአርማታውን ጥራት ይቀንሰዋል፡፡
2. አሸዋን በይዘት መለካት ወይም መስፈር፡- ይህ አሸዋን በይዘት ወይም በሳጥን ለመስፈር ሂደት
የሚያገለግል ይሆናል፡፡ ይህም በምንለካበት ሰዓት ሳጥናቸው የሚያፈስ መሆን የለበትም በምንሰፍርበት
ወቅትም ከሳጠኑ መጨረሻ ወይንም ልኬቱ ካለበት በላይ የተሞላ ከሆነ መጠረግ ይኖርበታል፡፡
በአጠቃላይ እነዚህ ውህድ የሚለኩበት ሳጥን ከ 1 ከረጢት ሲሚንቶ ጋር እኩል ይዘት አላቸው፡፡

በክብደት ውህድን የመለካት ወይም የመስፈር አይነት /weight baching/

59
በዚህ የመስሪያ ዘዴ ሁሉም ግብዓቶች የሚለኩት በክብደት ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ ይህ አይነቱ የግብዓት
አሰፋፈር ዘዴ የሚያገለግለው ከፍተኛ የሆነ የአርማታ ወይም የሞርታር ብዛትና ጥራት ለሚጠይቅ ስራ
ይሆናል፡፡
ይህ በክብደት የመለካት ዘዴ በይዘት ከምንለካው ጋር በምናነጻጽርበት ጊዜ በጣም ትክክለኛ የመስፈሪያ ሂደት ሆኖ
እናገኛለን ይንን ለመለካት ሚዛንን መጠቀም እንችላለን፡፡
በሰው ጉልበት ሞርታርን የማዋሀድ ዘዴ/ Hand Mixing /
ሞርታርን በሰው ጉልበት በምናዋህድበት ጊዜ ውሃን ወደ ውስጥ የማያስተላልፍ ቦታ ያሰፈልገናል፡፡
ሞርታሩን በሰው ጉልበት በምንቀይጥበት ጊዜ መከተል ያለበን ቀድም ተከተል እንደ ሚከተለው ይሆናል፡፡

የግብአት ውህድ እና አሰራር ቅደም ተከተል


1. የሞርታሩን ጥሬ እቃ ሰፍረን ከማምጣታችን በፊት ልናደባልቅበት ያስበንበትን ቦታ ማፅዳት ወይም
አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን ማፅዳት
2. 2 ሜትር በ 3.5 ሜ የሆነ ላሜራ ማዘጋጀት ይህ የማይገኝ ከሆነ በአርማታ የተሞላው መሬት ላይ
ማዘጋጀት ይቻላል፡፡
3. ይህን ካዘጋጀን በኋላ በሬሾ መሰረት የተዘጋጀውን አሸዋ መስፈር፤
4. ይህን ከሰፈርን በኋላ በሬሾ መሰረት የተዘጋጀውን ሲሚንቶ አሸዋው ላይ መበተን እና አንድ አይነት
ከለር እስከሚሆን ድርስ ማደበላለቅ /ማዋሀድ/
5. በሚገባ ያገላበጥነውን ውህድ መሀሉን በመከፍት ለውሃ ማዘጋጀት እና ቀስ እያልን ውሃ ማፍሰስ እና
ከሞርታሩ እጠቃላይ ብዛት ¾ በመቁረጥ እያገላበጥን ማዋሀድ በተጨማሪም ምንም አይነት ውሃ
በምናደባልቅበት ጊዜ እንደይፈስ መጠንቀቅ፡፡
6. የሚቦካው ሞርታር በጣም መቅጠን ወይም መድረቅ የለበትም፡፡
7. በዚህ ወቅት የማዳባለቅያ ጊዜው ከ 3 ደቂቃ የበለጠ አይሆንም
8. በመጨረሻ አዋህደን ከጨረስን በኋላ የተጠቀምን ቦታ እና የእጅ መሳሪያ ቦታውን ማጽዳት
ይኖርብናል፡፡ በተጨማሪም ለቀጣዩ ስራችን ቦታውን ዝግጁ ማደረግ ይኖርብናል፡፡

በማሽን በመጠቀም ሞርታርን የማዋሀድ ዘዴ/Machine mixing


የምንሰራው/ምንሞላው/ የሞርታር መጠን በጣም ቡዙ ከሆነ በሰው ጉልበት ለማዋሃድ በጣም አሰልቺና
አድካሚ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በማሽን መጠቀም ጉልበትንና ሰዓትን መቆጠብ ይችላል፡፡

60
ሞርታርን በማሽን የማደባለቅ ዘዴ ቅደም ተከተል
የሞርታር ግብዓትን የማደባለቂያ ማሽናችን ወይም (Mixer) ውስጥ በምንከትበት ጊዜ መከተል ያለብን ቅደም
ተከተል እንደሚከተለው ነው
የውህድ ቅደም ተከተል
1. በመጀመሪያ ደረጃ የተወሰነ ውሃ ድርሃም ውስጥ ወይም የማዋሃጃ ቋት ውስጥ መክተት
2. በመቀጠል መጠቀም ካለብን የአሸዋ መጠን ላይ ግማሹን እናስገባለን
3. በማስቀጠል መጠቀም ያለብንን ሲሚንቶ ሙሉ በሙሉ እንከታለን፡፡
4. በመጨረሻ የቀረውን አሸዋ መጨመር
5. እነዚህን ደረቅ ግብዓቶች ከጨመርን በኋላ አስፈላጊውን ውሃ ቀስ በቀስ ማዋሃጃ ቋት ውስት በመጨመር
ተፈላጊውን ሞርታር አዋህደን መጨረስ እንችላለን
 በአጠቃላይ የማሽናችን ፍጥነት ከ 16 R.P.M (Revulsion per mint to 2 R.P.M ይሆናል
 የማደባለቂያ ቆይታችን ከ 1 እስከ 8 ደቂቃ ውስጥ ይሆናል የማደባለቂያ ቆይታችን ከአንድ
ደቂቃ በታች የሚሆን ከሆነ የአርማታችን ጥራት የወረደ ይሆናል
 በአብዛኛው የማደባለቂያ ቆይታችን 8 ደቂቃ ቢሆን ይመረጣል ይህ ሰዓት የሚቆጠረው
ሁሉም ግብዓት ማደባለቂያ ውስጥ ከገቡ በኋላ ይሆናል፡፡

ሊሾ በሚሞላበት ቦታ ላይ የማስቀመጥ ዘዴ ቅደም ተከተል

ሞርታር ወደ ትክክለኛ ቦታ ላይ በምናስቀምጥበት ሰዓት መደረግ ያለበት ቅደም ተከተል


 ሞርታርን በተቻለ አቅም ወደ መጨረሻ የመሙያ ቦታ መውሰድ ይኖርብናል፡፡
 ወለል/floor/ በሚሞላበት ሰዓት ሞርታር መጀመር ያለበት ከአደኛው መአዘን ጥግ ሆኖ እንደ ቦታው
ሁኔታ ፋሻ/dado/ መውጣት እና ሙሌቱም መጠቅጠቅ ይኖርበታል፡፡
 ሞርታሩ በፍጹም በተለያየ ክልል መቀመጥ የለበትም ክምሩም በጣም የተለቀ መሆን የለበትም
የሞርታሩን የምንጠቀምበት መንገድ አግድም መሆን አለበት፡፡

61
 በአጠቃላይ ሞርታር መበተን ወይም መሞላት ያለበት በአግድም ሲሆን የምንሞላበት
የውፍረት/thickness/ መጠነኛ መሆን አለበት:: ይህም ከ 3-7 ሴ.ሜ ሆኖ እያንዳንዱ ሙሌትም ባግባቡ
መጠቅጠቅ ይኖርበታል፡፡
 የሞርታር አሞላል ቅድመ ጥንቃቄ ወይም ሞርታር ከሞሞላቱ በፊት መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ
መለየት/ማወቅ
 ማንኛውንም አይነት ሞርታር የሚሞላ ስራ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ባጠቃላይ ለስራው ጥራትና
ጥንካሬ ወሳኝ ነው፡፡
 አርማታ ከመሞላቱ በፊት ከታች የተዘረዘሩት ነገሮች ከሚሞላበት ቦታ ነጻ መሆን አለባቸው
በቀዝቃዛ ወቅት ሞርታርን በረጋ ነገር ላይ በበረዶና በሌላ ቁርጥራጭ ነገሮች ላይ
ማስቀመጥ የለብንም፡፡
ሞርታሩን የምንሞላው ቀደም ብሎ በአርማታ ኮንከሪት የተሞላ ቦታ ሆኖ የደረቀ ከሆነ
አዲስ የሚሞላው ሞርታር እንዲቀበል መቆርቆር ይኖርበታል፡፡
ሞርታር ከመሞላቱ ማንኛውም ቦታ በውሃ ወይም ሲሚንቶና ውሃ በተቀላቀለበት (ቦያካ)
ማራስ ወይም ማርጠብ ይኖርብናል፡፡ ይህ የሚሆነው የሞርታሩን ውሃ እንዳይመጠው እና
በፍጥነት እርጥበቱን በማጣት እንዳይሰነጣጠቅ ነው፡፡

በጠጨማሪ ደካማ የሆነ የአርማታ ኮንክሪት አካል ካለ ማለትም በሲምንቶና አሸዋ ብቻ የተሞላ አካል ከሆነ
መቆርቆርና ውሃ መፍሰስ አለበት በተጨማሪም ቆሻሻና የተለያዩ ነገሮች ካሉ መወገድ ይኖርባቸዋል፡፡
ውሃ ማጠጣት/curing/
 የውሃ ማጠጣጫ ዘዴዎች /አይነቶችን /እና
 የውሃ ማጠጣት ጥቅም
1. ወለል ስራ፣ተኩስ እና የመሳሰሉት በተመሳሳይ ሁኔታ ውሃ መጠጣት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ወለል ውሃ
ከጠጣ በኋላ በእርጥብ ጆንያ፣የሲሚንቶ ወረቀት፣ ወይም በአሸዋ በመሸፈን በፀሃይ አማካኝነት
ሚፈጠረውን ትነት ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡
 የውሃ ማጠጣት ሂደት እንደ ስራው አይነት ስራው በሚካሄድበት አካባቢ እንዲሁም ለስራው
እንደሚውለው የሲሚኒቶ አይነት ሊለያይ ይችላል ፡፡

የውሃ ማጠጫ ዘዴዎች አይነት


1. በጎማ የማጠጣት ዘዴ

62
2. ሶሌታን በአሸዋ በመሸፈን
3. ወለልን በአሸዋ ወይም በሌላ ማቴሪያል በመገደብ
4. በጆንያ በመሸፈን የሚደረግ የማጠጫ ዘዴዎች እና ሌሎችም

የውሃ ማጠጣት ጥቅም


1. የሞርታሩን ጥንካሬ ያጎለብተዋል፤
2. የቆይታ ጊዜውን ያራዝመዋል፤
3. የሊሾው ስራ እንዳይሰነጣጠቅ ይረዳዋል፡፡
4. ይህም ወለሉ ውሃ የማስተላለፍ አቅሙን ይቀንሰዋል፡፡

ማፅዳት
የሥራ ቦታን ማፅዳት
የግንባታ ሥራ ቦታ በየጊዜው ከሥራ በኋላ በአግባቡ መፅዳት ይኖርባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ሥራ ከተሠራ በኋላ/ሥራ
ከጨረስን በኋላ/ ለቀጣዩ ቀን ቦታው ፅዱና ምቹ እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት፡
1. በቀጣዩ የሥራ ቀን ያለምንም መሰላቸት/በመነቃቃት/ ሥራን ለመሥራት ይረዳል፤
2. አደጋን ይቀንሳል፤
3. መልሶ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቁሶችን በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡
የእጅመሣሪያዎችናማሽኖችንማፅዳት
ሞርታርን በምንሠራበት ወቅት /በምንቀላቅልበት/ ወቅት የተለያዩ የእጅመሣሪያዎችንና ማሽኖችን እንጠቀማለን፡፡ ሥራውን
ካጠናቀቅን በኋላ የተጠቀምንባቸውን የእጅ መሣሪያዎችና ማሽኖች በጥንቃቄና በአግባቡ መፅዳት /መታጠብ ይኖርባቸዋል/
ለምሳሌ አካፋ፣የግንበኛ ማንኪያ፣መፋስ፣የማቀላቀያ ማሽን በቀጥታ ከሞርታር ጋር ግንኙነት አላቸው፡፡ በመሆኑም ከሥራ
በኋላ የማይፀዱ ከሆነ የማጣበቂያ ጥሬ ዕቃው እላዩ ላይ በመጣበቅ ይጠነክርና ለሥራ የማይመች ይሆናል፡፡ ስለዚህ
ሥራዎችን ስንጨርስ የእጅ መሣሪያዎችን እንዲሁም ማሽኖችን ማጽዳት ለረዥም ጊዜ ያለብልሽት /ያለምንም ችግር/
ጠቀሜታ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

የግል ሥራ ፈጠራ /ኢንተርፕርነርሽፕ /የቢዝነስ ማሻሻያ ጥበብ ሥልጠና CON FCW 1 17 0910

63
64
65
66
67
68
69
70
የመመዘኛ ፓኬጅ

የስልጠናው አይነት :- የሊሾ ስራ


የተሰጠው ሰዓት ፡- 5 ሰዓት
የተካተቱ የብቃት አሀዶች

CON FCW1 01 09 10 carry out simple calculation

(ልኬት ወሳሰድ)

CON FCW1 10 0910 cement screed (ሊሾ ስራ)

CON FCW1 02 0910 use construction hand and power tools

( የእጅ መሳርያ እና ማሽን )


CON FCW1 18 0910 Apply kaizen
/ካይዘንን መተግበር/

CON FCW1 17 0910 develop and under standing entrepreneurship

(የግል ስራ ፈጠራ)

71
የተመዛኝ ሙሉ ስም
የመታ/ቁጥር
ፊርማ

የመዛኙ ሙሉ ስም

ፊርማ

የመመዘኛ ፓኬጅ ጠቅላላ ምዘና

1.1 ቴከኒክና ሙያ ፕሮግራም 1.2 የአጫጭር ጊዜ ሰልጠና

የብቃት አሀዶች የብቃት አሀድ :- 01፣10፣02፣18፣17

ክፍል 1.5

በተግባር ማሳየትና የቃ
1.6 የምዘና መርጃው የሚሰበስብበት መንገድ

እውቀትን ማረጋገጥ
ጥያቄ መጠየቅ

ያለዉን/ያላትን
በሙያው ላይ
1.9 ሰልጣኙ የሚከተሉትን የብቃት አሀዶቸ በትክክል መተግበር
አለበት/አለባት
የስራና የአካባቢን ጥንቃቄ መጠበቅ
X
የእጅ መሳሪዎችን መለየት እና መጠቀም
X
ድሮዊንግ ማንበብ እና መተግበር መቻል
X X
ጥሬ እቃዎችን መለየት እና ማመጣጠን መቻል
X X
ሊሾ ስራ መስራት መቻል X X
አከባብውን መጽዳት X

የተሰራውን ሊሾ ውሃ ማጠጣት ማቻል X


ካይዘንን መተግበር X
ኢንተርፕሩነር X

72
X
ቀን
ያረጋገጠው ሰው ስምና ፊርማ ቀን

የተግባር ጥያቄ መመሪያ (Instruction)


1 የምንጠቀማቸው መሳርያውችነ መለየት
2 የምንሰራበትን ቦታ ማጽዳት / ማስተካከል፡
3 ስራውን መጀመር
4 ስራውን ማጠናቀቅ

የቃል ጥያቄ መመሪያ


የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቃል መልስ/ሽ
1. ማንኛውንም ስራ ከመጀመራችን በፊት ምን ማድረግ አለብን?
2. በሊሾ ስራ ጊዜ ከምንጠቀምባቸው አልባሳት ውስጥ ቢያንስ ሶስቱን ጥቀስ/ሺ?
3. የሊሾ ጥቅም ምንድን ነው?
4. የሊሾ አይነቶችን ጥቀስ/ሺ?
5. የሊሾ ስራ ቅደም ተከተል ዘርዝር/ሪ?
6. ለሊሾ ስራ የሚያገለግሉ ግብዓቶችን ዘርዝር/ሪ?
7. የዉሃ ማጠጣት ጥቅም እና አይነቶችን ዘርዝር/ሪ?
መልስ
1 -የስራ ልብስ መልበስ
- የስራ አካባቢን ምቹ ማድረግ
-ማሽንን ማፅዳት
2. ጫማ ፤ጎግል፤ ጋንት ፤ ሄልሜት ፤ ቱታ
3. እረጅም ጊዜ መቆየት ይቻላል፤
 የተስተካከለ ወለል እንዲኖር ይረዳል፤
 ተሰርቶ ካለቀ ከ 3-7 ቀን አገልግሎት ይሰጣል፤
 እረጅም ጊዜ ኮመቆየት አንፃር ኢኮኖሚካል ነው፤
 በማንኛውም አይነት ቅርፅ መስራት ይችላል፡፡

4. 1. unbonded (በሽፋን የሚሰራ)

2. floating (በመፋስ የሚጠናቀቅ)

3. heated (በማሽን እና በሙቀት ሀይል የሚሰራ)

73
4. bonded (በኮንክሪት ላይ የሚሰረሰራ)

5 1.የሞርታሩን ጥሬ እቃ ሰፍረን ከማምጣታችን በፊት ልናደባልቅበት ያስበንበትን ቦታ ማፅዳት ወይም


አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን ማፅዳት

2. 2 ሜትር በ 3.5 ሜ የሆነ ላሜራ ማዘጋጀት ይህ የማይገኝ ከሆነ በአርማታ የተሞላው መሬት ላይ ማዘጋጀት
ይቻላል፡፡
ይህን ካዘጋጀን በኋላ በሬሾ መሰረት የተዘጋጀውን አሸዋ መስፈር፤
3. ይህን ከሰፈርን በኋላ በሬሾ መሰረት የተዘጋጀውን ሲሚንቶ አሸዋው ላይ መበተን እና አንድ አይነት ከለር
እስከሚሆን ድርስ ማደበላለቅ /ማዋሀድ/
4. በሚገባ ያገላበጥነውን ውህድ መሀሉን በመከፍት ለውሃ ማዘጋጀት እና ቀስ እያልን ውሃ ማፍሰስ እና
ከሞርታሩ እጠቃላይ ብዛት ¾ በመቁረጥ እያገላበጥን ማዋሀድ በተጨማሪም ምንም አይነት ውሃ
በምናደባልቅበት ጊዜ እንደይፈስ መጠንቀቅ፡፡
5. የሚቦካው ሞርታር በጣም መቅጠን ወይም መድረቅ የለበትም፡፡
6. በዚህ ወቅት የማዳባለቅያ ጊዜው ከ 3 ደቂቃ የበለጠ አይሆንም
7. በመጨረሻ አዋህደን ከጨረስን በኋላ የተጠቀምን ቦታ እና የእጅ መሳሪያ ቦታውን ማጽዳት ይኖርብናል፡፡
በተጨማሪም ለቀጣዩ ስራችን ቦታውን ዝግጁ ማደረግ ይኖርብናል፡፡

6. 1. ሲምንቶ፤ አሸዋ ፤ቴራዞ ችብስ፤ ውሃ

7. የሞርታሩን ጥንካሬ ያጎለብተዋል


የቆይታ ጊዜውን ያራዝመዋል፤
ሊሾው ስራ እንዳይሰነጣጠቅ ይረዳዋል፡፡
ይህም ወለሉ ውሃ የማስተላለፍ አቅሙን ይቀንሰዋል፡፡

74

You might also like