Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

1.

ከሚከተሉት የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል ስለ መንፈስ ቅዱስ ርቱዕ (ትክክለኛ) ትምህርት ያስተማረውን ምረጡ

ሀ) የሳሞሳታው ጳውሎስ

ለ) ኢሬኒየስ

ሐ) ኦሪገን

መ) አትናቴዎስ

2.አብና ወልድ አካል እንዳላቸው፣ መንፈስ ቅዱስም ሦስተኛ የሥላሴ አካል ስለመሆኑ የሚቀርበው የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃ ምንድን
ነው?

ሀ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት መንፈስ ቅዱስ የሚያከናውናቸው ተግባራት አካል መሆኑን ያመለክታሉ፡፡

ለ) በማቴ 28፡19 የምናገኘው ሥላሴያዊ አገላለጽ መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና ወልድ አካል ያለው መሆኑን ያመለክታል፡፡

ሐ) ኢየሱስ፣ መንፈስ ቅዱስን “ሌላ አጽናኝ” ብሎ መጥራቱ የተለየ አካል መሆኑን ያመለክታል፡፡

መ) ሁሉም

3.ቀጥሎ ከተጠቀሱት ምርጫዎች መካከል መንፈስ ቅዱስ አምላክ ስለ መሆኑ የሚያስረዳው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የቱ ነው?

ሀ) በአንዳንድ ምንባባት፣ መንፈስ ቅዱስና እግዚአብሔር በተቀያያሪነት መገለጻቸው

ለ) የእግዚአብሔር ብቻ የሆኑ ባሕርያት ያሉት መሆኑ

ሐ) ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነትና በእኩል ሥልጣን የሚሠራቸው ነገሮች መኖራቸው

መ) ሁሉም

4.ከሚከተሉት መካከል በብሉይ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ያልሆነውን ምረጡ

ሀ) መፍጠር

ለ) ትንቢትንና ቅዱሳት መጻሕፍትን መስጠት

ሐ) እስራኤላውያንን በመንፈስ ማጥመቅ

መ) ለሕዝቡ መሪዎች የአመራር ጥበብ መስጠት

5.በኢየሱስ ሕይወት የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የጀመረው መቼ ነው?

ሀ) በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀበት ወቅት

ለ) በአይሁድ ምኩራብ ስለ እርሱ በኢሳይያስ መጽሐፍ የተጻፈውን ባነበበት ወቅት

ሐ) በእናቱ ማኅፀን በተጸነሰበት ጊዜ

መ) በሞቱና በትንሳኤው ጊዜ

6.ከሚከተሉት ምርጫዎች ስለ ጸጋ ሥጦታዎች ትክክል የሆነው የቱ ነው?

ሀ) አንድ ሰው የጸጋ ስጦታዎችን በብርቱ ቢፈልግ ሁሉንም የጸጋ ሥጦታዎች መቀበል ይችላል

ለ) ዳግም የተወለደ አማኝ ሁሉ በልሳን የመናገር ጸጋ ሊኖረው ይገባል


ሐ) ሁሉም የጸጋ ስጦታዎች በእኩል ደረጃ በጉልህ ባይታዩም አስፈላጊዎች ናቸው

መ) አንድ የጸጋ ሥጦታ የተሰጠው ሰው ሥጦታውን በፈለገው ጊዜና ቦታ ሁሉ መጠቀም ይችላል

7.ከሚከተሉት ምርጫዎች መካከል ነቢያትና ሐዋሪያትን አስመልክቶ ትክክል የሆነውን ምረጡ

ሀ) የአዲስ ኪዳን አማኞች የሚለማመዱት ትንቢት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንዳሉት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ሥልጣናዊና ስህተት አልባ
ተደርጎ መቆጠር ይችላል

ለ) የሐዋሪትና የነቢያት አገልግሎት መሠረት የመጣል አገልግሎት ነው

ሐ) ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ባለው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ሐዋሪያትን መሾም የተለመደ ነገር ነበር

መ) የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን በቃሉ ውስጥ የማናገኛቸውን አዳዲስ መገለጦች የሚያመጡ ነቢያትን ማበረታታትና መሾም አለባት

8.የትምህርተ-መንፈስ ቅዱስን ጥናት አስፈላጊ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል አንዱን ጥቀስ/ሺ

9.መንፈስ ቅዱስን ለመረዳት የሚደረገው ጥረት፣ ከሌሎቹ አስተምህሮዎች ይልቅ ፈታኝ የሆነው በምን ምክንያት ነው? (አንድ ምክንያት
ጥቀስ/ሺ)

10. መንፈስ ቅዱስ ከዳግም ልደት በኋላ ባለው የክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ከሚሰራቸው ሥራዎች አንዱን ጻፍ/ፊ

________

You might also like