G-4 Env, Tal Science Final TB

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 178

አካባቢ ሳይንስ

የመማሪያ መጽሐፍ አራተኛ ክፍል

አራተኛ ክፍል

በ ቤኒ ሻ ን ጉ ል ጉ ሙዝ ክ ል ል ትምህ ር ት ቢሮ
አካባቢ ሳይንስ
የመማሪያ መጽሐፍ
አራተኛ ክፍል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ


የተዘጋጀ
አዘጋጆች
1. ታሪኬ ተሾመ (Msc)
2. ደረጀ ሆርዶፋ (MA) ገምጋሚዎች
3. በላይ ገመቹ (Msc) 1.ሙሃመድ ሰይድ (Msc)
4. ሰፊነው ውለታው (BA) 2. ፍቃዱ ከበደ (MA)
5. አብዱረህማን አሊ (Bsc) 3. ስንታየሁ አበራ (Bsc)

በ ቤኒ ሻ ን ጉ ል ጉ ሙዝ ክ ል ል ትምህ ር ት ቢሮ
© መብቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ትምህርት ቢሮ የተጠበቀ ነው፡፡ 2014ዓ.ም

በ ቤኒ ሻ ን ጉ ል ጉ ሙዝ ክ ል ል ትምህ ር ት ቢሮ
መግቢያ
ትምህርት የስልጣኔ ምንጭ እና በር ከፋች መሆኑ ይታወቃል፡፡
አካባቢያችን እና የምንኖርባት ዓለም ለማወቅ እና ለመረዳት
የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል፡፡ በአካባቢያችን
ብዙ ውስብስብ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህን በውል ተገንዝበን
አካባቢያችንን ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብ እና የሰውን ልጅ ኑሮ
ለማሻሻል የአካባቢ ሳይንስ መማር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት የሀገራችን መንግስት ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ


ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንፃር የተቀናጀ ሳይንስ
ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጥራቱን ጠብቆ
እንዲሰጥ እየተደረገ ነው፡፡

ይህ የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ መማሪያ መጽሐፍ በውስጡ


አምስት ምዕራፎችን የያዘ ሲሆን በምዕራፉ ይዘት ውስጥ
ለተማሪዎች ተሳትፎ፣ አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ትኩረት የሚሹ
ጉዳዮች ትኩረት ተሰጧቸዋል፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች
በአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመርኩዘው የሚያከናውኗቸው
በርካታ ተግባራት አሉ፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ተማሪ ይህንን
የመማሪያ መጽሐፍ በሚገባ እንዲጠቀምበት እንመክራለን፡፡

አዘጋጆች

በ ቤኒ ሻ ን ጉ ል ጉ ሙዝ ክ ል ል ትምህ ር ት ቢሮ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ማውጫ

ይዘት ገጽ
ምዕራፍ አንድ .......................................................................................................................1
1. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መገኛ .....................................................................................1
1.1 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል...................................................................................................1
1.2.የካርታ ፅንሰ ሃሳብ ..................................................................................................................2
1.3 በካርታ ላይ የቦታዎችን መገኛ ማወቅ ....................................................................................5
1.3.1 ንፍቀ ክበባት ....................................................................................................................6
1.3.2 አቅጣጫ ...........................................................................................................................7
1.3.3 አንፃራዊ መገኛ ..................................................................................................................8
1.3.4 ፍጹማዊ መገኛ .............................................................................................................. 10
1.4 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታዋቂ ቦታዎች መገኛ ............................................................... 15
1.5 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ ክልሎች .................................................................................. 20
1.5.1 በክልላችን የሚገኙ ዞኖች የሚገኙበት አቅጣጫ፣ ርቀትና መገኛ ቦታዎች ........................ 21
1.5.2 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልዞኖች ከክልሉ ዋና ከተማ ያላቸው ርቀት ............................... 22
የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ ጥያቄዎች ............................................................................ 23
ምዕራፍ ሁለት .................................................................................................................... 25
2. ሳይንስን ማስተዋወቅ ...................................................................................................... 25
2.1 ለሰውነታችን የሚያስፈልጉ ምግቦች ..................................................................................... 25
2.1.1 ምግብና ጤናማ ኑሮ ...................................................................................................... 25
2.1.2 አስፈላጊ ንጥረ ምግቦች .................................................................................................. 26
2.1.2.1 ሀይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦች..................................................................................... 28
2.1.2.2ገንቢ ምግቦች ................................................................................................................. 29
2.1.2.2 የስብናቅባትምግቦች .................................................................................................... 31
2.1.2.3 ቫይታሚኖች .............................................................................................................. 34
2.1.2.4 ማዕድናት ................................................................................................................... 36
2.1.2.5 ውሃ ............................................................................................................................ 37
2.1.3 የተመጣጠነ ምግብ....................................................................................................... 40
2.1.3.1የተመጣጠነ ምግብ ምንነት ........................................................................................... 40
2.1.3.2 ባህላዊ የምግብ ዓይነቶች............................................................................................. 43
2.1.3.3 የኢትዩጵያ ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት መመሪዎች ........................................................ 43
2.1.3.4 በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ የምግብ ክፍሎች .............................................................. 47

i|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

2.2 የሰው ውስጣዊ የአካል ክፍሎች ........................................................................................... 48


2.2.1 የሰው ውስጣዊ አካል መዋቅር፣ ተግባርና ባህሪያት .......................................................... 49
2.2.2 ስርዓተ- ልመትን የሚያከናውኑ የአካል ክፍሎች ............................................................. 53
2.3ቁስ አካል ............................................................................................................................. 55
2.3.1 የቁስ አካል ትርጉም......................................................................................................... 55
2.3.2 የቁስ አካል ባህሪያት ........................................................................................................ 57
2.3.3 የቁስ አካል ለውጦች ........................................................................................................ 61
2.4ብርሃን እና ጥላ .................................................................................................................... 66
2.4.1 ብርሃን ........................................................................................................................... 66
2.4.2 የብርሃን ባህሪያት........................................................................................................... 67
2.4.3 የብርሃን ጥቅም .............................................................................................................. 67
2.4.4 የጥላ አፈጣጠር .............................................................................................................. 68
የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ ጥያቄዎች ............................................................................ 68
ምዕራፍ ሦስት .................................................................................................................... 70
3. ተፈጥሮአዊ አካባቢያችን ................................................................................................ 70
3.1 የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል የአየር ንብረት............................................................................. 70
3.1.1 የአየር ንብረት እና የአየር ሁኔታ ልዩነት ....................................................................... 70
3.1.3 የአየር ሙቀት አለካክና ምዝገባ ..................................................................................... 72
3.1.4 የዝናብ መጠን፣ አለካክና ምዝገባ .................................................................................... 79
3.1.5 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአየር ንብረት ክፍፍል ........................................................ 86
3.1.6 የአየር ንብረት ቅጣይ ደንቢዎች .................................................................................... 87
3.2 የተፈጥሮ ሀብቶች................................................................................................................ 90
3.2.1 የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶች .......................................................................................... 90
3.2.2 የተፈጥሮ ሀብት ጥቅም .................................................................................................. 91
3. ውሃ ................................................................................................................................ 94
3.2.3 ለተፈጥሮ ሀብት መራቆት መንስኤዎች እና የሚያስከተሏቸው ጉዳቶች ......................... 99
3.2.4 የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ .......................................................................................... 100
3.3 የቆሻሻ አወጋገድ ............................................................................................................... 105
3.3.1 አግባብነት የሌለው የቆሻሻ አወጋገድ............................................................................ 105
3.3.2 ተገቢነት ያለው የቆሻሻ አወጋገድ ተግባራት................................................................. 106
3.3.3 የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ............................................................................................... 107
3.3.4 በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ጉድለት የሚከሰቱ በሽታዎች .................................................. 109
3.3.5 የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ ጠቀሜታ ............................................................................ 110

ii | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች.......................................................................................... 111


ምዕራፍ አራት .................................................................................................................. 114
4.ማህበራዊ አካባቢያችን ................................................................................................... 114
4.1 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ባህሎች ..................................................................... 114
4.1.1 የባህል ምንነት ............................................................................................................. 114
4.1.2 ቁሳዊ ባህል.................................................................................................................. 115
4.1.3. መንፈሳዊ ባህል...................................................................................................... 117
4.2 የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ የሚረዱ ጠቃሚ ባህላዊ ተግባራት ........... 123
4.3 የክልሉ ዋና ዋና ምጣኔ ሀብቶች ........................................................................................ 126
4.3.1 ግብርና ........................................................................................................................ 126
4.3.2 የማዕድን ቁፋሮ ........................................................................................................... 128
4.3.3 ኢንዱስትሪ .................................................................................................................. 129
4.4 የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴዎች በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖዎች ................... 131
4.4.1የግብርና ምርት ............................................................................................................. 132
4.4.2ማዕድን ......................................................................................................................... 133
4.4.3 ንግድ ........................................................................................................................ 135
4.4.4 ገበያ መር የሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ምርት ውጤቶች ....................................................... 135
4.5 በክልላችን የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብት ምርት ውጤቶች እና ሽያጭ ...................................... 137
4.5.1 በህጋዊ በሆነ መንገድ የሚከናወን ሽያጭ ...................................................................... 138
4.5.2 ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚከናወን ሽያጭ ..................................................................... 138
4.6 የመጓጓዣ ዘዴዎች ............................................................................................................ 139
4.7 ቅርስ ................................................................................................................................ 141
4.7.1 የቅርስ ምንነት ............................................................................................................. 141
4.7.2 የቅርስ ጥቅም .............................................................................................................. 144
4.7.3 የቅርሶች መበላሸትና መጥፋት...................................................................................... 145
4.7.4 የቅርሶች እንክብካቤ ..................................................................................................... 146
የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ ጥያቄዎች .......................................................................... 147
ምዕራፍ አምስት ............................................................................................................... 151
5. ወቅታዊ ጉዳዮች .......................................................................................................... 151
5.1 ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ ........................................................................................................... 151
5.1.1 ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ/የሚተላለፍባቸው መንገዶች ............................................................ 152
5.1.2 ኤች. አይ. ቪ /ኤድስ የማይተላለፍባችው መንገዶች ..................................................... 154
5.1.3 ኤች.አይ. ቪ ኤድስ በህፃናት ላይ የሚያስከትለው ችግር ............................................... 155

iii | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

5.1.4 ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ የሚያደርሳቸው ተፅዕኖዎች .............................................................. 156


5.2 በቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸው ኬሚካሎች ........................................................................ 160
5.3 አደንዛዥ ዕፆች ................................................................................................................. 162
5.3.1 ለአደንዛዥ ዕፅ የተጋለጡ ሰዎች የሚያሳዩት ምልክቶች ................................................ 163
5.4 ድርቅና ረሃብ .................................................................................................................... 165
5.4.1 ለድርቅ መከሰት መንስኤዎችና የሚያስከትላቸው ጉዳቶች ............................................ 166
5.4.2 የድርቅ መቋቋሚያ መንገዶች ...................................................................................... 168
የምዕራፉ የማጠቃለያ መልመጃዎች .................................................................................. 170

iv | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ምዕራፍ አንድ
1. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መገኛ
1.1 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ተማሪዎች ክልል ማለት ምን ማለት ነው?
እናንተ የምትገኙበት ክልል ማን ይባላል?
ክልል ማለት የአስተዳደር መዋቅር እና ወሰን ሲሆን በውስጡ
የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች እናህዝቦች በጋራ የሚኖሩበት ነው፡፡
በክልል ስር የዞን፣ የወረዳ እና ቀበሌ መዋቅር ይገኛል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ በኢትዮጵያ ከሚገኙ አስራ አንድ ክልሎች


ውስጥ አንዱ ሲሆን በውስጡም በሶስት ዞኖች፣ በሦስት ከተማ
አስተዳደር፣ 21 ወረዳዎች፣ በአንድ ልዩ ወረዳ እና 476 የገጠር
እና የከተማ ቀበሌዎች የተከፈለ ነው፡፡

1|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 1.1 የኢትዮጵያ ካርታ

1.2.የካርታ ፅንሰ ሃሳብ


ካርታ ምንድን ነው?
በአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ካርታ በጣም አስፈላጊ እና ጠቃሚ
መሳሪያነው፡፡ ስለሆነም የካርታን ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ
ይጠበቅብናል ፡፡

ካርታ የአንድን ቦታ አጠቃላይ ወይም ከፊል ገጽታ መርጦ፣


መጠኑን አሳንሶ በዝርግ ወረቀት ላይ የሚያሳይ መሳሪያነው፡፡
በካርታላይ የአንድን ሀገር ድንበር፣ መልካዓ-ምድር፣ የአየር

2|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ንብረት እና የተፈጥሮ ሀብት እንዲሁም ሌሎችን ገጽታዎች


ማሳየት ይቻላል፡፡

ካርታ የአንድን ቦታ ስፋት፣ ከፍታ፣ርቀትእና አቅጣጫ


መገኛየምናሳይበት መሳሪያ ነው፡፡ በካርታ ላይ የአንድን ቦታ
ትክክለኛ መጠን እንዲሁም ሁሉንም ገፅታ ማሳየት አይቻልም፡፡
ስለዚህም ካርታ የአንድን ቦታ ስፋት፣ ርቀት፣ ከፍታ እና ገጽታን
መጠኑን አሳንሶ እና የተወሰኑ ዋና ዋና ገፅታዎችን የሚያሳይ
ነው፡፡ የአንድን ቦታ አጠቃላይ ወይም ከፊል ገፅታ መጠን
አሳንሰን እና መርጠን በካርታ ላይ የምናሳይበት ዘዴ የካርታ
ሥራ ይባላል፡፡

ለምሳሌ የክልላችንን አጠቃላይ ገጽታ በትንሽ ወረቀት ላይ


የምናሳየው ዋና ዋና ገጽታውን መርጠን መጠኑን አሳንሰን ነው፡፡

ካርታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ገጽታዎችን እንዲሁም


በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት በግልጽ ለማሳየት ይጠቅማል፡፡
ካርታዎች ዝርዝር የመሬት አቀማመጥ ሁኔታዎችን ከቦታቸው
ድረስ ሂዶ ማየት ሳያስፈልግ ማጥናት ያስችላሉ፡፡ ካርታ በጥናት
እና ምርምር ስራ ወቅት ምርምሩ የሚካሄድበትን ቦታ ለማሳየት
ይጠቅማል፡፡ በድንበር ምክንያት በክልሎች እናበግለሰቦች
መካከል የሚነሱ ግጭቶችንም ለመፍታት ይረዳሉ፡፡ የአየር
ፀባይን ለማሳየት ይጠቅማሉ፡፡ ከዚህም በላይ ወደፊት ምን
መደረግ እንዳለበት የሚጠቅሙ ታሪካዊ ቦታዎችንም ለማጥናት
የሚያስችሉ ሰነዶች ናቸው፡፡ ካርታ የቦታዎችን አቀማመጥ፣

3|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

በቦታዎች መካከል ያለውንርቀት፣ የቦታዎችን ስፋት እና አቅጣጫ


ለማሳየት ይጠቅማል፡፡

የጥንት ሰዎች የውሃ ክምችት ያለበትን ቦታ፣ ጥሩ የአደን


አካባቢ እና የመንገዱን አቅጣጫ ለመጠቆም አሸዋማአፈር ላይ
ምልክቶችን ያስቀምጡ ነበር፡፡

ካርታ የራሱ የተለየ ፍች አለው፡፡ በካርታ ላይ የሚመለከቱ ልዩ


ልዩ ነገሮች ሁሉ በልዩ ልዩ ቀለማት ወይም በሌላ ልዩ ልዩ
ምልክቶች ወይም በአኅጽሮት /በማሳጠር/ ቃላት ተለይተው
ይቀመጣሉ፡፡

4|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል1.2 የቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልልካርታ

1.3 በካርታ ላይ የቦታዎችን መገኛ ማወቅ


ተማሪዎች የአንድን ቦታ መገኛ በካርታ ላይ እንደት ማወቅ
ይቻላል?

የቦታ መገኛ ማለት በመሬት ገፅ ላይ ቦታ፣ አካባቢ፣ ሀገር ወይም


አንድ ነገር በትክክል የሚገኝበትን የምንገልፅበት ነው፡፡

ካርታ ለመጠቀም የካርታን ንባብ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ካርታን


ለማንበብና ለመተርጎም መጀመሪያ ማወቅያለባችው ነገሮች

5|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነሱም፡- ንፍቀ ክበባት፣ አቅጣጫ፣ ኬክሮስ


/የኬክሮስ መስመሮች/፣ እናኬንትሮስ/ የኬንትሮስ መስመሮች/
በካርታ ላይ መለየት ተገቢነው፡፡

የአንድ አካባቢ መገኛ በሁለት ዋና ዋና ዘዴዎች ይገለፃል፡፡


እነሱም አንጻራዊ መገኛ እና ፍጹማዊ መገኛ ይባላሉ፡፡ ስለዚህ
ከዚህ በመቀጠል ስለንፍቀ ክበባት፣ አቅጣጫ፣ ኬክሮስ እና
ኬንትሮስ ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

1.3.1 ንፍቀ ክበባት


ከምድር ወገብ በስተሰሜን የሚገኘው ግማሹ የመሬት ክፍል
ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ሲባል በስተደቡብ ያለው ደግሞ ደቡባዊ
ንፍቀ ክበብ ይባላል፡፡ ከምድር ወገብ ሌላ እንደገና መሬትን
ለሁለት የሚከፍል የሀሳብ መስመርአለ፡፡ ይህም ግሪኒዊች
ሜሪዲያን ይባላል፡፡ ከግሪንዊች ሜሪዲያን በስተምዕራብ ያለው
የመሬት ክፍል ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ ሲባል በስተምስራቅ ያለው
ደግሞ ምስራቃዊ ንፍቀ ክበብ ይባላል፡፡

ሥዕል 1.3 አራቱ ንፍቀ ክበባት

6|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

1.3.2 አቅጣጫ
አቅጣጫ ማለት ምን ማለት ነው?

አንድ ቦታ ወይም አንድ ነገር በመሬት ላይ ወይም በካርታ ላይ


በየትኛው አቅጣጫ እንደሚገኝ ለመናገር የመነሻ ነጥብ
ያስፈለጋል፡፡ ማንኛውም የመነሻ ነጥብ ለራሱ አራት መሰረታዊ
አቅጣጫዎች አሉት፡፡ እነሱም፡- ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና
ደቡብ ይባላሉ፡፡ ጠዋት ጠዋት ፀሐይ የምትወጣበት የምስራቅ
አቅጣጫ ሲሆን ማታ ማታ የምትጠልቅበት ደግሞ ምዕራብ
አቅጣጫ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት አቅጣጫዎች ከለየን በኋላ ፊታችንን
ወደ ምስራቅ አዙረን ቀኝ እና ግራ እጃችንን ብንዘረጋ፣ በቀኝ
እጃችን በኩል የሚገኘው አቅጣጫ ደቡብ ሲሆን በግራ እጃችን
በኩል ያለው ደግሞ ሰሜን ይባላል፡፡ በነዚህ አራት አቅጣጫዎች
መካከል ሌሎች አራት ተጨማሪ አቅጣጫዎች ይገኛሉ፡፡
በአጠቃላይ ዋና ዋና አቅጣጫዎች ስምንት ናቸው፡፡ በሥዕል
1.4ላይ ስምንቱ ዋና ዋና አቅጣጫዎች ተመልክተዋል፡፡

7|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 1.4 ፡- 8ቱ ዋና ዋና አቅጣጫዎች

1.3.3 አንፃራዊ መገኛ


ተማሪዎች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አንፃራዊ መገኛ በካርታ
ላይ አሳዩ፡፡

የአንድ ቦታ ክልል፣ ዞንወይም ወረዳ መገኛ ከአካባቢው ከሚገኙ


ተፈጥሮአዊ ነገሮች ወይም ሰው ሰራሽ ነገሮች አንፃር ያለበት
ቦታ፣ የሚገኝበት አቅጣጫ እና አቀማመጡ ሲገለፅ አንፃራዊ
መገኛ ይባላል፡፡

ለምሳሌ፡- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኢትዮጵያ በሰሜን


ምዕራብ የሚገኝ ሲሆን፡-

 በሰሜን እና በሰሜን ምስራቅ የአማራ ክልል


 በምስራቅና በደቡብ የኦሮሚያ ክልል

8|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 በምዕራብ ሱዳን፣ በደቡብ ምዕራብ ደቡብ ሱዳን የሚያዋስነው

ሥዕል 1.5 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ ክልሎች ካርታ

ተግባር 1.1

ተማሪዎች በክልላችሁ የሚገኘውን የህዳሴ ግድብ አንፃራዊ


መገኛ ከካርታው ላይ ፈልጋችሁ አሳዩ፡፡

9|ገጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

1.3.4 ፍጹማዊ መገኛ


ፍጹማዊ መገኛ ማለት ምን ማለት ነው?
ፍጹማዊ መገኛ ማለት አንድ ቦታ በካርታ ላይ በትክክል የት ቦታ
እንደሚገኝ የኬክሮስ እና የኬንትሮስ መስመሮችን በመጠቀም
የምንገልፅበት ዘዴ ፍጹማዊ መገኛ ይባላል፡፡

በሉል ወይም በካርታ ላይ የአግድም መስመሮች (ኬክሮስ) እና


የቋሚ መስመሮችን (ኬንትሮስ) መስመሮችን በመጠቀም ፍጹማዊ
መገኛን በትክክል ማሳየት ይቻላል፡፡

ሉል የመሬትን ትክክለኛ ቅርጽ የሚወክልና የሚያሳይመሳሪያ


ነው፡፡

የኬክሮስ መስመሮች
ተማሪዎች የምድር ወገብ ማለት ምን ማለት ነው?
የኬክሮስ መስመሮች ወደ ጎን የተሰመሩ ሲሆን መነሻቸው የምድር
ወገብ ነው፡፡
የኬክሮስ መስመሮች በሉል ወይም በካርታ ላይ ከምዕራብወደ
ምስራቅ ወይም ከምስራቅወደ ምዕራብ የተሰመሩ የሀሳብ
መስመሮች ናቸው፡፡ ከኬክሮስ መስመሮች ውስጥየምድር ወገብ
የተባለውሉልን ወይም ካርታን ለሁለት እኩል ቦታ ላይ
የሚከፍለው የኬክሮስ የሀሳብ መስመር የምድር ወገብ ይባላል፡፡

10 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 1.6 የኬክሮስ እና የኬንትሮስ መስመሮች

ተግባር 1.2

ተማሪዎች

 የክልላችሁን አንፃራዊ መገኛ በቡድን በመወያየት ዘርዝሩ፡፡


 ትምህርት ቤታችሁን አንድ የታወቀ ቦታ መነሻ በማድረግ
አዋሳኞቹን ዘርዝሩ፡፡
 የክልላችሁን ካርታ በልሙጥ ወረቀት በመሳል
ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡

ምድር ወገብ ማለት የአንድን ቦታ ወይም አገር አቅጣጫ እና


ርቀት ለመግለፅ፤እንዲሁም አንድ ቦታ ወይም አገር የሚገኘው
በሰሜን ወይም በደቡብ በኩል መሆኑን ለማወቅ የመነሻ መስመር
ሆኖ ያገለግላል፡፡

11 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የኬንትሮስ መስመሮች

ካርታ ላይ የቦታዎችን መገኛ ለማወቅ የኬክሮስ መስመሮች ብቻ


ማወቅ በቂ አይደለም፡፡ በተጨማረም የኬንትሮስ መስመሮችንም
ማወቅ የግድ ያስፈልጋል፡፡

የኬንትሮስ መስመሮች በካርታ ላይ ወይም በሉል ላይ ከሰሜን


ወደ ደቡብ ወይም ከደቡብ ወደ ሰሜን የተሰመሩ የሀሳብ
መስመሮች ናቸው፡፡ እነዚህም መስመሮች ከምድር ወገብ አካባቢ
በመስፋት ወደ ዋልታዎች አካባቢ ደግሞ ወደ አንድ ይመጣሉ፡፡
መስመሮቹ በሁለቱ ዋልታዎች ላይ በማረፍ መሬትን ዞረው
የሚገጥሙ ክብ መስመሮች ናቸው፡፡

ሁሉም የኬንትሮስ መስመሮች በሰሜን እና በደቡብ ዋልታዎች


ላይ ስለሚገናኙ እንደ ኬክሮስ መስመሮች ተጓዳኝ አይደሉም፡፡

የኬንትሮስ መስመሮች ከሰሜን ወደ ደቡብ የሚሰመሩ እና


ሰሜናዊን እና ደቡባዊን ዋልታዎች የሚያገናኙ የምድርን
ማገሮች (ኬክሮስ) የሚያቋርጡ መስመሮች ናቸው፡፡ የእነዚህ
መስመሮች ቁጥር ደግሞ የሚጀምረው በግሪኒዊች (በእንግሊዝ
ሀገር) ከሚያልፈው መስመር ወደ ምስራቅ ወይም ወደምዕራብ
በመቁጠር ነው፡፡ በግሪኒዊች የሚያልፈው ኬንትሮስ ቁጥር
ዜሮ/0/ነው፡፡ መስመሩ ግሪኒዊች ሜሪዲያን ይባላል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍጹማዊ መገኛ

 ከ9 17 ሰሜን ኬክሮስ እስከ 12 06 ሰሜን ኬክሮስእና

12 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 ከ34 10 ምስራቅ ኬንትሮስ እስከ 37 04 ምስራቅ ኬንትሮስ


ነው፡፡
አስታውስ፡- ይህየደቂቃምልክት ነው፡፡

ሥዕል1.7የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍጹማዊ መገኛ

መልመጃ 1.1
ሀ. የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑእውነት ትክክል ካልሆኑ
ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡

1. የጥንት ሰዎች ካርታን ይጠቀሙ ነበር፡፡


2. የአንድ ቦታ ትክክለኛ መገኛ የምንገልጽበት
ዘዴአንፃራዊ መገኛ ይባላል፡፡

13 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

3. ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ከምድር ወገብ በታች


የሚገኝ የመሬት ክፍል ነው፡፡
4. ካርታን ለመጠቀም የካርታ ንባብ ማወቅ
አያስፈልግም፡፡

ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል


ምረጡ፡፡

1. ------የአንድን ቦታ መገኛ፣ ስፋት፣ ከፍታ፣ ርቀትና አቅጣጫ


የሚናሳይበት መሳሪያ ነው፡፡
ሀ/ መስመሮች ለ/ አቅጣጫ ሐ/ ካርታ መ/ ንፍቀ ክበባት
2. ከሚከተሉት ውስጥ የካርታ ጥቅም ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የአየር ጠባይን ለማሳየት
ለ/ግጭትን ለመፍታት
ሐ/ የተፈጥሮ ሀብትን ለማሳየትአይጠቅምም
መ/ ታሪክን ለማጥናት

3. ከምድር ወገብ በስተ ሰሜን የሚገኘው ግማሹ የመሬት


ክፍል-----ንፍቀ ክበብ ይባላል፡፡
ሀ/ ደቡባዊ ለ/ ሰሜናዊ ሐ/ ምስራቃዊ መ/
ምዕራባዊ
4. የኬክሮስ መስመሮች መነሻ የሆነው የሀሳብ መስመር የቱ
ነው?
ሀ/ ግሪኒዊች ሜሪዲያን ለ/ ኬንትሮስሐ/ የምድር ወገብ
መ/ ንፍቀ-ክበብ

14 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጥ/ጭ

1. ካርታ ማለት ምን ማለት ነው?


2. የክልላችሁን አንፃራዊ መገኛ ካርታ ወይም ጎግል በመጠቀም
ግለፁ፡፡
3. የኬክሮስ እና የኬንትሮስ መስመሮችን ልዩነት ግለጹ፡፡
4. የክልላችሁን ፍጹማዊ መገኛ የክልሉን ካርታወይም ጎግል
(Google) በማድረግ ግለጹ፡፡

1.4 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታዋቂ ቦታዎች መገኛ


ተማሪዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ

ቦታዎችን ዘርዝሩ፡፡

ታዋቂ ቦታዎች ማለት በክልሉ ውስጥ የሚገኙ እና ለክልሉ


ህብረተሰብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉልህ
ጠቀሜታ ያላቸውቦታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡-

 በአሶሳ ከተማ የሚገኘው የሸህ ሆጀሌ አል ሀሰን የችሎት


አደራሽ፣
 በማንኩሽ ከተማ የሚገኘው የደጃች መሀመድ ባንጃው ቤተ-
መንግስት፣
 በጉባ ወረዳ የሚገኘው ኦሜድላ/ቀ.ኃ. ሥ በር ዛፍ/፤
 በሸርቆሌ ወረዳ የሚገኘው የቤላሻንጉል ድንጋይ፣
 በምዥጋ ወረዳ የሚገኘው የቦሀ-አያ ወንዝ ፏፏቴ፣
 በሸርቆሌ ወረዳ የሚገኘው የሲኞር (ኡንድኖክ ሰው ሰራሽ
ዋሻ)

15 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 በማኦ-ኮሞ ልዩ ወረዳ የሚገኘው የያመሰራ መስጊድ እና


የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ተግባር 1.3
ከላይ ከተዘረዘሩት ታዋቂ ቦታዎች ውጭ ካሉ
በመጥቀስ የሚኖራቸውን ፖሊቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና
ማህበራዊ ፋይዳቸውን ተወያዩ፡፡

ህዳሴ ግድብ

በአሁኑ ጊዜ የህዳሴው ግድብ ለክልላችን ብሎም በሀገራችን


ከሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች አንደኛው እና ግንባር ቀደሙ ሲሆን
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በጉባ ወረዳ ይገኛል፡፡
የግድቡ መሠረተ ድንጋይ የተጣለው መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም
ሲሆን የግድቡሥራ ተጠናቆ ሲያልቅ 5150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ
ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ ግድብ ለክልሉ
ሆነለሀገሪቱ ለኃይል ምንጭ፣ ለዓሳእርባታ፣ ለመስኖ አገልግሎት፣
ለመዝናኛና ለመሳሰሉት የሚውል የኢኮኖሚ ጀርባ አጥንት ነው፡፡
በአባይ ወንዝ ላይየተገነባው የህዳስ ግድብ መብራት እና
የኤሌክትሪክ ኃይል ይሰጣል፡፡የኤሌክትሪክም ኃይል
በኢንዱስትሪዎች ሁሉ ስራ ሳይቆራረጥ እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡

16 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል1.8 ታላቁ የህዳሴ ግድብ(በጉባ ወረዳ የሚገኝ)

መልከዓ -ምድር

ተማሪዎች መልካዓ-ምድር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?


የክልላችን መልካ-ዓምድር ምን ይመስላል? ተወያይታችሁ
ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡

ተማሪዎች በአጭር አገላለፅ መልካዓ-ምድር ማለት የምድር መልክ


ማለት ነው፡፡ የምድራችን መልክ አንድ ወጥ አይደለም፡፡
ምድራችን ወጣገባ፣ አቀበትና ቁልቁለት የበዛበት ነው፡፡ ስለዚህ
መልካዓ-ምድር ከፍተኛና ዝቅተኛ ቦታዎችን ያጠቃልላል፡፡
ከፍተኛ ቦታዎች የምንላቸው ተራሮችን፣ አምባዎችና ኮረብታዎች
(ፕላቶ) ሲሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች የሚባሉት ደግሞ ሜዳዎች፣ ረባዳ
ቦታዎችና ሸለቆዎች ናቸው፡፡

17 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልአብዛኛው ቆላማ ሲሆን የተወሰኑት


ለምሳሌ ያህል የማኦ-ኮሞ ልዩ ወረዳ እና ወምበራወረዳ ደጋማ
ይዘት ያላቸው ናቸው፡፡ በመሆኑ በሞቃታማ የአየር ንብረት
ይታወቃል፡፡ ሙቀቱም ከፍተኛ የሚሆንባቸው ለስድስት ወራት
ሲሆን እነዚህም ከታህሳስ እስከ ግንቦት ያሉት ወራት ናቸው፡፡
በቀሪዎቹ ወራት በመጠኑም ቢሆን ዝቅተኛ የሙቀት መጠን
እናያለን፡፡ በክልሉ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚታየው
በሚያዝያ ወር ነው፡፡

ተግባር1.4
ተማሪዎች በቡድን ተከፋፍላችሁ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ
እና በቡድን መሪያችሁ አማካኝነት መልሶቻችሁን በቃል አቅርቡ፡፡
1. በአካባቢያችሁ የሚገኙ የተራሮች ስም ዘርዝሩ፡፡
2. በአካባቢያችሁ ሜዳማ ስፍራ አለ? ስሙ ማን ይባላል?
3. በአካባቢያችሁ የሚገኙ ወንዞችን ስም ዘርዝሩ፡፡
4. በአካባቢያችሁ ሸለቆ ወይም ጎድጓዳ ስፍራ አለ?
ከ 1- 4 ያሉትን ጥያቄዎች ከሰራችሁ በኋላ መልካዓ-ምድር
ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተወያዩ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ ቦታዎች

በክልሉ የተለያዩ ከፍተኛ ቦታዎች ወይም ተራሮች ይገኛሉ፡፡


ከፍተኛ ቦታዎች ማለት ከባህር ጠለል 1000 ሜትር በላይ ከፍታ
ያላቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

18 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለምሳሌ፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገሰንገሳ ተራራ በወምበራ


ወረዳ፣ የበላያ ተራራ በዳንጉር ወረዳ፣ ፋማጸሬ በኩርሙክ ወረዳ፣
አባሞቲ ተራራ በባምባሲ ወረዳ፣ የዋሻ ተራራ በመንጌ ወረዳ፣
የኢንዚ ተራራ በአሶሳ ወረዳ፣ የጃሎ ሌቃ ተራራ በካማሽ ወረዳ
እንዲሁም የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ሸሞሎ ተራራ የሚጠቀሱ
ናቸው፡፡

ሥዕል1.9 በኩርሙክ ወረዳ የሚገኙት የፋማፀሬና የጐሌ ተራሮች

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ ወንዞች

ተማሪዎች በክልላችን የሚገኙ ወንዞችን ስም ዘርዝሩ፡፡


በክልሉ ውስጥ ብዙ ወንዞች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አባይ፣
ዳቡስ፣ በለስ፣ ሆሃ፣ ዲዴሳ እና ሌሎችም ወንዞች ይገኛሉ፡፡ የአባይ
ወንዝ ክልሉን ለሁለት ይከፍለዋል፡፡

ተማሪዎች በአካባቢያችሁ የሚገኙ ወንዞችን በመዘርዘር ለምን


ለምን ጠቀሜታ እንደሚውሉ በክፍል ውስጥ ተወያዩበት፡፡

19 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ክልሉ በአባይ ወንዝ ተፋሰስና በባሮ አኮቦ ወንዝ ተፋሰስ


መካከል የሚገኝ በመሆኑ የበርካታ ወንዞች ባለቤት ነው፡፡ እነዚህ
ወንዞች ለመካከለኛ እና ለከፍተኛ መስኖ ልማት፣ ኤሌክትሪክ
ኃይል ማመንጫ፣ ለዓሳ ዕርባታ እና ለመሳሰሉት ይውላሉ፡፡

ሥዕል 10 የዳቡስ ወንዝ

1.5 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ ክልሎች


አዋሳኝ ማለት ምን ማለት ነው?

የአንድቦታ ወይም ክልል ኩታገጠም ወይም ድንበር የሚጋሩ


ቦታዎች አዋሳኝ ይባላሉ፡፡

የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል በኢትዮጵያ በሰሜን ምዕራብ የሚገኝ


ሲሆን የሚያዋስኑትም ክልሎች የአማራ ክልል እና የኦሮሚያ
ክልልናቸው፡፡ ክልሉን የሚያዋስኑ ክልሎች አቅጣጫዎች
ለምሳሌ፡-

 በሰሜን እና በሰሜን ምስራቅ የአማራ ክልል

20 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 በምስራቅና በደቡብ የኦሮሚያ ክልልናቸው፡፡ከላይ ያለውን


ሥዕል 1.1 የኢትዮጰያ ካርታ ይመልከቱ፡፡

1.5.1 በክልላችን የሚገኙ ዞኖች የሚገኙበት አቅጣጫ፣ ርቀትና


መገኛ ቦታዎች
ተማሪዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ስንት ዞኖች አሉ?
ስማቸውን ዘርዝሩ፡፡

በክልላችን ውስጥ ሶስት ዞኖች አሉ፡፡ እነሱም አሶሳ ዞን፣


መተከልዞን እና ካማሽ ዞን ናቸው፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሶስት ዞኖች እንዳሉ ከላይ


ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጅ እነዚህ ዞኖች የሚገኙት በተለያየ
አቅጣጫ ነው፡፡ የመተከል ዞን ከክልሉ ካርታ በመካከለኛና
በስተሰሜን ምስራቅ በኩልሲገኝ የካማሽ ዞን ደግሞ የሚገኘው
በደቡብና በደቡብ ምስራቅ በኩል ነው፡፡ ሶስተኛው ዞን ደግሞ
የአሶሳ ዞን ሲሆን በክልሉ ካርታ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ
በኩል ይገኛል፡፡

21 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ተግባር 1.5 የቡድን ስራ

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጥንድ ጥንድ በመሆን የክልሉን ካርታ


መሠረት በማድረግከተወያያችሁ በኋላ ለክፍል ጓደኞቻች ግለፁ፡፡

1. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዞኖች የሚገኙበትን አቅጣጫ


በተገቢው ሁኔታ ግለፁ፡፡
2. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዞኖች ከክልሉ ዋና ከተማ በምን
ያህል ርቀት እንደሚገኙ ተወያታችሁ መልሶቻችሁን ለክፍል
ጓደኞቻችሁ ግለፁ፡፡

1.5.2 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልዞኖች ከክልሉ ዋና ከተማ


ያላቸው ርቀት
በክልሉ የሚገኙ ሦስቱ ዞኖች ከክልሉ ርዕሰ ከተማ አሶሳ ያላቸው
ርቀት እንደሚከተለው ነው፡፡

የመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ከአሶሳ ከተማ ያለው ርቀት


360 ኪሎ ሜትር ሲሆን የካማሽ ዞን ካማሽ ከተማ ደግሞ ከአሶሳ
ከተማ ያለው ርቀት 260 ኪሎሜትር፣ ሶስተኛው ዞን የአሶሳ ዞን
ሲሆን የሚገኘውም በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ስር ነው፡፡

22 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ ጥያቄዎች


ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ እውነት ትክክል
ካልሆነ ሐሰት በማለት መልስ/ሽ

1. ካርታ የአንድን ቦታ መገኛ ለማወቅ ይረዳል፡፡


2. ክልል ማለት አንድ አይነት ብሔረሰብ ብቻ የሚኖርበት
ማለት ነው፡፡
3. አንድ ቦታ ከሌላ ቦታ አንፃር የሚገኝበትን አቅጣጫ
የምንገልጽበት ዘዴ አንፃራዊ መገኛ ይባላል፡፡
4. ካርታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ገጽታዎችን ያሳያል ፡፡

ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል


መረጥ/ጭ/

1. ከሚከተሉት ውስጥ የአንድ ቦታ ፍጹማዊ መገኛ ለመግለጽ


የሚያገለግለው የቱ ነው?
ሀ/ ታዋቂ ቦታዎች ለ/አዋሳኝቦታዎች
ሐ/ የኬክሮስ እና የኬንትሮስ መስመሮች መ/ ህንፃዎች
2. የህዳሴ ግድብ በየትኛው ወረዳ ይገኛል?
ሀ/ ወምበራ ለ/ ካማሽሐ/ ጉባ መ/ፓዊ
3. ከሚከተሉት ውስጥ ልዩ የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ አሶሳ ለ/ ካማሽ ሐ/ መተከል መ/ ዳንጉር
4. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስንት ዞኖች አሉት?
ሀ/ አራትለ/ አምስት ሐ/ ሶስት መ/ ሁለት

23 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

5. ከሚከተሉት ውስጥ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን የማያዋስነው


የቱ ነው?
ሀ/ አፋርለ/ ኦሮሚያ ሐ/አማራ መ/ ሱዳን

ሐ. የሚከተሉትን ባዶ ቦታዎች ትክክለኛውን መልስ ሙላ/ይ፡፡

1. ------- ማለትአንድን ቦታ በከፊል ገጽታ መርጦ፣ አሳንሶ እና


አቅልሎ በዝርግ ወረቀት ላይ የሚያሳይ ንድፍ ሀሳብነው፡፡
2. በካርታ ላይ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ተሰምረው የሚገኙ
የሀሳብ መስመሮች ------- ይባላሉ፡፡
3. የህዳሴ ግድብ የተገነባው በ------ ወንዝ ላይ ነው፡፡

መ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ፃፍ/ፊ

1. የካርታን ጠቀሜታ በአጭሩ ግለጽ/ጭ፡፡


2. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች ክልሎችን ጻፍ/ፊ፡፡

24 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ምዕራፍ ሁለት
2. ሳይንስን ማስተዋወቅ
2.1 ለሰውነታችን የሚያስፈልጉ ምግቦች
2.1.1 ምግብና ጤናማ ኑሮ
ምግብ ምንድን ነው?
ምግብ ለሰውነታችን ምን ጥቅም ይሰጣል?

ምግብ ማለት ማንኛውም የሚበላእና የሚጠጣለ ሰውነታችን


ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው፡፡ ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ
ለመኖር ምግብ ያስፈልገዋል፡፡ ለሰው ልጅም ከሚያሰፈልጉት
መሠረታዊ ነገሮች ምግብ አንዱ ነው፡፡

ምግብ በየዕለቱ ለምናከናውናቸው ስራዎች ወይም እንቅስቃሴዎች


ለምሳሌ: -እንጨት ለመፍለጥ፣ እርሻ ለማረስ፣ ዕቃ ከቦታ ቦታ
ለማንቀሳቀስ ጉልበት ያስፈልጋል፡፡ ይህም ጉልበት የሚገኘው
በየቀኑ ከምንመገበው ምግብ ነው፡፡ በተጨማሪም ምግብ ሰውነትን
የሚገነባ፣ የሚጠግን እና በሽታን ለመቋቋም የሚያስችል ነው፡፡

በሌላ በኩል ተማሪዎች በየቀኑ ታድጋላችሁ፡፡ የሚያድግ ነገር


ሁሉ ምግብ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ ምግብ ማለት ሰዎች፣
እንስሳት እና እፅዋት ለዕድገታቸው እና ጉልበት ለማግኘት
የሚጠቀሙበት ነው፡፡

25 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ተግባር 2.1

ተማሪዎች በየቀኑ የምትመገቧቸው ምግቦች የተለያዩ ናቸው?


ወይስ አንድ ዓይነት ነው? የተለያዩ ከሆኑ ዝርዝራቸውን
ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡

ምግብ ለሰውነታችን የሚሰጠው ጥቅም፡-

 ለአካል ጥንካሬ
 ለዕድገት
 በሸታን ለመከላከል
 ኃይል እና ሙቀት ለመስጠት
 ሰውነትን ለመገንባት

2.1.2 አስፈላጊ ንጥረ ምግቦች


ንጥረ ምግብ ምንድን ነው?

ተማሪዎች የንጥረምግብ ዓይነቶች ላይ ተወያዩና ምሳሌ ስጡ፡፡


ንጥረ ምግብ ማለት በምግብ ውስጥ የሚገኙና ሰውነታችን
ተግባሩን በተገቢው መንገድ እንዲያከናውን የሚረዱ ነገሮች
ንጥረ ምግቦች ይባላሉ፡፡ንጥረ ምግቦች ለሰውነታችን ገንቢ፣
ኃይልናሙቀትሰጪ እና በሸታ ተከላካይ ናቸው፡፡

በምግብ ውሰጥ ስድስት ዋና ዋና ንጥረ ምግቦች አሉ፡፡ እነሱም፡-

ሀ/ሀይልና ሙቀት ሰጪ

26 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለ/ገንቢ

ሐ/ስብና ቅባት

መ/ቫይታሚኖች

ሠ/ማዕድናትና

ረ/ውሃ ናቸው፡፡

2.1.2.1 ሀይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦች


ሀይልና ሙቀት ሰጪ ምግብ ማለት ምን ማለት ነው?
ሀይልና ሙቀት ሰጪ ከስድስቱ ንጥረ ምግቦች አንዱ ሲሆን
ለሰውነታችን ሀይልና ሙቀትን የሚሰጥ የንጥረ የምግብ ዓይነት
ነው፡፡ ሰውነታችን ስራውን በደንብ ለማከናወን ኃይል ያሰፈልገዋል
ሀይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦች የምንላቸው ከምንመገባቸው የምግብ
ዓይነቶች ውስጥ ለምሳሌ፡- ዳቦ፣ ድንች፣ ጥራጥሬ፣ ስኳር ድንች፣
ማር፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ገብስ፣ ስንዴ፣ ሩዝ፣ እንሰት፣ ሸንኮራ አገዳ፣
ሥራ ሥር እና ከመሳሰሉት እናገኛለን፡፡
ከላይ የዘረዘርናቸው የሀይልና ሙቀት ሰጪ የምግብ ዓይነቶች
ሰውነታችን ተገቢውንሥራ ለማከናውን ይረዳዋል፡፡ ለምሳሌ
ለመቆፈር፣ ለማረስ፣ ለመሸከም፣ ለመሮጥ፣ ለመዝለልና
ለመሳሰሉት ሁሉ ኃይል የምናገኘው ከሀይልና ሙቀት ሰጪ
ምግቦች ነው፡፡

28 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ድን ች ዳቦ

ኬክ

ሥዕል 2.1 ሀይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦች

ተግባር 2.2

ተማሪዎች በየቀኑ የምትመገቧቸውን ምግቦች ዘርዝሩ፡፡


ከተዘረዘሩት ምግቦች ውስጥ ሀይልና ሙቀት ሰጪ የሆኑት
የትኞቹ ናቸው?

2.1.2.2ገንቢ ምግቦች

ገንቢ ምግብ ማለት ምን ማለት ነው?

29 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ገንቢ ምግብ ማለት የአካላችን ህዋሳትን ለመገንባትና ለመጠገን


የሚረዳ ንጥረ ምግብ ነው፡፡ ገንቢ ምግብ ለታዳጊ ህፃናት
የተስተካከለ ዕድገት እንዲኖራቸውና አካላቸውን በመገንባት
ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡
እንዲሁም ገንቢ ምግቦች የተጐዱ የአካል ህዋሳትን ለመጠገን፣
የሚሞቱ ህዋሳትን በአዳዲስ ህዋሳት ለመተካት ይጠቅማሉ፡፡
ገንቢ ምግቦችን የምናገኝባቸው የምግብ አይነቶች በሁለት
ይከፍላሉ፡፡

እነሱም ፡ 1)ከእንስሳትና
2) ከእፅዋት ናቸው፡፡

ከእንስሳት የምንናገኛቸው ገምቢ ምግቦች፡-ዓሳ፣አይብ፣ወተት፣


አጓት፣ ቅቤ፣ እንቁላል፣ሥጋ ወዘተናቸው፡፡

30 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 2.2ገንቢ ምግቦች

ከእፅዋት የምናገኛቸው ገንቢ ምግቦች፦ ባቄላ፣ አተር፣ አጃ፣


ምስር፣ አኩሪ አተር፣ አደንጓሬና ሽምብራ ወዘተ ናቸው፡፡

2.1.2.2 የስብናቅባትምግቦች
ስብና ቅባት ማለት ምን ማለት ነው?

የስብና ቅባት ምግቦች ለሰውነታችን ኃይልና ሙቀት የሚሰጡ


ንጥረ ምግቦች ናቸው፡፡ የስብና ቅባት ንጥረ ምግቦች የበለጠ
ከፍተኛ ኃይልና ሙቀት ለአካላችን ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም
የምንመገባቸው ምግቦች ጥሩ ጣዕም እንዲኖራቸው ለማድረግ
ይረዳሉ፡፡
ለምሳሌ፡- ወጥ ሲሰራ ዘይትና ቅቤ የሚጨመረው ለዚህ ነው፡፡

31 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ስብናቅባት ከየትኞቹ የምግብ ዓይነቶች የሚገኝ ይመስላችኋል?


ከቅባት እህሎች፡- ሰሊጥ፣ ኦቾሎኒ፣ ሱፍ፣ ኑግ፣ ዘይት፣ ተልባ
ወዘተ ከእንስሳት ውጤቶች ደግሞ ጮማ ሥጋ፣ ወተት፣ ዓሳ፣ ቅቤ
የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ሥዕል 2.3 በቅባት የበለፀጉ ምግቦች

32 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ 2.1 በብዙ መጠን ለሰውነታችን የሚያስፈልጉ ንጥረ ምግቦች የሚገኙበት


የምግብ አይነትና የሚሰጡት ጥቅም

የንጥረ ነገረ የምናገኝባቸው የምግብ የሚሰጠው ጥቅም


ምግብ ምንጮች
ዓይነቶች
ሀይልና ዳቦ፣ ድንች፣ ማር፣ በቆሎ፣ ኃይልና ሙቀት
ሙቀት ሰጪ ብስኩት፣ ቆሎወዘተ ሰጪ

ገንቢ ዓሳ፣ ሥጋ፣ ወተት፣ አይብ፣ ለአካል ግንባታና


እንቁላል፣ አኩሪ አተርወዘተ ጥገና

ስብና ቅባት ዘይት፣ ኑግ፣ ሰሊጥ፣ ተልባ፣ ከፍተኛ ኃይልና


ቅቤ፣ ጮማ ሥጋ ወዘተ ሙቀት ሰጪ

መልመጃ 2.1

ሀ/ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል


ካልሆኑ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡
1. ስኳር ድንች ሀይልና ሙቀት ሰጪ የምግብ ዓይነት ነው፡፡
2. ገንቢምግቦች ከሀይልና ሙቀት ሰጪ የምግብ ዓይነቶች
ይመደባሉ፡፡
3. ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ለማደግ ምግብ
ያስፈልገቸዋል፡፡
4. ዓሳ፣ ሥጋ እና እንቁላል ከስብና ቅባት ምግቦች ውስጥ
ይመደባሉ፡፡

33 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

5. አደንጓሬ፣ አተር እና ሽምብራ ከእንስሳት የምናገኛቸው


ገንቢ ምግቦች ናቸው፡፡

ለ/ ከሚከተሉት ውስጥ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

1. ከሚከተሉት የምግብ ዓይነቶች ውስጥ ሀይልና ሙቀት


ሰጪምግብ የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ዳቦ ለ/ ወተትሐ/ ዓሳ መ/ ጎመን
2. ከሚከተሉት ምግቦች ውስጥ ገንቢ ንጥረ ነገር የያዘው ምግብ
የቱ ነው?
ሀ/ ጥራጥሬለ/ ቅቤ ሐ/ ሰሊጥመ/ ወተት
3. ምግብ ለሰውነታችን የሚሰጠው ጥቅም
ሀ/ ለዕድገት ለ/ በሽታን ለመከላከል
ሐ/ ለጥንካሬ መ/ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

ሐ. የሚከተሉትን ባዶ ቦታዎች በትክክለኛው መልስ ሙሉ፡፡

1. ____የአካላችን ህዋሳትን ለመገንባትና ለመጠገን የሚረዳ


ንጥረ ምግብ ነው፡፡
2. ገንቢ ምግቦች ከመገኛቸው አንፃር በሁለት ይከፈላሉ፡፡
እነሱም ___እና ___ናቸው፡፡
3.ኑግ፣ ሰሊጥ እና ጮማ ሥጋ ከ-------ንጥረ ምግቦች ይመደባሉ፡፡

2.1.2.3 ቫይታሚኖች

ቫይታሚን ማለት ምን ማለት ነው?

34 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ቫይታሚን ማለት ሰውነታችንን ከበሽታ የሚከላከሉ ንጥረ ምግቦች


ናቸው፡፡በቂ ቫይታሚን የሚመገብ ሰው በቀላሉ ለበሽታ
አይጠቃም፡፡ የቫይታሚን ዓይነቶች፡- ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን
ቢ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ዲ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ተማሪዎች የቫይታሚን የምግብ ምንጮችን ዘረዝሩ፡፡


ቫይታሚን የምናገኝባቸው የምግብ ዓይነቶች፡- ብርቱካን፣
ፓፓያ፣ ሎሚ፣ ሙዝ፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ጎመን እና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡

ተግባር 2.3

ተማሪዎች የምግብ ዓይነቶችን ዘርዝሩና የትኞች


የምግብ ዓይነቶች ቫይታሚን ኤ፣ቫይታሚን ቢ እና
ቫይታሚን ሲ የያዙትን የምግብ ዓይነቶች በመለየት
ለክፍል ጓደኞቻችሁ አብራሩ፡፡

35 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠርዥ 2.2 የቫይታሚን ዓይነቶች፣ጥቅም፣የሚገኝባቸው ምግቦችና የንጥረ ምግቡ


እጥረት የሚያስከትለው በሽታ

ተ/ የቫይታሚን የምግብ ምንጮች ለሰውነታችን የንጥረ ምግቡ


ቁ ዓይነቶች የሚሰጡት ጥቅሞች እጥረትየሚያስከት
ለው በሽታ
1. ቫይታሚን ጉበት፣ ወተት፣ እይታዎ የተሟላና የዳፍንት ወይም
ኤ ካሮት፣ ብርቱካን፣ የተሰተካከለ እንዲሆን በጨለማ ማየት
አበባ ጎመን ይረዳል አለመቻል
2. ቫይታሚን ዓሳ፣ ስንዴ፣ አጃ፣ ቀይ የደም ህዋሳትን ድካም፣ አቅም
ቢ አተር፣ ባቄላ፣ ወተት፣ በማዘጋጀት በሰውነት ማጣት፣ በቀላሉ
ሥጋ፣ እንቁላል ውስጥ በማዘዋወር መዛል
ሂደት ውስጥ ሚና
አለው
3. ቫይታሚን ሎሚ፣ ብርቱካን፣ የቆዳና የድድ ጤናን የድድ መድማት፣
ሲ ቲማቲም፣ ጎመን፣ ከመጠበቅ ረገድ የቆዳ መላጥና
ሚጥሚጣ፣ በርበሬ ከፍተኛ ሚና አለው መቁሰል
4. ቫይታሚን ከፀሐይ ብርሃን ፣ የአጥንት ጥንካሬን የአጥንት መሳሳት
ዲ ከወተትና ከወተት ይጠብቃላል
ተዋፅኦ

2.1.2.4 ማዕድናት
ማዕድን ማለት ምን ማለት ነው?
ተማሪዎች በማዕድን የበለፀጉ ምግቦችን ዘርዝሩ፡፡
ማዕድን ማለት የሰውነት ህዋሳት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ
ከሚረዱ ንጥረ ምግቦች አንዱነው፡፡

36 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ማዕድናት ለሰውነታችን የሚያስፈልጉት በጣም በአነስተኛ መጠን


ነው፡፡ በማዕድን የበለፀጉ ምግቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ብርቱካን፣ እንቁላል፣ ባቄላ፣ አተር እና ዓሳ መጠነኛ ካልስየም
ይገኝባቸዋል፡፡ ፎስፈረስ ደግሞ በዓሳ እና በምግብ ጨውውስጥ
ይገኛል፡፡ የብረት ማዕድን ከእንጀራ እና ጉበት ውስጥ ይገኛል፡፡

ሠንጠርዥ 2.3 የማዕድን ዓይነት፣ ጥቅምና የሚገኝባቸው ምግቦች

የማዕድን የምግብ ምንጮች ለሰውነታችን የሚሰጡት የንጥረ ምግቡ


ዓይነቶች ጥቅሞች እጥረት
የሚያስከትለው
በሽታ
ካልስየም ወተት፣ አይብ፣ ጥርስና አጥንትን የአጥንት
እንቁላል፣ ዓሳ፣ ባቄላ ያጠናክራል መወላገድና
ወዘተ መሳሳት
ፎስፌረስ ዓሳና በምግብ ጨው ለአጥንትና ጥርስ ጥንካሬ የአጥንት
ይሰጣል መሳሳት
ብረት/አይረን/ ጉበት፣ ቀይ ጤፍ፣ የደም ማነስ ይከላከላል ደም ማነስ
ሥጋ
አዮዲን ከምግብ ጨው፣ ከዓሳ የእንቅርት በሽታን የእንቅርት
ይከላከላል በሽታ

2.1.2.5 ውሃ
ተማሪዎች ውሃ ለሰውነታችን ምን ጥቅም ይሰጣል?

ውሃ ሰውነታችን ተግባሩን ያለ ችግር እንዲያከናውን ከሚረዱ


ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ውሃ በሰውነታችን ህዋሳት ውስጥ በከፍተኛ
መጠን ይገኛል፡፡ እንዲሁም ከስልሳ እስከ ሰባ በመቶ

37 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የሰውነታችን ክብደት ውሃ ነው፡፡ አንድ ጤናማ ሰው በቀን


ከሦስት እስከ አስር ብርጭቆ ውሃ ወይም ከአንድ ሊትር እስከ
ሦስት ሊትር ያስፈልገዋል፡፡

የውሃ ጥቅም

 ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በደም ውስጥ


ያጓጉዛል፡፡
 የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
 በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲፈጭና እንዲልም ይረዳል፡፡
 ጠቃሚ ንጥረ ምግቦች ወደ ሚፈለገው የሰውነታችን ክፍል
እንዲደርሱ ይረዳል፡፡
 ከሰውነት ውስጥ ቆሻሻን በላበት፣ በሽንት፣ በዓይነ-ምድር
መልክ እንዲወገድ ይረዳል፡፡
 የሰውነት ክብደትን ያስተካክላል፡፡

ሰውነታችን ውሃን እንዴት ያገኛል?


ሰውነታችን ውሃን በሶስትመንገድ ያገኛል፡፡ እነሱም
1. ከምንመገበውምግብ
የምንመገባችው ምግቦች በውስጣቸው አብዛኛውን እጅ ውሃ
ይዘዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ገንፎ፣ ወጥ፣ ሾርባ፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት
ወዘተ
2. ከምንጠጣው ውሃ
3. ከሌሎች መጠጦች

38 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለምሳሌ፡- ከቦረዴ፣ ከጠላ፣ ከሻይ፣ ከወተት፣ ከለስላሳወዘተ


ሰውነታችን ውሃን ያገኛል፡፡

መልመጃ 2.2

ሀ. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፈደል


ምረጡ፡፡

1. ቫይታሚን ‘’ኤ’’ንከየትኛው የምግብ ዓይነት እናገኛለን?


ሀ/ ካሮት ለ/ ድንች ሐ/ አተር መ/ ተልባ
2. ከምንመገበው ምግብ ውሰጥ ካልስየም የሚሰጠው ጥቅም
ሀ/ በሸታን ይከላከላል ለ/ ደም ማነስ ይከላከላል
ሐ/ የእንቅርት በሽታን ይከላከላል መ/ ጥርስና አጥን
ያጠነክራል
3. የብረት/አይረን/ ምንጭ ያልሆነው ምግብ የቱ ነው?
ሀ/ ጉበት ለ/ ቀይ ጤፍ ሐ/ ቀይ ሥጋ መ/ እንቁላል
4. ለሰውነታችን ከሚያስፈልጉት ንጥረ ምግቦች በጣም አነስተኛ
መጠን የሚያስፈልገው የትኛው የምግብ ዓይነት ነው?
ሀ/ ቫይታሚን ለ/ ማዕድን ሐ/ ቅባት መ/ውሃ

ለ.ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጥ/ሰጭ/


1. ከሰውነታችን ውሰጥ ውሃ በምን መልክ ይወገዳል?
2. ሰውነታችን ውሃን ባያገኝ ምን ችግር ይገጥማዋል?
3. በማዕድን የበለፀጉ ምግቦች ከየት ይገኛሉ?
4. የሰው ልጅ ምግብ ባያገኝ ምን ይሆናል?

39 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

2.1.3 የተመጣጠነ ምግብ

2.1.3.1የተመጣጠነ ምግብ ምንነት


ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ ማለት ምን ማለት ነው?

የተመጣጠነ ምግብ ማለት፡- መጠኑ በቂ የሆነና የተለያዩ የንጥረ


ምግብ ዓይነቶችን የያዘ ማለት ነው፡፡ የተመጣጠነ ምግብ ሀይልና
ሙቀት ሰጪ፣ ገንቢ፣ ስብናቅባት እንዱሁም ማዕድናትና
ቫይታሚኖችን በበቂ መጠን የያዘ ነው፡፡

የተመጣጠነ ምግብ ለሰውነታችን የሚሰጠው ጥቅም፡-

 ጤናን ለመጠበቅ
 ለዕድገት
 ኃይል ለማግኘት
 በሸታን ለመከላከል

40 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 2.4፡-የተመጣጠነ ምግብ

ተግባር 2.4

ተማሪዎች በተከታታይ የምትመገቡትን ቁርስ፣ ምሳና እራት


ዘርዝሩ እና የተመጣጠነ ምግብ የያዘ መሆኑን ከጓደኞቻችሁ ጋር
ተወያዩ፡፡

የተመጣጠነ ምግብ ያለመመገብ የሚያስከትለውችግር፡-

1. የአጥንት መወላገድ እና የአጥንት መሳሳት


2. የደም መርጋት
3. የድድ መድማት
4. የደም ማነሰ

41 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

5. የእንቅርት በሽታ
6. ድካም፣ አቅም ማጣት፣ በቀላሉ መዛል
7. የዳፍንት ወይም በጨለማ ማየት አለመቻል እና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡

መልመጃ 2.3

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል


ካልሆኑ ሐሰት በማለት መልሱ

1. የተመጣጠነ ምግብ ማለትሁልጊዜ ስጋ እና


እንቁላልመመገብማለት ነው፡፡
2. የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ዕድገትን ይገድባል፡፡
3. የተመጣጠነ ምግብ ማለትስድስቱን ንጥረ ምግቦች አካቶ
የያዘ ማለት ነው፡፡

ለ. የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል


ምረጥ/ጭ፡፡

1. የተመጣጠነ ምግብ ለሰውነታችን የሚሰጠው ጥቅም


ሀ/ በሽታን ለመከላከል ለ/ ሀይል ለማግኘት
ሐ/ ለጤናማ እድገትመ/ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡
2. የተመጣጠነ ምግብ ባለመመገብ የሚከሰት ችግር የቱ ነው?
ሀ/ የደም ማነስ ለ/ የድድ መድማት
ሐ/የአጥንት መወላገድመ/ ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

42 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

2.1.3.2 ባህላዊ የምግብ ዓይነቶች


ተማሪዎች ባህላዊ ምግብ የምንላቸው የትኞቹ ናቸው?

ባህላዊ ምግብማለት በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች


አዘውትረው የሚጠቀሙት የምግብ ዓይነትና የዚያማህበረሰብ
ማንነት መገለጫ ነው፡፡ ባህላዊ ምግብ የሚዘጋጀው እዚያው
በአካባቢያቸው ባለው ሀብት ወይም ግብዓት ነው፡፡

ባህላዊ ምግብ በማህበረሰቡ በጣም ተወዳጅ የሆነ የምግብ ዓይነት


ነው፡፡ እነዚም ባህላዊ ምግቦች ከቦታ ቦታ የሚለያዩ ሲሆኑ
አዘገጃጀታቸውም ይለያያል፡፡

ለምሳሌ ባህላዊ ምግቦች የምንላቸው፡-ጭንቦ፣ ቄንቄስ፣ ቁንጹ፣


አገንባኝ፣ ካማ፣ ማጢማሮ፣ ቦረዲ/ቦርዴ፣ ገንፎ፣ ቆሪ፣ ጥሻ(ቂጣ)፣
አገሮ፣ ሠሊጥ፣ አነባበሮ፣ ጨጨብሳ፣ ላላቃ (ከቅጠላቅጠልየሚዘጋጅ)፣
ወጂያ (ከቀርከሃየሚዘጋጅ)፣ ቡያ፣ ቡላ፣ ዶሮ ወጥ፣ እንሰት፣ ክትፎ፣
ቆሎ፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

2.1.3.3 የኢትዩጵያ ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት መመሪዎች


ተማሪዎች በአካባቢያችው ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት ካለ አሰራሩን
ለክፍል ጓደኞቻችሁ አስረዱ፡፡

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔርብሔረሰቦች መገኛና ብዙ ባህላዊ መገለጫ


ያላት ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን በርካታ ባህላዊ አመጋገብ፣
አለባበስና የተለያዩ ቋንቋዎች ያሏት ስትሆን፣ ይህም የማንነቷ
መገለጫ ነው፡፡

43 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ

የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ ማለት የተለያዩ ምግቦችን


ለማዘጋጀት የምንጠቀመው መመሪያ ነው፡፡

የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ የሚያጠቃልለው፡-

1. የንጥረ ነገር ዝርዝር


2. የንጥረ ነገር መጠን
3. የዝግጅት መመሪያ

የምግብ አዘገጃጀት ሂደት የሚያስፈልገው፡-

 የንጥረ ነገር ዓይነት


 ለእያንዳንዱ የምግብ ዓይነት ትክክለኛው የንጥረ
ምግብ ዓይነት ዝግጅት
 ንጥረ ነገር መምረጥ፣መለካትና ማዋሀድ ነው፡፡

የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ አስፈላግነት፡-

 አጭርና ግልጽ የሆነ የንጥረ ነገር ለማስቀመጥ


 የሚያስፈልገው የንጥረ ነገር መጠን ለማስቀመጥ
 የሚዋሀድበትን መንገድ ለማስቀመጥ

ትክክለኛ አመጋገብ አሰልቺ አይደለም፡፡ ለጤናማ ኑሮ


ትክክለኛውን የአመጋገብ ስርዓት በራስ ለማዘጋጅት በቀላሉ
የሚቀርቡ፣ ቀለል ያሉና አስደሳች/ተወዳጅ/ የሆኑ የምግብ
አዘገጃጀቶችን ማቀረብ ይቻላል፡፡

44 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለምሳሌ፡- የዶሮ ወጥ አሰራር


ግብዓቶች፡-
 የዶሮ ሥጋ
 ጨው፣ በርበሬ፣ ዘይት፣ ቅቤ፣ ቅመማ ቅመም
 ሸንኩርት (1-4) ኪሎ ግራም
 ውሃ
 ሎሚ
 እንቁላል
 አብሽ
 መከለሻ
 ነጭሽንኩርት

የአሰራር ቅደም ተከተል

1. መጀመሪያ አንድ ብረት ድስት ውሃ ይፈላል፣ የተዘጋጀው


ሽንኩርት ይላጥ እና ይከተፋል፡፡
2. ዶሮ ይታረዳል
3. በፈላውውሃ የታረደውን ዶሮ መገሸር እና ላባውን
ማጽዳት/መንጨት
4. ቀጫጭን ላባዎችን በእሳት ነበልባል መለብለብ
5. ዶሮውን መበለት፣ ማጠብ እና በሎሚ መዘፍዘፍ
6. የተከተፈውን ሽንኩርት ከበሰለ በኃላ፣ ዘይትጨምሮ በደንብ
ማብሰል እና በርበሬ ጨምሮ በደንብ ማቁላላት፡፡
7. የተፈጨውን ነጭሽንኩርት ቁሌቱ ላይ በመጨመር፣ ውሃ
እየጨመሩ ማብሰል

45 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

8. በቂ ውሃ መጨመር
9. ታጥቦ የተዘጋጀውን የዶሮ ሥጋ መጨመር እና ማብሰል
10. የዶሮውሥጋ እንደበሰለ የገበታጨው፣ ቅቤ፣ መከለሻ
መጨመር እና የበሰለ እንቁላል ጨምሮ ከምድጃውማውረድ
11. በእንጀራ መመገብ ይቻላል፡፡

ሥዕል 2.5 የዶሮ ወጥ

46 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠርዥ 2.4 በቤኒሻንጉል ጉሙዝክልል ከሚኖሩ ብሔረሰቦች መካከል የተወሰኑ


የምግብ አይነቶችና የሚዘጋጁበት ቁሶች

ብሔረሰብ የምግብ የሚዘገጁበት ቁሶች


ዓይነት
ቤኒሻንጉል የቄንቄስ ወጥ ከቄንቄስ ተክል ፍሬ
ገንፎ የማሽላ ዱቄት ወይም የበቆሎ ዱቄትና
ውሃ
የቁንጹ ወጥ፣ ከለጋ ቀርቀሃ

ሽናሻ ማጢማሮ የዱባ ቅጠል፣ ካማ/ሴዶ፣ ጨው፣ በርበሬ


ጭንቦ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ጨው፣ ወተት
ቦርዲ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዳጉሳ፣ ብቅል፣ እንኩሮ
ጉሙዝ ገንፎ፣ የማሽላዱቄት ወይም የበቆሎ ዱቄትና ውሃ

ቦርዴ የማሽላ ዱቄት ወይም የበቆሎ ዱቄት፣


ብቅል፣ እንኩሮ እና ውሃ
ካማ ካማ፣ ጨው፣ ውሃ
ላላቃ ላላቃ፣ ጨው፣ ውሃ፣ ጥሻ

2.1.3.4 በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ የምግብ ክፍሎች


ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛ የሆነች እና የራሳቸው
የማንነት መገለጫ የሆነ ባህላዊ ምግቦች ያሏቸው ህዝቦች
የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡

47 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ባህላዊ ምግቦች ከተለያየ ዓይነት የሚሰሩ ሲሆኑ ከብዙ በጥቂቱ


የሚከተሉትናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- አነባበሮ፣ ዶሮወጥ፣ ድፎ ዳቦ፣
ገንፎ፣ እንጀራ፣ ቡላ፣ ቆጮ፣ ጭንቦ፣ አንጮቴ፣ ክትፎ ወዘተ
ናቸው፡፡

ሠንጠርዥ 2.5 የባህላዊ ምግብ ክፍፍል

ከእህል የሚዘጋጁ ከእፅዋት የሚዘጋጁ ከእንስሳት የሚዘጋጁ


እንጀራ ቡላ ዶሮወጥ
ድፎ ዳቦ ቆጮ ክትፎ
አንባሻ አንጮቴ ጥሬ ሥጋ/ቁርጥ/
ጭኮ ሴዶ/ካማ
አነባበሮ ቁንጹ
ጨጨብሳ
ገንፎ
ጭንቦ

2.2 የሰው ውስጣዊ የአካል ክፍሎች


ተማሪዎች ውስጣዊ የአካል ክፍሎች የሚባሉት ምንምን ናቸው?
የሰውውስጣዊ የአካል ክፍሎች ከምንላቸው መካከል፡- አንጎል፣
ልብ፣ ሳንባ ኩላሊት እና ጉበት ይጠቀሳሉ፡፡

48 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

2.2.1 የሰው ውስጣዊ አካል መዋቅር፣ ተግባርና ባህሪያት

ተግባር 2.5

ተማሪዎች የሰው ውስጣዊ አካል መዋቅር እና ተግባር


ዘርዘሩ፡፡

የአንድ ሰውውስጣዊ መዋቅር ዋናዋና የአካል ክፍሎችን ያቀፈ


ነው፡፡የሰው አካል የአካሉን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ
ሚዛናዊ በሆነ መንገድ የሚሰሩ ስርዓቶች ጋር የተዋሀዱ ናቸው፡፡

ለምሳሌ፡- የምግብ መፈጨት ስርዓት፣ የመተንፈሻ አካል ስርዓት


የነርቭ ስርዓት የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ሥዕል 2.6የሰውውስጣዊ አካል ክፍሎች

49 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሀ. አንጎል

አንጎል የማዕከላዊ ስርዓተ ነርቭ ክፍል ሲሆን የሚገኘውም በራስ


ቅል አጥንት ውስጥ ነው፡፡

የአንጎል ክፍሎች እና ተግባራት፡-

የሰው አንጎል የተወሳሰበ ስርዓት አለው፡፡ አንጎል ከምንኖርበት


አካባቢ መልዕክት ተቀብሎ የሚያቀናጅ በጣም ውስብስብ የሆነ
አካል ነው፡፡

አንጎል ሁሉንም የአእምሮ ሂደቶች እና የንቃት ህሊና


እንቅስቃሴዎችን ይቆጣጠራል፡፡ ለምሳሌ፡- ንግግርን፣
እንቅስቃሴን፣ ማሰብን፣ ማሰላሰልን፣ እይታን ወዘተ ይቆጣጠራል፡፡
አንጎል ከአምስቱ የስሜት ህዋሳት መልክት ይቀበላል፣
ይተረጉማል፣ ይተነትናል፣ ፈጣን ምላሽም ይሰጣል፡፡

አንጎል በሶስት ዋናዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነሱም፡-

1. አንጎለ ገቢር
2. አንጎለ አምርት
3. ሰረ ሰርጊ በመባል ይታወቃሉ፡፡

አንጎለ ገቢር፡- ትልቁ የአንጎል ክፍል ሲሆን ማሰብን፣ ስሜትን፣


መማርን፣ ንግግርን፣ ማየትን፣ መስማትን ወዘተ ይቆጣጠራል፡፡

አንጎለ አምርት፡- የኋለኛው የአንጎል ክፍል ሲሆን እንቅስቃሴን


እና የሰውነት ሚዛንን ይቆጣጠራል፡፡

50 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሰረ ሰርጊ፡-የኋለኛው የአንጎል ክፍል ሲሆን መተንፈስን፣


የልብምትን፣ የምግብ ልመትን እና የደምዝውውርን ይቆጣጠራል፡

ሥዕል 2.7 የሰው አንጎል ክፍሎች

ለ/ ልብ

ልብ ማለት ምን ማለት ነው?


ልብ ከሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ ዋነኛው ሞተር ነው፡፡
ልብ ማለት ከጠንካራ ጡንቻ የተሰራ ሲሆን ምግብና ኦክስጂን
የያዘውን ደም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚረጭ ነው፡፡
ደም ማለት ፈሳሽ የሆነና የተለያየ ንጥረ ምግብ እና ኦክስጂንን
የያዘ ነው፡፡
ሐ/ ሳንባ

ሳንባ ማለት ለስላሳ የሰውነት ክፍል ሲሆን በደረታችን አጥንት


ጀርባ የሚገኝ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ የሳምባ ዋነኛ ተግባር
ከአካባቢ አየር/ኦክሲጅን/ በመውሰድ ወደ ደም በመላክ እና

51 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ከደምም የተቃጠለ አየር በመቀበል ወደ ውጭ ያስወጣል፡፡ ሳንባ


የሰውነትን ቆሻሻን ከሚያስወግዱ አካላት አንዱ ነው፡፡ ሳንባ
ሁለት ክፍሎች ሲኖሩት የቀኝ ሳምባ እና የግራ ሳንባ በመባል
ይታወቃሉ፡፡ ሁለቱም የሳንባ ክፍሎች እኩል መጠን እና ክብደት
የላቸውም፡፡ ምክንያቱም የግራ ሳንባ ክፍል ከቀኝ የሳንባ ክፍል
በትንሹ ያነሰ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት የግራ የሳንባ
ክፍል ከልብ ጋር ቦታ ስለሚጋራ ነው፡፡

መ/ኩላሊት
ኩላሊት ማለት ምን ማለት ነው?
ኩላሊት ማለት በሰው ልጅ በግራ እና በቀኝ የሆድ ክፍል የሚገኝ
ባቄላ መሰል የአካል ክፍል ነው፡፡ ኩላሊት ቆሻሻን ከሰውነታችን
ከሚያስወግዱ የአካል ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
የኩላሊት ተግባራት፡-
- የውሃ እና የደም መጠንን ማስተካከል
- የሰውነታችንን ፈሳሾች ኬሚካዊ ባህሪያት ማስተካከል እና
የመሳሰሉትን ያከናውናል፡፡
- ከሰውነታችን ቆሻሻን በሽንት መልክ ያስወግዳል፡፡

ሠ/ጉበት

ጉበት ማለት በላይኛው የሆድ ክፍል ውስጥየሚገኝ ትልቁ የአካል


ክፍል ነው፡፡ የጉበት ዋነኛ ተግበር ደምን ከጎጂ ነገሮች ማጽዳት
ነው፡፡

ጉበት ለሰውነታችን ከሚሰጠው ብዙ ጥቅሞች ውስጥ ጥቂቶቹ፡-

52 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 የሀሞት ፈሳሽን ያመነጫል፡፡ ሀሞት የምግብ መፈጨትን


የሚያግዝ ኬሚካል ነው፡፡
 የምግብ ልመትን ያፋጥናል፡፡
 ገንቢ ምግቦችን (ፕሮቲን)፣ ሀይልና ሙቀት ሰጪ (ካረቦ
ሀይድሬት)፣ ስብና ቅባቶችን (ፋት) ያከማቻል፡፡

2.2.2 ስርዓተ- ልመትን የሚያከናውኑ የአካል ክፍሎች


ስርዓተ-ልመት ማለት ምን ማለት ነው?
ስርዓተ -ልመት ማለት ከአፍ እስከ ፊንጢጣ ድረስ ያለውን
የአካል ክፍል የያዘ ቱቦ ነው፡፡ በዚህ ዑደት ውስጥ የሚካተቱ
የአካል ክፍሎች፡-
አፍ፣ ጉሮሮ፣ ጨጓራ፣ አንጀት እና ፊንጢጣ ናቸው፡፡
አፍ፡-ምግብን በመጀመሪያ የምናኝክበት እና የምናደቅበት
የስርዓተ-ልመት አካል ክፍል ነው፡፡ ምግብ ለመጨረሻ ጊዜ
የሚደቀው በትንሹ አንጀት ውስጥ ነው፡፡
ጉሮሮ፡-ምግብን ከአፍ ወደ ጨጓራ የሚወስድ ቱቦ ነው፡፡
ጨጓራ፡- ምግብን በዋነኝነት የሚፈጭበት የአካል ክፍል ነው፡፡
አንጀት፡- አንጀት በሁለት ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነሱም፡- ትንሹ
አንጀት እና ትልቁ አንጀት ይባላሉ፡፡
ትንሹ አንጀት፡- ምግብን መፍጨት እና ከተፈጨ ምግብ ውስጥ
ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በመውሰድ ወደ ደም የሚያዋህድ የአካል
ክፍል ነው፡፡
ትልቁ አንጀት፡- ውሃን ከቆሻሻ የሚያጣራ እና ቆሻሻን
በጊዜያዊነት የሚያጠራቅም የአካል ክፍል ነው፡፡

53 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 2.8 የስርዓተ- ልመት አካል ክፍሎች

መልመጃ 2.4

ሀ. የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ ፡፡

1. ከሚከተሉት ውስጥ የአንጎል ክፍል ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ/አንጎል ገቢርሐ/ አንጎል አምርት
ለ/ሰረሰር መ/ሰረ ሰርጊ
2. ትልቁ የአንጎል ክፍል የቱ ነው?
ሀ/ አንጎል ገቢርሐ/ አንጎል አምርት
ለ/ሰረሰር መ/ ሰረ ሰርጊ
3. የደም ተግባር የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ኦክሲጅንን ማጓጓዝ ለ/የላመ ምግብን ማጓጓዝ
ሐ/ውሃን ማጓጓዝ መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

54 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

4. የተቃጠለ አየር ከሰውነታችን ለማስወጣት የሚረዳን የአካል


ክፍል የቱ ነው?
ሀ/ ሳንባ ሐ/ ጉበት
ለ/ ኩላሊት መ/ ደም
5. ከሚከተሉት ውስጥ የስርዓተ-ልመት የአካል ክፍል የሆነው
የቱ ነው?
ሀ/ ኩላሊት ሐ/ ጨጓራ
ለ/ሳንባ መ/ አንጎል

ለ. የሚከተሉትን ባዶ ቦታዎች በትክክለኛው መልስ ሙሉ፡፡

1.የሰው ውስጣዊ የአካል ክፍል ከምንላቸው ውስጥ ዋና ዋናዎቹ---


-------፣---------፣-----------፣------------ እና ----------- ናቸው፡፡

2. --------------- የስርዓተ- ነርቭ ክፍል ሲሆን የሚገኘውም በራስ


ቅል አጥንት ውስጥ ነው፡፡

2.3ቁስ አካል
2.3.1 የቁስ አካል ትርጉም

ቁስ አካል ማለት ምን ማለት ነው?


ተማሪዎች ማንኛውም በአካባቢያችሁ የሚገኙትን ነገሮች አንድ
በአንድ ጥቀሷቸው ለምሳሌ፡- ጥቁር ሰሌዳ፣ ደብተር፣ ወንበር፣
ውሃ፣ አየር እና የመሳሰሉት፡፡ እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ
ክብደት አላቸው ወይስ የላቸውም? ቦታስ ይይዛሉ ወይስ
አይዙም? እነዚህ ነገሮች በጥቅሉ ምን ይባላሉ?

55 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ቁስ አካል ማለት ማንኛውም ክብደት (መጠነ ቁስ) ያለውና ቦታ


የሚይዝ ነገር ነው፡፡ የምንበላው ምግብ፣ የምንጠጣው ውሃ፣
የምንተነፍሰው አየር፣ የምንለብሰው ልብስ፣ የምንጽፍበት ወረቀት፣
የምንቀመጥበት ወንበር፣ የሚዘንበውዝናብ፣ ዳመናው፣ አቧራው
እና የመሳሰሉት በሙሉ ቁስ አካል ናቸው፡፡

ተግባር 2.6 የቡድን ውይይት

ከዚህ በላይ በተመለከተው ገለፃ መሠረት አየር የቁስ አካል


ምሳሌ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡አየር እንዴት ቁስ አካል ሊሆን
ይችላል? አየር ክብደት አለው? አየር ቦታ ይይዛል? እነዚህን
ጥያቄዎች በቡድን ተወያዩበትና የውይይቱን ፍሬ ነገር ለክፍል
ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡

የተግባር የሙከራ2.1

አየርቦታእንደሚይዝናክብደትእንዳለውለማየትከዚህበታችየተገለጹት
ንቀላልሙከራዎችንበመስራትመረዳትይቻላል፡፡
ተማሪዎች፡-

1. መጀመሪያ አንድ ባዶ ትንሽ የዘይት ጀሪካን አዘጋጁ


2. ትልቅ የውሃ ባልዲ አዘጋጁ እና ውሃ ሙሉት
3. የተዘጋጀውን ትንሽ የዘይት ጀሪካን ውሃ በተሞላው ባልዲ
ውስጥ ለማስጠም ሞክሩ፡፡ ምን ተመለከታችሁ?

56 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ይህ ቡቅ ቡቅ የሚለውበጀሪካኑ ውስጥየነበረው አየር ቦታውን


ለውሃ እየለቀቀ መሆኑን ተገነዘባችሁ? ይህም ማለት አየር ቦታ
እንደሚይዝ የሚያመለክት ሙከራ ነው፡፡አየር ክብደት እንዳለው
ለማረጋገጥ ደግሞ የሚከተለውን ሙከራ ስሩ :-

1. ሁለት ባዶ ፊኛዎችን አዘጋጁ


2. ሁለቱንም ባዶ ፊኛዎች መዝኗቸው እና ክብደታቸውን
መዝግቡ
3. አንደኛውን ፊኛበአየር በደንብ ሙሉት

ሁለቱንም ፊኛዎች ክብደታቸውን መዝኑ እና በተራ ቁጥር


ሁለት ከመዘናችሁት ክብደት ጋር አነፃጽሩት፡፡ በአየር
የተሞላውፊኛ አየር ካልተሞላው መብለጡን ተገነዘባችሁ?
ይህ ማለት አየር ክብደት መኖሩን አረጋገጣችሁ ማለት
ነው፡፡

2.3.2 የቁስ አካል ባህሪያት

የተለያዩ ቁሳቁሶችን አንዱ ከአንዱ የምንለየው በምናቸው ነው?


ለምሳሌ፡- የሚከተሉት ቁሳቁሶች በምናቸው አንዱ ከአንዱ
እንለያለን?
 ደቃቅ ከሰል እና ደቃቅ ጠመኔ
 ውሃ እና ብርጭቆ
 የሎሚ ጭማቂ እና የብርቱካን ጭማቂ
 አሸዋ እና ጨው

57 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ማንኛውም ቁስ ከሌላው የሚለይበት የራሱ የሆነ ባህሪያት አሉት፡፡


ስለዚህ የቁስ ባህሪያት አንዱን ቁስ ከሌላው ለመለየት የሚያስችለን
ዝርዝር ፀባዮች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በመቅመስ፣ በቀለም፣ በማየት፣
በማሽተት እናበመሳሰሉት መለየት ይቻላል፡፡

ቁስ አካሎች ሁለት ዋና ዋና ባህሪያት አላቸው፡፡ እነሱም፡-

 ፊዝካዊ/አካላዊ/ ባህሪያትና
 ኬሚካዊ ባህሪያት ናቸው፡፡
ሀ. ፊዝካዊ/ አካላዊ/ ባህሪያት

ፊዝካዊ /አካላዊ/ ባህሪያት ማለት ቁስ አካል ማንነታቸውን


(የተፈጥሮ ስሪታቸውን) ሳይለውጡ የሚያሳዩት ባህሪያት ናቸው፡፡
ይህም ማለት አንድ ቁስ አካል የአካባቢው መጠነ ሙቀትና
የአካባቢ አየር ግፊት ቋሚ ሆነው ቁስ አካሉ ስሪቱን ሳይቀይር
የሚያሳያቸው ባህርያት ናቸው፡፡ በመደበኛ ሁኔታ የቁስ አካል
አካላዊ ባህርያት የማንነቱ ገላጭና ኢ-ተለዋዋጭ ጠባዩ ነው፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የቁስ አካል ፊዝካላዊ/አካላዊ/ ባህሪያት
ምሳሌዎች ናቸው፡፡ እነሱም

 ቀለም
 እፍጋት (ደንሲቲ)
 ጥንካሬ (ሃርድነስ)
 ቅልጠተ- ነጥብ፣ ፍሌተ- ነጥብ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ቀለም

58 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ቀለም ማለት ቁስ አካላት የሚያንጸባርቁት ወይም የሚያመነጩት


የብርሃን ጨረር ነው፡፡ለምሳሌ ቁስ አካላት ቀይ ቀለም
የሚኖራቸው ከሰባቱ የብርሃን ቀለማት ስድስቱን አሳልፈው ቀዩን
ስለሚያንጸባርቁትነ ው፡፡

ተግባር 2.7
ተማሪዎች በክረምት ወራት ቀሰተ-ዳመና አይታቸሁ

ታውቃላችሁ? ካያችሁ የተመለከታችሁትን ቀለማት ዘርዘሩ፡፡

ሰባቱ የብርሃን ቀለማት የምንላቸው፡- ሃምራዊ፣ ኢንዲጎ፣ ሰማያዊ፣


አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ብርቱካናማ እና ቀይ ቀለም ናቸው፡፡

እፍጋት፡- ማለት የአንድ ቁስ አካል መጠነቁስ ለይዘቱ ሲካፈል


የምናገኝው ነው፡፡

መጠነቁስ
እፍጋት =
ይዘት

ሁለት የተለያዩ ፈሳሾች እኩል እፍጋት የላቸውም፡፡ለምሳሌ የውሃ


እና የዘይትን እፍጋት መመልከት ይቻላል፡፡ሁለት እኩል መጠን
ያላቸውን ውሃ እና ዘይት ወስደን በአንድ ብርጭቆ ውስጥ
ብንጨምር ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ውሃው ወደታች ሲዘቅጥ ዘይቱ
ደግሞ በውሃው ላይ ይንሳፈፋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት
የዘይት እፍጋት ከውሃ እፍጋት ያነሰ በመሆኑ ነው፡፡

59 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የውሃ ሁነት
የውሃ ሁነት ማለት በተለያየ መጠን-ሙቀት እና የአየር ግፊት
በጠጠር፣ በፈሳሽ እና ትነት መገኘት ማለት ነው፡፡
ቅልጠተ-ነጥበ ፍሌተ-ነጥበ

ጠጣር(በረዶ) ፈሳሽ(ውሃ) ጋዝ(ውሃ ትነት)

ነጥበ ጥጥር ነጥበ ቅዝቅዝ

የውሃ ነጥበ ቅልጥት እና ነጥበ ጥጥር ባህር ጠለል ላይ መነሻቸው


ከ 00C ሲሆን ነጥበ ፍሌት እና ነጥበ ቅዘቅዘ መነሻቸው ከ1000C
ነው፡፡

ነጥበ ቅልጠት እና ነጥበ ፍሌት ወደፊት የሚሄዱ ሁነታዊ


ለውጦች ሲሆኑ ነጥበ ጥጥር እና ነጥበ ቅዝቅዝ ወደኋላ የሚመለሱ
ሁነታዊ ለውጦች ናቸው፡፡

0
C ይህ
አስታውሱ ምልክት ዲግሪ ሴንቲግሬድ በመባል ይታወቃል፡፡
፡-
አገልግሎቱም የሙቀትን መጠን ይለካል፡፡

ለ. ኬሚካዊ ባህርያት

ኬሚካዊ ባህሪያት ማለት ቁስ አካላት ማንነታቸውን ሲቀይሩ


ወይም ወደ ሌላ አዲስ ቁስ አካል ሲለወጡ የሚያሳዩት ባህሪያት
ናቸው፡፡ የሚከተሉት ባህሪያት የኬሚካዊ ባህሪያት ምሳሌዎች
ናቸው፡፡

 መንደድ/መቃጠል
 መዛግ/ዝገት

60 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 መበስበስ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የተግባር ሙከራ 2.2

ተማሪዎች የሚከተለውን ቀላል ሙከራ በመስራት ኬሚካዊ


ባህሪያትን መረዳት ይቻላል፡፡

ለሙከራውየሚያስፈልጉቁሳቁሶች፡- ወረቀት፣ ክብሪት፣ ማንደጃ እና


ሳህን

ተማሪዎች ሙከራውን ስትሰሩ በአካባቢያችሁ ተቀጣጣይ ነገር


ማለትም እንደነዳጅ ያሉ ነገሮች አካባቢያችሁ አለመኖራቸውን
አረጋግጡ፡፡

የአሰራር ቅደም ተከተል፡-

ያዘጋጃችሁትን ወረቀት ከማንደጃ ሳህኑ ላይ አሰቀምጡት፡፡


ከዚያም ክብሪቱን ጫሩ እና ወረቀቱን አቀጣጥሉት፣ መንደዱን
እንደጨረሰ ምን አገኛችሁ? ያገኛችሁት መጀመሪያ ከነበረው
ወረቀት ጋር ተመሳሳይ ነው? አዲስ ነገር ካገኛችሁ የተካሄደው
ለውጥ ኬሚካዊ ባህሪ ማለት ነው፡፡

2.3.3 የቁስ አካል ለውጦች

ቁስ አካል ከአንድ ዓይነት መልክ ወደ ሌላ ዓይነት መልክ


ይለወጣል፡፡

ለምሳሌ፡-

 እንጨት ሲቃጠል ወደ አመድና ጪስ ይለወጣል፡፡


 ጨው ሲሟሟ ከጠጣር ወደ ፈሳሽ ይለወጣል፡፡

61 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 ውሃ ሲፈላ በመትነን ከፈሳሽ ወደ ጋስ ይለወጣል፡፡


 ጠመኔ ስንጽፍበት ደቃቅ ወይም ብናኝ ይሆናል፡፡
 ሚስማር፣ ማጭድና ማረሻ የመሳሰሉት እርጥበት ባለበት
ቦታ ሲቆዩ ይዝጋሉ፡፡

የተወሰኑት ቁስ አካል ለውጦች የቁስ አካሉን ማንነት (የተፈጥሮ


ስሪት) አይለውጡም፡፡ ሌሎች ለውጦች የቁስ አካሉን ማንነት
(የተፈጥሮ ስሪት) ሙሉ በሙሉ የሚለውጡና አዲስ ቁስ አካል
ከአዲስ ባህሪ ጋር የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ቁስ አካል
ሁለት አይነት መሰረታዊ ለውጦችን ያካሂዳል፡፡ እነርሱም አካላዊ
/ፊዝካዊ/ እና ኬሚካዊ ለውጦች ይባላሉ፡፡

ሀ. አካላዊ /ፊዝካዊ/ ለውጦች፡-

ቁስ አካሎች ማንነታቸውን ሳይለውጡ ከአንድ መልክ ወደ ሌላ


መልክ የሚለወጡበት ዓይነት ለውጦች አካላዊ /ፊዚካዊ/ ለውጦች
ይባላል፡፡ አካላዊ /ፊዚካዊ/ ለውጥ በቁስ አካሉ ላይ የስሪት ለውጥ
የማያመጣ ሂደት ነው፡፡ አካላዊ ለውጥ የቁስ አካልን ቅርፅ፣
መጠንና ሁነትን ይቀይራል፡፡ በአካላዊ /ፊዝካዊ/ ለውጦች ወደ
ሌላ የተለወጡ ቁስ አካሎች በቀላሉ ወደ ነበሩበት ሊመለሱ
ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የውሃ መትነን አካላዊ /ፊዚካዊ/ ለውጥ ሲሆን
ውሃ ሲተን ከፈሳሽ ሁነት ወደ ትነት (ጋስ ሁነት) ይለወጣል፤
ትነቱም ሲቀዘቅዝ ከጋዝ ሁነት በቀላሉ ተመልሶ ፈሳሽ ውሃ
ይሆናል፡፡ በመሆኑም አካላዊ /ፊዚካዊ/ለውጦች ጊዜያዊ ለውጦች
ናቸው፡፡

62 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የሚከተሉት ለውጦች የአካላዊ /ፊዚካዊ/ ለውጦች ምሳሌዎች


ናቸው፡፡

 የበረዶ መቅለጥ
 የሰም መቅለጥ
 የውሃ መፍላት
 የጨው መድቀቅ/የጨው በውሃ መሟሟት/
 የወረቀት መቆራረጥ
 የስኳር መሟሟትና የመሳሰሉት አካላዊ /ፊዚካዊ/
ለውጥ ናቸው፡፡

ለ. ኬሚካዊ ለውጦች፡
ቁስ አካሎች ማንነታቸውን በመለወጥ ከአንድ ዓይነት ወደ ሌላ
የተለየ ዓይነት የሚለወጡ ከሆነ ለውጡ ኬሚካዊ ለውጥ ይባላል፡፡
ኬሚካዊ ለውጥ ነገሮች ስሪታቸውን ወይም የዓይነት ለውጥ
እንዲያመጣ ምክንያት ይሆናል፡፡ በኬሚካዊ ለውጥ አዲስ ቁስ
አካል ከአዲስ ባህሪ ጋር ይፈጠራል፡፡

በኬሚካዊ ለውጥ ወደ ሌላ ቁስ አካል የተለወጠን ቁስ አካል


ወደ ነበረበት ዓይነት መመለስ ይከብዳል፡፡

ለምሳሌ የወረቀት መቃጠል ኬሚካዊ ለውጥ ነው፡፡ በመሆኑም


ወረቀቱ ከተቃጠለ በኋላ የተለየ ሌላ ቁስ አካል ወይም አመድ
ስለሚሆን ከአመዱ መልሶ ወረቀት መስራት አይቻልም፡፡

የሚከተሉት ለውጦች የኬሚካዊ ለውጦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

63 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 መቃጠል
 ዝገት
 መበስበስ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
መቃጠል

ተማሪዎች አንድ ነገር ለመቃጠል ምን ያስፈልጋል?

አንድ ነገር ለማቃጠል በመሰረታዊ ደረጃ አየር (ኦክሲጅን)


ያስፈለጋል፡፡ ያለ አየር (ኦክሲጅን) ነገሮችን ማቀጣጠል
አይቻልም፡፡ ለምሳሌ፡- እሳት ለማቀጣጠል እፍ በምትሉበት ጊዜ
ከአፋችሁ ውስጥ በሚወጣው የተቃጠለ አየር (ካርቦን ዳይ
ኦክሳይድ) አማካኝነት በእሳቱ ዙሪያ ያለውን አየር (ኦክሲጅን) ወደ
እሳቱ ስታስጠጉት እሳቱ መቀጣጠል ይጀምራል፡፡ ይህም ማለት
አየር (ኦክሲጅን) ቁስ አካላትን ለማቀጣጠል ይጠቅማል፡፡

መበስበስ

መበስበስ ማለት ሕይወት ያላቸው ነገሮች ከሞቱ በኋላ በውስጣችው


ወይም በውጫዊ ተህዋሲያን (ባክቴሪያ) አማካኝነት በውስጣቸው
ያለው ቁስ ነገሮች ወደ አፈርነት የሚቀየርበት ሂደት ነው፡፡
እንዲሁም ሕይወት የሌላቸው ነገሮች በዝናብ እና በፀሐይ
መፈራረቅ ምክንያት ወይም በባክቴሪያዎች አማካይነት ወደ
አፈርነት የሚቀየሩበት ሂደት መበስበስ ይባላል፡፡

64 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

መልመጃ 2.5

ሀ/ የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክልኛ መልስ የያዘው ሆሄ/ፊደል/


ምረጡ

1. ከሚከተሉት ውስጥ ቁስ አካል የሆነው የቱ ነው?


ሀ/ ድንጋይ ለ/ ውሃ ሐ/ ወረቀት መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
2. ፊዝካዊ/አካልዊ/ ባህሪያት የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ቀለም ለ/ መዛግ ሐ/ መንደድ መ/ መበስበስ
3. ከሚከተሉት ውስጥ የኬሚካዊ ለውጥ የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የወረቀት መቆራረጥ ለ/ የወረቀት መቃጠል
ሐ/ የውሃ መፍላት መ/ የሰም መቅለጥ
4. የቁስ አካል ስንት ዓይነት ለውጦች አሉት?
ሀ/ 4 ለ/ 2 ሐ/ 3 መ/ 5
5. ከሚከተሉት ውስጥውሃ መገኘት የሚችልበት አካላዊ ሁነት
የቱ ነው?
ሀ/ ጥጥር ሐ/ ጋሰ
ለ/ ፈሳሽ መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
6. ውሃ ሲፈላ ወደ ምን ሁነት ይለወጣል?
ሀ/ወደ ቅዝቅዝ ሐ/ ወደ ጋስ
ለ/ ወደ ፈሳሽ ውሃ መ/ ወደ በረዶ
7. ከሚከተሉት ውስጥ ፈሳሽ የሆነው ቁስየቱ ነው?
ሀ/ውሃ ለ/በረዶ ሐ/ጨው መ/ ስኳር

65 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

2.4ብርሃን እና ጥላ
2.4.1 ብርሃን

ተግባር 2.8

ተማሪዎች ብርሃን ምንድነው? ብርሃንን ከምን ከምን እንደምናገኝ


በቡድን ተወያዩና በግል ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ መብራት
የጠፋበት የመኝታ ክፍላችሁ ስትገቡ የምትተኙበትን አልጋ ማየት
ትችላላችሁ? ባትሪ፣ ፋኖስ ወይም ሌላ ብርሃን ሰጭ መብራት
አብሩና ተመልከቱ፡፡ ምን አያችሁ?

ተማረዎች ብርሃን ማለት ምን ማለት ነው?

ብርሃን ማለት ነገሮችን በዓይን እንዲታዩ የሚያደረግ የተፈጥሮ


እና ሰው ሰራሽ ጨረር ነው፡፡ የብርሃን ምንጮች በሁለት
የሚከፈሉ ሲሆን፣ በተፈጥሮአዊ መንገድ የሚገኘው ሲሆን
ምንጮቹም ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ከዋክብት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ሰው ሰራሽ የብርሃን ምንጮች የምንላቸው ደግሞ ሻማ፣ ፋኖስ፣
ጧፍ፣እሳት፣ኤለክትሪክየእጅባትሪየመሳሰሉት ናቸው፡፡

66 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 2.9 የብርሃን ምንጮች

2.4.2 የብርሃን ባህሪያት


ብርሃን በቀጥተኛ መንገድ እንድሚጓዝ ከጥንት ጀምሮ የታወቀ
ሀቅ ነው፡፡ደግሞም የብርሃን ቀጥተኛ ጉዞ አልፎ አልፎ ሊስተጓጎል
እንድሚችል ሌላው የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ ብርሃን የሚጓዝበትን
አቅጣጫበሦስት መንገዶች ይቀይራል፡፡

ለምሳሌ፡-የብርሃን መንፀባረቅ/ሪፍሌክሽን/፣የብርሃን
መሰበር/ሬፍራክሽን/ መወላገድ/ዲፍራክሽን/ ናቸው፡፡

አንድ ጨርረ ከአንድ አካል ወጥቶ ወደ ሌላ አካል ሲገባ የጨረሩ


የሞገድ ርዝመትና ፍጥነት ይቀየራል፡፡ ሆኖም ግን ድግግሞሹ
ባለበት ይጸናል፡፡ የተለያየ የብርሃን ቀለማት እኩል አይሰበሩም፡፡
ቀይ ብርሃን ቀስ ብሎ ሲሰበር ወይንጠጅ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ
ይሰበራል፡፡ ስለሆነም ከሁሉም ቀለም የተሰራ ነጭ ብርሃን
በብርሃን ስባሪ ሲከሰት ነው፡፡

2.4.3 የብርሃን ጥቅም


ብርሃን ነገሮችን በዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ የተፈጥሮ ጨረር
ነው፡፡ ያለብርሃን ቁስ አካላትን ማየት አይቻልም፡፡

67 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለምሳሌ፡- የፀሐይ ብርሃን መውሰድ ይቻላል፡፡

የፀሐይ ብርሃን ለእፅዋት ዕድገት ያስፈልጋል፡፡ ይህም እፅዋት


ምግባቸውን ለማዘጋጀት በዋናነት የፀሐይ ብርሃን ያስፈልጋቸዋል፡
፡ እንዲሁም ልብስ አጥበን ለማድረቅ የፀሐይ ብርሃን አሰፈላጊ
ነው፡፡

የፀሐይ ብርሃን ምግብን በማድረቅ ለረጅም ጊዜ ለማቆየት


ይረዳል፡፡ ብርሃን እንደ ሙቀት የራሱ የሆነ ሀይል ወይም ጉልበት
አለው፡፡ ይህ የብርሃን ጉልበት በዋናነት የሚጠቅመው ጨለማን
ለማስወገድ ነው፡፡

2.4.4 የጥላ አፈጣጠር


ጥላ ማለት ምን ማለት ነው?
ጥላ በመሰናክል አካል ምክንያት ብርሃን የማያገኝ ቦታ ነው፡፡
ይህ ቦታ ብርሃን አስተላላፊ ካልሆነ አካል በስተጀርባ ይገኛል፡፡
ይህ ጥላ የሚፈጥረው ቅርፅ ብርሃን እንዳያልፍ ያደረገውን አካል
ትክክለኛ ምስል ነው፡፡

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ ጥያቄዎች


ሀ/ የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ
ሐሰት በማለት መልስ/ሽ

1. ባህላዊ የምግብ ዝግጅት ሂደት የሚወሰነው ባህሉ በሚገለጽበት


አካባቢ ነው፡፡
2. ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ባህላዊ ምግቦች መገኛ ናት፡፡
3. ባህላዊ ምግብ የአንድ ሀገር ማንነት አይገልጽም፡፡

68 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለ/ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጥ/ጭ

1. በምግብ አዘገጃጀት ውስጥ የሚካተተው የቱ ነው?

ሀ/የንጥረ ነገር ዝርዝር ለ/የንጥረ ነገር መጠን

ሐ/የዝግጅት መመሪያ መ/ሁሉም መልስ ናቸው


2. ምግብን በመመሪያ መሰረት ማዘጋጀት ለምን ያስፈልጋል?

ሀ/ ትክክለኛ የሆነ ምግብ ለማግኘት


ለ/ አሰልቺ ያልሆነ ምግብ ለመፍጠር
ሐ/ የተመጠነ እና ሁሉን ንጥረነገር የያዘ ምግብ ለማግኘት
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
3. የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ዶሮወጥ ለ/ጨጨብሳ ሐ/ አነባበሮ መ/ ፒዛ
4. ከሚከተሉት ውስጥ አካላዊ ለውጥ የሆነው የቱ ነው?
ሀ/የብረት መዛግ ለ/ የበረዶ መቅለጥ
ሐ/ የቁስ አካል መበስበስመ/ የወረቀት መቃጠል
5. ከባህር ጠለል የውሃ ቅልጠት መጠነ ሙቀትየሆነው የቱ ነው?
ሀ/ 00C ለ/1000C ሐ/1500C መ/500C
6. ከሚከተሉት ውስጥ ኬሚካዊ ለውጥ የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የውሃ መትነን ለ/ የውሃ መቀዝቀዝ
ሐ/ የቁስ አካል መበስበስ መ/ የሰም መቅለጥ

ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡

1.የብርሃንንባህሪያትጥቀሱ፡፡
2. ጥላ ማለት ምን ማለት ነው?

69 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ምዕራፍ ሦስት
3. ተፈጥሮአዊ አካባቢያችን
3.1 የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል የአየር ንብረት
ተማሪዎች፡-

አየር ንብረት ማለት ምን ማለት ነው?

የአካባቢያችሁ የአየር ንብረት ምን ዓይነት ነው?

የአየር ንብረት በአንድ አካባቢ የተመዘገበ የሙቀት መጠን፣


የዝናብ መጠን፣ የአየር እርጥበት፣ የነፋስ ፍጥነት ወዘተ
መረጃዎችን በማስላት የሚገኝ አማካይ ውጤት ነው፡፡

የአየር ንብረቶች ሞቃታማ ወይም ብርዳማ፣ ዝናባማ ወይም


ደረቃማ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በተለያዩ የመሬት ክፍሎች የምናገኘው
የአየር ንብረት የተለያየ ሊሆን የቻለው በተለያዩ የአየር ንብረት
ወሳኝ ሁኔታዎች ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የመሬት ከፍታ፣
ከውኃ/ውቅያኖሶችና ባህር/ አካላት ያለው ርቀትና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡

3.1.1 የአየር ንብረት እና የአየር ሁኔታ ልዩነት


ተማሪዎች የአየር ሁኔታ ማለት ምን ማለት ነው?
የአካባቢ አየር ሁኔታና የአየር ንብረት ልዩነታችው ምንድን ነው?
የአየር ሁኔታ ማለት በየዕለቱ በአንድ አካባቢ የሚኖር የዝናብ፣
የሙቀት፣ የንፋስ ወዘተ ሁኔታ መግለጫ ማለት ነው፡፡

70 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የአየር ሁኔታ በጣም ተለዋዋጭ ነው፡፡ ጧትይቀዘቅዛል፣ ቀን ላይ


ይሞቃል፣ ወደ ማታ ይበርዳል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጰያ ሬዲዩና
ቴሌቭዥን ድርጅት የሚተላለፈው የአየር ሁኔታ ትንበያ በመባል
ይታወቃል፡፡ይህ ከአየር ሙቀትና ቅዝቃዜ አንፃር ሲሆን
የዝናብም ሁኔታ በጣም ተለዋዋጭ ነው፡፡ ምክንያቱም ክረምት
ላይ ብዙ ዝናብ እናገኛለን፡፡ በበጋ ወቅት ግን ደረቅ ሁኔታ
ይታያል፡፡ የነፋሱም አቅጣጫና ፍጥነት በየጊዜው ይቀያየራል፡፡
የአየር ንብረት ማለት በአጭሩ አማካይ የአየር ሁኔታ ማለት
ነው፡፡ የአየር ንብረት ለረጅም ጊዜ ተለክቶ የተገኘ የአንድ
አካባቢ አማካይ የሙቀትና የዝናብ ሁኔታ ነው፡፡ ሙቀትና ዝናብ
እንደ ዋና ቀረቡ እንጂ የአየር ግፊት፣ የአየር እርጥበትና የነፋስ
ሁኔታም መጥቀስ ይቻላል፡፡

ተግባር 3.1

1. በየዕለቱ በሬድዮ እና በቴሌቭዥን የሚተላለፈው የአየር

3.1.2መረጃ ምንን ይገላጻል?


የአየርሁኔታናየአየርንብረትአባላት
2. የአየር ሁኔታ እና የአየር ንብረትን ልዩነት ግለጹ፡፡

ተማሪዎች የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት አባላትን በቡድን


ተወያይታችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ ግለጹ፡፡

71 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት አባላት የሚባሉት፡- ሙቀት፣ ዝናብ፣


የአየር ግፊት፣ የአየር እርጥበት እና የንፋስ ሁኔታንም
ያጠቃልላል፡፡

3.1.3 የአየር ሙቀት አለካክና ምዝገባ


ተማሪዎች የአየር ሙቀት ማለት ምን ማለት ነው?

ተማሪዎች የአየር ሙቀት መለኪያ መሳሪያ ምን ይባላል?

የከባቢ አየር ሙቀት ከፀሐይ ብርሃን የሚገኝ ኃይል ነው፡፡


የከባቢ አየር ሙቀትን ሞቃት፣ ቀዝቃዛ ወይም በጣም ቀዝቃዛ
ነው ብለን መናገር እንችላለን፡፡ ይህ አገላለጽ ከሰዎች ሰዎች
ይለያያል፡፡ ለአንዱ ሞቃት ከሆነለሌላው ላይሆን ይችላል፡፡
ስለዚህ የከባቢ አየር ሙቀትን በትክክል ለመግለጽበመሳሪያ
መለካት አስፈላጊ ነው፡፡የከባቢ አየር ሙቀትን ለመለካት
የምንጠቀምበት መሳሪያ ሙቀት ሜትር ይባላል፡፡

የተለያዩ የሙቀት ሜትሮች አሉ፡፡ ዘወትር የምንጠቀምበት


የፈሳሽ ሙቀት ሜትር ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የአየር
ሙቀት መጠን ሲጨምር በሙቀት ሜትሩ ውስጥ ያለው ፈሳሽ
መጠን ስለሚጨምርና የአየር ሙቀት መጠን ሲቀንስ ደግሞ
የፈሳሹ መጠን ስለሚቀንስ ነው፡፡ የፈሳሹ መጠን በሙቀት ኃይል
መጨመርና መቀነስ በሙቀት ሜትር ውስጥ ያለውን ተንቀሳቃሽ
የብረት ምልክት ወደ ላይና ወደታች እንዲቀሳቀስ ያደርጋል፡፡

72 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

በሙቀት ሜትሩ ውስጥያለው የብረት ምልክት ወደ ላይ ሲወጣ


ሙቀት ከፍተኛ መሆኑንና ወደታች ሲወርድ ሙቀቱ ዝቅተኛ
መሆኑን ያመለክታል፡፡

የአየር ሙቀት የሚለካው በ24 ሰዓት ውስጥ ሁለት ጊዜ ነው፡፡


የሚለካውም የቀኑን ከፍተኛና ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ነው፡፡

የቀኑን ከፍተኛ ሙቀት ለመለካት የምንጠቀመው በመልዕል


ሙቀት ሜትር ነው፡፡ ይህ መሳሪያ በሜሪኩሪ የሚሰራ ሙቀት
ሜትር ሲሆን በ24 ሰዓት ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ ሙቀት
መጠን ይመዘግባል፡፡

ሥዕል 3.1 መልዕል ሙቀት ሜትር

የቀኑ ዝቅተኛ የአየር ሙቀት መለኪያ መንዕስ ሙቀትሜትር


ይባላል፡፡ ይህ መሳሪያ በአልኮል የሚሰራ ሙቀት ሜትር ሲሆን
በ24 ሰዓት ውስጥ የሚኖረውን ዝቅተኛ የሙቀት መጠን
ይመዘግባል፡፡

73 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 3.2 መንዕስ ሙቀት ሜትር

የቀን የአየር ሙቀት በ24 ሰዓት ውስጥ ይለዋወጣል፡፡በዚህ


ምክንያት በ 24 ሰዓት ውስጥ አንድ ጊዜ ከፍተኛ፣ አንድ ጊዜ
ደግሞ ዝቅተኛ ሙቀት ይኖራል፡፡ በቀሪዎቹ ጊዜያት የሚኖረው
ሙቀት በ ሁለቱ መካከል ይሆናል፡፡ ይህ ሁኔታ እለታዊ ልከ
ሙቀት ትመት ይባላል፡፡

እለታዊ ልከ ሙቀት ትመት ማለት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን


ውስጥ የሚከሰት የልከ ሙቀት መለዋወጥ ነው፡፡ የፀሐይ ብርሃን
በአናታችን ላይ የሚሆነው ከቀኑ በ6 ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ የከባቢ
አየር ሙቀት ግን በዚህ ሰዓት ከፍተኛ አይሆንም፡፡

ከፍተኛ የከባቢ አየር ሙቀት የሚኖረው ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 9


ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት መሬት
ከከባቢ አየር ዘግይቶ ስለሚሞቅ ነው፡፡ የቀኑም ዝቅተኛ ሙቀት
የሚኖረው ፀሐይ እንደጠለቀች ወይም ለሊት ሳይሆን ፀሐይ
ከመውጣቷ ቀደም ብሎ ከንጋቱ 11 ሰዓት አከባቢ ነው፡፡

74 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የአየር ሙቀት በየወሩ የመለዋወጥ ባህሪይ አለው ፡፡ ይህ የአየር


ሙቀት ለውጥ ደግሞ ዓመታዊ ልከ ሙቀት ትመት ይባላል፡፡
ዓመታዊ ልከ ሙቀት ትመት ማለት በአንድ አመት ውስጥ
በአንድ በተወሰነ ቦታ ላይ የሚከሰተው የልከ ሙቀት መለዋወጥ
ነው ፡፡

ዓመታዊ ልከ ሙቀትን ለማወቅ በመጀመሪያ በአንድ ዐመት


ውስጥ ያሉትን ወራት መዝግበን የእያንዳንዱን ወር አማካይ
ወራዊ ልከ ሙቀት እንሠራለን፡፡ ይህ የሚሰራው የወሩን ከፍተኛ
ሙቀትና የወሩን ዝቅተኛ ሙቀት ደምሮ ለሁለት በማካፈል
የተገኘውን ውጤት በእያንዳንዱ ወር ስር በመመዝገብ ነው፡፡

በሚከተለው ሠንጠረዥ ከቀረበው መረጃ የአሶሳ ጣቢያ ዓመታዊ


ልከ ሙቀት ትመት ምን እንደሚመስል እንመለከታለን፡፡

75 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ 3.1 የአሶሳ አካባቢ ዓመታዊ ልከ ሙቀት /በዲግሪ ሴንቲ ግሬድ/ የ2010ዓ.ም ነው፡፡

ወራት መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ስኔ ሐም ነሐ
አማካይ 25.5 25.7 28.1 29.4 29.1 31.6 30.9 29.8 28.2 24.1 23.9 29.1
ከፍተኛ

አማካይ 15.8 15.1 14.5 14.6 13.3 14.4 13.3 15.5 17.0 16.2 16.3 13.3
ዝቅተኛ
አማካይ 20.8 20.4 21.3 22 21.2 23 22.1 22.65 22.6 20.15 20.1 21.2
ዓመታዊ
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ከላይ በሠንጠረዥ 3.1 እንደተመለከተው በአሶሳ አካባቢ በ2010 ዓ.ም ከፍተኛ አማካይ አመታዊ
ሙቀት የተመዘገበባቸው ወራት የካቲት፣ ሚያዝያ እና ግንቦት ሲሆኑ ዝቅተኛ ሙቀት
የተመዘገበባቸው ደግሞ ሐምሌ፣ ሰኔ እና ጥቅምት ወራት ናቸው፡፡

76 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ 3.2 የካማሽ አካባቢ ዓመታዊ ልከ ሙቀት /በዲግሪ ሴንቲ ግሬድ/ የ2009ዓ.ም ነው

ወራት መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ስኔ ሐም ነሐ
አማካይ 28 28.8 29.4 30.9 33.9 34.2 36.1 34.3 29.9 28.6 26.6 26.8
ከፍተኛ
አማካይ 17.2 17.5 16.9 15.8 15.8 19.3 21.2 20 18.3 17.8 17.4 16.6
ዝቅተኛ
አማካይ 22.6 23.15 23.15 23.35 24.85 26.75 28.65 27.15 24.1 23.2 22 21.7
ዓመታዊ
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ከላይ በሠንጠረዥ 3.2 እንደተመለከተው በካማሽ አካባቢ በ2009 ዓ.ም ከፍተኛ አማካይ አመታዊ
ሙቀት የተመዘገበባቸው ወራት መጋቢት፣ ሚያዝያና የካቲት ሲሆኑ ዝቅተኛ ሙቀት ደግሞ ነሐሰ፣
ሐምሌና መስከረም ወራት ናቸው፡፡

77 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ 3.3 የማንኩሽ አካባቢ ዓመታዊ ልከ ሙቀት /በዲግሪ ሴንቲ ግሬድ/ የ2007 ዓ.ም ነው

ወራት መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ስኔ ሐም ነሐ
አማካይ 32.5 32.5 34.2 34.7 34.6 38 38.8 39.1 34.4 31.5 30.6 31.1
ከፍተኛ
አማካይ 16.5 17 14.8 14.2 15.1 13 13.4 16.7 18.4 20.7 18.4 18.2
ዝቅተኛ
አማካይ 24.5 24.75 24.5 24.45 24.85 25.5 26.1 27.9 26.4 26.1 25 24.65
ዓመታዊ
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ከላይ በሠንጠረዥ 3.3 እንደተመለከተው በማንኩሽ አካባቢ በ2007 ዓ.ም ከፍተኛ አማካይ ዓመታዊ
ሙቀት የተመዘገበባቸው ወራት ሚያዝያ፣ ግንቦት፣ መጋቢት እና ሰኔ ሲሆኑ ዝቅተኛ ሙቀት
የተመዘገበባቸው ደግሞ መስከረም፣ ህዳር እና ታህሳስ ወራት ናቸው፡፡

78 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ3.4 የ2006 ዓ.ም የሚያዚያ ወር አማካይ ሙቀት መጠን/በድግሪ ሴንቲግሬድ/

ተ.ቁ የወሩ አማካይ


የጣቢያው ስም አማካይ አማካይ /የከፍተኛና
ከፍተኛ ዝቅተኛ ዝቅተኛ/

1 ሰዳል 22.7 22.7 22.7


2 ሸርቆሌ ጊዜን 39.9 19.1 29.5
3 አባዲ 34.2 24.6 28.4
4 ማንኩሽ 39.1 16.7 27.9
5 ካማሽ 35.1 20.7 27.9
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ከላይ በሠንጠረዥ 3.4 እንደተመለከተው በ2006 ዓ.ም የሸርቆሌ


ጊዜን አካባቢ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ሲኖረው በአንፃሩ ደግሞ
ሰዳል አነስተኛ ሙቀት ነበረው፡፡ ይህም የሙቀት መጠን ከቦታ
ቦታ የሚለያይ መሆኑን ያመለክታል፡፡

3.1.4 የዝናብ መጠን፣ አለካክና ምዝገባ


ተማሪዎች የዝናብ መጠን መለኪያ መሳሪያ ምን ይባላል?
በአንድ ቦታ ላይ በተወሰነ ጊዜ የዘነበው የዝናብ መጠን በዝናም
ሜትር አማካይነት ተለክቶ ይታወቃል፡፡

የዝናም ሜትር በአንድ ቦታ ላይ የዘነበውን የዝናብ


መጠንለመለካት የሚያገለግል መሣሪያ ነው፡፡ የዝናቡ መጠን
የሚታወቀው በመለኪያው መሳሪያ ውስጥ የተጠራቀመውን የዝናብ
መጠን ከብርጭቆው ላይ በሴንቲ ሜትር ወይም በሚሊ ሜትር
የተፃፈውን በማንበብ ነው፡፡

79 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የዝናም መጠን ንባብ ከዝናም ሜትር በየቀኑ ይወሰዳል፡፡


በአንድ ቀን የሚነበብ የዝናም ሜትር የሚገልፀው የቀኑ የዝናብ
መጠን ምን ያህል እንደሆነ ነው፡፡ የአንድ ወር አማካይ የዝናብ
መጠን የሚታወቀው በተከታታይ በወሩ ውስጥ የዘነበውን የዝናብ
መጠን ደምሮ ለ30 ቀን ተከፍሎ የሚገኘው ውጤት ነው፡፡

ሥዕል 3.3 የዝናም ሜትርና የዝናብ መጠን መለኪያ ብርጭቆ

አጠቃላይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን የሚታወቀው ደግሞ በ12


ወራት ውስጥየተመዘገበውን የዝናብ መጠን በመደመር ይሆናል፡፡
ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን የሚታወቀው ከ30-35 ዓመታት
ያለውን የዝናብ መጠን በመደመር ለ30-35 ተካፍሎ የሚገኝ
ይሆናል፡፡

ከታች በሠንጠረዥ 3.5፣ 3.6 እና 3.7 የተመለከተውን የአሶሳ፣


የካማሽና ማንኩሽ አካባቢዎች የዝናብ መጠን ተመልከቱ፡፡

80 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ3.5፡- የአሶሳ አከባቢ ዓመታዊ የዝናብ መጠን /በሚሊ ሜትር/ የ2010 ዓ.ም
መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥ የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐ

215.5 167.1 17.1 1.5 0.0 0.7 28.7 22 235.2 422.7 88.4 218.9

ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ይህንን የዝናብ መጠን ሠንጠረዥ መሠረት በማድረግ ከፍተኛ


የዝናብ መጠን የተመዘገበባቸው ወራት ሰኔ፣ ግንቦት፣ ነሐሴ እና
መስከረም ሲሆን ምንም ዝናብ ያልነበረው ደግሞ የጥር ወር ነው፡
፡ የዓመቱ አጠቃላይ የዝናብ መጠን ደግሞ አንድ ሺ አራት መቶ
አስራ ሰባት ነጥብ ስምንት (1417.8) ሚሊ ሜትር ነው፡፡

ሠንጠረዥ3.6የካማሽ አከባቢ ዓመታዊ የዝናብ መጠን /በሚሊ ሜትር/የ2009 ዓ.ም


መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐ
390.3 109.3 20.8 0.0 0.0 29.9 22.5 102.5 172.5 311.7 413.1 432
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ይህንን የዝናብ መጠን ሠንጠረዥ መሠረት በማድረግ ከፍተኛ


ዝናብ መጠን የተመዘገበባቸው ወራት ነሐሴ፣ ሐምሌ፣ መስከረም
እና ሰኔ ሲሆኑምንም ዝናብ ያልነበራቸው ወራት ደግሞ ታህሳስ
እና ጥር ናቸው፡፡ የዓመቱ አጠቃላይ የዝናብ መጠን ሁለት ሺ
ሰባት ነጥብ ስድስት (2007.6) ሚሊ ሜትር ነው፡፡

81 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዝ 3.7 የማንኩሽ አከባቢ ዓመታዊ የዝናብ መጠን /በሚሊ ሜትር/ የ2007 ዓ.ም
መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐ
214 51.0 0.0 0.0 0.0 0.0 0.0 13 211 255 243 248
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ይህንን የዝናብ መጠን ሠንጠረዥ መሠረት በማድረግ ከፍተኛ


ዝናብ መጠን የተመዘገበባቸው ወራት ሰኔ፣ ነሐሴ እና ሐምሌ
ሲሆኑ ምንም ዝናብ ያልነበራቸው ወራት ደግሞ ህዳር፣ ታህሳስ፣
ጥር፣ የካቲትና መጋቢት መሆናቸውን መናገር እንችላለን፡፡
የዓመቱ አጠቃላይ የዝናብ መጠን አንድ ሺ ሁለት መቶ ሰላሳ
አምስት (1235) ሚሊ ሜትር ነው፡፡

ሠንጠረዥ 3.8 የ2006 ዓ.ም የሰኔ ወር የዝናብ መጠን /በሚሊ ሜትር/

ተ.ቁ የጣቢያው ስም የዝናብ መጠን


1 ወንበራ 143
2 ቶንጎ 178
3 ኩርሙክ 162
4 ሆሞሻ 95.9
5 ማንዱራ 184.8
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

ከላይ በሠንጠረዥ 3.8 እንደተመለከተው ማንዱራ አካባቢ በሰኔ


ወር የተሻለ የዝናብ መጠን ሲኖረው በአንፃሩ ደግሞሆሞሻ አካባቢ
አነስተኛ ዝናብ መጠን አለው፡፡ ይህም የሚያመለክተው የዝናብ
መጠን ጊዜ እና ከቦታ ቦታ የሚለያይ መሆኑን ያመለክታል፡፡

82 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

መልመጃ 3.1

ሀ/ ከዚህ በታች ያለውን ሠንጠረዥ መሠረት በማድረግ ቀጥለው ለቀረቡት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ፃፍ/ፊ

ሠንጠረዥ 1፡ የባምባስ አካባቢዓመታዊ ልከ ሙቀት /በዲግሪ ሴንቲ ግሬድ/ የ2010 ዓ.ም ነው፡፡

ወራት መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ስኔ ሐም ነሐ
አማካይ 28.1 28.5 28.7 30.9 30.6 32.1 33.4 32.2 30.7 27.3 25.9 26.5
ከፍተኛ
አማካይ 18.2 18.5 18 18.5 13.8 15.9 16 16.9 17.9 18 18.3 17.7
ዝቅተኛ
አማካይ 23.15 23.5 23.35 24.7 22.2 24 24.7 24.55 24.3 22.65 22.1 22.1
ዓመታዊ
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

1.ከፍተኛ አማካይ የሙቀት መጠን ያላቸውን ወራት ቢያንስ ሶስቱን ዘረዝር/ሪ/


2.ዝቅተኛ አማካይ የሙቀት መጠን ያለው ወር የትኛው ነው?
3.ዝቅተኛ አማካይ ዓመታዊ የሙቀት መጠን ያላቸውን ወራት ቢያንስ ሁለቱን ጻፍ/ፊ

83 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለ/ ከዚህ በታች ያለውን ሠንጠረዥ መሠረት በማድረግ ቀጥለው ለቀረቡት


ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ፃፍ/ፊ

ሠንጠረዝ 2፡ የባምባስአካባቢ ዓመታዊ የዝናብ መጠን /በሚሊሜትር/ የ2010 ዓ.ም


መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐ
220.5 90.1 5.2 0.0 0.0 4.2 47.4 14.2 216.6 191.6 248.7 256
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

1. በጣም ከፍተኛው የዝናብ መጠን ያለው የትኛው ወር ነው?


2. በጣም ዝቅተኛ የዝናብ መጠን ያላቸውን ሁለቱን ወራት
ስም ፃፍ/ፊ፡፡
3. ምንም የዝናብ መጠን ያልተመዘገበባቸው ወራትን ስም
ጥቀስ/ሽ፡፡

84 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሐ/ ከዚህ በታች ያለውን ሠንጠረዥ መሠረት በማድረግ ቀጥለው ለቀረቡት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ፃፍ/ፊ

ሠንጠረዥ 3፡ የወንበራ፣ አብረሃሞ እና ዳምቤ አካባቢዓመታዊ የዝናብ መጠን/በሚሊሜትር/ የ2005 ዓ.ም


ጣቢያ መስ ጥቅ ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐ ድምር
ወምበራ 188.0 49.0 12.0 0.0 0.0 0.0 0.0 0.0 85.0 87.0 189.0
163.0 773
አብረሃሞ 211.0 112.0 32.0 0.0 0.0 0.0 4.0 0.0 133.0 164.0 220.0 222.0
1098
ዳምቤ 0.0 0.0 0.0 0.0 240.8 305.0 305.5 234.9 215.0 191.3 0.0 0.0
1492.5
ምንጭ፡ የአሶሳ ሜትዎሮሎጂ ጣቢያ

1. ከፍተኛ የዝናብ መጠን ያለውየትኛው የሜትዎሮሎጂ ጣቢያነው?


2. መካከለኛ የዝናብ መጠን ያለውየትኛው የሜትዎሮሎጂ ጣቢያነው?
3. ዝቅተኛ የዝናብ መጠን ያለውየትኛው የሜትዎሮሎጂ ጣቢያነው?

85 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

3.1.5 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአየር ንብረት ክፍፍል


ተማሪዎች የአየር ንብረት ክፍፍል ከምን አኳያ እንደሆነ
አብራሩ፡፡

ዓለም አቀፍ የደን ምርምር ማዕከል-ሲፎር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ


ክልላዊ መንግስት ዘላቂ የቀርቀሃ አስተዳደር ዕቅድ መርሆዎች
በሚል ርዕስ በ2010 ዓ.ም ባደረገው ጥናት መሠረት የቤኒሻንጉል
ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት 50,380 ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት
ያለው ሲሆን፣ በሶስት ዞኖች ማለትም አሶሳ፣ ከማሽ እና መተከል፣
በ21 ወረዳዎች የተከፋፈለ ነው። አሶሳ የክልሉ ዋና ከተማ
ስትሆን ክልሉ ሶስት የአየር ንብረት ዞኖች አሉት።

 የመጀመሪያውና የክልሉን 75 ከመቶ የሚሸፍነው ከፍታው


ከ1,500 ሜትር ከባሕር ጠለል በላይ ያለው ክፍል ሲሆን፤
ይህ ዞን በአማካይ ከ400 ሚሊ ሜትር ያልበለጠ ዓመታዊ
የዝናብ መጠን ያገኛል።
 ሁለተኛው ክፍል ከ1,500 እስከ 2,500 ሜትር ከባሕር
ጠለል በላይ ከፍታ ያለው ሆኖ ከክልሉ 25 ከመቶ ድርሻ
አለው።
 ከክልሉ አንድ (1) ከመቶ ብቻ ድርሻ ያለው ሶስተኛው ዞን
ከ2,500 ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ያለው ሆኖ ተራራማና
ሜዳማ ቦታዎችን ያቀፈ ነው። በዚህ መሠረት አብዛኛው
የክልሉ አየር ንብረት ቆላማ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

86 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

3.1.6 የአየር ንብረት ቅጣይ ደንቢዎች


ተማሪዎች የአየር ንብረት እንዲለዋወጥ የሚያደርጉት ምክንያቶች
ምን ምን ናቸው?

አየር ጠባይ በየዕለቱ የሚከሰት ለውጥ ነው፡፡ የአየር ንብረት


ደግሞ ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ ይህም የሚሆነው በአየር ጠባይና
በአየር ንብረት አባላት መለዋወጥ ምክንያት ነው፡፡ ለዚህ የአየር
ጠባይና አየር ንብረት አባላት መለዋወጥ ምክንያት የሚሆኑት
የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የአንድ ቦታ ከምድር ወገብ የመራቅ እና የመቅረብ


 የአንድ ቦታ ከባህር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ
 የአንድ ቦታ ከባህር ያለው ርቀት
 የባህር ሞገድ
 የመሬቱ አቀማመጥ
ከላይ ከተጠቀሱት በአገራችንና በክልላችን በጣም ተጽዕኖ
የሚያሳድረው የአንድ ቦታ ከባህር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ
ነው፡፡

የአንድ ክልል የአየር ንብረት አንድ የተወሰነ የአከባቢ


ሁኔታንለመቅረጽ የሚሰሩ የሜትሮሎጅ ተለዋዋጮች ስብስብ
ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የአየር ንብረት ምክንያቶች እነዚህን
ባህሪዎች ለአንድ አካባቢ መስጠት እንዲቻል በተመሳሳይ ጊዜ
እርምጃ ይወስናል፡፡ የሚሰሩ ተለዋዋጮች በከባቢ አየር ደረጃ

87 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ብቻ የተገኙ ብቻ ሳይሆኑ በምድር ገጽ ከፍታ ላይ ያሉትን


ሁሉንም የከፍታ ደረጃዎች ይነካል፡፡

አየር ንብረትና ከፍታ

የአየር ንብረት ለውጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡


ከእነዚህ አንዱ ከፍታ ነው፡፡ አንድ ከፍታ ስፍራ ስንወጣ አየሩ
ይቀዘቅዛል፣ ወደ ዝቅተኛ ስፍራ ስንወርድ ግን አየሩ ይሞቃል፡፡

ስለዚህ ከፍተኛ ቦታዎች አነስተኛ ሙቀት ሲኖራቸው ዝቀተኛ


ቦታዎች ግን ከፍተኛ ሙቀት አላቸው፡፡

በክልላችን ከፍተኛ ስፍራዎች ቅዝቃዜ የሚጎላባቸውና ዝቅተኛ


ስፍራዎች ደግሞ ሙቃታማነት የሚከሰትባቸው ምክንያቱ ይኸው
ነው፡፡ስለዚህ በክልላችን ያሉት ከፍተኛ ቦታዎች ቀዝቃዛና
ዝናባማ ሲሆኑ፣ አብዛኞዎቹ ዝቅተኛ ስፍራዎች ግን ሞቃታማ እና
አልፎ አልፎ ደረቃማ ናቸው፡፡

መልመጃ 3.2

ሀ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጥ/ጭ

1. የዝናብ መጠን መለኪያ መሣሪያ ምን ይባላል?


ሀ/ ሙቀት ሜትር
ለ/ዊንድቬን
ሐ/ ሳንቲ ሜትር
መ/ዝናም ሜትር
2. ከሚከተሉት ዝቅተኛ የዝናብ መጠን ያለው ቦታ የቱ ነው?

88 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሀ/ኩርሙክ ለ/ወምበራ ሐ/አሶሳ መ/ ባንባሲ


3. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ ዝናብ የሚኖረው በምን
ወቅት ነው?
ሀ/ በክረምት ለ/ በበጋ ሐ/ በመከር መ/ በበልግ
4. አብዛኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አየር ንብረት ምን
ዓይነት ነው?
ሀ/ ደጋማ ለ/ ቆላማ ሐ/ በረሃማ መ/ ወይናደጋማ
5. ከሚከተሉት ውስጥ ለአየር ጠባይና የአየር ንብረት አባላት
መለዋወጥ ምክንያት የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የአንድ ቦታ ከባህር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ
ለ/የባህር ሞገድ
ሐ/ የአንድ ቦታ ከባህር ያለው ርቀት
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ፃፍ/ፊ

1. የአንድን ቦታ ዕለታዊ የአየር ሙቀት እንዴት ማወቅ እንችላለን?


2. የቀን ከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚኖረው ስንት ሰዓት ላይ ነው?
3.በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛና ዝቅተኛ የሙቀት መጠን
ያላቸው ቦታዎችን ዘርዝር/ሪ፡፡
4. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚኖረው
በምን ወቅት ነው?

89 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

3.2 የተፈጥሮ ሀብቶች


ተማሪዎች የተፈጥሮ ሀብቶች የምንላቸው ምን ምን ናቸው?
የተፈጥሮ ሀብቶች የምንላቸው ተፈጥሮ ለሰው ልጆች የለገሰቻቸው
ነገሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ተክሎች፣ እንስሳት፣ ውሃ፣ የፀሐይ ብርሃን፣
ንፋስ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
በተጨማሪ የተፈጥሮ ሀብቶች የሚባሉት በአካባቢያችን በተፈጥሮ
የሚገኙ ሰው ሰራሽ ያልሆኑ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፡፡ እነሱም አፈር፣
ውሃ፣ አየር፣ ደን ወይም እፅዋት፣ እንስሳት፣ አዕዋፋት፣ ጨው፣ ብረታ
ብረት፣ የነዳጅ ዘይት፣ የተፈጥሮ ጋዝናየመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡

3.2.1 የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶች

የተፈጥሮ ሀብቶች የሚታደሱና የማይታደሱ ተብለው በሁለት


ይከፈላሉ፡፡ የሚታደሱ የተፈጥሮ ሀብቶች የሚባሉት አፈር፣ እፅዋት፣
ውሃ፣ አየር እና የመሳሰሉት ሲሆኑ የማይታደሱ ደግሞ የድንጋይ
ከሰል፣ የነዳጅ ዘይት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ሀ. የሚታደሱ የተፈጥሮ ሀብቶች፡-

የሚታደሱ /የሚተኩ/ የተፈጥሮ ሀብት የምንላቸው ከተጠቀምናቸው


በኋላ እንደገና መተካት የምንችላቸው ናቸው፡፡

ለምሳሌ፡- ተክሎች፣ ውሃ፣ እንስሳት፣ አዝእርቶች፣ አየር እና አፈር


ናቸው፡፡

ለ. የማይታደሱ የተፈጥሮ ሃብቶች

90 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የማይታደሱ /የማይተኩ/ የተፈጥሮ ሀብቶች አንድ ጊዜ


ከተጠቀምንባቸው በኋላ መልሰን ልንተካቸው የማንችላቸው ሀብቶች
ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- የተፈጥሮ ድፍድፍ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ
ማዕድናት፣ ብረታ ብረቶች፣ ጨው፣ ወርቅ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ተግባር 3.2

ተማሪዎች ለሁለት ቡድን በመከፈል ከታደሽ እና ኢ-


ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብቶች የትኞቹ ብዙ እንክብካቤ
እንደሚያስፈልጋቸው ተከራከሩ፡፡

3.2.2 የተፈጥሮ ሀብት ጥቅም


የተፈጥሮ ሀብቶች ለሰው ልጆች ሁሉ እጅግ ጠቃሚ ነገሮች ሲሆኑ፣
ከነዚህም ጥቅሞች ጥቂቶችን ለመዘርዘር እንሞክራለን፡፡

1. ደኖች

ደን ማለት የዛፎች ስብስብ ነው፡፡ በድሮ ጊዜአብዛኛው የክልላችን


መሬት ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነ ነበር፡፡ አሁን ግን ደኖች በጣም
በመመናመናቸው የተነሳ ሸፋናቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡
ይህምሊሆን የቻለው ሰዎች ደኖችን በመመንጠራቸውና
በማቃጠላቸው ምክንያት ነው፡፡
የደን ጥቅም

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ከሚገኙ የደን ዓይነቶች አንዱ የቀርቀሃ ደን


ሲሆን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውሚና ከፍተኛ ነው፡፡

91 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የቀርቀሃ ደን አገሪቱ ለዓለም ገበያ ከምትልከው የደን ምርት ውስጥ


ያለው ድርሻ 0.02 በመቶ ብቻ ቢሆንም ለቤት ውስጥ በሚሰጠው
ግልጋሎትና በአገር ውስጥ ገበያ ባለው ድርሻ ሳቢያ በአገሪቱ
ብሔራዊ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

በኢትዮጵያ ከቀርቀሃ ገበያ የሚገኘው ዓመታዊ ገቢ ወደ 56


ሚሊዮን ብር የሚገመት ሲሆን፤ ሩብ ሚሊዮን ሕዝብም ኑሮውን
በቀርቀሃ ምርትና ግብይት ላይ እንደመሰረተ ይገመታል። ምንም
እንኳን በአሁኑ ጊዜ ያለው የቀርቀሃ ምርት ገበያ ውስን ቢሆንም፣
ዘርፉ በፌዴራልና በክልል ደረጃ ተገቢው የግብዓትና የፖሊሲ
ትኩረት ከተሰጠው ከፍተኛ እምቅ የኢኮኖሚ አቅም እንዳለው
ይታመናል።

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአሁኑ ጊዜ የቀርቀሃ ዘንግ ዋነኛ


የቀርቀሃ የገበያ ምርት ሲሆን፤ የቀርቀሃ ምንጣፍ (ሳጠራ)፣
ቅርጫትና የቤት ዕቃዎች ሌሎች ዋና ዋና የቀርቀሃ ምርቶች
ናቸው።

ሥዕል 3.4 ቀርከሃ ደን

92 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ተማሪዎች የደን ጥቅም ምንድነው? ተወያዩበት፡፡

ደን ለሀገራችን እና ለክልላችን እድገትና ልማት በጣም አስፈላጊ


ነው፡፡ ደን በተዘዋዋሪና በቀጥታ ብዙ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ከደን
የምናገኛቸው ጥቅሞች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የደን ሀብት በከሰል መልክ ወይም በማገዶ እንጨትነት ከፍተኛ


ጥቅም ይሰጣል፡፡
 ደኖች ለዱር እንስሳት ምግብና መጠለያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡
 የደን ሀብት ለልዩ ልዩ ነገሮች ወይም ቁሳቁሶች መስሪያ
ያገለግላል፡፡ ለምሳሌ፣ ለቤት መሥሪያ፣ ለድልድይ መስሪያ፣
ለጠረጴዛ፣ ለወንበር፣ ለወረቀት፣ ለቀለም፣ ለሙጫ፣ ለመድኃኒት
እና ለመሳሰሉት መሥሪያነት ያገለግላሉ፡፡
 ደን የአየር ሁኔታ ለሰው ተስማሚ እንዲሆን ይረዳል፡፡
 ደንየዱር እንስሳት መኖሪያ በመሆኑ ጎብኝዎችን (ቱሪስቶችን)
በመሳብ ገቢ ያስገኛል፡፡
 የተፈጥሮ የአየር ሚዛንን በመጠበቅ የአየር መዛባት እንዳይከሰት
ይረዳል፡፡

2. አፈር

አፈር የሚገኘው ከተሰባበረና ከደቀቀ አለት ወይም ቋጥኝ እና


ከሞቱ እፅዋትና እንስሳት ብስባሽ ነው፡፡

93 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የአፈር ጥቅም
አፈር በጣም ጠቃሚ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት ነው፡፡ ለሰው ልጅ እና
ለእንስሳት ምግብ የሚያገለግሉ እፅዋት የሚበቅሉትና የሚያድጉት
በአፈር ውስጥ ነው፡፡ ለእፅዋት ዕድገት የሚያስፈልጉ ብዙ ማዕድናት
የሚገኙትም በአፈር ውስጥ ነው፡፡ እንደዚሁም አፈርን ከጭድ ጋር
አቡክተን ለቤት መምረጊያ እና ጡብ በማዘጋጀት ለቤት መስሪያነት
እንጠቀምበታለን፡፡

3. ውሃ

አብዛኛው የዓለማችን ክፍል በውሃ ተሸፍኖ ይገኛል፡፡ 75%


የሚሆነው የመሬት ክፍል የተሸፈነው በውሃ ነው፡፡

ውሃ ለተክሎችም ሆነ ለእንስሳት ለመኖር ከሚያስፈልጉ ነገሮች


አንዱና ዋነኛውነው፡፡ በአካባቢያችን ለመጠጥም ሆነ ለሌሎች
ጥቅሞች የምናውለውን ውሃ የምናገኘው ከዝናብ፣ ከምንጭ፣ ከወንዝ፣
ከጉድጓድ ወይም ከቧንባ ነው፡፡

የውሃጥቅም

ውሃ ለሕይወት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በየቀኑ የምንጠጣው፣


ምግባችንን የምናዘጋጅበትና ንፅህናችንን የምንጠብቅበት አስፈላጊና
ዋና የተፈጥሮ ሀብት ውሃ ነው፡፡

የውሃ ተፈላጊነት ከፍተኛ የመሆኑን ያህል ለመጠጥና ለቤት


አገልግሎት የምናውለው ውሃ ንፅህና በደንብ የተጠበቀ ካልሆነ
በጤናችን ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

94 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ውሃ ለጤንነት ተስማሚ ነው ሊባል የሚችለው ለአይን ጠርቶ


በመታየቱ ብቻ ሳይሆን በሽታን በሚያመጡ ጥቃቅን ነፍሳት
/ተውሃስያን/ ያልተበከለና በውሃ የሚመጡ በሽታዎችን
የማያስተላልፍ ሲሆን ነው፡፡ ውሃ ለመጠጥና፣ ለቤት ውስጥ ሥራዎች
አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች አገልግሎቶች ጥቅም ይውላል፡፡
ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ለመስኖ እርሻ
2. ለኢንዱስትሪ

3. ለኤለክትሪክ ማመንጫ

4. ለመጓጓዥያ

5. ለዓሳ እርባታ እና ለመሳሰሉት ናቸው፡፡

4. የዱርእንስሳት

የዱር እንስሳት የሚባሉት በየብስ ላይ የሚኖሩትን፣ በውሃ ውስጥ


የሚዋኙትን፣ በዛፍ ላይ የሚንጠለጠሉትን፣ በአየር ላይ የሚበሩትን፣
በደረት የሚሳቡትን ሁሉ የሚያጠቃልል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሰው
አዘውትሮ በማይኖርበትና በማይዘዋወርበት በዱር አካባቢ የሚኖሩ
ናቸው፡፡

የዱር እንስሳት ከነሕይወት የሚወለዱትን፣ ከእንቁላል


የሚፈለፈሉትን ምግባቸው ሥጋና እፅዋት የሆኑትን የዱር እንስሳት
ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ክልላችን ውስጥ ብዙ ዓይነት የዱር እንስሳት
አሉ፡፡

95 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የዱር እንስሳት የምንላቸው ለምሳሌ እንደ አንበሳ፣ ነብር፣ ጅብ፣


ዝንጀሮ፣ አዞ፣ ጥርኝ፣ ዝሆን፣ አሳማ፣ ከርከሮ፣ ቀበሮና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡

ሥዕል 3.5 የዱር እንስሳት

የዱር እንስሳት ጥቅም

የዱር እንስሳት ብዙ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ


ያህል፡-

96 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 የዱር እንስሳት ቱሪስቶችን በመሳብ ለአገራችን የገቢ ምንጭ


ያስገኛሉ፡፡
 አንዳንድ የዱር እንስሳት ቆዳቸው ለጫማና ለቦርሳ መስሪያ፣
ጥርሳቸው ለጌጣጌጥ፣ሥጋቸውለምግብነት ያገለግላሉ፡፡
5. ማዕድን

ማዕድናት ሲባል በመሬት ውስጥተቀብረው የሚገኙ የተፈጥሮ


ሀብቶች ናቸው፡፡ ማዕድናትን ቆፍሮ በማውጣት ለልዩልዩ ጥቅሞች
ማዋል ይቻላል፡፡ ማዕድናት ከልዩልዩ ስፍራ በተለያየ መጠን
ስለሚገኙ የአመራረታቸውም ሁኔታ እንደዚሁ ከሥፍራ ሥፈራ
ይለያያል፡፡

የማዕድን ቁፋሮ በሀገራችን ብሎም በክልላችን ምጣኔ ሀብት እስከ


አሁን ድረስ አስተዋጽኦው በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ይህም ሊሆን
የቻለው የማዕድን ፍለጋና ቁፋሮ ከፍተኛ ገንዘብና የሰለጠነ የሰው
ኃይል ስለሚጠይቅ ነው፡፡

የማዕድን ዓይነቶች

ተማሪዎች በአካባቢያችሁ የሚገኙ ማዕድናት ካሉ ዘርዝሩ፡፡

የማዕድን ዓይነቶች በርካታ ናቸው፡፡ የማዕድን ዓይነቶች የሚባሉት


ብረታብረት፣ ወርቅ፣ ብር፣ እርሳስ፣ የተፈጥሮ ዘይት፣ የድንጋይ
ከሰል፣ የኖራ ድንጋይ፣ እምነበረድ፣ ድንጋይ እና ሌሎችም በርካታ
ማዕድናት ሰው ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው ማዕድናት
ናቸው፡፡

97 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 3.6 የወርቅ ማዕድን

የማዕድን ጥቅም

ማዕድን ለሰው ልጅ ብዙ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ዋና ዋና የማዕድን


ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 ማዕድናት ለእንዱስተሪ ጥሬ ዕቃነት ያገለግላሉ፡፡ ለምሳሌ


ብረትና መዳብ የተለያዩ ዕቃዎችን ለማምረት ያገለግላሉ
 ማዕድናት ኃይል ለማመንጨት ያገለግላሉ፡፡ ለምሳሌ የተፈጥሮ
ዘይት፣ የተፈጥሮ ጋዝና የድንጋይ ከሰል
 ማዳበሪያ ለማምረት ጥሬ ዕቃ በመሆን ያገለግላሉ፡፡ ለምሳሌ
ፖታሽ፣ ሰልፈርና ናይትሬት
 ለግንባታ አገልግሎት ይውላሉ፡፡ ለምሳሌ የኖራ ድንጋይ፣
እምነበረድ፣ ሸክላ አፈርና ድንጋይ
 የተለያዩ ጌጣጌጦችን ለመስራት ያገለግላሉ፡፡ ለምሳሌ ወርቅ፣
ብር፣ አልማዝ

98 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ከላይ ከተዘረዘሩት ማዕድናት በክላችን መገኘታቸው ተረጋግጦ ሥራ


ላይ እየዋሉ ያሉት የሚገኙባቸው ዞኖችና ወረዳዎች እንደሚከተለው
ይሆናል፡፡
ወርቅ-በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ፣ ኩርሙክ እና ሆሞሻ ወረዳዎች፣
በመተከል ዞን ጉባና ቡለን፣ በካማሽ ዞን በካማሽ፣ ዳምቤና ሰዳል
ወረዳዎች ይገኛል፡፡
የድንጋይ ከሰል- በካማሽ ዞን /በምዥጋና ካማሽ ወረዳዎች፤
እምነበረድ- በካማሽ ዞን/ ሰዳል ወረዳ፣ መተካል ዞን በቡለን እና ጉባ
ወረዳዎች ይገኛል፡፡
3.2.3 ለተፈጥሮ ሀብት መራቆት መንስኤዎች እና
የሚያስከተሏቸው ጉዳቶች

ለተፈጥሮ ሀብት መራቆት የተለያዩ መንስኤዎችና ምክንያቶች


አሉ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በክልላችን ለሚገኙት የተፈጥሮ ሀብቶች
መመናመን መንስኤዎችና ያስከተሉትን ጉዳቶች እንመለከታለን፡፡

መንስኤዎች

ለተፈጥሮ ሀብቶች መራቆት ዋና መንስኤዎች በሁለት ይከፈላሉ፡፡


እነሱም ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ናቸው፡፡

ሰው ሰራሽ ምክንያቶች

ሰው ኑሮውን ለማሸነፍ በሚያደርጋችው የእለት ተዕለት


እንቅሰቃሴዎች የሚከሰቱ ናቸው፡፡ እነሱም፡-

 የደን መመንጠር

99 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 ህገወጥ የማዕድን ቁፋሮ


 ህገ-ወጥ አደን
 የከተሞች መስፋፋት
 ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች መስፋፋት
 የህዝብ ቁጥር መጨመር
 ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት መጨመር
ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች
 የሰደድ እሳት
 አውሎ ንፋስ
 የእሳት ገሞራ ፍንዳታ
ከላይ የተዘረዘሩት ለተፈጥሮ ሀብት መመናመን ምክንያቶች
የሚያስከትሉት ጉዳቶች፡-
 የውሃ እና የአየር መበከል
 አሲዳማ ዝናብ
 የአፈር መሸርሸር
 የዱር እንስሳት መጠለያ ማጣት
 የዱር እንስሳት መሰደድ
 የምርት መቀነስ የመሳሰሉት ዋናዋና ችግሮች ይከሰታሉ፡፡
3.2.4 የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ

የደን እንክብካቤ

ዛፎች እጅግ አስፈላጊ ሲሆኑ ብቻ በሚፈለገው መጠን በመቁረጥ


በምትካቸው ችግኞችን እየተከሉ መጠናቸው እንዲጨምር አድርጐ

100 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

መጠቀሙ የደን እንክብካቤ ይባላል፡፡ ደንን ለመንከባከብ ከሚረዱት


መንገዶች ውስጥ ጥቂቶቹ፡-

 ችግኞችን መትከል፣
 አስፈላጊ ሆነው በተቆረጡ ዛፎች ምትክ ችግኞችን መትከል፡፡
 ችግኞችን ከአገልግሎታቸው አንፃር መትከል፣ ለምሳሌ
ለፍራፍሬ፣ ለመዝናኛ፣ ለእርሻ ማዳበሪያ፣ ለጌጣጌጥ፣ ለወረቀት
መሥሪያ፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለጐማ፣ ለማገዶ፣ ለቤት
መሥሪያና ለመሳሰሉት ስለሚጠቅሙ ለአካባቢው ከሚሰጡት
ጥቅም አንፃር መትከል፡፡
 የሰደድ እሳት እንዳይከሰት ቁጥጥር ማድረግና ከተከሰተም
በመረባረብ ወዲያውኑ ማጥፋት፣
 ለእርሻና ለግጦሽ በማይሆኑ መሬቶች ላይ ችግኞችን
በመትከል በደን እንዲሸፈኑ ማድረግና የመሳሰሉትናቸው፡፡
አፈር እንዳይሸረሸር መከላከያ መንገዶች
ተማሪዎች የአፈር መሸርሸር ምክንያቶች የምትሏቸውን ዘርዝሩ፡፡
አፈርን መንከባከብ ከቻልን በአካባቢችን ያሉትን የተፈጥሮ
ሀብቶቻችንን ሁሉ ተንከባከብን ማለት ነው፡፡ አፈርን ካልጠበቅነውና
ካልተንከባከብነው እፅዋት መብቀልና ማደግ ስለማይችሉ ሰው እና
እንስሳት በሕይወት ለመኖር አይችሉም፤ አካባቢያችንም ምድረበዳ
ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አፈር በተለያዩ ነገሮች እንዳይሸረሸርና
ለምነቱን እንዳያጣ ተንከባክበንና ጠብቀን መያዝ አለብን፡፡

101 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

አፈር እንዳይሸረሸርና ለምነቱን እንዳያጣ የሚከተሉት ዘዴዎች


በመጠቀም መከላከል ወይም መንከባከብ ይቻላል፡፡

ሀ/ መሬቱን በእፅዋት (በዛፍ) መሸፈን


ለ/ ከእንስሳት መብዛት የተነሳ የሚፈጠረውን የሳር መራቆት መቀነስ
ሐ/ እርከን መስራት፡- ተራራማ አካባቢዎች ላይ አፈር በጎርፍ
ታጥቦ እንዳይሄድ እርከኖችን በመስራት መከላከል ይቻላል፡፡
መ/ በመግቻ ማረስ፡- የእርሻ መሬትን ሙሉ በሙሉ ማረስ የአፈር
መሸርሸርን ለመከላከል ስለማያስችል በየተወሰነ ርቀት ላይ በሳር
የሚሸፈኑና የማይታረሱ ቦታዎችን መተው ያስፈልጋል፡፡

የተራቆተ መሬት በእፅዋት መሸፈንተዳፋት ቦታዎችን እርክን መስራት

ሥዕል 3.7 አፈር እንዳይሸረሸር መከላከያ ዘዴዎች

102 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ውሃን ከብክለት መከላከል

የውሃ ብክለት ማለት ምን ማለት ነው?

ተማሪዎች ውሃ እንዴት ይበከላል? ብክለቱን እንዴት መከላከል


ይቻላል? እንድሁም የውሃ ብክለት የሚያስከትለውን ችግር በቡድን
በመወያየት ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡

የውሃ ብክለትን መከላከል በውሃ ንፅህና ጉድለት ከሚመጡ


በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመጠጥም ሆነ
ለሌሎች የቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውል ውሃ የምናገኘው
ከዝናብ፣ ከምንጭ፣ ከወራጅ ወንዝ፣ ከጉድጓድ ወይም ከኩሬ እና
ከመሳሰሉት ነው፡፡ እነዚህ የውሃ መገኛዎች በጥንቃቄና በአግባቡ
ስለማይያዙ ለጤና ጠንቅ በሆኑ ነፍሳቶች /ተውሃሲያን/ ይበከላሉ፡፡

ውሃ በአይን ሲያዩት የጠራ ስለሚመስል ሁሉም ስፍራ የምናገኘው


ውሃ ንፁህ ነው ማለት አይቻልም፡፡

ውሃ የሚበከልባቸው ዋና ዋናምክንያቶች፡-
1. በየሜዳው መፀዳደት
2. ከፋብሪካ በሚወጡ መርዛማ ኬሚካሎች
3. ከከተሞችና ከመኖሪያ ቤቶች በሚፈሱ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች
ሊበከልይችላል፡፡

103 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 3.8 ውሃ በሰው ዓይነ-ምድር ሲበከል

የዱር እንስሳት እንክብካቤዎች

የዱር አንስሳት ከፍተኛ ጥቅም ስለሚሰጡ በእንክብካቤ


መያዝያለባቸው የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ናቸው፡፡

ለዱር እንስሳት መደረግ ያለበት እንክብካቤ

 በሚኖሩበት አካባቢ አስተማማኝ የሆነ ምግብ፣ውሃና መጠለያ


እንድያገኙ ደኖች እንዳይጨፈጨፉ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
 የዱር እንስሳት የተጠለሉበትን አካባቢ ሰዎች ያለአጋባብ
እንዳያጠፉ መጠበቅ /መከለል፡፡
 ማንም ሰው ያለፍቃድ እንደፈለገ እያደነ እንዳይገድላቸው እና
ጥበቃ እንድያደርግላቸው ማስተማር፡፡

104 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 የዱር እንስሳትን በሕገወጥ መንገድ ማደንና መግደል የሀገር


የተፈጥሮ ሀብት ፀር ከመሆኑ ባሻገር የሀገር ኢኮኖሚን
ስለሚጎዳ በሕግ መከልከል፡፡
 የዱር እንስሳትን ለመንከባከብ እንዲያስችል ሁኔታዎች
በሚፈቅዱበት አካባቢ የዱር እንስሳትን በፓርኮች ውስጥ
በማድረግ መንከባከብ ይኖርብናል፡፡

ሥዕል 3.9 በህገ ወጥ መንገድ አደን ማካሄድ ለዱር እንስሳት መመናመን ምክንያት ነው፡፡

3.3 የቆሻሻ አወጋገድ


3.3.1 አግባብነት የሌለው የቆሻሻ አወጋገድ
ተማሪዎች በአካባቢያችሁ ቆሻሻን የምታሰወግዱበትን መንገድ
ዘርዝሩ፡፡

105 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

በአካባቢያችን መጥፎ የቆሻሻ አወጋገድ የምንላቸው አካባቢያችንን


ወይም ሰፈራችንን ሊጎዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ
ዋናዋናዎቹ፡-

1. ከቤት ውስጥ የሚወጡ ደረቅ ቆሻሻዎችን አላስፈላጊ ቦታበየ


ሜዳና መንገዶች ላይ መጣል፡፡ ለምሳሌ፡- ተረፈ ምግቦች፣
ፕላስትኮች፣ ብረታብረቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልጣጭ የተሰባበሩ
ጠርሙሶች፣ ብርጭቆዎች፣ የሸክላ ዕቃዎች፣ አሮጌ የቤት ዕቃዎች፣
አመድ፣ አጥንት፣ የፀረ ተባይ መድኃኒት ዕቃዎች፣ ወዘተ ናቸው፡፡

2. ከቤት ውስጥ የሚወጡ ፈሳሽ ቆሻሻዎችን አላስፈላጊ ቦታ


መድፋት፡፡ ለምሳሌ፡-የቤት ዕቃ እጣቢዎች፣ አተላ፣ አምቡላ እና
የመሳሰሉት ናቸው፡፡

3. የሰዎች ዓይነ-ምድር እና ሽንት በሜዳ ላይ መፀዳዳት


4. ከእንስሳት የሚወጡ ቆሻሻዎችን በየሜዳው መጣል፡፡ ለምሳሌ፡-
የከብቶች እበት፣ የፍየሎችና የበጐች ኮረኮር፣ የዶሮ ኩስ እና
የመሳሰሉት ናቸው፡፡

3.3.2 ተገቢነት ያለው የቆሻሻ አወጋገድ ተግባራት


ትክክለኛ የቆሻሻ አወጋገድ የምንላቸው ለሰው ልጆች ጤናና
ለአካባቢው ውበት/ንጽህና/ አስፈላጊ የሆኑ ናቸው፡፡ ሰዎች
ቆሻሻዎችን ደረቅና ፈሳሽ መሆናቸውን በመለየት ማስወገድ
አለባቸው፡፡ በአካባቢያችን ትክክለኛ የቆሻሻ አወጋገድ ዘዴ
የምንላቸው የሚከተሉት ናቸው፡-

106 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 ለደረቅ ቆሻሻዎች ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ቆፍሮ ማዘጋጀትና


ከቤት የሚወጡ ደረቅ ቆሻሻዎችን በተዘጋጀው ጉድጓድ
መጣልና ማቃጠል፡፡
 ለፈሳሽ ቆሻሻዎች ማስወገጃ ቦታ ማዘጋጀት እና በተዘጋጀው
ቦታ መድፋት
 ለሰዎች ሽንትና ዓይነ-ምድር ቆሻሻ ማስወገጃ የሽንት ቤት
ማዘጋጀትና በአግባቡ መጠቀም፡፡
 ከእንስሳት የሚወጡ ቆሻሻዎችን በአግባቡ በማጠራቀም
ለመሬት ማዳበሪያነት፣ ለኃይል ምንጭነት መጠቀም፡፡

3.3.3 የአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ

ተማሪዎች አካባቢያችንን የሚያቆሽሹ ነገሮች ምን ምን ናቸው?


አካባቢያችንን የሚያቆሽሹ ነገሮች ደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻዎች
ናቸው፡፡ እንዲሁም የሰው ዓይነ ምድር እና ከፋብሪካ የሚወጡ
መርዛማ ኬሚካሎች አካባቢን ይበክላሉ፡፡

ተግባር 3.3
በአካባቢያችሁ ያሉትን ደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን ዓይነት
በቡድን ተወያይታችሁ ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡

ደረቅ ቆሻሻ የምንለው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ከመኖሪያም ወይም


ከመስሪያ ቦታዎች እየተጠረጉ የሚጣሉ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-

 የአትክልትና ፍራፍሬ ልጣጭ

107 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 የተሰባበሩ ጠርሙሶች
 የተሰባበሩ የሸክላ ዕቃዎች
 የከብቶች እበት
 ፋንዲያ
 አመድ፣
 አሮጌ የቤት ዕቃዎችና አጥንት የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ሥዕል 3.10 የደረቅ ቆሻሻ ክምችት

ደረቅ ቆሻሻ በትክክለኛ መንገድ ካልተወገደ በሽታ አስተላላፊ


ለሆኑት አይጥ፣ ዝንብ፣ ትንኝ እና ለመሳሰሉት ነፍሳት መራቢያ እና
መደበቂያ ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ደረቅ ቆሻሻን ከመኖሪያ
ቤቶች እና ከመስሪያ ክልል ራቅ አድርጎ ማቃጠል ወይም መቅበር
ያስፈልጋል፡፡

ፈሳሽ ቆሻሻዎች የሚባሉት ደግሞ ከመኖሪያ ቤት ወይም ከመስሪያ


ቤት የሚወጡ ፈሳሽ የሆኑ ቆሻሻዎች ናቸው፡፡ ለመጠጥና ለምግብ
መስሪያ ውሃ የምናገኝምባቸው በአካባቢያችን የሚገኙ ምንጮችና

108 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የጉድጓድ ውሃዎች በዝናብ ጎርፍ፣ ከፋብሪካ በወጡ ፍሳሾች፣ በሰው


ዓይነ-ምድር፣ ከእንስሳት በሚወጡ ቆሻሻዎች ስለሚበከሉ
አስፈላጊውን ጥንቃቄና ጥበቃ ልናደርግላቸው ይገባናል፡፡

3.3.4 በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ጉድለት የሚከሰቱ በሽታዎች

የግል ንፅህናችንን ባለመጠበቅና ባለመጠንቀቅ በተለያዩ በሽታዎች


በቀላሉ ልንያዝና ልንጠቃ እንችላለን፡፡ በግልና በአካባቢ ንፅህና
ጉድለት የሚመጡ ዋና ዋና በሽታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. የውሃ ወለድ በሽታዎች

የውሃ ወለድ በሸታዎች የሚባሉት በተበከለ ውሃ አማካይነት


የሚመጡ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- አሜባ፣ ጃርዲያ፣ ኮሌራ፣ ታይፎይድ፣
ወስፋት፣ አጣዳፊ ተቅማጥ፣ የሆድ ትላትል በሽታዎች እና
የመሳሰሉት ንፅህናው ያልተጠበቀ ውሃ በመጠጣት የሚከሰቱ የውሃ
ወለድ በሽታዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ተግባር 3.4

በአካባቢያችን የረጋ ውሃ መኖር ምን ዓይነት የጤና


ችግር እንደሚያመጣ በቡድን ተወያዩና ለመምህራችሁ
ተናገሩ፡፡

109 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለ. የአየር ወለድ በሸታዎች


የአየር ወለድ በሽታዎች በአየር መበከልበአየር ከሰው ወደ ሰው
የሚተላለፉ በሸታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ እንደ ጉንፋን፣
ኢንፍሎዌንዛ፣ የሳንባ በሽታ የመሳሰሉት በሽታዎች በግልና በአካባቢ
ንፅህና ጉድለት የሚከሰቱ የአየር ወለድ የበሽታ ዓይነቶች ናቸው፡፡

ተግባር 3.5
በአካባቢያችሁ የሚከሰቱ የአየር ወለድ በሽታዎችን
ዘርዝሩ፡፡

3.3.5 የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ ጠቀሜታ

የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ ምን ጠቀሜታ አለው?


የቤታችሁን ንጽህና መጠበቅ ምን ጥቅም ይሰጣችኋል?
የአካባቢያችን እና የቤታችንን ንጽህና መጠበቅ ብዙ ፋይዳዎች
አሉት፡፡ ከነዚህም ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ሰውነታችን ጤናማ ይሆናል፡፡
2.አካባቢያችን ውብና ማራኪ ይሆናል፡፡
3.ንጹህ አየር እንድንተነፍስ ይረዳናል፡፡

110 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 3.11 ሰዎች ቆሻሻን ሲያፀዱ

የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች


ሀ/ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ
ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ ፡፡
1. ጠዋት መቀዝቀዝ፣ ቀን ደግሞ መሞቅ የአየር ንብረት ይባላል ፡፡
2. የሙቀት መጠን መለኪያ ሙቀት ሜትር ይባላል ፡፡
3. የዝናብ መጠን መለኪያ የለውም ፡፡
4. የአየር ንብረትና የአየር ሁኔታ የተለያዩ ናቸው፡፡
ለ/ ከሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል
ምረጡ
1. የተፈጥሮ ሀብት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ደን
ለ/ የዱር እንስሳት
ሐ/ ፋብሪካዎች
መ/ማዕድናት
2. የአፈር ጥቅም የሆነው የቱ ነው?

111 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሀ/ ለእርሻ ስራ
ለ/ለሸክላ ስራ
ሐ/ ለመስኖ ስራ
መ/ሁሉም
3. ለተፈጥሮ ሀብት መራቆት መንስኤ የሆነው የቱ ነው?
ሀ/የደኖች መመንጠር ለ/ህገ ወጥ አደን
ሐ/የሰደድ እሳት መ/ሁሉም መልስ ናቸው
4. ከሚከተሉት አንዱ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴ ነው
ሀ/እጽዋት መትከል
ለ/የዱር እንስሳት መኖሪያ መከለል
ሐ/የሰደድ እሳትን መከላከል
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
5. የአከባቢ ንፅህና አጠባበቅ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ መፀዳጃ ቤት ማዘጋጀት
ለ/ የፈሳሸ ቆሻሻን ማስወገጃ ማዘጋጀት
ሐ/ተረፈ ምርቶች ከግቢ ውጭ መድፋት
መ/ደረቅ ቆሻሻዎች ማቃጠል
6. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ በንፅህና ጉድለት የሚከሰት በሽታ
ነው?
ሀ/የእግር ስብራት ለ/ አሜባ
ሐ/ ኤች.አይ. ቪ ኤድስ መ/ጨብጥ
7. የአካባቢ ንጽህና መጠበቅ ጠቀሜታው ምንድነው?
ሀ/ሰውነታችን ጤናማ እንድሆን ይረዳናል፡፡

112 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለ/አካባቢያችን ውብና ማራኪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡


ሐ/ንጹህ አየር እንድንተነፍስ ይረዳናል፡፡
መ/ሁሉም መልስ ናቸው፡፡
8. ከሚከተሉት ውስጥ የማይታደስ የተፈጥሮ ሀብት የሆነው
የትኛው ነው?
ሀ/አፈርለ/የድንጋይ ከሰል ሐ/ ደንመ/ እንስሳት
ሐ/ ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ፃፍ/ፊ
1. በአየር ንብረትና በአየር ሁኔታ ላይ ተፅኖ የሚያስከትሉ ነገሮች
ምንድን ናቸው?
2.የአየር ንብረት አባላት የሚባሉትን ጥቀስ/ሽ:
3. በክልላችን የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን ዘርዝር/ሪ፡፡

113 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ምዕራፍ አራት
4.ማህበራዊ አካባቢያችን
4.1 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ባህሎች

4.1.1 የባህል ምንነት


ተማሪዎች ባህል ማለት ምንማለት ነው?
ባህል በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በሃዘን፣ በደስታ፣ በስራ ወዘተ
በሚደረገው የእርስበርስ ግንኙነት የሚፈጠር መስተጋብራዊ ክስተት
ነው፡፡ ባህል ተከታታይ በሆነ የማህበረሰብ መስተጋብር
እንደሚፈጠር ሁሉ የሚያድገውም ተከታታይ በሆነ የማህበረሰብ
እንቅስቃሴ ነው፡፡

ባህል የአንድ የተወሰነ ማህበረሰብ ወይም ብሔረሰብ መለያ ነው፡፡


ባህል በረጅም ጊዜ እንቅስቃሴ የሚያድግ እና የሚዳብር ስለሆነ
የማህበረሰብ ቅርስ በመሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ
ነው፡፡

ተግባር 4.1

ተማሪዎች በአካባቢያችሁ ከሚከወኑ ባህሎች መካከል


የተወሰኑትን አብራሩ፡፡

ባህል እጅግ ሰፊ ፅንሰ ሃሳብ ያዘሉ ነገሮችን የሚዳስስ መሆኑ


ይታወቃል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡ እነሱም፡-

1. ታሪክ፣ ሃይማኖት እና አስተሳሰብ


2. የማምረቻ፣ የቤትና የቤት ቁሳቁስ አሰራር ዘዴዎች

114 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

3. የምግብ አዘገጃጀት
4. አለባበስ
5. የሃዘን እና የደስታ መግለጫዎች
6. የበዓላት አከባበር፣
7. የተለያዩ ጨዋታዎች፣
8. ዘፈኖች እና ሌሎችንም ያጠቃልላል፡፡

ባህል በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ይከፈላል፡፡ እነሱም

1. ቁሳዊ ባህል እና
2. መንፈሳዊ ባህል ይባላሉ፡፡

4.1.2 ቁሳዊ ባህል


ቁሳዊ ባህል ማለት ምን ማለት ነው?
ቁሳዊ ባህል ማለት የሚታዩ፣ የሚዳሰሱ፣ ግዝፈት ያላቸው እና ቦታ
የሚይዙ ናቸው፡፡ ቁሳዊ ባህሎች የምንላቸው እንደ ከበሮ፣ ክራር፣
የሃይማኖት አልባሳት፣ የእምነት ቦታዎች፣ አመራረት፣ አለባበስ፣
የአኗኗር ዘይቤ፣ አመጋገብ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ቁሳዊ ባህሎች መንፈሳዊ ባህሎቻችንን ተግባራዊ የምናደርግባቸው


መሳሪያዎች ሲሆኑ ከነዚህም ከበሮ፣ ክራር፣ የሃይማኖት አልባሳት፣
የእምነት ቦታዎች፣ ወዘተ ያጠቃልላሉ፡፡

አመራረት

አመራረት ከቁሳዊ ባህሎች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የክልሉ


ህብረተሰብ ለማምረቻነት የሚጠቀሙባቸውን ባህላዊ የእርሻ

115 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

መሳሪያዎችን እንደ ትባ፣ ጋውድ፣ ማረሻ፣ሞፈር፣ቀንበር፣ወገል፣


መርገጫ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡

አለባበስ

ተማሪዎች በአካባቢያችሁ ያሉ የአለባበስ አይነቶችን አብራሩ፡፡

አለባበስ የአንድ ማህበረሰብ መለያ ምልክት ነው፡፡ አለባበስን


የሚወስነው የአየር ንብረት ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ በክልሉ ያሉ
ብሔረሰቦች በተለያዩ ዞኖች የተለያዩ ዓይነት አለባበስ አላቸው፡፡

ሥዕል 4.1የክልሉ ብሔረሰቦች አለባበስ

116 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

አመጋገብ

አመጋገብ የአንድ ማህበረሰብ መለያ ምልክት ነው፡፡ ይህም ሲባል


የአንድ ብሔረሰብ አመጋገብ የዚያን ብሔረሰብ የማንነቱ መገለጫው
ነው፡፡ ባህላዊ ምግብ ማለት በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች
አዘውትረው የሚጠቀሙት የምግብ ዓይነትና የዚያ ማህበረሰብ
ማንነት መገለጫ ነው፡፡ ባህላዊ ምግብ የሚዘጋጀው እዚያው
በአካባቢያቸው ባለው ሀብት ወይም ግብዓት ነው፡፡ በክልላችን
የሚኖሩ ብሔረሰቦች የተለያዬ ባህላዊ አመጋገብ አላቸው፡፡ ለምሳሌ
በክልላችን ከሚኖሩ ብሔረሰቦች መካከል የጉሙዝ፣ የቤኒሻንጉል፣
የሽናሻ፣ የማኦና ኮሞን ከዚህ በታች ካለው ሠንጠረዥ ማየት
ይቻላል፡፡
ሠንጠረዥ 4.1 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ ብሔረሰቦች ዋና ዋና ባህላዊ የምግብ
ዓይነቶች

ብሔረሰብ የምግብ ዓይነት


ቤኒሻንጉል ገንፎ፣ የቄንቄስ ወጥ፣ የቁንጹ ወጥ
ሽናሻ ጭንቦ፣ ማጢማሮ፣ ቦርዴ
ጉሙዝ ገንፎ፣ ቦርዴ፣ ካማ፣ ላላቃ
ማኦ ገንፎ፣ ማር
ኮሞ ገንፎ

4.1.3. መንፈሳዊ ባህል

መንፈሳዊ ባህል ስንል የማይዳሰሱ እና የማይጨበጡ ሲሆኑ


በድርጊት እና በትውፊት መልክ ከትውልድ ወደ ትውልድ

117 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የሚተላለፉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የግጭት አፈታት ዘዴ፣ የጋብቻ


ሁኔታ፣ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ የሃዘን መግለጫዎች፣ የተስካርሰነ-
ሰርዓት፣ የበዓላት አከባበር ወዘተ ናቸው፡፡

ሥዕል 4.2 የክልሉ ብሔረሰቦች ባህላዊ ጭፈራ

የግጭት አፈታት ዘዴ
ግጭት ምንድነው?

ግጭት ማለትበሁለት እና ከዛ በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል ሊከሰት


የሚችል ያለመግባባት ሂደት ነው፡፡ ይህም አለመግባባት በግለሰቦች፣
በቡድኖች፣ በጎሳዎች፣ በብሔሮች፣ በክልሎች እና በሀገራት መካከል

118 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ወይም በፖለቲካዊ ጉዳዮች የተነሳ ሊፈጠር


የሚችል አለመግባባት ነው፡፡

የግጭት አፈታት ዘዴ ባህላዊ የፍትህ ስርዓት ሲሆን ግጭቶቹ


የሚፈቱት ባለጉዳዮቹ ተቀራርበው እንዲወያዩ እና እንዲደራደሩ
በማድረግ ነው፡፡ ግጭቱን የሚፈቱት የሀገር ሽማግሌዎች በሚመሩት
በራሳቸው ማህበረሰብ ዘንድ ከበሬታ፣ ተቀባይነት ያላቸው እና
በማህበረሰቡ የሚመረጡ ናቸው፡፡ በመሆኑም በፍትህ ሂደቱ
የማህበረሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ሲሆን በአብዛኛው የገጠሩ ማህበረሰብ
ዘንድ ተቀባይነት አለው፡፡

በክልላችን የሚኖሩ ብሔረሰቦች የማኦ ብሔረሰብ፣ የቤኒሻንጉል


ብሔረሰብ፣ የጉሙዝ ብሔረሰብ፣ ሽናሻ ብሔረሰብ፣ የኦሮሞ
ብሔረሰብ፣ የአማራ ብሔረሰብ እና የመሳሰሉት የየራሳችው የሆነ
የግጭት አፈታት ዘዴ አላቸው፡፡ ይህ የግጭት አፈታት ዘዴዎች
ከዚህ በታች በሠንጠረዥ 4.2 ቀርበዋል፡፡

119 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ 4.2 የክልላችን ብሔረሰቦች የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎች

የብሔረሰብ የግጭቱ መንስኤዎች የግጭት አፈታት ዘዴ


ስም

ማኦ በድንበር፣ ስርቆት፣ የሰው በአካባቢ ሽማግሌዎች እርቅ


ምስት መድፈር፣ ግዲያ፣ በማድረግ
ጠለፋ፣ በስራቦታ እና
የመሳሰሉት

ቤኒሻንጉል ስርቆት፣ ጠለፋ፣ አካባቢ ሽማግሌዎች ወይም አሽህ


አካልማጉደል፣ ግዲያ (አልቃሪያ) እርቅ ማድረግ
የመሳሰሉት

ጉሙዝ በድንበር፣ በስርቆት፣ ጠለፋ፣ የአካባቢ ሽማግሌዎች ማለትም


ግዲያ እና የመሳሰሉት ወንዶች እና ሴቶች ናቸው

ሽናሻ በድንበር፣ በስርቆት፣ ጠለፋ፣ የአካባቢሽማግሌዎች ሲሆኑ ሦስት


ግዲያ እና የመሳሰሉት ደረጃች (ቡራ፣ ኔማ እና ፄራ)
አላቸው

ተግባር 4.2

በክልላችን ከሚገኙት ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ውስጥ


የምታውቁትን መርጣቹ ለክፍል ጓደኞቻችሁ አብራሩ፡፡

ባህላዊ የግጭት አፈታት ጠንካራ ጎኖች

1. የመደበኛ ፍርድቤቶችን ጫና ይቀንሳል፡፡

120 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

2. የበለጠ ተደራሽ እና አሳታፊ ነው፡፡


3. በአካባቢው ቋንቋ ስለሚዳኙ ቋንቋውን ባለመቻል ምክንያት
የሚፈጠረውነን ያለመግባት ችግር ያስወግዳል፡፡
4. ጊዜ ቆጣቢ ነው፡፡
5. ፍትሃዊ ፣ ወጭቆጣቢ ነው፡፡
6. የብሔረሰቡ ማንነት መገለጫ ስርዓት ነው፡፡

ባህላዊ የግጭት አፈታት ክፍተቶች

1. ሴቶችን እና ወጣቶችን አሳታፊ አለማድረጋቸው፡፡


2. መደበኛ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ተፈፃሚ እንዳይሆን
ማድረግ ፡፡
3. የሚወሰኑ ቅጣቶች ከግጭቱ ጋር የማይጣጣሙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ጋብቻ

ጋብቻ ማለት ለአቅመ አዳም እና ለአቅመሄዋን የደረሱ ሁለት


ተቃራኒ ፆታዎች የሚጣመሩበት ሂደት ነው፡፡ የሚጣመሩት
ፆታዎች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው የራሳቸውን ኑሮ የሚመሰርቱበት
ስርዓት ነው፡፡ የራሱን ባህል ይዘት ጠብቀው በመከወን ዘመን
ከተሻገሩት ልዩ ልዩ ባህላዊ እሴቶች መካከል አንዱ ባህላዊ የጋብቻ
አፈፃጸም ስነ ስርአት ነው፡፡

121 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ጠቃሚ ባህሎች እና ጐጂ ልማዳዊድርጊቶች

ባህሎች ከሚሰጡት ጠቀሜታ እና ከሚያስከትሉት ጉዳት አንፃር


በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡- ጠቃሚ ባህሎች እና ጐጂ ባህሎች
ተብለው ይከፈላሉ፡፡

ጠቃሚ ባህሎች

ጠቃሚ ባህል የምንላቸው የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት በሚያደርጓቸው


ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የፈጠራቸው እና
ያዳበራቸው እንዲሁም ጠቃሜታ ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ባህሎች
ለቀጣዩ ትውልድም ሊተላለፉ የሚገቡናቸው፡፡ ለምሳሌ፡-

 ስራን መውደድ
 መከባበር
 መቻቻል
 የሀገር ፍቅር ስሜት
 ጀግንነት
 የጋራ ሀብትን መንከባከብ
 በሃዘንና በደስታ ተካፋይ መሆን
 መረዳዳት
 የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ እና
 ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲወገዱ የሚደረግ ጥረትን ማገዝ
እና ዝግጁ መሆን ከጠቃሚ ባህል ይመደባሉ፡፡

122 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ጐጂ ልማዳዊድርጊቶች

ጐጂልማዳዊ ድርጊቶች የምንላቸው የሰው ልጅ ከዕለት ተዕለት


በሚያደርጓቸው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ
የፈጠራቸው እና ያዳበራቸው ድርጊቶች ሲሆኑ ለድርጊቱ የተጋለጡ
የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የስነ-ልቦና እና የጤና ችግር በመፍጠር
ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው፡፡ በመሆኑም በክልላችን ጐጂ
ልማዳዊ ድርጊቶች የምንላቸው፡-

 ያለአቻ ጋብቻ እና ያለእድሜ ጋብቻ


 ግግ ማስወጣት
 እንጥል ማስቆረጥ
 ጉሮሮ ማስቧጠጥ
 የሰውነት መተልተል
 የሴት ልጅ ግርዛት
 መጠናቸው ያልታወቀ የባህል መድኃኒቶች መጠቀምን እና
የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
4.2 የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ
የሚረዱ ጠቃሚ ባህላዊ ተግባራት

ተማሪዎች የተፈጥሮ ሀብትን ለመንከባከብ የሚጠቅሙ ባህላዊ


ተግባራትን ዘርዝሩ፡፡

ክልላችን ብዙ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሲሆን እነዚህን የተፈጥሮ


ሀብት ለመከላከልና ለመጠበቅ የሚደረጉ ባህላዊ ተግባራት አሉ፡፡
ከነዚህም ተግባራት ውስጥ የተወሰኑትን እናያለን፡፡ የክልሉ

123 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ማህበረሰብ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶች እንክብካቤ ተግባራትን


ያከናውናሉ፡፡ ከነዚህም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ተዳፍት ቦታዎች ላይ እርከን መስራት


2. በጓሮ አካባቢ እና በእርሻ ዙሪያ ችግኞችን መትከል
3. ጣምራ የእርሻ ዘዴዎችን መጠቀም (ለምሳሌ፡- በዛፎች ሥር
የቡና፣ ዝንጅብል፣ ወዘተ) መትከል
4. ትልልቅ ዛፎች እንዳይቆረጡ ክልከላ ማድረግ (የጎሳ መሪዎች፣
ሽማግሌዎች በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ከደኖች እና
ከቤተክሪስትያን አካባቢ ትልልቅ ዛፎች እንዳይቆረጡ
ይከለክላሉ)፡፡
5. የውሃ ምንጮችን መጥረግ እና መንከባከብ ወዘተ ናቸው፡፡

በክልላችን አከባቢን ለመጠበቅ ከሚጠቅሙት ባህላዊ ልምዶች


ውስጥ አንዱ ቀርከሃን መትከል ነው፡፡ ቀርቀሃ አስቸጋሪ የአየር
ጠባይ እና የመሬት ሁኔታን ተቋቁሞ በፍጥነት የሚያድግ ተክል
በመሆኑ ለአከባቢ ተሃድሶ የላቀ ጠቀሜታ አለው፡፡ ቀርቀሃ በባህሪው
ብዙ ስነ ምህዳራዊ ጥቅሞች አሉት፡፡

ቀርቀሃ ብዙ የተፈጥሮ ችግሮችን የመፍታት አቅም አለው፡፡


ለምሳሌ፡- የአፈር መሸረሸርን ይከለክላል፣ የአፈር ለምነትን
ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ የመጠቀም ልምድ አንደኛው ጠቃሚ


ባህል ሲሆን ያለአግባቡ የተፈጥሮ ሀብትን መጠቀም ደግሞ

124 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለወደፊት (ለመጭው) ትውልድ አለማሰብ መሆኑን መረዳት


አስፈላጊ ነው፡፡

ለምሳሌ ያክል በክልላችን ከሚኖሩት ብሔረሰቦች የማኦ ኮሞ የደን


እንክብካቤ እንመልከት፡፡ የማኦ ብሔረሰብ የተፈጥሮ ደን ከሌለ
የሕይወት ዑደታቸው እና አጠቃላይ የመኖር ህልውናቸው ላይ
ተፅዕኖ ይፈጥራል ብለው ስለሚያምኑ በተፈጥሮ ደን ጥበቃ እና
እንክብካቤ ያላቸው ትኩረት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በትላልቅ ዛፎች
ስር ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ቡና እና ሌሎችም አትክልቶች የሚተክሉ
ሲሆን በዛፎች ላይ ደግሞ ባህላዊ የንብ ቀፎ ይሰቅላሉ፡፡ እነዚህን
የዛፍ እና አጠቃላይ ተፈጥሮአዊ ደኖች የሚገኙ ጥቅሞችን
ስለሚያውቁ ማኦዎች ትላልቅ ዛፎችን አይቆርጡም፡፡ ዛፎችን
ካለምንም ምክንያት እና ቅድመ ሁኔታ የሚቆርጥ የማህበረሰቡ
አባል ከተገኘ በአካባቢው ባህል መሰረት የቅጣት እርምጃ
ይወሰድበታል፡፡

መልመጃ 4.1

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ


ሐሰት በማለት መልሱ፡፡

1. ባህል ከአንድ ማህበረሰብ ወደ ሌላ ማህበረሰብ የሚወራረስ ነው፡፡


2. መንፈሳዊ ባህል የምንላቸው የማይዳሰሱ አና የማይጨበጡ
ናቸው፡፡
3. ባህላዊ የግጭት አፈታት ሴቶችንና ወጣቶችን አያሳትፍም፡፡
4. ባህሎች ጠቀሜታ የላቸውም፡፡

125 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

5. ሽምግልናና እርቅ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ናቸው፡፡

4.3 የክልሉ ዋና ዋና ምጣኔ ሀብቶች


ተማሪዎች ምጣኔ ሀብት ማለት ምን ማለት ነው?
ምጣኔ ሀብት ማለት ማህበረሰቡ ያለውን ውስን የተፈጥሮ ሀብት
እንደት መጠቀም እንዳለበት የሚያጠና ነው፡፡ ምጣኔ ሀብት
ማህበረሰቡ የተፈጥሮ ሀብትን በመጠቀም በምን መልኩ ማምረት፣
ማሰራጨት እና እንደት ለፍጆታው ማዋል እንዳለበት የሚያሳይ
ነው፡፡

የክልላችን ህዝብ በሚከተሉት የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴዎች ላይ


ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ እነሱም በግብርና፣ ማዕድን ቁፋሮ፣
ኢንዱስትሪ፣ ንግድ እና ትራንስፖርት ናቸው፡፡ ከዚህም በመቀጠል
እያንዳንዱን በዝርዝር ትማራላችሁ፡፡

4.3.1 ግብርና
ግብርና ማለት የአዝዕርት እና የከብት እርባታን በአንድነት
የሚያጠቃልል የስራ ዘርፍ ነው፡፡ በአብዛኛው የክልላችን ህዝብ
የሚተዳደረው ሰብሎችን በማምረት እና ከብቶችን በማርባት ነው፡፡
ስለዚህ ግብርና በሁለት ዋናዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነሱም፡-
የሰብል ምርት እና የእንስሳት እርባታ ናቸው፡፡

ሀ. የሰብል ምርት

በክልላችን ከሚገኙ የሰብል አይነቶች ውስጥ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣


ዳጉሳ፣ እና የመሳሰሉትን በክልላችን የሚበቅሉ ናቸው፡፡ ከዚህ

126 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

በተጨማሪ ጥራጥሬዎች፣ የቅባት እህሎችና እንደ ቡና ያሉ የግብርና


ውጤቶችም ይመረታሉ፡፡

የቅባት እህሎች የሚባሉት እንደ ሰሊጥ፣ ለውዝ፣ ሱፍ፣ ጎመንዘር፣


አኩሪ አተር እና ኑግ በአብዛኛው የክልላችን ቦታዎች የሚመረቱ
ናቸው፡፡

ምንም እንኳ የክልላችን መሬት ለእርሻ ስራ ምቹ ቢሆንም ብዙ


ሰዎች ለምግብ እህል እጥረት ይጋለጣሉ፡፡

ተማሪዎች ይህ ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ይህ የሆነው ብዙ


የምግብ ሰብል ማምረት ስለአልተቻለ ነው፡፡ ታዲያ ብዙ የምግብ
ሰብል ማምረት የሚቻለው እንዴት ነው?

የክልላችን የእርሻ አስተራረስ ኋላቀር በመሆኑ የሚገኘውም ምርት


አነስተኛ ነው፡፡ ዘመናዊ እርሻ ግን የተሻለ በመሆኑ የሚገኘው
ምርት ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ምርታማነትን ለመጨመር የሚጠቅሙ
ዋናዋናዘዴዎች የምንላቸው፡-

1. ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎችን መጠቀም


2. የአፈር ማዳበሪያ መጠቀም
3. ውሃን በማቆርና ወንዞችን በመገደብ ለመስኖ እርሻ መጠቀም
4. ምርጥ ዘር መጠቀም
5. የተባይ መከላከያዎችን መጠቀም
6. ገበሬዎች ስለዘመናዊ እርሻ እንዲያውቁ ማስተማር እና
ሌሎችም ናቸው፡፡

127 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ለ. የእንስሳት እርባታ

ክልላችን ለእንስሳት እርባታ አመቺ ነው፡፡ በተለይ የቀንድ እና


የጋማከብት እርባታ የተለመደ ነው፡፡

የእንስሳት እርባታ እንደሰብል ምርት ሁሉ በባህላዊ እና በዘመናዊ


ዘዴዎች ይከናወናሉ፡፡ ባህላዊ ዘዴዎች ኋላቀር ስለሆነ የሚገኘውም
የምርት መጠን አነስተኛ ነው፡፡ በክልላችን የሚከናወነው የእንስሳት
እርባታ በአብዛኛው ባህላዊ ሲሆን በዘመናዊ በጥቂቱ ይከናወናል፡፡
ከክልላችን የእንስሳት ውጤቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ሥጋ፣ ወተት፣
ማር፣ ሰም፣ ቆዳ እና ሌጦ ናቸው፡፡

ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘዴ

1. እንስሳት በቂ እና ንፁህ ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያ እና ህክምና


ስለሚያገኙ ምርታቸውም ከፍተኛ ይሆናል፡፡
2. የእንስሳት ዝርያ የተሻሻለ ስለሆነ ጥሩ ምርት ይሰጣሉ፡፡
3. የተሻለ የገቢ ምንጭ ያስገኛሉ፡፡

4.3.2 የማዕድን ቁፋሮ

የማዕድን ቁፋሮ ማለት ማዕድናትን ከመሬት በማውጣት መጠቀም


ማለት ነው፡፡ በክልሉ ውስጥ ብዙ ዓይነት ማዕድናት ይገኛሉ፡፡

እነዚህ የማዕድናት አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነሱም፡-ወርቅ፣


እምነበርድ፣ የድንጋይ ከሰል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የማዕድን ቁፋሮ ምጣኔ ሀብት እስከ አሁን ድርስ አስተዋጽኦው በጣም


አነስተኛ ነው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው የማዕድን ፍለጋና ቁፋሮ ከፍተኛ

128 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ገንዘብና የሰለጠነ የሰው ኃይል ስለሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም


በሀገራችንም ሆነ በክልላችን አቅም ይህን ለማሟላት ስለማይቻል
የማዕድን ፍለጋ እና ቁፋሮ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ማዕድን ለሰው ልጅ ብዙ ጥቅም ይሰጣል፡፡ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት


ናቸው፡-

 ማዕድናት ለኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃነት ያገለግላሉ፡፡


ለምሳሌ የድንጋይ ከሰል ለኃይል ምንጭነት ያገለግላሉ፡፡
 ለግንባታ አገልገሎት ለምሳሌ የኖራ ድንጋይ፣ እምነበርድ
ሸክላ አፈረና ድንጋይ፡፡
 ጌጣጌጦችን ለመስራት ለምሳሌ ወርቅ ብርና አልማዝ
ናቸው፡፡

4.3.3 ኢንዱስትሪ
ኢንዱስትሪ ሌላው የምጣኔ ሀብት ዘርፍ ነው፡፡ የኢንዱስትሪ
የግብርና፣ የደንና ማዕድን ውጤቶችን በመለወጥ ለአጠቃቀም
የሚያመቻች እንቅስቃሴ ነው፡፡

በክልላችን ሁለት ዓይነት ኢንዱስትሪዎች አሉ፡፡ እነሱም፡-

1. የጎጆኢንዱስትሪ እና

2. ዘመናዊ ኢንዱስትሪ ናቸው፡፡

የጎጆ ኢንዱስትሪ
የጎጆ ኢንዱስትሪዎች ባህላዊ ኢንዱስትሪም በመባል ይታወቃሉ፡፡
የጎጆ ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ መሳሪያዎቻቸው ኋላ ቀር ናቸው፡፡

129 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ስራው የሚሰራው በእጅ እና በባህላዊ መንገድ ነው፡፡የማምርት


አቅሙም በጣም አነስተኛ ነው፡፡
የጎጆ ኢንዱስትሪዎች ለሀገራችን ኢኮኖሚ ያላቸው ጠቀሜታ በጣም
ከፍተኛ ነው፡፡ የምንጠቀምባቸው የእርሻ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ
የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች እና የሀገር ባህልልብሶች ከጎጆ ኢንዱስትሪ
የምናገኛቸው ናቸው፡፡
የጎጆ ኢንዱስትሪ ከሚባሉት ዋናዋናዎቹ

 የሽመና ስራ
 የሸክላ ስራ
 የብረት ቅጥቀጣ ስራ
 የቆዳ ስራ
 የጌጣጌጥ ስራ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ዘመናዊ ኢንዱስትሪ

ዘመናዊ ኢንዱስትሪ የሚባሉት በነዳጅ ወይም በኤሌክትሪክ ኃይል


የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፡፡

ዘመናዊ ኢንዱስትሪዎች በአጭር ጊዜ ብዙ ማምረት ይችላሉ፡፡


ዘመናዊ ኢንዱስትሪዎች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡- ቀላል
ኢንዱስትሪና ከባድ ኢንዱስትሪ ናቸው፡፡

ሀ. ቀላል ኢንዱስትሪ

ቀላል ኢንዱስትሪ ማለት ቀለል ያለ ጥሬ ዕቃን በመጠቀም


ያለቀለት ምረትን እና የዛን አካል ለምሳሌ የማሸግ፣ የማከማቸት፣

130 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የመሸጥ እና የማከፋፈል ሂደትን ያካተተ ነው፡፡ ቀላል ኢንዱስትሪ


የሚባሉት የግብርና እና የእፅዋት ውጤቶችን በጥሬ ዕቃነት
የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የምግብ ኢንዱስትሪዎች፣
የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች፣ የመጠጥ ኢንዱስትሪዎች፣ የስኳር
ኢንዱስትሪዎች፣ የወረቀት ኢንዱስትሪዎች እና የመሳሰሉት
ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ለ. ከባድ ኢንዱስትሪ፡-

ከባድ ኢንዱስትሪ ማለት ከፍተኛ መጠን ያለው የማመረቻ ዘዴ


ሲሆን ሰፊ ቦታ፣ በርካታ ገንዘብ እና የሰው ሀይል የሚጠይቅ ነው፡፡
ከባድ ኢንዱስትሪ የሚባሉት ማዕድንን እንደጥሬ ዕቃነት
የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- የብረታብረትና
የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

4.4 የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴዎች በተፈጥሮ ሀብት ላይ


የሚያሳድሩት ተፅዕኖዎች
ተማሪዎች የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ
የሚያሳድሩትን ተፅዕኖዎች ዘርዝሩ፡፡

የሰውልጅ የዕለት ተዕለት ኑሮውን ለማሸነፍ የተለያዩ የምጣኔ


ሀብት እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል፡፡ እነዚህ የምጣኔ ሀብት
እንቅስቃሴዎች እንደሰዎች የኑሮ ደረጃ የተለያየ ነው፡፡ እነዚህን
የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴዎች በተፈጥሮ ሀብትላይ ተፅዕኖ
የሚያሳድሩት በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን ማየት ይቻላል፡፡

 የግብርና ምርት

131 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 ንግድ
4.4.1የግብርና ምርት

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ አብዛኛው የሚተዳደረው በግብርና


ምርት ነው፡፡ ይህ ምርት በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡
፡ እነዚህም ተፅዕኖዎች ለክልሉ ተፈጥሮ ሀብት ውድመት ዋነኛ
መንስኤዎች ናቸው፡፡

ከፍተኛ የህዝብ ብዛት መጨመርን ተከትሎ የእርሻ መሬት ፍላጎት


ማደግ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ኋላቀር የአስተራረስ ዘዴ፣ የፈረቃ
እርሻ መስፋፋት፣ አካባቢን ያላገናዘበ እርሻ፣ የእንስሳት መንጋ
መስፋፋት፣ ልቅ የግጦሽ ስምሪት የእርሻም ሆነ የግጦሽ ላይ
የአፈር እና የውሃ እንክብካቤ ስራ አለመሰራቱ በአካባቢው ላይ
ከፍተኛ ተፅዕኖና የአካባቢ ውድመትን እያስከተለ ይገኛል፡፡
ከውድመቶቹም መካከል የውሃ መበከል፣ የአፈር አሲዳማነት
መጨመር፣ የደን መመናመን፣ የግብርና ምርት ማነስ
የሚያስከትሏቸው ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡

ሥዕል 4.3 የቀርከሃ እንጨት ተቆርጦ ለሽያጭ ሲውል

132 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

4.4.2ማዕድን

ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እድገት የማዕድን ሀብት ጉልህ ሚና


እንዳለው የበርካታ ሀገራት ዕድገት ማሳያ ነው፡፡ የማዕድን ሀብት
ካለቀ የሚተካ ባለመሆኑ ሀብቱን ባግባቡ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡
በመሆኑም ክልላችን በማዕድን ሀብቷ የታደለች ነች፡፡
በክልሉ ውስጥ በሰፊው ከሚገኙ ማዕድናት ውስጥ የእምነበረድ
ማዕድን በጉባ ወረዳ፣ በሰዳልና በቡለን ወረዳዎች ሲሆን የወርቅ
ማዕድን ደግሞ በሸርቆሌ፣ መንጌ፣ ኩርሙክ፣ በካማሽ፣ በዳምቤና
በሰዳል ወረዳዎች ይገኛል፡፡ እንዲሁም የድንጋይ ከሰል በካማሽ
ዞን በምዥጋ ወረዳ እና ካማሽ ወረዳ ላይ በሰፊው እየተመረተ
በስራ ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ማዕድናት በባህላዊ እና በዘመናዊ


መንገዶች ይመረታሉ፡፡ እነዚህ ማዕድናት በሚመረቱበት ጊዜ
በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ከእነዚህም
ተፅዕኖዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

- የህብረተሰብ መፈናቀል
- የመጠጥ ውሃ መበከል
- በሰራተኞች ላይ የመታፈን የጤና አደጋ እነዚህ ጥቂቶቹ
ናቸው፡፡

የእንጨት ከሰል
የአካባቢው ማህበረሰብ ኑሮውን ለመደጎም በአካባቢው ያለውን ደን
እየጨፈጨፈ ከሰል ማክሰል እና ለገበያ ማቅረብ በስፋት በሶስቱም

133 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ዞኖች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እና እየተለመደ የመጣ ሲሆን


ከፍተኛ የሆነ የደን ውድመትን እያስከተለ ነው፡፡ በሰዎች ጤና ላይ
ከፍተኛ ጉዳትንም እያስከተለ ይገኛል፡፡ በሳይንሳዊ መንገድ
ተጠንቶ በክልሉ ነዋሪዎች ላይ የደረሱ ጉዳቶች የሚያሳይ መረጃ
ባይኖርም የከሰል አመራረት ግን በሰራተኞች እና በአካባቢው ላይ
የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡

ከጉዳቶችም መካከል፡-

 መርዛማ ጭስ
 የበረሃማነት መስፋፋት
 የአየር ንብረት መዛባት
 የሳንባ በሽታ (ኒሞኒያ) ወይም የአተነፋፈስ ችግር
 ሲልሲሰ (ሲሊኮን በተባለ ንጥረ ነገር የሚመጣ በሽታ)
እነዚህ ተፅዕኖዎች እየተባባሱ ከሄዱ አምራቹን ማህበረሰብ
በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል፡፡

ሥዕል 4.4 ደን በመጨፍጨፍ ለሽያጭ የሚዉል የእንጨት ከሰል

134 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

4.4.3 ንግድ

ንግድ ማለት ምን ማለት ነው?

ንግድ ማለት በሰዎች መካከል የሚከናወንዕቃን የመሸጥ፣የመግዛትና


የመለወጥ እንቅስቃሴ ነው፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተወሰነው ማህበረሰብ የሚተዳደረው
በንግድ ስራ ነው፡፡ ይህ የንግድ ስራ በክልሉ የምጣኔ ሀብት
እንቅስቃሴ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተፅዕኖዎችን ያሳድራል፡
፡ ለምሳሌ በክልሉ ሰፊ የሆነ የወርቅ ምርት ይገኛል፡፡ በዚህ
የወርቅ ምርት ላይ የተሰማሩት አብዛኛዎቹ በህገወጥ መንገድ
ሲሆን ይህም ህገወጥ ንግድ የክልልን ገቢ ብሎም የሀገርን የውጭ
ምንዛሬ ላይ የራሱየሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

4.4.4 ገበያ መር የሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ምርት ውጤቶች


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልየተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት ምርቶች
ይገኛሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ በቀጥታ ለገበያ የሚውሉ ሲሆኑ ከነዚህም
መካከል፡-
 የቀርቀሃ ምርት
 ማዕድናት (ወርቅ፣ እምነበረድ፣ የድንጋይ ከሰል ወዘተ)
 የቅባት እህሎች፣ የእህል ምርቶች፣
 የአትክልትና ፍራፍሬ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የቀርቀሃ ምርት
የክልሉ ማህበረሰብ ኑሮውን ለማሻሻል ከሚጠቀምባቸው የእንጨት
ምርቶች አንዱ የቀርቀሃ ምርት ነው፡፡ ይህም ማለት የንግድ

135 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

እንቅስቃሴው በዚህ ቀርቀሃ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ያሳያል፡፡


ከጠቀሜታዎቹም መካከል ለቤት መስሪያ፣ ለጥራር መስሪያ፣
ለእንጀራ መሶብ መስሪያ ወዘተ ምርቶችን ሰርተው ለገበያ
በማቅረብ በገቢምንጭነት ይጠቀሙበታል፡፡

ሥዕል4.5 የቀርከሃ ምርቶች

ማዕድናት

በክልሉ ውስጥ በስፋት ወርቅ፣ የእምነበረድ እና ድንጋይከሰል


ሲገኝ በከፍተኛ ሁኔታ የንግድ እንቅስቃሴ እንድኖር አድርጓል፡፡
በተለይ የወርቅ ምርት በባህላዊ መንገድ የሚመረት እና ሰፊውን
ማህበረሰብ በንግድ እንቅስቃሴ ያስተሳሰረ ማዕድን ነው፡፡

የቅባት እህሎች

በክልሉ ውስጥበስፋት የሚመረቱ ገበያ መር የተፈጥሮ ሀብቶች


ውስጥ አንዱ የቅባት እህሎች ሲሆኑ እንደ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ለውዝ ያሉ
የቅባት እህሎች በሰፊውይመረታሉ፡፡ ለምሳሌ ሰሊጥ በመተከል ዞን
በጉባ ወረዳ፣ ዳንጉር፣ ቡለን እና በካማሽ ዞን በሁሉም ወረዳዎች
በሰፊው ይመረታሉ፡፡

136 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

መልመጃ 4.2

ሀ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል


ምረጥ/ጭ

1. ከሚከተሉት ውስጥ በክልላችን የማይገኘው የማዕድን ሀብት


የቱ ነው?
ሀ/ ወርቅ ለ/እምነበረድ ሐ/ጨው መ/ የድንጋይ ከሰል
2. አብዛኛው የክልላችን ህዝብ መተዳደሪያ ስራ የሆነው የቱ
ነው?
ሀ/እርሻ ለ/ ንግድ ሐ/ዕደ-ጥበብ መ/ ማዕድን ቁፋሮ
3. ከሚከተሉት ውስጥ አላቂ ማዕድን የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ወርቅ ለ/እፅዋት ሐ/ አፈር መ/ውሃ
ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ
1. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚመረቱትን የቅባት
እህሎችን ዘርዝሩ፡፡
2. የማዕድን ጥቅሞችን ዘርዝሩ፡፡

4.5 በክልላችን የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብት ምርት ውጤቶች


እና ሽያጭ
በክልሉ በርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ዋና
ዋናዎቹ ደን፣ አፈር፣ የዱር እንስሳት፣ ማዕድናት፣ ውሃና
የመሳሰሉት ናቸው፡፡

በክልላችን የተፈጥሮ ሀብት ውጤቶች ሽያጭ በሁለትመልኩ


ይከናወናል፡፡

137 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

4.5.1 በህጋዊ በሆነ መንገድ የሚከናወን ሽያጭ


ይህ የሽያጭ ሂደት ሰዎች በማህበር ተደራጅተው ወይም ግለሰብ
ድርጅት ከፍተው ህጋዊ የምርት ፍቃድ አውጥተው እና
የምርቶቻቸውን ውጤት ለህጋዊ ነጋዴዎች የሚሸጡበት ነው፡፡

እነዚህ ድርጅቶች /ማህበራት/ ምርቶቻቸውን ለንግድ ድርጅቶች


የሚሸጡት በጅምላ ወይም በችርቻሮ ሊሆን ይችላል፡፡

ለምሳሌ፡- እምነበረድ፣ የድንጋይ ከሰልና ወርቅ (በባህላዊ እና


በዘመናዊዘዴ)፣ ቀርቀሃ፣ አሸዋ፣ ድንጋይና የመሳሰሉት ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡

4.5.2 ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚከናወን ሽያጭ


ህጋዊ ያልሆነ የተፈጥሮ ሀብት ውጤት ሽያጭ ሲባል መንግስት
በማያውቀው መንገድ ወይም በድብቅ ህጋዊ ባልሆነመንገድ
የሚሸጡበት ሂደት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች/ግለሰቦች/ ለመንግስት
ምንም ግብር የማይከፍሉ እና በመንግስት ዘንድ የማይታወቁ
ለራሳቸው ጥቅም ብቻ የቆሙ ናቸው፡፡ ስለሆነም እነዚህ ህጋዊ
ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ውጤት ሻጮች ናቸው፡፡ እነዚህ
ለተፈጥሮ ሀብት መውደም ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ
ናቸው፡፡

እነዚህ ህጋዊ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ውጤት ሻጮች የሚባሉት


በሕገ ወጥ በባህላዊ መንገድ ወርቅ ቆፍረውበማውጣት የሚሸጡ፣
ያለፍቃድ ከዱር እንጨት ቆርጠው የሚሸጡ፣ ከሰል አክስለው

138 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የሚሸጡ፣ ትላልቅ ዛፎችን ቆርጠው ጣውላ በማውጣት የሚሸጡና


የመሳሰሉት ናቸው፡፡

4.6 የመጓጓዣ ዘዴዎች

ተማሪዎች መጓጓዣ ማለት ምን ማለት ነው? ምንስ ጠቀሜታ


አለው?

መጓጓዣ ማለት ሰውና ዕቃን ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ


የምንጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ የመጓጓዣ ዘዴዎች የሚባሉት፡-
የመንገድ ትራንስፖርት፣ የባቡር ትራንስፖርት፣ የአየር
ትራንስፖርት እና የውሃ ትራንስፖርት ናቸው፡፡ መጓጓዣ አንድ
የምጣኔ ሀብት ዘርፍ ነው፡፡

የመጓጓዣ ዓይነቶችን እና ጥቅሞቻቸውን ከአንደኛ እሰከ ሦስተኛ


ክፍል አካባቢ ሳይንስ በስፋት ተምራችኋል፡፡

የመጓጓዣ ዓይነቶች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፤ እነሱም

1. ባህላዊ መጓጓዣ
2. ዘመናዊ መጓጓዣ ናቸው፡፡
1. ባህላዊ መጓጓዣ
ተማሪዎች ባህላዊ መጓጓዣ ማለት ምን ማለት ነው?

ባህላዊ መጓጓዣ ማለት ከጥንት ጀምሮ በማህበረሰቡ የሚዘወተሩ


ሰዎችን እና ዕቃዎችን ከቦታ ቦታ የሚያጓጉዙበት ዘዴ ነው፡፡

በክልላችን ከሚዘወተሩ የባህላዊ መጓጓዣ ዓይነቶች ውስጥ አህያ፣


ፈረስ፣ በቅሎ፣ ጋሪ እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡

139 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 4.6 ባህላዊ መጓጓዣ

2. ዘመናዊ መጓጓዣ

ዘመናዊ መጓጓዣ ማለት ደግሞ ፈጣን እና ጥራት ባለው


መንገድ ሰዎችን እና ዕቃዎችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ
የሚጓጓዝበት ዘዴ ነው፡፡ ዘመናዊ መጓጓዣ ከሚበሉት ውስጥ
መኪና፣ ሞተር ሳይክል፣ ባጃጅ፣ አውሮፕላን፣ መርከብ እና
ባቡር ናቸው፡፡

ሥዕል 4.7 ዘመናዊ መጓጓዣ

140 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ተግባር 4.3
ተማሪዎች የቤተሰቦቻችሁን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ
አብራሩ፡፡

4.7 ቅርስ

4.7.1 የቅርስ ምንነት


ቅርስ ማለት ምን ማለት ነው?
ቅርስ ማለት ካለፈው ትውልድ እየተወረሰ የሚተላለፍ የአንድ ሀገር
ህዝብ የብዙ ዘመናት የስራ ውጤቶች ክምችት ነው፡፡

ሰዎች ባለፉት የኑሮ ዘመናቸው ሰርተዋቸው እና ተገልግለውባቸው


ያለፉት ቅርሶች ሁሉ የታሪክ እና የባህል ቋሚ የህዝብ ሀብት
ናቸው፡፡ የታሪክ እና የባህል ቅርሶች የአንድ ግለሰብ ወይም
የአንድ ትውልድ የፈጠራ ውጤት ብቻ ሳይሆኑ የብዙ ሰዎች የስራ
ውጤትና የዘመናት ስብስብ ስራዎች ናቸው፡፡

ቅርሶች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ


ናቸው፡፡ ተፈጥሮአዊ ቅርስ ማለት የሰው ልጅ እውቀት እና የእጅ
ጥበብ ያላረፈበት ማለት ነው፡፡ እነዚህም የተለያዩ መልከዓ-
ምድራዊ አቀማመጥ፣ የዱር እንስሳት እና አዕዋፋት ተፈጥሮአዊ
ክስተቶች የሚታዩባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- የቅልጥ
አለት ፍንዳታዎች፣ ተራራ እና ሸለቆዎች ወዘተ ያጠቃልላል፡፡

141 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ባህላዊ ቅርስ ማለት የሰው ልጅ እውቀት እና ጉልበት ያረፈበት


አንድ ትውልድ በቆየበት ዘመን ከተፈጥሮ እና ከማህበራዊ
አካባቢው ጋር ባደረገው መስተጋብር፣ ንክኪ እና እንቅስቃሴ
ያገኘው የሥራ ፈጠራ ውጤት ነው፡፡

ባህላዊ ቅርሶች የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርስ ተብሎ በሁለት


ይከፍላሉ፡፡
ይህውም የሚዳሰስ ወይም ግዝፈት ያለው ቅርስ ማለትም በእጅ
የሚዳሰስ፣ በዓይን የሚታይ ባህላዊ እና ታርካዊ ቅርስን ያካተተ
ሲሆን የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ተብለው በሁለት
ይመደባሉ፡፡
ሀ. የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች
የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ማለት ከቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ
የማይቻሉ በመሠረት ተገንብተው በቋሚነት የተቀመጡ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡-

 በአሶሳ ከተማ የሚገኘው የሸህ ሆጀሌ አል ሀሰን የችሎት


አዳራሽ፣
 በማንኩሽ ከተማ የሚገኘው የደጃች መሀመድ ባንጃው ቤተ-
መንግስት፣
 በመተከል ዞን በወምበራ ወረዳ በሳንቂ ቀበሌ የሚገኝ
የጨለለቃ ዋሻ፣ የመታሰቢያ ሐውልት፣ የመቃብር ቦታ እና
የመሳሰሉት ናቸው፡

142 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 4.9 አሶሳ ከተማ የሚገኘው የሸህ ሆጀሌ አልሀሰን የችሎት አዳራሽ

ለ. የሚንቀሳቀሱ ቅርሶች

የሚንቀሳቀሱ ቅርሶችደግሞ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታመንቀሳቀስ


የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህም የብራና ላይ ጹሑፎች፣ ወርቅ፣ ብር፣
እና ከነሐስ የተሰሩ ገንዘቦች፣ የዝሆን ጥርስ እና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡

ተግባር 4.4
ተማሪዎች በአካባቢያችሁ የሚገኙትን ቅርሶች በመጎብኘት
ለክፍል ጓደኞቻችሁ አብራሩ፡፡

143 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ቅርስ ለመባል መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

ቅርሶችን መጠበቅ እና መከባከብ ብሎም ከትውልድ ወደ ትውልድ


ማስተላለፍ የሁሉም ሀላፊነት ነው፡፡

ለቅርሶች እንክብካቤ እና ጥበቃ ከመደረጉ አስቀድሞ የመለየት፣


የመመዝገብ እና መረጃ የማሰባሰብ ተግባር ይከናወናል፡፡ በዚህም
መሠረት አንድ ቅርስ ቅርስ መሆኑን ለማረጋገጥ ከሚከተሉት
መመዘኛዎች ቢያንስ አንዱን አሟልቶ መገኘት አለበት፡፡ እነሱም

1. ለታሪክ እና ለባህል ጥናት ያለው ጠቀሜታ፣


2. በስነ-ጥበባዊ እና በኪነ-ህንፃ አሰራር ጥበብ ልዩ መሆኑ፣
3. በዕድሜው ጥንታዊ የሆነና የአንድን ዘመን የታሪክ እና
የባህል አሻራ የሚያሳዩ መሆኑ፣
4. አስደናቂ ብቸኛ መሆኑ፣
5. ለሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ያለው ጠቀሜታ የጎላ ከሆነ
ቅርስ ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

4.7.2 የቅርስ ጥቅም


ተማሪዎች ቅርስ ለምንይጠቅማል?
ቅርስ ትውልድ ስላለፈው ህብረተስብ ይበልጥ እንዲያውቅ
እንደማስተማሪያ ከማገልገሉም በላይ፣ ያለፈውን ትውልድ የፈጠራ
ውጤት መነሻ በማድረግ እውቀት በመቅሰም ከዘመኑ ጥበብ ጋር
በማዛመድ ይበልጥ በማሻሻል የፈጠራ ችሎታውን ለማዳበር
ይረዳል፡፡

144 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ቅርሶች በርካታ ጥቅሞች ያሏቸው ሲሆን ዋና ዋናዎቹ


እንደሚከተለው ይጠቀሳሉ፡፡ እነሱም

1. መንፈሳዊ ጠቀሜታ
2. ታሪካዊ ጠቀሜታ
3. ስነ-ጥበባዊ ጠቀሜታ
4. ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
5. ፖለታካዊ ጠቀሜታ
6. ማህበራዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ናቸው፡፡

4.7.3 የቅርሶች መበላሸትና መጥፋት


ቅርሶች በሁለት መንገድ ሊበላሹ ወይም ሊጠፉ ይችላሉ፡፡
1. በሰው ሠራሽ መንገድ
2. በተፈጥሮአዊ መንገድ ነው፡፡

1. ሰው ሠራሽ ጥፋት፡- ቅርሶች በጦርነት፣ በስርቆት፣ በዝርፍያና


ሽያጭ ጥፋት ይደርስባቸዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ከቤተክሪስትያንና
ገዳማት እንድሁም ከቤተመዘክሮች እና ሙዚየሞች ቅርሶች
እየተሰረቁ እና እየተዘረፉ ይሸጣሉ፡፡ ቅርሶች በአልባሌ ቦታ
በመቀመጥም ሊበላሹ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በውስጥ የእርስበርስ
ጦርነትና ከውጭ ወራሪ ኃይል ጋር በሚደረግ ጦርነት ይቃጠላሉ፤
ይዘረፋሉ፣ እናም ይወድማሉ፡፡

2. የተፈጥሮ አደጋ፡- ቅርሶችን ከሚያበላሹት የተፈጥሮ አደጋዎች


ውስጥ የጎርፍ አደጋ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የቅዝቃዜና የሙቀት
መፈራረቅ ወዘተ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ የታሪክ ቅርሶች

145 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ከጊዜ ብዛት የተነሳም በማርጀት፣ እድሳት በማጣት፣ በመፈራረስ


እና በመሰባበር ላይ ይገኛሉ፡፡

ለምሳሌ፡- በማንኩሽ ከተማ የሚገኘው የደጃች መሀመድ ባንጃው


ቤተ-መንግስት በእርጅና ምክንያት ፈራርሶ ይገኛል፡፡

4.7.4 የቅርሶች እንክብካቤ


ተማሪዎች ቅርሶቻችንን እንዴት አድርገን መንከባከብ እንችላለን?
ቅርስ ለአንድ ሀገር ወይም ማህበረሰብ ጠቀሜታው ብዙ ነው፡፡
ለምሳሌ ጽሑፍ ባልነበረበት ዘመን ልጆች ታሪክን እና የሥልጣኔ
ደረጃን ለማወቅ ያገለግላሉ፡

ቅርሶች ህዝቦችን እርስበርሳቸው እንዲተዋወቁ እና ልምድ


እንዲለዋወጡ ይረዳሉ፡፡ ቅርሶች አንድ ህዝብ ከሌላው ተለይቶ
የሚታወቅበትን ባህሉን ማለትም አለባበሱን፣ አመጋገቡን፣ ወጉን
እናልማዱን እንዲሁም ታሪኩን ለመገንዘብ ያስችላሉ፡፡ ቅርሶች
የቱርስቶች መስህብ በመሆን ከፍተኛ ገቢ ያስገኛሉ፡፡ ቅርሶች
የዘመኑን የፈጠራ ሥራ ያነቃቃሉ፡፡
በአጠቃላይ ቅርሶች በታሪክነታቸው እና በኢኮኖሚያዊ
አሳተዋጽአቸው ረገድ ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ናቸው፡፡

ቅርሶቻችን እንዳይበላሹ እና ከፍተኛ ጉዳት እንዳይደርስባቸው


አስፈላጊውን እንክብካቤ ልናደርግላቸው ይገባናል፡፡ ቀደም ሲል
ከላይ የተገለጹት አደጋዎች እንዳይደርሱባቸው እና እንዳይጎዱ
ከፍተኛ ቁጥጥር መደረግ ይኖርበታል፡፡

146 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ቅርሶች እንዳይበላሹ እና እንዳይመዘበሩ እያንዳንዱ ዜጋ


የመንከባከብ፣ የመጠበቅና የመቆጣጠር ግደታ አለበት፡፡

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ ጥያቄዎች


ሀ. የሚከትሉትን ዓረፍተ ነገሮች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል
ካልሆኑ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡

1. ባህል ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል፡፡


2. የባህል መገልጫዎች በህብረተሰቡ አይታወቁም፡፡
3. ቁሳዊ ባህል የምንላቸው የማይዳሰሱ እና የማይጨበጡ ናቸው፡፡
4. አለባበስ የአንድ ማህበረሰብ መለያ ምልክት ነው፡፡
5. ባህላዊ የግጭት አፈታት ጠቀሜታ የለውም፡፡
6.ማንኛውም ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ባህላዊ መገለጫ አለው፡፡

ለ/በ “ሀ”ሥር የተዘረዘሩትን በ“ለ” ሥር ካሉት ጋር አዛምዱ፡፡

ሀ ለ
1. የሰብል ምርት ሀ. እምነበረድ፣ ወርቅ
2. የእንስሳት ውጤት ለ. ቀርከሃ፣ የማገዶ እንጨት፣ከሰል
3. የማዕድን ውጤት ሐ. ጨርቃጨርቅና ሳሙና
4. የደን ውጤት መ. በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ
5. የኢንዱስትሪ ውጤት ሰ. አይብ፣ ቅቤ፣እርጎ
ረ. ወንዞችና ተራሮች

147 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሐ/የሚከተሉት ጥያቄዎች ውስጥ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን


ፊደል ምረጡ፡፡
1. ከሚከተሉት ውስጥ ባህላዊ የግጭት አፈታት ጠንካራ ጎን
ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ፍትሀዊ መሆኑ ለ/ ወጭ ቆጣቢ መሆኑ
ሐ/ አካባቢያዊ መሆኑ መ/ ጊዜ የሚወስድ መሆኑ
2. ከሚከተሉት ውስጥ ጠቃሚ የሆነ ባህል የቱ ነው?
ሀ/ ስራን መውደድ ለ/ መከባበር
ሐ/ የሀገር ፍቅር ስሜት መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
3. ጎጂ ልማዳዊ ድረጊት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ያላቻ ጋብቻ ለ/ ግግ ማስወጣት
ሐ/ የሰውነት መተልተል መ/ የጋራ ሀብትን መንከባከብ
4. የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ አለመጠቀም የሚያስከትለው ጉዳት
የቱ ነው?
ሀ/ የምረት መቀነስ
ለ/ የአየር መዛባት
ሐ/ የዱር እንስሳት መመናመን
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
5. -------ማለት የአዝዕርትና የከብት እርባታን በአንድነት
የሚያጠቃልል የስራ ዘርፍ ነው:
ሀ/ ግብርና ለ/ ማህድን ቁፋሮ ሐ/ መጓጓዣ መ/ኢንዱስትሪ
6. ኢንዱስትሪበስንት ይከፈላል?
ሀ/ በ3 ለ/ በ2 ሐ/ በ4 መ/ በ5

148 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

7. ከሚከተሉት ውስጥ የጎጆ ኢንዱስትሪ ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ/ የሽመና ስራ ለ/ የሸክላ ስራ
ሐ/ ብረት ቅጥቅጣ መ/ የብስኩት ፋብሪካ
8. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማይገኝ ቅርስ የቱ ነው?
ሀ/ የሼህ ሆጄሌ የችሎት አደራሽ
ለ/ የደጃ አዝማች ባንጃው ቤተ-መንግስት
ሐ/ የጎንደር ቤተ-መንግስት
መ/ የጨለለቃ ዋሻ
9. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኝ ማዕድን የቱ ነው?
ሀ/ ወርቅ
ለ/ እምነበረድ
ሐ/ የድንጋይ ከሰል
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
10. ከሚከተሉት ውስጥ የቀርቀሃ ጠቀሜታ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ለቤት መስሪያነት ለ/ ለእንጀራ መሶብ
ሐ/ለማረሻ መስሪያመ/ የወንበረ መስሪያ
11. ቅርሶችን እንደ ቅርስነት እንዲቆጠሩ የሚያደርጋቸው ነገር
የቱ ነው?
ሀ/ ለታሪክ ያለው ጠቀሜታለ/ ጥንታዊ መሆኑ
ሐ/ ለስነ ጥበብ ያለው ጠቀሜታ መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
12. ከሚከተሉት ውስጥ የቅርስ ጥቅም ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ለማስተማሪያነት ለ/ ለፈጠራ መነሻነት
ሐ/ ለጥናትና ምርምር አለመጥቀሙ መ/ ለታሪክ ጠቀሜታነት

149 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

13. ከሚከተሉት ውስጥ ለሰው ልጆች ከቦታ ወደ ሌላ ቦታ


ለመንቀሳቀስ የሚጠቅመው የቱ ነው?
ሀ/ማዕድን ለ/ መጓጓዣ ሐ/ ግብረና መ/ ንግድ

መ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ

1. በቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኙትን የተፈጥሮ


ሀብቶችን ዘርዝሩ፡፡
2. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ በአብዛኛው የሚተዳደርበት የስራ
ዘርፍ ምንድነው?
3. በቂየምግብ ሰብል ለማምረት መደረግ ያለባቸውን እርምጃዎች
ጥቀሱ፡፡
4. ባህላዊየኃይል ምንጭ የሆኑትን ዘረዝሩ፡፡
5. ባህላዊ የኃይል ምንጭ መጠቀም የሚያስከትለውን ጉዳት
ዘረዝሩ፡፡

150 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ምዕራፍ አምስት
5. ወቅታዊ ጉዳዮች
5.1 ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ
ተማሪዎች ስለ ኤች.አይ. ቪ ኤድስ በሽታ በሶስተኛ ክፍል አካባቢ
ሳይንስ ትምህርታችሁ ተምራችኋል፡፡ ተማሪዎች በ3ኛ ክፍላችሁ
የተማራችሁትን በማስታወስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡
ኤድስ ምንድን ነው? በምን በምን ይተላለፋል? እንዴት መከላከል
ይቻላል?
ኤድስማለት የሰውን ልጅ በሽታ የመከላለከል አቅም የሚያዳክም
በሽታ ሲሆን የሚመጣውም ኤች. አይ. ቪበተባለ ቫይረስ ምክንያት
ነው፡፡ ኤች.አይ. ቪ ማለት የሰውን ልጅ በሽታ የመከላከል አቅም
የሚያዳክም ቫይረስ ሲሆን የሚያጠቃውም የሰውን ልጅ ብቻ ነው፡፡

ተግባር 5.1

ተማሪዎች ኤድስ ማለት ምን ማለት ነው?

ኤች. አይ. ቪ የተፈጥሮ በሽታን የሚከላከልን ነጭ የደም ህዋስን


የሚያጠቃ ቫይረስ ነው፡፡ በአጠቃላይ ኤድስ ኤች.አይ. ቪ ቫይረስ
ወደ ሰውነታችን ሲገባና የሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅም
ሲዳከም የሚከሰት የበሽታ ምልክት ነው፡፡ ኤድስ እድሜ፣ ፆታ፣
ዘር፣ ሃይማኖት ወዘተ ሳይለይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል

151 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ያጠቃል፡፡ኤድስ መፈወሻ መድኃኒት ወይም ክትባት የሌለው


በሽታ በመሆኑ እጅግ አደገኛ ነው፡፡

ተግባር 5.2

ተማሪዎች የኤች. አይ. ቪ ቫይረስ እና የኤድስን


ልዩነት በቡድን ተወያይታችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ
አብራሩ፡፡

5.1.1 ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ/የሚተላለፍባቸው መንገዶች


ስለ ኤች.አይ. ቪ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች ማወቅ ራሳችንን
ከኤድስ ለመጠበቅ ይረዳል፡፡ በመሆኑም የቫይረሱ ዋናዋና
መተላለፊያ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. በተበከለ ደም
2. ልቅ በሆነ የግብረስጋ ግንኙነት
3. ከእናት ወደ ልጅ
4. በስለታማ ነገሮች
5. በሽተኛው በተጠቀመባቸው የጥርስ ቡሩሾች

ሀ. የተበከለ ደም

 በቫይረሱ የተበከለ ደም በመውሰድ ኤች.አይ. ቪ ኤድስ ይተላለፋል፡፡


 በበሽታው የተያዘ ሰው የተጠቀመባቸውን ቁሳቁሶች ምሳሌ ምላጭ፣
መርፌ ወዘተ መጠቀም ኤች. አይ. ቪን ያስተላልፋል፡፡

152 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 በበሽታው የተያዘ ሰው በተወጋበት መርፌ መወጋት ኤች. አይ. ቪ


ቫይረስን ያስተላልፋል፡፡
 በህገ ወጥ መርፌ ወጊዎች መታከም ቫይረሱን ያስተላልፋል፡፡

ሥዕል 5.1 የኤድስን በሽታ ሊያስተላልፉ የሚችሉ ቁሳቁሶች

ለ. ልቅ በሆነ የግብረሰጋ ግንኙነት

ብዙ ሰዎች ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች ጋር ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ


ግንኙነት በመፈፀም በቫይረሱ ይያዛሉ፡፡ ልቅ የሆነየግብረ ስጋ
ግንኙነት ማለት ጥንቃቄ የጐደለው ከብዙ ሰዎች ጋር የግብረ ስጋ
ግንኙነት መፈፀም ማለት ነው፡፡

ሐ. ከእናት ወደ ልጅ

ኤች.አይ. ቪ ቫይረስ ካለባት እናት የሚፀነሰው ህፃን በሚወለድበት


ወቅት በወሊድ ጊዜ በጥንቃቄ ጉድለት ወይም ከወሊድ በኃላ በጡት
ወተት አማካኝነት ኤች. አይ. ቪ ሊተላለፍበት ይችላል፡፡
በመሆኑምእናንተም ሆናችሁ ሌሎች ጓደኞቻችሁ የኤች.አይ. ቪ
መተላለፊያ መንገዶችን በመገንዘብ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል፡፡

153 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 5.2 የኤድስን በሽታ በማጥባት ከእናት ወደ ልጅ ይተላለፋል

5.1.2 ኤች. አይ. ቪ /ኤድስ የማይተላለፍባችው መንገዶች

ኤች.አይ. ቪ /ኤድስ የማይተላለፍባቸው መንገዶችን ማወቅ ስለኤድስ


ያለንን ፍራቻ ይቀንሳል፡፡ ያለፍርሃትና መጠራጠር ከኤች.አይ.ቪ
ቫይረስ ጋር አብረው ለሚኖሩት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ
ማድረግ ያስችላል፡፡ ኤች.አይ. ቪ የማይተላለፍባቸው መንገዶች፡-

 በጋራ መፀዳጃ ቤት መጠቀም


 አብሮ በመብላት እና መጠጣት
 አብሮ በመጫወት እና መማር
 በመጨባበጥ
 በትንፋሽ እና በወባ ትንኝ ንክሻ ወዘተ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ/
አይተላለፍም፡፡

154 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

አብሮ መብላትአብሮ በመጫወትመጨባበጥ

ኤድስ

አብሮ በመማር በወባ ትንኝበትንፋሽ

ሥዕል 5.3 የኤድስ በሽታ የማይተላለፍባቸው መንገዶች

ኤች.አይ. ቪ/ኤድስን መከላከል እንዴት ይቻላል?


ራስን ከኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ለመጠበቅ በርካታ አማራጮች አሉ፡፡
እነሱም፡-
1. ስለታም ነገሮችን በጋራ አለመጠቀም

2. ከተበከለ ደም ጋር ንክኪ አለማድረግ

3. የጥርስ ቡሩሽን በጋራ አለመጠቀም

4. ቆዳን ከመበጣት፣ ንቅሳት ከመነቀስ፣ የሴት ልጅ ግርዛት እና

ማድማት ልምዶች ማስወገድ፡፡

5.1.3 ኤች.አይ. ቪ ኤድስ በህፃናት ላይ የሚያስከትለው ችግር


ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ በህፃናት ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል?
ኤች.አይ. ቪ ኤድስ በህብረተሰቡ ውስጥ ከሚያስከትለው ማህበራዊ
ቀውስ ውስጥ አንደኛው ህፃናትን ያለ ወላጅ እንዲቀሩ ማድረጉ ነው፡
፡ህፃናት ደግሞ ወላጅ በማጣታቸው የተለያዩ ችግሮች
ይደርሱባቸዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ፡-

155 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 የእንክብካቤ ማጣት /የምግብ፣ የልብስ ወዘተ/


 የትምህርት ማቋረጥ
 ለጎዳና ሕይወት መዳረግ
 የተስተካከለ ጤናማ ስብዕና ይዞ አለማደግ ወዘተ ናቸው፡፡
እነዚህና የመሳሰሉት ችግሮች ህፃናትን የኤች.አይ. ቪ/ኤድስ ችግር
ተጠቂ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለሆነም ሁሉም የህብረተሰብ አካል ለነዚህ
ህፃናት እንክብካቤና ድጋፍ ማድረግ አለበት፡፡

5.1.4 ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ የሚያደርሳቸው ተፅዕኖዎች

ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ በሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ላይ ሁለንተናዊ


የሆነ ቀውስ ያስከትላል፡፡ እነዚህም ቀውሶች፡-

ሀ. ማህበራዊ ቀውሶች

ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ አምራች የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል


ስለሚገድል፣ የጥገኛ ቁጥርን ይጨምራል፣ ለስደት ይዳርጋል፡፡

አረጋውያን እራሳቸው በሚጦሩበት ዕድሜ ወላጅ አልባ የሆኑ


ህፃናትን ተንከባካቢ ይሆናሉ፡፡ ኤች.አይ. ቪ /ኤድስ ገዳይ በሽታ
በመሆኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊተላለፉ በሚገባቸው ጠቃሚ
ባህላዊና ልማዳዊ እሴቶቻችን ላይ ክፍተት ይፈጥራል፡፡

ለ. ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች

ኤች. አይ. ቪ /ኤድስ ሁሉንም የስራ መስክ የሚያቃውስና ብዙ


ወጪ የሚያስከትል በሽታ ነው፡፡ ኤች. አይ. ቪ /ኤድስ በግለሰብም
ሆነ በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡

156 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

አንድየኤች.አይ. ቪ/ኤድስ በሽተኛ በመታመሙ/ሟ ምክንያት


በተደጋጋሚ ከሥራ ይቀራል/ትቀራለች፡፡ በዚህም የተነሳ
የቤተሰቡን እና የሀገርን ኢኮኖሚ ይጎዳል፡፡ ከፍተኛ የህክምና
ወጪ ያወጣል/ታወጣለች፡፡ ለእነዚህ ነገሮች በሙሉ የሚወጣው
ወጪ ለተቀረው ቤተሰብ ሊቀር የሚገባውን ሀብት ያሟጥጣል፡፡

በተጨማሪም አንድ ወጣት በኤች.አይ. ቪ/ኤድስ ምክንያት ያለ


ዕድሜው/ ዕድሜዋ በሚሞትበት/ በምትሞትበት ጊዜ ለብዙ ጊዜ
ያካበተው/ችው እውቀትና ልምድም ለሀገርና ለወገን ጥቅም ሳይሰጥ
አብሮት/ሯት ይሞታል፡፡

ሐ. በትምህርት ላይ የሚከሰቱ ቀውሶች

ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ በትምህርት ላይ የሚያሳድራቸው ቀውሶች


የሚከተሉት ናቸው፡-

 ተማሪዎች ትምህርታቸውን ማቋረጥ፣


 መማር የሚችሉ ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ፣
 የታመሙ መምህራን በመደበኛ ሥራ ላይ መገኘት
አለመቻል፣ እና በመማር-ማስተማር ሂደት ላይ ጫና
መፍጠር፣
 በሰው ኃይል እጦት ምክንያት ትምህርት ቤቶች መዘጋት፣
ለትምህርት ሊውል የሚገባው ወጪ ወደ ጤና መዞር፣
 ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ መማር የማይችሉ ህፃናት ቁጥር
መብዛት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

157 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ኤች.አይ. ቪ/ኤድስን ለመከላከል የህብረተሰቡ ሚና

የኤች.አይ. ቪ/ኤድስ ችግር ለማንኛውም ለአንድወገን የሚተው


ችግር አይደለም፡፡ ሁሉንምወገኖች በጋራ ሊያሳትፍ የሚገባ ችግር
ነው፡፡

ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ የጤና ችግር ብቻ ባለመሆኑ የማይነካው እና


የማይጎዳው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ- ልቦናዊ ሁኔታ
ስለሌለ የኤድስ በሽታ የዕድገት እና የልማት ፀር ነው፡፡

የበሽታውንም ስርጭት ለመግታት የሁሉም መንግስታዊ፣


ሃይማኖታዊ፣ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሙያ
ማህበራት፣ የግል የልማት ዘርፎች እና የሌሎችንም ከፍተኛ
ርብርቦሽ የሚጠይቅ ነው፡፡ ሁሉም ዘርፎች በአስተዳራዊ ጉዳዮች፣
በገንዘብ፣ ቁሳቁስ ረገድ ብዙ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የኤድስ በሽታ ማህበራዊ ችግር ነው፡፡ መፍትኤውም እንዲሁ


ማህበራዊነው፡፡ ኤድስን ማህበራዊ ችግር የሚያደርገው
የሚያስከትለው ጉዳት ብቻ አይደለም፡፡ የችግሩ መነሻም ሆነ
መተላለፊያውያው ህብረተሰቡ በመሆኑነው፡፡

መልመጃ 5.1

ሀ. የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ


ሐሰት በማለት መለሱ፡፡
1. ኤች.አይ. ቪ/ኤድስ ካለባቸው ህፃናት ጋር አብሮ በአንድ
ክፍል መማር ኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ያስተላልፋል፡፡

158 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

2. ኤች. አይ. ቪ /ኤድስ በሽታ ሴቶችን ብቻ ያጠቃል፡፡


3. የኤች. አይ. ቪ /ኤድስ ስርጭትን መግታት ይቻላል፡፡
4. የኤች. አይ. ቪ /ኤድስ ክትባት የለውም፡፡
5. የጥርስ ቡርሾች በጋራ በመጠቀም ኤች.አይ.
ቪ/ኤድስአይተላለፍም፡፡
ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል
ምረጡ፡፡
1. የኤች. አይ. ቪ /ኤድስ መተላለፊያ መንገድ የሆነው የቱ
ነው?
ሀ/ በተበከለ ደም
ለ/ በስለታማ ነገሮች
ሐ/ ከእናት ወደ ልጅ
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
2. ከሚከተሉት ውስጥየኤች. አይ. ቪ /ኤድስ መተላለፊያ
መንገድ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ በመጨባበጥ ለ/ በግብረስጋ ግንኙነት
ሐ/ በስለታማ ነገሮች መ/ ከእናት ወደ ልጅ
3. ከሚከተሉት ውስጥ ኤች. አይ. ቪ /ኤድስበህፃናት ላይ
የሚያስከትለው ችግር የቱ ነው?

ሀ/ የትምህርት ማቋረጥ ለ/ ለጎዳና ሕይወት መዳረግ


ሐ/ የምግብ እጥረት መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

159 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

5.2 በቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸው ኬሚካሎች


ተማሪዎች ኬሚካል ምንድን ነው?

ኬሚካል የግል ንጽህናችንን ለመጠበቅ ጤናማ ለሆነ ሕይወት


መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን የልብሳችንን ንጽህና ለመጠበቅ
የሚንጠቀምባቸው የፈሳሽ ሳሙናዎችሲነሱ አብዛኞቹ የፈሳሽ
ሳሙናዎች በጤንነታችን ላይ የሚያደርሱት ጉዳት እጅግ በጣም
የከፋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እርግጥ ነው፤ አብዛኞቻችን ማንኛውም
ዓይነት የልብስ ፈሳሽ ሳሙና እንዳልሆኑ ስንሰማ እጅግ በጣም
እንገረማለን፡፡ ለመሆኑ ፈሳሽ የልብስ ሳሙና እንዴት ተፈጠረ?
በሳይንስ ሳሙናን ለመስራት በዋነኝነት የሚያገለግሉት ዘይት እና
የቅባት ውጤቶች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አደገኛ ለሆነ
ተቀጣጣይ ቦንብ ሲውሉየነበሩናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት በእያንዳንዳችን ቤት ውስጥ የሚገኙት ማንኛውም


ዓይነት ሳሙና የሚሰሩት ፔትሮ ኬሚካል ከሚባል ንጥረ ነገር
ነው፡፡ ከነዚህ ኬሚካሎች ውስጥ አብዛኞቹ ለጤና እጅግ በጣም ጎጂ
ናቸው፡፡ እነዚህም ኬሚካሎች አብዛኞቹ በሀገራቸው ውስጥ
የሚገኙት የሳሙና አምራች ድርጅቶች አንዳንዶቹ በሙሉ
ምርታቸው እንዳይጠቀሙ ሌሎች ደግሞ የሚጠቀሙበትን የመጠን
ልክ በማስቀመጥ እና መጠኑን እንዳያልፍ ማድረግ የሚያስችል
ሕግ በማውጣት ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ወደ ሀገራችን
ስንመጣ ግን ምንም እንኳን በአምራች ድርጅቶች ላይ በተወሰነ
መልኩ ሕጉ ቢኖርም ነገር ግን እነዚህ አደገኛ ኬሚካሎች

160 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

በውስጣቸው በያዙት ንጥረ ነገር በጤንነታችን እና በአካባቢያችን


ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ሥዕል 5.4 በቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸው የተለያዩ ኬሚካሎች

እነዚህ አደገኛ ኬሚካሎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ከእነሱም ሽቶ


(ዶድራንት)፣ የተባይ ማጥፊያ መድኃኒት፣ በረኪና የመሳሰሉት
ይጠቀሳሉ፡፡

ሽቶ

ሽቶ እርግጥ ነው ሁላችንም ፈሳሽ ሳሙና ስንገዛ ከዋጋው ቀጥሎ


መጀመሪያ የሚናየው የሳሙናውን ሽታ ነው፡፡ ነገር ግን አምራች
ድርጅቶች ሳሙና ላይ የሚጠቀሙበት ሽቶ በውስጡ ፒቲሌም
የተባለ አደገኛ ኬሚካል የያዘ ነው፡፡ ይህም ኬሚካል የስነ ተዋልዶ
ችግር የሚያመጣ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢ አየር እና
ውሃን በመበከል በጉበት በሽታ የመጋለጥ እድልን ከፍ ያደርጋል፡፡

161 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ነገር ግን ሁሉም የሽቶ ዓይነቶች ሳይሆኑ ከዚህ ፒቲሊየም የተሰሩ


ናቸው፡፡

በልብስ እጥበት ወቅት በተለይ ደግሞ ብዙ ልብሶችን በአንድ


ጊዜ ለረጅም ሰዓት ካጠቡ የእጃችን ቆዳ ከተለመደው ውጭ ነጭ
በማድረግ የማድረቅና የማቃጠል ስሜት ይፈጥራል፡፡

መልመጃ 5.2

ሀ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ

1. በቤታችን ውስጥ የምንጠቀምባቸው ኬሚካሎች በቤተሰባችን


ላይ ምን ጉዳት ያደርሳሉ?
2. በቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸውን ኬሚካሎች ዘርዝሩ፡፡

5.3 አደንዛዥ ዕፆች


ተማሪዎች አደንዛዥ ዕፆች ምንድን ናቸው
አደንዛዥ እፅ ማለት የሚያደነዝዙ፣ የሚያነቃቁ ኬሚካሎች ወይም
ንጥር ነገሮች ሆነው የሰዎች ባህሪይ በተወሰነ መልኩ ሊቀይሩ
የሚችሉናቸው፡፡ ንጥረ ነገሮቹ እንደ ፓራስታሞል፣ አስፕሪን፣
ሃሽሽኮኬን፣ ማሪዋና የመሳሰሉትን የሚያካትቱ ናቸው፡፡ እነዚህ
ንጥረ ነገሮች መድኃኒት የሆኑና መድኃኒት ያልሆኑ ተብለው
በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡
መድኃኒት የሆኑ አደንዛዥ ዕፆች፡- ፓራስታሞል፣አስፕሪን
ወዘተናቸው፡፡

162 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የአደዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት ማለት ያለ ሐኪም ፍቃድ ማንኛውንም


ጤንነትና አእምሮን የሚጎዳ አደንዛዥ ንጥረ ነገር ተጠቃሚ መሆን
ማለት ነው፡፡
ያለ አግባብ መድኃኒት መጠቀም፡- በሐኪም ፈቃድ የታዘዘን
መድኃኒት ከመጠን በላይ መጠቀም ወይም ያልታዘዘን መድኃኒት
መጠቀም ማለት ነው፡፡
የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት መንስኤዎች

 የአቻ ግፊት
 አዲስ ነገር ለመሞከር መፈለግ
 ጭንቀትን፣ ችግርን እንዲሁም ብቸኝነትን ለመቋቋም
በማሰብ
 እራስን ለማዝናናት በማሰብ
 በሱስ ተጠቃሚ ጓደኞች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት
 ለጥናት ይጠቅማል ብሎ ማሰብ ወዘተ ናቸው፡፡
መድኃኒት ያልሆኑ አደንዛዥ ዕፆች፡- ሃሽሽ፣ ኮኬን፣ ማሪዋና፣
አልኮል፣ ጫት፣ ሲጋራ፣ እና የመሳሰሉትን የሚያካትቱ ናቸው፡፡

5.3.1 ለአደንዛዥ ዕፅ የተጋለጡ ሰዎች የሚያሳዩት ምልክቶች


1. የባህሪ ለውጦች

በአስራዎቹ እድሜ ውስጥ የሚገኙ የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም


እንደሚተነብይ አስቀድሞ የሚሰጥ የማስጠንቀቅያ ምልክት ባህሪይ
ወይም በአኗኗር ላይ የሚደረግ ማንኛውም ለውጥ ነው፡፡ ይህ
ድንገተኛ የጓደኛ ለውጥ፣ ከቤተሰብ እና ከጓደኛ መራቅ፣ ማግለል፣

163 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የግንኙነት አለመኖር ወይም ቀደም ሲል በነበራቸው


እንቅስቃሴዎች ላይ ግደ የለሽነት ሊያካትት ይችላል፡፡ ሌላ
የማስጠንቀቂያ ምልክት ዕፆችን ለመግዛት ሊያገለግል የሚችል
ገንዘብ ወይም ሌሎች የቤት ዕቃዎች ይጎዳል፡፡

2.የስሜት ለውጦች

ልጆች በቤት ውስጥ በጣም የሚበሳጩ በንግግር የሚጎዱ አንዳንዴ


አመፀኛ የመሆን፣ ትምህርታቸውን የማቋረጥ፣ ከቤት መሸሽ፣
ንብረት ማበላሸት፣ ድብርት፣ የስሜት አለመረጋጋት እና
ግድየለሽነት የሚከሰቱ ለውጦች ናቸው፡፡

3. የአካል ለውጦች

የአደንዛዥ ዕፅ መድኃኒቶች በሰውነት ላይ አካላዊ ጉዳት


ያደርሳሉ፡፡ ምልክቶቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

 ደም አፊሳሽ አይኖች
 ድንገተኛ የክብደት መቀነስ
 ንፅህናቸውን አለመጠበቅ
 መንቀጥቀጥ
 የጉንጭ መቅላት
 የቁስል ምልክቶች
 ድብርት፣ ድካም እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

164 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

5.4 ድርቅና ረሃብ


ተማሪዎች ድርቅ ምንድን ነው?
ድርቅ ማለት አንድ ቦታ የሚጠበቀውን የመደበኛ የዝናብ መጠን
እና ስርጭት በጣም ዝቅተኛ ወይም ሙሉ በሙሉ ዝናብ ሳይኖር
ሲቀር የሚከሰት አስከፊ የአየር ንብረት መዛባት ወይም ክስተት
ነው፡፡
በድርቅ ወቅት ያልተለመደ ደረቅ አየር ለረጅም ጊዜ በመቆየት
ለድርቅ ለተጋለጡ ቦታዎች በግብርናና በሌሎች ስራዎች ላይ
ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡

ድርቅ ከዓለም ዋና ዋና አካባቢያዊ አደጋዎች አንዱ ነው፡፡ ድርቅ


አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው ለወራት ወይም ለዓመታት
በተከታታይ ዝናብ ከመደበኛ አማካይ መጠን በታች ሲዘንብ ነው፡፡

በተጨማሪም ድርቅ የእፅዋትንና የእንስሳት ፍላጎቶችን ለማቅርብ


ውሃ በቂ ያልሆነበት፣ ተሻጋሪ የአየር ንብርት መዛባት ፣ በዚህ ልዩ
ቦታ የሚኖሩትን የሰው ልጆች ጨምሮ ወደ ውሃ ድርቅ ሊያመራ
የሚችል በዋናነት በዝናብ እጥረት የሚከሰት ችግር ነው፡፡

የድርቅ አይነቶች በሶስት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-

1. የሜትሮዎሎጂ ድርቅ፡- ዝናብ በማይዘንብት ጊዜ ይከሰታል


ወይም በጣም ትንሽ ዝናብ ለተወሰነ ጊዜ ሲኖር የሚከሰት
ነው፡፡
2. የግብርና ድርቅ፡- የአካባቢን የሰብል ምርትን ይቀንሳል፡፡
ብዙውን ጊዜ በዝናብ እጥረት ይከሰታል ፡፡

165 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

3. የውሃማ አካላት ድርቅ፡- የሚመጣው የውሃ ክምችት ከአማካኝ


በታች በሚሆንበት ጊዜ ነው፡፡ በመደበኛነት በዝናብ እጥርት
የሚከሰት ነው፡፡

5.4.1 ለድርቅ መከሰት መንስኤዎችና የሚያስከትላቸው ጉዳቶች


ለድርቅ መከሰት መንስኤዎች
ለድርቅ መከሰት መንስኤ የሚሆኑ ነገሮች ብዙ ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ
የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የአየር ንብረት ለውጥ


 የአካባቢ መሬት መራቆት

1.የአየር ንብረት ለውጥ፡- ለአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛ ምክንያት


የሰው ልጅ ተግባራት ናቸው፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ የሙቀት መጠንን ከፍ በማድርግ የውሃ
ትነትን ያስከትላል፡፡ ይህ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ትነት ደግሞ የውሃ
አካላት ድርቀት ያስከትላል፡፡ የግብርና ምርትን አንዲቀንስ
በማድርግ ለረሀብም ያጋልጣል፡፡

2. የአካባቢ መሬት መራቆት፡- ለአካባቢ መሬት መራቆት


ምክንያት ከሆኑት ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የደን መጨፍጨፍ
 ከልክ ያለፈ ግጦሽ
 ከልክ ያለፈ እርሻ
 በረሃማነት ናቸው፡፡

166 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 5.5 በደን መጨፍጨፍ ምክንያት የተራቆተ መሬት

ድርቅ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች

 የአየር ንብረት ለውጥያስከትላል


 የውሃ ድርቀትን ያስከትላል
 አፈር ለምነትን እንዲያጣ ያደርጋል
 የሰብል ምርት እጥረት ያስከትላል
 ረሃብና እርዛትን ያስከትላል
 የጅምላ ስደትያስከትላል
 የእፅዋት ዘር፣ ከብቶችና የከብት ጉልበት
እጥረትያስከትላል
 በረሃማነትን ያስከትላል
 የሰውና የእንስሳት ሞት ያስከትላል
 የብዝሃ ሕይወት መጥፋትና የአካባቢ ገጽታ መበላሸት
የመሳሰሉት ናቸው፡፡

167 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሥዕል 5.6 በድርቅ ምክንያት የሚከሰት የእንስሳት ሞት

ረሃብ፡- ማለት በጣም ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት ነው፡፡


ስለሆነም ረሃብ የድርቅ ውጤት ነው፡፡

መልመጃ 5.3

ሀ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡

1. ለድርቅ መከሰት መንስኤ የሆኑትን ዘርዝሩ፡፡


2. ድርቅ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ፃፉ፡፡
3. የድርቅ እና የረሃብ ልዩነትን ዘርዝሩ፡፡

5.4.2 የድርቅ መቋቋሚያ መንገዶች


ድርቅን ለመቋቋም ብዙ የመፍትኤ እርምጃዎች ሲኖሩ ከእነዚህም
ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
 የግብርና ምርት ውጤት እንዲጨምርና ጎርፍ እንዲቀንስ
መሬትን በጥንቃቄ መጠቀም፣
 በተራቆቱ ቦታዎች ላይ ችግኞችን መትከል፣

168 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

 ተጠባባቂ የምግብ እህል ማዘጋጀት (ለምሳሌ፡- ጥራጥሬ) እና


ሌሎች፣
 የውሃና አፈር እንክብካቤ ተቋማት ፕሮግራሞችን ማስፋፋት፣
 የዝናብ ውሃን ማቆር፣ መሰብሰብና ማጠራቀም፣
 ድርቅ በሚያጠቃባቸው አካባቢዎች አርሶ አደሮች በዝናብ
ላይ አነሰተኛ ጥገኝነት ያላቸው ሰብሎችን እንዲያመርቱ
ማበርታታት፣
 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን ቆፍሮ እንዲጠቀሙ ማድርግ፣
 ውሃእንዳይባክን ከተጠቀምን በኃላ በማከም እንደገና
መጠቀም፣
 ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑትን የህብርተሰብ ክፍሎች ሌላ ቦታ
ማስፈርና እንዲያገግሙ ማድርግ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ሥዕል 5.7 በተራቆተ መሬት ላይ ችግኝ መትከል

169 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

የምዕራፉ የማጠቃለያ መልመጃዎች


ሀ.የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ
ሐሰት በማለት መልሱ፡፡

1. ኤች. አይ. ቪ /ኤድስ ገዳይ በሽታ አይደለም፡፡


2. የተበከለ ደም ኤች. አይ. ቪ/ኤድስን አያስተላልፍም፡፡
3. በጋራ የመፀዳጃ ቤት መጠቀም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን
አያስተላልፍም፡፡
4. ቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸው ኬሚካሎች ጉዳት
አያስከትሉም፡፡
5. አደንዛዥ ዕፆችን መጠቀም ምንም ጉዳት አያመጣም፡፡

ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

1. ከሚከተሉት ውስጥ ለደን መራቆት ምክንያት ያልሆነው የቱ


ነው?
ሀ/ የደን መጨፍጨፍ ለ/ ከልክ ያለፈ ግጦሽ
ሐ/ችግኞችን መትከል መ/ የእርሻ መሬትን ማስፋፋት
2. ከሚከተሉት ውስጥ ለአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት መንስኤ
የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የአቻ ግፊት ለ/ እራስን ለማዝናናት
ሐ/ ለጥናት ይጠቅማል ብሎ በማሰብ
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
3. ከሚከተሉት ውስጥ የአደንዛዥ ዕፅ ጉዳት የሆነው የቱ ነው?
ሀ/የጤና ችግር ለ/ የማህበራዊ ችግር

170 | ገ ጽ
የአራተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ የመማሪያ መጽሐፍ

ሐ/ የኢኮኖሚ ችግር መ/ ሁሉም መልስ ናቸው


4. ከሚከተሉት ውስጥ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የሚያጠቃው
የማህበረሰብ ክፍል የቱ ነው?
ሀ/ ህፃናትን ለ/ ወጣቶችን
ሐ/ ጎልማሶችን መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
5. ከሚከተሉት ውስጥ ከአደንዛዥ ዕፅ የሚመደበው የቱ ነው?
ሀ/ ሃሽሽ ለ/ ቡና ሐ/ጭማቂ መ/ ወተት

ሐ. የሚከተሉትን ባዶ ቦታዎች በተስማሚው ቃልወይም


ሐረግሙሉ

1. የሰውን ልጅ በሽታ የመከላከል አቅም የሚያዳክም ቫይረስ---


-ይባላል፡፡
2. ---------- ማለት በጣም ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት ነው፡፡
3. ለድርቅ መከሰት ዋና ዋና የሆኑ መንስኤዎች--------እና -----
------- ናቸው፡፡

መ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ

1. አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች የሚያሳዩትን የስሜት ለውጦች


ዘርዝሩ፡፡
2. የአደንዛዥ ዕፅ መድኃኒቶች በሰውነት ላይ የሚያሳዩትን
ምልክቶች ዘርዝሩ፡፡
3. ድርቅን ለመቋቋም መወሰድ ከሚገባቸው የመፍትኤ
እርምጃዎች አራቱን ፃፉ፡፡

171 | ገ ጽ

You might also like