Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 2

ከሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም.

ጀምሮ የመውጫ ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት


የሚኖሩ ዲስፕሊንና የምንከተለው ፕሮቶኮል

1. ከተፈቀደላቸው የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ለእለቱና ለዛ ፈተና


ከተመደቡ አስተባባሪዎች፣ ለፈተናው ከተመደቡ ፈታኞች ውጭ
የትኛውም አካል ወደ መፈተኛ ላብ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
2. ፈተናው በኦንላይን ስለሚሰጥ የአይሲቲ ሙያተኞች በመፈተኛ ላቦች አቅራቢያ
በመሆን ድጋፍ ይሰጣሉ፡፡
3. የፀጥታ ሃይል ወደ ላቡ እንዲገባ አስገዳጅ ሁኔታ ከተፈጠረ በማንኛውም ጊዜ
ሊገባ ይችላል፡፡ ዝርዝሩ በተቋም ደረጃ በሚሰጥ ኦሬንቴሽን ይገለፃል፡፡
4. የዩኒቨርስቲ የበላይ ኃላፊዎችን ጨምሮ የትኛውም አካል በምንም ሁኔታ
ስልክ፣ ስማርት ዋች፣ ታብሌት እና ተመሳሳይ ቁሶችን ይዞ ወደ ላቦች
መግባት አይችልም፡፡
5. የአይሲቲ ሙያተኞች በመፈተኛ ላቦች የሚሰጡት ድጋፍ ከትምህርት
ሚኒስቴር ባልደረቦች ወይም ከዩኒቨርስቲው አመራር ድጋፍና አመራር
ማግኘትን ስለሚያካትት በልዩ ሁኔታ በዩኒቨርስቲው ተመዝግቦ የሚያዝና
የሚታወቅ ቁጥር ያለው ስልክ ይዘው ወደ መፈተኛ አዳራሽ እንዲገቡ ሊፈቀድ
ይችላል፡፡
6. ማንኛውም ተፈታኝ ወደ መፈተኛ ላብ ከመምጣቱ በፊት ስልክ፣ ስማርት
ዋች፣ ታብሌት እና ተመሳሳይ ቁሶችን አለመያዙን አረጋግጦ መምጣት
ይኖርበታል፡፡ ይህን ክልከላ በመተላለፍ በመፈተኛ ላቦች ውስጥ ስልክ፣
ስማርት ዋች፣ ታብሌት እና ተመሳሳይ ቁሶችን ይዞ የተገኘ ተፈታኝ
ያስመዘገበው ውጤት ተሰርዞ ከአንድ ዓመት በኋላ በሚኖር የመውጫ ፈተና
እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡
7. ለአካል ጉዳተኛና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የሚመደቡ ግለሰቦች በሁሉም
ተፈታኝ የተጣለው ክልከላ ይመለከታቸዋል፡፡
8. በአንዳንድ ፕሮግራሞች ካልኩሌተር መምጣት ይፈቀዳል፡፡ በተጨማሪም
በአንዳንድ ፕሮግራሞች ለማስልያ የሚረዳ ንፁህ ወረቀት በዩኒቨርሰቲዎች
በኩል ሊፈቀድ ይችላል፡፡ ይህም ሆኖ ስልክ፣ ስማርት ዋች፣ ታብሌት እና
ተመሳሳይ ቁሶችን እንደ ካልኩሌተር መጠቀም ፈፅሞ አይፈቀደም፡፡ ሥራ ላይ
የሚውሉ ካልኩሌተሮች የተራቀቁና ፕሮግራመብል እንዳይሆኑ ተገቢውን
ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡
9. በማንኛውም ወቅት ከተፈቀደላቸውና ለድጋፍ ከተመደቡ የአይ.ሲ.ቲ
ባለሙያዎች በስተቀር የተፈታኙን መፈተኛ ኮምፒውተር መንካት በጥብቅ
የተከለከለ ነው፡፡
10. ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ላቦች ተፈትሸው እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት
ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ
እንዲገለል ይደረጋል፤
11. ለጀኔረተሮች ነዳጅ የሚያቀርቡትን ጨምሮ አስፈላጊ ሌሎች ድጋፍ
የሚሰጡ ሰራተኞች በፈተና ቀናት በሥራ ላይ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ በዚህ
ወቅት የዓመት እረፍት መስጠት ፈፅሞ አይቻልም፡፡
12. ተፈታኞች ፈተናው ከመጀመሩ ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ወደ መፈተኛ ላቦች
ገብተው መጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡
13. አስተባባሪዎችና የአይሲቲ ሙያተኞች በትምህርት ሚኒስቴር ለእለቱ
የመውጫ ፈተና ድጋፍ ለመስጠት ከተመደቡ ባልደረቦች እና ከዩኒቨርስቲው
ከፍተኛ አመራር ብቻ ውሳኔና አቅጣጫ ይቀበላሉ፡፡
14. ተቋማት እዚህ የተዘረዘሩትን ጨምሮ በፈተና ወቅት ስላሉ ክልከላዎችና
የአሰራር ሥነ ሥርዓት ለተፈታኝ ተማሪዎችና ለሚመለከታቸው አካላት
በጉልህ በሚታይ ቦታና አቀራረብ መረጃ እንዲደርሳቸው ያደርጋሉ፡፡

You might also like