Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

#በዲንዮሴፍፍስሃ

የወንድማችን ዳዊት አብርሃም መጽሐፍ -“ዕቅበተ እምነት በእንተ ነገረ ድኅነት”

-መ/ር ዳዊት የጻፋቸው መጽሐፍት ልዩ የሚያደርጋቸው ነገሮች አሉ፡፡ ያልተጻፈበት ርእሰ ጉዳይ ላይ
ትኩረት ማድረጉ ከብዙ ጸሐፊያን የሚለይበት ነው፡፡ በ 130 ገጽ የተቀነበበውን “ኦርቶዶክሳዊ ሥነ
ሰብእ” መጽሐፉን ስንመለከት በዚህ ርእስ የጻፈ ከዳዊት አብርሃም ውጭ አንድም የማውቀው ሰው
የለም፡፡ ይህ በተወሰነ መልኩ የምዳስሰው መጽሐፍም በአይነቱ ልዩ ነው፡፡ ራሱን ችሎ የዕቅበተ እምነት

ሥራ ነገረ ድኅነት (Soteriology) ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ብዙም የለምና፡፡ በዚህም


ጸሐፊው ሊበረታታና ሊመሰገን የሚገባው ነው፡፡ ስለዳረክልኝ አበርክቶ አመሰግናለሁ፡፡ ዐሥራ ሁለት
ምዕራፎችን የያዘ ሲሆን በእያንዳንዱ ዋና ርእስ ንዑስ ርዕሶችንም በጥሩ ሁኔታ የተብራሩ ናችው፡፡ የሽፋን

ሥዕሉን ማብራሪያን እስከ ዋቢ መጽሐፍቱ ድረስ 264 ገጽ ነው፡፡

- የአቡነ ሽኖዳን ትምህርቶች መሠረት ቢያደርግም ሌሎች ምንጮችንም ተጠቅሟል ጸሐፊው፡፡ ስለ


መጽሐፉ ሽፋን ሥዕል “ኩርዓተ ርእሱ” ማብራሪያም ይሰጣል፡፡ በእንግሊዞች የተሰረቀው ኩርዐተ ርእሱ ዐፄ
ዮሐንስ ለማስመጣት ተግተው ነበር ባይሳካላቸውም፡፡ ሽፋን በማድረግ የተጠቀመበት ምክንያትም
መጽሐፉም ሆነ ሥዕሉ ኦርቶዶክሳዊውን የመዳን ትምህርት የሚገልጡ ስለሆኑ ነው ብሎ ያስረዳናል፡፡
-ነገረ ድኅነት ምንድን ነው? ለምንስ አስፈለገ? ወዘተርፈ አይነት ጥያቄዎችን ማብራራት አይደለም
የመጽሐፉ ዋና አላማ ነገር ግን የአባቶቹን ፈለግ ተከትሎ ዳዊት አብርሃም በቁጭት ግልጽና ቀለል ባለ

አቀራረብ ዕቅበተ እምነት (Apologetics) ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ በተለይ የተሐድሶ


አራማጆች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ ምላሽ ይሰጣል፡፡

-በነገረ ድኅነት ላይ የሚሳሳቱት ፕሮቴስታንቶች የስህተታቸው መንሥኤዎች የሚላቸው በአንዲት ነጠላ


ጥቅስ ላይ መመሥረት፣ጥቅሱን ከዐውዱ ነጥሎ መጥቀስ፣ ጥቅሱን ከዳራው መነጠል፣ከሌሎች ጥቅሶች
አንጻር ለማየት አለመቻል፣ከጥቅሱ ንባብ ይልቅ የራስን ትርጓሜ አስበልጦ ማቅረብ፣አንድን ጥቅስ
ለተቃርኖ አስተያየት መጠቀም፣በጥቅሱ ውስጥ ያልነበረ ቃል መጨመር፣ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎችን አምርሮ መጥላት ለምሳሌ የያዕቆብ መልእክትን ወዘተርፈ፡፡ ጸሐፊው የስህተቶቹን
መንሥኤዎች እያነሳ ማብራሪያም ይሰጥበታል፡፡ በተለይ መዳን በእምነት ብቻ ለሚለው የተሳሳተ
አስተሳሰብ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ ቀለል ባለቋንቋ አብራርቶታል፡፡

-ጸሐፊው ኦርቶዶክሳዊ የነገረ መለኮት አረዳድ ዘዴዎችና መገለጫዎች መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ በበቂ
ማስረጃዎች ላይ መመሥረቱ፣ካጠቃላዩ አስተምህሮ ጋር የተቃኘ መሆኑ፣ትውፊታዊ ፈለግን የተከተለ

መሆናቸውን በተወሰነ መልክ ያስረዳናል፡፡ ስለ ጌታችን አዳኝነት መዳን በጌታ ሲባል ምን ማለት ነው ?
እንዴት ? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን አስተምህሮ
ያስረዳል፡፡

-ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መዳን የተናገራቸውና ስለእርሱ የተነገሩትን ከማብራሪያ ጋር


ከገጽ-78-91 ማንበብ ይቻላል፡፡ መዳን በጌታችን ስም በሚል አምስተኛው ምዕራፍ ላይ

የሚቃረኑ የሚመስሉትን “የጌታን ስም የሚጠሩ ሁሉ ይድናል”(የሐዋ፣2፡21) እና የማቴ.7፡21

“ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚወርስ አይደለም”የሚለውን ሲያብራራ ይህ


የሚያስገዝበን ነገር በጌታ ስም አዳኝነት ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁለት አይነት ወገኖች መኖራቸውን ነው

ይላል፡፡ ሌላ ማብራሪያ ለማንበብ መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡት፡፡ ምዕራፍ 6 መዳን በእምነት በሚል
ከገጽ -104-118 ቤ/ን በእምነት መዳን ስትል ምን እያለች እንደሆነ ትክክለኛውን ነገረ ድኅነት
ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አደርጎ ጸሐፊው በጥሩ ሁኔታ ያስረዳናል፡፡ ለመዳን የሚበቁ

(
የእምነት አይነቶች ሕያው እምነት፣ በፍቅር የሚሠራ እምነትና እመን ትድናለህ የሐዋ .16፡31)፡፡

-ሃይማኖት የሚያድን መሆኑን የተሐድሶዎች ሰህተትት እየጠቆመ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሃይማኖት ምን


እንደሚለን ትክክለኛውን ትምህርት ያስረዳል፡፡ በተለይ ከገጽ-111-116 ያለውን ያንብቡት፡፡

መጽሐፉ ብዙ ርእሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል ስለ አማኞችና የተመረጡት፣ ምሥጢራተ ቤ/ንና ነገረ


ድኅነት፣መዳን በምግባር ጭምር የሐዋርያትን መልእክታት እየጠቀሰ የሚያብራረበት ክፍል፣ ጸጋና
ተጋድሎ፣መዳንን እርግጠና ስለመሆንና የተመረጡ አማንያን፡፡ ስለዚህ መጽሐፉ የሌላችሁ
ገዝተው ቢያነቡት ገዝታችሁ ማናልባት የረሳችሁት ካላችሁ እንድታነቡት ስል አሳስባለሁ፡፡ጸሐፊው
ወንድማችንም የበለጠ መጽሐፉን በሐሳብ አዳብሮትና አሻሽሎት ተስፋ አደርጋለሁ እንደሚያሳትመው፡፡

-666፣ አስማት፣ ጠንቋይ፣ ጋኔል፣ ሉሲፈር፣…..የሚሉ ወሽካታና ሰይጣንን የሚሰብኩ መጽሐፍትን


ሲያነቡ ከሚውሉ ሕይወት ያለውንና ማንኛውም አንባቢ አንብቦ ሊረዳው በሚችለው መንገድ
የቀረበልንን የዳዊት አብርሃምን መጽሐፍ ብናነብ በጣም ይሻላል፡፡ ያንብቡ ያስነብቡ፡፡

You might also like