Professional Documents
Culture Documents
የመንበር ጉዳይ
የመንበር ጉዳይ
ከርዕሰ አድባራት እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተክርስቲያን አካባቢ
ወጣቶችና ነዋሪዎች ምዕመናን የቀረበ የቅድመ ጥንቃቄ ማመልከቻ
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ለሽሮሜዳ መህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጽ/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ መስተደድር ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት
በቤተክርስቲያን የአስተዳደር ሂደት ውስጥ ዋና ውሳኔ ሰጪ የሆነው የሰበካ ጉባኤ ውሳኔና ስምምነት በሌለበት ፣
በአጠቃላይ በማንአለብኝነት ለታሪክ እና ለቅርስ ተገቢውን ትኩረት እና ጥበቃ ባልተከናወነበት ከምንም በላይ
ጥልቅ ምርምር እን ጥናት ሳይከናወን ለዋናው ቤተመቅደስ ሊፈጥር የሚችለው ጉዳት ባልተጠናበት መልኩ
መንበሩን ቆርጠን እናነሳለን በሚል እንቅስቃሴ ማህበረ ካህናቱን እና ህዝቡን በሚያውክ ሁኔታ የቅርስ
ውድመት ለመፈጸም እንቅስቃሴ እየተከናወነ ስለሆነ ከምንም በላይ ሰላም ወዳድ የሆነው ማህበረ ካህናት እና
ምእመናኑ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ስለሆንን ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር ተገቢ የሆነ የማወያየት እና የጥናት ጉዳይ
መቅደም ስላለበት የቀጠናችን የፖሊስ ጽ/ቤት ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተል እና የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት
ጠቅላላ ከምንም በፊት ሰላም መቅደም ስላለበት ተገቢውን የማግባባት ስራ እንዲሰራ እያሳሰብን ትልቅ ጉዳይ
እና ታሪክ ከምንም በላይ የ 150 አመታት በላይ ቅርስ ለሆነ ቅዱስ ንዋየቅዱሳት ተገቢ የሆነ ጥናትና ጥበቃ
ከምንም በላይ ፍጹም መግባባት እንዲቀድም እያሳሰብን በዚህ መሀል ለመስከረም 1 የሚከበረውን የመልአኩ
የቅዱስ ራጉኤል እና የአዲስ አመት በአል በሰዎች ዘንድ ሙገሳ ለማግኘት ሲባል በድጋሚ ለነባሩ ቅርስ ተገቢ
ማሳረፍያ ባልተዘጋጀበት በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሊከሰት የሚችለው ጉዳት ባልታወቀበት ለሚደርሰው
የታሪክ እና የቅርስ ውድመት ተያይዞ ለሚከሰተው የሠላም መደፍረስ ሙሉ በሙሉ የቤተክርስቲያኒቱ
አስተዳደር አካላት ተጠያቂ መሆናቸውን ለማሳሰብ እየወደድን ይህን ማመልከቻ ከአንድ ገጽ የአካባቢው
ነዋሪዎች ፊርማ ጋር አያይዘን የላክን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ግልባጭ ፦
በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ለአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤ/ክ ጽ/ቤት