Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 14

መለከት #2

2
www.tlcfan.org 0
መለከት #2

የእግዚአብሔር መንግስቱ ሕጎች

የእግዚአብሔር ሕግና የሙሴ ሕግ የተለያዩ ናቸው ወይስ አንድ? ሕጉ የተሰጠው


ለእስራኤሎች ብቻ ወይስ ለሰው ልጆች ሁሉ? የእግዚአብሔር ሕግ የተሰጠው በማን ነው? በመለአክት
ወይስ በሙሴ? አስርቱ ትዕዛዛት በታቦት ውስጥ ሲሆኑ የሙሴ ሕግጋት ደግሞ በታቦቱ አጠገብ
የተቀመጡ ናቸው። ከዚህ የተነሳ አስሩ የከበሩ የቀሩት በታቦቱ አጠገብ ያሉት ደግሞ የተናቁ፣ ጊዚያዊና
ሃላፊ ጥላዎች ናቸው የሚል እምነት አለ። ይህ እውነት ነውን? የእግዚአብሔር ሕግ የተሰጠበት አላማ
ምንድን ነው? የእነዚህን ሁሉ ጥያቄ መልሶች ለማግኘት የእግዚአብሔር ቃል ቀረብ ብሎ መመልከትና
መመርመር ይጠይቃል። በዚህ ጽሁፍ ውስጥም የምናደርገውም ይህንኑ ነው። በእርግጥ ይህን ጽሁፍ
አንብበን ስንጨርስ ከላይ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች በሙሉ ከእግዚአብሔር ቃል የሆኑ መልሶችን
እናገኛለን።

የእግዚአብሔር ቃል ሁሉን እንድንፈትንና ትክክለኛ የሆነውን በቃሉ አረጋግጠን እንድንይዝ


ያሳስበናል። አብዛኞቻችን ግን እንዲያው በደፈናው የተነገረንን የምንቀበል እንጂ ቃሉን እንደ ቤርያ ሰዎች
የምንመረምር አይደለንም። ይህ ደግሞ አደጋ አለው። ከዚህ ቸልተኝነታችን የተነሳ አብዛኞቻችን አማኞች
እውነትን ወደ ማወቅ ከመድረስ ይልቅ የስህትት ትምህርት ላይ ወድቀን ለእግዚአብሔር ያለን ቅንዓትና
ንጽሕናችን ጎድሏል። ይህም እንደ ሄዋን ሰይጣን በተንኮሉ ሃሳባችን አዕምሯችን ስላበላሸው ነው።
2.ቆሮ.11፥1-3 ሌላው የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ነገር ደግሞ አንዳንዶች አማኞች የተማሩትን
ምንም በቃሉ ሳይፈትኑና በቃሉ ሳያረጋግጡ በየመድረኩና ሚዲያው የተገራቸውን እንደ እውነት
መቀበላቸው ነው። ይህ ደግሞ እንደ ገደል ማሚቱዎች የሰሙትን የሚያስተጋቡ የስህተት ትምሕርት
አፈሙዞች አድርጓቸዋል። ዛሬ በዚህ የጥናት ክፍል ግን በደንብ ጠጋ ብለን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ
ዘልቀን በመግባት እውነቱን እንማራለን። የልብ መዘጋጀት ከሰው ነውና እንግዲህ ልባችንን እናስፋ።

የሙሴ ሕግና የእግዚአብሔር ሕግ

አስሩ ሕግጋት የእግዚአብሔር ሲሆኑ የቀሩትን ሕግጋትና ትዕዛዛትን በሙሉ የሙሴ ሕጎችና
ትዕዛዛት ናቸው የሚል እምነት አለ። ይህ ፈጽሞ የተሳሳተ አስተሳሰብ ወይም የቃል መረዳት
በቤተክርሲያን ውስጥ ሰርጎ በመግባቱ ቤተክርሲያን ከኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ከሐዋርያትና ነብያት
የወረሰችውን ትክክለኛ የትምህርት ጎዳና እንድትስት አድርጓታል። ከእነርሱም መንገድ መነውለላችን
ያመጣብን ችግር በቀላሉ ልንቀርፈው ወደማችለው የቤተክርሲያ ውድቀት ውስጥ ከቶናል። ድል
ከሚነሱት ጻድቃብ መካከል በመሆን ፋንታ ለሰይጣንና ፈተናው እጅ ወደ ሰጡትና ድል ከማይነሱት
አማኞች ጋር እንድንፈረጅ አድርጎናል። አሁን በጊዜው መሰረት ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቃል በቶሎ
ልንመለሰና እያንዳዳችን ቃሉን በቃሉ ብቻ ልንተረጉም ይገባናል። አሁንም ይህንን እንደ ቃሉ ለመረዳት
ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሙሴ ሕግ ተብሎ ከሰፈረበት ጥቅስ በመነሳት ሌሎቹንም
ቃሎች አስከትለን ሁሉን አብረን እንመለከታለን።

“የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፥


መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን
መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ።የእስራኤልም ልጆች ሲያዩ በዚያ ስፍራ በድንጋዮቹ
ላይ የሙሴን ሕግ ጻፈባቸው።”ኢያሱ 8፥31,32

“ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም


በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።” ኢያሱ 1፥7

www.tlcfan.org 1
መለከት #2

“(የያሕዌንም) የእግዚአብሔርንም ሕግ መጽሐፍ አነበቡ ዕዝራም እግዚአብሔርን ማወቅ


ያስተምርና ያስታውቅ ነበር፥ ሕዝቡም የሚነበበውን ያስተውሉ ነበር።”ነህሚያ.8:፥8
“ኢዩ ግን በእስራኤል አምላክ (በያሕዌ) በእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ
አልተጠነቀቀም እስራኤልንም ካሳተው ከኢዮርብዓም ኃጢአት አልራቀም።” 2 ነገ.10፥31

እንግዲህ ከላይ ባየነው ቃሎች መሰረት የሙሴ ሕግና የሙሴ የሕግ መጽሐፍት እራሱ
የእግዚአብሔር ሕግ እንደሆነ እንመለከታለን። ሙሴ የራሱ የሆነ ምንም ሕግ የለውም። ይህም ማለት
ሙሴ ምንም ሕግን አላወጣም። ሙሴ ራሱ ለሕዝቡ ሲነግራቸው እንዲህ አለ፦
“ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉአትን ሥርዓትና ፍርድ
አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር (ያሕዌ) በዚያን ጊዜ አዘዘኝ።” ዘዳ.4፥14

“እርሱም እንዳዘዘን በአምላካችን በእግዚአብሔር (ያሕዌ) ፊት እናደርጋት ዘንድ ይህችን ትእዛዝ


ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።” ዘዳ.6፥25

“ዛሬ እኔ (ሙሴ) አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ


አምላክህን እግዚአብሔርን (ያሕዌን) እንዳትረሳ ተጠንቀቅ”ዘዳ.8፥11
መቼም ይህን ቃል ተመልክቶ ሙሴ የሰጠን የራሱን ሕግ ነው የሚል አይኖርም።
ምክንያቱም ቃሉ ሁሉን ምንም በማያሻማ መልኩ ያስቀምጠዋልና ነው። ለዚህ ትምህርታችን መልስ
እንዲሆን አንዳንድ ትቅሶችን ጠቀስኩ እንጂ ይህን የሚያረጋግጡ ጥቅሶች በቃሉ ውስጥ ሞልተዋል።
ሙሴ ምንም አይነት ከእራሱ የሆነ አዲስ ሕግን አላመጣም። ለሕዝቡ እንዲያስተምረው ከያሕዌ
እግዚአብሔር ሕጎቹንና ትዕዛዛቱን ለሰው ልጆች ሁሉ ተቀበለ እንጂ። ስለዚህ የሙሴ ሕግ የሚባሉት ሁሉ
የእራሱ የእግዚአብሔር ሕጎች ናቸው። በእግዚአብሔር ሕግና በሙሴ ትዕዛዛት መካከል ምንም ልዬነት
እንደሌለ ከቃሉ እንመለከታለን። የእግዚአብሔር ሕግጋት በጽላት ላይ የተጻፉት ብቻ ሳይሆኑ በሙሴ
የሕግጋት፣ የትዕዛዛት መጽሐፍት ላይ የተጻፉት ሁሉ ናቸው። ለዚህ ነው የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ
የጻፈውን፣ የሰጠኝን፣ ያዘዘኝን፣ ያሳየኝን፣ ያመለከተኝ፣ ያሳሰበኝን የሚሉ ቃላቶችን በማከል የሕግ
ባለቤትነትንና ብቸኛ ሰጪነትን ስፍራ እግዚአብሔር ለእራሱ ይወስዳል።

ሕጉ ለማንና በማን ተሰጠ?

ይህ እግዚአብሔር ሕግ የተሰጠው ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ነውን? ለዚህ መልስ


ለማግኘት እግዚአብሔር ሕግ ለማን እንደተሰጠ ከዚሁ ጋር አያይዘን በግልጽ መመልከትም ያስፈልገናል
ማለት ነው። የእግዚአብሔር ሕግ የተሰጠው ለእነርሱ ብቻ ከሆነ ደግሞ ሌሎቹ የሰው ልጆች ልዪ ሕግ
ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው። ይህ ግን ከእውነት የራቀ መረዳት ነው።
“ለእናንተ በጉባኤው ላላችሁ በእናንተም መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ሥርዓት ይሆናል፥
ለልጅ ልጃችሁም የዘላለም ሥርዓት ይሆናል እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ (በያሕዌ)
በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል። ለእናንተና ከእናንተ ጋር ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ
ሕግና አንድ ፍርድ ይሆናል።” ዘሁ.15፥15-1

ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠን አንድ ሕግና አንድም አይነት ፍርድ እንደሆነ በቃሉ በግልጽ
እንመለከታለን። ስለዚህ ለእስራኤሎች ሌላ ሕግ ደግሞ ለሌላው ሰው ሌላ ሕግ ነው የሚለውን የተሳሳተ
ሃሳብ በቃሉ መሰረት ከአዕምሯችን ልናስወግደው ይገባል። ስለዚህ በአጠቃላይ የሙሴ ሕግና
የእግዚአብሔር ሕግ የተባለው በእርሱ በኩል ለእስራኤሎች ሁሉ የመጣው ሕግና ትዕዛዛት
ከእግዚአብሔር ከእራሱ የመጣ ሲሆን ለእስራኤሎች ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆችም ሁሉ እንደሆነ ይህ
በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

www.tlcfan.org 2
መለከት #2

ሌላው ይህን ከላይ ያለውን ሁለቱን ሃሳብ ጠቅልለን ልናይ የምችልበት ቃል ደግሞ
የሚገኘው በዘሁልቁ ምዕራፍ ሃያ ዘጠኝን ላይ ነው። ይህ ምዕራፍ በሙሉ ብናነበው ሌሎቹን የተሰጡትን
ሕግጋትና ትዕዛዛት የምናገኝበትም ምዕራፍ ነው። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር በዓላት፣ ስለ
መስዋዕትና ስርየት ሕግጋቶች ተጽፎ እናገኛለን። ነገር ግን በዚህ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ የተባለውን
በደንብ በትኲረት እንድትመለከቱት እወዳለሁ። ይህ የመጨረሻ ቁጥር ላይ እንደምናየው ሙሴ ለሕዝቡ
የነገረውን ትዕዛዛት ሁሉ ያዘዘው እግዚአብሔር እንደሆነ ያረጋግጥልናል።
“ሙሴም ለእስራኤል ልጆች (ያሕዌ) እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው።” ዘሁ.29፥40
“የእስራኤልም አምላክ (ያሕዌ) እግዚአብሔር በሰጠው በሙሴ ሕግ ፈጣን ጸሐፊ ነበረ
የአምላኩም (የያሕዌ) የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ የሻውን ሁሉ ሰጠው።”
ዕዝራ.7:፥6
“በመጀመሪያውም ወር በአንደኛው ቀን ከባቢሎን ሊወጣ ጀመረ፥ መልካሚቱም የአምላኩ እጅ
በእርሱ ላይ ነበረችና በአምስተኛ ወር በመጀመሪያው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ። ዕዝራም
(የያሕዌን) የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና
ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።” ዕዝራ.7፥9-10
“ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው
በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ (ያሕዌ) እግዚአብሔርም
ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሐፊውን ዕዝራን ተናገሩት።”
ነህምያ.8፥1

“ (የያሕዌ) የእግዚአብሔርንም ሕግ መጽሐፍ አነበቡ ዕዝራም እግዚአብሔርን ማወቅ


ያስተምርና ያስታውቅ ነበር፥ ሕዝቡም የሚነበበውን ያስተውሉ ነበር። ሐቴርሰታ ነህምያም
ጸሐፊውም ካህኑ ዕዝራ ሕዝቡንም የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ። ዛሬ ለአምላካችን
(ለያሕዌ) ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ነው አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ አሉአቸው ሕዝቡ ሁሉ
የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና።” ነህምያ.8፥8-9
“በሰባተኛውም ወር ባለው በዓል የእስራኤል ልጆች በዳስ ይቀመጡ ዘንድ በከተሞቻቸውና
በኢየሩሳሌምም። ወደ ተራራ ሂዱ የዘይትና የበረሀ ወይራ የባርሰነትም የዘንባባም የለመለመውን
ዛፍ ቅርንጫፍ አምጡ፥ እንደ ተጻፈውም ዳሶችን ሥሩ ብለው ይናገሩ ያውጁም ዘንድ (ያሕዌ)
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።. . . ከምርኮም የተመለሱት
ማኅበር ሁሉ ዳስ ሠሩ፥ በዳሱም ውስጥ ተቀመጡ። ከነዌም ልጅ ከኢያሱ ዘመን ጀምሮ እስከዚያ
ቀን ድረስ የእስራኤል ልጆች እንዲህ ያለ አላደረጉም ነበር። እጅግም ታላቅ ደስታ ሆነ።
ከመጀመሪያውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት( የያሕዌ)
የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን ያህል አደረጉ በስምንተኛውም
ቀን እንደ ሕጉ የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።” ነህምያ.8፥14፣ 17-18፣ ዘሌ.23

ስለዚህ ከላይ በተከታታይ በተመለከትናቸው የእግዚአብሔር ቃሎች መሰረት ያረጋገጥነው


ሙሴ የእግዚአብሔር ሕግጋቶችን ወደ ሕዝቡ ለማድረስ የተመረጠ መልክተኛ እንጂ ሕግ ሰጪና አውጪ
አለመሆኑን ነው። እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ሕጉን ሰጠን ይህ ሕግ ደግሞ ለሁላችን ነው።
“ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው
እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ
በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ። ይህም
እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን
በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።” ሮሜ.2፥14-15

www.tlcfan.org 3
መለከት #2

ሕጉ በማን በኩል መጣ?

ሙሴ የእግዚአብሔር መልክተኛ ነው። ሕግም የመጣው በመልክተኛው በኩል ነው።


በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “አጊሎስ” የሚለው ቃል በቀጥታ በአማርኛውና በእንግሊዘኛው መጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ መለአክ ተብሎ ተተርጉሟል። የ”አጊሎስ” ትክክለኛ ትርጉሙ ግን መልክተኛ ነው። ይህን
ቃል በራእይ መጽሐፍ ላይም እናገኘዋለን። ስለ ሰባቱ ቤተክስቲያን ዬሐንስ በራእይ ምዕራፍ 2ና3 ላይ
ሲጽፍ “ወዳለው ወደ በቤተክስቲያን መለአክ( አጊሎስ)” እንዲህ ብለህ ጻፍ ሲል። ወዳለው መልክተኛ ፣
መጋቢ፣ መሪ ማለቱ ነበር። ስለዚህ ሕግ መለአክት በኩል መጣ ሲል በእግዚአብሔር መልክተኛ በሆነው
በሙሴና ከጊዜ ጊዜ በተነሱት አባቶችና ነብያቶች በኩል እንደመጣ ለመናገት እንደሆነ በቃሉ ትክክለኛ
ትርጉም መሰረት ትክክለኛ ሃሳቡን በመመልከት እንችላለን።

“በመላእክት (ከጌታ በተላኩ መልክተኛዎች) የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና


አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል
ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን?” ዕብ.2፥2, ገላ.3፥19

“ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን


ገደሉአቸው (መልክተኞች ወይም መላአክቶችን)፤ በመላእክት (በመልክተኛው ሙሴ/ በገደላችኋቸው
መልክተኞች) ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን
እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም።” ሐዋ.7፥52-53

“ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ ጽላቶቹም


በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር። ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ
ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።”
ዘጸ.32፥15-16
“እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመናው በጨለማውም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ
እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ተናገረ ምንም ምን አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ
ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጣቸው።” ዘዳ.5፥22

በእግዚአብሔር እና በሙሴ በመካከል ማንም አልነበረም። ከዚህ ተነስተን ለሙሴ ሕግን


የሰጠው እግዚአብሔር መሆኑ ባየናቸው ቃሎች መሰረት እናረጋግጣለን። ስለዚህ ቃሉ እርስ በእርሱ
ብዙዎች እንደሚሉት አይጋጭም ማለት ነው። ስለዚህም ቃሉን በትክክለኛ ትርጉም ስንተረጉመውና
ስናነበው መለአክ የተባለው ሙሴ እንደ ነበር እንመለከታልን። ጳውሎስ እራሱ እንደ መለአክት
ተቀበላችሁን ይላል ትክክለኛ ትርጉሙ መልክተኛ ማለት ነው። ገላ.4፥14 ስለዚህ በሰውና በእግዚአብሔር
መካከለኛ ሆኖ በሲና ተራራ ህጉን ሊቀበል የቆመው ሰው የሆነው የእግዚአብሔር መልክተኛ ሙሴ ነው።
እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስ አምሳል ነው።ሐዋ.7፥37 ሕዝቡም ሙሴ በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል
እንዲሆንላቸው በጠየቁት መሰረት መካከለኛ ሆኖላቸው ነበር። ዘዳ.5፥23-28 ስለዚህ ሕግ በመለአክት
በኩል መጣ ሲል በመልክተኛ በኩል ማለቱ እንደሆነ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

የሙሴ ሕግጋትና አስርቱ ትዕዛዛት

አንዳዶች አስርቱ ትዕዛዛት በእግዚአብሔር ጣት ስለ ተጻፉ ዘላለማዊ ሲሆኑ ሌሎቹ


በመጽሐፍ የተጻፉት ሕግጋት ደግሞ ጊዚያዊ ናቸው ይላሉ። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው
አስርቱን ትዕዛዛት ብቻ ሳይሆን በእርሱ ላይ ጨምሮ 603 ሕግጋት፣ ትዕዛዛትና ስርዓቶችን ሰጥቶታል።
ደግሞ ይህ እንዳለ ሆኖ ልንዘነጋው የማይገባው እግዚአብሔር ንጉስ እንደ መሆኑ መጠን ከእርሱ አፍ
የሚወጣ ቃል ሁሉ ለሰው ልጆች ሁሉ ሕግ መሆኑን ነው።

www.tlcfan.org 4
መለከት #2

ስለዚህ ሕግ ስንል ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣውን ቃል ሁሉ የሚጠቀልል ነው። ይህ


ደግሞ አባቶቻች ከቃሉ አሰባስበው ቁጥር ከሰጧቸው ከ613 ሕግጋቶች ያለፈ ነው ማለት ነው። ሰው
ደግሞ ሊኖር የተገባው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ ነው። ሰለዚህም እግዚአብሔር ደግሞ
ሕጉን በአፉ ለእያንዳዳችን በመናገር በልባችን ላይ ሊጽፈው ይፈልጋል። ይህ በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር
ለሰው ልጆች ሁሉ የገባው ተስፋ ቃል ነው።

“እርሱም (ኢየሱስም) መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር (ከያሕዌ) አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ


በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።” ማቴ.4:፥4

“ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን
በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ
ይሆኑልኛል። . . . መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው
ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ”
ዕብ. 8፥10፣ 10፥15-16፣ ኤር.31፥33

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥


የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም
ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” 2.ጢሞ.3፥16-17

“ሕዝቡም ሁሉ ነጐድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ


ሕዝቡም ባዩ ጊዜ ተርበደበዱ፥ ርቀውም ቆሙ።ሙሴንም። አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን
እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን አሉት።” ዘጸ.20፥18-19

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እስራኤላዊ ሆነ አብሮ ከግብጽ ለወጣው ድብልቅ ሕዝብ


በጆሯቸው አስርቱን ትዕዛዛት ለያንዳንዱ አሰምቷቸዋል። ሕዝቡ የሸሸው እግዚአብሔር ሌላውን ጨምሮ
እንዳይናገርና በልናቸው ላይ እንዳይጽፈው ነው። የሸሹበት ምክንያታቸውም መሞት ስላልፈለጉና ስለ
ፈሩ ነው። እውነት ሕጉ ማንኛውንም ግብጻዊ አስተሳሰብ፣ የግብጽ ሕግ፣ ስርዓትና ወግ ያመጣው ባሕሪን
የመግደል ጉልበት አለው። ሕግ የሞት አገልግሎት ይሰጣል። ይህን ቆም ብለን እስቲ እናስብ። በአንድ ቀን
እየኖራችሁና እየጠበቃችሁት የነበረው የፈርኦን ሕግ፣ ወግና ስርዓት ሁሉ በአንዴ ቢቀየር እንደ እነርሱ
ትሉ ይሆንን? ወይስ የእግዚአብሔርን ሕግ በደስታ ተቀብላችሁ ትሰሙትና ትታዘዙታላችሁ?

“ደግሞም ሌላ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ መንጎችና ላሞችም እጅግ ብዙም ከብቶች


ከእነርሱ ጋር ወጡ።” ዘጸ.12:፥38

“ (ያሕዌ) እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመናው በጨለማውም ውስጥ ሆኖ


በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ተናገረ ምንም ምን አልጨመረም።
በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጣቸው። ተራራው በእሳት ሲነድድ
ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች
ሽማግሌዎቻችሁም፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ አላችሁም። እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና
ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል እግዚአብሔርም (ያሕዌ)
ከሰው ጋር ሲነጋገር ሰውዮውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።አሁን እንግዲህ ይህች
ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን (የያሕዌ)
የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን። ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን
በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን
ነው?አንተ ቅረብ፥ አምላካችን እግዚአብሔር (ያሕዌ) የሚለውን ሁሉ ስማ አምላካችን (ያሕዌ)
እግዚአብሔርም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን እኛም ሰምተን እናደርገዋለን።
በተናገራችሁኝም ጊዜ ( ያሕዌ) እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ጽምፅ ሰማ (ያሕዌ)

www.tlcfan.org 5
መለከት #2

እግዚአብሔርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ የተናገሩህ ሁሉ


መልካም ነገር ነው።ለእነርሱም ለዘላለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥
እንዲፈሩኝ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ምነው በሆነላቸው!
ሄደህ። ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ በላቸው። አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፥ ርስት አድርጌ
በምሰጣቸውም ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዓቴን
ፍርዴንም ሁሉ እነግርሃለሁ። (ያሕዌ) እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ
ዘንድ ጠብቁ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።በሕይወት እንድትኖሩ፥
መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ (ያሕዌ)
እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።” ዘዳ.5፥22-33
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ምኞቱን ገለጠ። ምናለ እንዲህ አይነት ልብ ሁሌ
በሆነላቸው አለ። ይህም እርሱ የሚለንን ሁሉና የሚያዘንን ሁሉ እሺ ብሎ የሚሰማ ከፍቃዱ ጋር
የሚስማማን ልብ ቢኖረን ማለቱ ነው። “ወደ ድንኳናቸው ተመለሱ በላቸው” የሚለው ትንቢታዊና
ሚጥራዊ ቃል ነው። ይህ ቃል ራሱን የቻለ ለብቻው በጥልቀጥት ልንመልከተው የሚገባ ክፍል ነው።
ይህን ለሌላ ቀን ትምህርት ትቼው በተነሳንበት ጥያቄዎችና ርዕስ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ።
አስርቱ ትዕዛዝ በታቦቱ ውስጥ የሚሆኑ ሲሆን ሌሎቹ የተቀሩት ደግሞ በታቦቱ አጠገብ
ተጽፈው ይቀመጡ ነበር። ስለዚህም ምክንያት ሰዎች በውስጥ ያለው እንጂ ዘላለማዊ በታቦቱ አጠገብ
የተቀመጠው ጊዚያዊና የተሻረ ሕግጋት እንጂ ዘላለማዊ አይደለም ያላሉ። ይህም የውስጡ ከውጪ ካለው
እንደሚበልጥ ያሳያል የሚል ሃሳብም ይሰነዘራል። ይህንን ሃሳብ እስቲ ጠጋ ብለን እንመልከተው። ይህ
ሃሳብ የመነጨው በዘዳግም መጽሐፍ ከሚገኘው ቃል በመነሳት ነው።
“ይህን የሕግ መጽሐፍ ውሰዱ፥ በዚያም በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን በአምላካችሁ
(ያሕዌ) በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት።” ዘዳ.31፥26
“ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን ( ያሕዌ) እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ
የተናገራችሁን አሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ ( ያሕዌ)
እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ። ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ ጽላቶችንም በሠራሁት
ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው (ያሕዌ) እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ።” ዘዳ.10፥4-5
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትለው የእግዚአብሔር ቃል ወይም ሕግጋት በሁለት ቦታ
ተቀምጠው እንመለከታለን። ይህም በታቦቱ ውስጥና በታቦቱ አጠገብ ነው። ይህ ታዲያ የሁለቱን
መበላለጥ ለማሳየት ነው ወይስ ሌላ የሚናገረው መልክት አለው? ኢየሱስ በምድር ቆይታው
በሃይማኖተኞች የተጣመመውንና ጉልበት አልባ የደረጉትን የእግዚአብሔር ሕግ እኔ ግን እላለሁ በማለት
ትክክለኛ የስልጣንና ክብር ስፍራውን ለሕጉ ሰጥቷል። ከዚህም ባሻጋር ሰዎችን የእግዚአብሔር ሕግ
እንዲያስተውሉ በምሳሌ ሕጉን ፈትቶ አስተምሯ፣ እንደ ሕጉም ፈርዷል። የደቀመዛሙርቱን አዕምሮም
ለሕጉ መረዳት ከፍቷል። ማቴ.15 ና 23, ሉቃ.24 ስለዚህ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሰጠን እራሱ ኢየሱስ
(ያሹዋ) የተናገረው ቃል ነው።
“መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው።ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ
አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ
ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ
የምትለው ናት። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።” ማቴ.22:፥36-40
እነዚህ ሁለቱ ሕግጋት ታላላቅ ሕግጋት እንደሆኑ በኢየሱስ ተገልጿል። እንግዲህ እነዚህ
ታላላቅ ሕግጋት እግዚአብሔር (ያሕዌ) መውደድና ባልጀራችን መውደድ ናቸው። እነዚህ ሕጎች የት ነው
የሚገኙት? እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ። ይህ በአስርቱ ትዕዛዛት ላይ ይገኛልን?
“አንተም አምላክህን (ያሕዌ) እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም
ኃይልህ ውደድ።” ዘዳ.6:፥5

www.tlcfan.org 6
መለከት #2

“አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ እኔ


እግዚአብሔር (ያሕዌ) ነኝ።” ዘሌ.19፥18
እነዚህ የእግዚአብሔር ሕግጋት በአስርቱ ውስጥ አይገኙም። ይልቁንም የሚገኙት የሙሴ
ሕግ ተብሎ በተጠቀሰው በታቦቱ አጠገብ በሚገኘውና በሚቀመጠው የእግዚአብሔር ሕግጋት መጽሐፍ
ውስጥ ነው። ስለዚህ ደግሞ አሁን ተነስተን በኢየሱስ ታላላቅ የተባሉት ሕጎች በጭ ስላሉ የውጩ
ይበልጣል እንበልን? በፍጹም አንሳት። የእግዚአብሔር ሕግ በውስጥም ሆነ በውጭ ቢቀመጥ ፈጽሞ
ጊዚያዊ አይደለም፣ አንዱም ከአንዱ አይለይም። በውጭም ሆነ በውስጥ ያሉት ሕግጋት ፍቅር በሆነው
በእግዚአብሔር የተጻፉ ናቸው። በመጽሐፍ የተጻፈውና በታቦቱ ፊት የተቀመጠው አስሩን ትዕዛዛት
በዝርዝር ለማስተማር ብቃትን ለሚሰጥ ወይም የሚያብራራ ነው። ። ሁለቱን ሕግጋት ያዘጋጀው
እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ ያለውን እንስማና ይንንን እናረጋግጥ፦
“(ያሕዌ) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን እነርሱን ታስተምር
ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው።” ዘጸ.24፥12
እግዚአብሔር ለሙሴ በድናጋይም ሆነ በመጽሐፍ የተጻፉትን ሕግጋቶች ሰጥቶታል።
በከበረው ድጋይ ጽላት ላይ የተጻፈው የእግዚአብሔር ሕግ አስር ሲሆኑ እነርሱን ለሁለት ከፍለን
ብንመለከትው ደግሞ በኢየሱስ ከሙሴ ሕግጋት መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት ሁለቱ ታላቅ ሕጎች ጋርም
አንድ ሆነው እናገኛቸዋለን። ይህ በራሱ የሁሉንም ሕጎች አስፈላጊነትና አንድ መሆናቸውን ያሳያል።
የሕጉ ተመሳሳይ ነገሮች በኢየሱስ ዋንኛ ተብለው ተጠቅሰዋል። እነርሱም ፍርድ፣ ምሕረትና ታማኝነት
ናቸው። እነዚህም በሙሉ የሚመነጩት ከፍቅር ነው። ማቴ.23፥23
በዘጸአት ሃያ ላይ ያለውን የእግዚአብሔር አስርቱን ትዕዛዛት ከ1ኛው ሕግ እስከ 4ኛው ሕግ
እግዚአብሔር ስለመውደድ ሲሆን ከ5ኛው ሕግ እስከ 10ኛው ሕግ ደግሞ ባልጀራችንን ስለ መውደድ
የሚናገር ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕግ በታቦቱ ውስጥ ሆነ ውጭ የሚሰጠው መልክት ፍቅር ነው።
ምክንያቱም ሁለቱም ሕግጋት የመጣው ከአንዱ ፍቅር ከሆነው ከእግዚአብሔር ስለሆነ ነው። ደግሞም
በእነዚህ በሁለቱ ሕግጋቶች ላይ ሁሉ ሕጎችም ሆኑ ነብያት ተንጠልጥለዋል። ይህም ተወግደዋል ማለት
ሳይሆን የክብር ስፍራቸውን ይዘዋል፣ ከፍ ብለው ተሰቅለዋል ማዕረጋቸውን አግኝተዋል ማለት ነው።

“በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።” ማቴ.22፥40

ሌላው ደግሞ ኢየሱስ (ያሹዋ) በተፈተነ ወቅት ለሰይጣን የመለሰውና ሰይጣንን ድል


የነሳው እነዚህን የተጻፉትን ሕግጋት በመጠቀምም ነበር። ኢየሱስ ለሰይጣን ከአስርቱ ትዕዛዛት አንድ ሕግ
እንኳን አልጠቀሰለትም። ኢየሱስ ሰይጣንንና ሃጢያትን እንቢ ለማለት የጠቀሰውና የተጠቀመዉ የሙሴ
ሕግ በመባል ከሚታወቀውን ከእግዚአብሔር ሕግጋቶች ነው። አስተውሉ ይህንንም አትርሱ በኢየሱስ
ታላላቅ ሕግጋት የተባሉት ፈጽሞ በአስርቱ ትዕዛዛት ውስጥ አይገኙም። ደግሞም የእግዚአብሔር ሁሉም
ሕግጋቶች ጠላትን ለማንበርከክ ሆነ አመጽን ለመቃወም እውነተኛ መሳሪያ ነው።

እኛስ ዛሬ የኢየሱስን ፍለጋ መከተል አለብንን? ወይስ የራሳችንን አዲስ ሕግና ስርዓት
መፍጠር ያስፈልገናልን? ከእግዚአብሔር ሕግ የምንፈልገውን በመውሰድ ሌላውን መተው አለብን?
መልሱን ለእናንተ ተዋለሁ። ኢየሱስ ግን በጊዜው ለሚከተሉት ሕዝብና ለደቀመዝሙርቱ ያስተማረውን
ትምህርት እንመልከት።

“በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው።ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ


ወንበር ተቀምጠዋል። ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ
አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።” ማቴ.23፥1-3

www.tlcfan.org 7
መለከት #2

ኢየሱስ በሙሴ ወንበር የሚለው በሙሴ ሕግጋት የሚለውን የሚተካ ነው። እነዚህ ጻፎችና
ፈሪሳዊያን የሚናገሩት ትክክል የሆነውን ዘላለማዊውን የእግዚአብሔር ሕግ ነው። ችግራቸው
የተናገሩትን አለመኖር፣ የሰበኩትን ሆኖ አለመገኘት ነው። ችግሩ እነርሱ እንጂ የእግዚአብሔር ሕግ
አልነበረም። ኢየሱስ የሚሏችሁን ስሙት ደግሞም እናንተ እንደ እነርሱ አትሁኑ! የሚሏችሁን መስማት
ብቻ ሳይሆን አድርጉትም አላቸው። ስለዚህ በኢየሱስ ትምህርት መሰረት በሙሴ በኩል የመጣውን ሕግ
ሁሉ መታዘዝ አለብን? አዎን አለብን። ይህ ከማንም የመጣ ትምህርት አይደለም። ከእርሱ ከኢየሱስ
ክርስቶስ የመጣ እርሱን እከተላለሁ የሚል ሁሉ ሊኖርበት የተገባ ትምህርት ነው።
ስለዚህ በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ሕግ ከሙሴ ሕግ ፈጽሞ የሚለያይ አይደለም።
በታቦቱ ውስጥና ውጭ ያለውም ሁለቱም ሕግጋቶች በጥቅሉ 613ቱ የተጻፉልን ሕግጋቶች ዘላለማዊና
እኩል ክብር ያላቸው ናቸው። ይህ ባይሆን ኖሮ ኢየሱስ ታላላቅ ሕጎች ብሎና እንድንጠብቃቸውና
እንድንታዘዛቸው ባላስተማረንም ነበር። ሙሴ ሁሉ ያደረገው፣ ሁሉን ያስተማረው፣ ሁሉን ያዘዘው
እግዚአብሔር የጻፈውን፣ ያዘዘውን፣ያሳየውን፣ የተገለጠለትንና ያሰማውን ብቻ ነው። ዘጸ.25፥9

“እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ


የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ
ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና።” ዕብ.8፥5

የማደሪያው ድንኳን ሶስት ክፍል ሲኖረው ቅድስተ ቅዱሳን ታቦቱ የሚገኝበት ሰፍራ
ነው። ሁለቱ ሕግጋቶ ማለትም በጽጋይም ሆነ በመጽሐፍ የተጻፉት ሕግጋቶች የሚገኙት እዛው ክፍል
ውስጥ ነው። ይሁንና አስተውለን ስንመልከተው ሁለቱም በቅድስተ ቅዱሳን ክፍል ውስጥ የተጠቀለሉና
አንድ የሆኑ ናቸው። ታቦቱም ሆነ ቅድስተ ቅዱሳን በሰው ልጆች ልብና መንፈስ የሚመሰል ነው።
እግዚአብሔር ደግሞ ሁል ጊዜ ሕጉን በቅድስተ ቅዱሳን በውስጥና በውጭ እንዳስቀመጠው ሕጉ
በመንፈሳችንና በነፍሳችን ላይ እንዲቀመጥ ወይም እንዲጻፍ ይፈልጋል።
“እንግዲህ እነዚህን ቃሎች (በታቦቱ ውስጥ) በልባችሁና(መንፈስ) በነፍሳችሁ (ከታቦቱ
ውጭ) አኑሩ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል
እንደክታብ ይሁኑ።” ዘዳ.11፥18

“ነገር ግን ታደርገው ዘንድ ቃሉ በአፍህ( ውጭ)ና በልብህ ውስጥ ለአንተ እጅግ ቅርብ ነው።” ዘዳ.11፥18

“ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር ሕጌን
በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።”
ኤር.31፥33

“በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ። አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።”


መዝ.119፥10-11

ስለዚህም ሙሴ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ሲገባ የሚያገኘው እግዚአብሔርን፣


የእግዚአብሔር ፍቃድ፣ አዕምሮና ድምጽ ነው። የክርስቶስ አዕምሮም ከዚህ የሚለይ አይደለም። ሰው
ቅድስተ ቅዱሳንን ሲገባ የእግዚአብሔር ፍቃድንና ድምጽ ያገኛል። የእግዚአብሔር ሕግጋት በኢየሱስ
ክርስቶስ ያለ የእግዚአብሔር ፍቃድ፣ ልብና ሃሳብ ነው። እኛም ይህ ሕግ በልባችን ላይ ሲጻፍ የክርስቶስ
አዕምሮ አለን ማለት እንችላለን። ይህ በኢየሱስ የነበረ ከሕጉ የመጣ ወይም የተገኘ ሃሳብ በእናንተም
ዘንድ ይኑር የሚለው የጳውሎስ መልክትም ነው። ፊሊ.2፥5 ይህ ደግሞ በእኛ ሕይወት እንዲሆን ወይም
እንዲፈጸም የግድ የልብ መገረዝ ሊመታብን የግድ ያስፈልጋል። ይህን ደግሞ ሊያደግ እግዚአብሔር እራሱ
እንዲህ ብሎ ቃል ገብቶልናል፦

www.tlcfan.org 8
መለከት #2

“ሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ (መንፈስ)


በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ አምላክህ እግዚአብሔር ልብህን የዘርህንም ልብ
ይገርዛል።” ዘዳ.30፥6

ማወቅ ያለብን የተሻረው ሕግ ሳይሆን ኪዳን ነው። አሮጌው ኪዳን እኛ እንድናደርግ


ነበር የሚያዘው። አዲሱ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ሕጉን በልባችን ላይ መጻፍ ብቻ ሳይሆን በትዕዛዛቱ
እርሱ እራሱ ያስኬደናል። ይህንም ለማድረግ እግዚአብሔር እራሱ ልባችንን የገርዛል። መታዘዝ ከልብ
እንደሚጀምር ነው። ሕግጋቱ ሁሉ የተቀመጡት በማደሪያው ድንኳን ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ
ነው። ይህ ግን የሆነው ቁጭ አድርገን በግድግዳ ላይ ሰቅለን እንድናየው ሳይሆን እንድንታዘዘው ነው።
“ነገር ግን ታደርገው ዘንድ ቃሉ (ውጭ) በአፍህና በልብህ (ውስጥ) ለአንተ እጅግ ቅርብ ነው።”
ዘዳ.30:፥14

“ከሁለተኛውም መጋረጃ ወዲያ ቅድስተ ቅዱሳን የምትባለው ድንኳን ነበረች፥በዚያም ውስጥ የወርቅ
ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት
የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥” ዕብ.9፥3-4

ዛሬ ብዙዎች ሰዎች ሕግን ለማውገዝ፣ ለመሻር፣ ለመቃወም፣ ለማፍረስ፣ ላለማስተማር. .


. ወዘተ የሚጠቀሙት የጳውሎስን ጥቅሶች ነው። የዳንኤልን ትንቢትንም ብዙዎች ዘንግተዋል። ዳን.7፥
25 ሌላው የሚገርመው ደግሞ ሕጉንና ትዕዛዛቱን በሚቃወሙበት አንደበታቸው ደግሞ የሚፈልጉትን
እንደ አስራትና መባ የመሳሰሉትን ሕጎች ደግሞ ተከተሉት እያሉ ያስተምራሉ ያስፈራራሉ!!! የጳውሎስን
መልክቶች እርሱ ከጻፈበት መንፈስ ውጭ በማጣመም መረን የሚያወጣን አመጽን የሚዘራን ሃሳብ
በትውልድ መካከል ያስተምራሉ። ይህን ሲያደርጉ ደግሞ ራሳቸውን ከኢየሱስ ትምህርት፣ ከሐዋርያት
ትምህርት፣ ከነብያት ትምህርቶችና ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ሲያጋጩ እናገኛቸዋለን። ጳውሎስ የኢየሱስን
ምሳሌነት እደሚከተልና እኛም የእርሱን ምሳሌ እንድንከተል ይነግረናል። ጳውሎስ በመልክቶቹ ሁሉ ሕጉ
በልባችን እንዴት፣ ለምን እንደሚጻፍም ጠለቅ ያለ ማብራሪያንም ይሰጠና።
“እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። ( Follow my example, as I follow the
example of Christ)” 1.ቆሮ.11፥1

“ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል። በልብህ። ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ


ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ወይም። በልብህ። ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን
ለማውጣት ነው።ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም (በመንፈስና ነፍስ) ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም
የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።” ሮሜ.10፥6-8

በመጨረሻ አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ፦ አንድ ብርቱካን ብትዘሩ ዛፉን ቀድማችሁ


ትተክላላችሁን ወይስ ሁሉን ዛፍ ሊሰጠን የሚችለውን ፍሬውን። እርግጠኛ ነኝ ፍሬውን ወይም ዘሩን
እንደምትሉኝ። ዘሩ ምንም እንኳን በጣም ትንሽ ቢመስል ሁሉንም ዛፍ በውስጡ ጠቅልሎ እንደያዘ
መረዳት አያዳግትም። እግዚአብሔር ዘር የሆነው ቃሉንና ሕጉን በልባችን ይጽፋል። ያን ጊዜ እውነተኛ
የሆነ ከእምነት የሚገኝን መታዘዝ ለእግዚአብሔር በውስጣችን እንደ ዛፍ ያድጋል ፍሬንም ይሰጣል።

“ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት
አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ
ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ
ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ
መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤በእነርሱም መካከል
የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ።” ሮሜ.1፥1-6

www.tlcfan.org 9
መለከት #2

“የሰውንም (አዳማዊና የማይታዘዝ አመጸኛ) አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት (ሕግ፣ ትዕዛዝ፣


ፍቃድ፣ ቃል) ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ
አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል
ተዘጋጅተናል።በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ። ማንም የክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ ቢሆን፥
ይህን እንደ ገና በራሱ ይቁጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ ነን።”
2.ቆሮ.10፥7
“ቀንም ቀጥረውለት ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያው ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ እግዚአብሔር
መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት ጠቅሶ እያስረዳቸው፥
ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ይገልጥላቸው ነበር።” ሐዋ.28፥23

ሐዋርያው ጳውሎስ ብዙዎች እንደሚያስተምሩት የእግዚአብሔር ሕግን አልሻረም። ይህ


ክስ በእርሱ ላይ በፊትም በአባቶች ዘመን ቀርቦበት ነበር። ጳውሎስ የሻረው ወይም የጣሰው ሰውና
ሃይማኖት ሰራሽ ወግ፣ ስርዓትንና ከኪዳኑ ጋር አብረው የተቀየሩትን ትእዛዝ ነው። የእግዚአብሔር
ሕግጋትን ጳውሎስ ፈጽሞ ሁሉንም አልሻረም። ይህንንም ደግሞ ያደረገው የኢየሱስን ፈለግ በመከተል
ነው። ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ያለውን ከእራሱ ቃል ተመልከቱ፦ (ሮሜ.3:፥31, 6፥16, 7፥7፣ 22፣
25,8፥4፣7,፣ 1ቆሮ.10, ዕብ.3ና4፣ 5፥14,7፥15-28, 8፥4-13, 9ና10 ) በሙሉ ያንቡቧቸው።
ሕግ የተሰጠው ለምንድ ነው?
እግዚአብሔር የመለኮታዊ የእግዚአብሔር ሕግ አላማ ትክክልና ትክክል ባልሆነው መካከል
መለየት ነው። ሕግ ሃጢያትን ምን እንደ ሆነ ያብራራል። እውነትን ከውሸት ይለያል። ከዛም ፍርድን
በመበየን ትክክል ያልሆነውን ያስወግዳል ወይም ያስተካክላል። ሕግ ሃጢያተኛ ካልሆኑና ሃጢያት ካልሰሩ
በቀር በማንንም ላይ አይፈርድም ወይም ማንንም አይኮንንም። ነገር ግን ሁሉ ሃጢያትን ሰርተዋል
የእግዚአብሔርም ክብር ጐሏቸዋል ያላል። ሮሜ 3፥23 ስለዚህ ሕግ ለማዳን ወይም ለማጽደቅ አላማ
እንዳልተሰራ ለሁላችን ግልጽ ነው። ይሁንና ሕጉ እግዚአብሔር ሃጢያት ምን እንደ ሆነ የሚያሳውቅበትና
ሕይወት የሚገኝበት ቃል ነው።
“ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤
ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።” ሮሜ.3፥20,7፥7
እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝበ እስራኤል ሕጉን ሲሰጥ የጀመረው አስርቱን ትእዛዛት
በመስጠት ነው። እነዚህ ትዕዛዛት የተሰጡት ሙሴም ሆነ ሕዝቡ እንዲታዘዙትና እንዲያደርጉት ነው።
ይህም እግዚአብሔርን የመታዘዝ ለሕዝቡ የቀረበ ፈተና ነው። ማንም እስራኤላዊ ጣዖት እያመለከ፣
ዝሙት እየሰራ እየሴሰነ፣ ጎረቤቱንና ወንድሙን እየሰረቀ፣ ቤተሰቦቹን እያዋረደ፣ እየዋሸ፣ በሃሰት
እየመሰከረ፡ እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ ሊል አይችልም። ስለዚህም ሌላው ደግሞ ሕጉ የተሰጠበት ሌላው
አላማ የእግዚአብሔር ባሕሪ ለመግለጥና ከሰው ምን እንደ ሚጠበቅ ማስረጃን ለመስጠት ነው።

ሌላው ደግሞ የሕግ አላማ ለሰው እግዚአብሔር እንዴት እንደሚፈርድ ለማሳየትና


ትክክለኛ ፍርድን ባሪያዎቹ እንዴት በሕዝቡ መካከል የእርሱን ፈለግ ተከትለው ፍርድን ለማምጣት
እንዲችሉ ለማስተማርም ነው። ሕግ ከሌለ ፍርድ የለም። ፍርድ ካለ ደግሞ ሕግ ይኖር ዘንድ ግድ ነው።
የሌባው ፍርድ፣ የአመንዝራው ፍርድ፣ የባለ እዳው ፍርድ የመሳሰሉትን ሁሉ የሚፈረደው በሕጉ መሰረት
ነው። እግዚአብሔር ከዚህ ውጪ የሃጢያት ፍርድን የሚመዝንበት የሚበይንበት ሌላ ሕግ የለውም።
ስለዚህ ሕግ ከሌለ ፍርድ ፈጽሞ እንደማይኖር እንወቅ። ሕግ ተሽሯል ሲሉን ቀጥለውም ምን እያሉ
እንደሆን እናስተውል!! ሰው የሕግ አላማ ምን እንደ ሆነ ጠንቅቆ ካላወቀ በተለያዮ የተሳሳቱ መረዳቶች
ላይ ሊወድቅ ይችላል። አሁንም ደግሜ እላለሁ ስው ሕግን በመጠበቅ ሊጸድቅ ፈጽሞ አይችልም።
ስለዚህ ሁሉ ምክንያት እግዚአብሔር ሕግን ለአማኙ እንዲጠብቀውና እንዲታዘዘው ተሰጥቶታል።

www.tlcfan.org 10
መለከት #2

“21 አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥


22 እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር
ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ 23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር
ጎድሎአቸዋል፤ 24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
25 እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤
ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ
ዘንድ ነው፥ 26 ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ
ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው። 27 ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል።
በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። 28 ሰው ያለ
ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና። 29-30 ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ
ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት
ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው። 31
እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።”
ሮሜ.3፥21-31

ሕግ አላማ የለውም፣ አያስፈልግምና ሊሻር ይገባዋል ማለት ፈጽሞ የተሳሳተ መረዳት


ነው። እንደውም ሕግ በእምነት እግዚአብሔር በመስማት ይጸናል። ሕጉ ታላቅ አላማ አለው። ሕጉ
የመንግስቱ አንዱ መሰረት ነው። እግዚአብሔር ሕጉን በግብጽ ሳይሆን ከግብፅ አውጥቶ በምድረ በዳ
ለሕዝቡ እንደሰጠ ዛሬም ለእኛ እንዲሁ ነው። ሕግ ማንም አያጸድቅም ስንል ማንንም ከግብፅ፣ ከሞት
ባርነት፣ ከሃጢያት ነጻ አያወጣም ማለታችን ነው። ምክንያቱን ሕዝቡ ከግብፅ እንዲወጡ ያስቻላቸውና
ሞት ወደ እያንዳዳቸው ቤት እንዳይገባ ያደረገው በእነርሱ ፋንታ በሞተው ሕያው በግ ደም የተነሳ ነው።
ይህ የኢየሱስ ደም ጥላ ነበር። ሁሉ በእምነት ይህን ደም በመቃናቸው ላይ በመቀባታቸው ከሞት
አመለጡ። ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገራቸው ሞት እነርሱን አልፎ እንዲሄድ ያደረገው የበጉ ደም የኢየሱስ
ደም ነው። ዕብ.11፥28 መቃኑና ጉበኑም በአዲስ ኪዳን ልብን፣ ሕሊናንና ሁለንተናን የሚተካ ነው።

ለእኛ በዚህ በመጨረሻ ዘመን ላለን የፋሲካ በግ አለን። እርሱም ስለ እኛ ደሙን


በመስቀል ላይ ያፈሰሰልን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህን ደም ይህን የመስቀሉን ሥራ በእምነት
ካልተቀበልን ከሞት ወደ ሕይወት መሻገር ወይም መጽደቅ ፈጽሞ አንችልም። 1.ቆሮ.5፥7,8, ዮሐ.1፥29,
ኢሳ.53 ሁላችን በምድር ላይ ያለን የሰው ልጆች ሁሉ ሃጢያትን ሰርተናል። ከዚህ ሃጢያታችን የተነሳ ሞት
ይገባናል። ምክንያቱም የሃጢያት ደሞዝ ሞት ነውና። ሮሜ.6፥23 ነገር ግን እግዚአብሔር ገና ሃጢያተኞች
ሳለን ስለ ወደደን በእራሱ ሕግ ከእኛ ሥራ ሳይሆን ከእርሱ ፍላጎት የተነሳ አንድ ልጁ ስለ እኛ በመስቀል
እንዲሞት ሰጠን። ዛሬም እርሱ በላከልን ስጦታ በሆነው በውድ ልጁ በኢየሱስ የምናምን ሁሉ በኢየሱስ
ደም እንዲሁ ያለ ምንም ስራ በእምነት ብቻ ከሃጢያታችን ያነጻናል ያጸድቀናል። ይህም ቀድሞ የተደረገን
ሃጢያት ሁሉ በእግዚአብሔር ችሎታ መደምሰስ ፈጽሞ በልጁ ደም ሃጢያታችንን ከእኛ ላይ አጥቦ
በማስወገድ ነው። ይህ ከእኛ ሥራ የሚገኝ አይደለም። ስለዚህ በራሳችን የምንመካበት ምንም ነገር
የለንም። ነገር ግን እርሱ የሰራልን ሥራ ብቻ በትህትናና በደስታ በመቀበልና በማመን የሚገኝ
የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው።

ፋሲካችንን ኢየሱስ ካመንን በኃላ ወይም ከጸደቅን በኃላ መንፈሳዊ እድገታችን ወይም
መዳናችን እዛጋር አያበቃም። ዘጸ 12 ላይ እንደምንመለከተው ደሙን በእምነት በመቃናቸው ካደረጉ
በኃላ በዚያ አላቆሙም። በጌታ መሆን የጌታ አያደርግም። በቤታቸው ውስጥ የፋሲካውን በግ ስጋ
በእሳት ጠብሰው ማለዳ እስኪሆንላቸው ማለት ብርሃን እስኪበራላቸው ድረስ ጨርሰው በሉት።ዮሐ.6
ይህ ከሞት ካመለጥን ወይም ከዳንን በኃላ ወዲያው የሚቀጥል የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የዳኑ ሁሉ ሰዎች
ተግባር ሊሆን የሚገባው ነው። ከዚያም ሕጉን ወደ ምንቀበልበት ያወጣናል። ሆሴ.2፥16

www.tlcfan.org 11
መለከት #2

ይህን የበጉን እራስ፣ እግርና የሆድ እቃ ስጋ በእሳት ጠብሰን በመብላት ከግብፅ


እንወጣለን። ከዛም በቀይ ባሕር ጥምቀትን ተጠምቀን ለሕጉ በጎ ሕሊናን እንቀበላለን።
(ዘጸ.12,1.ቆሮ.10፥1-2, 1ጴጥ.3፥20-21) በዚያም ሕጉን እንቀበላለን። ያኔ የፈርኦን ሳይሆን የጌታ
እንሆናለን። ምድረ በዳው ደግሞ የእግዚአብሔር ሕግ በልባችን የሚጻፍበት፣ የሚነገርበት፣
የምንፈተንበትና የምንሰለጥንበት ጊዜና ስፍራ ነው። እንግዲህ ሕጉ የተሰጠው በግብፅ ካልሆነ የሕግ
አላማ ሕዝቡን ከሞት ወደ ሕይወት ለማምጣት፣ ለማጽደቅ ወይም ከግብፅ ለማውጣት እንደማይሆን
በግልጽ መመልከት እንችላለን።
ከሞት የሚያድነን ደሙ በእምነት መቀበል ሲሆን ከግብጽ የሚያወጣን ደግሞ
በመንፈስ ቅዱስ እሳት በመጥበስ (መገለጥ) ስጋውን መብላት ነው። “ቃል ሥጋ ሆነ” ዮሐ.1፥14 ተብሎ
እንደ ተጻፈ የምንበላው ሥጋ የኢየሱስ ፍጥረታዊ ሥጋ ሳይሆን የሕይወት ቃሉን የአፉን ቃል ነው።
ሐዋርያት ይህ እውነት ገብቷቸው ነበር። ነገር ግን ዛሬም ሆነ ያኔ ይህ ሚስጥር ያልገባቸው የሚሰናከሉ
ብዙ ደቀመዛሙርቶች አሉ። ዮሐ.6፥52-69 ሕጉ አላማ ያለውና መዳናችንን ለመፈጸም አስፈጊ ነው። ነገር
ግን ሕግ ከሞትም ሆነ ከዓለም ማለት ከግብፅ አያወጣንም። ሕግን ጠብቄ ከሞት ድኛለሁ ብሎ በሥራው
ሊመካ የሚችል ሰው አንድስ እንኳን ሰው ሊኖር አይችልም። ከሞትና ከአለም ለመዳናችን ትምክህት
ቢያስፈልገን በመስቀል ላይ ስለ እኛ የሞተውና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድጎ የተነሳው በክብር አርጎ
በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው ዳግም በመንግስቱ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። የሚመካ በጌታ
ይመካ።
“ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን
ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።” ገላ.6፥14

የሕጉ አላማዎች ምን እንደ ሆኑ፦ ሕጉ በጣም አስፈላጊ እንደ ሆነ በይበልጥ ማወቅ


ከፈለግን ከሞት በደሙ ጸድቀው ቃሉን በመንፈስ በመብላታቸው ከግብፅ ወጥተው በቀይ ባሕር
ተጠምቀው ምድረ በዳ የወጡትን ሕዝብ ሕይወት በቅርበት መለከት ይግባናል። ሕጉ የተሰጠው ቀይ
ባሕርን ከተሻገሩ ምድረ በዳ ከገቡ በኃላ መሆኑን አስተውሉ። እንግዲህ የሕጉ አላማ የሚፈጸመውም
ከዚያ ስፍራ ጀምሮ ነው። በደሙ የሆነው እምነታችን ከሞት ወደ ሕይወት መሻገራችን በምድረ በዳ
የምንቀበለውን ሕግ ያጸናዋል እንጅ አይሽረውም። እምነት በሕግ ወይም በስራ ይጸናል። ያቆብ.2፥26

ሕጉ በውስጣችን የተሰወረውን የግብጽ ባሕሪ የምንመለከትበት መነጽር ነው። ሕጉ


አዳማዊ ሕግን የምሰብርበት ወይም የምንገድልበት ሰይፍ ነው። ሕጉ ከግብፅ ከወጣን በኃላ
ከወንድሞቻችን ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን የምንማርበት ነው። ሕጉ ጠላታችንን እንዴት መዋጋት
እንዳለብን የምንማርበት ነው። ሕጉ ከጥምቀት በኃላ ለሚፈጸሙ የግል ሃጢያቶች ፍርድን
የምንበይንበት ወይም በንስሃ ራሳችንን የምናስተካክልበት ነው። ሕጉ እግዚአብሔር እንዴት ማምለክ
እንዳለብን የምንማርበት ነው። ሕጉ ወደ ልጁ መልክ እንዴት መምጣት እንደምንችል የምንማርበት
ነው። ሕጉ እግዚአብሔር አሁንና በነጩ ዙፋን ፍርድ እንዴት እንደሚፈርድ የምናውቅበት ነው። ሕጉ
ትንቢታዊና ዘመንንም የምናውቅበት ነው። …ወዘተ በአጠቃላይ ሕጉ ሕዝበ እስራኤል በምድረ በዳ
ከእግዚአብሔር የተማረውን ሁሉ ነገር የምናደርግበትና ወደ ከንዓን ወደ ተሰፋይቱ ምድር ወደ እርሱ
እረፍት ለመግባት ታላቅ ዝግጅት የምናደርግበት ታላቁ የእግዚአብሔር መርህ ነው። ሕይወት
የሚገኝባቸውን የእግዚአብሔር ሕግ ያልሰማ ያልታዘዘ ፈጽሞ ዮርዳኖስን አይሻገርም። ነገር ግን ከሞት
ወደ ሕይወት በደሙ ተሻግሯል። አንደኛውን እድገት ፈጽሞ ወደ ሁለተኛው ገብቷል በሶስተኛው ክፍል
ግን ፈጽሞ አይገባም ወይም አይገኝም። ሕግ የተሰጠበት አላማና አጠቃቀሙ ወደፊት ከዚህ ቀጥሎ
በምንማራቸው ትምህርቶች የበለጠ እየተብራራና ግልጽ እየሆነ ይመጣል። (Gal።3፡24 Wherefore the
law was our schoolmaster to bring us unto Christ, that we might be justified by faith.)

www.tlcfan.org 12
መለከት #2

www.tlcfan.org 13

You might also like