03.

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 12

መለከት #3

3
www.tlcfan.org 0
መለከት #3

አስሩ ቃሎች (አሰሬት ሃ ሚትስቮት)


አስርቱ የእግዚአብሔር ሕግጋት በዕብራይስጡ አስሩ ቃሎች ፣አስሩ አዋጆች ፣ አስቱ የቃል
ኪዳን ቃሎች በመባል ይታወቃሉ። እስጢፋኖስ ደግሞ ሕይወት ያለባቸው ቃሎች ብሎ በመንፈስና በጸጋ
ተሞልቶ ሰለ ሕጉ ይመሰክራል። በዘፍጥረት 26፥5 ላይ የምናገኘው ቃል ላይ አብርሃም ትዕዛዛቴን
ጠብቋል የሚለው ቃል ላይ የምናገኘው ቃል በዕብራይስጡ አሰሬት ሃ ሚትስቮት የሚለውን ነው።
ከዘጸ.16፥28፣ ዘሌ.25፥14 ጋር እንዲሁም ከታች ከዘረዘርኳቸው ጥቅሶች ጋር አነጻጽረን ይህን እንደሚል
መመልከት እንችላለን።
“ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በማኅበሩ ውስጥ
የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ ሕይወት ያላቸውን ቃላት ተቀበለ፤” ሐዋ.7፥38
“በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም
አልጠጣም። በጽላቶቹም አሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።” ዘጸ.34፥28
“ታደርጉትም ዘንድ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን አሥሩን ቃላት ነገራችሁ በሁለቱም በድንጋይ
ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።” ዘዳ.4፥13
“ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ
የተናገራችሁን አሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ
እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።”ዘዳ.10፥4

አብዛኛው ሰው እግዚአብሔር 10ቱን ትዕዛዛት በሲና ተራራ ላይ ለሕዝበ እስራኤል እንደ


ሰጣቸው ያምናሉ። ዘጸ.20፥1-17 ይህ የተፈጸመው ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ ባርነት ነጻ ከወጡ ከሁለት
ወራት በኋላ ነው። ለእኛም ከግብጽ (ከአለምና ስይጣን) ግዛት የወጣንና ወደ ምድረ በዳ ፈተናና
ልምምድ ውስጥ የገባን የትምህርታችን መጀመሪያ የሚሆነው ይህ ሕግና ስርዓት ነው።

ሕጉንና ትዕዛዛቱን በስድስት ከፍለን መመልከት


እግዚአብሔር ሕግጋትን እንደ ሕዝበ እስራኤሎች ዘመን ከፋፍሎ መመልከት ትክክለኛ
የሆነ የሕግጋቱን ትርጉምና አፈጻጸም በቀላሉ ለማወቅ ይረዳናል። የእግዚአብሔር ሕግ ከግብጽ ወጥቶ
ምድረበዳ ለገባው ሕዝብ ሆነ ለነብያትና ሐዋርያት ኢየሱስን ለሚከተሉት ሁሉ መሰረት ነበሩ።
(1ኛ ) Laws— ሕግ ፣ ትዕዛዝ በሰጪው የተወሰኑ ስራዎችና ምግባሮች…
(2ኛ) Statutes— በሕግ ሰጪው የታደሱ ሕጎችና ትዕዛዛቶች / መስዋዕቶች፣ክህነት…
(3ኛ) Judgments— በሕጉ የሆኑ ፍርዶች፣ ቅጣቶች፣ ውሳኔዎች…
(4ኛ) Ordinances—በሕጉ የሆኑ በዓላት፣ የመቅደሱ ሕግጋት፣ የካህኑ፣ የአገጋልጋዮ…
(5ኛ) Precepts— ትምህርቶች፣ ስለ ውጊያ፣ ስልጣን፣ ስለ ምድርና መርህ የሆኑ ሕጉች…
(6ኛ) Covenants— ቃልኪዳኖች፣ ስምምነቶች፣ በሁለት ወገን የሚደረጉ ውሎችና ሕጎች

በዚህ መልኩ ከፋፍለን ሕግጋቱን ማየት እንችላለች። ሌላው ደግሞ ልናውቀው የሚገባው
የእግዚአብሔር ሕግ ትንቢታዊ ነው። ሕጉ ለመጪው ዘመን የሚሆነውንም የሚናገር፣ የሚያስተምርና
የዘመናትን ትንቢታዊ በጥላነት የያዘ ነው። ጥላውና መጋረጃው ተገፎለት ወደ ውስጥ ማየትት የቻለ
ወይም ሕጉን እንዲያሰተውል በጌታ አዕምሮ የተከፈተለት አማኝ ሁሉ እነዚህን ትንቢቶችን ማየት
ይችላል። ነብያት የሚናገሩትንም ትንቢቶች የምንመረምለው በእግዚአብሔር ጣት በተጻፉት እና
በእግዚአብሔር በተሰጡት ሕግጋት ነው። ከእግዚአብሔር ሕግጋት ጋር የማይስማማ ማንኛውም
ትንቢትና ራእይ ፈጽሞ ከእግዚአብሔር አይደለም። የእግዚአብሔር ሕግጋትን ትንቢታዊነት
በትምህርታችን እየገፋን ስንሄድ ግጽ ሆኖ እናየዋለን።

www.tlcfan.org 1
መለከት #3

ከሲና በፊት ሕጉ ለአባቶች ተሰጥቶ ነበርን?

ሕጉ በሙሴ በኩል ከመምጣቱ በፊት ለአባቶቻችንም ተገልጦላቸው እንደነበር


ከእግዚአብሔር ማየት እንችላለን። አዳም ከእግዚአብሔር ትእዛዝን ተቀብሏ። ስለ መስዋዕት ሕግ ስለ
በፋሲካው በግም መስዋዕትነት ከእግዚአብሔር ተምሯል። ልጁም አቤል የአባቱን ፈለግ ሲከተል ቃየን
ደግሞ የአመጽን የሕግ የለሽን ኑሮ መርጧል። ቃየን ለእግዚአብሔር መስዋዕትን የማምጣት ሕግንና
አትግደል የሚለውን ሕግ በዋነኝነት ተላልፏ። አቤል የእግዚአብሔርን ሕግና ትዕዛዛቱን በመታዘዙም
እግዚአብሔርን ደስ አሰኝቷል። ዘፍ.4፥1-8, ሮሜ.8፥7-8, ዕብ.11:፥4-6

ከዚያም በኋላ አባቶች ሕግጋትንና ትዕዛዛትን ሲጠብቁ በዘፍጥረት ላይ በተለያየ ስፍራ


እናገኛለን። በተለይ ስለ አብርሃም በዘፍጥረት 26፥5 ላይ የተነገረው ቃል ይህን ያጸናዋል። “አብርሃም
ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።” ይህ ከመቶ አመታቶች በፊት
ሕግ በሙሴ ከመሰጠቱ በፊት የተፈጸም ነው። ስለዚህ ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ሕግ ለሕዝበ
እስራኤል በሲና በእግዚአብሔር ጣት ተጽፎ በሙሴ በኩል ቢሰጣቸውም የእግዚአብሔር ሕግ ከዘፍጥረት
አንድ ጀምሮ እንደ ነበር የእግዚአብሔር ቃል ራሱ ያስተምረናል። አባቶቻችን አስራት አውጥተዋል፣
መስዋዕት ለእግዚአብሔር አድርገዋል ወንድማዊ ፍቅርንና የተለያዩ ሕግጋትን ሲፈጽመዋል በዘፍጥረት
ላይ አብዛኛዎቹን ሕግጋት በቀላሉ እናገኛቸዋለን።

ሃጢያት ማለት የእግዚአብሔር ሕግ መተላለፍ ወይም ሕግ የለሽነት ኑሮ መኖር እንደሆነ


የእግዚአብሔር ቃል ያስተምረናል። 1.ዬሐ.3፥4 “Everyone who sins breaks the law; in fact, sin is
lawlessness.” የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ስለ ሃጢያት መናገር የጀመረው ከዘፍጥረት 4፥7 ጀምሮ
ነው። ሕግ ከሌለ ደግሞ ሃጢያት ፈጽሞ የለም ስለዚህ ሃጢያት ያለ ሕግ አይታወቅምና ቃሉ ሃጢያት
እንዳለ ሲናገር ሕግ እንዳለም እያረጋገጠ መሆኑን በቀላሉ እንረዳለን ። ስለዚህም ነው እግዚአብሔር
ቃየንን እንዲህ ያለው፦

“መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት


በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት።” ዘፍ.4፥7

ይህ በራሱ የእግዚአብሔር ሕግ እንዴት በዘፍጥረትም ተገልጦ እንደነበር በግልጽ ያሳየናል።


ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕግ ለአባቶቻችን ከአዳም ጀምሮ ተገልጦ እንደነበር በተለያየ መልኩ እንረዳለን።
ከአስርቱ ትዕዛዛት በመጀመሪያ ላይ የሚገኘውንም ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክቶች አይሁንልን የሚለውን
ትዕዛዝን ያቆብ በዘፍጥረት 35:1-4 ሲፈጽመው እንመለከታለን። የእግዚአብሔር ለአባቶቻችን ተገልጦ
ስለነበር ያቆብ ጣኦታትንና ምሰላቸውን ከእግዚአብሔር ፊት አስወገደ አርቆ ቀበራቸው። እግዚአብሔርን
ብቻ አምላኩ አደረገ።
“እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ
ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን አድርግ። ያዕቆብም
ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ
አስወግዱ፥ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፤ ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤
በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር
መሠውያን አደርጋለሁ። በእጃቸው ያሉትንም እንግዶችን አማልክት ሁሉ በጆሮአቸውም
ያሉትን ጕትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፤ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የአድባር ዛፍ
በታች ቀበራቸው። ተነሥተውም ሄዱ፤ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት
ከተሞች ሁሉ ወደቀ፥ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።” ዘፍ.35፥1-5

www.tlcfan.org 2
መለከት #3

እግዚአብሔር ያቆብን አዘዘው እርሱም ታዘዘው ምንም ለንብረቱ ሳይሳሳ ጌጣ ጌጡንና


አማልክቶችን አውጥቶ ቀበረ። እግዚአብሔር ትዕዛዛቱን ለሚጠብቁ ሁሉ የገባው ተስፋም በእርሱ ላይ
ወዲያው ተፈጸመ። ይህም በዙሪያቸው ባሉት ሁሉ ከተሞች ላይ ፍርሃትን እግዚአብሔር ጣለባቸው።
ያቆብ ከአስሩ የመጀመሪያውን ትዕዛዝ የጠበቀው እንዲህ በማድረግ ነበር። ይህ ደግሞ ለብዙ መለኮታዊ
በረከቶችና ለውጦች በር ከፍቶለት ነበር።

ከአስሩ አንደኛውና ሁለተኛው ትዕዛዛት

እግዚአብሔር የእኛ ባለቤትነት (Ownership)

እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ስላወጣቸው ብቻ ወዲያውኑ እንደ ወጡ ሕዝቡ


ሁሉ የእርሱ ባሪያዎች ሆነዋ። እግዚአብሔር የሕዝቡ ባለቤት ወይም ባለንብረት ነው። በግብጽ እያሉ
የፈርኦን ባሪያዎች ንብረቶች ነበሩ። ቀይ ባሕርን ተሻግረው ምድረበዳ ከገቡ በኋላ ግን የእግዚአብሔር
መሆናቸውን እራሱ አረጋግጦላቸዋል። እግዚአብሔር ምንም አይነት ሕግ ከመስጠቱ በፊት ባለቤትነቱና
ማንነቱ እንዲታወቅለት ይፈልጋል። እግዚአብሔር በሲና ተራራ ወርዶ ለሕዝቡ ራሱን አስተዋወቀ።
ማንም ሰው አንዳይመካ መዳንም በሌላ በማንም ስለሌለ ደግሞም መዳን በስራ ስላልሆነ እንዲሁም
ያዳነን ሙሴ ወይም አሮን ነው ብለን ግራ እንዳንጋባና እንዳንዘነጋው እግዚአብሔር እርሱ እንዳዳነን
እራሱ ገለጸልን። እእግዚአብሔር ሕዝቡን ያዳናቸው ስለ ገባው የተስፋ ቃልና ስለወደዳቸው ብቻ እንጂ
እነርሱም ምንም ስራ ስለሰሩለት አልነበረም።
“እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት
ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።” ዘጸ.20፥1-6
“5. እኔ የእግዚአብሔርን ቃል እነግራችሁ ዘንድ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔርና
በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችኋልና፥ ወደ
ተራራውም አልወጣችሁምና። እርሱም አለ፦ 6. ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት
ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።” ዘዳ.5፥6
”ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥
ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን
እጅ አዳናችሁ።” ዘዳ.7፥8
“ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸውና እንደ ባሪያዎች አይሸጡ።” ዘሌ.25፥42
የእግዚአብሔር አስሩን ሕግጋት ሙሴ ከመሞቱ በፊት እንደገና ደግም በዘዳግም ላይ
ለእስራኤል ሕዝብ ባደረገው ዳግም ንግግሩ ላይ ለሕዝበ እስራኤል ትዕዛዙን ደግሞ እንደገና ነግሯቸዋል።
ይህም ሕዝቡ ይህን መዘንጋት ስለሌለበት እረስቶትም ከሆነ ደግሞ እንደገና እንዲያስታውስና
እንዲያስተውልም ነው። ዛሬም ምንም እንኳን ትእዛዛቱን አውቃለሁ ብንልም ይህንን አንብበን
ስንጨርስ ብዙ መንፈሳዊ እውነቶችን እንደምናገኝ አምናለሁ። ደግሞ አንዳዶቻችን ምናልባትም እንደ
ሕዝበ እስራኤሎች ዘዳግም በድጋሚ ሕጉ ለእኛ ሊነገረን ያስፈልገን ይሆናል። ዘጸ.20፥1-6 ፣ ዘዳ.5፥5-7
“የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ
ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። 7 እንደ እኔ ያለ ማን
ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም
ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ። ኢሳ.44፥6
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤ በፀሐይ
መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን
አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። . . .

www.tlcfan.org 3
መለከት #3

. . . ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው?
ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ
አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም።” ኢሳ.45፥5,21
እግዚአብሔር ንጉስ ስለሆነና ብቸኛ ቤዛችንና አምላክ ስለሆነ የሕጉ ምንጭና የሁሉ ፈጣሪ
እርሱ ብቻ ነው። ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የለም!!!! እግዚአብሔር ደግሞ የለም ካለ የለም ነው።
ሰይጣን መጥቶ አምላክ ነኝ ቢል፣ ሰባኪዎችም መጥተው ሰይጣን አምላክ ነው ቢሉን ፣ ሰው መጥቶ
እኔ አምላክ ነኝ ቢለን። ፈጽሞ ስህተትና እውነት ስላልሆነ በፍጹም አንቀበልም። ከእግዚአብሔር ሌላ
ምንም አምላክ የለም!!!!!!!!።

ከእግዚአብሔር ሌላ አምላክ እንደሌለ ዛሬ ከልባችን ልናምን የገባል። እግዚአብሔርም አለ


“ያወጣሁ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ” ሕዝቡን ከግብጽ ያወጣው እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ
ተናገረ። ከዚያም በመቀጠል የእራሱ ስለሆንን፣ ስላዳነን፣ ስላጸደቀንና የእርሱ ባሪያዎች ስለሆን እንደ
ባሪያ ደግሞ የጌታችንና የንጉሳችንን ሕግ ከጌታችን እንቀበላለን ይህም ልንታዘዘው ነው። ሰው ነጻ
ያወጣውን ጌታ አምላክ ባለቤትነት ማወቅ ሲሳነው ሕጉን ይተላለፋል። ደግሞም በሌላ መልኩ ሕግ
ሰጪውንም ሕጉን የሚያስተምሩትን ይንቃል። የእግዚአብሔር ሕግ በተናቀበትና በሌለበት ስፍራ ሁሉ
አመጽና አለመከባበር እንደሚነግስ ምንም ጥርጥር የለም።
እግዚአብሔር ነጻ በማውጣት ሕግ በመቤዥት ሕግ ስለተቤዥን የእኛ ባለቤትና ባለንብረት
እርሱ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ሕጉን እንድንጠብቅለት እኛን ለማዘዝ ባለሙሉ መብት መሆኑ እንድናይ
ያደርገናል። እርሱ አሁን የእኛ ጌታ ሲሆን እኛ በእርሱ ነጻ ወጣን የምንል ሁሉ የእርሱ ባሪያዎች ነን።

” እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን?
አይደለም። ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ (በሲና ተራራ ስር)
ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት
ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ። ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት
(ፈርኦን፣ ሰይጣን፣ አለም) ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት (ትዕዛዛት)
ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ
ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ
ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ።” ሮሜ.6፥14-19

ከአስርቱ ትዕዛዛት ጋር አብሮ በሙሴ በኩል የተሰጠን በመጽሐፉ ላይ የተጻፈው ትዕዛዝ


ስለ መቤዥት ሕግ ይናገራል። ሕጉ ከባርነት ነጻ የወጣው ሰው ነጻ ላወጣው ወንድሙ መገዛትና
መታዘዝ እንዳለበት ይናገራል። ነጻ ያወጥው ወይም የተቤዥው ጌታው ይሆናል ማለት ነው። ይህ
ወደፊት ስንደርስበት በዝርዝር የምናየው የእግዚአብሔር የመቤዥት ሕግ ሚስጥር ነው። ከባርነት ነጻ
ያወጣንን እርሱን መሆኑን የሚያረጋግጥልን ዋናው ምክንያት የእኛ ባለቤትነቱን ለማስረገጥ ነው።
ስለዚህ ለተቤዠን አምላክ፣ ጌታና ወንድም የመታዘዝ ባለ እዳዎች ነን። ይህ ከባሪያ ነት ወደ ልጅነት
ካላደግን እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት የሚቀጥል የፍቅር ባርነት ስርዓት ነው። “ ያገልግልህ”
“እንደ ምንደኛና እንደ መጻተኛ ከአንተ ጋር ይሁን፤ እስከ ኢዮቤልዩም ዓመት ያገልግልህ።”
ዘሌ.25፥40
ልጁ ምንም እንኳን የሁሉ ጌታ ቢሆን እንኳን በህጻንነቱ ወቅት ከባሪያ ምንም ተለይቶ
አይታይም። ይህም የሚሆነው አባቱ እስከ ቀጠረት ቀን ድረስ ብቻ ነው። ያ እግዚአብሔር ለእርሱ
የቀጠረለት የእድገት ፍጻሜው ቀን እስኪመጣ ድረስ ሕጻኑ ከመጋቢዎች በታች ይሆናል። ገላ.4፥1-7

www.tlcfan.org 4
መለከት #3

ዮሐንስ በወንጌሉ ስለ ልጅነት ሲናገር እንሆን ዘንድ (to become) ስልጣን እንደተሰጠን
ይነግረናል። ዮሐ.1፥12-13 ጳውሎስ ደግሞ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነርሱ የእግዚአብሔር
ልጆች ናቸው ይለናል። ሮሜ. 8፥14-17 ይህ ጠለቅ ያለ ጥናት የሚፈልግ ክፍል ነው። ይሆኑ ዘንድ ተስፋ
ወደ ፊት የምፈጸም ሂደትን የሚያሳይ ሲሆን ልጆች ናቸው የሚለው የጳውሎስ ቃል ቀደሞ ፍጻሜን
ሙላትን ሆኖ መገኘትን የሚያመለክት ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ሂደት ከባርነት ወደ ልጅነት
የምንሰለጥንበት የመንፈሳዊ እድገት ደረጃዎችን ያጠቃልላል።

በባሪያና በልጅ መካከል ትልቅ ልዪነትና የእድገት ክፍተት አለ። ብልቶቻችንን ሊቀደሱ
ለድድቅ ባሪያዎች አድርገን ስናቀርብና ከእግዚአብሔር ፍቃድና ሃሳብ ጋር እንደ ካሌብና ኢያሱ
በምድረበዳ ውስጥ ስንስማማና በመንፈስ እንደተመሩ እኛም ስንመራ እነርሱ ድል ነሺ ልጆቹ እንደሆኑ
እኛም እንዲሁ እንሆናለን። ጽድቃችን የሚጀምረው እኛ የእግዚአብሔር ባሪያዎች በማድረግ ነው። ይህን
ስንል ደግሞ ልጆች አይደለንም ማለትም አይደለም። ነገር ግን ልጅነታችን የሚጀምረው ከባርነት አይነት
ሕይወት ነው ይህም ገና ስላላደግን ሕጻን ስለሆንን ነው። ስለዚህ በዝርዝርና በጥልቀት ማወቅ ከፈለጋቹ
የእግዚአብሔር ልጆች የሚለውን መጽሐፌን ያንብቡ።

እግዚአብሔር ከአለምና ከሴጣን ግዛት በታረደው በግ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከባርነት


ነጻ ያወጣን እንድንታዘዘው መሆኑን ማወቅ አለብን። የምንታዘዘው ነጻ ለመውጣት ወይም ለመጽደቅ
አይደለም። ነገር ግን ነጻ ስለወጣንና ስለጸደቅን እግዚአብሔርን እንታዘዘዋለን። እግዚአብሔርን
መታዘዛችን በፊታችን ያስቀመጠውን መለኮታዊና መንፈሳዊ እድገታችንን እስከ ምንፈጽም የሚቀጥል
የአማኞች ሁሉ የእለት ተእለት ኑሮና ሕይወት ነው። እግዚአብሔርን መታዘዝና ከእርሱ ፍቃድ ጋር
መስማማት የአማኙን መንፈሳዊ ብስለትን የሚያሳይ ነው።
እግዚአብሔር እርሱን እንድንታዘዘው ደግሞ እራሱ እግዚአብሔርን ልባችንን ገርዞ በልባችን
ላይ ሕጉን ይጽፋል። ከእግዚአብሔር ፍቃድና ቃል ጋር በሙሉ ልብ መስማማት ውስጥ “Full
agreement with God” እስከምንገባ ቀን የጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ነን። ይህ በኢየሱስ ክርስቶስ
ሕይወት ለእኛ የተገለጠ ሃሳብና የክርስቶስ አዕምሮ ነው።

መንፈሳዊ ብስለት ሲሆንልና በመንፈስ መመራት ስንጀምር ከባርነት ሕይወት ወጥተን


ወደ ነጻና በሳል ልጅነት እናድጋለን። የዚህ ውጤትና ፍጻሜው የእግዚአብሔርን የሆነው እንደ ቃሉ
መውረስ ነው። አንደኛውም የውርስ ተስፋችን በትንሳኤ የማይሞተውን መልበስ ነው። ነገር ግን ገና
ከግብጽ ወጥተን በእግዚአብሔር ቃልና ሕግ እውቀት ማነስ ሕጻን በሆንበት ጊዜ ሁሉ ምንም ልጅ
ተደርገን በእግዚአብሔር ፊት ብንቆጠርም ከባሪያ ግን ከቶ አንለይም። ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ
ብስለት እንድንመጣ ከሚያግዙንና ከሚያስተምሩን መጋቢዎች ስር ያደርገናል። ወይም እያባበለ ሕጉን
በልባችን ሊጽፍ ወደ ምድረበዳ ያወጣናል። ይህ የመንፈሳዊ እድገትና የመፈተኛ ዘመን ነው። ይህ ደግሞ
በኢየሱስ ሕይወትም የተገለጠ የእግዚአብሔር ድንቅ አሰራሩ ነው።

” ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን
ከቶ ከባሪያ አይለይም፥”ገላ.4፥1
ከባርነት ነጻ የወጡት ልጆቹ ግን ከእርሱ ፍቃድ ጋር ወደ ሙሉ መስማማት ወደ ሚደሩስበት
የእድገት ደረጃ ሲመጡ ሕጉ እራሱ ሕይወታቸውና የማንነታቸው ክፍል ይሆናል። ቃሉ በሕይወታቸው
ባሕሪ ሆኖ ይገለጣል። ይህም ለፍቃዱ ምንም አይነት ተቃውሞ ‘’resistance’’ በልባችን ከሌለ ወደዚህ
ሙላት እንደመጣን በትክክል እናውቃለን።

www.tlcfan.org 5
መለከት #3

ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ

ዘጸ.20፥3 መሰረት በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ሌላ አምላክ ለማምለክ ሆነ የእርሱን


ትዕዛዝ የሚቃረን ነገር የማድረግ ምንም አይነት መብት የለንም። በኢየሱስ ክርስቶስና ከዛም በመንፈስ
ቅዱስ ከተተረጎመልንና በልባችን ከተጻፈልን ሕግ ውጪ ምንም አይነት ነገር የመከተል መብት የለንም።
ደግሞም በዋጋ ተገዝተናል የራሳችን አይደለንም። በመንግስቱ ለመኖርና በመንግስቱ አገዛዝ ስርዓት ስር
ለመግባት የምንፈልግ ሁሉ ይህ በትክክል እንደ እግዚአብሔር ቃል ሊገባን ይገባል። ነገር ግን እንቢ ብንል
ብናምጽና በሕግ የለሽ ኑሮ ሕይወታችንን ልንመራ ብንፈልግ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ፈጽሞ
አንገባም።
“በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ
ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥
በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ
ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ
ዓመፀኞች፥(you who break Gods laws) ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።”
ማቴ.7፥21-23

“ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን።ወይስ ዓመፀኞች


የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም
ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ
ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች
የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።. . . ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር
የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ
ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።”
1.ቆሮ.6
“ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።
ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤
ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች
አይደላችሁም። የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ጣዖትን
ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥
ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥
እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” ገላ. 5
በሌላ አባባል አንድ ሰው የእግዚአብሔር የመንግስቱ ዜጋ ለመሆኑ በንጉሱ ስም ማንነት፣
ቃልና የመንግስቱን ሕግ ለማክበርም ሆነ ለመታዘዝ ቃለ መሃላ መግባት ይጠበቅበታል። ይህ ልክ
በመጸሐፈ ሩት ላይ በሩት ሕይወት እደታየው አይነት ውሳኔ ነው። “አምላክሽ አምላኬ” ሩት.1፥16
በመንግስቱ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ሕግ መተላለፍ ፍርድንና እርማትን መንግስቱን ከመውረስ
ብቃት ወጉደልን ያስከትላል። እግዚአብሔር ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ ሲል ከእርሱ ሌላ
ማንም አምላክ ስለሌለ ነው። ይህ ደግሞ የእርሱ ትዕዛዝና ቃል ነው። እርሱ ብቸኛ አምላክ ስለሆነ ነው።
ከማንም አማልክት ጋር ልናስቀምጠው፣ በምንም ልንመስለውና ልናስተካክለው አንችልም። ሌላ
አማልክት አይሁልህ ካለ አይሁኑልህ ነው። በቃ!!!!። ኢሳ.46፥5

የእግዚአብሔርን የመንግስቱን ሕግ የሚሰብሩና የማያከብሩ ሁሉ ‘’Kingdom criminals”


የመንግስቱ ወንጀለኞች ናቸው። በአለም ላይ የእግዚአብሔር ሕግ በሙላት የተቀበለ የምድር መንግስት
አሁን የለም። በምድር ታሪክ ውስጥ ከሙሴ በታች የነበረው የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን
መንግስት አኗኗር በምድር ለመኖር የቀረበ ትውልድና ሕዝብ ነበር።

www.tlcfan.org 6
መለከት #3

ይሁንና ከአዳማዊው አእምሮ የተነሳ፣ ከስጋም ድካም የተነሳ በሙሴ ዘመንም ትውልዱ
ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ አልቻለም። ይልቁንም አብዛኞቹ ዘመናቸውን የጨረሱት በማመጽ
በመጨረሻም እንደ እራሳቸው የሆነ የሰው ንጉስ ሳኦልን በማንገስ ነው። እግዚአብሔርም ስለ እያንዳንዱ
ጥፋታቸው እንደ ሕጉ የሚገባቸውን ያህልና መጠን ቅጣትን ቀጥቷቸው ነበር። ዕብ.12 በዚያ
ሊማሩበት፣ ከእርሱ ሊሰሙበትና በመንፈስ ሊመሩበት በወጡበት ምድረ በዳ ጥጃ ሰርተው እንደ
አዳኛቸው አድርገው በማምለክ የመጀመሪያውን ትዕዛዝ ሕዝቡ ሰብረውታል።

እግዚአብሔር ደግሞ ሕጉን ደግሞ ሲሰጠን እንዲሰበር ሳይሆነ በታቦቱ ውስጥ እንዲቀመጥ
ወይም በልባችን ውስጥ እንዲጻፍ ነው። ይህ በሙሴ ሕይወትና በሕዝቡ መካከል በተፈጠረው ጥላዊ
ትምህርት ለእኛ በግልጽ የተቀመጠልን ነው። ሙሴ የመጀመሪያውን ሕግ ስብሮ በጥጃውና አመድ
በጥብጦ ሕዝቡን አጠጥቷቸዋል። ነገር ግን ለሁለተኛ ጊዜ ይህ አስርቱ ትዕዛዛት በጽላቱ ላይ ሲጻፍ ግን
አልተሰበረም ይልቁኑ በታቦቱ ውስጥ ተቀመጠ። ዛሬም ይህን የመጀመሪያ ትዕዛዝ በመስበር ሕጉን
ልንሰብር አይገባም። ዳግም የተሰጠን በልባችን እንድንይዘው ነው። “ትዕዛዜን በልብህ ሸሽግ” ምሳሌ 7

የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው። መዝ.19፥7 ፣ሮሜ.7፥23 በወደቀው ሰው ማንነት ተጽኖ


ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የልቡ ዝንባሌ ያለው እንደ አዳም በእግዚአብሔር ሕግ ላይ ማመጽ ወይም
መተላለፍ ላይ ነው። ያለውን ወርቅ ስብስቦ የራሱን ጥጃ ማቆምና በልቶ ጠጥቶ ከበሮውን አንስቶ
መዝፈን ነው። ይህ የዛሬዋ በውድቀት ላይ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሕይወትን በግልጽ የሚያሳይ ነው።
የሚያመለኩት የቤተ ክርስቲያን መሪና ሽማግሌዎችን ወይም ሕንጻው የሆነበት ዘመን ላይ መጥተናል።
በዚያም ያለ እግዚአብሔር ሕግ የሆነ ከበሮና ዘፈን ይዘፈናል። ሰውም በሚዞርለት ጆሮጆ ውስጥ
አምልኮው እንዲቀጥል የመሪዎችን ኑሮ የሚደጉም እንደ አባቶቻችንና እናቶቻችን በምድረ በዳ
እንዳደረጉ የጆሮ ጌጡንና ገንዘቡን ጥጃውን ለማቆም ይሰጣል። በየሳምንቱ የሕንጻ መግዣ፣ ኮንፍረስ
ማድረጊያ፣ የተራራ ጸሎት ማዘጋጃ እየተባለ ሕዝቡም ምንም ከእግዚአብሔር ሳይሰማ ገንዘቡን ጌታ
ባልፈቀደበት ስፍራ ያከማቻል። ይህን እናንተ በቃሉ መነጽር አጥርታችሁ እንድታዮት ለእናንተ
እተወዋለሁ። እግዚአብሔር ምን ይላል ብሎ ቀረብ ብሎ በቃሉ ሁሉን መመርመር በሳልነት ነው።

ይህ በእንዲህ ሁኔታ እንዳለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር በመጣበት ወቅት የእግዚአብሔር


መንግስት በውስጣችን እንዳለ ደግሞ ገልጦልናል። ሉቃ.17፥21 ይህን ቃል ካለመረዳት የተነሳ የዘመኗ
ቤተ ክስርቲያን ችግር ውስጥ ገብታለች። ይህም መንግስቱ ፍጥረታዊ መልክ እንደማይኖራት
የሚያመለክተው ትምህርቷ ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግስት ከእኛ ውጭ አይመሰረትም ማለቱ
ነውን? በፍጹም አትሳቱ። መንግስቱ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ ደግሞ በምድር እንድትሆን የአባታችን
ፍቃድ ነው። ይህም እንዲሆን እድንጸልይ ከጌታ ተምረናል። የእግዚአብሔር የመንግስቱ ሕይወት
በውስጣችን አለ። ነገር ግን በውጭ ባለው የመንግስት አገዛዝ ላይ ይገለጥ ዘንድ የግድ በሙላት በአካሉ
ቤተ ክርስቲያን ላይ ቀድሞ መንግስቱ ሊገለጥ የገባዋል። በኢየሱስ ዳግም ምጸአት መንግስቱ ለጻድቃን
ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል። ያኔ ደግሞ መንግስቱ በምድር ይሆናል ወይም ይጸናል። ራእይ.20

“መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት


ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም
ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።” ዳን.7፥27

የእግዚአብሔር መንግስት ስራ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ስራውን


ጀምሯል። ይህም የመንፈሳዊ እድገትና ብስለታቸው በፈቀደላቸው መጠን ለእግዚአብሔር በመገዛትና
በመንግስቱ ሕግ ስር በመተዳደርና በመተዘዝ የሚታይም ነው። ይህም የመጀመሪያው ትንሳኤ
እስከሚፈጸም ድረስ ከባርነት ነጻ በወጡት በመንግስቱ ዜጎች ሁሉ ላይ የሚቀጥል ሕይወት ነው።

www.tlcfan.org 7
መለከት #3

ነገር ግን የመጀመሪያው ትንሳኤ በሚሆንበት ቀን ግን ድል የሚነሱትና የመጀመሪያው


ትንሳኤ ተካፈይ የሚሆኑ አማኞች ሁሉ መንግስቱን በክብር ይወርሳሉ። ያኔም በአዲሱና በማይሞተው
አካል ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር ሕግ 100% ይታዘዙታል። በአዳማዊና በሚበሰብሰው አካል ወይም
ድንኳን ውስጥ ሆነን ሕጉን ሙሉ በሙሉ ልንጠብቅ አንችልም። ይህ ስለማይሆን ግን እግዚአብሔር
መታዘዝ እናቆማለን ማለት አይደለም። ከላይ እንዳየነው ኢየሱስና ጳውሎስ ስለ መንግስቱ መውረስ
የተናገሩትን ማስተዋል ይገባናል። ራዕይ.20፥4-6 እነዚህን በዚህ በማይቻለውን በአስቸጋሪው ዘመን
ፈጽመው የገባውን ተስፋ ታምነው ታዘውታልና በሚመጣው ዘመን በመንግስቱ ሌሎች የሚያሰለጥኑና
የሚያስተምሩ ሆነው ይሾማሉ።
ይህም ሲሆን የእግዚአብሔር መንግስት አገዛዝ ከሰው ልብ ውስጥ ባለፈ ሁኔታ በሚታይና
በሚጨበጥ መልኩ በምድር ላይ መንግስቱ ይገለጣል። መንግስቱ በሰማይ እንደሆነች በምድርም
ትሆናለች። እግዚአብሔር የማይጠፋን መንግስት በማይጠፉና በማይሞቱ የመንግስቱ ድል ነሺ ዜጎች
ለዘላለም ያጸናል። በመጀመሪያ ከሰው ዘር ሁሉ ድል የነሱ ድል ነሺ አማኞች መንግስቱን አስቀድመው
ይወርሳሉ። ለሌሎች የሰው ልጆችና ድል ላልነሱት አማኞች ሁሉ ምሳሌዎች ይሆናሉ። ከዚያም ብዙ
ትውልዶች እግዚአብሔርን ለመማር ወደ እነርሱ ወደ ድል ነሺዎች ይመጣሉ።
”ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ
ሄደው። ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ እርሱም
መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ” ኢሳ.2:፥3
“ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ
በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።” ኢሳ.26፥9

እነዚህም ትውልዶች ከእነዚህ ከማይሞቱ ትውልዶች የእግዚአብሔር መንገድና ጽድቅን


ይማራሉ። የእግዚአብሔርንም ሕግ ኢየሱስ እደተረጎመው በመተርጎምና በሕይወታቸው ላይ
እንዲተገበር ማድረግን ይማራሉ። ማንኛውም ሃይማኖት የፈጠረው ፍልስፍናና ወግና ስርዓት ሁሉ
ፈጽሞ ይወገዳል። ዳንኤል የእግዚአብሔር መንግስት በትንቢታዊ ራእይ እንደገለጠው በምድር ላይ
በክብር ይቆማል። መንግስቱ ከአንድ ድንጋይ ተነስታ ምድርን እስከምትሞላ ከፍ ከፍ እያለች ታድጋለች።

አንደኛው ትዕዛዝ የሚያስተምረን ማን የእኛ ብቸኛ አምላክ፣ ንጉስ፣ ገዢ፣ ባለቤት እና ማን


የምድር ጌታና ባለቤት መሆኑን ነው። እርሱን ብቻ ለማምለክ የምንወስንበትና የሕይወታችን ብቸኛ
አምላክ የምናደርግበት የመጀመሪያው ሕግ ነው። በሌላ አንጻር ደግሞ የእግዚአብሔር ታላቅነት
የምናይበትም ሕግ ነው። ከእርሱ ውጭ ሌላ አምላክ የለምና ነው። የእግዚአብሔር መንግስት በአንድ
ንጉስና አምላክ ብቻ የሚመራ ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ሕግ ይህ ንጉስ ማን እንደሆነ እንድናውቅ
አይናችንን ይከፍታል።

ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጣውና ሕግ ለሙሴ በሲና ተራራ የሰጠው በአዲስ
ኪዳንም የገለጠው ብቸኛ የሰማይና የምድር ነገስታት ሁሉ ንጉስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዘጸ.15፥
2 ፣ ኢሳ.12፥1-3 የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ሕግ የሚያሳየንና የሚያመለክተን ይህ ከባርነት ነጻ
ያወጣን ንጉስና አምላካችን አንድ መሆኑ ነው። ይህም አምላክ ለእኛ በአካል የተገለጠው የናዝሬቱ እየሱስ
ክርስቶስ ነው። ለብዙ ሺ አመታት ይህንን በምድር ያሉ ነገስታት ሆኑ የሃይማኖት ሰዎች ሊቀበሉት
አልቻሉም። በዳንኤል ትንቢትና ራእይ እንደተገለጠው ለአውሬዎቹ መንግስታት ሁል ጊዜ ራሱን
ሳይገልጥላቸው ቀርቶ አያውቅም። ነገር ግን እውነተኛውን፣ ብቸኛውን ንጉስ አልተቀበሉትም። ዳዊት
ለጊዜው በአቢሴሎም እንደተገፋና ግዛቱን ለጊዜው ጥሎ እንደሄደ እንደገና በክብር ደግሞ እንደተመለሰ
እንዲሁ ኢየሱስ ክርስቶስም በክብር መመለሱ የማይቀር ነው። ማራናታ!!!!!

www.tlcfan.org 8
መለከት #3

የአለም መንግስታት ፈጽሞ በእግዚአብሔር መንግስት እስከሚፈርሱ ድረስ ተተካኩ እንጂ


እስካሁን እንደቆሙ ናቸው። ዳንኤል ያየው የምድር ነግስታት ምስል ሰው ነበር። ከላይ እስከታች ድረስ
አሁን እስከደረስንበት እስከተከፋፈለ መንግስት ዘመን ድረስ ተቀያየሩ እንጂ ያው ሰው ያው መንፈስ ገና
እንደቆመ ነው። ምድርን የሚሞላው በድንጋዪ የተመሰለው የእግዚአብሔር መንግስት ከላይ እስኪመጣ
ድረስ መልኩን በመቀያየር ሰው ምስሉ ሲሰራ ይቆያል። አሁን ግን በዘመኑ መጨረሻ ላይ እንደመጣን
አውቀን እንደ ዳንኤልና ጓደኞቹ ድል ለመንሳት የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እናንሳ። በእኛም ዘንድ
ከአምላካችን ሕግ በቀር ምንም አይገኝብን። ለማንኛውም የአለም ሲስተም፣ የሃይማኖት ስርዓትና ወግ
አልገዛም አልሰግድም እንበል።

የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነዖር እራሱን አምላክና ገዢ ለማድረግ ፈለገ። እግዚአብሔር ብቸኛ


አምላክና ገዢ መሆኑን እስከሚያውቅ ድረስ ክቡር ሆኖ ሳለ እንደ እንስሳ፣ እንደ በሬ ሳር እንዲበላ ወደ
ሜዳ ሰደደው። ዳን. 4፥25-27 ይህም የእግዚአብሔር የበላይ ገዢነትና ብቸኛ አምላክነት መሆኑን ያውቅ
ዘንድ ነው። እርሱ በምድር የተቀረጸን የሰው ምስል አሰርቶ ሕዝቡን ለጣኦትና ለተቀረጸ ምስል አሰገደ።
ከአራቱ ድል ነሺ አማኞች በቀር ሁሉ ወድቆ ሰገደ። ለእግዚአብሔር መንግስት አገዛዝና ሕግ ስለተገዙ
እግዚአብሔር ስለ ስሙ ጣልቃ ገብቶ ራሱን በሁሉ ነገር ገለጠ። በጥራጥሬ ጮማ ከበላው በላይ፣
በእሳት እስራት በመፍታት፣ በሌሎች ላይ ሁሉ ከፍ ከፍ በማድረግ እግዚአብሔር ከድል ነሺዎች ጋር
አብሮነቱን በሁሉ ፊት ገለጠ። “ ከእኔ በቀል ሌላ አምላክ የለም። እኔን ብቻ አምልክ ለእኔ ብቻ ስገድ”
ያለ አምላክ ለሚታዘዙት ክብሩንና ባርኮቱን በዘመናት ሁሉ ይገልጣል። አሁንም ይህን ለእኛ ሊገልጥ በጎ
ፍቃዱ ነውና እርሱን ብቻ አምላክ እርሱን ብቻ ጌታና ራስ አድርገው። ከእርሱም በላይ ማንንም ሰው
ሆነ ጻድቃን የበላይ አናድርግ። አንስገድላቸው፣ አናምልካቸው፣ ይህ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር
ትዕዛዝ ነው።

በምድር ያሉ ነግስታትና የዘመኗ ቤተ ክስቲያን እግዚአብሔር ከመታዘዝ ስለወደቁ


እግዚአብሔር አሁን ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ድል ነሺዎችን ለመንግስቱ ሕግና ስርዓት መልምሎ
በየስፍራው ሕጉን በልባቸው ላይ ለመጻፍ ይጣራል። ደግሞ ድምጹን ሰምተው የመጡትን ማሰልጠን
አሁን ጀምሯል። ደግሞ ያልሰሙትን ወደዚህ ድል ነሺ ሕይወት ይጣራል። ራእይ.2 ና3 ሰዓቱም ሲደርስ
በፊት ድል የነሱ አማኞችና አሁን በሕይወትም ያሉ ድል የነሱ ቅሬታዎች በትንሳኤ በመንግስቱ ውስጥ
ያስተዳድራሉ። ራእይ.20 ይህም ድል ነሺ የማይሞትና የማይበሰብስው ትውልድ የመጀመሪያውን
የእግዚአብሔር ሕግ ጨምሮ የእግዚአብሔርን ሕግጋት የሚያውቅ፣ የሚያከብር የሚያደርግ ትውልድ
ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ለእርሱ ያዘጋጀለትን የመንግስቱ ስፍራና ዙፋን ከእርሱ በትንሳኤ ይቀበላል።
ከክርስቶስም በታች በመሆን የመግስቱን ሕግ በመጠቀም ያስተዳድራ። 1.ቆሮ.15፥52፣ ዳን.2፥35

ይህ እውነት በሁላችሁ ዘንድ የታወቀ እንዲሆን እወዳለሁ። ሁሉ አማኞች ድል አይነሱም።


እውነተኛ ሰምተው የሚታዘዙ አማኞች ግን ድል በመንሳት የመንግስቱ ወራሽና ዜጎች ይሆናሉ። ይህ
በምድረበዳ በሕዝበ እስራኤል ኑሮ ግልጽ ብሎ ታይቷል። ይህም ሌዋዊያን ብቻ በዚያንን ጊዜ ይፈርዱና
ያስተዳድሩ እንደነበርና ሕጉን አሰማም አንታዘዝም ያሉት በምድረበዳ እንደቀሩ የታዘዙትና የታመኑት
ዬርዳኖስን ተሻግረው ከንዓንን እንደ ወረሱ ማለት ነው። ዘሁ.18፥20-21 የእግዚአብሔር መንግስት
የሚመራው በብሉይ እንደነበር በካህን ንጉሶች ነው። ይህም ክህነት እንደ ብሉይ በሌዊ ሳይሆን በመልከ
ጸዲቅ አይነት ክህነት ነው። ራእይ.5፥ 9-10 እነዚህ የዚህ መንግስትና ክህነት ተካፋይ የሚሆኑ ድል ነሺ
አማኞች ብቻ ከኢየሱስ ጋር ይገዛሉ ይነግሳሉ።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥
በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም

www.tlcfan.org 9
መለከት #3

ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ


አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።”
ራእይ.5፥9-10

“በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ


ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ
ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።”
ራእይ.20፥6

በቁጥር 4 ያቀጥላል ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

www.tlcfan.org 10
መለከት #3

www.tlcfan.org 11

You might also like