Professional Documents
Culture Documents
05.
05.
05.
5
www.tlcfan.org 0
መለከት #5
በሸመገለው ፊት የመነሳት ሕግ
ከአስርቱ ትእዛዛት መካከል አንዱ፦ “አባትህንና እናትህን አክብር እግዚአብሔር አምላክህ
በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።” የሚል ነው። ዘጸ.20፥12 ይህ ሕግ የሚያያዘው ወይም
የሚዛመደው በዘሌዋውያን 19፥32 ላይ ከሚገኘው ጥቅስ ጋር ነው።
“በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ይህ የዳንኤል ራእይ ሰለሙታን ትንሳኤ ያየው ወደፊት የሚፈጸም ራእይና ትንቢት ነው። የተለያዮ
የእንግሊዘኛ ትርጉሞች ላይ ቃሉን ብናይ የበለጠ ቃሉን ግልጽ ያደርገዋል። Young's Literal
Translation “myriads of myriads do RISE UP.” The concordant Literal Translation “ a
thousand touseands are irradiating Him, and ten thousand ten thousands are RISING
before Him.” ብሎ ያስቀምጠዋል።
www.tlcfan.org 1
መለከት #5
ስለዚህ አለመስረቅ ባሕሪያችን የእለት ተእለት ኑሯችን ይሆናል። መስረቅ ደግሞ ተፈጥሯችን
መሆኑ ያከትማል። በአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕግንና ትዕዛዛቱን አጠባበቅ እንደ ብሉይ ኪዳን
ሃላፊነቱን በሰዎች ላይ የሚጭን ሳይሆን እግዚአብሔር ሕጉን እንድንጠብቅ ሕጉን ባሕሪያችን አድርጎ
በውስጣችን ሊቀርጽ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ሊሰጠን ሃላፊነቱን በራሱ በእግዚአብሔር ላይ ይጭናል።
ለዚህ ነው ሕጉ ከትእዛዝ ባለፈ መልኩ ትንቢታዊነቱ በአዲስ ኪዳን በይበልጥ የተገለጠው። ትእዛዝ ሊጣስ
ወይም ሊሰበር ይችላል። ይህም ፍርድን ያስከትላል። ትንቢት ግን ፈጽሞ የሚጣስ ወይም የሚሰበር
አይደለም። ምክንያቱም ትንቢቱ እውን እንዲሆን የተናገረው እግዚአብሔር ለማጽናትና ለመፈጸም ከቃሉ
ጀርባ ስለሚተጋ ነው። እንዳለውና እንዳሰበው እንደተናገረውም የሚጸናለት ብቸኛ አምላክ እግዚአብሔር
ብቻ ነው።
ሕዝበ እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት እንቢ ሲል። እግዚአብሔር ሙሴን ፈተነው።
ይህንንም ፈተና ለሙሴ አዲስ የስራ እድል በመክፈት ነው። ሙሴ ግን እንቢ አለ። ዘሁ.13‐14
እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤል ሁሉ ሊያጠፋና ከሙሴና ከእርሱ ዘር ጋር ብቻ ሊቀጥልና ለእርሱ ሌላ
ትውልድ ሊሰጠው እንደሚፈልግ ለሙሴ ነገረው። ሙሴ ግን ለእርሱ እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔር
ይህን ሕዝብ ወደ ማለላቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና በምድረ በዳ ገደላቸው ብለው
ይናገራሉ።’’ አለው። እግዚአብሔር ሙሴን ከሰማ በኋላ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔርም አለ፦ እንደ ቃልህ
ይቅር አልሁ 21. ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።’’ ታላቅ
የተስፋ ቃል ገባ።
www.tlcfan.org 2
መለከት #5
እኔ ሕያው ነኝና የሚለው ቃል እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊያደርግ እንደወሰነ ከማሳየት አልፎ
በማንነቱ ላይም ጭምር ያተኮረ ተስፋ እንደሆነ ይሳያል። እግዚአብሔር እሞክራለሁ አላለም፣ ከቻልኩ
አላለም ወይም ሰዎች የምላቸው ከሰሙኝ አላለም። ነገር ግን በእራሱ ማንነት ታምኖ ይህን ሊፈጽም
ወሰነ፣ ቃል ገባ፣ ተነበየ። ምድር በክብሩ ካልተሞላች እኛ የሚገባውን ስላላደረግን ሳይሆን እግዚአብሔር
የገባውን ተስፋ ስላልፈጸመ ወይም ስላላደረገ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ግን ሕዝበ እስራኤልን ወደ
ተስፋይቱ ምድር በማስገባት ቃሉ እንደሚፈጸመው እንዳሳየ ምድርንም በክብሩ በመሙላት የተስፋ
ቃሉን ይፈጽማል።
ይህ የእስራኤል ሕዝብ ከንዓንን መውረስ ምሳሌ ግን የቃሉ ፍጻሜ አልነበረም። ይልቁኑ ወደፊት
ለሚፈጸመው ለእግዚአብሔር ታላቁ ሰራው መለኮታዊ ትንቢታዊ ጥላም ነበር። በእርግጥ ገና ምድር
በክብሩ ትሞላለች። መሃላው አንድ ከንዓንን ብቻ በክብሩ መሙላት ሳይሆን ምድርና ሞላዋን ውሃ
የባሕርን ፊት እንደሚሸፍን ምድርን በእግዚአብሔር ክብር መሙላት ነው። ይህ ደግሞ በውስጧ ያለውን
ፍጥረት ሁሉ የሚጨምር ነው።
ይህ የሕዝበ እስራኤል ታሪክ ግን የዳስ በዓልን ዮርዳኖስ ተሻግረው ማድረግን እንቢ ያሉትን
ፍቃዳቸውን በፍቃዱ ጥሎ ራሱን በእነርሱ አከበረ ከንዓን ስለ ስሙና ማንነቱ አወረሳቸው። በሌላ አባባል
እግዚአብሔር እንቢ ብንልም እሺ እንድንል ያደርገናል። ይህም የደነቆረውን ጆሮና የታወረውን አይን
በመክፈት ነው። ዘጸ.4፥11 የሰው ፍቃድ ወይም ምርጫ ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር ፍቃድና ምርጫ ስር
ነው። ይህም ማለት ሰው በሚያደርገው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድና ሃሳብ መፈጸሙን ፈጽሞ
አያግድም ማለት ነው። እግዚአብሔር ሁሉን አዲስ ያደርጋል። እግዚአብሔር ሁሉን ይለውጣል።
እግዚአብሔር ሁሉን ያድናል። 1.ጢሞ.4፥10 ይህ ማለት ግን ሰዎች ባለመታዘዝ ሕይወት እንዳሉ ያድናቸል
ማለት አይደለም። ሁሉን ያድናል ማለት ልባቸውን በፍቅሩና ምሕረት በተሞላው ፍርዱ በመቀየር
ባሕሪውና ማነቱን በማይቃረን ስርዓቱ ሁሉን በማይጥስ መልኩ ሁሉን አዲስ በማድረግ ነው። ይህም
ተሃድሶ ደህንነት በእሳት የሚገለጥ ተሃድሶ ነው። ሚል.3 ስለ ነጻ ፍቃድ በበለጠ ለማወቅ ነጻ ፍቃድ
የሚለውን መጽሐፍ ያንብቡ።
ይህም ትንቢት የሚፈጸመው በሸመገለው ፊት ሁሉ በነጩ ዙፋን ፊት ሲነሱ ነው። ዳንኤል በራእዮ
እንዳየው ዙፋኑ ራሱ ነበልባልና መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ። ዙፋን ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር
የሕግ ምሳሌ ነው። ንጉስ ሁል ጊዜ ዙፋን ላይ ሲቀመጥ ትእዛዝ እንደሚወጣ በሰው ልጆች ታሪንና
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠ እውነት ነው። የእሳትም ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር የሚለው
ቃል ከእርሱ የሚወጣውን ሕግ የሚያመለክት ነው። “ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፥ እልፍ አእላፋትም
በፊቱ ቆመው ነበር ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ።” ዳኤ.7 ይህ ደግሞ የሚያሳየው በፊቱ በትንሳኤ
የተነሱት መልካምና ክፉ ያደረጉትን በጠቅላላው ወይም በሁለተኛው ትንሳኤ የተነሱትን ሰዎችን ሁሉ
የሚፈድበትን ሕጉን የሚያሳይ ነው።
ራእይ 20 ደግሞ ይህንኑ ታሪክ በሌላ መልኩ ይገልጥልናል። ድል ነሺዎች ከነጩ ዝፋን ፍርድ
በፊት በመጀመሪያው ትንሳኤን እንደሚቀበሉና የቀሩት ሙታን ግን በመጀመሪያውና ለጻድቃንና ለድል
ነሺዎች ብቻ በተወሰነው ትንሳኤ እንደማይነሱ ይነግረናል። ነገር ግን በሁለተኛው ትንሳኤ በነጩ ዙፋን
ፊት በዘመናት በሸመግለው ፊት ለፍርድ እንደሚነሱ ይነግረናል። ከሚነሱትም ክፉ ያደጉ ማለትም
በሕይወት መጽሐፍ ስማቸው ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ በእሳት ባሕር ውስጥ ፍርዳቸውን እንደሚቀበሉ
ይነግረናል። ይህ እሳት እኛ እንደምናውቀው ምግን እንደምናበስልበት አይነት ፍጥረታዊ እሳት አይደለም።
ይህ እሳት ደግሜ እላለሁ የእግዚአብሔር ሕግ ምሳሌ ነው።
www.tlcfan.org 3
መለከት #5
“እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ በሴይርም ተገለጠ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥
ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው።”
ዘዳ.33፥2
“በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን?
ይላል እግዚአብሔር፦’’ ኤር.23:፥29
የእሳት ባሕር ራሱን የቻለ ፍርዱ የሚፈጸምበት ዘመን አለው። የእሳት ባሕር ፍርድ ለዘለዓለም
የሚቀጥል ፍርድ አይደለም። ሁሉ ነገር ጅማሬ እንዳለሁ ሁሉ ፍጻሜም አለው። ደግሞ ከዘላለም እስከ
ዘለዓለም የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም አይደለም። ማንኛውም ቃሉን በዋናው ትርጉም የሚያጠና
ዘላለም ተብሎ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተረጎመውን ቃል ትክክለኛ ትርጉም እንዳልሆነ ይረዳል። ዘላለም
የሚለውን ቃል ግሪኩ የሚለው “ኢዬን” ነው። ይህ ደግሞ ዘመን ማለት ነው። (eon, or age/ age-
during) ስለዚህ የዚህ የእሳት ባሕር ዘመን ሲፈጸም ያኔ የኢዮቤልዮ ሕግ ፍጻሜ ዘመን ይሆናል። የፍርድ
ሁሉ ፍጻሜ ኢዮቤልዮ ነው። ምሕረት በፍርድ ላይ ይመካል። ይህም የሁሉ እዳ ፈጽሞ ከሁሉ ላይ
ሲደመሰስ የሚፈጸም ነው።
www.tlcfan.org 4
መለከት #5
www.tlcfan.org 5