Professional Documents
Culture Documents
ጥርስ ከተነቀለ በኋላ መ
ጥርስ ከተነቀለ በኋላ መ
ሐኪም ያስነከሶትን ጎዝ ወይም ፋሻ ለ 30 ደቂቃ ነክሶ መያዝ አላስፈላጊ የሆነን ደም ፍሰት ይከላከላል። ክተወሰነ
ሰዓት በኋላ ደም የቀላቀለ ምራቅ ይኖራል። ይህንንም መዋጥ እንጂ መትፋት የለቦትም።ከበድ ያሉና አቅምን
የሚጠይቁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን አለማድረግ። ከመጠን ያለፈ የደም ፍሰት በሚኖርበት ሰዓት በጎዝ
ወይም በፋሻ መጥረግና ቦታው ላይ ጎዝ ወይም ፋሻ ለ 30 ደቂቃ ነክሶ መያዝ። ጥጥ መጠቀም የለብንም። ይህንን
ለ 3 ጊዜ ሞክረው ደም ካልቆመ ሐኪሞትን ማማከር ይኖርቦታል።
ጥርሶትን ከተነቀሉ ለ 24 ሰዓት በማንኛውም አይነት ፈሳሽ መጉመጥመጥ የለቦትም።ይህም የደም መርጋትን
ሒደትን ያስተጓጉላል። በተጨማሪም ያካል እንቅስቃሴን ማሶገድ ይኖርቦታል።
ለስለስ ያሉ ምግቦችን ቀዝቀዝ አድርጎ መጠቀም ተገቢ ነው።በሚያኝኩበት ጊዜ የተነቀለበትን ተቃራኒ ጎን
ይጠቀሙ።ሞቃት ምግቦችንና ሰውነትን ሊያስቆጣ የሚችል ምግቦችን ያስወግዱ።
ጥርስ በተነቀለበት አከባቢ ውጭውን የፊታችን ክፍል በጨርቅ በተጠቀለለ በረዶ መያዝ እብጠትን ይከላከላል።
የአፍ ንፅህናዎን መጠበቅ አላስፈላጊ የሆነን የባክታሪያ እድገትን ይከላከላል።በተለመደው የአፍ ንፅህና አጠባብቅ
በቀን ሶስት ያፅዱ። ጥርስ ከተነቀለበት አከባቢ ልስልስ ብሎ ብሩሽ ያፅዱ። ምግብ ከተጠቀሙ በኋላ አላስፈላጊ
የሆነን ለምን ለመቀነስ አፎትን በደምብ ያፅዱ።
ጥርስ ከተነቀሉ በኋላ ላሉት ሰባተ ተከታታይ ቀናት ሲጋራ ወይም ትንባሆ አለማጨስ። ማጨስ ብክለትን
ወይም የቁስሉን ቶሎ የመዳን ሒደት ይከላከላል። እንዲሁም ህመም እንድንል ያደርጋል።
በውስጣቸው የጋዝ ይዘት ያላቸውን መጠጦች ያስወግዱ። እነዚህ መጠጦች የደም መርጋት ሂደትን ያስጓጉለል።
እንዲሁም የረጋውን ደም ከቦታው እንዲለቅ ያደርጋል።
በሐኪም የታዘዘሎትን ፀረ-ባክቴሪያ መድሀኒት በአግባቡ መጠቀምና መጨረስ ያስፈልጋል። የመድሀኒቱን
መጠንና በምን ያህል ጊዜ ልዩነት መወሰድ እንዳለበት አስተውለው ያንብቡ ወይም ይጠይቁ።
በሐኪም የታዘዘሎትን ማስታገሻ መድሀኒት በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። የመድሀኒቱን መጠንና በምን ያህል
ጊዜ ልዩነት መወሰድ እንዳለበት አስተውለው ያንብቡ ወይም ይጠይቁ።
ጥርስ ከተነቀሉ ከ 24 ብንል 0.12% chlorhexidine በሚባል የአፍ መጉመጥመጫ ለ 10 ቀናት ይጉመጥመጡ።
0.12%chlorhexidine ,ፀረ-ባክቴሪያ ሲሆን የአፍ ውስጥ ባክቴሪያ በመቀነስ ብክለት እንዳይኖር ያደርጋል።ይህም
የጎንዮሽ ጉዳትን ቀንሶ ለክፋ ችግር እንዳንጋለጥ ያደርጋል።
ይህን አድርግዋል?
ጥያቄ