ክፍል ሦስት

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 5

//

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
“ ኁሉ በአግባብና በሥርዓት ይኹን ” 1 ቆሮ 14÷40
ክፍል ሦስት

ንዋያተ ቅድሳት
 ንዋይ ማለት “ ገንዘብ ” ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ማለት ደግሞ “ የተለየ ፤ የተከበረ ፤ የተመረጠ ” ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ
ንዋያተ ቅድሳት ማለት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ የተቀደሱ የተለዩ ንዋያት ማለት ነው፡፡

 ንዋያተ ቅድሳት በዓይነታቸው ፣ በምሳሌነታቸውና በመንፈሳዊ አገልግሎታቸው በዐምስት ዋና ዋና ክፍሎች በመክፈል አጠር ባለ
መልኩ እንመለከተለን ፡-

1. አልባሳት
 ቀሚስ
ካህናት የሚለብሱት ልብስ እስከ ተረከዛቸው ድረስ የሚደርስ መኾን አለበት፡፡ ስለዚኸም ካህኑ ልብሰ ተክህኖ ከመልበሱ በፊት ልኩ
የኾነውን መርጦ ይለብሳል፡፡ ከለበሰ በኋላ ረዘመ ብሎ አጭር አጠረ ብሎ ረዥም ለመፈለግ ማውለቅ አይገባም፡፡ ምሳሌነቱ ፡-
ቀሚሱ - የመለኮት ምሳሌ ፤ ካህኑ - የሥጋ ምሳሌ ፤ ቀሚሱ - በቁመታቸው ልክ ይኹን የተባለበት ምክንያት -ቢረዝም - መለኮት
ሥጋን አልተዋሐደም ወይም ከሥጋ መለኮት በተዋሕዶ ጊዜ በልጧል እንደ ማለት ነው፡፡ ቀሚሱ ቢያጥር - መለኮት በተዋሕዶ ጊዜ
ከሥጋ አንሷል ይባል ነበር፡፡ ስለዚኸ መለኮትና ሥጋ ያለመበላለጥ ያለመተናነስ መዋሐዳቸውን እንዲያጠይቅ በቁመት ልክ ይለበሳል፡፡
ዝናሩ / መታጠቂያ ገመዱ / - ጌታ በአይሁድ የተጐተተበት ገመድ ምሳሌ ነው፡፡

 ካባ ( ካባ ላንቃ )

ከካባው ጋር ለምድ አብሮ ተሰፍቶ የሚገኝ የለምዱ ዕግር በየቦታው እንደ ላንቃ እየኾነ ስለሚወርድ ካባ ላንቃ ተብሏል፡፡
በምሳሌነት -
የክብርና የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌም ነው፡፡ ራዕ. 21÷18 ከወርቅ የሚበልጡ ምን ምን ናቸው ቢባል፤ የእግዚአብሔር ሕግ፡፡
መዝ. 119÷72 ፤ እምነት፡፡ 1 ጴጥ 1÷6-7 ፤ ጥበብ ኢዮ. 28÷12÷19 ፤ የተዋጆንበት የክርስቶስ ደም፡፡ 1 ጴጥ. 1÷18-19 ናቸው፡፡
እነዚኽ ነገሮች ብቻ ከወርቅ ይበልጣሉ ማለት ነው፡፡ ካህናት የሚደርቡት ካባ ዐምስት መርገፍ አለው፡፡

 ቆብ

ምሳሌነቱ ፡-

የመነኮሳት ቆብ - መነኮሳቱ የሚያደርጉት ቆብ በምሳሌነት ጌታን በዕለተ ዐርብ ሲሰቅሉት የአይሁድ ንጉሥ ነኝ ብለኻልና ይኽው
አነገሥንህ ብለው የሾኽ አክሊል ጉንጉን በራሱ ላይ ደፍተውበታልና ነው፡፡

 ሙጣሕት
በአንገት ተጠልቆ ፊት ለፊት የሚወርድ ልብስ ነው፡፡ ምሳሌውም፡- የፍኖተ ቅዱሳን ምልክት ነው፡፡ ከፊት ረዥም መንገድ ይጠብቅሀል
ማለት ነው፡፡

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ክፍል ሦስት


//

 ፈረጅያ
ጳጳሳት የሚለብሱት እጅ ሰፊ ቀሚስ ነው፡፡ እጀ ሰፊ መኾኑ ብዙ መክሊት እንደተሰጣቸው የሚያመለክት ነው፡፡

 ምንጣፍ
በቤተክርስቲያን ያማሩና የለሰለሱ ምንጣፎች ይነጠፋሉ፡፡ ይኽም እግዚአብሔረ እስራኤላውያንን እሾክ እንዳይወጋቸው እንቅፋት
እንዳይመታቸው በብርሃን አምድ የመምራቱን ምስጢር የሚያስተውስ ነው፡፡

2. የቅዳሴና የጸሎት መገልገያ ንዋያተ ቅድሳት

 ጽንሐሕ- የእጣን ማጠኛ ፣ ማጨሻ ነው።ምስሌውም

ማዕጠንት ( የፍሕሙ ማስቀመጫ ሙዳይ መሰል እቃ )- የእመቤታችን ምሳሌ ፤ ፍሕሙ / እሳቱ / - የመለኮት ምሳሌ ፤ ሦስቱ ገመዶች
- የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ምሳሌ ሲኾን ፤ በአንድ ሲገናኙ ደግሞ የአንድነታቸው ምሳሌ ነው ፤ በገመዶች / ሰንሰለት / ላይ ያሉት ኻያ
አራቱ ሻኩራዎች የኻያ አራት ካህናተ ሰማይ ምሳሌ ነው ፤ የጽንሐው ክዳን - የእመቤታችን የድንግልናዋ ምሳሌ ነው ፤ የጽንሐው
ድምጽ - የስብሐተ መላእክት ምሳሌ ነው፡፡

 ደወል

በቤተክርስትያናችን ለአገልግሎት ከሚውሉ ነዋያተ ቅድሳት መካከል አንዱ ደወል (መጥቅዕ) ነው፡፡ ደወል ለመንፈሳዊ አገልግሎት
ይውል የዠመረው በጻድቁ ኖኀ ዘመን ነው፡፡

የጠዋት ደወል
በዚኸ ሰዐት የሚደወለው ለጸሎትና ለተግባር ነው፡፡ መርከብን ምክንያት አድርጎ የታደጋቸው እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፡፡
እንዳይዘጋቸውም የተለያዩ ተግባራትን / ሥራዎችን / ያከናውኑ ነበርና ሰዓት መድረሱን ለማመልከት ደወል ይጠቀሙ ነበር፡፡

የቀትር ደወል
የመመገቢያ ሰዐት መድረሱን ለማብሰር ይደወላል፡፡

የሠርክ ሰዐት ደወል


ለጸሎትና በተለያዩ ተግባራት በአንድነት የዋሉትን ወደ ተዘጋጀላቸው የመርከቡ ክፍል ለማሰናበት ይደውላሉ፡፡
ዛሬም ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ደወልን ለመንፈሳዊ አግልግሎት ትጠቀምበታለች፡፡ በሰዓታት በማኀሌትና
በቅዳሴ ጊዜ ደወል ይመታል፡፡ ድንገተኛና የምዕመናን ርዳታ የሚሻ ችግር በቤ/ክ ሲፈጠር ለኀዘንና ለደስታ /ንግሥ/ ጊዜያት ኁሉ ደወል
ይመታል፡፡ ቤ/ክ ጥሪዋነ የምታቀርብበት ኀዘኗን የምታሳውቅበት ደስታዋን የምትገልጥበት መሣሪያዋ÷ድምጿ ደወል ነው፡፡
ቃጭል
ከደወል ያነሰና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካህናት ለአገልግሎት የሚጠቀሙበት ነው፡፡ የቃጭል ድምጽ የወንጌላዊው ዮሐንስ ስብከትና
በዕለተ ዓርብ በእግረ መስቀሉ ኾኖ ያለቀሰው ምሳሌ ነው፡፡ በሥርዓተ ቅዳሴ ጊዜ ከደወል ጋረ በአንድነት ይጠቀሙበታል፡፡

ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ እየተመታ መገባቱ - ሰው አምላክ ሆነ ፣ አምላክ ሰው ሆነ የሚለውና ዜና ብሥራት ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ .
1÷14

ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ያልበቃችኹ ጸሎተ ቅዳሴውን ለመካፈል የመጣችኹ ግቡ ሲል ነው፡፡ ማቴ. 4÷17

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ክፍል ሦስት


//

ፃኡ ሲል - የሚታወቀው ቃጭል ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ያልበቃችኹ ወደ ክርስትና ለመመለስ ትምህርቱን ያላጠናቀቃችኹ ውጡ
ማለቱ ነው፡፡

በእግዚኦታ ጊዜ - የሚታወቀው ቃጭል - ጌታ ሆይ በደል ሳይኖርብኸ ለሰው ብለኽ ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀልን ተቀበልህ ሞትህ
እያሉ ያለቀሱት ልቅሶ ምሳሌ ነው፡፡

ሙዳይ- በንዋያተ ቅድሳት ውስጥ ሙዳይ የምንለው / እጣን ማስቀመጫን / ማቅረቢያን/ነው፡፡ በዚኽ ሙዳይ ውስጥ ካህኑ ቅዳሴ
ከመግባቱ በፊት ዐምስት ቆቀር መርጦ ያኖራል፡፡ ሙዳይ - የእመቤታችን ምሳሌ ነው ፤ በሙዳይ ውስጥ የሚቀመጠው ዕጣንም -
የጌታችን ምሳሌ ነው

መቅረዝ
ማብሪያ ፣ የመብራት ዕቃ ፣ የቀንዲል የሻማ መኖሪያ የሚቆም ወይም የሚንጠለጠል ባለብዙ አጽቅ ማለት ነው፡፡ ዘካ. 4፡2 ፣ ኢራ.
26፡17 በብሉይ ኪዳን ሙሴ እንዲሠራቸው ከታዘዛቸው ንዋየተ ቅድሳት አንዱ ነበር፡፡ ምሳሌውም ፡- ተቅዋም- የእመቤታችን
ምሳሌ ፤ ቅርንጫፎቿ ሰባት መኾናቸው - የፍጹምነት ምሳሌ፡፡ ምሳ. 24፡16
ሦስት መሸቢያ ከላይ መውጣቱ - በሦስቱ ዘመናት / ዘመነ መሳፍንት ፣ ዘመነ ነገሥት እና ዘመነ ካህናት / የተጻፉ መጻሕፍትን
ምሳሌ መካከለኛይቱ - የወንጌል ምሳሌ ፤ አዕፁቅ - የሐዋርያት የመምህራን ምሳሌ፡፡ አዕፁቅ ብርሃንን እንዲያሳይ
የመጽሐፍትን ምስጢር የሚገልጡ መምህራን ናቸው ፤ እሳቱ - የመስኮት ፣ ፈትሉ አምላካችን የነሣው ሥጋ ፣ ዘይቱ
የመንፈስ ቅዱ ምሳሌነት አላቸው፡፡

አትሮኖስ
አትሮኖስ መንበረ መጻሕፍትም በመባል ይታወቃል፡፡ አትሮኖስ የእመቤታችን ማሕፀን ምሳሌ ነው፡፡ መጽሐፍ የጌታ ምሳሌ ነው፡፡
ጽዋዕ
የጌታችን ክቡር ደሙ የሚከብርበት ነው፡፡ በዕለተ ዓርብ ጌታችን ተሰቅሎ ደሙን ባፈሰሰ ጊዜ መላእክት በብርሃን ጽዋዕ ደሙን
ተቀብለውታል፡፡
ምሳሌውም ፡- ጽዋዕ - የጌታችን ጎን ምሳሌ ነው ፤ ጎኑን በወጉት ጊዜ ደሙ እንደፈሰሰ እርፈ መስቀል ወደ ጽዋው በጠለቁ ጊዜ ደሙን
ይዘው ይወጣሉና ነው፡፡ አንድም- የእመቤታችን ምሳሌ ነው፡፡ ምክንያቱም ደመ መሲህን ይዟልና፡፡

ጻህል
ሕብስቱ ተለውጦ ወደ ሥጋ አምላክነት የሚለወጥበት ምስጢር ነው፡፡ ከወርቅ ፣ ከብረት ፣ ከብር ሊሠራ ይችላል፡፡ ምሳሌውም፡- ጻህል
የማሕፀነ ማርያም የቤተልሔም ዋሻ ፣ የጌታ መቃብርር የተወለደበት ግርግም ምሳሌ ነው፡፡

እርፈ መስቀል
ጨለፈ ፣ ቀዳ ፣ ጠለቀ ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ስያሜው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም ለምእመናን ስለሚሰጥበት
እርፈ መስቀል ተባለ፡፡ እንደ ማንኪያ ዓይነት የኾነ ቅዱስ ንዋይ ነው፡፡ በደሙ መቀበያ በኩል ጎድጎድ ያለ ቅርጽ ያለው ከወደታች መስቀል
ቅርጽ ያለበት ነው፡፡ ኢሳይያስ ከለምጹ የነጻበት ፍሕም መያዣ ጉጠት ምሳሌ ነው፡፡ ኢሳ. 6፡6
መሶበ ወርቅ
በቅዳሴ መዠመሪያ ሕብስተ መለኮቱን ይዞበት ዲያቆኑ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ከካህናት ጋር የሚገባበት ነው፡፡ ይኽ ከገሊላ ወደ
ኢየሩሳሌም ህብስተ ሕይወት ክርስቶስ ለመሔዱ ምሳሌ ነው፡፡
ጃንጥላ
በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ታቦተ ሕጉ በዐውደ ምህረት ሲወጣ ወርቃማ ቀለም አልያም እንደ በረዶ የነጣ ጃንጥላ ይዘረጋል፡፡
ቅዱስ መስቀል
ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ክፍል ሦስት
//

መስቀል የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዙፋን ነው፡፡ ጌታችን ክቡር ደሙን አፍስሶ ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ
ለዓለም የሰጠበት ነው፡፡
መስቀል የሚሠራባቸው ቁሶች ከምሳሌያቸው ጋር የሚከተሉት ናቸው፡፡

የእንጨት መስቀል - ጌታችን በእፀ መስቀል የመሰቀሉ ምሳሌ ነው፡፡


የወርቅ መስቀል - የባሕርይ ንጉሥ የመኾኑ ምሳሌ ነው፡፡
የመዳብ መስቀል - የአማናዊ ደሙ ምሳሌ ነው፡፡
የብር መስቀል - በአስቆሮቱ ይሁዳ ተላልፎ በ 30 ብር የመሸጡ ምሳሌ ነው፡፡
የነሐስ መስቀል - የብሩህነቱ ምሳሌ ነው፡ የነሐስ መስቀል /መዳብ መስቀል/ ንጹህ ሆኖ የፈሰሰው የአማናዊ ደሙ ምሳሌ ነው፡፡
የብረት መስቀል - በብረት የመቸንከሩ ምሳሌ ነው፡፡

የመስቀል ዓይነቶች
ዕፀ መስቀል - ጌታ የተሰቀለበት ነው፡፡
የመጾር መስቀል - በቅዳሴ ጊዜ ስራዒ ዲያቆን የሚይዘው ነው፡፡
የእጅ መስቀል - ሊቃነጳጳሳት ፣ ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናት የሚይዙት ምእመናንን የሚባርክበት ነው፡፡
የዐንገት መስቀል - ምእመናንን በማተባቸው አስረው በአንገታቸው በማድረግ ለጌታቸው ያላቸውን ፍቅር የሚገልጡበት ነው፡፡

እነዚኽ ከላይ የተገለጡት የመስቀል ዓይነቶች በቅርጻቸው የተለያየ ምስጢር ሲኖራቸው የተለያየ ስያሜም አላቸው፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!


የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብጹዓን ሰንበት ትምህርት ቤት
ትምህርትና ሥልጠና ክፍል
የሙከራ ፈተና ሦስት
የትምህርቱ ዓይነት ፡- ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

1. ንዋያተ ቅድስት ማለት ምን ማለት ነው;


2. ስለ ቅዱሳት አልባሳት አጠር ያለ ገላጻ በማድረግ ስለ ካባ ላንቃ ምንነት እና ምሳሌ አጠር ያለ ገላጻ ጻፉ;
3. ስለ ሙጥሃት ምንነት እና ምሳሌ አጠር ያለ ገላጻ ጻፉ;
4. ስለ ቅዳሴ እና ጸሎት መገለገያ ንዋየ ቅድሳት አጠር ያለ ገላጻ በማድረግ ስለ ጽናሐሕ ምንነት እና ምሳሌ አጠር ያለ ገላጻ
ጻፉ;
5. ስለ ደውል ምንነት እና ምሳሌ አጠር ያለ ገላጻ ጻፉ;

6. ስለ ቅዱስ መስቀል አጠር ያለ ገለጻ በማድረግ የመስቀል ዓይነቶችን ዘርዝራቹህ ጻፉ;

ማሳሰቢያ
- የሙከራ ፈተናው በ ቀጣይ በሌላ ወረቀት ወይም በጀርባው መልስ ተስርቶ መመለስ ይኖርበታል፡፡
- ተማሪዎች ከመማሪያ ጽኁፉ (ሃንድአውቱ) በተጨማሪ ተያያዥ ጉዳይ ላይ የተጻፉ ሌሎች አጋዥ መጽሃፍትን
እንዲያነቡ ይጠየቃሉ፡፡
- ተማሪዎች
ትምህርት እና ሥልጠናበሚያነቡት
ክፍል ርዐሰ ጉዳይ ዙሪያ ጥያቄ ቢኖራቸው ጥያቄያቸውን
ሥርዓተ ክፍል ሦስት ክፍል/ ለቤተአብርሃም
በጽሁፍ ለትምህርት
ቤተክርስቲያን
ክፍል/ ወይም ለሚመለከተው የክፍሉ አባለት ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
//

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ክፍል ሦስት

You might also like