Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 7

//

ክፍል ሥምንት

፫. ምስጢረ ጥምቀት

የጥምቀት የቃሉ ትርጓሜ

ጥምቀት ቃሉ አጠመቀ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲኾን ትርጓሜውም -.በገቢር ሲኾን መንከረ ፤ መድፈቅ ፤ መዝፍቅ በተግብሮ

ሲኾን መንክር ፤መድፈቅ ፤ መዝፈቅ ፤ መላ አካልን በውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲገለጽ ማጥመቅ ፤

መጠመቅ ፤ መጥለቅ ፤ መቀበር የሚሉትን ትርጓሜ ይሰጠናል፡፡ ጥምቀት ለልዩ ልዩ መጠሪያዎች ተጠርቶ ይገኛል፡፡ በግሪክ ኤጲፋንያ

በግእዝ አስተርእዮ በዐማርኛ መገለጥ ሲባል ቲዮፋኒ ተብሎም ይጠራል፡፡ ትርጓሜውም የሥላሴ መገለጥ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም

በጌታ ጥምቀት አብ በደመና ኾኖ የምወደው ልጄ ይኽ ነው ሲል ፤ ወልድ በተለየ አካሉ በእዳ ዮሐንስ ሲጠመቅ ፤ መንፈስ ቅዱስ

በርግብ አምሳል ኾኖ የታየ ወይም የተገለጠ ስለኾነ ነው፡፡ ጥንተ ስሙ ባብቲዝማ ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲኾን ትርጉሙም

አንድን ነገር ማቅለምን ያመለክታል፡፡ እደሚታወቀዉ አንድን ነገር የማቅለም ሥራ ለማከናወን ዕቃውን በቀለም ውስጥ መዝፈቅ

ወይም መንከር ግድ ይላል፡፡ ( በጥምቀትም ከርሱ ጋር ተቀብራቹኋል ፤ በርስዋም ከሙታን ለይቶ ባስነሣው በእግዚአብሔር

ረዳትነትና በሃይማኖት ከርሱ ጋር ተነሥታችኋል ) ቆላ. 2 ÷ 12 ተብሎ እንደተመሰከረ የጥምቀት ሃይማኖታዊ ተምሳሌትነቱ

ከክርስቶስ ጋር አብሮ መቀበር ነው፡፡

† ጥምቀት ለምን አስፈለገ

የመዠመሪያ ሰው አዳም ከትዕዛዘ እግዚአብሔር ዘንግቶ በምክረ ዳቢሎስ ተታሎ ዕፀ በለስን ከመብላቱ የተነሣ ሰው ኁሉ ኹለተኛ

ከውሃና ከመንፈስ በጥምቀት ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባ ዘነድ አይቻልም፡፡ እንዲል ዮሐ 3÷3-6

ስለዚኽም በጥምቀት - የኀጢአት ስርየት ይገኛል፡፡ ሐዋ 2÷38 ፤ ሐዋ 38÷22 ፤ 1 ቆሮ 6÷11

- ከክርስቶስ ጋር አብረን እንሞታለን፡፡ ከነርሱም ጋር እንነግሣለን፡፡ ሮሜ.6÷8 ፤ ሮሜ.6÷3-4፡፡ -- -----

- ከጌታችን ከኢየሱስ ጋር አንድ እንኾናለን፡፡ ገላ 3÷27

- የቅድስት ቤተክርስቲያን አባል እንኾናል፡፡ ቆላ 2÷11

† ጥምቀት በብሉይ ኪዳን

ጥምቀት እንድ ውሃ ፈሳሽ እንድ እንግዳ ደራሽ የተፈጸመ ምስጢር ሳይኾን አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን በነቢያት ትንቢት እና ምሳሌ

የተገለጠ ምስጢር ነው፡፡ ይኸውም ዳዊት ስለ ጥምቀት በተናገረው ቃሉ

 ባሕር ዐይታ ሸሸች ዮርዳኖስ ወደ ኋላው ተመለሰ ብሎ ተነግፘል፡፡ መዝ 113÷3-4

 የእግዚአብሔር ድምጽ በውኾች ላይ አምላክ እንጎደጎዳ እግዚአብሔር በብዙ ውኾች ላይ መዝ 29÷31 መዝ 67÷22 በማለት

ስለጥምቀት አስቀድሞ ትንቢት ተናግሯል፡፡

 ጥሩ ውሃንም እረጭባቹኋለኹ፡፡እናንተም ትጠራላቹ …ዐዲስም ልብ እሰጣቹኋለኹ ሕዝ 36÷26 ይላል፡፡

 ተመልሶ ይምረናል ክፍተታችንም ይጠቀጥቃል ኀጢአታችንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል፡፡ ሚክ 7÷19 ተብሎ ተፅፏል፡፡

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ትምሕርተ ሃይማኖት ክፍል ሥምንት


//

† የጥምቀት ምሳሌ በብሉይ ኪዳን

አብርሃም ለዐምስት ነገሥተ ሰዶም ረድቶ አራቱን ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን ወግቶ ድል ነሥቶ ሲመለስ ኃይል ቢሰማው

ልጅኽን ከሰማየ ሰማይ ይወርዳልከድንግል ማርያም ይወለዳል ብለኽ ነበር ፤ ከዚኽ ዘመን ደርሼ የቃሉን ትምህርት የእጁን

ታምራት ዐያለሁን? ይቀርብኛል ብሎ ጸለየ፡፡ ጌታም ከማረከው ዐሥር አንዱን ይዘኽ ዮርዳኖስን ተሸግረኽ ከመልከ ጼዴቅ

ዘንድ ድረስና አምሳሉን ታያለኽ እንጂ ከዘመኑ አትደርስም አለው መልከ ጼዴቅንም አብርሃም ይመጣልሃልና ኅብስተ

አኮቴትን ጸጋዓ በረከትን ስጠው አለው፡፡ መልኬ ጼዴቅም ብሩኩ ቅዱስ ለእግዚዘብሔር ፤ የእግዚአብሔር ወዳጅ ብሎ

ሰጠው፡፡ ዘፍ 1÷17-18 አብርሃም ሕብስቱን በልቶ ወይኑን ጠጥቶ ፤ ከዐሥር አንዱን ሰጠው፡፡

ምሳሌዉም፡- ዮረዳኖስ የጥምቀት ፤ አብርሃም የምዕመናን ፤ መልከ ጼዴቅ የካህናት ኅብስት አኮቴት ጽዋዓ በረከት

- የሥጋው የደሙ አምሳል ነው፡፡ አብርሃም ዮርዳኖስ ባይሻገር መልኬጼቅን ባለወቀውም ነበር ፤ ምእመናንም ባይጠመቁ ሥልጣነ

ክህነትን ባላውቁም ነበር፡፡ ሥልጣነ ክህነነትን ለማሳወቅ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፡፡ አብርሃም ለመልከ ጼዴቅ ፤ አብርሃም ዮርዳኖስን

ተሸግሮ ባይኼድ መልከ ጼዴቅን ባላወቀውም ነበር፡፡ እንዳላ ቄርሎስ

በተጨማሪ በጻድቁ አብርሃም ዘመን ግዝረትን የፈጸሙ 1 የተገረዙ / ኁሉ የአብርሃም ልጆች / ይባሉ እንደ ነበር ያልተገረዙ ኁሉ

ከአብርሃም ልጅነት የወጡ ነበር፡፡ አኹንም የተጠመቀ ኁሉ - የእግዚአብሔር ልጅ በመባል ሲኖር ፤ ያልተጠመቀ ደግሞ -

ከእግዚአብሔር ልጅነት ይለያሉና ግዝረት ለጥምቀት ምሳሌ ኾነ፡፡ ዘፍ. 17 ÷ 14 ፤ 2 ቆሮ. 2÷10-12

ኢዮብም ደዌ ሥጋ ታሞ ሳለ - ከጌታዮ ከፈጣሪዮ የሚያወቃቅሰኝ ጽኑ ዳኛ ፤ የውል ሸማግሌ አይገኝም እንጂ ባገኝስ

በጥሬ ዱቄት ባንድ ዱቄት ባንድ ኹለት በተከፈልኹት ነበር፡፡ ጌታም ከአምላክ መዋቀስ ትችላለኽን መወቃቀስ ይቅርና

ምድርን በምን ላይ ዘርግቻታለኹ ፤ አቁሜያታለኹ መጠኗስ ምን ያኽል ነው ቢለው አቤቱ እንዲኽማ ካልከኝ አፌን በእጄ

እይዛለኹ እንጂ አለው፡፡ ኢዮ 38÷4 ጌታም የኢዮብን ትህትና ዐይቶ በዮርዳኖስ ታጠብ አለው ቢታጠብ ከዳዌው

ተፈወሰ፡፡ ምሳሌውም ፡- ዮርዳኖስ - የጥምቀት ፤ ኢዮብ - የምእመናን ፤ ደዌው - የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ

አምሳል ነው፡፡

ንእማን ሶርያዊም ለምድ ቢወጣበት ከደዌዮ ቢፈውሰኝ ብሎ ወርቅ ይዞ ወደ ኤልሳዕ ሲኼድ ፤ በዮርዳኖስ ታጠብ ብሎ

ከመንገድ ሳለ ላከበት ነቢየ እግዚአብሔር ሲባል ለቃሉ ጸለዮ ለእጁ ዳሶ ፈውሰኛል ብሎ ነበር እንጂ የውሃ ውሃ ምን አለኝ

ቃሀ እንዲሉ ፤ የውሃ ውሃማ የዐገሬ ውሃዋች ባብና ፋረስ ምን አሉኝ ብሎ ወደ ዐገሩ ሊኼድ ሠረገላውን መለሰ፡፡ ባብና

ወፍርፋ እንዳለ ሰዋቹ ግን ቢኸን ትፈውሳለኸ ፤ ባይኸን የዐገርኽ መንገድ ይቀርብሀል ታጠብ አሉት ፤ ቢታጠብ ተፈወሰ፡፡

ወርቁን ግምጃውን ወስዶ ኤልሳዕን እነኾን ተቀበለኝ ቢለው የእግዚአብሔርን ጸጋ ለማወቅ ፤ በብር እሸጠዋለኹን

አልቀበልም አለው፡፡ 2 ነገ. 5÷6-20

ምሳሌውም ፡- ዮርዳኖስ - የትምቀት ፤ ንእማን - የምእመናን ፤ ለምዱ - የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ አምሳል

ነው፡፡

የኖኅ መርከብ - የጥምቀት ምስል ስትኾን በመርከቧ ተጠልለው የዳኑ ሰዋች - የአማንያን ምሳሌ ፤ በንፍር ውሃ የጠፍ -

የኢ አማንያን ምሳሌ ናችው፡:በመርከብ ውስጥ የነበሩት እንደዳኑ - በጥምቀት አምነው የተጠመቁ ኁሉ ከሲኦል ባሕር

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ትምሕርተ ሃይማኖት ክፍል ሥምንት


//

ከመስጠም ሲድኑ ፤ ከመርከቧ ውጭ የነበሩት ሰጥመው እንደ ጠፍ - በጥምቀት ባለማመን ጸንተው ያልተጠመቁም

በሲኦል ባሕር ሰጥመው ይቀራሉ፡፡ ዘፍ. 7÷17 1 ጴጥ. 3÷20-22

እስራኤላዊያን በግብጽ ከ 430 ዘመን በላይ በግዝረት / በባርነት / ከመኖሩ በኋ እግዚአብሔር አምላክ ከዚኸ ስቃይ

ለማውጣት ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴን ከመካከላቸው አሥነስቶ በግዞት ከነበሩበት ከግብጽ ባርነት ነፃ የወጡት ባሕረ

ኤርትራን ከተሻገሩ በኋላ ነው፡፡ ባሕረ ኤርትራ ለፈርዖንና ለሰራዊቱ ሞትን ሲያስከትል ለእስራኤዊያን ግን ሕይወት ፤

ደስታንና ነጻነትን አጎናጽፏቸዋል፡፡ ክርስቲያኖችም በጥምቀት በርኩሳን አገንንት ከመገዛት ከዘላዓለም ሞት ነፃ ወጥተዋል

የኤርትራን ባሕር ለፈርዖንና ለስራዊቱ ድል መንሻ እንደ ኾነ በጥቅምትም አጋንንት ድል ኾነዋል፡፡ እስራኤላውያን -

የክርስቲያን ፤ ግብጻውያን - የአጋንንት ፤ ባሕርረ ኤርትራን መሻገራቸው -የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ 2 ቆሮ. 10 ÷ 1 – 2

ትንቢቱን ያናገረ ምሳሌውን ያስመሰለ እሱ ባወቀ አይደለምን ምስጢሩ እንደምንድር ነው ቢሉ አዳምና ሔዋን ከገነት

ወጥተው ለደብር ቅዱስ ሳሉ ዲያብሎስ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ስቃይ አጸናባቸው ፤ ወዲያው ምትሐቱን ጥቂት ብርሃን

አስመስሎ ቢያሳያቸው አንተ ባለብርሃን ይኽን ጨለማ አርቅልን አሉት፡፡ ስመ ግብርነታችኹን ጽፋችኹ ስጡኝና

ላርቅላችኹ ቢላቸው በመከራ ያሉ ናቸውና ይኹንብን ጻፍብን አሉት፡፡ በብራና ብጽፋ ይደመስሳል ፤ ብሎ አዳም ገብሩ

ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ ብሎ በኹለት ዕብና ሩካም ቀርጾ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲዖል መካከል ጥሎት ነበርና

የአዳምንና የሔዋንን ስመግርናት በኪደተ እግሩ ለማጥፋት በዮርዳኖስ ተጠመቀ የዕዳ ደብዳቤዎቻችንን አጠፋልን

እንዳለ፡፡ ቆላ. 2÷14

† የጥምቀት አመሠራረት በሐዲስ ኪዳን

ጥምቀት በሓዲስ ኪዳን የመሠረተው የኁሉ መሠረትና መሥራች የኾነው ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

ነው፡፡ ሲመሠርተውም በሦስት መልኩ ነው፡፡

1. በትምህርት - ጌታ ለኒቆድሞስ ስለ ምስጢረ ጥምቀት ሰው ዳግመኛ ከውሃን ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔርን

መንግሥት ሊያይ አይችልም ብሎ አስተምሮታል ዮሐ›3 ÷5

2. በትዕዛዝ - ሐዋርያትን መርጦ ካጸናቸው በኋላ ርሱ ወደ ሰማይ እንዳረገ ዓለምን ዞረው ወንጌልን እንዲሰብኩ አሕዛብንና

ያላመኑትን ኁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርቴ አድርጉ ብሎ በማዘዝ መሥርቶታል፡፡

ማቴ. 28 ÷19

3. በተግባር - እኛ ክርስቲያኖች ራሱ አምላክ ከኀጢአት በቀር ሲያደርጉ ለልጅዎቹ አድርጉ ያለን አንዳች ነገረ የለም፡፡ ተጠምቆ

ተጠመቁ ፤ ጾሞ ጹሙ ፤ መከራ ተቀብሎ ተቀበሉ፡፡ ስለዚኸ ጥምቀቱንም በሠላሳ ዘመኑ በእደ ዮሓንስ በባሕረ ዮርደሰኖስ ተጠምቆ

በተግባር መሥርቶታናል፡፡ በምስጢረ ጥምቀት ሙሉ ጸጋ የተሰጠው ግን በበዓለ ሃምሳ ለሐዋርያት በጽርሓ ጽዮን የመንፈስ ቅዱስ

ጸጋ መውረድ በኋላ ነው፡:

† የእግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ ጥምቀት

የተነገሩ ትንቢቶችንም ኾነ ሲሠራባቸው የቆዩትን የጥምቀት ምሳሌዎች ወደ አማናዊነት በተግባር የለወጣቸውና የፈጸማቸው

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ያን ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ፈቀደለት ኢየሱስ

ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ እነኾ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በራሱ ላይ ሲቀመጥ

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ትምሕርተ ሃይማኖት ክፍል ሥምንት


//

ታየ እነኾ ድምጽ ከሰማይ መጥቶ በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይኽ ነው አለ፡፡ ማቴ 3÷13-17 ማር 1÷11 ፤ ሉቃ 3÷21-

22 ፤ ዮሐ 1÷32-33 ወንጌላውያን በአንድ ቃል እንደገለጹት የክርስቶስ ጥምቀት የአንድነትና የሦስትነት ሕልውና የተገለጸበት

ምስጢር ነው፡፡ እስከ ሐዋርያት ትምህርት ድረስ የነበሩ ሰዎች ያውቁት የነበረው የዮሐንስ ጥምቀት ብቻ ነበር ግን የጸጋ ልጅነት

አላገኘበትም፡፡ ይኽን ያስገኘው የጌታ ጥምቀት ነው፡፡ የጌታ ጥምቀት በመንፈስ ቅዱስ ኾኖ ፍጹም የኀጢአት ስርየት ልጅነትን

የሚያሰጥ / ያሰጠ / ሲኾን የዮሐንስ ጥምቀት ግን ለንስሐ በውሃ ብቻ ነበር፡፡ ሐዋ 19÷1-5 በዚኽም የተነሣ የጥምቀትን ትምህርት

ያስተማረው በተግባርም ያሳየውና ሐዲስ ኪዳንን ጥምቀት የመሠረተው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ 1 ጴጥ 2÷21

መች ተጠመቀ ቢሉ ፡- ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በሠላሳ ዘመኑ በዘመነ ሉቃስ በወርኀ ጥር በ 11 ኛው ቀን

ማግሰኞ ዕለት ከሌሊቱ በዐሥር ሰዓት ነው፡፡

† ለምን ተጠመቀ ቢሉ ?

እከብር አይል ክቡር አጽድቅ አይል ጻድቅ የኾነ አምላክ ለምን መጠመቅ አስፈለገው ቢባል እንደ አይሁድ የመንጻት ልማድ

ከኀጢአት ለመታጠብ ወይም ደግሞ እንደ ኀጥአን መጽብሐን ከዮሐንስ ዘንድ ለንስሐ እንደ ተጠመቁት ጥምቀት አይደለም፡፡ ዘሌ.

15÷1-8 ፤ ማቴ. 3÷5-6

ይልቁንም ስለሚከተሉት ምክንያቶች እንጂ፡-

 ለእኛ ሥርዓተ ጥምቀትን ( ዳግሞ ልደትን ) ለመመሥረት፡፡ ዮሐ. 13÷12-19

 ትሕትናን ለማስተማር - ዮሐንስን መጥተሕ አጥምቀኝ ከማለት ይልቅ ወደ እርሱ ኼዶ በባርያው እጅ መጠመቁ

ትሕትናውን ያሳያል፡፡ መምጣቱ ደግሞ ለዮሐንስ ክብር ስለኾነ ክብሩን በሚያመለክት የክብር ቃል መጥምቁ ዮሐንስ

ተባለ፡፡ ምነው ጌታ ፈጣሪ እግዚእ ሲኾን ወደ ትሁት ዮሐንስ ኼደ ቢሉ -ሥጋ መልበሱ ለትህትና ነውና፡፡ በዚያውም

ላይ ለነገሥታት ለመኳንት ቀሳውስትን መጥታችኹ አትምቁን ባሉ ነበርና፡፡ እኔ የሰማይንና የምድር ንጉሥ ስኾን ፤

ኼጄ ተጠምቄያለኹና እናንተም ኼዳችኹ በቀሳውስት እጅ ተጠመቁ ሲል ነው፡፡

 ውሃውን ለመባረክ - ለጥምቀት ልጅነትን የሚያሰጥ ይኾን ዘንድ ኃይልን ለመስጠት፡፡

 አንድነትንና ሦስትነትን ለመግለጥ ነው፡፡

 በትንቢት የተነገረውን ኁሉ ለመፈጸም

 የአዳምን የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስ

† በሠላሳ ዘመኑ ለምን ተጠመቀ? ቅዱስ ዲዮስቆሮስ

በግልጽ ተመላለሰ እንደ ሰውም ታየ በየጥቂቱ አደገ በሠላሳ ዘመኑ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፡፡ በማለት ጌታ በሠላሳ ዘመኑ መጠመቁን

አረጋገጧል፡፡ ሉቃ 3÷23 ጌታ በሠላሳ ዘመኑ ለመጠመቁ ምክንያት ነበረው ይኸውም፡-

 ለጊዜው በሕገ ኦሪት መሠርት ለክህነት አገልግሎት መመረጥ የሚዠምረው በሠላሳ ዘመን ነበርና እርሱም የሊቀ ካህናት

ተግባር ፤ መምህርነቱንና የአዳኝነቱ ሥራ በጥምቀት በሠላሳ ዘመኑ ዠመረ፡፡ ዘኁ. 4÷23 ፤ ዘኁ. 4÷1-3 ፤ ዘኁ. 46÷48

፤ 1 ዜና. 23÷24 ፤ዕዝ. 3÷8

 አዳም የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ኾኖ ተፈጥሮ በአርባ ቀን ያገኛትን የልጅነት ጸጋ በኀጢአት ምንክንያት ስለአስወሰደ አዳም

የተወሰደበትን ልጅነት ለማስመለስ ጌታ በሠላሳ ዘመኑ ተጠምቋል፡፡

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ትምሕርተ ሃይማኖት ክፍል ሥምንት


//

 ክህነት በዚኽ ዕድሜ መሰጠት / መፈጸም / እንዳለበት ሊያስተምረን ነው፡፡ ከዚኽ ዕድሜ በፊት ትምህርቱን ቢያጠናቅቅ

እንኳን የሰከነች ዕድሜ ሠላሳ ዘመን / ዓመቱ / ካልኾነ አይሾምም፡፡

† በማን ስም ተጠመቀ

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጌታን ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለኹ አንተን በማን ስም ላጥምቅሕ በአብ ስም

እንዳላጠምቅሕ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅሕ ወልድ አንተነሕ በመንፈስ ቅዱስ ስም

እንዳላጠምቅሕ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትሕ ባንተም ሕልው ነው፡፡ ታዲያ በማን ስም ላጥምቅሕ ብሎ ቢጠይቀው ጌታም መልሶ -

እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕሪ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ ብለኽ አጥምቀኝ አለው

እንደተባለውም መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስም ጌታውን አጥምቆታል፡፡

† መንፈስ ቅዱስ ለምን በግብር አምሳል ወረደ?

 በኖኅ ዘመን ርግብ የጥፋት ውሃ ጎድሏል ስትል የወይራ ዝንጣፊ ይዛ መጥታለች፡፡ መንፈስ ቅዱስም የኀጢአት ባሕር

ጎደለ ሲል በርግብ አምሳል ወረደ፡፡

 አንድም ርግብ ቢመቷት ቢያባፘ እንቁላሏን ቢያበላሹባት ቢሰብሩባት ቤቷን ካላፈረሱባት በስተቀር ቦታዋን አትለቅም፡፡

መንፈስ ቅዱስ ኀጢአት ሠርተውፈፁም ካልካዱት በቀር ከፍጥረታቱ አይለይም፡፡

 ርግብ የዋህ ናት ቂም በቀልም አትይዝም መንፈስ ቅዱስም በቀል ይቅርባይነውና በርግብ አምሳል ወረደ፡፡ ስለዚኽ

በአምሳለ ርግብ ወረደ፡፡

 አወራረዱም አንድ ክንፉን ወደላይ አንድ ክንፉን ወደታች አደርጎ አሰይፎ ነው ያሉ እንደኾነ አብ ብሉየ መዋዕል ሕይወት

ነው አንተም ብሉየ መዋዕል ሕይወት ነኽ እኔም ብሉየ መዋዕል ሕይወት ነኝ ሲል ነው፡፡

† ለምን በውሃ ተጠመቀ ?

ጥምቀት በውሃ የኾነበት ምክንያት እንደሚከተለው እንመለከታለን ፡-

 ነብዩ ሕዝቅኤል የነበረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ሕዝ. 3÷6-25

 ውሃ የሕይወት ምልክት ነው፡፡ ዘፍ. 2, ፤ ዮሐ. 1÷14, ፤ መዝ. 1÷3 ፤ ራዕ. 21÷6 ፤ ራዕ. 22÷1 ፤ ዕብ, 10÷22

 ውሃ አሳትን ያጠፋል እናንተም ብትጠመቁ ከገሃነም እሳት ትድናላችኹ ሲል ነው፡፡

 ውሃ በኁሉም ቦታ ለኁሉም ሰው ይገኛል ጥምቀት ለመላው የሰው ዘር የተሰጠ ነው፡፡

 ውሃ የሰውነት ጉድፍ እንደሚያጠራ ኹሉ እንደዚኹ በውሃ የሚደረግ ጥምቀት የነፍስን እድፍ ያስወግዳል ያነጻል፡፡

ከጥንት ዠምሮ ውሃ ለሰው ልጅ ሕይወት ሰጪ ነው በውሃ መጠመቅ የዐዲስ ሕይወትና የመንጻት ምልክት ነው፡፡

እንዲኹ የአሮጌ ሰውነት / ሰው / ሞትና የዐዲስ ሰው በድጋሚ መነሣት ነው፡፡ ውሃ የማንጻት ኃይል አለው፡፡ የጥምቀት

ውሃ ተራ ውሃ አይደለም፡፡ ነግር ግን የእግዚአብሔር ቃል ያለበት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሌለበት ውሃ ተራ ውሃ

ነውና የእግዚአብሔር ቃል ያለበት ግን የማንጻት የመቀደስ ኃይል አለው፡፡ የሕይወት ውሃ ነውና፡፡ በዐዲስ ልደት

በሚኾን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ የሚያድን ነው፡፡ ቲቶ 3÷5-7

 ውሃ ውሂዝ ነው ማለትም ፈሳሽነው ፤ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይደርሳል ምስጢረ ጥምቀትም በውሃ ይፈጸማል፡፡

 ውሃ አትክልት ያለመልማል ማርና ወተት ግን ያደርቃል ውሃ አትክልትን እንድሚያለመልም በውሃ ተጠምቀን

ልምላሜ ሥጋና ነፍስን እንድናገኝ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በውሃ እንድንጠመቅ አዘዘን፡፡

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ትምሕርተ ሃይማኖት ክፍል ሥምንት


//

 ዕብ. 11÷29 በውሃ ፈርኦን ድል እንደነሣን እጅም በውሃ ተጠምቀን ኀጢአትን ድል አነሣልን፡፡ ይኸውም ግብጽን

በውሃ ካጠፋ በኋላ ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ

በውሃ ተጠመቀ፡፡

 አንድም ማርና ወተት ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም፡፡ ውሃ ግን ከላይ እንደገለጽነው ለኁሉ ይገኛል ለኁሉ

በሚገኘው ሲል በውሃ ተጠመቀ፡፡ጥምቀትም መሠረቱ በኁሉ ነውና እንዳለ አብጥሊስ

የክርስቲያኖች ጥምቀት

ሰዎች ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔር መንግሥት አይወርስም እንደተባለ የእግዚአብሔርን መንግሥት

ለመውረስ እምነታችንን ለማጽናት ከሥላሴ ልጅነት ለማግኘት ከማኅፀን ዮርዳኖስ ከአብራክ መንፈስ ቅዱስ በጥምቀት

እንወለዳለን፡፡ ዮሐ 3÷5 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዐመታት ደረጃ ለጥምቀት የተወሰነ የዕድሜ ገደብ

የለም፡፡ ነገር ግን ወንድ ልጅ በ 40 ቀን ሴት በ 80 ቀን ትጠመቃለች፡፡ ሕፃናት እንደሚጠመቁ የሚደረገው መጽሐፍ ቅዱስን

መሠረት በማድረግ ነው፡፡

† ሕፃናት ሳያምኑ ለምን ይጠመቃሉ

 የመዠመሪያዎቹ ሰዎች አዳምና ሔዋን ከተፈጠሩበት ሥፍራ ከኤልዳ ወደ ገነት የገቡት አደዘም በ 40 ቀኑ ሲኾን ሔዋን

ደግሞ በ 80 ቀኗ ነው፡፡ በዚኽ መሠርት ልጅነት የሚያገኙበት በእግዚአብሔር መንግሥት የሚታጩበት ጥምቀት

ታጠምቃለች፡፡ ኩፋ. 4÷9

 በቤተሰባቸው እምነት ሕፃናትን ታጠምቃለች፡፡ ማር. 2÷5 ፤ ማቴ. 15÷22-28

 እኛ የምናስበው ስለ ሕፃናት ሰማያዊ ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን እውነት እውነት እልሃለው ሰው ከውሃን ከመንፈስ

ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔርመንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ዮሐ. 3÷5 ስላለ ነው፡፡ታዲያ ስለምን ሕፃናት

አናጠምቅም? ስለምንስ ለእግዚአብሔር ፍርድ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን ጌታችን የላይኛውን ኃይልለ ቃል ሲናገር

ሕፃናትን አልተወም፡፡

† አንዲት ጥምቀት

ጥምቀት የማይደገም አንድ ብቻ የኾነበት ምክንያት፡-

 በሥጋ ከወላጆቻችን የምንወለደው አንድ ጊዜ ብቻ እንደኾነ ኹሉ ከመንፈስ አባታችን የምንወልደው መንፈሳዊ ልደታችንም

አንድ ጊዜ ብቻ ስለኾነና ስማይደገም፡፡ ዮሐ 3÷6-8

 የጥምቀት ምሳሌ የኾነው ግዝረት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚፈጸም ጥምቀትም አንድ ጊዜ ብቻ ይፈጸማል፡፡ ቆላ 2÷11-13

 ከጌታ ሞትና ትንሣኤ ተሳታፊ የምንኾንበት ምስጢር በመኾኑ ጌታም የሞተውና የተነሣው እንድ ጊዜ ብቻ ነውና፡፡ ቆላ 2÷12 ፤

ሮሜ 6÷3-41
†. ጥምቀት በቅዱሳን አባቶች አንደበት
የሚያስተምር ከመጠመቃቸው በፊት ሰዎችን ይኽን ትምህርት ያስተምር ፤ እንዲኽ ይማሩ እንዲኽ ይመኑ ፤ እንዲኽ ይታመኑ ፤ እንዲኽ በሥላሴ
ስም አምነው ይጠመቁ የሦስቱ አካላት መለኮት አንድ እንደኾነ ሐዋርያት ያስተማሩዋት ቅድስት ቤተክርስቲያን የተቀበለቻቸው ቅዱሳት
መጽሐፍት የተናገሩትን ኁሉ ይመኑ፡፡ ማቴ. 28 ፤ ማቴ. 19 ፤ 1 ጢሞ.4÷11-16 ፤ ዮሐ.20÷31 ቅዱስ ቄርሎስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብጹዓን ሰንበት ትምህርት ቤት

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ትምሕርተ ሃይማኖት ክፍል ሥምንት


//

ትምህርትና ሥልጠና ክፍል

የሙከራ ፈተና - ሥምንት

የትምህርቱ ዓይነት ፡- ትምሕርተ ሃይማኖት

1. ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው;


2. ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ምን ይመስላል;
3. ከጥምቀት ምሳሌዎች ውስጥ አንዱን ጠቅሳቹህ አብራሩ;
4. ጥምቀት ለምን ያስፈልጋል;
5. ስለ እግዚኣብሔር ወልድ ጥምቀት አጠር ያለ ጽሁፍ ጻፉ;
6. ሕጻናት ሳያምኑ ለምን ይጠመቃሉ;

ማሳሰቢያ

- የሙከራ ፈተናው በ ቀጣይ በሌላ ወረቀት ወይም በጀርባው መልስ ተስርቶ መመለስ ይኖርበታል፡፡
- ተማሪዎች ከመማሪያ ጽኁፉ (ሃንድአውቱ) በተጨማሪ ተያያዥ ጉዳይ ላይ የተጻፉ ሌሎች አጋዥ መጽሃፍትን
እንዲያነቡ ይጠየቃሉ፡፡
- ተማሪዎች በሚያነቡት ርዐሰ ጉዳይ ዙሪያ ጥያቄ ቢኖራቸው ጥያቄያቸውን በጽሁፍ ለትምህርት ክፍል/
ለቤተአብርሃም ክፍል/ ወይም ለሚመለከተው የክፍሉ አባለት ጥያቄያቸውን መቅረብ ይችላሉ፡፡

ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ትምሕርተ ሃይማኖት ክፍል ሥምንት

You might also like