Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 81

⚜🙏⚜🙏⚜ዜማ⚜🙏⚜🙏⚜

#ዜማ_እንዴት_እና_መቼ_ተጀመረ❓

🤲🙏ምስጋናን በዜማ ማቅረብ ከሥነ ፍጥረት የተጀመረዉ በመላእክት ዘንድ ኋላም በሰው ልጆች ነዉ።ስለ መላእክት ምስጋና
እንዲሁም በዜማ ስለማመስገናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደዚህ ሰፍሮ ይገኛል።

👉የተፈጠሩትን ሁሉ እኔን ለማመስገን ፈጠርኳቸው። ኢሳ ፵፫÷፯

👉የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግኑ ዘንድ አዳምን ከልጆቹ ጋር ፈጠረው። ፫ኛ መቃ.፪÷፲፪

👉ሱራፌልም በዙርያዉ ቆመው ነበር … አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ፣ቅዱስ ፣ቅዱስ ፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ምድር ሁሉ በክብሩ
ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር፡፡ ኢሳ ፮÷፪-፫

👉ቅዱሳን መላእክት ሃያ አራቱን ሰዓት ምስጋናቸው እረፍት እረፍታቸው ምስጋና ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረዉና ያለዉ ፣
የሚመጣዉም ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ እያሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።ራእይ ፬÷፰

👉በምስጋና ቃል እግዚአብሔርን እንደሚያመሰግኑት መላእክት እንሁን... በዜማ የሚያመሰግኑ አሉ የሚዘምሩም አሉ፡፡ ቅዱስ
አትናቴዎስ

⚜ዜማ(መዝሙር) አጀማመር - በሕገ ልቦና

🙏በሰዉ ልጆች ዘንድ ከሀዘንና ከመገለል ከብቸኝነት ከትካዜ የተነሳ ዜማ ማኅዜኒ (የኀዘን ዜማ) ቀድሞ እንደተጀመረ አበዉ
ይተርካሉ።

#ዮባል መከራ ስለጸናበት የቃየልን በደል እያስታወሰ በገና በመደርደር ድምጹን እያሰማ የሐዘን እንጉርጉሮ /ማኅዘኒ/ ያሰማ
ነበር።እርሱም በገናና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበር እንዲል። ዘፍ ፬÷፲፮

🙏ዜማ በሕግ ጠባያዊ የተገኘ ስለነበር በጊዜ ብዛት ሥጋዊ ፍትዎትን ቀስቅሶ በደብር ቅዱስ የነበሩ የሴት ልጆችን ሳይቀር ወደ ጥፋት
መርቷል፡፡ ሄኖክ ፭÷፫-፰

🙏 በሕገ ተፈጥሮ ተገኘውን ዜማ ተከትለው ደግሞ ደጋግ አበው አማናዊ መዝሙር ዘምረዋል።

👉አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ የሰሌን ዘንባባ (በቀልት)ይዞ ሰባት ቀን መሠውያውን እየዞረ በሰንበት ዘምሯል፡፡ ኩፋ፲፫÷፳፩

⚜ዜማ(መዝሙር) አጀማመር- በሕገ አሪት

#ቅድመ_ቅዱስ_ዳዊት

👉እስራኤል ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ ማርያም እህተ ሙሴ ከሕዝቡ ጋር በከበሮ ለእግዚአብሔር ዘምራለች፡፡ ኦሪት ዘጻ.
፲፭÷፲፱-፳፩

👉በእስራኤል ላይ ስትፈርድ የነበረችው ነቢዪቱ ዲቦራ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ዘምራለች፡፡ መጽ. መሳ. ፭÷፩-፴፩
#በቅዱስ_ዳዊት_ዘመን

👉ቅዱስ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት የሚዘምሩ መዘምራንን ማደራጀቱ ተጽፏል፡፡ ፩ኛ ዜና ፲፮÷፬-፲፯

👉 ቅዱስ ዳዊት ለፍርድ አደባባይ በማይውልበት ቀን ከመዘምራኑ ጋር በአንድነት በበገና ይዘምር ነበር፡፡ ፩ኛ ዜና ፮÷፴፩-፵፬ ነህምያ
፲፪÷፳፰-፵፯

👉ሕዝበ እስራኤል

➡️በበዓለ ፋሲካ መዝ.፻፲፪ ፣ ፻፲፯ ፣ ፻፴፬

➡️በዕለተ ሰንበት መዝ.፺፩ ፣ ፺፱

➡️በመባቻ ቀን መዝ.፹÷፩-፱ ይዘምሩ ነበር፡፡

🛎#ማጠቃለያ

🙏#ዜማ_ከክርስቶስ_ልደት_በፊት 🙏
ምንም እንኳን ዜማ ከመላእክት ጋር አብሮ የተገኘ መሆኑን ከላይ ገልጠን በማስረጃ ያቀረብን ቢሆንም ዜማ ከክርስቶስ ልደት በፊት
በሰዎች ዘንድ እንዴት ተጀመረ? ብሎ መመርመሩ አስፈላጊ ይሆናል። በመሠረቱ ይህ ርዕስ በጣም ሰፊና ጥልቅ ምርምርን የያዘ
እንደመሆኑ መጠን ዜማ እንዴት? የት?መቼ?ማን ጀመረው?በሚባልበት ጊዜ በዚህ ጊዜ ተጀመረ እገሌ ጀመረው ለማለት አስቸጋሪ
ይሆናል፤ምክንያቱም አንዳንድ ሊቃውንት ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ አብዛኞቹ የሚሰጡት መልስ ከ፭ኛው መቶ ዓመት ወይም ክፍለ
ዘመን ወዲህ ስለተደረገው ድርጊት እንጅ ከዚያ በፊት ስለሆነው ሁሉ አብዛኛውን ጊዜ ሊቃውንቱ የሚረዱበት የዜማ ታሪክና የሥነ
ጽሑፍ ዕድገት እንዳሁኑ ጎልቶ ያልታየበት ዘመን ከመሆኑም በላይ ዘመናቱም በቁጥር ሲለኩ እጅግ ርቀት ያላቸው ሆነው
በመገኘታቸው ለተጠየቀው ጥያቄ እምብዛም ያህል አጥጋቢ መልስ ለማግኘት አዳጋች ሆኖ ይገኛል ፤ ሆኖም ዓይነ ህሊናችንን ወደ
ቅዱስ መጽሐፍ መለስ አድርገን ስንመለከት ጉልህ የሆኑ አንዳንድ ማስረጃዎችን እናገኛለን፤ ይህውም በኦሪት ዘፍጥረት በምዕራፍ ፬
ከቊጥር ፲፮- ፳፪ ያለውን ስናነብ የቃየል ስድስተኛ ትውልድ በሆነው በዩባል ጊዜ የዜማ ወይም የሙዚቃ መሣሪያዎች እንደነበሩ
ለመረዳት እንችላለን ፤ቃሉም እንደዚህ የሚል ነው “ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ ከኤደንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር
ተቀመጠ፤ ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም ፣ሄኖኅንም ወለደች ከተማም ሠራ፤ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖኅ አላት ሄኖኅም
ጋይዳድን ወለደ፤ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ፤ሜኤልም ማቱሳኤልን ወለደ፤ማቱሳኤልም ላሜኅን ወለደ፤ለሜኅም ለራሱ ሁለት
ሚስቶችን አገባ የአንዲቱም ስም አዳ፤የሁለተኛይቱም ስም ሴላ ነበረ፤ አዳም ያባልን ወለደች እርሱም በድንኳን የሚቀመጡ የዘላኖች
አባት ነበረ ፤ የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፤እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ”ይላል።(ዘፍ ፡ ም፡ ፬፣ቊ፡፲፮-፳፪)
በመሠረቱ ከቃሉ እንደምንረዳው ምንም እንኳን የዜማ አጀማመር እንዴትና መቼ የት?እንደሆነና እገሌ ጀመረው ብሎ ዘመናቱን
ለይቶ በትክክል ባይነግረንም ቅሉ በዘመኑ መኖሩን ለመረዳት ያስችለናል፤ ከዚህም በስተቀር የዜማን ሁኔታ በአሁኑ ይዞታ
ስንመለከተው ከሰዎች ሕይዎት ጋር አብሮ ያለና ወደፊትም የሚኖር በመሆኑ ዜማ ከሰዎች ልጆች ሕይዎት ጋር አብሮ ተገኝቷል ቢባል
አባባሉ አጠራጣሪ ሊሆን አይችልም። (ሊቀ ካህናት ርእሰ ደብር ጥዑመ ልሳን ካሣ)

⚜ዜማ(መዝሙር) አጀማመር -በሐዲስ ኪዳን

👉በጌታችን ልደት ለመጀመርያ ጊዜ ሰውና መላእክት አንድ ላይ ሆነው ዘምረዋል ።ሉቃ ፪÷፲፬

👉የኢየሩሳሌም ሕፃናትና አረጋውያን ለጌታችን ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት እያሉ ዘምረውለታል፡፡


👉ሐዋርያት ምስጢረ ቁርባንን ከተቀበሉ በኋላ ዘምረዋል፡፡ ማቴ ፳፮÷፴

👉በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔም እርስ በእርሳችሁ ተነጋገሩ እንዳለ ቆላ.፫÷፲፮

ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ በፍልጵስዩስ ወኅኒ በጸሎትና በዜማ ያመሰግኑ ነበር፡፡ ዝማሬያቸዉም የወኅኒ ቤቱን ደጆች አስከፍቷል
እነሱንም ከእስራት አስፈትቷል፡፡ የሐዋ ሥራ.፲፮÷፲፱-፳፮

══════════════════

⚜መንፈሳዊ ዜማ(መዝሙር) በኢትዮጵያ⚜

#ቅድመ_ኦሪት

🙏ኦሪት ገና ወደ ኢትዮጽያ ከመግባቱ በፊት ስብሐተ እግዚአብሔር ፤ አምልኮተ እግዚአብሔርና ፈሪሃ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
ሕዝብ ዘንድ አብሮ ነበር ፡፡ ከዚህ ሁኔታ በመነሳት ከሕገ ኦሪት መምጣት በፊት በኢትዮጵያ ዜማ ነበር ማለት ይቻላል ፡፡

#ጊዜ_ኦሪት
በቀዳማዊ ሚኒልክ ዘመን በሊቀ ካህናቱ በዘካሪያስ እጅ ታቦተ ጽዮንና ሌዋዉያን ሲመጡ የመዝሙር መጻሕፍትና በተመሳሳይ
የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ አብረዉ መጥተዋል ፡፡ በዘመነ ኦሪት የመጡ የዜማ መሳሪያዎች ፤ አለባባስና
የመዝሙር አጠቃቃም ስልቶች ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን እየተገለገለችበት ትገኛለች ፡፡ ለምሳሌ ከዜማ መሳሪያዎች መካከል
ከበሮ ፤ ጸናጽል ፤ መለከት ፤ መሰንቆ ፤ በገና ይገኙበታል ፡፡ ከአለባበስም ረጅም ቀሚስ ፤ ጥምጥም ፤ መጎናጸፊያ (ጋቢ ) እና ካባ
ይገኙበታል ፡፡

🙏🙏🙏#ቅድመ_ቅዱስ_ያሬድ🙏🙏🙏

👉“ወበዉዕቱ መዋዕል አልቦ ማኅሌተ ቅኔ በልዑል ዜማ ዘእንበለ ለሆሣሥ” ይላል። ግንቦት ፲፩ ስንክሳር

➡️ትርጉሙም በቀስታ ፤ በዝግታ ነዉ እንጂ ድምጽን ከፍ አድርጎ በመናገር ፤ ጉሮሮ በማሳመር ፤ ቃልን በማራቀቅ ወይም በማጉላት ፤
ለቃላት ቀለም በመስጠት ፤ የሚጮህ ዜማ አልነበረም ማለት ነዉ ፡፡

👉አንድም "ወበዉዕቱ መዋዕል አልቦ ማኅሌተ መዝሙር ዘከመ ይእዜ በልዑል ቃል ዘእንበለ በትሑት ቃል።"

➡️ትርጉሙም በዚያ ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ ማለት ነው።
🙏🙏🙏#የቅዱስ_ያሬድ_መመረጥ🙏🙏🙏

እግዚአብሔር ቀደም ሲል በመዝሙረ ዳዊት ፸፯ ÷ ፳፭ “የመላእክትንም እንጀራ የሰዉ ልጆች በሉ”የተባለዉና በመዝ ፸፫ ÷፲፬
ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸዉን ሰጠሃቸዉ፡፡ በማለት በልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንዲመሰክር ያደረገዉን ኢትዮጵያዉያን
የመላእክት እንጀራ የተባለዉን ምስጋና በመላእክት ምስጋና በማመስገን ከመላእክት ጋር እንዲተባበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ
ሃይማኖትና አምልኮተ እግዚአብሔር በልዩ የመላእክት ጣዕመ ዜማ እንዲታጀብ ፈቃዱ በመሆኑ ከአክሱም ጽዮን ካህናተ ደብተራ
መካከል ቅዱስ ያሬድን ለሰማያዊ የመላእክት ጣዕመ ዜማ መረጠ ፡፡ይህንን ሰማያዊ ዜማ ቤተ-ክርስቲያናችን እንስካሁን ደስ
እየተገለገለችበት ትገኛለች።
══════════════════

🛎ማጠቃለያ

🙏ዜማ ቅድመ ቅዱስ ያሬድ ወይም ከሕገ ኦሪት መምጣት በፊት በንባብ ዜማ በቀስታ ፤ በዝግታ፤ በትሑት በማስተዛዘል ነበር ።
የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ ከታቦተ ጽዮን ጋር አብረው ወደ ሃገራችን መምጣት የመዝሙረ ዳዊቱም
አገልግሎት እንደ አሁኑ ያሬዳዊው ዜማ ከመሆኑ በፊት በኦሪቱ ስርዓት በነበረው ዜማ ይካሄድ እንደ ነበር ያስረዳል።

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

🙏⚜🙏⚜🙏ምስጋና🙏⚜🙏⚜🙏

👉ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ዓለማትን ከመፍጠሩ አስቀድሞ በአንድነት በሦስትነት ሆኖ አንድነቱ ሦስትነቱን
ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነትና በሦስትነት ሲቀደስ፣ ሲመሰገን ይኖር ነበር፡፡ምስጋናውም
አልተጓደለም፤ ባሕርዩ ባሕርዩን ያመሰግን ነበር፡፡ (“ፍጥረትን ሁሉ ከመፍጠሬ በፊት ምስጋናዬ ከእኔ ጋር ነው፤ ከፈጠርነው ፍጥረት
መመስገን የምንሻ አይደለንም ምስጋናችን የባሕሪያችን ነው።” (መጽሐፈ አክሲማሮስ)፡፡

👉ፍጥረትን ኹሉ ሳይፈጥር የአብ፣የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ምስጋና አልተቋረጠም፡ጌታችንም በዮሐንስ ወንጌል ላይ “አሁንም አባት
ሆይ ዓለም ሳይፈጠር ከአንተ ዘንድ በነበረኝ
ክብር አንተ በራስህ አክብረኝ” ብሏል፡፡ ዮሐ.፯፥፭

👉ስለዚህ ምስጋና በዚህ ጊዜ ተጀመረ ማለት አይቻልም፡፡

👉እግዚአብሔር ክብሩ በባሕርዩ ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ስሙን እንዲቀድሱና ክብሩን እንዲወርሱ መላእክትንና ሰውን ለባውያን፣
ነባቢያንና ማእምራን /አስተዋዮችና ዐዋቂዎች/ አድርጎ ፈጠራቸው፡፡

#ምስጋና_በሰው_ልጆች_ዘንድ

👉የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ዓላማ አንዱ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “የመላእክትን
እንጀራ የሰው ልጅ በላ” መዝ ፸፯(፸፰)፤፳፭ ብሎ እንደተናገረው። አዳምና ሔዋን እንደተፈጠሩ በቅዱሳን መላእከት ምስጋና
ያመሰግኑ ነበር፡፡

👉ለአዳም የመጀመሪያውን ምስጋና ያስተማሩት ቅዱሳን መላእክት እንደሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን ያስተምራሉ፤ ነገር ግን
አዳምና ሔዋን ንጽሐ ጠባያቸው ሲያድፍባቸው በኃጢአት ሲወድቁ ከእግዚአብሔርና ከቅዱሳን መላእክት ተጣሉ፤ ከመላእክት
ምግብም ተለዩ።እግዚአብሔር ግን እንደብሊቀ ነቢያት
ሙሴ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ፣ እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል የመሳሰሉትን ነቢያት እያስነሣ ይህን የቅዱሳን መላእክትን ምስጋና እንዲሰሙ
ያደርግ ነበር፡፡ የሰው ልጅ ግን ሰማ እንጂ አብሮ ለመዘመር አልቻለም ነበር። ነገር ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በቤተልሔም እንደ ሕፃናት በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ተወልዶ ባዩት ጊዜ ተለያይተው የነበሩት ሰውና መላእክት በአንድነት
አመስግነዋል፡፡ ሉቃ. ፪፥፬

🛎እግዚአብሔርን የምናመሰግንባቸው ምክንያቶች በጥቂቱ

🤲እግዚአብሔር ስለፈጠረን፣ ሕልውና ስለሰጠን እናመሰግነዋለን፡፡

🤲እግዚአብሔር ስለሰጠን ተፈጥሮአዊ ተሰጥኦዎች እናመሰግነዋለን፡፡

🤲 ስላለንበት ስለምንኖርበት እምነት እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን፡፡

🤲እግዚአብሔር እስከዚህ ሰዓት እንድንኖር ስለፈቀደልን እናመሰግነዋለን፡፡

🤲እንደ ኃጢያታችን ስላላደረገብን እናመሰግነዋለን፡፡

🤲 እግዚአብሔር ስለጠበቀን፣ ስለመራን፣ ስለረዳን፣ ፍቅሩን ስለሰጠን እናመሰግነዋለን፡፡


🤲በውስጣችን ስለሚሰራው ጸጋ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን፡፡

🛎ስለ ማመስገን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነሱ ጥቅሶች

🤲ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ አጥንቶቼም ሁሉ፣ የተቀደሰ ስሙን፡፡መዝ ፻፫

🤲ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔር፣ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ።መዝ ፻፫

🛎እንዳናመሰግን የሚያደርገን ምንድነው?

👉የተሰጠን በጎ የሆነውን ነገር አለማወቅ

👉የወደፊቱን አለመመልከታችን ዕብ ፲፩፥፩

👉የተቀበልናቸው ነገሮች ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከእኛ የተቀበልነው አድርገን ማሰብ

════◉❖◉═════

⚜🙏⚜🙏⚜🙏ዜማ⚜🙏⚜🙏⚜🙏

#መንፈሳዊ_ዜማ_እንዴትና_መቼ_ተጀመረ❓

👉መንፈሳዊ ዜማ የተጀመረው በጥንተ ፍጥረት በቅዱሳን መላእክት ነው፡፡

👉እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ የተፈጠሩትን ፍጥረታት ከፈጠረ በኋላ መላእክትን ተሰውሮባቸዋል፡፡ የፈጠራቸውን አምላክ
እስኪያውቁ ድረስ በችግር ውስጥ የቆዩት ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔር ብርሃንን በፈጠረ ጊዜ በሥራ ተገለጠላቸው፡፡ የብርሃን
መፈጠርም ለእነርሱ ዕውቀትና ጥበብ ኾኗቸው “ቅዱስ ፣ቅዱስ፣ቅዱስ እግዚአብሔር “በማለት ፈጣሪያቸውን በዜማ
አመስግነውታል፡፡ “ወዝንቱ ብርሃን ኮኖሙ ጥበበ ወአእምሮ፤#ትርጉሙም ይህም ብርሃን ጥበብና ዕውቀት ኾናቸው እንዲል
መጽሐፍ።
👉#ቅዱስ_አትናቴዎስም በቅዳሴው “በምስጋና ቃል እግዚአብሔርን እንደሚያመሰግኑ መላእክት እንምሰል በየማዕርጋቸው፣
በየነገዳቸው ፣በየሠራዊታቸው ፣በየስማቸው፣በየቁጥራቸው፣ የሚጋርዱ አሉ ፤የሚከቡም አሉ፤ በዜማ የሚያመሰግኑም አሉ፤
የሚዘምሩም አሉ” በማለት ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን በዜማ እንደሚያመሰግኑት ተናግሯል ፡፡

🛎#ማጠቃለያ

🤲🙏 ምስጋናን በዜማ ማቅረብ ከሥነ ፍጥረት የተጀመረዉ በመላእክት ዘንድ ኋላም በሰው ልጆች ነው።

🛎ስለ መላእክት ምስጋና እንዲሁም በዜማ ስለማመስገናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነሱ ተጨማሪ ማስረጃዎች።

👉የተፈጠሩትን ሁሉ እኔን ለማመስገን ፈጠርኳቸው። ኢሳ ፵፫÷፯

👉የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግኑ ዘንድ አዳምን ከልጆቹ ጋር ፈጠረው። ፫ኛ መቃ.፪÷፲፪

👉ሱራፌልም በዙርያዉ ቆመው ነበር … አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ፣ቅዱስ ፣ቅዱስ ፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ምድር ሁሉ
በክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር፡፡ ኢሳ ፮÷፪-፫

👉ቅዱሳን መላእክት ሃያ አራቱን ሰዓት ምስጋናቸው እረፍት እረፍታቸው ምስጋና ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረዉና ያለዉ ፣
የሚመጣዉም ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ እያሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።ራእይ ፬÷፰

⚜ዜማ(መዝሙር) አጀማመር -በሕገ ልቦና

🙏በሰዉ ልጆች ዘንድ ከሀዘንና ከመገለል ከብቸኝነት ከትካዜ የተነሳ ዜማ ማኅዜኒ (የኀዘን ዜማ) ቀድሞ እንደተጀመረ አበዉ
ይተርካሉ።
ዮባል መከራ ስለጸናበት የቃየልን በደል እያስታወሰ በገና በመደርደር ድምጹን እያሰማ የሐዘን እንጉርጉሮ /ማኅዘኒ/ ያሰማ
ነበር።እርሱም በገናና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበር እንዲል። ዘፍ ፬÷፲፮

🙏ዜማ በሕግ ጠባያዊ የተገኘ ስለነበር በጊዜ ብዛት ሥጋዊ ፍትዎትን ቀስቅሶ በደብር ቅዱስ የነበሩ የሴት ልጆችን ሳይቀር ወደ ጥፋት
መርቷል፡፡ ሄኖክ ፭÷፫-፰

🙏 በሕገ ተፈጥሮ ተገኘውን ዜማ ተከትለው ደግሞ ደጋግ አበው አማናዊ መዝሙር ዘምረዋል።
👉አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ የሰሌን ዘንባባ (በቀልት)ይዞ ሰባት ቀን መሠውያውን እየዞረ በሰንበት ዘምሯል፡፡ ኩፋ፲፫÷፳፩

⚜ዜማ(መዝሙር) አጀማመር- በሕገ አሪት

#ቅድመ_ቅዱስ_ዳዊት

👉እስራኤል ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ ማርያም እህተ ሙሴ ከሕዝቡ ጋር በከበሮ ለእግዚአብሔር ዘምራለች፡፡ ኦሪት ዘጻ.
፲፭÷፲፱-፳፩

👉በእስራኤል ላይ ስትፈርድ የነበረችው ነቢዪቱ ዲቦራ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ዘምራለች፡፡ መጽ. መሳ. ፭÷፩-፴፩

#በቅዱስ_ዳዊት_ዘመን

👉ቅዱስ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት የሚዘምሩ መዘምራንን ማደራጀቱ ተጽፏል፡፡ ፩ኛ ዜና ፲፮÷፬-፲፯

👉 ቅዱስ ዳዊት ለፍርድ አደባባይ በማይውልበት ቀን ከመዘምራኑ ጋር በአንድነት በበገና ይዘምር ነበር፡፡ ፩ኛ ዜና ፮÷፴፩-፵፬ ነህምያ
፲፪÷፳፰-፵፯

👉ሕዝበ እስራኤል

➡️በበዓለ ፋሲካ መዝ.፻፲፪ ፣ ፻፲፯ ፣ ፻፴፬

➡️በዕለተ ሰንበት መዝ.፺፩ ፣ ፺፱

➡️በመባቻ ቀን መዝ.፹÷፩-፱ ይዘምሩ ነበር፡፡

🛎#ማጠቃለያ

🙏ምንም እንኳን ዜማ ከመላእክት ጋር አብሮ የተገኘ መሆኑን ከላይ ገልጠን በማስረጃ ያቀረብን ቢሆንም
#ዜማ_ከክርስቶስ_ልደት_በፊት በሰዎች ዘንድ እንዴት ተጀመረ? ብሎ መመርመሩ አስፈላጊ ይሆናል። በመሠረቱ ይህ ርዕስ
በጣም ሰፊና ጥልቅ ምርምርን የያዘ እንደመሆኑ መጠን ዜማ እንዴት? የት?መቼ?ማን ጀመረው?በሚባልበት ጊዜ በዚህ ጊዜ
ተጀመረ እገሌ ጀመረው ለማለት አስቸጋሪ ይሆናል፤ምክንያቱም አንዳንድ ሊቃውንት ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ አብዛኞቹ የሚሰጡት
መልስ ከ፭ኛው መቶ ዓመት ወይም ክፍለ ዘመን ወዲህ ስለተደረገው ድርጊት እንጅ ከዚያ በፊት ስለሆነው ሁሉ አብዛኛውን ጊዜ
ሊቃውንቱ የሚረዱበት የዜማ ታሪክና የሥነ ጽሑፍ ዕድገት እንዳሁኑ ጎልቶ ያልታየበት ዘመን ከመሆኑም በላይ ዘመናቱም በቁጥር
ሲለኩ እጅግ ርቀት ያላቸው ሆነው በመገኘታቸው ለተጠየቀው ጥያቄ እምብዛም ያህል አጥጋቢ መልስ ለማግኘት አዳጋች ሆኖ
ይገኛል ፤ ሆኖም ዓይነ ህሊናችንን ወደ ቅዱስ መጽሐፍ መለስ አድርገን ስንመለከት ጉልህ የሆኑ አንዳንድ ማስረጃዎችን እናገኛለን፤
ይህውም በኦሪት ዘፍጥረት በምዕራፍ ፬ ከቊጥር ፲፮- ፳፪ ያለውን ስናነብ የቃየል ስድስተኛ ትውልድ በሆነው በዩባል ጊዜ የዜማ
ወይም የሙዚቃ መሣሪያዎች እንደነበሩ ለመረዳት እንችላለን ፤ቃሉም እንደዚህ የሚል ነው “ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ
ከኤደንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ፤ ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም ፣ሄኖኅንም ወለደች ከተማም ሠራ፤
የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖኅ አላት ሄኖኅም ጋይዳድን ወለደ፤ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ፤ሜኤልም ማቱሳኤልን
ወለደ፤ማቱሳኤልም ላሜኅን ወለደ፤ለሜኅም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ የአንዲቱም ስም አዳ፤የሁለተኛይቱም ስም ሴላ ነበረ፤
አዳም ያባልን ወለደች እርሱም በድንኳን የሚቀመጡ የዘላኖች አባት ነበረ ፤ የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፤እርሱም በገናንና
መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ”ይላል።(ዘፍ ፡ ም፡ ፬፣ቊ፡፲፮-፳፪) በመሠረቱ ከቃሉ እንደምንረዳው ምንም እንኳን የዜማ
አጀማመር እንዴትና መቼ የት?እንደሆነና እገሌ ጀመረው ብሎ ዘመናቱን ለይቶ በትክክል ባይነግረንም ቅሉ በዘመኑ መኖሩን
ለመረዳት ያስችለናል፤ ከዚህም በስተቀር የዜማን ሁኔታ በአሁኑ ይዞታ ስንመለከተው ከሰዎች ሕይዎት ጋር አብሮ ያለና ወደፊትም
የሚኖር በመሆኑ ዜማ ከሰዎች ልጆች ሕይዎት ጋር አብሮ ተገኝቷል ቢባል አባባሉ አጠራጣሪ ሊሆን አይችልም።(ሊቀ ካህናት ርእሰ
ደብር ጥዑመ ልሳን ካሣ)

⚜የዜማ(መዝሙር) አጀማመር - በሐዲስ ኪዳን

👉በጌታችን ልደት ለመጀመርያ ጊዜ ሰውና መላእክት አንድ ላይ ሆነው ዘምረዋል ።ሉቃ ፪÷፲፬

👉የኢየሩሳሌም ሕፃናትና አረጋውያን ለጌታችን ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት እያሉ ዘምረውለታል፡፡

👉ሐዋርያት ምስጢረ ቁርባንን ከተቀበሉ በኋላ ዘምረዋል፡፡ ማቴ ፳፮÷፴

👉በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔም እርስ በእርሳችሁ ተነጋገሩ እንዳለ ቆላ.፫÷፲፮

ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ በፍልጵስዩስ ወኅኒ በጸሎትና በዜማ ያመሰግኑ ነበር፡፡ ዝማሬያቸዉም የወኅኒ ቤቱን ደጆች
አስከፍቷል እነሱንም ከእስራት አስፈትቷል፡፡ የሐዋ ሥራ.፲፮÷፲፱-፳፮

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

⚜መንፈሳዊ ዜማ(መዝሙር) በኢትዮጵያ⚜

#ቅድመ_ኦሪት

🙏ኦሪት ገና ወደ ኢትዮጽያ ከመግባቱ በፊት ስብሐተ እግዚአብሔር ፤ አምልኮተ እግዚአብሔርና ፈሪሃ እግዚአብሔር
በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ አብሮ ነበር ፡፡ ከዚህ ሁኔታ በመነሳት ከሕገ ኦሪት መምጣት በፊት በኢትዮጵያ ዜማ ነበር
ማለት ይቻላል ፡፡

#ጊዜ_ኦሪት

በቀዳማዊ ሚኒልክ ዘመን በሊቀ ካህናቱ በዘካሪያስ እጅ ታቦተ ጽዮንና ሌዋዉያን ሲመጡ የመዝሙር መጻሕፍትና
በተመሳሳይ የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ አብረዉ መጥተዋል ፡፡ በዘመነ ኦሪት የመጡ የዜማ
መሳሪያዎች ፤ አለባባስና የመዝሙር አጠቃቃም ስልቶች ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን እየተገለገለችበት ትገኛለች ፡፡
ለምሳሌ ከዜማ መሳሪያዎች መካከል ከበሮ ፤ ጸናጽል ፤ መለከት ፤ መሰንቆ ፤ በገና ይገኙበታል ፡፡ ከአለባበስም ረጅም
ቀሚስ ፤ ጥምጥም ፤ መጎናጸፊያ (ጋቢ ) እና ካባ ይገኙበታል ፡፡
🙏🙏🙏ቅድመ ቅዱስ ያሬድ🙏🙏🙏

👉“ወበዉዕቱ መዋዕል አልቦ ማኅሌተ ቅኔ በልዑል ዜማ ዘእንበለ ለሆሣሥ” ይላል። ግንቦት ፲፩ ስንክሳር

➡️ትርጉሙም በቀስታ ፤ በዝግታ ነዉ እንጂ ድምጽን ከፍ አድርጎ በመናገር ፤ ጉሮሮ በማሳመር ፤ ቃልን በማራቀቅ
ወይም በማጉላት ፤ ለቃላት ቀለም በመስጠት ፤ የሚጮህ ዜማ አልነበረም ማለት ነዉ ፡፡

👉አንድም "ወበዉዕቱ መዋዕል አልቦ ማኅሌተ መዝሙር ዘከመ ይእዜ በልዑል ቃል ዘእንበለ በትሑት ቃል።"

➡️ትርጉሙም በዚያ ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ ማለት ነው።

🙏🙏🙏የቅዱስ ያሬድ መመረጥ🙏🙏🙏

እግዚአብሔር ቀደም ሲል በመዝሙረ ዳዊት ፸፯ ÷ ፳፭ “የመላእክትንም እንጀራ የሰዉ ልጆች በሉ”የተባለዉና በመዝ
፸፫ ÷፲፬ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸዉን ሰጠሃቸዉ፡፡ በማለት በልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንዲመሰክር ያደረገዉን
ኢትዮጵያዉያን የመላእክት እንጀራ የተባለዉን ምስጋና በመላእክት ምስጋና በማመስገን ከመላእክት ጋር እንዲተባበሩና
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖትና አምልኮተ እግዚአብሔር በልዩ የመላእክት ጣዕመ ዜማ እንዲታጀብ ፈቃዱ በመሆኑ
ከአክሱም ጽዮን ካህናተ ደብተራ መካከል ቅዱስ ያሬድን ለሰማያዊ የመላእክት ጣዕመ ዜማ መረጠ ፡፡ይህንን ሰማያዊ
ዜማ ቤተ-ክርስቲያናችን እንስካሁን ደስ እየተገለገለችበት ትገኛለች።

🛎#ማጠቃለያ

🙏ዜማ ቅድመ ቅዱስ ያሬድ ወይም ከሕገ ኦሪት መምጣት በፊት በንባብ ዜማ በቀስታ ፤ በዝግታ፤ በትሑት
በማስተዛዘል ነበር ። የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ ከታቦተ ጽዮን ጋር አብረው ወደ ሃገራችን
መምጣት የመዝሙረ ዳዊቱም አገልግሎት እንደ አሁኑ ያሬዳዊው ዜማ ከመሆኑ በፊት በኦሪቱ ስርዓት በነበረው ዜማ
ይካሄድ እንደ ነበር ያስረዳል።

════◉❖◉═════

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

#ቤተ_ዕንዚራ
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

🤴#ልበ_አምላክ_ቅዱስ_ዳዊት🤴

✝ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለ ልደቱ ሲናገር "እስመ ናሁ በኃጢአት ተፀነስኩ ወበ አመፃ ወለደተኒ እምየ" ይላል
(መዝ. ፶፩:፬) አበው ሊቃውንት ይሄንን ሲያስረዱ የቅዱስ ዳዊት አባት ደጉ እሴይ ከነገደ ይሁዳ የኢዮቤድ ልጅ ሲሆን
ሚስቱን ሰሊብን አንድ ጐልማሳ በዝሙት ዐይን ሲፈልጋት ተመልክቶ ነበር:: አንድ ቀንም መንገድ ሔድኩ ብሎ ያንን
ጐልማሳ መስሎ ተመልሶ አብሯት አድሯል:: በዚያች ሌሊትም ቅዱስ ዳዊት ተጸንሷልና "እስመ ናሁ በኃጢአት ተፀነስኩ
ወበ አመፃ ወለደተኒ እምየ"ብሏል ብለው ይተረጉማሉ::

👉ቅዱስ ዳዊት ከሕጻንነቱ ጀምሮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ነበር። ሕጻን ሳለ በእረኝነት የአባቱን በጎች አያስነካም
ነበር።አንበሳውን በጡጫ ነብሩን በጡጫ ብሎ የያዙትን ያስጥላቸውም ነበር(፩፡ሳሙ፡ም፡፲፯ ቊ፡፴፬- ፴፯) በጥቂቱ
በበግ እረኝነት ስለ ታመነ ለእሥራኤል እረኛ ሊሆንም ተመርጧል። “ከሕዝቤ ወገን ለይቼ በክብረ መንግሥት ከፍ ከፍ
አደርገው ዘንድ አንደ ልቡናዬ የሚሆን አገልጋዬ ዳዊትን መረጥሁት ቅዱስ ቅብዐ መንግሥትንም ቀባሁት” ብሎ
የአማልክት አምላክ የነገሥታት ንጉሥ የገዥዎች ገዢ የሚሆን ልዑል እግዚአብሔር እንደተናገረና፤ በንጉሥነት ላይ
የነቢይነትን ክብር የተጎናጸፈ እርሱ ራሱ ቅዱስ ዳዊትም “የአባቴን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት መርጦ ወስዶ ክቡር
ቅብዐ መንግሥት ቀባኝ” ብሎ እንደመሰከረ ፤ ቅዱስ ዳዊትን ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ ከሰባቱ የእሴይ ልጆች
ተመርጦ በ፲፪ አመቱ በእደ ሳሙኤል ነቢይ ቅብዓ መንግሥት በተቀባበት ጊዜ ሰባት ሀብታት ተሰጥተውታል።እኒህ
የተሰጡት ሰባት ሀብታትም የሚከተሉት ናቸው።

🤴#ሀብተ_መንግሥት፦ የገደለውን ማስገደል የቀማውን ማስመለስ።

👳‍♂#ሀብተ_ክህነት፦ በደብተራ ኦሪት ከሚያገለግሉት ጋር አንድ ሆኖ መቆጠር።

💪#ሀብተ_ኃይል(ጉልበት)፦ አንበሳውን በእርግጫ ነብሩን በጡጫ ብሎ መግደል።(፩፡ሳሙ፡ ም፡፲፯ ቊ፡፴፬-፴፯)

⚔#ሀብተ_መዊዕ(ጠላትን ድል መንሳት)፦ ጦሩ በተደረደረበት ኃያላኑ በተሠለፉበት የዳዊት ሎሌ መጣ መጣ ባሉ ጊዜ


ይፈርስ ነበርና፤ አንድም የጠላት ጦር በተሰለፈበት የጦር አለቆች በሠፈሩበት ገብቶ የጦሩን መሪ በድንጋይ ግንባሩን
ፈጥፍጦ መግደል።(፩፡ሳሙ፡ ም፡፲፯ ቊ፡፵፱-፶፩)

🙏#ሀብተ_በገና፦ ዕንጨቱን ጠርቦ ወይም አለዝቦ ቁርበቱን ጎልቦ ጅማቱን ወትሮ በገና መደርደር።

😇#ሀብተ_ትንቢት፦ መቶ ሃምሳ ዳዊት ወይም መዝሙር መድረስ ፤ በብዙ አርእስት የሚቆጠሩ ነገረ ትንቢትና ቃለ
ምዕዳን መተንበይ።

🤲#ሀብተ_ፈውስ፦ በገናን እየደረደረና መዝሙር እየዘመረ ድውይን ህሙምን መፈወስና የመንፈስን ጭንቀት
ማስወገድ።በዚህ በተሰጠው ሀብተ ፈውስ በገና በመምታትና መዝሙር በመዘመር ጊዜና ሰዓት እያየ በርኩስ መንፈስ
ይሰቃይ የነበረ ሳኦልን ይፈውሰው እንደነበር ሁሉ ዛሬም ቢሆን በርኩስ መንፈስ ተይዘው የሚሰቃዩትን ሲፈውሳቸው
ይታያል። (መዝሙረ ዳዊት አንድምታ መቅድም )

👉ቅዱስ ዳዊት በተሰጠው ሰማያዊ ጸጋ እና ሃብት መዝሙሮችን አዘጋጅቷል። ኁልቁ መዝሙሩ ፻፶ ነው። ፻፶ ውንም
መዝሙር በ ፲ አርእስት በአራት ለይኩን ፣በአምስትኛ ለይበሉ ከአምስት ከፍሎታል። ምክንያቱም ለጊዜው
#በአምስቱ_መጻህፍተ_ሙሴ ምሳሌ ነው ፍጻሜው ግን ከጊዜው ሳይደርስ እንደ ደረሰ ሆኖ በትንቢት ለተናገራቸው
#አምስቱ_አዕማደ_ምሥጢር ምሳሌ ሆኖ ለመቆየት ነው።

👉ቅዱስ ዳዊት ፪፻፹፰ መዘምራን ካህናት ነበሩት፤ እነዚህ ፪፻፹፰ መዘምራን በ ፬ አለቆች ይመሩ ነበር፤ የአለቆቹም
ስም እንደሚከተለው ነው።

👉#አሳፍ (መዝ ፡ ፹፯፣ቊ፡፵፱ ፡ቊ፡፹፩)

👉#ቆሬ (መዝ ፡ ፹፯፣ቊ፡፵፰)

👉#ኤማን

👉#ኤዶትም

👉መዝሙር ሰማንያ ስምንት (፹፰) ከላይ የተጠቀሱት ፪፻፹፰ ቱ መዘምራን በየአለቆቻቸው ከ ፬ ተከፍለው አንዱ ወገን
በበገና፣ አንዱ ወገን በመሰንቆ ፣ አንዱ ወገን በከበሮ፣ አንዱ ወገን በቃጭል፣ አሥራ ሁለት አሥራ ሁለት እየሆኑ በሃያ
አራቱ ጊዜያት በደብተራ ኦሪት እየተሰበሰቡ በንባብ የሚሆነውን ምስጋና በንባብ፤ በዜማ የሚዘመረውን በዜማ ይዘምሩ
ነበር፤ ዳዊትም ከአደባባይ በማይውልበት፣ ነገር በማይሰማበት ጊዜ እየተገኘ ከእነርሱ ጋር በበገና ይዘምር እንደ ነበር
ተጽፏል። (፩ኛ ዜና መዋዕል ፡ ም፡ ፮ ቊ: ፴፩ ፵፬) (፪ኛዜና መዋዕል ፡ ም፡ ፳፱፣ ቊ፡ ፳፭- ፴፩)(ነሕምያ ፡ ም፡ ፲፪፣ ቊ፡
፳፰- ፵፯)

👉ከላይ ከተጠቀሱት የመዘምራን አለቆች ፩ኛው የሆነው አሳፍ በጣም የታወቀ ዘማሪ እንደነበር ቅዱስ አትናቴዎስ
ጠቅሶ ሲናገር “የበዓላትን በኵር ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት ኑ እናመስግናት ኑ እናክብራት ኑ በዓል እናድርጋት ይህችም
ቅድስት ሰንበተ ክርስቲያን ናት ፤ይህች ቀን እግዚአብሔር ሥራ የሠራባት ናት እንበል በእርሷም ደስ ይበለን ፤ሃሴትም
እናድርግ፤ እንደ ነቢዩ እንደ አሳፍም በረዳን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ እያልን እንዘምር”ሲል ዘማሪነቱን አጉልቶና
አምልቶ ጽፎለታል። (ቅዳሴ አትናቴዎስ ፡ቊ፡፶፭-፶፮)

🛎በዘመነ ብሉይ መዝሙረ ዳዊት በተለያዩ በዓላት እንዲዘመር በእሥራኤላውያን ዘንድ ተመድቦ ነበር ፤ ለምሳሌ

👉#በበዓለ_ፋሲካ(መዝ ፩፻፲፪፡፩፻፲፯፡፩፻፴፬)

👉#በበዓለ_ሰንበት (መዝ ፺፩፡፺፱)

👉#በመባቻ_ቀን (መዝ ፹ :፫-፬) እነዚህ ነበሩ፤ ቅዱስ አትናቴዎስም ይህንን በማስመልከት “በመባቻ ቀን ነጋሪት ምቱ
በነቢዩ በዳዊት መዝሙር በታወቀች በበዓላችን ቀን በእውነት ሃሌ ሉያ እንበል እግዚአብሔር ሥራውን ይሠራ ዘንድ
የጀመረባት በእውነት የታወቀች ናት” በማለት በበዓላት ጊዜ መዝሙር መዘመር እንደሚገባ ጽፏል (ቅዳሴ አትናቴዋስ
ቊ፡፶፱-፷፩)።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉ለእኛም ለኢትዮጵያ ሰዎች በቀዳማዊ ምኒልክ ጊዜ ታቦተ ጽዮንና መጻሕፍተ ነቢያት ሲመጡ መዝሙረ ዳዊቱ
መጥቶልናል፣ነገር ግን ንባቡ ብቻ መጥቶልናል እንጅ መዘምራኑ ይዘምሩት እንደ ነበረው ሆኖ የመዝሙሩ ግጥም
የዜማው ጣዕም ከበገናው ተስማምቶ አልመጣንልም። ምክንያቱም ቅዱስ ዳዊት የደረሰው በቋንቋው በዕብራይስጥ
ነበረ። ለእኛ ግን የመጣልን ከዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ተመልሶ ስለ ሆነ አንድ ንግግር ከአንድ ልሳን ወደ አንድ ልሳን
ሲመለስ ንባቡ ተመዛዝኖ ቤቱ ተመጣጥኖ ሊገኝ የማይቻል በመሆኑ ይመስላል።ስለዚህም እስከ አጼ ገብረ መስቀል
ዘመነ መንግሥት በበገና መደርደሩ በዜማ ስልት ከከበሮና ከጽናጽል መተባበሩ ቀርቶ በንባቡ ብቻ የሚጸለይ ጸሎት
ሆኖ ኖረ ሊባል ይችላል።(መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ)

════◉❖◉═════

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

⚜🙏⚜#ኦርቶዶክሳዊ_መዝሙር⚜🙏⚜

✝#የመዝሙር_ትርጉም✝

👉መዝሙር በቁሙ ምስጋና፣ ውዳሴ፣ ጸሎት ማለት ነው፡፡

👉መዝሙር የሚለው ቃል «ዘመረ» አመሰገነ ከሚለው የግዕዝ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ምስጋና ማለት ነው፡፡

👉መዘመር በቤተ-ክርስቲያን የዝማሬ ሥርዓት መሠረት በዜማ የሚቀርብ ምስጋና ነው፡፡

👉መዝሙር ልዩ ልዩ ስልትና ቃና ባለው ድምፅ የሚዜም፣ በዜማ መሣሪያ የሚቀርብ መንፈሳዊ ማኀሌት ነው፡፡ (ኤፌ
፭፥፲፱)

👉መዝሙር ምስጋና ፣ ልመና ወይም መማጸን፣ ማራራት፣ ማስደሰት፣መደሰት፣ ማዜም ማለት ነው፡፡(መዝ ፴፪÷፩-፭ መዝ
፻፵፱÷፩ መዝ ፻፶÷፩- ፮፣ መዝ ፹÷፩-፫ ማቴ ፳፮÷፴፣ማር ፲፬÷፳፮ የሐ.ሥራ ፲፮÷፳፭፣ራዕ ፫÷፲፮-፳፭ ፣ራዕ ፲፬÷፩-፫ ፣
ማቴ ፳፩÷፱፣ ማር ፲፩÷፱፣ ሉቃ ፲፱÷፴፮-፴፰)

👉መዝሙር ከመንፈስ ቅዱስ የአገልግሎት የጸጋ ስጦታዎች አንዱ ነው፡፡“እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ
አለን”(ሮሜ ፲፪፡፮)።ዳዊት ንጉሠ እስራኤል ከተሰጡት ሰባት ሀብታት መካከል አንዱ ስጦታ ሀብተ ዝማሬ/በገና ነበር፡፡

👉መዝሙር የከንፈር ፍሬ (መሥዋዕት) ነው፡፡ (መዝ ፻፲፭፡፰፣ ሆሴ ፲፬፡፪ ዕብ ፲፫፡፲፭ መዝ ፵፱ ፲፬።)


👉ስንኙ/ግጥሙ/ንባቡ በተመረጡ ቃላት ተዘጋጅቶ ድምጾች በስልትና በሥርዓት ሲዋሐዱ በሚፈጥሩት ዜማ በንዋያተ
መዝሙር/ማኅሌት ታጅቦ በግል/በኅብረት የሚቀርብ ጸሎት፣ ውዳሴ፣ ምስጋና ነው።

🛎በስንኝ የተወሰነ ንባብ(ግጥም)❓

👉ትምህርተ ሃይማኖትን (ዶግማን)፣ ትውፊትና ቀኖናን በዘይቤም በምስጢርም የጠበቀ

👉እግዚአብሔርን ማወቅ ለሚወዱና የነፍስ ድኅነትን ለሚሹ የሚጠቅም የሚረባ መልእክት ያለው

👉ምዕመናን ለማስተማር ብቃት ያለውና መልእክቱ ሰማያዊ መንፈሳዊ የሆነ፣ ምድራዊ ሥጋዊ ያይደለ

👉ክርስትናን በትክክለኛ መልክና ጠባዩ እንድንረዳው የሚያደርግ - የመስቀል፣ የገድል፣ የምናኔ፣ የተስፋ፣ የቁርጠኝነት
(የጥብዓት) ሃይማኖት መሆኗን የሚገልጽ፡፡

👉ወደ ልብ የሚገባ ዘወትርም ሲያጽናና የሚኖር ሰምተነው ስንጨርስ እንደ ነፋስ ሽው ብሎ የማያልፍ እንደ ንጹሕ ዘር
በልባችን መሬት የሚቆይ የሚበቅል የሚያፈራ - የሚያራ

👉ከአሥራውና ከአዋልድ መጻሕፍት ጋር በንባብም በምሥጢርም የተስማማ

👉የቋንቋ አገባብ ሥርዓትን የጠበቀ

⚜የቤት/የቀለም ምጣኔው የተስተካከለ፣

⚜በርዕሱ፣ በአዝማቹና በዘማቾቹ መካከል መዘበራረቅ የማይታይበት፣

⚜ጸያፍ ቃላት የሌሉበት፣

⚜ግልጽ የማያሻማ መልእክት ያለው፣

📮 ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር በዋነኛነት ሦስት ነገሮችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

✅የቤተ-ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት የጠበቀ መሆን፤

✅የመዝሙር መሳርያዎቹ ቤተ-ክርስቲያን የምትቀበላቸው መሆን፤

✅ዜማው ያሬዳዊ መሆን፤

✍እነዚህን መስፈርቶች ያሟላ መዝሙር ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ይባላል።

❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖

👉"ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እጅግ የበዛ የመሳሪያ እጀባ እጅግ የተንዛዛ እና የበዛ ቅላፄ ከማውጣት መቆጠብ መቻል
አለባቸው ፡፡ እንዲሁም ቤተ-ክርስቲያን በምትቀበላቸው የመዝሙር መሳሪያዎች ብቻ መጠቀም መቻል
አለባቸው፡፡"(እ.ኤ.አ ሰኔ ፲፫/፳፻፫ ዓ.ም በግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስር
የሚገኘው የዕምነት የትምህርት እና የስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ህግ አውጪ መዝሙርን በሚመለከት ካወጣው ባለ
ስምንት ነጥብ መስፈርት አንዱ)

❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖

✝#መዝሙርና_ያሬዳዊ_ዜማ✝

👉የቅዱስ ያሬድ ዜማ ልዩ ጠባይ አለው፡፡ ዜማው ሰማያዊ በመሆኑ ሕሊናን ወደ ሰማያት የመንጠቅ ሥጋዊ ደስታንና
ኃጢአትን ከማሰብ የመጠበቅ፤ ሰማያዊውን ድንቅ የምስጋና ምሥጢር የማሳወቅ ታላቅ ኃይል አለው፡፡ ዜማው
ከእግዚአብሔር የተገኘ ስጦታም በመሆኑ ብልየት /እርጅና/ ውላጤ /መለወጥ/የማይታይበት ዘወትር ሕያው የሆነ
ብቸኛ ዜማ ነው፡፡

🛎 ይህ ሰማያዊ ዜማ ከሌሎች ዜማዎች የሚለይበት ጠባይ

👉በአዝማናት ተለይቶ በወቅት ተከፋፍሎ የሚዜም መሆኑ

👉የተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ያለው መሆኑ

👉 ዜማው ሀሳብን የሚገዛ ከሥጋ ይልቅ በመንፈስ መመላለስን የሚያስተምር መሆኑ

👉 ዜማው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ምሥጢር የተሞላ መሆኑ

🛎 አንድ መዝሙር የቤተ-ክርስቲያን መዝሙር ሊያሰኙት የሚችሉት መስፈርቶች ዋና ዋናዎቹ

👉የቤተ-ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት በዘይቤና በምስጢር ጠብቆ ሲገኝ

👉ከመፅሐፍ ቅዱስና ከአዋልድ መጻሕፍት መሠረተ ሃሳብ ጋር የማይጋጭ /የማይቃረን/ ሆኖ ሲገኝ

👉መንፈሳዊ የመዝሙር (ያሬዳዊ) ዜማን ጠብቆ ሲገኝ

👉በቤተ-ክርስቲያን የመዝሙር መሳሪያዎች ብቻ ሲዘመር

👉በግጥሙ ስንኝ ውስጥ የሚታዩት ቃላት ግልጽነትና አግባብነት ያላቸው ሲሆኑ፤ እንዲሁም ግጥሙ ወጥነት ያለውና
እርስ በእርሱ የማይቃረን መልእክት ሲኖረው

👉ምዕመናን ለማስተማር ከፍተኛ ብቃት ያለው ሲሆን

✝#የመዝሙር_አገልግሎት✝

🤲የእግዚአብሔርን ስም የምናመሰግንበት ነው።


ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ላይ ካነሳቸው ሀሳቦች መካከል በይበልጥ ተደጋግሞ የተገለፀው ምስጋና ለስሙ እንደሚገባ
ነው ።ይህንንም በቅርብ በሩቅ፣ በግል በኅብረት ፣እንዲሁም በጥያቄ በትእዛዝ እያረገ ያቀርበዋል። ለምሳሌ

#በቅርብ_ሲያመሰግን

🙏" በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።"(መዝ ፱:፪)

#በሩቅ_ሲያመሰግን

🙏"እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት" መዝ ፴፪/፴፫፡፪

🤲የእግዚአብሔር ሥራውና ችሎታው ባህርያቱንም ጨምሮ እያሰታወስን የምናደንቅበት (አንክሮ)።

🤲ነገረ ሥጋዊውን የምንመሰክርበት።

🤲ኃጢአታችን እያሰብን የምንጸጸትበት።

🤲ፀሎትና ልመና ከምልጃ ጋር የምናቀርብብት።

🤲የቤተ-ክርስቲያንን ቀኖናና ዶግማ የምንመሰክርበት።

🤲የቅዱሳንን ተጋድሎ በየዘመናቱ የሠሩትን ገቢረ ተአምራት ለትውልዱ የምንመሰክርበት።

🤲የወንጌሉን ቃል የምናብራራበት።

🤲ትውልዱን ወደ ንሰሐ የምንጠራበት።

🤲ጠላት ዲያብሎስ የምናሳፍርበት ነው።

════◉❖◉═════

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

✝#ዘማሪነት_እና_የመዘምራን_ሕይወት✝
🛎#ዘማሪነት

👉ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ነው።

👉የትምህርተ ሃይማኖት፣ የቅዱሳት መጻሕፍት በሳል ዕውቀት እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሕይወትን የሚጠይቅ አገልግሎት ነው።

👉 በልምድ ብቻ የሚገኝ ሙያ አይደለም፡፡

👉ለአገልግሎት ጥሪ ምላሽ የሚሰጥበት የትህትና ሕይወት ነው።

👉ሙያዊ ችሎታን ለእይታ የሚያቀርቡበት የሙያ ዘርፍ አይደለም፡፡

👉እንደ ዩሐንስ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፣ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ በሥጋ ወደሙ ራሳችሁን አዘጋጁ፣ ከቂም
ከበቀል ራሳችሁን አንጹ…በማለት ቃለ እግዚአብሔርን በዜማ የምናስተምርበት ነው። ስለዚህ ዘማሪያን መምህራን ናቸው።

👉ምድራዊ መላእክት መሆን ነው።

➢ "እግዚአብሔርን አመስግኑት መላዕክቱ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ"(መዝ ፻፵፰፥፪)

➢ "ሰማዕታትን በደም፣ ጻድቃን በገዳም፣ ሐዋርያትን በአጽናፍ ዓለም፣ መላዕክትን በምስጋና በአርያም" እንዲል፡፡(አባ ጊዮርጊስ
ዘጋሥጫ)

🛎#የመዘምራን_ሕይወት

✅መዘምራን የምስጋና መስዋዕት አቅራቢዎች፣ በምድር የመላእክት አገልግሎት ፈጻሚዎች እና አስተማሪዎች ናቸው፡፡ ለእግዚአብሔር
የሚቀርብ መስዋዕት መልካም ንጹህ እንደሆነ ሁሉ መዝሙሩም መመረጥና ከቤተ-ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት አንጻር መመርመር
ይኖርበታል፡፡ (ዘሌ ፳፫፡፲፪)

✅መዝሙሩም ብቻ ሳይሆን መስዋዕት አቅራቢዎችም ራሳቸው ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ሊሆኑ ይገባል (ሮሜ ፲፪፡፲፪)፡፡ አለበለዚያ
ግን የቃየል መስዋዕት ሆኖ ይቀራል (መዝ ፻፲፭፡፰)

✅ የመዘምራን አለባበስ ሥርዓት የጠበቀ መሆን ይገባዋል።ይኽም የልብስን ብቻ ሳይሆን የአቋቋምንና የልብ /የውስጥ/ ስሜትንም
ሁኔታ ያጠቃልላል፡፡ የሥራ ልብስ እንዳለ ሁሉ ለመዝሙርም የራሱ ልብስ ይኖረዋል፡፡ "ሴቶች በሚገባ ልብስ በእፍረትና
እራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ እግዚአብሔርን እንፈራለን በሚሉ ሴቶች ደግሞ መልካም ከማድረግ እንጂ
በሹርባ በወርቅ ወይም በዕንቁ ዋጋ እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለም "(፩ጢሞ ፪፥፱-፲)

ከአለባበስ ሥርዓት መውጣት ከመንፈሳውያን የማይጠበቅ ነው፡፡ ለአለባበሳችን መነሻ የሆኑን ልክ እንደ መዝሙሩ ሁሉ ቅዱሳን
መላእክት ናቸው፡፡ "ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር ለእያንዳንዱም ክንፍ ነበረው በሁለቱም ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍኑ
ነበር...።"(ኢሳ ፮፡፩) ከዚህ የምንረዳው በፍርሃት ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንዳለን በማሰብና በመሸፋፈን መዘመር እንዳለብን
ነው። ዛሬ የካህናቱ አለባበስ የመዘምራኑ ጥንግ ድርብ ከላይ እሰከታቸ ያለው ሁሉ ከመላእክት የክንፍ ሁኔታ ጋር ምስጢር ያለው
ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ወንደሞች ሆይ ከእኛ እንደተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን " እንዳለ ፡፡(፪ኛተሰሎ ፫-፮)

🛎#ከአገልጋይ_መዘምራን_ምን_ይጠበቃል❓

📮በጸሎት መትጋት፦መዝሙር ከመዘመሩ በፊትም ሆነ ከተዘመረ በኋላ ጸሎት ያስፈልጋል መዘምራን የሆነው በራሳችን ጥበብና ድምፅ
ማማር አለመሆኑን ተገንዝበን ለመረጠንና በቦታው እንድናገለግል ላደረገን አምላክ ምስጋና በማቅረብ ለወደፊቱም በቸርነቱ
እንዲጠብቀን ዘወትር የጸሎት ሰዎች መሆን ይገባናል ። የበለዓምን አህያ ፣ የቢታንያን ደንጋዮች ያናገረ፣ የሆሣዕናን አህያ የመረጠ
እግዚአብሔር ዛሬም ከምንም ቦታ ዘማሪያንን ሊያስነሳ ይችላልና ተመርጠን እንዳንጣል ጸሎት ያስፈልጋል ፡፡ ለመዝሙር ክብር
በመስጠት ልክ እንደ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ከልብ መዘመር እንጂ እንደ ሜሊኮል መታበይ አይገባም ፡፡ (፪ኛ ሳሙ ፮፡፩ -ፍ.ም)

📮በማን ፊት እንደቆሙ ማወቅ፦ንጹሃ ባሕርይ የሆነ አምላክ ዘንድ በምን መልኩ መቅረብ እንዳለብን ቤተ-ክርስትያን በሰፊው
ታስተምረናለች፡፡ መዝሙር እግዚአብሔር የሚመሰገንበት የእርሱ የሆነ ሁሉ የሚዘከርበት በመሆኑ መዝሙር በሚዘመርበት ቦታ
ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩን ባለመዘንጋት መዘምራን ሲዘምሩ በእግዚአብሔር ፊት እንደቆሙ በማሰብ እንጂ የሚያውቁትንና
የሚያደንቀቸውን ሰው ፍለጋ ዓይንን በማማተር መሆን የለበትም።ይህ እራሱ መታበይ ነውና የአገልግሎቱ ዋጋም በምድር እንዲቀር
ያደርጋል፡፡

📮ያወቁትን ለሌላው ማሳወቅ (ማስተማር)፦ በቤተ ክርስቲያናችን የምናገኛቸውን ማናቸውንም ነገሮች እስከ ዘመናችን የደረሱት
በትውፊት አንዱ ለአንዱ እየሰጠ ፣እያስተላለፈ፣ እየተቀበለ መሆኑ አይካድም ፡፡ በአባቶችና በትውልድ መካከል መለያየት እንዳይኖር
ያወቁትን እያሳወቁ መጓዝ ይገባል ፡፡

📮እራስን ለእግዚአብሔር ማስገዛት፦ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መስዋዕቱ ተመለከተ ንጹህ መስዋዕት አቅርቧልና
እግዚአብሔር መስዋዕቱን ተቀበለ፡፡(ዘፍ ፬፥፬)
እግዚአብሔር ከሚቀርበው መዝሙር በፊት ዘማሪውን ይመለከታል ስለዚህ ዘማሪው በንጽህና ሊቀርብ ይገባዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስም "ወንድሞች ሆይ ሰውነታችሁን ቅዱስ እና ንጹህ መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርህራሄ
እለምናችኋለሁ" ሲል ይመክረናል፡፡ በኃጢያት የረከሰ ከንፈር በንስሐ፣ በሥጋ ወደሙ መቀደስ አለበት፡፡
📮ጸጋን ማወቅ፦የጸጋ ስጦታ ልዩ ልዩ ነውና፡፡ ሰባኪያነ ወንጌል ስብከትን፤ መዘምራን መዝሙሩን ፣በገና ደርዳሩዎች በገናቸውን ፣
መሰንቆ መቺዎች መሰንቋቸውን....... እየደረደሩ እና እየገዘገዙ መዝሙርን ሊያቀርቡ ይገባል።

📮ጥንቃቄ ማድረግ፦ የመዘምራን አገልግሎት ለዓይን የሚታይ እንደመሆኑ መጠን ለተመላካቾች ፣ ለአድማጮች በመዝሙራችን
የምናስተላልፈውን እኛ በተግባር እየፈጸምን ማሳየት ይኖርብናል፡፡ "ትህትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፡፡"(፩ኛጴጥ.፭፥፭)
"ስለምናገለግለው ለዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን፡፡"(፪ኛ ቆሮ ፰ ፥፳)

📮ቸልተኛ አለመሆን፦"የእግዚአብሔርን አገልግሎት በቸልታ የሚያደርግ ሁሉ እርጉም ይሁን፡፡"እንዲል መጽሐፍ(ኤር.፵፰፥፲


ዮሐ.፲፬፥፭)

📮መዝሙሩን በቃል መያዝ፡- አድማጮች የመዝሙሩን መልእክት አእምሮአቸው ሳይረበሽ ለመረዳትና ለመያዝ እንዲችሉ።

📮ለመዝሙር ሥርዓት መገዛት፦ ዘማርያን ቤተ-ክርስቲያናችን በየጊዜው ለምታወጣው ደንብና መመሪያ መገዛት አለባቸው፡፡
መዝሙር የቤተ ክርስቲያን ሀብት እንደመሆኑ መጠን በመዋቅር ደረጃ ቤተ-ክርስቲያኒቱ የመዝሙር ክፍል በሥሯ ይዛ በሥርዓትም
እንዲመራ መመሪያ አውጥታለች ፡፡መዘምራን ለዚህ መመሪያ መገዛት ይኖርባቸዋል።

📮መዝሙሩን ከራስ ህይወት ጋር በማገኛት እራስን መመርመር ያስፈልጋል፦ መዝሙር የሚዘመረው ለአድማጩ ብቻ አይደለም፡፡
ንስሐ ግቡ እያለ የሚዘምር አንድ ዘማሪ ለራሱ ንስሐ የሚገባ መሆን ይጠበቅበታል።

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

ቤተ-ዕንዚራ:
✝#ንዋያተ_ማኅሌት(ንዋያተ መዝሙር)✝

👉የዘማርያኑን ሕሊና የሚያነቃቁ፣ ድምፅን ለማስማማት የሚረዱ፣ መዝሙሩን የሚያደምቁ ፣መንፈሳዊ ትርጉም ያላቸውና
በትውፊት የወረስናቸው መሣሪያዎች ናቸው።

👉የማኅሌት መሣሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሐዲስ ኪዳን ወንጌል፣ የክርስቲያን ሰውነት፣ ምግባርና ሃይማኖት ተብለው
ተተርጉመዋል፡፡

📖መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ ፦

⚜ወንጌል ከኦሪት ጋር የተስማማ ሕግ ነውና (መዝ ፹፥፪)

📖ግነዩ ለእግዚአብሔር በመሰንቆ ፦

⚜በሃይማኖት ጸንታችሁ ለእግዚአብሔር ተገዙ።

📖ወበመዝሙር ዘ፲ቱ አውታሪሁ ዘምሩ ሎቱ ፦

⚜ዐሥር ሕዋሳት ባለው ሰውነት ምግባር ይዛችሁ ተገዙ። አንድም በወንጌል ጸንታቸሁ፣ ሕግጋቱ ዐሥር በሚሆኑ በኦሪት
ጸንታችሁ በመዓልትም በሌሊትም ተገዙ፡፡ (መዝ ፴፪፥፪፣ ፺፪)

✝#የንዋያተ_ማኅሌት_አገልግሎት✝

👉 መዝሙርን አስማምቶ ለመዘመር ማገዝ።

👉 በቤተ ክርስቲያናችን የሚገኙ የዜማ መሣሪያዎች ልክ እንደ ዜማው ትምህርትም ይሰጣሉ ፡፡ተመልካችን በሚታይ ነገር መስሎ
ለማስተማር ይረዳሉ።እነዚህ የዜማ መሣሪያዎች ፍጹም ሰማያዊውን ሥርዓት የሚያመለክቱንና የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ
ክርስቶስን መከራ በዓይነ ሕሊናችን እያየን ወደ ንስሐና እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ የሚያደርሱን ከመሆናቸውም ሌላ ጥልቅ በሆነ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጒም የተሞሉና ምሳሌነት ያላቸው ስለሆኑ ለሚያያቸውም ሆነ ለሚጠቀምባቸው መንፈሳዊ ትምህርት
በመስጠት አዕምሮን በመመገባቸው አንደበት የሌላቸው ሰባክያን ናቸው፡፡

•••

🛎የዐቢይ ጾምን፣ የሰዓታትን ቁመትና የገዳማትን ሥርዓት ስንመለከት ንዋያተ መዝሙር ረዳቶች እንጂ ዋናዎች እንዳይደሉ
እንረዳለን፡፡

✅ለመሣሪያዎቹ የሚሰጠው ዋጋ ከዘማሪውና ከመዝሙሩ ይዘትና ዓላማ መብለጥ የለበትም።

•••
📮ከመንፈሳዊ ዓላማ የሚያወጡ ፍጹም ዓለማዊ የሆኑ ሥጋን አስደስተው ነፍስን የሚያደክሙ መሣሪያችም አሉ፡፡ ከቤተ
ክርስቲያናችን ውጪ የሆኑ የዘፈን መሣሪያዎች አሠራራቸውም ለዘፈን አገልግሎት በመሆኑ መንፈሳዊ ትርጒምና በረከት
የላቸውም፡፡ የዘፈኑ ዜማ፣ደራስያኑም የዓለም ሰዎች በመሆናቸው የድርሰቱ ዓላማም የሰውን ሥጋዊ ስሜት ማርካት ብቻ በመሆኑ
ለመንፈሳዊ ሕይወት ጥማት ማርኪያ ሊውሉ አይችሉም። ሥጋን የሚያስደስተውንና ነፍስን የሚያሳዝነውን፣ አምላክን
የሚያስረሳውን ጭፈራና ሁካታን የሚያባብሰውን መሣሪያ ቤተ ክርስቲያናችን ፈጽሞ አትቀበልም፡፡

•••

👉የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ መሣሪያዎች እጅግ መንፈሳዊና ራስን በንስሐ በማንጻት ነፍስን በማርካትና ሥጋዊ ስሜትን
በመቆጣጠር በተመስጦ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ እግዚአብሔር ለእኛ ለሰው ልጆች የሰጠን ጸጋዎች ናቸው፡፡

✝#የቅዱስ_ሲኖዶስ_ውሳኔ✝

👉የቤተ ክርስቲያናችን ራስ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፪ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ለመንፈሳዊ ዜማ አገልግሎት እንድንጠቀምባቸው
የደነገገልን የዜማ መሣሪያዎች የሚከተሉት ብቻ ናቸው።

✅ከበሮ

✅ጸናጽል

✅መቋሚያ

✅በገና

✅መሰንቆ

✅ዋሽንት

✅መለከት

✅እንዚራ

📮እነዚህ የዜማ መሳሪያዎችም በሁለት(፪) ይከፈላሉ።

🟢የውስጥ ንዋያት፡-

➢በቅኔ ማኅሌት የቁመት አገልግሎት ይሰጣሉ።

➢እነኚህ የዜማ መሳሪያዎች ሥርዓት ከተሠራባቸው ገዳማት በቀር በሁሉም አድባራትና ገዳማት አሉ። በአውደ ምሕረት፣
በአደባባይና በጉባኤም ይኖራሉ።
🛎#መቋሚያ፣ #ከበሮ፣ #ጸናጽል

🔴የውጭ ንዋያት፡-

➢ወደ መቅደስ(ቅኔ ማኅሌት) የማይገቡ

➢ በቤት፣ በአደባባይ እና በጉባኤ የሚያገለግሉ ናቸው።

🛎#መሰንቆ፣ #በገና፣ #ዋሽንት፣#መለከት ፣#እንዚራ

✍የመዝሙር መሳሪያዎቹ እኒህ እንዲሆኑ የተወሰኑት ትውፊት፣ ምሳሌና ምስጢር ያላቸው በመሆኑ ነው፡፡

•••

👉ቤተ-ክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ የአባቶቻችንን ቃል በመያዝ እነ ጠቢቡ ሰሎሞን በጥበባቸው ያልቀየሩትን በቅድስና ያጸኑትን
መያዝ እንዳለብን ስታስረዳን “አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍርስ” (ምሳሌ ፳፪፡፳፰ ) እያለች በዚህ በዚህ
አመስግኑ ተጠቀሙ ብላ ሥርዓት ሠርታ፣ ሕግ አውጥታ ሰጥታናለች፡፡

•••

👉ለቤተ-ክርስቲያን አለመታዘዝ ራስዋ ለሆነው ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አለመታዘዝ ነውና ልናከብራት
ይገባል፡፡ “ክብርህን ለባዕድ አትስጥ የሚሻልህንም ለሌላ ወገን አትስጥ” ተብሏል፡፡ (መጽ.ባሮክ ፬፡፫ )

✝#የዜማ_መሳሪያዎች_አመዳደብ✝

📮የዜማ መሳሪያዎች አመዳደብ በአገልግሎት

👉ለመንፈሳዊ ዜማ ግልጋሎት የሚውሉ የቤተ ክርስቲያን የዜማ መሳርያዎች

👉ለሕዝባዊ ዜማ ግልጋሎት የሚውሉ ባህላዊ የዜማ መሳርያዎች

👉ለዘፈን(ለሙዚቃ) የሚያገለግሉ የዜማ መሳርያዎች

•••

📮የዜማ መሳሪያዎች አመዳደብ በጥንት ጊዜ

➢በቅዱስ መጽሐፍ ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ የዜማ ዕቃዎች አገልግሎት የተጠቀሰ ሲሆን በጥንት ጊዜ ሦስት ዓይነት የዜማ እቃዎች
እንደ ነበሩ ተጠቅሰዋል፡፡እነዚህም፡-
✅አውታር ያላቸው የዜማ ዕቃዎች፡- በገና፣ መሰንቆ

✅የሚነፋ የዜማ ዕቃ፡- መለከት፣ እምቢልታ፣ ዋሽንት

✅እርስበረስ በማማታት ወይም በእጅ በመምታት ድምጽ የሚሰጡ፡- ከበሮ፤ ነጋሪት፣ ጸናጽል

•••

📮የዜማ መሳሪያዎች አመዳደብ በዘመናዊ የዜማ ትምህርት

➢በዘመናዊው የዜማ ትምህርት የዜማ መሳሪያዎች በአምስት(፭) ይከፋላሉ።

🔔እርስ በርስ በማጋጨት ድምጽ የሚሰጡ (Ideophone)

🎻የክር (የአውታር) መሳሪያዎች (Chordaphone)

🥁የምት የዜማ ዕቃዎች (Membraphone)

🎷የትንፋሽ መሳሪዎች (Aerophone)

🎹በኤሌክትሪክ አማካኝነት ድምጽ የሚፈጥሩ መሳሪያዎች (Electrophone)

•••

📮መንፈሳዊ የዜማ መሳሪያዎች በ፭ ደረጃዎች ይከፈላሉ፡፡

🔸አውታር ያላቸው፦በገና፣ መሰንቆ

🔸በእስትንፋስ የሚነፉ፦ዋሽንት፣ መለከት፣

🔸እርስ በርሳቸው በመምታት(በእጅ በመምታት)፦ ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መሰንቆ

🔸በቅኔ ማኀሌት የምንጠቀምባቸው፦ ከበሮ፣ መቋሚያ ፣ ጸናጽል

🔸ከቅኔ ማኀሌት ውጪ የምንገለገልባቸው፦ በገና፣ መሰንቆ፣ ዋሽንት፣መለከት፣እንዚራ

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮
#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

👉@betenzira👈

👉@bete_enzira👈

ቤተ-ዕንዚራ:

🟢ከበሮ

🛎#አሠራር

⚜ከበሮ ስፋትና ክብደት ካላቸው የዜማ መሣሪዎች አንዱ ነው፡፡ከበሮ ከዕንጨት ፍልፍል ወይም ከብር እንዲሁም የከብት ቆዳ
የሚሠራ የዜማ መሳሪያ ነው። ዙሪያውን ሱቲ (ጨርቅ) ይለብስና ላዩ ላይ ደግሞ ጥልፍልፍ ጠፍር ይታሠርበል። የከበሮው አፍ
ከአንዱ በኩል ሰፋ ያለ ሆኖ ከተቃራኒው በኩል ደግሞ በጣም ጠበብ ያለ ቅርጽ ያለው ተደርጎ ይበጃል፡፡ በውስጡም ከ፭ እስከ ፯
ጠጠሮች ይደረግበታል፡፡

📮ለማኅሌት የሚመታው ከበሮ ከሐገረሰብ ጭፈራና ሌሎች አጋጣሚዎች ጥቅም ላይ ከሚውሉት ከበሮዎች በአመታቱ፣ አሠራሩና
ምሥጢር አዘልነቱ የተለየ ነው፡፡

🛎#አመታት

♦️ቁጭ ተብሎ (በቁምና በዐቢይ መረግድ ጊዜ)

♦️ተቆሞ (በሽብሸባ ጊዜ) ወይም ወዲህና ወዲያ እየተመላለሱ ትከሻቸው ላይ በማንገት ይመታል፡፡

•••

👉ጊዜን እየጠበቁ በሁለት እጅ ማለትም በቀኝ እጅ ሰፊውን፣ በግራ እጅ ጠባቡን ተመትቶ ወዲያው በማከታተል ቀኙ ይመታል።
እንደየዜማው አገባብ ጠባቡ ክፍል ሁለት ጊዜ ወይም አንድ ጊዜ ከተመታ በኋላ ሰፊው አፍ ይመታል፡፡ ሰፊው ክፍል በሙሉ መዳፍ
ጠበቅ ተደርጎ በኀይል የሚመታ ሲሆን ጠባቡ ክፍል ግን በስሱ በዝግታና በቀስታ በግራ እጅ በአራቱ ጣቶች ነካ እየተደረገ
ይመታል፡፡
🛎#የከበሮ_ትዕምርትነት/ምሳሌነት/

✅ከበሮ፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡

✅የከበሮው ሠፊው ክፍል፦ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በሁሉም ቦታ የመላ መሆኑን ያስረዳል፡፡

✅የከበሮው ጠባቡ ክፍል፦አምላክ በሰውነቱ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን ። አንድም የትስብእትን (የሥጋን) ውሱንነት
ያስረዳል፡፡

✅ሁለቱ የከበሮ አፎች በአንድ ላይ መያያዛቸው፦ የተዋሕዶ ምሳሌ ነው፡፡ መለኮትና ትስብእት አንድ የሆኑት በተዋሕዶ ነውና፡፡

✅ተጠላልፈው የሚታዩት ጠፍሮች፦ አይሁድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘው ከጲላጦስ ትእዛዝ ውጪ አብዝተው
በገረፉት ጊዜ የግርፋቱን ሰንበር የሚያስታውስ ነው፡፡

✅በትከሻ ላይ የሚነገተው ማንገቻ፦ጌታችን በዕለተ ዐርብ የተገረፈበትን ጅራፍና የታሠረበትን ገመድ ያስታውሳል፡፡

✅በከበሮ ውስጥ የሉት ጠጠሮች፦ አይሁድ ጌታን ሲገርፉት ገበጣ ለተጫወቱበት ጠጠር ምሳሌ

✅ከጠፍሩ በታች ከበሮው የተሸፈነበት ሱቲ ወይም ጨርቅ፦አይሁድ ያለበሱት ከለሜዳና የመግነዙ ምሳሌ ነው፡፡

✅በሱቲ የተሸፈነውና በቆዳ የተወጠረው ከበሮ በዝግታና በፍጥነት መመታቱ፦ ነቢዩ ኢሳይያስ “ጀርባዬን ለግርፋት ፊቴን ለጽፋት
ሰጠሁ” ሲል ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነበየው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ፊቱን በሻሽ ሸፍነው አምላክ ከሆንክ በጥፊ
የመታህ ማነው? እያሉ በመዘባበት በጥፊ መመታቱን ለማጠየቅ።

•••

⚜የከበሮው አመታትም መጀመሪያ ሲጀመር በጣም ዝግ ብሎ እየተቆጠረ ይጀምርና በኋላ እየፈጠነ በመሄድ በመጨረሻም
ለመቁጠር በማይቻል ሁኔታ አመታቱ እየፈጠነ ይሄዳል። ይኽም የአመታቱ ሥርዓት የጌታን መመታት ይገልጻል፡፡ ሮማውያን
በሕጋቸው የሚሰቅሉትን አይገርፉትም፤ የሚገርፉትንም አይሰቅሉትም፡፡ ጌታን ግን ገርፈው ለመስቀል ስላሰቡ መጀመሪያ ግርፋቱን
ሲጀምሩ እየቆጠሩ መግረፍ ጀምረዋል፣ በኋላ ግን ቁጥሩን እያሳሳቱ፣ እየተፈራረቁ ብዙ ገርፈውት ስለነበር የከበሮው ምትም
እየፈጠነ በመሄድ ለቆጠራ አስቸጋሪ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱ የጌታን ግርፋት ለማጠየቅ ነው።

🛎#ማጠቃለያ

🔰ከበሮ፦የጌታችን የኢየሱስ ክረስቶስ ምሳሌ

🔰የከበሮው ሰፊው ገጽ፦ የመለኮት ሰፊነት ምሳሌ

🔰የከበሮ ጠባቡ ገጽ፦ የሥጋ ውሱንነት ምሳሌ

🔰የከበሮ ጥልፍልፍነት እና ጠፍር ፦ የጌታችን የግርፋቱ ሰንበር ምሳሌ

🔰የከበሮ ልባስ ጨርቁ፦ የመግነዙ ወይም አይሁድ ጌታን ያለበሱት የቀይ ከለሜዳ ምሳሌ

🔰የከበሮው ማንገቻ፦ ጌታችን ታስሮ የተጐተተበት አንድም የተገረፈበት ጅራፍ ምሳሌ


🔰በከበሮ ውስጥ የሉት ጠጠሮች፦ አይሁድ ጌታን ሲገርፉት ገበጣ ለተጫወቱበት ጠጠር ምሳሌ

🔰ሁለቱ ሰፊውና ጠባብ ገጾች በአንድ ላይ መገናኘታቸው፦የተዋሕዶ ምሳሌ

🔰ከግራ ከቀኝ መመታቱ፦ ጌታ በጥፊ ለመመታቱ ምሳሌ

@betenzira

🟢ጸናጽል

⚜ጸናጽል፡- ጸንጸለ፣መታ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸንጸለ ማለት #አቃጨለ፣#ደወለ ማለት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ
ዳዊት በመዝሙር ፻፶፡፭ “እግዚአብሔርን ድምጹ መልካም በሆነ ጸናጸል አመስግኑት” በማለት ጸናጽል ለመዝሙር አገልግሎት
ያለውን ታላቅ ድርሻ ገልጾልናል፡፡

🛎#አሠራር

⚜ጸናጽል ከወርቅ፣ ከብር፣ ከነሐስ ወይም ከብረት ከሚሠራ የዜማ መሣሪያ ነው፡፡ አሰራሩም ከግራና ከቀኝ ሁለት አምዶች፣
ከመሃል ሁለት ቀጫጭን ጋድሞች፤ ከእናት ላይ ቀስተ ዳመና፣ መሃል ካሉት ሁለት ጋድሞች ላይ በአንደኛው ሦስት በሁለተኛው
ሁለት ሻኩራዎች ያሉት ሆኖ ከሥር መጨበጫ (እጀታ) ያሉት ነው።(፪ዜና ፱፥፭ ፪ዜና ፭፥፭፤ ፪ሳሙ ፩፥፭)

🛎#የጸናጽል_ትዕምርትነት/ምሳሌነት/

✅ጸናጽል፦ አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየው የወርቅ መሰላል ምሳሌ ነው፡፡ይህቺም ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት
ሰማይና ምድርን፣ ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች አማናዊት ሰዋሰወ ወርቅ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ “ያዕቆብ
በፍኖተ ሎዛ ያየሽ የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ” እንዲሁም “በካህን አሮን ልብስ ላይ ያለሽ ጸናጽል አንቺ ነሽ” እንዳለ (አባ ሕርያቆስ
በቅ.ማርያም ቁ. ፴፫ )

🌈የጸናጽል ቀስተ ደመናው፦ የጸናጽሉን ጫፍ የቀስተ ደመና ቅርጽ ያለው ሆኖ ከሁለቱ ብረቶች/የግራና የቀኝ/ ጋር የተያያዘ ሆኖ
ይሠራል፡፡ ይህ የቀስተ ደመና ቅርጽ ያለው ብረት ልዑል እግዚአብሔር ለኖኅ ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ እንደማያጠፋት ቃል
ሲገባለት የሰጠው የቀስተ ደመና የቃል ኪዳን ምልክት (ዘፍ ፱፡፰-፲፯) ምሳሌ

✅በውስጡ ያሉት ሁለት ጋድሞች፦ በጸናጽሉ ግራና ቀኝ የሚገኙት የጸናጽሉ መውጫና መውረጃ ምልክቶች የእመቤታችን የቅድስት
ድንግል ማርያም ምሳሌ

✅ሻኩራዎቹ፦ ይወጡባትና ይወርዱባት የነበሩት የመላእክት ምሳሌ አንድም የፍጥረተ ዓለም ምሳሌ አንድም የአዋልድ መጻሕፍት
ምሳሌ
✅የሻኩራዎች ድምፅ፦ የመላእክት ምስጋና ምሳሌ

✅ሁለቱ ዓምዶች፦ የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን አንድም የፍቅረ ቢጽ (ባልንጀራን እንደ ራስ የመውደድ) እና ፍቅረ እግዚአብሔር
ሕግጋት ምሳሌ

✅በአንደኛው ጋድሞ ላይ ያሉት ሦስት ሻኩራዎች፦ የሥሳሴ ሦስትነት ምሳሌ

✅በአንድ ጋድሞ ላይ ሦስቱ መገናኘታቸው፦ የሥላሴ የአንድነታቸውን ምሳሌ

✅ከሥር ያሉት ሁለት ሻኩራዎች፦ የወልድን ሁለት ልደት "ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ያለ አባት"
መወለዱን የሚያጠይቁ ናቸው።

✅የቅጠሎቹ(ሻኩራዎች) ብዛት አምስት መሆናቸው፦ የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌ

✅መጨበጫ(እጀታ)።የሕገ እግዚአብሔር ምሳሌ ፤ መያዣው አንድ መሆኑ በመለኮት፣ በአገዛዝ፣ በሥልጣን አንድ አምላክ መሆኑን
ያስረዳናል፡፡

🙏#በጸናጽል_መዘመራችን

“አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በምሳሌ ያየሽ አማናዊቷ የወርቅ መሰላል እመቤታቸን ድንግል ማርያም ሆይ ልመናችንን ወደ
ልጅሽ አሳርጊልን” ብለን መለመናችን ነው፡፡ አንድም በጸናጽል መዘመራችን “አምላካችን ለኖኅ የገባህለትን ቃል ኪዳን አስበህ ማረን
ዘወትር ይቅርታህና ቸርነትህ ፈጥኖ ይደረግልን” ብለን መለመናችን ነው፡፡

🛎#ማጠቃለያ

🔰ጸናጽል፦ አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየው የወርቅ መሰላል ምሳሌ ነው፡፡ ይህቺም እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ናት፡፡

🔰የጸናጽል ቀስተ ደመናው፦የኖኅ የቃል ኪዳን ምልክት ምሳሌ

🔰የጸናጽሉ ሁለት ጋድሞች፦የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ

🔰ሻኩራዎቹ፦ የመላእክት ምሳሌ አንድም የፍጥረተ ዓለም ምሳሌ አንድም የአዋልድ መጻሕፍት ምሳሌ

🔰የሻኩራዎች ድምፅ፦ የመላእክት ምስጋና ምሳሌ

🔰ሁለቱ ዓምዶች፦ የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን አንድም የፍቅረ ቢጽ እና ፍቅረ እግዚአብሔር ሕግጋት ምሳሌ

🔰በአንደኛው ጋድሞ ላይ ያሉት ሦስት


ሻኩራዎች፦ የሥሳሴ ሦስትነት ምሳሌ

🔰በአንድ ጋድሞ ላይ ሦስቱ መገናኘታቸው፦ የሥላሴ የአንድነታቸውን ምሳሌ

🔰ከሥር ያሉት ሁለት ሻኩራዎች፦ የወልድን ሁለት ልደታት ያጠይቃሉ

🔰የቅጠሎቹ(ሻኩራዎች) ብዛት አምስት መሆናቸው፦ የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌ

🔰መጨበጫ(እጀታ)።የሕገ እግዚአብሔር ምሳሌ።


@betenzira

🟢መቋሚያ

⚜መቋሚያ፡- ቆመ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጒሙም #ተነሣ፣ #ቀጥ_አለ ማለት ነው፡፡

👉መቋሚያ አስቀድሞ በብሉይ ዘመን የነበረ ነው። "ይህች በእጅህ ያለችው ምንድን ናት አለው፡፡ ሙሴም በትር ናት አለ፡፡"(ዘፀ ፬፡
፪) ይህ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን የከፈለበት በትርም የመስቀል ምሳሌ ነው፡፡

♦️ሙሴ የጌታ፣ ግብፅ የሲዖል፣ ባሕረ ኤርትራ የገሃነመ እሳት፣ የሙሴ በትር የመስቀል ምሳሌ ሆነው ይተረጐማሉ፡፡

👉አባ እንጦንስና ቅዱስ ያሬድ በማኅሌትና በጸሎት ጊዜ መቋሚያ ለቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት እንዲውል አድርገዋል፡፡ ይህንም
ያደረጉበት ምክንያት ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ትዕምርተ መስቀል ያለበትን በትሩን በፊቱ እያቆመ ይሰግድና ይጸልይ እንደነበረ ሁሉ
እነርሱም ያንን አስበው እንደሆነ ሊቃውንት ይናገራሉ።(ዕብ ፲፩:፳-፳፩)

🛎#አሠራር

⚜ከጫፉ የመስቀል፣የቀርነ በግዕ(በበግ ቀንድ) ቅርጽ ያለው ነው። መቋሚያ ዘንጉ ከእንጨት፣ መደገፊያው ከእንጨት፣ ከብረት፣
ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ሊሠራ ይችላል፡፡ (ኩፍ፯፡፯፤ዕብ ፮፡፩)።መቋሚያ ርዝመቱ እንደ ተገልጋዩ ቁመት ሊሆን ይችላል፡፡

🛎#የመቋሚያ_ትዕምርትነት/ምሳሌነት/

✅መቋሚያ፦ እግዚአብሔር ለአዳም የሰጠው የተሰፋ መስቀል ምሳሌ ነው፡፡ አንድም መቋሚያ የእፀ መስቀል መሳሌ ነው፤

✅መዘምራን በአገልግሎት ላይ በትክሻቸው መሸከማቸው፦ ጌታችን ስለኛ ሲል መስቀሉን መሸከሙን ለማጠየቅ ነው፡፡በቤተ
ክርስቲያናችንም መቋሚያ የሚያዘው የክርስቶስን መከራ ለማሰብ ነው፡፡

📖ከታሪክ ማኅደር📖

•••
በጐጃም ክፍለ ሀገር መሬትዋፋ በምትባል ሥፍራ ይኖሩ የነበሩ መምህር ዐፅቀ ድንግል የሚባሉ የዐፄ ልብነ ድንግል ወንድም
"መቋሚያ መያዝ" የክርስቶስን መከራ ማሰብ መሆኑን አምነው በተደገፉት ቁጥር እንዲወጋቸውና የክርስቶስን መከራውን
እንዲያስታውሱ ፲፭ እሾህ የፈሰሰበት መቋሚያ አሠርተው ነበር፡፡ ይህንንም አርአያ አድርገው በሸዋ ክፍለ ሀገር በመንዝ የነበሩ
መነኮሳት እንደዚያው እያደረጉ ይሠሩበት ነበር ፡፡ የክርስቶን መከራ በማሰብ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ እንደሚዳንበትም
አምነው መቋሚያቸውን #ተአምኖ ብለው ሰይመውታል፡፡

✅አሠራሩ የበግ ቀንድ ቅርጽ መሆኑ፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "የዓለምን ኀጢአት የሚያስተሠርይ የእግዚአብሔር በግ" መሆኑን
ይገልጻል፡፡

🛎#የመቋሚያ_አገልግሎት

⚜መቋሚያ በማኅሌት ጊዜ በካህናት እጅ በሚውልበት ጊዜ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

👉 ብቸኛ መሣሪያ ሆኖ ያለ ከበሮ እና ያለ ጸናጽል በዝማሜ ብቻ ያገለግላል፡፡ ይህም ከመሬት ጋር በሚጋጭበት ጊዜ ድምፅ
ስለሚያወጣ ነው።

👉እንዲሁም ከጸናጽልና ከከበሮ ጋር በመዋሐድ በሽብሸባ ጊዜ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

👉ከዚህ በተጨማሪም በረጅም የሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ለምሳሌ እንደ ቅዳሴ ባለ ላይ ቀሳውስትም ሆኑ ምእመናን ለድጋፍ
ይገለገሉበታል፡፡

🛎#ማጠቃለያ

🔰መቋሚያ፦ እግዚአብሔር ለአዳም የሰጠው የተሰፋ መስቀል ምሳሌ ነው፡፡ አንድም መቋሚያ የእፀ መስቀል መሳሌ ነው።

🔰መዘምራን በአገልግሎት ላይ በትክሻቸው መሸከማቸው፦ ጌታችን ስለኛ ሲል መስቀሉን መሸከሙን ለማጠየቅ ነው፡፡

🔰የበግ ቀንድ ቅርጽ ያለው መሆኑ፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "የዓለምን ኀጢአት የሚያስተሠርይ የእግዚአብሔር በግ" መሆኑን
ይገልጻል፡፡

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮

#ቤተ_ዕንዚራ
╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

👉@betenzira👈

👉@bete_enzira👈

ቤተ-ዕንዚራ:

🟢ዋሽንት

⚜ዋሽንት ከቀርከሃ ወይም ከሸንበቆ ወይም ከብረት ሊሠራ የሚችል አንጓ ያለው የዜማ መሣሪያ ነው፤ ዋሽንት በተናጠል ወይም
በቡድን ከሌሎች የዜማ መሳሪያዎች ጋር አንድ ሆኖ መዘመር የሚያስችል የዜማ መሳሪያ ነው።

👉ዋሽንት ቅኝት ያለው አስደሳች መሣሪያ ሲሆን እንደሌሎች የዜማ መሣሪያዎች በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በበዛት ተጠቅሶ
ባይገኝም በትንሹ በትንቢተ ዳንኤል (ም፡፫ ቊ፡፭ እና ፲ ) እንዲሁም በአንደኛ ቆሮንቶስ ም ፲፬፡ቊ፡፯ ላይ ተጠቅሶ ይገኛል።

•••

👉በጥንት ጊዜ በነገሥታቱ ዘንድና ታቦተ ሕጉ ሲወሳ ይዘመርበት እንደነበር ይነገራል ዛሬም ቢሆን ታቦተ ሕጉ ሲወጣ የሚጠቀሙበት
አባቶች አሉ።

📮ቀደም ሲልም በሀገራችን ዋሽንት የሬድዮ ፕሮግራም መክፈቻ ሆኖ ሲያገለግልም ነበር።

🛎#የዋሽንት_ትዕምርትነት/ምሳሌነት/

✝ዋሽንት፦ የወንጌል ምሳሌ ነው ፡፡

✝ከዋሽንት የሚወጣው ድምጽ፦ መልካም እንደሆነ ልቡናን እንደሚመስጥ ደስ እንደሚያሰኝም ሁሉ ወንጌልም እግዚአብሔር ነገሠ
ዲያቢሎስ ተሻረ የሚለውን ደስ የሚያሰኝ የምሥራች ድምፅ ታሰማለችና።

✝የዋሽንት ቀዳዳዎች፦

🔰 አራት ቢሆኑ፦ የአራቱ ወንጌላውያን ምሳሌ

🔰አምስት ቢሆኑ፦የአምስቱ አዕማደ ምስጢር ምሳሌ


🔰ስድስት ቢሆኑ፦ የስድስቱ ቃላተ ወንጌል ምሳሌ

@betenzira

🟢መለከት(ቀንደ መለከት)

⚜መለከት ከቀንድ ወይም ከብረት እና ከብር የሚሰራ ለቅስቀሳና ለዐዋጅ መንገሪያ የሚውል በዕለተ ምጽዓት የሚነፋ የዜማ መሳሪያ
ነው፡፡

🌍ድምጹም ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የሚሰማ መሳሪያ ነው፡፡(ማቴ፬፥፩)

📖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ ለመዝሙር አገልግሎት ይጠቀምባቸው ከነበሩት መሳሪያዎች አንዱ እንደነበር
ተጠቅሷል። (ዘፍ ፬፡፳፩)

📯መለከት በትንሣኤ ዘጉባኤ የጌታን መምጣት ያበስራል፡፡(ማቴ ፳፬፥፴፩ ፣ ፩ኛ ተሰ ፬፡፲፮)

📯መለከት ሰዎችን ለግዳጅ ያዘጋጃል፡፡በጥንት ጊዜ ሰዎች ለጦርነት ሲጠሩ ነጋሪት ይጎሰማል መለከት ይነፋል፡፡ በአጠቃላይ መለከት
ሰዎችን ለግዳጅ ዝግጁ እንድንሆን ያስጠነቅቃል፡፡(ሕዝ ፴፫፡፩-፮)

•••

📯መለከት እንዴት አገልግሎት ላይ እንደሚውል በቅዱሳት መጻሕፍት በየአንቀጹና በየምዕራፉ ላይ ተጠቅሶ ይገኛል(ዘፍ ፡ም፡፬፡ቊ፡
፳፩፤ኢያ ፡ም፡፮፡ቊ፡፳፤ ዘኁ ፡ም፡፲፡ቊ፡፩-፲፤፪ኛ ዜና መዋዕ ፡ም፡፭፡ቊ፡፲፪-፲፬)

🔰መለከት ቀንደ መለከትም ይባላል።ይህም ከቀንድ መሠራቱን ያሳያል (፪ኛ ሣሙ ፡ም፡፮፡ቊ፡፲፭፤፩ኛ ዜና መዋ ፡ም፡፲፭፡ቊ፡፳፰፤መዝ
፹፡ቊ፡፫፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ ፲፭)

✅#በመለከት_መዘመራችን
በጌታ ዳግም ምጽዓት በትንሣኤ ዘጉባኤ የምናገኘውን አዲስ ሕይወት በማሰብ ራሳችንን ከወዲሁ በንስሐ እንድናዘጋጅ እንዲረዳን
“በዕለተ ምጽአት ዕጣ ተርታችን ጽዋ ፈንታችን ከቶ ከየትናው ወገን ይሆን?” በማለት ራሳችንን ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድንዘጋጅ
ያሳስበናል፡፡

@betenzira

🟢እንዚራ

⚜እንዚራ በእስትንፋስ የሚነፋ ወይንም በእጅ የሚመታ ወይንም የሚደረደር ንዋየ ማኅሌት ነው። “በከበሮ ወበእንዚራ እንዚራሁ
ለበኩርኪ እለ ይነፍሑ እንዚራተ” ሲል ይገኛል።

📖እንዚራ በመጽሐፍ ቅዱስ በትንቢተ ኢሳ ፭:፲፪ ላይ የተገለጸ የመዝሙር መሳሪያ ነው። (ወሰትይዎ ለወይን እንዘ የኅልዩ በመሰንቆ
ወበከበሮ ወበዕንዚራ ይሰትይዎ ለወይን)። አንድምታውም

⚜"መሰንቆውን ከበሮውን በገናውን እየመቱ እየዘፈኑ ወይኑን ለሚጠጡት ወዮላቸው።

⚜አንድም መሰንቆ እየመቱ ከበሮ እየጸፉ በገና እየደረደሩ ወይኑን ለሚጠጡት ሰዎች ወዮላቸው።" ይላል።

🔰የትንቢተ ኢሳይያስ አንድምታ መጽሐፍ እንዚራን በገና ብሎ ይፈታዋል።(#ወበዕንዚራ ያለውን #በገና ብሎ ፈትቶታል) በዚህ
ምክንያት ይመስላል በገና በአባቶች ዘንድ እንዚራም እየተባለ መጠራቱ።

🔰 እንዚራ አሁን ላይ ስለጠፋ መልኩ እና ይዘቱ በውል ባይታወቅም። እንዲሁም አገልግሎት ላይ ሲውል ባይታይም ቅዱስ ሲኖዶስ
ግን ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበላቸው የዜማ መሣሪያዎች ውስጥ አንዱ ሆኖ እንዲያገለግል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

@betenzira

🟢መሰንቆ

⚜መሰንቆ፡- መሰንቆ የሚለው ቃል ወይም ስም የተገኘው(ሰንቀወ) ካለው ግሥ ሲሆን ትርጉሙም ሰነቃ፣ ሞዘቀ፣ መታ፣ አስጮኸ፣
ደረደረ፣ ከረከረ ከመሣሪያው ጋር ጮኸ፣ አዜመ፣ዘመረ፣ገጠመ፣አጉረመረመ፣ማለት ነው።
•••

📖ያነዝሩ ወይሰነቅዉ ሠናየ ሰንቅዊ ከመ ዘይሰነቁ ውስተ ቤተ ላኅ ሰንቅዉ ሎቱ በመዝሙር (ኢሳ፡ም፡፭፡ቊ፡፲፪ ፤ ኢዩ፡ም፡፳፩፡ቊ፡፲፪
፤ኢሳ፡ም፡፳፫፡ቊ፡፲፮ ፤ ሢራ፡ም፡፳፪፡ቊ፡፮ ፤ ዮዲት፡ም፡፲፮፡ቊ፡፩)።

👉መሰንቆ በነጠላ በብዙ መሰናቅው፣ መሰናቁት፣ መሰንቆታት ተብለው ይጠራሉ።

📮መሰንቆ በቁሙ ዜማ ማለት ነው።መሰንቆ ወመዝሙር (ሢራ፡ም፡፵፡ቊ፡፳፩) መሰናቅው፣ቃለ መሰናቁት፣ መሰንቆታት፣ የሚል
በየሥፍራው ተጽፎ ይገኛል።(አርጋኖን ፫፡ ቅዳሴ ማሪያም፡ራዕ፡ም፡፲፬፡ቊ፡፪፤መሳ፡ም፡፲፩፡ቊ፡፴፬፤ም፡፳፩፡ቊ፡፳፩፤ ፪ኛ ሣሙ ም፡፮፡
ቊ፡፭)

🛎#አሠራር

⚜መሰንቆ የፈረስ ጭራና ማንገቻ ያለው በቆዳ የተጠፈረ ወይም የተለበደ አውታሩ በግራ እጅ ጣቶች አንቃሳቃሽነት ደጋን መሰል
በሆነና በፈረስ ጭራ በተያዘ እንጨት በቀኝ እጅ እየተመታ በዕጣን ታሽቶ ድምጽ የሚያሰማ የክር የዜማ መሣሪያ ነው።

@betenzira

🛎#መሰንቆ_በመጽሐፍ_ቅዱስ

📖መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ

✍ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት
ጉባኤ ያገኙሃል።(፲፥፭)

📖መጽሐፈ ኢዮብ

✍ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ በእምቢልታ ድምፅ ደስ ይላቸዋል።(፳፩፥፲፪)


📖ትንቢተ ኢሳይያስ

✍አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ።(፳፫፥፲፮)

📖መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ

✍ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆም በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽል በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው
ይጫወቱ ነበር።(፮፥፭)

📖መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ

✍ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት መከታ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ። (፲፥፲፪)

📖መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ

✍ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ
ነበር።(፲፫፥፰)

✍ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን
ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን ኣለቆች ተናገረ።(፲፭፥፲፮)

✍ዘካርያስ፥ ዓዝዔል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሤያ፥ በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ነበር።(፲፭፥፳)

✍እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆ እያሉ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል
ኪዳን ታቦት አመጡ።(፲፭፥፳፰)

✍አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድኤዶም፥
ይዒኤል በመሰንቆና በበገና አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር።(፲፮፥፭)

✍ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች
ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።(፪፭፥፩)

📖መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ


✍መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ጥሩ።በፍታ ለብሰው ጸናጽልና
በገና መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በመሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር።
ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ።(፭፥፲፪)

✍ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እንደዚህም ያለ
በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።(፱፥፲፩)

✍በበገናም በመሰንቆም በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገቡ።(፳፥፳፰)

✍ይህንም ትእዛዝ እግዚአብሔር በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን
ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ቤት አቆመ።(፳፱፥፳፭)

📖መጽሐፈ ነህምያ

✍የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ
ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።(፲፪፥፳፯)

📖መጽሐፈ ኢዮብ

✍ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ፥ በእምቢልታ ድምፅ ደስ ይላቸዋል።(፳፩፥፲፪)

✍ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥ እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ ቃል ሆነ።(፴፥፴፩)

📖መዝሙረ ዳዊት

✍እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።(፴፫፥፪)

✍ክብሬ ይነሣ፥ በገናና መሰንቆም ይነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።(፶፯፥፰)

✍እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።(፸፩፥፳፪)

✍ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር።(፹፩፥፩)

✍አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።(፺፪፥፫)


✍ለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።(፺፰፥፭)

✍በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።(፻፰፥፪)

✍በአኻያ ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።(፻፴፯፥፪)

✍ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ።(፻፵፯፥፯)

✍ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።(፻፵፱፥፫)

✍በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።(፻፶፥፫)

📖ትንቢተ ኢሳይያስ

✍ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ አንጀቴም ስለ ቂርሔሬስ እንደ መሰንቆ ትጮኻለች።(፲፮፥፲፩)

✍አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ።(፳፫፥፲፮)

✍የከበሮው ሐሤት ቀርቶአል፥ የደስተኞች ድምፅ ዝም ብሎአል፥ የመሰንቆ ደስታ ቀርቷል። (፳፬፥፰)

✍እግዚአብሔር በላዩ በሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ
ይዋጋቸዋል።(፴፥፴፪)

📖ትንቢተ ሕዝቅኤል

✍መሰንቆና በገና ከበሮና እምቢልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም
ያደረገችውን አላስተዋሉም።(፭፥፲፪)

@betenzira

🛎#የመሰንቆ_ትዕምርትነት/ምሳሌነት/
✝መሰንቆ፦የሐይማኖት ምሳሌ ነው።

✝የመሰንቆ አውታር አንድ መሆኑ፦ ሐይማኖት አንዲት የመሆኗ ምሳሌ።(ኤፌ ፬፥፬) "አንዲት ጥምቀት አንዲት ሐይማኖት..."
እንዲል።

⚜አንድም መሰንቆ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነው። “የዳዊት መሰንቆ አንቺ ነሽ” እንዳለ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ
ማርያም

✝አውታሩ(ክሩ) ቀጥ ብሎ መውረዱ፦ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቀጥተኛ ሐይማኖት መሆኑን ያጠይቃል፡፡

✝ዕጣን፦ የጌታ ምሳሌ።የምሥራቅ ነገሥታት ካመጡለት እጅ መንሻ መካከል ዕጣን አንዱ ነው።"አምድኡ ዕጣነ ከመ አምላክ ውእቱ"
አምላክ ነውና አምላክነቱን ለማጠየቅ ዕጣን አመጡለት እንዲል መሰንቆም የአምላከ አማልክት ማመስገኛ ነውና በዕጣን
ይታሻል።በሌላ ነገር ቢያሹት ድምፅ አያወጣምን? ቢሉ አዎን የእግዚአብሔር ምስጋና የሚከብር በራሱ ነውና ።ይህም ባይሆን ድምፁ
ደስ ባላሰኘ ነበር።

✝አውታር፦ የእመቤታችን ምሳሌ

✝የመሰንቆ ክር በዕጣን ታሽቶ ድምፅ መስጠቱ፦ ክሩ በዕጣን ታሽቶ ድምጽ ለመስጠት እንደበቃ እመቤታችንም ጌታን በመውለዷ
ወላዲተ አምላክ ለመባል በቅታለችና፡፡ክሩ በዕጣን ታሽቶ የተለያየ ድምጽ እንደሚሰጥ ሁሉ እመቤታችንም የጌታ እናት በመሆኗ
“ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል” (ሉቃ ፩፡፵፰) ብላ እንደተናገረችው የተለያዩ ሊቃውንት በተለያየ ምስጋና አመስግነዋታልና፡፡

✝ከመሰንቆ የሚወጣው ድምፅ፦ የእመቤታችን የምስጋናዋ ምሳሌ

✝ከአንድ አውታር አምስት ዓይነት ድምፅ ማውጣቱ፦አንዲቷ ቤተ-ክርስቲያን በ፭ቱ አዕማደ ምስጢራት የመቃኘቷ ምሳሌ ።

✝መሰንቆ ላይ ያሉት አምስት መስቀሎች፦ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምስቱ ቅንዋተ መስቀል (ሳዶር፣ አላዶር፣
ዳናት፣ አዴራ፣ ሮዳስ) ምሳሌ።እኒህም መስቀሎች

💠በመሰንቆ ጫፍ የሚደረገው መስቀል

💠ምሰሶው እና መቃኛው ተመሳቅለው የሚፈጥሩት የመስቀል ቅርጽ

💠ምሰሶውና የድምጽ ሳጥኑ ተመሳቅለው የሚፈጥሩት የመስቀል ቅርጽ

💠በርኩማው እና አውታሩ(ክሩ) ተመሳቅለው የሚፈጥሩት የመስቀል ቅርጽ

💠አውታሩ እና ደጋኑ በመገዝገዝ ሰዓት የሚፈጥሩት የመስቀል ቅርጽ


✝የመሰንቆ መምቻው(ደጋን)፦ የኪዳነ ኖኅ ምሳሌ ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ለኖኅ ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ ላያጠፋት ቃል
የገባለት ምሳሌ ነው፡፡ (ዘፍ ፱፡፲፩-፳) ይህም የመሰንቆ መምቻ በቀስተ ደመና ይመስላል፡፡አባታችን ኖኅ ከጥፋት ውኃ የዳነበት
መርከብ ደግሞ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነው፡፡“ኖኅ ከጥፋት ውኃ የዳነብሽ መርከብ አንቺ ነሽ” በማለት አባ
ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ቁ ፴፩ እንደተናገረው፡፡

✅#በመሰንቆ_መዘመራችን

“ለአባታችን ለኖኅ በገባህለት ቃል ኪዳን መሠረት ኃጢአታችንን ተመልክተህ አታጥፋን ማረን” ብለን መለመናችን ሲሆን በሌላ
በኩል ደግሞ “አባታችን ኖኅን ከጥፋት ውኃ ያዳንሽ አማናዊቷ ሐመር /መርከብ/ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የኃጢአት
ማዕበል ጎልብቶ የፈተናውም ማዕበል በርትቶ በክህደት በጥርጥር ማዕበል እንዳንሰጥም ዛሬም ለእኛ ፈጥነሽ ድረሽልን” በማለት
እመቤታችንን መለመናችን ነው፡፡

•••
አንድም በመሰንቆ መዝሙር በዘመርን ቁጥር ውለታ ተከፈለልንን፣ ብለን በማሰብ ፈጣሪያችንን በፍጹም ልባችን እናመሰግነዋለን፡፡
ፍቅሩንም እያሰብን ዘወትር በኃጢአታችን እንጸጸታለን፡፡

🛎#ማጠቃለያ

🔰መሰንቆ፦የሐይማኖት ምስሌ አንድም መሰንቆ የእመቤታችን ምሳሌ ነው።

🔰አንድ አውታር መሆኑ፦የሐይማኖት አንድ መሆንን ያመለክታል፡፡

🔰ቀጥ ብሎ መውረዱ፦ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቀጥተኛ ሐይማኖት መሆኑን ያጠይቃል፡፡

🔰በዕጣን መታሸቱ፦ነገረ ተዋሕዶን ይዘክራል

🔰ዕጣኑ፦የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ

🔰አውታር፦ የእመቤታችን ምሳሌ

🔰ከመሰንቆ የሚወጣው ድምፅ፦ የእመቤታችን የምስጋናዋ ምሳሌ

🔰ከአንድ አውታር አምስት ዓይነት ድምፅ ማውጣቱ፦የ፭ቱ አዕማደ ምስጢራት ምሳሌ።


🔰መሰንቆ ላይ ያሉት አምስት መስቀሎች፦ የአምስቱ ቅንዋተ መስቀል ምሳሌ።

🔰ደጋን(መገዝገዣ)፦የኖኃ ቃል ኪዳን ምልክት የሆነቸው የቀስተ ደመናው ምሳሌ ነው፡፡

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

👉@betenzira👈

👉@bete_enzira👈

ቤተ-ዕንዚራ:

🟢 በገና

⚜ በገና አውታር ካላቸው የዜማ እቃዎች (Chordaphone) የሚመደብ ሲሆን በእድሜው ትልቅነትም ከ አምስት ሺህ

ስምንት መቶ ዓመት በላይ እድሜ ያለው፤ ለአውታር መሳሪያዎች አባት ሊባል የሚችል ነው፡፡

•••

በመመሰጥ ኃይሉ፣ በእርጋታው፣ ብቻውን የሚዘመርበት በመሆኑ፣ በሥነ ቃሉ እና በመሳሰሉት ዕሴቶቹ የተለየ ነው፡፡

እንዲሁም በሰማይም በምድረም አገልግሎት ያለው ለመንፈሳዊ ግልጋሎት ብቻ የምንጠቀምበት


የእያንዳንዱ አካል ክፍሎቹ አሰራር ፣ ሥያሜና

ምሳሌነታቸውም መንፈሳዊ የሆኑ፤ ደርዳሪዎቹንም ወደ መንፈዊ ሕይወት የሚመራው መንፈሳዊ መሳርያ ነው፡፡

📮ስለ በገና የተለያዩ አባቶች ያስቀመጡት ትርጉም

✅ ሰዋሰዋዊ ትርጉም

✝አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በሁለት መልኩ "ሲጠብቅና ሲላላ" ብለው በማመሳጠር በገናን ሲተረጉሙት፣

👉በገና፡- በዕብራይስጥ "ናጌን" ይባላል። ትርጉሙም

❖ሲላላ፦ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ፣ ማለት ነው፡፡

❖ሲጠብቅ ፡- ነደደ፣ ተቆጣ... ያሰኛል ብለዋል፡፡

👉በገናን በቁሙ መዝሙር ማለት ነው ብለውም ፈትተውታል፡፡ለዚህም ማስረጃ ቅዱሱ መጽሐፍ ነው።

📖ግነዩ ለእግዚአብሔር በመሰንቆ ወበመዝሙር ዘአስርቱ አውታሪሁ።

፨"እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት"መዝ.፴፪/፴፫፡፪

📖ኣፀምእ፤ ምሳሌ በእዝንየ፤ ወእከስት በመዝሙር ነገርየ፡፡

፨ “ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ ነገሬን በበገና እገልጻለሁ።” መዝ ፵፰/፵፱፡፬-፭

📖መዝ ፶፮/፶፯፡፰፣ መዝ ፸/፸፩፡፳፪፣ መዝ ፹/፹፩፡፪፣ መዝ ፺፩/፺፪፡፫ መዝ ፻፯/፻፰፡፪፣ መዝ ፻፵፫/፻፵፬:፱ መዝ

፻፵፱/፻፶፡፫
👉ሁሉም ላይ የግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ በገናን መዝሙር በማለት ይጠቅሳል፡፡ከላይ በተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ

ጥቅሶች ውስጥም “ወበመዝሙር” የሚሉት በገናን ሲገለጽ ወይም ለማጠየቅ ነው፡፡

✝ከሳቴ ብርሃን ተሰማ በገናን እንዲህ ተርጉመውታል።

👉በገና፡- በዐሥር አዉታር ጅማት በገናን ሠራ፣ ቃኘ፣ ደረደረ፣ ድምጽን እያጣራ፣ እያጣቀሰ፣ እየነዘረ... በገናን በገነ…..

ብለውታል

👉በገነኛ፡- በገናን የሚመታ፣ በገናን የሚያውቅ ደርዳሪ... ማለት ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡

✅ሥነ ቃላዊ ትርጉም

👉በገነ፡- አደረቀ፣ አቃጠለ፣ አነደደ...ማለት ነው፡፡ በገናም ከዚህ የሚወጣ ስም ነው፡፡ የዚህን ትርጉም ማግኘት ዋና

ምክንያትም የበገና ሁለገብ ሰውነት (ሞላ ነገሩ) በደረቅ ነገሮች ማለትም በደረቅ እንጨትና በደረቅ ቆዳ እንዲሁም

በደረቅ ጅማት የሚሠራ ወይም የሚዘጋጅ ስለሆነ በገና ተባለ ተብሎ ይተረጐማል፡፡

👉በገና፡- "በ" እና "ገና" በመነጣጠል የሚያስገኘውን ትርጉም በመጠቀም... በ ... ገና.... በገና በዓል ወይ በገና

ወቅት የሚደረደር የምስጋና መሣርያ ስለሆነ በገና ተባለ ተብሎ ይተረጎማል፡፡

👉በገናን በገነ፦ ማለት ደረደረ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በገና ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር... ማለት ነው።ለዚህም

ማስረጃችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው ።


#በገና_ምስጋና

📖"አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሃለሁ"መዝ ፵፪/፵፫፡፬

#በገና_ድርደራ

"ለእግዚኣብሔር በገና ደርድሩለት" መዝ ፵፰፡፭

#በገና_መዝሙር

"እግዚኣብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት" መዝ ፴፪/፴፫፡፪

🔰ማጠቃለያ

👉ከሁለቱም ወገን (ሰዋሰዋዊ እና ሥነ ቃላዊ) በሚወሰዱ የትርጉም መመሳሰል በመነሳት በምስጢር ከበገና

መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ጋር የተሻለ ቀረቤታ ያለውን ትርጉም ስንመለከት፡-

✅በገነ፦ ቃኘ፤ ደረደረ፣ መታ….የሚል ትርጉም ይሰጠናል፡፡

👉በገነኛው ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ በገናን ሲተረጉም መዝሙር፣ ምስጋና፣ድርደራ... በማለት ሲገልጽ
እናገኘዋለን፡፡

@betenzira

#በገና_በመጽሐፍ_ቅዱስ
👉በገና ለመጀመሪያ ጊዜ በመጸሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በዘፍ ፬፡፳፩ ላይ ሲሆን "የላሜህ ልጅ ዮባል" በገና እና

መለከት ለሚይዙ አባት እንደ ሆነ ተጠቅሷል፡፡ ይህ ታሪክ ሌሎች በገና እና መለከትን የሚይዙ እንደ ነበሩ ዮባል

አለቃቸው እንደ ነበረም ያስረዳል፡፡

👉ከዚያ ዘመን ጀምሮ በገና እግዚአብሔርን የማመስገኛ የዜማ ዕቃነቱ ታውቆ እንደ ሌሎቹ የቤተ መቅደስ የዜማ

ዕቃዎች በሌዋውያን በተመረጡ አለቆች አማካኝነት አገልግሎት ይሰጥ ነበር፡፡

👉በአጠቃላይ በገና በመጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ዮሐንስ ድረስ ከ ፶ ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡

ተ.ቁ የመጽሐፉ ስም የድግግሞሽ ብዛት

፩ ኦሪት ዘፍጥረት-------------፪

፪ ፩ኛ ሳሙኤል---------------፯

፫ ፪ኛ ሳሙኤል---------------፩

፬ ፩ኛ ነገሥት-----------------፩

፭ ፪ኛ ነገሥት-----------------፩

፮ ፩ኛ ዜና መዋዕል-----------፯

፯ ፪ኛ ዜና መዋዕል-----------፬

፰ መጽሐፈ ነሕሚያ-----------፩

፱ መዝሙረ ዳዊት-----------፲፯

፲ ትንቢተ ኢሳይያስ-----------፪
፲፩ ሰቆቃወ ኤርምያስ----------፩

፲፪ ትንቢተ ሕዝቅኤል-----------፩

፲፫ ትንቢተ ዳንኤል-------------፬

፲፬ ራዕየ ዮሐንስ---------------፬

@ b eten zira

#የበገና_ታሪካዊ_አጀማመር

⚜በገና በትክክል መቼና እንዴት ተጀመረ የሚለው ጥያቄ መልሱ ከባድ ቢሆንም የጥበባት ምንጫቸው መጽሐፍ

ቅዱስ በመሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገልጾ የምናገኘው የምስጋና ወይም የዜማ መሣሪያ በገና

መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡

🔔 በገናን ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅ የዩባል /ኢዮቤል/ ልጆች ነበሩ። (ዘፍ.፬፡፲፱-፳፬)

👉መምህር ሙሴ ኃይሉ የአንድምታ ትርጓሜ

ምጮችን በማከል ይህን ታሪክ ስለ በገና ይበልጥ ሊያስረዳን በሚችል መልኩ እንደሚከተለው አብራርተውታል።

•••
"በገና ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅ ዮባል/ኢዩቤል/ ልጆች ነበሩ። ይኸውም አይነ ስውር የነበረ ላሜህ

አያታቸው በበረሃ እየሄደ እያለ ቃኤል ተቅበዝባዥ ነበረና ለብቻው በዱር ተሰውሮ ሲንኮሻኮሽ ሰምቶ መንገድ ይመራው

ለነበረው ለረድዕ(መንገድ መሪ)”እጄ ይሞቅብኛል፣ቅጠሎች ሲንኮሻኮሹ እሰማለሁ፣ አራዊት መጥቶብናል መሰለኝ

እና ድንጋይ አቀብለኝ።” ካለው በኋላ ድንጋዩን ተቀብሎ በሰማው አቅጣጫ ቢወረውር ቃኤልን ግባሩን መትቶ ገደለው።

ቀርበውም ሲመለከቱ ቃየል ሆኖ ሲያገኘው መሪር የሆነን ለቅሶ አለቀሰ።ከዚህ በኋላ ሁለቱ የላሜህ ሚስቶች፤ ላሜህ

ይህን ጸጸቱን በነገራቸው መሰረት ለልጆቻቸው ነግረዋል። ይህ ሁኔታ በተዋረድ እየተነገረ መጥቶ የላሜህ የልጅ

ልጆች(የዮባል ልጆች) ይህ ታሪክ እነርሱ ጋር ሲደርስ ከአቤል ጀምሮ በአባቶቻቸው ላይ የሆነውን ከባድ የመገዳደል

ታሪክ በማሰብ እና በማዘናቸው “ከደረቁ ቁሳቁሶች በገናን አበጅተው በመስራት እያንጎራጎሩ (በማኅዘኒ) ሃዘናቸውን

ገልጸዋል።" በዚህ መሰረት በገና ከአዳም ዘጠነኛ(፱) ትውልድ ላይ መደርደር ጀምሯል።የትውልድ ሰንሰለቱም እንዲህ
ነው

🔰አዳም፡- ቃኤልን ይወልዳል

🔰ቃኤል፡- ሄኖሕን ይወልዳል

🔰ሄኖሕ፡- ጋይዳድን ይወልዳል

🔰ጋይዳድ፡- ሜኤልን ይወልዳል

🔰ሜኤል፡- ማቱሣኤልን ይወልዳል

🔰ማቱሣኤል፡- ላሜሕን ይወልዳል

🔰ላሜሕ፡- ዮባልን ይወልዳል

🔰ዮባል፦ በገና ለሚደረድሩ አባት ነበር።(ስማቸው በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አልተገለጸም።)


👉በመሆኑም ከአዳም ዘጠነኛ ትውልድ የሆኑ የላሜሕ የልጅ ልጆች በሆኑት በእነዚህ አበው ምክንያት በገናን ተዘጋጅቶ

መደርደር ተጀመረ፡፡

@ b eten zira

#በገና_በኢትዮጵያ

👉የበገና ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ አመጣጥ ታሪክ ሁለት(፪) ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡

1⃣#በገና_ኢትዮጵያዊ_መነሻ_ያለው_ነው❗️

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

⚜በገና የሀገራችን ኢትዮጵያ የሥልጣኔዋ ውጤትና በሕገ ልቡና የማመንዋ ውጤት ነው፡፡ ወይም በገና መሥራትና

ማመስገን የተጀመረ እዚሁ ሀገራችን ነው የሚል አስተምህሮ ነው፡፡

•••

መዛግብት የቀዳማዊ ምኒልክ አያት የንግሥት

ሳባ(ንግሥት ማክዳ) እናት ንግሥት "አዝሚና" በገና ደርዳሪ እንደነበሩ ይናገራሉ።

👉መጽሐፈ ሱባኤ ከአዝሚና በተጨማሪ "አፄ" የተባለ የኢትዮጵያ ንጉሥ በመቶ የሚቆጠሩ በገና ደርዳሪዎችና

መዘምራን እንደነበሩት ይናገራል።


•••

የ"ተዋሲያ" ወይም የ"ሳቢ" የመጨረሻ ሴት ልጁ አዝሚና የምትባል ቆንጆና ዘፋኝ ልጅ ነበረችው። እርሱም ከዋይዝ

ከተማ እንድታስደስተው መጥታ በሳባ ትኖር ነበር።አፄን አምላኩን በበገና፣በከበሮ፣ በእምቢልታ እየዘመሩ በፊቱ

የሚያመሰግኑለት መቶ ጃንደረቦች ሶስት ሞቶ ደናግላን ሴቶች ነበሩት።” (መጽሐፈ ሱባኤ ገጽ ፻፷፰)

•••

⚜በገና ፍጹም ኢትዮጵያዊ ነበር የሚለውን አመለካከት በተመለከተ ተጨማሪ ማስረጃዎች።

🔰በበገና የምናዜማቸው ዝማሬዎች ኢትዮጵያዊ ቃና እና ጣዕም ያላቸው መሆን።

🔰በገና ላይ የምንጠቀምባቸው ቅኝቶች ፍጹም ኢትዮጵያዊ መልክ መያዛቸው እንዲሁም

🔰በገና የሚሠራባቸው ግብዓቶች ከጥንትም ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመስራት የሚጠቀሙባቸው

ግብዓቶች መሆናቸውና ፤ ከሥነ ቃሉ ሁሉ ጋር ተደምሮ ሲታይ ኢትዮጵያዊ የመሆኑ ሚዛን ይደፋል ይላሉ።

🛎 ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው በገና ትክክለኛው በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በገና ስለመሆኑ ማስረጃዋች

🔰ቅዱስ ዳዊት ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምራለሁ ባለው መሰረት አሁን ያለው በገና ዐሥር አውታር ያለው

መሆኑ።

🔰ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምሥጢር ሀገሩ ስለሆነች በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ይመሰገንባቸው የነበሩት የዜማ

ዕቃዎች እንደ መሰንቆ፣ ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መለከት እና የመሳሰሉት ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉት ንዋየ ቅዱሳት

ቅርጻቸው ሳይለወጥ መኖራቸው።


🔰በገና በታቦተ ጽዮን ፊት አገልግሎት ይሰጥ ስለነበረ እና ታቦተ ጽዮንም በፈቃደ እግዚአብሔር በንጉሥ ሰሎሞን ልጅ

(ምንሊክ) ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በሀገራችን መኖሯ።

🔰በኢትዮጵያውያን ባሕል ለቤተ ክርስትያን እና ለቤተ መንግሥት ዕቃዎች ልዩ ክብር ስለሚሰጥ በገና በቤተ-

ክርስትያንም በቤተ-መንግሥትም አገልግሎት የሚሰጥ ስለሆነና ስለነበረ ቅርጽና ይዘቱን ሳይለቅ የመኖር ዕድል
በማግኘቱ።

👉በእነዚህ ምክንያቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው በገና በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በገና ስለመሆኑ ማስረጃዋች
ናቸው።

•••

👉የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ መምህርት ወለተማርያም፣ እንዲሁም ከሀገራችን

ነገሥታት አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ዩሐንስ፣ አፄ ምኒልክ፣እቴጌ ጣይቱ፣ልጅ እያሱ (በነጋድራስ ተሰማ እሸቴ) ተምረው፤

እንዲሁም ንጉሡ ሚካኤልና ሌሎችም ይደረድሩ እንደነበር የሚናገሩ አፈታሪኮች አሉ፣ ነገሥታቱም በሥርዓተ ቤተ

ክርስቲያን ያደጉ ስለነበር በገና መደርደር ባይችሉም እንኳ የራሳቸው በገና ደርዳሪ እንደ ነበራቸው ይነገራል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

2⃣ #በገና_እስራኤላዊ_መነሻ_ያለው_ነው❗️

🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱
⚜አንድም በቀዳማዊ ምኒሊክ ጊዜ ከታቦተ ጽዮን ጋራ አብረው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የዜማና

የሥርዓተ አምልኮ ንዋያተ ቅድሳት፣ መጻሕፍት...ወዘተ አንዱ ሆኖ የመጣ ነው የሚሉ አሉ። በተጨማሪም

•••

በቀዳማዊ ሚኒልክ ዘመን በሊቀ ካህናቱ በዘካሪያስ እጅ ታቦተ ጽዮንና ሌዋዉያን ሲመጡ የመዝሙር መጻሕፍትና

በተመሳሳይ የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ ከበገናው ጋር አብረዉ መጥተዋል የሚሉም አሉ፡፡

•••

ለዚህም ማሳያ በዘመነ ኦሪት የመጡ የዜማ መሳሪያዎች ፤ አለባባስና የመዝሙር አጠቃቃም ስልቶች ዛሬም ድረስ ቤተ

ክርስቲያን ቅርጻቸው እና ትውፊታቸው ሳይቀየር ለዘመናት እየተገለገለችባቸው መገኘቷ ነው ፡፡ ፡

•••

ከዜማ መሳሪያዎች መካከልም ከበሮ ፤ ጸናጽል ፤ መለከት ፤ መሰንቆ ፤ በገና ይገኙበታል ፡፡ ከአለባበስም ረጅም ቀሚስ

፤ ጥምጥም ፤ መጎናጸፊያ (ጋቢ ) እና ካባ ይገኙበታል ፡፡

👉ይህ አመለካከትም ይበልጥ በሀገራችን ጠበብት ሊቃውንት በስፋት ይተረጉማል፣ ይተረካል... ይታመናልም፡፡

🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱

════◉❖◉═════

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

👉@betenzira👈

👉@bete_enzira👈

ቤተ-ዕንዚራ:

🟢#የበገና_መንፈሳዊ_አገልግሎት

🔰እግዚአብሔርን ለማመስገን ፤ ጸሎት ልመናን ወደ እርሱ ለማቅረብ

👉በገና የሚያገለግለው ለመንፈሳዊ ትሩፋት ማለትም ለምሥጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ተመርጦ ለቤተ-
ክርስቲያን አገልግሎት ይውላል፡፡ ዝማሬ ከሚቀርብባቸው መንገዶች በገና አንዱ እና በብዙ ምክንያቶች ተመራጭ
በመሆኑ፣ ለእግዚአብሔር እንዲሁም እርሱ ይመሰገኑ ዘንድ ላለላቸው ሁሉ ምስጋና መሠውያ መሳሪያ ነው። በገና
ሰማያዊ ንዋየ ማኅሌት መሆኑን በዩሐንስ ራዕይ ተመዝግቦ እናገኛለን።

“በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፤ሰባትም ቀንዶችና ሰባት
አይኖች ነበሩት፣ እርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው። መጥቶም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ
ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፍን ወሰደው። መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ እንስሶችና ሃያ አራቱም ሽማግሌዎች በበጉ ፊት
ወደቁ፤እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበት የወርቅ እቃ ያዙ።መጽሐፍንም ትወስድ ዘንድ፣
ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ተገድለሃልና፣ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ፣ከወገንም
ሁሉ፣ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግስትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው በምድርም ላይ
ይነግሳሉ እያሉ አዲስ ቅኔን ይዘምራሉ።"(ራዕይ ፭፥፮ -፲)

•••
ስለዚህ በገና ከመላእክት ወገን የሆኑት አርባዕቱ እንስሳ እና ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት
የክብር ዕቃቸው ነው።

•••

እንዲሁም በመጽሐፈ ሔኖክ ዘአዶናይ ራፋኤል ስለበገና ሲያብራራ "ቅዱሳን የሆኑ መላእክት በጽርሐ አርያም መንበረ
ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ለሕያው እግዚአብሔር ፳፬ ሰዓታት ሙሉ ምስጋና የሚያቀርቡበት የተቀደሰ መሳሪያ ነው"
በማለት በሚገባ አረጋጥዋል፡፡

🔰መንፈሳዊ ሕይወትን ለማጠንከር

👉በገና በዝማሬ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት በመሆኑ የምሥጋናን ሕይወት እንድንኖር በማድረግ መንፈሳዊ
ሕይወታችንን ያለመልማል።እግዚአብሔርን ማመስገን እርሱ ያከበራቸውንም እንደየማዕረጋቸው ምስጋና ለሚገባቸው
ምስጋና ማቅረብ የመንፈሳዊ ሰው ቀዳሚ ሃብቱ ነው።

•••

ከዚህም ባሻገር በበገና የምናገኘው ተመስጦ እራሳችንን መመልከት እንድንችል ስለ ኃጢአታችን የሚወቅሰንን
መንፈስ ቅዱስን በማቅረብ ለንስሐ እና ለፈሪሃ እግዚአብሔር እንድንበረታ ያደርጋል።በዚህ ተመስጦ ውስጥ ከበገና
ዝማሪያት ከምናገኘው መልእክት ጋር ተደምሮ የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ለኛ ያለውን ጽኑ በምህረትና በይቅርታ
የተሞላ የማያቋርጥ ፍቅሩን እንድናስተውል ይረዳናል።

•••

ይህ ሁሉ ተደምሮ በገና በቤታችን ጭምር ዕለት ዕለት አብሮን የሚኖር መሳሪያ መሆኑ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ያለው
አስተዋጽኦ የጎላ ያደርገዋል።

🔰ለተመስጦ

👉በገና በፍጹም እርጋታ፣ ያለምንም የሰውነት ውዝዋዜ፣ በተረጋጋና በማስተዋል መንፈስ የሚደረደር በመሆኑ፣ እንዲህ
ተደርጎ ሲደረደርና ሲዘመርበት ትልቅ የተመስጦን ሁኔታ ይፈጥራል።

•••

በዚህም ተመስጦ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ፣ ሰውን የሚያስተምሩ እና የሚመክሩ፣
የተፈጥሮን ጥልቅ ምስጢር እየመረመሩ፣ ምስጋናን ለፈጣሪ የሚያቀርቡ ድንቅ ዝማሪዎችን እና ቅኔዎችን እንደተቀኘ
ከመዝሙሩ የምንረዳ ሲሆን አባቶቻችንም ብዙ እንዳተረፉበት እና በተመስጦ እንደተቀኙበት ዘመናትን ከዘለቁ
የመዝሙር ግጥሞቻቸው ማስተዋል እንችላለን።

🔰ታቦተ ሕጉን በዝማሬ ለማክበር

👉በገና የእግዚአብሔርን የቃልኪዳን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ ገብታ በድንኳን በኖረችበት ጊዜ (፩ኛ ዜና.
፲፭፡፳፰)

👉የእግዚአብሔርን ታቦት ከዳዊት ከተማ ንጉሥ ሰሎሞን ወደ አሰራው ቤተመቅደስ በምትገባበት ጊዜ ዕብራውያን
በደስታ ሆ እያሉ ቀንደ መለከት እና እምቢልታን እየነፉ ጸናጽልና መሰንቆም በገናንም እየመቱ የእግዚአብሔርን
የቃልኪዳን ታቦት እንዳመጡ እና እንዳመሰገኑ መጽሐፍት ያስረዳሉ፡፡

🔰በጠላት ላይ ድል ለማግኘት

👉እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ ድል በሰጣቸው ጊዜ... ( ፪ኛ ዜና. ፳፯-፳፰ )

👉ያዕቆብ ከላባ በኮበለለ ጊዜ ላባ ለያዕቆብ ሲናገረው... (ዘፍ. ፴፩፡፳፯ )

ከላይ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በገና እንደ ሌሎች የቤተ መቅደስ የዜማ ዕቃዎች አገልግሎት ይሰጥ
እንደ ነበረ ተገልጧል፡፡

@betenzira

🔰 ከኀዘን ለመጽናናት

👉በገና በተለያየ ምክንያት ከሚደርስ ኀዘን ለመጽናናት ወይንም ለማጽናናት አገልግሎት ላይ ይውላል። ይህም
በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ ከተጠቀሰበት የዩባል ልጆች ዓላማ ጋር የሚገናኝ ነው። የዩባል ልጆች ዓላማ በዘራቸው
ከሆነው የእርስ በርስ መገዳደል ታሪክ ኀዘን መጽናናት ነው።

✅በዚህም በገና ቃለ ማኅዘኒ ተብሏል።

•••
⚜ይሄው ፈለግ በመዝሙረ ዳዊት እንደምንረዳው በአሳዛኝ ወቅቶች ሁሉ የበገና አገልግሎት የማይቋረጥ መሆኑን
ነው።በኢትዮጵያውያን ዘንድም እንዲሁ በተለይ በጾምና በጸሎት፣ በጽሞና፣ በንስሐ እና ሰዎች በሞት በሚለዩበትም ጊዜ
በገና ለመጽናናት አገልግሎት ሲውል ይታያል።

🔰ትንቢት ለመናገር

👉ቅዱስ ዳዊት የተናገራቸው ቃለ ትንቢቶች በሙሉ በበገና እየደረደረ ነው፡፡

📖"ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስሱ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው
መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል"

🔰ከመናፍስት ሥቃይ ለመዳን

📖"እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፡፡ ክፉ
መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር" (፩ኛሳሙ.፲፮፡፳፫) እንዲል፡፡

🔰የሀገር ሉዓላዊነትን ለመግለጽ

👉በገና የሃገር ሉዓላዊነት የሚያወሱ መዝሙሮችን ለመዘመር ይረዳል። "ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ"... የሚለው መዝሙር
ለዚህ አገልግሎቱ ተጠቃሽ መዝሙር ነው።

🔰ነፍስን ያለ ጣር ከሥጋ ለመለየት

👉በገና ጻረ ሞት ወይም ስቃይ ሳይኖር ነፍስን ከስጋ የመለየት ሃብት እንዳለው ሐምሌ የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር
ያስረዳል።

•••

ስለ አባ ኪሮስ የተጻፈና ምእመናን ስለ እመቤታችን መዝሙር በሚዘምሩበት ወቅት እግዚአብሔር እልፍ አእላፍ
መላእክት፣ነቢያትን ሐዋርያትን እንጦንስና መቃርስን ይዞ እንደ ወረደ ያን ጊዜም ቅዱስ ዳዊት በአካለ ነፍስ አብሮ
እንደተገኘ ያስረዳሉ።

•••
ቅዱስ ዳዊት ጻድቁ አባታችን “በማንኛው አውታር፣ በማንኛው ዜማ፣ በማንኛውስ ወገን በመጀመሪያው ነውን? በሁለተኛ
ነውን? ወይስ በሶስተኛ ልዘምርልህ?” ባላቸው ጊዜ “የዐሥሩን አውታር በየወገናቸው ዜማቸውን ልሰማ እወዳለሁ”
አሉት፡፡ ያን ጊዜም ዳዊት በገናውን አዘጋጅቶ እየደረደረ “ፈጽመን ደስ እንሰኝባት ዘንድ አግዚአብሔር የሠራት ቀን ናት
እግዚአብሔርን በመፍራት በሕጉ የሚኖሩ ብጹዓን ናቸው” እያለ ዘመረ፡፡ ዳግመኛም “ጎረመስኩ ነገር ግን የሚጣል
ጻድቅ አላየሁም” ብሎ ሲጮህ የአባ ኪሮስ ነፍስ ከሥጋ ተለየች ይላል። ዳግመኛ የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ
የከበረ ነው እያለ በልብሱ ዘርፍ እንኳ አውታር እየመታ ይደረድር ነበረ፡፡"(ገድለ አቡነ ኪሮስ)

•••

በተመሳሳይ ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በበገና ጣዕመ ዝማሬ ነፍሷ ከሥጋዋ በሚለይበት ወቅት
ጻእረ ሞት ወይም ያያት ስቃይ ሳይኖራት በበገና ጣዕመ ዝማሬ አማካኝነት ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየ”።

"ዳዊት በበገና ዕዝራ በመሰንቆ እያጫወቷት፣

ሳታውቀው አለፈች ያን መልአከ ሞት።"

የሚለው በክብረ በዓል የሚዘመረው መዝሙር እውነታውን ያስረዳናል። ከዚህ በተጨማሪም፣ በብዙዎቹ ቅዱሳን
እረፍት ጊዜ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ለመቀበል ሲመጣ ቅዱስ ዳዊትም እንደሚገኝ በርካታ ገድላት እና ድርሳናት
ይናገራሉ።

@betenzira

🟢#የበገና_ማህበራዊ_አገልግሎት

👉በገና እንደ ንግሥ፣በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጋብቻ ፣ ድል በማድረግ ጊዜ ባሉ የደስታ ጊዜያትም እግዚአብሔር
ይመሰገንበታል። በበጎ ሥራቸው ለሃይማኖትና ለሀገር ውለታ ለዋሉ፣ እንዲሁም ታላላቅ እና ልዩ የሆኑ ሀገራዊ ክስተቶች
፣የቤተ-ክርስቲያን ታሪክን የበገና ደርዳሪዎች በበገናቸው መወድስ በማቅረብ ያነሷቸዋል።

•••

እንዲሁ በኃዘን ጊዜ፣ ሰው ሲሞት ፣ቁጣና መቅሰፍት ሲደርስ እና የመሳሰሉት አሳዛኝ ክስተቶች ሲገጥሙም በገና
ተማጽኖ እና ማጽናኛ ይቀርብበታል።

•••

ዛሬም ቢሆን በገና በክርስቲያኖች ዘንድ በደስታ ጊዜ፣ በሠርግም ይሁን እንዲሁ ሰው በሚሞትባቸው በሐዘን ወቅት
ለአገልግሎት በመዋል ላይ ይገኛል።
•••

🔰አሁን አሁን በአንዳንድ አጋጣሚዎች በገና ከቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውጪ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ምክንያቶች
ሲደረደር ይታያል።ይሁን እንጂ ይህን ዓይነቱ ሁኔታ የሚቃወሙ አባቶች አሉ።ምክንያታቸው ደግሞ በገና የተለየ
እንደመሆኑ ለድርደራው የተለየ ቦታ እና ክብር ሊኖረው ይገባል በማለት ነው።

•••

ለበገና የታሪክ ምንጭ የሆኑት መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ ድርሳናት እና ትውፊት እንደሚነግሩን በገና በማንኛውም ቦታ
ዝም ተብሎ የሚደረደር አለመሆኑን ነው።ከቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳት አንዱ እንደመሆኑ ክብሩም እንዲሁ
የተጠበቀ ነው።

•••

በታላላቅ የአደባባይ በዓላት፣ እንደ ጥምቀት፣ መስቀል፣ እና የንግሥ በዓላት በታቦቱ ፊት በጉዞ ወቅት በገና
ይደረደራል፣እግዚአብሔር ይመሰገንበታል።

@betenzira

🔰በገና መቼ ነው የሚደረደረው❓

⚜አሁን አሁን በምእመናን ዘንድ የበገና መዝሙር መስማት የሚዘወተረው በአጽዋማት ወቅት በተለይም በዐቢይ ጾም
ጊዜ ቢሆንም፤ ከዚህ ወቅት ጋር ብቻ የሚገድበው ነገር ኖሮ አይደለም።

•••

ታሪኩን የሚያውቁ ሲናገሩም እንዲህ ያለው ሁኔታ የመጣው በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ፣ቤተ
ክርስቲያን በነበራት የሬድዮ መርሐ ግብር፤በዐቢይ ጾም ወቅት ይተላለፍ የነበረው መዝሙር የበገና ስለነበረ ሕዝቡ
ከዚህ በመነሳት በዚህ ጾም ወቅት የበገና መዝሙር መስማትን ባሕል እያደረገው እንደ መጣ ይታመናል።

•••

ይሁን እንጂ በገና በቀደምት ኢትዮጵያውያን ዘንድም ሆነ፤ በዕብራውያን ዘንድ፤ በማናቸውም ጊዜ ዓመቱን ሙሉ
አገልግሎት ላይ የሚውል የዜማ መሳሪያ ነው።

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

ቤተ-ዕንዚራ:

🔰ቀንበር (ጋድም)

👉ቀንበር ከበገና ከላይኛው ክፍል የሚገኝ አግዳሚ ሲሆን ቀጥ ያለ ወይም የቀንደ መለከት ቅርጽ ሊኖረው ይችላል። አውታሩ
የሚወጠርበት እና መቃኛው የሚያርፍበት ክፍል ነው። የሚሠራውም ከደረቅ እንጨት ተጠርቦ እና ለዝቦ እንዲሁም በልዩ ጥበብ
ተውቦ ነው።

•••

➟ምስጢሩ፦

👉ቀንበር የአኀዜ ኵሉ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው።

👉ቀንበር ከበገናው በላይ መገኘቱም፦ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ ያለ ሁሉን የፈጠረ፣ሁሉን የሚያስተዳድር
ጌታ፣የሁሉ የበላይ መሆኑን ያጠይቃል።

✓አንድም የሥልጣነ የእግዚአብሔር ምሳሌ

✓አንድም የእግዚአብሔርን ልዕልና ያመለክታል።

@betenzira

🔰መቃኛ

👉ከቀጫጭን ጠንካራ እንጨቶች የሚሠራ ሲሆን አውታሩን ቀንበሩ ላይ አሥሮ ይይዛል። አስተሳሰሩም የራሱ ብልሃት ያለው
ነው።ለመቃኘት አውታሮቹን ለማጥበቅና ለማላላት እንዲረዳ ተደርጎ ይታሠራል።

•••

➟ምስጢሩ፦
መቃኛ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል፡፡ ሕግጋትን በመስጠት የምዕመናን ሕይወት የሚጠብቅ እርሱ ነውና፡፡ አንድም ዐሥሩ ትዕዛዛት
መንፈሳውያን የሚያደርጉ የመንፈስንም ፍሬ የሚሰጡ በመሆናቸው ነው።
👉አንድም፡ ምድራዊ ሕይወታቸውን በቅድስና፣ በሰማዕትነት፣አሸንፈው ወይም ይህን ዓለም ድል ነስተው ወደ አሸናፊዋ ሰማያዊቷ
ቤተ-ክርስቲያን አካል በተቀላቀሉ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰማዕታት ይመሰላል፡፡

👉አንድም፦የመላእክት ምሳሌ ነው።

@betenzira

🔰ጌጥ (መስቀል፣ቀርነ በግዕ)

👉መስቀል፦ እግዚአብሔር ስለ ሰው ልጆች ፍጹም ፍቅሩን የገለጠበት ነው።

👉ቀርነ በግዕ፦የበግ ቀንድ ማለት ነው።በብሉይ ኪዳን የተለያዩ ንዋያተ ቅድሳት ከቀንድ ይሠሩ ነበር ለምሳሌ

⚜ቀርነ ቅብዕ/የዘይት መያዣ(፩ኛ ሳሙ.፲፮፥፩)

⚜ቀንደ መለከት(ኢያ.፮፥፭)

📖በመጽሐፍ ቅዱስ ቀንድ ኃይልን፣ ሥልጣንን፣ ክብርን፣ ንግሥናን ያመለክታል።

🐏🐏🐏#በግዕ(በግ)🐏🐏🐏

👉በግ በየዋህነቱ የሚጠቀስ የቤት እንስሳ ሲሆን በብሉይ ኪዳን ለመሥዋዕት ከሚሆኑ እንስሳት ዋነኛውና በተለይም በፋሲካ
የሚሠዋ እንስሳ ነው።

👉በቅዱሳት መጻሕፍት በግ የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ተጠቅሷል።

👉ምእመናንም በበጎች ተመስለዋል።

📮በግ በመጽሐፍ ቅዱስ📮

📖እስራኤል ከግብጽ በወጡበት ቀን የሠዉት የፋሲካው በግ። (ዘጸ.፲፪፥፫-ፍጻሜ) ይህ በግ የክርስቶስ ምሳሌ እንደሆነ ንዋይ ኅሩይ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ ፩ኛ ቆሮ.፭፥፯-፰ ላይ "...እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ
አስወግዱ።ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤ ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ
እርሾም አይደለም።" ብሎ ገልጦ አብራርቶታል።
•••

📖በይስሐቅ ፋንታ የተሠዋው "እግዚአብሔር ያዘጋጀው በግ" ። አብርሃም ልጅህን ሠዋልኝ ብሎ እግዚአብሔር የጠየቀውን ጥያቄ
ለመፈጸም ልጁንና ለመሥዋዕት የሚሆነውን እንጨት ይዞ ከልጁ ከይስሐቅ ጋር እግዚአብሔር ወደ አዘዘው ስፍራ ለመሄድ
ተነሳ፤አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ሁለቱም
አብረው ሄዱ። ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው። አባቴ ሆይ? አለ እርሱም እነሆኝ ልጄ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው
አለ፤ የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት ነው?" አለው።(ዘፍ ፳፪፥፮-፯) አብርሃምም ልጄ ሆይ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል
አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ።"(ዘፍ.፳፪፥፰)

•••
እንዳለውም እግዚአብሔር በግን አዘጋጀ። ይህ በግ የአማናዊው በግ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ይህንንም የሐዲስ ኪዳኑ ነቢይ
የብሉዩ ሐዋርያ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ብላቴናው ይስሐቅ ከሺህ ዓመታት በፊት "የመሥዋዕቱ በግ ወዴት ነው?" ብሎ
የጠየቀውን ጥያቄ በሐዲስ ኪዳን "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ወያሴስል ኃጢአት ዓለም። "እነሆ የዓለምን ኃጢአት
የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።"ብሎ መልሶለታል።(ዮሐ.፩፥፳፱፣፩፥፴፮)ስለዚህ በግ የክርስቶስ
ምሳሌ ነው።

🐏🐏🐏#ቀርን(ቀንድ)🐏🐏🐏

👉የኃይለ እግዚአብሔር፣ የሥልጣነ እግዚአብሔር፣ የመስቀል ምሳሌ ነው።ቀንድ ያለው ማንኛውም ፍጥረት በእርሱ ላይ ነጣቂ
ጠላት በመጣበት ጊዜ በጠላቱ ላይ በቀንዱ እንዲበረታታበትና ራሱንና መንጋዎቹን ሁሉ ከመነጠቅ እንዲታደግና እንዲያድን እንዲሁ
በአምሳሉ የተፈጠረው የሰው ልጅ በነጣቂው ጠላት ዲያብሎስ የተንኮል ወጥመድ ውስጥ ገብቶ ከአባቱና ከጠባቂው እንዲሁም
ከመንጋው ተለይቶ ሊነጠቅ ባለ ጊዜ ልዑል አምላክ የሆነ እርሱ አርዓያውን ነሥቶ ፍጹም ሰውን ሆኖ በጠላቱ ላይ በቀንዱ
እንዲበረታታ በአምላክነቱ ኃይልና ሥልጣን አዳምን ጠልፎ በጣለው ኃጢአትና ሞት፣ በሞት ጌታዋም በዲያብሎስ ላይ
ተበረታታባቸውና አርዓያውን ይዞ በዲያብሎስ ግዛት ስር የነበረውን በግ አዳምን እረኛም በግም ሆኖ አዳነው።

•••
ይህንን ሲያስተውል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት በትንቢት መነጽር ዓይቶ ታላቅ ምሥጢር ተናገረ እንዲህ
ሲል "...እስመ ኃረያ እግዚአብሔር ለጽዮን...ወበህየ አበቊል ቀርነ ለዳዊት ወአስተዴሉ ማኅቶተ ለመሲሕየ ወአለብሶሙ ኃፍረተ
ለጸላእቱ ወቦቱ ይፈሪ ቅድሳትየ።" ትርጉሙም "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥
እንዲህ ብሎ "ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ፤ አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም
እንጀራ አጠግባለሁ፤ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል፤በዚያ ለዳዊት ቀንድን
አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ። ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ
ያብባል።"(መዝ.፻፴፩፥፩-ፍጻሜ)

•••

ትርጉሙም፦ "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ። ይህች ለዘላለም
ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ፤ አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ፤
ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።" ያለው ስለ እመቤታችን ሲሆን
•••

"በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ። ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን
ቅድስናዬ ያብባል" ያለው ደግሞ ስለ ጌታ፣ ስላለው ኃይልና ሥልጣን እንደሆነ ግልጽ ነው።

•••

📖ቀንድ ኃይልና ሥልጣንን እንደሚያመለክት የሚያስረዱ ሌሎች በርካታ ጥቅሶችም አሉ።

(፩ኛ ነገ.፳፪፥፲፩፣ሉቃ.፩፥፷፱፣፩ኛ.ሳሙ. ፪፥፩፣፪፥፲፣ ሕዝ.፳፱፥፳፩)

👉አንድም ቀርነ በግዕ የመስቀል ምሳሌ ነው። ከላይ እንደገለጽነው ቀንድ አንድም በጠላት ላይ መበረታቻ አንድም ለጠላት ድል
የማድረጊያ ትእምርት/ምልክት ነው።

•••

መስቀል የጌታ(የበጉ) ቀንድ ይባላል። በግ ቀንዱን ለመውጋት አይጠቀምበትም(ጠላትን አይወጋበትም) እንዲሁ ለትእምርት
የተቀመጠ ነው እንጂ። እንዲህ ስንል እንዳይጸንብን "ምሳሌ ዘየሐጽጽን ልብ እንበል። በግ ነጣቂ ተኩላ በመጣበት ጊዜ ከዚያ ቦታ
ይሸሻል እንጂ ዞሮ ጠላቱን እንደማይወጋ እንዲሁ ጠላት ዲያብሎስ በልበ አይሁድ አድሮ በግዕ በተባለ ጌታ ላይ ነገር በሠራበት
መከራ ባጸናበት ጊዜ ቀንድ በተባለ መስቀሉ ሊወጋውና ሊጥለው እየተቻለው "አምላኪየ አምላኪየ ነጽረኒ ወለምንት ኃደገኒ፣
ጸማህኩ፣ ኦ አባ ኅድግ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ" እያለ በመሸሽ አምሳል ይለምንላቸው ራሱ ዲያብሎስንም ያታልለው
ነበር እንጂ ቀጥቅጦ ያለፈቃዱ በኃይል አልገዛውም።

•••
ነገር ግን ጠላት የበጉን ቀንድ እያየ ቀንድ አለውና ይወጋኛል ብሎ እየፈራ በበጉ ላይ እንዳይበረታታበት እንዲሁ ዲያብሎስም
የመስቀሉን ኃይልና ትእምርትነት አንድም አምላክነቱን ከሩቅ እያየ ፈራ ተባ እያለ ክብር ይግባውና ዕሩቅ ብእሲ መስሎት "ሔጄ
የዚህን ሰው እንደ አባቶቹ ሥጋውን ወደ መቃብር ነፍሱን ወደ ሲዖል ላውርድ ይሆንን?" እያለ ይፈራ ይጨነቅ እንደነበርና
በመጨረሻም "አምላኬ አምላኬ፣ ተጠማሁ ሲል ቢሰማው 'ይህስ ዕሩቅ ብእሲ ነው' ብሎ እንዳለው ሊያደርግ ሲጠጋ በመለኮታዊ
ኃይሉ በእሳት ዛንዠር በነፋስ አውታር አሥሮ ሲዖልን እንደበዘበዛት ትምህርተ ኅቡዓት የተባለ የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ
በግልጽ ያስረዳል። (ትር. ትም. ኅቡ)

•••
አንድም በጎች የምንባል እኛ ምእመናን ቀንዱ መስቀል ነው ሐተታ እንደቀደመው ነው። እኛ ምእመናን በቀንድ መስቀል
ትእምርትነት ዲያብሎስን ድል እያደረግነው እንኖራለንና ነው። ለዚህም ነው መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት "ወወሀብኮሙ ትእምርተ
ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምሥጡ እም ገጸ ቅስት ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሀቸው
ወዳጆችህም እንዲድኑ" ብሎ የተቀኘው።(መዝ. ፶፱፥፬፤ ፺፬፥፮፤ ፺፱፥፫-፬፤ ማቴ. ፳፭፥፴፫ ፣ ሕዝ. ፴፮፥፴፰፣ ዮሐ. ፲፥፬፤ ፲፬፥፭)

@betenzira
•••
አንድም፦ በግ በቀንዱ ጠላቱን እንዲወጋበት ጌታም ሥጋውን በቆረሰበት ደሙን ባፈሰሰበት በቅዱስ መስቀሉ ሠይጣንን፣ ሞትና
መቃብርን ቀጥቅጦ ከኃይሉ በታች አድርጎታልና ቀንድ በመስቀል ይመሰላል። ቅዱስ ጳውሎስ " እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን
ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው
አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል
ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።" ብሎ ገልጦታል። (ኤፌ. ፪፥፲፬-፲፮)

•••

ዳግመኛም ጥልን በመስቀሉ ከገደለ በኋላ ሰላምና እርቅን ደግሞ ያደርግበታል። " እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥
በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።"
እንዲል። (ቆላ. ፩፥፲፱)

ልሣነ ዕፍረት ቅዱስ ጳውሎስ በድጋሜ "...ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ
መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት(ኃይል፣ ሥልጣን፣ ክብር፣ መውጊያ) ከእኔ ይራቅ።" ያለው።(ገላ. ፮፥፲፬)

🔰ማጠቃለያ

👉ቀርነ በግዕ፦የመስቀል አንድም የኃይለ እግዚአብሔር፣ የሥልጣነ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው። ኃይለ እግዚአብሔርም ሥልጣነ
እግዚአብሔርም የሚገለጠው/የተገለጠው በዙፋኑ በመስቀል ነውና በመስቀል ይጠቃለላል።

@betenzira

🔰ምሰሶ

👉በግራ በቀኝ የሚገኝ ቋሚ እንጨት ሲሆን፤ የሚሠራውም ልክ እንደ ቀንበሩ ከእንጨት ተጠርቦና ለዝቦ እንዲሁም በልዩ ጥበብ
ተውቦና አጊጦ ነው።

•••

➟ምስጢሩ፦

❇️የቀኝ ምሰሶ፦ የፍቅረ እግዚአብሔር ምሳሌ

👉አንድም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ

👉እንድም የመጋቤ ብሉይ የቅዱስ ሚካኤል ምሳሌ


❇️የግራ ምሰሶ፦ የፍቅረ ቢጽ (ሰው) ምሳሌ

👉አንድም የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ

👉አንድም የመጋቤ ሐዲስ የቅዱስ ገበርኤል ምሳሌ

❇️ሁለቱ ምሰሶዎች የግራ እና የቀኝ ምሰሶ በአንድ ቀንበር መያያዛቸው አንዳች ትምህርት የያዘ ነው። ይህም "ፍቅረ እግዚአብሔርን
እና ፍቅረ ቢጽን (ቀኝ ምሰሶ እና ግራ ምሰሶ) አንድ ላይ ብንጠቀልላቸው ፍቅር የሚልን ትርጉም ይሰጡናል፤ ፍቅር ደግሞ በበገናው
ቀንበር የተመሰለው አኀዜ ኵሉ እግዚአብሔር ነው።

@betenzira

🔰አውታር

👉ከበግ አንጀት ወይም ከበሬ ጅማት ታጥቦና ተልጎ፣ተገመዶ፣ተወጥሮ፣ከሮ፣በግኖና ደርቆ በቁጥር ተቀምሮ ይሠራል።

•••

➟ምስጢሩ፦

👉 አውታር የዐሥርቱ ትዕዛዛት ምሳሌ ነው፡፡እኒህም

📖ከኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ፣(ዘፀ ፳፡፫-፮

📖የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፣(ዘፀ ፳፡፯)

📖የሰንበትን ቀን አክብር፣(ዘፀ ፳፡፰-፲፩)

📖አባትህንና እናትህን አክብር፣(ዘፀ ፳፡፲፪)

📖አትግደል፣(ዘፀ ፳፡፲፫)

📖አታመንዝር፣(ዘፀ ፳፡፲፬)

📖አትስረቅ፣(ዘፀ ፳፡፲፭)

📖በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር፣(ዘፀ ፳፡፲፮)

📖የባልንጀራህን ገንዘብ አትመኝ፣(ዘፀ ፳፡፲፯)

📖ባልንጀራህን አንደ ራስህ ውደድ፣(ዘሌ፲፱፡፲፰)


•••

✓አንድም የበገና አውታሮች በጽላቱ ወይም በታቦቱ ላይ የሚጻፉ አልፋ፣ ወዖ፣ ቤጣ፣የውጣ የሚባሉት ኅቡዕ ቃላቶች ምሳሌ።

✓ትርጉማቸውም አልፋ ምስራቅ፤ ወዖ ምዕራብ፤ ቤጣ ሰሜን፤ የውጣ ደቡብ ማለት ነው።

👉በቁጥር እና በፊደል ለየብቻ ሲተነተኑ፡-

➡️፩አ፣ ፪ል፣ ፫ፋ፣ ፬ወ፣ ፭ዖ፣ ፮ቤ፣ ፯ጣ፣ ፰የ፣ ፱ው፣ ፲ጣ ይሆናሉ።

👉እንዲሁም በፊደላት ብቻ የበገናው አውታሮች ስም በመሆን ያገለግላል።

❇️(አ፣ ል፣ ፋ፣ ወ፣ ዖ፣ ቤ፣ ጣ፣ የ፣ ው፣ ጣ)

•••

✓አንድም የበገና አውታሮች በሦስቱ ዓይነት የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልቶች (ድምጸ ዜማ) ይመሰላሉ፡፡ እነዚህም ግዕዝ፣ አራራይ፣
ዕዝል ሲሆኑ የእያንዳንዷ የበገና አውታርን ይወክላሉ፡፡

👉በቁጥር እና በፊደል ሲተነተኑ፡-

➡️፩ግ፣ ፪ዕ፣ ፫ዝ፣ ፬አ፣ ፭ራ፣ ፮ራ፣ ፯ይ፣ ፰ዕ፣ ፱ዝ፣ ፲ል ይሆናል፡፡

👉በፊደላት ብቻ ያለ ቁጥር ሲጻፍ

❇️(ግ፣ ዕ፣ ዝ፣ አ፣ ራ፣ ራ፣ ይ፣ ዕ፣ ዝ፣ ል)

🛎ዕዝል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጹም ሰው ፍጹም አምላክ ሆኖ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም
ከተወለደ በኋላ በቅዱስ ያሬድ ጊዜ ነው የመጣው። ዕዝል ከላይ የስም ተራውን ሳይጠብቅ መንፈስ ቅዱስን አልፎ በወልድ
የተሰየመው ለዚህ ነው በማለት ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ትርጉማቸው፦

❇️ግዕዝ፦በአብ

❇️ዕዝል፦ በወልድ

❇️አራራይ፦በመንፈስ ቅዱስ፣

✓አንድም ለቅዱስ ያሬድ ድምጸ ዜማን ባቀበሉት ፫ቱ ዓይነት በራሪ ወፎች ይመሰላሉ

•••

✓አንድም የበገና አውታሮች በዐሥሩ የስሜት ሕዋሳት ይመሰላሉ፡፡


📖ግነዩ ለእግዚአብሔር በመሰንቆ ወበመዝሙር ዘዐሥርቱ አውታሪሁ።

📖"እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት" መዝ ፴፪/፴፫፡፪

⚜ወበመዝሙር ዘዐሥርቱ አውታሪሁ፡ትርጉሙም

❇️ዐሥር አውታር ያለውን በገና እየደረደራችሁ ተገዙ።ቆላ ፫፡፲፮

❇️አንድም ፡ ዐሥር ሕዋሳት ባለው ሰውነት ምግባር ይዛችሁ ተገዙ።

❇️አንድም ፡ ሕግጋቱ ዐሥር በሚሆኑ በአሪት ጸንታችሁ በማዓልትም በሌሊትም ተገዙ።

❇️አንድም ፡ ወበስብሐተ ሐዲስ ቃል ስጋ ሆነ እያላችሁ አመስግኑ።

⚜⚜⚜⚜የስሜት ሕዋሳት⚜⚜⚜⚜
ውጫዊ ሕዋሳት ውሳጣዊ ሕዋሳት

👀ዓይን ዓይነ ልቦና

👃አፍንጫ አንፈ ልቦና

🦻ጆሮ እዝነ ልቦና

👅ምላስ አፈ ልቦና

🖐መዳፍ እደ ልቦና

⚜ አንድም ዐሥሩ የስሜት ሕዋሳት

✓አፍንጫ

✓ጆሮ

✓ምላስ እና አንደበት

✓ብልት

✓ሁለት ዐይን

✓ሁለት እጅ

✓ሁለት እግር

...እነዚህን የስሜት ሕዋሳት ዐሥር በሚሆኑ በአሪት ሕግጋት አጽንታችሁ በማዓልትም በሌሊትም ተገዙ።
•••

✓አንድም የበገና አውታሮች በቅዱስ ዳዊት መዝሙረ አርዕስት ይመሰላሉ፡፡

👉ለቅዱስ ዳዊት ከተሰጠት ሀብቶች መሐከል ሀብተ ትንቢት ነው። ይህም ፻፶ውን መዝሙሮች አስተካክሎ ለጸሎት ለምስጋና
ማቅረቡ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ፻፶ውን መዝሙሮች በዐሥር አርዕስት ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ እነዚህም፡-

📖ተግሳጽ ለኩሎ

📖ትንቢት በእንተ ክርስቶስ

📖ትንቢት በእንተ ርዕሱ

📖ትንቢት በእንተ መነናዊያን

📖ትንቢት በእንተ ትሩፋት

📖ትንቢት በእንተ ሕዝቅያስ

📖ትንቢት በእንተ ኤርምያስ

📖ትንቢት በእንተ መቃብያን

📖ትንቢት በእንተ ዘለፋ ካህናት

📖ትንቢት በእንተ ሰሎሞን ወልዱ

•••

✓አንድም የበገና አውታሮች ዐሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት ምሳሌ ።

➣ዐሥር ቁጥር በዕብራውያን የፍጹምነት መገለጫ በመሆኑ ፍጹምነት ደረጃ መድረሳቸውን ለመግለጥ

➣አንድም ዐሥርቱን ሕግጋቱን በመፈጸም የሚገኝ በመሆኑ

➣አንድም በዐሥርቱ የስሜት ሕዋሳት ንጹህነት የሚገኙ በመሆኑ።

🛎ዐሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት በሶስት ክፍል ይመደባሉ።

✝ንጽሐ ሥጋ፦ በውስጡ ሶስት ማዕረጋት ይገኛሉ። ወጣንያን ናቸው ባለ ሰላሳ(፴) ፍሬ

✝ንጽሐ ነፍስ፦ በውስጡ አራት ማዕረጋት ይገኛሉ። ማዕከላዊያን ናቸው ባለ ስልሳ(፷) ፍሬ

✝ንጽሐ ልቦና፦ በውስጡ ሶስት ማዕረጋት ይገኛሉ። ፍጹማን ናቸው ባለ መቶ(፻) ፍሬ


⚜ንጽሐ ሥጋ(ወጣኒያን)⚜

🟢ጽማዌ፦ዝምታ ወይም አውቆ ፈቅዶ በመናገርና በመቀባጠር ከሚመጣው ኃጢአት መቆጠብ።

🟢ልባዌ፦ልብ ማድረግ።

🟢ጣዕመ ዝማሬ:- ሳይሰልቹና ሳይቸኩሉ ምሥጢርና ትርጓሜውን እያወጡ እያወረዱ በንቁ ሕሊና ማመስገንና መጸለይ።

⚜ንጽሐ ነፍስ(ማዕከላውያን)⚜

🟡አንብዕ:-ስለ ራስ ኃጢአት ማልቀስ፣ስለ ወገን ማንባት፣ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋትወ መከራ
እያሰቡ፣በእመቤታችን ላይ የደረሰውን አምስቱ ሀዘናትን እያሰቡ ማዘን።

🟡ሑሰት:-ባሉበት ስፍራ ሆነው ሌላ ቦታ የሚደረገውን ነገር ማወቅ።

🟡ኩነኔ:-ሥጋን ለነፍስ ማስገዛት።

🟡ፍቅር:-ሰውን ሁሉ በአንድ ዐይን መመልከት።

⚜ንጽሐ ልቦና(ፍጹማን)⚜

🔴ንጻሬ መላእክት:-ቅዱሳን መላእክትን በዐይነ ሥጋ መመልከት

🔴ተሰጥሞ ብርሃን:-እግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ በሆነው በሚያስደንቀው ብርሃን ውስጥ መዋኘት።

🔴ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ(ከዊነ እሳት):- ሰውነት ለአጋንንት የሚያቃጥልና የማያስቀርብ መሆን።

•••

✓አንድም የበገና አውታሮች የዐሥርቱ ዓለመ መላእክት(ከተሞች)ምሳሌ።እነዚህም ከተሞች በሦስት ሰማያት ይገኛሉ።

☁️ኤረር (፩ኛ ሰማይ)

☁️ራማ (፪ኛ ሰማይ)

☁️ኢዮር (፫ኛ ሰማይ)

•••

✓አንድም፦በዐሥሩ የዜማ ምልክቶች


ይመሰላሉ።እኒህም
➣ድፋት፣ሂደት፣ቅናት፣ይዘት፣ቁርጥ፣ጭረት፣ ርክርክ፣ደረት፣ድርስ፣አንብር

@betenzira

📮የበገና አውታሮች ፲፪ ቢሆኑ (ለሚሉ መላምቶች)

✍ናቫል የሚባል የዜማ መሳሪያን እስራኤላውያን ቅዱስ ዳዊት የደረደረበት በገና ነው ብለው የሚያምኑት መሳሪያ ሲሆን ለቤተ
መቅደስ አገልግሎት እንደዋለም ያስራዳሉ ፤ ፲፪ አውታሮችም አሉት። ከዚህ ተነስተው በዘርፉ ያሉ የጥናት እና የምርምር
ባለሙያዎች በገና ባለ ፲፪ አውታር የሆነ የዜማ መሳሪያ ነው የሚል መላምት አስቀምጠዋል። ባሕረ ጥበባት ቅድስት ቤተ
ክርስቲያናችንም እንዲህ ለሚሉ መላምቶች ምሳሌ መስላ አስቀምጣልናለች ።

🔰የበገና አውታሮች ፲፪ ቢሆኑ‼️

👉በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ። እኒህን ቢቆጥሯቸው ፲፪ ይመጣሉ።

👉አንድም ፡-በቅድስት ድንግል ማርያም ይመሰላሉ።እኒህን ቢቆጥሯቸው ፲፪ ይመጣሉ።

👉አንድም ፡-የ፲፪ቱ ሊቃነ መላእክት ምሳሌ።

👉አንድም፦ የ፲፪ቱ ደቂቀ ያዕቆብ(ነገደ እሥራኤል) ምሳሌ።

👉አንድም፦የ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ምሳሌ።

@betenzira

🛎 የአውታር ትዕምርትነት ማጠቃለያ

🔰አውታር የዐሥርቱ ትዕዛዛት ምሳሌ ነው።

🔰አንድም በጽላቱ ወይም በታቦቱ ላይ የሚጻፉ አልፋ፣ ወዖ፣ ቤጣ፣የውጣ የሚባሉት ኅቡዕ ቃላቶች ምሳሌ።

🔰አንድም በሶስቱ ዓይነት የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልቶች (ድምጸ ዜማ) ይመሰላሉ፡፡

🔰አንድም በዐሥሩ የስሜት ሕዋሳት ይመሰላል፡፡

🔰አንድም የቅዱስ ዳዊት መዝሙረ አርዕስት ምሳሌ፡፡

🔰አንድም ዐሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት ምሳሌ።

🔰አንድም የዐሥርቱ ዓለመ መላእክት ምሳሌ።


🔰አንድም የዐሥሩ ያሬዳዊ የዜማ ምልክቶች ምሳሌ።

📮የበገና አውታሮች ፲፪ ቢሆኑ (ለሚሉ መላምቶች)

🔰በ"አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ" ይመሰላሉ።

🔰አንድም በ"ቅድስት ድንግል ማርያም" ይመሰላሉ።

🔰አንድም የ፲፪ቱ ሊቃነ መላእክት ምሳሌ

🔰አንድም በ፲፪ቱ ደቂቀ ያዕቆብ(ነገደ እሥራኤል) ምሳሌ

🔰አንድም የ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ምሳሌ

@betenzira

🔰የድምጽ ሳጥን (ገበቴ)

👉ከአንድ ወጥ እንጨት ተፈልፍሎ(ገበቴ) ወይም የጣውላ እንጨቶችን በማገጣጠም እና የደረቀ ቆዳ ተፍቆና ተዳምጦ በማልበስ
የሚሠራ ነው። የሚለብሰው ቆዳም አገልግሎት ድምፅን ማስተላለፍ ሲሆን፤የበገናው ድምፅ የሚወጣውም ከዚህ ሳጥን ነው።

•••

➟ምስጢሩ፦

👉የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ። ከድምጽ ሳጥኑ (ገበቴው) የበገናው ድምጽ እንደሚገኝ ከእመቤታችን አካላዊ
ቃል ወልድ ጌታችን መድኃኒታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገኘቱን ያጠይቃል።

@betenzira

🔰በርኩማ፦

👉ትንሽ ዱካ መሳይ ከእንጨት የሚሠራ ሲሆን፣ይህም ዐሥሩን እንዚራዎች ለማስቀመጥ ያገለግላል።በድምፅ ሳጥኑና በአውታሩ
መካከል በመግባት እንዚራና አውታሩ በርሱ ላይ ተቀናብረው የንዝረትን ድምፅ እንዲፈጥሩ ያገለግላል።ይህም ድምፅ ደግሞ ወደ
ገበቴው ገብቶ ጎልቶ እንዲሰማ ያደርጋል።

•••
➟ምስጢሩ፦

👉ነብዩ ሙሴ ዐሥርቱን ትዕዛዛት ከእግዚአብሔር የተቀበለበት የደብረሲና ተራራ ምሳሌ

@betenzira

🔰መወጠሪያ

👉ከእንጨት የሚሠራ ሲሆን ከታችኛው የበገና ክፍል የሚገኝ ሆኖ አውታሮቹን ከቀንበሩ ጋር ለመወጠር ይጠቅማል።

•••

➟ምስጢሩ፦

👉 መወጠርያ በሰዎች መኖርያ /ምድር/ ምሳሌ ነው፡፡

👉አንድም፦ መወጠሪያ በምድር ላይ ያሉ የአዳም ዘር (የሰው ልጆች) ምሳሌ ነው።

❇️ዐሥሩ አውታሮች ቀንበሩንና፣ መቃኛውን፣ መወጠሪያውን ማገናኘታቸው አንዳች ትምህርት ያለው ነው። ይህም "የሰው ልጆች
(መወጠሪያ) በትዕዛዛተ እግዚአብሔር (አውታር) መሰላልነት ከምድር መኖሪያቸው (መወጠሪያ) ተጋድሎዋቸውን ጨርሰው
(መቃኛ) ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባታቸው እና ከፈጣሪያቸው እግዚአብሔር (ቀንበር) ጋር ለዘለዓለም በደስታ የመኖራቸው
ምሳሌ ነው።

🔰የመወጠሪያ ጠፍር

👉ዐሥሩን አውታሮችን የያዘ ከእንጨት የተሠራውን አግዳሚ መወጠሪያ ከግራ እና ከቀኝ በመሆን ከበገናው የድምጽ ሳጥን ላይ
ወጥሮ የያዘ ከቆዳ የሚሠራ ጠፍር ነው።

❇️የብዙዎቹ የጥንት በገኖች መወጠሪያ ጠፍር የድምጽ ሳጥኑን(ገበቴውን) ከላይ ያለበሰውን ቆዳ በመብሳት ከውስጠኛው የድምጽ
ሳጥን ክፍል ላይ የሚታሰሩ(የሚመቱ) ሲሆን በአሁን ጊዜ ያሉት በገናዎች ደግሞ ይህንኑ ጠፍር ከድምጽ ሳጥኑ የውጪኛው ክፍል
ላይ በምስማር የሚመታ ተደርገው ይበጃሉ።

👉አንጋፋው የበገና ደርዳሪ መጋቤ ስብሐት አለሙ አጋ ስለ በገና አካል ክፍሎች በዘመሩት የበገና መዝሙራቸው ላይ ስለ መወጠሪያ
ጠፍር እንዲህ ብለዋል።

•••
አውታሩ ግና የያዘውን እንጨት፣
መስሎታል በድንግል መሰረተ ሕይወት።
የዚህን የመያዣውን ጠፍር፣
መስሎታል በኪሩቤል አምሳል።

•••

➟ምስጢሩ፦

👉የእግዚአብሔርን ዙፋን የተሸከሙት የኪሩቤል (ኪሩብ) ምሳሌ።

@betenzira

🔰እንዚራ

👉ከቁርጥራጭ ቆዳዎች የሚሠራ ሲሆን በገና በሚደረደርበት ጊዜ አውታሮቹ ድዝዝዝ.... እና ጥዝዝዝ.... የሚል የንዝረት ድምፅ
እንዲያወጡ የሚያደርግ ነው።ቦታውም በርኩማ ላይ ሲሆን ፤ አውታሮቹ በርኩማ ላይ አርፈው በሚያልፉበት በሚሸፍኑት ርቀት
አማካይ ላይ በአውታሩና በበርኩማው መካከል በመግባት ከፍና ዝቅ አድርጎ በማስተካከል ተፈላጊውን የንዝረት ድምፅ እንዲሰጡ
ያደርጋል።

•••

➟ምስጢሩ፦

👉እንዚራ ተጋድሎ ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ይመሰላል፡፡

👉እንዚራ በዐሥሩ አውታር ላይ እንዳሉ፤ ክርስቲያኖችም ዐሥሩ አውታር የተመሰሉባቸውን አጠቃላይ ትዕዛዛተ እግዚአብሔርን
መሪ በማድረግ፤ በዓለም ኑሯቸው መንፈሳዊ ሕይወትን ለማበልፀግ ይጋደላሉና ነው፡፡

@betenzira

🔰ድሕንጻ(መግረፊያ)

👉ከቀንድ ወይንም ከእንጨት የሚሰራ መግረፊያ ሆኖ በግራ ምሰሶ ላይ የሚታሰር ሲሆን አገልግሎቱም ዐሥሩን አውታሮች ከወዲያ
ወዲህ እያለ በመግረፍ ልዩ ድምፅ እንዲሠጡ የሚያደርግ ነው።

"በድኅንጻ መንፈስ ዝብጢ አውታረ መሰንቆሁ ለልብየ ወአስተንፍሲ ውስተ አፉየ ከመ እኩን እንዚራሁ ለበኵርኪ...."
እንዲል(መጽሐፈ ሰዓታት)
•••

➟ምስጢሩ፦

👉ድሕንጻ በክርስቶስ ይመሰላል፡፡ድኅንጻ ዐሥሩን አውታሮች እየተመላለሰ እንደሚገርፋቸው፤ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም
በብሉይ ኪዳን የሰጣቸውን ዐሥሩን ትዕዛዛት በሐዲስ ኪዳንም አጽንቷቸዋልና።

🔰የድሕንጻ ጠፍር

👉የበገናውን ድሕንጻ በአንደኛው ጫፍ በኩል አንጠልጥሎ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ ከግራ ምሰሶ ላይ ሸምቅቆ በመያዝ ድሕንጻውን
ከበገናው ጋር በአንድነት አስተሳስሮ የሚኖር ጠፍር ነው።

👉አንጋፋው የበገና ደርዳሪ መጋቤ ስብሐት አለሙ አጋ ስለ በገና አካል ክፍሎች በዘመሩት የበገና መዝሙራቸው ላይ ስለ ድሕንጻ
ጠፍር እንዲህ ብለዋል።

•••
ድሕንጻውም የዚህ የዐሥሩ አውታር፣
ቅዱስ ቅዱስ የሠማይ ጌታ የምድር።
የታሪኩ የድሕንጻው ጠፍር፣
መስሎታል በፊታቸው ወርቅ አምሳል።

•••

➟ምስጢሩ፦(የበገና አባቶችን እና ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን መጠየቅ ያሻዋል)

@betenzira

🔰ማፈኛ

👉ማፈኛ ፦የድምጽ ሳጥኑን (ገበቴውን) ያለበሰውን ቆዳ ዙሪያውን ወጥረው በመያዝ ከገበቴው ላይ ረግቶ እንዲቀመጥ እና
እንዳይረግብ ያደረገው ጥልፍልፍ ስፌት ነው።

➟ምስጢሩ፦

👉ምድርን ተሸክመው ባሉ ብሔሞት እና ሌዋታን የሚባሉ ግሩማን ዘንዶዎች ምሳሌ ነው።


❇️አንዳንድ መምህራን ደግሞ ማፈኛ ማለት መወጠሪያ ማለት ነው ይላሉ...(በእዚህ ሐሳብ ላይ አባቶችን መጠየቅ የበለጠ ጥናት
ማድረግ ያሻዋል።)

@betenzira

🔰ከድምጽ ሳጥኑ (ገበቴው) ጀርባ ላይ ያለው ቀዳዳ (የመስቀል ቅርጽ ምልክት)

🛎ታሪክ

👉የዚህን ቀዳዳ ታሪክ ሐተታ እንደሚከተለው በግጥም መልክ ቀርቧል።

•••
አሸናፊው ዳዊት የድሉን ነገር፣
ለንጉሡ ነግሮ ሲጨርስ በክብር፣
ዮናታንም ይህን ድል አይቶ ለድንቅ፣
ለንጉሡ ልጅ ነበረና ታላቅ፣
ከልቦናው የፍቅር ውኃ ቢፈልቅ፣
ከዳዊት ጋር ነፍሱ ታወረች በጥብቅ፣
እንዲህ ሆነው በደስታና በተድላ፣
ከዘመቻ ከተመለሱ በኋላ፣
ሴቶች ሁሉ መጥተው ከእስራኤል ከተማ፣
ተቀበሉት እየዘፈኑ በዜማ፣
እንዲህ አሉ የጸብ ምክንያት ሊሆኑ፣
ሳኦል ንጉሥ ሺ ገዳይ ነበር ሥልጣኑ፣
እልፍ ገዳይ ዳዊት ነው ብለው ዘፈኑ፣
ይህን ሰምቶ ሳኦል ተቆጣ ወዲያው፣
ዳዊትንም በምቀኝነት አየው፣
መንግሥት እንጂ ሌላ ምን ነገር ቀረው፣
ዛሬውኑ ዓሥር ሺ ለሱ ሰጥተው፣
ለኔ ደግሞ ሺ ብቻ ሰጡኝ ምነው፣
እንዲህ ብሎ እስከ ፍጻሜ ዘመን፣
ጠላት ሆነው አምላክ ያላለው ላይሆን፣
በመንግሥቱም ታመመ ሳኦል ንጉሥ፣
ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚሠቀየው መንፈስ፣
እንደ ቀድሞው ዳዊት ወደሱ ሔደና፣
መልካም ድምፅ ሲዘምርለት በገና፣
ቢመልሱልኝ ለበጎ ብድር ክፋት፣
ያለው መዝሙር አይደለምና ተረት፣
በእግዚአብሔር ፊት ለኃጢአትና ለበደል፣
ከሕንፃው ጋር አጣብቆ ወግቶ ለመግደል፣
ወረወረ ጦሩን በዳዊት ሳኦል፣
እሱም ዳነ በቅልጥፍናው ባሕል፣
በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን ፈራው፣
ልዑል አምላክ እንዳልተለየው ቢያየው።

•••

✍አለቃ ተገኝ ታምሩ (የአማርኛ ሐረግ በቅኔዎች ሕግ)

•••
በንጉሡም አድሮበት ነበር ቅናት፣
ብዙ ጊዜ እረጅም ዘመን ወራት፣
እንዲህ ሆኖ የያዘው በሽታ ሲነሣበት፣
ያስጠራዋል በገና እንዲጫወትለት ዳዊት፣
ስቡሕ ብሎ በገና ሲይዝ በፊት፣
ይሸሻሉ ከሳዖል ላይ ያሉት ቅስፈት፣
እየራቁ የወር ጐዳና መሬት።
እንዲህ ብሎ በልቡ አደረ ቅናት፣
ጦር አንስቶ እጁን ሲቃጣ አይቶት፣
ቅዱስ ሚካኤል በገናህን መክት ብሎት፣
መከተበት በገናይቱን በሳት።

•••

❇️ስለዚህ ይህ ከበገናው ጀርባ የሳኦል ጦር የበሳው ቀዳዳ ቅዱስ ዳዊትን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነግሮት ከተወረወረበት ጦር
በበገናው አማካኝነት መክቶ ስለመዳኑ ለማስታወሻ የተደረገ ምልክት ነው።

@betenzira
❇️ይህንን ታሪክ ለማጠየቅ ብዙዎቹ የጥንት የበገና ሠሪዎች ከበገናቸው ጀርባ ክብ ብስ በማድረግ በገናቸውን ይሠሩ ነበር።
ብዙዎቹ የቅርብ ጊዜ በገና ሠሪዎች ደግሞ ከጀርባ ያለውን ብስ የመስቀል ቅርጽ ወይንም የድምጽ ሳጥኑን ድፍን አድርገው
ያበጁታል።

•••

❇️አንዳንድ የበገና አባቶች፣የበገና ሠሪዎች እና መምህራን የድምፅ ሳጥን የእመቤታችን የቅድስት የድንግል ማርያም፣የማኅፀነ ድንግል
ይልቁንም የድንግልናዋ ምሳሌ በመሆኑ ፤የድምጽ ሳጥኑ ምንም ዓይነት ቀዳዳ እና ክፍተት ሊኖረው አይገባምና ከበገናው ጀርባ
ያለውን ቀዳዳ የተቀረጸ የመስቀል ምልክት ብቻ አድርገው ከውጭ በመለጠፍ(በመፈልፈል) የበገናቸውን ድምጽ ሳጥን ድፍን
አድርገው ይሠራሉ።

•••

❇️ሌሎች ደግሞ ከበገናው ድምጽ ሳጥን ጀርባ ያለውን ብስ ✞የመስቀል ቅርጽ✞ እንዲኖረው አድርገው ቀዳዳውን ያበጁታል።

👉ቀዳዳው የመስቀል ቅርጽ እንዲኖረው መደረጉ ቅዱስ ዳዊት በበገናው ምከታ ከሳዖል ጦር (ፍላፃ) እንደዳነ ፤ በሐዲስ ኪዳንም
በመስቀሉ ያመንን እኛ ክርስቲያኖች መስቀል ከድያብሎስ ፍላፃ የዳንበት፤ የምንድንበት ምልክታችን የመሆኑ ምሳሌ።

•••

👉 አባቶቻችን እንዳስተማሩን ይህንን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን መስቀል በዘወትር ጸሎታችን "… መስቀል ኃይልነ መስቀል
ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ፤ … መስቀል
ኃይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው፡፡ አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምንበታለን፡፡ ያመነውም እኛ በመስቀሉ
ኃይል እንድናለን፤ ድነናልም።" እያልን ለመስቀሉ ያለንን ክብር እንገልጻለንና፤ በክርስቶስ መስቀል ኃይል መዳናችንንም ስንመሰክር
እንኖራለንና ፣እንዲሁም በበገናችንም ዘወትር ስለ ነገረ መስቀሉ እንዘምራለና፣እንጸልያለንና ይሄን ለማጠየቅ ከበገናው ጀርባ ያለውን
ቀዳዳ የመስቀል ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጓል በማለት ያስረዳሉ።

(ከላይ በተነሱት ሁለት ሐሳቦች ላይ የበገና አባቶችን ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን መጠየቅና የበለጠ ጥናት ማድረግ ያሻዋል።)

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════
╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

👉@betenzira👈

👉@bete_enzira👈

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

👉@betenzira👈

👉@bete_enzira👈

ቤተ-ዕንዚራ:

📮የበገና ዓይነቶች በመጽሐፍ ቅዱስ📮

👉በገና በመጽሐፍ ቅዱስ ዓይነቱ እና ቅርጹ በውል ባይገለጽም ባለ ስምንት አውታር እና ባለ ዐሥር አውታር ያላቸው በገናዎች
እንደነበሩ ያስረዳናል።

🔰ባለ ስምንት አውታር በገና

📖ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ፲፭፥ቁ ፲፮-፳፩

፲፮.ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን


ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን አለቃዎች ተናገረ።

•••

፲፯.ሌዋውያኑም የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሣፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳን ልጅ
ኤታንን።
•••

፲፰.ከነርሱም ጋራ በኹለተኛው ተራ የኾኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ቤንን፥ ያዝኤልን፥


ሰሚራሞትን፥ይሒኤልን፥ዑኒን፥ኤልያብን፥በናያስን፥መዕሴያን፥መቲትያን፥ኤሊፍሌሁን፥ሚቅንያን፥ በረኛዎችንም ዖቤድኤዶምንና
ይዒኤልን አቆሙ።

•••

፲፱.መዘምራንም ኤማንና አሣፍ ኤታንም በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር።

•••

፳.ዘካርያስ፥ዓዝዔል፥ሰሚራሞት፥ይሒኤል፥ዑኒ፥ ኤልያብ፥መዕሴያ፥በናያስ በመሰንቆ ምስጢር ነገር ያዜሙ ነበር።

•••

🚩መቲትያ፥ኤልፍሌሁ፥ሚቅኒያ፥ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል፥ዓዛዝያ ስምንት አውታር ባለው በገና ይዘምሩ ነበር።

🔰ባለ ዐሥር አውታር በገና

📖መዝሙረ ዳዊት ፴፪፥፪

🚩እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ዐሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።

📖መዝሙረ ዳዊት ፻፵፫፥፱

🚩አቤቱ፥ዐዲስ ቅኔ እቀኝልኻለኹ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልኻለኹ።

📖መዝሙረ ዳዊት ፺፩፥ቁ ፩-፫

፩.እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ልዑል ሆይ፥ለስምኽም ዝማሬ ማቅረብ፤

፪.በማለዳ ምሕረትን፥በሌሊትም እውነትኽን ማውራት፤

🚩ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋራም በመሰንቆ።


🔰ባለ መቶ አምሳ አውታር በገና

❇️የመዝሙረ ዳዊት(መዝሙር ፻፶)አንድምታ ላይ ደግሞ ስለዚህ በገና እንዲህ ተገልጾ እናገኛለኝ።

📖ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በቅዱሳኑ

...ስለ ትሩፋን ተናግሮታል እግዚአብሔርን በቅዱሳኑ እላንት አመስግኑት።አንድም በወዳጆቹ አድሮ ያለ እግዚአብሔርን
አመስግኑት።አንድም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ የሚመሰገን እግዚአብሔርን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያላችሁ አመስግኑት።

📖ሰብሕዎ በጽንዐ ኃይሉ

...ጽኑዕ ኀያል እያላችሁ አመስግኑት

📖ሰብሕዎ በክሂሎቱ

...ከሃሊ እያላችሁ አመስግኑት

📖ሰብሕዎ በከመ በዝኀ ዕበዩ

...ዐብይ እግዚአብሔር እያላቸው አመስግኑት

📖ሰብሕዎ በቃለ ቀርን

...ነጋሪት እየመታችሁ አመስግኑት

📖ሰብሕዎ በመዝሙር ወበመሰንቆ

...መሰንቆውን እየመታችሁ አመስግኑት

📖ሰብሕዎ በከበሮ ወበትፍሥሕት

...ደስ እያላችሁ ቀንዳውን እየመታችሁ አመስግኑት

📖ሰብሕዎ በአውታር ወበእንዚራ

🚩አውታር ጥብልቃና ይባላል።መቶ አምሳ አውታር ያለው ነው። በዓፄ መልከ ሰገድ ጊዜ ወደ ሀገራችን መጥቶ ነበር። እንዚራ ተራ
በገና ነው። ያን እየመታችሁ አመስግኑት።
📖፭.ሰብሕዎ በጸናጽል ዘሠናይ ቃሉ

...ድምጹ ያማረ ናቁስ ይባላል።እንደ መረዋ ያለ ነው ከፈላሻ ቤት ይገኛል።ይህን እየመታችሁ አመስግኑት።

📖ሰብሕዎ በጸናጽል ወበይባቤ

...ተራ ጸናጽል እየመታችሁ በፍጹም ምስጋና አመስግኑት

📖ኵሉ ነፍስ ይሴብሖ ለእግዚአብሔር

...እላንት ብቻ አይደላችሁም ሥጋዊ ደማዊ ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግነዋል።ይሄን ቢቆጥሩት መቶ አምሳ ይሆናል የመቶ
አምሳው መዝሙር ምሳሌ።

👉(ስለዚህ መቶ አምሳ አውታር በገና የበገና አባቶችን ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን መጠየቅና የበለጠ ጥናት ማድረግ ያሻዋል።)

@betenzira

📮ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው በገና ትክክለኛው በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በገና ስለመሆኑ ማስረጃዋች

🔰ቅዱስ ዳዊት ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምራለሁ ባለው መሰረት አሁን ያለው በገና ዐሥር አውታር ያለው መሆኑ።

🔰ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምሥጢር ሀገሩ ስለሆነች በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ይመሰገንባቸው የነበሩት የዜማ ዕቃዎች እንደ
መሰንቆ፣ ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መለከት እና የመሳሰሉት ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉት ንዋየ ቅዱሳት ቅርጻቸው ሳይለወጥ
መኖራቸው።

🔰በገና በታቦተ ጽዮን ፊት አገልግሎት ይሰጥ ስለነበረ እና ታቦተ ጽዮንም በፈቃደ እግዚአብሔር በንጉሥ ሰሎሞን ልጅ (ምንሊክ)
ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በሀገራችን መኖሯ።

🔰በኢትዮጵያውያን ባሕል ለቤተ ክርስትያን እና ለቤተ መንግሥት ዕቃዎች ልዩ ክብር ስለሚሰጥ በገና በቤተ-ክርስትያንም በቤተ-
መንግሥትም አገልግሎት የሚሰጥ ስለሆነና ስለነበረ ቅርጽና ይዘቱን ሳይለቅ የመኖር ዕድል በማግኘቱ።

👉በእነዚህ ምክንያቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው በገና በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በገና ስለመሆኑ ማስረጃዎች ናቸው።
@betenzira

📮ተመራማሪዎች እና ጥንታዊ መዛግብት ስለ ቅዱስ ዳዊት በገና ምን ይላሉ❓

🔰ባለ ዐሥር አውታር

❇️ኪኖር፦ኪኖር እስራኤላውያን ቅዱስ ዳዊት የደረደረበት በገና ነው ብለው ያምናሉ።

🚩፲ አውታሮች አሉት። በ፲ቱ ትዕዛዛት ይመስሏቸዋል።

🚩ይህ መሣሪያ ብርኩማ ያለው ሲሆን እንዚራ ግን የለውም።

👉ይሁንና ኪኖር የኢትዮጵያ ክራርን የማያክል አነስተኛ የዜማ መሳርያ ነው።

🔰ባለ ዐሥራ ሁለት አውታር

❇️ናቫል፦ናቫል እስራኤላውያን ቅዱስ ዳዊት የደረደረበት በገና ነው ብለው ያምናሉ። ለቤተ መቅደስ አገልግሎት እንደዋለም
ያስራዳሉ።

🚩 ፲፪ አውታሮች አሉት።

🚩 ብርኩማና እንዚራ ያላቸው እንዲሁም የሌላቸው ማስረጃ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች አሉ።

👉በዚህ ዘመን እስራኤላውያን ኪኖርን ቢያመርቱም ናቫልን እያመረቱ ግን አይደለም።

🔰ባለ ሃያ ሁለት አውታር

❇️እስራኤላውያን ባለ ፳፪ አውታር በገናም አላቸው።

🚩በ ፳፪ቱ ሥነ ፍጥረትና ፳፪ቱ የእግዚአብሔር ስሞች ይመስሉታል።

👉ምርምሮች እንደሚገልጹት እስራኤላውያን ከግብጽ ምርኮ በኋላ በግብጽ ካዩት በገና መሰረትነት እንደሠሩትና እንደዘመሩበት
ይናገራሉ።ሌሎች ደግሞ ጥንቱንም እስራኤላውያን መሣሪያው ነበራቸው የሚሉም አሉ።
✍ርዕሰ ደብር ብርሃኑ አካል (ባንድ ወቅት ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ)

♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾♾

📮ተጨማሪ ጥናቶች📮

🔰በቀደምት እሥራኤላዊያን ዘንድ ኪኖር (‫ )ִּכּנֹור‬ተብሎ ይታወቅ የነበረ የዜማ መሣሪያ ነበር። በእሥራኤል የዜማ ታሪክ ውስጥም
ትልቅ ቦታ አለው።

•••

🔰ዞሃር(‫ )ֹזַה ר‬የተሰኘው ጥንታዊ የአይሁድ መጽሐፍ እንደሚነግረን ከሆነ፥ ከመኝታው በላይ ይቀመጥ የነበረው የዳዊት በገና
ከሰሜን የሚነፍስ ንፋስ በውስጡ ባለፈ ጊዜ ዜማን ያወጣ ነበር።

•••

🔰ይህንን የሚተረጉሙ ሊቃውንት፥ በገናን በሰው ልጅ ሰውነት ይመስሉታል - ከሰሜን የሚነፍስ ነፋስ በገናን በመንካት ዜማን
እንደሚያወጣ እንዲያደርገው ሁሉ፥ ቅዱስ መንፈስ የሰውን ልጅ ሰውነት ሲነካ ዜማን እንደሚያፈልቅ ይናገራሉ።

•••

👉የኢትዮጵያ ጥናት ሊቅ የነበሩት ኤድዋርድ ኡሌንዶርፍ 'ኢትዮጵያና መጽሐፍ ቅዱስ' በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ፥ በኢትዮጵያ
የሚገኘው በገና ከጥንቱ የእስራኤል በገና ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ እምብዛም እንዳልሆነ ጠቅሰው አልፈዋል።

@betenzira

🛎ማጠቃለያ

🔰ከላይ ለመዳሰስ የሞከርናቸው ሐሳቦች

🛎በመጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ዓይነት በገናዎች ተጠቅሰው በአገልግሎት ላይ ውለዋል። እኒህም ባለ ስምንት አውታር እና ባለ ዐሥር
አውታር በገናዎች ናቸው።
•••

🛎በመዝሙረ ዳዊት አንድምታ ላይ ደግሞ ጥብልቃና የሚባል ባለ መቶ አምሳ አውታር በገና እንዳለ እና ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ
ተገልጿል ።

•••

🛎በዘርፉ ያሉ የውጭ እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተመራማሪዎች አገኘናቸው ያሏቸው የምርምር ውጤቶች እና መላምቶች እንዲሁም
የታሪክ መዛግብትን መነሻ በማድረግ ቅዱስ ዳዊት የደረደረበት በገና እንደሆነ በምዕራባውያን ዘንድ የሚታመንባቸው እንደ

🚩ኪኖር(ባለ ዐሥር አውታር)፣

🚩ናቫል( ባለ ዐሥራ ሁለት አውታር)፣እንዲሁም

🚩ባለ ሃያ ሁለት አውታር የዜማ መሣሪያዎች


በእስራኤላውያን ዘንድ ይገኛሉ።

•••

🛎እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአስተምህሮ መሰረቷ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በዚህ ቅዱስ
መጽሐፍ ላይ በገነኛው ቅዱስ ዳዊት "እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ዐሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።" ብሎ
ባዘዘን መሰረት እንዲሁም "አቤቱ፥ዐዲስ ቅኔ እቀኝልኻለኹ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልኻለኹ።" ብሎ በዐሥር አውታር
በገና መዘመርን ባስተማረን መሰረት እኛም የመንፈስ ልጆቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብለን የምናምነውንና ፤አባቶች በትውፊት
ጠብቀው ያስረከቡንን ይህን ቅዱስ ባለ ዐሥር አውታር በገና ተረክበን ክብሩን፣ ሥርዓቱን እና ትውፊቱን ጠብቀን፤ እኛም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ዛሬም እያመሰገንን እንገኛለን፣ እንኖራለንም።

════◉❖◉═════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮

#ቤተ_ዕንዚራ

╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯
👉@betenzira👈

👉@bete_enzira👈

You might also like