Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 32

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት በኪችነር ሐመረኖህ


ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ፒተርስበርግ ኦንታሪኦ
የተዘጋጀ መሪ ሕገ ደንብ

በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗ ጠቅላላ ጉባዔ የጸደቀ ፡፡

.............. ቀን ......... ዓ.ም ..... (2022)

ያልጸደቀ

0 | Page
ማውጫ

የመሪ ሕገ ደንቡ ዓላማና አስፈላጊነት ------------------------------------------------------ ፪


ጠቅላላ ሕግ (bylaw ) ------------------------------------------------------------ ፪
ሕገ ደንብ (Bylaws) ----------------------------------------------------------------------- ፬
አንቀጽ ፩ ትርጓሜ -------------------------------------------------------------------- ፬
አንቀጽ ፪ መዋቅርና ተጠሪነት ----------------------------------------------------------- ፭
አንቀጽ ፫ የሰበካ ጉባኤ አባልነት ------------------------------------------------------- ፮
አንቀጽ ፬ ጠቅላላ ጉባዔ ---------------------------------------------------------------- ፲
አንቀጽ ፭ የሰበካ መንፈሳዊ የአስተዳደር ጉባዔ ---------------------------------------- ፲፩
አንቀጽ ፮ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አስመራጭ ኮሚቴ ---------------------፲፮
አንቀጽ ፯ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ተግባርና ኃላፊነት --------------- ፲፯
አንቀጽ ፰ ማኅተም --------------------------------------------------------------------- ፳፬
አንቀጽ ፱ ቃለ ጉባዔ --------------------------------------------------------------------- ፳፬
አንቀጽ ፲ መዝገብ ቤት -------------------------------------------------------------------፳፬
አንቀጽ ፲፩ ውል ---------------------------------------------------------------------------፳፭
አንቀጽ ፲፪ ብድር ----------------------------------------------------------------------፳፭
አንቀጽ ፲፫ ተቆጣጣሪ (ኦዲተር) -------------------------------------------------------፳፭
አንቀጽ ፲፬ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪዎችና ማስታወቂያዎች -------------------------------፳፮
አንቀጽ ፲፭ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ------------------------------------------------------፳፮
አንቀጽ ፲፮ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜና ስለማሻሻል -------------------------------------- ፳፯
አንቀጽ ፲፯ የማህበሩ መበተን ------------------------------------------------------- ፳፰

የመሪ ሕገ ደንቡ ዓላማና አስፈላጊነት

ይህ መሪ ሕገ ደንብ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት

1
ለኪችነር ሐመረኖህ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ፒተርስበርግ ኦንቴሪዮ በምትገኝ አጥቢያ እስከ አሁን ድረስ በሥራ
ላይ ያለውን የመተዳደሪያ ደንብ በዚህ መሪ ሕገ ደንብ ተሻሽሎ እንዲዘጋጅ ታስቦ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አበይት ዓላማ
መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ነው።

❖ ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ መንበረ ፓትርያርክ ያለውን መዋቅራዊ ግንኙነት ግልጽና ወጥነት ያለው
ለማድረግ፤

❖ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ ቀኖናና ሥርዓት


የተከተለና ከቃለ አዋዲው ጋር የተስማማ የመተዳደሪያ ደንብ እንዲኖራት ለማስቻል፤

❖ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በመንፈሳዊ አገልግሎት ያለውን ሂደት ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ፤

❖ የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ ወደ አንድነት መምጣት ።

❖ የቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ዘርፍ መብዛት እና የምመናን ቁጥር እየጨመረ መምጣት

❖ ኃ ቤተክርቲያን

___________________________________________________________________________________________________________________________________

2
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት
የኪችነር ሐመረኖህ ኪዳነምህረት
የኪችነር ሐመረ ኖህ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ መተዳደሪያ ህገ ደንብ (ByLAW)

1. ስያሜ፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት የኪችነር ሐመረኖህ
ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል።

2. የቤተ ክርስቲያኑ አገልግሎት የሚፈፀምበት አድራሻ

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church


Kitchener Hamerenoah Kidane Mihret
1677 Snyder's Rd E, Petersburg, ON
N0B 2HO
PO Box 158

3. የቤተ ክርስቲያኗ ተግባርና ዓላማዎች

ሀ. የእግዚአብሔርን ወንጌለ መንግስት መስበክና ትምህርቱንም ማስፋፋት

ለ. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት መሰረት በኪችነር ዋተርሎ እና አካባቢው
ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ ተተኪ ትወልድ ከሕፃንነት ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስን፣ ግብረገብነትን፣ ሥርዓተ ቤተ
ክርስቲያንን፣ ታሪካቸውንና ባሕላቸውን እንዲያውቁ ማስተማርና በመልካም መንፈሳዊ ሥነ ምግባር ታንጸው ብቁ
ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ፤

ሐ. የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ፣ ቀኖና እና
ሥርዓት) ጥላ ስር በአንድነትና በፍቅር ተሰባስበው ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁና እምነታቸውን እንዲያስፋፉ
ማድረግ፤

መ. ምእመናኑን በወንጌል ትምህርት ማነፅና የሃይማኖታቸውን መሰረት በማሳወቅ ከሌሎች ጋር በአኩልነት፣


በመከባበር፣ በሰላም፣ በአንድነትና በፍቅር እንዲኖሩ ማስተማር፤

ሠ. ለአዳዲስ ስደተኞች ለመቋቋሚያ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና መርዳት፤

ረ. ለቤተ ክርስቲያኗ አባላትና እምነቱን ለተቀበሉ ክርስቲያኖች በሙሉ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ሕግና ሥርዓት
በተከተለ መንገድ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን (ክርስትና፣ ጥምቀት፣ ጋብቻ፣ ጸሎተ ፍታት) መፈጸም፤

ሰ. ለቤተ ክርስቲያኗ አባላት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይ መንፈሳዊ ምክር መስጠት፤

3
ሸ. ከላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ንብረትና ሀብት ማፍራት፣ መግዛት፣ መሸጥና
በሊዝ መያዝን ያጠቃልላል፡፡

አንቀጽ ፩. ትርጓሜ

፩.፩ ለቃሉ ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ

ሀ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት ፓትርያርኩን፤ ሊቃነ ጳጳሳትንና ጳጳሳት
የሚያደርጉት ቤተ ክርስቲያኗን በበላይነት የሚመራ ዓቢይ ጉባዔ ማለት ሲሆን፣ የመንበረ ሐዋርያትን መንበር የወረሰ፣
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራና መቀመጫውም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሆነ የቤተ ክርስቲያኗ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጭ
መንፈሳዊ ጉባኤ ማለት ነው።

ለ. ፓትርያርክ ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማለት ነው፡፡
ሐ. እናት ቤተክርስቲያን ማለት መቀመጫው አዲስ አበባ በሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በበላይነት የሚመራ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን (የኢ.ኦ.ተ.ቤ) ተለዋጭ መጠሪያ ስም ነው።

መ. የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለምስራቅ ካናዳ
አካባቢው ሀገረ ስብከት የተሾሙ ሊቀ ጳጳስ ማለት ነው።
ሠ. ደብር ወይም አጥቢያ ቤተርስቲያን ማለት በምስራቅ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት የኢ.ኦ.ተ.ቤ ህዝበ
ክርስቲያን በአንድነት በመደራጀት እምነቷን፣ ዶግማዋን፣ ቀኖናዋንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በመጠበቅ ለሃይማኖታዊ
አምልኮ የሚጠቀምበት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና የምዕመኑ ህብረት ማለት ነው።
ረ. የደብር አለቃ ወይም የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ማለት በሙያ ብቃቱ፣ በአስተዳደር ችሎታው፣

በክህነት አገልግሎቱና ሥነ ምግባሩ፟ በጠቅላላ ጉባዔ ተመርጦ በምስራቅ ካናዳ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ጸድቆ ፥ በቤተ
ክርስቲያኑ በበላይነት የሚያገለግል መንፈሳዊ አባት ማለት ነው።
ሸ. የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ማለት ለዚህ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ የሚያስፈልጉትን አባላት
ለመምረጥና ለመመረጥ የሚችሉ ካህናት፤ ምዕመናን/ትና የሰንበት ት/ቤት አባላትን ያካተተ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባዔ
ማለት ነው።

ቀ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ማለት የደብር አለቃውንና በቤተ ክርስቲያኗ አባላት ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ
አባላትን ያካተተ የሥራ አስፈጻሚ አካል ማለት ነው።

በ. የሰበካው ወይም የአጥቢያው አባል ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዓት ተቀብሎ
የተጠመቀ፣ ይህን መተዳደሪያ ደንብ ሙሉ ለሙሉ የተቀበለና ለደንቡ ተገዢ የሆነ እንዲሁም በባህረ መዝገብ ተመዝግቦ
የአባልነት መታወቂያ ካርድ ያለው ግለሰብ ማለት ነው።
4
ተ. ጠቅላላ ጉባኤ ማለት የቤተ ክርስቲያኗ ሁሉም አባላት የሚሳተፉበት ስብሰባ ማለት ነው።

ቸ. ኮሚቴ ማለት በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተመረጡ የሰበካ ጉባዔ አባላትን የያዘና
ተጠሪነቱም ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የሆነ አካል ማለት ነው።

ኀ. የማህበር ሕግ ማለት በኦንታሪኦ ክፍለ ሀገር በየጊዜው ሊለወጥ/ሊሻሻል የሚችል የተራድዖ/ለትርፍ ያልተቋቋሙ
ድርጅቶች የሚተዳደሩበት ሕግ ማለት ነው።

፩.፪. የቃላት ፍች

ሀ. በነጠላ ቁጥር የተገለጹት ቃላት ለብዙ ቁጥሮች፣ በተባዕታይ ጾታ የተገለጹት ቃላት ለአንስታይ ጾታና ለቤተ ክርስቲያን
እንዲሁም በተቃራኒው ያገለግላሉ። በአማርኛውና በእንግሊዝኛው ሕገ ደንቦች መካከል የትርጉም ወይም የአንቀጽ ቁጥር
መፋለስ ካጋጠመ የአማርኛው ሰነድ ተፈጻሚ ይሆናል።

አንቀጽ ፪. መዋቅርና ተጠሪነት

፪.፩. የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗ ተጠሪነት ለምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት ነው ።

፪.፪. ቤተ ክርስቲያኗ ከቅዱሰ ሲኖዶስ የሚወጣውን ሕግ፤ ደንብና መመሪያ፤ እንዲሁም የሰንሰለት ዕዝ ጠብቆ ከመንበረ
ፓትርያርክ፤ ከጠቅላይ ቤተ ክህነትና ከምስራቅ ካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደረጃ የሚተላለፈውን መንፈሳዊ
መመሪያ ተቀብላ ትፈጽማለች።

፪.፫. የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት የኢ.ኦ.ተ.አብያተ ክርስቲያናት የበላይ ኃላፊ ናቸው። በዚህም
መሠረት ሊቀ ጰጰሱ፡-

ሀ. ከአጥቢያው ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ እና ማህበረ ምዕመናን በሚቀርብ ጥያቄ መሰረት ለቤተ ክርስቲያኗ
የደብር አለቃ ሹመት ይጸድቃሉ።

ለ. በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት በየደረጃቸው የቤተ ክርስቲያን ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ የቅስናና የዲቁና ማዕረግ
ይሰጣሉ

ሐ. ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ እና ማህበረ ምዕመናን በሚቀርብ ጥያቄ መሰረት
አገልጋይ ካህን ይመድባሉ፤

5
መ. የደብር አለቃ ወይም አገልጋይ ካህን በአብዛኛው ማኅበረ ምዕመናን ዘንድ በተለያዩ ጉዳዮች ተቀባይነት ካላገኘ ከሀገረ
ስብከቱ ጽሕፈት ቤትና ከአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጋር በመምከር አስተዳደራዊ
መፍትሔ ይሰጣሉ፤

ሠ. በሃይማኖት ጉዳዮች በሙሉ የበላይ ኃላፊና ባለሥልጣን ናቸው፤ ሆኖም የቤተ ክርስቲያኗ ውስጣዊ አስተዳደር፣ ገንዘብና
ንብረት ጉዳይ በተመለከተ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ኃላፊነት ነው፤

ረ. በዓመታዊ በዓለ ንግስ ላይ በመገኘት ማኅበረ ምዕመናኑን ይባርካሉ፣ አጥቢያው የመጓጓዣና የመስተንግዶ ወጭዎችን
ይሸፍናል።

አንቀጽ ፫. የሰበካ ጉባኤ አባልነት

፫.፩ የሰበካ ጉባኤ አባልነት መስፈርት፡-

ሀ. ዕድሜው ፲፰ ዓመት የሞላውና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ተቀብሎ የተጠመቀና
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚያከብርና ጠብቆ የሚያስጠብቅ፤

ለ. የቤተ ክርስቲያኒቷን መተዳደሪያ ደንብ ተቀብሎ/ላ የተመዘገበ/ች እና በማንኛውም ሁኔታ አባልነቱን ያላቋረጠ፤ በአባልነት
ለመመዝገብ የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ጥያቄ አቅርቦ በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ ተቀባይነት እንዳገኘ
በአባል መዝገብ ውስጥ ይመዘገባል፤

ሐ. ከሌላ የኢ.ኦ.ተ.ቤ አባል ከሆኑ አብያተ ክርስቲያናት የመጣ ምዕመን ከነበረበት ሰበካ ቤተ ክርስቲያን በቂ ማስረጃ ካቀረበ
በቋሚ አባልነት የመመዝገብ መብት ይኖረዋል፤

መ. በደብሩ በመደበኛነት የሚያገለግሉ ካህናት የአባልነት ክፍያ ሳይከፍሉ የሰበካ ጉባኤ አባል መሆን ይችላሉ፣ መምረጥና
መመረጥ ይችላሉ።

፫.፪ የአባላት መብቶች

ሀ. ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትሰጣቸውን (የምትፈጽማቸውን) የቤተክርስቲያኗን ዶግማ ሕግና ስርዐት በተከተለ መንፈሳዊ


አገልግሎቶች የማግኘት፤

ለ. የቤተ ክርስቲያን የአባልነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሲጠይቅ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የማግኘት፤

ሐ. በጠቅላላ ጉባዔ ላይ በአካል ተገኝቶ ሀሳብ የመስጠት፣ የውሳኔ ሃሳብ ላይ የመሳተፍ፣ ድምጽ የመስጠት፤ የሰበካ መንፈሳዊ
አስተዳደር ጉባኤውን መምረጥና የመመረጥ መብቶች ይኖሩታል።

6
መ. አንድ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባል በሕገ ደንቡ የተደነገጉትን መብቶች (ከሚስጢራተ ቤተ ክርስቲያን
በስተቀር) የሚያገኘው በሕገ ደንቡ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች እና መስፈርቶች አሟልቶ ሲገኝ ብቻ ነዉ።

፫.፫ የሰበካ ጉባኤ አባል ግዴታ

ሀ. የዚህን መተዳደሪያ ደንብ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ የሚያከብርና የሚያስከበር መሆን አለበት፤

ለ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤና በቤተ ክርስቲያኗ ጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነውን የአባልነት መዋጮ በወቅቱ መክፈል
ይኖርበታል፤ አባሉ(ሏ) በተለያዩ ችግር ምክንያቶች (በሕመም፣ ሥራ በማጣት ወዘተ.) አስተዋጽኦ መክፈል ቢያቋርጥ
የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው ጉዳዩን ተመልክቶ ያለ ክፍያ በአባልነት እንዲቀጥል መወሰን ይችላል።

ሐ. በቤተ ክርስቲያኗ እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ ይጠበቅበታል፤

መ. አንድ የመንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባል ወይም የንዑሳን ኮሚቴ አባል ሥራውን መቀጠል በማይችልበት ሁኔታ ወይም
ከኃላፊነቱ ወይም ከአባልነቱ በሚነሣበት ጊዜ ወይም ሀገሩን ቢለቅ በእጁ የሚገኘውን ወይም በእሱ ኃላፊነት ሥር
ያለውን ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኗን ንብረትና ሰነድ ለቤተ ክርስቲያኗ ጽ/ቤት ማስረከብ አለበት፤

ሠ. ልጆችና ዘመዶች ለአቅመ አዳም ሲደርሱና ሥራ በሚኖራቸው ጊዜ ራሳቸውን ችለው አባል ሆነው እንዲመዘገቡና
ግዴታቸውን ያሟሉ ዘንድ ወላጆች ማበረታታት አለባቸው፤

ረ. ወላጆች ልጆቻቸው የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓትና ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው ያውቁ ዘንድ በሰንበት ት/ቤት እንዲሳተፉ
ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤

ሰ. እያንዳንዱ አባል ወይም ቤተሰብ የንስሐ አባት እንዲኖረዉ ያስፈልጋል፤

ሸ. የሰበካ ጉባኤ አባልነት ክፍያ መጠን በአንድ ሰውና በቤተሰብ ደረጃ ተለይቶ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ተጠንቶ
ከቀረበ በኋላ በጠቅላላ ጉባዔ ይወሰናል፤

ቀ. አሥራት በኩራት የሚያወጡ ምዕመናን የሰበካ ጉባኤ አባልነት ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለባቸው

፫.፬. አባልነትና የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

ሀ. የቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ አባል ያልሆነ ምዕመን በየትኛውም የቤተ ክርስቲያኗ የአገልግሎት

ክፍሎች ወይም ኮሚቴ ውስጥ ገብቶ ማገልገል አይችልም፣


7
ለ. የክህነት ማዕረግ ያላቸው አባቶች እና ወንድሞች በኑሮ ምክንያት ወደ አጥቢያው ሲመጡ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሥርዓት
መሰረት ወደ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ደጅ የሚጠኑበት ጊዜ በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ እና ማህበረ ካህናቱ
ወስነው ለሰበካ ጉባዔ ያሳውቃሉ።፡ ደጅ የሚጠኑበት ጊዜ ስለማንነታቸው አና ስለ ክህነት ማዕረጋቸው ትክክለኛነት
መረጃ የሚሰበሰብበት ጊዜ ነው።፡

፫.፭ ከአባልነት ስለመሰናበት

አንድ የሰባካ ጉባዔ አባል አባልነቱ የሚቆመው፡-

ሀ. ለቤተ ክርስቲያኗ ጽ/ቤት በጽሑፍ አባልነቱን ማቋረጡን ሲያሳውቅ፣

ለ. በሞት ሲለይ፣

ሐ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ልዩ ውሳኔ አንድ አባል ከአባልነት ሲሰናበት አባል መሆኑ ይቋረጣል። ሆኖም
ውሳኔው በአባላት ጠቅላላ ጉባዔ መጽደቅ ይኖርበታል። ከአባልነት ለመሰናበት ከሚከተሉት ምክንያቶች አንዱ ወይም
ከዚያ በላይ ሲፈጸሙ ነው።-

፩. ያለበቂ ምክንያት የአባልነት አስተዋጽዖውን ለአንድ ዓመት ሲያቋርጥ፤

፪. ከላይ በቁጥር ፫.፫ የተጠቀሱትን የአባልነት ግዴታዎች ሳያሟላ ሲቀር፤

፫. የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ፣ እምነትና ሥርዓት የሚያሰናክል አካሄድ ሲከተል፤

፬. በካህናት እና/ወይም አባላት መካከል አንድነትን ለማናጋት ብጥብጥን ሲፈጥርና መከፋፈል እንዲፈጠር ሲያደርግ፤

፭. የቤተ ክርስቲያኗ የአገልግሎት በአግባቡ እንዳይከናወን እክል ሲፈጥር፣

፮. ከተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ እምነትና ሥርዓት በተቃርኖ መሰለፍና ከዚህም አፍራሽ ተግባር በሥራ
አስፈጻሚው ተመክሮ አለመመለስ፤

፯. የቤተ ክርስቲያንና አባላቶቿን ክብር የሚነካና የሚያስነቅፍ ተግባር ላይ ተሳትፎ ሲገኝ፤ ናቸው።

ከዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውጭ የሚንቀሳቀሱ አባላት በሚያጋጥሙበት ጊዜ ሥራ አስፈጻሚው ከእነዚህ አባላት ጋር


ይወያያል፣ ይመክራል፣ በካህናት አባቶች እንዲመከሩ ያደርጋል። አልመለስ ያሉትን ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣ እንደ
ጉዳዩ ክብደትም ከኃላፊነታቸው ያነሳቸዋል። ከአባልነት ለመሰናበት የሚያስችል ጉድለት የተገኘባቸውን ለጠቅላላ
ጉባኤ አቅርቦ ያስወስናል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው በአባሉ ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት አባሉ በጠቅላላ ጉባኤው ፊት
ቀርቦ ጉዳዩን የማስረዳት ዕድል ይኖረዋል። አንድ አባል ከአባልነት መታገዱ በደብዳቤ ሊገለጽለት ይገባል፤
የታገደበት ምክንያቶችም በደብዳቤው መብራራት ይኖርበታል።

8
መ. አንድ ካህን ወይም ዲያቆን ከላይ በአንቀጽ ፫.፫ የተመለከቱትን ግዴታዎች ባይወጣና እና በአንቀጽ ፫.፭ ሐ ሥር
የተዘረዘሩትን ፈጽሞ ቢገኝ፡-

፩ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የመጀመሪያ የቃል ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። የዚህ ዝርዝር ውሳኔ ሪፖርት ወደ
ሊቀ ጳጳሱ ጽሕፈት ቤት መላክ ይኖርበታል፤

፪ ለሁለተኛ ጥፋት የሰበካ መንፈሳዊ አስተደደር ጉባኤ ከሊቀ ጳጳሱ ጋር በመማከር የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፤

፫ በሦስተኛ ተመሳሳይ ጥፋት ከአግልግሎት ይታገዳል። የመጨረሻው የሥነ ሥርዓት ውሣኔ ላይ የሚደረሰው የሰበካ
መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው ጉዳዩን በተመለከተ ለጠቅላላ ጉባዔው ካቀረበና ከጸደቀ በኋላ ነው። ሆኖም
የመጨረሻ ውሳኔ ሊፀና የሚችለው በሊቀ ጳጳሱ ታይቶ ሲጸድቅ ብቻ ይሆናል፡፡

ሠ. የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ከላይ በአንቀጽ ፫.፫ የተመለከቱትን ግዴታዎች ባይወጣና እና በአንቀጽ ፫.፭ ሐ ሥር
የተዘረዘሩትን ፈጽሞ ቢገኝ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው ጉዳዩን ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በዝርዝር ያቀርባል፣
ሊቀ ጳጳሱም በሀገረ ስብከቱ ውስጠ ደንብና በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሰረት አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ
ይወስዳሉ።

ረ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባል በአንቀጽ ፫.፫ የተመለከቱትን ግዴታዎች ባይወጣና እና በአንቀጽ ፫.፭ ሐ ሥር
የተዘረዘሩትን ፈጽሞ ቢገኝ ለመጀመሪያው ስሕተት መንፈሳዊ ምክርና ተግሳጽ ይሰጠዋል፤ ለሁለተኛው የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያና፣ በሦስተኛው ጥፋት ግን እስከ ሚቀጥለው ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ
ተለይቶ ይቆያል። የማሰናበቻው እርምጃ ውሣኔ የሚሰጠው በጠቅላላ ጉባዔ ሲሆን ግለሰቡ ጉዳዩን የማስረዳትና
የመከላከል መብት ይኖረዋል።

9
አንቀጽ ፬. ጠቅላላ ጉባዔ

፬.፩ የጠቅላላ ጉባዔ ስልጣን እና ተግባር

የደብሩ ጠቅላላ ጉባዔ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ የበላይ ውሳኔ ሰጭ አካል ነው፤ የሚከተሉት አበይት ስልጣንና ተግባር
ይኖሩታል፦

ሀ. የደብሩን ዓመታዊ ዕቅድና በጀት ያጸድቃል፤

ለ. ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ የሆኑ ፖሊሲዎች፣ ሕጎችና ደንቦችን ያጸድቃል፣ ይደነግጋል፣ እንደአስፈላጊነቱ ያሻሽላል፤

ሐ. በዚህ ሕገ ደንብ አንቀጽ ፭፣ ፮ እና ፲፭ በተደነገገው መሰረት ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው የሚቀርቡለት
ጉዳዮችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፤

መ. በአንድ ወር ውስጥ _ 5000.00 (አምስት ሽህ) የካናዳ ዶላር በላይ በጀት የሚጠይቁና ጠቅላላ ጉባዔው ካጸደቀው
በጀት ያልተካተቱ ያልተጠበቁ የንብረትና የአገልግሎት ግዢዎች ላይ ልዩ ውሳኔ ይሰጣል፤

ሠ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤውን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ መመሪያ ይሰጣል፤

ረ. የደብሩን ዓመታዊ የሥራ፣ የሂሳብና የኦዲት ሪፖርቶችን ያጸድቃል፤።

ሰ. የአጥቢያውን ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላትን ይመርጣል ያስመርጣል።

፬.፪ የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

ሀ. የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ በዓመት አንድ ጊዜ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው በሚወስነው ቀንና ቦታ ይካሄዳል።

ለ. ከመደበኛው ዓመታዊ ጉባዔ ውጭ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሂደትና እና የሂሳብ ሪፖርት የሚሰማበት
ስብሰባ መደረግ አለበት እንዲሁም አስቸኳይ ጠቅላላ ስብሰባ ጉባዔ ሊጠራ ይችላል። ከጠቅላላ አባላቱ ውስጥ
ሁለት ሶስተኛው የፈረሙበት ሰነድ ወይም ስድስት የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በጽሑፍ ጉዳዩን
በዝርዝር ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አቅርበው ሲጠይቁ ልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ሊጠራ ይችላል።

ሐ. የጠቅላላ ጉባዔ አጠራር

፩ የስብሰባው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት እንዲሁም አስቸኳይ ጉባዔ ከሆነ የተጠራበት ጉዳይ በዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ
ወይም በዐውደ ምህረት በቃል መገለጽ አለበት።

፪ በአጋጣሚ አንድ አባል ጥሪው በአግባቡ ባይደርሰው ወይም የስብሰባ ማስታወቂያው አባላት በሚያገኙባቸው
በሁሉም ቦታ ባለመውጣቱ ብቻ ጠቅላላ ስብሰባው አይታጎልም/አይሰናከልም።

10
፫ ከአቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ካላጋጠመ በስተቀር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ስብሰባው ፲፭ ቀናት ሲቀረው
ማስታወቂያው መለጠፍ ወይም መነገር ይኖርበታል፡፡

፬.፫ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሥርዓት

ሀ. የስብሰባ ሥርዓት

ጠቅላላ ጉባዔው በፀሎት ይከፈታል፤ በፀሎት ይዘጋል። የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ሊቀ መንበር ስብሰባውን
ይመራሉ። ሊቀ መንበሩ ካልተገኙ፣ ም/ሊቀ መንበር፣ ሁለቱም ካልተገኙ ዋና ጸሐፊው ጠቅላላ ጉባዔውን ይመራል።
ሦስቱም ካልተገኙ ጠቅላላ ጉባዔው ጊዜያዊ ሰብሳቢ ይመርጥና ስብሰባው ይካሄዳል።

ለ. ምልዓተ ጉባዔ

የአባልነት ግዴታቸውን ከተወጡ አባላት ከግማሽ በላይ ወይም 50% + 1 ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል።

ሐ. ድምፅ አሰጣጥ

ማንኛውም የውሳኔ ሐሳብ በአብላጫ ድምፅ ያልፋል። ሰብሳቢው በቅድሚያ ድምፅ ሊሰጥ አይችልም። ሆኖም የተሰጠው
ድምፅ እኩል በኩል ከሆነ ሰብሳቢው የወሳኝነት ድምፅ ይሰጥና እሱ የተስማማበት ውሳኔ ያልፋል። አባልነቱን አሟልቶ
የተገኘ አባል ሁሉ አንድ ድምፅ ይኖረዋል፣ በቤተሰብ ደረጃ የተመዘገቡ አባላት ሁለት ድምጽ ይኖራቸዋል።፡ድምፅ
የሚሰጠው እጅ በማውጣት ወይም እንደ አስፈላጊነቱ በምርጫ ሳጥን ይፈጸማል። በውክልና ድምፅ መስጠት አይፈቀድም።

አንቀጽ ፭. የሰበካ መንፈሳዊ የአስተዳደር ጉባዔ

፭.፩ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ሥራ አስፈጻሚ አባላት

የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ዋና አስተዳዳሪውን ጨምሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ አባላት
ይኖሩታል።

፩. ሊቀ መንበር (የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ መነኩሴ ወይም ቄስ ያለ ምርጫ የሚገቡ)

፪. ምክትል ሊቀ መንበር (ከምዕመናን)

፫. ፀሐፊ
11
፬. ስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ኃላፊ

፭. ሕዝብ ግንኙነት ፤ ልማትና በጎ አድራጎት ክፍል ኃላፊ ፡

፮. የማህበራዊና ስደተኞች ጉዳይ ክፍል ኃላፊ

፯. ንብረትና ሂሳብ ክፍል ኃላፊ

፰. ገንዘብ ያዥ

፱. የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ኃላፊ

፭.፪ የቤተ ክርስቲያኗ ጽ/ቤት

የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር እና ፀሐፊ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔው
ወይም የቤተ ክርስቲያኗ ጽ/ቤት አባላት ሲሆኑ አንድ ወጥ የሆነ የጋራ ዕቅድና ሪፖርት ይኖራቸዋል።

፭.፫ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ስልጣንና ተግባራት

የቤተ ክርስቲያኗ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የሚከተሉትን ስልጣንና ኃላፊነት ይኖሩታል።

፭.፫.፩. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ስልጣን


ሀ. የቤተ ክርስቲያን ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ ሥርዓትና ሲኖዶሳዊ መዋቅር የመጠበቅና
የማስጠበቅ ግዴታ ይኖርበታል፤

ለ. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የሚሰጣቸው ትህምርትም ሆነ የሚዘምሩት መዝሙር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ሃይማኖት ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት መሠረት መሆኑን የማረጋገጥ፣ ሥራቸውና ጠባያቸው ከክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር
ውጭ እንዳይሆን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት። በሰንበት ት/ቤት ያልተመዘገቡ ወጣቶችን እንዲመዘገቡ፣
በሃይማኖትና በሥነ ምግባር እንዲጸኑ ያደርጋል።

ሐ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ በዚህ ሕግ ደንብ ውስጥ የተቀመጠውን ደንብ ወይም ሕግ የመጠቀም (የመተግበር)
ሥልጣን ያለው ከመሆኑም በላይ በሕጉ ውስጥ ያልተጠቃለሉ ሆኖም ግን በየጊዜው ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ይሆናሉ
ተብለው በጠቅላላ ጉባኤ የሚወጡትንና የሚደነገጉትን ሕጎችና ደንቦች የመተግበርና የማስፈጸም ስልጣን አለው።
ሆኖም ሕጎቹ ከክፍለ ሀገሩ ሕግ ጋር የሚጋጩ መሆን የለባቸውም።

መ. የቤተ ክርስቲያኗን የአስተዳደርና የሂሳብ ሥራ ይቆጣጠራል፣ ያስተዳድራል፤ በተጨማሪ የደብር አለቃውን፤ የካህናትንና
የዲያቆናትን የአገልግሎት ክፍያ አቅም እንደፈቀደ ይወስናል፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ይቆጣጠራል።

12
ሠ. ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የተሳካ ለማድረግ ኮሚቴዎች ያቋቁማል፣ የኮሚቴ አባላትን ይመርጣል፣ የስራ
ተግባራቸውን መመሪያ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል።

ረ. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ ፭.፫.፩.ሸ በተቀመጠው ጣሪያ መሰረት ማንኛውንም ወጪ ያጸድቃል።

ሰ. የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ ምክትል ሊቀ መንበርና እና ሂሳብ ሹም በቼክና ሂሳብ ነክ በሆኑ ሰነዶች ላይ ይፈርማሉ።
በቼክ ላይ ከሶስቱ ኃላፊዎች ቢያንስ የሁለቱ ፊርማ መኖር አለበት። የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳዳሪ የሚመለከቱ ወጪዎች
በሙሉ በምክትል ሊቀ መንበርና እና ሂሳብ ሹም ብቻ ይፈረማሉ።ሸ. በአመታዊ ጉባኤ ከጸደቀው በጀት ያልተጠቃለሉና
ያልተጠበቁ ወጪዎች ካጋጠሙ የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ ሳይጠብቅ በአንድ ወር ውስጥ እስከ ፟$5000.00 (አምስት

ሺህ) የካናዳ ዶላር ወጪ ማጽደቅ ይችላል፣ ከዚህ በላይ ለሚጠይቁ ወጪዎች የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ ማግኘት
ያስፈልጋል።

ቀ. ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ወይም ማንኛውንም ሕንጻ ለመስራት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ያቋቁማል፣
ሥራውንም በበላይ ይቆጣጠራል፣ ለዚሁ አላማ የሚውለውን ገንዘብ በዋናው የባንክ አካውንት ውስጥ ንዑስ

አካውንት ተከፍቶለት በቤተክርስቲያኑ የሂሳብ አስራር መሰረት ይተዳደራል።

በ. ማንኛውም የቤተክርስቲያን ፕሮጄክቶች የባንክ አካውንት ቢያስፈልጋቸው ከቤተከርስቲያኗ ዋና አካውንት ስር ንኡስ


አካውንት ተከፍቶ በተራ ቁጥር “ቀ” በተጠቀሰዉ መሰረት ይተዳደራል።

፭.፫.፪ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ተግባራት


ሀ. ዓመታዊ የሥራና የበጀት ዕቅድ እንዲሁም የረዥም ጊዜ ስልታዊ ዕቅዶችን አውጥቶ ለዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል፡፡
በጠቅላላ ጉባዔ የፀደቁት ዕቅዶች በሥራ ላይ ያውላል፤ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ዘገባ ያዘጋጃል፣ ለአባላት ጠቅላላ
ጉባዔ ያቀርባል፡፡ ከዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በተጨማሪ የመጀመሪያ ስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሂደትና እና የሂሳብ
ሪፖርት ለአባላት ያቀርባል።

ለ. ከቤተ ክርስቲያን እምነትና ዓላማ ሳይወጣ ቤተ ክርስቲያንን ወክሎ ከሦስተኛ ወገን ጋር ውል ይደራደራል፣ ይፈራረማል፤
ጥቅሟንና ሀብቷን ለማስጠበቅ ይከሳል፣ ይከላከላል፡፡

ሐ. ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት የሚሰጡ የካህናትን እና የሌሎች ባለሞያዎችን ቅጥር ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ
ሲፈቀድለት ውል ተፈራርሞ ይቀጥራል፣ ደመወዝ ይወስናል፣ አገልግሎታቸውንም ይቆጣጠራል፣ለሐገረ ስብከቱ
ያሳዉቃል;;

መ. ከላይ አንቀጽ ፩ ንዑስ አንቀጽ ሰ በተጠቀሰዉ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ የቤተክርስቲያኑን አስተዳዳሪ መርጣ፣ ደምዎዝ ወስና

የአገልግሎት ውል ፈርማ ለሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ታሳውቃለች።

13
ሠ.የአባላት ስምና አድራሻ የሚይዝ የተሟላ መዝገብ ይኖረዋል፡፡ የአባልነት ግዴታቸውን ያሟሉ መሆኑን እያረጋገጠ
ከስድስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለአባላት የመታወቂያ ወይም የአባልነት ካርድ ይሰጣል፡፡

ረ.የልደት፣ የጥምቀት፣ የጋብቻና የሞት የምስክር ወረቀት ወቅቱን ጠብቆ ይሰጣል።

ሰ.ዓመታዊ የአባላት መዋጮ ክፍያን ይተምናል፣ በጠቅላላ ጉባኤ ያስወስናል።

ሸ. የቤተ ክርስቲያኑን ገንዘብ በቤተ ክርስቲያኑ የባንክ አካውንት ያስቀምጣል፤ የሂሣብና የንብረት አያያዝ ሕጋዊ አሰራርን
የተከተለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ቀ. ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችንና ሰነዶንችን መዝግቦ ይይዛል፡፡

በ. የቤተክርስቲያን ሕንጻ እና በይዞታው ያሉ የአገልግሎት መኖሪያ ንብረቶች እና ቅጽር ግቢውን በሙሉ አስፈላጊውን
እንክብካቤ ያደርጋል፣ ጥገና ያስደርጋል መደረጉንም ያረጋግጣል።

ተ. ገቢና ወጪ ደብዳቤዎች በአግባቡ ቁጥር ይዘው የሚመዘገቡበትን መዝገብ ይይዛል፡፡

ቸ. ለሌሎች አርአያ ለሆኑ አባላት ለመልካም አገልግሎታቸው ማበረታቻ የምስክር ወረቀትና ሽልማት ይሰጣል።

ኀ. በስልጣን ተዋረድ ከሊቀ ጳጳሱ፤ ከሌሎች የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች፤ ሌሎች የክርስትና እምነት
ካላቸው ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ጥቅም አብሮ ይሰራል።

ነ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት መካከል አለመግባባቶች ከተፈጠሩ ጉዳዩ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር
ጉባኤው መፈታት አለበት። በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው ሊፈታ ያልቻለ አለመግባባት ለአባላት ጠቅላላ
ጉባዔ ቀርቦ ጠቅላላ ጉባዔው በሚያቋቁመው ልዩ ኮሚቴ እንዲፈታ ይደረጋል።

ኘ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀ መንበር ወይም ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው
የሚወክለው ተወካይ በሀገረ ስብከቱ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉ ወጪያቸውን በመሸፈን ይልካል፤ በሀገረ
ስብከቱ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል። የሁለቱን ወጪዎች ለመሸፈን አቅም ካልፈቀደ የደብር
አለቃው ቤተ ክርስቲያኑን ይወክላል። ለሌሎች ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ለሚደረግ ውክልና ግን የሰበካ መንፈሳዊ
አስተዳደር ጉባኤ የበጀት አቅም እየታየ ይወሰናል።

አ. በደብሩ በቂ ካህናት ካሉ የካህናት ጉባኤ እንዲቋቋም ያደርጋል፤

፭.፬ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የአገልግሎት ዘመን

ሀ. በአንድ የምርጫ ዘመን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሁለት ዓመት ያገለግላሉ።
14
ለ. አንድ የሥራ አስፈጻሚ አባል ከአንድ ምርጫ ዘመን ወይም፟ ሁለት አመት ቆይታ በኋላ እንደገና መመረጥ ይችላል።
ሆኖም አንድ የሥራ አስፈጻሚ አባል ከሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን ማለት ፟ አራት አአመት ተከታታይ ዘመን በላይ
መመረጥ አይችልም። ከአንድ ምርጫ ዘመን ወይም ከሁልት አመት በኋል መመረጥ ይችላል።

ሐ. በአንድ የምርጫ ዘመን የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባል ከጎደለ በዚህ ምርጫ ዘመን በተጠባባቂነት ካሉት
፟በእጣው መሠረት የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባል ይሆናል። በተጠባባቂነት ያሉት አባላት የአስተዳደር ጉባኤ
አባል ከሆኑ ወይም በተለያየ ምክኒያት አስተዳደር ጉባኤ አባል መሆን ካልቻሉ እና ተተኪ አስተዳደር ጉባኤ አባል
ካስፈለገ ጠቅላላ ጉባኤው አባላትን ይወስናል።

መ. የሥጋ ዝምድና ያላቸው ወይም የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባልነት በአንድ
የምርጫ ዘመን አብረው ማገልገል አይችሉም።

፭.፭ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የስብሰባ ሥርዓት

ሀ. የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ሊቀ መንበር በመሆኑ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር
ጉባኤውን ስብሰባ ይመራል፣ ሊቀ መንበሩ በስብሰባው ካልተገኘ ምክትል ሊቀ መንበሩ ወይም እሱ ካልተገኘ ዋና
ጸሐፊው ስብሰባውን ይመራል፡፡

ለ. በስብሰባ ላይ ከተገኙት የሥራ አስፈጻሚ አባላት ከግማሽ በላይ ድምፅ የሰጡበት ውሣኔ የጸና ይሆናል፡፡ ለድምፅ
የቀረበውን ሐሳብ የሚደግፉና የሚቃወሙት አባላት እኩል እስካልተከፈሉ ድረስ ሰብሳቢው ድምፅ አይሰጥም፡፡
በእኩል ድምጽ ሲከፈል ግን ሰብሳቢው ድምፅ ይሰጥና እሱ ድምፅ የሰጠበት ውሳኔ ያልፋል፡፡

ሐ. ቃለ ጉባዔ በጸሐፊው ይዘጋጅና በቀጣዩ ስብሰባ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በስብሰባው በነበሩት የሰበካ መንፈሳዊ
አስተዳደር ጉባኤ አካላት ታይቶ ይፈረማል፡፡ በጽሑፍ ቀርቦ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው አካላት የተፈረመ
ቃለ ጉባዔ ውሣኔ ሁሉ የጸና ነው፡፡

መ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል፣ ሁሉም ስብሰባዎች
የሚካሄዱት ይህን መተዳደሪያ ደንብ በጠበቀ ሁኔታ ይሆናል።

ሠ. ከደብር አለቃው በስተቀር የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት የሚያገለግሉት ያለምንም ክፍያ በበጎ ፈቃድ ነው።

ረ. ጸሐፊው ባልተገኘበት ስብሰባ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ጊዜያዊ ጸሐፊ ይሰየማል።

፭.፮ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት የመምርጫ መስፈርት

ሀ. የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን እምነት፤ ሥርዓትና ዶግማ ሕግጋት ሙሉ በሙሉ የተቀበሉና ለማስከበር የተዘጋጁ፣

ለ. በዚህ ሕገ ደንብ የተቀመጡትን የአባልነት መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ተቀብለው ያሟሉና ለማስፈጸም የተዘጋጁ፣
15
ሐ. የጠቅላላ ጉባዔን ውሳኔዎች ሙሉ በሙሉ ተቀብለው የሚያስፈጽሙ፣

መ. ከ 3 ወር በላይ የሰበካ ጉባኤ ወርሃዊ ክፍያ ዕዳ የሌለባቸው፣

ሠ. ጊዜያቸውን ለአገልግሎት መስዋዕት ለማድረግ የተዘጋጁ፣

ረ የማስተዳደርና የማስተባበር ፀጋ ያላቸው፣

ሰ. ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚፋጠኑ (የሚተጉ)፤

ሸ. የንስሀ አባት ያላቸው።

ቀ. ቢያንስ በአባለንት አንድ አመት የቆየ መሆን አለበት ።

፭.፯ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባልነት ስለመሰናበት

አንድ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባል የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ባይወጣና ከቤተ ክርስቲያኗ ዓላማ ውጭ
ሲንቀሳቀስ ቢገኝ፦

ሀ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ልዩ ውሳኔ የሚቀጥለው የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ እስኪካሄድ ድረስ ከሥራ
አስፈጻሚነት ሊታገድ ይችላል፤

ለ. በአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ልዩ ውሳኔ ከሥራ አስፈጻሚነት ሊሰናበትና በምትኩ ሌላ ሊተካ ይችላል።

አንቀጽ ፮. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አስመራጭ ኮሚቴ

የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ምርጫ የሚካሄደው በጠቅላላ ጉባዔ በሚመረጥ አስመራጭ ኮሚቴ ብቻ
ይሆናል።

፮.፩ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት መስፈርት

ሀ. ከ፫ ወር በላይ የሰበካ ጉባኤ ወርሃዊ ክፍያ ዕዳ የሌለባቸው፣

ለ. ሥራው ተከታታይ ስለሆነ የምርጫው ሂደት እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቂ ጊዜ የሚኖራቸው።

፮.፪ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት

ሀ አስመራጭ ኮሚቴ ሶስት አባላት ይኖሩታል፤ እነሱም ሰብሳቢና ጸሐፊ ከመካከላቸው ይመርጣሉ፣

16
ለ. የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባልነት በዕጩነት አይቀርቡም፡፡

፮.፫ የአስመራጭ ኮሚቴ ተግባራት

ሀ. የምርጫ ሰነዶችን (ቅጾችን) ካዘጋጁ በኋላ በጠቅላላ ጉባኤ አባላት ስብሰባ ላይ ከአባላት ጥቆማዎች ይቀበላሉ፣
የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ከመከናወኑ አንድ ወር አሰቀድሞ (ህዳር) ይመረጣሉ፣ እስከ አንድ ወር ድረስ

የምርጫ ሰነዶችን ቅጾችን አዘጋጅተው ከምዕመን ጡቀማ ተቀብለው ታህሳስ ወር ውስጥ በጠቅላላ ጉባዔ የእጣ

ምርጫ ይደረጋል። በጥር ወር ርክብክብ ይደረጋል።

ለ. የእጣ ምርጫው ቀንና ሰዓት አስመራጭ ኮሚቴው ለአባላት በቅድሚያ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

ሐ. የአስመራጭ ኮሚቴ በጥቆማ ከቀረቡለት አባላት መካከል መርምሮና አጣርቶ ያቀረባቸውን ፟፟ 11-13 እጩዎችን ለጠቅላላ
ጉባኤው ምርጫ አቅርቦ ፟ 7 የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላትን ያስመርጣል። ያስመርጣል (በተጨማሪ ከታች
“፟ ተ”ን ይመልከቱ) ።

መ ከሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ውስጥ በበሰንበት ትምህርት ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በሚቀርብ ጥቆማ ለሰበካ መንፈሳዊ

አስተዳደር ጉባኤው የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ኃላፊውን መርጦ ያቀርባል ።

ሠ. በመርጫው እለት ተመራጮች እና ተጠባባቂዎች በእጣ ይለያሉ።

ረ. አስመራጭ ኮሚቴ ከአለፈው የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አካላት ወደ አዲስ ተመራጭ የሰበካ መንፈሳዊ
አስተዳደር ጉባኤ አካላት ርክክብ ወቅት አረካካቢ ሆኖ ይሰራል፡፡ የሥልጣን ሽግግሩ መካሄዱን በማረጋገጥ ይህንን
ለአባላቱ ካሳወቀ በኋላ የአስመራጭ ኮሚቴው አገልግሎት ያበቃል፡፡

ሰ. ከነባሩ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ወደ አዲሱ ተመራጭ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አካላት የኃላፊነቱ
ርክክብ የሚፈጸመው አሸናፊ ተመራጮችን ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ከሁለት ሣምንታት ባልበለጠ ጊዜያት ውስጥ
ይሆናል፡፡ የኃላፊነቱ ርክክብ ከመፈጸሙ በፊት አዲሱ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ተግባሩን አይጀምርም፡፡

ሸ. አዲስ የተመረጡት የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ጋር እንደ ሙያቸውና
ዝንባሌያቸው በስምምነት የሥራ ክፍፍል ያደርጋሉ።

ቀ. አስመራጭ ኮሚቴው በምርጫው ሂደት የተጠቀመባቸውን ሰነዶች፣ ቃለ ጉባዔዎችና የምርጫ ቅጾች በሙሉ በጽ/ቤቱ
ይቀመጡ ዘንድ ለአዲሱ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ያስረክባል፡፡

17
በ. በሥልጣን ሽግግሩ ወቅት ክትትል የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅዶች ሥራ ላይ ያውላቸው
ዘንድ አዲሱ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ከነባሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጋር ዝርዝር ውይይትና የልምድ
ልውውጥ ያካሂዳል፡፡

ተ. የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ በቀጥታ የሰበካ መንፈሳዊ ሊቀመንበር ይሆና

አንቀጽ ፯. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ተግባርና ኃላፊነት

፯.፩ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ (ሊቀ መንበር)

ሀ. የአባላት ጠቅላላ ጉባዔና የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤውን ስብሰባ ይመራል፣

ለ. መንፈሳዊ አገልግሎቶችንና ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከቱ ጉዳዮችን ከማህበረ ካህናቱን በመያዝ


ይመራል፤

ሐ. ጸሎተ ቅዳሴው፣ ሚስጢራተ ቤተ ክርስቲያንና ስብከተ ወንጌል ሳይጓደል በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት
መርሀ ግብሩን ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤

መ. ምዕመናን መንፈሳዊ ሕይወታቸውን እንዲያጎለብቱ፣ ንስሐ እንዲገቡና ከተሳሳተ እምነት (ከኑፋቄ) ራሳቸውን
እንዲጠብቁ ምክርና ትምህርት ይሰጣል፤ ካህናቱም የንስሀ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩና በመንፈሳዊ ህይወታቸው
እንዲያተጉ መመሪያ ይሰጣል፤

ሠ. ቤተ ክርስቲያንን ለሚያገለግሉት ቀሳውስትና ዲያቆናት መመሪያ ይሰጣል፤ መንፈሳዊ ትምህርቶችና አገልግሎቶች


እንዲጠናከሩ ያደርጋል፤

ረ. በህመምና በሀዘን ምክንያት ወደ ከቤተ ክርስቲያን የቀሩትን ምዕመናንና ካህናት ይጎበኛል፤ ያጽናናል፤

ሰ. በመንፈሳዊ ስብሰባዎች ቤተ ክርስቲያኑን በመወከል ይሳተፋል፤ እንደአስፈላጊነቱ ከሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት


ጋር ግንኙነት ያደርጋል፤

ሸ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ግብዣ የሚመጡ የቤተክርስቲያን ካህናት ወይም ሰባኪ ወንጌል ተቀብሎ
እንደሙያ ችሎታቸው እንዲያገለግሉ ይመድባል፤

ቀ. የልደት፣ የጥምቀት፣ የጋብቻና የሌሎች መንፈሳዊ አገልገሎቶች የምስክር ወረቀት ላይ ይፈርማል፤

በ. ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ እና ካህናት ጋር በመመካከር ለቤተ ክርስቲያኑ የዘወትር አገለግሎት የሚውሉ
ልዩ ልዩ ንዋየ ቅድሳትን ይጠብቃል፣ መሟላታቸውንም ይቆጣጠራል፤ ሲጎድሉም እንዲሟሉ ያደርጋል፤

ተ. ለስራ ማስኬጃ ካለው ገንዘብ ለምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሚያ በወር ከ $500.00 ያልበለጠ ወጭ ያለ ሰበካ
መንፈሳዊ አስተዳደር ውሳኔ የማዘዝ ሥልጣን አለው፤
18
ቸ. እንደ አስፈላጊነቱ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዉሳኔ የማያስፈልጋቸዉን መልዕክቶች ለምዕመናን ያቀርባል፤(የስተላልፋ)

ኅ. ዋና ጸሐፊው ባረቀቀው መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ደብዳቤ ላይ ይፈርማል

ነ. ከምክትል ሊቀ መንበሩ ወይም ምክትል ሊቀ መንበሩ በቅርብ ከሌለ ፟ከሒሳብ ሹም ጋር በጥምረት በወጪ ቼክ ላይ
ይፈርማል፤ ሆኖም ለራሱ የሚከፈል ቼክ ላይ መፈረም አይችልም፡፡

ኘ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ሲጸድቅ ቤተ ከርስቲያኑን ወክሎ ይደራደራል፣ ውሎችንም ይፈርማል፡፡

ከ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የምርጫ ሂደትን ተከታትሎ ለሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባዔ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ
ሪፖርት ያቀርባል።

፯.፪ ምክትል ሊ ቀ መንበር

ሀ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ተግባርና ኃላፊነታቸውን በሚገባ መወጣታቸውን ይከታተላል ፡፡

ለ. የቤተ ክርስቲያኒቱን ሂሳብና ንብረቶችን ይቆጣጠራል።

ሐ. የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ በማይገኙበት ጊዜ ጠቅላላ ጉባዔና የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤውን ስብሰባዎች
ይመራል፡

መ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ሲጸድቅ ቤተ ከርስቲያኑን ወክሎ ይደራደራል፣ ውሎችንም ከአስተዳዳሪው ጋር
በጣምራ ይፈርማል፡፡

ሠ. የኮሚቴዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል፡፡

ረ. እንደ አስፈላጊነቱ ወቅታዊ መግለጫዎችንና ማስታወቂያዎችን ለምዕመናን ያቀርባል፡፡

ሰ. በዋና ጸሐፊው የተረቀቁ አስተዳደራዊ ደብዳቤዎችና ሰነዶች አስተዳዳሪዊ በቅርብ ካሌሉ ይፈርማል።

ሸ. የቤተ ክርስቲያኑን ሕገ ደንብ፣ ደኀንነት፣ አንድነትና መብት ያስከብራል፣ ያስጠብቃል።

ቀ. የወጭ መጠየቂያ በሂሣብ ሹሙ በሚቀርብለት ጊዜ መርምሮ ያጸድቃል፡፡

በ. ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ወይም አስተዳዳሪው በቅርብ ከሌሉ ብቻ ፟ ከሒሳብ ሹሙ ጋር በጥምረት በወጪ ቼክ
ላይ ይፈርማል፤ ሆኖም ለራሱ የሚከፈል የሥራ ማስኬጃ ቼክ ላይ መፈረም አይችልም፡፡

፯.፫ ጸሐፊ

ሀ. ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና ከምክትል ሊቀ መንበሩ ጋር በመመካከር የአባላት ጠቅላላ ጉባዔና የሥራ አስፈጻሚ
ጉባኤ የሚወያዩባቸውን አጀንዳዎች ያዘጋጃል፣ ለስብሰባ ተሳታፊዎች ከስብሰባው አስቀድሞ ይልካል፤
19
ለ. በስብሰባ ላይ የተገኙትን አባላት ስም ዝርዝር ይመዘግባል፤ ቃለ ጉባዔ ይይዛል፡፡ በአለፈው ስብሰባ ላይ የተያዘውን
ቃለ ጉባዔ በአባላላት ወይም ጠቅላል ጉባኤ ላይ በንባብ ያሰማል፤ ወይም በአለፈው ስብሰባ ላይ የተያዘውን ቃለ
ጉባዔ ከሚቀጥለው ስብሰባ ከአምስት ቀን በፊት በማድረስ የቀረበውን ቃለ ጉባኤ በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ
ያጸድቃል፤

ሐ. የጽሕፈት ቤቱን ዕቅድና ሪፖርት ያዘጋጃል፤ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤውን የዕቅድ ዝግጅትና የሥራ
አፈጻጸም ሪፖርት ያስተባብራል፣ ያጠናቅራል፤

መ. ቋሚና አዲስ ተመዝጋቢ አባላትን ይመዘግባል፤ ለቋሚ አባላት የመታወቂያ ወረቀት ይሰጣል፣ መታወቂያውም
በወቅቱ መታደሱን ያረጋግጣል፤

ሠ. የልደት፣ የጥምቀት፣ የጋብቻና የፍታት መመዝገቢያ ቅጽ ያዘጋጃል፤

ረ. የቤተክርስቲያኑን ማኀተም ይይዛል፣ ወጪ ደብዳቤዎች፣ የምስክር ወረቀትና ሰነዶች ላይ ማኀተም ያደርጋል፤

ሰ. ወጪና ገቢ ደብዳቤዎችን በመዝገብ መዝገቦ በማህደር ይይዘል፣ ደብዳቤዎች በወቅቱ ለተገቢው አካል
መድረሳቸውንና ውሳኔ ማግኘታቸውን ይከታተላል፤

ሽ. የቤተ ክርስቲያኑን የፖስታ ሣጥን ቁልፎችን ይይዛል የደረሱትን ደብዳቤዎች በጊዜው ለተገቢው የሥራ ከፍል
በወቅቱ እንዲደርስ ያደርጋል፤

ቀ. የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና ምክትል ሊቀ መንበሩ በሌሉበት ጊዜያት የቤተ ክርስቲያኑን ሥራ ይመራል፤

በ. አጥቢያው በዓመታዊና የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንዲመራ ያደርጋል፣

፯.፬. ስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ኃላፊ

ሀ. የስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ኃላፊ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚሰጥባቸው ዕለታት የትምህርት
መርሐ ግብር በማዘጋጀት አስተዳዳሪውን በማማከር መምህራን ይመድባል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤

ለ. ለምዕመናን/ት እና ታዳጊ ወጣቶች ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መርሐ ግብር በማዘጋጀት አስተዳዳሪውን
በማማከር መምህራን ይመድባል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
20
ሐ. ልዪ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር በማዘጋጀት አስተዳዳሪውን በማማከር መምህራን ይመድባል፣ አፈጻጸሙን
ይከታተላል፤

መ. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጉባዔ ታይተውና በማዕከል የተፈቀዱ የሕትመት፣
የምስልና የድምጽ ውጤቶች እንዲሰራጩ ያደርጋል፣ ያልተፈቀዱ ውጤቶች እንዳይሰራጩ ይቆጣጠራል፤

ሠ. ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውቅና ያልተሰጣቸው ሰባኪዎችና አጥማቂዎች አገልግሎት


እንዳይሰጡ ይቆጣጠራል፤

ረ. እንደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅምና ሁኔታ አስተዳዳሪውን በማማከር የአብነት ትምህርት ቤት ያቋቁማል፣ ከፊደል ጀምሮ
የንባብ፣ የጽሕፈት፣ የጸዋትወ ዜማ፣ የአቋቋም፣ የግዕዝ፣ የቅዳሴ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክና የትርጓሜ ትምህርት
እንዲሰጥ ያደርጋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፤

ሰ. ከቅዱስ ሲኖዶስ በሚወጣው መመሪያ መሰረት ህጻናትን ፊደል፣ ንባብ፣ መሠረት ሃይማኖት ተምረው በክርስቲያናዊ
ሥነ ምግባርና በሃይማኖት ተኮትኩተው እንዲያድጉ ያደርጋል፤

ሸ. በህጻናት ክፍል ወይም በሰንበት ትምህርት ቤት ለሚሰጠው ትምህርት አስተዳዳሪውን በማማከር መምህራን
ይመድባል፣ ትምህርቱን በበላይነት ይቆጣጠራል፤

ቀ. ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ በሰዓቱ ተገኝተው መማራቸውን ይቆጣጠራል፣ የትምህርት ችሎታቸውንም መዝኖ
የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ ያደርጋል፤

በ፣ ቤተ መጻሕፍት እንዲቋቋም ያደርጋል፣ ህጻናት፣ ምዕመናንና ካህናት በቤተ መጻሕፍት ተገኝተው ወይም መጽሐፍት
እየተዋሱ እንዲያነቡና እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ያደርጋል፤

ተ. ወላጆች ልጆቻቸው በሰንበት ት/ቤት ተመዝግበው መንፈሳዊ ዕውቀት እንዲቀስሙ ማድረግ ክርስቲያናዊ ግዴታቸው
መሆኑን ያሳውቃል፣ ይከታተላል፤

ቸ. ተማሪዎችና መምህራን በሰበካ ጉባዔ አባልነት ተመዝግበው መታወቂያ ካርድ እንዲያገኙ ያደርጋል።

፯.፭. የሕዝብ ግንኙነት ልማትና በጎ አድራጎት ክፍል ኃላፊ

፯.፭. ፩. ሕዝብ ግንኙነት

ሀ. ከአባላት የሚመጡ አቤቱታ፣ ቅሬታና አስተያየቶች የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ እንዲመለከተው ያቀርባል፤

ለ. አዲስ አባላትን ይቀበላል፣ ያስተናግዳል፣ ከአባላትና ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ጋር
ያስተዋውቃል፣ ስለ ቤተ ክርስቲያኑ አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል፣ በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድጋፍ ይሰጣል፤

ሐ. የቤተ ክርስቲያኑን የመገናኛ አዉታር በየነ መረብ እና ማህበራዊ መገናኛወች ያዘምናል ይቆጣጠራል

21
መ. በየመገናኛ ዘዴወችን በመጠቀም የቤተክርስቲያንን ወቅታዊ ሁኔታ ለምዕመናን ግንዛቤ እንዲያገኙ ያደርጋል

ሰ. የዉጭ እና የዉስጥ ግንኙነት ከሰበካ ጉባኤ አባላት ጋራ በመምከር የልምድ ልዉዉጥ ወይም መልዕክት
ያስተላልፋል

ሽ. በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉ ምዕዕመናን በመመዝገብ እና ከጽ/ት ቤት ጋር በመተባበር ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን አገልግሎት
ያቀርባል ይከታተላል፣ይከታተላል፣

፯.፭.፪ ልማት እና በጎ አድራጎት

ሀ. የተለያዩ የልማት ምክረ ሀሳቦችንና የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በጥናት እያዘጋጀ በአስተዳደር ጉባዔው ካጸደቀ

በኋላ ተግባራዊ ያደርጋል።

ለ. የአጥቢያው ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ባላቸው ጉልበት፣ ዕውቀትና ሀብት የቤተ ክርስቲያኑን ልማት

እንዲያግዙ ያስተባብራል።

ሐ. በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ ያሰባስባል፣ ለተፈለገው ዓላማ በተፈለገው
ጊዜ መድረሱን ያረጋግጣል፤

መ. በኢትዮጵያ ገጠር ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ጊዜያዊና ዘላቂ ፕሮጀክቶች
ከምእመናንና ከተለያዩ በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ያሰባስባል፣ እናም ለዚሁ አላማ ከቆሙ ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች ጋር
በመተባበር ይሰራል ፤ ለተፈለገው ዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል፤ ለበጎ አድራጊዎች እና ለሰበካ ጉባኤ ወቅታዊ
ሪፖርት ያቀርባል

ሠ በበሽታ ደዌ ወይም በድንገተኛ አደጋ ሆስፒታል ተኝተዉ ጠያቂ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ጥቆማ
ከደረሰዉ ከሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር ተመካክሮ አባላት እንዲጠይቁ ያስተባብራል።

አዛውንት

፯.፮ ንብረትና ሂሳብ ክፍል ኃላፊ

ሀ. የሂሣብ ሰነዶችንና መዛግብትን ይይዛል፤ የሂሣብ ዘገባና መግለጫዎችም ለሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ለአባላትና
ለሌሎችም እንደ አስፈላጊነቱ ያቀርባል፤

ለ. የቤተ ክርስቲያኑን ገቢና ወጪ በዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ መርሕ መሰረት መዝግቦ ይይዛል፤

22
ሐ. የቤተ ክርስቲያኑ ወጪዎች ከተወሰነው የበጀት ድልድል ጋር የሚስማማ መሆኑን ያረጋግጣል፣ እንደአስፈላጊነቱ
የወጭ መጠየቂያ ያዘጋጃል፤

መ. እንደአስፈላጊነቱ የፌዴራል ታክስ፣ የክፍለ ሀገሩ ታክስ እንዲሁም ሌሎችም ዕዳዎች በተገቢው ወቅት መከፈላቸውን
ያረጋግጣል፡፡ በየዓመቱም የታክስ ቅጾችን ሞልቶ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ያስገባል፤

ሠ. የቤተ ክርስቲያኑን ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት በተገቢው አኳኋን መዝግቦ ይይዛል፣ አጠቃቀማቸውን
ይቆጣጠራል፤

ረ. ቤተ ክርስቲያኗ የሚያስፈልጋትን አቅርቦቶች (መገልገያዎች) ያሟላል፤

ሰ. የቤተ ክርስቲያኗ የውስጥና የቅጽር ግቢዋ ጽዳት መጠበቁን ያረጋግጣል፤

ሸ. የቆዩና አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን መዝግቦ በጨረታ እንዲሸጡ እንዲሁም አሮጌና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ
ዕቃዎች እንዲጣሉ ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጉባኤ አቅርቦ በማጸደቅ ይፈጽማል፤

ቀ. በደብሩ ቼክ ፈራሚ ሆኖ ከተመደበ፣ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ወይም ምክትል ሊቀ መንበሩ በቅርብ
በማይኖሩበት ጊዜ ከአንዳቸው ጋር በጥምረት በቼክ ላይ ይፈርማል፣ ሆኖም ለራሱ የሚከፈል የሥራ ማስከጃ ቼክ
ላይ መፈረም አይችልም፡፡

፯.፯ ማህበራዊ እና ስደተኞች ጉዳይ ክፍል ኃላፊ

ሀ በስደት ያሉ ወገኖቹን ወደ ካናዳ ለማስመጣት ቤተ ክርስቲያኗ ባላት የስፖንሰርሽፕ ዕድል የአጥቢያ


ቤተክርስቲያኗ አባል የሆኑት ቅድሚያ የማግኘት መብት ይኖራቸዋል። ሆኖም በስፖንሰርሽፕ ዕድል ለመጠቀም
የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባል፦

● የሰበካ ጉባኤ አባልነት መስፈርት አሟልቶ የተመዘገበ፣

● የሰበካ ጉባኤ አባልነት ግዴታዎችን በአግባቡ የተወጣ፣

● አንድ አዲስ አባል በቤተ ክርስቲያን አባልነት ከተመዘገበ በኋላ ስደተኛ ወገኑን ስፖንሰር ለማድረግ
የሚችለው አንድ አመት በአባልነት ተመዝግቦ ወርሃዊ ክፍያ በወቅቱ በመክፈል ከቆየ በኋላ ነው። ሆኖም
ቤተ ክርስቲያኒቷ መስፈርቱን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ አባላት ዕድሉን ሰጥታ መጨረሻ ላይ የተረፋት ኮታ
ካለ የጊዜ ገደቡ ባይሞላም ተጠቃሚ መሆን ይችላል፤

23
● ስደተኞችን ስፖንሰር ለማድረግ ቅጽ ከሞሉና ካስገቡ በኋላ በሂደት እያለ አባሉ የአባልነት መዋጮ
በተከታታይ ለሦስት ወራት ሳይከፍሉ ከቆየ ለስፖንሰርሺፕ ማስያዝ ያለባቸውን የገንዘብ መጠን
በየወሩ/በተወሰነ ጊዜ እየከፋፈሉ እንዲከፍሉ ቤተ ክርስቲያን ያመቻቸችላቸውን የክፍያ ዘዴ ትብብር
(Privilege) ተነስቶ ቀሪውን የማስያዣ ገንዘብ (Deposit) ባንድ ጊዜ እንዲከፍል እና ክፍያ ካቆመበት ወር
ጀምሮ የአንድ ዓመት የአባልነት ክፍያ በቅድሚያ እንዲከፍል ይደረጋል፤

● አንድ የቤተ ክርስቲያን አባል ወይም ቤተሰብ ስፖንስር ማድረግ የሚችለው በዓመት ውስጥ አንድ ግለሰብ
ወይም አንድ ቤተሰብ ብቻ ይሆናል። የሚኖረው ኮታ ካልሞላ ግን ተጨማሪ ሰው ስፖንሰር እንዲያደርግ
ሊፈቀድለት ይችላል፤

● አንድ የቤተ ክርስቲያን አባል ስፕንስር ማድረግ የሚችለው በዓመት ውስጥ አንድ ግለሰብ ወይም አንድ
ቤተሰብ ብቻ ይሆናል። ሆኖም በቤተሰብ ደረጃ ልዩ የአባልነት ክፍያ ከተወሰነና ቤተሰቡ ክፍያውን በነፍስ
ወከፍ ከፈጸመና በቂ ኮታ ካለ በዓመት ውስጥ አስከ ሁለት ግለሰብ ወይም ሁለት ቤተሰብ ስፖንሰር
ማድረግ ይፈቀድላቸዋል። የሚኖረው ኮታ ካልሞላ ግን ተጨማሪ ሰው ስፖንሰር እንዲያደርጉ
ሊፈቀድላቸው ይችላል።

ለ በምዕመናን መካከል የጠነከረ አንድነት፣ መንፈሳዊ ግንኙነትና ፍቅር እንዲጎለብት ያደርጋል፤

ሐ በበሽታ ደዌ ወይም በድንገተኛ አደጋ ሆስፒታል ተኝተዉ ጠያቂ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ጥቆማ
ከደረሰዉ ከሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር ተመካክሮ አባላት እንዲጠይቁ ያስተባብራል።

መ በአባላት ላይ ደስታ፣ ህመምም ሆነ ሀዘን ሲደርስ ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ያሳውቃል፣ ድጋፍ
ለሚያስፈልጋቸው አባላትን አስተባብሮ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል።

ሠ. የተለያዩ ማህበራዊ፣ ሀይማኖታዊ፣ባህላዊ እና ሌሎች ገቢ ማስገኛ ዝግጅቶችን (መልቲ ካልቸሪል) ሁሉንም የኮሚቴ

አባላትና የሰንበት ት/ቤት በማካተት ማዘጋጀት ።

ረ ከአባላትና አባል ካልሆኑ የስደተኞች ጉዳይ ማመልከቻ በመቀበል ይመዘግባል፣ በካናዳ የስደተኞች ደንብ እንዲሁም
በቤተ ክርስቲያኗ ደንብና መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን ሂደት ከአከናወነ በኋላ ወደ ሚመለከተው የካናዳ
መንግስት አካል ይልካል፤
ሰ.. ጉዳያቸው ተቀባይነት አግኝቶ አዲስ ለገቡ ስደተኞች የካናዳን የኑሮ ሁኔታ እንዲለማመዱ ለማድረግ መረጃ፣ ምክር
እና ሌሎች ድጋፎችን ያደርጋል፤ ስደተኞችን ከሚያቋቁሙና ድጋፍ ከሚያደርጉ አካላት ጋር ያገናኛል፤
24
ሸ. በእንግሊዘኛ የዕውቀት ደረጃ ብቁ ላልሆኑ ስደተኞች በቀጠሮ ቦታ የትርጉም ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

ቀ ስደተኞችን የገቢያ ቦታዎችን፣ መጽሀፍት ቤት፣ የተለያዩ ዕቃዎች መሸጫ ሱቆች ማሳየትና ከትራንስፖርት
አገልግሎት ጋር ያስተዋውቃል፤
በ. ስለ ቤተ ክርስቲያኑ አጠቃላይ መረጃ ለስደተኞችይሰጣል፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጡ ይጋብዛል፤ ከአባላትና
ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ጋር ያስተዋውቃል፣ በሚያስፈልጋቸ ው ሁሉ ድጋፍ ይሰጣል።

፯.፰. ገንዘብ ያዥ

ሀ. የቤተ ክርስቲያኑን የሂሣብ መዛግብት፣ ሰነዶች፣ ደረሰኞችንና በስጦታ የተገኙ ንብረቶችን በአግባቡ ይይዛል፤

ለ. ገንዘብ በተቀበለ በሁለት የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የባንክ ሂሣብ ገቢ ያደርጋል፤

ሐ. የባንክ ቼኮችንና የባንክ ሰነዶችን ይይዛል፡፡ በምክትል ሊቀመንበሩ የተፈረመ በሂሳብ ሹሙ የወጭ ሰነድ ማዘዣ
ክፍያ ይፈፅማል:: ክፍያውን የሚፈፅመው በሊቀመንበሩ እና ም/ሊቀመንበሩ ተፈርሞ በሚቀርብለት የቼክ ሰነድ
ላይ ይሆናል ሆኖም ሊቀመንበሩ ወይንም ም/ሊቀመንበሩ በአካባቢው ከሌሉ እነሱን በመተካት የሒሳብ ሹም
ይፈርማል::

መ. ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ጌጣ ጌጦችና ጠቃሚ ሰነዶች የሚቀመጡበትን የባንክ ሰነድ ማስቀመጫ ሣጥን ቁልፍ ይይዛል፤

ሠ. የአባልነት መዋጮ፣ ስጦታና ከበጎ አድራጊዎች የሚገኙ ገቢዎችን በየአርስታቸው መዝግቦ ይይዛል፤ዛ

፯.፱.የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ኃላፊ

ከሰንበት ትምህርት ቤት ከስራ አመራር አባላት ውስጥ ከሰንበት ትምህርት ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በሚቀርብ ጥቆማ
በአብላጫ ድምጽ የተመረጠው የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ኃላፊ ይሆናል። ኃላፊው ደግሞ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር
ጉባኤው የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ተወካይ ይሆናል። ሆኖም ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ስራ አመራርነት ሲሻር በሰንበት
ትምህርት ቤቱ አዲስ ከሚመረጡ አባላት ወዲያውኑ ይተካል። የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፦

ሀ. የሰንበት ት/ቤትን ያቋቁማል፣ ህጻናትና ወጣቶችን በዕድሜ ከፋፍሎ ያደራጃል፣ ከደብሩ ስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ
ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጋር በመተባበር ዲያቆናትና ቀሳውስት በማስተማር እንዲሳተፉ ያደርጋል፤
ለ. ከደብሩ ስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጋር በመተባበር ህጻናትና ወጣቶችን እንደዕድሜያችው
መጠን መምህራን በመመደብ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በማዕከል ደረጃ በሚወጣው ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ትምህርት
እንዲያገኙ ያደርጋል፤
ሐ. በሰንበት ትምህርት ቤት ተምረው ብቃት ያላቸውን ወጣቶች እየመረጠና ተጨማሪ ሥልጠና እንዲያገኙ እያደረገ
ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ፈቃድ እንዲያገኙ በማድረግ እንዲያስተምሩ ያደርጋል፤
25
መ. ከደብሩ ስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጋር በመተባበር ሣምንታዊ የትምህርት መርሐ ግብር
በማዘጋጀት የቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት፣ የሃይማኖት ትምህርት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የተሰጥዎ ትምህርት
እንዲሰጥ ያደርጋል፤
ሠ. ህጻናትና ወጣቶች በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሃይማኖት እንዲጸኑ፣ የቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት እንዲያውቁና እንዲያከብሩ፣
ግብረገብ እንዲሆኑ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ መመሪያ እየተቀበለ እንዲማሩ ያደርጋል በቅርብ
ይከታተላል፤
ረ. የሰንበት ት/ቤት መዘምራን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሊቃውንት ጉባኤ የተመረመሩና በማዕከል የተፈቀዱ መንፈሳዊ
መዝሙራትን እንዲያጠኑ መረሐ ግብር ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፤
ሰ. ከቤተ ክርስቲያኑ የስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጋር በመመካከር ቤተ መጻሕፍት እንዲቋቋም
ያደርጋል፣ ወጣቶች በቤተ መጻሕፍት ተገኝተው ወይም መጽሐፍት እየተዋሱ እንዲያነቡና እውቀታቸውን
እንዲያዳብሩ ያደርጋል፤
ሸ. ከሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በበዓላትም ሆነ በልዩ ዝግጅቶች በትርዒት መልክ የሚቀርቡ መንፈሳዊ ዝግጅቶች
በቅድሚያ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ታይቶ ከተመረመረና ከተፈቀደ በኋላ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፤
ቀ. የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በበዓላትም ሆነ በልዩ ዝግጅቶች የሚሰበስቡት ገንዘብ ለአጥቢያው ገንዘብ ያዥ ገቢ
ይሆናል፣ ሰንበት ት/ቤቱ የሚያስፈልገውን ወጪ በዓመታዊ ዕቅድ ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አቅርቦ
ሲጸድቅለት ወጪ አድርጎ በአግባቡ ተጠቅሞ ያወራርዳል፤
በ. የሰንበት ትምህርት ቤት አመራር ሊሆኑ የሚገባቸው ዕድሜያቸው ከ፲፮ ዓመት በላይ የሆኑ ወጣቶች በሰበካ
መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው አስመራጭነት በመላው የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ይመረጣሉ።
የሚያገለግሉትም ለሁለት ዓመታት ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ከፈለጓቸው ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ
ተመርጠው ያገለግላሉ፤
ተ. የሰንበት ት/ቤት መዘምራን መንፈሳዊ በዓላት በሚያከብሩበት ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችንን እምነትና ሥርዓት በተከተለ
ሁኔታ የመለያ ልብስ (ዩኒፎርም) እንዲዘጋጅላቸው ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጥያቄ ያቀርባል፣ በአግባቡ
እንዲጠቀሙበት ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
ቸ. በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤና በሰንበት ትምህርት ቤት መካከል ቀልጣፋ የሥራ ግንኙነት እንዲኖር ድልድይ
ሆኖ ያገለግላል፤
ኅ. ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የሰንበት ትምህርት ቤት ዕቅድ፣ በጀትና የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ያቀርባል፤
ነ. የሰንበት ትምህት ቤት ጥያቄዎችን ለሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፤
ኘ. ሰንበት ትምህርት ቤቱን የተመለከቱ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ውሳኔዎችን ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት
ያደርሳል፤
አ. የሰንበት ትምህት ቤት አባላት በሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትና ጉዳይ መሳተፋቸውን ያረጋግጣል።

26
ከ. ወጣት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በተለያዩ አግባብ በሆኑ የቤተክርስቲያን የስራ ዘርፎች ላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
እንዲያደርጉ ያስተባብራል፣ ይደግፋል።

አንቀጽ ፰. ማኅተም

፰.፩ የማኀተም ይዘትና አጠቃቀም

ሀ. የቤተ ክርስቲያኑ ማኀተም ክብ ሆኖ በመሀሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ትውፊት የጠበቀ የመስቀል ቅርጽ ያለውና በዙሪያው የቤተ
ክርስቲያኑ ስም “በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት የኪችነር ሐመረ ኖህ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን” የሚል
በአማርኛና በእንግሊዘኛ ፊደላት የተጻፈ ቅርጽ ያለው ነው ።

ለ. የቤተ ክርስቲያኑን ማኀተም የሚይዘው የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው ጸሐፊ ነው።

ሐ. ማኀተም በሰነድ ላይ የሚታተመው በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ሲወሰን ብቻ ነው።

አንቀጽ ፱. ቃለ ጉባዔ
የአባላት ጠቅላላ ጉባዔና የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የሚወያዩባቸው ጉዳዮች ቃለ ጉባዔ በጠቅላላ ጉባዔ ወይም
በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ እንደአገባቡ ከጸደቀና ከተፈረመ በኃላ በቤተ ክርስቲያኑ ጽ/ቤት ይቀመጣል፡፡ አበይት ውሳኔዎች
የተወሰኑበት ቃለ ጉባዔ በእግሊዝኛም ተተርጉሞ ከተፈረመበት በኋላ መቀመጥ ይኖርበታል።

አንቀጽ ፲. መዝገብ ቤት
ማንኛውም የቤተክርስቲያኗ ሰነዶች ማለትም ደብዳቤዎች፣ የባንክ ሰነዶች፣ የሥራና የሂሳብ ሪፖርቶች፣ ውሎች፣ ደንቦችና
ሕጎች እንዲሁም ሌሎች ሰንዶችና መዛግብት በሙሉ በቤተ ክርስቲያኑ ጽ/ቤት ይቀመጣሉ፡፡

አንቀጽ ፲፩. ውል
የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያን እምነትና ዓላማ ሳይወጣ ቤተ ክርስቲያንን ወክሎ ከሌላ ወገን ጋር
የሥራ ወይም የአገልግሎት ውል በመደራደር ይገባል፣ እንደአስፈላጊነቱ ቅጥር ይፈጽማል።

27
አንቀጽ ፲፪. ብድር
የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ለህንጻ ቤተ ክርስቲያንና ሌሎች አበይት ግዥዎችን ለመፈጸም በቤተ ክርስቲያኑ ስም
ዋስትና በመግባት የብድር ውል በመፈጸም ከባንክ ብድር መበደር ይችላል። ሆኖም ብድሩን በጠቅላላ ጉባዔ ማጸደቅ
ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ ፲፫. ኦዲተር

፲፫.፩ የኦዲተር ምርጫ

ሀ. ተጠሪነቱ ለአባላት ጠቅላላ ጉባዔ የሆነ ሁለት አባላት ያሉበት የሂሣብና ንብረት ኦዲተር ኮሚቴ በጠቅላላ ጉባዔ
ይመረጣል፣

ለ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ሆኖ እያገለገለ ያለ አባል ሆነ በቅጥር የሚያገለግል አባል ኦዲተር ሆኖ መመረጥ

አይችልም፣ተመራጩ ኦዲተር በአገልግሎት ላይ ካለው የሥራ አስፈጻሚ አባል የቅርብ ቤተሰብ መሆን የለበትም፤

ሐ. አንድ ኦዲተር ሥራውን በአግባቡ ካልተወጣ በጠቅላላ ጉባዔ ልዩ ውሣኔ ሊሰናበት ይችላል፤

መ. ኦዲተር ለሥራ ሲሾምም ሆነ ሲሰናበት በጽሑፍ ወዲያውኑ ሊገለጽለት ይገባል፤

ሠ. ኦዲተሩ መደበኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል መሆን አለበት፤

፲፫.፪ የኦዲተር ተግባርና ኃላፊነት

ሀ. የሚሰበሰብ ገንዘብ፣ ክፍያና ወደ ባንክ የሚገባ ገቢ በትክክል መሰራታቸውን መከታተያ ሥርዓት ያዘጋጃል፤

ለ. የቤተክርስቲያን የሂሣብ ሆነ የንብረት ዝውውሮችን (ልውውጥ) ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት፣ ወጪና ኪሳራ፣ ደረሰኞችን፣
የሚከፈሉ ገንዘቦችንና ለመሳሰሉት በአግባቡ መፈጸማቸውን ያረጋግጣል፤

ሐ. ለጠቅላላ ጉባኤ አጠቃላይ አመታዊ የቁጥጥር ሪፖርት ያቀርባል፣ በተጨማሪ የገንዘብና ንብረት አያያዝና የአመራር
መንገዶችን በተመለከተ የማሻሻያ ወይም የአዲስ አሰራር ሃሳቦች ያቀርባል፤

መ. ከነባር ወደ አዲስ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ሥልጣን በሚሸጋገርበት ጊዜ የተሰናባቹን የሰበካ መንፈሳዊ
አስተዳደር ጉባኤ የሂሳብና ንብረት ኦዲት አድርጎ ሂሳብ ይዘጋል፣ ለጠቅላላ ጉባዔም ሪፖርቱን በወቅቱ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ ፲፬. የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪዎችና ማስታወቂያዎች

28
፲፬.፩ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪዎች

የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪዎች የሚከናወኑት ቢያንስ ከሁለት ሳምንት በፊት በሚከተሉት ጥሪ ማስተላለፊያ መንገዶች ነው

ሀ. በዓውደ ምህረት በአስተዳዳሪው ወይም በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ም/ሊቀ መንበር ወይም ሰበካ መንፈሳዊ
አስተዳደር ጉባኤ በሚወክለው ሥራ አስፈጻሚ ይነገራል፤

ለ. በቤተ ክርስቲያኒቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ይለጠፋል፤

ሐ. አባሉ በተመዘገበበት አድራሻ በኢሜል ወይም በስልክ መልዕክት ይላካል፤

መ. ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ በሚፈጸም የጸበል ጸዲቅ መርሀ ግብር በአዳራሽ ውስጥ ይነገራል።

፲፬.፪ ማስታወቂያዎች

ሀ. መንፈሳዊና የማህበራዊ ጉዳዮች ማስታወቂያዎች በሙሉ የሚነገሩት በደብሩ አለቃ፣ በምክትል ሊቀ መንበር ወይም ሰበካ
መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው በሚወክለው ሥራ አስፈጻሚ ብቻ ይሆናል።

ለ. የሶስተኛ ወገን ማስታወቂያ የሚነገረው ወይም በማስታወቂያ ሰሌዳ የሚለጠፈው መንፈሳዊና ማህበራዊ ጠቀሜታው
ታይቶ በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ሲጸድቅ ብቻ ነው።

ሐ በቤተ ክርስቲያኗ የማህበራዊ ሚዲያወች ሊገለጽ ይችላል፤

አንቀጽ ፲፭. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

ሀ. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ለተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች የሚከፈለውን ክፍያ ለአባላትና አባል
ላልሆኑት ለይቶ ይወስናል፣ እንደአስፈላጊነቱም በየጊዜው ሊያሻሽል ይችላል፤

ለ. በአንቀጽ ፫.፪. ሠ ከተደነገገው በስተቀር በአባልነት መብት ተጠቃሚ ለመሆን የአባልነትን ግዴታ ማሟላትና ቢያንስ
ለስድስት ወራት የአባልነት አስተዋጽኦ መክፈል ያስፈልጋል፤

ሐ. የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ከገቢያቸው ከመቶ አስር (አስራት በኩራት) እንዲከፍሉ ወይም እንዲለግሱ ይጠበቅባቸዋል፤

መ. የቤተ ክርስቲያንን ተንቀሳቃሽ ንብረት ከምክትል ሊቀ መንበሩና ጸሐፊው የጽሑፍ ፈቃድ ካልተገኘ በስተቀር ለግል
መጠቀም አይቻልም፤፡

29
ሠ. የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ያባከነ፣ ያጎደለ ያጭበረበረ ወይም የተጣለበትን አደራ ያጎደለ ማንኛውም የሰበካ መንፈሳዊ
አስተዳደር ጉባኤ እና የንኡስ ኮሚቴ አባል በክፍለ ሀገሩ ወይም በካናዳ ሕጎች መሠረት እንደአስፈላጊነቱ በሕግ
እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡

ረ. በፈቃዳቸው አባልነታቸውን የሰረዙ ወይም በጥፋታቸው ከቤተ ክርስቲያን የተሰናበቱ ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን ላይ
የንብረት ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም፤ በቀደመ አባልነታቸው ጊዜ ያዋጡት ገንዘብ የቤተ ክርስቲያኑ ሀብት ይሆናል፡፡

ሰ. ለሌሎች ተመሳሳይ ኃይማኖታዊ ወይም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ግለሰብ እርዳታ ተብሎ የተሰበሰበ ገንዘብ
በሚኖርበት ጊዜ ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ አሥር መቶኛው (10%) ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ገቢ ይሆናል፡፡
ማንኛውም ግለሰብ ወይም ካህን የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከማካሄዳቸው በፊት ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ
ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፡፡

ሸ. አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗ አጠቃላይ አገልግሎቷንና ሥራዎቿን የምትመራበት ዝርዝር መመሪያዎችን የያዘ የመንፈሳዊ
አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ መቅረጽ ይኖርባታል፤

ቀ. እያንዳንዱ አባል ሲመዘገብ ያለምንም ክፍያ የዚህን የመተዳደሪያ ደንብ ቅጂ የማግኘት መብት አለው፤ ቤተ ክርስቲያኗም
የመስጠት ግዴታ አለባት፤

በ. ያለ አጥቢያ ቤተክርስቲያኗ ጠቅላላ ጉባዔ ልዩ ድንጋጌ (ውሣኔ) በዚህ ጠቅላላ ደንብና ዝርዝር ደንብ ላይ መጨመር
ወይም መቀነስ አይቻልም፤

ተ. የአጥቢያ ቤተክርስቲያኗ ሰበካ ጉባኤ እንደ ቤተ ክርስቲያኗ አቅም ተገቢዉን የገንዘብ ፈሰሥ ለሐገረ ስብከቱ ክፍያ
ይፈጽማል።

አንቀጽ ፲፮. ሕገ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜና ስለማሻሻል

፲፮.፩ ሕገ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ

ይህ ሕገ ደንብ የአጥቢአ ቤተክርስቲኗ ጠቅላላ ጉባዔ ካጸደቀበት _ __________________________ ዓ ም ቀን ጀምሮ የጸና


ይሆናል። ከዚህ በፊት የወጡ የቤተ ክርስቲያኗ ሕገ ደንቦች በዚህ ሕገ ደንብ ተሽረዋል።

፲፮.፪ ሕገ ደንቡን ስለማሻሻል

ይህ ሕገ ደንብ ከቤተ ክርስቲያኗ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ከሦስት እጅ ሁለቱ እጅ እንዲሻሻል ከተስማሙ ሊሻሻል ይችላል።

30
አንቀጽ ፲፯. የማህበሩ መበተን

1. ማህበሩ በተለያዩ ምክንያቶች መቀጠል ባይችልና ቢበተን (ቢፈርስ) ንብረቶቹ ለአባላት አይከፋፈሉም፤ ያሉት ዕዳዎች
ከተከፈሉ በኋላ ወይም ለዕዳ ክፍያ መጠባበቂያ ከተቀመጠ በኋላ የሚተርፈው ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኑ ንብረት
ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት ይዛወራል።

2. ያለአባላቱ ጠቅላላ ጉባኤ ልዩ ውሣኔ የቤተ ክርስቲያኑ አገልገሎት ሊቋረጥና ሊበተን አይችልም፡፡

31

You might also like