Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1771 እና 1772 መሠረት የተሰጠ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ

ቀን
ቁጥር
ለአቶ አብዱራህማን ረዲ አህመድ
የሩማን ዳቦ ቤት ባለቤት
አዲስ አበባ
እርስዎ ታህሳስ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በተደረገ የቤት ኪራይ ዉል ስምምነት ከይርጋለም አዲስ ጨርቃ ጨርቅ
ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባ በቀድሞዉ ወረዳ 19 ቀበሌ 55 በአሁኑ ንፋስ ስልክና ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ
10 ክልል አንድ ክፍል ቤት ለሦስት ዓመታት ለዳቦና ሌሎች ምርቶች መሸጫ ለድርጅት አገልግሎት ለሦስት ዓመት
የሚቆይ ዉል አማካኝነት መከራየትዎ ይታወቃል፡፡ የዉሉ ጊዜ ታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ተጠናቋል፡፡
የዉሉ ጊዜ ሲጠናቀቅ ዉሉ ካልተራዘመ በስተቀር የተከራዩትን አንድ ክፍል ቤት በተከራዩት ዓይነት ከማናቸዉም እዳ ነጻ
አድርገዉ ሊያስረክቡ በተስማሙት መሰረት በታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ከተከራዩት ዉጭ አስፋፍተዉ
ለያዙት በጠቅላላ 173 ሜትር ካሬ ይዞታና ቤት በካሬ ሜትር በወር ብር 3፣000 /ሦስት ሺ ብር/ ሂሳብ እንዲከፍሉ
በደብዳቤ ተገልጾልዎታል፡፡ እርስዎም በአካል ቀርበዉ ካሬ ሜትሩ ከ 173 ካሬ ወደ 20 ካሬ ዝቅ አድርገዉ የሚያስተካክሉና
የኪራዩ መጠንም እንዲሻሻልልዎት በጠየቁት መሰረት ከድርጅታችን ጋር ያለዎትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ከግምት ዉስጥ
በማስገባት በካሬ ሜትር ከቫት በፊት ብር 3፣000 /ሦስት ሺ ብር/ የነበረዉ በካሬ ሜትር ከቫት በፊት ብር 2,700 /ሁለት
ሺ ሰባት መቶ ብር/ ሂሳብ እንዲሆን ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጾልዎታል፡፡

የተከራዩት አንድ ክፍል ሆኖ ግቢዉን በማስፋፋት ከተከራዩት መጠን በላይ እየተጠቀሙ በመሆኑ በተደጋጋሚ
በተከራዩት ልክ እንዲያስተካክሉ ወይም አስፋፍተዉ የያዙትን ተገቢዉን ኪራይ እንዲከፍሉ ቢነገርዎትም የያዙትን
ለቀዉ ለማስተካክል ፈቃደኛ ባለመሆንዎ ክፍያዉንም በያዙት ልክ ስላልፈጸሙ ለሚገለገሉበት ተጨማሪ ይዞታ ጭምር
ተገቢዉን ክፍያ እየፈጸሙ ባለመሆንዎ በአጠቃላይ 173 ሜትር ካሬ እየተጠቀሙ ስለሆነ በ 26/8/2015 ዓ.ም. በያዙት
ይዞታ ልክ ታስቦ ያለብዎትን ቀሪ ሂሳብ ከፍለዉ ቦታዉ ለግንባታ የሚፈለግና የሚጀመር ስለሆነ በቤቱ ዉስጥ የሚገኙትን
ማሽኖች እንዳይበላሹ በ 15 ቀን ዉስጥ እንዲያነሱ የሚፈለግብዎትን ቀሪ ሂሳብ በ 10 ቀን ዉስጥ እንዲያጠናቅቁ እና
የተከራዩትን አንድ ክፍል ቤት አስፋፍተዉ ከያዙት ይዞታ ጭምር ለቀዉ እንዲያስረክቡ ዉሉ የሚቋረጥ ለመሆኑ
ማስጠንቀቂያ የተሰጠዎት ቢሆንም ይዞታዉን ያልቀነሱ፤ ንብረትዎን ያላነሱ፤ በተጠቀሙበት ልክ የማስተካከያዉን ክፍያ
ያልከፈሉ በመሆኑ በ 15 ቀናት ዉስጥ በያዙትና በተጠቀሙበት 173 ሜትር ካሬ ልክ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት
አስቀድሞ በደረሰዎት በካሬ ሜትር ብር 3,000 /ሦስት ሺ ብር/ ሂሳብ ከታህሳስ 08 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚታሰብ ከፍለዉ
ንብረትዎን አንስተዉ ለቀዉ እንዲያስረክቡ ነገር ግን በማስጠንቀቂያዉ መሠረት ባይፈጽሙ ተገቢዉን ዳኝነት በመክፈል
በፍርድ ቤት ክስ የሚመሠረትብዎት እና የጠበቃ አበል የቴምብር ቀረጥ የፍርድ ቤት ክፍያ እና ለልዩ ልዩ ወጪና ኪሳራ
የሚጋለጡ መሆኑን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1771 እና 1772 መሠረት ሕጋዊ ማስጠንቀቂ የተሰጠዎት መሆኑ ይታወቃል፡፡
የተሰጠዎት የማስጠንቀቂያ ጊዜ ተጠናቋል፡፡
የድርጅታችን የፋይናንስ ክፍል እርስዎ የዉሉ ጊዜ ከተጠናቀቀበት ከታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የበጀት
ዓመቱ መዝጊያ እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ድረስ 173 ሜትር ካሬ በወር ከቫት በፊት በካሬ ሜትር ብር 2,700 /ሁለት ሺ ሰባት
መቶ ብር/ ሂሳብ የወሩ ኪራይ ከቫት በፊት ብር 467,100 /አራት መቶ ስልሳ ሰባት ሺ አንድ መቶ ብር/ ላይ 15 ፐርሰንት
ተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 70,065 /ሰባ ሺ ስልሳ አምስት ብር/ ሲጨመርበት በወር ብር 537,165 /አምስት መቶ ሠላሳ
ሰባት ሺ አንድ መቶ ስልሳ አምስት ብር/ ስለሚሆን ከታህሳስ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ድረስ የ 7 ወራት
ኪራይ በጠቅላላ ከነቫቱ ብር 3,760,155 /ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ሺ አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ብር/
ስለሚፈለግብዎት ለዚህም ተገቢዉ ደረሰኝ የተያዘ ስለሆነ ክፍያዉን በሦስት ቀናት በድርጅቱ አስተዳደር ቀርበዉ
በሚሰጥዎት የባንክ ሂሳብ ገቢ በማድረግ ካላጠናቀቁ በፍርድ ቤት ክሱ የሚመሠረትና ለተጨማሪ ወጪ የዳኝነት ክፍያ
ብር 40,451.50 /አርባ ሺ አራት መቶ ሃምሳ አንድ ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ ፤ የጠበቃ አበል ክስ በሚቀርብበት ገንዘብ 10
በመቶ ብር 376, 015 /ሦስት መቶ ሰባ ስድስት ሺ አሥራ አምስት ብር/ ከተርን ኦቨር ታክስ ጋር፤ የቴምብር ቀረጥ
በሚቀርበዉ ክፍያ ልክ እና የፎቶ ኮፒ ልዩ ልዩ ወጪዎች ጨምሮ ለመክፈል የሚገደዱ መሆኑን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1771
እና 1772 መሰረት እናስጠነቅቃለን፡፡

ይርጋለም አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር

በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1771 እና 1772 መሠረት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ


ቀን
ቁጥር
ለአቶ አብዱራህማን ረዲ አህመድ
አዲስ አበባ
እርስዎ ታህሳስ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በተደረገ የቤት ኪራይ ዉል ስምምነት ከይርጋለም አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ
ኃ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባ በቀድሞዉ ወረዳ 19 ቀበሌ 55 በአሁኑ ንፋስ ስልክና ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል
አንድ ክፍል ቤት ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በወር ብር 60,000 /ስልሳ ሺ ብር/ ሂሳብ ለሦስት ዓመታት ለዳቦና
ሌሎች ምርቶች ማምረቻና መሸጫ ለድርጅት አገልግሎት መከራየትዎ ይታወቃል፡፡ የዉሉ ጊዜ ተጠናቋል፡፡ የዉሉ ጊዜ
ሲጠናቀቅ ዉሉ ካልተራዘመ በተከራዩት ዓይነት ከማናቸዉም እዳ ነጻ አድርገዉ ሊያስረክቡ ተስማምተዋል፡፡
የተከራዩት አንድ ክፍል ሆኖ ነገር ግን ግቢዉን በማስፋፋት ከተከራዩት መጠን በላይ እየተጠቀሙ በመሆኑ በተደጋጋሚ
በተከራዩት ልክ እንዲያስተካክሉ ወይም አስፋፍተዉ የያዙትን ተገቢዉን ኪራይ እንዲከፍሉ ሲነገርዎት ቆይቷል፡፡ ነገር
ግን ይዞታዉን አላስተካከሉም ወይም ለሚገለገሉበት ተጨማሪ ይዞታ ተገቢዉን ክፍያ አልፈጸሙም፡፡ በዚህም ታህሳስ 1
ቀን 2015 ዓ.ም. በተጻፈ ከታህሳስ 8 ቀን ጀምሮ አስፋፍተዉ የያዙትን ጭምር ተለክቶ በአንድ ካሬ ከቫት በፊት ብር
3,000 /ሦስት ሺ ብር/ ሂሳብ እንዲከፍሉ የተወሰነ መሆኑን እንዲያዉቁት ተደርጓል፡፡
እርስዎም በጽህፈት ቤት በመቅረብ አስፋፍተዉ የያዙት 173 ሜትር ካሬ ተቀንሶ 20 ካሬ ልክ እንዲሆን ስለጠየቁ
የያዙትን ይዞታ ወደ 20 ካሬ ዝቅ እንዲያደርጉና በካሬ ሜትር 2,700 /ሁለት ሺ ሰባት መቶ ብር/ ሂሳብ እንዲከፍሉ
በ 18/4/2015 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጾልዎታል፡፡ ነገር ግን ይዞታዉን ወደ 20 ካሬ ስላልቀነሱ እና በአጠቃላይ 173
ሜትር ካሬ እየተጠቀሙ ስለሆነ በ 26/8/2015 ዓ.ም. በያዙት ይዞታ ልክ ታስቦ ያለብዎትን ቀሪ ሂሳብ ከፍለዉ ቦታዉ
ለግንባታ የሚፈለግ ስለሆነና ግንባታ የሚጀመር ስለሆነ በቤቱ ዉስጥ የሚገኙትን ማሽኖች እንዳይበላሹ በ 15 ቀን ዉስጥ
እንዲያነሱ የሚፈለግብዎትን ቀሪ ሂሳብ በ 10 ቀን ዉስጥ እንዲያጠናቅቁ እና የተከራዩትን አንድ ክፍል ቤት አስፋፍተዉ
ከያዙት ይዞታ ጭምር ለቀዉ እንዲስረክቡ ዉሉ የሚቋረጥ መሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶዎታል፡፡ ይዞታዉን አልቀነሱም፤
ንብረቱን አላነሱም፤ በተጠቀሙበት ልክ የማስተካከያዉን ክፍያ ከፍለዉ አላጠናቀቁም፡፡
ስለዚህ ይማስጠንቀቂያ ከደረሰዎት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ 15 ቀናት ዉስጥ በያዙትና በተጠቀሙበት 173 ሜትር ካሬ
ልክ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት አስቀድሞ በደረሰዎት በካሬ ሜትር ብር 3,000 /ሦስት ሺ ብር/ ሂሳብ ከታህሳስ 08
ቀን 2015 ዓ.ም. በሚታሰብ ከፍለዉ ንብረትዎን አንስተዉ ለቀዉ እንዲያስረክቡ በዚህ ደብዳቤ አስቀድመን
እያስጠነቀቅን በዚህ መሠረት ባይፈጽሙ ግን ተገቢዉን ዳኝነት በመክፈል በፍርድ ቤት ክስ የምንመሠርት እና የጠበቃ
አበል የቴምብር ቀረጥ የፍርድ ቤት ክፍያ እና ልዩ ልዩ ወጪና ኪሳራ የሚጋለጡ መሆኑን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1771 እና
1772 መሠረት እናስጠነቅቃለን፡፡
ይርጋለም አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር

You might also like