2014 Preaching

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 10

ትፀኑ ዘንድ በእግዚአብሔር እመኑ!

የያዕቆብ መልእክት 1
1 የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም
ለእናንተ ይሁን።
2-3 ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና
ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፡፡
4 ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።
5 ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥
ለእርሱም ይሰጠዋል።
6 ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን
ማዕበል ይመስላልና።
7-8 ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ
አይምሰለው።
9-10 የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።
11 ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት
ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።
12 በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን
የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
13 ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ
ማንንም አይፈትንም።
14 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
15 ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።
16 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ/አትታለሉ/።
17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም
የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
18 ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
19 ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም
የዘገየ ይሁን፤
20 የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።
21 ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም
የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
22 ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
23 ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
24 ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
25 ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ
የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
26 አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ
አምልኮ ከንቱ ነው።
27 ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች
ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23


ስለ እምነት ስናነሳ በመጽሐፍ ቅዱስ ሶስት ሰዎች ያስገርሙኛል፡፡

1 ኛ አብርሃም ነዉ፡፡ የአብርሃምን እምነት እግዚአብሔር በፈተነዉ ጊዜ ዘፍጥረት 22 ላይ እንዲህ አለዉ የምትወደዉን
አንድ ልጅህን ይስሃቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ በሚነግርህ ተራራ ላይ ልጅህን ሰዋልኝ አለዉ፡፡

የሚገርመዉ አንድ ልጃቸዉን ይዞት ስወጣ አብርሃም ለወላጅ እናቱ ለሳራ እንከዋን አልተናረም፤ ነገር ግን ዛሬ የጉጉት
ልጃቸዉ የሆነ ይስሃቅ ልሰዋ ነዉ፡፡ ለምን ግን አብርሀም ዝምታዉን መረጠ?

 አብርሃም ጨካኝ ስለሆነ?

 አብርሃም የሰዉን አንገት ወቁረጥ እንደተራ ነገር ስለሆነበት?

ለምን በዝምታ ይዞት ሄደ ካላችሁኝ አብርሃም ልጁን ይዞት ሲወጣ በተነገረዉ ተራራ ላይ ሰዉቶ የልጁ ስጋ ወደ አመድ
ከተለወጠ በኋላ ባዶ እጁን እንደማይመለስ ጠንቅቆ ያምናል፡፡

አብርሃም ሠዋልኝ ያለኝኝ ጌታ አዉቀዋለሁ ከዚህ በፊትም ከሞቀ ከአባቶቼ መንደር ዉጣ ስለኝ ወጥቼ ያላየሁትን
አዲስ ነገር በሕይወተ ተደርጎ አይቻለሁ፤ አሁንም ዉጣና ወደ ሞሪያም ሂድ ካለኝ አንድ ሌላ አስገራሚ ታሪክ እንዳለ
አምናለሁ በማለት ነዉ፡፡

ዛሬ አንድ በእምነት ከ ሁኔታዉ ከታጠረበት፤ይመቸኛል ብሎ ካለበት በእምነት ለሚወጣ ሰዉ ቃል ልናገር ነዉ፤ ባዶ


እጅህን አትመለስም!!

አብርሃም የሚያምነዉ በዚህን ጊዜ እግዚአብሔር ከፈለገ አመዱን ሰብስቦ ካልሆነ ከላይ እንደ ሱፐር ማን አዝንቦ
ይሰጠኛል እንጂ…

ባዶ እጅሽን አትመለሽም!

ብዙዎች ስሰብኩ እኔም ለበርካታ ጊዜ ሲሰብክ አብርሃም ለሳራ ያልተናገረዉ እንዳትከለክለዉ ነዉ… ብያለሁ ይላሉ…

በፍፁም የአብርም እምነት ጥልቅ ነዉ! አብርሃም የሚያምነዉ እንደዚህ ነዉ፡፡

‹‹እኔና ሳራ ለልጅ የሚሆን ሆርሞን ማዋጣት በማንችለዉ ጊዜ በቃሉ ከሆነ ዘር ይስሃቅን ከሰጠን፤ በምንም
አይታማም››

አብርሃም ያመነዉ ባጭሩ በሙታን ትንሳኤ ነዉ!!

ሙት ማህፀንን ህያዉ ካደረገ……

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23


2 ኛ አስደናቂ ሰዉ 2 ኛ ነገስት 4፡1 ላይ ያለች ከነብያት ወገን የነበረችዉ ባልቴት ነች፤ይህች ሴት ኤልሳዕን
እንዳገኘችዉ ጩኸት አቀለጠችዉ፤

ስማኝ ባሌ አገልጋይ ነበር፤እግዚአብሔርንም ይፈራ ነበር፤ ባሌ አሁን ሞቷል፤ ሲሞት ግን 3 ነገሮችን ብቻ ትተዉልኝ
ነዉ የሞተዉ፡፡፡

1. ኛ ዕዳ
2. ልጆቼን ነዉ
3. አምላኩን ነዉ፡፡

አንተ ደግሞ ከነብያት አንዱ ነህ ስስተሙ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ ታዉቀዋለህ!

እኔ የሚለዉ ኤልሳዕ ባለሀብት ነዉ

ኤልሳዕ አራጣ አበዳሪ ነዉ ወይስ የሃገሪቱ ንጉስ ነዉ

እና እኔ ምን ላደርግ ነዉ! ልጆችሽ እንዳይወሰድ አኖይንትንግ ኦይል ልቀባባቸዉ ምን ላድርግ አይ በምንም መንገድ
ይሁን በምን አንተ ገንዘብ ይዘሕልኝ እንዳልመጣህ አዉቃለሁ፤ግን ዕዳዬ መከፈል አለበት፡፡

ማለት ባሌ ሲሰብክ ቢያንስ አዳምጨ ነበር እንዲህ ሲል‹‹ ፃድቅ ስጣል ዘሩም እህል ስለምን አላየሁም››

ሶ ዋት ልጆቼ አይጣሉም!

ባክህ ለአንድ አማኝ ልናገር ነዉ!

አትጣልም!

ኤልሳዕ አየና አሃ አንቺማ ግማሽ ስራን ጨርሰሽ ነዉ የመጣሽዉ፡፡ ታዲያ ምን አለ በቤትሽ?

በጣም ጥንጥ ዘይት ጭላጭ okay go to your neighbor and collect the jars?
What, why, how,when where የለም ማድጋዎችን ሰብስቢ፤ በዚያዉ በኋላ እንዳይቆጭሽ እንዳታስንሽ
…..
የአንዳንድ ሰዉ እምነትኮ ገላግሌ ነዉ! በቃ በእምነት ጨርሶ ነዉ ምጠጉት ከዚያም የእግዚአብሄር ሰዉ ዘይት
ይሙላበት ሲል….ካለበት ዘይት እየተ…..
የእኛዎቹ ነገርኮ ልክ እንደ ፈርዖን ሕልሙንም ትርጉሙንም አንተዉ ንገረኝ ነዉ የሚሉን፡፡
ፓስተር እንድትፀልይልኝ ፈልጌ ነበር okay በምን ጉዳይ ልፀልይ ታዲያ… አይ ጌታ ራሱ ይገልጥልሃል፡፡

እናስ በቃ አንተ ዝምብለህ አስባት እያልክ ፀልይልኝ!

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23


 እኔ እኮ እንዳንዶቹ የሚያየን የአገልግሎታችን መሠረት እንኳን የእነርሱ ርዕስ የሚመስላቸዉ አሉ፡፡
ኼረ እንተባበር ጎበዝ ልክ እንደዚህች ሴት What, why, how,when where ትተህ ጉዳይህን ተናገርና
ግማሽ መንገድ ና!

 3 ኛዋና የመጨረሻዋ እዚያችዉ ቀጥላ የሚትገኝ ሱኔማዊት ሴት ናት ይህችን ሴት ኤ ልሳዕ ለእነርሱ


ታደርግ የነበረዉን መልካምነት በማየት ለጉድለቷ ልፀልይ ባሰበ ጊዜ ልጅ እንደለላት ተናገረች፤
ተፀለየ ወለደች አደገ፤ከዕለታት አንድ ቀን ፤አባዬ ራሴን ራሴን አለ ለእናቱ አደረሱ እንዳቀፈችዉ
ሞተ፤እና ምን ሆነ ካላችሁኝ የዚህችንህን ሴት ታሪክ ማንም ወንድ አይደግመዉም እንኳን ወላድ
ሴት!
ወሰደችዉ በነብዩ አልጋ እንደ ጤነኛ ሰዉ አድርጋ አጋደመችዉ፤ ለባሏ አህያ ላክልኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰዉ
ሄዳለሁ አለች፤ እርሱ ቀኑ እሁድ አይደለም በሰላም ነዉ ልጁ ፕስ ነዉ ስላት ኸሬ የሆነች አጠር ያለች ጉዳይ
ከእርሱ ጋር አለኝ አለችና ሄደች፤ ልክ በሩቅ አያትና ግያዝ ሱኔማዊት መጣች ብሎ ሰላምታ አቀረበ ተጠጋት

ሰላም ነዉ ስላት ሰላም ነዉ ብላ አለፈችና የእግዚአብሔር ሰዉ እግር ይዛ……..

ግያዝ ይህንን ጉዳይ ጌታ ከእኔ ሰዉሮታል ስለዉ ኽሬ ምን ችግር ከኔ ትሰማ የለ፤፤


እንዲህ ነዉ ማመን በቃ!
ዛሬም በእምነት ና ኤልሳዕን የቀባ ጌታ ነዉ እኛን የቀባን እንጂ ዜኒት ተቀብተን አይደለም የሚናገለግለዉ፡፡
ወደ አነበብነዉ ክፍል ስገባ በአጭሩ
ጥቂት ወሳኝ ነጥቦችን ላንሳ!
 በእምነት እንቅስቃሴያቸዉ ምክንያት ተሰደዉ በምድረ በዳ እየተንከራተቱ የተለያየ ፈተና
በኢየሩሳለም እየቀመሱ ያሉ ሰዎች ናቸዉ፡፡
 እነኚህን ሰዎች በዚህ ሁኔታ ዉስጥ ያዕቆብ አግኝተዉ አይዟችሁ ጌታ እኔ አለሁላችሁ ይላል
የመንከራተት ዘመን በቃ ይላል አይደለም ያለዉ!

 ከዚህ በኋላም ልዩ ልዩ ፈተና ስለሚደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፤ ማለት? ይህ ፈተና ተራ


ፈተና አይደለም፡፡ ዛሬ ሰባኪዉ ያዕቆብ ነዉ!
 አንዳንድ ፈተና ቤተሰብህን ነክቶ ብቻ ነዉ የሚያልፈዉ

 አንዳንዱ ደግሞ ክስህን ብቻ

 አንዳንዱ ደግሞ የስራ ቦታህን

 አንዳንዱ ደግሞ ጤናህን

ይኽ ፈተና ቀላል ነዉ

ቤተሰብ ቢበተን በሽማግለ በምንም ይመለሳል፡፡

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23


ክስህ ብጎድል የሆነ ጊዜ ላይ ሞልቶ ይፈሳል

ከአንዱ ስራ ቢትባረር ሌላኛዉ ይጠብቅሃል

ዛሬ ብትታመም ነገ ትድናለህ!

አንዳንድ ፈተና ግን ከዚህ ያለፈ ነዉ እምነትህን ለመንካት ነዉ የሚመጣዉ፡፡

እንዲህ ዓይነቱን ፈተና ብዙዎች ከመፅሐፍ ቅዱሳችን ተፈትነዋል ኢዮብ ግን ያስደንቀኛል፤ ከአብርሃም ቀጥሎ

ኢዮብ በሃብት ተፈተነ መዝሙሩን ቀጠለ

በግመሎች ተፈተነ መዝሙሩን ቀጠለ

በልጆቹም ተፈተነ መዝሙሩን ቀጠለ

በጤናዉ ተፈተነ መዝሙሩን ቀጠለ

አንድ አባል ግን በፍቃደኝነት ባክ አደረገ ምስቱ!

‹‹ እስከ ምን ድረስ ታምነዋለህ ስለዉ ቢሞት እንኳ ሲል..››

መከራዎቹ ተሰባስቦ ተመካከሩ ይህ ሰዉ ገገማ ነዉ አሉት ተጠራርተዉ እንደመጡ ተጠራርጎ ጠፉ!

እመን እንጂ ልክ እንደ ኢዩብ ተሳስቦ/ተጠራርተዉ/ የመጡብህ መከራ ተጠራርጎ ይጠፋል!!!

 እኛ ይህ እምነታችንን የሚፈትን ፈተና ለምን መጣ ሲሉ በሕይወታችሁ አንድ ድንቅ ማዕረግ ልጨምርላችሁ


ነዉ፤ ምን ትዕግስትን ይጨምርላችሁ ዘንድ ነዉ፡፡
 በክርስትና ሕይወት ዉስጥ ዕድገት ያስፈልጋል የሚናድገዉ ደግሞ በእምነት እንጂ በቁመት አይደለም!
ወታደር ማዕረግ ሲሰጥ ከትምህርት በተጨማሪ ከሚታየዉ ኩዋሊቲ አንዱ ታጋሽ ታታሪነት ነዉ አለኝ አንድ ወዳጄ!

ኮንስታብል ሆኖ ታጋሽና ታታሪ ከሆነ አስር አለቃ……ጀነራል ድረስ ይሰጠዋል!

አንዳንዱ ግን ማዕረጉም ሳያድግ ጊዜዉም ሳይገፋ በጊዜ ጡረታ ይደርስበታል!

ምንድር ነዉ ምክንያት ስል አይ ራስህን በወታደር አለም ዉስጥ ራስህን በየጊዜ በሚሰጠዉ ፈተና ዉስጥ ማሳደግና
ማሻሻል አለብህ አለኝ፡፡

እምነት ልኖረን ይገባል! ቁሳዊ ነገር ላይ ብቻ ያልተንጠለጠለ…ዘልቆ የሚያይ!

ልክ እንደ አብርሃም

‹‹ ሮሜ 4፡3 ዘፍ 15፤6‹‹ አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት›› ይላል፡፡


እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23
ምን ማለት ነዉ!

ወገኖቼ አንድ ነገር እንድታዉቁ እወዳለሁኝ ‹‹ የሰማይ ቢዝነስ የሚሰራ በእምነት ነዉ!

This is how Devine business works!

ከአንተ የሚገኝ በእግዚአብሄር ፊት ዋጋ የሚኖረዉ ምንድር ነዉ?

እምነት ብቻ!
ኤፌ 1፡3 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ
አንተ ታምናለህ ……እርሱ ደግሞ ፅድቅ ይሰፍርልሃል!
በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
አባትና አምላክ ይባረክ፡፡
ስለምኑ……በአይን ያልታየዉ….

1 ኛ ቆሮ…..2፡9 ከ ያዕ 1፡16 ጋር እናስተያይ!

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23


መሠረታዊ የክርስቲና
አስተምህሮ
/የደኅንነት/
ትምህርት
እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23
ይህ መሠረታዊ ክርስቲና አስተምሮ መጽሐፍ የተፃፈዉ፡ -
በወዳጁ ወንድማችን ፓስተር ሳሙኤል ሳላቶ ነዉ፡፡

ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን በመጽሐፉ ይዘት፤በአስተምሮት ጥራት እና


በመለዕክቱ ግልፀኝነት ሙሉ በሙሉ ታምናለች፡፡

ስለሆነም ይህንን መጽሐፍ ለቤተ-ክርስቲያኒቱ የደህንነትና መሠረታዊ አገልግሎት ትጠቀማለች፡፡

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23


ህዳር/2014 ዓ.ም

ደስታችሁን ቅርብ ቦታ አታስቀምጡት

 ደስታና ብርጭቆ ተመሳሳይ ናቸዉ፡፡


ብርጭቆ ፅዱና ምቹ ሆኖ ስታዩት እጅግ ያስደስታል፤አንዳንድ ብርጭቆ ያልጠማዉንም ዉኃ ጠጣበት
ጠጣበት ያሰኛል፡፡
ነገር ግን ምንም እንኳ የሚያጓጓ ቢሆንም አያያዝና አቀማመጥ በጥንቃቄ ልሆን ይገባል፡፡
ብርጭቆ ሕፃናት በሚነኩበት አይቀመጥም፤ በሚታይ ነገር ግን በቀላሉ ሕፃናትም ቆሻሻም በማይነካ ቦታ
ይቀመጣል፡፡
የሰዉ ልጅ ደስታም እንደዚህ ነዉ! ደስታችሁን ሰዉ ሁሉ እንድያይላችሁ ይፈልጋል፡፡ ከሃዘንተኛ ሰዉ ይልቅ
ደስተኛ ሰዉ የሰዉን ልጅ ትኩረት የመሳብ አቅሙ ከፍተኛ ነዉ፡፡
ታዲያ ይህንን ደስታ አንድ ሰዉ በዉድ ዋጋ የገዛትን ያችን ብርጭቆ ለቤቱ ማሳመሪያ ሰዉ ሁሉ
በሚያይበት፤ቆሻሻም በማይነካበት፤ደጋግመህ እይ እይ በሚያሰኝ ከፍ ባለ ቦታ ላይ እንደሚስቀምጥ
ደስታችሁን አላፊ አግዳሚ በማይነካበት፤ከፍ ባለ ቦታ አስቀምጡት፡፡
እርሱ ከፍ ያለ ቦታ ዬት ነዉ?

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ/አትታለሉ/።


17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም
የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
ሰኞ አስቆ ማክሰኞ የማይሄድ፤ በጋ መጥቶ ከረምት የማይሄድ፤
ነብዩ ስኖር ልሳን የሚያናግር እነርሱ ስሄዱ ደግሞ ብሶት የሚያናግር መንፈስ/ደስታ እርሱ ትክክለኛ
አይደለም፡፡
እኛኮ በቃ ጌታ ከዛሬ ጀምሮ ሳቅ በሳቅ አደረኩሽ እስኪ ሳቂ ስንል
በለለ…ኪኪኪኪ
ግን ልክ ከቸርች እንደወጣች ለቅሶ……
ለምን ቀድሞም የሳቀችዉ እዉነተኛ ሳቅ የሆነዉን ክርስቶስን ሰምታ ሳይሆን ትላንት በሰፈርሽ
ያገላመጠሽ ሰዉዬ/እዚያ ጎረቤት ያለ ምናምን በቃ ተገልብጧል፡፡ ስለተባለች ነዉ!

ሳቁ እዉነተኛ የሳቅ ምንጭ ከሆነ ከጌታ ከኢየሱስ ከሆነ ግን …..


ማዘን እያለብህ ለምን ትስቃለህ ይሉኛል እንዳልስቅ

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23


እንኳንስ የሚያዩኝ እነም ያስቀኛል ለምን እንደምስቅ
ያለሁበት ዓለም ለቅሶ አይታወቅም
በፈረቃ አልቅሸ በፈረቃ አልስቅም
ኢየሱስ የዘላለም ነዋ
ኢየሱስ ሳቄ ነዋ!

ቃሉ ስናገር ፍልጵስዩስ 4፡7 እንዲህ ይላል

6 ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን


አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።
7 አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ
ይጠብቃል።
የአንዳንድ ሰዉ ደስታ ያለዉ ክስ ዉስጥ ነዉ!

የአንዳንዱ አካዉንት ዉስጥ ነዉ!

የአንዳንዱ አሜሪካ ነዉ!

የአንዳንዱ ካዝና ዉስጥ ነዉ!

የአንዳንዱ ሱቅ ዉስጥ ነዉ!

የአንዳንዱ መኪኖቹ ላይ ነዉ!

ኪሱ ስከሳ አብሮ የሚከሳ

ባንኩ ስቃጠል አብሮ የሚቃጠል

ዶላሩ ስቆም አብሮ የሚቆም

የኛ ግን ብል በማይበላበት ሌባ በማይሰርቅበት………….በክርስቶስ ነዉ!

ስማ ሁኔታ ያሳቃቸዉ በሁኔታ ያለቅሳሉ

ጌታ ያሳቃቸዉ በምንም አይናወጡም!

እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1 ኛ ቆሮ. 1፡23

You might also like