Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

ክፍል አንድ

የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተከታታይ ትምሕርት በዲያቆን ፍቅረ አብ እነሆኆ ዛሬ ግንቦት 1 ተጀመረ እስከ መጨረሻው
ያፀናን ዘንድ መልካም ፍቃዱ ይሁንልን !

መልካም ትምህርት!!!

ማሳሰቢያ

ሼር የማያረግ አያንብ ለእራሱ አውቆ ለሰው የማያሳውቅ ባያውቅ ይሻላል ተማሩ አስተምሩ!!

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✝

💒ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን💒

ትርጉም

ሥርዓት ማለት " ሠርአ ሠራ" ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ የምዕላድነት ዘር ያለው ስም ነው።

ትርጉሙ፦ ሕግ፣ደንብ፣አሠራር፣መርሐ ግብር ማለት ነው።

ቤተ ክርስቲያን ማለትም ሁለት ትርጉም ያለው በዘርፍና በባለቤትነት የተቀመጠ ስም ነው።

፩ ትርጉም ፦ የክርስቲያን ቤት፣የክርስቲያን መሰብሰቢያ፣የክርስቲያን መገኛ ማለት ነው።ይህም ማለት ክርስቲያኖች


በአንድነት በመሰብሰብ የሚፀልዩበት ፣ቅዱስ ጋውን እና ቅዱስ ደሙን የሚቀበሉበት ፣ የሚሰግዱበት ፣ከእግዚአብሔር
ጋር የሚገናኙበት ቦታና የፀሎት ቤት ማለት ነው።

ጥቅስ በቅዱስ መፅሀፍ

፩ ኢሳ 56፦7 ፪ ኤር 7፦10-11

፫ ማቴ 21፦13 ፬ ማር 11፦17

፭ ሉቃ 19 ፦46 አንብቡ።
፪ ትርጉም የክርስቲያን ወገን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የሚጠራበት ስም ነው ።"ቤተ እስራኤል ፣ቤተ ያዕቆብ ፣ቤተ
አሮን"ሲል የእስራኤል ወገን ፣የያዕቆብ ወገን ፣የአሮን ወገን ማለት እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን ማለትም የክርስቲያን ወገን
ማለት ነው።

ጥቅስ የተወሰኑ

፩ መዝ 117፦3 ወይም መዝ 113 ፦1

፪ ማቴ 16፦18 ወይም 18፦17

፫ የሐ.ሥ 18፦22 ወይም 20፦38

አንብቡ

በአጠቃላይ አነጋገር የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ወይም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲባል ግን የቤተ ክርስቲያን ሕግ የቤተ
ክርስቲያን ቀኖና የቤተ ክርስቲያን የአሰራር መርሐ ግብር ማለት ነው።

የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጥልቅ እና ምጡቅ የሆነውን የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በመጠኑም ቢሆን
ለመማርና ለማስተማር ለማወቅና ሥርዓቱን ለመፈፀም ለሚችሉ ሁሉ የሚረዳ ነው።

💒የሥርዓተቤተ ክርስቲያን ምንጮች💒

፩ መፃሕፍተ ብሉያት

፪ >> ሐዲሳት

፫ የሐዋርያት ሲኖዶስ

፬ ሥርዓተ ፅዮን

፭ አብጥሊስ

፮ ትዕዛዝ

፯ ዲድስቅልያ

፰ ፍትሕ መንፈሳዊ

፱ የ 3 ጉባኤያት ( የኒቅያ፣ የቁስጥንጥንያ ፣ የኤፌሶን ውሳኔዎች )

፲ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
፩፩ በ 4 መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን በየጊዜው የተነሱት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የፃፏቸው ልዩ ልዩ የስርዓት
መፃሕፍት ናቸው።

አንብቧቸው

ሁሩ ወመሀሩ ውስተ ኩሉ አፅናፈ አለም እንደተባለ እናንተም አስተምሩ ።

ብዙ ስርአቶችን እንመለከታለን ለዛሬው

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን

የእናንተ አስተያየት እኔን የበለጠ እንፅፍ ያደርገኛል ስለዚህ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ ይኸው ሊንኩ ላኩልኝ።

@seratbetkrestiyan_bot

@seratbetkrestiyan_bot

@seratbetkrestiyan_bot

ኑ እንሰባሰብ

ለመቀላቀል ሊንኩን ይንኩ

አዘጋጅ ✍#ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚

💛 @seratebtkrstian 💚

💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍

You might also like