Professional Documents
Culture Documents
(Then) (There) ?
(Then) (There) ?
1
መቼ ተፃፈ? - የጊዜ አመልካች ማን? /ተናጋሪው ማነው/? የሚነገርለትስ?
ማን ፃፈው? - የጸሐፊውን አመልካች ምን? ርዕሱ ምንድነው ቅደም ተከተሉስ?
ለማን ተፃፈ ?- ተደራሲያንን አመልካች የት? ድርጊቱ እየተከናወነ ያለው የት ነው?
የት ተፃፈ ? - የቦታ አመልካች መቼ? ድርጊቱ የተፈፀመው መቼ ነው?
እንዴት ተፃፈ? - ሁኔታን አመልካች እንዴት? የተደረሲያን ምላሽ እንዴት ነበር?
2
ክፍሉ ለዛሬው ምዕመን ምን ትምህርት ይሠጣል?
ማህበራዊና ታሪካዊ ትችት/Socio-historical criticism/
የመጽሐፉ ክፍል በተጻፈበት ዓውድ/ዓለም ውስጥ በመሆን የክፍሉን አሳብ መረዳት እንድንችል ያደርገናል፡፡
በጊዜ ብዛት የተሸፈነውን/ምሥጢር የሆነውን ባሕላዊውን ዓለም ቆፍረው እንዲደርሱበትና እንዲያገኙ ማህበራዊና
ታሪካዊ ትችት ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡
የቀደሙቱ ባለታሪኮች የነበሩበትን
3
1 በዓውዱ ብርሃን መተርጎም
ከክፍሉ ውጪ ያለው ዓውድ /external context
የክፍሉ ዓውድ /internal context
በዚህ ጊዜ ራስን መጠየቅ የሚገቡ ጥያቄዎች ፡-
ካለሁበት ባህል ጋር የክፍሉ አሳብ ምን ያህል ይስማማል/ ክፍሉ የሚናገረው ነገር የታወቀ ነውን?
ሌሎች አንባቢያን እንዴት አድርገው ተርጉመውታል?
4
ልንመለከታቸው የሚገቡን ነገሮች:-
የመጽሐፉ ክፍል አከራካሪ ነው /argumentative?
ስላቅ አለው /satirical?
የሚያዝናና ነገር አለው/አዝናኝ/ entertaining?
ሥነ-ምግባራዊ /didactic?
ገላጭ/ምሳሌአዊ/ illustrative?
5
ለጥሩ ሐቲትና በዚያዉም መጽሐፍ ቅዱስን በተሻለ ማስተዋል ለማንበብ ቁልፍ ነገር
ምንባቡን በጥንቃቄ ማንበብና
ስለ ምንባቡ ትክክለኛ ጥያቄዎችን መጠየቅ መቻል ነዉ፡፡
ከአዉደ ንባቡ
ከይዘቱ
ከዓዉዳ ንባብ የሚዛመዱ ጥያቄዎች ደግሞ
ታሪካዊና
ሥነ ጽሑፋዊ ተብለዉ በሁለት ይካፈላሉ፡፡
1 ታሪካዊ ዓዉዳ ንባብ
ከመጽሐፍ መጽሐፍ የሚለያየዉ ታሪካዊ ዓዉዳ ንባብ ከአያሌ ነገሮች ጋር ይዛመዳል፡፡ ከእነዚህም መካከል
6
እንዲህ ዓይነቱ ሰነድ እንዲጻፊ ያደረገዉ የዚያን ጊዜ የእስራኤል/የቤ/ክ ሁኔታ ምን ነበር? ለሚሉ ጥያቄዎች
አሳብ ማግኘቱ አስፈላጊ ነዉ፡፡
ይህ ጥያቄ ከአንዱ ሥነ ጽሑፋዊ ቅርጽ ወደ ሌላዉ ስንሄድ የሚለያይ ቢሆንም ሁል ጊዜም ወሰኝ ጥያቄ
ነዉ፡፡
የሐቲት ዓላማ
መጽሐፉን የጻፈዉ ሰዉ ለማስተላለፍ የፈለገዉን መልዕክት ማግኘት ነዉ፡፡
አንደኛ ተግባር የይዘት ጥያቄዎች፡-
በተጨማሪም “ታሪካዊ ዓዉደ ንባብ” ከሚለዉ ሥር የተጠቀሱትን ነገሮች ያካቲታል፡፡ ከእነዚህም መካከል
እንደ ዲናር ፤
የሰንበት መንገድ ወይም
“የከፍተኛ ቦታዎች” ፤ወዘተ…ፍቺዎች ለአብነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
በአብዛኛዉ እነዚህ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ የሚቀርቡ የፍቺ ጥያቄዎች ናቸዉ፡፡ ጳዉሎስ በ 2 ኛቆሮ.5፡16
ላይ “ክርስቶስንም በሥጋ እንደሆነ ያወቅነዉ ብንሆን እንኳ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ
7
አናዉቀዉም” ሲል የጻፈዉን በሚያነብበት ጊዜ “በሥጋ” የተባለለት ማን ነዉ? ክርስቶስ ነዉ ወይስ እርሱን
የሚያዉቀዉ ሰዉ? ብሎ መጠየቅ አለበት፡፡
ጳዉሎስ ክርስቶስን የሚናዉቀዉ “ከዓለማዊ አስተሳሰብ አንጻር አይደለም” ለማለት የፈለገዉ አሳብ
አሁን ክርስቶስን የምናወቀዉ “በምድራዊ ሕይወቱ አይደለም” ከሚላዉ ፍጹም የተለየ ነዉ፡፡
እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን ለመመለስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወጭ ሌላ እገዛ ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም አንድ ሰዉ
ለእንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎች የሚሰጣቸዉ መልሶች ጥራት በሚጠቀሚባቸዉ ምንጮች ጥራት ላይ
ይወሰናል፡፡
ምንም እንኳ ሥነ አፈታት የሚለዉ ቃል ሐቲትን ጨምሮ ሁሉንም የትርጉም መስክ የሚያጠቃልል ቢሆንም
ጥንታዊ ምንባቦች ለአሁኑ ዘመን ስለሚኖራቸዉ ተዛምዶ በሚያስረዳ ጠበብ ያለ አገባብም ያገለግላል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጽሁፍ ዉስጥ ቃሉን የሚንጠቀመዉ “እዚህ አሁን” መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? በሚላዉ
አሳብ ዙሪያ የሚነሱትን ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ነዉ፡፡
አንድ ሰዉ በእዚህና አሁን የማይጀምርበት ምክንያት ተገቢዉ የአፈታት ጥበብ ቁጥጥር የሚገኘዉ
የመጽ/ቅዱስ ምንባብ በተጻፈበት የመጀመሪያ አሳብ ዉስጥ በመሆኑ ነዉ
8
የይሖዋ ምስክሮች የክርስቶስን አምላክነት መካዳቸዉ፣ወይም
በማር 16፡18 ን መሠረት በማድረግ እባብ የሚይዙ ሰዎች፣ወይም
የብልጽግና ሰባኪዎች በ 3 ኛዮሐ 2 ላይ ተመስርተዉ የሚያስተላልፉት ትም/ት የተዛባ አተረጓጎምን የተከተለ ነዉ
የእያንዳንዳቸዉ ስህተት የተንጸባረቀዉ ስነ አፈታት ላይ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ የአፈታት ጥበባቸዉ በጥሩ
ሐቲት ቁጥጥር ያልተደረገበት መሆኑ ነዉ፡፡
የወይይት ጥያቄ
ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እየጠመዘዙ እንዳሻቸዉ የሚተረጎሙባቸዉ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች
የትኞቹ ናቸዉ? ክፍሉን ምን ብላዉ ይተረጉማሉ?
አንድ ሰዉ ዮፍታሔ እንዳደረገዉ የሞኝነት ስለት ተስሎ ልጁን እንዳይገድል (መሳ.11፡29-40) ወይም ሴቶች
ፀጉራቸዉን ከኋላ እንዳያጎፈሩ (በማርቆ.13፡15 “ከሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይዉረድ” ስለሚል)
የሚከለክላቸዉ ምንድነዉ?
በእርግጥ ማንም ሰዉ እንዲህ ዓይነቱን የሞኝነት ተግባር እንዳይፈጽም የጋራ ግንዛቤዉ ማድረግ
ይረደዋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለራሳችን ምን እንደሚል ለማወቅ እንፈልጋለን፡፡
ነገር ግን ደስ ያለንን እንድል አድረገን ስናበቃ መንፈስ ቅዱስን “ተጠያቂ” ልናደርገዉ አንችልም፡፡
የመጀመሪያዉን አሳብ ያስተላለፈዉ እርሱ ነዉና ፡፡
ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ ለእኛ የሚያደርግልን እገዛ የመጀመሪያዉን ፍቺ እንድናገኝ መርዳትና
የተገኘዉን አሳብ ከሁኔታችን ጋር ለማዛመድ በታማኝነት በምንጣጣርበት ጊዜ ከጎናችን መቆም ነዉ፡፡
አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ መጀመሪያ ያላስተላለፈዉን መልዕክት ዛሬ ሊያስተላፍ
አይችልም፡፡
በሌላ አገላለጽ ለእኛ እንደሚተላለፈዉ እዉነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ፍቺ
እግዚአብሔር መጀመሪያ በተናገረበት ጊዜ እንዲተላለፍ የፈለገዉ ነዉ፡፡
ይህ የመነሻ ነጥብ ነዉ፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ አሳብ ትክክለኛነት የሚያጸድቀዉ ማን ነዉ?
በእግዚአብሔር ቦታ የሚወስነዉ ማን ነወ?
በዚህ ጉዳይ ላይ
የሮም ካቶሊካዊት ቤ/ክ ይፋዊ አስተምህሮ የምንባብን የተሟሉ ፍቺዎች ሁሉ ይወስናል፡
ፕሮቴስታንቶች ግን እንዲህ ዓይነት ሥልጣን-አዘል አካል ስሌለለን አንድ ሰዉ የጠለቀ መልዕክት
እንዳገኘ በሚነገርበት ጊዜ በጥንቃቄ ልንይዘዉ ይገባል፡፡
በተለይም የተጠቀሰዉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አሁን ተገኘ የተባለዉን ፍቺ የማይሰጥ ከሆነ ጥብቅ
ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ነዉ፡፡
እጅግ ብዙ ኑፋቄዎች የተከሰቱት በዚህ መንገድ ነዉ፡፡
9
በእብራይስጥ
አረማይክና
በፅርዕ (በግሪክ)
በአብዘኛዉ የብሉይ ኪዳን ክፍል በእብራይስጥ፤
የዳንኤል ግማሽና ከዕዝራ 2 ምንባቦች የዕብራይስጥ እህት ቋንቋ በሆነዉ በአረማይክና
ጠቅላላዉ አዲስ ኪዳን በፅርዕ (በግሪክ) ተጽፎአል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት የሚያስፈልገዉ በተጣራ ሁኔታ ከእነዚህ
የሰነድ ጥያቄ
የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዉ የመጀመሪያዉ ጭንቀት
እርሱ የሚጠቀምበት የዕብራይስጥ/የፅርዕ/ግሪክ ቃል ከጸሐፊዉ ብዕር
ከፈለቀዉ/እየተናገረዉ ከሚጽፍ ሰዉ ከወጣዉ የመጀመሪያዉ ቃል ጋር የሚቀራረብ
መሆኑን ማረጋገጥ ነዉ፡፡
ምንም እንኳ በብሉይና አዲስ ኪዳን መካከል የሰነድ ችግሮች የተለያዩ ቢሆኑም መሠረታዊ
ጉዳዮች ተመሳሳይ ናቸዉ፡፡
የመጀመሪያ ሰነዶች በእጃችን የሉም፣
ምንም እንኳ አብዘኛዎቹ የብሉይም ሆኑ አዲስ ኪዳን መጽሐፍት ሰነዶች ከመካከለኛዉ ዘመን
የኋለኛዉ አጋማሽ ቢመጡና ተመሳሳይነት ቢኖራቸዉም እነዚህ የኋለኞቹ ሰነዶች ከቀደምት
ቅጂዎችና ትርጉሞች በከፍተኛ ደረጃ ይለያሉ፡፡
10
ጥንታዊዉ መረጃ በሌሎች ጥንታዊ የሮም ግዛቶች ተመሳሳይ የዕድሜ አቻዎች
ሲጠናከር፤መረጃዉ እንደ ወሳኝ ይቆጠራል፡፡
ዉስጣዊ መረጃ ከጻሐፊዎችና ከገልባጮች ጋር የተያያዘ ነዉ፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች
ሁለት/ከዚያ በለይ የተለዩ ምንባቦች በሚያጋጥሟቸዉ ጊዜ በአብዘኛዉ የትኞቹ
ስህተት እንደሆኑ ያዉቃሉ፡፡
ለዚህም ምክንያቱ ምሁራን የገልባጮችን ልማዶችና ዝንባሌዎች በጥንቃቄ በማጥናት
ሊያዉቋቸዉ መቻላቸዉ ነዉ፡፡
በላቲንና በኋለኞቹ የፅርዕ ትርጉሞች ዉስጥ ሊካተት የቻላዉ ከቁጥር 27 ተወስዶ ነዉ፡፡
11
የቋንቋ ጥያቄ
ታሪካዊ ርቀት፡- ይህ
በቃላት
በሰዋሰዉና
በፈሊጣዊ አነጋገሮች ረገድ
በመነሻ (በመጀመሪያ) ቋንቋና
በተቀባይ ቋንቋ መካከል የሚገኙትን ልዩነቶች የሚያሳይ ነዉ፡፡
ቃል በቃል፡-
12
የመነሻዉ ቋንቋ ቃላትና ሐረጎች ስሜት በሚሰጥ መልኩ በተቀባይ ቋንቋ ዉስጥ ቃል
በቃል እንዲተላለፉ የሚደረግበት አተረጓጎም ነዉ፡፡
ቃል በቃል ትርጉም ታሪካዊ ርቀቱን እንዳለ ጠብቆ ያሸጋግራዋል፡፡
ነፃ፡-
የመጀመሪያዉን ትክክለኛ ቃላት ለመጠበቅ ሳይጨነቁ አሳቡን ብቻ ለማስተላለፍ
የሚደረግ ጥረት ነዉ፡፡
ነፃ ትርጉም በተቻለዉ መጠን ታሪካዊ ርቀትን ለማስወገድ ይጥራል፡፡
አቻዊ ተዛምዶ፡-
ይህ የመነሻዉን ቋንቋ ቃላት ፈሊጣዊ አነጋገሮችና ሰዋሰዋዊ መዋቅሮች በተቀባዩ ቋንቋ
አቻዊ አገላለጾች ለመተካት ጥረት የሚደረግበት አተረጓጎም ነዉ፡፡
እንዲህ ዓይነቱ አተረጓጎም የታሪካዊና ሐቃዊ ጉዳዮችን ታሪካዊ ርቀት እንዳለ ሲጠብቅ የቋንቋ
፣የሰዋሰዉና የስልት ጉዳዮችን ከተቀባይ ቋንቋዉ ጋር ያዛምደዋል፡፡
ሮቤርት ያንግም በ 1862 ባሳተመዉ ቃል በቃል ትርጉሙ (1 ኛቆሮ.5፡1 ን) “በእናንተ መካከል ግልሙትና
እንዳለ ይወራል፤ እንዲህ ዓይነቱ ግልሙትና በአሕዛብ መካከል እንኳ አልተሰማም፤ የአባቱን ሚስት
የወሰደ ሰዉ በእናንተ ዘንድ አለና (!)”ሲል ተተርጉሟል፡፡
13