Professional Documents
Culture Documents
Practic
Practic
10/01/2016 ዓ.ም
ሰንደፋ ኢትዮጵያ
1
ምስጋና
በመጀመሪያ ለሁለም ነገር ስኬት ላበቃኝ ለዓለማቱ ጌታ ለሆነው ለአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ምስጋና ይገባው ።በመቀጠል
ለኢ/ፖ/ዩኒቨርሲቲ መምህራን ፣ለመስክ አሰልጣኞቼ ፣ጓደኞቼ እና ለቪ አይ ፒ እና ዲ/ጥ/ፖ/ መምሪያ ሬጅመንት 1 ሻንበል
1 ለሚገኙት አመራርና አባላት ከልብ የመነጨ ምስጋና ላቀርብ እወዳለሁ።
i
የተግባር ሌምምዴ ሪፖረት 2015
ዓ.ም
ማውጫ
ርዕስ ገፅ
1. መግቢያ.......................................................................................................................................4
2. የተለማመዱበት ቦታ አጠቃላይ መግለጫ/የሰሩበት የፖሊስ ተቋም አደረጃጀት...............................................5
3. በየስራ ክፍል ያለው የፖሊስ አባላት ብዛት...........................................................................................6
4. የተግባር ልምምድ ቦታ አዘውትሮ የሚፈፀሙ የወንጀል አይነቶች በቅደም ተከተል 10
5. የሚፈፀሙ ወንጀሎች መንስኤዎቻቸዉ እና እነዚህ ወንጀሎች ያስከተሉት ችግር...............................................11
5.1 የሚፈፀሙ ወንጀሎች መንስኤዎቻቸው፡...........................................................................................11
5.2 ወንጀሎቹ ያስከተሉት ችግር:........................................................................................................12
6. በልምምድ ወቅት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት........................................................................................13
6.2 በወንጀል መከላከል በቪአይፒ እና ዲፕሎማቲክ መምሪያ በሬጅመንት አንድ በሻምበል አንድ አራት የተከናወኑ
ተግባራት.......................................................................................................................................13
7. በዋና ዋና ተግባራት ክንውን የተገኘው ትምህርት/Lesson/.........................................................................14
7.1 በወንጀል መከላከል መስክ በቪአይፒ እና ዲፕሎማቲክ ፖ/መምሪያ በሬጅመንት አንድ ሻምበል አንድ የተገኘ
ትምህርት፡.....................................................................................................................................14
8. በንድፈ-ሀሳብና በተግባር መካከል ያለው ልዩነት፡.....................................................................................15
9. ህብረተሰቡ በፖሊስ ስራዎች ላይ ያለው ተሳትፎና እገዛ..............................................................................16
10. አባሎች እና አመራሮች ህገ-መንግስቱን እና ሌሎች ህጎችን በማክበርና በማስከበር የፖሊስን ስራ የመፈፀም ብቃት....17
11. የአባሎች እና የአመራሮች ፖሊሳዊ ዲሲፕሊንና ስነ-ምግባር ሁኔታ...............................................................18
12. በልምምድ ወቅት ዕጩ መኮነኑን ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች......................................19
13. በልምምድ ቦታ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች..............................................................................................22
14. የመፍትሄ ሀሳቦች /Recommendations/.........................................................................................22
15. ማጠቃለያ....................................................................................................................................24
16. ዋቢ መረጃዎች..............................................................................................................................24
1. መግቢያ
በሀገራችን ኢትዮጵያ የወንጀል አይነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመምጣቱ እና የአፈፃፀም ዘዴው ውስብስብ እና
ዘመኑ ባፈራቸው የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በመታገዝ የችግሩን አስከፊነት በመቀነስና ከዘመኑ ጋር የዘመነ የፖሊስ ሃይል
ለማፍራት መንግስት በያዘው እቅድ መሰረት የ 13 ኛ ዙር ድህ-ምረቃ ፕሮግራም ዲፕሎማ ዕጩ መኮነኖችን ተቀብሎ
በማስተማር ላይ ይገኛል ፡፡ይህንን ተከትሎ ከ 1 ዓመት ትምህርት እና ስልጠና በኋላ የተግባር ልምምድ በወንጀል
መከላከል ዋና መምሪያ ቪ አይ ፒ እና ዲ/ጥ/ፖ/መምሪያ ማለትም በወንጀል መከላከል የስራ ዘርፍ በተለያዩ የስራ መስኮች
ለአንድ ወር ከ 9 ቀናት የተግባር ልምምድ እያደረኩ በእለት ተእለት ያከናወንኳቸውን የስራ ክንውን የሚገልፅ ሪፖርት
ነው።
ከነዚህ የሰው ሃይል ዉስጥ 4 ወንድ እና 01 ሴት ከጅ ሲሆን እስረኛ 1 የታገደ 5 በተጨባጭ በስራ ላይ ያለው ወንድ 68 እና
ሴት 7 በድምሩ 75 ናቸው፡፡
2. ሻንበል ምክትል 01 - 01
3. ሻንበል አስተዳደር 01 01
4. ሻንበል ግልጋሎት 01 01
5. ሃይል አስተዳደር/ ሃላፊነት 02 02
የሌላቸው/
6. መቶ አዛዥ 04 - 04
7. መቶ ምክትል 03 01 04
8. መቶ አስተዳደር 03 03
9. ጓድ መሪ 09 03 12
10 ጓድ ምክትል 12 12
11 ቲም አዛዥ/ በአሁኑ ያላደጉ/ 08 08
12 ቲም ምክትል 06 01 07
/በነበሩበት/ያላደጉ
13 አባል 31 4 35
ጠ/ ድምር 82 9 91
2. ዋ/ኢ/ር 01 01
3. ኢ/ር 01 - 01
4. ም/ኢ/ር 07 07
5. ዋ/ሳጅን 15 15
6. ሳጅን 16 02 18
10. ወላይታ 05 - 05
11. ሃድያ 06 01 07
12. ከምባታ 03 - 03
13. ጉራጌ - - -
14. ጋሞ 01 01 02
15. ከፋ 01 01 02
16. ቤንች - - -
17. ኙዌር - - -
18. ዳውሮ 01 - 01
19. ባስኬቶ 01 - 01
20. ኮንታ 03 - 03
21. በርታ - - -
22. ጌድዮ - - -
23. አሪ 02 01 03
24. ስልጤ 01 - 01
25. አገው 01 - 01
ጠ/ድምር 82 9 91
7. 2002 ዓ.ም 08 - 08
8. 2003 ዓ.ም - - -
9. 2004 ዓ.ም 03 - 03
10. 2005 ዓ.ም 03 - 03
11. 2006 ዓ.ም 03 - 03
12. 2007 ዓ.ም 09 02 11
13. 2008 ዓ.ም 12 01 13
14. 2009 ዓ.ም 04 - 04
15. 2010 ዓ.ም 13 02 15
16. 2011 ዓ.ም - - -
17. 2012 ዓ.ም 05 01 06
18. 2013 ዓ.ም 08 02 10
19. 2014 ዓ.ም 02 01 03
ጠ/ድምር 82 9 91
የኪስ የስርቆት ወንጀል፡- ይህ የወንጀል አይነት የሚፈፀመው በብዛት በታክሲ፤ ህዝብ በሚበዛባቸው ገበያ
ቦታዎች፤ አትክልት ገበያዎች፤ የታክሲ ማውረጃዎችና የህዝብ ባስ መጫኛ ቦታዎች፤ ከተሳፋሪዎች በመመሳሰል
ወዘተ የሚፈፀሙ ወንጀልናቸው፡፡
ቅሚያ:- ይህ የወንጀል ዓይነት የሚፈፀመው በቀንም ይሁን በማታ የሚፈፀም የወንጀል ዓይነት ሲሆን
በብዛት የሚፈፅሙ በማታ በተለይ ብራስ/ ቦሌ ድልድይ የጎዳና ልጆች በ መምሰል ቅሚያ ያካሂዳሉ ፡፡
የመኪና እቃ ስረቆት
የማታለል ወንጀል
የሻምበሏ የጥበቃ ቀጠና በቋሚነት በአዱስ አበባ በቦሎ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሃያት ሆስፒታል አካባቢ ሃያት ካንፕ ሲሆን
በስጋት የተያዙ ቀጠናዎች 3 ናቸው። ከነዚህም በተጨማሪ አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በጥምረት በመሆን አልፎ አልፎ የሚደረግ
የተለያዩ ፍተሻዎች ኤድናሞል አካባቢ ፣ 22 አካባቢ ፣ ዳሽን ባንክ አካባቢ ፣ አዲሱ ስቴዲየም አካባቢ እና ጅብሰም ት/ቤት
አካባቢ ድንገተኛ ፍተሻ ይደረጋል። ከዚህ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ቪ አይ ፒ በስራ ጉዳይ ወደ ውጭ ሲወጣና ሲገባ እጀባ
ይካሄዳል።
በመጨረሻ የወንጀል መከላከል ዋና አላማው ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ እና የአንድ ሀገር እድገት እና
ልማት እንዲሁም ብልፅግና እንዲስፋፋ ለማድረግ ወንጀል መከላከል ቁልፍ እና ወሳኝ መሆኑን በዚህ በተግባር ልምምዴ
ተረድቻለሁ፡፡
በንድፈ-ሀሳብ ያለው በፖሊስ ስራ ውስጥ ወንጀልን መከላከል፣ወንጀል ሲፈፀም በፖሊሳዊ ህግ መሰረት ህገ- መንግስትን
ማክበርና ማስከበር ሲሆን ነገር ግን በተግባር የሚታየው ወንጀልን ለመከላከል እና ወንጀል ሲፈፀም የህግ ሰንሰለቱን
አለመጠበቅ ይታያል። ለምሳሌ፡- ወንጀል ሲፈፀም ወንጀለኞችን በጉልበት ለማሳመን መሞከር፤ ለምሳሌ አዲስ አበባ
እና ፌ/ል ፖሊስ ጋር በጥምር ስራ ስንሰማራ ተጠርጣሪ ሲያዝ መደብደብ እና መሳደብ በሁለቱም አባላት ላይ የስነ-
ምግባር ችግር ይታያል።
በንድፈ-ሀሳብ አመራሮች እና እያንዳንዱ የፖሊስ አባሎች ፖሊሳዊ ሰላምታ በፖሊሳዊ ህግ እና ስነ-ስርዓት መሰረት
ሰላምታ መሰጠት አለበት ሲባል ነገር ግን በተግባር ፖሊሳዊ ሰላምታ ያለመስጠት ችግር አለ፡፡
በንድፈ-ሀሳቡ መሰረት አመራሮች እና አባሎች ለወንጀል መከላከል ስራ ከመውጣታቸው በፊት
ዝግጁነታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ሲባል በተግባር ግን በጥቂት አመራሮች ኦረንቴሽን ወይም ስለ ስራው ገለፃ
ያለመስጠት ሁኔታ ይታያል።
ፂም-ፀጉር በአግባቡ ያለመስተካከል፣ደንብ ልብስ አሟልቶ ያለመልበስ በአንዳንድ አመራር እና አባሎች ላይ ይታያል።
አንዳንድ አባሎች ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሂደው ቀን አሳልፈው የመምጣት እና ፈቃድ ሳይሰጣቸው የመንቀሳቀስ
ሁኔታ ይታያል።
በአዎንታዊ ጎን፡-የፖሊስ የስራ አድካሚና አሰልች እንደመሆኑ መጠን የአከባቢው ማህበረሰብ ወንጀልን
መከላከል ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ወንጀል የሚፈፀምባቸውን ቦታዎች እና ለወንጀል መንስኤ
የሚሆኑትን ቦታዎችን ያሳዩናል፤እንዱሁም የተለያዩ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀምባቸው ፍትህ ለማግኘት
ሲል እኛን በመተማመን እስከ መኖሪያ ካምፕ ድረስ በመምጣት አቤቱታቸውን እና ጥቆማ ያቀርባሉ፡፡
በወንጀል የሚሰማሩ ግለሰቦች ግን በፖሊስ ላይ አሉታዊ ምልከታ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ፖሊስ የህዝብ
አገልጋይ ሳይሆን የመንግስት የፖለቲካ ስራ የሚደግፍና የሚሰራ ነው የሚል አስተሳሰብ ያላቸው ጥቂት
ግለሰቦች አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በወቅቱ በሚታየው በንሮ ውድነት ምክንያት በየመንደሩ በተለያዩ
ሸቀጣሸቀጥ ላይ የዋጋ ጭማሪ ሲከሰት ህዝቡ በመንግስት ላይ በማማረር ፖሊስንም በዛው ተግባር
ማየት ሌላ ህገወጥ ቤቶች ሲፈርሱ ፖሊስንም በፖለቲካ አይን ማየት ሁኔታዎች ይታያል ።
አባሎች አመራሮች በሚሰጡት ትዕዛዝ መሰረት በቅንነት፤በግልፀኝነት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያለምንም
ቅሬታ በአግባቡ የስራ ግዴታቸውን በህገ-መንግስቱ መሰረት ስራቸውን በብቃት እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
ደካማ ጎን፡-አብዛኛው የሻምበል አመራሮች እና አባሎች ፖሊሳዊ ዲስፕሊን እና ስነ-ምግባር የተሻሉ ቢሆንም በአንዳንድ
አባሎች አልፎ አልፎ የሚታይ የዲስፕሊን ግድፈቶች እንደሚከተለው አስቀምጫቸዋለሁ፡-
2 በፖሌን ቆጠራ ሰዓት ሚሊተሪ አሙዋልቶ ከፖሌን ቆጠራ በኻላ በተሰጠ አስተያየት እንዲስተካከል
አለመልበስ/ሚሊተሪ ለብሶ ከስክስ አለማድረግ/በሲሊፐር
ተደርጉዋል
መቆጠር
15 ከፍተኛ የሆነ የማብራት መቆራረጥ መኖር አከባቢው የሀብታምሰፈር ስለሆነ በአብዛኛው ጀኔረተር ነው
እሚጠቀሙት እንዲስተካከል ተደጋጋሚግዜ ለሚመለከተው
አካል ብናቀርብምሊስተካከል አልቻለም።
17 የመዝሙር እና የሙዚቃ ከፍተኛ የጩኸት ድምፅ መኖር በግል እንዲስተካከል ጥረት አድርጊያለሁ
እንደተቋም ሰራዊቱ የሚኖርበትን ካምፕ በከተማው እስታንዳርድ ልክ መገንባት፣በየስራ ክፍላቸው መስራትና ማሟላት ፣በሻንበል ሁለትና
ከዚያ በላይ ፖትሮሎች እንዲመደቡ ማድረግ፣ዋናውና አንገብጋቢው ጉዳይ የሰራዊቱ ደመወዝ እና የሬሽን ጉዳይ በአፋጣኝ መፍትሄ
የሚፈልጉ ጉዳዮች ናቸው ።
በተጨማሪ በሁሉም ካምፕ የተሟላ የመፀዳጃ ቤቶችንና የግቢውን ቆሻሻ ማስወገጃ በየግዜው በማምጣት ፅዳት ማድረግ አለበት፤ ውሃ፤
መብራትና ሻወር ቤት በመስራት ሰራዊቱ እንዲጠቀሙ እና እንድገለገሉ መደረግ መቻል አለበት፡፡
ተቋሙ የሰራዊቱን የተሽከርካሪ ችግር ለመፍታት ከመንግስትም ሆነ ተቋሙ ቢያንስ በሻምበል ደረጃ አንድ
ፓትሮልና አንድ እስታንድባይ መኪና መመደብ አለበት። እንዱሁም አባሎችን በስራ በሚሰማሩበት ጊዜና ሰዓት
በሚፈለገው ቦታ ላይ በፍጥነት በመድረስ ስራቸውን በቅልጥፍና ማከናወን አለባቸው ።
15. ማጠቃለያ
ይህ የተግባር ልምምድ የተደረገው በፌ/ፖ/ወን/መከ/ኦፕሬሽን ዋ/መምሪያ በቪ አይ ፒ እና ዲ/ጥ/ፖ/መምሪያ ሬጅመንት 1
ሻምበል 1 ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ነው
የቀጠና ብዛት ሶስት በአጠቃላይ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በአካባቢው ይገኛሉ። በነዚህ ተቋማት
ወንጀል እንዳይፈጸምባቸው እና የአከባቢው ማህበረሰብ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ ለማድረግ በቋሚነትና በእግር
እንቅስቃሴ በማድረግ በቀንም ሆነ በሌሊት የጥበቃ ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በጥምረት ድንገተኛ የፍተሻ ስራ ፣ የእጀባ
ስራ እንዲሁም አልፎ አልፎ ድንገተኛ የአሰሳ ስራዎች አሉ። በዚህ የስራ ክፍል ላይ ለወደፊት በስራ ላይ እንዴት መስራት
እንዳለብኝ በተግባርና በተጨባጭ ሁኔታ የተለያዩ ልምዶችን ማወቅና መገንዘብ ችያለሁ።
16. ዋቢ መረጃዎች
1. የግል ማስታወሻ ደብተር ፣የቀን ውሎ ማስረጃ
2. የተመደብኩበት ሻምበል ፅ/ቤት ውስጥ ያለ ዶክመንት እና የተለያዩ ሪፖርቶች