Attachment

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 7

ፍም እሣት

የሙዚቃ ክሊፕን እንደ መስክ የአውድ ጥናት


ስነ ቃል ለተባለው ኮርስ ማሳያነት የቀረበ

በግሩም አረዳ

ግንቦት 2015

1
1. መግቢያ

“ፍም እሣት” የተሰኘውን ዘፈን ያቀነቀኑት ድምፃዊ ጃኪ ጐሲ (ጐሣዬ ቀለሙ) እና ናቲ ማን (ናትናኤል አያሌው)
ናቸው፡፡ የግጥምና ዜማ ድርሰቱ የድምፃውያኑ የጋራ ሥራ ነው፡፡ ሙዚቃ ቅንብሩ ዮኒ ውብ በተባለ ባለሙያ ተሠርቷል፡፡
የሙዚቃ ፊልሙን ቀረፃ፣ ቅንብር እና መረሄ ተውኔትነቱን የሠሩት ኤልያስ ወርቅነህ፣ ብሩክ፣ ዘነበ፣ ናትናኤል፣ ተስፋዬ
ይባላሉ፡፡ ይህ ነጠላ ዘፈን (በአልበም ያልታቀፈ) በ 2005 መጨረሻዎቹ ተሰርቶ ለህዝብ ጆሮ የደረሰ ነው፡፡ የሙዚቃ
ፊልሙ ግን እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር በጥር ወር 2006 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ማለፉን በማስመልከት የተሰራ ነው፡፡

በመሆኑም ይህ ጽሁፍ ክሊፖን እንደ ክዋኔና አጋጣሚ በመውሰድ፤ የክሊፑን የግጥም እንደ ቴክስት በመውሰድ፣ የግጥምና
ምስል ቅንብሩን እንደ መቼትና አውድ በመውሰድ፣ ዘፋኞቹን እንደ ከዋኝ በመውሰድ፣ ጨፋሪዎቹን እና አጃቢዎቹን እንደ
ቀጥተኛ ተሳታፊ በመውሰድ ተመልካቾችን እንደ ታዳሚ በመውሰን ተተንትኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በክሊፑ ውስጥ
የቀረቡ ዋና ዋና ፍካሬያዊ ትርጉም ያላቸው ቁሶችና ሁነቶች ጭምር በትዕምርትነት ተተንትነዋል

2. የግጥም ትንተና

ሀገር በተለያዩ ውክልናዎች ሊቀርብ ይችላል፡፡ ፍም እሣት በተሰኘው ዘፈን ኢትዮጵያ በህዝቦቿ ተወክላ ቀርባለች፡፡
በሙዚቃ ግጥሙ የኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነት እና የጀግንነት ገፅታ ጐላ ብሎ ቀርቧል፡፡

2.1. የኢትዮጵያ አንድነት

የኢትዮጵያ ህዝቦች አለን ከሚሉት ልዩ መገለጫቻቸው አንዱ አንድነታቸውን ነው፡፡ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር
ብሔረሰቦች ሀገር ናት፡፡ ህዝቦቿ የተለያየ አይነት ባሕል፣ ወግ፣ ትውፊት አላቸው፡፡ ይህ ልዩነታቸው በጠላት ጊዜ አንድ
ይሆናል፡፡ ለአንድ አላማ ያብራል፡፡ በታሪካቸው ብዙ ዓይነት የጦርነት ጊዜም አሣልፈዋል፡፡ በሁሉም ዓይነት የጦርነት
አውድ ውስጥ አንድም ጊዜ የተከፋፈለ አቋም አላሣዩም፡፡ ኢትዮጵያውያንን በመለያየት፣ በመከፋፈል ያሰበውን ያሣካ
ጠላት የለምና፡፡ ኢትዮጵያ በተሣተፈችባቸው ታላላቅ ጦርነቶች ተለይቶ የሚጠቀስ፣ የሚወሣ፣ ብሔር የለም፡፡ ይህም
የሆነው አንድነታቸው በጣም ጠንካራ እና በቀላሉ የሚናድ ባለመሆኑ ነው፡፡ ህብረታቸው እሣትን ይፈጥራል፤
አንድነታቸው ፍምን ይመስላል፡፡

ማነው የሚለየው፣ የሚለየው


ይሄ ትውልድ ፍም እሳት ነው
ማነው የሚከፍለው፣ ሚከፍለው
ይሄ ትውልድ ፍም እሣት ነው፡፡
ሌላው የአንድነት መገለጫ ሆኖ የሚነገርላቸው ተግባር አብሮ መብላት፣ መጠጣታቸው ነው፡፡ ይህ ልማድ ከጥንትም
የሚታወቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ማዕድ በአንድ መሶብ (ትሪ) የቀርባል፡፡ ተከቦ ይበላል፡፡ መጐራረሱ፣ እንጀራ
ተቆራርሶ፣ አንተ ብላ እኔ በቃኝ መባባሉ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የመፈቃቀድ መገለጫዎች ናቸው፡፡
ይህ ማህበራዊ አንድነት ኢትዮጵያን በልዩት ያሣውቃል፡፡ በግጥሙም የተገለፀው ይሄው ነው፡፡

ልክ እንደጥንቱ እንደልማዴ
ብቻውን መብላት አይለምድም ሆዴ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በቅኝ ያልተገዛች ሀገር ናት፡፡ በቅኝ የተገዙ ሀገራት ህዝቦች ቋንቋና ባህላቸው ስለተደመሠሠ
እና ስለተዳከመ የቅኝ ገዢዎቻቸውን ቋንቋ ነው የሚጠቀሙት፡፡ ኢትዮጵያ የራሷ ቋንቋና ፅሁፍ ያላት ሀገር መሆኗ
በግጥሙ ከመገለፁም ባሻገር ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በቋንቋና በፅሁፍ ረገድ አንድ ወጥ የሆነ፣ መሠረታቸውን የሚወከል
መገለጫ የላቸውም፡፡ በዘፈን ግጥሙ ይህ ጉዳይ ከመነሣቱም በላይ ሌሎች አፍሪካ ሀገራት ይህን መገለጫ ይከተሉ፣
የኢትዮጵያን አንድወጥነት (አንድነት) አርዓያ ያርጉ የሚል መልዕክት ተላልፏል፡፡
በፍቅር ያመነ ባለው ቃል የፀና

2
ሀረጉን የማይመስል ይከተለንና

ኢትዮጵያውያን በቅኝ አለመገዛታቸው ካረገላቸው (ካስገኝላቸው) አስተዋፅኦ አንዱ በራስ የመተማመን እና ተከባብሮ፣
ተፈቃቅሮ የመኖር ባሕል ነው፡፡ በቅኝ የተገዙ ሀገሮች ቋንቋቸው ብቻ ሣይሆን በራስ የመተማመን ሥነልቦናቸው ምን
ያህል እንደተጐዳ ከሚያሣየው መገለጫቸው አንዱ የቅኝ ገዢዎቻቸውን ቋንቋ መናገራቸው ነው፡፡ በተጨማሪም
ነጮችን ሲያዩ መሽቆጥቆጣቸው፣ መደናገራቸው ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔርና ብሔረሰቦች መካከል ግን ምናልባት እጅግ
ከጥቂቶቹ በስተቀር ሁሉም የራሣቸውን ቋንቋና ባሕል ይዘው የቆዩ ናቸው፡፡ እንደሌላው የአፍሪካ ሀገሮች ጨቋኝ የቅኝ
ግዛት ተፅዕኖ ማንነታቸውን፣ አንድነታቸውን፣ ፍቅራቸውን አላጠፋውም፡፡ ይህን ልዩ የታሪክ ክፍል ግጥሙ “የእውነት
ዘር” በማለት ይገልፀዋል፡፡ ከየትም፣ ከማንም ያልተዳቀለ፣ ያልተከለሠ፣ መሠረቱን አንድነቱን ይዞ የፀና ዘር (ትውልድ)
ለማለት፡፡

በእኛው ቅኝት ገብቶ


ይህን ሰምቶ
የእውነትን ዘር ዘርቶ
ተማምኖ የሚኖር ተከባብሮ
ጥላቻን ንቆ ሽሮ
ከእራቱም ማዕዘናት ያሉ የኢትዮጵያ ህዝቦች የራሣቸው ወግ፣ ባህልና ታሪክ ያላቸው እንደሆነ ቢታወቅም እርስ
በርሣቸው የሚገናኙበት እና የሚወራረሡት የጋራ ሀብት አላቸው፡፡ ከቅድመ አክሱም ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው
የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያስረዳው የኢትዮጵያ ህዝብ የሁሉም ዓይነት ብሔሮች የደም፣ የባህል፣ የወግና፣ የታሪክ ትስስር
ህብረ-ብሔራዊ ማንነትን የሚያላብሥ፣ አያሌ የጋራ ቅርሶችና ዕሴቶች ያሉት ሀገር መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ሂደትም ህዝቡ
ህብረ-ባሕላዊ ትስስርና መስተጋብር ያለው፣ የጋራ መንፈሣዊና ቁሣዊ ቅርፆችንና ሰላማዊ አብሮነትን የያዘ ነው፡፡
ስለሆነም እንደግጥሙ ሀሣብ ኢትዮጵያዊነት ማለት የተለያዩ ብሔር ብሔረሠቦቿ በሁሉም ደምና ድካም የተጋመዱ፣
በጊዜ ሂደት በመሠረቱት አንድነታቸው ልዩ የታነፀ የጋራ ውርስ ያላቸው ህዝቦች ናቸው ማለት ነው፡፡

የታለ አንድነቱ
የፍቅር ተምሣሌቱ
ከሠሜን ከምዕራቡ
ከደቡብ ከምስራቁ

2.2. የኢትዮጵያ ጀግንነት

ፍም እሣት ኢትዮጵያን የሚገልፅ ሃረግ ነው፡፡ ጀግንነት፣ አይበገሬነት፣ ሃይለኝነት የእሣት ተምሣሌነት ነውና፡፡

ማነው ሚደፍረው፣ ሚደፍረው


ይሄ ትውልድ ፍም እሣት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለደፈራት፣ ለመጣባት ጠላት የፍም ያህል የምትግል፣ የእሣት ያህል የምታቃጥል ነች፡፡ በታሪኳ ሁሉ ለጠላት
ያልተንበረከከ ህዝብ ነው ያላት፡፡ ይህ ሃቅ መገለጫዋ የሆነ ሀገርን ከቶውንስ ማን ሊደፍር፣ ማን ሊነካ እንደሚችል ግጥሙ
ይጠይቃል፡፡

“ማነው ሚደፍረው፣ ሚደፍረው”፡፡ እያለ፡፡

ኢትዮጵያ ብዙ የጦርነት አውዶችን ያሣለፈች ሀገር ናት፡፡ በተለያየ የጦርነት ወቅትም ጀግኖቿ እና የጀግንነት ዝናዎቿ
ተቆጥረው የሚያልቁ፣ ተነገረው የማይጨርሱ አይደሉም፡፡ ወንድ ሴት፣ እስላም ክርስቲያን፣ ኦሮሞ ጉራጌ ሣይል
ለኢትዮጵያ ሁሉም መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች በተጋድሎ ያቆሙት ልዩ ታሪክ ያላቸው
ስለመሆኑ የግጥሙ ስንኝ ይነግረናል፡፡

3
ለፍቅር አንደኛ
ከነኩት አርበኛ
ቢቆጠር ስንቱ ጀግና
አያልቅም የእኔ ዝና
ዝናዬ፣ ነይ ዝና፣ ዝናዬ፣ ነይ ዝና
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ብቻ ሣይሆን በአለም አቀፍ ህብረተሰብ ዘንድም የገዘፈ የነፃነትና የሰብዓዊ ክብር ተምሣሌት
በመሆን በተደጋጋሚ ትገለፃለች፡፡ ከዚህም አልፎ የብዙ አፍሪካ ሀገሮች የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል የነፃነት ፋና እና ተስፋ
ሆናለች፡፡ ይህም አርአያነቷ የሦስቱ ቀለማት ሠንደቅ ዓለማዋ የብዙ አፍሪቃ ሀገራት ውልደት በመሆን ተገልጿል፡፡
ሦስቱም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት በተለያየ አቅጣጫ ተሠድረው፣ የብዙ አፍሪካ ሀገራት ባንዲራ ሆነው በማገልገል
ላይ ናቸው፡፡ ይህ የጀግንነት ተምሣሌት ኢትዮጵያውያን ለብቻቸው በማለየት ወይም ለፖለቲካ ገናናት ሲባል የፈጠሩት
አፈታሪክ ሣይሆን የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ ግዛት ሲላቀቁና ዓርማቸውን ሲመርጡ በየጊዜው ከተናገሩት ቃልና አሁንም
ድረስ ተመዝግቦ ከሚገኝ ሠነድ የተወሠደ ህያው ማዕረግ ነው፡፡ የግጥሙ ስንኝም ይህን ሀሣብ ለማጉላት (ለማስታወስ)
ቆሟል፡፡

ዓርማሽ ገኖ
ከአጥናፍ አጥናፍ ተምሣሌት ሆኖ
በእኛ ድካም ስምሽ ይጠራ
ለአንቺ ይዋል ሁሉም በየተራ

3. የግጥምና ምስል ቅንብር ትንተና


“ፍም እሣት” የተሠኘው ክሊፕ አውድ የእግር ኳስ ጫወታ ነው፡፡ በዚህ አውድ ውስጥ የተለያየ ሚና ያላቸው
ባለድርሻዎች አሉ፡፡ እነሱም እግር ኳስ ተጫዎቾች፣ እግር ኳስ መጋጠሚያ ሥፍራ (ስታዲየም)፣ እግር ኳስ ተመልካቾች
ወይም ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን የሚወክሉት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ደስታ ፈንጠዝያ ላይ ናቸው፡፡
ምክንያቱም በተጋጣሚያቸው ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና፡፡ ደጋፊውም ድሉን በተለያየ ስሜት ውስጥ ሆኖ በማጣጣም
ላይ ነው፡፡ ክሊፑ ከዚህ በተጨማሪ አባት አርበኞችን ያሣያል፡፡ የሚታዩት አርበኞች የክብር ሽልማታቸውን እና
ማዕረጋቸውን የሚያሣይ ልብስ አድርገዋል፡፡ ቀደም ብለን የግጥሙን ሃሣብ ስንተነትን ማዕከላዊ ሃሣቡ አንድነት እና
ጀግንነት ነው እንዳልን ሁሉ እነዚሁ ጉዳዮች በምስሉ እንዴት እንደተገለፁ በቀጣይ እናያለን፡፡

3.1. አንድነት በምስል ውስጥ

የአንድነት መገለጫ ትዕይንቶች፤ ተመሣሣይ ጭፍራ፣ ተቃቅፎ (ተያይዞ) በጋራ መዝለል፣ በአንድ መኪና ብዛት ያላቸው
ሰዎች፣ ተቀጣጥሎ መጨፈር እና አንድ ዓይነት ልብስ ናቸው፡፡ እንመልከታቸው፡፡

1. ተመሣሣይ ጭፍራ

በምስሉ ላይ ህፃን፣ ወጣት፣ ሴት፣ አዛውንት ተመሣሣይ የሆነ ጭፈራ ነው የሚያሣዩት፡፡ በተለየ ስልት ደስታውን ሲገልፅ
የሚታይ ጨፋሪ የለም፡፡ ሁሉም በአንድ አይነት ለመንቀሣቀስ ስምምነት አድርገዋል፡፡ የሁሉም ተግባር አንድነታቸውን
የሚያሣይ ትዕይንት ነው፡፡

2. ተቃቅፎ (ተያይዞ) መዝለል

መተቃቀፍ፣ እርስ በርስ (አንዱ ከአንዱ መጠላለፍ) መያያዝ ስምምነትን ፍቅቅርን ያሣያል፡፡ መተቃቀፋቸው፣
መያያዛቸው፣ ህብረት እንዲፈጥሩ እንዲዋደዱ አድርጐአቸዋል፡፡

3. በአንድ መኪና ብዛት ያላቸው ሠዎች

4
በክሊፑ ላይ የሚታዩ መኪኖች መያዝ ከሚችሉት (ከሚፈቀድላቸው በላይ) ሰው ይዘዋል፡፡ ሰዎቹ በተለየየ መኪና
ተበታትነው ሊታዩ ይችሉ ነበር፡፡ አንድን ዕቃ በጋራ መጠቀም በአንድ በኩል የድህነት መገለጫ ሊሆን ይችላል፡፡ በክሊፑ
የምናየው ምስል የሚያስተላልፈው ግን ፍቅር ካለ አንድነት ካለ ምንም ነገር ሊበቃ አንደሚችል የሚያሣይ ነው፡፡

4. ተቀጣጥሎ መጨፈር (ሰለሜ ጭፈራ)

አንድነትን የሚያመላክት የጭፈራ ዓይነት ነው፡፡ ጭፈራው የደቡብን በተለይም የሃድያን ብሔረሰብ የአጨፋፈር ስልት
የሚያሣይ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ እዚሁ ክሊፕ ላይ መታየቱ የግጥሙን ሀሣብ በእጅጉ ያጐላዋል፡፡

ጭፈራው አንድ መሪ ከፊት ሆኖ ሌሎች በርካታ ሰዎች እሱን ከፊት ይዘው በመቀጣጠል የሚጓዙበት (የሚወዛወዙበት)
ሂደት ነው፡፡ መሪው በታጠፈበት በዞረበት ሠዎቹ ይታጠፋሉ፣ ይዞራሉ፡፡ ይህ የጭፈራ ዓይነት በአንድ መመራትን፣
በህብረት መንቀሣቀስን፣ ሣይነጣጠሉ፣ ሣይገነጣጠሉ፣ ሌላ የተለየ ሃሣብ ሣይዙ መጓዝን፣ አብሮ መኖርን የሚያመላክት
ነው፡፡

5. ተመሣሣይ ልብስ

በክሊፑ የሚታዩ እግር ኳስ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ተመሣሣይ ልብስ አድርገው ነው የሚታዩት፡፡ የአልባሣት
ተመሣሣይነት የአመለካከት፣ የመንፈስ አንድነትን የሚያመላክት ነው፡፡

3.2. ጀግንነት በክሊፑ ውስጥ

በክሊፑ ጀግንነት የሚታይባቸው ትዕይንቶች፤የቀድሞው እና የአሁኑ ትውልድ ሠራዊት፣ በየቦታው የሚረጭ እሣት፣
የፉከራ እና የቀረርቶ ውዝዋዜ ናቸው አንድ በአንድ እንመልክታቸው፡፡

1. የቀድሞና የአሁኑ የሠራዊት አባላት

በክሊፑ ላይ የሚታዩት የሠራዊት አባላት በቀድሞ እና በአሁን ትውልድ ውስጥ በጦርነት የተካፈሉ ናቸው፡፡ በተያየ
የማዕረግ አና የሽልማት ልብስ የሚታዩት አርበኞች ኢትዮጵያ በጥንት ጊዜ ያስመዘገበችውን የጦርነት ድል፣ የጀግንነት
ታሪክ የሚያወሡ ናቸው፡፡ የአሁኑን ትውልድ በመወከል በወታደር ማዕረጋቸው እያጨበጨቡ የሚታዩት የሠራዊት
አባላት ተመሣሣይ ድል እና ጀግንነት መጐናፀፋቸውን ያመለክታሉ፡፡

2. በየቦታው የሚረጨው እሣት

እሣት በጨፋሪዎቹ ወጣቶች መካከል በየቦታው ሲረጭ ይታያል፡፡ እሣቱ የሚታየው በተከለለ ቦታ ላይ ሣይሆን በደስታና
በወኔ በሚዘሉ ወጣቶች መሃል ነው የሚንቦለቦለው፡፡ ይህም በአንድ በኩል ኢትዮጵያ የእሣት ያህል በመሆኗ ማንም
የማይጠጋት፣ የማይችላት መሆኗን ሲያሳይ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ህዝቦች እሣትም የማይበግራቸው፣
የማይመልሣቸው ደፋሮች፣ ብረቶች መሆናቸውን ያመላክታል፡፡

3. የቀረርቶ የፉከራ እንቅስቃሴ

በምስሉ ላይ ከሚታየው የዝላይ እና የዳንስ እንቅስቃሴ በተጨማሪ ድምፃውያኑ ከሚሉት የፉከራ እና የቀረርቶ ግጥም
ጋር ጀግና ግዳይ ሲጥል፣ ድል ሲያገኝ የሚያሣየው ዓይነት እንቅስቃሴ በድምፃውያኑ እና በጨፋሪዎቹ ይታያል፡፡ በዚህም
እንቅስቃሴያቸው የወጣቶቹ (የኢትዮጵያ ህዝቦች) የዘወትር ተግባር ጀግንነት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡

5
4. የትዕምርቶች ትንተና
1. ስታድየም እና ኳስ ተጫዋቾች፤

ስታዲየም የውድድር፣ የፍልሚያ፣ የድል መደረጊያ እና ማድረጊያ ቦታ ነው፡፡ የግጥሙ ሃሣብ በምስል ሲለገፅ ይህን ቦታ
ማሣየቱ ስለጀግንነት ሊያወሳን መሆኑ ይገባናል፡፡ ሜዳው የጦር አውድማ፣ ተጫዋቾቹ የጦር ባለሙያዎች ናቸው፡፡

ሜዳው (የጦር አውድማው) ሁለት ተፈላሚዎችን ማሣየት ቢኖርበትም አላሣየም፡፡ የአሸናፊዎች ጭፈራና ደስታ ብቻ
ነው የሚታየው፡፡ ይህም የሆነው ባላጋራዎቹ (ተጋጣሚዎቹ፣ ጠላቶቹ) ከደረሰባቸው ከባድ ጥቃት የተነሣ በድናቸው
ለመታየትም ያልበቃ መሆኑን ይነግረናል፡፡ ይህም የአሸናፊዎቹን ሃያልነት የበለጠ ያጐላብናል፣ ድላቸውን ያገዝፍልናል፡፡

2. አርበኞች ከኋላ ወጣቶች ከፊት

በምስሉ ላይ የሚታዩት አርበኞች ጥንት የነበሩትን ጀግኖች የሚያስታውሱ ናቸው፡፡ አዲሱ ትውልድ ከነሱ ፊት ይታያል፡፡
ይህም አዲሲቷ ኢትዮጵያ የቀደመው ግልባጭ፣ መሣይ መሆኗን ያሣያል፡፡ በተጨማሪም ይኸው ትውልድ በቀድሞዎቹ
ደም እና አጥንት ላይ የተመሠረተ፣ የቆመ መሆኑን ይነግረናል፡፡

3. አርበኞችን እየጨበጡ ማለፍ

የቀደመው እና የአሁኑ ትውልድ አንድነት ያለው መሆኑን ያሣያል፡፡ ተደጋጋፊ፣ ተፈቃቃሪ፣ ተቀጣጣይ መሆናቸውንም
ያመለክታል፡፡ ሃይል፣ ብርታት፣ ጀግንነት መቀባበልንም የሚጠቁም ትዕምርት ነው፡፡

4. የፈረሶች ተግተልትሎ ማለፍ

ፈረስ የሃይል፣ የጉልበት፣ የጥንኮሬ ተምሣሌት ነው፡፡ በክሊፑ ፈረሶች በሚጨፍረው ሰው መሃል እየተግተለተሉ ሲያልፉ
ይታያሉ፡፡ ይህም ህዝብ ውስጥ ያለውን ወኔ እና ጥንካሬ የሚያሣይ ነው፡፡

5. እጅ በግንባር

እጅ በግንባር የተለያየ ተምሣሌት አለው፡፡ በወታደራዊ ቋንቋ የሠላምታ፣ የታዛዥነት፣ የመስዋዕትነት፣ የማክበር፣
የዝግጁነት ተምሣሌት ነው፡፡ በምስሉ ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩት ባለወኔ ወጣቶች ይህን ምልክት ማሣየታቸው ከላይ
በተምሣሌትነት የገለፅናቸውን ሁሉ ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲሰጡ ሲያበረክቱ መታየታቸውን ይገልፃል፡፡

6. ቀይ ቀለም

ቀይ ቀለም የጀግንነት፣ የመስዋዕትነት፣ የሃይለኝነት ምሣሌ ነው፡፡ በክሊፑ ላይ ይሁነኝ ተብሎ፣ ታስቦበት በተለያየ ቦታ
ላይ ገብቷል፡፡ በዋናነት ሲጨፍሩ የሚታዩት የብሔራዊ የእግር ኳስ አባላት ቁምጣ ቀይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን መለያ (ማለያ) ሦስት አይነት ነው፡፡ ከሰባቱ አንዱ ነው ቀይ፡፡ ከሦስቱ ቀይ የሆነው ማሊያ
ብቻ ተመርጦ ነው እዚህ ክሊፕ ላይ ግልጋሎት ሲሰጥ የሚታየው፡፡

የአዲስ አበባ ስታዲየም የተመልካች መቀመጫ አይነቶች የተለያዩ ናቸው፡፡ በክሊፑ የሚታየው ቀይ የሆኑት ብቻ ናቸው፡፡

ዘፈኑን ለማድመቅ በአጃቢ ከገቡት ሙዚቃዎች ጥሩንባ ብቻ ይታያል፡፡ የዚህ ጥሩንባ ቀለም ቀይ ነው፡፡ እነዚህ እና ሌሎች
በጀርባ ምስልነት፣ በአልባሣትነት፣ ተመሣሣይ መሆን የግጥሙን ሃሣብ ለማጉላት ይሁነኝ ተብለው የገቡ እንደሆነ
መረዳት ይቻላል፡፡

5. ማጠቃለያ

6
በአጠቃላይ በክሊፑ አውድ የቀረቡት ሁሉም ነገሮች በእማሬውና በፍካሬው ከፈጠሩት፣ ክሊፑ ከሚያሣየው አውድና
መቼት ጋር ማለትም ከእግር ኳስ መጋጠሚያ ሥፍራ፣ ከተጨዋቾች እና ከደጋፊዎች ጋር አብሮ የሚሄድ ነው፡፡
በተፈጠረው አውድ ውስጥም መተላለፍ የተፈለገው ዋና መልዕክት (ጭብጥ) ትዕምርታዊ ሆኖ፣ ጥበባዊ ለዛውን ጠብቆ
ቀርቦ ታይቷል፡፡ ክሊፑ በገሃዱ የሚታየውን ኢትዮጵያዊ አንድነት፣ ህብረት፣ መተሳሰብን፣ ጀግንነትን፣ እና ነጻነትን ወክሎ
አቅርቧል ማለት ይቻላል፡፡
***//***

You might also like