Professional Documents
Culture Documents
Customs Risk Management Training Manual - 2
Customs Risk Management Training Manual - 2
ግንቦት 2009
ማውጫ
ምዕራፍ አንድ...................................................................................................................................................4
1 ምንጮች /Reference |
1.1. መግቢያ...........................................................................................................................................4
1.2. ዓላማ..............................................................................................................................................6
1.3. ትርጉም...........................................................................................................................................6
1.4. የጉምሩክ ሀላፊነቶች...........................................................................................................................9
1.5. በጉምሩክ ስራ ላይ ያሉ ተጽእኖዎችና ምክንያቶቻቸው...............................................................................10
1.6. የጉምሩክ ሥጋት ሥራ አመራር ዓላማ....................................................................................................10
1.7. ለሥጋት ሥራ አመራር ትገበራ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች...............................................................................11
1.8. የሥጋት ሥራ አመራር መርህ...............................................................................................................11
1.9. የባለስልጣኑ የስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ መርሆዎች...................................................................................12
2.1. የስጋት ስራ አመራር አላማዎች.............................................................................................................12
1.10. የስጋት ስራ አመራር ስርዓት ጠቀሜታዎች...........................................................................................13
1.11. የሥጋት ሥራ አመራር ደረጃዎች.......................................................................................................15
ምእራፍ ሁለት................................................................................................................................................17
2.1. የስጋት ስራ አመራር ታሪካዊ ዳራ...............................................................................................................17
2.2. ሥጋት ሥራ አመራር ከአለም አቀፍ አሰራር አንጻር....................................................................................18
2.3. የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን...........................................................18
ምእራፍ ሶሥት................................................................................................................................................20
3.1. የስጋት ስራ አመራር ሂደት ደረጃዎች /Risk Management Process/...............................................................20
I. ማዕቀፍ ማስቀመጥ /Establish the Context/.......................................................................................21
II. ስጋት መለየት /Identifying Risks/...................................................................................................22
III. ስጋትን መተንተን /Analyzes Risk.................................................................................................24
IV. ስጋት መመዘን እና ደረጃ መስጠት /Assess & Prioritize Risks..........................................................28
V. ስጋትን ማስተናገድ/Addreess Risk....................................................................................................29
VI. ክትትልና ግምገማ /Monitor and Review/.....................................................................................31
VII. ግንኙነት እና ምክክር.....................................................................................................................33
ምእራፍ አራት.................................................................................................................................................34
የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር ትግበራ በዋናው መ/ቤት እና በቅ/ጽ/ቤቶች.......................................................................34
በዋናው መ/ቤት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት.....................................................................................................34
የገቢ እቃ አወጣጥ የሥጋት ሥራ አመራር............................................................................................................38
የስጋት መምረጫ መስፈርቶች/Risk Assesment Criteria/..............................................................................38
የቅ/ጽ/ቤቶች የስጋት ስራ አመራር ቡድን ዋና ዋና ተግባራት.....................................................................................51
የገቢናወጪ ዕቃዎች ትራንዚት የስጋት መምረጫ መስፈርቶች...................................................................................53
2 ምንጮች /Reference |
የገቢ ትራንዚት..........................................................................................................................................53
የወጪ ትራንዚት........................................................................................................................................54
የገቢ መንገደኞች ስጋት መምረጫ መስፈርቶች.......................................................................................................55
ማጠቃለያ......................................................................................................................................................59
ምንጮች /Reference.....................................................................................................................................61
ምዕራፍ አንድ
1.1. መግቢያ
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደርን ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን
እያደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህም አንዱና ዋነኛው የጉምሩክ አሠራርን ሙሉ በሙሉ የስጋት ሥራ አመራርን መሠረት
ያደረገ ሆኖ የተቀላጠፈ አገልግሎትና ቁጥጥር የተጣጣመ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ የስጋት ሥራ አመራር
ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው የአሠራር ሥርዓት ሲሆን ለህጋዊ ነጋዴዎች የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት፤
ለህጉ ተገዥ ባልሆኑት ላይ ደግሞ ተገቢውን ቁጥጥር ለማድረግ እና ወደ ህግ ተገዥነት ለማምጣት የሚያስችል
3 ምንጮች /Reference |
ዘመናዊ የአሰራር ዘዴ ነው፡፡ መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች በመሰብሰብና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመተንተን
ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥን ከውጤታማ ቁጥጥር ጋር አጣጥሞ ለመተግበር የሚያስችል ስልት ነው፡፡
እየሰፋ ከመጣው የወጪ ፣ የገቢ እና ፣ የመንገደኞች ለተለያዩ ጉዳዮች ከሀገር ወደ ሀገር የሚደረግ እንቅስቃሴ አንጻር
ሁሉንም የጉምሩክ ስራዎች በመቆጣጠር ማከናወን ካለው ውስን ሃብት /የሰው፣የጊዜ፣ የገንዘብ እና ሌሎች/ እና
ውስብስብነት አንፃር የሚታሰብ አይሆንም፡፡ በዓለም ላይ እየጨመረ ከመጣው የጭነት /Cargo/ እንዲሁም የንግድና
የሰዎች እንቅስቃሴ የተነሳ ሁሉንም ሰዎችና ጭነቶች መቆጣጠር ለጉምሩክ ተቋማት የማይቻል እየሆነ መጥቷል፡፡
በየዕለቱ የጉምሩክና የታክስ ባለሙያዎች የትኛው ድርጅት ፣እቃ ወይም ተጓዥ ላይ ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸው መለየትና
ማወቅ አለባቸው ለዚህም የሰው ፣ የዕቃና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ብቻ ሳይሆን መለየት የሚችሉበት ምክንያት ወይም
መስፈርቶች ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህም መለያ ምክንያቶች የሥጋት አመላካቾች /Risk Indicators/ እና የኋላ ልምዶች
/Trends/ ናቸው፡፡ የሥጋት አመላካቶችን እና የኋላ ልምዶችን መጠቀም ትክክለኛ ምርጫ እንድናካሂድ ይረዳናል፡፡ ስጋት
ስራ አመራር ስርዓት ውጤታማ የቁጥጥር እና የተቀላጠፈ የመስተንግዶ ስርዓትን፣ የደንበኞች እርካታ እና ታማኝነትን
በማሳደግ ህገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር ገቢን ለማሳደግ ተመራጭ የማኔጅመንት ጥበብ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለስልጣኑ ገቢን በብቃት ለመሰብሰብ፣ ኮንትሮባንድን ለመከላከል እና የህብረተሰቡን ደህንነት
ለመጠበቅ በገቢና ወጪ ዕቃዎች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር ስጋትን መሰረት ባደረገ አኳኋን እንዲፈጸም እየሰራ ይገኛል፡፡
በስጋት ሥራ አመራር ያልተደገፈ አገልግሎት አሰጣጥ ንግድን የማሳለጥ ተግባር ከማስተጓጎሉ ባለፈ ቁጥጥር ሊደረግባቸው
የሚገቡ ስጋቶችን ለይቶ ትኩረት ማድረግ ሲገባው በሁሉም ላይ ቁጥጥር በማድረግ አላስፈላጊ የሆነ መስተጓጎል እንዲሁም
የሃብት ብክነት ያስከትላል፡፡
የጉምሩክ ቁጥጥርን የስጋት ሥራ አመራርን መሰረት ባደረገ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ሲኖሩት
በዋናነት ንግድና ኢንቨስትመንትን ለመደገፍ፤ህጋዊ ነጋዴዎችን ለማበረታት እና ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን
ለመቆጣጠርና ወደ ህጋዊ ስርዓት ለማምጣት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
የስጋት ስራ አመራር የሕግ ተገዥነትን ለማምጣት የሚያግዝ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን የተቋሙ ዕቅድ እንዳይሳካ የሚያደርጉ
አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ለማስተናገድ የሚረዳ የአመራር እና የአስተዳር ዘዴ ነው፡፡
የስጋት ስራ አመራር በዋናነት በአገልግሎት አሰጣጥ እና በቁጥጥር ስርዓት መካከል ሚዛናዊነትን ለማስጠበቅ የሚጠቅም
ከመሆኑ በተጨማሪ ትኩረት በከፍተኛ የስጋት ቦታዎች ላይ እንዲሆን በማድረግ ውስን የሆነውን የተቋሙን ሀብት
ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣንም ይህንን ውጤታማነት ለማምጣት የስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ እና ስትራቴጂ
ቀርፆ እንዲተገበር በማድረግ አበረታች ውጤቶች እየታዩ ነው፡፡ በዚህም ያለውን ውስን የሰው ፤ የማቴሪያልና የፋይናንስ
4 ምንጮች /Reference |
ሀብት ከፍተኛ ስጋት ቦታዎች ላይ በማዋል ህጋዊ ግብር ከፋይን በመለየት ቀልጠፋ አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ ባልሆኑት
ላይ ደግሞ ውጤታማ ቁጥጥር በማድረግ የደንበኞችን እርካታ በማምጣት ገቢን በብቃት እንዲሰበሰብ እና የግብር ከፋዮች
የህግ ተገዥነት ደረጃ ከፍ እንዲል እየሰራ ይገኛል፡፡
1.2. ዓላማ
የዚህ ስልጠና ሰነድ ዓላማ የስጋት ስራ አመራር መርህን የተከተለ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የቁጥጥር
ስርዓት እንዲኖር የሚያግዝ ግንዘቤ መስጠት እና የባለስልጣኑ ሠራተኞች የሥጋት ሥራ አመራርን
መሠረት ያደረገ ሥራ በየሥራ ክፍላቸው እንዲያከናውኑ የሚያግዝ ግንዛቤ መፍጠር ነው፤
ስጋት ስራ አመራር እንዴት ለተቋሙ ግብ ስኬት ጠቃሚ እንደሆነ እና ሳይንሱ የተቋሙን ዕሴት
ለማጎልበት እንዴት እንደሚያግዝ ለማስገንዘብ ነው፤
በታክስ ሕግ ተገዥነት ስጋት ሥራ አመራር የስራ ክፍል የሚመደቡ ባለሙያዎች ሰነዱን በራሳቸው
በማንበብ እውቀታቸውን ለማሳደግ እና ሥራችውን ሲከናውኑ የአሰራር መርህ እንዲሆናቸው
ለማድረግ ነው፤
1.3. ትርጉም
ስጋት ማለት ፡- eÒƒ TKƒ ¾ ተቋሙ ¯LT እ”ÇÃd" ›K<ታ© የሚፈጠር ማንኛውም አይነት ክስተት TKƒ
’¨<:: ከኢትዮጵያ ገቢዎችን ጉምሩክ ባለስልጣን አንፃር ስጋት ማለት ኰንትሮባንድ፣ ንግድ ማጭበርበር፣
ግብርና ታክስ አለመክፈል ወይም ስወራ፣ የስነ ምግባር ችግር ወዘተ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
5 ምንጮች /Reference |
ስጋት ስራ አመራር በአለን ውስን ሀብት ውጤታማ ውሳኔ እንድንወስን የሚረዳን የስራ አመራር ጥበብ
(Management Science) ነው፡፡
የታክስ ሕግ ተገዢነት ማለት ፡- ግብር ከፋይ የሚጠበቅበትን የግብርና ቀረጥ ግዴታዎችን በግብር ታክስ እና
በጉምሩክ ህግ መሰረት በወቅቱ አሳውቆ መክፈል ማለት ሲሆን ይህም ሰፋ ባለ ትርጉሙ ሲገለጽ፡
የታክስ ህግ ተገዢ አለመሆን፡ አንድ ግብር ከፋይ በግብር ህጉ የሚጠበቅበትን የግብር እና የቀረጥ ግዴታ
አለመወጣት ማለት ሲሆን እነዚህም ግዴታዎች
የታክስሕግ ተገዥነት
የታክስ ሕግ ተገዥነት ማለት የግብርና ቀረጥ ህጎችን ተቀብሎ ግዴታዎችን በፍቃደኝነትና በታማኝነት
መወጣት ማለት ነው፡፡
6 ምንጮች /Reference |
የታክስ ሕግ ተገዥነት ስራ አመራርማለት የታክስ ህግስጋቶችን በስጋት ስራ አመራር መርህ መሰረት መለየት፣
መተንተን፣ ቅደም ተከተል ማስቀመጥናማስተናገድ የሚያስችል ሲሆንግብር ከፋዮችን ወደ ህግ ተገዥነት
ለማምጣት የሚያስችል የአሰራር ሂደት ነው፡፡
የጉምሩክ ትራንዚት፡- ማለት ዕቃዎች ወይም መንገደኞች በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ ከአንድ የጉምሩክ ጣቢያ
ወደ ሌላ የጉምሩክ ጣቢያ በተፈቀደ መስመር የሚተላለፉበት የጉምሩክ ስነ ሥርዓት ነዉ፡፡
ካርጎ ስካኒንግ ማሽን፡- ማለት ማለት ወደ ሀገር የሚገቡ ወይም ከሀገር የሚወጡ ተሽከርካሪዎች የያዟቸው
ጭነቶች ወይም ከአገር የሚወጡ እና ወደ ሀገር የሚገቡ ጓዞች የሚፈተሹበት የዕቃ መፈተሻ መሳሪያ ነዉ፡፡
ቀይ ስጋት ደረጃ፡- ማለት ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ማለት ሲሆን ዕቃዎች ወይም መገደኞች ላይ አካላዊ ፍተሻ እና
የሰነድ ምርመራ እንዲደረግ የሚያችል አመላካች የሥጋት ደረጃ ወይም የማለፊያ መስመር (channel) ነው፡፡
ቢጫ ስጋት ደረጃ፡- ማለት መካከለኛ የስጋት ደረጃ ማለት ሲሆን ሰነድ ምርመራ እንዲደረግ የሚያችል
አመላካች የሥጋት ደረጃ ወይም የማለፊያ መስመር (channel) ነው፡፡
አረንጓዴ ስጋት ደረጃ፡- ማለት ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ማለት ሲሆን በመድረሻ ጣቢያ የደረሱ ዕቃዎች ወይም
መንገደኞች የሰነድና የአካላዊ ፍተሻ ሳይደረግባቸው የገቢ ዕቃ ሰነድ እንደቀረበ ወይም መንገደኛው እንደደረሰ
በመልቀቅ በድህረ- ዕቃ አወጣጥ ኦዲት እና በሌሎች ዕቃ ከተለቀቀ በኋላ ቁጥጥር በሚያደርጉ የህግ ማስከበር
የስራ ክፍሎች ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ መስመር ነው፡፡
ሰማያዊ ስጋት ደረጃ፡- ማለት በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ የስጋት ደረጃ የሚመደቡ የተመረጡ የኢኮኖሚ
አንቀሳቃሽ ድርጅቶች(AEO) የሚስተናገዱበት የስጋት ደረጃ ሲሆን በመድረሻ ጣቢያ የደረሱ ዕቃዎች የሰነድና
የአካላዊ ፍተሻ ሳይደረግባቸው የገቢ ዕቃ ሰነድ እንደቀረበ ተለቀው በድህረ- ዕቃ አወጣጥ ኦዲት እና በሌሎች
ዕቃ ከተለቀቀ በኋላ ቁጥጥር በሚያደርጉ የህግ ማስከበር የስራ ክፍሎች ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚችሉ
መሆኑን የሚገልጽ መስመር ነው፡፡
ብርቱካናማ የስጋት ደረጃ፡- ማለት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ወይም ሊወጡ የተዘጋጁ ዕቃዎችን የጫኑ
ተሽከርካሪዎች በከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ መሆናቸውን የሚገልጽ መስመር (channel) ሲሆን በስካኒንግ
ማሽን/አካላዊ ፍተሻ እንዲደረግባቸው የሚገልጽ መስመር ነው፡፡
ነጭ ስጋት ደረጃ፡- ማለት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ወይም ሊወጡ የተዘጋጁ ዕቃዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች
በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ላይ መሆናቸውን የሚገልጽ መስመር (channel) ሲሆን በስካኒንግ ማሽን/አካላዊ ፍተሻ
ሳይደረግባቸው እንዲለቀቁ የሚገልጽ መስመር ነው፡፡
7 ምንጮች /Reference |
የልዩ መብት ተጠቃሚ፡ ማለት በየጉምሩክ የልዩ መብት ተጠቃሚዎች የአሰራር ስርአት መሰረት በአሰራር ስርአቱ
መሰረት ተመርጠው የተቀላጠፈ መስተንግዶ እንዲያገኙ የሚደረጉ ድርጅቶች ናቸው፡፡
የተመረጡ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ድርጅቶች፡ ማለት ማለት በተቀቋሙ የተቀመጠውን መስፈረት አሟልተው
ከተቋሙ ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመው የተመረጡ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ በመባል መበቱ የተሰጣቸው
ድርጅቶች ናቸው፡፡፡
የስጋት ስራ አመራር ደረጃ፡ማለት በተደረገ የስጋት ትንታኔ መነሻ ወይም በተቀመጠ የስጋት መስፈርት መሰረት
የአንድን ዕቃ ወይም መንገደኛ የመስተንግዶ መስመር የሚገልጽ ነው፡፡
8 ምንጮች /Reference |
ሁሉንም መቆጣጠር አለመቻል
ተጽእኖዎቹ ለምን ?
እነዚህን አላማዎች ለማሳካት ከተለመደው የቁጥጥር አስተሳሰብ በመውጣት ሥጋትን መሰረት ያደረገ እና
በሥጋት ሥራ አመራር ላይ የተመሰረተ አሰራርን መተገበር ይገባል፡፡
የተቀላጠፈ ሥጋት
ቀልጣፋ የእቃ
መስተንግዶ ሥራ ህግ ማስከበር
ሀገራዊ እና አለም
አመራር
አወጣጥ ሥርአት የመረጃ አቀፋዊ ደህንነት
ዝቅተኛ ወጪ ልውውጥ የህብረተሰብ ጤና
ከፍተኛ ደረጃ የመረጃ እና እና ደህንነት
የአገልግሎት የስጋት ትንታኔ የተሻለ ገቢ
ማስቻያ
አሰጣጥ አሰባሰብ
የሰው ሀብት ሥራ አመራር፣ ዘመናዊ
ዎች ቴክኖሎጂ፣ የሰው ሀብት ልማት እና ህግ
9 ምንጮች /Reference |
1.7. ለሥጋት ሥራ አመራር ትገበራ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች
የበላይ አመራሩ እና የአጠቃላይ ሰራተኛወ የአመላካከት ለውጥ
ስጋት ስራ አመራርን ለሁሉም አካላት ማሳወቅ
በሥጋት ሥራ አመራር ላይ ለሚሰሩ ባለሞያዎች የተለየ ስልጠና መስጠት
ፖሊሲ እና ስተራቴጂ
አደረጃጀት
የህግ ከለላ
ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ተሰባስበው የተደራጁ መረጃዎች
ለህጋዊ ግብር ከፋይ የተመቻቸና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ግብር ለመክፈል የሚወስድባቸውን
ወጪ እና ጊዜ በመቀነስ የደንበኞችን እርካታን ማሳደግ፤
ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥን ከውጤታማ ቁጥጥር ጋር አጣጥሞ መተግበር ፤
ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት፤
የውስጥ እና የውጭ ስጋቶችን መቀነስ፤
10 ምንጮች /Reference |
የንግድ ማጭበርበርን እንዲቀንስ ማስቻል፤
ቁጥጥሩን ለህግ ተገዢ ባልሆኑት ላይ በማድረግ ህገወጥነት እንዲቀንስ ማድረግ፤
ግልጽ፣ ፍትሐዊ እና ተደራሽ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ የውጪ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት፤
የግብር ከፋዩን የህግ ተገዢነትን ማሳደግ፤
ውስን ሀብትን ከፍተኛ ስጋት ቦታዎች ላይ በማዋል የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማ ማድረግ ወ.ዘ.ተ.
የስጋት ስራ አመራር ስርአት በሁሉም የባለስልጣን መ/ቤቱ አሰራር ላይ እንዲተገበር ማድረግ ወ.ዘ.ተ.
ለንግዱ ማህበረሰብ
ለህጋዊ ግብር ከፋይ የተመቻቸ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ግብር ለመክፈል የሚወስድባቸውን
ወጪ እና ጊዜ ለመቀነስ ይረዳል፣
ህጋዊ ቁጥጥር እና የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥን በማጣጣም የደንበኞችን እርካታን ለማምጣት
ያስችላል፣
ፈጣን የእቃ አወጣጥ ሥርአት
የተቀላጠፈ መስተንግዶ
የተሻለ የህግ ተገዥነት
አላስፈላጊ መዘግየቶችን በመቀነስ ወጪውን መቀነስ
11 ምንጮች /Reference |
ከተቀሙ ጋር የተሻለ ግንኙነት እና መተባበር ይፈጥራል
በአለም አቀፍ እና በሀገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተወዳዳሪ መሆን ያስችለዋል
የግብር ከፋዩን የህግ ተገዢነትን በማስፋት በፈቀደኝነት የሚከፈለውን ቀረጥና ታክስ በማሻሻል ገቢን
ያሳድጋል ፣
ለተቀሙ
ትክክለኛ መረጣ እንዲያደርግ ያስችለዋል
ግልጽ የሆነ የውሳኔ አሰጣጠጥ
ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የተሻለ ግንኙነት እና መተባበር ይፈጥራል
ሕግ አክባሪነትን በማበረታታት የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት
ሕገ ወጥነትን በመቆጣጠር ገቢን በብቃት ለመሰብሰብ
የሀገር ደህንነትን ለመጠበቅ
ሕጋዊ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለመደገፍ
ስጋትን መሰረት በማድረግ ፍትሃዊ የጉምሩክ መስተንግዶ ለመስጠት
ኮንትሮባንድ፣ ታክስ ስወራ እና ታክስ ማጭበርበርን ለመቀነስ
የገምሩክ ዕቃ አወጣጥ ጊዜን እና ወጪን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ
የሕግ ተገዥነትን ለማሳደግ
ÁK”” ውስን ¾c¨<' ¾T‚]ÁM' ¾‚¡•KAÍ= እ“ ¾óÓ”e ሀብትን ከፍተኛ ስጋት ቦታዎች ላይ
በማዋል የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማ ያደርጋል ፣
ክልከላና ገደብ የተደረገባቸውን ዕቃዎች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግባቸው በማስቻል የማህበረሰቡን
ደህንነት ያስጠብቃል፣
ሁሉንም ግብር ከፋይ በእኩል እና ግልጽ በሆነ መስፈርት ለመመዘን ይረዳል፤
ግልጽ፣ ፍትሐዊ እና ተደራሽ አገልገሎት እንዲሰጥ በማድረግ የውጪ የውጭ ቀጥተኛ
ኢንቨስትመንትን ያበረታታል፤
ታ¡e e¨^“ ንግድ ማጭበርበር Là ¾}cT\ Ów` ŸóÄ‹” እ”É”KÓ }Óv\U እንዲቀንስ Áe‹K“M ፣
ቁጥጥሩ ፣ ፍተሻው እና ኦዲት ማድረጉን ለህግ ተገዢ ባልሆኑት ላይ በማድረግ ህገ ወጥነት እንዲቀንስ
ያደርጋል ወ.ዘ.ተ.
ታ T˜ Ów` Ÿóà ¾’u\ ¨Å IÑ-¨Ø’ƒ ¾SH@dž¨<” H>Ń እ”É”S´” Ã[Ç“M::
¾Ów` cwdu=¨< vKVÁ ¾ðKѨ<” S`Ù ¾SY^ƒ }Óv` Ãk`“ ueÒƒ u}S[Ö< Là ¾Se^ƒ vIM
ÃÇw^M'
u}c\ Y^‹ w³ƒ SK"ƒ Ãk`“ u}c\ Y^‹ Ø^ƒ“ ¨<Ö?ƒ SK"ƒ'
12 ምንጮች /Reference |
1.11. የሥጋት ሥራ አመራር ደረጃዎች
ስትራቴጂያዊ
ሥጋት ሥራ
አመራር
ኦፕሬሽናል
ሥጋት ሥራ
አመራር
ታክቲካል ሥጋት ሥራ
አመራር
ስጋት ሥራ አመራር እንደየ ሥጋት ደረጃው፣ እንደሚያስከትለው ተጽእኖ እና ሥጋቱን ለማስወገድ ወይም
ለመቀነስ እንደሚሳተፉት አካላት በሦስት ደረጃዎች ሊከፈል ይችላል፡-
13 ምንጮች /Reference |
ሥጋቶቹ ከእለት ተእለት ተግባሮቻችን ጋር የሚያያዙ እና በስራ ክፍል እና በባለሞያ ደረጃ ሊፈቱ የሚችሉ
የሥጋት ዓይነቶች ናቸው፡፡
ዝቅተኛ ከፍተኛ
የተቀላጠፈ መስተንግዶ
14 ምንጮች /Reference |
ምእራፍ ሁለት
2.1. የስጋት ስራ አመራር ታሪካዊ ዳራ
ስጋት/Risk የሚለው ቃል Risque ከሚል የፈረንሳይ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም አደጋ/danger ማለት ነው፡፡
ከዚህም አንጻር ስጋት ማለት አደጋ የመከሰት ዕድል ወይም ሁኔታ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ስጋት ስራ አመራር
እንደ ሳይንስ አዲስ ቢሆንም በሰው የሕይወት ዘይቤ ውስጥ ግን ለረዥም ዘመናት እንደነበረ በዘርፉ የተሰማሩ
አካላት ይጠቁማሉ፡፡ በተለይም ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ከመስፋፋቱ በፊት ስጋት በአማልክት ትዕዛዝ ወይም
ፈቃድ አማካኝነት በሰው ልጆች እና በተፈጥሮ ላይ የሚከሰት አደጋ ተደርጎ ይቆጠር ነበረ፡፡ በመሆኑም ሰዎች
እነዚህን አደጋዎች ቀድመው በማወቅ ለመዘጋጀት ሲሉ የባህላዊ ዕምነት አዋቂዎች፣ ልምዶችን እና
ትውፊቶችን ይጠቀሙ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በተፈጥሮ እና በሰዎች ሕይወት ላይ የሚከሰቱ አደጋዎቸን
ቀድሞ መከላከል ሳይቻል ረዥም ጊዜያት ተቆጥረዋል፡፡ ዘመናዊ የሆነ የስጋት ስራ አመራር ጥበብ የጀመረው
ከአውሮፓዊያኑ የኢንዱስትሪ አቢዮት በኋላ ሲሆን ከቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አደጋዎችን
ለመከላከል ነበር፡፡ በትላልቅ ግድቦች፣ ድልድዮች፣ በአየር፣ በየብስ እና በባህር ትራንስፖርት፣ በነዳጅ
ማስተላለፊያ መስመሮችና ታንከሮች፣ በባይሎጅካልና ኬሚካል ንጥረ ነገሮች አጠቃቀም እና አያያዝ፣
በፋይናስ እና ንግድ ስራ፤ በፕሮጀክቶች አስተዳደር እና ሌሎች አሰራሮች ላይ ስጋትን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ
የመከሰት እዱሉና ተጽዕኖው በመተንተን የመቀነስ እና የመከላከል ስራ ትኩረት እያገኘ መጣ፡፡
የስጋት ስራ አመራር በተደራጀ እና በተጠናከረ መልኩ በተለይም በፋይናንስ ተቋሟት አሰራር ውስጥ
የተጀመረው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ቢሆንም በታክሰ አስተዳደር ውስጥም ከተጀመረ ጥቂት
የማይባሉ ጊዜያትን አስቆጥሯል፡፡ የታክስ ሕግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር በታክስ አስተዳደር ስጋትን
በመለየት፣ በመተንተን፣ ቅደም ተከተል በማስቀመጥና ትኩረት በከፍተኛ የስጋት ቦታ ላይ እንዲሆን በማድረግ
የታክስ ሕግ ተገዥነት ለማምጣት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ነው፡፡
15 ምንጮች /Reference |
2.3. የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን
የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር በኢትዮጵያ የተጀመረው በ 1996 ዓ.ም ሲሆን አሰራሩም በደንብ ያልተደራጀ፣
በሲስተም ያልታገዘና የማንዋል አሠራርን ብቻ የተከተለ እንዲሁም በተወሰኑ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ
የሚተገበር ነበር፡፡ በ 2 ዐዐዐ ዓ.ም.ተቋሙ የ BPR ጥናት በማጠናቀቅ ከፍተኛ ለውጥ ያካሄደ ሲሆን ከለውጡ
በኋላ በስጋት ሥራ አመራር የአሰራር ስርዓት ላይ መሻሻል ታይቷል፡፡ ይህም የስጋት ደረጃዎችን ለመጣል
የሚያስችሉ መረጃዎች ከቅ/ጽ/ቤቶች እየተሰበሰቡ እና በማዕከል የስጋት ትንታኔና የስጋት ፕሮፋይል እየተዘጋጀ
በአሰሰኩዳ ሴልክቲቪቲ ማትሪክስ አማካኝነት ስጋት በሲስተም እንዲጣል ማድረግ ተችሏል፡፡ የስጋት
መረጃዎችን በተመለከተ በተበጣጠሰ እና ኋላቀር በሆነ መንገድ ይያዙ የነበረ ሲሆን ለውጡን ተከትሎ የስጋት
መረጃዎች በራስ አቅም እና ጥረት በሲስተም የሚያዙበት አሰራር ተዘርግቶ ለስጋት ስራ አመራር ጠቃሚ የሆኑ
መረጃዎች በ Trader Payers Profile Data Base /TRDP/ የሚያዙበት አሰራር ተፈጥራል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን
በቅርብ ጊዜያት በገቢ ዕቃዎች መስተንግዶ ላይ ብቻ ሲጣል የነበረው የስጋት ስራ አመራር መሰረቱን በማስፋት
በመንገደኞችና በመንደኞች ጓዝ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈጻጸም፣ በትራንዚት ዕቃዎች ስነ-ስርዓት አፈጻጸም
እና በወጪ ዕቃዎች ስነ-ስርዓት አፈጻጸም ላይ መተግበር ተችላል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ለውጥች ቢኖሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ
አንጻር ለውጡን በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል ያስፈልጋል፡፡ በተለይም በቁጥጥር ላይ ያተኮረ የጉምሩክ ስነ-
ስርዓት አፈጻጸም በተመረጠ መልኩ ስጋት ስራ አመራር መሰረት ባደረገ ሁኔታ ሊከናወን ይገባል፡፡ በዚህም
ምክንያት የኢትዬጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን ለተቀላጠፈ የንግድ እቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር
እንዲሁም ለተገልጋይ ሕብረተሰብ ፍትሐዊ፣ ፈጣን፣ ተገማች እና አመኔታን ያተረፈ የጉምሩክ አገልግሎት
በመስጠትና የጉምሩክ ቁጥጥር በማካሄድ ረገድ የግልጽነትና ተጠያቂነት አሰራርን ለማስፈን በአዲሱ የጉምሩክ
አዋጅ እንቀጽ 6 ከንዑስ (1) እስከ (3) በጉምሩክ አሰራር የስጋት ስራ አመራር መርህን ተግብራል፡፡
የስጋት ስራ አመራር
16 ምንጮች /Reference |
3/ ባለስልጣኑ የስጋት ስራ አመራርን መሰረት በማድረግ በተሰጠ አገልግሎት ላይ የታዩ የሕግ
ጥሰቶችን በመለየት ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ኦዲትን እና ሌሎች የቁጥጥር ስልቶችን
መሠረት ያደረገ ቁጥጥር ተግባራዊ እንዲደረግ ሊወስን ይችላል::
ምእራፍ ሶሥት
3.1. የስጋት ስራ አመራር ሂደት ደረጃዎች /Risk Management Process/
የስጋት ስራ አመራር አላማ የታክስ ስጋቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመለየበት፣ በመተንተን፣ ደረጃ በማውጣት፣
ማስተናገድ ነው፡፡ በመሆኑም የታክስ ሕግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስጋት ስራ አመራር ሂደትን /Risk
Management Process/ተከትሎ የሚከናወን ሲሆን በዚህም ስጋቶችን ለመቀነስ የተወሰዱ እርምጃዎች እና ስልቶች
እየተገመገሙ የተሻለ የሕግ ተገዥነት እንዲፈጠር የሚደረግበት ሂደት ነው፡፡ በየአለም ጉምሩኮች ሕብረት የተዘጋጀው
የስጋት ስራ አመራር መርህ (Guide) የተለያዩ የስጋት ስራ አመራር ደረጃዎች እንዳለው ያስቀምጣል፡፡ እነዚህም የስጋት
ሰራ አመራር ሂደት ደረጃዎች ተመጋጋቢ ሲሆኑ ውጤት ከማምጣታቸው እና ከሕግ ተገዥነት ደረጃ አንጻር ክትትልና
ግምገማ ይደረግባቸዋል፡፡
17 ምንጮች /Reference |
የስጋት ማዕቀፍ
Communicate and Consult /Establish context
ክትትልና ግምገማ
ግንኙነትና ም ክክር
Risks
ስጋትን መተንተን
/analyzes risk
ስጋንትን መመዘን እና
ደረጃ መስጠት /assess &
prioritize risks context
ስጋትን ማስተናገድ/
Addreess risk
18 ምንጮች /Reference |
የስጋት ቦታዎችን መለየት
ባለድርሻ አካላትን መለየት
የስጋት መስፈርቶችን ማውጣት / የመለየት
ተቋሙ ለሥጋት ያለው የመቀበል ዝንባሌ/ Risk Appetiet/ የማስቀመጥ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡
ማእቀፍ ስናስቀምጥ የሚከተሉትን ጉዳዮች ታሳቢ ሊደረጉ ይገባል
i. የህግ ማዕቀፍ
የታክስ ስጋትን ስጋት ስራ አመራር የሚያከናወንበትን የሕግ አግባብ፣ የስጋት መምረጫ መስፈርቶች እና
የስጋት መመዘኛ ዘዴዎችን የሚቀመጥበት ሂደት ነው፡፡
የኢኮኖሚ ማዕቀፍ የሚቀመጠው ኢኮኖሚው አጠቃላይ ካመነጨው ምርት ምን ያህሉ ገቢ መሰብሰብ እንደሚችል
ለማወቅ እና ሊሰበሰብ ከሚችለው ገቢ አንጻር ከግብር ከፋዩ ምን ያህሉ እንደተሰበሰበ ለማወቅ ነው፡፡ ይህ
የሚከናወነው የስታትስቲክስ ቀመር በመጠቀም፣ በተለያዩ ጥናቶች፣ መረጃዎች ትንተና መሠረት ቢሆንም
ለስጋት ግብዓት እንዲሆን ግምታዊ መጠኖችን በመውሰድ መሥራት፣ እንደ አስፈላጊነቱ የታክስ ልዩነት(Tax-
Gap) በማስላት ነው፡፡ አጠቃላይ የግብር ዕምቅ አቅም፣ መጠን እና የተሰበሰበ የታክስ መጠን ተመጣጣኝ መሆን
አለመሆን መገምገምን ያካትታል፡፡
የማሕበራዊ ማዕቀፍ አጠቃላይ የሕብረተሰቡ የትምህርት፣ የጤና፣ ባህልና አኗኗር የሚጠናበት ሁኔታ ሲሆን
የማህበራዊ እድገት ደረጃ በተለይም ከሕዝብ ቁጥር፣ ወደ ስራ ለመሰማራት የደረሰ ምን ያህል ሕብረተሰብ
እንደሚገኝ እና ከዚህ ውስጥ ምን ያህሉ በግብር ህጉ መሰረት ግብሩን በወቅቱ እና የሚጠበቀብትን ያህል
እየከፈለ መሆኑ የሚጠናበት እንዲሁም ሕብረተሰቡ ለግብር ያለው ባህል፣ ግንዛቤ፣ እና አመለካከት
የሚዳሰስበት ሂደት ነው፡፡
የፖለቲካ ማዕቀፍ አጠቃላይ ሀገሪቱ የምትከተለው ፖሊስና ስትራቴጂ፣ የተለያዩ የታክስና ግብር ሕጎች
የሚዳሰሰቡት ሂደት ነው፡፡
19 ምንጮች /Reference |
II. ስጋት መለየት /Identifying Risks/
ስጋት የሚለየው ምን፣ ለምን፣ የት፣ መቼ እና እንዴት እንደ ተከሰተ በማጣራት ሲሆን ለቀጣይ የስጋት ትንታኔ
መሰረት ነው፡፡ ስጋት በሚለይበት ወቅት ቀድመው ሲወሰዱ የነበሩ ዕርምጃዎች፣ ተገልጋዮች፣ ባለድርሻ አካላት
እንዲሁም ጠንካራና ደካማ ጎኖች መለየት አለባቸው፡፡
ሥጋቶቻችን ምንድናቸው ?
የት አካባቢ ይከሰታሉ?
መቼ ሊከሰት ይችላሉ?
ለምን ሊከሰቱ ይችላሉ?
እንዴት ሊከሰቱ ይችላሉ?
በማን ሊከሰቱ ይችላሉ?
የሥጋት ምንጮች ውስጣዊ እና ውጫዊ ሊሆኑ ይችላሉ
ውስጣዊ
20 ምንጮች /Reference |
በኢንተለጀንስ ትንታኔ፡- ከተለያዩ ምንጮች የተሰባሰቡ መረጃዎች ላይ ትንታኔ በማድረግና ለቀጣይ
ሥራ ዝግጁ በማድረግ፣
የፍተሻ ውጤቶችን ሪፖርት በመጠቀም
የኦዲት ግኝቶችን በመጠቀም
የሥጋት የመከሰት እድል ከዚህ በታች ከተመለከቱት አንዱን የመከሰት እድል ሊይዝ ይችላል፤
21 ምንጮች /Reference |
ሥጋት የመከሰት እድል መግለጫ አመላካቾች
የመከሰት እድሉ ከፍተኛ የሆነ/ በአብዛኛው ሁኔታ ሲከሰት የነበረ እና ወደ ብዙ ጊዜ የተከሰተ/ ለምሳሌ በአመት
በእርግጠኝነት የሚከሰት ፊትም የሚከሰት ከሦስት ጊዜ በላይ
የመከሰት እድሉ መካከለኛ አልፎ አልፎ የሚከሰት አልፎ አልፎ የተከሰተ/ ለምሳሌ በ
የሆነ/ ሊከሰት የሚችል ስድስት ወር አንድ ጊዜ
የመከሰት እድሉ ዝቅተኛ የሆነ/ በተለየ ሁኔታ የሚከሰት በረዥም ጊዜ ቆይታ የተከሰተ /
ላይከሰት የሚችል ለምሳሌ በ አመት አንድ ጊዜ
ስጋት የመከሰት ዕድል (likelihood) ማለት ቀደም ካሉ መረጃዎች በመነሳት ወደፊት ስጋት የመከሰት
እድሉን የምንለካበት ነው፡፡
በስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ መሰረት ስጋት የመከሰት ዕድል/Likelihood/ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ወይም
የመከሰት እድሉ መካከለኛ ወይም የመከሰት እድሉ ዝቅተኛ መሆኑን ለመወሰን ከዚህ በታች የተመለከቱት
ታሳቢ ይደረጋሉ፡-
22 ምንጮች /Reference |
10< x≤ 20% መካከለኛ/ Medium
ሥጋቱ ከተከሰተ የሚያሰከትለው ተጽእኖ ከዚህ በታች ከተመለከቱት አንዱን ሊይዝ ይችላል፤
23 ምንጮች /Reference |
ማስታወሻ፡ (የገንዘብ መጠኑ በተወሰነ ጊዜ ሊወሰን ይችላል፣ ለምሳሌ 3 ዓመት)
በተመሳሳይ በስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ መሰረት ሥጋቱ ከተከሰተ የሚያሰከትለው ተጽእኖ ከፍተኛ ወይም
መካከለኛ ወይም ዝቅተኛ መሆኑን ለማስላት እና ለመወሰን ከዚህ በታች የተመለከቱት ታሳቢ ይደረጋሉ፡-
የሥጋት ደረጃዎች
ሥጋቱ የሚያስከትለው ተጽእኖ
24 ምንጮች /Reference |
ልዩነት የተገኘባቸው ሰነዶች ቁጥር= 3
አጠቃላይ የተከፈለ ቀረጥ እና ታከስ= 2,000,000
በልዩነት የተሰበሰበ ቀረጥ እና ታከስ= 450,000 ቢሆን
= 3/20*100=15%= መካከለኛ
= 450,000 *100
2,000,000
=22.5%= ከፍተኛ
የመጨረሻው የአስመጭው የስጋት ደረጃ በጥምርታው መሰረት ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው፡፡
25 ምንጮች /Reference |
ጥቅምና ጉዳትንስ?
ሥጋትን መቀበል
ስጋትን መቀነስ
ሥጋትን ማስተላለፍ
26 ምንጮች /Reference |
ስጋትን መቀበል ስጋትን ለማስተንገድ ከምንጠቀምበት ስልቶች መካከል አንዱ ሲሆን ስጋትን በመቀበል
የምናስተንግደው በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መፈታት የማይችሉ ስጋቶችን ነው፡፡ ይህም በተወሰነ የጊዜ
ገደብ ውስጥ መፍታት ባለመቻላችን ከተቀበልናቸው ስጋቶች ይልቅ ትኩረታችንን መፍታት በምንችለው እና
በሚገባን ስጋቶች ላይ እንድናደርግ ይረዳናል፡፡ ስጋቶችን ከታች በቀረቡ ዘዴዎች መሰረት ልንቀበላቸው
እንችላለን፡፡
ምንም እንኳን የተለያዩ የስጋት መስተንግዶ ስልቶችን ብንጠቀም ስጋትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ላይቻል
ይችላል፡፡ የሚቻለው ስጋት የመከሰት ዕድል እና ስጋቱ የሚስከትለውን ተጽዕኖ መቀነስ ነው፡፡ ስጋትን
የምንቀንሰው ስጋት የመከሰት ዕድል እና ስጋቱ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ዝቅተኛ እንዲሆን በማድረግ ነው፡፡
በማስተማርና በመመካከር
በመከታተል
ቅድመ መከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም
27 ምንጮች /Reference |
ሥጋቶቹን ከእኛ በተሻለ ሊያስተዳድሩ ለሚችሉ አካላት ማስተላለፍ ተመራጭ በሚሆንበት ወቅት ለምሳሌ
ስጋትን ለሚመለከተው ሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ ማስተናገድ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ለተጓዳኝ ተቆጣጣሪ
መስሪያ ቤቶች ስጋቱን በማስተላለፍ በነሱ በኩል ቁጥጥር መደረጉን እያረጋገጡ ማስተናገድ ይቻላል፡፡
የሥጋት ሥራ አመራር ውጤታማነትን እንደሌሎቹ ደረጃዎች በተራ ሳይሆን በየደረጃው / በእያንዳንዱ የስጋት ሥራ
አመራር ሂደት / መከታተል እና መገምገም አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን መንገዶች ልንከተል እንችላለን -
የሕግ ተገዥነት ደረጃን መለካት በርካታ ጠቀሜታዎች ሲኖሩት ዋነኛዎቹየስጋት ስራ አመራር በተለይም (Risk
Assessment) ዘዴዎችን በመገምገም ማሻሻያ ለማድረግ፣ የታክስ ህግ ተገዠነት ዕንቅፋቶችን ለመፍታት እና የገቢ
አሰባሰብና የህግ ማስከበር ስራዎችን ለመመዘን ነው፡፡
29 ምንጮች /Reference |
ምእራፍ አራት
የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር ትግበራ በዋናው መ/ቤት እና በቅ/ጽ/ቤቶች
የሥጋት ሥራ አመራር በዋናው መ/ቤት እና በቅ/ጽ/ቤቶች የተደራጀ ሲሆን በዋናነት በሚከተሉት የጉሩክ
አሰራሮች ላይ በማኑዋል እና በሲስተም ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡
1. በትራንዚት
2. በገቢ እቃ አወጣጥ
3. በወጪ እቃ አወጣጥ እና
4. በመንገደኞች
30 ምንጮች /Reference |
በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች የተያዙ ሪከርዶች/ /seizure reports፡- ከልዩነት አጣሪ፣ከድንገተኛ ፍተሻ፣ከድህረ
ዕቃ አወጣጥ፣ከኢንተሊጀንስ/
ከታክስ ቅ/ጽ/ቤቶች / ከግብር አሰባሰብ ፣ ከታክስ ኦዲት ፣ ከኢንተሊጀንስ/
በአጠቃላይ ከትሬደር ሪስክ ዳታ ፕሮፋይል ዳታቤዝ፣
ከሌሎች የህግ ማስከበር አካላት ( Law Enforcement)
መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ በመመዘን፣ በማደራጀት እና ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥ ለስጋት
ትንታኔ ጥቅም ላይ ማዋል ፡፡
የግብር ከፋይ የታማኝነት ፒራሚድ በመስራት በሚቀመጠው የህግ ተገዥነት ደረጃቸው መሰረት
የመስተንግዶ ስትራቴጂ በመቅረጽ እንዲተገበር ማድረግ ፤
የግብር ከፋይ የሪሰክ ፕሮፋይል ዳታ ቤዝ በማደራጀት የግብር ከፋይ ፕሮፋይል መስራትና ጥቅም ላይ
ማዋል ፤
የስጋት ስራ አመራር ስርአት በመንገደኞች መስተንግዶ ላይ እንዲተገበር በማድረግ የተቀላጠፈ
አገልግሎት መስጠት ፤
በታክስ አሰባሰብ እና ጉምሩክ ስነስርአት አፈጻጸም ላይ አዳዲስ የሚከሰቱ ስጋቶችን በየወቅቱ በመለየት
የስጋት መስተንግዶ ስትራቴጂ መንደፍ ፤ መተግበር እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካለት ማስተላለፍ ፤
በተመረጡ የንግድ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ግብር ከፋዮች ላይ የስጋት ትንተና በመስራት
(campaign ) በማድረግ የግብር ክፍያ አፈጻጸማቸው እንዲሻሻል ማድረግ፤
የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር ስርአት በአሲኩዳ ++ ሴሌክቲቪቲ ሞጁል በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች
ተግባራዊ እንዲሆን ማስቻል እንዲሁም ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ፤
የታክስ ስጋት ስራ አመራር ስርአት በሲግታስ ሞጁል በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆን ማስቻል
እንዲሁም ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ ፤
የተጣጣመ የታክስ ስርአት እንዲኖር ለክልሎች ተገቢውን ድጋፍ መስጠት ፤
የመረጃ ማሰባሰቢያ እና ለሌሎች የሥጋት ሥራ አመራር አገልገሎት የሚሰጡ ሲስተሞችን ከሌሎች
የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በዋናው መ/ቤት ባሉ
ዳይሬክቶሬቶች እንዲተገበር ማድረግ ፤
በስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ መርህ መሰረት ስጋት የመከሰት እድልን / likelihood / እና ስጋቱ
የሚያስከትለውን ተጽእኖ / consequence / በመስራት ስጋትን መተንተን /Risk Analysis/ እና የስጋት
ደረጃ ማውጠት /Risk scoring/
31 ምንጮች /Reference |
የስጋት መምረጫ መስፈርቶች ላይ የስጋት ትነታኔ በመስራት እና የስጋት ደረጃ በማውጣት
ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ በማኑዋል በተደራጀ ሰነድ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት ወይም
በኤሌክተሮኒክስ ዘዴ ወደ ሲስተም /አሲኩዳ ++ እና ሲግታስ/ እንዲካተት በማድረግ በሁሉም
ቅ/ጽቤቶች መተግበር፤
ከተሰራጩ የስጋት መምረጫ መስፈርቶች እና ፕሮፋይሎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ
ከተጠቃሚዎች እና ከሲስተም ግብአት በማሰባሰብ ፣ግብረ መልሱን በማጠናቀር ያስከተሉትን ውጤት
በመገምገም እና በመመዘን ማሻሻያዎችን መስራት
በመንግስት ልዩ አገልገሎት እዲጠቀሙ የተፈቀደላቸውን አምራች ድርጅቶች በሲስተም በዝቅተኛ
የስጋት ደረጃ እንዲስተናገዱ በማድረግ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት
በዝቅተኛ የሥጋት ደረጃ የሚስተናገዱ መንግስታዊና አለም አቀፍ ድርጅቶችን እና ዲፕሎማቶችን
በመለየት በዝቅተኛ የሥጋት ደረጃ እንዲስተናገዱ ማድረግ
የስጋት ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ / የህግ ተገዥን ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን/ ግብር ከፋዮችን እና
አስመጪዎችን ችግራቸውን ወይም ምክንያታቸውን መለየት ወይም በማጥናት፣ እንደ እስፈላጊነቱ
ማስተማር፣ ኦዲት እንዲደረጉ ለኦዲት ክፍሎች መስጠት፣ የከፉትን ደግሞ በኢንተለጀንስ ክትትል
እንዲደረግባቸው ማድረግ
በተደጋጋሚ በዝቅተኛ የሥጋት ደረጃ ላይ የሚገኙትን / የህግ ተገዥን ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑትን/
ግብር ከፋዮች እና አስመጪዎችን ከየቅ/ጽ/ቤቶቹ በማሰባሰብ አጠቃላይ የዕውቅና መስጫ፣ የማበረታቻ
መድረክ በማዘጋጀት ማበረታታት፣ በየቅ/ጽ/ቤቱ የተቀላጠፈ መስተንግዶ እንዲያገኙ ማስቻል
ቅ/ጽ/ቤቶችን መደገፍ
በዋናው መ/ቤት የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር የሚያከናውነው ከጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ
ስጋቶችን በገቢ፣ ወጪና ተላላፊ ዕቃዎች እና መንገደኞች ላይ በመለየትና በመተንተን በኤሌክቶሮኒክ እና
በተለያዩ መንገዶች በወጥነት በአገር አቀፍ ደረጃ (national) ስጋቶቹ እንዲስተናገዱ ማድረግ ነው፡፡ በዋናው
መ/ቤት የጉምሩክ ስጋት ስራ አመራር ከታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች መረጃዎችን ማሰባሰብና ማደራጀት
በጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈፃፀም የሚፈጠሩ ስጋቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የስጋት ምዘና/Risk Assessment/
ለማከናወን ጥራት ያለው መረጃ ማሰባሰብና መደራጀት ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ መረጃዎች ከውስጣዊ እና
ውጫዊ አካላት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ወይም በማኑዋል ሊሰበሰብ ይችላል
32 ምንጮች /Reference |
የውስጥ የመረጃ ምንጮች
ከጉምሩክዳታቤዝ /ASYCUDA++/፣
ከትሬደር ሪስክ ዳታ ፕሮፋይል ዳታ ቤዝ /በጉምሩክቅ/ጽ/ቤቶች በማኑዋል ከታች ከተጠቀሱ የስራ
ክፍሎች የተያዙ መረጃዎች
ከልዩነትአጣሪ
ከድንገተኛ ፍተሻ
ከድህረ ዕቃ አወጣጥ
ከኢንተሊጀንስ
ከመንገደኞች የሥራ ሂደት
የውጪ የመረጃ ምንጮች
ከሌሎች የህግ ማስከበር አካላት /ከደህንነት፣ፖሊስ፣ወ.ዘ.ተ
ከሦስተኛ ወገን የመረጃ ምንጭ ለምሳሌ፡-
ከባንኮች
ኢንሹራንሶች
ከአየር መንገዶች
ከንግድ መርከብ
ከንግድና ኢንዱስትሪ
ከኢንተርኔት
ከአለም አቀፍ ተቋማት ድህረገጽና ዳታቤዝ /WCO - CEN/
33 ምንጮች /Reference |
ዕቃዎች ላይ በሲስተም የስጋት ደረጃዎች እየተጣለ በስጋት ደረጃዎች መሰረት የተሳለጠ አገልግሎት መስጠት
እና ቁጥጥር በማድረግ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለደንበኞች አገልግሎት ይሰጣል፡፡መስፈርቶቹም፡-
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ከታች እንደሚከተለው የቀረቡት መምረጫ መስፈርቶች አሲኩዳ ሴሌክቲቪቲ
ሪስክ ሞጁል ውስጥ ተካተው የስጋት ደረጃዎችን ለመወሰን ያገለግላሉ፡፡
አሲኩዳ++ ሴሌክቲቪቲ
የአስመጪዎችየስጋት ፕሮፋይል
የጉምሩክ አስተላላፊዎች
የስጋት ፕሮፋል
34 ምንጮች /Reference |
የዕቃዎች ታሪፍ /Tariff/
የዕቃዎች ዋጋ / Value/
የዕቃዎች ስሪት ሀገር
የስጋት ደረጃ የመስተንግዶ ስተራቴጂዎች
ቢጫ ሰነድ ምርመራ
ሰነድ(ፌዝቬት
)
አረንጓዴ መልቀቂያ /PCA Intellegence/
የስጋት ፕሮፋይል ማለት የሥጋት ቴምፕሌት ሲሆን የሥጋት አመላካቾችን /Risk Indicators/ በመጠቀም
ኢላማዎች /Targets ለመምረጥ የምንጠቀምበት ነው፡፡ እነዚህ አመልካቾች የተከሰቱ ወይም ሊከሰቱ የሚችሉ
ሥጋቶችን ይጠቁሙናል፡፡ ፕሮፋይሎች ከፍተኛ ሥጋት ያላቸውን ትራንዛክሽኖች ወይም ክስተቶችን ምንም
ወይም ዝቅተኛ ሥጋት ካላቸው ለመለየት ያስችሉናል፡፡ ይህም ውስን የሆነውን የሰውና የገንዘብ ሀብታችንን
በተገቢው ሁኔታ መጠቀም እንድንችል ይረዳናል፡፡ የስጋት ፕሮፋይል ከታች የተዘረዘሩትን ይዘቶች ያካትታል፡-
35 ምንጮች /Reference |
ፕሮፋይሉ ለምን ያህል ጊዜ አገልግሎት እንደሚሰጥ፣
ተገቢውን ሀብት (የሰው፣ የገንዘብ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን)፡፡
36 ምንጮች /Reference |
ከጉምሩክ ዳታቤዝ /ASYCUDA++/
ከታክስ ዳታቤዝ /SIGTAS/
ከ TPRDP ዳታቤዝ/ በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች የተያዙ ሪከርዶች/ /seizure reports/
ከልዩነት አጣሪ
ከድንገተኛ ፍተሻ
ከድህረ ዕቃ አወጣጥ
ከኢንተሊጀንስ
ከታክስ ቅ/ጽ/ቤቶች
ከግብር አሰባሰብ
ከታክስ ኦዲት
ከኢንተሊጀንስ
ከሌሎች የህግ ማስከበር አካላት /ከደህንነት፣ፖሊስ፣ ወ.ዘ.ተ
ከሦስተኛ ወገን የመረጃ ምንጭ
ከባንኮች
ኢንሹራንሶች
ከ ህግ ማስከበር አካላት /ደህንነት
ከአየር መንገዶች
ከንግድ መርከብ
ከንግድና ኢንዱስትሪ
ከተለያዩ ሰነዶች ለምሳሌ ቢል ኦፍ ሎዲንግ/የማስጫኛ ሰነዶች/ ኤርዌይቢል ኢንቮይስ ወ.ዘ.ተ
ከኢንተርኔት
ከአለም አቀፍ ተቋማት ድህረ ገጽና ዳታ ቤዝ /WCO - CEN/
የተሰበሰቡ መረጃዎችን መመዘንና ማደራጀት
የመረጃውን ትክክለኛነትና ተአማኒነት ማጥራት
የአንድ መረጃ ጥቅም የሚወሰነው በትክክለኛነቱ፣በጥራቱና በተአማኒነቱ ነው ስለዚህ መረጃው ከትክክለኛና
ከታማኝ ምንጭ ስለመገኘቱ ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
የተሰበሰቡ መረጀዎች ፕሮፋይል ሊሰራለት ከታሰበው ድርጅት ዕቃ ወይም ሀገር ጋር ተያያዥ ስለመሆኑ መለየትና
ማጣራት
መረጃውን መተንተን (Analyze the data)
መረጃውን ስንተነትን የሚከተሉትን ጉዳዮች ልንመለከት እንችላለን፡-
የጋራ ባህሪያትን መለየት
ግንኙነቶችን መለየት
37 ምንጮች /Reference |
የሥጋት አመላካቶችንና ዕውነታዎችን መለየት/Indicators and trends identification/
ልንከተል የሚገባንን የሥጋት መስተንግዶ ማስቀመጥ/Risk treatment/
የሥጋት ትንታኔ ማካሄድ እና የሥጋት ደረጃ ማውጣት/Risk Analysis and Risk Score
በሥጋት ሥራ አመራር ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ በተቀመጠው መሰረት የተሰበሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ
የሥጋት ትንታኔ /Risk Analysis/ እንደሚከተለው ይሰራል፡-
በቅድሚያ ሥጋት የመከሰት እድል / Likelihood እና ሥጋቱ የሚያስከትለው የኢኮኖሚ ተጽእኖ /
Consequence ይሰራል
በመቀጠል ተሰብስቦ በተተነተነው መረጃ መሰረት የስጋት ደረጃዎችን እንደደረጃቸው በሚከተለው መልኩ
ይቀመጣል
ፕሮፋይል ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት የሚያስከትለው ተፅዕኖ መሞከርና መታየት አለበት፡፡በመቀጠል ፕሮፋይሉ
በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶችና በዋናው መ/ቤት ባሉ ዳይሬክቶሬቶች ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
ፕሮፋይሎች ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ ያስከተሉትን ተጽእኖ ወይም ያስከተሉትን ውጤት በመገምገም እና
በመመዘን ቀጣይ የማሻሻያዎች ስራዎችን ይሰራል፡፡
ፕሮፋይል ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ ከሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶችና በዋናው መ/ቤት ካሉ ዳይሬክቶሬቶች ግብረ-መልስ
/ግብዓት/ በማሰባሰብ ቀጣይ ማሻሻያ ማድረግ
ፕሮፋይሎች የተሰወነ ጊዜ አገለግሎት ከሰጡ በኋላ በሚሰበሰቡ ግብዓቶች /መረጃዎች/ መሰረት መሻሻል አለባቸው
ምክንያቱም፡-
ሰዎች በየጊዜው አዳዲስ ነገሮችን በመጠቀም የወንጀል ተግባር ስለሚፈፅሙ
38 ምንጮች /Reference |
የግብር ከፋዮች ባህሪ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ
ፕሮፋይሎች ሁሌም ትክክል ላይሆኑ ስለሚችሉ
ከተጠቃሚዎች የተለየ ግብዓት /ግብረ-መልስ/ ሲኖር
የአስመጪዎች የስጋት ፕሮፋል የሚዘጋጀው ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎችን በማሰባሰብና በማደራጀት የስጋት ትንታኔ
በመመዘኛ መስፈርቶች መሰረት በማከናወን ሲሆን በዋናነት ስ ጋት የመከሰት ዕድል /Likelihood እና ስጋቱ
የሚያስከትለው ተጽዕኖ /Consequence በማስላት ነው፡፡ስጋት የመከሰት ዕድል /Likelihood ለማስላት አንድ
አስመጪ ወይም የጉምሩክ አስተላላፊ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ካቀረባቸው ዕቃዎች ወይም ዲክላራሲዮኖች እንጻር
የጥፋተኝነት ሪከርድ የተገኘባቸውን ፐርሰንቴጅ በማስላት ነው፡፡ እንዱሁም ስ ጋቱ የሚያስከትለው ተጽእኖ
/Consequence/ የሚሰላው አስመጪው በራስ ተነሳሽነት ካቀረበው የገንዘብ መጠን በተጨማሪ መንግስት ሊያጣ
የነበረውን በልዩነት የተከፈለ የገንዘብ መጠን ለአጠቃላይ ለተከፈለ የገንዘብ መጠን ፐርሰንቴጅ በማስላት ሊያደርስ የነበረው
ተጽዕኖ Consequnce በማስቀመጥ ነው፡፡ ይህም ከላይ በምእራፍ ሶስት በቀረበው ቀመር መሰረት የሚሰራ ይሆናል፡፡
የጉምሩክ አስተላላፊውች የስጋት ፕሮፋል አሰራር ከአስመጪዎች የስጋት ፕሮፋይል አሰራር ጋር በተመሳሳይ
መልኩ የሚከናወን ቢሆንም በግብዓትነት ከሚውሉ መረጃዎች ጋር ተያይዞ ልዩነቶች አሉ፡፡ ለጉምሩክ
አስተላላፊዎች የስጋት ፕሮፋይል ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎች በዋናነት የሚሰበሰቡት አስተላላፊዎች
የሚፈጽሙት ጥፋት የጉምሩክ አስተላላፊዎች በመመሪያ 64/2003 ዓ.ም በተገለጹ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡
የታሪፍ ስጋት ደረጃ በአምስት ንዑስ-መስፈርቶች ድምር አማካይ ውጤት የሚገኝ ሲሆን እያንዳንዱ ንዑስ-
መስፈርት በስጋት ስያሜና (RisK Assignments) እና በስታቲስቲካል ካልኩሌሽን (statistical calculation)
የሚሠራ ነው፡፡ አምስቱ ንዑስ-መስፈርቶች፡-
I. ጥቅል የቀረጥና ታክስ መጣያ ምጣኔ መሰረት የስጋት ትንተና መስራት (Aggregate
Computation Risk)
39 ምንጮች /Reference |
ይህ ንዑስ-መስፈርት በእያንዳንዱ ዕቃ (HS code) ላይ የሚጣለውን ጥቅል ቀረጥና ታክስ ምጣኔ
መሠረት በማድረግ የሚሰራ ሲሆን የእቃዎችን ታሪፍ ምጠኔ በእያንዳንዱ ኤች ኤስ ድምር መስራት
(Agregate Duty and Tax) በኤች ኤስ የታሪፍ አግርጌት ድምር ስትንዳርድ ዲቬሽን ከርቭ
በመጠቀም ይሰራል፡፡
የዕቃዎች ዋጋ /Value/
የዕቃዎች ዋጋ ስጋት ደረጃ በሁለት ንዑስ-መስፈርቶች ድምር አማካይ ውጤት መሰረት በስታቲስቲካል
ካልኩሌሽን (statistical calculation) የሚሠራ ነው፡፡
40 ምንጮች /Reference |
1. ዕቃዎች ለጠቅላላ ቀረጥና ታክስ አስባሰብ ያላቸው ድርሻ (contribution to revenue
collection
ይህ ንዑስ መስፈርት በአያንዳንዱ ዕቃ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውሰጥ የተከፈለ ቀረጥና ታክስ
በዓመት ውስጥ ለተሰበሰበው ገቢ ያለው ድርሻ በመቶኛ ተሰልቶ የሚሰራ ነው፡፡ ይህ ተግባር
በቀጣይም ስታንዳርድ ዲቪዮሽንን መሠረት በማድረግ የሚሠራ ሲሆን የስጋት ደረጃውም
ለጠቅላላ ገቢ አሰባሰብ ባላቸው ድርሻ መሠረት የሚጣል ይሆናል፡;
የሀገራት ስጋት ትንተና እቃዎች ከተለያዩ ሀገራት በሚመጡበት ጊዜ የሚኖራቸው መጭበርበር ምን ያህል
እንደሆነ ለማወቅ ከዚህ ቀደም ከነበሩ የገቢ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ይሰራል፡፡የስሪት ሀገር ስጋት ደረጃ
በአራት ንዑስ መስፈርቶች መሰረት ይጣላል፡፡
41 ምንጮች /Reference |
እንደተገኘ በማስላት ነው፡፡ ስጋቱ የሚያስከትለው ተጽዕኖ የሚሰላው ከእያንዳንዱ ሀገር የተሰበሰበ
የቀረጥና ታክስ በልዩነት ከተሰበሰበው እንጻር በማስላት ነው፡፡ በመጨረሻም (consequence and
likelihood combination matrix) በመጠቀም ስጋት የሚጣል ይሆናል፡፡
3. ሀገራት ከዚህ ቀደም ያላቸው ተሞክሮ (Previous Risk knowledge on Countries)
ይህ ንዑስ መስፈርት ሀገራት ከዚህ ቀደም ከሚልኳቸው ዕቃዎች ጋር በተያያዘ ያላቸውን የሕግ
ተገዥነት ተሞክሮ በመለየት የሚጣል ነው፡፡ ይህም በየሀገራት ስጋት በመሰየም (Risk Assignment)
የሚሠራ ይሆናል፡፡
4. የአካላዊ ፍተሻ ውጤት (Examination result Risk)
ይህ ንዑስ መስፈርቱ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በአካላዊ ፍተሻ የሚኙትን ልዩነቶች
በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በመለየት ስጋት የሚጣልበት አሰራር ነው፡፡ ይህም የሚጣለው የስሪት ሀገርና
የጭነት ሀገር ተመሳሳይ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ ነው፡፡
በመጨረሻም የአራቱን ንዑስ መስፈርቶች ድምር ውጤት ስታንዳርድ ዲቪዮሽንን በመጠቀም ስጋት
የሚጣል ይሆናል፡፡
ልዩ ፈቃድ/Special Requirement
ገደብ የተደረገባቸው እቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት የሚመለከታቸው ባለስልጣን መ/ቤቶች
ማረጋገጫ እየሰጡባቸው የሚገቡትን በመለየት ስጋት ደረጃ ማስቀመጥ፡፡ የማህበረሰቡን ደህንነት ከመጠበቅ
አንጻር እቃዎቹን ተከታትሎ ተገቢውን ማስረጃ ቀርቦባቸው ወደ ሀገር እንዲገቡ ስልሚያደርግ አስፈላጊ ነው፡፡
42 ምንጮች /Reference |
በታሪፍ መጽሀፉ ከተዘረዘሩት እቃዎች ልዩ ፈቃድ የሚያስፈልጋቸውን ዝርዝር መለየት በተለዩት መሰረት ስጋት
ደረጃቸውን በመካከለኛ ማስቀመጥ ሌሎችን /ከዚህ ውጪ/ ያሉትን በዝቅተኛ ስጋት ደረጃ ማስቀመጥ፡፡
በስጋት ስራ አመራር አመለካከት የመንግስት ድርጅቶች ማለት የመንግስት ባለበጀት መ/ቤቶች ማለት ሲሆን
መንግስት ከዕቃዎች ግዚ ጋር ተያይዞ የቁጥጥር ስርዓት ያለው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
ድርጅቶቹ ለባለስልጣን መ/ቤቱ እንደ አጋር ተደርገው ሊቆጠሩ የሚችሉ በመሆኑ ስጋት የመፈጠር እና ስጋቱ
የሚያስከትለው ተፅእኖ በዝቅተኛ የስጋት ድረጃ ላይ ያስመድባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ያለንን ውስን ሀብት
በሌሎች ሥጋቶች ላይ ማዋል ተገቢ ይሆናል፡፡
የዲፕሎማትና አለም አቀፍእና አህጉር አቀፍ ድርጅቶች/ Diplomatic and International Organizations
List/
የበቬና ኮንቬንሽን እና በሌሎች ስምምነቶች ያለመፈተሸ መብት ያላቸው ድርጅቶች በዝቅተኛ የስጋት ድረጃ
ላይ በሲስተም እንዲመደቡ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ እነዚህ መብት ያላቸው አካለት በዝቅተኛ የሥጋት
ደረጃ ይመደባሉ፡፡
መንግስት ሀገራችን ካለችበት ድህነት በአጭር ጊዜ ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ደረጃ እንድትሰለፍ ለማድረግ የልዩ
የጉምሩክ አገልግሎት አሰራር ዘርግቷል፡፡ ይህም ለሀገራችን ልማት ከፍተኛ ሚና የሚኖራቸውን
የአምራችና የላኪ ዘርፍ እንዲሁም ኢንቨስትመንትና ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ በልዩ ሁኔታ የተቀላጠፈ
43 ምንጮች /Reference |
የጉምሩክ አገልግሎት የሚያገኙበት አሰራር ዘርግቷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ድርጅቶቹ መስፈርቱን
አሟልተው ከሚመለከታቸው አካላት በኩል ሲላኩ በዘርፉ የተሰማሩበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በማጣራት
ቢስተም በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ እንዲስተናገዱ የማኑፋክቸሪንግ ሊስት ውስጥ ይካተታሉ፡፡ ከተስተናገዱ
በኋላ በድህረ ዕቃ አወጣጥ እና በኢንተነጀንስ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡
የአለም ጉምሩኮች ሕብረት Safe Framework of Standards to Secure and Facilitate Global Trade
እንደሚጠቁመው ታማኘ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ማለት በአለም አቀፍ ደረጃ ከዕቃዎቸ እንቅስቃሴ ጋር
በተያያዘ የጉምሩክ ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ህጎች እንደሚያከብር በጉምሩክ አስተድደር በኩል
ማረጋገጫ የተሰጠው አካል ማለት ነው፡፡ ታማኝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ/ AEO አሰራር መተግበር ተቋሙ
ከተገልጋዮች ጋር መልካም ግንኙነት/partnerships እንዲፈጥር የሚያግዝ ሲሆን ተቋሙ በተለያዩ
ዘርፎች ለተመደቡ ድርጅቶች ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ለአምራችና ላኪዎች፣
አጓጓዝ ድርጅቶች፣ ወኪሎች፣ ወደቦች፣ መጋዘኖች፣ ተርሚናሎች እና ወ.ዘ.ተ፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ
የስጋት ስራ አመራር በጉምሩክ በኩል ለድርጅቶች ታማኘ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት ማረጋገጫ
ለመስጠት የሚረዳ መመዘኛ ነው፡፡ ድርጅቶች በራሳቸው ፈቃድ ለታማኘ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት
ሲያመለክቱ ባለሥልጣኑ ድርጅቶችን ለመምረጥ እንደ እንድ መስፈርት የድርጅቶችን በጉምሩክ ስነ-
ስርዓት አፈጻጸምና ከግብረ አከፋፈል ጋር ያላቸውን የታማኝነት ደረጃ/የፕሮፋይል የስጋት ደረጃ
ይጠቀማል፡፡
በመሆኑም ለተመረጡ ታማኝ ለሆኑ ቀለል ያለ የዕቃ ዲክላራሲዮን አቀራረብና የዕቃ አወጣጥ ሥነ
ሥርዓት ተፈጻሚ ሲሆን ዕቃዎችን ለመለየት የሚያስፈልጉ ውስን መረጃዎች እስከቀረቡ ድረስ
የተሟላው የዕቃ ዲክላራሲዮን በቀጣይነት እንዲቀርብ በመፍቀድ ዕቃዎቹን በሰማያዊ የስጋት ደረጃ
እተመደቡ ይስተናገዳሉ፡፡ በዚህ ስርዓት የሚገቡ እቃዎች በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ላይ እንዲመደቡ
ያስቻለው የሕግ ተገዥነትን ለማበረታታ ሲሆን በድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት በኩል የዕቃ ዲክላራሲዮን
ትክክለኛና ተአማኒነት ያለው መሆኑን እና ሌሎች የጉምሩክ ግዴታዎች መከበራቸውን ማረጋገጥ
ስለሚቻል ነው፡፡
መኪና ከሌሎች ዕቃዎች አንጻር በባህሪው የማጭበርበር ድርጊት ሊፈጸምበት የሚችል ዕቃ ነው፡፡ የመኪናን
ቀረጥና ታክስ ለማስላት መኪናው የተመረተበትን ዓመት፣ የመኪናውን ሞዴል እና የመኪናወን ሞተር ቁጥር ከቀረበው ሰነድ
44 ምንጮች /Reference |
ጋር ማመሳከር ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም መኪና እና የመኪናን ሰነድ ባለማመሳከር የሚፈጠረው የስጋት ተፅዕኖ ከፍተኛ
በመሆኑ ሁሉም መኪናዎች በስስተም በከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ ይመደባሉ፡፡
ጥሬ ዕቃዎች የሚባሉት ለምርት አገልግሎት ግብዓት የሚሆኑ በኢንቨስትመት ማበረታቻ ስርዓት የተካተቱ
የሁለተኛ መደብ ዕቃዎች እና የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ቅናሽ ያላቸው ዕቃዎች ናቸው፡፡ የመካከለኛ ስጋት
ዕቃዎች /Yellow List Commodities/የሚባሉት ደግሞ ፍተሻ ለማድረግ የጉምሩክ ላብራቶሪ
የሚያስፈልጋቸው በመሆናቸው ምክንያት በተጓዳኝ መ/ቤቶች በኩል ቁጥጥር የሚደረግባቸው የኬሚካልነት
ባህሪ ያላቸው ዕቃዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ዕቃዎችን በተመለከተ የሚፈጠሩ ስጋቶች በዶክመንት ምርመራ
ማስተናገድ የሚቻል በመሆኑ እንዲሁም ስጋቱን ለተጓዳኝ መ/ቤቶች በማስተላለፍ በእነሱ በኩል ቁጥጥር
መደረጉን እያረጋገጡ ለማስተናገድ በማሰብ በሲስተም በመካከለኛ ስጋት ደረጃዎች ላይ እንዲመደቡ
ይደረጋል፡፡
የስጋት ስራ አመራር የራንደም መረጣን አዳዲስ ስጋቶችን በመለየት እንዲስተናገዱ ለማድረግ ስለሚያግዝ
እንደ አንድ የስጋት መምረጫ ምስፈርት ይጠቀማል፡፡ በዚህም ምክንያት በየቀኑ በዝቅተኛ እና መካከለኛ
የስጋት ደረጃዎች ከሚስተናገዱ ሰነዶች መካከል አምስት በመቶ በሲስተም በከፍተኛ የስጋት ደረጃ
እንዲስተናገዱ ያደርጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የራንደም መረጣ የስጋት መምረጫ መስፈርቶች እና የስጋት
ደረጃዎች ተገማች /predictable/ ሆነው ያልተፈለጉ አሉታዎ ተፅዕኖዎች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ
ይጠቅማሉ፡፡
45 ምንጮች /Reference |
አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በተዘጋጁ ሲስተሞች ወይም በማኑዋል መያዝና መጠቀም ለዋናው
መ/ቤትም ማስተላለፍ ፣
በቅ/ጽቤቱ ዙሪያ ያሉ አዳዲስ ስጋቶችን መለየት፣መተንተን እና ማስተናገድ ለዋናው መ/ቤትም
ማስተላለፍ ፣
በየጊዜው ሪፖርት ለሚመለከታቸው ክፍሎች እና ለዋናው መ/ቤት ማቅረብ ፣
የስጋት ስራ አመራር ውጤታማነትን መገምገም እና ግብረ መልስ መስጠት ፣
የቅ/ጽ/ቤቱን ግብር ከፋዮች በሴክተር እና በደረጃ በመከፋፈል የህግ ተገዥነት ደረጃቸውን ማጥናት
ወይም መለየት የህግ ተገዥነት ደረጃን የሚያሳይ የታማኝነት ባህሪ ደረጃ የሚያሳይ ፒራሚድ
ማዘጋጀት፣
በህግ ተገዥነት / በታማኝነት ደረጃቸው አይነት ሊተገበሩ የሚገባቸውን የመስተንግዶ ስትራቴጂዎች
መንደፍ ስትራቴጂዎችን አቅዶ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመተባበር መተግበር ፣
ለህግ ተገዥ መሆን ለማይፈልገውን እና የከፋውን በመለየት ለቅ/ጽ/ቤቱ ኢንተለጀንስ ክፍል እና
ለዋናው መ/ቤት ማስተላለፍ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ ፣
እንዲሁም ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ላይ ያሉ ግብር ከፋዮችን መደገፍ ቀላልና ቀልጣፋ መስተንግዶ
እንዲያገኙ ማድረግ ፣ እውቅና እንዲሰጥ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ፣
TPRDP ላይ የሚገቡ መረጃዎች በሁሉም ክፍሎች በአግባቡ እና በሚፈለገው ጥራት መግባታቸውን
በመከታተል ስለአፈጻጸሙ ለዋናው መ/ቤት ሪፖርት ማድረግ
በአሁኑ ወቅት ከገቢ ዕቃዎች ጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈጻጸም በስተቀር ሌሎቹ ማለትም ትራንዚት ቁጥጥር፣
ወጪ ዕቃዎች፣ መንገደኞች እና የመጋዘንን ቁጥጥር በሲስተም የታገዘ የስጋት ስራ አመራር ባለመኖሩ የማኑዋል
አሰራር መተግበር አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በማኑዋል የሚጣሉ የስጋት ደረጃዎች አሰራር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት ላይ የሚደረግ ቁጥጥር ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና በተመረጠ ሁኔታ በማይሆንበት ጊዜ
ያልተፈለገ የጊዜ እና የሀብት ብክነት በማስከተል ሀገርን ይጎዳል፡፡ ቁጥጥሩን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ
በስጋት ስራ አመራር መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በትራንዚት ላይ ላሉ ዕቃዎች ስጋት ለመጣል
ከታች የተገለጹት የስጋቶች መምረጫ መስፈርቶች ያስፈልጋሉ
46 ምንጮች /Reference |
ከኢተለጀንስና ከተለያዩ አካላት ጥቆማ የሚቀርብባቸው፤
የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ከሌላቸው ሀገራት የተመረቱ ወይም የተጫኑ
በአደንዛዝ ዕጽዝውውር ከታወቁ ሀገራት የተጫኑ ከሆነ
በመንገድ ወረቀቱ ላይ ጨረር አመንጪ ዕቃዎች የተገለጹ ከሆኑ፤
በመንገድ ወረቀቱ (T1) ላይ ሪማርክ የተፃፈ ከሆነ፤
ኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎች ሲመጡ
ዕቃዎች ካላቸው ባህሪ አንጻር የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጸምባቸው በየወሩ በፍተሻ እና ሰነድ
ምርምራ ሪፖርት የቀረበባቸው፤ /ከ TPRDP ወይም ከሌሎች በሲስተም ወይም በማኑዋል
ከሚገኙ መረጃዎች/፤
ሶስት እና ከዚያ በላይ የከባድ ጥፋት ሪከርድ ባለባቸው የጉምሩክ ስነ-ስርዓት አስፈጻሚዎች
የሚስተናገዱ ሰነዶች፤ /ከ TPRDP ወይም ከሌሎች በሲስተም ወይም በማኑዋል ከሚገኙ
መረጃዎች/፤
የልዩ የጉምሩክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች እና የታማኝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች (AEO) ዕቃዎች
ከሌሎች ጭነቶች ጋር ተቀላቅለው ሲመጡ፤
በሚያዙ የጥፋት መረጃ መሰረት በተደጋጋሚ የአገላለጽና የትርፍ ልዩነት የሚገኝባቸው ድርጅቶች
ሲያስመጡ፤ ወይም በተደጋጋሚ የሰነድ ምርመራ፣ የፍተሻ እና የድህረ ዕቃ አወጣጥ ግኝት
የሚገኝባቸው አስመጭዎች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች፤ (ከ TPRDP ወይም ከሌሎች በሲስተም
ወይም በማኑዋል በተያዙ መረጃዎች መሰረት)፤
ከጭነቱ ጋር የማይሄድ የተጋነነ ትራንስፖርት ወጪ፤ (ከዕቃው ጋር ተመጣጣኝ ያልሆኑ
የትራንስፖርት ክፍያዎች መኖሩ ሲረጋገጥ)፤
ተሽከርካሪው ከሚጠበቅበት ጊዜ በላይ ዘግይቶ ሲደርስና አሳማኝ ምክንያት ካልቀረበ፤
መኪናው በተነሳበት ሁኔታ የደረሰ ካልሆነና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር (ሲሉ የተበጠሰ ከሆነ)
የንግድ እቃዎች በብትን ጭነቶች ሲመጡ፤
የሲል ቁጥር ልዩነት ሲኖር፤
በክፍልፋይ የሚጓጓዙ ጭኖቶች፤
ትላልቅ ወይም ግዙፍ እቃዎች ሆነው በአይን በማየት ብቻ የሚለዩ (የፋብሪካና የፕሮጀክት
ማሽነሪዎች እና ዕቃዎች)፣
በመንግስታዊና በመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚገቡ ዕቃዎች፣
47 ምንጮች /Reference |
በትምህርት ተቋማት የሚገቡ የትምህርት መገልገያ መሳርያዎች፤
በታማኝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች (AEO) የሚገቡ ዕቃዎች፣
በቬና ኮንቬንሽን እና በሌሎች ስምምነቶች መሰረት ያለመፈተሸ መብት የተሰጣቸው
ሲያስመጡ፣
በጉምሩክ ልዩ አገልግሎት ተጣቃሚ የሆኑ አምራች ድርጅቶች የሚገቡ፣
ክፈት ጭነቶች ሲመጡ በማየት ብቻ ማለፍ የሚችሉ ከሆነ፤
የወጪ ትራንዚት
በወጪ ዕቃዎች ላይየሚደረግ ቁጥጥር ስጋትን መሰረት ያደረገ ሆኖ ቁጥጥርና የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጡ ሚዛናዊ የሆነ
እንዲሆን ስጋት ስራ አመራር ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪ ሀገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸው ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው
እንዲወጡ ይረዳል፡፡ ወጪ ዕቃዎች ላይ በማኑዋል ስጋት ለመጣል ከታች የተገለጹት የስጋቶች መምረጫ መስፈርቶች
ያስፈልጋሉ፡፡
የቁም እንስሳት፣
ጫት፣ቡና፣አበባ፣የቅባት እህሎች፣ ቅመማ ቅመሞች፣
ቆዳ፣
ሌሎች የተጓዳኝ መ/ቤቶች ፈቃድ የሚጠየቅባቸው ዕቃዎች፣
ለ) በዋጋ ወይም በብዛት ቀረጥና ታክስ ከማይከፈልበት መጠን በላይ የሆኑ ወይም
ክልከላ ወይም ገደብ የተደረገባቸውን ዕቃዎች የያዙ መንገደኞች
እንዲጠቀሙበት በቀይ ምልክት የተለየውን የማለፊያ መስመር፡፡
በመደንገግ በራስ ተነሻሽነት የሕግ ተገዢ እንዲሆኑ የሚያደርግ መስመር እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ነገርግን
በተመረጠ ሁኔታ ስጋት መሰረት አድርጎ በአረንጓዴ ምልክት ከሚያልፉት መካከል ቁጥጥር ለማድረግ
የስጋት መምረጫ መስፈርቶች አስፈላጊ ናቸው፡፡ በዛው አዋጅ ንዑስ አንቀጽ 3 ባለሥልጣኑ
በመንገደኞች ላይ የሚፈጸመውን የጉምሩክ ቁጥጥርና የያዟቸውን ዕቃዎች የመልቀቅ ተግባር
ለማቀላጠፍ አግባብ ካላቸው ሌሎች አካላት ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና
በቅድሚያ ሊገኙ የሚችሉ የተሳፋሪዎች መረጃዎች ካሉ እነዚህኑ ሊጠቀም ይችላል፡፡ በመሆኑም
የመንገደኞች ቅድመ መረጃ በመጠቀም እንዲሁም ከታች የተገለጹትን የስጋት መምረጫ መስፈርቶችን
መሰረት በማድረግ ሥጋትን መጣል ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለሥልጣን መ/ቤቱ የመንገደኞችን
49 ምንጮች /Reference |
የሥጋት ደረጃ ለመወሰን መመሪያ ቁጥር 96/2006 አውጥቶ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን የሚከተሉትን
መስፈርቶች ይጠቀማል፡፡
50 ምንጮች /Reference |
ተመላላሽ መንገደኛ(በሦስት ወር አንድ ጊዜና ከዛ በላይ) በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ውጭ
ሀገር ወይም በሀገር ውስጥ የሚመላለስ፤
ከዚህ በፊት ሪኮርድ የተያዘበት መንገደኛ፤
የጉዞው መነሻ ሀገራት ከከፍተኛ ስጋት ደረጃ ያላቸው ሀገራት ሲሆን፤
የተቆጣጣሪ መ/ቤቶች ፈቃድ የሚጠይቅ ዕቃ የያዘ መንገደኛ፤
ለኤግዚቪሽን ጉዳይ ምርትና አገልግሎት ለማስተዋወቅ እና ለማዘጋጀት የሚመጡ፤
በግል ጉዳይ ከሀገር ወጥተው የሚመለሱ፤
ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ካላቸው ሀገሮች ተላልፈው (through transit) የሚመጡ፤
በዝቅተኛ ስጋት ደረጃ እንዲስተናገዱ የተዘረዘሩት ዲፕሎማቲክ መብት ካላቸው መንገደኞች
ውጪ አምስት በመቶ በራንደም መረጣ፤
የመንገደኛው የትውልድ ሃገር በከፍተኛ ስጋት ደረጃ የሚመደብ ሲሆን
የመንገደኛው የተለየና ያልተለመደ አካለዊ እንቅስቃሴ ሲያሳይ (ለምሳል መነጫነጭ፤
ያልተለመደ ላብ፤ ቅብጥብጥነት፤ ሚዛን ጠብቆ ያለመሄድ ወዘተ)
ከሦስተኛ ወገን መረጃ ሲገኝ፤
መንገደኞች ይዘውት የሚመጡት ጥቅል ከሚመጡበት ዓላማ አንጻር ብዛት ሲኖረው
(ለምሳሌ ለትምህርት ወይም ለስብሰባ ሄዶ ሲመለስ ብዛት ያላቸው ሻንጣዎች
ሲይዝ/ስትይዝ)፤
በኢትዮጵያ በኩል ወደሌሎች ሀገሮች ትራንዚት የሚያደርጉ መንገደኞች ሆኖው በሀገር
ውስጥ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን፤
መንገደኛች ይዘዋቸው በሚመጡ ዕቃዎች ላይ የጥርጣሬ ሪማርክ የተደረገበት፣ ከኢንተለጀንስ
እና ከሌሎች አካለት የጥርጣሬ መረጃ የቀረበበት ሲሆን
51 ምንጮች /Reference |
ማጠቃለያ
የስጋት ስራ አመራር ስጋቶችን በሳይንቲፊክ ዘዴ የምንለይበት፣ የምንተነትንበት፣ የምናስተናግድበት እና የምንገመግምበት
ምርጥ የስራ አመራር ጥበብ ሲሆን በዚህም ዕድሎች የሚለዩበት ሊፈጠሩ የሚችሉ ኪሣራዎች የምንቀንስበት ወይም
የምናስወግድበት እንዲሁም በአለን ውስን ሀብት ውጤታማ ውሳኔ እንድንወስን የሚረዳን የማኔጅመንት ጥበብ ነው፡፡
የስጋት ስራ አመራር ስርዓት በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን እንደአሠራር ከተጀመረ ጥቂት ጊዜያትን ያስቆጠረ
ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጦችን እያመጣ ይገኛል፡፡ ይህም የስጋት ደረጃዎችን ለመጣል የሚያስችሉ መረጃዎች
ከቅ/ጽ/ቤቶች እየተሰበሰቡ እና በማዕከል የስጋት ትንታኔና የስጋት ፕሮፋይል እየተዘጋጀ በአሰሰኩዳ ሴልክቲቪቲ ማትሪክስ
አማካኝነት ስጋት በሲስተም እንዲጣል ማድረግ ተችሏል፡፡
የስጋት መረጃዎች በራስ አቅም እና ጥረት በሲስተም የሚያዙበት አሰራር ተዘርግቶ ለስጋት ስራ አመራር ጠቃሚ የሆኑ
መረጃዎች በ Tax Payers Profile Data Base የሚያዙበት እና ለተጠቃሚዎች የሚሰራጩበት አሰራር ተፈጥራል፡፡
ከዚህ ጎን ለ ጎን በቅርብ ጊዜያት በገቢ ዕቃዎች መስተንግዶ ላይ ብቻ ሲጣል የነበረው የስጋት ስራ አመራር መሰረቱን
በማስፋት በመንገደኞችና በመንደኞች ጓዝ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈጻጸም፣ በትራንዚት ዕቃዎች ስነ-ስርዓት አፈጻጸም እና
በወጪ ዕቃዎች ስነ-ስርዓት አፈጻጸም ላይ መተግበር ተችሏል፡፡
ስጋት ስራ አመራር ለኢትዬጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን ውጤታማ ቁጥጥር እና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት
ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፡፡ ባለስልጣኑም ለተገልጋይ ሕብረተሰብ ፍትሐዊ፣ ፈጣን፣ ተገማች እና አመኔታን ያተረፈ
የጉምሩክ አገልግሎት በመስጠትና የጉምሩክ ቁጥጥር በማካሄድ ረገድ የግልጽነትና ተጠያቂነት አሰራርን ለማስፈን በአዲሱ
የጉምሩክ አዋጅ የስጋት ስራ አመራር መርህን ተግብራል፡፡ ይህም የሕግ ተገዥነት በማሳደግ አገልግሎት አሰጣጡንና
የቁጥጥር ሥርዓቱን ሚዛናዊ ባደረገ ሁኔታ በሚቀመጡ መስፈርቶች መሠረት የተለያየ የሥጋት ደረጃ በማውጣት የሕግ
ተገዢ የሆኑት በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ላይ እየተመደቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት የሚያገኙበት እና የሕግ ተገዢ የማይሆኑት
በከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ እየተመደቡ ጠንካራ ቁጥጥር እየተደረገባቸው እንዲስተናገዱ ይደረጋል፡፡
ስጋት ትንታኔ በዋናው መ/ቤት እና በቅ/ጽ/ቤች በተለያዩ መልኩ ይከናወናል፡፡ በዋናው መ/ቤት ስጋት ስራ አመራር
የሚያከናውነው ከጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ስጋቶችን በገቢ፣ ወጪና ተላላፊ ዕቃዎች እና መንገደኞች ላይ
በመለየትና በመተንተን በአገር አቀፍ ደረጃ (national) ስጋቶቹ እንዲስተናገዱ ማድረግ እና መከታተል ነው፡፡ በቅ/ጽ/ቤቶች
ስጋት ስራ አመራር በሲስተም የሚጣሉ የስጋት ደረጃዎች በመከታተል ከቅ/ጽ/ቤቱ አንጻር የሚፈጠሩ ስጋቶችን ለማስተናገድ
እንዲሁም በሲስተም የስጋት ደረጃዎች መጣል በማይቻልበት ወቅት በማኑዋል የስጋት ትንታኔ በማከናወን የስጋት
52 ምንጮች /Reference |
ደረጃዎችን ለመጣል ነው፡፡ በመጨረሻም በዋናው መ/ቤትም ሆነ በቅ/ጽ/ቤቶች የስጋት ስራ አመራር ውጤታማነት
እየተገመገመ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጥሙ ችግሮች እና አዳዲስ ስጋቶች እንዲስተናገዱ ማሻሻያዎች ይደረጋሉ፡፡
ምንጮች /Reference
Awustralia Tax Office, Developing Effective Compliance Stratagey, (2009), “Guide for
Compliance Officers”
COSO (2004) “Guide to EnterpriseRisk Management Frequently asked Question”
Plain English ISO 31000 (2009)“Risk Management Dictionary”
The Organisation for Economic Co-operation and Development (OECD) document on
Compliance Risk Management,(2004) “Managing and Improving Tax Compliance”
53 ምንጮች /Reference |
WCO Safe Frame Work of Standards, (2012), ‘Secures and Facilitate Global Trade’.
World Customs Organization, (2003), “Risk Management Guide”.
በ IMF የተዘጋጀ የስጋት ስራ አመራር ረቂቅ ማኑዋል
የስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ እና እስትራቴጂ
የታክስ ሕግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስራ መዘርዝር እና ማኑዋል
የኢትዮጵያ ገ/ጉ/ባለስልጣን የጉምሩክ አዋጅ 589/2007 ዓ.ም
54 ምንጮች /Reference |