... - BenishangulGumuzEducationBureauFacebook 1699557733788

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 37

Log in

Benishangul Gumuz
󰟙 Education Bureau's post

Benishangul Gumuz 󰟝
Education Bureau
Apr 3, 2019󰞋󰟡

የትምህርት ቤቶች የሚኒ ሚዲያ አሰራር ማኑዋል

መስከረም 2006 ዓ/ም


አዲስ አበባ፣

ማውጫ
አርዕስት ገጽ
የዋሉ መነሻዎች 1.
የሚኒ ሚዲያ ምንንት 2.
የሚኒ ሚዲያ አስፈላጊነት 3.
የሚኒ ሚዲያ ታሪካዊ አነሳስና እድገት 4.
የማኑዋል አስፈላጊነት 6
የማኑወሉ ወሰን 6
በት/ቤት ውስጥ ሚኒ ሚዲያ ስልመመስረት 7
የሚታዩ ማኑቆዎች 8
የማኑዋሉ አላማዎች 9
የትምህርት ቢቴ ሚኒ ሚዲያ መርሆዎች 9
የሚኒ ሚዲያግ የኮሙኒኬሽን ስራ የትኩረት
አቅጣጫዎች 12
የባለ ድርሻ አካላትና የኮሙኒኬሽን ፍላጐት
ስለመለየት 12
አደረጃጀትና አሰራር 14
አቅርቦትና ተሳትፎ 20
በሚኒ ሚዲያ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚሳተፉ
አካላትና የስራ ድርሻቸው 22
የሚኒ ሚዲያ ስነ -መግባር 28
የትኩረት ፣ የድጋፍና የግምገማ ስርአት 30
ማጠቃለያ 31
አባሪዎች

መግቢያ
በአገራችን የተጀመረው ህዳሴ የጠለቀ መሰረት
እንዲይዝ ለማድረግ የተለወጠ አመለካከት ያለው፣
መልካም ስነ-ምግባር የተላበሰ፣ ዴሞክራሲያዊና
ልማታዊ አስተሳሰብ ያለው፣ ጤንነቱን የተጠበቀ
ትውልድ መፍጠር እንደሚገባቸው ይታመሃለ፡፡
የሚነደፉ የልማት እቅዳችን ተፈጻሚ ለማድረግ
መረጃ ያለውና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ
የሚያደርግ ህብረተሰብ ያስፈልጋል፡፡ የህዝቡን መረጃ
የማግኘት መብት ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ የመረጃ
Log in
ስርጭት ኔት ወርክ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመፍጠር
መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
Benishangul
ሚኒ ሚዲያን Gumuz ጥረትም
የማልማትና የማስፋፋት
󰟙 Education Bureau's post
የዚሁ አገራዊ እንቅስቃሴ አንድ አካል ሆኖ የሚታይ
ነው፡፡
ከዚህ አንጻር በት/ቤት ቅጥር ግቢ የሚቋቋም
ውጤታማ የሆነ አነስተኛ የኮሙኒኬሽን አውታር
ወይም ሚኒ ሚዲያ በመጠቀም መምህራንና
የትምህርት ቤት አስተዳደር ሰራተኞች ከተማሪዎች
ጋር በመተባበር በቀጣይ አመታት ጐልተው የሚወጡ
አገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ይዘው
በተሻለ ሙያዊ ዝግጁነትና ጥራት የሚሰሩበትን ሁኔታ
መፍጠር ተገቢ ይሆናል፡፡
በአግባቡ ታቅዶ የተዘረጋ የት/ቤት የኮሙኒኬሽን
ስርአት በአጠቃላይ የመማር ማስተማሩ ሂደት
በማጠናከርና የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ጥሩ
አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡ በእርግጥ
በሚኒ ሚዲያ በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ለመሆን ጥሩ
እቅድና የአስተዳደር ስርአት መዘርጋትን ይጠይቃል፡፡
ስለሆነም “የሚኒ ሚዲያ ስትራቴጂካዊ ቅኝትና
የማህበረሰቡ ተጠቃሚ”በሚል ርዕስ የዳሰሳ ጥናት
የተደረገ ሲሆን በጥናቱ ግኝት መነሻነትም ዘርፉን
በአግባቡና በስርአት የመምራት ሁኔታ ጊዜ
የማሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር
ጋር በመመካከር እና በመግባባት ማኑዋሉን በጋራ
ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡ ይህ ማኑዋል በት/ቤት ውስጥ
የሚኒ ሚዲያ ስርአት በመዘርጋት እና ስራውን
የሚመሩ መዋቅሮችን በማዘጋጀት፣የኤዲቶሪያል
ፖሊሲዎችን በመቅረጽ እንዲሁም ውጤታማ
የትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያ ስርአት ለመፍጠር
የሚያስችሉ አስፈላጊ ግብአቶችን በማሏላት ረገድ
መከናወን ያለባቸውን ተግባራትና ስልቶች
በማመላከት ረገድ ጠቃሚ አስተዋጽኦ ያበረክታል
ተብሎ ይታመናል፡፡

የማኑዋሉ መነሻዎች ፡-
ከ20 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችና ሌሎች
የትምህርት ማህበረሰብ አባላትን ለማግኘት
የሚያስችል የኮሙኒኬሽን አማራጭ በመሆኑና
በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ትልቅ ጠቀሜታ
ሊያስገኝ የሚችል መሆኑ፣
በሚኒ ሚዲያ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ
ተዋናይ የሆኑና መሆንም ያለባቸው
አካላት/ትምህርት ቤቶች፣ ኮሙኒኬሽን ዘርፎች፣
ሚዲያና የአስፈጻሚ አካላት ኃላፊዎች/ በተናጠልና
በቅንጅት በመንቀሳቀስ እስካሁን ለተገኘው ለውጥ
ያበረከቱት አስተዋጽኦ እንደተጠበቀ ሆኖ በባለድርሻ
አካላት መካከል የአመለካከት፣ የአሰራር፣
የአደረጃጀት፣ የክህሎትና የግንኙነት ችግር ያለባቸው
በመሆኑ ፣ ስራው በተማከለና በግልጽ የስራLog in
ክፍፍል
እንዲሁም በቁርኝነት ሊመራና ሊከናወን
Benishangul
አልቻለም፡፡በዘርፉ በግልጽ Gumuz
የሚታዩና በስራውም ላይ
󰟙 Education Bureau's
ሁልህ ተጽዕኖ ያሳረፉ ችግሮችን የለየ post
የመፍትሄ
አቅጣጫ ያመላከተ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣን
የሚጠይቅ ሁኔታ መኖሩ፣
በትምህርት ማህበረሰቡ አካባቢ ለውጥ
ለማምጣት ታቅደው ከሚፈጸሙ ተግባራት ጋር
ተመጋጋቢ የሆነ የሚኒ ሚዲያ ስራ ማከናወን
የሚያስፈልግ መሆኑ፣ ከዚህ በመነሳት የስራውን
ይዘት በትክክል መምረጥና መልዕክቶችን ቀርፆ
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተግባብቶ በብቃት
ማስተላለፍ የሚገባ መሆኑ፣
በብቁ ስትራቴጂና ታክቲክ ላይ ተመስርቶ በሚሄድ
የአስተሳሰብ ትግል ውስጥ በጋሪ መጓዝ አስፈላጊ
መሆኑና አፈጻጸሙን እየተከታተሉ በየጊዜው በጋራ
መገምገም ተገቢ በመሆኑ፣
በዚህ ረገድ እስካሁን ከተካሄዱ ተግባራት ሊወሰዱ
የሚገባቸው ትምህርቶች በአግባቡ ተቀምረው የስራ
መመሪያ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማረጋገጥ የሚጠይቅ
መሆኑ፣
ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር፣ የአገራችንን
ትክክለኛ ገጽታ ለማስተዋወቅ በተለይ ከዴሞክራሲና
ሰብአው መብት ጥበቃ አኳያ የትምህርት ማህበረሰብ
ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ በጠራ
ቅኝትና እቅድ በመመራት አበክረን መስራት የሚገባን
ወቅት መሆኑ፣
በአጠቃላይ ሚኒ ሚዲያን በተለይ ደግሞ የትምህርት
ቤት ሚኒ ሚዲያዎችን በመጠቀም መልዕክቶችን
የማስተላለፍ ብቃት መገንባት የሚገባ መሆኑ፣ በዚህ
ረገድ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅና የመማር
ማስተማር ሂደት ከማሳለጥ በተጨማሪ በልማትና
ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር ሂደት ውስጥ ንቁ
ተሳታፊ በመሆኑና ውጤት በማስመዝገብ የተሻለ
ልምድና ችሎታ ካላቸው ሚኒ ሚዲያ ክበባት
በመማር ይህንኑ በፍጥነት የሚስፋፋበትን ሁኔታ
መፍጠር የሚገባ መሆኑ ማኑዋሉ ሊያተኩርባቸው
የሚገባ ዋና ዋና መነሻዎች ተደርገው ተወስደዋል፡፡
የሚኒ ሚዲያ ምንነት፡-
“ሚኒ ሚዲይ አንድ ለብዙ (one to many) ተብሎ
በሚጠራ የኮሙኒኬሽን ቴክሃሊጂ አማካይነት
፣በአንድ የተወሰነ አካባቢ በሚገኙ የማህበረሰብ
አባላት መካከል የሚደረግ የሃሳብ ልውውጥ ነው”
ተራሎ ሊተገጐም ይችላል፡፡ “አንድ ለብዙ” በሚል
የሚጠቀሰው የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስርአት፣
በአንድ የተቀፀረ አካባቢ በሚገኙ የተወሰኑ ሰዎች
ሃሳብ የሚለዋወጡበት ዝግ የኮሙኒኬሽን አውድ
ነው፡፡ በመሆኑም፣ ሚኒ ሚዲያ ስንል፣ በአንድ
የት/ቤት ቅጽር ግቢ የሚዘረጋ የኢንተርኮም ስርአት፣
ከአንድ የተወሰነ ቦታ ዘልቆ የሚሄድ አድማስ Log in
የሌለው
የሬዲዮ ግኝኙነትን፣ ቀደም ሲል ተዘጋጅቶ፣የቀርጾ
ዝግጅቶችን Benishangul Gumuz
እንደ ድምጽ ማጉያ፣ ማይክሮፎን እና
󰟙 Education Bureau's
አምፕሊፋየር የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን postበመጠቀም
የሚደረግ ስርኸትን ያካትታል፡፡
በመሆኑም፣ ሚኒ ሚዲያ ከአንድ ቅጽር ዘልቆ
የሚሄድ አድማስ ባለው የሬዲዮ ሞገድ ለጠቅላላው
ህዝብ የሚሰራጩ ዝግጅቶችን አይጨምርም፡፡
ምክንያቱም፣ እንደ ሬዲዮ ጣቢያዎች የህዝብ ሃብት
የሆነውን የአየር ሞገድ ለመጠቀም ከኢትዮጵያ
የብሮድካስት ባለሰልጣን የአየር ሞገድ ፈቃድ
ማግኘት ያስፈልጋል፡፡
ቴክኖሎጂ ሰዎች እርስ በርስ በቀላሉ መረጃ
ለመለዋወጥ የሚችሉባቸዉን በርካታ እድሎች
ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም ግለሰቦች ሆኑ የተለያዩ አካላት
መልዕክት ሊያስተላልፋቸው የሚፈልጉዋቸውን
ሰዎች ፍላጐት መሰረት ባደረገ መልኪ
መልዕክቶቻቸውን ማስተላለፍ የሚችሉበት ሰፊ እድል
ተፈጥሯል፡፡ ሚኒ ሚዲያም ከዚህ አኳያ የተፈጠረ
ምቹ የኮሙኒኬሽን ዘዴ ነው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡
ሚኒ ሚዲያ ማለት አነስተኛ ቁጥር ባለውና አንድ
ተመሳሳይ ተግባር ላይ ላለ የህብረተሰብ ክፍል
በጽሁፍ ወይም ባለውና አንድ ተመሳሳይ ተግባር ላይ
ላለ የህብረተሰብ ክፍል በጽሁፍ ወይም በድምጽ፣
በምስል ወይም ሶሰቱንም አንድ ላይ ለማቅረብ
የሚያስችል ስርአት ነው ተብሎ ሊገለጽ የሚችል
ቢሆንም፡፡ ማኑዋሉ መዳሰስ የፈለገው ጉዳይ ግን
ለትምህርቱ ማህበረሰብ በብሮድካስ ሚዲያ
የሚቀርብ፣ የህብረተሰቡንም ሙሉ ተሳትፎና
የባለቤትነት ድርሻ የሚጠይቅ የመረጃ ማስተላለፊያ
ዘዴን ነው፡፡
የሚኒ ሚዲያ ታሪካዊ አነሳስና እድገት፡-
በልማት እንቅስቃሴና የፖሊሲ ትግበራ ላይ
የተመሰረተ ብሄራዊ መግባባትና ይሁንታ
ከኮሙዚኬሽን ውጭ ሊፈጠር የሚችል ባለመሆኑ
የምስራቅ እስያ ልማታዊ መንግስታት በተለይ ህንድና
ብራዚል በሰፊ ልማታዊ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን
ስራዎች ላይ አትኩረው በመስራት የሚፈለገውን
ይሁንታና መግባባት ፈጥረዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም
የመላውን ህብረተሰብ የጋራ ልማታዊ ስምሪትና
በዚህም ላይ የተመሰረተ ህብረተሰባዊ
ትራንስፎርሜሽን ሊያመጡ ችለዋል፡፡
የተለያዩ ጽሁፎች እንደሚያብራሩት በታይዋንና በካሪያ
የተካሄደው ልማታዊ ኮሙኒኬሽን ለተናጠል
ጋዜጠኞች ስምሪት የተተወ ሳይሆን የልማታዊ
ፖሊቲካ ኢኮኖሚ ግንባታውን ተከትሎ በልዩ ልዩ
የአስተሳሰብ መገነቢያ መስኮች የተካሄደ ነበር፡፡
በትምህርት ስርአቱ ውስጥ ከመወአለ ህጻናት ጀምሬ
በሚኑ ሚዲያ በሚተላለፍ ልማታዊ አስተሳሰብ
Log in
አዲሱን ትውልድ የሚገነባ እንቅስቃሴ ተካሂዷል፡፡
ስለሆነም በትምህርት ስርአቱ ውስጥ ልማታዊ
ኮሙዩኒኬሽንBenishangul Gumuz
ተግባራዊ ተደርጐ ወጣቱን ትውልድ
󰟙 Education
በትክክለኛ አስተሳሰብና ስነ ምግባርpost
Bureau's ቀርፆ
የማውጣት ሚና እንዲጫወት ተደርጓል፡፡ በአገሮቹ
ውስጥ የነበሩት መገናኛ ብዙሃንም የህብረተሰቡንና
የባለሃብቱን ልማታዊ ጥረቶችና ያስገኙትን ውጤት
ሳቢ በሆነ መንገድ እያቀረቡ ለማስተዋወቅና
ከእነዚህም ትምህርት እንዲቀስም በማድረግ
በህብረተሰብ ደረጃ የልማታዊ አስተሳሰብ የበላይነትን
ሊፈጥሩ ችለዋል፡፡ በገጠር የተካሄደውን የመሬት
ክፍፍልና የግብርና መርታማነት የማሳደግ እንቅስቃሴ
መነሻ በማድረግ አርሶ አደሩ ለልማታዊ አስተሳሰቦች
እንዲጋለጥና ከስንፍናና የተመጽዋችነት አመለካከት
እንዲላቀቅ አድረገዋል፡፡ ከጥቃትና አነስተኛ ተቋማት
እስከ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች የተካሄደውን ልማትም
እንደዚሁ ጥራት ያለውና ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪን
ለመገንባት በሚስችል ቅኝት የሚኒ ሚዲያና
የኮሙዩኒኬሽን ስራ ሰርተውበታል፡፡ በአጭሩ
የፖለቲካ ኢኮኖማውን ልማታዊነት ተከትሎ በተካሄደ
የትምህርትና የሚኒ ሚዲ ቅስቀሳና የመረጃ አቅርቦት
እንዲሂም በህብረተሰብ ደረጃ የሚካሄደውን
ተግባራዊ ልማታዊ እንቅስቃሴ ማዕከል በማድረግ
በተካሄደ ሰፊ ልማታዊ ኮሙኒዩኬሽን በፈጠሩት የጋራ
መግባባት ህብረተሰቦቹ በማያቋርጥ የለውጥ ሂደት
ውስጥ ገብተው ዛሬ ለደረሱበት የበለጸገ ህብረተሰብ
በቅተዋል፡፡
በሃገራችንም ይሄ አነስተኛ የመረጃ ማሰራጫ
ዘዜ/ሚኒ ሚዲያ /አሁን ያለውን ቅርጽ አያያዝ እንጂ
በነገስታቱ ጌዜ የተለያዩ አዋጆችን ለማስነገርና
መልክቶች ለማስተላለፍ ጥቅም ላይ ይውል
እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ከት/ሚኒስቴር
የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተውም ሚኒ ሚዲያ
በት/ቤቶች የተቋቋመው በ1960ዎቹ የትምህርት
በሬዲዮ አገልግሎት መምጣትን ተከትሎ እንደሆነና
ከደርግ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ ደግሞ ሚኒ
ሚዲያ በስፋት በየቀበሌው እና በየመንደሩ ለፖለቲካ
ፕሮፖጋንዳ ስራ አገልግሎት ተቋቁሞ እንደነበር
አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡

ከዚያም ሚኒ ሚዲያዎች በክበቦች ደረጃ


እየተደራጁና በሚመለከታቸው መምህራን እየተመሩ
ተማሪዎች ፕሮግራም አዘጋጅተው እንደሁኔታው
ለየት/ቤቶቻቸው የሚያቀርቧቸውን ዝግጅት
በመከፋፈል በተዘረጋው እቅድ መሰረተ ተማሪዎች
እረፍት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ እንዲያቀርቡ ሊደረግ
ቆይቷል፡፡ በዚህ መሰረትም ሚኒ- ሚዲያው አሳታፊ
ስለሚሆን ተማሪዎች ይዝናኑበትል፣ ይማሩበታል፡፡
የሚኒ ሚለዲያ ተቋማት በት/ቤት ብቻ ሳይሆን
በሌሎች ተቋማትም አገልግሎት እንዲሰጡ Log in
እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ የትራፊክ ደህንነትን
ለማጠናከር Benishangul Gumuz
በአንዳንድ ከተሞች በአውቶቡስ
󰟙 Education Bureau's post ትምህርት
መናሃሪያዎች ውስጥ ስፒከሮች ተሰቅለው
ይሰጣቸዋል፡፡ አንዳንድ የፀረ-ኤድስ ክበባትም
እንዲሂ በአንዳንድ ከተሞች ማዕከላዊ ቦታ የሚኒ
ሚዲያ መሳሪያዎች ተክለው በተዘጋጀው ፕሮግራም
መሰረት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
ህብረተሰቡ ከበሽታ ራሱን እንዲከላከልና በበሽታ
የተያዙትም ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ
እንዳለባቸው ወዘተ በወጣቶቹ የተዘጋጀ ትምህርት
ይሰጣል፡፡
ከቅርብ ጉዞ ወዲህ ደግሞ በአንዳንድ የመንግስት
የአስተዳደርና የሴክተር መ/ቤት መዋቅሮችም የሚኒ
ሚዲያ ተቋማት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡
ለአብነት የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች /በተለይ በወረዳ
ደረጃ/ እና የፀረ ኤች አይ ቪ ሴክተሪያት መዋቅሮች
ህዝቡን በየመስካቸውና እንደየ አላማቸው
ለማስተማር ይጠቀሙበታል፡፡ አንዳንድ የከተማ
ቀበሌዎችም እንዲሁ የሚኒ ሚዲያ ተቋማትን
በማደራጀት የቀበሌው ህብረተሰብ መጨበጥ
ያለበትን ግንዛቤ እንዲጨብጥ የቅስቀሳ ስራ
ያካሂዱበታል፡፡
በሚኒ ሚዲያው የአሰራር ሂደት ከኮሙኒኬሽን
ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚመለከታቸው ሰራተኞች
በተጨባጭ በየአካባቢው የሚገኙ የአማተር
ክበባትንም የሚያሳትፉ ወረዳዎች እንዳሉ ለማወቅ
ተችሏል፡፡ ተሞክሮ ለመቀመር በመንግስት
ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካኝነት ተደርጐ በነበረ
ጉብኝት እንደታየሙም የሚኒ ሚዲያ ተቋማት
አገልግሎት እንደየወረዳውና ት/ቤቱ ሰራተኞች
የፈጠራ ችሎታ የተለያየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት
የሚኒ ሚዲያ ተቋማት ሰፊ የመረጃ አገልግሎት
በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
የሚኒ ሚዲያ አስፈላጊነት
የትምህርት ማህበረሰቡ በዲሞክራሲ፣ በመልካም
አስተዳደር፣ በልማትና በሀገር ገጽታ ግንባታው ሂደት
ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን በማስቻልና ወጣቱ
ትውልድ በስነ ምግባር የታነጸ፣ በእውቀት የተገነባ እና
በሁለንተናው ብቁ ሆኖ የነገ ሀገር ተረካቢ እንዲሆን
እንዲሁም በትምህርት ማህበረሰቡ መካከል
ያልተገደበ ነፃ የመረጃና የሀሳብ ልውውጥ ስርአትን
ለመገንባት እንደ ሚኑ ሚዲያ ያሉ የአነስተኛ የሚዲያ
ቻናሎች አገልግሎት አስፈላጊነት አጠያያቂ
አይሆንም፡፡
በመሆኑም የዚህን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ዘርፍ
አብዝሀነትና ልማት በማመጣት በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ
ለመሆን የሚኒ ሚዲያ ተግባራዊ አፈጻጸም ተገቢውን
ትኩረት ሰጥቶ ለመንቀሳቀስ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
በተለይ በሀገራችን ቀጣይነት ያለው ጠንካራLog ሚኒ in
ሚዲያ ለመገንባትና በዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚታዩትን
የሙያ ብቃትBenishangul
ማነስ፣ የይከትናGumuz
ጥራት አብህሃነት
󰟙 Education Bureau's post
ጉድለቶች፣ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ዝቅተኛነት፣
እንዲሁም የባለቤትነትና የአስተዳዳሪነት ሚና
ውስነነት ለመቅረፍ የሚያስችል ስልት ተግባራዊ
በማድረግ ተፈላጊውን ውጤት ለማምጣት መረባረብ
ይገባል፡፡ በተጨማሪም በአስፈላጊነቱና በተግባራዊ
አፈጻጸሙ ላይ አንድ ወጥ የሆነ ግንዛቤ በመፍጠር፣
በመሳሪያዎች አያያዝ፣ አጠቓቀምና የአስረዳደር
ስርአት የተሻለና ወጥ እንዲሆን በማድረግና
የመሳሰሉትን ችግሮች በዘላቁነት ለመፍታት የአሰራር
ስርአት መዘርጋትና ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል፡፡
የማኑዋሉ ወሰን
የተለያዩ ተቋማት የመረጃ ተደራሽነታቸውን
በማስፋፋት አላማቸውን ለማሳካት ሚኒ ሚዲያዎችን
የሚጠቀሙ ቢሆንም አገልግሎቱ በስፋት እየተሰጠ
ያለው በትምህርት ቤቶች በመሆኑ ማኑዋሉ
በትምህርት ተቋማት በተለይ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ
ትምቤቶች በሚሰጡ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎቶች
ላይ ብቻ እንዲያተኩር ተደርጓል፡፡ ሚኒ ሚዲ በጽሁፍ
በሚሰጡ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎቶች ላይ ብቻ
እንዲያተኩር ተደርጓል፡፡ ሚኒ ሚዲያ በጽሁጽፍ እና
በኤሌክትሮኒክስ የሚከፈል ቢሆንም ይህ ማኑዋል
የተወሰነው ግን አሁን በተጨባጭ በሚኒ ሚዲያ
ክበብ አማካኝነት በሚዘጋጁ የብሮድካስት ሚኒ
ሚዲያ ውጤቶች ላይ ነው፡፡
በት/ቤት ውስጥ ማኒ ሚዲያን ስለመመስረት
በት/ቤት ሚኒ ሚዲያ ለመመስረት ስናስብ
በቅድሚያ ልናሟላቸው የሚገቡ አንዳንድ ቁልፍ
ጉዳዮች አሉ፡፡ ቁልፍ ጉዳዮቹንም በሶስት ከፍሎ
ማየት ጠቃሚ ነው፡፡ እነዚሀ ቁልፍ ጉዳዮች /1/
የኤዲቶሪያል እና ይዘት ጉዳዮች /2/ የአስተዳደር እና
የሰራተኛ ጉዳዮች እንዲሁም /3/ ቴክኒካዊ ጉዳዮች
ናቸው፡፡
አንድ ትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያ ለማቋቅም
ሲያስብ፣ በቅድሚያ ሚዲያው ምን አላማ
እንያሳካለት እና ምን ሚና ሲጫወት እንደሚፈልግ
በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡ ሚናው እና
አላማው ከተወሰነ በኋላ፣ ቀጣዩ ውሳኔ የሚሻ ጉዳይ
በሚኒ ሚዲያው ምን አይነት ይዘት ያላቸውን
ዝግጅቶች፣ በምን አይነት ያቀራረብ ቅርጽ ተጠቅመን
በየስንት ጊዜው እናስተላልፍ የሚለው ይሆናል፡፡
እንግዲህ ከዚህ በኋላ ፣ ት/ቤቱ ሚኒ ሚዲያውን
በብቃት ለማቋቋምና ስራውን ለማካሄድ ምን ያህል
ሀብት ያስፈልጋል የሚለውን ጉዳይ ወደ
መገምገምም ሊሸጋገር ይችላል፡፡ ት/ቤቱ የሚኒ
ሚዲያ አገልግሎቱ እንዴት እንደሚመራ ወይም
እንደሚተዳደር ግልጽ ሃሳብ ሊኖረው ይገባል፡፡
በመሆኑም Log in
የእለት ተእለት የሚኒ ሚዲያ አገልግሎቱን በብቃት
ለማካሄድ Benishangul
በስራ አስኪያጅነትGumuz
የሚመረጠውን ኃላፊ
󰟙 Education
ጨምሮ ፣ ማን- ምን ኃላፊነት ይያዝ?post
Bureau's
ምን አይነት የሚኒ ሚዲያ እና ምን አይነት
ቴክኖሎጂ መጠቀም ተገቢ ነው?ተቋሙ ምን አይነት
መልእክቶች እንዲተላለፍ ይፈልጋል?
ለሚኒ ሚዲያ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የመቅረጹ፣
ይዘቶችን የማቀናበሩ እና ጽሁፎችን የማዘጋጀቱ
ኃላፊነት የማን ይሆናል? የሚሉ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ
ማሳለፍ ያስፈልጋል፡፡
የት/ቤቱ አስተዳደር የሚኒ ሚዲያ በማቋቋሙ ጉዳይ
ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ የሚኒሚዲያ
አገልግሎቱን ራዕይ እና ተልዕኮ ለመቅረጽ ይቻል
ዘንድ ከት/ቤቱ ማህበረሰብ የተለያዩ ባለድርሻ
አካላት ጋር በመነጋገር ግልጽ እቅድና የአሰራር ስርአት
መፍጠር ይኖግበታል፡፡ ራዕይና ተልዕኮውም፣
ራዕይ፣ የሚኒ ሚዲያው ወደፊት የት መድረስ
እንደሚፈልግ ማመልከት አለበት፡፡ራዕይ የረጅም ጊዜ
ግብን ወይም ተቋሙ የሚመኘው እጅግ የላቀ
መድረሻ የሚገልጽ ነው፡፡
ተልዕኮ ፣ የሚኒ ሚዲያውን አላማ እና ሚና
የሚጠቅስ፣ እነዱሁም የተጠቀሰውን ራዕይ እንዴት
ማሳካት እንደሚቻል የሚጠቁም ይሆናል፡፡
የሚታዩ ማነቆዎች
ት/ቤቶች ሚኒ ሚዲያን በስትራቴጂክ እቅድ ውስጥ
አካትተው እየሰሩ መሆናቸው፣ ሚኒ ሚዲያው
መንግስትና ህዝብን የሚያቀራርብ የህብረተሰብን
ተሳትፎና የትምህርት ስራን በማስተዋወቅ፣ስድስቱን
የትምህርት ጥራት ፖኬጆችን በማስተላለፍ ፣
በየት/ቤቱ የተቋቋሙ ልዩ ልዩ ክበባት
እንቅስቃሴዎቻቸውን በማስረዳት ፣ ብሄራዊ
መዝሙርን ከማስጠናት አንስቶ ልዩ ልዩ የትምህርት
ቤት ትዕዛዛትን በማስተላለፍ አገልግሎት እየሰጡ
ቢሆንም በየት/ቤቱ ባለው ሚኒ ሚዲያ ላይ በበጐ
ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ የቋንቋ መምህራንና
ተማሪወች ስራውን የሚሰሩት ከመማርና ከማስተማር
ስራቸው በተጓዳኝ ስለሆነ እንደተደራቢ ስራ
የመቁጠርና ተጨማሪ ጫና የሚያሳድርባቸው መሆኑ
ታውቋል፡፡ እንዲሁም መምህራን ባለመስራታቸው
የሚቀርባቸው ጥቅም ስለሜለ ኃላፊነቱን በአብዛኛው
ተማሪዎች ተረክበው ጠማሰሩበት ሁኔታ እንዳለና
ይህም በይዘት አመራረጥ ላይ የራሱን ችግር
እንደፈጠረ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
በሚኒ ሚዲያው የሚተላለፈው መልዕክት
በአብዛኛው በስፖርትና በሙዚቃ ላይ ከማተኮሩም
በላይ አልፎ አልፎ ሚሚያው ለባህል ወረራ
እንዲጋለጥ አድርጐታል፣ ወቅታዊ አገራዊ
የመንግስት መረጃን በማስተላለፍ ረገድም ሰፊ
ክፍተት እንዳለና አልፎ አልፎ የሚተላለፍበት Log
ሁኔታin
ቢኖርም ወጥነት ባለው መልኩ የማስተላለፍ
Benishangul Gumuz
ውስንነት ይታያል፣
󰟙 Education Bureau's post
ከማቴሪያልና ከገንዘብ አቅም ጋር በተያያዘ መልኩ
የሚመደበው በጀት አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ለሚኒ
ዲያ አስፈላጊው ቁሳቁስ ያለመሟላት ፣ ጥራቱን
የጠበቀ መረጃ ያለማቅረብ፣ በአንዳንድ ቁሳቁሶች
ላይ ብልሽት ሊያጋጥም ስራ የማቋረጥ፣ በአንዳንድ
ት/ቤቶች ያለውን ቁሳቁስና ገንዘብ በአግሪቡ
ያለመጠቀም/ ይህ በዋነኝነት ንብረት የማስተዳደር
ኃላፊነትን መምህራን በመሸሻቸው የሚከሰት ነው/
ክፍተቶች ተስተውለዋል፡፡
የበጐ ፈቃደኞች አቅም ለማጐልበት አልፎ አልፎ
ጥረት ቢደረግም ትልቁ ችግር ግን የሰለጠኑ ሰዎች
ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ክፍተት እንደሚፈጥርና
እንደገና ከማደራጀት አኳያ ውስንነት እንደሚታይ
ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሚተላለፉ መልዕክቶች ላይ
ክትትል ከማድረግ አንጻርም በሚኒ ሚዲያዎች
የሚተላለፉት መልዕክቶች የቱን ያህል ችግር
ቢኖርባቸውም በቋሚነት ክትትል የማድረግ ኃላፊነትና
ከኮሙኒኬሽን ቢሮዎች ጋር በአብዛኛው ተቀራርቦ
የሚሰራበት ሁኔታ የሚጐድለው ሆኖ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በወሳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን
የመቃኘት ስራ ላይ በማተኮር ሌሎችንም ማነቆዎች
በተግባር ውስጥም ጭምር እንደሚፈታ ታሳቢ
በማድረግ የትምህርት ማህበረሰብ በላቀ ደረጃ
የመረጃ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሰራር መዘርጋት
ተገቢ ይሆናል፡፡
የማኑዋሉ ዓላማዎች
የትምህርቱ ማህበረሰብ በትምህርት ቤት ሚኒ
ሚዲያዎች በላቀ ሁኔታ መጠቀም የሚችሉበትን
ስርአት ማጐልበት፡
የተለወጠ አመለካከት ያለው፣መልካም ስነ-ምግባር
የተላበሰ፣ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ አስተሳሰብ
ያለው፣ ጤንነቱን የጠበቀ ትውልድ መፍጠር
የትምህርት ማህበረሰቡ የትምህርት ጥራትን
በማሻሻል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና የተለያዩ
ሃገራዊ መረጃዎችን ማግኘት የሚችልበትን መንገድ
ለማመቻቸት ነው፡፡

የትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያ መርሆች


ሰኩላሪዝም /secularism/
የትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያዎች ከማንኛውም
ሃይማኖታዊ አድልዎ ወይም ውግንና የፀዳ ሴኩላር
አገልግሎት መስጠትና ሕገመንግስታዊ ግዴታቸውን
በማብቃት መወጣት አለባችው ፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ ማንኛውንም ዓይነት ኃይማኖታዊ አድልዎ
የሚያንፀባርቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ እንቅስቃሴ
ወይም ድርጊት መፈፀምም የዜጋውን ከአድልዎ
የጸዳ መንግስታዊ አገልግሎት የማግኘት መብት Log in
የሚጋፋ ስለሆነ የትምህርቱ ማህበረሰብ እንዲህ
Benishangul
አይነት ድርጊት እንዳይከናወንGumuz
መከታተል ይኖርበታል፡፡
󰟙 Education
ትምህርት ቤቶች ሁሉም ዜጋBureau's post
በአመለካከቱ፣በኃይማኖቱ … ወዘተ ምንም ልዩነት
ሳይደረግ የሚገለገልባችው ስፍራ መሆናችው ታውቆ
በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያዎች ይሄው
በተሟላ መልኩ ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጥ
የእያንዳንዱ ማህበረሰብ ኃላፊነት ነው፡፡

ተሳትፏአዊነት /participatory/
በህብረተሰብ ደረጃ የተጠቃሚነት ልዩነትን
ከሚያስችሉ ችግሮች መካከል የመረጃ እውቀት
ልዩነትና ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚከሰት የተጠቃሚነት
እድል ልዩነት አንዱ ነው፡፡ በቂ መረጃ ያገኙ
የህብረተሰብ ክፍሎች በእድሉ የመጠቀም
ችሎታችው ይሰፋል፡፡ የመረጃ ድህነት ያባችው ዜጐች
ደግሞ ከተሳትፎና ተጠቃሚነቱ መገለላችው
አየቀርም፡፡ በመሆኑም የህዝብንና የዜጐችን
የመሳተፍና የመጠቀም እድል በማስፋት ከተፈለገ
ለዜጐች የሚተላለፈውን መረጃ መጠን በከእተኛ
ደረጃ ተደራሽነትን ደረጃም በእጅጉ ማሳደግ ይገባል፡፡

የጋራ መግባባት /conseneus/


ሚኒ ሚዲያ በሰዎች መካከል የሃሳብ ልውውጥን
በማካሄድና የጋራ መግባባት መፍጠር ህብረተሰብን
ወደ አንድ የጋራ ተግባር ሊያመራ ይችላል፡፡
በመንግስትና በህብረተሰብ፣በህብረተሰብና በልዩ ልዩ
ድርጅቶች፣ ኩባንያዎችና ተቋማት መካከልም
መግባባት ለመፍጠር ሚኒ ሚዲያ ልዩ ሚና
ይጫወታል፡፡ በስርአት የሚመራ የሚዲያ ስራ
ማከናወን መቻል ወይም አለመቻል የጋራ መግባባትን
የመፍጠር ውጤትን ያስከትላል፡፡

የሕግ የበላይነት መከተል /Efficiency &


effectiveness/
የሕግ የበላይነት ስንል የሁሉንም ዜጐች መብቶችና
ጥቅሞች በእኩልነት የሚጠቀሙበት የዴሞክራሲያዊ
ስርዓት ግንባታ መሰረት የሆነ መርህ ነው፡፡ በመሆነም
ዜጐች በህገመንግስታችንና ከዚሁ በመነጩ ህጐች
መሰረት ነበር፤ በብሔር፤ብሔረሰብ ፤በቀለም፤በፆታ፤
በቋንቋ በሃይማኖት፤በፓለቲካ፤ በማህበራዊ
አመጣጥ፤ በሀብት፤ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም
ምክኒያት ልዩነት ሳያደረግ ዜጐች ሁሉ በህግ ፊት
እኩልና በመንግስት ተቋማት በእኩልነት የመገልገል
መብታችው ሊጠበቅ ይገባል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም
ሁሉም የትመህርቱ ማህበረሰብ ይህንኑ ለማረጋገጥ
በጋራም ሆነ በተናጥል መንቀሳቀስ ይጠበቅባርዋል፡፡
ቀልጣፋና ውጤታማነት /efficiency & Log in
effectiveness/
የዚህ መርህ Benishangul Gumuzቤት ሚኒ
ዋነኛ ይዘት ትምህርት
󰟙 Education Bureau's post
ሚዲያዎች የማቀድ ፣ የመአፀምም መለካትና
ተጠቃሚ መሆን ወየም የክበባችውን ስራ በተገቢው
አደረጃጀት፣ ፍጥነትና ግብአት የሰውኃይል፤
የማቴሪያልና የገንዘብም ሆነ ሌላ ሀብት በመጠቀም
የሚፈለገውንና የሚገባውን ውጤት ማምጣት
መቻል ነው፡፡ በተለይ ይዘቶችን ከማዘጋጀትና
ከማቅረብ አኳያ የጊዜም ይሁን የሃብት ብክነት መኖር
የለበትም ነው፡፡ ቅልጣፌ በተሰጠችው የተማሪዎች
እረፍት ሰዓት ፍጥነትና ተገቢውን ሀብት ተጠቅሞ
መስራትን ሲነግረን፤ ውጤታማነት ግን የሚፈለገው
የአስተሳሰብ ለውጥ መምጣቱን የሚነግረን ነው፡፡
በመሆኑም ሚኒ ሚዲያዎች ተልእኮአችውን
ተወጥተዋል ስንል በቅልጣፌ የራሱ ዋጋ ያለውን
ያህል ያለውጤታማነት ብቻውን እየበተኑ የመሄድ
ያህል ይሆናል፡፡ ያለ ቅልጣፌም እንዲሁ
ውጤታማነት የሚታሰብ አይደለም፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት የትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያዎች
የሚመሩባችው መርሆች ተጣምረው በትምህርት
ቤቶቹ ተጨባጭ ሁኔታ የአሰራር ስረአቱን
ለማጐልበት የምንመራባችው መሆኑን በመገንዘብ
ለተግባራዊነታችው መንቀሳቀስ አለብን፡፡

ግልጽነትና ተጠያቂነት
ግልጽነት የዉሳኔ አሰጣጥ ሂደት ምን
እንደሚመስል ፣በምን መርህና ህግ እደሚመራ .
እንዴት እንደሚፈፀም ፣በማን እንደሚፈጸም፣መቼ
እንደሚፈፀም ወዘተ ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ በይፋ
ከማሳወቅ አንስቶ ፣ምን እንደተወሰነ፣ምን
እንደተፈጸመ የአፈጻጸሙን ሙሉ መረጃ በሚቻለዉ
መንገድ ሁሉ በግልጽ መስጠት ነዉ፡፡
የዚህ መርህ መሰረታዊ ቁም ነገሩ ዜጎች በቂ
መረጃ ያላቸዉ ያወቁ ሆነዉ ተገቢዉን አቋም መያዝ
የሚያስችላቸዉ መሆኑ ነዉ፡፡ መረጃ በማጣት
ምክንያት አለአግባብ የሚፈጠር አለመግባባት
፣አለመተማመንና ጥርጣሬ ማስወገድ ነዉ፡፡
እንዲሁም ስህተትን በቀላሉ ለማወቅና ለማረም
የሚያስችልበት ሁኔታ መፍጠሩ ነዉ፡፡
በአጭሩ የተገባ ቃል መጠበቅ አለመጠበቁን
በተለያዬ መንገድ ቃል ለተገባለት ህዝብ/ዜጋ
ወይም ተገልጋይ በሥርዓት ማሳወቅ ነዉ፡፡ ቃል
የጠበቀ ያሳካ የሚመሰገንበት፣የሚበረታታበትና
የሚሸለምበት ፣ቃል ያልጠበቀ የሚመከርበት ወይም
የሚወቀስበት ካሆነለት ወደሚሆንለት ቦታ
የሚዛወርበት. ሆን ብሎ ማጥፋት ከሆነ የሚቀጣበት
ስርዓት ነዉ፡፡
መርሆቹን የማስፈፀሚያ አቅጣጫዎች/ስልቶች/ Log in
ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን መርሆዎች
በትምህርቱ Benishangul Gumuz
ማህበረሰብ ዉስጥ ለማስረጽ በተለይ
󰟙 Education Bureau's post
በጋራ መግባባት ፣ በሴኩላሪዝም፣ በግልጽነትና
በተጠያቂነት ፣በህግ የበላይነት ላይ የሚከተሉትን
አቅጣጫዎች ወይም ስልት መከተል አስፈላጊ
ይሆናል፡፡
ለተማሪዎቹ የሚቀርቡት መረጃዎችን የተማሪዎችን
የትምህርት ደረጃ ፣የአረዳድና የትምህርት አቀባበል
ሁኔታን ያገናዘበ እንዲሆን ይሆናል፡፡
እንዲሁም በቀላሉ በተማሪዎች አእምሮ ዉስጥ
ለማስረጽ በሚያስችሉ ፎርማቶች የመቅረብ፤
ከዚህ አኳያ መረጃዎችን
በግጥም፣በመዝሙር፣በጭዉዉት፣ በጥያቄና መልስ
እንዲሁም በክርክር መልክ የማዘጋጀትና
የማደራጀት፤
በመርሆዎቹ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር
በእያንዳንዱ መርህ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲደረግ
ምቹ ሁኔታን የመፍጠር፤
የሚኒ ሚዲያና የኮምንኬሽን ሥራ የትኩረት
አቅጣጫዎች
የኮምንኬሽን ሥራዉ ዒላማ ያደረገዉ ማንን ነዉ?
የሚተላለፈዉ መልዕክት ምንድን ነዉ? መልዕክቱን
ለማስተላለፍ ምቹ መድረክ ምን ዓይነት ነዉ?
አንድ ተቋም መልዕክቱን ለማስተላለፍ የሚፈለገዉ
ለየትኛዉ ማህበረሰብ እንደሆነ መለየት
ይኖርበታል፡፡ይህንንም ለማድረግ መነሳት
የሚገባቸዉ ጥያቄዎች፤
የሚሰራዉ የኮምንኬሽን ስራ ግቦች ምንድን
ናቸዉ?
ዒላማ ለተደረጉት ቡድኖች መልዕት በማስተላለፍ
የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት የምንችለዉ እንዴት
ነዉ?
ዒላማ ለተደረጉት ቡድኖች ትክክለኛና ባህልን
ያገናዘበ መረጃ ማስተላለፍ እንችል ዘንድ ሊተላለፉ
የሚታሰቡት ቁልፍ መልዕክቶች በአግባቡ መቀረጽ
ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ መነሳት
የሚገባቸዉ ጥያቄዎች፤
የሚተላለፈዉ ዋነኛ መልዕክት ምንድን ነዉ?
መልዕክቶቹስ እንዲያስገኙ የሚፈለገዉ ዉጤት
ምንድን ነዉ?
ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት መልዕክቱ በአግባቡ
መተላለፉን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሂደቶች ምንድን
ናቸዉ? መልዕክቱን ለማህበረሰዉ ለማተላለፍ
የሚያስችለዉ ተስማሚ መድረኮች የትኞቹ ናቸዉ?
ዉጤታማ ኮምንኬሽን መፈጠሩን ለማረጋገጥ
እነኝህን መድረኮች እንዴት ልንጠቀምባቸዉ
እንችላለን? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ሊገኝ
ይገባል፡፡ይህንንም ለማድረግ መነሳት የሚገባዉ
ጥያቄ፤ Log in
መልዕክቱን ለማተላለፍ የሚያስችሉ የተለያዩ
አማራጮች Benishangul
ምን ምን ናቸዉ?Gumuz
ዒላማ ከተደረጉት
󰟙 Education Bureau's
ቡድኖች በአስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችለዉpost
ተስማሚ መሳሪያ ምንድን ነዉ?

እናም፤ የሚኒ ሚዲያ መቋቋም ሂደት ያጋጠሙ


ጥያቄዎች ወይም ፍች ያጡ ችግሮች
ሲኖሩ፤በየደረጃዉ ያሉ የኮምንኬሽን ቢሮዎች
ለት/ቤቱ ተጨባጭ ሁኔታ ተስማሚ የሆነዉን
የሚኒሚዲያ ስርዓት በመለየት፤ ተገቢ ይዘቶችን
በመምረጥ እንዲሁም ለሚያጋጥሙ እክሎች
መፍትሄ በመፈለግ ረገድ እገዛ ሊያደርጉ
ይችላሉ፡፡ቢሮዎቹ፣ የሚቋቋሙት ሚኒሚዲያዎች
ተማሪዎች የላቀ ትምህርትና ልምድ ማግኘት
የሚችሉበት ይሆኑ ዘንድ የማገዝ ኃላፊነት የያዙ
ናቸዉ፡፡
የባለድርሻ አካላትንና የኮምንኬሽን ፍላጎትን
ስለመለየት
የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት ለመጀመር ሲታሰብ
በቅድሚያ መልዕክት ሊተላለፍ የታሰበዉ ለማን
እንደሆነ ምን ዓይነት መልዕክት ማስተላለፍ
እንደሚፈለግ እዲሁም ዒላማ ከተደረጉት
ማህበረሰቦች ለመድረስ እና ለነሱ ሊተላፍ
የተፈለገዉ መልዕክት ተስማሚ የሆነዉ ምቹ መድረክ
የቱ እንደሆነ መለየት ይኖርበታል፡፡
ሀ/ ባለድርሻ አካላትን መለየት
የጥሩ ኮሚንኬሽን ዕቅድ ዋነኛ ግቡ ተቋሙን
ከተቋሙ ባለድርሻ አካት ጋር ማገናኘት መቻሉና
ሁለቱን አካት በማገናኘት የላቀ ዉጤት ለመፍጠር
ይቻል ዘንድ ተገቢዉን
መሳሪያና መልዕክት መጠቀም ማስቻሉ ነዉ፡፡
በመሆኑም የኮሙንኬሽን ስራዎችን የመጀመሪያዉ
ወሳኝ ጉዳይ የተለያዩ ባለድርሻ
ማህበረሰቦችን/አካትን/መለየት እና እነዚህ አካት
በትምህርት ቤቱ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ዉጥ
ያላቸዉን ፍላጎት መገምገም ነዉ፡፡
ለ/ መልዕክትን ማስተላፍ
በኮምንኬሽን ዕቅዱ ባለድርሻ አካላት በግልጽ
ከተለያዩ በኋላ ቀጣዩ ስራ ትምህርት ቤቱ
ለተማሪዎች ማስተላለፍ የሚፈልገዉ መልዕክት
ይዘት ምን ሊሆን እንደሚገባ መወሰን ነዉ፡፡ ይህም
ይዘት አስተማሪ እና መረጃ ሰጪ ጉዳዮችን
የሚጠቃልል ይሆናል፡፡ የሚተላለፉት ትምህርታዊ
ዝግጅቶችም ሁልጊዜም መሰረታዊ የትምህርት
ዕሴትን የሚያንፀባርቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
በሚቀርቡት ትምህርታዊ የዖዲዮ ቪዥዋል
ዝግጅቶች ትምህርት ቤቱ አላማዉን ላማሳካት
ይረዳዋል፡፡ በቅጽር ግቢዉ ተወስኖ የሚካሄደዉ
ኮምንኬሽን ለት/ቤቱ የመማር-ማስተማር ሂደት Log in
አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚኒሚዲያ
አገልግሎትBenishangul
መፍጠር Gumuz
󰟙 Education
ከት/ቤቱ ለተማሪዎችBureau's
የሚተላለፉpost
አንዳንድ
መግለጫዎችን ለማቅረብ
በክፍል ዉስጥ በሚሰጡት ት/ቤቶች ላይ ትኩረት
አድርገዉ በተማሪዎችና አስተማሪዎች የተሰናዱ
ትምህርታዊ ዝግጅቶችን ለተማሪዎች ማቅረብ
ለማማር ማስተማሩ ሂደት ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉ
በሬዲዮና በቴሌቪዥን የተላለፉ ዝግጅቶችን ቀድቶ
መልሶ ለማሰራጨት ሊያገለግል ይችላል፡፡
ሁለተኛ የሚኒሚዲያ ቻናል መምረጥ ፣መልዕክትን
ለማስተላለፍ ተገቢ ቻነል የመምረጥ ሥራ ዒላማ
የተደረጉ ቡድኖችን የተመለከተ ጥናት ማካሄድ እና
ዉጤታማ በሆነ መንገድ መልዕክትን ለማስተላለፍ
የሚያስችል የሚዲያ መድረክ የትኛዉ እንደሆነ
መለየትን ይጠይቃ፡፡
ከፍ ሲል የተገለፀዉ የሚኒሚዲያ አድማስ ከአንድ
ቅጽር የማያልፍና ከት/ቤቱ ገቢ አልፎ የማይሄድ ዝግ
ሥርዓት ነዉ፡፡ ይህም ማለት የቻነሎቹ የሥርጭት
አድማ ዉስብስብ ያልሆነና በቅብብሎሽ የስርጭት
ዘዴ /relay systems/ የሚጠቀም ስርዓት
ነዉ፡፡እንድሁም የተለያዩ ማይክሮፎኖችን በመጠቀም
መረጃን ከአንድ ጣቢያ ወደ ብዙ ማሰራጫ ነጥቦች
በአንድ ጊዜ መረጃ የሚተላለፍበት ነዉ፡፡
2. የሚኒ ሚዲያ አስተዳደርና ሰራተኞች
እንደ ማንኛዉም የ‹‹አንድ ለብዙ›› (One-to-
many) የኮምንኬሽን ዘዴ ሚኒ ሚዲያ የራሱ
ድርጅታዊ የአስተዳደር ስርዓት ሊኖረዉ ይገባል፡፡
የኮሙንኬሽን ስራዉ ለተማሪዎች ሳቢያና አስደሳች
እንድሆን የማድረጉ ጥረት ማቀድን፣ መከታተልን እና
አስተዳደራዊ ግምገማን ይጠይቃል፡፡ ስራችንን
በተማሪዎች ግብረ-ምላሽ ላይ ተመስርተን ለማሻሻል
እንድችል ዘንድ የግብረ ምልስ ሥርዓት ሊኖረን
ይገባል፡፡
3. የሚኒ ሚዲያ ዝግጅት ቡድን ምስረታ
ሚኒ ሚዲያ ስንል በቀላል አገላለጽ የትምህርት
ቤትን እንቅስቃሴዎች የተመለከቱ ዜናዎች እና
ዕለታዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ስርዕት ነዉ ማለት
ይቻላል፡፡ ከዚህም ሌላ ሰፋ ያሉ መረጃዎችን
የሚያካትቱ ሊሆኑ ይችላ፡፡ ይህ ስራ በሚኒ
ሚዲያዉ ምን ዓይነት ይዘት እናቅርብ የሚል
የኢዲቶሪያል ዉሳኔ የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
የምንሰጠዉ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት ሰፊ ከሆነ
በዛዉ መጠን ስራዎቹን በኃላፊነት የሚከታተል እና
የሚያስተዳድር የአስተዳደር ቡድን እንዲኖር ማድግ
አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ሆኖም አገልግሎቱ ሰፊ መረጃዎችን የማያካትን
እና መግለጫዎችን እና ማስታወቂያዎችን ብቻ
በማቅረብ የሚወሰን ከሆነ ቀላል አስተዳደራዊ Log in
መዋቅር ማድረግ በቂ ይሆናል፡፡የሆነ ሆኖ ዉስን
መረጃዎችንBenishangul
የሚስተላልፍ Gumuz
አገልግሎት ቢሆንም
󰟙 Education Bureau's
እንኳን ጽሑፎቹን የሚያርም የመረጃዎቹን post
ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ እና መረጃዎቹ
ለተማሪዎች ያላቸዉን ተገቢነት የመመዘን ኃላፊነት
የሚይዝ አንድ አካል ሊመደብ ይገባል፡፡በአንጻሩ
ከሚኒ ሚዲያ ሊገኝ የሚችለዉን አገልግሎት ሙሉ
ለሙሉ ለመጠቀም እና ሰፊ መረጃዎችን
ለማስተላለፍ ከተፈለገ የኢዲቶሪያል ዉሳኔ
የሚያደርግ እና በአስተዳደራዊ ጊዳዮች ላይ ዉሳኔ
የሚሰጥ ቡድን መቋቋም ይኖርበታል፡፡እንደ ሞደል
ሲወሰድ የሚችል የሚኒ ሚዲያ አወቃቀር
የሚከተሉትን አካላት ሊያካትት ይችላል፡፡

4. የተለያዩ የሚኒሚዲያ አካላት ኃላፊነቶች


ሀ/ የአስተባባሪ ኮሚቴ
የአስተባባሪ ኮሚቴዉ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎቱን
አቅጣጫ የሚያስቀምጥ እና አፈጻጸሙንም
የሚገመግም ሲሆን የአገልግሎቱን ግቦች እና
መርሆዎችን ለማስቀመጥ አሰራሩንም ገምግሞ
ለማሻሻል መደበኛ በሆነ ጊዜ እየተገናኘ ይወያያል፡፡
የአስተባባሪ ኮሚቴዉ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ
የተለያዩ ፍላጎቶች የሚያንፀባርቅ ይሆን ዘንድ
በድርጅታዊ መዋቅሩ ቻርት የተጠቀሱትን አካላት
በአባልነት ሊያቅፍ ይገባል፡፡ ይህዉ ኮሚቴ የበጀት
እና የፋይናንስ ጉዳዮች የግልጽነት እና የተጠያቂነት
መርህ የተከተለ አግባብ የሚከናወኑ መሆናቸዉን
የማረጋገጥ ኃላፊነትም ሊይዝ ይገባል፡፡
ለ/ አስተባባሪ
አስተባባሪዉ በጀትን ጨምሮ የሚኒ ሚዲያዉን
የዕለት ተዕለት አሰራር የመከታተል ኃላፊነት
ይኖረዋል፡፡ እንዲሁም የሚኒ ሚዲያ አገልግሎቱ
የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በታቀደ፣በተቀናጀ እና
የተነደፈዉን ዕቅድ በተከተለ አኳኳን መፈጸሙን
ያረጋግጣል፡፡ የቴክኒክና የኤዲቶሪያል ድጋፍ ቡድኑ
ሰራተኞች ሥራቸዉን በአግባቡ ለማከናወን
የሚያስፈልጋቸዉን ሀብት ማግኘታቸዉን የማረጋገጥ
ኃላፊነትም ይኖረል፡፡ የሚኒ ሚዲያ ስራዉ ዕቅድን
መሠረት አድርጎ የሚከናወን መሆኑን ከማረጋገጥ
ባሻገር የዝግጅት ማቅረቢያ የጊዜ ሰሌዳ
የማዉጣት ኃላፊነትንም ይኖረዋ፡፡
ሐ/ የኤዲቶሪያል እና የይዘት ቀረጻ ቡድን
የኢዲቶሪያል እና የይዘት ቀረጻ ቡድን የሚኒ ሚዲያ
ስርዓቱ ዋና ተዋናይ ነዉ፡፡ በርግጥም ከብዙ ጉዳዮች
አንጻር ሲታይ የሥርዓቱ ዋነኛ ተዋናይ ተደርጎ
ሊወሰድ ይችላል፡፡ ግልጽና ለመረዳት በማያስቸግር
አግባብ የተነሳ የጊዜ ሰሌዳን ተከትሎ ሳቢና ጥራት
ያለዉ፤እንዲሁም የተማሪዎችን ፍላጎት የሚንፀባርቅ Log in
ዝግጅት የማቅረብ ጉዳይ ለሚኒ ሚዲያዉ
አገልግሎትBenishangul
መዉደቅ ወይም Gumuz
መነሳት ወሳኝ ጉዳይ
󰟙 Education Bureau's post ሃሳብን
ነዉ፡፡ የኤዲቶሪያልና የይዘት ቀረጻ ሠራተኞች
የማመንጨት፣ መግለጫዎችን የማቀናበር እንዲሁም
የመረጃዎችን ትክክለኝነት የማጣራትና የማረጋገጥ
ሃላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ስራ የሚኒ ሚዲያ
ስርዓቱ ዋነኛ ተዋናዮች በሆኑት፤ እንዲሁም
የሚቀርቡት ዝግጅቶች ሰፊ ተቀባይነት እንዲኖራቸዉ
እገዛ በሚያደርጉት እና የሚቀርቡት ዝግጅቶች
የተማሪዎችን ፍላጎት የሚንፀባርቁ መሆናቸዉን
ለማረጋገጥ በሚችሉት ተማሪዎች ሊከናወን
ይችላል፡፡
መ/ የዝግጅት አቅራቢዎች
የዝግጅት አቅራቢዎች የሚኒ ሚዲያ ስርዓቱ ዋነኛ
ተዋናዮች ናቸው፡፡ የሚኒ-ሚዲያ ቡድኑ ዝግጅቶችን
በግልጽ የሚያቀርቡና የሚስተላልፉ ጥሩ የዝግጅት
አቅራቢዎች ሊኖሩት ያስፈልጋል፡፡የዝግጅት
አቅራቢዎቹ ከሠራተኛው ወይም በሚኒ-ሚዲያዉ
አገልግሎቱ ተሳታፊ ከሆኑ ተማሪዎች የሚመረጡ
ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከሠራተኞች እና ከተማሪዎች
እንዲውጣጡ ማድረግ የተማሪዎችን ፍላጎት
በማንፀባረቅና የክትትል ሥራ በመሥራት መካከል
ሚዛን እንድጠብቅ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም
ተማሪዎቹ የሚኒ ሚዲያ ኮምንኬሽን መድረኩን
በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም የሚስችል ክህሎት
የሚቀስሙበትን እና አርአያ የሚያገኙበትን እድል
ያመቻቻል፡፡
ሠ/ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ቡድን
በሚኒ ሚዲያ አገልግሎቱ አንዳንድ ጥገና እና
እድሳት የሚጠይቁ ጉዳዮች ሲኖሩ የቴክኒክ ድጋፍ
ሰጪ ቡድን እገዛ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ሆኖም
የሥርጭት ስርዓቱ ዉብስብ ባለመሆኑ ከፍተኛ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ወይም የጥገና
አገልግሎት የሚጠይቅ ሁኔታ አይኖርም ፡፡ይሁን እና
በቴክኒክ እክል ምክንያት አገልግሎቱ ለረጅም ጊዜ
የሚቋረጥበት ሁኔታ እንዳይፈጠር እና አስፈላጊዉን
ጥገና በፍጥነት ለማድረግ ይቻል ዘንድ የጥገና
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አድራሻ መያዝ
አስፈላጊ ነዉ፡፡
አሠራር
1. የዝግጅት አቅራቢዎች ኃላፊነት
የሚኒ ሚዲያ አገልግሎቱ ስርጭት ከጀመረ በኋላ
የዝግጅት አቅራቢዎች እና የኤዲቶሪያል ሠራተኞች
ሊከታተሉት የሚገባ ግልጽ እና ቋሚ የአሰራር
ሥርዓት ሊኖር ይገባል፡፡ሥርጭቱ የሚደረገዉ
በተማሪዎች የዕረፍት ሰዓት መሆኑ ቢታወቅም
የሚተላለፉት ዝግጅቶችን ይዘትና የሠራተኞችን
ኃላፊነት የሚያመለክት ግልጽ የሥራ ምደባ
ሠንጠረዥ ማዘጋጀትና አስፈላጊ ከሆነም በየሳምንቱ Log in
ማሻሻያ ማድረግ ይገባል፡፡
Benishangul
ምን እንደተሠራና ሥራውንGumuz
ማን እንደሰራው
󰟙 Education Bureau's
የሚያመለክት መዝገብ እንዲኖር ማድረግ post አስፈላጊ
ነዉ፡፡ ይህም ለሚኒ ሚዲያ አገልግሎት አመራር
ጠቃሚ መረጃ ለመያዝ የሚያስችል እና በሠራተኛ
ምደባ ዉሳኔ እና የዝግጅት ሰሌዳን በመከለስ ረገድ
ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
የት/ቤት የሚኒሚዲያ አገልግሎት ሳይስተጓጎል
ሥራው እንዲቀጥል የማድረጉ ኃላፊነት የሁሉም
ሠራተኞች ኃላፊነት ሲሆን ይህም የዕቅድና የጊዜ
ሰሌዳ ዉሳኔ ማሳለፍን ይጠይቃል፡፡ብዙውን ጊዜ
እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉት ዕቅድ
ለማውጣት በሚደረግ ስብሰባና ሥራ
አስኪያጁ፤የኤድቶሪያልና የይዘት ሠራተኞች
እንዲሁም የዝግጅት አቅራቢዎች በሚሳተፉበት
ሳምንታዊ የሥብሰባ መድረኮች ይሆናል፡፡እያንዳንዱ
ስብሰባ ግልጽ አላማ ሊቀመጥለት እና ለወደፊት
ሊሰሩ ለታቀዱ ሥራዎችና ዝግጅቶች የጊዜ ሰሌዳ
ማውጣት ይኖርበታል፡፡የሚቻል ከሆነም ይህንኑ
የይዘትና የጊዜ ሰሌዳ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ
መለጠፍ ጠቃሚ ነዉ፡፡
2. የአስፈጻሚዎች ቅጽ
የዝግጅት አቅራቢዎች ሥራቸውን ሲያከናውኑ
ሊከተሏቸው የሚገቡ የተለያዩ ያሠራር ሂደቶች እና
የተከናወኑ ጥሩ ሥራዎችን የሚያመለክቱ
መዛግብቶች ይኖራሉ፡፡ከሁሉ አስቀድሞ
የአስፈጻሚዎች ቅጽ (Operators log) መያዝ ግደታ
ነዉ፡፡ ይህ የአስፈጻሚዎች መዝገብ በሚኒ ሚዲያ
የተላለፉ ዝግጅቶችን ያቀረቡ ሰራተኞች ሥራ
የሚገለጽበት ቅጽ ነዉ፡፡
አንድ የዝግጅት አቅራቢ ፕሮግራሙን ለማቅረብ ወደ
ስቱዲዮ ከመግባቱ በፊትና አቅርቦ ከወጣ በኋላ
ኃላፊዉ በአስፈጻሚዎች ቅጽ ላይ ሁል ጊዜም
ፊርማዉን ማኖር ይኖርበታል፡፡የዝግጅት አቅራቢዉም
አየር ላይ በሆነበት ጊዜ ለሚፈጠሩ ማናቸዉም
ጉዳዮች በኃላፊነት የሚጠየቅ መሆኑን በቅጹ ላይ
በመፈረም ያረጋግጣል፡፡
3. የይዘት ቅጽ
በየጊዜው የሚመደቡ አስፈጻሚዎች ስም ዝርዝር
በቅጽ ተመዝግቦ እንደሚቀመጥ ሁሉ፤ ማናቸውም
በሚኒ ሚዲያ የሚያቀርቡ ዝግጅቶች
የሚመዘግቡበት ቅጽ ሊኖር ይገባል፡፡እንድህ ያሉ
ቅጾቸ ሲሆኑ፤ የፕሮግራም አስተዋዋቂዎች ምን
ዓይነት ዝግጅት መቼ እንደሚተላለፍ አስቀድመው
ለማወቅ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ት/ቤቱ
በፕሮግራም ጣልቃ ማስታወቂያዎች በማስነገር
ጥያቄ ሲቀርብ ጣልቃ በገባው ማስታወቂያ
ምክንያት ዝግጅት የሚቋረጥ መሆኑን አስቀድሞ
ለማወቅ የሚችልበትን ዕድል ያስገኛል፡፡ ይህLog in
የይዘት
ቅጽ በሚኒሚዲያዉ የተላለፉትን ዝግጅቶችና
ርዕሳቸዉንBenishangul Gumuz ጉዳዮች ሁሉ
በዝግጅቱም የዳሰሳቸዉን
󰟙
ለመመዝገብEducation Bureau's
ይዉላል፡ ፡ይህም post
ዝግጅቶች
እንዳይደጋገሙና የኤዲቶሪያል ሠራተኞች የተለያዩ
ዝግጅቶችን ለማቅረብ እንዲጥሩ ያደርጋቸዋል፡፡

የሚተላለፉ ማናቸዉም ዝግጅቶችከሚኒ ሚዲያ


ፖሊሲዉ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ
ይቻል ዘንድ አቅራቢዎች ሊያቀርብ በተዘጋጀዉ
ፕሮግራም ላይ ቅር የሚላቸዉ ነገር ሲገጥማቸዉ
ዝግጅቱን ከማቅረባቸዉ በፊት የኤዲቶሪያል
ሠራተኞች ወይም ስራ አስኪያጁ ስለ ጉዳዩ
እንዲያዉቁ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ንባብና ንግግር
በድምጽ ማጉያ ወይም በማይክራፎን አማካኝነት
በሚተላለፍ የሚኒ ሚዲያ አገ/ት የምናደርገዉ ንባብ
ወይም ንግግር አድማጮችን የተባለዉን ነገር
በትክክል ለመስማት በሚያስችላቸዉ አኳኋን ግልጽ
ሊሆን እንደሚገባ መረዳት አስፈላጊ ነዉ፡፡ በሚኒ
ሚዲያ የሚቀርብ ንባብ እና ንግግር ለአድማጮች
በግልጽ የሚሰማ ይሆን ዘንድ ግልጽነት እንዲኖረዉ
የሚረዱ አንድአንድ ጠቃሚ ነጥቦች አሉ፡፡
እነዚህም፤
• ማይክራፎን በመጠቀም ስንናገር እና ስናነብ
በራሳችን ስልክ ከአንድ ሰዉ ጋር እየተነጋገርን
እንደሆነ ማሰብ፤
• ድምጻችንም ከሰው ጋር ስንነጋገር ከምናወጣው
መደበኛ ድምጻችን ከፍ ባላለ ወይም ባላነሰ አኳኋን
መናገር
• የአነጋገር ፍጥነታችንም ከአንድ ሰው ጋር
ስንነጋገር ከሚኖረን መደበኛ ፍጥነት ዝግ ያለ
ወይም የፈጠነ አለማድረግ በዓረፍተ ነገር
መካከልም ረዘም ያለ ፋታ አለመውሰድ፤
• የምናቀርበውን ነገር በማይጎረብጠንና ምቾት
በማይነሳን የቃላት ምርጫ ማቅረብ አለብን ዋናው
ጉዳይ ማስተላለፍ ያምንፈልገው መልዕክት
በአግባቡ መተላለፍ መቻሉ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ
መልዕክታችን በአግባቡ የሚተላለፈዉ ምቾት
በማይነሳ ቃላት ሃሳባችንን ለመግለጽ ስንችል ነዉ፡፡
5. የማይክሮፎን አጠቃቀም
• ማይክሮፎኑ ክፍት በሆነ ጊዜ መነጋገሪያውን በእጅ
አለመምታት ወይም አለማንፏቀቅ እንዲሁም
መነጋገሪያውን ከመክፈታችን በፊት ዝግጁ
መሆናችንን እና መመቻቸታችንን ማረጋገጥ፤
• ሁል ጊዜም አፋችንን በቀጥታ ከማይክራፎኑ ፊት
ለፊት አድርገን መናር ያስፈልጋል፡፡
ይህን ካላደረግን የድምጻችንን ጥራት ያጓድለዋል፡፡
• ድምጽ ማጉያዉ ጥራት ያለው መሆኑንና
ለመስማማት በሚያስቸግር መጠን ድምፁ Log in
ከፍ ያለ
አለመሆኑን ማረጋገጥ
Benishangul Gumuz
󰟙
አቅርቦትናEducation
ተሳትፎ Bureau's post
1.አቅርቦት
ለአጀንዳ መረጣም ሆነ ለጽሁፍ ዝግጅት እንዲሁም
ስራ ለመስራት እና አስፈላጊዉን ቴክኖሎጅ
ለመጠቀም የሚያስችል በቂ ቁሳዊ ሀብት ሊመደብ
ይገባል፡፡ በሚኒ ሚዲያ የሚቀርቡ ዝግጅቶችን
ለማቀናበርና ለማዘጋጀት ይህንም ዝግጅት በት/ቤት
ቅጥር ለማስተላለፍ የምንጠቀምበት ቴክኖሎጅ
እንድኖር ማድረግ ይኖርብናል፡፡
በመሆኑም ለተጠቀሱት ቁሳቁሶችና ስራዎች
አስፈላጊዉን በጀት መመደብ
ይስፈልገናል፡፡ተፈላጊዎቹ መሳሪያዎች ተዘርዝረዉ
እንዲቀመጡ ማድረግ ሥራዉን ለመስራት
የሚያስችል አቅም እንዲፈጠር
ያደርጋል፡፡በአብዛሃኛዉ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት
የሚከተሉት ጉዳዮች ሊሟሉለት ይገባል፡፡
ጥናት ለማድረግ የሚያስችል ጊዜ
የስብሰባ ክፍል
ዝግጅት ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች
እና
ለሚኒ ሚዲያ የሚያገለግል ትንሽ ስቱዲዮ
2. ተሳትፎ
ሚኒ ሚዲያ በትምህርት እንቅስቃሴ ዉስጥ ሁነኛ
ሚና ሊይዝ ይችላል፡፡ በወጉ ታቅዶ የሚሰራ ከሆነ
የሚኒ ሚዲያ አገልግሎቱ የተማሪዎችንና የሌሎችን
ሠራተኞች ቀልብ የሚስብ የሚያሳትፍና የሚዝናና
አገልግሎት ሊሆን ይችላል፡፡ከዚህም በላይ
ተማሪዎች ፈጠራን ያካተተ ሥራ ለመስራት ዕድል
የሚሰጥ እና ተሳትፏቸዉም በቀሪዉ የህይወት
ዘመናቸዉ ሊጠቀሙበት የሚችሉበትን ክህሎት
መገንባት የሚያስችላቸዉ ይሆናል፡፡
ጥሩ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት ማስታወቂ ብቻ
የሚቀርብበት ሳይሆን ተማሪዎች እና ሠራተኞች
የፈጠራ ክህሎታቸዉን ለማዉጣት የሚችሉበትን
ሁኔታ የሚፈጥር በይዘቱም የተለያዩ ነገሮችን
ለማካተት ጥረት የሚያደርግ ነዉ፡፡ በመሆኑም
በሠራተኞች አቅጣጫ ሰጭነት እና ድጋፍ እየታገዙ
በሁሉም ደረጃ ያሉ ተማሪዎች እንዲሳተፉ
ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡
ተማሪዎች ከአስተባባሪዉ /ከክበቡ
ተጠሪ፣ከኤዲቶሪያል ቡድኑ፣ ከአዘጋጆችና ከዝግጅት
አቅራቢዎች ጎን ሆነዉ እንዲሳተፉ ማድረግ ፤
እንዲሁም አመለካከታቸዉን በሚኒ ሚዲያ መድረክ
ማቅረብ የሚችሉበትን ዕድል መፍጠር
ይቻላል፡፡ስለሆነም የእነሱን ተሳትፎ ማበረታታት
በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡ በሚኒ ሚዲያ በበጎ
ፈቃደኝነት የሚሰሩ ተማሪዎችን ለመመልመል Log
እናin
ስራቸዉን ለመምራት የሚያግዙ በርካታ ጉዳዮች
Benishangul
አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል፤ Gumuz
󰟙 Education Bureau's post
በት/ቤቱ የምልመላ ፖሊሲ እንዲኖር ማድረግና
ተማሪዎች በሚኒ ሚዲያዉ መሳተፍ እንደሚችሉ
እንዲያዉቁ ማድረግ፤
ተሳትፎ ለማድረግ የሚፈለጉ ተማሪዎችን ጊዜን
አክብረውና ዉሳኔ አድርገው መስራት
እንደሚኖርባቸው መረጃ መስጠት፤
ለበጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች የሚሆን ቀላል የስነ-
ምግባር ደንብ እንዲኖር ማድረግ
ተማሪዎች በአስተባባሪ ኮሚቴው ውስጥ ውክልና
እንዲኖራቸዉ ማድረግ
ለተማሪዎች ስለሚኒ ሚዲያ አገልግሎት እና
በውስጡ ስላሉ የተለያዩ የሥራ ዘርፎች እንዲያዉቁ
ለማድረግ አጭር የሥልጠና ፕሮግራም መንደፍ፤
3. ትስስር
ሚኒ ሚዲያዎች በዋናነት በትምህርት ቤቶቻቸው
አስተዳደር ይመሩ እንጂ ማዕከላቱን በመጠቀም
ረገድ የተለያዩ አካላት የራሳቸዉ ድርሻ አላቸው፡፡
እነሱም በዋነኝነት፡-
የዞን አስተዳደር ፣የከተማ አስ/ር ፣የወረዳና የቀበሌ
አስ/ር /ማዘጋጃ ቤቶች
የሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች እና የህዝብ ግንኙነት
ኃላፊዎች
በከተማ ዉስጥ የተደራጁ የሚኒ ሚዲያ ክበብ
አባላት ፣ አማተሮች የሴቶች/የወጣቶች ወዘተ
ማህበራት
የአ/አደር ፣የአ/አደርና የከተማ ህዝብ አደረጃጀቶች
አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
የፌደራልና የክልል የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲዎች ፣
ሬዲዮ ፋናን የመሳሰሉ ሀገር አቀፍ ሽፋን ያላቸዉ
የግል መገናኛ ብዙሃን እና
የት/ቤቶች ሚኒ ሚዲያ ከበብ አባላት ሲሆኑ፣
ለትምህርቱ ማህበረሰብ መቅረብ የሚገባዉ
ዝግጅት ሲኖራቸዉ በትምህርት ሚኒስተር
፣በመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮዎችና በሚኒ ሚዲያ
የፕሮግራም ይዘት አዘጋጆች አማካኝነት ጽሁፋቸዉ
ቀርቦ እየታየ በሚኒ ሚዲያው አማካኝነት ሊተላለፍ
ይችላል፡፡
በሚኒ ሚዲያ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚሳተፉ
አካላትና የሥራ ድርሻቸዉ
እያንዳንዱ አካላት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ
የራሱ የሥራ ድርሻ ያለዉ ሲሆን ይህም ከተሰጠዉ
ተልዕኮ አንጻር የተለየ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት
በሥራ ዉስጥ የሚካተቱ አካላት የሚኖራቸዉ ድርሻ
ከሞላ ጎደል ከዚህ እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
በፌደራል የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ጽ/ቤቱ የሚዲያ ማልማትና ማስፋፋት ሂደቱLog in
በታቀደዉና በተገቢዉ መንገድ እንዲከናወን
Benishangul
የሚመራ ፣ብሔራዊ Gumuz
መግባባት የመፍጠርና የሀገር
󰟙
ገጽታ የመገንባት ኃላፊነት አለበት፡፡post
Education Bureau's
እንዲሁም፤
ሀ. የሚኒ ሚዲያ ደንብ ፣መመሪያዎችና ማንዋሎች
ያወጣል ፣ያሻሽላል፣ተግባራዊ ያደርጋል፣ የሚዲያ
ተደራሽነት የሚስፋፋበት ን አሰራር ይዘረጋል፡፡
ለ. የአገሪቱ ሚኒ ሚዲያ አሁን ያለበትን አጠቃላይ
እድገት ፣ተደራሽነትና ሽፋን እንዲሁም ውስንነቶችንና
ክፍተቶችን
የሚመልስ የተሟላ ጥናት በየጊዜዉ በማካሄድ
ለሚዲያ ማስፋፋት ስራ በግብዓትነት
እንዲጠቀሙበት ያደርጋል፡፡
ሐ. ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማስፋፋት
የሚኒ ሚዲያ ልማት ስራዎች ተግባር ላይ
እንዲዉሉ ያደርጋል፤
መ. ለሚኒ ሚዲያ ልማት የሚዉል ሀብት ለማግኘት
የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ድጋፍ
የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ሲገኙም በአግባቡ
ስራ ላይ እንድዉሉ ያደርጋል፤
ሠ. ከፐብሊክ ሚዲያዉ ጋር በማቀናጀት በቀጣይነት
የሚጠናርበትን አቅጣጫ ይተልማል
ረ. ከአዲሱ ሚዲያ ጋር አጣጥሞ ከመጠቀም አኳያ
ያሉትን መልካም ተሞክሮዎች ይቀምራል፤ በፍጥነት
የሚስፋፋበት ሁኔታ ይፈጥራል፤
ሰ. እንደአስፈላጊነቱ አጀንዳ የመለየት ፣መቅረጽ እና
የማሰራጨት ስራ ይሰራል፤
ሸ. የአጀንዳ ስርጸትን ይለካል፤
ቀ. ሙያዊ የአቅም ግንባታ ስልጠናና ግምገማዊ
ስልጠና እንድካሄድ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤
በ. ሀገር አቀፍ የሚኒ ሚዲ ፎረም በጋራ ይመሰረታል፤
ፎርሙንም ሁለት ጊዜ ይሰበስባል፤
ተ. የተሸለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሞዴል ሚኒ
ሚዲያዎችን ከት/ት ሚኒስተር ጋር በመሆን ይለያል፤
ሀገር አቀፍ ተሸላሚ እንዲሆኑም ሁኔታዎችን
ያመቻቻል፤
ቸ. የትምህርት ማህበረሰቡን አቅም ያገናዘቡ እና
እያዝናኑ የሚያስተምሩ መልዕክቶች እንዲወረጹና
እንዲሰራጩ ያስተባብራል፤
ትምህርት ሚኒስተር
ሀ. በት/ት ቤት ሚኒ ሚዲያ ክበባት አሰራር ላይ
ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
ለ. ከመንግስትና ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር
በመተባበር አሰራር እና አደረጃጀቶችነ ይዘረጋል፤
ሐ. የሚኒ ሚዲያ ክበባት በጥራት መረጋገጫ
ፓኬጅ መረሃ ግብሮች ተካተዉ በስትራቴጂያዊ ዕቅድ
እንዲገቡ ያደርጋል፤
መ. ለሚኒ ሚዲያ ክበባት አሰራር መጠናከር በጀት
ይመድባል፤ Log in
ሠ. የክልል ት/ት ቢሮዎች ለስራዉ ልዩ ትኩረት
እንዲሰጡት Benishangul
የማስተማር ስራ Gumuz
ይሰራል፤
󰟙 Education Bureau's
ረ. የሀብት ማፈላለግ እና ቁሳቁስ የማሟላትpost
ተግባራትን ያከናዉናል፤
ሰ. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሸለሙ ሞደል ሚኒ
ሚዲያዎችን ከመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ጋር በመሆን
ይለያል፤
ሸ. ሀገር አቀፍ የሚኒ ሚዲያ ፎረም እንዲመሰረት
ያስተባብራል፤
የክልል /ከተማ የመንግስት ኮሙንኬሽን ቢሮዎች
ሀ. በየክሉ ሚኒ ሚዲያዉ ስለሚገኝበት ነባራዊ
ሁኔታ ክትትል ያደርጋል፤ በተለይም በሚዲያ
ተጠቃሚ ያልሆኑትን አካባቢዎች ወይም የህ/ሰብ
ክፍሎች ይለያል፤ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉበትን
ሁኔታ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን
ያመቻቻል፤
ለ. በተቀመጠዉ መመዘኛ መስፈርት ክፍሎች
የሚዲያ ተጠቃሚ ያልሆኑባቸዉን ምክንያቶች
የመተንተን ፣የመፍሄ ሃሳቦችን ከአጭር
፣ከመካከለኛና ረዥም ጊዜ አንጻር የማመንጨት ስራ
ይሰራል፤
ሐ. በተለያዩ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት አሰጣጥ
ዘዴዎች አማካኝት እንደ አግባብነታቸዉ ተግባራዊ
ለማድረግ እቅድ አዉጥተዉ የመንቀሳቀስ
አስፈላጊዉ በጀት እንዲመደብም የማመቻቸት
ስራዉን ይመራል፤
መ. የሚኒ ሚዲያ ተደራሽነት በቀጣይ
የሚስፋፋባቸዉ አካባቢዎች አስፈላጊዉን ድጋፍ
እንዲያገኙ የማድረግና፣ የማመቻቸት ስራ ይሰራል፤
ሠ. የሚኒ ሚዲያ ተደራሽነት የተስፋፋባቸዉን
ትምህርት ቤቶች በተመለከተ መረጃ የመያዝ፣
የተገኘዉን ልምድ የመቀመር፣ በየክፍሎቻቸዉ ባሉ
ሌሎችም አካባቢዎች እንዲስፋፉ ጥረት ያደርጋሉ፤
ለትምህርት ቤቶቹ ሚኒ ሚዲያዎ የሚሆኑ
የትምህርት ማኅበረሰቡን እዉቀት ደረጃን ያገናዘቡ
እና እያዝናኑ የሚያስተምሩ ይዘት ያላቸዉን ግብዓቶች
ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመመካከር
ያዘጋጃ፤ለዝግጅቶቹ በዚህ መልኩ ድጋፍ ያደርጋሉ
ረ. የተሸለ አፈጻጸም ያለቸዉን ሞደል ሚኒ
ሚዲያዎን ይለያሉ
የፌደራል/የክልል /ከተማ መገናኛ ብዙሃን
ኤጄንሲዎች
ሀ. አገ/ት በአግባቡ የማይሰጡትን ሚኒ ሚዲያዎች
በመለየት ሂደት ዉስጥ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር
ተባብረዉ የመስራት ፣ተደራሽ ያልሆኑ ማህበረሰቦችን
ተጠቃ ሊሆኑ የሚችሉባቸዉን አማራጮች
የማጥናት፣ ተግባራዊ ያደርጋሉ
ለ. በአገልግሎት አሰጣጡ ሂደት የተገኘዉን ልምድ
ወደ ሌሎች እንዲሰራጭ የማድረግ የማስፋፋት Log in
ሥራን ከቴሌቪዥን ጣቢዎች ፤ከሬዲዮ ጣቢያዎና
ከህትመትBenishangul
ዉጤቶች ወዘተGumuz
አኳያ የመስራት፣
󰟙
ለትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያዎች post
Education Bureau's የሚሆኑ
ይዘቶችን ማዘጋጀት
ሐ. የተመረጡና ለትምህርት ማህበረሰቡ የሚሆኑ
ፕሮግራሞችን በሚኒ ሚዲያ እንዲተላለፉ
ሁኔታዎችን ያማመቻቸት፤
መ. በየአቅራቢቸዉ ለሚገኙ ሚኒ ሚዲያዎች
በሳምንት የተወሰነ ደቂቃ የዓየር ሰዓት በመመደብ
ምርጥ የተባሉ የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራሞች ክልላዊ
ሽፋን እንዲኖራቸዉ ማድረግ፤
ሠ. በአስተዳደር ክልሎቻቸዉ ዉጥ አዳድስ
ለማቋቋም ሚኒ ሚዲያዎች ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ
ይሰጣሉ፤
የክልል ትምህርት ቢሮዎች
ሀ. ሚኒ ሚዲያዎች ያልተሰራባቸዉን ወይም
በአካባቢ የሚሰራባቸዉን ቦታዎች የመለየት ሥራ
ከሌሎች አካላት ጋር በመተባር ያካሄዳል፤ ከሚኒ
ሚዲያ፣ ከእስኩል ኔትና ከትምህርት በሬድዮ
ማሰራጫ ጣቢዎች አገልግሎት ጋር የተያያዙ
መረጃዎችን የማሰባሰብ የማደራጀት፣ለሚፈጽመዉ
አካል መረጃዉን የመስጠት ስራ ይሰራሉ፤
ለ. በነዚህ የመረጃ ማስተላለፊያ ዘዴዎች
በመጠቀም የላቀ ዉጤት ያስመዘገቡትን በመለየት
ተሞክሮዉን ወደ ሌሎች የማስፋፋት ስራ
ይሰራሉ፤የላቀ ዉጤት ያስመዘገቡ ሞደል ሚኒ
ሚዲያዎችን የመለየት ሥራ ይሰራሉ፤
ሐ.በዚህ መሰረት ለሚፈጠሩ አዳዲስ ሚኒ
ሚዲያዎች አስፈላጊዉን የመረጀ አገልግሎትና
ድጋፍ የመስጠት ስራ ይሰራሉ
መ. የሚኒ ሚዲያ ክበባት በትምህርት ፓኬጅ
ዉስጥ ተካተዉ በስትራቴጂያዊ ዕቅድ እንዲመሩ
ግፊት የማድረግ ስራ ይሰራሉ፤
ሠ. ከሚሞከተዉ አካል ጋር በመሆን በዘርፉ
ለሚሳተፉና ዘርፉን ለሚመሩት አካት በየ ጊዜዉ
የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
ረ. አቅም በፈቀደ መጠን በጀት የመመደብና
ማቴሪያል የማሟላት ስራ ይሰራሉ፤
ሰ. አፈጻጸሙን መከታተልና ግብረ- መልስ የመስጠት
ተግባር ይከናዉና፡፡
ሸ. ሀብት የማፈላለግ ስራ በተናጠልና ከሌሎች ጋር
በመቀናጀት ይከናዉናሉ፡፡
የፌዴራል/የክልል/ከተማ መንግስት መ/ቤቶች
ሀ. ለሚኒ ሚዲያ ክበባት የሚሆኑ መረጃዎችን
በጥንቃቄም ሆነ ያለጥንቃቄ ያቀርባሉ
ለ. ከተሰጣቸዉ ተልዕኮ አኳያ ለሚኒ ሚዲያዎች
የሚሆን ግብዓት ያዘጋጃ፤ ወይም እንዲዘጋጅ
ያደርጋሉ
ሐ. አቅም በፈቀደ መጠን የሚኒ ሚዲያ ክበባት Log in
እንዲጠናከሩ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ስራ ይሰራሉ
Benishangul
መ. በት/ቤቶች Gumuz በአግባቡ
ያሉ ሚኒ ሚዲያዎች
󰟙
በዕቅድና Education
ስርዓት ባለዉBureau's post
አቅጣጫ እንዲማሩ
ለማድረግ የሚያስችል ስራ ይሰራሉ፡፡
ኅብረተሰቡ/ወመተህ/ ወጣት የሚገባዉ ኃላፊነት
በሚኒ ሚዲያ ተጠቃሚ የሆኑ ትምህርት ቤቶች
የመንግስትን የልማት ጥረት ይበልጥ ዉጤታማና
አዋጭ በሆኑ ተግባር ላይ ለማዋል የዘርፉን ልማት
ለማጠናር እንዲቻል ከዚህ የሚከተለዉን ኃላፊነት
መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡
የሚኒ ሚዲያ ክበባት ከተደራሽነትና አብዝሃነት
አንጻር ያለባቸዉን ችግሮችና መፍትሄ ይሆናሉ
የሚሏቸዉን አማራጮች ለሚመለከተዉ የበላይ
አመራሮችና ገንዘባቸዉን በአግባቡ በስራ ላይ ለማዋ
ይጥራሉ፤
ሀ. በሚኒ ሚዲያ ልማትና ማስፋፋት ስራ ዉስጥ
እዉቀታቸዉን ፣ጉልበታቸዉንና ገንዘባቸዉን
በአግባቡ በስራ ላይ ለማዋል ይጥራሉ፤
ለ. በቀላል ቴክኖሎጅና ማቴሪሎች እንዲሁም
በአካባቢያቸዉ በሚገኙ ግብዓቶች በመጠቀም
የሚኒ ዲያ ተደራሽነትን ለማስፋፋት ይሰራሉ፤
ሐ. የሚኒ ሚዲያ ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ
ያደረጉትን ጥረት የተጠቀሙበት ስልትና ዘዴ የሥራ
ትጋትና የሚኒ ሚዲያ አመራር ችሎታቸዉን
ለማጠናር ቀጣይነት ያለዉ ስራ ይሰራሉ፤
መ. መንግስት በሚሰጠዉ የሚዲያ ማልማትና
ማስፋፋት አቅጣጫ የሚኒ ሚዲያ ተደራሽነትን
ለማስፋፋት ያደረጉትን ጥረትና ያስገኙትን ዉጤት
ከራሳቸዉ አልፎ ለሌሎች አርአያ ፣ማስተማሪያና
የሚዲያ ልማት ፋና ወጊ ለመሆን በሚያስችል
አኳኋን በጋራ ይሰራሉ፤
ሠ. የሚዲያ ተጠቃሚነታቸዉን ያረጋገጡ
አካባቢዎችና ማህበረሰቦች ያላቸዉን ልምድ
ለዘርፉ አጋሮቻቸዉ የተለያዩ የማስፋፋት ዘዴዎችን
በመቀየስ ማለትም በዉይይት መድረኮች፤
በጉብኝቶች፣ በመልካም ተሞክሮዎች ቅመራና
ማስፋፋት የምክክር መድረኮችን በመፍጠር
እንዲሁም ታሪካቸዉን በጽሁፍና በዶክመንተሪ
ፊልም በመቅረጽ በሞደልነት መጠቀም እንዲቻል
አስፈላጊዉን ትብብር ያደርጋሉ፤
ትምህርት ቤቶች
ሀ. የት/ቤቶች ሚኒ ሚዲያን አደረጃጀት በመጠቀም
በማንዋሉ መሠረት ክበባቱን ያደራጃሉ፤
ለ. የሚኒ ሚዲያ እቅድና ስርዓት ያዘጋጃሉ፤
ያስፈጽማሉ ይገመግማሉ፤
ሐ. የዕቅድ ክፍተቶችን በመለየት ያሻሽላሉ፤
መ. በት/ቤቶች የሚኒ ሚዲያ አሰራርና አደረጃጀትን
በማጎልበት የሚያስችል ስራ ይሰራሉ፤
ሠ. የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማጎልበትና Log in
ለማስፋት ስልት ይቀይሳሉ፤ስራ ላይ ያሳላሉ፤
ረ. የተለያዩBenishangul
አካላትን ተሳትፎ Gumuz
ለማጎልበትና ቁሳቁ
󰟙 Education Bureau's
ድጋፎችን ለማሰባሰብ ይሰራሉ፤ የተገኘውም post
የተገኘዉም በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን
ይከታተላ፤ያረጋግጣሉ፤
ሰ. ከተሞክሮ በመነሳት የትምህርት ማህበረሰቡን
ፍላጎት መሠረት አድርገው ይሰራሉ
ቀ. የሚኒ ሚዲያ ክበባት ሥራዎችን መደበኛ በሆነ
ሁኔታ ያከናውናሉ፤
በ. ሪፖርት የማድረግና ግብረ-መልስ የመቀበል
ተግባራችን ያከናውናሉ፡፡
የመንግሥት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ከሕዝብ
ክንፎች በተለይ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ሊኖረው
የሚገባ ቅንጅታዊ ሚና
የተሻሉ ልምዶችንና ችሎታዎችን በመቀመር
በፍጥነት የሚስፋፉበትን ሁኔታ በጋራ መረለም፤
ከመዋዕለ ህጻናት ጀምሮ በሚኒ ሚዲያ
መልዕክቶች እንዲተላለፉ በመደገፍ አዲሱ ትዉልድ
በትክክለኛ አስተሳሰብና ስነ- ምግባር ተቀርጾ
እንዲወጣ ማድረግ
በአመት አንዴ ወይም ሁለቴ የጋራ ሮረም
ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ በማዘጋጀትና
የአሰራር ግልጽነት በመፍጠር የህ/ሰቡን
ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
የአገሪቱ ሚኒ ሚዲያ አሁን ያለበትን አጠቃላይ
እድገት ፣ተደራሽነትና ሽፋንን እንዲሁም ዉንነቶችንና
ክፍተቶችን የሚመልሱ አዉደ ጥናቶችን በየጊዜዉ
በጋራ ማካሄድ፤
ከሚመለከተዉ አካል ጋር በመሆን በዘርፉ
ለሚመሩት አካላት በየጊዜዉ የአቅም ማጎልበቻ
ስልጠና መስጠት
የላቀ ዉጤት ያስመዘገቡ የትምህርት ቤት ሚኒ
ሚዲያሮች የሚበረታቱበት ስርዓት በጋራ መዘርጋትና
መፈጸም፤
የትምህርት ማኅበረሰቡ በዴሞክራሲ ፣በመልካም
አስ/ር በልማትና ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር
ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የተገኘውን ይህን
መልካም ዕድል በተዋሃደና በተቀናጀ አግባብ
መጠቀም
የሚኒ ሚዲያ ሥነ-ምግባር
በሚኒ ሚዲያ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በከፍተኛ
ጥንቃቄ ፣ሙያዊ ስነ-ምግባርና ክህሎት በማዘጋጀት
የመልዕክቱን ወቅታዊነት ፣ተአማኒነትና ይዘት ሙያዊ
በሆነ ሚዛን መመዘንና የአንድን ወገን ብቻ ሳይሆን
ተደራሹንም እያሳተፈና ዉጤቱን እየገመገመ
መራመድ የሚችል አቅም መገንባት አስፈላጊ ነዉ፡፡
ስለዚህ በሚኒ ሚዲያ የሚሳተፉ ባለድርሻዎች
ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሙያዊ ስነ-ምግባሮች ላይ
ግንዛቤያቸዉን የማስፋትና የመተግበር ኃላፊነት Log in
አለባቸዉ፡፡
አዳዲስ Benishangul Gumuzአመለካከቶችን
ሃሳቦችን መረጃዎችንና
󰟙
ለማቅረብEducation Bureau's
/ለማሰራጨት/ post
መርሃ ግብሮቹን
በጥንቃቄ የማዘጋጀት
በትምህርት ማኅበረሰቡን ውስጥ ልማታዊ
የለውጥ አስተሳሰብ እንዲጎለብ ማድረግ
የትምህርቱ ማኅበረሰብ በልማት ላይ እንዲረባረብ
የማነሳሳት ሚና መጫወት
የትምህርቱ ማኅበረሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት
ማዕከል ያደረገ ሥራ ማቅረብ
ግንባር ቀደም የለውጥ አብነቶችን ማስተዋወቅ
አመርቂ የልማት ስኬት ታሪኮችን ማስተጋባት
በኮምንኬሽን ስትራቴጂ መመራጽ
የልማት ዘገባ የማቅረብ ሙያዊና ተቋማዊ ብቃት
በቀጣይነት መገንባት
መረጃዎቹ ተደራሽ ከመደረጋቸው በፊት
ከተጨባጭ ምንጮች መገኘታውንና በአግባቡ
መደራጀታቸውን የማረጋገጥ፤
የዜና፣ የመዝናኛና የትምህርት ማኅበረሰቡ
አገልግሎት መርሃግብሮችን ሚዛናዊነት የመጠበቅ፤
የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ፍላጎት ከማሟላት
አኳያ ሚዛናዊ የማድረግ፤
መርሃ ግብሮቹን የኅብረተሰቡን ሰብዕናና ሃይማኖት
ከሚያንኳስሱ ይዘቶች ነጻ የማድረግ፤
በትምህርት ማኅበረሰቡ መካከል ያለውን መልካም
ግንኙነት የማጠናከርና በመሃላቸዉ ሊኖሩ የሚችሉ
አለመግባባቶችን የማስወገድ፤
በትምህርት ማኅበረሰቡን ውስጥ የተከሰቱ ጾታዊ
ጥቃቶችን ፣የሕግ ጥሰቶች የመሳሰሉትን ዘገባዎች
ለተማሪው ተደራሽ በሚደረግበት ጊዜ ከፍተኛ
ጥንቃቄ የማድረግ፤
በመረሃ-ግብር ስርጭት ጊዜ ተደራሲያንን በተለይ
ሕጻናትንና ወጣቶችን የማሰብና አርአያና የመሆን፤
የግለሰብ መልዕክቶች በሚሰራጩበት ጊዜ ትኩረት
የመስጠትና ከፍተኛ ጥንቃቄ የማድረግ
ማጉረምረምን፣ ትችትን ፣ግጭትን ፣አሉባልታና
የመሳሰሉትን ኢ-ስነ-ምግባራዊ ድርጊቶችን በተቻለ
መጠን የማስወገድ፤
አከራካሪና የትምህርት ማኅበረሰቡን ፍላጎት መሰረት
ያደጉ ርዕሰ ጉዳዮች ከነሙሉ ይዞታቸው
ለተደራሲያን የማሰራጨት
ግጭት የሚያባብሱ መረጃዎችን ተደራሽ
ከማድረግ ይልቅ ሳቢ፣ ማራኪና ጠቃሚ በሆኑት ላይ
ትኩረት የመስጠት፤
በትምህርት ማኅበረሰቡን ችግሮች ዙሪያ የመወያያ
መድረክ የሚፈጠርበት ጊዜ በትኩረት በጎ
ገጽታውን ሊያጎላ የሚችል፣ ሊወሰድ የሚገባው
መፍትሄ የሚጠቁምና በማን መከናወን እንዳለበት
በግልጽ የሚቀርብ እንዲሆን የማድረግ Log in
በቡድን የመስራት ባህልን የማዳበር
Benishangul
በክበቡ የሚደረገው Gumuz
ዉይይት፣ ግምገማና ቅስቀሳ
󰟙 Education Bureau's post
ንቁ ተሳታፊ የመሆን
አመራሩን የማክበር እንዲሁም በተቀመጠዉ
አስተዳደራዊ ሂደት መሰረት ጥያቄዎችን የመጠየቅ
በሚነሱ ማንኛዉም አለመግባባቶች ላይ
ዲሞክራሲያዊ በሆነና የትምህርት ማኅበረሰቡን
ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የመወያየት
መረጃዎን በወቅቱ ተደራሽ የማድረግ፣ በቂ
የዝግጅት ጊዜ የውሰድና ከአመራሩ ጋር የጋራ
መግባባት ላይ የመድረስ
ማንኛውም ዓይነት የጦር መሳሪያ ወደ ሚኒ
ሚዲያው ስቱዲዮ ይዘው እንዳይገቡ የመጠበቅ
ስቱዲዮ ውስጥ አገልግሎት ለመስጠት ሲገባ
ከማንኛውም ሱስ ከሚያስይዙ ነገሮች ፀድቶ
የመገኘት
እንግዳም ሆነ ጓደኛ ወደስቱዲዮ እንዲገባ
ከመጋበዙ በፊት የስቱዲዮ መመሪያዎችን ግልጽ
የማድረግ
ባጠቃላይ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ሚዛናዊ፣
ትክክለኛ፣ የትምህርት ማኅበረሰቡን ደህንነትና ነጻነት
የሚጠብቁ፣ የወንጀል ድርጊቶችን የማይደግፉ፣
የብሔሮች ፣ብሔረሰቦችና የሕዝቦችን መብት
የሚያከብር፣ጦርነትን የማይቀሰቅሱ እና የሕጻናት ፣
የሴቶችና የአረጋዊያንን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን
ደህንነት የማይጎዱ መረጃዎችን እንዲሆኑ መሥራት፡፡
የክትትል ፣የድጋፍና የግምገማ ስርዓት
አባላቱ እርስ በእርሳቸዉና በመላው ታዳሚ
ማትም በትምህርቱ ማህበረሰቡ መገምገምና ገንቢ
አስተያየቶችን መቀበል
ከሌሎች የሚኒሚዲያ አባላት ጋር ተገናኝተው
ልምድ የሚለዋወጡበት ቀጣይነት ያለ መድረክ
ማዘጋጀት
በየዕለቱ በሚቀርበው ዝግጅት በየጊዜዉ
አስተያየቶችንና እርምቶችን መውሰድ
ዝግጅት ለሚያቀርቡለት ማኅበረሰብ በተወሰነ ጊዜ
የታዳሚ ጥናት /audience research/ ማድረግ
የሚኒ ሚዲያኌ መመሪያ /ኤዲቶሪያል
ፖሊሲ/ተዘጋጅቶ ስራ ላይ እንድዉል
ማድረግ፤ዝግጅቶችም ከመቅረባቸዉ በፊት
ስለጥራታቸዉና ህጉን አክብረዉ ስለመሰናደታ
በገምጋሚዉ ኮሚቴ መገምገም አለባቸዉ
ተግባራዊ እንቅስቃሲያቸዉን ለየአካባቢያቸዉ
የኮሙንኬሽን መዋቅር ሪፖርት ማድረግ
በበላይ የሚያስተዳድርና በየጊዜዉ ችግሮችን
ለመፍታት የሚችል የአካባቢዉ አስተዳደር አካል
የሚሳተፍበት ፎረም መመስረት
ባጠቃላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ወደ ተግባራዊ
እንቅስቃሴ ከገቡ በኋላ የሚያጋጥማቸዉንLog in
እንቅፋት ተከታትሎ ለመለየትና ለመፍታት
የሚያስችሉ Benishangul
ወቅታዊ ድጋፎች Gumuz
መሰጠታቸዉን
󰟙 Education Bureau's post
አንዲሁም በተግባራዊ ርብርቡ ሂደት የሚገኙ
ምርጥ ልምዶችን ተከታትሎ በመለየትና በመቀመር
ለማስፋፋት የሚያስችል ስራ በቀጣይነት እየተሰራ
መሆኑን ማረጋገጥ የሚኒ ሚዲያዎችን አገልግሎት
አሰጣጥ የላቀ ከማድረግ አኳያ ልዩ ተፈላጊነት
ያለዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ከዚህ አኳያ ሶስት ዋና ዋና
የክትትልና የድጋፍ መስተጋብሮች ተግባራዊ
ይደረጋሉ፡፡ እነሱም
1. የጋራ ግምገማ መድረክ ተጠናክሮ እንዲቀጥል
ማድረግ
2. የሪፖርትና ግብረ-መልስ ስርዓት ማጠናር
3. የሱፐርቪዥን አሰራር መዘርጋትና ተግባራዊ
ማድረግ ናቸዉ፡፡
ማጠቃለያ
የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት በሥራው ለሚሳተፉ
ወገኖች ሁሉ ትምህርት ሰጪ እና አዝናኝ የሆነ ልምድ
የሚያድል ነው፡፡ የተማሪዎች የጠራ ችሎታ
የሚገለጥበትን ልዩ መድረክም የሚያመቻች ነው፡፡
ለተማሪዎች አስደሳች የሚሆንና የፈጠራ
ክህሎታቸው ለማዳበር የሚያግዝ ነው፡፡ የት/ቤት
የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት ቁልፍ መርሀ ፤ ሥራው
በተማሪዎች የሚመራ እና ተማሪዎች ፍላጎት ስሜት
የሚያንዝባርቅ እንዲሆን የማድረግ መርሀ ነው፡፡
ተማሪዎችና መምህራን የሚሳተፉበትና
የሚመካከሩበት፤ የት/ቤት የተለያዩ ፍላጎቶች
የሚያንፀባርቁበት የአስተዳዳር መዋቅር መገንባት
የፈጠራ ጥበብ የሚታይበት ዘርፈ ብዙና አስደሳች
ዝግጅቶችን የሚያቀርቡ ተማሪዎች በእረፍት
ጊዜያቸው ተሳትፎ በማድረግ የፈጠራ ክህሎታቸውን
ለማዳበር የሚችሉበት የሚዲያ አገልግሎት
እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ስለዚህ በሚዳያ በዋነሃነት በትምህርት ቤቶች ሚን
ሚዲያ ባለድርሻ አካላት ዘንድ የሚታየውን የአሰራር
ክፍተት ለመሙላት ፣ በሚኒ ሚዲያወች መካከል
በተለይ አገራችንን ሚዲያ ስፋተና ደረጃ ከፍ
ከማድረግ አኳያ ያለው ግንኙነት ጤናማና
በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ
የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ማኑዋል ይፈጥራል ተብሎ
ይታመናል፤ በተለይ ደግሞ በሀገር ደረጃ የተቀረፀው
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተግባራዊ
ለማድረግ በሚካሄደው እንቅስቃሴ የህብረተሰቡን
ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና በዚህም ሂደት
አስተሳሰቡን ለማዳበር በሚደረገው እንቅስቃሴ
ውስጥ ማኑዋል ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡
ባጠቃላይ ማኑዋሉ የአፈፃፀም አመራርን
ከአመለካከት፣ ከአደረጃጀት፣ ከአሰራር ፣ ከክህሎትና
Log in
ከግንኙነት አንፃር ለመፈተሽ እድል የሚሰጥ ሲሆን
የአሰራሩን አቅጣጫ በመከተልና የሀገራችንን ነባራዊ
Benishangul
ሁኔታ ከግምት Gumuzበሂደት የሚኖሩ
ውስጥ በማስገባት
󰟙 Education Bureau's post
ተጨማሪ ልምዶችን ከትግበራ ጋረ በማዋሃድ
የሚዳብርና የሚሻሻል ይሆናል፡፡ እንዲሁም ከሚኒ
ሚዲያ ማኑዋሉ ጋር ተጣጥመው መሄድ የሚገባቸው
ሌሎች የአሰራራ ስርዓቶች ካሉ በቀጣይነት በሚኖር
የጋራ ፎረምና ትግበራ የሚሻሻልና የማጣጣልና
የማጣጣም ሥራ የሚሰራበት ይሆናል፡፡

አባሪዎች
አባሪ አንድ ፡- የሚዲያ ማስፋፋት ሥራ
የሚከናወንባቸው አካባቢዎች ዝርዝር መመዘኛ
መስፈርቶች
ተ.ቁ የመመዘኛ መስፈርቶች የተሰጠው ነጥብ
በመቶኛ
1. ከአመለካከት አንፃር 30
1.1 ልማታዊ የለውጥ አስትሳሰብ ለማምጣት
ዝግጁ የሆነ 7
1.2 የግብዓት እጥረቶችን በራሱ ለመፍታት ጥረት
የሚያደርግ ሁሉንም ነገር ከመንግስት የማይጠበቅ 9
1.3 የሕዝብን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማእከል ያደረገ
ሥራ የሚያቀርብ 5
1.4 ግንባር ቀደም የሚዲያ ተጠቃሚነት አብነቶችን
የሚያስተዋውቅ 5
1.5 ሚዛናዊ አስተሳሰብ የሚገነባ 4
2. ከክህሎት አንፃር 20
2.1 የሚዲያ ተደራሽነትና አብዝሃነትን ለማስፋፋትና
አገልግሎት ለመስጠት ወቅታዊና የተሻለ አሰራር
የዘረጋ 7
2.2 በውስን ሀብትና የአካባቢ ግብዓቶችን
በመጠቀም መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ ዝግጁ
የሆነ 5
2.3 የልማት ዘገዛ የማቅረብ ሙያዊና ተቋማዊ ብቃት
በቀጣይነት ለመገንባትና ለማረጋገጥ ዝግጁ የሆነ 5
2.4 ሥራውን በጊዜ ከፋፍሎ የሚተገብርና
የሚያከብር 3
3. የሥራ አመራርና አደረጃጀት 12
3.1 በጽሁፍ የተደገፈ እቅድ ያለውና ተግባራዉ
ለማድረግ ዝግጁ የሆነ 5
3.2 የአደረጃጀትና የሥራ መዋቅር ያለውና ተግባራዊ
ለማድረግ ዝግጁ የሆነ 4
3.3 የአገልግሎት መስጫ ማእከላት አደረጃጀትን
የተከተለ መሆኑ 3
4 አሠራር 24
4.1 በአፈፃፀም ክትትል ውጤት ላይ የተመሰረተና
ለተፈጠሩ የአፈፃፀም ችግሮች መፍትሄ የመስጠት
አሰራር ያለው 9
4.2 እለታዊ የሆነ የጥናት፣ የደንብ ፣ መመሪያ፣
የማኑዋል፣ የፕሮጀክት ሰነዶች በጋራ ተዘጋጅቶ Log in
ተግባራዊእንዲሆኑ ጥረት የሚያደርጉ 6
Benishangul
4.3 በባለድርሻ Gumuz
አካላት መካከል የተቀናጀና የሚናበብ
󰟙 Education
አሰራር የዘረጋ 5 Bureau's post
4.4 ተደጋጋፊነት ያለው የግልጽነት የተጠያቂነት
አሰራር እንዲሰፍን ጥረት ያደረገ 4

5 መንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም 12


5.1 ከምንግስት የተመደበለትን በጀት ለሚፈልገው
ዓላማ ያዋለ 2
5.2 መንግስት በዘረጋው የሚዲያ መሠረት ልማት
ለመጠቀም ያደረገው ጥረት 5
ድምሩ 100%

አባሪ ሁለት፡- የውጤታማ አፈፃፀም አመላካቾች


ተ.ቁ የአፈፃፀም አማላካቾች መግለጫ
1 የሚዲያ ተደራሽነት ያልተስፋፋባቸው አካባቢዎች
ብዛት፣
2 ሚዲያ ያልተጠቀመባቸው ቋንቅዎት ብዛት፣
3 የሚዲያ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በሚደረገው
ጥረት ውስጥ ተጠቃሚ ሲሆኑ የሚችሉ የሌሎች
አካባቢዎች ብዛት፣
4 አካባቢዎ የሚዲያ ተጠቃሚ በማድረግ ሂደት
ውስጥ የሚሳተÕ የድጋፍ ሰጪ አካላት ብዛት፣

አባሪ ሦስት ፡- ሚዲያ የተስፋፋባቸው አካባቢዎች


መረጃ መቀመሪያ ቅጽ
ተ.ቁ ርእስ ጉዳዮች መግለጫ
1. የአባባቢዎች ጥሬ ሃቆች ፣/መቼ እንደሚቋቋም፣
ሕጋዊ አደረጃጀቱ፣ ከመንግስት የሚያገኛቸው
ድጋፎች፣ ወዘተ/
2. የማስፋፋቱ ሥራ ሂደት ውጤታማነት መግለጫ፣
3. አባካቢዎቹን ያጋጠማቸውን ችግሮችና
ተግዳሮቶቹን ለመቅረፍ የተወሰዱ የመፍትሄ
እርምጃዎች፣
4. የአባባቢዎቹ የወደፊቱ እቅድሃ ይህንንም
ለማስፈፀም ያለው ዝግጅትና መግለጫ፣
5. አካባቢዎቹን በሚዲያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
በማብቃት የተሳተፉ ድጋፍ ሰጪ አካላትና የድጋፍ
አሰጣጥ አግባቡ፣

አባሪ አራት ፡- የከተማ ሚኒ ሚዲያ ለማቋቋም


የሚያስፈልጉ ዝርዝር መሳሪያዎችና ወጪአቸው
ተ.ቁ ብዛት የእቃው አይነት መግለጫ የአንዱ ዋጋ
ጠቅላላ
1 4 ሆርን እስፒከር 1,200 4,800
2 1 አምኘሊፋየር/መካከለኛ 2,000 2,000
3 1 የእጅ ማይክ 50.00 50.00
4 2 ቴፕ 1500 3,000
5 10 የቴፕ ካሴት 5.00 10.00 Log in
6 1 ጃክ/ከቴፕ ወደ አምፕሊፋይር የሚወስድ/
Benishangul Gumuz
10.00 10.00
󰟙
7 8 ሜትርEducation Bureau's ወደ
ገመድ ከአምፕሊፋይር postሆርኖች
የሚሄድ/ 200 1,600
8 1/በደርዘን/ ትንዟ ባትሪ ድንጋይ 50.00 50.00
9 1 ጠረጴዛ 1,000 1,000
10 2 ወንበር 250.00 500
ጠቅላላ ድምር ወጪ 6,265 13,020

የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መርኃ-


ግብር ተግባራትን ከትምህርት ቤት ሚኒ-ሚዲያዎች
ጋር ማስተሳሰር
ለትምህርት ቤት ሚኒ-ሚዲያዎች ተጠሪ ሠልጣኞች
የቀረበ
1.ኮሙኒኬሽን ምንድን ነው
• ትርጓሜ
በመልዕክት አስተላላፊውና ተቀባዩ መካከል
የሚከናወን የመረጃ ልውውጥ
አስረጂ፡-
…ከዚህ በታች በሰፈረው ጽሑፍ መሰረት ተገባራዊ
ይኹን….
ልጅቷ ተሳስታ ስትናገር ፈታኞቹ ርስ በርስ ተያዩ፡፡
በቀለ፤ እባክህ ዝም በል!
ነጩን ጨርቅ ሲያውለበልቡ ተኩሱ ሁሉ ባንዳፍታ
ፀጥ አለ፡፡

• አላባዉያን/Elements
የግኑኝነት አሳለጮች ናቸው፡፡እነርሱም፡-
መልዕክት ላኪ
የሚላከው መልዕክት
መልዕክቱ የሚላክበት መንገድ -
በቃል፣በፖስታ፣በስልክ፣በቴሌግራም…
መልዕክት ተቀባይ
የመልዕክቱ ግብረ-መልስ
• የኮሙኒኬሽን ሂደት
ሐሳብ
መመስጠር
መልዕክት
ተቀባይ
መተርጎም
መግባባት

• አጋጆች
አለማቀድ
ግልጽ አለመሆን
በአግባቡ አለመስማት
ደካማ የርስ-በርስ ግኑኝነት መኖር
የተዛባ መልዕክት መኖር
የመልዕክት ጭነት መብዛት Log in
የሚሹትን ብቻ መርጦ መስማት /የተነገረውን
Benishangul Gumuz
በቅጡ አለመስማት/
󰟙 Education
ሙያዊ ቃላትን ማብዛት Bureau's post
አካላዊ እንቅስቃሴዎችና ነውር-ተግባራት
አለማተኮር
ፍላጎተቢስነት
ለመልዕክት ተቀባዩ የጉዳዩ አይረቤነት
የአመለካከት ሁኔታ
አካላዊ ኢሙሉነት

• ማሳለጫዎች
መልዕክቱን ግልጽና አጭር ማድረግ
በሚገባ ማቀድ
የድምጽ ምጣኔን በሚገባ መከወን
የተቀባዩን ፍላጎት ማጤን
ተገቢ ቋንቋ መጠቀም
ትጉህ አድማጭነት
ግብረ-መልስ መቀበል
2.የኮሚኒኬሸን አይነቶች
• ቃላዊ - (አንዱ ከሌላው/ከብዙዎች ጋር
የሚያደርገው)
• ኢ-ቃላዊ (በሰዎች መካከል በጥቀሻ፣በሚታዩ
የተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴዎች)
• ጽሑፋዊ
• መደበኛና - የራሱ ሒደት ያለው - በደብዳቤ (ቀንና
ቀጥር ፊርማ ያለው)፣በፋክሰ፣ኢሜል፤
ኢመደበኛ- …እስቲ ካገኘኸው ንገርልኝ…
• ምልክታዊ -በመብራት፣በተለያዩ የሚታዩ
ምስሎች…
3.የድምጽ /አነባበብ /ምጣኔ
• የሥርዓተ-ነጥቦችና የንብባብ ተዛምዶ

የቡድን ሥራ

የተቀመጠችበትን ወንበር ሳታፀዳ በመቀመጧ ልብሷ


አቧራ ቅሟል ሀገር ደህና ብላ ብላ ወደቤት ስትገባ
ታላቅ እህቷ አንቺ ልጅ ምናለ የሰው ድካም ቢገባሽ
ስቀመጪ ተጠንቀቂ አላልኩም መቼ ነው የሚገባሽ
እኔ አንቺን እንደናት እንደ ሞግዚት እንደ እህት እንደ
ገረድ ላንቺ ምን ያልሆንኩት አለ ኤጭ አሁንሰ በዛ
4.የሚኒ-ሚዲያው ይዘት አመራረጥ
• የሚቀርበው ፕሮግራም ከሚኒሚዲያው ዓላማ
ጋር ያለውን ተዛምዶ ማጤንና ግቡን ሳይስት
መዘጋጀቱ

የቡድን ሥራ
በትምህርት ቤታችሁ አንድ ክፍል ሴክሽን ኤ፣ቢና ሲ
መካከል የሚደረግ የጥያቄና መልስ ውድድርን Log in
ትንቅንቅ የሞላበት ነበር፡፡የተማሪዎቹ ትጋትና
Benishangul
ሲመልሱ የነበረው ፍጥነት Gumuz
ባለፈው መንፈቀ-ዓመት
󰟙
ከነበረው የበለጠ ፍጥነትና ግልጽነትpost
Education Bureau's ተላብሷል፡፡
የተማሪዎቹን የአመላለስ ሁኔታ ስዕላዊ በሆነ ሁኔታ፣
ከአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መርሃ-
ግብር አንጸር የልጆቹን ሁኔታ አዛምዳችሁ በመዘገብ
በ2 ደቂቃ የሚቀርብ ዘገባ ስሩና አቅርቡ፡፡
5.የዜና አዘጋገብ
• ዜና - አዲስ መረጃ፣አዲስ ኩነት፣ወይም ድርጊት
(ኮንሳይስ የእንግሊዝኛ መዝገበ-
ቃላት)የሚጻፍ፣የሰዎች የድርጊት
እንቅስቃሴ፣የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ጉዳዮች ክስተት
ዘገባ፣በችኮላ የሚዘጋጅ ሥነ-ጽሑፍ፣ሰው ሲሰማው
የሚደነቅበት (ማዕረጉ፤76-77)
አንድ ዜና ሲዘገብ፤ ምን ተከናወነ፣መች ተከናወነ፣ ማን
አከናወነው፣ የት ተከናወነ፣ለምን ተከናወነ የሚሉትን
ጉዳዩች በሚገባ ማሟላት አለበት፡እኒህ ጠያቂ ቃላት
በተለይ ለዜና መግቢያ (ሊድ) ወሳኝ ናቸው፡፡ይሁን
እንጂ የግድ ሁሉንም (6ቱንም ጠያቂ ቃላት አጣምሮ
ይሰራ ከተባለ ደግሞ እንዳያሰለች መጠንቀቅ ያሻል)
በኒህ ጠያቂ ቃላት የተገነባ መሪ መግቢያ ከተከወነ
የዜናው ግማሽ ተከወነ ማለት ነው፡፡
• ጥሩ ዜና የሚባለው ምን ምን ነገሮች ሊኖሩት
ይገባል
መግቢያ ጽሑፍ
(መክፈቻ አንቀጽ)
የመክፈቻ አንቀጽ
አብራሪ ቃላት
የመክፈቻ አንቀጽ
አዳባሪ መረጃዎች
የዜና
መደምደሚያ

መግቢያ ጽሑፍ
(መክፈቻ አንቀጽ)
አብራሪ ቃላት
አዳባሪ
ደምዳሚ

የቡድን ሥራ
ስለዚህ ስልጠና በአስራ ሦስት መስመር የሚያልቅ
ዜና ጻፍ፡፡ ትኩረት! የስልጠናውን አላማና ግብ አትርሳ!

6. የቀረቡ ፕሮግራሞች የሰነድ አያያዝና አጠባበቅ

የቡድን ሥራ
• ለምን እንሰንዳለን /በጽሑፍ በድምጽ
• የአፃፃፍ የህዳግ ሁኔታ- በወረቀቱ የግራ ህዳግ Log in
ከ3-4 ሳ.ሜ. ገባ ብሎ ከራስጌ ህዳግ 2 ሳ.ሜ ዝቅ
ብሎ ፣ከቀኝ Benishangul
ህዳግ 2 ሳ.ሜ.Gumuz
ገባ ብሎ ና ከግርጌ
󰟙 Education Bureau's
ህዳግ 3 ሳ.ሜ. ከፍ ብሎ በሚገባ መተው post አለበት፡፡
ይህ የሚሆነው ፤ የተተዉት ስፍራዎች በሙሉ
ዜናው/ጽሑፉ ከመቅረቡ በፊት ለአርታዒው
ሲቀርብለት ከርዕሱ አንስቶ የሚሰጠው እርምት ካለ
ተገቢ የማረሚያ ስፍራ እንዲያገኝና በሚገባ ታርሞ
ከተነበበ በኋላም ለመሰነድ እንዲመች ነው፡፡በስተቀኝ
ባለው ሰፋ ባለው ስፍራ ወረቀቱ በመብሻ ተበስቶና
በፋስትነር ታስሮ ሲቀመጥ ዋናው የጽሑፍ ስፍራ
ከመቀደድ ይድናልና ነው፡፡

• የአቃፊ ፋይል ፋይል ዝግጅትና አቀማመጥ


በየዓመቱ ወይም ሴሚስተሩ የተለየ፣ በክላሰር ላይ
በጉልህ ተለይቶ የሚጻፍ የተዘጋጀውን ፕሮግራም
የለየ መሆን አለበት ምሳሌ የሳይንስ ማሕደር የሚል
ፕሮግራም ከሆነ የርሱ ብቻ ተለየቶ
ይታሰራል፣ስፖርት፣ሌሎችም እንዲሁ፡፡ከዚያም ለዚሁ
ሲባል በተዘጋጀው የፋይል አቃፊ ይቀመጣል፡፡
7.አድማጭ /ተደራሲዎችን/ መለየት
• ለማንነው ፕሮግራም የሚሠራው
• የተደሪሲያኑ/አድማጩ/ የዕውቀት ደረጃ ምን ላይ
ይገኛል፣ ዕድሜያቸው፣ ጾታቸው
8.ሲግኔቸር ቲውን ምንድነው /መለያ መግቢያ
ሙዚቃ/
• ጥቅሙ- አድማጩን ያነቃል፣ፕሮግራሙን
እንድንወድደው ያደርጋል፣አንድ ዓይነት ብቻ ነው
አይቀያየርም
• አመራረጡ በአዘጋጆቹ ተመርጦ ይወሰናል
• ከፕሮግራሙ ጋር ተዛምዶ ያለው ቢሆን ይመረጣል

9. ሙዚቃ
• አመራረጡ- ከወቅታዊነት ጋር/የቆዩ ሙዚቃዎች
የሚሰሙ ከሆነም እንዲሁ ይመረጣሉ፣ከቀረበው
የጽሑፍ ተዛምዶ ያለው፡፡

ምሳሌ፡- መምህሩ በ1967 ዓ.ም. የእድገት በሕብረት


የሥራና የዕውቀት ዘመቻ ልምዳቸውን ሲያካፍሉ ቃለ
መጠይቅ ከመደረጉ በፊት፣ከተደረገ በኋላ ወይም
በመካከሉ ስለ ዘመቻው የተዘመሩ ሙዚቃዎችን
ከዩቱብ ቀድቶ ማስደመጥ
10. ቃለ-መጠይቅ
• አንድ በሚገባ ተበራርቶ ሊታወቅ የሚፈለግ ነገር
ሲኖር የሚጠየቅ፣ጭውውት፣ልምድም ማካፈል
ሊሆን ይቻላል ሊሆን ይችላል
• ጠያቂው እንዴት ይዘጋጃል- ሰለሚጤቀው ሰው
በቂ መረጃ መሰብሰብ፣ ስለሚጠይቀው ነገር የተለያዩ
መረጃዎችን ማገላበጥና የሚያውቁ ሰዎችንም
መጠየቅ ይገባል፡፡ ቢቻል የተጠያቂውን ቅርብ Log in
ጓደኞች አግኝቶ የተለየ ገጠመኞቹን ማወቁ
ቃለመጠይቁን Benishangul
ያዋዛዋል፡፡ Gumuz
󰟙 Education
• ስልቱ- በተቻለ መጠን Bureau's
የሚመቸውንpost
ጊዜ
እንዲመርጥ ማድረግ ፣ተጠያቂው ሙሉ ነጻነት
እንዲሰማው ማድረግ፣ቀጥታ የሚተላለፍ ካልሆነ
(በጽሑፍ የሚቀርብ በቴፕ የሚቀዳ ከሆነ) የአርትዖት
ሥራ ስለሚሠራለት ነጻነት መስጠቱ ተገቢ ነው፡፡
በተወሰነ የቀጥታ የአየር ሰዓት የሚቀርብ ከሆነ ግን
ከሚፈለገው ዋና ፍሬ ነገር ተናጋሪው እንዳይዘልል
ማስጠንቀቅ ወይመ በዘዴ ማገድ ይገባል፡፡

የቡድን ሥራ

ትምህርት ቤታችሁ ዙሪያውን በእንጨት የታጠረ


ነበር፡፡ አሁን በማኅበረሰቡ ትብብር በግንብ ታጠረ፡፡
5 ተገቢ ጥያቄዎች
Yetegenelij አዘጋጅተህ
Omani and የትቤቱን ርዕሰ-
19 others
መምህር ቃለ መጠይቅ አድርግ፡፡ከአጠቃላይ
የትምህርት
󰤥 20 ጥራት ማስጠበቂያ 󰤦 1 መርሃ-ግብር󰤧 አንጸር
አዛምደው፡፡ ከዚያም በተግባር አቅርበው (Role
play) Kindu Kassaw
11.መልዕከት ስልጠናውቀረፃ ምንድነው
ቢያልፈንም እድሜ
• ለአንድ ፕሮግራም
ለቴክኖሎጅ መረጃው ዓላማና
የሚፈለገው በሙሉ ግብደርሶናል
መለየት
5 yrs
• የሚቀርብለትን አድማጭ መለየት
• ምንድነው አድማጩ/ወቅቱ
የሚፈልገው፣የሚመኘው፣
Recent Post by Pageብሎ መመርመርና
መዘጋጀት
Benishangul Gumuz
12. አርትዖት 󰟝
Education Bureau
• አርትዖት የተሻለ የመጻፍ ችሎታ ያለው ሰው
Jan 10, 2022󰞋󰟡
የሚሠራው ራሱን የቻለ ተግባር ነው
የቤ.ጉ.ክ.መ.
ከርዕስ ጀምሮ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው የ2014 ዓ.ም
ፊደልን፣ ቃላትን፣የአንቀጽ
የትምህርት ዘርፍ አፈፃፀም
ፍሰትን፣በተወሰነው ውይይት
ሰዓት ሊቀርብ በኢቲቪ
የሚችል መሆኑን
የተላለፈ ዜና ፤
ገምቶ አርሞ ያሳልፈዋል፡፡
• ጥቅሙ- የተመጠነና ሳቢ እንዲሆን ያደርጋል

Abdela Mohamed and 61 others

󰤥 62 󰤦 󰤧6

Benishangul Gumuz 󰟝
Education Bureau
Jan 6, 2022󰞋󰟡 Log in
26 የትምህርት ቤት ኮምፒውተሮችን በመደበቅ
ከአሸባሪውBenishangul
የህወሓት ኃይሎችGumuz
ዘረፋ የታደጉት
󰟙 Education
ግለሰብ... See more Bureau's post

Osa Man and 36 others

󰤥 37 󰤦 󰤧4

Benishangul Gumuz 󰟝
Education Bureau
Jan 6, 2022󰞋󰟡

የክልሉ ትምህርት ዘርፍ አፈፃፀም ላይ ውይይት


ተካሄደ
++++++++++++++++++++... See more

+4

አላህ ወኪል and 50 others

󰤥 51 󰤦3 󰤧4

Micky Man Abebe


Let us to start rebuild

Related Pages
Log in

Benishangul Gumuz
󰟙 Education
Amhara FinanceBureau's
Bureau post Assosa Uni

󱙶 Follow

You might also like