Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 13

ሰላም የህጻናት መንደር ቁ.

1 ት/ቤት
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው።ምሳ 1፣7

አፈ ታሪኮች

በ 7 ኛ ለ ተማሪዎች ቡድን 6 የተዘጋጀ

ለመምህር ሰናይት አለማየሁ


መግቢያ
ይህ የ ቡድን ስራ ስለ አፈ ታሪክ በደንብ
የ ሚያስረዳ ስራ ነው።ስለዚህም አፈ
ታሪክ ሲባል ውሸት እየተነገረ ሳይሆን
ጥንት የነበረ እውነት ፣ በአባቶቻችን
እየወረደ የመጣ ነው።
ግን ሙሉ በሙሉ እውነት ነው ማለት
አይቻልም።
ማውጫ
አፈ ታሪኮች
...................................................4
ልዩ ልዩ አፈ
ታሪኮች.......................................5
በቅሎ..................................................................
5
የሌሊት
ወፍ......................................................6
አጼ ልብነ
ድንግል.............................................7
አባ
መላ.............................................................8
የወንጪ
ሃይቅ...................................................9
መደምደሚያ...................................................1
0
ዋቢያት............................................................11

አፈ ታሪኮች
አፈ ታሪክ ማለት ድሮ የነበሩ አባቶቻችን
ያዩትን ለልጆቻቸው በመናገር ከትውልድ
እየተላለፈ የመጣ በቃል የሚነገር የስነ-
ጽሁፍ ዓይነት ነው።አፈታሪክ
እንደየቦታው እና እንደ እውነትነቱ
ሊለያይ ይችላል።በዋናነት ግን በሁለት
ይከፈላል። እነርሱም፦
1.እውነተኛ አፈ ታሪክ፦ትክክለኛ
የሆነ፣በእውነታው አለም የሚነገር እና
ምስክሮች ያሉት የአፈ ታሪክ አይነት
ነው።
2.ሃሰተኛ አፈ ታሪክ፦ይህ ደግሞ ምስክር
የሌለው፣ዝም ብሎ የሚወራ የ ዓፈ
ታሪክ አይነት ነው።

ልዩ ልዩ አፈ ታሪኮች
በቅሎ
በጥንት ጊዜ አህያ እና ፈረስ ተዳቅለው
በቅሎን ይወልዳሉ። በቅሎም አድጋ
ከወላዶቿ ትለያለች።ከዛም አንድ ቀን
በቅሎ ሳር እየጋጠች ሳለ በጣም
ጠገበች።ከጥጋቧም የተነሳ ሰማይ ቅርብ
ስለ ነበረ ሰማይን ትረግጥ ጀመር።ይህንን
ያየ ፈጣሪ ተቆጥቶ በቅሎን ጠራትና
እንዲህ አላት።<በጥጋብሽ ሰማይን
ረግጠሻልና ከእንግዲህ ወዲህ መሃን
ሁኚ።ሰማይንም ከአንቺ አርቃለሁ>አላት
ይባላል።

የሌሊት ወፍ
በሆነ ጊዜ የሌሊት ወፍ የነበረችበት
አካባቢ አደገኛ ረሃብ ይነሳል።ከረሃቡም
የተነሳ ብዙ ወፎች ይጠቃሉ።የተረፉት
ደግሞ እየተበደሩ እና እያበደሩ ረሃቡን
ተጋፈጡት።ይህ ረሃብ ግን እነሱን
ማሸነፍ አቅቶት ሄዳና አዲስ ቀን
ወጣ።ከዛም ሁሉም የተበደሩትን
በመመለስ ኑሮ ቀጠሉ።የሌሊት ወፍ ግን
ያኔ ሸማዋን ዘርግታ የተበደረችውን
መመለስ ስላቃታት ማምለጥን
መረጠች።ብዙተበድራ ስለነበር ወፎቹ
በጥብቅ ይፈልጓት ጀመር።እሷ ግን
በሌሊት ማደን፣በቀን ደግሞ ማረፍ
ጀመረች።በዚህም ምክንያት የሌሊት
ወፍ ተባለች።ይባላል።

አጼ ልብነ ድንግል
የ አጼ ልብነ ድንግል አባት በጊዜአቸው
እጅግ የተከበሩ እና የታወቁ ገዢ
ነበሩ።ታዲያ አንድ ቀንየኮሶ መድሃኒት
ለመጠጣት ቤት ይውላሉ።
ይህንኑ መድሃኒት የምታጠጣቸው
መልከቀናዋ የቤት አገልጋይ ተቀምጠው
በነበሩበት ማረፊያ ቤት እየገባች እና
እየወጣች ስታገለግላቸው በአጋጣሚ
ከእሳቸው ትጸንሳለች።ያገልጋይቱን ሆድ
መግፋት ያየችው ሚስት እሷን
በመግረፍ ምስጢሯን እንድታወጣ
ታደርጋለች።ይህ ምስጢርም ከተጋለጠ
በኋላ ቤተ ዘመድ ሁሉ በተፈጠረው
ውርደት በመቆጨት የሚወለደው ልጅ
አልጋ ወራሽ እንደሚሆን በማሰብ ሴራ
ይጠነስሳሉ።በተጠነሰሰውም ሴራ
መሰረት የሚወለደው ልጅ ዓይነ ስውር
እንዲሆን በማሰብ ሚስት ያገልጋይቱን
ሆድ በምስጢር በተልባ እንዲታሽ
ታደርጋለች።ሴራውም እንዲሳካ
በተደጋጋሚ የማሸት ተግባሩ
ቀጠለ።በመጨረሻም ሲወለድ አይነ
ስውር በመሆን ፈንታ የሚያምር
ዓይኖች ያሉት ሆኖ ተወለደ።ይባላል።

የወንጪ ሃይቅ እንዴት


ተፈጠረ?
በድሮ ጊዜ በጉራጌ አውራጃ የነበሩ
የወንጪ ሰዎች በጣም ጥጋበኞች
ነበሩ።ከጥጋባቸውም የተነሳ ክፉ ነገሮችን
ያደርጉ ነበር።እናም አንድ ቀን
የምታምር እህት ያለችው ሰውዬ እህቱን
እንዳያገቡበት እራሱ ሊያገባት
ወሰነ።ለጓደኞቹም ሲነግራቸው
ተስማምተው ድግስ ደገሱ።ይህንን ያዩ
ሽማግሌዎች አናይም ብለው
ወጡ።ሲጨፍሩ እና ሲደሰቱ ፈጣሪ
ተቆጣና ማዕበል
ለቀቀባቸው።ሽማግሌዎቹም ያሉበት
ደሴት በመሆኑ ሃይቅ ተባለ።ይባላል።

መደምደምያ
ዛሬ የ ሃገርን ታሪክ የሚለውጡ ታሪኮች
ውሸት ናቸው ተብለው የቀሩ ብዙ
ናቸው።ስለዚህ በመጻፍ ውሸቶችን
እውነት እናድርግ።
ዋቢያት
የ ስነ ጽሁፍ ተዋስያን በዘሪሁን አበበ
ታላላቅ ሰዎች
የስነ ዜጋና ስነ ምግባር መጽሃፍ 7 ኛ
ክፍል

You might also like