አብይ

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 31

እስኪ በስመአብ ብዬ ልጀምር ምስጋና

ፈጣሪ አምላኬዬን ሳለሁ በቁመና

መንግስት ላመጣልን ሀገር የሚያቀና

የኢትዮጳያን ህዝብ መጦ በትህትና

ዶ/ር አብይ አህመድ መረመረውና

የተመመ ሁሉ ዛሬ አገኘ ጤና

ሀገሪቱን ዞሮ በአብይ መኪና

እስከ አሜሪካ ተሰጥቶት ብኩርና

ጠ/ሚ የአመጣው ስልጠና

ወደኋላ አይሉም ይቀጥላ ገና

ወደፊት ይሰማ አብይ አብይ ዜና

እውነት ስራ ሰርቶ በስልጣን የጸና

የገሰገሰ ሰው በእምነት ጎዳና

ሃይማኖት አትጠፋም ምን ብትኖር መንምና

ታሪኩም አይጠፋ ምንም ቢሞት ጀግና

ሁሌ ይታወሳል በታሪክ በዝና

ኢትዮጲያ አለቀሰች አይኗን ተደግና

ዙሪያዋን ሸፍኗት ጉምና ደመና

ጎዳናዋ ታጥሮ በጸረ ሙስና

ሀብቷንም ጨርሰው ተጫውተዋት ሚና


ሀጢያትን ብንሰራ ዛሬ በሸፈና

ተደብቆ አይቀርም ይወጣል ገመና

ያስፈልጋል መኖር ጠርቶ በንጽህና

ምን ያደርጋል አሁን ይሄሁሉ ብልግና

እድትኖር ሚያድጉ ሀገሪቱን መክና

ኢትዮጲያም ወደ ሀኪም ሄደችና ፈጥና

መርምረኝ አለችው አብይን ጨክና

እንደ መረመራት ያው ተነሳች ድና

ዛሬ ወጣችልን አዲስ በአዲስ ሆና

ለኢትዮጲያ ህዝብ ልታላ ቡና

ግጥም ያቀረበው ጽፎ በህሊና

ከአዊ ግምጃ ቤት ቀጠናው አዘና

ሁሉም ያመስግነው በእውቀቱ ዜማ

ፈጣሪ አምላኩን ያለውን በራማ

ኢትዮጲያን ደስ ሲላት ከአብይ ጋራ ቆማ

ኢሳያስ ሊመጣ በአብይ ጋን ሹማ


ያው ተቀበለችው በጠጅ ህብስት ጮማ

አብይን ስትሸልም ኢሳያስን ስማ

ሽልማቱ ሳይቀር የካባ ወርቅ ግርማ

ኢሳያስና አብይ በአዋሳ ከተማ

ለሰላም ለፍቅር በሰንደቅ አላማ

በአቀደው ራእይ በአብይ አላማ

ኢሳያስና አብይ ቢፈርሙ ፊርማ

ኢትዮጲያም በሙሉ ህዝቡ ተስማማ

በሙስና ህመም ሀገራችን ደክማ

ውስጥ ለውስጥ መንምና ፈጅቷት እንደ ሳማ

ሙስና መሽታ ተይዞባት አድማ

ያው ተመረመረች ለአብይ አስቀድማ

መረመራት እንጂ ልትወድቅ ነበር ዘማ

ኢትዮጲያ ሀገራችን ዳነችልን ታማ

ደስ ይበልህ እንጂ ዶ/ር ከእንዲህማ

ተይ እባክሽን ነፍሴ ዛሬ ተመከሪ

ሐሰቱን ተይና እውነቱን መስክሪ

አሁን ማንን አየሽ በዚህ አለም ቀሪ

ኢትዮጲያ ሀገራችን ከእንግዲማ ኩሪ

ንጉስ አግኝተሻል እውነተኛ መሪ

አምላክ አዝዞልሽ ሰላ እንድታድሪ

በድብቅ በሽታ እንዳትቸገሪ


አሞሽ እንደሆነ ለዶክተር ንገሪ

በተሎ እንድትድኚ ሂጂ ተመርመሪ

ዛሬም እንደ ገና እንዳትጨመሪ

ነግሬሻለሁኝ በእውነት ጠንክሪ

ዶክተርም አለልሽ የቅርብ ተጠሪ

ፈጣሪ የሰጠሸ ሰላም እንድትኖሪ

ደግሞ ለፈጣሪሽ በአብይ ቃል ዘምሪ

ለድሀም እዘኚ ለመንግስት ገብሪ

ፈጣሪ ስጥቶሻል የአለም አብሳሪ

በጉቦ ሙስና እዳትወረሪ

ሰላምና ፍቅር ኢትዮጲያ ፍጠሪ

ከእንግዲህ በኋላ ተይው አታማሪ

እጅሽን አንስተሽ ወደ አብይ ዙሪ

ምንም አትሆኚ ገና በአምላክ ፈክሪ

ፍቅርና ሰላም ዛሬ ተሞከረ

ለኢትዮጵያ ህዝብ መንግስት አስተማረ

ህዝቡም በሙሉ ህግን አከበረ

በኢትዮጵያ መንግስት እየተመከረ

የኢትዮጵያ መንግስት እንኳን ተፈጠረ

ለተበዳዮቹ ገንዘብ አስበደረ

ችግር ላገኛችው ስለተቸገረ

ደሙን ለተበዳይ ይለግስ ጀመረ


የኢትዮጵያ ህዝብ ወጣ እየፎከረ

ለሰላማዊ ሰልፍ ለባብሶ እያማረ

በዚህ መንግስት ጊዜ ችግር ተባረረ

አረሙን ከላው እየመነጠረ

በሐሰት ምስክር ሰው ስለታሰረ

የሐሰት ምስክር ህጉን አስቸገረ

እውነት ብንናገር ይሻለን ነበረ

ይህ መንግስት አያስርም ካልተመሰከረ

በዚህ መንግስት ጊዜ ሐሰት ጉቦ ቀረ

እንዲህ ያለ መንግስት ለድሐ የጣረ

እውነቱንና ሐሰቱን እየመረመረ

የታሰረውን ሁል በይቅርታ አስማረ

የኢትዮጲያ መንግስት ጠ/ሚንስተሩ

የኢትዮጵያን ህዝብ መብትን አስከበሩ

አስመራን በሙሉ ዞረው በየሐገሩ

ከውጪ አሜሪካ ሔደው ቢያስተምሩ

ኢትዮጵያና አስመራ ዛሬ ተፋቀሩ

ዶ/ር አብይ አህመድ እንኳን ተፈጠሩ

ከኢሳያስ ጋራ እንደተማከሩ

በመካከላቸው ታየና ችግሩ

ኢትዮጲያና አስመራ ፈረሰ ድንበሩ

በዚህ መንግስት ጊዜ ተከፈተ በሩ


የኢትዮጲያ ህዝብ በሰላም አደሩ

ኢትዮጲያና አስመራ አንድ ሆነ ብሔሩ

መጣላት ቀረና በድንበር በአፈሩ

ከእንግዲህ በኋላ ችግርን አትፍሩ

አሟችሁ እንደሆን ሂዱ ተመርመሩ

የኢትዮጲያ ሀኪም አለና ዶክተሩ

ምን ቢሄዱ ባየር በሰማይ ቢበሩ

ሞት አይቀርምና ጥሩ ስራ ስሩ

ምንም ተስፋ የለው ተቀምጠው ቢያወሩ

ዶ/ር አብይ አህመድ ብለው አበሰሩ

ዶ/ር አብይ አህመድ ያረገው ሙከራ


ለኢትዮጲያ ህዝብ ፊደል እየመራ
ሐሰት እንዲወድም በእውነት እንዲሰራ
ጠቅላይ ምንስቴሩ የኢትዮጵያ ጮራ
ወጣልን ጸሐዩ ከፈጣሪ ጋራ
ህዝቡን በሙሉ ወጣ በባንዲራ
የኢትዮጲያ ህዝብ ከእንግዲህ አይፍራ
ህዝብ ነጻ ወጥቷል ከችግር መከራ
የኢትዮጲያ መንግስት ይሰጠናል ስፍራ
ትንሹን ትልቁን ያው እያሰማራ
ተማማሩ እያለ የስራ ፈጠራ
ከእንግዲህ ውድቅ ነው ጥላቻና ሴራ
በጣም ያስደስታል የጀመረው ስራ
ኢትዮጲያንም ዙሮ ሂዶ እስከ ኤርትራ
እንደ ሐዋርያት ወጥቶ በተራራ
ተገናኙ ዛሬ ኢትዮጲያና አስመራ
ይህ መንግስት ይኖራል ለዘላለም ሲጠራ
በየሀገሩ ዘርቷል የፍቅር አዝመራ
ጎንደርና ትግሬ መጣች ተጨምራ
ከእንግዲህ አይባልም ኦሮሞና አማራ
ከኤርትራ ጎንደር በዋለው ፉከራ
ኢትዮጲያና አስመራን አይተው ተደምራ
ቀድሞ ታማ ነበር ጎዳናዋ ታጥራ
ዛሬ በአብይ ዶክተር ዳነች ተመርምራ
አብይ ባቀደው የስራ በረራ
ሁሌ እንዲጸናልን እላለሁ አደራ
ኢትዮጵያና አስመራ ተጣልተው በድንበር

ዛሬ አስተራረቀ ፈቅዶለት እግዚአብሔር

ጠቅላይ ምንስቴሩ ለለሳም ለፍቅር

በእውነት ተገልጾ ስራው እንዲጀመር

ፈጣሪ ሾሞታል ቀድሞውን ሲፈጠር

የኢትዮጲያን ህዝብ ያው ለማስተዳደር

ክፉን በጎውን ለኛ እንዲቀጣጠር

ከህዝባችን ጋራ ያኑረው ከሀገር

ኢትዮጵያና አስመራን አድርጎ በድምር

ጠቅላይ ምንስቴሩ በእውነት ሲያስተምር

ሚያስተምረው ሁሉ አብይ አብይ ነገር

በጣም ያስደስታል የአብይ ስነምግባር

ከእንግዲህ በኋላ ይወገዳል ችግር


ብዬ አስባለሁኝ የለኝም ጥርጥር

ምን ምን እያሉ ነው አስመራና ጎንደር

ከውጭ እስከ አፍሪካ ከደቡብ እሰከ አፋር

የኢትዮጲያ ህዝብ በሙሉ ባህርዳር

ከእንግዲህ በኋላ አንገዛም በዘር

ጎንደር እውነተኛው አይገዛም በብር

በገንዘብ መገዛት በሐሰት ምስክር

በዚህ መንግስት ጊዜ ሁኗልና ነውር

በጠቅላይ ምንስቴር ተወግዟል በምድር

መጣላትም ቀርቷል በድንበር በአፈር

ከእንግዲህ በኋላ ጥላቻማ ይቅር

በሚበቃን መሬት ሶስት ከስንዝር

ኢትዮጲያ አውጥታለች እውነተኛ ምሁር

አሟችሁ እንደሆን ሂዱ ወደ ዶክተር

በነጻ እንድንወጣ ሁሉም እንመርመር

በሁሉም አለልን ጠቅላዩ ምንስቴር

ኢትዮጲያን በሙሉ እበለው ኖር ክበር


የኢትዮጲያ ህዝብ የልቡ ደረሰ

ኢትዮጲያና አስመራ ድንበሩ ፈረሰ

ድልድይ እንዲሰራ እየተዳሰሰ

ኢትዮጲያና አስመራ ከእንግዲህ ታደሰ

ፍቅር እንደ ዝናብ ኤርትራ ፈሰሰ

የድሮውን ፍቅር ሰውም አስታወሰ

ፍቅር እንደ ሸማ እየተላበሰ

በአብይ ዶክተር ጊዜ መጣ እየለገሰ

ፍቅርና ሰላም ዛሬ ተመለሰ

ጥላቻ አልቀረም እንደ ደፈረሰ

በጠቅላይ ምንስቴር በእርቅ ተደመሰሰ

ኢትዮጲያና አስመራ እቃ ተዋዋሰ

ከወዲያም ከወዲህ ያው ተመላለሰ

ነጋዴም ነገደ ገበሬም አረሰ

በፍቅር በሰላም ዛሬ ተቀደሰ

ፍቅር ተወደደ ጥላቻ ረከሰ

ሐሰትና ጎቦ በጣም ተወቀሰ

እውነተኛ ንጉስ ኢትዮጲያ ነገሰ

ከግራ ወደ ቀኝ በእውነት ነፈሰ

ፍቅር ዝናብ ዘንቦ ምድር ለሰለሰ

በፈጣሪ ፍቃድ ሁከቱ ታገሰ


ኢትዮጲያና አስመራ ዛሬ አመሰገኑ

ስለተገናኙ ወገን ከወገኑ

ዶ/ር አብይ አህመድ ሰብስቦ በውኑ

ኢትዮጲያና አስመራ በአንድ ላይ ሆኑ

አይዟችሁ ኢትዮጲያ አለፈልን ቀኑ

ያስደስል በጣም ወደፊት ዘመኑ

የተማመነ ነው የአብይ ስልጣኑ

ለጠቅላይ ምንስቴር ለዚህ ለሚስኪኑ

አይዞህ እንበለው እንቁም ከጎኑ

ኢትዮጲያና አስመራ በቃል ተማመኑ

ድልድይ እንዲሰራ በእውነት ወሰኑ

ጠቅላይ ምንስቴሩ አየነ በአይኑ

ኤርትራን አላቸው ወደ ኢትዮጲያ ኑ

የፍቅር ጎዳናው ተከፍቷል ጎበኑ

ኢትዮጵያ ሀገራችን ስትል ወዬ ወዬ


ዶክተር አብይ አላት ምነው እናትዬ

አሞኝ ነው ብትለው በዝቶ በሽታዬ

መጥተሽ ተመርመሪ ኢትዮጲያ እምዬ

ገንዘብስ የለኝም አለችው አብዬ

እኔ ላስመርምርሽ ገንዘቤን ከፍዬ

ቆሜለሁኝና ለሀገሬ ብዬ

ወደ ኋላ አልልም ኢትዮጲያ አንቺን ጥዬ

ደ/ር አብይ አላት አይዞሽ መመኪያዬ

ኢትዮጲያም አለችው ከኔም አልተለዬ

ታሞ የነበረው ቆሳስሎ ገላዬ ዶ/ር አብዬ

ቆሞ በፊት በኋላዬ

ተመርምሬ ዳንኩኝ ገባሁ በስራዬ

ተመርምሬ ድኜ አልቆ ፈተናዬ

በዚህ መንግስት ጊዜ ተሳካ ኑሮዬ

በሽታው ለቀቀኝ ዛሬ ከጀርባዬ

ጠቅላይ ምንስቴሩ ሆነልኝ ተስፋዬ

ፈርሶ የነበረው ተሰራ ጎጆዬ

አመሰግናለሁ ተመስገን ጌታዬ

በአብይ ጊዜ ነው ብርሀኑ የታዬ

ዘመን የወደደው ነገር በየግሉ


አብይም ይሰማል ፍርድን እንደ ቃሉ
ጠቅላይ ምንስቴሩ ሲመክሩን ሲውሉ
የኢትዮጲያ ህዝብ እስኪ አስተውሉ
ስንዴ እና እንክርዳድ አብረው እንደይበቅሉ
ዛሬ መንግስታችን ያው ያስረዳሉ
ትምህርታቸውን ሁል ላደመጠ ሁሉ
አምላክ መርጧቸዋል ቅድም የታደሉ
ለኢትዮጲያ ህዝብ እንዲያገለግሉ
የህዝብን ችግር እየተቀበሉ
ለድሀ ለሀብታም ብለው ሳያደሉ
የሰው መብት ሳይነኩ ይመረምራሉ
እውነተኛ ንጉስ ችግር ይፈታሉ
ተበዳዩን ሁሉ ፍርድን ይሰማሉ
ምንም ችግር የለ ዶ/ር አብይ ሳሉ
ድሃን አትበድሉ ፍርድን አታጉሉ
ባካችሁ ተስማሙ ሰውን አታግሉ
ጠቅላይ ምንስቴሩ ሲሉ ይገኛሉ
ኢትዮጲያና አስመራ ያሸበርቃሉ
የፍቅርና የሰላም እንጀራ እየበሉ
ፍቅር ዝናብ ዘንቦ ማአር ይጠጣሉ
ኢትዮጲያና አስመራ ይመላለሳሉ
ውሃ እንዳይበላቸው ድልድይ ይሰራሉ
ጠቅላይ ምንስቴሩ ያው ይታገላሉ
ለኢትዮጲያ ህዝብ መስዋት ሊከፍሉ

የኢትዮጲያ ህዝብ በጣም ተሳሳቁ

ከአስመራ ጋራ ስለተራረቁ

ኢትዮጲያና አስመራን ለእርቅ እንዳበቁ


ዶክተር አብይ አህመድ ቁመው አስመረቁ

የኢትዮጲያን ህዝብ መብት እያስጠበቁ

ጠቅላይ ምንስቴሩ የትንሽ ትልቁ

ለፍቅር ለሰላም ምንጭን አፈለቁ

ኢትዮጲያና አስመራ በጣም ተደነቁ

በዚህ መንግስት ጊዜ ስለተዋወቁ

የአስመራ ህዝብ ዛሬ አሸበረቁ

ፍቅር ፀሀይ ወጥቶ ሁሉም እየሞቁ

ድልድይ እንዲሰራ ዛሬ አጠናቀቁ

እስኪ የሰው ገንዘብ እረፉ አትስረቁ

ጥፋተኛውን ሁል አውጡ አትደብቁ

አብይም ብለዋል እንኑር በሀቁ

ኢትዮጲያና አስመራ በጣም ተዋደዱ

ዶ/ር አብይ አህመድ ሄደው ቢያማልዱ

ተገናኙ ብለው ዘመድ ከዘመዱ

ጠቅላይ ምንስቴሩ ሳያደሉ ላንዱ

የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት ፈረዱ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ እንኳን ተወለዱ


አድምጧቸው እስኪ ትምህርትን ሲያስረዱ

ዛሬ ሆኖ አይደለ የአምላክ ፍቃዱ

ከኢትዮጲያ አስመራ የነጻ መንገዱ

በስራችሁ ትጉ ለድሃውም እርዱ

ከእንግዲህ በኋላ አትወራረዱ

ከኢትዮጲያ አስመራ ሄዳችሁ ነግዱ

ብለው አስተማሩ ለሴቱ ለወንዱ

የእዕምነት አባቶች ወንጌልን ስበኩ

ለገንዘብ ብላችሁ ሌላ አታምልኩ

ጠቅላይ ምንስቴሩ ቁመዉ ከመድረኩ

በእግዚአብሔር መስቀል እየተባለኩ

ጠቅላይ ምንስቴሩ የሰው መብት ሳይነኩ

ያሰቡትን ነገር ሁሉን እንዳሳኩ

ኢትዮጲያና አስመራ በፍቅር እረኩ


እውነተኛ ንጉስ አዲሱ ተተኩ

ከእንግዲህ እንዲሰራ በአዳዲስ መልኩ

ከአስመራ ላይ ሆነው ቡና እንዳበረኩ

ዘመድ እንዲገናኝ ተከፈተ ስልኩ

ቅሬታም ያላችሁ መንግስት አታውኩ

ለፍቅር ለሰላም እስኪ ተንበርከኩ

ፍቅር ነው ሚገዛ በአምላክ ተመኩ

ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ውጪ ላኩ

የሰላም መልዕክት ለፓትራያሪኩ

ከእንግዲህ አይጠፋም የአብይ ተሪኩ

እስኪ ለፈጣሪ እንጸልይ እንስገድ

እንዲህ ያለ መንግስት በጣም የሚወደድ

ለኢትዮጲያ መንግስት በእውነት ሲፈርድ

ገና ይመርጠዋል ኢትዮጲያ በፍቃድ

ትንሹ ትልቁ መጪው ሁሉ ትውልድ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ የህዝባችን ዘውድ

ኢትዮጲያና አስመራን ያስተራርቀው ዘንድ

ኢትዮጲያና አስመራ ዛሬ ሆኑ ዘመድ

ዶ/ር አብይ አህመድ በአወጣው እቅድ


ከእንግዲህ በኋላ ችግሩ ይወገድ

በደለኛው ሁሉ ጥሎ እንዳይሰደድ

ስብሳባ እያረገ ከሰኞ እስከ እሁድ

ኢትዮጲያ እንድትድን ከመከራ ከጉድ

በየሀገሩ ዙሮ ነጻ አደረገ መንገድ

ለመለየት ብሎ ስንዴ እና እንክርዳድ

በጣም ያስደስታል የእርሱ አረማመድ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ ዶ/ር አብይ አህመድ

የአስመራ ህዝቦች እንኳን አገዛችሁ

ዶ/ር አብይ አህመድ ሲገባ ሀገራችሁ

ሰላማዊ ዝናብ ማር ዘነበላችሁ

የኢትዮጲያ ህዝብ ከእንግዲህ አይዞአችሁ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ ድልድይ ሰራላችሁ

ምትሸጋገሩት ውሃ እዳይበላችሁ

የሐይማኖት ሐገር ጎንደር እንዴት ናችሁ

እንኳንስ ፈጣሪ ለዚሁ አበቃችሁ

በሐይማኖት ጋሻ እንደተዋጋችሁ

ለሰላም ለፍቅር ለዚህ ደረሳችሁ

ጠቅላይ ምንስቴሩ ሆኖ ከጎናችሁ

ፍቅርና መብትን አስከበረላችሁ

የኢትዮጲያ ንጉስ እንደነገራችሁ

ያላችሁን ሁሉ ፍቃ ፈጽማችሁ
ኢትዮጲያና አስመራ በአንድ ላይ ሆናችሁ

ከወዲም ከወዲህ ትነግዳላችሁ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ እንዲህ ሁኑ አላችሁ

ኢትዮጲያ በሙሉ ሁሉም ተስማታችሁ

በፍቅር በሰላም ኑሩልኝ እባካችሁ

በእምነት አባቶች ብሎ አስወገዛቸሁ

ኢትዮጲያና አስመራ ተጣልተው በወሬ


አብይ አስተራርቆ ተገናኙ ዛሬ
የኢትዮጲያ ህዝብ አይዟችሁ ሀገሬ
በአዲሱ መንግስት ቀርቷል ጥርጣሬ
ተገናኙ ብሎአል አስመራና ትግሬ
ሰላም አስወርዷል ሄዶ እስከ ሽሬ
ኢትዮጲያንም ዞሮ በደቡብ በኮሬ
በአሶሳ በቻግኒ በኮሶበር በሬ
አፉ ሚጣፍጠው እንደሾላ ፍሬ
ከእንግዲህ ይበቃል ይል ጀመር ገበሬ
በህመም ታፍኜ ሁሌ ተወጥሬ
ከእንግዲህ በኋላ ልሙት ተናግሬ
እንደ ሻየ እንዳልሄድ እጅግሬን ታስሬ
አሁን እማ ይሂድ ይንቀሳቀስ እግሬ
በአብይ ግዜ ነው ያለፈ ችግሬ
በጣም ያስደስታል የአብይ ጥንካሬ
ሁሌም እናክብር የአብይን ድማሬ
ሰላማዊ ሰልፉን የአምላክም ዝማሬ
ኢትዮጲያን ትላለች ዋ በመፈጠሬ
ከስራ ቦታዬ ኖርሁኝ ተባርሬ
እስከ ዛሬ ድረስ እኔ በመኖሬ
በጣም ያስደንቃል ስኖር ተማርሬ
ዳግመኛም ትለላች ዳንሁኝ ተመርምሬ
ከጠቅላይ ሚንስቴር ሄጄ ከዶክተሬ
አገኘሁ ደህና ሀኪም ሀገሪቱን ዞሬ
ሚጠባብቀኝን እንዳይፈጀኝ አውሬ
ጥሩ መንግስት መጣ ለህዝብ ተወካይ

ለኢትዮጲያ ህዝብ እንዲወጣ ጸሐይ

ተሸመ የተባለ ለካ እውነት ነው ወይ

ለኢትዮጲያ ህዝብ የተባለው አብይ

ስሙም የከበረ ከምድር ከሰማይ

እንዲቀጥልልን ባአመጣው ራዕይ

የእምነት አባቶች እባካችሁ እንጸልይ

ኢትዮጲያም በሙሉ ሁላችን በጸባይ

እንዲፈጸምለት የጀመረው ጉዳይ

እንዲስማማ ብሎ አስመራና ትግራይ

የኢትዮጲያን ህዝብ ሁሉንም ባንድ ላይ

ሁሌ ይመክራል አስተውለን ብናይ


የላይኛው ጌታ አዝዞልን ከላይ

እንዲየስተዳድረን በገቢረ ሰናይ

እውነተኛ ንጉስ የህዝብ አገልጋይ

የኢትዮጲያን ህዝብ እንዳይበላው አባይ

ከኢትዮጲያ አስመራ አሰራለት ድልድይ

እስኪ ይህንን ግጥም አንብበው ባስቸኳይ

ያስደስት ከሆነ እጽፋለሁ ተሻይ

ዶ/ር አብይ አህመድ ጠ/ሚ ሆይ

ሚጻውን ሚስጥር መጥቼ እንድወያይ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ በሞባይል ያስጠሩይ

የእግዚአብሔር መንግስት ከሁሉም በላይ ነው


ለአንዱ ሳያዳላ አስታክሎ ሚፈርደው
ለድሀ ለሀብታም ብሎ ማያደላው
ጠቅላይ ሚንስተሩን ፈጣሪ የሾመው
የተወለደ እለት አምላክ የባረከው
ለኢትዮጲያ ብሎ እግዚአብሔር ፈጠረው
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ለድሀ ደጋፊው
ወደፊት ነው እንጂ ወደ ኋላ ማይለው
ለኢትዮጲያ ህዝብ ደሙን የለገሰው
አምላክ ይጠብቀው በወጣ በገባው
እስከ ዘላለሙ እስከ መጨረሻው
ሀገሪቷን ዞሮ ፍቅር ያወረደው
ከአፍሪካ አስከ ውጪ ሄዶ የጎበኘው
እንደ ሐዋርያት ፈጣሪ የላከው
ለኢትዮጲያ ህዝብ ይቆይልን እድሜው
ለጠቅላይ ሚንስቴር ግጥም ያቀረበው
የላይኛው ጌታ አምላክ ባሳሰበው
ጠቅላይ ምንስቴሩ አብይ ባአቀደው
የኢትዮጲያ ህዝብ እንቁም ከጀርማው
ከሴት ከደም ከብር ነጻ የሆነ ሰው
እንኳን በቀን ቀርቶ ቢሄድ በጨለማ
እሾህም አይወጋው አውሬውም አይበላው
አንዱ ይህ ነውና የሰው ልጅ በሽታው
ዶ/ር አብይ አህመድ እንደ መረመረው
ሙስና በሽታ የሄደበት ጠፋው
የያዘው በሽታ ህዝቡን ለቀቀው
ኢትዮጲያና አስመራ በድንበር ተጣልቶ
አብይ አስታረቀ በመካከል ገብቶ
የዛን የዚንም በደላውን ሰምቶ
ላንዱ ሳያደላ ሁሉንም ገምቶ
ፈጣሪ እንደሾመው በእውነት አሳክቶ
መንግስት ባይኖርማ ምን የውጠን ከቶ
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ልቦናውን ሰፍቶ
ትንሹን ትልቁን በስራ አሰማርቶ
ለኢትዮጲያ ህዝብ በጎደለው ሞልቶ
ይኑርል እንጂ እንደ ሺ እንደ መቶ
እድሜውን ይስጥልን ፈጣሪ አብዝቶ
ኢትዮጲያን አስማማው በቆራጥ ተነስቶ
ከህዝቡ ጋራ ቃሉን ተወያይቶ
እስከ አስመራ ሄዶ ጎዳናውን ከፍቶ
ሰላም እንዲፈጥር እንዲኖር ተስማምቶ
ሰላም አሰፈነ ሁሉን አረጋግቶ
እስረኛውን ሁሉ ተውሶ አስፈትቶ
ታማሚውን ሁሉ በእውነት ጎብኝቶ
ለኢትዮጲያ ህዝብ ህይወቱን ሰውቶ
ምን ጊዜም ሞት አይቀር በእድሜ ቆይቶ
መሞት ያስፈልጋል ጥሩ ስራ ሰርቶ
ኢትዮጲያ አይረሳውም የአብይን ፎቶ
ታሪኩም አይጠፋ ሳለም ቢሆን ሞቶ
ያወጣልን ራዕይ በእውነት አትቶ
በቃሉ ተናግሮ በህዝብ አስተችቶ
ዘላለም ይኖራል በኢትዮጲያ ጸንቶ
በዚህ መንግስት ጊዜ ታየልን መብራቱ
ንጉስ መጦልናል ለወንዱ ለሴቱ
ለብሔረሰቡ ለጎጥ ጎረቤቱ
ኢትዮጲያም ደስ አላት ሲመጣ ረድኤቱ
ትንሹ ትልቁ በረታ ጉልበቱ
ሽማግሌው ሳይቀር ሁሉም አዛውንቱ
የኢትዮጲያ ህዝብ ተጠበቀ መብቱ
ጠቅላይ ምንስቴሩን አምላክ በእውነቱ
ፈጠሪ አጽናልን ገና ወደፊቱ
ተነግሮ አያልቅም የአምላክ ቸርነቱ
ሰው ጥሩ ቢሰራ ሳለ በህይወቱ
የዚህ አለም ኑሮ አላፊ ነው ከንቱ
ሁሌ እምኖር መስሎት የሠው ሞኝነቱ
መቶ ዓመት ያስባል ደርሶ ሳለ ሞቱ
መቼ ይታወቃል የአምላክ ምጽአቱ
ኢትዮጲያና አስመራ በጣም ተደሰቱ
ስለተፈጸመ ታቅዶ ስርዓቱ
ዶ/ር አብይ አህመድ በ 40 ውስጥ ዓመቱ
የላይኛው ጌታ በሰጠው እውቀቱ
ኢትዮጲያና አስመራ አልቆ ውይይቱ
ዘመድ ተገናኘ ልጅ ከእናት ከአባቱ
እስከ ዛሬ ኖሮ እውነት በመጥፋቱ
በዚህ መንግስት ጊዜ ተከፈተ ቤቱ
ይህ መንግስት የሰራው አይጠፋም ሀውልቱ

ኢትዮጲያ ሀገራችን ተሰማት ደስታ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ ሲጀምር ሀተታ

ከአፉ ሚወጣውን ከአንደበቱ ሰምታ

ሰላማዊ ሰልፉን ህዝቧንም አይታ

ለጠቅላይ ሚንሰቴር ላቅተርብ አቤቱታ

ይቀበላልና ሁሉንም በሰላምታ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ ወይ ያለው ችሎታ

ያስተዳድረናል ሁሉን በጸጽታ

ሰላም እንዲፈጥር እንዲሆን እልልታ

ለተበዳዮቹ የረዳው እርዳታ

ታማው ጎብኝቶ ጥዋትና ማታ

ሚቆጣጠረውን በፈንታ በፈንታ

ባጋጠመው ችግር በቦንቡ ፍንዳታ


እንዲህ ያለ መንግስት እስረኛ ሚያስፈታ

እስረኛውን ሁሉ ፈቅዶ በይቅርታ

ያኑርልን እንጂ የላይኛው ጌታ

ሁላችን እንብላ በአንድ መሶብ ገበታ

ከእንግዲህ አይባልም ደጃ አዝማች ገለታ

ሁሉም ስራ ይስራ ይውጣና ጡረታ

መባል ቀርቷና ይሄ የኔ ቦታ

የእምነት አባቶች ተነሱ ለጸሎት


ለላይኛው ጌታ ለሁላችን አባት
የእግዚአብሔር መንግስት አንድ ነው በእምነት
መንግስት ይኑርልን ለኢትዮጲያ አብነት
መንግስት ቢኖር አደል ውለም ምንገባበት
አድሮ ይታወቃል አውነትና ንጋት
ኢትዮጲያና አስመራ ተዳምረን ባንድነት
እስኪ እንለምነው ፈጣሪን በእውነት
ለእኛ እንዲያጸናልን ተተኪውን መንግስት
የህዝብ እሮሮ እስኪ ይታይለት
ዛሬ እኔም ልግለጸው ያለኝን ስሜት
ከሁሉም በበላይ ይበልጣል ሐይማኖት
የእውነቱን ነገር ተናግሬ ልሙት
ምንም ቢሆን ንጉስ አለምን ቢገዛት
የደፈረ እንደሆን የፈጣሪውን መብት
ፈጣሪ ይመጣል ሳያስበው ድንገት
ክብርና ጸጋ እድሜውን ለማግኘት
የፈጣሪውን ቃል ማክበር ነው ያለበት
ሀብታምና ደሀን በአንድ አይን ማየት
ኃላፊ ነውና ንብረትና ሹመት
ጥሩ መንግስት ሁኖ መኖር በነጻነት
ስሙም እንዲነግስ በዓመት በዓመት
ሰኔ 16 የኪዳነ ምህረት
በቦንብ ፍንዳታው ባጋጠመው ጥፋት
ኢትዮጲያ እናታችን ታማ ተኝታበት
ዶ/ር አብይ አህመድ መርምሮ አዳናት
ደም አንሷት ነበረ ደም አስለገሰላት
ሁል ጊዜ አይረሳም ያደረገው ሀውልት

ጠቅላይ ሚንስቴሩ መጣ ሲገሰግስ


ለተበዳዎቹ ለድሃዎች ሊዋስ
ሲታመሙ ታሞ ሲያቅሱ ሚያለቅስ
ተመልከት ኢትዮጲያ አረ የአሁኑ ይባስ
እንዲህ ያለ መንግስት ደሙን የሚለግስ
እኔ አይቼ አላውቅም እንዲህ ያለ ንጉስ
እስረኛ የሚዋስ ቀማኛ ሚስመልስ
እውነተኛ መንግስት እንደ ቴድሮስ
ነጋዴም ይነግድ ገበሬውን ይረስ
የሚል መንግስት መጣ በአዲሱ ፖሊስ
አምላክ ቢያኖርልን ኢየሱስ ክርስቶስ
ኢትዮጲያም ውጡና እናድርግ የደስ ደስ
ሰላማዊ ሰልፉን በአዲሱ ኮንፈረንስ
የአብይን ባንዲራ ሁላችን በመልበስ
የኢትዮጲያ ሀገራችን ስተሆን አዲስ በአዲስ
ኢትዮጲያና አስመራ ድልድዩ ሲፈርስ
ዶ/ር አብይ ጊዜ ወርዶ መንፈስ ቅዱስ
ከእንግዲህማ ይብቃ ጥላቻና ተኩስ
ብሎ ተናረ አብይ ለኢሳያስ
ለጠቅላይ ሚኒስቴር ይህ ጽሑፍ ይድረስ
ከሰላምታ ጋራ ከቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰላም ፍቅር አለው አብይ አብይ ጥቅስ
መርምረው ይረዱት አንበው ቀስ በቀስ
ከሰላምታ ጋራ በእግዚአብሔር መንፈስ

ሁል ጊዜ ኢትዮጲያ ትመሰገናለች

የኢትዮጲያን በኩር አብይን መረጠች

በዚህ መንግስት ጊዜ አዲስ በአዲ ሆነች

ገናም ወደፊቱ ፍሬ ታፈራለች

አብባም አፍርታ ትለመልማለች

ለውጥ ያመጣሉ የሁሉም ሀገሮች

ኢትዮጲያ ሀገራችን ጥሩ ጊዜ አገኘች

አብይ ልብሷን ለብሳ እዩኝ እዩኝ አለች

ከእንግዲህ አይዟችሁ የኢትዮጲያ ልጆች

ጊዜ ወጥቶልናል ለትንሽ ትልቆች

ለኢትዮጲያ ህዝብ ለሴቱም ለወንዶች


መንግስት መጥቷልና ህዝብ የማይሰለች

ለኢትዮጲያ ህዝቦች ለሁሉ የሚመች

በጸሎት እዘኑ የእምነት አባቶች

ሁሉም በየቋንቋው ክርስቲያን ሙስሊሞች

በፍቅረ ዝናብ ይጽቁ አታክልቶች

አታክልት ማለትም የህዝብ መሪዎች

ኢትዮጲያ ሀገራችን ጩኸቷን አሰማች

በዚህ መንግስት ጊዜ የልቧን ደረሰች

ከአስመራ ጋራ ሂዳ ተደመረች

ኢትዮጲያ እናታችን አይቶ ታማ ሳለች

ዶ/ር አብይ አህመድ ከእግዚአብሔር በታች

ኢትዮጲያ ሀገራን ተመርምራ ዳነች

እስኪ ላመስግናት ኢትዮጲያ ሀገሬን


አብይ አብይ ፍሬ የምታፈራውን
እንዲህ ያለ መንግስት የት ይገኛል አሁን
እባክህ ፈጠሪ እሱን ጠብቅልን
ኢትዮጲያና አስመራ በአንድ ተደምረን
የኢትዮጲያን መንግስት መቀበል አለብን
ኢትዮጲያና አስመራ ስለተስማማልን
ከእንግዲህ በኋላ ምንም ችግር የለን
ዶ/ር አብይ አህመድ ስንቱን አሳየኸን
እንዲህ ያለ ጸሐይ እንዲህ ያለ ብርሃን
የኢትዮጲያ ህዝብ ዛሬ ቀን ወጣለን
አንተን ሚያኖርልን ጸሐይ እንሞቃለን
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ዞሮ ሀገሪቱን
ፍቅርና ሰላም ዛሬ አሰፈነልን
የላይኛው ጌታ አምላክ ቢያኖርልን
ዶ/ር አብይ አህመድ ባክህን መርምረን
በጎቦ በሽታ አለቅንልህ ታመን
የያዘን በሽታ በቶሎ ይልቀቀን
ጠቅላይ ሚንስቴሩ በርታ ጉልበትህን
የኢትዮጲያ ህዝብ አለንልህ ከጎን
የኢትዮጲያን ህዝብ አስጠብቀው መብቱን
በእውነት መስራት ነው ሞት ላይቀር ሰቀቀን
ለዚህ ያበቃኸን ጌታዬ ተመስገን
ስተኛ ስነሳ እልኸለሁ አሜን
ምስጋናውም ይድረስ ለፈጠሪ ይሁን

ጠቅላይ ምንስቴሩ እንኳን ሰላም ገባህ


የላይኛው ጌታ ለዚሁ ያበቃህ
ፈጣሪ ሹሞሃል በ 40 ቀን እድልህ
እባክህ ተከታተል ጠንክረህ በስራህ
የኢትዮጲያ ህዝብ አለነ ከጎንህ
ከእንግዲህ በኋላ ይበርታ ጉልበትህ
የላይኛው ጌታ አንተን ይጠብቅህ
ከኢትዮጲያ ጋራ ከሁሉ ወገንህ
ምንም ተስፋ የለ ለድሀ አንተ ካልኖርክ
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ፈጣሪ እንደሾመህ
የኢትዮጲያን ህዝብ በነጻ አወጣህ
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ስማ እስኪ ልንገርህ
አንድ ነገር አለኝ ጥብቅ የማስብህ
ጻድቃን ሰማዕታትን እንዳትረሳ ባክህ
መላዕክትም ሁሉ በክንፍ ሲያሻግሩህ
ወላዲተ አምላክን ድንግልን ጨምረህ
በነሱ ሀይል ነው የሚረዝም እድሜህ
በወጣኀው ሁሉ የሚጠባበቁህ
ዶ/ር አብይ አህመድ አይረሳም ስምህ
ኢትዮጲያና አስመራን አንድ በማድረግህ
ይቆራል ገናም ሺ ዓመት እንደገዛህ
ለሀገሪቱ ብለህ መስዋትን ከፍለህ
ኢትዮጲያን በሙሉ አንተ ስላስማማህ
ገናም ወደፊቱ አይጠፋም ታሪክህ

እውነተኛ ንጉስ ተሸሞአል በአለም


ለጊዜው ቢሰማ የዛንም የዛንም
እውነተኛ ንጉስ ለአንዱ አያደላም
እግዚዓብሔር ማለት ነው በሐሰት አይፈርድም
አንድ ሰው አይፈርድም አንድ እንጨት አይነድም
እውነተኛ ንጉስ አያዘነብልም
የላይኛው ጌታ አዝዞታል ቅደውም
ጠቅላይ ሚንስቴሩን ለፍቅር ለሰላም
የኢትዮጲያን መንግስት አይንካብን ህመም
መድሐኒት ነውና ለህዝበ አዳም
እንዲህ ያለ መንግስት ወደፊት አይመጣም
በጣም ተደስቷል ትንሹም ትልውቁም
እንዲህ ያለ መንግስት ለድሀ የሚቆም
ስሙም አብይ ነው መጣ በአብይ ጾም
ሁሌ ይጠራል የእውነተኛ ስም
እውነተኛ መንግስት ስሙ አይረሳም
ከፊት እስከ ኋላ ውሌታው አይጠፋም
አብይ አብይ አለ በእውምን በህልም
ሚስጢሩ አብይ ነው ይህ ስነ ግጥም
ለሁሉ ቅርስ ነው አደራ ይታተም
ሹመት ኃላፊ ነው ሌላው እንኳን ቢሾም
አብይ የአቀደው እንዳይጣስ ዳግም
በዚህ ቃል ካልሆነ ኢትዮጲያ አይስማማም

ጠቅላይ ሚንስቴሩ ለኛ ሲል ተሹሟል


ለኢትዮጲያ ህዝብ ለሁሉ ይመቻል
ትንሹ ትልቁ ኢትዮጲያ ወዶታል
አሜሪካ ሳይቀር ገናም ይመርጠዋል
እንዲህ ያለ መንግስት የት ሀገር ይገኛል
በፍቅር በሰላም ተስማሙልኝ የሚል
ለኢትዮጲያ ህዝብ ጊዜ ወጥቶልናል
በዚህ መንግስት ጊዜ ችግር ተወግዷል
በጠቅላይ ሚንስቴር በፈጣሪ ሐይል
የኢትዮጲያ ህዝብ መብቱ ተጠብቋል
እንዲህ ያለ መንግስት በእውነት ይመጣል
የኢትዮጲያ ህዝብ ሁሉም ተደስቷል
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ለሁላችን ቆሟል
ኢትዮጲያንም ዞሮ አስመራን በጥቅል
ከፈጣሪ ጋራ ሰላም አስወርዷል
እስከ ውጪ ሄዶ ሁሉንም አስማምቷል
ለኢትዮጲያ ህዝብ በተናገረው ቃል
ያአወጣው ራዕይ ወደፊት ይኖራል
ከእንግዲህ አይኖርም የሀገር ክፍፍል
ድሃም አይበደል ፍርድም አይጓደል
በላይኛው ጌታ በእግዚአብሔር ልዑል
ዶ/ር አብይ አህመድ ብለው ተናግረዋል
ፈጣሪ ብቻ ነው ቃሉ የማያብል
ይቅርታ አውርዱ ይላል ቃለ ወንጌል
ምስጋና ነገሬ ከዘህ ላይ ይበቃል

ግእዝ ጉባኤ ቃና
ኢትዮጵያ ወለት ነጺራ ለእግአብሔር ስቡህ ሀርያመ አንተ አንስአቶ ለአብይ ሱራህ
ዘአምላኬ ይቤሉከ ህዝብ ለንጉሰ አብይ ኪያከ መሀረነ እንዘታስምአነ በአብይ ቃልከ ጸረ
ሙስና

You might also like