Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 30

1

2
ኑ እንቅረብ
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (2)
ስጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ::

3
4
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ ( 2)
ስጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ::
መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት
ከዋክብት ከሰማይ የተነጠፉለት
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት:: 5
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ ( 2)
ስጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ::
ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን
ትጋብዘናለች ስጋና ደሙን
የአማኑኤል ስጋ ይኽው ተዘጋጀ
ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ:: 6
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ ( 2)
ስጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ::
መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በዕልልታ
በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ
ይህችን ዕድል ፈጥነን እንጠቀምባት
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይባት::
7
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ ( 2)
ስጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ::
አሁኑን ቅረቡ ታውጇል አዋጁ
የይለፍ ደብዳቤ ስንቁን አዘጋጁ
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ::
8
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (2)
ስጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ::

9
ይህ ቁርባን ክቡር ነው
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍፁም ሰማያዊ /2/
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ/2/

10
ዋ. . . ምን አፍ ነው የሚቀበለው
ዋ. . . ምን ጥርስ ነው የሚያላምጠው
ዋ. . . ምን ሆድ ነው የሚሸከመው
ነበልባል ያለበት የሚያቃጥል ነው
በንፅህና ሆኖ ላልተቀበለው
የሚያፍገመግም የሚጎዳ ነው:: /2/ 11
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍፁም ሰማያዊ /2/
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ /2/
አምላካችን ሆይ አንተ ይቅርባይ
እንደቸርነትህ በደልን አትይ /2/
አሜን አሜን ብለን ተቀብለናል
በድፍረት ሳይሆን በፍርሀት ቀርበናል::/2/
12
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍፁም ሰማያዊ /2/
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ /2/
ማክበር ይገባናል በንጽህና ሆነን
ደፍረን አናቅለው እንዳያቃጥለን /2/
እንደምታዩትም ይህ ቁርባን ፈራጅ ነው
እንደሌላው ሳይሆን የተቀደሰ ነው::/2/
13
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍፁም ሰማያዊ /2/
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ /2/
ሱራፌል ኪሩቤል ፀወርተ መንበር
ለመያዝ ያልቻሉት ፈርተውት በክብር 2
እኛ ተመገብነው አገኘን ድኅነት
በነፍስ በስጋችን ሆነልን ሕይወት:: /2/
14
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍፁም ሰማያዊ /2/

እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ/2/

15
እንደ ቸርነትህ አቤቱ ማረን /2/
እንደ ምረትህም ይቅርታን ስጠን /2/
ከኃጢአቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ /2/
ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ/2/
16
እኔም አበሳዬን በደሌን ሳውቀው /2/
ከቶም የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው /2/
አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ /2/
አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ /2/
ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን /2/
መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሃን/2 17
አሁን ትጠብቅ ዘንድ ሀገራችንን ሀይማኖታችን
ጌታ ሆይ ላክልን መንፈስ ቅዱስን ጴራቅሊጦስን
አሁን ትባርክ ዘንድ ፀሎታችንን ልመናችንን
ጌታ ሆይ ላክልን ቅዱስ ሚካኤልን፣
ቅዱስ ገብርኤልን::
18
19
አባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ /2/
መንግሥትህ ትምጣልን ብርሃን እንድናይ/2/
ፈቃድህ በሰማይ ሕይወት እንደሆነ /2/
እንዲሁም በምድር ሰላምን ሰጠነ /2/
ስጠነ ለዛሬ የዕለት ምግባችንን /2/
በደላችንንም ይቅር እንድትለን /2/ 20
ጌታ ሆይ አታግባን ከክፉ ፈተና /2/
አንተ ካልረዳኸን ኃይል የለንምና/2/
ኃይልና ምስጋና መንግስትም ያንተው ናት/2/
አሜን ለዘለዓለም ይሁንልን ሕይወት/2/

21
እመቤቴ ማርያም ሆይ /2/
የመላኩ ገብርኤል ሰላምታ እንዲበዛልሽ
ሰላም እንላለን እኛም ልጆችሽ /2/
በሀሳብሽ ድንግል ነሽ /2/በስጋም ድንግል ነሽ
የልዑል እናቱ ደግሞም የአሸናፊ
ማህበራችንን በእውነት ደግፊ /2/ 22
ከሴቶች ሁሉ አንች ተለይተሽ /2/ የተባረክሽ ነሽ
ብሩክ ከሆነው የማህጸንሽ ፍሬ
ፀጋን እንዲያድለን ለምኝልን ዛሬ/2/
ፀጋና ክብርን የተመላሽ ሆይ/2/ ደስ ይበልሽ
ያወርድ የነበረው ለእስራኤል መና
ቸሩ ፈጣሪያችን ከአንች ጋር ነውና /2/
23
ለምኝ ኢየሱስን ይቅር እዲለን /2/ በደላችንን
የሀጢአት ባርነት ከእኛ እንዲጠፋ
ተማጽነንብሻል እንድትሆኝን ተስፋ
እንድትሆኝን ተስፋ::

አሜን!!!
24
25
እመቤቴ ማርያም እልለምንሻለሁ፣
በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄአለሁ፣
እመቤቴ ስሚኝ እለምንሻለሁ፡፡
እመቤቴ ስሚኝ እለምንሻለሁ፡፡ 26
ኃዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለሁ፣
ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለሁ፣
እመቤቴ ስሚኝ ተማፅኜሻለሁ፡፡
እመቤቴ ስሚኝ እለምንሻለሁ፡፡ 27
ኃዘኑም በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ፣
እንደምን ልቻለው እኔ ደካማ ነኝ፣
የአማኑእኤል እነት ፈጥነሽ ድረሽልኝ፡
የአማኑእኤል እነት ፈጥነሽ ድረሽልኝ ፡፡
28
በጣም ተንገዳገድኩ ልወድቅ ነው እኔ፣
እመ አምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ፣
ምንም አጋር የለኝ ከአንቺ በቀር ለኔ፡
ምንም አጋር የለኝ ከአንቺ በቀር ለኔ ፡፡
29
እመቤቴ ማርያም እልለምንሻለሁ፣
በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄአለሁ፣
እመቤቴ ስሚኝ ተማፅኜሻለሁ፡፡
እመቤቴ ስሚኝ እለምንሻለሁ፡፡ 30

You might also like