Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 25

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ትምህርት ሚኒስቴር

የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ

(ረቂቅ)

ታህሳስ 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ

0
መግቢያ

በትምህርት ፖሊሲው ትኩረት ከተሰጣቸው አበይት ጉዳዮች አንዱ የመምህራን ጉዳይ ነው፡፡ መምህራን ጥራት
ያለው ትምህርት በመስጠት የወደፊት አገር ተረካቢ እና መልካም ዜጎችን የማፍራት ኃላፊነት አለባቸው። ይህን
ኃላፊነት መወጣት ይችሉ ዘንድ በየደረጃው የሚያስተምሩ መምህራን ሊያሟሏቸው የሚገቡ ፕሮፋይሎች
በዝርዝር ተዘጋጅተዋል፡፡ በፕሮፋይሉ መሰረትም የማሰልጠኛ ስርአተ ትምህርት በማዘጋጀትና መምህራንን
በማሰልጠን በሚመጥናቸው ደረጃ ተመድበው እንዲያስተምሩ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በማስተማር ላይ ያሉ መምህራንንም ለማበረታታትና የስራ ተነሳሽነታቸውንም ለማሳደግ የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት
ያስፈልጋል፡፡ በማስተማር ስራቸው ውጤታማ የሆኑ መምህራንን ለማበረታታት የተለያዩ ስልቶች የተዘረጉ ሲሆን
ከነዚህም ውስጥ የመምህራን የደረጃ እድገት ስርዓት አንዱ ነው። መምህራን በስራ አፈጻጸም ውጤታቸው፣
በቆይታ ጊዜያቸውና በየደረጃው የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ የደረጃ እድገት ተጠቃሚ
ይሆናሉ፡፡ ይህን ለማስፈጸም ያስችል ዘንድ የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቶ
እየተሰራበት ይገኛል፡፡ መመሪያው በተለያዩ ጊዜያት የመጡ ለውጦችንና አደረጃጅቶችን ተከትሎ ማሻሻያዎች
ሲደረጉበት የቆየ ሲሆን አሁን በሀገራችን እየተደረገ ካለው የትምህርት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለውጦችንና
አደረጃጅቶችን ሊያስተናግድ የሚያስችል ወጥ የሆነ የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
አሻሽሎ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተዘጋጅቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
1. አጭር ርእስ
ይህ መመሪያ የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር-----/2015 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-
ሀ) ትምህርት ሚኒስቴር ማለት በአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 በተሰጠው
ስልጣን መሰረት ትምህርትን ለመምራት የተቋቋመ መስሪያ ቤት ነው፡፡

1
ለ) መምህር ማለት ከመንግስት የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ዩኒቨርሲቲ በተፈቀዱ የስልጠና ሞዳሊቲዎች በመምህርነት ሙያ
ተመርቆ በመንግስት ትምህርት ቤት በቋሚነት ተቀጥሮ በማስተማር ላይ የሚገኝ ማለት ነው፡፡
ሐ) የመምህራን ማህበር ማለት በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በቁጥር 0344
የተቋቋመ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን በአንድ ጥላ ስር በማደራጀት ከትምህርት ቤት እስከ ፌዴራል
የተቋቋመ የሙያ ማህበር ነው፡፡
መ) የትምህርት ተቋም ማለት አግባብ ባላቸው ህጎች በመንግስት የተቋቋሙ የትምህርትና ስልጠና ተግባር የሚያከናውን ማለት ነው
ሠ) የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል ማለት መምህራን በስራ ቆይታ ጊዜ፣ በውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ውጤትና በሌሎች
መስፈርቶች እየተገመገሙ ከአንድ የደረጃ እድገት መሰላል ወደሚቀጥለው ደረጃ የሚሸጋገሩበት ስርዓት ነው፡፡
ረ) ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ማለት መምህራን ሙያዊ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በስልጠናና በልምድ ልውውጥ ለማደበርና
ለማሳደግ እንዲያስችላቸው የተዘረጋ መርሀ ግብር ነው፡፡
ሰ) የመምህራን ፕሮፋይል ማለት ተፈላጊው የመምህራን እውቀት፤ ክህሎትና ሙያዊ ስነምግባር ዝርዝር ነው፡፡
ሸ) የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ማለት መምህራን በስራ ላይ ስልጠና የትምህርት ዝግጅታቸውን የሚያሻሽሉበት መርሀ ግብር ነው፡፡
ቀ) የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ማለት በፌዴራል የመንግስት ሰራተኞ ስራ አፈጻጸም ምዘና መመሪያ መሰረት በጊዜ፣ በወጪ፣
በጥራትና በመጠን የተገኘ የስራ ክንውን ውጤት ነው፡፡
በ. ትይዩ የደረጃ እድገት ማለት መምህራን በስራ ላይ ስልጠና የትምህርት ደረጃቸውን ሲያሻሽሉ ቀደም ብለው ይዘውት የነበረውን
የመምህርነት ደረጃ እንደያዙ ለትምህርት ደረጃው የተፈቀደውን ጥቅማ ጥቅም በትይዩ የሚያገኙበት ስርዓት ነው፡፡
ቸ) ማህደረ ተግባር ማለት መምህራን በመማር ማስተማር ሂደት ያከናወኗቸው አንኳር ሙያዊ ተግባራትን የሚያሳይ ሰነድ ነው፡፡
በዚህ መመሪያ በወንድ ጾታ የተገለጸው ሴቶችንም ያጠቃልላል፡፡
3. የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ በየደረጃው በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ተቀጥረው የመምህርነት ሙያ ሥልጠና ወስደው
በማስተማር ላይ የሚገኙ መምህራን ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

4. አስፈላጊነት
ሀ) በተለያዩ ጊዚያት የወጡ የደረጃ እድገት መመሪያዎችን እና ማብራሪያዎችን ወቅታዊ በማድረግ በወጥነት
ማስተናገድ በማስፈለጉ፣

ለ) 9 የነበረው የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል በአዲሱ የስራ ምዘናና ምደባ ወደ 7 በመታጠፉ ከዚህ
አንጻር መስፈርቶችን አጣጥሞ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

ሐ) በዓመት አንድ ጊዜ ህዳር ወርን ጠብቆ ይሰጥ የነበረው የመምህራን የደረጃ እድገት በዓመት ሁለት ጊዜ
ሀምሌ 1 እና ጥር 1 እንዲሰጥ የተደረገ በመሆኑ፣

መ) ነባሩን የመምህራን የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ላይ የተገለጹ መስፈርቶችን ወቅታዊና
እየተደረገ ካለው የትምህርት ስርአቱ ለውጥ ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ ይህ የመምህራን የደረጃ እድገት
መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡
2
5. ዓላማ
የመመሪያው ዓላማ የመምህራንን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የስራ ፍላጎትና ተነሳሽነት በማሳደግ የመማር
ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል ነው፡፡

ክፍል ሁለት
6. የመምህራን ፕሮፋይል
6.1 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን ፕሮፋይል
የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን የአፍ መፍቻ ቋንቋን ጨምሮ ስለሚያስተምሩት ትምህርት ይዘት፣
የጨዋታ ሳይንስ ሙያዊ ብቃት፣ የሀገር በቀል እውቀት፣ በምዘና ክህሎት፣ በትምህርት መሳሪያዎች አዘገጃጀትና
አጠቃቀም፣ በክፍል አመራርና አስተዳደር፣ በእቅድ አዘገጃጀትና ትግበራ፣ በግምገማ ችሎታ፣ በትምህርት ፖሊሲና
ስትራቴጂዎች እውቀት፣ ስለሚያስተምሯቸው ህጻናትና በመካከላቸው ሊኖሩ ስለሚችሉ የችሎታና የፍላጎት
ልዩነቶች እውቀት እንዲሁም በህጻናት ትምህርትና እንክብካቤ ላይ የተመሰረተ ፕሮፋይል ይዘው ተገኝተዋል፡፡

6.2 የአንደኛ ደረጀ (1-6) ትምህርት መምህራን ፕሮፋይል

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን ተማሪዎች በእድሜ፣ በአካል፣ በስነልቦና እና በአእምሮ እድገት ደረጃ ልዩነት
እንዳላቸው የተገነዘቡ፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋን ጨምሮ ለሚያስተምሩት ትምህርት ይዘት ሰፊ እውቀት፣ የማስተማር
ስነዘዴ፣ የሀገር በቀል እውቀት፣ እቅድ ዝግጅትና ክንውን፣ የክፍል አስተዳደር፣ በትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች
እውቀት፣ በጥናትና ምርምር፣ ልዩነቶችንና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን የማስተናገድ ክህሎት ይዘው ተገኝተዋል፡፡

6.3 የመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ (7-12) ትምህርት መምህራን ፕሮፋይል

የመካከለኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን በሚያስተምሩተ ትምህርት ይዘት እውቀት፣ በሙያዊ ክህሎት፣
ለሙያው ያላቸው አመለካከት፣ በክፍል አያያዝ፣ በትምህርት እቅድ ዝግጅትና አተገባበር፣ በሀገር በቀል እውቀት፣
በትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እውቀት፣ በጥናትና ምርምር፣ የቴክኖሎጂ እውቀት እንዲሁም ዘርፈ ብዙ
ጉዳዮችን በማስተናገድ ሰፊ ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተጨማሪም በዚህ ደረጃ ያሉ ተማሪዎች ካላቸው
አካላዊና ስነልቦናዊ ተጽዕኖ አኳያ የምክር አገልግሎት መስጠትን፣ ጾታዊ ችግሮችን መረዳትና መፍታት፣ እጽና ሱስ
ነክ የመሳሰሉ ጎጂ ልማዶችን መከላከል፣ የባህሪ ልዩነቶችንና ብዝሀነትን ማስተናገድ የሚያስችል ክህሎት ያላቸው
ናቸው፡፡

ክፍል ሶስት
7. የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያና የትይዩ የደረጃ እድገት አፈጻጸም
ለደረጃው የሚመጥን የትምህርት ዝግጅት ሳይኖራቸው በማስተማር ላይ የሚገኙ መምህራን በስራ ላይ ስልጠና
የትምህርት ደረጃቸውን ማሻሻል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለሆነም መምህራን የትምህርት ደረጃቸውን አሻሽለው
ማስረጃ ሲያቀርቡ በትይዩ ደረጃ እድገት የሚያዝላቸው በሚከተለው አግባብ ይሆናል፡፡
3
7.1 በመንግስት ትምህርት ተቋማት የትምህርት ደረጃቸውን በመንግስት ወጪ ያሻሻሉ መምህራንን በተመለከተ
7.1.1 መምህራን በማስተማር ላይ ሆነው በትምህርት ሚኒስቴር ለመምህራን ስልጠና በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት
መሰረት የትምህርት ደረጃቸውን ሲያሻሽሉ ቀደም ሲል ይዘውት የነበረውን የደረጃ እድገት እንደያዙ
የሚቀጥሉ ሆኖ የትምህርት ደረጃቸውን ባሻሻሉበት ደረጃ የተቀመጠውን የደመወዝ መጠን በትይዩ
የሚያዝላቸው ይሆናል።
7.1.2 ለመምህራን ስልጠና በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት በስራ ላይ ስልጠና ትምህርታቸውን ተከታትለው
የትምህርት ደረጃቸውን ስለማሻሻላቸው የትምህርት ማስረጃ ሲያቅርቡ ትምህርት ላይ የቆዩበት ጊዜ
ለደረጃ እድገት የሚቆጠርላቸው ይሆናል፡፡
7.1.3 ለመምህራን ስልጠና በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት በመደበኛ መርሀ ግብር ከማስተማር ውጭ ሆነው
የትምህርት ደረጃቸውን አሻሽለው ሲመጡ ትምህርት ላይ የቆዩበት ጊዜ ለደረጃ እድገት አይቆጠርም፡፡
የትይዩ የደረጃ እድገት የሚሰራላቸው ወደ ትምህርት ተቋም ከመሄዳቸው በፊት በነበሩበት የደረጃ እድገት
መሰላል መሰረት ይሆናል፡፡
7.1.4 የትምህርት ደረጃቸውን አሻሽለው የትምህርት ማስረጃ ሰርቲፊኬት የሚያቀርቡ መምህራን የትይዩ
የደረጃ እድገት የሚያዝላቸው ከተመረቁበት ቀን ጀምሮ ሲሆን መምህራንም የትምህርት ማስረጃቸውን
እስከ 3 ወር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7.1.5 በመንግስት ዕቅድ የትምህርት ደረጃቸውን ያሻሻሉ መምህራን የትምህርት ማሻሻያው ሲያዝላቸው
በሰለጠኑበት የትምህርት አይነት የመምህር እጥረት ባለባቸው ትምህርት ቤቶች ተመድበው የመሥራት
ግዴታ አለባቸው፡፡

7.2 በመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በግላቸው የትምህርት ደረጃቸውን ያሻሻሉ

መምህራንን በተመለከተ

7.2.1 በስራ ላይ ያሉ መምህራን በግላቸው ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት መሰረት በመምህርነት ሙያ
የትምህርት ደረጃቸውን ሲያሻሽሉና የተማሩት የትምህርት መስክ ከሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት
ጋር አንድ አይነት ከሆነ፣ ክፍት ቦታና በጀት መኖሩ ተረጋግጦ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያው ተይዞላቸው
ከተመደቡበት ቀን ጀምሮ የትይዩ የደረጃ እድገት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ይሁን እንጂ ክፍት የስራ መደቡና
የትምህርት ደረጃቸውን ያሻሻሉ መምህራን ብዛት ካልተመጣጠነ በውድድር የሚመደቡ ይሆናል፡፡

4
ክፍል አራት
8. መምህራን የደረጃ ዕድገት ለማግኘት ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

8.1 ከቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን የሚጠበቁ መስፈርቶች

8.1.1 በጀማሪ መምህርነት የሚመደቡት

ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በመምህርነት ሙያ በሰርተፍኬት (12+1) የሰለጠኑ ሲሆን
ቀደም ብሎ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+1 ወይም 10+3 ወይም 12+1 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ
የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

8.1.2 ከጀማሪ መምህርነት ወደ መለስተኛ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በመምህርነት ሙያ በሰርተፍኬት (12+1) የሰለጠኑ ሲሆን
ቀደም ብሎ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+1 ወይም 10+3 ወይም 12+1 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ
የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣

1. በጀማሪ መምህርነት 2 ዓመት ያገለገሉ፣

2. በጀማሪ መምሀርነት ባገለገሉባቸው የ 2 ዓመታት (4 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 70% እና በላይ
ያገኙ፣
3. የመምህርነት የሙያ ትውውቅ (Induction) ለ 2 ዓመት (4 ሴሚስተር) በአግባቡ ተከታትለው ያጠናቀቁ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፡፡

5
5. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.1.3 ከመለስተኛ መምህርነት ወደ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በመምህርነት ሙያ በሰርተፍኬት (12+1) የሰለጠኑ ሲሆን
ቀደም ብሎ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+1 ወይም 10+3 ወይም 12+1 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን
በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣

1. በመለስተኛ መምህርነት 3 ዓመት ያገለገሉ፣

2. በመለስተኛ መምህር ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 75% እና በላይ
ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
4. በትምህርት ቤቱ በሚቋቋሙ ክበባት ወይም ኮሚቴዎች ቢያንስ በአንዱ የተሳተፉ፣
5. በትምህርት ቤቱና በተማሪዎች የመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action
Research) ያካሄዱ፣
6. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፡፡
7. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.1.4 ከመምህርነት ወደ ከፍተኛ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በመምህርነት ሙያ በሰርተፍኬት (12+1) የሰለጠኑ ሲሆን
ቀደም ብሎ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+1 ወይም 10+3 ወይም 12+1 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ
የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣

1. በመምህርነት ደረጃ ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በመምህር ደረጃ ባገለገሉቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 80% እና
በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣

6
5. በትምህርት ቤቱ በዩኒት መሪነት ወይም በትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት
ኃላፊነት ወይም በክበባት ኃላፊነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴ ውስጥ በኃላፊነት ወይም አባልነት የተሳተፉና
በአንዱ ቢያንስ ለአንድ ዓመት በአጥጋቢ ሁኔታ የሰሩ፣
6. ብዛታቸው ከ 2 ላለነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ ለእድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች
ለሆኑ መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን
በአማካሪነት ተመድበው የሰሩ፣
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና
ሕጻናትን በመለየት ድጋፍና አገልግሎት የሰጠ ወይም እንዲያገኙ ያደረጉ፣
8. በትምህርት ቤቱና በተማሪዎች የመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action
research) ያካሄዱና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፡፡
9. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.1.5 ከከፍተኛ መምህርነት ወደ ተባባሪ መሪ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በመምህርነት ሙያ በሰርተፍኬት (12+1) የሰለጠኑ ሲሆን
ቀደም ብሎ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+1 ወይም 10+3 ወይም 12+1 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን
በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣

1. በከፍተኛ መምህርነት ደረጃ ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በከፍተኛ መምህርነት ደረጃ ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም
84% እና በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በትምህርት ቤቱ በዩኒት መሪነት ወይም በትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት
ኃላፊነት ወይም በክበባት ኃላፊነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴ ውስጥ በኃላፊነት ወይም አባልነት የተሳተፉና
በአንዱ ቢያንስ ለአንድ ዓመት በአጥጋቢ ሁኔታ የሰሩ፣
6. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ ለእድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች
ለሆኑ መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን
በአማካሪነት ተመድበው የሰሩ፣
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና
ሕጻናትን በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያኙ ያደረገና የትምህርት ውጤታቸውን ለማሻሻል
የሰራ፣

7
8. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ እና በላይ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research)
ያካሄደና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረበ፡፡
9. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ
አሰጣጥ እድሳት ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.1.6 ከተባባሪ መሪ መምህርነት ወደ መሪ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በመምህርነትሙያ በሰርተፍኬት (12+1) የሰለጠኑ ሲሆን
ቀደም ብሎ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+1 ወይም 10+3 ወይም 12+1 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን
በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣

1. በተባባሪ መሪ መምህርነት ደረጃ ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በተባባሪ መሪ መምህርነት ደረጃ ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ
አፈጻጸም 87% እና በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በትምህርት ቤቱ በዩኒት መሪነት ወይም በትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት
ኃላፊነት ወይም በክበባት ኃላፊነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴ ውስጥ በኃላፊነት ወይም አባልነት የተሳተፉና
በአንዱ ቢያንስ ለአንድ ዓመት በአጥጋቢ ሁኔታ የሰሩ፣
6. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ ለእድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች
ለሆኑ መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን
በአማካሪነት ተመድበው የሰሩ፣
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ታጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና
ሕጻናትን በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያኙ ያደረጉ እና የትምህርታቸውን እንዲያሻሽሉ የሰሩ፣
8. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ እና በላይ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research)
ያካሄዱና ለህብረተሰቡ ለውይይት ያቀረቡ፡፡
9. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ
አሰጣጥ እድሳት ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.1.7 ከመሪ መምህርነት ወደ ከፍተኛ መሪ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በመምህርነት ሙያ በሰርተፍኬት (12+1) የሰለጠኑ ሲሆን
ቀደም ብሎ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+1 ወይም 10+3 ወይም 12+1 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን
በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣

8
1. በመሪ መምህርነት ደረጃ ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤
2. በመሪ መምህርነት ደረጃ ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም
90% እና በላይ ያገኘ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም በዩኒት መሪነት ወይም በትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ኃላፊነት ወይም
በክበባት ወይም በተለያዩ የትምህርት ቤት ኮሚቴዎች ውስጥ በኃላፊነትና በአባልነት ያገለገሉ በተጠቀሱት
አማራጮች የሰሩት ተደምሮ ከሁለት ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት ስለመፈጸማቸው ከኃላፊዎች
የጽሑፍ ማረጋገጫ የተሰጣቸው፣
6. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ ለእድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች ለሆኑ
መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን
በአማካሪነት ተመድበው የሰሩ፣
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና
ሕጻናትን ለይቶ በማወቅ ልዩ ድጋፍ የሰጡ፣ አገልግሎት እንዲያኙ ያደረጉና የትምህርት ውጤታቸው
እንዲሻሻል የሰሩ፣
8. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ሁለት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄዱ፤
ጥናቱን ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፣ የድርጊት መርሀ ግብር ያዘጋጀና ከሚመለከተው
ጋር በትብብር የሰራ፡፡
9. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ
አሰጣጥ እድሳት ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

ከላይ ለተዘረዘሩት ተግባራት መምህራን ለውድድር ለሚቀርቡበት ደረጃ እድገት የቆይታ ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ
ስለመሆናቸው በሚመለከተው የትምህርት ቤት ኃላፊ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8.2 በአንደኛ ደረጃ (1 ኛ-6 ኛ) መምህራን የሚጠበቁ መስፈርቶች

8.2.1 በጀማሪ መምህርነት የሚመደቡት

ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሙያ በዲፕሎማ (12+2) የሰለጠኑ ሲሆን ቀደም ብሎ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+3 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

9
8.2.2 ከጀማሪ መምህርነት ወደ መለስተኛ መምህርነት ለማደግ
ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሙያ በዲፕሎማ (12+2) የሰለጠኑ ሲሆን ቀደም ብሎ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+3 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣

1. በጀማሪ መምህርነት 2 ዓመት ያገለገሉ፣

2. በጀማሪ መምህርነት ባገለገሉባቸው 2 ዓመታት (ለ 4 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 70% እና በላይ ያገኙ፣
3. የመምህርነት ሙያ ትውውቅ (Induction) ለ 2 አመታት (ለ 4 ሴሚስተር ) በአግባቡ ተከታትለው ያጠናቀቁ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፡፡
5. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.2.3 ከመለስተኛ መምህርነት ወደ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሙያ በዲፕሎማ (12+2) የሰለጠኑ ሲሆን ቀደም ብሎ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+3 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፡-

1. በመለስተኛ መምህርነት 3 ዓመት ያገለገሉ፤

2. በመለስተኛ መምህርነት ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 75% እና በላይ
ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በትምህርት ቤቱ በሚቋቋሙ ክበባት ወይም ኮሚቴዎች ቢያንስ በአንዱ የተሳተፉ፣
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄዱ፡፡
7. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.2.4 ከመምህርነት ወደ ከፍተኛ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሙያ በዲፕሎማ (12+2) የሰለጠኑ ሲሆን ቀደም ብሎ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+3 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፡-

10
1. በመምሀርነት ደረጃ 3 ዓመት ያገለገሉ፤

2. በመምህርነት ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሰሜስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 80% እና በላይ ያገኙ፣

3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣

4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣

5. በዩኒት መሪነት ወይም በትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት
ወይም በክበባት በኃላፊነት/በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት ወይም በአባልነት ያገለገሉ
እና በተጠቀሱት አማራጮች ከአንድ ዓመት ያላነሰ የሰሩ፣

6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄደና ጥናቱን ለትምህርት
ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፤

7. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ ለእድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች
ለሆኑ መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን
በአማካሪነት ተመድበው የሰሩ፣

8. ለሚያስተምሩት የትምህርት ደረጃ የተዘጋጀውን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ መጽሐፍ

የገመገሙ እና አጠናቅረው ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤

9. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና
ሕጻናትን በመለየት ድጋፍ የሰጠና አገልግሎት እንዲያኙ ያደረጉ፡፡

10. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.2.5 ከከፍተኛ መምህርነት ወደ ተባባሪ መሪ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሙያ በዲፕሎማ (12+2) የሰለጠኑ ሲሆን ቀደም ብሎ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+3፣ ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተጠቃሚ ይሆናሉ፣

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፡-

1. በከፍተኛ መምህርነት 3 ዓመት ያገለገሉ፤

2. በከፍተኛ መምህር ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 84% እና በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
ለትምህርት ቤቱ መምህራን ጽብረቃ (Reflection) ያደረጉ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም
በክበባት በሃላፊነትና አባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነትና አባልነት ያገለገሉ እና በተጠቀሱት
አማራጮች ከአንድ ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣
11
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ እና በላይ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄና ጥናቱን
ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፣
7. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ ለእድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች
ለሆኑ መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን በአማካሪነት ተመድበው
የሰሩ፣
8. ለሚያስተምሩት የትምህርት ደረጃ የተዘጋጀውን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ መጽሐፍ የገመገሙ እና
አጠናቅረው ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤
9. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሁኑ ተማሪዎችንና ሕጻናትን
በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደረጉና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሰሩ፡፡
10. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.2.6 ከተባባሪ መሪ መምህርነት ወደ መሪ መምህርነት ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሙያ በዲፕሎማ (12+2) የሰለጠኑ ሲሆን ቀደም ብሎ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+3 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተጠቃሚ ይሆናሉ፣

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፡-

1. በተባባሪ መሪ መምህር ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በተባባሪ መሪ መምህርነት ባገለገሉባቸው ተከታታይ የ 3 ዓመት (የ 6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 87%
እና በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
ለትምህርት ቤቱ መምህራን ጽብረቃ (Reflection) ያደረጉ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም
በክበባት በኃላፊነት ወይም በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት ወይም አባልነት ያገለገሉ እና
በተጠቀሱት አማራጮች ከአንድ ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ሁለት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄዱና ጥናቱን ለትምህርት
ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፣
7. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ ለእድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች
ለሆኑ መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን
በአማካሪነት ተመድበው የሰሩ፣
8. ለሚያስተምሩት የትምህርት ደረጃ የተዘጋጀውን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ መጽሐፍ የገመገሙ እና
አጠናቅረው ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤
12
9. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና
ሕጻናትን በመለየት ድጋፍና አገልግሎት እንዲያኙ ያደረጉ፣ ውጤታቸው እንዲሻሻል የሰሩ፣
10. ለሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ለማጣቀሻነት የሚያገለግል አጋዥ ጽሁፍ ለተማሪዎች ያዘጋጁ፡፡
11. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.2.7 ከመሪ መምህር ወደ ከፍተኛ መሪ መምህር ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት ሙያ በዲፕሎማ (12+2) የሰለጠኑ ሲሆን ቀደም ብሎ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት 10+3 ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ
ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፡-

1. በመሪ መምህር ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በመሪ መምህርነት ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመት (6 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 90% እና በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩና
ለትምህርት ቤቱ መምህራን ጽብረቃ (Reflection) ያደረጉ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በቅርንጫፍ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም በክበባት
ሀላፊነት/በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት/በአባልነት ያገለገሉ በተጠቀሱት አማራጮች
ከሁለት ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ሁለት እና በላይ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research)
ያካሄዱና ጥናቱን ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፤
7. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ እድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች ለሆኑ
መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከኮሌጅ ለሚመጡ እጩ መምህራን በአማካሪነት ተመድበው የሰሩ፣
8. ለሚያስተምሩት ትምህርት የተዘጋጀውን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ መጽሐፍ የገመገሙ እና አጠናቅሮ
ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤
9. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ውይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና
ሕጻናትን በመለየት ድጋፍ የሰጠና አገልግሎት እንዲያኙ ያደረጉ፣
10. በሚያስተምረው የትምህርት ዓይነት ለተማሪዎች ማጣቀሻነት የሚያገለግል አጋዥ ጽሁፍ ያዘጋጁ፣
11. በሌሎች መምህራን የተዘጋጁ ጽሑፎችን ወይም ጥናቶችን ወይም መሰል ሥራዎችን በመገምገም የተሳተፉ፣
12. የማሰልጠኛ ጽሐፍ በማዘጋጀት ለትምህርት ቤቱ መምህራን ስልጠና የሰጡ፡፡
13. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ
አሰጣጥ እድሳት ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

13
ከላይ ለተዘረዘሩት ተግባራት መምህራን ለውድድር ለሚቀርቡበት ደረጃ እድገት የቆይታ ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ
ስለመሆናቸው በሚመለከተው የትምህርት ቤት ኃላፊ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8.3 ከመመካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ (7-12) መምህራን የሚጠበቁ መስፈርቶች

8.3.1 በጀማሪ መምህርነት የሚመደቡት

ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ (12+4) የተመረቁ ሲሆን ይህ መመሪያ ስራ ላይ
ከመዋሉ በፊት (12+3+PGDT) እና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ፣ እንዲሁም 7-8 በ 10+3 ወይም 12+12
መምህራን በዚህ የደረጃ እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

8.3.2 ከጀማሪ መምህር ወደ መለስተኛ መምህር ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ (12+4) የተመረቁ ሲሆን ይህ መመሪያ ስራ ላይ
ከመዋሉ በፊት (12+3+PGDT) እና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራንም በዚህ የደረጃ እድገት
መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፡-

1. በጀማሪ መምህርነት 2 ዓመት ያገለገሉ፣

2. በጀማሪ መምህርነት ባገለገሉባቸው 2 ዓመታት (4 ሴሚስተር) አማካይ የስራ አፈጻጸም 70% እና በላይ ያገኙ፣
3. የመምህርነት የሙያ ትውውቅ (Induction) ለ 2 አመታት (ለ 4 ሴሜስተር) ተከታትለው ያጠናቀቁ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፡፡
5. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.3.3 ከመለስተኛ መምህር ወደ መምህር ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ (12+4) የተመረቁ ሲሆን ይህ መመሪያ ስራ ላይ
ከመዋሉ በፊት (12+3+PGDT) እና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራንም በዚህ የደረጃ እድገት
መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣-

1. በመለስተኛ መምህርነት 3 ዓመት ያገለገሉ፣

14
2. በመለስተኛ መምህርነት ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የሥራ አፈጻጸም ውጤቱ 75%
እና በላይ ያገኙ፣

3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣

4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በቅርንጫፍ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም በክበባት
ሀላፊነት/በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት/በአባልነት ያገለገሉ በተጠቀሱት አማራጮች
ከሁለት ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action Research) ያካሄዱ፤
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና ሕጻናትን
በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደረጉና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሰሩ፡፡
8. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.3.4 ከመምህር ወደ ከፍተኛ መምህር ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ (12+4) የተመረቁ ሲሆን ይህ መመሪያ ስራ ላይ
ከመዋሉ በፊት (12+3+PGDT) እና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራንም በዚህ የደረጃ እድገት
መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣-

1. በመምህርነት ደረጃ ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፣

2. በመምህርነት ደረጃ ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የሥራ አፈጻጸም ውጤት 80% እና
በላይ ያገኙ፣

3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣

4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በቅርንጫፍ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም በክበባት
ሀላፊነት/በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት/በአባልነት ያገለገሉ በተጠቀሱት አማራጮች
ከሁለት ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣

6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄደና ጥናቱን ለትምህርት
ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፤

7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና ሕጻናትን
በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደረጉና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሰሩ፣
15
8. ለሚያተምሩት ትምህርት የተዘጋጀውን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ መጻህፍ የገመገሙ እና አጠናቅረው
ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤

9. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ እድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች ለሆኑ
መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከዩኒቨርሲቲ ለሚመጡ እጩ መምህራን በአማካሪነት ተመድበው
የሰሩ፡፡

10. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.3.5 ከከፍተኛ መምህር ወደ ተባባሪ መሪ መምህር ለማደግ፣

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ (12+4) የተመረቁ ሲሆን ይህ መመሪያ ስራ
ላይ ከመዋሉ በፊት (12+3+PGDT) እና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራንም በዚህ የደረጃ
እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣-

1. በከፍተኛ መምህርነት ደረጃ ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በከፍተኛ መምህርነት ደረጃ ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የሥራ አፈጻጸም ውጤት
84% እና በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩና
ለትምህርት ቤቱ መምህራን ጽብረቃ (Reflection) ያደረጉ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በቅርንጫፍ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም በክበባት
ሀላፊነት/በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት/በአባልነት ያገለገሉ በተጠቀሱት አማራጮች
ከሁለት ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ አንድ እና በላይ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄዱና ጥናቱን
ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፤
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና ሕጻናትን
በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደረጉና የተማሪዎችን ወጤት ለማሻሻል የሰሩ፣
8. ለሚያተምሩት ትምህርት የተዘጋጀውን መርሀ ትምህርት (syllabus)፣ የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ
መጻህፍ የገመገሙ እና አጠናቅረው ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤
9. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ እድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች
ለሆኑ መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከዩኒቨርሲቲ ለሚመጡ እጩ መምህራን በአማካሪነት
ተመድበው የሰሩ፣
16
10. በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ለተማሪዎች ማጣቀሻነት የሚያገለግል አጋዥ ጽሁፍ ያዘጋጁ፡፡
11. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ
አሰጣጥ እድሳት ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

8.3.6 ከተባባሪ መሪ መምህር ወደ መሪ መምህር ለማደግ

ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ (12+4) የተመረቁ ሲሆን ይህ መመሪያ ስራ ላይ
ከመዋሉ በፊት (12+3+PGDT) እና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራንም በዚህ የደረጃ እድገት
መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣-

1. በተባባሪ መሪ መምሀርነት ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በተባባሪ መሪ መምህርነት ደረጃ ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የሥራ
አፈጻጸም ውጤት 87% እና በላይ ያገኙ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
ለትምህርት ቤቱ መምህራን ጽብረቃ (Reflection) ያደረጉ፣
4. በአግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በቅርንጫፍ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም በክበባት
ሀላፊነት/በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት/በአባልነት ያገለገሉ በተጠቀሱት አማራጮች
ከሁለት ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ሁለት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄዱና ጥናቱን ለትምህርት
ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፤
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና ሕጻናትን
በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደረጉና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሰሩ፣
8. ለሚያተምሩት ትምህርት የተዘጋጀውን መርሀ ትምህርት (syllabus)፣ የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ
መጻህፍ የገመገሙ፤ የማሻሻያ ሀሳብ ያቀረቡ እና አጠናቅረው ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤
9. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ እድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች ለሆኑ
መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከዩኒቨርሲቲ ለሚመጡ እጩ መምህራን በአማካሪነት ተመድበው
የሰሩ፣
10. በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ለተማሪዎች ማጣቀሻነት የሚያገለግል አጋዥ ጽሁፍ ያዘጋጁ፡፡
11. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

17
8.3.7 ከመሪ መምህር ወደ ከፍተኛ መሪ መምህር ለማደግ
ሀ) ከመንግስት የትምህርት ተቋማት በመምህርነት ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ (12+4) የተመረቁ ሲሆን ይህ መመሪያ ስራ
ላይ ከመዋሉ በፊት (12+3+PGDT) እና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ ያሉ መምህራንም በዚህ የደረጃ
እድገት መሰላል አፈጻጸም መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) በ‹‹ሀ›› ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም፣-

1. በመሪ መምሀርነት ለ 3 ዓመታት ያገለገሉ፤

2. በመሪ መምህርነት ደረጃ ባገለገሉባቸው ተከታታይ 3 ዓመታት (6 ሴሚስተር) አማካይ የሥራ አፈጻጸም
ውጤት 90% እና በላይ ያዘጋጁ፣
3. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ በማዘጋጀት ለ 3 ተከታታይ ዓመታት የተሳተፉና በትክክል የተገበሩ፣
ለትምህርት ቤቱ መምህራን ጽብረቃ (Reflection) ያደረጉና የተሰጣቸውን ግብረ መልስ ተግባራዊ ያደረጉ፣
4. አግባቡ የተደራጀ ማህደረ ተግባር ያላቸው፣
5. በዩኒት መሪነት ወይም በቅርንጫፍ ማዕከል ኃላፊነት ወይም በዲፓርትሜንት ኃላፊነት ወይም በክበባት
ሀላፊነት/በአባልነት ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች በኃላፊነት/በአባልነት ያገለገሉ በተጠቀሱት አማራጮች
ከሁለት ዓመት ያላነሰ በአጥጋቢ ውጤት የፈጸሙ፣
6. በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ሶስት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ያካሄዱና ጥናቱን ለትምህርት
ቤቱ ማህበረሰብ ለውይይት ያቀረቡ፤
7. ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ተማሪዎች ወይም ሴት ተማሪዎችን ወይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችንና ሕጻናትን
በመለየት ድጋፍ የሰጠ፣ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደረጉና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሰሩ፣
8. ለሚያተምሩት ትምህርት የተዘጋጀውን መርሀ ትምህርት (syllabus)፣ የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መማሪያ
መጻህፍ የገመገሙ፤ የማሻሻያ ሀሳብ ያቀረቡ እና አጠናቅረው ለሚመለከተው አካል ያስረከቡ፤
9. ብዛታቸው ከ 2 ላላነሱ ጀማሪ መምህራን ወይም ለደረጃ እድገቱ ከሚወዳደሩት የደረጃ እድገት መሰላል በታች ለሆኑ
መምህራን ወይም ለተግባር ልምምድ ከዩኒቨርሲቲ ለሚመጡ እጩ መምህራን በአማካሪነት ተመድበው
የሰሩ፣
10. በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ለተማሪዎች ማጣቀሻነት የሚያገለግል አጋዥ ጽሁፍ ያዘጋጁ፣
11. በሌሎች መምህራን የተዘጋጁ ጽሑፎችን ወይም ጥናቶችን ወይም መሰል ሥራዎችን በመገምገም የተሳተፉ፣
12. የማሰልጠኛ ጽሐፍ በማዘጋጀት ለትምህርት ቤቱ መምህራን ስልጠና የሰጡ፡፡
13. የመምህራን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው /መንግስት የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እድሳት
ምዘና ተግባር ስርአት ሲዘረጋ የሚተገበር/

ከላይ ለተዘረዘሩት ተግባራት መምህራን ለውድድር ለሚቀርቡበት ደረጃ እድገት የቆይታ ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ
ስለመሆናቸው በሚመለከተው የትምህርት ቤት ኃላፊ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

18
9. ዝውውርና የደረጃ እድገት አፈጻጸም
9.1 መምህራን በመምህርነት ሙያ ከአንድ ትምህርት ቤት ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ወይም ወረዳ ወይም ዞን
ወይም ክልል/ከተማ አስተዳደር በሚዛወሩበት ወቅት ማህደረ ተግባር፣ የደረሱበት የደረጃ እድገት መሰላል፣
የደረጃ እድገቱን ያገኙበት ዘመን፣ የትምህርት ደረጃ እና የደረጃ እድገቱን ካገኙ በኋላ የተሰራላቸው የስራ
አፈጻጸም ውጤት በሚሰጣቸው መሸኛ ደብዳቤ ላይ ተገልጾ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
9.2 መምህራን ከመምህርነት የስራ መደብ በራሳቸው ጠያቂነት ሳይሆን በስራ አስፈላጊነት በመንግስት እውቅና
ወደ ትምህርት ጽ/ቤት ወይም ወደ ሌላ መንግስታዊ መስሪያ ቤት ተዛውረው እንዲሰሩ ሲደረግ፤ በደረሱበት
ደረጃ እድገት መሰላል ከቆይታ ጊዜው 2 ዓመትና በታች አገልግለው የተዛወሩ ከሆነ ወደ መምህርነት ሙያ
ሲመለሱ መጀመሪያ በነበሩበት ደረጃ ተመልሰው የመቆያ ጊዜውን ጠብቀውና ተገምግመው ቀጣዩን የደረጃ
እድገት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
9.3 መምህራን ከመምህርነት የስራ መደብ በማንኛውም ምክንያት 2 ዓመትና ከዚያ በላይ ከመምህርነት ሙያ
ውጪ ከቆዩ ወደ መምህርነት ሙያ መመለስ አይችሉም፣ ይህ የትምህርት ቤት አመራሮችን (ር/መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮችን) አይመለከትም፡፡
9.4 በመምህራን ማህበር አባልነት በየደረጃው በጽ/ቤት የሚያገለግሉ መምህራን እንደ ማንኛውም መምህር
የደረጃ እድገት ሥርዓቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን በሙሉ ጊዜ እና በተመላላሽነት በማህበሩ ጽ/ቤት የሚያለግሉ
መምህራን የሚገመገሙት ለማህበሩ አባላት በተዘጋጀው የመገምገሚያ መስፈርት ይሆናል፡፡ የምርጫ
ዘመናቸው ተጠናቆ ወደ ማስተማር ሲመለሱ በደረሱበት የደረጃ እድገት መሰላል የሚመደቡ ሲሆን የቆይታ
ጊዜውንና ሌሎችን መስፈርቶችን ሲሟሉ ቀጣዩን የደረጃ እድገት የሚያገኙ ይሆናል፡፡

9.5 መምህራን በደረሰባቸው የጤና ችግር ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ከማስተማር ሥራ እንዲገለሉ በመንግስት
ሆስፒታል በሀኪሞች ቦርድ ሲረጋገጥ መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው ቦታ በጊዜያዊነት መድቦ ያሠራቸዋል፡፡
መምህራንም በተመደቡበት ጊዜያዊ ቦታ ላይ አጥጋቢ ውጤት ካገኙ ከማስተማር ሥራ በተገለሉበት ጊዜ
ከነበሩበት ቀጥሎ ወደ አለው የደረጃ እድገት ለአንድ ጊዜ ብቻ ለውድድር ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ
መምህራን በ 2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከህመማቸው አገግመው ወደ ማስተማር ሥራቸው ሊመለሱ ካልቻሉ
በመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ደንብ መሠረት ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ ተዛውረው እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
9.6 መምህራን በደረሰባቸው የጤና ችግር ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ከማስተማር ሥራ እንዲገለሉ በመንግስት
ሆስፒታል በሀኪሞች ቦርድ ሲረጋገጥ የደረጃ እድገት የሚያገኙበት ጊዜ ከደረሰ ከመታመማቸው በፊት
በነበራቸው የስራ አፈጻጸም ውጤት መሰረት ለአንድ ጊዜ ብቻ ለደረጃ እድገት ውድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
9.7 መምህራን በደረጃ እድገት ኮሚቴው የአሰራር ችግር ወይም ስህተት ምክንያት ካሉበት ደረጃ ወደ ሚቀጥለው
ደረጃ ማደግ ካልቻሉ፤ የተፈጠረው ችግር እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ከታወቀ ለደረጃው የሚጠበቀውን
የስራ አፈጻጸም ውጤትና ሌሎች መስፈርቶችን አሟልተው ሲገኙ የደረጃ እድገት ማግኘት ከነበረባቸው ጊዜ
ጀምሮ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ከስድስት ወር በኋላ ችግሩ ከታወቀ የሚጠበቅባቸውን የስራ አፈጻጸም
ውጤትና ሌሎች መስፈርቶች አሟልተው ከተገኙ በቀጣዩ የደረጃ እድገት የውድድር ጊዜ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
19
ይደረጋል፡፡ ሆኖም በዚህ ምክንያት የደረጃ እድገት ጊዜው የሚዛባባቸው መምህራን ቀጣዩን የደረጃ እድገት
የሚያገኙት በደረጃ እድገት ኮሚቴው የአሰራር ችግር ወይም በስህተት የታለፈውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ
ይሆናል፡፡
9.8 መምህራን ከአንድ የደረጃ እድገት መሰላል ወደ ቀጣዩ የደረጃ እድገት መሰላል ማለፍ ካልቻሉ ድጋሜ
ለውድድር የሚቀርቡት ለሚወዳደሩበት ደረጃ የሚጠይቀውን የቆይታ ጊዜና የደረጃ እድገት መወዳደሪያ
መስፈርቶችን ሲያሟሉ ይሆናል፡፡ ይህ የድጋሜ ውድድር እድል በእያንዳንዱ የደረጃ እድገት መሰላል ለአንድ
ጊዜ ብቻ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በተሰጠው የውድድር እድል የደረጃ እድገት ተጠቃሚ ከሆኑ
ለሚቀጥለው ደረጃ እድገት ለውድድር የሚቀርቡት የድጋሜ የደረጃ እድገቱን ካገኙበት ቀን ጀምሮ
የሚጠበቅባቸውን የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም፣ የመቆያ ጊዜና ለደረጃ እድገት መወዳደሪያ የተቀመጡ
መስፈርቶችን አሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡፡

9.9 መምህራን ከአንድ የደረጃ እድገት መሰላል ወደ ቀጣዩ የደረጃ እድገት መሰላል ማለፍ፣ አለማለፋቸውን
የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ በ 10 ቀናት ውስጥ በሚመለከተው አካል ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
9.10 ሴት መምህራን በወሊድ ፍቃድ ላይ እያሉ የደረጃ እድገት የሚያገኙበት ጊዜ ከደረሰ ከወሊድ በፊት
በነበራቸው የስራ አፈጻጸም ውጤት መሰረት ለደረጃ እድገት ውድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
9.11 በትምህርት ደረጃ ማሻሻያ በትይዩ የሚገኝ እድገትና በቆይታ ጊዜ የሚገኝ የደረጃ እድገት በአንድ ጊዜ
ሲመጡ መምህራን በሁለቱም ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
9.12 ለመምህራን የሚደረግ የደመወዝ ስኬል ማሻሻያ የደረጃ እድገት የሚያገኙበትን ጊዜ አያፋልስም፡፡
9.13 ከትምህርት ዝግጅታቸው በታች ተመድበው የሚያስተምሩ መምህራን የደረጃ እድገት የሚሰጣቸው
በሚያስተምሩበት የትምህርት ቤት ደረጃ ሳይሆን ባላቸው የትምህርት ዝግጅት መሰረት ይሆናል፡፡
9.14 እያንዳንዱ ትምህርት ቤት በየዓመቱ የቆይታ ጊዚያቸውን ጨርሰው ለደረጃ እድገት ለሚወዳደሩ
መምህራን የደረጃ እድገት ከሚያገኙበት አንድ ወር በፊት በማስታወቂያ ሰሌዳ ሊያሳውቅ ይገባል፡፡ የደረጃ
እድገት ተወዳዳሪ መምህራንም በዚህ ጊዜ ውስጥ ለትምህርት ቤቱ ለደረጃ እድገት ውድድር እንደሚቀርብ
በጽሁፍ ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡
9.15 መምህራን ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላው ደረጃ የመቆያ ጊዜውን ጠብቀው በሚያድጉበት ወቅት የደረጃውን
የመነሻ ደመወዝ ደርሰውበት ወይም አልፈውት ከሆነ በሲቪል ሰርቪስ መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

10 . የመምህራን የደረጃ እድገት የሚያገኙበት ጊዜ

የመምህራን የደረጃ እድገት በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰራ ይሆናል፡፡ ይኸውም፡-

ሀ) ከጥር 1 እስከ ሰኔ 30 የተቀጠሩ መምህራን የደረጃ እድገት የሚያገኙት ከሀምሌ 1 ጀምሮ ይሆናል፡፡

ለ) ከሐምሌ 1 እስከ ታህሳስ 30 የተቀጠሩ መምህራን የደረጃ እድገት የሚያገኙት ከጥር 1 ጀምሮ ይሆናል፡፡

20
ክፍል አምስት

11 . የመምህራን የደረጃ እድገት አስፈጻሚ አካላትና ኮሚቴ አባላት

11.1 የትምህርት ቤት የደረጃ እድገት ኮሚቴ
11.1.1 የትምህርት ቤት የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት
የትምህርት ቤት የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለትምህርት ቤቱ ደረጃ እድገት ኮሚቴ ሲሆን አባላቱም፤-

1. የትምህርት ቤቱ ም/ር/መምህር ወይም ተወካይ --------------------------------- ሰብሰቢ

2. ከትምህርት ክፍል ኃላፊዎች በመምህራን የሚወከሉ 2----------------------- አባልና ጸሐፊ
3. የመሰረታዊ መምህራን ማህበር 2 ተወካይ --------------------------------------- አባል
የትምህርት ቤቱ የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ በትምህርት ቤቱ ለደረጃ እድገት ውድድር የቀረቡ መምህራንን ፋይል ትክክለኛነት
በማጣራት ለትምህርት ቤቱ ደረጃ እድገት ኮሚቴ ለውሳኔ ያቀርባል፡፡
11.1.2 የትምህርት ቤት የደረጃ እድገት ኮሚቴ አባላት
የትምህርት ቤት የደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለወረዳው ሲሆን አባላትም፤-

1. የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር --------------------------------------------------- ሰብሳቢ

2. የትምህርት ቤቱ ም/ር/መምህር ወይም ተወካይ -------------------------------- ፀሐፊ
3. የመሠረታዊ መምህራን ማሕበር 2 ተወካዮች አንዷ ሴት ------------------- አባል
4. በእጩነት የሚቀርበው መምህር የሚገኝበት የትምህርት ክፍል ኃላፊ ------ አባል

ከአምስቱ አባላት አንድ የመሠረታዊ መምህራን ማህበር ተወካይን ጨምሮ ከግማሽ በላይ አባላት በተገኙበት
የመምህራን የደረጃ እድገት እንዲሰራ ይደረጋል፡፡
11.2 የወረዳ የመምህራን የደረጃ እድገት ኮሚቴ
11.2.1 የወረዳ የመምህራን የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ

የወረዳው የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለወረዳው ትምህርትና ስልጠና ቦርድ ሲሆን አባላቱም፦

1. የወረዳው የመምህራን ልማት ዳይሬክተር/ ቡድን መሪ/ተወካይ----------ሰብሰቢ

2. የወረዳው የመምህራን ልማት ዳይሬክቶሬት/ቡድን ባለሙያ--------------- ጸሀፊ

3. የወረዳው የመምህራን ማህበር አንድ ተወካይ --------------------------------አባል

21
የወረዳው የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ በትምህርት ቤቶች ደረጃ ጸድቆ የተላከውን የደረጃ እድገት የሚያገኙ
መምህራን መረጃ እና ቃለ ጉባኤ አጣርቶ ለወረዳው የትምህርትና ሥልጠና ቦርድ ለውሣኔ ያቀርባል፡፡

11.2.2 የወረዳው የትምህርትና ሥልጠና ቦርድ

የወረዳ የትምህርትና ሥልጠና ቦርድ የመምህራንን የደረጃ እድገት ውሣኔ የሚያጸድቅ ይሆናል፡፡ አባላቱም፦

1. የወረዳ የትምህርትና ሥልጠና ቦርድ ኃላፊ ---------------------------------- ሰብሳቢ

2. የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ -------------------------------------------------ፀሐፊ
3. የወረዳ የመምህራን ልማት ዳይሬክተር/ ቡድን መሪ/ተወካይ--------------- አባል
4. የወረዳ የመምህራን ማህበር ተወካይ 2 (አንዷ ሴት) ----------------------- አባል

ከአምስቱ አባላት አንድ የመሠረታዊ መምህራን ማህበር ተወካይን ጨምሮ ከግማሽ በላይ አባላት በተገኙበት
የመምህራን የደረጃ እድገት እንዲጸድቅ ይደረጋል፡፡
11.3 በየደረጃው ያሉ የደረጃ እድገት ኮሚቴዎች ተግባራትና ሀላፊነት
11.3.1 የትምህርት ቤት የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ ተግባራት
ሀ) ለደረጃ እደገት የሚወዳደሩ መምህራንን ፋይል ከሚመለከተው ክፍል በመረከብ በትክክል ለውድድር የሚቀርቡ
ስለመሆናቸው ያጣራል፣

ለ) በትምህርት ቤት ለደረጃ እድገት ውድድር የሚሳተፉ መምህራንን ይለያል፣

ሐ) የተጣራውን ፋይልና ቃለጉባኤ በማደራጀት ለት/ቤቱ የደረጃ እድገት ኮሚቴ ያስረክባል፣

መ) ለውድድር የተለዩ መምህራን ስም ዝርዝር በትምህርት ቤቱ ር/መምህር አማካይነት ግልጽ በሆነ ቦታ

እንዲለጠፍ በማድረግ መምህራን እንዲያውቁት ያደርጋል፣

11.3.2 የትምህርት ቤት የደረጃ እድገት ኮሚቴ ተግባራት

ሀ) ከትምህርት ቤቱ የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ ተጣርቶ የቀረበለትን የመምህራንን መረጃ ፈትሾ ለደረጃ እድገት
ውድድር የሚቀርቡ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣

ለ) የትምህርት ቤቱን መምህራን የደረጃ እድገት ይሰራል፣

ሐ) በትምህርት ቤት ደረጃ የጸደቀውን የመምህራንን የደረጃ እድገት ለወረዳው ትምህርትና ስልጠና ቦርድ ይልካል፡፡

11.3.3 የወረዳ የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ ተግባራት

ሀ) ከየትምህርት ቤቱ የቀረቡለትን የመምህራን የደረጃ እድገት ማስረጃ ያጣራል፣

ለ) የመምህራን የደረጃ እድገት ማስረጃ ለትምህርትና ስልጠና ቦርዱ ያቀርባል፣

22
11.3.4 የወረዳ የትምህርትና ሥልጠና ቦርድ ተግባራት
ሀ) ከወረዳው የደረጃ እድገት ቴክኒክ ኮሚቴ ተጣርቶ የቀረበለትን የደረጃ እድገት ያገኙ መምህራን ዝርዝርና ፋይል
ይመረምራል፣

ለ) የደረጃ እድገት ማግኘት የሚገባቸውን መምህራን በመለየት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፣

12. የቅሬታ አቀራረብ

መምህራን በደረጃ እድገት አፈፃፀም ላይ ቅሬታ ሲኖራቸው የደረጃ እድገት ደብዳቤ በእጃቸው ከደረሰበት ቀን
ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቅሬታቸውን ያቀርባሉ፡፡ ሆኖም በተሰጠው ምላሽ
የማይስማሙ ከሆነ በየደረጃው ለሚገኘው የትምህርት መዋቅር አስተዳደር ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡ ቅሬታ የቀረበለት
አካልም ከደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ አንጻር በማየት ቅሬታ ከቀረበለት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15
ቀናት ውስጥ መርምሮ ተገቢ ምላሽ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ ከላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ ካልተሰጠ
ቅሬታ አቅራቢዎች ደረጃውን በመጠበቅ እስከ ክልል/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ድረስ ቅሬታቸውን ማቅረብ
ይችላሉ፡፡ ይህ ካልሆነ እስከ ክልል/ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ወይም አስተዳደርዊ ፍርድ ቤት
ቅሬታቸውን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡

ክፍል ስድስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
የመተባበር ግዴታ
ለዚህ መመሪያ አፈጻጸም ትብብር የተጠየቀ አካል የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

ተፈጻሚነት ስለሌላቸው ጉዳዮች

በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዮች ከመመሪያው ጋር የሚቃረኑ አሰራሮችና ልማዶች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡

23
ስለተሻሩ መመሪያዎች
ከዚህ ቀደም ስራ ላይ የነበሩ ማናቸውም የመምህራን የደረጃ እድገት መመሪያዎች ይህ መመሪያ ፀድቆ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ
ጀምሮ የተሻሩ ስለሆነ ተቀባይነት የላቸውም፡፡

መመሪያውን ስለማሻሻል

እንደ አስፈላጊነቱ መመሪያውን የማሻሻል ስራ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነት ይሆናል፡፡

መመሪያው ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከ---------ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

24

You might also like