Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

አንስታይ ሂስ

ዘመናዊያን የስነፅሁፍ ስራው ላይ በማተኮር ዝግ ንባብ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በአፅንኦት ያስተምራሉ፡፡
ይህም አንድን ስራ አድሎአዊ ሳይሆን ለመተንተን ስለሚረዳ በሚል አሳቢ ነው፡፡ ነገር ግን ማንኛውም አንባቢ
አንድን ስራ ሰየነብ የራሱ የሆኑ ቅድመ ግምታዎች ወይንም መረዳቶች አሉት፡፡እነዚህ ቅድሙ ግመታዎች
ወይም መረዳቶች አንባቢው የሚኖርበት ወይንም የኖረበት ቋሚ እሴቶችና እምነቶች መሰረት ያደረጉ ናቸው
፡፡እንደዚህ አይነት አተያይን መሰረት በማድረግ ከሚሰሩ መካከል የአንስታይን ሂስ ተጠቃሽ ነው፡፡ በአንስታይን
ሂስ ሃያሲው የስነፅሁፍ ስራውን ከተለመይውና የወንዶች የበላይነት በገነነበት ማህበረሰብ ውስጥ
እንደሚታየው ሳይሆን ከዚያ በተለየ አይን ለማየት ይጥራሉ፡፡

በሂስ አይነቱ የማንኛውም ስነፅሁፍ ማዕከላዊ ሃሳብ ስርተ ታፆ እና የወንዶችና የሴቶች ግንኙነት እንደመሆኑ ይህንን
ሂሳብ ማሳየት ትኩረቱ ነው /ፔክአ እና ከሌይ ፣1984 /፡፡የወንዶች የበላይነት በነገሰበት አለም ውስጥ የሚፃፉ
የስነፅሁፍ ስራዎች ምን የህል ታዊ ጉዳይ ላይ ሴቶች ተጨቋኝ ወይም የበታች ተደርገው እንደሚሳሉም
ለማጥናት በዚህ የስነፅሁፋዊ ሂስ አራማጆች ዘንድ የሚዘወተር ተግባር ነው ፡፡ ይህ የስነፅሁፍ እንቅስቃሴ
የተጀመረው አንስታይን እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው፡፡ የአንስታይ እንቅስቃሴ ሶስት ደረጃዎች
አሉት፡፡
 የመጀመሪያው እንደ ውሮፖወያኑ አቆጣጠር ከ 17 ዐዐዎቹ መለጨረሻ እስከ 19 ዐዐዎቹ መጀመሪያ

አካባቢ ያለው ሲሆን የእንቅስቃሴው ዋና አላማ በሁለቱ ፆታዎች መካከል ባለ እኩልነት ማጣት ላይ

ያተኩራል፡፡ በእነዚህ እቅስቃሴ ውስጥ ተጠቃሽ ከሆኑት መካከል አነዎልስቶንክራፍት ይገኙበታል፡፡

 ሁለተኛው የአንስታይ እንቅስቃሴ ከ 196 ዐ ዎቹ እስከ 197 ዐ ዎቹ በሁለተኛው የአለም ጦርነት

ወቅት በአሜሪካ የተነሳ ሊሆን ኤሊና ሸዋልተር፣ ሲሞንደበዋር የመሳሰሉትን ፀሐፍት ያካተተ ነበ፡፡

በዚህ ወቅት የነበረው ጥያቄ በሁሉ የስራ መስክ ሴቶች ከወንዶች እኩል ተሳታፊ መሆን እንደሚችሉ

የሚያመለክት ነበር፡፡

 ሶስተኛው እንቅስቃሴ 199 ዐዎች መጀመሪያ እስከ አሁን ድረስ ያለው ነው፡፡ይህ እንቅስቃሴ ከሴቶች

በተጨማሪ የተናቁ እና ከማህበረሰቡ የተገለሉ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን /ጥቁሮች ፣ በዘር

የተገለሉትን / ይጨምራል

አንስታይ ሂስ በስነፅሁፍ ውስጥ ሴቶች በባህል በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮች

የተደረገባቸውን ጫና ይፈትሻል/ታይሰን፣1999/፡፡ በአካላዊ አገዛዝ ወንዶችን ምክንያታዊ ፣ ጠንካራ፣

ተከላካይና ውሳኔ ሰጪ ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ ስሜታዊ/ምክንያታዊ ያልሆኑ፣ ደካማ ፣ አስዳጊና ተገዢ

ተደርጐ ሚናቸው ተለይቷል፡፡

1
ወንዶች ጠንካራና ስሜታቺውን የሚቆጣጠሩ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ ከዚህ በተለየ የሚያሳዩት

የማዘን የመከፋት ስሜት ከወንድኑታቸው የማይጠበቅ የሴት ባህሪ ተብሎ ይወሰዳል፡፡ የወንዶች ባህሪ

አይደለም ተብሎ የማኑሳው ነገር የሴቶች ባህሪ ነው፡፡ የሴቶች በስነፅሁፋዊ ሂሱ የማነሱ ጥያቄዎች

የሚኩተሉት ናቸው

 የወንድና የሴት ግንኙነት እንዴት ተስሏል?

 በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለው የሃይል ግንኙነቶች ምንድን ናቸው /ገፀ ባህሪያትየወንድ

የሴት የማሉት ሚና አለ?/

 የወንዶችና የሴቶች ሚና በግልፅ ተቀምጧል?

 ሴትነትና ወንድኑት የማይዟቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

 ሴትነትወንድነት በገፀ ባህሪያት ተገልጠዋል?

 ገፀ ባህሪያት ከተቃራኒ ፆታ የወሰዱት ባህሪ አለ?እንደት?ይህ የባህሪ ለውጥ በሌሎች ገፀ

ባህሪያት ዘንድ ያስገኘው ምላሽ ምንድን ነው?

 የስነፅሁፍ ስራው የአባዊ አገዛዝን ጭቆና /በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሢ፣ በማህበራዊና ስነልቦና/

እንዴት ይገለጠዋል?

 ስራው በአባዊ አገዛዝ ላይ ስላለው ተቃውሞ እና አህትማማችነት ምን ይላል?

 ስራው ስለሴቶች የፈጠራ ችሎታ የሚያወሳው ነገር አለ?

 ስራው በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነትና ስለአባዊ አገዛዝ ሃያሲያን የሚነግሩን ምንድን ነው?

 የሰነፅሁፍ ስራው በሴቶች የስነፅሁፍ ታሪክ እና ባህል ላይ ምን የሚጫወተው ሚና አለ?

You might also like