Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 6

የአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ የመዝናኛ ፕሮግራሞችና ስፖርት ክፍል

ከጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን

ጉዳዮች መምሪያ ጋር በመተባበር

የ 2014 ዓ.ም የገና በዓል ዝግጅት ምክረ ሃሳብ

ታህሳስ፡ 2014 ዓ.ም

መግቢያ

0
የአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ የመዝናኛ ፕሮግራሞችና ስፖርት ክፍል አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞችን ዕለት
ከዕለት በማዘጋጀት ለአድማጭ ተመልካች ማቅረቡ ይታወቃል፡፡ በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የሚከበሩ
ሀይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላትን መሰረት በማድረግ በአራቱም የሀገራችን አቅጣጫዎች በመዘዋወር የተለያዩ
ባህሎችን በማስተዋወቅና በማስቃኘት አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በዶክመንተሪ በሪያሊቲ ሾው እና
መድረክ በማዘጋጀት ለህበረተሰቡ እያደረሰ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ገንቢ የሆነ ግብረ መልሶችን እያገኘ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የ 2014 ዓ.ም የገና ዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ ጌዴኦ ዞን መዳረሻውን ሊያደርግ ያሰበ ሲሆን
ለእቅዱ መሳካትም ከጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ጋር በመተባበር በደመቀና በአማረ
ሁኔታ ፕሮግራሙን ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅቶች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የመዝናኛ ፕሮግራሞችና ስፖርት ክፍል ለተመልካች እንዲደርሱ
የሚፈለጉ መልዕክቶችን በመቅረጽ ገና ልዩ የበዓል ዝግጅቱን ለማከናወን ይህንን ፕሮፖዛል አዘጋጅቶ
አቅርቧል፡፡

1
አላማ

የዚህ ፕሮፖዛል ዋንኛ አላማ የአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ የመዝናኛ ፕሮግራሞችና ስፖርት ክፍል ከጌዴኦ ዞን
መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ጋር በመተባበር

የጌዴኦ ህዝብ በታሪኩ በሀገር ህልውና ቀልድ የማያውቅ ዳርድንበሯንም ለመጠበቅ ቀዳሚ ዘማች
ለነብሱ የማይሳሳ፣ ፈጣሪውን በተለያዩ የእምነቱ ስርዓት መሰረት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት ዘውትር
የሚማፀን እምነቱን ጠባቂ ባህሉን አክባሪ እንደመሆኑ መጠን ከፊታችን የሚመጣውን የገና በዓልም
የጌዴኦ ህዝብ የዘመን መለወጫ የሆነውን (የደራሮን) የአከባበር ሁኔታ መነሻ በማድረግ የሀገርን ሰላምና
ፀጥታ በማስጠበቅና ዳርድንበርን በማስከበሩ ዘመቻ ደጀን ለሆነው የመከላከያ ሰራዊት እየተደረጉ ያሉ
የዞኑን እንቅስቃሴዎች በማሳየት "ደግፍ፣ ጠብቅና ዝመት" በሚል መሪ ቃል የብሔረሰቡን ባህል፣ ወግ፣
ስርዓት፣ ተፈጥሯዊና ሰውሰራሽ መገለጫዎቹን ብሎም የተለያዩ ስርዓቶችን ማሳየትና ማሳወቅ የሚችሉ
ፕሮግራሞችን የሚያስቃኝ ሪያሊቲ ሾው ማዘጋጀት ነው፡፡ የጌዴኦ ዞን የበርካታ ፀጋዎች ባለቤት፣ ባለ አረንጓዴ
ወርቅ ባለቤት (ቡና)፣ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጡ ልዩ፣ የገዳ ሥርዓቱ እንደ ዘመናዊ የፖለቲካ ድርጅት አወቃቀር
እና አደረጃጀት ያለው፣ አስደናቂ የመካነ-መቃብርና በርካታ ዝርዝር የአከባቢው መገለጫና መታወቂያ ሀብቶች ባለቤት
ሲሆን በዋናነትም የጌዴኦ አባገዳና የባህል ሽማግሌዎች ሀገር በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ሲገጥማት ወቅታዊ ሁኔታውን
ከግምት ውስጥ ያስገቡ የተለያዩ ባህላዊ የፀሎትና የምልጃ የባሌ የገዳ ስርዓትን በመከወን አባቶች አባታዊ ግዴታዎችን
እንደሚወጡ ይታወቃል፡፡

በአሁኑም ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያም ከወትሮው በተለየና በጠነከረ መልኩ ሀገራዊ አንድነትን አጠናክረው
የሚቆሙ ልጆች የምትሻበት ወቅት በመሆኑ ፣ ሁሉም ከያለበት በአንድ ተሰባስቦ ከያለበት አከባቢ
መከላከያውን እንዲግፍ፣ ወደ ግንባር እንዲዘምትና አከባቢህን ነቅቶ እንዲጠብቅ መንግስት በሰጠው አደራ
መሰረት የጌዴኦ ዞንም በተለያዩ ዘርፎች ጠንክሮና ያለ አንዳች ድካም ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል በስንቅ
ዝግጅቱ፣ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራቱ በመትጋት ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ እንደተከበረ በልጆቿ ታፍራና
ተከብራ ትኖር ዘንድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ለማሳየት

በፕሮግራሙ የሚተላለፍ መልዕክቶች

መከላከያውን በመደገፍ፣ ወደ ግንባር በመዝመትና አከባቢያችንን በመጠበቅ ህልውናዋ ተጠብቆ በፅኑ መሰረት
ላይ የፀናች ከባንዳና በክፉ ከሚያያት ሁሉ የፀደዳች የበለፀገች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን፡፡

ፕሮግራሙ የሚያካትታቸው ጉዳዮችና አቀራረቦች

2
- የጌዴኦ ብሔረሰብን የዘመን መለወጫ ስርዓት፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህልና የተለያዩ ሀይማኖታዊ
ስርዓቶችን የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም
- የብሄረሰቡን ባህላዊ አመጋገብ፣ አለባበስ፣ አኗኗር፣ የቤት አሰራረ ጥበብ፣ የሚያስቃኝ ሪያሊቲ ሾው
- ታሪካቸው አስተማሪ የሆኑና ድጋፍ የተደረገላቸው የዘማች ቤተሰቦችን የህይወት ገፅ የሚያስቃኝ
ፕሮግራም በፕሮዳክሽን

ቃለ መጠይቅ

- አባ-ገዳዎች

- የሀገር ሽማግሌዎች

- የዘማች ቤተሰቦች

- የዞኑ ኃላፊዎች
- ባህላዊ የምግብ ዝግጅት በቅደም ተከተል የሚያስረዱ የብሔሩ ተወላጅ እናት
- ህፃናት የአከባቢውን ባህላዊ ዜማዎችና ጨዋተዎች የሚያሳዩ
- የቱሪስት መዳረሻዎችን ገለፃ የሚያደርግ ባለሙያ

በአጠቃላይ አከባቢውን ባህል፣ ወግና ልማድ ብሎም የአባቶች ስርዓት የሚያስቃኙ ርዕሰ ጉዳዮችን የሰነቁ
ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡

ፕሮግራሙ የሚከናወንበት ቦታ እና ቀን

- በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎችና በተመረጡ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት


- ከታህሳስ 17/04/14 እስከ ታህሳስ 24/04/14 ዓ.ም
-

ዝግጅቱ የሚቀርብበትና የሚተላለፍበት ቀን

- ታህሳስ 29/04/14 (ዝግጅቱ ቀደም ብሎ የሚቀረጽ ሲሆን የገና ዕለት ለህዝብ የሚቀርብ ነው)

የቀረፃ ዝግጅት

- ቀረፃው በአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ የካሜራና የኢንጂነሪንግ ቡድን ይከናወናል፡፡

የሁለቱ አካላት የስራ ድርሻ

የአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ የስራ ድርሻ

3
- ለፕሮዳክሽን ዝግጅቱ የሚያስፈልጉትን ዝርዝር ሁኔታዎች ይለያል
- ይህ ምክረ ሃሳብ በዞኑ ተቀባይነት እንዳገኘ የካሜራ ባለሙያ፣ ጋዜጠኛና መኪና ይመድባል
- ባህላዊ ስርዓቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ በተገቢው ጥንቃቄ በመቅረፅ ፕሮግራሙን አየር ላይ
ያውላል፤ (የአየር ሰዓት ያለክፍያ ይሰጣል)
- ዝግጅቱን አስመልክቶ ቀድሞ የፕሮሞሽን ስራ ይሰራል፤

የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊነት

- የባሌ የገዳ ስርዓትን የሚያስቃኝ ዝግጅት ማድረግ


- የጌዴኦ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል (ደራሮን) አስመልክቶ የቀረፃ ሁኔታውን ማመቻቸት
- የአባገዳና የባህል ሽማግሌዎችን ማዘጋጀት
- የጌዴኦ ብሔረሰብን ባህላዊ የምግብ መጠጥ ስርዓት የሚያስቃኙ ባለሙያዎችን መመደብ
- የብሔረሰቡን ባህላዊ ጭፈራዎችንና ዜማዎችን የሚያስቃኝ ባለሙያ መመደብ
- በአጠቃላይ ባህላዊ እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደተጠበቁ ይሻገሩ ዘንድ የአከባቢው
መገለጫ የሆኑ ባህላዊ ብሎም ሀይማኖታዊ ገፅታዎችን የሚያስቃኙ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት
አከባቢውን ማስተዋወቅ፡፡

ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮች

- የቅንጅት ችግር

- የጊዜ እጥረት

- የቀረፃ ቴክኒክ ችግር

- የሰው ሀይል እጥረት

የመፍትሄ ሀሳብ

- ሁለቱ ተቋማት በመናበብና ለጋራ ግብ የየበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማድረግ


- ቀድሞ ቴክኒካል ፕሮፖዛል እንዲዘጋጅ ማድረግ
- በመዝናኛ ላይ ፍላጎት ያላቸው በከተማው የሚገኙ ወጣቶችን ተሳታፊ ማድረግ
- ቀረፃውን ቀደም ብሎ መጀመር

ማጠቃለያ

4
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ህዝቦች ለዘመናት አብሮነታቸው አንዱ ከሌላው ጋር ያላቸው በጎ መስተጋብር
የማይካድ ሀቅ ሲሆን ሀገርም የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ድምቀት መታያ ነች፡፡

የጌዴኦ ህዝብም በታሪኩ በሀገር ህልውና ቀልድ የማያውቅ ዳርድንበሯንም ለመጠበቅ ቀዳሚ ዘማች
ለነብሱ የማይሳሳ፣ ፈጣሪውን በተለያዩ የእምነቱ ስርዓት መሰረት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት ዘውትር
የሚማፀን እምነቱን ጠባቂ ባህሉን አክባሪ እንደመሆኑ መጠን ከፊታችን የሚመጣውን የገና በዓልም
የጌዴኦ ህዝብ የዘመን መለወጫ የሆነውን (የደራሮን) የአከባበር ሁኔታ መነሻ በማድረግ የሀገርን ሰላምና
ፀጥታ በማስጠበቅና ዳርድንበርን በማስከበሩ ዘመቻ ደጀን ለሆነው የመከላከያ ሰራዊት እየተደረጉ ያሉ
የዞኑን እንቅስቃሴዎች በማሳየት "ደግፍ፣ ጠብቅና ዝመት" በሚል መሪ ቃል የደመቀና የተወደደ
ብሎም አስተማሪ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ታቅዶ የተዘጋጀ ምክረ ሃሳብ ሲሆን ለእቅዳችን መሳካትና
ለፕሮግራሙ ስኬት ሁሉም አካል በመተባበር ለበአሉ ዝግጅት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡

You might also like