Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

“ለመሆኑ ሁለን-አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ከየት ይጀምራሉ?

በትናንሽ ቦታዎች፤ ወደ ቤታችን ቅርብ በሆኑ

ስፍራዎች- በጣም ቅርብ እና በጣም ትንሽ ከመሆናቸው የተነሳ በየትኛውም የዓለም ካርታዎች ላይ ፈልገን

ልናያቸው እንኳ አይቻለንም፡፡ ሆኖም እነሱ የአንድ ግለሰብ ዓለም ናቸው፤ የሚኖርበት አካባቢ፣ የሚማርበት

ትምህርት ቤት ወይም ኮሌጅ፣ የሚሠራበት ፋብሪካ፣ የእርሻ ቦታው ወይም ቢሮው የሚገኙ ናቸው፡፡ በእነዚያ

ስፍራዎች ሁሉም ወንድ፣ ሴት እና ሕፃናት እኩል ፍትህን፣ እኩል እድልን፣ እኩል ክብርን ያለ አድልዎ እና ልዩነት

ይሻሉ፡፡ እነዚህ መብቶች በእነዚያ ቦታዎች ትርጉም ከሌላቸው በስተቀር የትም ቦታ ቅንጣት የምታህል

ትርጉም ሊኖራቸው አይችልም። ወደ እነዚህ ትንንሽ ስፍራዎች ተጠግተው ድጋፍ ለማድረግ የሚጨነቁ ዜጎች

እስካልተፈጠሩ እና እርምጃም እስካልወሰዱ ደረስ የታላቂቱ ዓለም እድገት ከንቱ መሆኑን እንመለከታለን፡፡”

ኤሌኖር ሩዝቬልት፤ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ 10 ኛ ዓመት ክብረ-በዓል (1958 እ.ኤ.አ)

You might also like